oliver

cheru.yaeyesus
  • No tags were found...

ye betel chaior mezmur

የቤቴል ኳየር መዝሙሮች

4/6/2012


ከፍ አድርገኸኛል

ከፍ አድርገኸኛል የኔ ጌታ

ከፍ አድርገኸኛል

ከፍ አድርገኸኛል የኔ ኢየሱስ

ከፍ አድርገኸኛል

1 ያለ ምንም ጥፋት ለሞት ስትነዳ

ለኔ ሀጢያት ብለህ ስትቀበል ፍዳ

የዛኔ ቀን ሆነልኝ የመዳኔ ምክኒያት

እርግማኔ ቀርቶ ሲመጣልኝ ምህረት

2 ከሀጥያተኛ ስፍራ አኔን አንስተኸኝ

የዘላለም ህይወት ጌታዬ ሰጠኸኝ

ለዚህ ማልበቃውን እኔን ከፍ አረከኝ

ስለዚህ ልበልህ ጌታ ክበርልኝ

3 የአምላኬ ብርሀን በእኔ ላይ በርቷል

የሀጥያቴን እዳ በደሙ አንፅቷል

እስከ ዘለዓለሙ ለቤቱ መርጦኛል

የመንግስቱ ወራሽ እኔን አድርጎኛል

4 አምላኬን ሁል ግዜ እባርከዋለው

ምስጋናዬም ዘውትር በአፌ ነው ያለው

ስራውም ድንቅ ነው አቤት የኔ ጌታ

ስራው ግሩም ነው ላክብረው በደስታ

P a g e | 2


ምን አይነት ደካማ ነኝ

ሰውነቴን ህያው መስዋዕት አድርጌ

ማቅረብ ሲገባኝ ፊትህ ቀድሼ

እንድትከብርበት እንድትነግስበት ሳልሰጥህ

ለምኞቴ አረኩት ሳልለይልህ

ዘነጋው ቃልህን አልተለወጠ ህይወቴ

አላከበርኩህም በሙሉ ማንነቴ

ምን አይነት ደካማ ነኝ መለወጥ ሚሳነኝ

ለውጥ የማያውቀኝ ቃልህ ሲነገረኝ

በእጅህ ንካኝና ለውጠኝ

ፀሀይ ወጥታ ደግሞ እስክትገባ

ቀኑ ነግቶ እስኪሆን ማታ

ክፋትን እያለምኩ በአዕምሮዬ

ሳላከብርህ ታለፈ ውሎዬ

ምሽቱ ቀረበ ሳልናገር ስለ ፅድቅህ

ፊትህ እንድሆን ስትጠራኝ

አብረኸኝ ልትሆን ልጄ ስትለኝ

ይችን ልጨርስ እያልኩ ኑሮዬን ላቃና

እመጣለው(ብዬ) ትንሽ ልቆይና

በማለት እያለው መልካሙ ቀረብኝ

ግዜዬን ሳልሰትህ ሕይወቴ ባከነብኝ

P a g e | 3


ፍቅር ፍቅር

ፍቅር ፍቅር እግዚአብሔር ፍቅር

የፍቅር ልጆች ስሊዚህ እንኑር በፍቅር

1 አሀ ግንዳችን ክርስቶስ አይደለም ወይ

አሀ በውድ ዋጋ የተገዛን

አሀ አንድ አይደል ወይ ሀገራችን

አሀ እርሱ ነው መገኛችን ደሙ ነው መገኛችን

እኮ ከየት መጣ አሀሀ የጎሳ ክፍፍል

አንድ አድርጎን የለም ወይ በልጁ አንድ አካል አንድ ብልት

በፍቅር አንድ አድርጎን አሀሀ አጣምሮን ካስቀመጠ

እንኑር በእርሱ ወግ በፍቅር የላዩ ከበለጠ

2 አሀ ወንድም ወንድሙን ሲጠላ

አሀ እርስበእርስ ስንጠላላ

አሀ እርሱን መምሰልን ትተን

አሀ በረናል በአለም ነገር ሄደናል በአለም ነገር

እኮ ምን ይጠቅማል አሀሀ የእከሌ ዘር ነኝ ማለት

አይኖርም በሰማይ በጎሳ ተከፋፍሎ መኖር

ባይሆን አሁን እንንቃ አሀሀ ይቅርብን መከፋፈል

ወንጌል ፍቅር እንጂ አይደለም ጎሳ ለይቶ ማደር

ምራኝ አባቴ ሕይወቴ አንተን እንዲመስል ኑሮዬ

ባረማመዴ እንዳርቅህ ከሚጠፉት እንዳልሆን

P a g e | 4


እኔስ በጌታዬ ደስ ይለኛል

እኔስ በጌታዬ ደስ ይለኛል

ሕይወት ከእርሱ ጋራ ተስማምቶኛል

ካቻምናን በድል አሳልፎኛል

አምናንም በክንዱ ደግፎኛል

አሁንም ከክብር ወደ ክብር ያሸጋግረኛል

1 ጠመዝማዛው መንገድ ዳገት ቁልቁለቱን

ህይወት ውጣ ውረድ ሲሆን በየለቱ

በሚያፀናው ክንዱ በሀይሉ ደግፎ

ቆምኩኝ በምስጋና በእርሱ ደስ እያለኝ

2 በዚያ ምድረበዳ አሩር በበዛበት

መናን እያበላ እኔን የመራበት

ከአለት ውሀ አፍልቆ ያጠጣኝ

እንዴት ይረሳኛል ጌታ ያረገልኝ

3 በለመለመው መስኩ የሚያሳድረኝ

በዕረፍት ውሀ ዘንድ ሁሌ የሚመራኝ

መልካም እረኛዬ የሚያሳጣኝ የለም

ጌታ ተስማምቶኛል ፍቅሩ አይሰለችም

4 በውጊያ ዘመኔ ያራመደኝ በድል

የጠላቴን ራስ ያስረገጠኝ ልዑል

ከክብር ወደ ክብር ያሸጋግረኛል

አዲስ ነገር እግዚአብሔር ዛሬም ያሳየኛል

P a g e | 5


በቁጣህ አትቅሰፈኝ

በቁጣህ አትቅሰፈኝ ጌታ

በቁጣህ አትቅሰፈኝ ኢየሱስ

ማረኝ ማረኝ ጌታ ሆይ ማረኝ

ማረኝ ማረኝ አባት ሆይ ማረኝ

1 በፊትህ ክፋትን አድርጌአለውና

ሀጢያቴም በደሌም እጅግ በዝትዋልና

ቅዱስ መንፈስህን አትውሰድብኝ

በቸርነትህ አቤቱ ማረኝ

2 አንተ ለእኔ ሞተህ ፍቅርህን አሳየኸኝ

እንዲሁ ወንድሜን እንድወድ አዘዝኸኝ

እኔ ግን ቃልህን ትዛዝህን ዘንግቼ

አለሁኝ ይልቁን ወንድሜን ጠልቼ

3 ክብርን ፍለጋ በብዙ የባከንኩ

ያንተን ፍቃድ ትቼ የራሴን ያስቀደምኩ

ቃልህን ያልታዘዝኩ ላንተ ያልተለየሁ

አለምን መስዬ ይኸው እንዲያው አለው

4 አገልጋይህ ሆኜ ስቆም በፊትህ

አንተን እንዳከብር ነው ምሳሌ ልሆንህ

በመውጣት መግባቴ ሌላው ወድቋልና

እባክህን ኢየሱስ ማረኝ እንደገና 5 መሀሪው አባቴ ወደ አንተ መልሰኝ

ምህረትን ሠጥተህ ወደ አንተ አስጠጋኝ

አባቴ ነህና በምክርህ ገስፀኝ

በቃልህ አቅንተህ ታማኝ ባሪያህ አድርገኝ

P a g e | 6


ያ በቂ ነው ለኛ መዳናችን

1 ሀጥያተኛ ሳለው ሞት የተገባኝ

በልጁ በደሙ አስገባኝ ከጉያው

ከእንግዲህ በኃላ ኩነኔ የለብኝም

በኔ ስራ ሳይሆን በእርሱ ፀደኩኝ

የዘላለም ህይወት አግኝቻለው እኔ

ከእንግዲህ በኃላ የለብኝም ኩነኔ/2x

አለም ሳይፈጠር በልጄ መርጦኛል

መርጦ አጽድቆ ደግሞ አክብሮኛል/2x

ከእንግዲህ ልጅ እንጂ ባሪያ አይደለሁም

አርነት ወጥቼ በእርሱ ድኛለሁ

በፈሰሰው ደሙ በመስቀል ጣር ሞቱ

እርግማኔን ሽሮ አረገኝ ህያው ልጁ/2x

ታድያ ምን ልበልህ ለውለታህ እኔ ምን ልክፈልህ

ክብር ነው ላንተ ምሰጥህ/4x

አመልክሀለው/12x

ዘምሩ አሀ ዘምሩ አሀ ለጌታ አሀ እልል በሉ አሀ/2x

ከሰይጣን እስራት እራሱ መርጦኛል

በከበረው ደሙ ነፃ አውጥቶኛል

የነበረብኝን የ እዳ ጽህፈት

በመስቀል ጠርቆ ሰጠኝ ነፃነት/2x

ታዲያ ምንድ ነው ከዚህ በላይ

ማምለጣችን ከዘላለም ስቃይ

ከአብቀኝ ከእርሱ ጋር መሆን

ያ ነው እኛን እንዲህ የሚያደርገን(የሚያዘምረን)

አንፈልግም ለምስጋና ርዕስ

አናለቅስም ለሚጠፋ ሀብት

የ አግዚአብሔር ልጆች መባላችን

ደግሞ የ እርሱ ወራሽ መሆናችን

ያ በቂ ነው ለኛ መዳናችን

ያ በቂ ነው ለኛ መዳናችን(መትረፋችን)

ከዘላለም ስቃይ በእርሱ ማምለጣችን

P a g e | 7


ነፍሴና

1 ሀብትን ሰብስቤ ስኖር በዚህ ዓለም

ከሌሎች እኩል ባለ እውቀት ሆኜ

በብር በወርቁ ልሸምት ፈልጌው

ምድሪቷን ዞሬ ሰላምን አጣው

ነፍሴና ህይወቴ የሚያርፍበት

እየሱስ ነው እፎይ ምልበት

2 ምንም ባይኖረኝ ባልጠጣ ባልበላ

ሁሉም ቢበተን ኑሮዬ ባይሞላ

ማይወሰድብኝ በምንም ሁኔታ

ልቤን ሞልቶታል ሰላሙ የጌታ

3 አለም ከሚሰጠው ሰላም ያለፈ

ወደ ውስጤ ነፍሴን አሳረፈ

ዘውትር እየሞላ ሕይወትን የሚያድስ

ሰላምን ሰቶኛል እንደወንዝ የሚፈስ

4 ደስ ይለኛል በእርሱ በዝቶልኛል ሰላሙ

በመስኩ ሆኜ በዚያ ለምለሙ

ልቤን ሀሳቤን እርሱ ጠብቆ

በደስታ ኖራለው ሀዘን ከኔ ርቆ

P a g e | 8


አቅሜ ሆይ

1 አውቃለው ያላንተ እንደማልበረታ

አቅም ካልሆንከኝ ትጥቄ እንደሚፈታ

በሄድኩበት ሁሉ አንተው ምራኝ

እንዳልደናቀፍ በእጆችህ ያዘኝ

አቅሜ ሆይ ብርታቴ

ጠራሀለው ሀይልህን ፈልጌ

ገስፀኝ ከአንተ እንዳርቅ

ታስፈልገኛህ ከሁሉ ይልቅ

2 ዝናቡ ሲወርድ ጎርፉ ሲመጣ

ንፋሱ ሲነፍስ ነፍሴን እንዳላጣ

የኑሮ ማዕበል ቤቴን ሲገፋ

እግሬን መቆም አቅቶት እንዳልጠፋ

3 ዘውትር የማየው የምሰማው

ከአንተ እያራቀኝ ግዜዬን በላው

ቃልህን ከልቤ እየነጠቀው

ህይወቴን የራሱ እንዳያደርገው

4 ባገኘው በሙሉ ልቤ እንዳይረታ

በምኞት ማዕበል ትጥቄ እንዳይፈታ

አቅም ሁነኝ ኢየሱስ በድካሜ ፋንታ

እንደቃልህ ልኑር ፍቅርህ ልቤን ገዝታ

P a g e | 9


ይሄ ነው ወይ

1 እርሱን እየተከተልኩ ብርሃን በኔ ከሌለ

እውነተኛ ፍቅሩ በውስጤ ካላደረ

መሆኔ ነው ወይ የእግዚአብሔር ልጅ

ከወንድሜ ጋራ ሳልወዳጅ

ይሄ ነው ወይ ያአምላክ ልጅ ምልክቱ

የተቤዠኝ ለዚህ ነው ወይ በሞቱ

ወራሹ እኔ ነኝ ወይ የሰማይ መንግስቱ

በምን እለያለው በአለም ካሉቱ

2 በጨለማ ስኖር ምን ይበሉ ያዩኝ

ልጁ ነኝ ብላቸው እንዴት ይመኑኝ

ተከታዩ መሆኔ በምን ይታወቃቸው

ያአምላክ ልጅነቴ እንዴት ይታያቸው

3 ለስጋዬ ምበላው ብቻ ካሳሰበኝ

ለብሼ ማጌጥበት ደግሞ ካስጨነቀኝ

በአለም ያሉትም ይህንን ይፈልጉታል

በአንተ ያላመኑትም ይህንን ይሹታል

4 በላይ ያለውን ልሻ የሚበልጠውን

ከምድር ያልሆነ ሰማያዊውን

ከእነርሱ እርቄ ይታይ ልጅነቴ

እንደ ልጅህ ልምሰል ደስ እንዲልህ አባቴ

እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማ በእርሱ የለም

አባቴ ከሆነ ልጁ ከሆንኩ እኔም

ይታወቅ/2x የአምላክ ልጅነቴ

ብርሃን ብቻ ይሁን ህይወቴ

P a g e | 10


ተባረክ የኔ ጌታ

1 መከራው ሲጠና ፈተናው ሲከብድ

ከአቅሜ በላይ ሁኔታው ሲያይል

አይኖቼን አነሳው ወደ ተራሮች

እረዳት ፍለጋ ሚሆነኝን ወዳጅ

ለካስ እረድኤቴ ሰማይን የፈጠርህ

ሁሉን ቻይ የሆንከው አንተ አባቴ ነህ

አልፈራም ከንግዲህ ከእኔ ጋር ስላለህ

የሚያስደነግጠኝ የሚያስፈራኝ የለም

አባቴ ከእኔ ጋር ነህ

ተባረክ የኔ ጌታ/2x

ስለማይነገር ስጦታህ

ስለ በዛልኝ ጥበቃ

ስለ ዋልክልኝ ውለታህ

ከፍ በል የኔ አሌኝታ

2 በምድረበዳው ጉዞ በሚያስጨንቀው

ማንም በሌለበት ሽብር በሞላው

ዙሪያዬን ሲዞር አጥፊው ሊውጠኝ

ወየው ጠፍው እያልኩ ፍርሀት ሲወረኝ

ድንገት ስትነሳ ድል መንሳት ለኔ ሆነ

ከተፍ ስትልልኝ ዲያቢሎስ አፈረ

ረዳት ሲያሻኝ ከጎኔ አልታጣህም

ቸል ብለኸኝም ላፍታም አልተውከኝም/2x

P a g e | 11


እግዚአብሔርን አመልከዋለው

እግዚአብሔርን አመልከዋለው

ምስጋናዬ ለሱ ብቻ ነው

ዝማሬዬ ለሱ ብቻ ነው

አምልኮዬ ለሱ ብቻ ነው

ስምህን ጠርቼ ድኛለሁ ከአውሬ

ስለዚህ አልፈራም ምድር ብትናወጥ

ቃልህ አፅንቶኛል አለሁኝ በህይወት

2 ለዘለዓለም የከበረ ስም ያለው

ኢየሱስ ብቻ ነው እንከን የማያውቀው

እሱ አምላክና ዘለዓለማዊ ነው

ለሚታመኑበት ምህረቱ ብዙ ነው

3 እንደ እግዚአብሔር ያለ ከቶ ይገኛል

ልጄን እየሱስን እንዲሁ ሰቶኛል

የመረጠን ጌታ ለርስቱ ለይቶ

ሀጢያተኞች ሳለን በደሙ ቀድሶ

P a g e | 12


እየሱሴ የልቤ ደስታ

እየሱሴ የልቤ ደስታ

ነፍሴ ረክታለች አንተን አግኝታ

እየሱሴ የልቤ ሰላም

አፈቅርሀለው ለዘለዓለም

1 አባቴ ነህ የውስጤ አዋቂ

ሳለወራህ ቀድመህ ዘላቂ

አሳቢዬ ከራሴ በላይ

አድጊያለው በእጆችህ ላይ

ላመስግንህ በምድር በሰማይ

2 ማን ሆነልኝ የሱስ እንዳነተ

ሳለቅስ አይተህ ሁሉን ተረድተህ

እንባዬንም ከአይኞቼ አብሰህ

ነፃ አረከኝ ጭንቀቴን ወስደህ

አሸነፍከኝ ፍቅርን አድርገህ

ኦሆሆ ኦሆሆ/2x

ሀሌሉ ሀሌሉያ/2x

P a g e | 13


እየሱስ እየሱሴ

ትልቅ ነው

ፍፁም ነው

ሁሉ የሆነው

በእርሱ ነው

1 ሰላሜ ነው እረፍቴ

የዘላለም ጋሻዬ

የመረጥከኝ ሳላይ አይተህ

አበዛኸኝ እንዲያው ወደህ

ምድረበዳው አንተው መርተህ

አሰፋኸኝ ህዝብን ሰተህ

እየሱስ እየሱሴ/2x

መጀመሪያዬ መጨረሻዬ

አልፋ ነህ ኦሜጋ

አንደኛዬ ለኔ ጌታ

አልተውከኝም አንዴም ላፍታ

2 አባቴ ነው አሳብዬ

እንዳልተፋ እረኛዬ

ያቀናልኝ ጎዳናዬን

አሳመረው መርገጫዬን

እርሱ ሆኖ መመኪያዬ

በእርሱ ፀና መቆሚያዬ

3 መሸሻዬ ከጠላቴ

ወዳንተ ነው እሩጫዬ

አስጠጋኸኝ ወደ ጉያህ

መንገድ ሆንከኝ እየመራህ

አስመለጥከኝ ከሚያስፈራው

ብርሃን ሆንከኝ በጨለማው

P a g e | 14


እግዚአብሔርን አመስግኑት

ምህረቱ ነው/3x

ቸርነት ያኖረን በቤቱ

ቸርነቱ ያቆመን በቤቱ

1 በሰማይ ያለልንን ጌታ

የመኖር እድልን ሚሰጠን

በእኛ ስራ ሳይሆን

በምህረት ይህን ቀን አየን

ጠላታችን ወድቆ

ከፍታው ተነጥቆ

ሸክማችን ቀሎልን

አረፍን በኢየሱስ

እግዚአብሔርን አመስግኑ ቸር ነውና/2x

ምህረቱ ለዘለዓለም ነውና

2 ችለን ሳይሆን ችሎልን

ጠላታችን ተሰብሮልን

በምድረበዳው ላይ

የሚያየንን አየን

ልኮልን እረዳት

አረካው ጥማችን

በስደት ሀገር ውስጥ

እሱ ሆኖ ጋሻችን

3 ተስፋን ሰቶልን ጌታ

ስንጠብቀው በዋይታ

ጊዜው ደርሶ መጣልን

ሳቅበሳቅ ሆኗል ቤታችን

አላሳፈረንም

የታመነው ጌታ

የቆየው ለእኛ ነው

ለሱ ግን ቀን አለው

አመስግኑት ሁሉ በእርሱ ሆነ

አመስግኑት ከኛ የሆነ ምን አለ

አመስግኑት ጠላታችን ሰጥሞ

P a g e | 15


በእግዚአብሔር ታስቢያለው

ታድያለሁ እኔ ታስቢያለሁ ባንተ

ታድያለሁ እኔ ተባርኬ ባንተ

1 አሳየኝ ልብህን ገልጠህልኝ ቃልህን

እውር ሆኜ ሳለው እውነቱ በራልኝ

ታድያለሁ ልበል አበራው ይህ አይኔን

ቀርቶ መሰባበር ሆነኝ አይቶ መኖር

2 አትራብም ነፍሴ አግኝታ ኢየሱሴን

የህይወት እንጀራ ሆኖላት ለነፍሴ

ምንም ነገር ሳይኖር አንተ ሆንኸኝ ተስፋ

በረከት ዘለዓለም ከቤቴ አይጠፋ

3 መዳኒት መጣልኝ ፈውስን አገኘውኝ

ትላቁን ስጦታ ህይወቱን ሸልሞኝ

ዘለዓለም እኖራለው ኢየሱስ ባለበት

በእርሱ አግኝቻለው ማያቀቋርጥ ህይወት

4 ያስጨነቀኝ ነገር ለመልካም ሆነልኝ

ተጽናናው በአንተ ፊትህን እያየሁኝ

ታድያለሁ ልበል አየሁኝ ይህን ቀን

ጠላቶቼ ጠፍተው እኔ አለሁ በህይወት

5 ንጉስ በዙፋኑ ተቀምጦ በግርማው

የብርሃናት አባት ሁሌም ብርሃን ነው

ሰላምህ በዝቶልኝ ኖራለው በደስታ

ሁሌ አከብርሀለው የሱስ የኔ ጌታ

P a g e | 16


ኢየሱሴ የልቤ ደስታ

የሱሴ የልቤ ነህ ደስታ

ጎኔ አለህ አትለየኝ ላፍታ

የአፌ የመከፈት ምክንያት

በጭንቄ ሆንክልኝ መጽናናት/2x

1 በስምህ አተረፍኩ እንጂ

ምንም አላጣው ከደጅህ

በለመለመ መስክ አደርኩ

በእረፍት ውሀ ዘንድ ተጓዝኩ

ነፍሴንም መለስካት ለስምህ

በፅድቅ መንገድ መራሀት

በእረኝነትህ አኖርካት

2 ቀንዴም በስምህ ከፍ አለ

በጠላቶቼ ላይ አየለ

የልመናዬን ቃል ሰማህ

ባንተ ያልሆነልኝም የለ

ሁሉንም ቻይነትህን በህይወቴ አኔ አወኩኝ

ለምኜህ ዘንበል አልክና

መሻቴም በአንተ ሞላና

አከበርኩህ ሴሎ ሄድኩና

አከበርኩህ ቤት ሄድኩና

ሰላም ካንተ ውጭ

እረፍት ካንተ ውጭ

ድስታ ካንተ ውጭ

አይገኝ ከሰው እጂ

3 ደስታህ ከምንጭህ ይፈልቃል

ማለዳ ማለዳ ይፈሳል

በማጣት ይሁን በማግኘት በስኬት ይሁን በውድቀት

በህይወት ጎዳና ሁሉ ጎሎ አያውቅም ነው ሙሉ

አትቆጥብ ለሁሉም ክፍት በልጅህ ላመነበት በየሱስ ላመነበት

P a g e | 17


ነገ መልካም ነው

ነገ መልካም ነው

መከታዬ እየሱስ ነው

ነገ መልካም ነው

ጋሻዬም እየሱስ ነው/2x

1 የተናገረውን የሚያደርገው ጌታ

እሱ ነው የእኔ የእኔም አሌኝታ

የምታመንበት መመኪያዬ እርሱ ነው

አዎን እላለሁኝ ነገ መልካም ነው

2 የመስዋአቱን በግ የሚያዘጋጀው ጌታ

ለሚደገፉበት የሚሆን መከታ

የአብረሀም አባት የይሳቅም መሪ

ይንገስ ይንገስ ይንገስ ብቻውን ይክበር

3 ደስ ይለኛል በርሱ አዎ ደስ ይለኛል

ልጁን እየሱስን እንዲሁ ሰቶኛል

ስላለ በውስጤ በቅድስ መንፈሱ

እኔም አመካለሁኝ ሁልግዜ በእርሱ

P a g e | 18


አልሰግድም

አልሰግድም

ለማያየኝ ለማይሰማኝ

በችግሬ ሰዓት መጥቶ ለማያድነኝ

እኔ አልሰግድም/2x

1 ክብር ለሚገባው ክብር እሰጣለው

አምልኮ ሚገባው እየሱስ ብቻ ነው

በምስል በምስል በወርቅ ለተሰራ

አልሰግድም አልሰግድም በእየሱስ ልኩራ

2 የስድራቅ የምሳቅ የአብድናጎ አምላክ

እኔን ያድነኛል ከእቶን እሳት

ባያድንም እንኳን እርሱ አምላኬ ነው

ጊዜና ሁኔታ ሁሉም ማይለውጠው/2x

3 ከአንበሶች ወጥመድ ዳንኤልን ያመጣህ

ታናሹን ሳሙኤል ወደ ክብር ያመጣህ

አንተን በማመኑ ሞገስን ሰጠኸው

እኔም የምሰግደው ለአንተ ብቻ ነው

P a g e | 19

Similar magazines