25.07.2013 Views

በኢህአዴግ ራዳር ስር የተንበረከከች አገር

በኢህአዴግ ራዳር ስር የተንበረከከች አገር

በኢህአዴግ ራዳር ስር የተንበረከከች አገር

SHOW MORE
SHOW LESS

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

8

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 191 ቅዳሜ ጥቅምት 18/ 2004

የአንበሳ አውቶቡስ ጉዞ እና ገጠመኞች

በናፍቆት ዮሴፍ

“ሰፈሬ ሽሮ ሜዳ እንደመሆኑ ከመርካቶ

17 ቁጥር አውቶቡስን ተሳፍሬ

ቅድስት ማሪያም ቤ/ክ ስንደርስ፣ አንድ

አዛውንት ኡኡታ አሰሙ ‹አውቶቡሱ

ሳይከፈት ወደ ፖሊስ ጣቢያ ይሂድልኝ›

ሲሉ ሹፌሩን ተማጠኑ፤ ሶስት ሺህ ብር

ተወስዶብኛል በሚል። ሹፌሩም አራት

ኪሎ አካባቢ (አሁን ፈርሷል) ፖሊስ

ጣቢያ አውቶቡሱን ይዘው ገቡ። ሁሉም

ሰው እንዲወርድ ተደረገ። ምን ዋጋ

አለው ሌባው ቀድሞ ወርዶስ ቢሆንስ

እያልን ወረድን

“የሆነ ሆኖ ሁሉም ሰው ወርዶ እንዲፈተሽ በአንድ

መቶ አለቃ ትዕዛዝ ከተላለፈ ከደቂቃዎች በኋላ

መቶ አለቃው ‹ሌባው ስለተገኘ ፍትሻውን አቁሙ›

ሲል ለባልደረቦቹ ትዕዛዝ አስተላለፈ። እጅግ መልከ

መልካም፣ አራቱም ጣቶቿ ላይ ወርቅ የደረደረች፣

አለባበሷ በእጅጉ የተዋበ ወጣት ላይ የመቶ አለቃው

አይን አረፈ።

“የወሰድሽውን ብር አምጪ” ብሎ ሲያምባርቅባት

የሁላችንም እጢ ዱብ አለ። “የምን ብር!? የሰውን

ማንነት ሳታውቅ አትናገር” ስትል ኮስተር ያለ መልስ

ሰነዘረች ወጣቷ። ይሁን እንጂ መቶ አለቃው፣

“ገብተሽ በጉማሬ አለንጋ ስትሞሸለቂ ታወጪ የለ?”

በማለት እየጎተተ ወሰዳት።

17 ቁጥር አውቶቡስ እና እኛ ተሳፋሪዎች ፖሊስ

ጣቢያው ውስጥ እንደተገተርን ደቂቃዎች፣ ብሎም

ሰዓታት አለፉ። ብዙ እናቶችና አባቶች፣ “ፍፁም

አታደርገውም፤ ለሌላ ጉዳይ ፈልጓት ይሆናል” ሲሉ

አጉተመተሙ። ልጅቷ ጠንከር ያለ አለንጋ ሳትቀምስ

አልቀረችም፣ “እሺ ተወኝ፤ የደበቅሁበትን ላሳይህ”

ስትል መሬት ተሰንጥቃ ብትውጠኝ ደስተኛ ነበርኩ።

በርካታው የአውቶቡሷ ተሳፋሪዎች የሚሆነውን

ለማየት አሰፈሰፍን። ልጅቷም ፖሊሱን እየመራች

የአውቶቡሷ መጨረሻ ወንበር ወደሚገኝበት ሄደች።

ሁሉም ይህን ጉድ ለማየት አሰፈሰፉ። የመጨረሻው

ወንበር ስትደርስ ሶስት ሺህ ብር ሶስት ቦታ በብር

ላስቲክ የታሰረ ስለነበር ከዛን በፊት አይቼው

በማላውቀው አይነት ወፍራም ፕላስተር ከወንበሩ

ስር ሶስት ቦታ አጣብቃዋቸለች። እሱን እየፈታች

ለፖሊሱ ስትሰጥ ያልደረሰባት የእርግማን እና የስድብ

አይነት አልነበረም። እኔ አፌ በድንጋጤ ተለጉሟል፤

በኋላ ግን “እንዴት ልታውቃት ቻልክ?” ስል መቶ

አለቃውን በድንገት ብጠይቀው፣ “አገር ምድሩን

ያጥለጠለቀው የእሷ ፎቶ ነው። ከዚህ በፊት በርካታ

የስርቆት ሪከርድ አለባት። ስንት ጊዜ መሰለህ ታስራ

የተፈታችው?” ሲል ምላሽ ሰጠኝ። እሷም ታሰረች፣

እኛም አውቶቡሳችን ውስጥ ገብተን ወደየምንሄድበት

ጉዟችንን ቀጠልን። የወጣቷም ያለመጠርጠር ጥረት

በዚህ አበቃ።”

ይህ ከላይ ያስነበብናችሁ ገጠመኝ አቶ ጥላሁን

ገዳሙ የተባሉ የ56 ዓመት ጎልማሳ ከ13 ዓመት

በፊት በአውቶቡስ ውስጥ ያጋጠማቸው እውነታ

ነው። አንበሳ የከተማ አውቶቡስ ከ1935 ዓ.ም ጀምሮ

በተለይም ዝቅተኛና መካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላላቸው

የህብረተሰብ ክፍሎች የማይረሳ ውለታ ባለቤት ነው።

ምንም እንኳን በአሁኑ ሰዓት የሀብታምና የድሀው

ልዩነት የሰማይና የምድርን ያህል ርቆ መካከለኛ

የኑሮ ደረጃ (Middle class) የሚባለው የህብረተሰብ

ክፍል የለም ብለን ለመናገር በሚያስችለን ደረጃ ላይ

ብንደርስም።

በአንበሳ የከተማ አውቶበስ ውስጥ እጅግ አስገራሚ፣

አሳዛኝ፣ አዝናኝና የተደበላለቀ ስሜትን የሚፈጥሩ

ትዕይንቶች የሚከሰቱበት የመጓጓዣ አውታር መሆኑን

ከማንም በላይ ተጠቃሚዎቹ ጠንቅቀው ያውቁታል።

ለዛሬም የተሳፋሪዎችን፣ የትኬት ቆራጮችን እና

የአንበሳ አውቶቡስ ሹፌሮችን ገጠመኞች እንቃኝ።

ከዚያ በፊት ግን ስለአንበሳ አውቶቡስ አገልግሎት

ጅማሮና የስራ ዘመኑ ጥቂት ማለት አግባብ ነውና

እነሆ።

ወራሪው የፋሺስት ጣሊያን መንግስት ሀገራችን ውስጥ

በነበረበት ጊዜ ይጠቀምባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችንና

የመኪና መለዋወጫ እቃዎችን በማሰባሰብ የስራና

መገናኛ ሚኒስቴር ይባል በነበረው መ/ቤት አማካኝነት

በ1935 ዓ.ም “የህዝብ ማመላለሻ” (ሕ.ማ) በሚል

ስም ነበር የተመሰረተው - አንበሳ የከተማ አውቶበስ

አገልግሎት።

ታህሳስ 2 ቀን 1944 ዓ.ም ህጋዊ ሰውነት በማግኘት

በአክሲዮን ከተቋቋመ በኋላ አረንጓዴና ቢጫ የተቀቡ

10 አውቶቡሶችን ይዞ ሥራ መጀመሩን የድርጅቱ

ማህደር ያመለክታል፤ እነዚህ አውቶቡሶች በከተማዋ

አራት መስመሮች ላይ የተሰማሩ እንደነበር ይነገራል።

ለህብረተሰቡ አገልግሎት ይሰጥ የነበረው የቀድሞው

ህዝብ ማመላለሻ የአሁኑ አንበሳ አውቶቡስ በዚያን

ወቅት የውጭ አገር ዜጎችን ጨምሮ 120 ሰራተኞች

ነበሩት።

በ1952 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይሰጥ የነበረው ትራንስፖርት

አገልግሎት መስመሩ ከ4 ወደ 14 እንዲያድግ ሲደረግ

በየመስመሩ ሲመደቡ የነበሩ አውቶብሶች ብዛትም

ከሁለት ወደ ሶስት ከፍ እንዲል ተደረገ። እንዲህ

እንዲህ አያለ በ1986 ዓ.ም በአዋጅ ቁጥር 187/1986

በ14 ሚሊዮን ብር ካፒታል “አንበሳ የከተማ አውቶቡስ

አገልግሎት ድርጅት” ተብሎ በአዲስ መልክ ራሱን

ችሎ ከተቋቋመ በኋላ በየጊዜው ቁጥሩ እየጨመረ

የሚሄደውን የከተማዋን ህዝብ ፍላጎት ለማሟላት

በተለያዩ ጊዜያት በርካታ አውቶቡሶችን በእርዳታና

በግዢ በማስመጣት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

በአሁን ሰዓት ድርጅቱ አዳዲስ 120 አውቶቡሶችን

ያስገባ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ አስሩ 18 ሜትር

እርዝመት ያላቸው፤ ተቀጣጣይ - አራዶች አኮርዲዮን

ይሏቸዋል - እንደሆኑ ከድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት

ኦፊሰር ከአቶ ሸዋረጋ ሳህሌ ለመረዳት ችለናል።

ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት በቀን 320 አውቶቡሶችን

ለስራ እንደሚያሰማራ የነገሩን አቶ ሸዋረጋ፣ ከ2740

በላይ ቋሚ ሰራተኞች እንዳሉትም ነግረውናል።

ስለአንበሳ አውቶቡስ አመሰራረት በጥቂቱ ከነገርናችሁ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ልዩ ቅኝት

ወደ ዋናው ሃሳባችን እንሆ ተመልሰናል።

የአንበሳ አጋጣሚዎች

አንበሳ አውቶቡስ ውስጥ ብዙ የሚከሰቱ ነገሮች

አንዳሉ ይደመጣል። በተለይ ደግሞ በሚፈጠረው

መተፋፈግና መነካካት የወንዶች ስሜት እንደሚነሳሳ

ይነገራል። የዚህ ሰለባ የሆነ አንድ ወጣት ተከታዩን

አጫውቶኛል፡- “ሁለት ወንዶችና አንድ ወጣት ሴት

ወደተሳፈርኩበት አውቶብስ ሲገቡ ተመለከትኩ።

ሆኖም ሴቷ ወደ እኔ በመጠጋት ትተሻሸኝ ጀመር።

ሁኔታዋ ሁሉ እኔን ወደ ሌላ ስሜት ውስጥ ከተተኝ።

በወቅቱ አውቶቡሱ ውስጥ ካሉት ወንዶች ውስጥ

ይህቺ ቆንጆ እኔን መርጣ በዚያ ሁኔታ ላይ መገኘቷ

ኩራት እንዲሰማኝ አድርጎኛል” ይላል ወጣቱ። ይሁን

እንጂ ወጣቱ በቆንጆዋ ሁኔታ ተማርኮ ስሜቱን

ሲያዳምጥ አብረዋት የነበሩት ሁለት ወንዶች ከኪሱ

1ሺህ አንድ መቶ ብር ሰርቀውት ከወረዱ በኋላ

መባነኑን ያስታውሳል። ቆንጆዋ ማደንዘዣ መሆኗ

ነው።

በአንድ ወቅት ነው አንድ ወጣት 19 ቁጥር አውቶቡስ

ውስጥ ተሳፍሮ ወደ አስኮ እየተጓዘ ነው። አንድ

ትልቅ አዛውንት ካፖርት ለብሰው ቆመዋል። “አባት

ልነሳልዎትና ወንበር ላይ ይቀመጡ አልኳቸው። ግን

ፈቃደኛ አልሆኑም” የሚለው ይህ ወጣት፣ መውረጃው

ሲቀርብ ለመውረድ ከወንበሩ ይነሳል። አዛውንቱ

የያዙትን ብረት ይዞ አውቶቡሱ እስኪቆም ለመጠበቅ

ሲሞክር አውቶቡሱ ይንገጫገጭና ልጁ ሚዛኑን

ይስታል። እናም የሚይዘው ሲያጣ ተንደርድሮ

የአዛውንቱ የካፖርት ኪስ ውስጥ ዘው ይላል።

አዛውንት ሆዬ ካፖርታቸው ኪስ ውስጥ ያለውን እጅ

ይይዙና እሪ ይላሉ። አውቶቡሱ ቆሞ ልጅና አዛውንቱ

ተያይዘው ፖሊስ ይደርሳል። “በህይወቴ አንደዚያ ያለ

ቅሌት ገጥሞኝ አያውቅም። በስንቱ ታቦት ብምል፣

ብገዘት ሰውየው ሊያምኑኝ አልቻሉም። ስለዚህ ጉዳዩ

እስኪጣራ ፖሊስ ጣቢያ አምሽቻለሁ” ሲል ባላሰበበት

መዋሉን ይናገራል።

ራሄል ይስማው ላፉት ስምንት አመታት የአውቶቡስ

ትኬት ቆራጭ ሆና ሰርታለች። በስራዋም ብዙ

ገጠመኞች አሏት። “አንድ ቀን 53 ቁጥር አውቶቡስ

ላይ እየሰራሁ ቲኬት ፈታሽ ይመጣል። አንዱ ትኬቱን

ጥሎት ስለነበር ፈታሹ ሁለት እጥፍ እንዲከፍል

ያስገድደዋል። ልጁ ዘና ብሎ፣ “እሺ እከፍላለሁ”

ብሎ ኪሱ ሲገባ ቦርሳው ተወስዷል” የምትለው

ራሄል፣ በዛን ሰዓት የነበረውን ድንጋጤ አሁንም

እንደምታስታውሰው ትናገራለች። በመጨረሻም

ሁኔታውን ሳይ እኔ ከፈልኩለት። እሱም ሌላ ቀን

እንደሚከፍል ነግሯት ስልኳን ተቀብሎ መውረዱን፣

በዚህም የተነሳ ለረጅም ጊዜ የፍቅር ጓደኛሞች ሆነው

መቆየታቸውን ትናገራለች።

ሞኖ ባንዶች

አውቶቡስ ውስጥ ሲጓዙ ምንም ድምፅ ሳይኖራቸው

የሚዘፍኑ አስቂኝ ማስታወቂያዎችን በመናገር

ከተሳፋሪው የሚቀፍሉ (የሚያባብሉ) [ዘመናዊ

የልመና አይነት ነው] በርካቶች ናቸው። እንደእነዚህ

አይነቶቹን ሰዎች እርሶ በተለይ አውቶቡስ ተጠቃሚ

ከሆኑ በተለያዩ ቁጥር አውቶቡሶች ላይ ያገኟቸዋል።

ራሳቸውን “ሞኖ ባንድ” እያሉ የሚጠሩም ያጋጥማሉ።

“ሞኖ ባንድ እንሰኛለን። እናንተን ለማዝናናት ምንጊዜም

ዝግጁ ነን። ይህን ማይክ የሰጠን እንዲህ አይነት

ሙዚቃ መሳሪያ አስመጪ ድርጅት ነው። የክብር

ስፖንሰራችን ደግሞ አንበሳ የከተማ አውቶቡስ ነው”

እና መሰል ነገሮችን በመደርደር ዘመናዊ ልመናዎች

ይካሄድበታል። አይ አንበሳ አውቶቡስ፤ “በእኔና በባስ

የማይመጣ የለም” ያለው ማን ነበር?

ቀዶ ጥገና

ቀዶ ጥገና ስንል የህክምናውን እንዳይመስልዎ።

በአውቶቡስ ውስጥም የቀዶ ጥገና በርካታ

ስፔሻሊስቶች እንዳሉ ልንጠቁምዎ እንጂ። በአንድ

ወቅት አንድ ጓደኛዬ የገጠመውን እንዲህ አጫዎተኝ።

ሰውየው ከጎጃም በርካታ ማር ጭነው አዲስ አበባ

ለነጋዴ ያስረክባሉ። እናም የዋሁና ገራገሩ የገጠር

ሰው በከረጢት ብራቸውን አንግተው ከኮታቸው ስር

አንጠልጥለዋል። ከዚያም ወደ ማረፊያቸው ይሄው

ጓደኛዬ ወደተሳፈረበት ስምንት ቁጥር አውቶቡስ

ውስጥ ይሳፈራሉ። አውቶቡሱ ትንሽ እንደተጓዘ

ቀዶ ጠጋኙ የሰውየውን ከረጢት (የሚጋፋ መስሎ)

በመቀስ ይሁን በምላጭ ከስሩ ይሸረክትና ብሩን በስር

በኩል ወስዶ አንዱ ፌርማታ ላይ ዱብ ይላል። ያኔ

አንገታቸው የቀለላቸው የማር ነጋዴ ደረታቸውን

ቢዳብሱ ጊዜ የከረጢታቸው ሆድ መቆዘሩ ቀርቶ ባዶ

ሆኗል።

እናም ሰውየው ኡኡ አሉ እንዲህ እያሉ፡- “እሪ

በል ሸዋ ጎጃም ተበላ እሪ በል ሸዋ ጎጃም ተበላ”።

እንዲህ ያሰኛሉ ቀዶ ጠጋኞች። ይህን የሰማ አንድ

ሌላ ሰው እንዳጫወተኝ ሁለት ጓደኛሞች እቃ ሊገዙ

መርካቶ ይሄዳሉ። አውቶቡስ ፌርማታው ላይ እያሉ

የአንዱ ስልክ ከኪሱ ይጠፋል። ሌላው ጓኛውን፣

“እንዴት ኪስህ ውስጥ ትይዛለህ” በማለት ተቆጣው።

ምክንያቱም እርሱ ሞባይል ስልኩን በማንጠልጠያ

አንገቱ ላይ አንጠልጥሎ ስልኩን ደረት ኪሱ ነው

የሚያስቀምጠው። እናም፣ “አሁን በቃ ተወስዷል።

ለሌላ ጊዜ አንደኔ እንዲህ አድርገህ ያዝ” ብሎ አንገቱ

ላይ ያለውን የስልክ ገመድ ሲስበው ስልኩ ተወስዶ

ገመዱ ብቻ ነው የቀረው። ኪሱን ቀዶ ጠጋኞቹ ቀደው

ስልኩን ወስደዋል። እንዲህ ናቸው ቀዶ ጠጋኞች፤

ከደረት ውስጥ ልብን ለመውሰድ ከአይን ላይ ኩል

ለመንጠቅ ረቀቅ ያለ ሰርጀሪ ይሰራሉ። ከእነርሱ

ይሰውረን ብሎ መፀለይ መልካም ነው።

“አንዴ ነው እቃ ለመግዛት በርከት ያለ ብር ይዤ

አውቶቡስ ውስጥ ነኝ። አንዱ ወጠምሻ አጠገቤ

ቆሟል። ይተሻሸኛል፤ ይገፋኛል። ‘ለምን ራስህን ችለህ

አትቆምም’ ስል ገሰፅኩት። ሆኖም ሊተወኝ አልቻለም”

ትላለች ለገሀር 32 ቁጥርን ስትጠብቅ ያገኘኋት

የትምወርቅ። ግፊያውና ፍትጊያው ሲሰለቻት አምርራ

መቆጣቷን የምትናገረው የትምወርቅ፣ “ቆይ ከእኔ

ምን ፈልገህ ነው እንዲህ የምትሆነው ብለው፣ ‘አንቺ

ገገምሽ አንጂ እኔማ ያጨቅሽውን ብር አይቼ ነው’

አለኝ - አይኑን በጨው አጥቦ፤ እንዴት አወቅክ

ብለው፣ ‘ከፈለግሽ አንኳን ቦርሳሽን ከስር የለበሽውን

የውስጥ ሱሪ ቀለም እነግርሻለሁ’ በማለት ቀልቤን

በድንጋጤ ገፈፈው” በማለት በጥርጣሬዋ ከሰርጀሪ

መዳኗን ታስታውሳለች። እነዚህ ቀዶ ጠጋኞች ቦርሳን

ብቻ ሳይሆን ውስጥንም ራጅ ማንሳት ይችላሉ እንዴ?

ያስብላል።

የቡድን ሥራ

አውቶቡስ ውስጥ ከሚፈጠሩ አጋጣሚዎች ውስጥ

የረቀቀው የሌቦች የቡድን ስራ ይጠቀሳል። ለዚህም

የተለያዩ ዘዴዎች ይፈበረካሉ። ከላይ እንደጠቀስነው

በሴት ተማርኮ ሲፈዝ ጓደኞቿ የሰረቁት አንድ ሺህ

አንድ መቶ ብር አንዱ የቡድን ስራቸው ውጤት

ነው። ‹‹የተግባረዕድ ተማሪ ሆኜ በአውቶቡስ ነበር

የምመላለሰው። እናም በወቅቱ የወር ክፍያ 48 ብር

ይዣለሁ›› በማለት ገጠመኙን የጀመረው ችሎታው

የተባለ ወጣት በወቅቱ በርከት ያሉ ወጣቶች አውቶቡስ

ውስጥ ገብተው በተንተን ብለው መቆማቸውን

ያስታውሳል። ከመካከላቸው አንዱ እጅግ ተጫዋችና

ሲበዛ ቀልድ አዋቂ ተሳፋሪዎች በሱ ጫወታ ሲፈዙ

ሌሎቹ ወደ ስራቸው ይሰማራሉ። ‹‹እኔንም የገጠመኝ

ይሄው ነው በልጁ ወሬ ተመስጨ ስፈዝ ለካስ ጓደኛው

ኪሴ ገብቶ 48 ብሩን ሊወስድ ይታገላል። በወቅቱ

ጠበብ ያለ ጅንስ ስለለበስኩ እጁ ሲነካኝ ነቃሁ››

በማለት እንዴት እንደተረፈ የሚገልፀው ችሎታው

አሁን ረቀቅ ያሉ ገፋፊዎች ስለተበራከቱ መጠንቀቅ

አንደሚያሻ ይመክራል።

መልካም አጋጣሚዎች

አንድ ነገር መጥፎ ጎን እንዳለው ሁሉ መልካም

ጎኖችም አይጠፉትም። የከተማ አውቶቡሶችም

እንዲሁ። ስርቆቱ ጾታዊ ትንኮሳውና መሰል ጥሩ

ያልሆኑ አጋጣሚዎች የሚፈጠሩ ቢሆንም መልካም

ነገርም ጎን ለጎን ይኖራል። ስማቸውን መናገር

ያልፈለጉ አንድ ጎልማሳ በአንበሳ አውቶቡስ ውስጥ

ለ17 አመታት አገልግለዋል። ድርጊቱ በተፈፀመበት

እለት ጠዋት ተነስተው በስራ ላይ ተገኝተዋል።

ሲያሸከረክሩ ውለው ከቀኑ ወደ 10 ሰዓት አካባቢ

ድንገት ታመው አውቶቡሱን መንዳት ያቅታቸዋል።

መሀል አስፋልት ላይ መኪናው ቀጥ ብሎ ይቆማል።

‹‹ምን እንደነካኝ ሳላውቅ ራሴን እንደመሳት አደረገኝ።

ምን እንደተፈጠረ አላውቅም ነበር›› የሚሉት እኚህ

ግለሰብ ከዚያም አንድ መስፍን የተባለ ወጣት እሳቸውን

አስነስቶ መሪውን በመጨበጥ ህዝቡን የሚፈልግበት

አድርሶ እርሳቸውንም ሀኪም ቤት ወስዶ ማሳከሙን

ያስታውሳሉ።

ሙሉጌታ የ60 ቁጥር አውቶቡስ ደንበኛ ነው።

ሁሌም ከአዲስ አበባ ደብረዘይት ከደብረዘይት አዲስ

አበባ ለመመላለስ ይህቺ አውቶቡስ ባለውለታው ናት።

ምክንያቱም በዛን ወቅት በአየር ኃይል ውስጥ ሬዲዮ

ኦፕሬተር ሆኖ ይሰራ ስለነበር ሁሌም ጠዋትና ማታ

ተመላላሽ ነው። ከሳምንቱ በአንዱ ቀን ከአየር ሀይል

ግቢ ስራውን አጠናቆ 60 ቁጥር ውስጥ ይገባል።

አውቶቡሱ ተጨናንቆ ስለነበር አንዲት ሴት ቦርሳዋን

እንዲይዝላት ትጠይቀዋለች። ይቀበላልም። ‹‹ቦርሳውን

ስትሰጠኝ መልኳን ልብ ብዬ አላየሁትም በኋላ ግን

ወደ አዲስ አበባ እየቀረብን ስንመጣ እንዴት ቦርሳዋን

አትጠይቀኝም እያልኩ አስብ ጀመር። ምክንያቱም ሰው

መንገድ ላይ እየወረደ አውቶቡሱ ቀለል ብሎ ስለነበር”

ይላል። ይሁን እንጂ አውቶቡሱ ለገሀር ደርሶ ሁሉም

ሰው ሲወርድ የቦርሳው ባለቤት የለችም ግራ ገባው።

‹‹ባለቦርሳ ብዬ እንዳልጠራ አንዷ ተነስታ የኔ ነው

ብትለኝስ ብዬ ዝም አልኩ›› ይላል ሙሉጌታ። እናም

በወቅቱ ቦርሳውን ወደቤቱ ይዞ ይሄድና መፈተሽ

ይጀምራል። በውስጡም ፖስፖርት፣ 5 ሺህ ጥሬ

ብር፣ የ19 ሺህ 500 ብር ቼክ፣ ሌሎች ወረቀቶች፣

የቀበሌ መታወቂያና የእጅ ሰዓት በቦርሳው ውስጥ

መኖሩን ማረጋገጡን ያስታውሳል። ‹‹ከራሴ ጋር

ብዙ ተሟገትኩ። መታወቂያው ላይ ባገኘሁት ስልክ

ልደውል አልደውል በሚል። -ደውልላት የሚለው ሀሳቤ

በማመዘኑ ደወልኩላት›› በማለት የነበረበትን የሀሳብ

አጣብቂኝ ይናገራል። ሙሉጌታ ስልኩን በደወለ ጊዜ

ያነሳው ወንድ ነበር። ስለሁኔታው ሲነግረው ‹‹መልሰን

እንደውል ትንሽ ችግር አጋጥሟት አልተረጋጋችም››

ብሎ አንደመለሰለት ከገለፀ በኋላ በዛን ወቅት

ተንቀሳቃሽ ስልክ ስላልነበረው የእናቱን የቤት ስልክ

ቁጥር መስጠቱን ይናገራል። ‹‹ደወለችልኝ ከዚያም

እናቷ በድንገት ታመው አደጋ ውስጥ እንደነበሩ

ስትሰማ ገና ዱከም ስትደርስ ደንግጣ አንደወረደችና

ፈፅሞ ቦርሳውን እንዳላስታወሰች ነገረችኝ›› ይላል

ሙሉጌታ።

ልክ በአራተኛው ቀን ደውላ ደብረዘይት ከመጣ

እንዲያቀብላት መጠየቋን የሚገልፀው ይህ ወጣት

ቦርሳውን ይዞ ደብረ ዘይት ይሄድና በተቀጣጠሩበት

ቦታ ይገናኛሉ። ቤቷ ይዛው ልትሄድ ብትሞክርም

የስራ ሰዓት በመድረሱ ከስራ ሲወጣ እንደሚያገኛት

ቀጠሮ ይዞ ወደ ስራው ያመራል። ሲወጣም በቀጠሮው

መሠረት ቤቷ ይሄዳል። ዝምድናው ከዚህ ይጀምራል።

አሁን ግን የሴትዮዋን ልጅ አግብቶ ሁለት ልጆችን

በመውለድ ባለቦርሳዋን አያት አድርጓታል። መልካም

አጋጣሚ ይሏል ይህ ነው።

‹‹በባስ ውስጥ እየሄድኩ ነው በቁመት ከእኔ እኩል

የሆነ ወጣት ፊት ለፊቴ ቆሟል አንድ ብረትም

ተጋርተን ይዘናል›› ትላለች ረዘምና ጠየም ያለችው

የ29 ዓመት ወጣት አይናለም ዳርሜለህ። ድንገት

ሳይታሰብ አውቶቡሱ ፍሬን ይዞ በመንገጫገጩ እሷና

ከፊት ለፊቷ የቆመው ወጣት ሚዛናቸውን ስተው

ሲወዛወዙ ከንፈራቸው መገጣጠሙን ትናገራለች።

‹‹እነሆ በዚያች በተቀደሰች አጋጠሚ የተነካካው

ከንፈራችን ዛሬም አልተላቀቀም /ተጋብተናል/ በማለት

አስገራሚውን ገጠመኘዋን ትናገራለች።

የስሜት አንበሶች

አንበሳ አውቶቡስ ውስጥ ተሳፍረው እየተጓዙ

ስሜታቸው አንበሳ ሆኖ ጾታዊ ትንኮሳ የሚያስከትሉትስ

ስንቶቹ ናቸው? መቼም እዚህ ጋዜጣ ላይ ለመፃፍ

ባይበቃም በአውቶቡስ ውስጥ የሚያጋጥሙ አፈንጋጭ

የወሲብ ጥቃቶች በርካቶች ናቸው። እንደውም

ገና የሴት ቀሚስ ሲነካቸው ደርሶ ወንድነታቸው

የሚገነፍል፣ በአይን ብቻ ሴትን ለመተኛት ጥረት

የሚያደርጉ ከዚያም አልፈው ተርፈው ‹‹በማንም

አያየኝም›› ድፍረት አስቀያሚ ድርጊት ሲፈፅሙ

በሆነ አጋጣሚ ለሰዎች እይታ ተጋልጠው ውርደት

የሚከናነቡ፣ ይህም ካልሆነ ጣጣቸውን ሰው ላይ

ለጥፈው እስከመሄድ የሚደርሱ ስንቶቹ ናቸው?

እነሆ ገጠመኝ።

‹‹በአንድ ወቅት በ46 ቁጥር ከገርጂ ወደ ካዛንቺስ

እየተጓዝኩ አንዱ ይተሻሸኛል። እናም እሸሻለሁ።

እርሱ እየተጠጋ ስሜቱን ለማርካት ይጣጣራል››

ትላለች ኤፍራታ አዲሱ የተባለች ወጣት። እንደ

ኤፍራታ ገለፃ ሰውየው ፍፁም ስሜት ውስጥ ስለነበር

ምንም ማስተዋል እንደተሳነው ታስታውሳች። ‹‹ነገሩ

ሲብስብኝ ለምን አታርፍም? የሚል ጥያቄ ሳነሳ

‹አርፈሽ ቁሚ ብዬሻለሁ› በማለት አንዴ በጥፊ

ሲያጮለኝ ጮህኩኝ›› የምትለው ኤፍራታ ሰዎች

ምንድነው ብለው መሀል ሲገቡ እሱ ኃፍረተ-

ስጋውን ከሱሪው ውጭ አድርጎት ነበር›› በማለት

በዕለቱ የደረሰባትን ውርደት አስታውሳ ትስቃለች።

በወቅቱ ሰዎች ባይገላግሉሽ ምን እርምጃ ትወስጂ

ነበር የሚል ጥያቄ አንስተንላት ‹‹ባገኘሁች አጋጣሚ

ከስሩ እንደችግኝ ነቅዬ ነበር በእጁ የምሰጠው››

በማለት ስቃ እኛንም አሳቀችን። በነገራችን ላይ በጣም

የሚያሳዝነው አንድ እናት የ7 ዓመት ሴት ልጃቸውን

አውቶቡስ ውስጥ ወንበር ላይ ለተቀመጠ ትልቅ ሰው

አደራ በማለት እናት ይቆማሉ። ከደቂቃዎች በኋላ

ኅጻኗ አውቶቡሱን በእሪታ ታቀልጠዋለች። ሰውየው

ጭናቸው ላይ አስቀምጠው ደፍረዋታል። ይሄውና

ተፈርዶባቸው ዘብጥያ ወርደው ይገኛሉ። እንዲህና

መሰል ሰቅጣጭ ክስተቶች በአንበሳ አውቶቡስ ውስጥ

ይካሄዳሉ።

አዎ በከተማ አውቶቡስ ውስጥ በርካታ ገመጠኞች

አሉ። አዝናኝም አሳዛኝም፣ አስነዋሪም፣ አስገራሚም።

እርሶ የትኛው አጋጣሚ ደርሶዎት ይሆን? ክፉው

ወይስ ደጉ? እንጃ ብቻ ከቀዶ ጠጋኞቹም ከቡድን

ሰራተኞቹም ከቀፋዮቹም ራስን መጠበቅና መጠንቀቁ

አይከፋም። መልካሙን አጋጣሚ መጠቀምም

ብልህነት ነውና አውቶቡስ ተጠቃሚዎች ሆይ ቸር

ይግጠማችሁ እንላለን።

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!