25.07.2013 Views

በኢህአዴግ ራዳር ስር የተንበረከከች አገር

በኢህአዴግ ራዳር ስር የተንበረከከች አገር

በኢህአዴግ ራዳር ስር የተንበረከከች አገር

SHOW MORE
SHOW LESS

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

መንግሥት በዜጎቹ ላይ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 191 ቅዳሜ ጥቅምት 18/ 2004

ለምን ምቀኛ ይሆናል?

በግርማ ሰይፉ

በ ገፅ 14

4ኛ ዓመት ቁጥር 191 ቅዳሜ ጥቅምት 18 2004 ዋጋ 7፡00 ብር

ከህዝብ ጥቅም ይልቅ

የራስን ፖለቲካዊ ምህዳር

ማስጠበቅ

በኢህአዴግ ራዳር ስር የተንበረከከች አገር

በ ገፅ 4

ስር ራዳር በኢህአዴግ

ካሳ ሳይሰጥ እንዳልቀረ ተጠቆመ

በሱራፍኤል ግርማ

የቀድሞዋ ሶማሊያ አካል በነበረችው ፑንትላንድ ውስጥ ሞት ተፈርዶበት

ዕለተ-ሞቱን ሲጠብቅ የነበረውን ኢትዮጵያዊ፤ ድምፃዊ ቴዎድሮስ

ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ ሳይታደገው እንዳልቀረ ለአርቲስቱ ቅርበት ያላቸው

የአውራምባ ታይምስ ምንጮች ገለፁ።

በውስጥ ገፅ

የአቶ መለስ የአደባባይ ምስክርነት

ከዳኝነት ነፃነት አንፃር

ከምንጮቻችን ባገኘነው መረጃ መሠረት፣ በሰው መግደል

ወንጀል ተከሶ በሞት እንዲቀጣ በጎሳ መሪዎች ውሳኔ የተላለፈበት

ኢትዮጵያዊው አስመሮም ኃይለሥላሴ ላጠፋው ነፍስ ካሳ 700

ሺህ ብር እስከ ትናንት ዓርብ ድረስ መክፈል ከቻለ በነፃ

እንደሚወጣ የሚያመለክት ዜና በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ

በ ገፅ 19

በውስጥ ገፅ

ማፊያ

በ ገፅ 3

“ሽብርተኝነት ለኢትዮጵያ ባዕድ የሆነ ነገር ነው

…በዚህ ሰበብ ሽብርተኝነትን እንዳናስተምር እሰጋለሁ”

አቶ መለስ ሲናገሩ አቃቤ ሕጎች፣ ዳኞችና ፖሊሶች ይኼንን

ተከትለው ይሄዳሉ ብለው እንኳን አያስቡም

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም

‹‹ንቦች አሜሪካ ውስጥ አስቸገሩ››

ሬዲዮ ፋና

‹‹ፋና ሆይ ንቦች ያላስቸገሩበት የት አይታችኋል?››

የታች ሰፈር ልጆች

በዳዊት ከበደ

ቴዲ አፍሮ በሶማሊያ ሞት ለተፈረደበት ኢትዮጵያዊ

ባሕርያቱና ከዴሞክራሲ

እጦት ጋር ያለው ቁርኝት

ሲፒጄ፣ ‘በጋዜጠኞች

ላይ የሽብርተኝነት

ውንጀላው ተጠናክሮ

ቀጥሏል’ ሲል ገለጸ

ባለፈው ሳምንት፣ ጠ/ሚኒስትር

መለስ ዜናዊ በአገሪቱ ውስጥ ያሉትን ጋዜጠኞች

በ“ተላላኪ መልዕክተኝነት” እና “ሽብርተኝነት”

መወንጀላቸውንና አንድ የመንግሥት ጋዜጣ ደግሞ

የነፃው ፕሬስ ኤዲተርን ከሽብርተኞች ጋር ግንኙነት

አለው በማለት የፀጥታ ኃይሎች በጋዜጠኛው ላይ

“እርምጃ እንዲወስዱበት” እንደጠየቀ በማስታወስ፣

በግሉ ፕሬስ ላይ እየተደረገ ያለውን የማሸማቀቅና

የማስፈራራት ዘመቻውን የጋዜጠኞች መብቶች

ተሟጋቹ አውግዟል።

ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ብዙዎቹ

በኢትዮጵያ ያሉ ጋዜጠኞች ከ“ሽብርተኛ”

ቡድኖች ጋር የሚሰሩ “ተላላኪ-መልዕክተኞች”

እንደሆኑና የታሰሩ ጋዜጠኞች ከሽብር ድርጊቶች

ጋር የሚያስተሳስራቸው ቁርኝት እንዳለ የሚያሳይ

ማስረጃ መንግስታቸው ያለው መሆኑን፣ ሌሎች

በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ጋዜጠኞችም ከሽብርተኞች

ጋር ትስስር እንዳላቸው ባለፈው ሀሙስ በፓርላማ

ባደረጉት ንግግር መጠቆማቸውን ሲፒጄ

ገልጿል።

ከሰኔ ወር ጀምሮ የመንግሥት

ባለሥልጣናት ስድስት የነፃው ፕሬስ ጋዜጠኞችን

በሽብርተኝነት ክስ ወንጅለው ማሰራቸውን

ያወሳው ሲፒጄ፣ የአውራምባ ታይምስ የቀድሞ

ምክትል ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፣

የፍትህ ጋዜጣ አምደኛ ርዕዮት ዓለሙ፣ ጋዜጠኛ

እስክንድር ነጋ እና ስለሺ ሐጎስ፣ እንዲሁም ጆሃን

ፐርሰንና ማርቲን ሽብዬ የተባሉ ሁለት ስዊድናውያን

ጋዜጠኞች በሽብርተኝነት ተጠርጥረው በእስር ላይ

እንደሚገኙ አስታውሷል።

የኢትዮጵያ የግል ፕሬሶችን “ጋጠ-

ወጦች” ሲሉ የገለፁት ጠ/ሚኒስትር መለስ

እነዚህን የግል ፕሬሶች ሞያቸውን ያልተረዱ ሲሉ

በውስጥ ገፅ

በ ገፅ 16

በ ገፅ 19

መቆሚያ ያጣው የዋጋ ግሽበት

ገንዘብ ያለገደብ የሚጨመርበት ኢኮኖሚ ለጊዜው ያደገ

እንደሚመስል ፊኛ ነው ‹‹ፊኛ ውስጥ አየር ሲጨመር

የፊኛው መጠን ይተልቃል፤ አየሩ ፊኛው ከሚችለው በላይ

ሲሆን ግን ፊኛው መፈንዳቱ አይቀርም››

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

2

የካቲት 2000 ዓ.ም

ተመሠረተ

አውራምባ ታይምስ፡- በብሉ

ኤርዝ ጀነራል ቢዝነስ ኃላ/የተ/

የግል/ማህበር ስር የሚታተም፤

በፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ

የሚያተኩር፤ በንግድ ሚኒስቴር

በቁጥር 020/2/6572/2001

የተመዘገበ ሳምንታዊ ጋዜጣ ነው፡፡

T’@Í=”Ó ›?Ç=}`

Ç©ƒ ŸuÅ

ª“ ›²ÒÏ

õì

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 191 ቅዳሜ ጥቅምት 18/ 2004 3

ምን ነካቸው?›› ፤ ‹‹ዛሬ

ላይ እንዲህ መቆጣት ለምን

‹‹ሰውዬው

አስፈለገ?››፣ ‹‹ለምንስ እንዲህ

አመረሩ›› እነዚህንና ሌሎች መሰል

አስተያየቶች አቶ መለስ ዜናዊ ባለፈው

ሀሙስ ጥቅምት 9 ቀን 20004 ዓ.ም

በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተገኝተው

ያቀረቡትን ማስጠንቀቂያ አዘል ንግግር

ተከትሎ በአዲስ አበባ የተለያዩ ስፍራዎች

(ለፖለቲካዊ ጉዳዮች ብዙ ትኩረት

በማይሰጡ ዜጎችም ጭምር) ሲሰነዘሩ

የሰነበቱ የግርምት አስተያየቶች ናቸው፡፡

የ1997ቱን ምርጫ ተከትሎ በአገሪቱ

ፖለቲካዊ ቀውስ በተፈጠረበት ወቅት

አቶ መለስ ከሰነዘሯቸው መሰል

ማስጠንቀቂያዎች ጋር አቆራኝተው

ለማነጻጸር የተገደዱ ወገኖችም አልጠፉም፡

፡ ቀላል የማይባል ቁጥር ያላቸው

ወገኖችም ማስፈራሪያው አነጣጥሮባቸዋል

ያሏቸውን የአውራምባ ታይምስና ፍትህ

ጋዜጣ አዘጋጆችን ሲያፅናኑና አማራጭ

ያሉትን ምክርና የመፍትሄ አስተያየት

ሲሰነዝሩ ተስተውለዋል፡፡

ህገ መንግስቱን ማክበር

ጥፋት ነውን?

ባለፈው ሀሙስ ከአንዱ በስተቀር

የኢህአዴግ አባላት የሆኑ ‹‹ተመራጮች››

ብቻ የተሰባሰቡበት የኢትዮጵያ

ፓርላማ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ

የሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች እጅግ አሰልቺና

ተመሳሳይነት ያላቸው አይነት ነበሩ። ወደ

መጨረሻ አካባቢ ግን ወ/ሮ አታለል መላኩ

(እሳቸውም ገዢውን ግንባር የሚወክሉ

የም/ቤቱ አባል) ያቀረቡት አቤቱታ አዘል

ጥያቄ ግን የጉዳዩ ባለቤቶችን ብቻ ሳይሆን

የብዙዎችን ትኩረት የሚስብ ነበር።

‹‹በሽብር ተጠርጥረው የታሰሩ ሰዎች

ጉዳይ በፍርድ ቤት ተይዞ ሳለ አንዳንድ

የግሉ ፕሬስ ተቋማት የሰዎቹን ነፃ መሆን

እየመሰከሩ ነው፡፡ የጋዜጦቹ ፍላጎትና

የአቶ መለስ የአደባባይ ምስክርነት

ከዳኝነት ነፃነት አንፃር

በዳዊት ከበደ

አላማ ግልፅ ሆኖ ሳለ መንግሥት ክስ

አለመጀመሩ ለዚህ ችግር አስተዋፅዖ

አበርክቷል።›› ነበር ያሉት የፓርላማ

አባሏ፡፡ በእኒህ የተከበሩ የፓርላማ አባል

የተሰነዘረውና ከላይ ሰረዝ የጨመርኩበትን

‹‹አላማችንና ፍላጎታችን›› ምን እንደሆነ

በድምዳሜ የተጠቀሰው ጥንቆላ ቢብራራ

ፍላጎቴ ቢሆንም እሱን ወደ ጎን ትቼ

ተጠርጥሮ በሕግ ጥላ ስር የሚገኝ

ሰው ከፍርድ በፊት ‹‹ነፃ ነው›› ወይስ

‹‹ወንጀለኛ›› በሚለው ጉዳይ ላይ ሕገ-

መንግስቱ የሚለውን ላስታውሳችሁ።

በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 20 ንዑስ ቁጥር

3 ላይ ተከሳሾች ‹‹በፍርድ ሂደት ባሉበት

ጊዜ በተከሰሱበት ወንጀል እንደጥፋተኛ

ያለመቆጠር መብት አላቸው›› ይላል።

ከዚህ አንጻር ይህንን ሕገ-መንግስታዊ

ድንጋጌ አክብሮ ‹‹ነጻ ናቸው›› ብሎ

የሚያምን ግለሰብ ይሁን ተቋም

‹‹ጋጠወጥ›› የሚባልበት ምክንያት

ምንድነው?

ህጉ በተጨባጭ ከእንግሊዝና ከአሜሪካ የተቀዳ ከሆነ፤ ኢትዮጵያ ሲደርስ ለምን የተቃዋሚዎችና የሚዲያዎች ስጋት ሆነ? ለምንድነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን በእንግሊዝ ፓርላማ

ቀርበው በሌቨር ፓርቲ አመራሮች ላይ ሲዝቱ አሊያም ደግሞ የዘ-ጋርዲያን ጋዜጣ አዘጋጆችን ‹‹ጋጠወጥ›› ሲሉ የማንመለከታቸው? ለምንስ ነው ፕሬዚዳንት ኦባማ በኮንግረስ ተገኝተው

የሪፐብሊካን አመራሮችን በሽብርተኝነት የማይወነጅሉት? ለምንስ ነው የኒው ዮርክ ታይምስ ኤዲተሮችን ‹‹የጋዜጠኝነት ሀሁ የማይገባቸው›› ብለው ሲዘልፉ የማንመለከታቸው?

አቶ መለስ ሕገ-መንግስቱን ስለማክበርና

ስለማስከበር ደጋግመው እየነገሩን

ነገር ግን ከላይ የጠቀስነውን ሕገ-

መንግስታዊ ድንጋጌ በመጣስ ተቃራኒውን

እንድንመሰክር ነው እየወተወቱን ያሉት፡

፡ እንኳን እኛ ይቅርና አንድን ጉዳይ

የሚይዙ ዳኞች እንኳን በተቻለ መጠን

የተከሳሽን የንጹህነት መርህ ግምት ውስጥ

በማስገባት ሊያስቀጣ የሚችል ተጨባጭ

ማስረጃ በአቃቤ ህጉ በኩል አሳማኝ በሆነ

መልኩ እንዲቀርብ ነው የሚጫኑት፡፡ ይህ

የሆነበት ምክንያት አንድም አቃቤ ህግ

ግዙፍ መንግስታዊ አካል እንደመሆኑ

ከተከሳሽ (ግለሰብ) ጋር ሲነጻጸር የአቅም

ውስንነት ግምት ውስጥ ስለሚገባ፤

ሁለተኛ ደግሞ ተከሳሹ እስኪፈረድበት

ድረስ ነጻ ነው ተብሎ ስለሚታሰብ ‹‹ነጻ››

የተባለው ግለሰብ ‹‹ወንጀለኛ ነው›› ብሎ

ለመደምደም ከፍ ያለው የቤት ስራ የአቃቤ

ህጉ በመሆኑ ነው፡፡ በተለይ ተከሳሹ

ጥፋተኛ ከተባለ በኋላ የሚወሰንበት

ቅጣት በግለሰቡ ሁለንተናዊ ነጻነት ላይ

ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት ግምት

ውስጥ በማስገባት ተከሳሹ በተጨባጭ

ወንጀሉን መፈጸሙና አለመፈጸሙ

ብዥታ በማይፈጥር መልኩ መረጋገጥ

ስላለበትም ነው፡፡ ታዲያ እነዚህን

ከመሳሰሉ አጠቃላይ ድንጋጌዎችና ስነ

አመክንዮ አንጻር የመንግስትን የመጨረሻ

ስልጣን ከጨበጡት አቶ መለስ አንደበት

‹‹ከበቂ በላይ ማስረጃ አለን፤ ሰዎቹ

ወንጀለኞች ናቸው›› የሚል የአደባባይ

ምስክርነት ሲቀርብ በዳኝነት ሂደቱ ላይ

የጎላ ተጽእኖ የማሳረፍ አቅም የሚኖረው

ማነው? እኛ ወይስ አቶ መለስ? ሕገ-

መንግስቱን የማክበርና የማስከበር ሂሳብ

እናወራርድ ከተባለ ስህተቱ ጨርሶ የእኛ

አይደለም፡፡ ህገ መንግስቱን ካከበርነው

በደንብ እናክብረው እንጂ!

የእኛ ጥፋት

ለመሆኑ ‹‹ተጠርጥረው በህግ ጥላ ስር

ያሉ ሰዎች “ድብደባ ተፈፅሞብናል”

እያሉ ነው፣ ቤተሰቦቻቸው እንዲጎበኟቸው

አልተፈቀደም›› ይህ ከሕገመንግስቱ ጋር

አብሮ አይሄድም፡፡ ህግን የማስከበር

ኃላፊነት በተጣለባቸው ሰዎች ህገ

መንግስቱ መደፍጠጥ የለበትም›› ብሎ

መጠየቅ “በቅድመ ሁኔታ የተሰጠን

ይቅርታ ሊያሰርዝ የሚችል ወንጀል”

የሚሆነው በምን አይነት የኦሪት ህግ

ነው? በሕግ ጥበቃ ስር ያሉ ሰዎች በሕገ-

መግስቱ መሠረት በተፋጠነ ሁኔታ ፍ/

ቤት ይቅረቡ ብሎ መጠየቅስ በ”ጋጠ-

ወጥነት” የሚያስፈረጀው በምን አይነት

ስነ-አመክንዮ ነው? እኛና ሚዲያዎቻችን

እንደሚሉት ሁሉ እናንተም

ወንጀለኛነታቸውን በአደባባይ መስክሩ

አለበለዚያ “የጋዜጠኝነት ሀሁ አታውቁም”

የምንባለውስ ለምንድነው? የጸረ ሽብር

አዋጁ ለሰፊ ትርጓሜ እጅግ የተጋለጠ

በመሆኑ ነው ለዚህ ሁሉ መቅሰፍት

ምክንያት እየሆነ ያለው፤ እናም አዋጁ

በድጋሚ ይሻሻል ብሎ ሀሳብን መግለጽ

‹‹በሽብርተኞች መልእክተኛነት››

የሚያስፈርጀው ብሎም ሽብርተኝነትን

እንደማበረታታትና የሚቆጠረው

ለምንድነው?

‹‹ቃል በቃል ከውጭ

የተቀዳው›› ሕግ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፀረ-ሽብርተኝነት

ሕጉ ‹‹እንከን የለሽ›› መሆኑን ለማስረዳት

‹‹ቃል በቃል ከምዕራባዊያን የተቀዳ››

መሆኑን ነግረውናል። የምንኖርበትን

አገር ተጨባጭ ሁኔታ ግምት ውስጥ

ሳይገባ አንድ ህግ እንዴት ቃል በቃል

ከውጭ ይኮረጃል፡፡ ሀሳቤን ይበልጽ

ግልጽ ለማድረግ እዚህ ላይ አንድ አብነት

መጥቀሱ ተገቢ ይመስለኛል፡፡ ሰሞኑን

ስለተጨማሪ እሴት ታክስ አሰራር

ለንግዱ ማህበረሰብ ግንዛቤ ለማስጨበጥ

በተጠራ የግንዛቤ ማስጨበጫ ወርክሾፕ

ላይ አንድ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ የተናገሩት ነው፡፡

ሰውዬው እንደገለፁት ኬንያ ተግባራዊ

ያደረገችው የተጨማሪ እሴት ታክስ

ሕግ ቃል-በቃል ከእንግሊዝ የታቀዳ ነው

አሉ። እናም እንግሊዝ የበረዶ ሸርተቴ

የሚያዘወትሩ ዜጎቿን ለማበረታታት

ስትል ‹‹የበረዶ ማንሸራተቻ መሳሪያዎች

ታክስ ሊከፈልባቸው አይገባም›› የሚል

ድንጋጌ በታክስ ሕጓ ላይ አስፍራለች።

በአገሯ ምንም አይነት በረዶ የሌላት

ኬኒያ ሕጉን ቃል-በቃል ከእንግሊዝ

ቀድታ ተግባራዊ ማድረጓን በመጥቀስ

ኃላፊው ተሳታፊውን ፈገግ አሰኙት።

ሰውየው አያይዘውም ኢትዮጵያ

ግን የታክስ ህጉን ከሌሎች አገሮች

ብትኮርጅም ከአገሪቱ ነባራዊ ሁኔታዎች

ጋር በማዛመድ ተግባራዊ አድርጋዋለች

አሉ። ታዲያ የጸረ ሽብር ህጉስ

ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ አንጻር ለምን

አልተቃኘም? እሺ እሱም ይቅር ህጉ

በተጨባጭ ከእንግሊዝና ከአሜሪካ

የተቀዳ ከሆነ፤ ኢትዮጵያ ሲደርስ ለምን

የተቃዋሚዎችና የሚዲያዎች ስጋት

ሆነ? ለምንድነው ጠ/ቅላይ ሚኒስትር

ዴቪድ ካሜሮን በእንግሊዝ ፓርላማ

ቀርበው በሌቨር ፓርቲ አመራሮች ላይ

ሲዝቱ አሊያም ደግሞ የዘ-ጋርዲያን

ጋዜጣ አዘጋጆችን ‹‹ጋጠወጥ››

ሲሉ የማንመለከታቸው? ለምንስ

ነው ፕሬዚዳንት ኦባማ በኮንግረስ

ተገኝተው የሪፐብሊካን አመራሮችን

በሽብርተኝነት የማይወነጅሉት? ለምንስ

ነው የኒው ዮርክ ታይምስ ኤዲተሮችን

‹‹የጋዜጠኝነት ሀሁ የማይገባቸው››

ብለው ሲዘልፉ የማንመለከታቸው?

አዎ! ምክንያቱ በጣም ግልጽ ነው፤

የአሜሪካም ሆነ እንግሊዝ ጠላቶች

ዜጎቻቸውና ተቋሞቻቸው አይደሉም፡፡

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

4

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 191 ቅዳሜ ጥቅምት 18/ 2004

በኢህአዴግ ራዳር ስር የተንበረከከች አገር

. . . ደርግ ሲገለገልበት

የነበረውን የአዲስ አበባ

የሬዲዮ ጣቢያ ለሰፊው

ህዝብ ጥቅም ሲል

ተቆጣጥሮታል። ግንቦት

20/1983 ዓ.ም”። ከፍተኛ

የህይወትና የአካል

መስዋዕትነት የተከፈለበት

እልህ አስጨራሽ የ17

ዓመታት የትግል ምዕራፍ

ተደምድሞ ዴሞክራሲያዊ

ስርዓት መስፈኑን

የሚገልፅ ዲስኩር መሆኑ

ግልጽ ነውና።

በተለያዩ ፖለቲካዊ ተሳትፏቸውና

ጽሑፎቻቸው የሚታወቁት ፕሮፌሰር

መስፍን ወ/ማርያም፣ “ኢትዮጵያ ከዬት

ወዴት?” በሚለው መጽሐፋቸው ላይ

የሚከተለውን ነጥብ አስፍረዋል፡- “ . .

. ሥርዓት ሥርዓትን ይወልዳል። የአፄ

ኃይለሥላሴ ሥርዓት የደርግን ሥርዓት

ወለደ፤ የደርግ ሥርዓት በበኩሉ አሁን

በኤርትራ እና በቀሩት የኢትዮጵያ ክፍሎች

ያሉትን ሥርዓቶች ወለደ። . . . ”

የደርግ መንግሥት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ

ይፈፅም የነበረው ግፍ እንዲሁም ህዝቡ

ያሰማው የነበረው ብሶት ወደ ትግል

እንዳስገባው በተደጋጋሚ የሚናገረውና

የደርግ ሥርዓት የወለደው ኢህአዴግ፣ ለ17

ዓመታት በደርግ ራዳር ውስጥ የነበረችውን

ኢትዮጵያን በገዛ ራዳሩ ውስጥ ካስገባት 20

ዓመታት ተቆጥረዋል።

ኢህአዴግ፣ ግንቦት 20/1983 ሀገሪቱን

‘ሙሉ በሙሉ’ ይቆጣጠር እንጂ፣ ቀስ

በቀስ በተለያዩ ዓመተ-ምህረቶች ጥቂት

የማይባሉ የሀገሪቱ ክፋዮች ከቁጥጥሩ ውጭ

መሆናቸውን መረጃዎች እያመላከቱ ነው።

“ ... ለሰፈው ህዝብ ጥቅም ... ?”

“ ... ለሰፊው ህዝብ ጥቅም ... ” ይህቺ

ሐረግ ለኢትዮጵያ ህዝብ አዲስ አይደለችም።

ከግንቦት 20/1983 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ

ድረስ ከአስር ዲጂት በላይ ለሚሆን ጊዜ

የተደመጠች እና ወደፊትም በአሁኑ ሰዓት

በሥልጣን ላይ የሚገኘው መንግሥት

እስካለ ድረስ የምትደመጥ ሐረግ ነች።

በአባባሏ ላይ ማንም ሰው ቅሬታ

የለውም። ብዙዎችን ከነልዩነታቸው

የሚያስማማው ጉዳይም፣ አንድ

መንግሥት ለሰፊው ህዝብ ጥቅም

መስራት እና መቆም እንዳለበት

ነው። ‹‹ይሁን እንጂ…›› ይላሉ

የኢትዮጵያ መንግስት ሰፊውን

ህዝብ ተጠቃሚ የሚያደርግ

ሥራ እየሰራ አለመሆኑን

የሚያምኑ ወገኖች። ‹‹…

አሁን ባለው ወቅታዊ

ሁኔታ ከሰፊው ህዝብ

ይልቅ ጥቂቶች

እንደ ሮኬት

በመወንጨፍ

ተ ዓ ማ ኒ ነ ት

የጎደለው እድገት

እያሳዩ ነው›› በማለት

የሰፊው ህዝብ ፅንሰ ሀሳብ

ግቡን አለመምታቱን በመጠቆም

ይከራከራሉ።

እስካሁን ድረስ በኢህአዴግ ታሪክ፣

የኢትዮጵያ ህዝብ ከጫፍ እስከ

ጫፍ እስከ ልዩነቱ ከመንግሥት ጎን

የቆመው፣ ለሰፊው ህዝብ ከፍተኛ ጥቅም

ይሰጣል ብሎ ባመነበት አንድ ጉዳይ ነው።

እሱም ከደሙና ከታሪኩ ጋር የተሳሰረው

የአባይ ጉዳይ ሆኖበት ነው። እንደውም፣

መንግሥት፣ በሀገሪቱ ውስጥ ሰፊውን

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ፊ ቸ ር

ከህዝብ ጥቅም ይልቅ የራስን ፖለቲካዊ ምህዳር ማስጠበቅ

አገር

የተንበረከከች ስር ራዳር በኢህአዴግ

በታዲዎስ ጌታሁን

ከጥቂት ጊዜያት ወዲህ፣ መንግሥት ሰፋፊ መሬቶችን ለውጭ ባለኃብቶች በወረደ ወይም

አንድ ኪሎ ሙዝ በማይገዛ (በአሁን ሰዓት አንድ ኪሎ ሙዝ 12 ብር ሲሆን አንድ

ሄክታር ድንግል መሬት ደግሞ እስከ አስር ብር ይሸጣል) ዋጋ መሸጡ እያስገረመ ሳለ፣

ባለኃብቶቹ፣ የሀገራቸውን ሥራ አጦች በአውሮፕላን ጭነው አምጥተው በተረከቡት

መሬት ላይ እንዲሰሩ ማድረጋቸው ብዙዎችን አስቆጥቷል።

ህዝብ የሚያስቆጣ መሠረታዊ ችግሮች

መኖራቸው ስላስፈራው እና የአረብ ሀገራት

አብዮት ወደ ኢትዮጵያ እንደይመጣ

ስለሰጋ ነው አባይን ለመገደብ የተነሳው

ብለው ያምናሉ። ምንም እንኳን ጠቅላይ

ሚኒስትር መለስ ዜናዊ፣ መንግሥታቸውን

ሥጋት ላይ የሚጥል ችግር በኢትዮጵያ

እንደሌለና ሰፊው ህዝብ ከመንግሥት ‹ሰፊ

ጥቅም› በማግኘቱ የ5 ዓመት ኮንትራት

እንደሰጣቸው ተናግረው የነበረ ቢሆንም።

ኑሮ፣ በተዓምር ወይስ በተዓምራዊ ዕድገት?

የሁለተኛ ዓመት የሥራ ዘመን ሦስተኛ

መደበኛ ስብሰባውን ጥቅምት 9 ቀን

2004 ዓ.ም ያከናወነው የኢፌዴሪ የህዝብ

ተወካዮች ም/ቤት፣ ከወትሮው ለየት ያለ

መንፈስ እና ንግግር ጎብኝቶት ነበር።

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ

መስከረም 29 ቀን 2004 ዓ.ም ባደረጉት

የምክር ቤት መክፈቻ ንግግር ላይ በሚቀርቡ

የማሻሻያ ሞሽኖች ላይ የመንግሥታቸውን

አቋም ለማስደመጥ በምክር ቤቱ የተገኙት

ጠ/ሚኒስትር መለስ፣ እንደ ከዚህ ቀደሙ

ሁ ሉ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ

ሽቅብ ‘መወንጨፉን’ በ‘ተዓምር’ መስለው

ተናግረዋል።

በምክር ቤቱ ብቸኛው የመድረክ ተወካይ

የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ፣ “ሀገራችን

ያስመዘገበችው እድገት የትክክለኛ

ፖሊሲዎች ውጤት ነው” የሚለው ዓረፍተ-

ነገር ከኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ጋር

የማይመሳሰል መሆኑን ቢናገሩም፣ በአቶ

መለስ ዜናዊ ተቀባይነት አላገኙም።

ጠ/ሚኒስትሩ፣ የሞተን ሰው ነፍስ ዘርቶ

ከመቃብር የማስነሳት ያህል ‘ተዓምራዊ’

ሲሉ የገለፁትን የኢኮኖሚ ዕድገት የምጣኔ

ኃብት ባለሙያ የሆኑት አቶ ተመስገን

ዘውዴ፣ ከህንፃ ግንባታዎች በስተቀር

በሌሎች ሴክተሮች ላይ የታየ ጉልህ

ለውጥ እንደሌለ በማስረገጥ ተዓምራዊውን

እድገት ዋጋ ያሳጡታል። ቀጠል ያደርጉና

“በእርግጥም የህንፃዎችንና የቪላ ቤቶችን

በብዛት መገንባት ለኢኮኖሚ እድገትና

ለህዝቡ ኑሮ መሻሻል እንደ ማሳያ

ሊያስቀምጡ የሚሞክሩ የኢህአዴግ ወገኖች

አይጠፉም። አነዚህ ወገኖች ግን አዲስ አበባ

ከተማ ውስጥ ያለው የህንፃዎች ግንባታ

በአጠቃላይ አገሪቱ ውስጥ ያለውን የኢኮኖሚ

እንቅስቃሴ ሊወክል ይችላልንን? የሚለውን

ጥያቄ መመለስ የሚችሉ አይመስለኝም”

በማለት የህንፃ ግንባታ አንድ ራሱን የቻለ

ነጠላ ዘርፍ መሆኑን ያስረዳሉ።

የኢፌዴሪ የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ

የባለፈውን ወር የአገር አቀፍ እና የክልሎችን

የሸማቾች ዋጋ መመዘኛ ኢንዴክሶችን

ባወጣበት ሪፖርት ላይ የምግብ ዋጋ

ግሽበት 51.3 በመቶ መድረሱን

ገልጿል። እንዲሁም፣ በመስከረም

ወር 2004 ዓ.ም የተመዘገበው የ12

ወራት ተንከባላይ አማካኝ አገራዊ

አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው

ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር

በ26.6 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን

ሪፖርቱ ጨምሮ ገልጿል።

የዋጋ ግሽበት እና የኑሮ

ውድነት ጣራ መንካታቸው

ለአቶ መለስ የሚያስገርም

ጉዳይ አልሆነም። ‹‹የኑሮ

ውድነትም ሆነ የዋጋ

ግሽበት እያለ

ኢኮኖሚ ማደግ ይችላል፤ እነዚህ ሁኔታዎች

ባሉበት ሁኔታ ኢኮኖሚ አያድግም ማለት

የኢኮኖሚን ሀሁ አለመገንዘብ ነው››

በማለት ብዙ ሚሊዮን ህዝብን ግራ እያጋባና

ከዕለት ዕለት ኑሮውን እያመሳቀለ ያለውን

የኑሮ ውድነት ‘ቀላል’ አድርገው ለማየት

ሞክረዋል።

ይህ ዓይነቱ (51.3 በመቶ) የዋጋ ግሽበት

በተከሰተበት ሰዓት ከፍተኛ የኢኮኖሚ

ዕድገት አስመዘግባለሁ ማለት ተጨማሪ

ገንዘብ ወደ ኢኮኖሚው ማፍሰስ መሆኑን

የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ያስረዳሉ።

‹‹ግሽበት ማለት ሌላ ተዓምር አይደለም፤

ጥቂት ምርትና እጅግ በርካታ ገንዘብ

በኢኮኖሚው ውስጥ መኖር ነው›› የሚሉት

አቶ ተመስገን፣ ‹‹ከፍተኛ ዕድገት ቢመጣ

መልካም ነበር ግን መወሰድ ያለባቸውን

እርምጃዎችና መዋጥ ያለባቸውን መራራ

ኪኒኖች ሳይውጡ የማይሆን ነገር

ነው” በማለት የመፍትሄ ሀሳባቸውን

እንደሚከተለው ያካፍላሉ፡- “ግሽበቱን

ለማስተካከልና የታቀደውን ዕቅድ ለማሳካት

መዋጥ ያለባቸው መራራ ኪኒኖች

ፊስካልና ሞኒተሪ መሳሪያዎች ናቸው።

በተለይ በሞኒተሪው በኩል ብሔራዊ ባንክ

ነፃ ወይም ከአስፈፃሚ አካላት ተፅዕኖ

ሊላቀቅ ይገባዋል። ብሔራዊ ባንክ ነፃ

ሆኖ ቢሰራ የወለድ መጠን እንዲጨምር

ያደርጋል። የወለድ መጠን ሲጨምር ሰዎች

ገንዘባቸውን ባንክ ማስቀመጥ ይጀምራሉ።

የዛኔ የኢኮኖሚው ውስጥ የገንዘብ ዝውውር

እየቀነሰ ይመጣል። … ብሔራዊ ባንክ

የንግድ ባንኮች የግዴታ ሊይዙት የሚገባውን

የተቀማጭ ገንዘብ መጠን (ሪዘርቭ

ሪኳየርመንት) እንዲጨምር ማድረግ

ያስፈልጋል። ይህም ገንዘብን ከኢኮኖሚው

ውስጥ ለመቀነስ ይረዳል” በማለት ምሁራዊ

አስተያየታቸውን ያጋራሉ።

የኢኮኖሚን ሀሁ እንደማያውቁ በጠ/

ሚኒስትር መለስ ‘የማረጋገጫ ሰርተፊኬት’

የተሰጣቸው አቶ ግርማ ሰይፉ፣

‹‹እንኳንስና 11.4 በመቶ ሊታደግ ቀርቶ

አምና ከነበረበትም የወረደ ህይወት ነው

የኢትዮጵያ ህዝብ እየመራ ያለው። ሰዉ

በቀን አንዴ መመገብ እንኳን አቅቶት

ባለበት ሁኔታ፣ “ኢኮኖሚው አድጓል ብሎ

ሽንጥን ገትሮ መከራከር እውነታውን መካድ

ነው። እኛኮ 11 በመቶ አድገናል ቢባልም

ሆነ 15 በመቶ፣ በተጨባጭ

ዕድገቱ የዜጎች ህይወት

ላይ ካልተንፀባረቀ ምንም

ለውጥ የለውም” በማለት

ህዝቡ ያለበትን ወቅታዊ

የኑሮ ሁኔታ በቁጭት

ይገመግሙታል።

“ተዓምራዊ እድገት ማለት እኮ

ቀላል ነገር አይደለም። በአሁን ሰዓት

ኢትዮጵያ ውስጥ ‘ተዓምር’ የሚያሰኝ

እድገት ተፈጥሮ ቢሆን ኖሮ የአዲስ ዘመን

ጋዜጣ ኮፒ ወደ 80 ሚሊየን ይጠጋ ነበር።

ምክንያቱም፣ የተዓምራዊው ዕድገት ተቋዳሽ

የሆነው 80 ሚሊየን ህዝብ፣ “ኢኮኖሚው

አላደገም’ ብለው የህዝቡን ብሶት የሚጮሁ

ነፃ ጋዜጦችን ተጠይፎ ከመንግሥት

ጎን ይቆም ነበር” የሚሉ ወገኖች፣ ህዝቡ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 191 ቅዳሜ ጥቅምት 18/ 2004

በተዓምራዊ ዕድገት ሳይሆን በአንዳች

ተዓምራዊ ኃይል እየኖረ መሆኑን ደግመው

ደጋግመው ያስረግጣሉ።

እነዚሁ ወገኖች ቀጠል በማድረግም፣

“መንግሥት ኢኮኖሚውን ለማስተካከል

ግሽበቱን ከመቆጣጠር ይልቅ የኢኮኖሚ

ባለሙያዎች የሚያቀርቡትን የመፍትሄ

ሀሳብ ተቆጣጥሮ ለማምከን መጣደፉ በጣም

ያስገርማል” በማለት ጭንቅላታቸውን

በሀዘኔታ ይነቀንቃሉ።

ዳቦ ገዢ VS ዳቦ ፈላጊ

ባለፉት የኢህአዴግ 20 ዓመታት ውስጥ፣

ከመንግሥት ራዳር ወጥተዋል ተብሎ

የሚነገርላቸውና ለብዛታቸውም የቁጥርና

የፊደል መረጃ የሚጠቀስላቸው ብዙ

ሺህ ‘ስራ አጥ’ ኢትዮጵያውያን አሉ።

የስራ አጦቹ ቁጥር ከሁለቱም መደብ

(ከተመረቀውም ካልተመረቀውም ወይም

ካልተማረው) የተውጣጣ ሲሆን፣ በአሁን

ሰዓት ያሉበት ደረጃ ደግሞ እጅግ አሳሳቢና

አፋጣኝ እርምጃ ከሚሹ ጉዳዮች መካከል

የሚካተት መሆኑ ብዙዎችን ያስማማል።

መንግሥት፣ በአምስት ዓመቱ የዕድገትና

ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ አሳካቸዋለሁ

ብሎ በልበ-ሙሉነት ከዘረዘራቸው ጉዳዮች

አንዱ ዩኒቨርስቲዎችን በቁጥር የማሳደግ

ነው። በዚህ ላይ ቅሬታ የሌላቸው ሰዎች

“በቁጥር ካደጉት ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ

ተመርቀው ለሚወጡ ቁጥራቸው የበዛ

ተማሪዎች ምን የተመቻቸ ነገር አለ?

ወይስ የመንግሥት ሥራ ማስመረቅ ብቻ

ነው?” በማለት ሊታሰብበት የሚገባ ወሳኝ

ጥያቄ ይሰነዝራሉ።

የህወሓት መሥራች አባል የነበሩትና

በአሁን ወቅት የአረና ፓርቲ የአመራር

አባል የሆኑት አቶ አስገደ ገ/ሥላሴ፣ “ሙስና

እና ኢንቨስትመንት በትግራይ” በሚለው

መጣጥፋቸው ላይ ያነሱት ጉዳይ አለ፤ “ ...

በሁሉም ዞኖች ያሉ ማኅበራት አብዛኛዎቹ

የከሰሙና የከሰሩ እንዲሁም ለዕለት ጉርስ

እየለቃቀሙ የሚኖሩ ናቸው። ለዚህም

የክልሉ የኢንዱስትሪና የከተማ ልማት

ቢሮ ኃላፊና የህወኃት ማዕከላዊ ኮሚቴ

አባል የሆኑት አቶ በየነ መክሩ በሰማዕታት

ሀውልት እንደተናገሩት፣ አብዛኛዎቹ

የጥቃቅንና አነስተኛ ማኅበራት ገንዘብ

አበደርናቸው፣ ሁሉም ከሰሩ ብለዋል።

“… በትግራይ ክልል የነበረ አናጢ፣ ግንበኛ፣

ለሳኝ በአጠቃላይ ሞያተኞችና የጉልበት

ሰራተኞችን በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ስራ

ፈጥረው ሲያሰሩ የነበሩ የህንፃ ተቋራጮች

(ኮንትራክተሮች) አብዛኛዎቹ በብልሹ

አስተዳደር ምክንያት ከክልሉ ለቀዋል››

በማለት ብልሹ አሰራር ምን ያህል ስራ

አጥ ዜጎችን እየፈጠረ እንደሚገኘም

ያመላክታሉ።

ዳቦ ለመግዛት ወደ ዳቦ ቤት ከሚሄደው

ሰው ይልቅ፣ ዳቦ ፍለጋ ወደ ቫካንሲ

ሰሌዳዎች የሚጎርፈው ሰው በበለጠበት

በዚህ ሰዓት፣ መንግሥት የሥራ ዕድል

ለመፍጠር መትጋት ሲገባው፣ ለብዙ ሥራ-

አጦች በልቶ ማደር ምክንያት የሚሆኑ

ባለኃብቶችን በብልሹ አሰራር ምክንያት

ከቦታ ቦታ ማሳደዱ ያስቆጫቸው አቶ

አስገደ፣ “ ... የትግራይ ባለኃብቶችና

ድርጅቶች የተመቻቸ የኢንቨስትመንት ቦታ

ባለማግኘታቸው እንደ አማራጭ ወደ ሌላ

ቦታ ሄደው ሲበለፅጉ ይታያል” በማለት ብዙ

ሥራ-አጦች እንጀራቸውን ከጉሮሯቸው ላይ

እየተነጠቁ መሆኑን ያስገነዝባሉ።

ከጥቂት ጊዜያት ወዲህ፣ መንግሥት ሰፋፊ

መሬቶችን ለውጭ ባለኃብቶች በወረደ

ወይም አንድ ኪሎ ሙዝ በማይገዛ (በአሁን

ሰዓት አንድ ኪሎ ሙዝ 12 ብር ሲሆን

አንድ ሄክታር ድንግል መሬት ደግሞ እስከ

አስር ብር ይሸጣል) ዋጋ መሸጡ እያስገረመ

ሳለ፣ ባለኃብቶቹ፣ የሀገራቸውን ሥራ

አጦች በአውሮፕላን ጭነው አምጥተው

በተረከቡት መሬት ላይ እንዲሰሩ

ማድረጋቸው ብዙዎችን አስቆጥቷል።

“ምክንያቱም . . . ” ይላሉ ተቆጪዎቹ፣

“ … ኢትዮጵያውያን ሥራ-አጦች ሊሰሩት

የሚገባውን ሥራ ባህር አቋርጠው የመጡ

ሰዎች መስራታቸው ኢትዮጵያውያን የበይ

ተመልካች እንዲሆኑ አስገድዷቸዋል፤ ይሄ

ደግሞ ከአንድ መንግሥት አይጠበቅም፤

ኢህአዴግ የኢትዮጵያ መንግሥት እንጂ

የህንድና የቻይና (ሥራ-አጦች) መንግሥት

አይደለም” በማለት መንግሥት አቋሙን

እንዲያስተካክል ማሳሰቢያ ይሰጣሉ።

ትግሉ ተቋጨ?

ምንም እንኳን ኢትዮጵያ እንደ ጃፓን

በኒዩክለር ጣጣ፣ እንደ ቱርክ በመሬት

መንቀጥቀጥ፣ … አትመታ እንጂ በሥራ

አጥነት፣ በኑሮ ውድነት፣ በቤት እጦት እና

ኪራይ ችግር … ወዘተ ክፉኛ እየተናወጠችና

እየተመታች እንዲሁም ዜጎቿ ከአቅም

በላይ በሆነ ችግር መኖሪያቸውን ለቀው

እየተሰደዱና በየበረሐው እየሞቱ

መሆናቸውን የተለያዩ አስደንጋጭ

ሪፖርቶች እያመላከቱ ነው።

በአሁን ሰዓት ኢትዮጵያ በከባድ ጎርፍና

ወጀብ አለመመታቷን “ተመስገን” በማለት

የሚገልፁ ወገኖች፣ ሀገሪቱ ቅጥ አምባሩ

በጠፋ የኑሮ ውድነት መሀል አናቷን

መበርቀሷ ግን በየደቂቃው እያባነናቸው

መሆኑን ከመናገር አልተቆጠቡም።

በ2003 ዓ.ም ታህሳስ ወር ላይ፣ ጠቅላይ

ሚኒስትሩን፣ የሚኒስትር ዴኤታዎችን

እና ሌሎች የመንግሥት ባለሥልጣናትን

በአንድ አዳራሽ አሰባስቦ የነበረው የኑሮ

ንረት፣ ዛሬ ከመንግሥት ራዳር የወጣበት

ምክንያት ምን እንደሆነ የተገለፀ ነገር

ባይኖርም፣ ኢኮኖሚስቶች ግን ጉዳዩ

(ንረቱ) ከመንግሥት አቅም በላይ መሆኑን

መረጃዎችን በማገላበጥ ያስረዳሉ።

“የነዳጅ ዋጋ መናር በሊቢያና በመሰል

ሀገራት አብዮት ይመካኛል። የሥጋ፣

የበርበሬ፣ የቡና … ዋጋ መናር በማን

ሊሳበብ ነው? ዋጋቸው ስንት እስኪገባስ

ድረስ ነው በዝምታ የሚታዩት?” የሚል

ጥያቄ የሚያቀርቡ ሰዎች ከመንግሥት

የሚሰጣቸው ምላሽ ከሀገሪቱ ወቅታዊ

ሁኔታ ጋር ፍፁም የሚቃረን መሆኑ

ያበሳጫቸዋል።

መንግሥት፣ ይሄ ዕቃ ተወደደ ሲባል

“አድገናል”፤ ኧረ ይሄ ዕቃ ከገበያው ጠፋ

ሲባል “አድገናል አድገናል”፤ ኧረ መፍትሄ

አምጡ በልቶ ማደር አለማደር ልማድ ሆነ

ሲባል፣ “አድገናል አድገናል፣ አድገናል”

የሚለው ህዝብ እንዳይቆጣው አስቀድሞ

ለመቆጣት ነው ይላሉ - የመንግሥትን

አመለ-ቢስነት በቅርበት የሚያውቁ ውስጠ-

አዋቂዎች።

“የኢትዮጵያ ህዝብ ስራ ማጣቱን፣

መራቡን፣ ኑሮ ከአቅሙ በላይ መሆኑን

… ለመግለፅ የግድ እንደ ቱኒዝያዊው

መሐመድ ቡአዚዝ ራሱን አቃጥሎ

መግደል አለበት ወይ?” የምትለውና

የአምስት ልጆች እናት የሆነችው ወ/ሮ

ቅድስት ተክሉ፣ ህዝቡ ክብሪት ጭሮ ራሱን

ባያቃጥልም፣ በመንግሥት ቸልተኝነት እና

በአንዳንድ ራስ-ወዳድ ነጋዴዎች የተጫረው

የኑሮ ንረት ቀስ በቀስ ህዝቡን አቃጥሎ

እየጨረሰው መሆኑን በማስጠንቀቂያ መልክ

ትናገራለች።

የጦር ሠራዊት እና የጦር መሳሪያ

በመሰብሰብ (በመያዝ) ከምስራቅ አፍሪካ

ሶስተኛ ደረጃ ይዞ የነበረውን የደርግ

መንግሥት በ17 ዓመታት ውስጥ ታግለው

በመጣል ኢትዮጵያን በራዳራቸው ሥር

ያስገቡት ኢህአዴጎች፣ ዛሬ ቤተ-መንግሥት

እና ያማረ ቤት ውስጥ እየኖሩ፣ እንደ

ውሃ በሚፈስ መኪና እየተመላለሱ ህዝቡን

የሚገዳደሩ ችግሮችን ምነው መታገልና

መጣል አቃታቸው? ወይስ ትግሉ ተቋጨ?

የሚል አነጋጋራ ጥያቄዎች እየተነሱበት

ነው - መንግሥት።

ሀና እና መሰሎቿ

ሚያዝያ 22/2000 ዓ.ም የስምንት ዓመት

ልጅ እና የሁለተኛ ክፍል ተማሪ ለነበረችው

ሀና አለማየሁ ጥሩ ቀን አልነበም፡። ቀኑ

እንደመምሸት ሲል ሀና ከወላጆቿ ቤት ወደ

አያቷ ቤት ጉዞ ትጀምራለች። (የወላጆቿ

እና የአያቷ ቤት አንድ ሰፈር ውስጥ ነው

ያለው)

ልጅቷ ቤት ከመድረሷ በፊት እስካሁን

ድረስ ማንነቱና ምንነቱ ያልታወቀ ሰው

ያገኛትና አታሎ ይዟት ይሄዳል። …

አስገድዶ ከደፈራት በኋላ ህይወቷ አለፈ።

ጧት ሀና ሰፈራቸው የሚገኝ ወንዝ ውስጥ

ተጥላ ተገኘች።

የኤልፓንና የቴሌን ህንፃ “ለጥቂት”

ከመጋዬት እና ከመውደም አድኖ

‘ተጠርጣሪ’ ያላቸውን ጋዜጠኞች በቁጥጥር

(በራዳሩ) ስር ያዋለ መንግሥት፣ በሀና እና

በመሰሎቿ ላይ ጥቃት ፈፅመው (ያውም

ገድለው) የተሰወሩ ተጠርጣሪዎችን እንዴት

መያዝ አቃተው? የሚል ጥያቄ ይነሳል -

በህብረተሰቡ ዘንድ።

ጥቃት ፈፅመው ከመንግሥት ራዳር ውስጥ

የተሰወሩት ተጠርጣሪዎች በመንግሥት

ቸልተኝነት ነው ያልተያዙት? ወይስ

ከመንግሥት አቅም በላይ ሆነው ነው?

ይላሉ የጥቃት ሰለባዎቹ ቤተሰቦች።

መንግሥት፣ ከህዝቡ ጥቅም ይልቅ የራሱ

ጥቅም እንደሚበልጥበት የሚናገሩ ወገኖች፣

የፖለቲካውን ምህዳር ‘ለመጠበቅ’ በሚል

ሰበብ የራሱን የሥልጣን ምህዳር እየጠበቀ

መሆኑኑ በመግለፅ “ጥቃት ፈፅመው

ያልተያዙ ህዝብ አሸባሪዎች አነፍንፎ

ለመያዝ ምነው አፍንጫና እጅ አጠረው?”

ይላሉ።

አንቀጽ

በታዲዎስ ጌታሁን

አራዳሹ ከጥግ እስከ ጥግ በሰው

ጢም ብሏል። ሁሉም ተሰብሳቢ ሰውዬውን

በጉጉት ይጠባበቃል። ሰውዬው በጉጉት

የሚጠበቀው ያለ ምክንያት አይደለም።

የተሰብሳቢዎቹ ችግር የሚቀረፈው

ሰውዬው ለበታቾቹ በሚያስተላልፈው

ትዕዛዝ በመሆኑ ሁሉም ደጅ ደጁን ያያል።

… ወዲያውም የአዳራሹ መግቢያ በር ላይ

ከፍተኛ ግርግር ተፈጠረ።

ደረታቸውንና ጡንቻቸውን

ያሳበጡት የሰውዬው ጠባቂዎች (ጋርዶች)

ነበሩ የግርግሩ መንስዔዎች።

ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ

እንዲሉ ምንም ዓይነት አስጊ ሁኔታ በሌለበት

ሰላማዊ አዳራሸ ውስጥ ወከባ ከፈጠሩ

በኋላ ሰውዬውን የተዘጋጀላቸው ቦታ ላይ

አስቀመጧቸው።

የተሰብሳቢውን ችግር ሰምተው

መፍትሔ ለማምጣት ፊት ለፊት የተሰየሙት

ሰውዬ አንድ በአንድ ጥያቄ ይቀርብላቸው

ጀመር።

‹‹በከተማችን ውስጥ የቤት ችግር

እየተስፋፋ ነው፤ እና ችግሩን ለመቅረፍ ምን

አስባችኋል?›› አለ አንድ ተሰብሳቢ።

ሁለተኛዋ ተሰብሳቢ ደግሞ

የሚከተለውን ጠየቀች፡- ‹‹በድህነት ውስጥ

የምንኖረው እስከ መቼ ነው? ኑሯችን

የሚሻሻለውስ እንዴት ነው?›› እንባዋ ጠብ

ጠብ አያለ ተቀመጠች።

አንድ አሽቃባጭና አጨብጫቢ

ተሰብሳቢ ደግሞ በሦስተኝነት ጥያቄውን

አቀረበ፡- ‹‹በዙሪያችን አሰፍስፈው የቆሙትን

ተቃዋሚዎቻችንን እንዴት ነው መከላከልና

እንቅስቃሴያቸውን ማዳከም ያለብን?›› ሲል

ሰውዬው ፈጠን ብለው፣ ‹‹ጥሩ ጥያቄ ነው!››

አሉ።

ጥሩ ነው ያሉትን ጥያቄ እየፈቱና

እንየበተኑ እንዲሁም ተቃዋሚዎቻቸውን

የማልፈስፈስ ስትራቴጂያቸው ምን

እንደሚመስል በስፋትና በጥራት አወሩ።

አወሩ። አሁንም ደግመው ደጋግመው አወሩ።

… ሚያዚያ 25 ቀን 1881 ዓ.ም፤

ንጉስ ምኒልክ ከጣሊያን መንግሥት ጋር፣

ሃያ አንቀጾች የያዘ ውል ለመዋዋል ውጫሌ

ተቀምጠዋል። ምኒልክና ጣሊያን በሌሎቹ

አንቀጾች ይዘት ቢስማሙም፣ መዘዘኛው

አንቀጽ አስራ ሰባት ግን ለከፋ ውዝግብ ወይም

ለአድዋ ጦርነት ዳርጓቸዋል።

‹‹የኢትዮጵያ መንግሥት ከውጭ

አገር መንግሥታት ጋራ የሚያደርገውን

ግንኙነት በኢጣሊያ መንግሥት አማካይነት

ማድረግ ይገባዋል›› ይላል የአንቀጽ 17

የጣሊያንኛ ትርጉም።

የአድዋ ጦርነት ያለመደማመጥ

ውጤት ነው። ጣሊያን፣ የልብ ትርታዋንና

ፍላጎቷን እንጂ፣ ኢትዮጵያ በአንቀጽ

17 ላይ ታሰማ የነበረውን የተቃውሞ

ድምፅ አታዳምጥም ነበር። ወይም ደግሞ

ተቃውሞውን ለመቀበል ዝግጁና ፈቃደኛ

አልነበረችም። ለዚህም ነው መሳሪያዋን ጭና

ወደአድዋ ተራሮች መትመም የጀመረችው።

… ‹‹መንግስት ዓይንና ጆሮ

አለው›› ይላል ኢህአዴግ። በእርግጥም ትልቅ

ጆሮ ነው ያለው መንግሥት። ግን አብዛኛውን

ጊዜ ጆሮውን ዘንበል የሚያደርገው ወደ

ህብረተሰቡ ጥያቄ ሳይሆን ወደ ተቃዋሚዎች

መንደር ነው።

‹‹የቤት ችግር አለ፤ ድህነት

ተንሰራፋ፤…›› የሚሉ ህብረተሰብዎች ስፍር

ቁጥር የላቸውም። ጆሮ እንዳለው በፓርላማ

የተናገረው መንግሥት ግን፣ ፈጥኖ ጆሮውን

የሚያዘነብለው ወደ ዶ/ር ነጋሶ፣ ኢንጂነር

ኃይሉ ሻውል፣ ቡርቱካን ሚደቅሳ … ነው።

በተቃዋሚዎች መንደር ምን

እንደተወራ (አንዳንዴ ከተቃዋሚዎቹ አባላት

እንኳን) ቀድሞ የመስማት ‹ችሎታ› አለው።

የህብረተሰቡን የልብ ትርታ እና ፍላጎት

ለመስማት ግን የወራትና የዓመታት እድሜ

ያስቆጥራል።

ይህም የሚያሳው፣ የመንበረ-

ክብሩን ግርማ-ሞገስ ከህብረተሰቡ ፍላጎት

አስበልጦ እና አስቀድሞ እንደሚያፈቅር ነው።

በነገራችን ላይ፣ ይሄ አይነቱ ፀባይ የዚህ

መንግሥት ብቻ አይደለም።

ኃይለሥላሴ፡- የእኚህ ንጉሥ

ሥርዓት እንደማንኛውም መንግሥት ትላልቅ

ጆሮ ነበረው። ችግሩ፣ ሥርዓቱ አስቀድሞ

ይሰማ የነበረው በወቅቱ ህዝቡ ያሰማ

የነበረውን ብሶት አልነበረም።

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ውስጥ

‹‹ክሮኮዳይልስ›› (አዞዎች) በመባል የሚታወቅ

የተራማጅ ተማሪዎች ቡድን ነበር። ይህ

ተራማጅ ቡድን በ1957 ‹‹መሬት ላራሹ

ይሰጥ›› የሚል መፈክር ተሸክሞ ሰልፍ

ወጣ። መፈክሩ ኢትዮጵያ ውስጥ ከተነሱት

መፈክሮች ሁሉ አደገኛው ነበር። የአፄው

ሥርዓት እንደአብዛኛዎቹ ሥርዓቶች ይሉኝታ

17

በቃልኪዳን ይበልጣል

የሚያጠቃውና የተቃውሞ ድምጾችን የመታገስ

ባህርይ ስላልነበረው ሰልፉ በፖሊስ ተበተነ።

አስር ኪ. ሜ. መንገድ ለማሰራት

የሚደክመው መንግሥት፣ ሰልፉን ለመበተን

ግን እስከ አስር ሺህ የሚደርስ ጦር ሠራዊት

ያሰልፋል።

ደርግም፣ ሀገሪቱ ውስጥ ስንትና

ስንት አንገብጋቢ ችግር እያለ፣ እሱ ግን

ተንገብግቦ መላ የሚያበጀው፣ የኢሕአፓን

የፖለቲካ እንቅስቀሴ ወገቡን ለመምታት

ነበር።

የኢህአፓ አባላት ማታ ቡና

እስከስንተኛ ድረስ አንደጠጡ ሳያውቅ

አይቀርም - ደርግ። ምክንያቱም ይቃወሙኛል

ለሥልጣኔ መናጋት ምክንያት ይሆናሉ

ብሎ የሚጠረጥራቸውን ሁሉ እግር በእግር

እየተከተለ እግረ-ሙቅ የሚያጠልቅ ሥርዓት

ነበር። እስራቱንና ጭቆናውን ለማፋፋም፣

በእስራኤሎች የሠለጠነው ‹‹ነበልባል ቡድን››

አዲስ አበባ እንዲመጣ በማድረግ፣ እንደ

ውጫሌው ስምምነት (አንቀጽ አስራ ሰባት)

አቋሙን በግድ ለመጋት ሞክሯል።

ደርግ፣ አቋሙን እንደጣሊያኖች

በአንቀጽ አይክፍለው እንጂ፣ በግልፅ ሲያራምድ

የነበረው ፍላጎቱ፣ ከአንቀጽ አስራ ሰባት ጋር

የጠበቀ መመሳሰል ነበረው።

የአንቀጽ አስራ ሰባት አጭር

ትርጉም፡- ሌሎችን ያለማዳመጥ እና የራስን

ፍላጎት ብቻ መከተል ነው። የደርግም አንደዚያ

ነበር - ሌሎችን ያለመስማት።

አንቀፅ 17 የአድዋን ጦርነት ወለደ።

የደርግ አንቀጽ አስራ ሰባታዊ አቋም (ሌሎችን

ያለመስማት አቋም) የአስራ ሰባት ዓመታታ

ኢህአዴግ የመናገር እንጂ ብዙም የማዳመጥ ልምድና ፍላጎት

የለውም። በተቃራኒው ደግሞ፣ ሌሎች የእሱን ማስጠንቀቂያዎች

የማዳመጥ ፍላጎት እና ልማድ እንዲኖራቸው ይፈልጋል። በዓለም

ላይ ቀላሉ ነገር መናገር ሲሆን ከባዱ ደግሞ ማዳመጥ ነው።

ለመናገር ለመናገርማ ወፈፌም ይናገራል

ጦርነት ወልዶ ደርግን አስወገደ።

ኢትዮጵያ፣ የተቃውሞ ድምጾችንና

ሰልፎችን ፈጥነው የሚያደምጡ፣ የህዝቡን

ችግር ደግሞ ቀ..ስ..ስ ብለው የሚሰሙ

መንግሥታት የተፈራረቁባት ምስኪን አገር

ነች።

የህዝብ እንባ ምናቸውም አይደል።

‹‹ተቃዋሚዎችን እንዴት እናልፈስፍስ?››

የሚል የአጎብጓቢዎች ጥያቄ ግን ‹‹ጥሩ›› ነው

ለእነሱ። እንዲህ ዓይነቱ ጥያቄ ውሃና የፀሐይ

ብርሃናቸው እንዲሁም ቫይታሚን ኤ፣ ቢ፣

ሲያቸው ነው።

ሥልጣናቸውን የሚያፋፉትና

የሚያጠነክሩት ተቃዋሚዎችን በማቀጨጭ

ነው።

ኢህአዴግ የመናገር እንጂ ብዙም

የማዳመጥ ልምድና ፍላጎት የለውም።

በተቃራኒው ደግሞ፣ ሌሎች የእሱን

ማስጠንቀቂያዎች የማዳመጥ ፍላጎት እና

ልማድ እንዲኖራቸው ይፈልጋል።

በዓለም ላይ ቀላሉ ነገር መናገር

ሲሆን ከባዱ ደግሞ ማዳመጥ ነው። ለመናገር

ለመናገርማ ወፈፌም ይናገራል። አንድ ሰው፣

ሌሎች በአግባቡና በሙሉ ልብ እንዲያዳምጡት

ከፈለገ፣ እሱም ለሌሎች ጆሮውን ወገግ አድርጎ

መክፈት አለበት። የግትርነት አቋም መለኪያና

ማሳያ እንዲሁም የራስ ወዳድነት ምልክት

የሆነው አንቀፅ 17 ለማንም አይጠቅምም -

በተለይ ለመንግሥት።

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

5

6

ፀጥታ እንፈልጋን። እርጋታ

እንፈልጋለን። ስክነት

እንፈልጋለን። በጥቅሉ

ሰላም እንፈልጋለን።

ለመሆኑ አራቱ አጫጭር

አረፍተ ነገሮች ባለቤት

‹‹እኛ›› ማን ነን? እኔና

መሰሎቼ። አረፍተ

ነገሮቹን በዚህ መልኩ ማዋቀሬ ምስጢር

ሲመረመር የሚጠቁመው፡- ሀ) እንደ

በርካታ ቀሺም ፖለቲከኞች የራሴን እምነት

ለማስረፅ ስለ ‹ሰፊው ህዝብ› በሚሏት

ተወዳጅ ሀረግ ለመጠለል መምረጤን

ነው፤ አሊያም ለ) ማንም ያልሰጠኝን

ውክልና ተሸክሜ ለአካባቢዬ ለመቆርቆርና

ለመሟገት ራሴን ማጨቴን ነው።

አንድን ነገር ግን በእርግጠኝነት

መናገር እችላለሁ። እንደ’ኔው በጩኸት

መደንበር ያታከታቸው፣ በየደቂቃው

መበርገግ ያንገሸገሻቸው፣ መዋከብና

መደንገጥ ያማረራቸው፣ ከቤታቸው

ወጥተው እስኪመለሱ በአደንቋሪ ድምጾችና

የጆሮን ታምቡር ሊበጥሱ በሚንደረደሩ

ሁከቶች ተሰንገው የሚሳቀቁ፣ በጥሞና

መጓዝም ሆነ በፀጥታ መተኛት የናፈቃቸው

ብጤዎቼ ጥቂት አይባሉም።

‹‹እዚህ ከተማ ውስጥ የራሱ የሆነ

የነጠረ ስብዕና ያለው ሰው ማግኘት አዳጋች

ነው። አንዱ የአንዱ ፎቶ ኮፒ ለመሆን

ነጋ ጠባ ይታትራል። ይሳካለትማል።

በብልጭልጭ ህንፃ ካበደው ቅንጡ

ሰፈር አንስተህ እስከጨርንቁሱ መንደር

ብታስስ የሚገጥምህ የሰው አይነት ብዙ

አይደለም። ሁሉም የጋራ አካፋዩን እየፈለገ

ተቧድኗል። ድንገት ድንቅ ኃሳብ አፍልቀህ

ተከታይህ ቢበራከት፣ አጀብህ አጀብ

ቢያሰኝ ያጨበጨበልህ ሁሉ ገብተኸው

እንዳይመስልህ። ከምንም በላይ ወረትና

ጊዜያዊ ሆይ-ሆይታ ይማረኩናል። ከፍሬ

ነገሩ በበለጠ አልባሱን ሙጥኝ እንላለን።

ከምስሉ ጋር እንጣበቃለን። በመሆኑም

በተደጋጋሚ በከንቱ እንለፈልፋለን።

እንደናቆራለን።” እንዲህ ያለኝ አንድ

ወዳጄ ነው። ከዓመታት በፊት ጩኸታሟ

ከተማ ያደረሰችብኝን መንፈሳዊ እንግልት

ተናዝዤ ዝምታዋን ብመኝ ግን ምኞቴን

የሚጋሩ ብዙሃን ከተባለው በተለየ

እውነተኛና ከተሞክሯቸው የሚመዘዝ

ነጥብ እንደሚኖራቸው አይታበልም።

ሰው ከጥንተ-ፍጥረት ጀምሮ

ከአከባቢው ጋር ሲታገል ኖሯል።

ተፈጥሮን ድል ነስቶ እንዳሻው ሊያሾራት

ተወተርትሯል። ጢሻውን እየመነጠረ፣

ጋራውን እያስገበረ፣ ጭንጫውን አያለሰለሰ፣

ወንዞች ወደመረጠው ስፍራ እንዲፈሱ

ቦይ እየቀየሰ፣ በተስማማው ቦታ ጎጆውን

እየቀለሰ፣ ተከማችቶ እየሰፈረ፣ ከተሞች

እየቆረቆረ ወደ ሥልጣኔ ተምዘግዝጓል።

ዝርያው በዝቶ ተባዝቶ ምድርን ሲሞላ፣

መፈናፈኛም ሲያጣ ዱርዱሩን እያፀዳ፣

እንስሳቱን እያባረረ ግዛቱን አስፍቷል።

ኑሮው ይቀልለትም ዘንድ መኖሪያውን

ጭስ በሚተፉ ማሽኖች ሞልቷል። ግና

ከማሽኖቹ ጋር የወደቀበት አቅል የሚያስት

ፍቅር ልቡናውን ሰውሮበት በዋይታ

የምታጣጥር መሬትን ዘነጋት። እንባዋ

ጎርፍ፣ ስቅታዋ ናዳ፣ ኡኡታዋ ድርቅ

ሆነው ሲወግሩት አይኑ መገለጥ ያዘ።

እነሆም አረንጓዴው ዘመን ጠባ። ሁሉም

በየአፉ አረንጓዴ ቃላትን ደሰኮረ። ከፋብሪካ

ቡልቅ ቡልቅ እያለ እንደሚወጣ ጥቁር

ጭስ፣ ወንዝ ውስጥ እንደሚጨመር

እጣቢ ወይም ተረፈ-ምርት ሁሉ መኪኖቹ

ማጉያዎቹ የሚያስፈተልኩት ልክ አልባ

ድምፅ ከባቢን በክሎ ጤናን ያቃውሳል

ተባል። የለም ዜጎች በሞላ ‹የምንኖርበት

ቀየ እርጋታና ዝምታ ያሻዋል› እያሉ

መወያየት ብሎም ለተግባር መሰለፍን

ለመዱ። ይሄን ለመሰለው ‹ቅንጦት›

ጊዜ የሌላት አዲስ አበባችን ግን ላንቃዋ

እስኪተረተር መጮህን ልማድ አድርጋ

ኖረች።

በቅርቡ ሬዲዮ ስከታተል

ባለቤቱና ርዕሱ ያመለጠኝ ጥናት ተጠቅሶ

የከተማችን የድምፅ ልቀት መጠን አደኛ

ደረጃ መድረሱን ሰማሁ። የጥናቱን ድጋፍ

ባላገኝም ከሙዚቃ እስከ መዝሙር ቤት፣

ከንግድ ትርኢት እስከ ግንዛቤ ማስጨበጫ

ቅስቀሳ ረባሽ ኬረዳሽ ድለቃቸውን

በየአጋጣሚው ይጋብዙኛልና እውነታውን

አልስተውም። አሁን አሁን አሁን እየተገነቡ

ያሉ የእግረኛ መንገዶች እንደተጠበቁ

ሆነው በአብዛኛው የሸገር ጎዳናዎች

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 191 ቅዳሜ ጥቅምት 18/ 2004

ኮመንትሪ

በጩኸት

ውስጥ መኖር

በቃልኪዳን ይበልጣል

በእግር እየተጓዙ ዘና ማለት አይታሰብም።

የመኪኖቹ ድንፋታ፣ የሸቃጮች የማያባራ

ውትወታ፣ ከየመደብሩ በር ያለከልካይ

የሚለቀቁ ዘፈኖች ዝብርቅርቅታ አናትን

ቢያዞር እንጂ አያጠራም።

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር

ከሀገራችን አዋቂዎች 15% ያህሉ

ለአዕምሮ መታወክ የተጋለጡ መሆናቸውን

መግለፁንም ሰምቻለሁ - ቀደም ባለ ጊዜ።

መቼም የዚህ ቁጥር አስደንጋጭነት

ግልፅ ነው። ባልደረጃ አቅማችን፣ ባልጠና

ጉልበታችን ስንቱን እክል እንችለዋለን?

ይበልጥ የሚያስከፋው ደግሞ ነባራዊው

እውነታችን ቁጥሩን ቁልቁል የሚያወርድ

መላ አለመቋጠሩ ነው። ያለመግቻ ሽቅብ

የሚመነደገው የዋጋ ንረት ለጭንቅላት

የሚያተርፈው ከባድ ጭንቀት ራሱን ችሎ

ህሊናን ቢያቃውስ አይደንቅም። ስራና ተስፋ

ለአንድ ሀገር ውድቀትም

ሆነ ዕድገት ተፅዕኖ

ከሚያሳድሩ ምክንያቶች

ዋና ዋናዎቹ የፖለቲካ፣

የህዝብና የተፈጥሮ

ኩነቶች ናቸው። እነዚህ

ሦስት ጎራዎች በአሉታዊ መንገድ

ሲቃኙ ሀገር ይጎዳል፤ ሀገር ይዳኸያል፣

ይራቆታል። በተቃራኒው መንገድ

ከላይ የጠቀስናቸው ምክንያቶች

ወይም መንስኤዎች በአዎንታዊ

መልኩ ሲጓዙ ሀገር ይለመልማል፣

ይበለፅጋል፣ ያድጋል። ፖለቲካው

ደግሞ ከዚህ ለየት ባለ መልኩ

የተለየ የሰውን ልጅ የእለት ተዕለት

ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ባህላዊ

እንቅስቃሴዎችን በመቆጣጠር ቁልፍ

ሚና ይጫወታል። ታዲያ በዙዎች

የዓለማችን መሪዎች ተራቀውበት፣

እንደ ልብ ተቀኝተውበት፣ ህዝቡንም

ደስታ አጎናፅፈውት አንቱ አስብለው

የሚያስኖሩትን ያክል፣ ብዙዎች

የ3ኛው ዓለም ሀገራት፣ በተለይ

የአፍሪካ መሪዎች፣ ፖለቲካን

ሳያውቋት ምስጢሯን፣ ዓላማዋን፣

ድርጊቷንና ግባቷን ሳይመረምሩት

በግዴለሽነትና በማን-አለብኝነት

እብሪትነት ሲሸልሉበት፣ ሲዘሉበት

ኖረዋል። አሁንም እየኖሩ ያሉ አሉ።

የምዕራቡ ዓለም

ለዕድገታቸው ዋናው ተጠቃሽ

ምክንያት ሁልጊዜም እንደምንለው

መልካም የፖለቲካ አስተዳደር

(Good Governance) ስላላቸው

ነው። ፌዴራሊዝምም ይሁን

ሴንትራሊዝም፣ ፖርሊያመንታሪም

ይሁን ፕሬዝዳንታዊል፣ ኒዮ-

ሊሊበራልም ይከተሉ ሊበራል ብቻ

በየትኛውም በተከሉት የፖለቲካ

ጥርጊያ ለመረጣቸው ህዝብ አሻራ

ለቃል ለማተባቸው ታማኝና አገልጋይ

ወጥ አቋም ነው ያላቸው።

ወደ እኛው አህጉር አፍሪካና

በተለይ ደግሞ በእኛዋ ኢትዮጵያ

‹‹እዚህ ከተማ ውስጥ የራሱ የሆነ የነጠረ ስብዕና ያለው ሰው ማግኘት አዳጋች ነው። አንዱ የአንዱ ፎቶ ኮፒ ለመሆን

ነጋ ጠባ ይታትራል። ይሳካለትማል። በብልጭልጭ ህንፃ ካበደው ቅንጡ ሰፈር አንስተህ እስከጨርንቁሱ መንደር ብታስስ

የሚገጥምህ የሰው አይነት ብዙ አይደለም። ሁሉም የጋራ አካፋዩን እየፈለገ ተቧድኗል። ድንገት ድንቅ ኃሳብ አፍልቀህ

ተከታይህ ቢበራከት፣ አጀብህ አጀብ ቢያሰኝ ያጨበጨበልህ ሁሉ ገብተኸው እንዳይመስልህ

ከሥንታየሁ ዓለማየሁ

[sent_maki@yahoo.com]

ካጡ ወጣቶች አንስቶ እስከተደላደለው

አባወራ ድረስ የሚናውዙበት የጫትና

የሺሳ ሱስ ጠብታዋን የቀውስ ፍንጭ ባህር

እስክታክል ሊያሰፋት ይቻለዋል። እጅግ

አናሳው የጤና ሸፋናችን ደግሞ መውጫ

ቀዳዳ እንዳይታለም ተስፋን ያጨልማል።

አስቡት እስኪ - ከብዙ ህዝቦቿ መካከል

ብዙዎች እርዳታ ያሻቸዋል እየተባለ ያለባት

ሀገር ያዘጋጀችው የአዕምሮ ህመምተኞች

ሆስፒታል አንድ ነው። ለድንጉጥነት፣

ለስሜት ነውጥና ለእንቅልፍ እጦት

በመዳረግ ለአዕምሮ ህመም መንገድ

እንደሚጠርግ የሚታመነው የድምፅ

ብክለትስ?

የወቅቱን የወግ ሞቅታ ተከትሎ

ከማራገብና ከልብ ጠብ የማይሉ ልፍስፍስ

ማስታወቂያዎችን በለሆሳስ ከማስነገር

በዘለለ ጠንካራ እርምጃዎች የሚፈልጉ

የፖለቲካውን እንቅስቃሴ ስንቃኝ

በእውነት መንግሥት ለራሱ ህልውና

እንጂ ለህዝብ ብሎ የሚሰራው ነገር ያለ

አይመስልም። ለዚህ ፅሁፍ መነሻ የሆነኝ

ባላፈው ሳምንት ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ

በፓርላማ ያደረጉት ንግግር ነው።

ጠ/ሚኒስትሩ በተለያዩ

ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ

አጀንዳዎች ላይ ማብራሪያ በሰጡበት

ወቅት በጣም ያሳዘነኝ ነገር ቢኖር

አሉታዊ ሀሳብ የተነሳባቸው አጀንዳዎች

ላይ ምላሽ ሲሰጡ በጋለና በደም

ፍላት ስሜት ሌቦች፣ የቁራ ጩኸት፣

ሀሁ ያልገባቸው የሚሉ ቃላትን

መጠቀማቸው ነው። አንድ መንግስት

በተለይ ደግሞ ዴሞክራሲያዊ ነኝ ለሚል

መንግስት ለህዝብ ስራውን ሊያቀርብ፣

ሊጠየቅና ሊመረመር ይገባዋል እንጂ

እራሱ ሰብስቦ እኔ የምለውን ብቻ

ስሙኝ፣ የእናንተ አስተያየትና ሀሳብ

ከንቱ ነው አይነት እሳቤ፣ ለምን እንዲህ

አልሆነም ሲባል ሀሁ አልገባችሁም፣

እንደ ቁራ አትጩሁ፣ አጭበርባሪ . .

. በማለት በመድብለ ፓርቲ ተሳትፎ

አምናለሁ ከሚል መንግስት አንዱ

ብቻ ሲፈነጭበት፣ ስራውን እራሱ

ይመስለኛል። ‹‹መልሶ ግንባታ››፣

‹‹እድሳት››፣ ‹‹ማስፋፋት››፣ ‹‹አዳዲስ

ግንባታዎች›› እና የመሳሰሉ ከአዲስ አበባ

ጋር ተያይዘው የሚነሱ ቃላትና ሀረጎች

ከተማዋ ያለችበትን ሁኔታ በጨረፍታም

ቢሆን ይጠቁማሉ። በብዙ አቅጣጫዎች

ዘመናዊ ከተማ ለመሆን በደፋ ቀና

ተወጥራለች። የመዘናዊነት መለኪያው

ምንድን ነው ወደሚለው ክርክር ሳንገባ

ለመኖር የምታመች ከተማ ትሆን ዘንድ

ግን እንፈልጋን። ትርጉም አልባና ቅጥ-

የለሽ የድምፅ ልቀት ምቾት ይነሳልና

ደንበኛ ስሬትና ልኬት በጅቶ ፋታ ብናገኝ

አንጠላም።

እውነት እውነት እላችኋለሁ

በጩኸት ውስጥ መኖር እጅጉን

ያስጨንቃል።

መንግሥት እራሱ

ጠ/ሚኒስትሩ በተለያዩ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ አጀንዳዎች

ላይ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት በጣም ያሳዘነኝ ነገር ቢኖር አሉታዊ ሀሳብ

የተነሳባቸው አጀንዳዎች ላይ ምላሽ ሲሰጡ በጋለና በደም ፍላት ስሜት ሌቦች፣

የቁራ ጩኸት፣ ሀሁ ያልገባቸው የሚሉ ቃላትን መጠቀማቸው ነው

ሰርቶ እራሱ ብቻ የሚያወድስበት፣

ስህተቱን የማያይበት ከሆነ፣ እውነት

ይህ አይነቱ መንግሥት ለራሱ እሱስ

ቢሆን የአስተዳደር ሀሁ ገብቶታል ወይ

ያስብላል።

ጠ/ሚ መለስ በተለያዩ ጉዳዮች

ላይ እንደተነተኑት፣ ንግግራቸውን

ሲጀምሩ፣ ለመንፏቀቅ ያሰበ መንግስት

ተንፏቋልና በመንፏቀቁ ሊመሰገን

አይገባም፤ ይልቁንስ በፍጥነት

ለመራመድ አስቦ የተራመደን

እናመሰግናለን። እኛም በፍጥነት

ለመራመድ አስበን ተራምደናል ነው

አገላለፁ። መንግስት ከአዲስ አበባ እስከ

ጅቡቲ መንገድ ስራ እንደሚያጠናቀቅ፣

ከ8000-10,000 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ

ኃይል እንደሚያመነጭ፣ ከዚህም

5ሺህ 500 አካባቢው ከአባይ ግድብ

እንደሚገኝ ሲገልፁ ባያልቅም ጅምሩ

ተስፋ ሰጪ ይመስላል። በንግዱ ዘርፍ

ደግሞ የጅመላ ንግዱ ዘርፍ ተወዳዳሪ

የሌለበት ስለሆነ የውጭ ኩባንያዎችን

በማስገባት ተዋናዮችን እንፈጥራለን

ብለዋል። እዚሁ ላይ ከአሁን በፊት

ከIMF ጋር በፈጠሩት ያለመግባባት ሳቢያ

ነው የውጭ ኩባንያዎችን ማስገባት

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 191 ቅዳሜ ጥቅምት 18/ 2004

እና

የማቃለል ዘመን

መጣ! የመቅለል እና

የመቃለል ዘመንም

ተከተለው።›› ይህችን

መሪ መግቢያ

ከወዳጄ ይስማዕከ

‹‹የማቅለል

ወርቁ ሶስተኛ ልብ

ወለድ ወሰድኳት - ዛሬ ስለሶስት ገጽ

መጻፍ መፈለጌን አስረግጥባት ዘንድ።

አምላካችን ካደለን ጸጋ የተነሳ አሁንም

ድረስ በምሕረቱ እና በበጎነቱ እንጠበቃለን።

አሜን!!!

እስትንፋሳችን ነውና ዛሬም እንጽፋለን።

ለመሆኑ ለምንድን ነው የምንጽፈው?

ሕገመንግሥቱ የሰጠን መብት ስለሆነ

እንጽፋለን። ወይም አብጦና ጎርብጦ

አልመቸን ያለ ነግር ሲኖርብን እንጽፍና

እንተነፍሳለን። ወይም መጻፍ ሙያችን፣

እንጀራችን ስለሆነ እንጽፋለን። እውነት

እውነት እላችኋለሁ ከዚህ የተለየ አጀንዳም

የለን። ያላቸው እንኳ ቢኖሩ እንደ ቡርቃ

ዝምታ ደራሲ ስደት የእጃቸው እንደሚሆን

አናጣውምና በሰብዓዊ ፍጡር እቃቃ

ለመጫወት ብርቱም፣ ንቁም አንሆንም።

አንድ ገጽ

ኢትዮጵያ ሀገራችን ከሰለጠኑ ሀገራት

እኩል የሰለጠነች ትሆን ዘንድ ይመኛሉ።

የትምህርት አለመስፋፋት፣ የመሃይምነት

መንገሥ ያስቆጫቸዋል። የፍትሕ

መጓደል፣ የታናሽ መበደል፣ የንጹህ

መገደል ያበሳጫቸዋል።

ወገባቸውን በብርቱ ድግ አደግድገው ደፋ

ቀና ይላሉ። ሀገራችውን ትሰለጥናለች

ብለው ባሰቡበት መንገድ ሁሉ ያታትራሉ።

የዘመን መምጣትና መሄድ፣ አለዚያም

የግለሰብ መውጣትና መውረድ አይደለም

የሚያሳስባቸው። የፍትሕ፣ የዴሞክራሲ፣

የልማት፣ የሥልጣኔ በሀገሪቱ መስፈን

ነው ጮቤ የሚያስረግጣቸው።

ከድሃው ጋር ያለቅሳሉ። ከበላው ጋር

ይስቃሉ። ከጭቁኑ ጋር ይታገላሉ። ነፃ

ከወጣው ጋር ሻማ ይለኩሳሉ። ሁሉን

በልኩ ያውቃሉ። ሁሉንም በየመጠኑ

ይገነዘባሉ።

በደሳለኝ ሥዩም

3ኮመንትሪ

ገጽ

ስለገንዘብ ደንታ የላቸውም። ስለሥልጣን

አይገዳቸውም። ስለኃብት አያሳስባቸውም።

የማሳው በአዝርዕት መሸፈን፣ የሰብሉ አብቦ

ማፍራት፣ የከብቶች ምቾት፣ የሜዳው

መልካም ገጽ፣ የተራሮችን መዓዛ ቁርስ

እና ምሳቸው አድርገው ያስቡታል።

ኢትዮጵያ ተደፈረች ከተባለ ያለማንም

ቀስቃሽ በቀረርቶና በሽለላ ኮራ እንዳሉ

ከፊት ይሰለፋሉ። ጠመንጃ አንግተው

ድንበር ያስከብራሉ። ሰንደቅ አላማዋን

ሲያዩ በእንባ ይታጠባሉ።

እኒህን የመሰሉ ዜጎች ባለፉት ጊዜያትና

መንግሥታት አይተናል። በኖርንበት

ዕድሜም ሁሉ አስተውለናል። ለሀገራቸው

ፋይዳ ካልኖረው የማይማሩ፣ ለወገናቸው

ካልጠቀመ ኃብት የማያከማቹ፣ በሁሉም

ነገራቸው ሀገር እና ወገን ይቅደም ያሉ

ምሁራን፣ ሠራተኞች፣ ነጋዴዎች፣ የኪነ-

ጥበብ ባለሙያዎች፣ ወታደሮች፣ የልዩ

ልዩ ሙያ ባለቤቶችን ይህች ሀገር ባለፉት

ዘመን ሁሉ አፍርታለች። ባለንበትም

ዘመን ሁሉ ታፈራለች።

ሁለት ገጽ

የሚምጉት አየር ደንታ የማይሰጣቸው፤

የቆሙበት ምድር ምንማቸው የሆነ፤

ወጥተው ለሚገቡበት ጎዳና ደንታ ቢስ

የሆኑ እንዴት ናችሁ ለሚላቸው ሕዝብ

ከበሬታ የማይሰጡ።

የዘመናት መለወጥ፣ የመንግሥታት

መገለባበጥ፣ የሰላም መደፍረስ፣ የጦርነት

መቀስቀስ ስሜት የማይሰጣቸው፣

የበሽታ ወረርሽኝ፣ የርሃብና የጎርፍ

አደጋ፤ የድርቅና ድንገተኛ ቀውስ ሁሉ

ትኩረታቸውን የማይስበው።

ያገኙትን በልተው፣ ያሻቸውን ጠጥተው

ካሰኛቸው ጋር አንሶላ ተጋፈው ጨለማው

ነግቶ የነጋው ጨልሞ ለመፈራረቅ ይብቃ

እንጂ ከዚህ በላይ ኑሮ የማይመቻቸው፤

ከዚህ ወዲያ ኑሮ የማይታያቸው

ከንቱዎችን ይህች ሀገር ትናንትም ዛሬም

አፍርታለች።

መኖር አይቆምምና ወደፊትም እነዚህ

ግራ የገባቸው የትውልድ ‹‹ቀዝቃዛዎች››

መፈልፈላቸው አይቀርም። ዜጎች ለሀገራዊ

ዘመቻ ደፋ ቀና ሲሉ ኬሻ ሙሉ ጫት

ዘርግፈው ላባቸውን በመሀረብ እየጠራረጉ

ያመነዥካሉ። ሀገሪቱን ለማሳደግ

ዜጎች በየእውቀታቸው፣ በየሙያቸው፣

በየቦታቸው ሲረባረቡ ጆሮን የሚበጥስ

ሙዚቃ አስከፍተው ለአይን እንዲያሳሱ

ከተኳኳሉ እንስቶች ጋር በሀሽሽ ጥምብዝ

ይላሉ። ከዚህ የዳንኪራ ቤታቸው ውጭ

ያለው ሀገርና ህዝብ ለነሱ ምንም ነው።

ለእያንዳንዱ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣

ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ፖለቲካዊ ጉዳይ

የአስተዳደር ሀሁ አልገባውም

የተፈለገው ወይስ እውነት ገበያውን

ለማረጋጋትና ከህዝቡ ጋር ለመታረቅ?

የሀገርን የኢኮኖሚ ደረጃና የህዝብን ኑሮ

ለማሻሻል ግን እንደ እኔ የራሱን ሀገር

ስራ ፈጣሪና ነጋዴ ማብዛትና መፍጠር

የማያወላውል እርምጃ ይመስለኛል።

ነገር ግን ከአለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር

ለመታረቅ ሲባል እውነተኛውን ገሃድ

የውስጥ ሀቃችንን አጣልተን መሆን

የለበትም ባይ ነኝ።

ክቡር ጠ/ሚኒስትሩ የንግድ

ዘርፎችንና የመሬት አስተዳደርን

ዘመናዊ እናደርጋለን ብለው ወዲህ

ደግሞ ስለ ግብር ክፍያ ስርዓት ሲጠየቁ

ወይም ሲገመገሙ ‹‹አብዛኛው ነጋዴ

እስከዛሬ ድረስ ሲከፍለው የኖረው

መክፈል ከሚገባው በታች ነው። ይሁን

እንጂ አሁን ግን መክፈል የሚባለውን

ክፈል ሲባል አልከፍልም ማለቱ ነገሩ

አወዛጋቢ አድርጎታል። አንዳንዱ ደግሞ

መክፈል ከሚገባው በታች እየከፈለ

በሙስና ኖሯል። በስነ-ምግባር ጉዳይም

ችግር አለ፤ አስከፋዩ እራሱ ሌላ ነው፤

ሌብነት አለ፤ ሌቦች እንደሆኑ እያወቅን

ማስረጃ ስላጣን ግን ዝም ብለናቸው

ኖረናል›› በማለት በራሱ የሚምታታ

ሃሳብ ገልፀዋል። በመጀመሪያ ደረጃ

ማስረጃ ከሌላቸው ሌቦች ለመሆናቸው

ምን ማረጋገጫ አላቸው? ማስረጃ

ይቀድማል ወይስ ማወቅ? ስለኑሮ

ውድነትና ዕድገት ሲወራም በየትኛው

የኢኮኖሚክስ ህግ እንደሆነ እንኳን

ማጣቀሻ ሳይሰጡ ሀገር ሲያድግ የኑሮ

ችግር ሊጠፋ አይችልም›› ብለው ተስፋ

አስቆርጠውናል።

እንደሚባኝ፣ ዘመናዊው የአንድ

ሀገር የዕድገት መለኪያ (development

measurement) እንደ ድሮው በGNP፣

GDP፣ PCI በመሳሰሉት አይደለም።

ይልቁንስ እነዚህ ባህላዊ መለኪያዎች

ከሆኑ ሰነባበቱ። ነገር ግን ዘመናዊው

መለኪያ የህዝቡ የኑሮ ደረጃና ብቃት

ታይቶ ሲሆን፣ ይህም ሲባል በጤና፣

በኢኮኖሚና እንዲሁም በማህበራዊ

እንደ ትምህርት ጥራት የመሳሰሉትን

በመገምገም ትክክለኛውን የህብረተሰቡን

ህይወት በማየት የሚወሰን ነው።

በመግለጫውም ላይ አላደግንም ለሚሉ

አለማወቅ ነው ሲሉ መፍትሄ ብለው

ያስቀሙጠት ደግሞ ይህን አለማወቅ

ማስወገደ ነው የሚለውን ነው።

ታላቁ ሶቅራጠስ፣ ‹‹አለማወቅን

ማወቅ የእውቀት መጀመሪያ ነው››

ብሎ ተናግሮ ነበር። ታዲያ ኢህአዴግ

አሁን አለማወቅን ካለማወቁ ጭምር

ይባስ ብሎ እሱ ያላወቀውን እውቀት

ሳናውቅ እንድናውቅ በግድ ይገፋፋናል።

እንደ’ኔ እምነት፣ በዚህ ጠ/ሚኒስትሩ

ባቀረቡት ሪፖርት ላይ ኢህአዴግ

አመርቂ ውጤት ያስመዘገበው ነገር

ቢኖር የፀረ-ሽብርተኝነት ሕግ በማፅደቅና

ሽብርተኞችን አሳዶ በመያዝ ሲሆን፣

አሁንም በቅርብ ሳምንታት ውስጥ ወደ

‹‹አለማወቅን ማወቅ የእውቀት መጀመሪያ ነው›› ብሎ ተናግሮ ነበር። ታዲያ

ኢህአዴግ አሁን አለማወቅን ካለማወቁ ጭምር ይባስ ብሎ እሱ ያላወቀውን እውቀት

ሳናውቅ እንድናውቅ በግድ ይገፋፋናል። እንደ’ኔ እምነት፣ በዚህ ጠ/ሚኒስትሩ ባቀረቡት

ሪፖርት ላይ ኢህአዴግ አመርቂ ውጤት ያስመዘገበው ነገር ቢኖር የፀረ-ሽብርተኝነት ሕግ

በማፅደቅና ሽብርተኞችን አሳዶ በመያዝ ሲሆን፣ አሁንም በቅርብ ሳምንታት ውስጥ ወደ ቃሊቲ

የሚወረወሩ እንዳሉ ታገሱን ብለው እንድንጠባበቅ ነግረውናል።

የሚቆርጡት ጮማ፣ የሚያንቆረቁሩት ውስኪ፣ የሚያሽከረክሩት መኪናና የሚሽከረከሩበት ወንበር ከእጃቸው

እንዳይወጣ በ‹‹ለምን›› ባዮች ላይ የድንጋይ ናዳ የሚያወርዱ። ይህች ሀገር እኒህን የመሰሉ ዜጎችን ባለፉት

ጊዜያትና መንግሥታት አፍርታ ታይታለች። በኖርንበትና ባለንት ዘመንም ይህ እውነታ ቀጥሏል።

ቃሊቲ የሚወረወሩ እንዳሉ ታገሱን

ብለው እንድንጠባበቅ ነግረውናል።

የጋዜጠኝነት ሀሁ

ያልገባቸው ባሉበት ወቅት

ስለእውነት አፍሪካዊነቴን ጠላሁ።

እነሆ በሰለጠኑት እንደ አሜሪካና

እንግሊዝ ባሉት አይደለም፣ በሀገር

ደረጃ ጠቅላላ ሕግ ይስተካከል ብሎ

ለሚናገር ጋዜጠኛ፣ በግለሰብ ስም

ጠርቶ ለሚሳደብና ለሚያንቋሽሽ

ሰው እንኳን እስርና እንግልት

አይደርስበትም። ምክንያቱም ህዝብ

የመሰለውን፣ የሚበጀውን እራሱ

በገሀድ በመሬት ላይ ያለውን ፖለቲካ

ስለሚያውቀው ከአንድ ግለሰብና

ጋዜጠኛ እንዲሁም የፖለቲካ

ፓርቲ ጋር እሰጣ’ገባ አይገባም፣

አያሳድድም። ይልቁንስ ለእነሱ ይህ

ጊዜን ማባከን ነው።

በአጠቃላይ፣ ይህ ሁሉ

እንቅስቃሴ የሚያሳየን መንግስት

እራሱን ከመጠበቅ ባለፈ እውነትን

ከመክደን በዘለለ ትልቅ ስራ

እንደሌለው ነው። ይህም ሲባል

ከሌሎች የሥራ ዘርፎች ይልቅ የፀረ-

ሽብርተኝነት እንቅስቃሴው እራሱን

የቻለ ቦርድ አቋቁሞ ለዛውም ምርጥ

ከተባሉት ከነእንግሊዝ ሕጉን ኮፒ

አድርገው ሲንቀሳቀሱ ሲታይ ምን

ያህል አንገብጋቢ ሥራ እንደነበረበት

ያሳያል። ምናለ እንደው ለሌላው

እውነተኛ የኑሮ ውጥንቅጣችን

እንዲህ ምርጥ ከሚባለው ሀገር

ፖሊሲ ኮፒ ቢያደርጉልን!

አለበለዚያ አንገብጋቢውን ትተው፣

ለፍርሀታቸው የሚሰሩ ከሆነ፣

እኛ ሳንሆን እነርሱ ናቸው ሀሁው

ያልገባቸው።

ሁሉ ግድ የለሽና ባዕድ ናቸው። ምንም

አይሞቃቸው፣ ምንምም አይበርዳቸው።

እነዚሀ ሁለተኛ የዜጎች ገጽታ መሆናቸው

ነው።

ሶስት ገጽ

የሰዎችን ደም በጽዋ እየተቀባበሉ

መጎንጨት የሚዳዳቸው፤ በጎ ነገር ለሀገር፣

ለህዝብ ስለተሰራ ብቻ የሚያማቸው፤

መልካም ሰውን አጋድመው ካልገፈፉ

በስተቀር ሰላም የማይሰማቸው።

የተባረኩት የተከሉትን ችግኝ ከጫፉ

ቀንጥሰው መጣል የእርካታቸው ምንጭ

የሆነ፤ በለመለመ መስክ ላይ ቤንዚን

ማርከፍከፍ ውዴታቸው የሆነ። የተማሩ

ሰዎችን ሲያዩ የሚነስራቸው። የምሁራንን

ሐሳብ ማዳመጥ ውድቀት የሚመስላቸው

ዜጎች።

ክርስቶስ እንዲሰቀል በርባን ግን እንዲፈታ

ከመጮኽ አልፈው ሐሳባችንን ደግፉ፣

አብራችሁ ጩኹ፤ ካልጮኻችሁ

እንገድላችኋለን ብለው አንባጓሮ ሚያነሱ፤

አዎንታዊ ሐሳብ በአእምሯቸው ታስቧቸው

የማያውቅ፤ የራበው ድሃ አስፓልት ዳር

ወድቆ ሲቆራመድ አጥንቱን እየቆጠሩ

ፈገግ የሚሉ።

የሚቆርጡት ጮማ፣ የሚያንቆረቁሩት

ውስኪ፣ የሚያሽከረክሩት መኪናና

የሚሽከረከሩበት ወንበር ከእጃቸው

እንዳይወጣ በ‹‹ለምን›› ባዮች ላይ የድንጋይ

ናዳ የሚያወርዱ።

ይህች ሀገር እኒህን የመሰሉ ዜጎችን

ባለፉት ጊዜያትና መንግሥታት አፍርታ

ታይታለች። በኖርንበትና ባለንት ዘመንም

ይህ እውነታ ቀጥሏል። የሚያብለጨልጭ

ብረት ከሰው ላይ ለመውሰድ ጣትን

ወይም አንገትን ቆርጠው በኪሳቸው

የሚደብቁ፤ ሥልጣኔን መናፈቅ፣

ዴሞክራሲን መስበክ፣ ልማትን ማምጣት

ለምላሳቸው እንጂ ለጭንቅላታቸው ሥራ

ያልሆነላቸው። እኒህ ሶስተኛ ገጽ ዜጎች

መሆናቸው ነው።

ለእነዚህ ማሳያ የሚሆኑት ደግሞ ሁሌም

አዲስ የመከራ ዘመን በሚያበስረው አዲስ

ዘመን ጋዜጣ ላይ የነገሱት ናቸው።

የብዕር አጣጣሉ ሁሌም አንድ ነው።

እገሌ ከ --- (ቦታ) እየተባለ ሥም

ይሰጠው እንጂ ሀሳብን ሳይሆን የፖለቲካ

ትንታኔን፣ የውሳኔ ሀሳብን፣ የመረረ

ጥላቻን የሚያራምድ አንድ መደበኛ

ግለሰብ እንደሚጽፈው ለሚያነቡ ሁሉ

የሚሰወር እውነታ አይደለም።

ብዙ ጊዜ ስድብ ይጻፍበታል። ግለሰቦችና

የግል ሚዲያዎች ይዘለፉበታል - የአዲስ

ዘመኑ ገጽ ሶስት። ካልታሰሩ፣ ካልተዘጉ

ሞቼ እገኛለሁ ይባልበታል። ስለዴሞክራሲ

በሚወራበት ሀገር በአንድ ሰላማዊ

ዜጋ ‹‹ሥም›› እየተጻፈ ግለሰቦች ክፉኛ

ይኮነኑበታል።

አዲስ ዘመን በመሰረቱ ገጽ ሶስትን

እንደተባለው ለተለያዩ ሐሳቦች

ማንሸራሸሪያነት እያዋለው እንዳልሆነ

ይታወቃል። ግን እስኪ የመንግሥትን፣

የፖሊስን፣ የፍርድ ቤትን፣ የይቅርታ

ቦርድን ወዘተ. ኃላፊነትና ሥልጣን ትቶ

ወይም ጣልቃ ገብቶ የሚፈተፍት ጽሑፍ

ማስተናገድ ጋዜጣውን እንደሚያስንቀው

አጥተውት ነው? ሌላው ሁሉ ቀርቶ

ማለቴ ነው።

ይሄኔ የአዲስ ዘመን ቅርጫት ቢፈተሸ

ስለእያንዳንዱ ስድባቸው እንደናቋቸው

የሚገልጹ የብዙ አንባቢዎች የቅሬታና

የቁጣ ደብዳቤ ብዛት ምን ያህል ይሆን?

እስቲ በ’ኔ ሞት የመቀመጫዋን ጉድ

ያላስተዋለች ዝንጀሮ ምሳሌ ከአዲስ ዘመን

ውጭ ለሌላ የሚጠቀስ ምሳሌ መሆን

ነበረበት?

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

7

8

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 191 ቅዳሜ ጥቅምት 18/ 2004

የአንበሳ አውቶቡስ ጉዞ እና ገጠመኞች

በናፍቆት ዮሴፍ

“ሰፈሬ ሽሮ ሜዳ እንደመሆኑ ከመርካቶ

17 ቁጥር አውቶቡስን ተሳፍሬ

ቅድስት ማሪያም ቤ/ክ ስንደርስ፣ አንድ

አዛውንት ኡኡታ አሰሙ ‹አውቶቡሱ

ሳይከፈት ወደ ፖሊስ ጣቢያ ይሂድልኝ›

ሲሉ ሹፌሩን ተማጠኑ፤ ሶስት ሺህ ብር

ተወስዶብኛል በሚል። ሹፌሩም አራት

ኪሎ አካባቢ (አሁን ፈርሷል) ፖሊስ

ጣቢያ አውቶቡሱን ይዘው ገቡ። ሁሉም

ሰው እንዲወርድ ተደረገ። ምን ዋጋ

አለው ሌባው ቀድሞ ወርዶስ ቢሆንስ

እያልን ወረድን

“የሆነ ሆኖ ሁሉም ሰው ወርዶ እንዲፈተሽ በአንድ

መቶ አለቃ ትዕዛዝ ከተላለፈ ከደቂቃዎች በኋላ

መቶ አለቃው ‹ሌባው ስለተገኘ ፍትሻውን አቁሙ›

ሲል ለባልደረቦቹ ትዕዛዝ አስተላለፈ። እጅግ መልከ

መልካም፣ አራቱም ጣቶቿ ላይ ወርቅ የደረደረች፣

አለባበሷ በእጅጉ የተዋበ ወጣት ላይ የመቶ አለቃው

አይን አረፈ።

“የወሰድሽውን ብር አምጪ” ብሎ ሲያምባርቅባት

የሁላችንም እጢ ዱብ አለ። “የምን ብር!? የሰውን

ማንነት ሳታውቅ አትናገር” ስትል ኮስተር ያለ መልስ

ሰነዘረች ወጣቷ። ይሁን እንጂ መቶ አለቃው፣

“ገብተሽ በጉማሬ አለንጋ ስትሞሸለቂ ታወጪ የለ?”

በማለት እየጎተተ ወሰዳት።

17 ቁጥር አውቶቡስ እና እኛ ተሳፋሪዎች ፖሊስ

ጣቢያው ውስጥ እንደተገተርን ደቂቃዎች፣ ብሎም

ሰዓታት አለፉ። ብዙ እናቶችና አባቶች፣ “ፍፁም

አታደርገውም፤ ለሌላ ጉዳይ ፈልጓት ይሆናል” ሲሉ

አጉተመተሙ። ልጅቷ ጠንከር ያለ አለንጋ ሳትቀምስ

አልቀረችም፣ “እሺ ተወኝ፤ የደበቅሁበትን ላሳይህ”

ስትል መሬት ተሰንጥቃ ብትውጠኝ ደስተኛ ነበርኩ።

በርካታው የአውቶቡሷ ተሳፋሪዎች የሚሆነውን

ለማየት አሰፈሰፍን። ልጅቷም ፖሊሱን እየመራች

የአውቶቡሷ መጨረሻ ወንበር ወደሚገኝበት ሄደች።

ሁሉም ይህን ጉድ ለማየት አሰፈሰፉ። የመጨረሻው

ወንበር ስትደርስ ሶስት ሺህ ብር ሶስት ቦታ በብር

ላስቲክ የታሰረ ስለነበር ከዛን በፊት አይቼው

በማላውቀው አይነት ወፍራም ፕላስተር ከወንበሩ

ስር ሶስት ቦታ አጣብቃዋቸለች። እሱን እየፈታች

ለፖሊሱ ስትሰጥ ያልደረሰባት የእርግማን እና የስድብ

አይነት አልነበረም። እኔ አፌ በድንጋጤ ተለጉሟል፤

በኋላ ግን “እንዴት ልታውቃት ቻልክ?” ስል መቶ

አለቃውን በድንገት ብጠይቀው፣ “አገር ምድሩን

ያጥለጠለቀው የእሷ ፎቶ ነው። ከዚህ በፊት በርካታ

የስርቆት ሪከርድ አለባት። ስንት ጊዜ መሰለህ ታስራ

የተፈታችው?” ሲል ምላሽ ሰጠኝ። እሷም ታሰረች፣

እኛም አውቶቡሳችን ውስጥ ገብተን ወደየምንሄድበት

ጉዟችንን ቀጠልን። የወጣቷም ያለመጠርጠር ጥረት

በዚህ አበቃ።”

ይህ ከላይ ያስነበብናችሁ ገጠመኝ አቶ ጥላሁን

ገዳሙ የተባሉ የ56 ዓመት ጎልማሳ ከ13 ዓመት

በፊት በአውቶቡስ ውስጥ ያጋጠማቸው እውነታ

ነው። አንበሳ የከተማ አውቶቡስ ከ1935 ዓ.ም ጀምሮ

በተለይም ዝቅተኛና መካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላላቸው

የህብረተሰብ ክፍሎች የማይረሳ ውለታ ባለቤት ነው።

ምንም እንኳን በአሁኑ ሰዓት የሀብታምና የድሀው

ልዩነት የሰማይና የምድርን ያህል ርቆ መካከለኛ

የኑሮ ደረጃ (Middle class) የሚባለው የህብረተሰብ

ክፍል የለም ብለን ለመናገር በሚያስችለን ደረጃ ላይ

ብንደርስም።

በአንበሳ የከተማ አውቶበስ ውስጥ እጅግ አስገራሚ፣

አሳዛኝ፣ አዝናኝና የተደበላለቀ ስሜትን የሚፈጥሩ

ትዕይንቶች የሚከሰቱበት የመጓጓዣ አውታር መሆኑን

ከማንም በላይ ተጠቃሚዎቹ ጠንቅቀው ያውቁታል።

ለዛሬም የተሳፋሪዎችን፣ የትኬት ቆራጮችን እና

የአንበሳ አውቶቡስ ሹፌሮችን ገጠመኞች እንቃኝ።

ከዚያ በፊት ግን ስለአንበሳ አውቶቡስ አገልግሎት

ጅማሮና የስራ ዘመኑ ጥቂት ማለት አግባብ ነውና

እነሆ።

ወራሪው የፋሺስት ጣሊያን መንግስት ሀገራችን ውስጥ

በነበረበት ጊዜ ይጠቀምባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችንና

የመኪና መለዋወጫ እቃዎችን በማሰባሰብ የስራና

መገናኛ ሚኒስቴር ይባል በነበረው መ/ቤት አማካኝነት

በ1935 ዓ.ም “የህዝብ ማመላለሻ” (ሕ.ማ) በሚል

ስም ነበር የተመሰረተው - አንበሳ የከተማ አውቶበስ

አገልግሎት።

ታህሳስ 2 ቀን 1944 ዓ.ም ህጋዊ ሰውነት በማግኘት

በአክሲዮን ከተቋቋመ በኋላ አረንጓዴና ቢጫ የተቀቡ

10 አውቶቡሶችን ይዞ ሥራ መጀመሩን የድርጅቱ

ማህደር ያመለክታል፤ እነዚህ አውቶቡሶች በከተማዋ

አራት መስመሮች ላይ የተሰማሩ እንደነበር ይነገራል።

ለህብረተሰቡ አገልግሎት ይሰጥ የነበረው የቀድሞው

ህዝብ ማመላለሻ የአሁኑ አንበሳ አውቶቡስ በዚያን

ወቅት የውጭ አገር ዜጎችን ጨምሮ 120 ሰራተኞች

ነበሩት።

በ1952 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይሰጥ የነበረው ትራንስፖርት

አገልግሎት መስመሩ ከ4 ወደ 14 እንዲያድግ ሲደረግ

በየመስመሩ ሲመደቡ የነበሩ አውቶብሶች ብዛትም

ከሁለት ወደ ሶስት ከፍ እንዲል ተደረገ። እንዲህ

እንዲህ አያለ በ1986 ዓ.ም በአዋጅ ቁጥር 187/1986

በ14 ሚሊዮን ብር ካፒታል “አንበሳ የከተማ አውቶቡስ

አገልግሎት ድርጅት” ተብሎ በአዲስ መልክ ራሱን

ችሎ ከተቋቋመ በኋላ በየጊዜው ቁጥሩ እየጨመረ

የሚሄደውን የከተማዋን ህዝብ ፍላጎት ለማሟላት

በተለያዩ ጊዜያት በርካታ አውቶቡሶችን በእርዳታና

በግዢ በማስመጣት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

በአሁን ሰዓት ድርጅቱ አዳዲስ 120 አውቶቡሶችን

ያስገባ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ አስሩ 18 ሜትር

እርዝመት ያላቸው፤ ተቀጣጣይ - አራዶች አኮርዲዮን

ይሏቸዋል - እንደሆኑ ከድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት

ኦፊሰር ከአቶ ሸዋረጋ ሳህሌ ለመረዳት ችለናል።

ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት በቀን 320 አውቶቡሶችን

ለስራ እንደሚያሰማራ የነገሩን አቶ ሸዋረጋ፣ ከ2740

በላይ ቋሚ ሰራተኞች እንዳሉትም ነግረውናል።

ስለአንበሳ አውቶቡስ አመሰራረት በጥቂቱ ከነገርናችሁ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ልዩ ቅኝት

ወደ ዋናው ሃሳባችን እንሆ ተመልሰናል።

የአንበሳ አጋጣሚዎች

አንበሳ አውቶቡስ ውስጥ ብዙ የሚከሰቱ ነገሮች

አንዳሉ ይደመጣል። በተለይ ደግሞ በሚፈጠረው

መተፋፈግና መነካካት የወንዶች ስሜት እንደሚነሳሳ

ይነገራል። የዚህ ሰለባ የሆነ አንድ ወጣት ተከታዩን

አጫውቶኛል፡- “ሁለት ወንዶችና አንድ ወጣት ሴት

ወደተሳፈርኩበት አውቶብስ ሲገቡ ተመለከትኩ።

ሆኖም ሴቷ ወደ እኔ በመጠጋት ትተሻሸኝ ጀመር።

ሁኔታዋ ሁሉ እኔን ወደ ሌላ ስሜት ውስጥ ከተተኝ።

በወቅቱ አውቶቡሱ ውስጥ ካሉት ወንዶች ውስጥ

ይህቺ ቆንጆ እኔን መርጣ በዚያ ሁኔታ ላይ መገኘቷ

ኩራት እንዲሰማኝ አድርጎኛል” ይላል ወጣቱ። ይሁን

እንጂ ወጣቱ በቆንጆዋ ሁኔታ ተማርኮ ስሜቱን

ሲያዳምጥ አብረዋት የነበሩት ሁለት ወንዶች ከኪሱ

1ሺህ አንድ መቶ ብር ሰርቀውት ከወረዱ በኋላ

መባነኑን ያስታውሳል። ቆንጆዋ ማደንዘዣ መሆኗ

ነው።

በአንድ ወቅት ነው አንድ ወጣት 19 ቁጥር አውቶቡስ

ውስጥ ተሳፍሮ ወደ አስኮ እየተጓዘ ነው። አንድ

ትልቅ አዛውንት ካፖርት ለብሰው ቆመዋል። “አባት

ልነሳልዎትና ወንበር ላይ ይቀመጡ አልኳቸው። ግን

ፈቃደኛ አልሆኑም” የሚለው ይህ ወጣት፣ መውረጃው

ሲቀርብ ለመውረድ ከወንበሩ ይነሳል። አዛውንቱ

የያዙትን ብረት ይዞ አውቶቡሱ እስኪቆም ለመጠበቅ

ሲሞክር አውቶቡሱ ይንገጫገጭና ልጁ ሚዛኑን

ይስታል። እናም የሚይዘው ሲያጣ ተንደርድሮ

የአዛውንቱ የካፖርት ኪስ ውስጥ ዘው ይላል።

አዛውንት ሆዬ ካፖርታቸው ኪስ ውስጥ ያለውን እጅ

ይይዙና እሪ ይላሉ። አውቶቡሱ ቆሞ ልጅና አዛውንቱ

ተያይዘው ፖሊስ ይደርሳል። “በህይወቴ አንደዚያ ያለ

ቅሌት ገጥሞኝ አያውቅም። በስንቱ ታቦት ብምል፣

ብገዘት ሰውየው ሊያምኑኝ አልቻሉም። ስለዚህ ጉዳዩ

እስኪጣራ ፖሊስ ጣቢያ አምሽቻለሁ” ሲል ባላሰበበት

መዋሉን ይናገራል።

ራሄል ይስማው ላፉት ስምንት አመታት የአውቶቡስ

ትኬት ቆራጭ ሆና ሰርታለች። በስራዋም ብዙ

ገጠመኞች አሏት። “አንድ ቀን 53 ቁጥር አውቶቡስ

ላይ እየሰራሁ ቲኬት ፈታሽ ይመጣል። አንዱ ትኬቱን

ጥሎት ስለነበር ፈታሹ ሁለት እጥፍ እንዲከፍል

ያስገድደዋል። ልጁ ዘና ብሎ፣ “እሺ እከፍላለሁ”

ብሎ ኪሱ ሲገባ ቦርሳው ተወስዷል” የምትለው

ራሄል፣ በዛን ሰዓት የነበረውን ድንጋጤ አሁንም

እንደምታስታውሰው ትናገራለች። በመጨረሻም

ሁኔታውን ሳይ እኔ ከፈልኩለት። እሱም ሌላ ቀን

እንደሚከፍል ነግሯት ስልኳን ተቀብሎ መውረዱን፣

በዚህም የተነሳ ለረጅም ጊዜ የፍቅር ጓደኛሞች ሆነው

መቆየታቸውን ትናገራለች።

ሞኖ ባንዶች

አውቶቡስ ውስጥ ሲጓዙ ምንም ድምፅ ሳይኖራቸው

የሚዘፍኑ አስቂኝ ማስታወቂያዎችን በመናገር

ከተሳፋሪው የሚቀፍሉ (የሚያባብሉ) [ዘመናዊ

የልመና አይነት ነው] በርካቶች ናቸው። እንደእነዚህ

አይነቶቹን ሰዎች እርሶ በተለይ አውቶቡስ ተጠቃሚ

ከሆኑ በተለያዩ ቁጥር አውቶቡሶች ላይ ያገኟቸዋል።

ራሳቸውን “ሞኖ ባንድ” እያሉ የሚጠሩም ያጋጥማሉ።

“ሞኖ ባንድ እንሰኛለን። እናንተን ለማዝናናት ምንጊዜም

ዝግጁ ነን። ይህን ማይክ የሰጠን እንዲህ አይነት

ሙዚቃ መሳሪያ አስመጪ ድርጅት ነው። የክብር

ስፖንሰራችን ደግሞ አንበሳ የከተማ አውቶቡስ ነው”

እና መሰል ነገሮችን በመደርደር ዘመናዊ ልመናዎች

ይካሄድበታል። አይ አንበሳ አውቶቡስ፤ “በእኔና በባስ

የማይመጣ የለም” ያለው ማን ነበር?

ቀዶ ጥገና

ቀዶ ጥገና ስንል የህክምናውን እንዳይመስልዎ።

በአውቶቡስ ውስጥም የቀዶ ጥገና በርካታ

ስፔሻሊስቶች እንዳሉ ልንጠቁምዎ እንጂ። በአንድ

ወቅት አንድ ጓደኛዬ የገጠመውን እንዲህ አጫዎተኝ።

ሰውየው ከጎጃም በርካታ ማር ጭነው አዲስ አበባ

ለነጋዴ ያስረክባሉ። እናም የዋሁና ገራገሩ የገጠር

ሰው በከረጢት ብራቸውን አንግተው ከኮታቸው ስር

አንጠልጥለዋል። ከዚያም ወደ ማረፊያቸው ይሄው

ጓደኛዬ ወደተሳፈረበት ስምንት ቁጥር አውቶቡስ

ውስጥ ይሳፈራሉ። አውቶቡሱ ትንሽ እንደተጓዘ

ቀዶ ጠጋኙ የሰውየውን ከረጢት (የሚጋፋ መስሎ)

በመቀስ ይሁን በምላጭ ከስሩ ይሸረክትና ብሩን በስር

በኩል ወስዶ አንዱ ፌርማታ ላይ ዱብ ይላል። ያኔ

አንገታቸው የቀለላቸው የማር ነጋዴ ደረታቸውን

ቢዳብሱ ጊዜ የከረጢታቸው ሆድ መቆዘሩ ቀርቶ ባዶ

ሆኗል።

እናም ሰውየው ኡኡ አሉ እንዲህ እያሉ፡- “እሪ

በል ሸዋ ጎጃም ተበላ እሪ በል ሸዋ ጎጃም ተበላ”።

እንዲህ ያሰኛሉ ቀዶ ጠጋኞች። ይህን የሰማ አንድ

ሌላ ሰው እንዳጫወተኝ ሁለት ጓደኛሞች እቃ ሊገዙ

መርካቶ ይሄዳሉ። አውቶቡስ ፌርማታው ላይ እያሉ

የአንዱ ስልክ ከኪሱ ይጠፋል። ሌላው ጓኛውን፣

“እንዴት ኪስህ ውስጥ ትይዛለህ” በማለት ተቆጣው።

ምክንያቱም እርሱ ሞባይል ስልኩን በማንጠልጠያ

አንገቱ ላይ አንጠልጥሎ ስልኩን ደረት ኪሱ ነው

የሚያስቀምጠው። እናም፣ “አሁን በቃ ተወስዷል።

ለሌላ ጊዜ አንደኔ እንዲህ አድርገህ ያዝ” ብሎ አንገቱ

ላይ ያለውን የስልክ ገመድ ሲስበው ስልኩ ተወስዶ

ገመዱ ብቻ ነው የቀረው። ኪሱን ቀዶ ጠጋኞቹ ቀደው

ስልኩን ወስደዋል። እንዲህ ናቸው ቀዶ ጠጋኞች፤

ከደረት ውስጥ ልብን ለመውሰድ ከአይን ላይ ኩል

ለመንጠቅ ረቀቅ ያለ ሰርጀሪ ይሰራሉ። ከእነርሱ

ይሰውረን ብሎ መፀለይ መልካም ነው።

“አንዴ ነው እቃ ለመግዛት በርከት ያለ ብር ይዤ

አውቶቡስ ውስጥ ነኝ። አንዱ ወጠምሻ አጠገቤ

ቆሟል። ይተሻሸኛል፤ ይገፋኛል። ‘ለምን ራስህን ችለህ

አትቆምም’ ስል ገሰፅኩት። ሆኖም ሊተወኝ አልቻለም”

ትላለች ለገሀር 32 ቁጥርን ስትጠብቅ ያገኘኋት

የትምወርቅ። ግፊያውና ፍትጊያው ሲሰለቻት አምርራ

መቆጣቷን የምትናገረው የትምወርቅ፣ “ቆይ ከእኔ

ምን ፈልገህ ነው እንዲህ የምትሆነው ብለው፣ ‘አንቺ

ገገምሽ አንጂ እኔማ ያጨቅሽውን ብር አይቼ ነው’

አለኝ - አይኑን በጨው አጥቦ፤ እንዴት አወቅክ

ብለው፣ ‘ከፈለግሽ አንኳን ቦርሳሽን ከስር የለበሽውን

የውስጥ ሱሪ ቀለም እነግርሻለሁ’ በማለት ቀልቤን

በድንጋጤ ገፈፈው” በማለት በጥርጣሬዋ ከሰርጀሪ

መዳኗን ታስታውሳለች። እነዚህ ቀዶ ጠጋኞች ቦርሳን

ብቻ ሳይሆን ውስጥንም ራጅ ማንሳት ይችላሉ እንዴ?

ያስብላል።

የቡድን ሥራ

አውቶቡስ ውስጥ ከሚፈጠሩ አጋጣሚዎች ውስጥ

የረቀቀው የሌቦች የቡድን ስራ ይጠቀሳል። ለዚህም

የተለያዩ ዘዴዎች ይፈበረካሉ። ከላይ እንደጠቀስነው

በሴት ተማርኮ ሲፈዝ ጓደኞቿ የሰረቁት አንድ ሺህ

አንድ መቶ ብር አንዱ የቡድን ስራቸው ውጤት

ነው። ‹‹የተግባረዕድ ተማሪ ሆኜ በአውቶቡስ ነበር

የምመላለሰው። እናም በወቅቱ የወር ክፍያ 48 ብር

ይዣለሁ›› በማለት ገጠመኙን የጀመረው ችሎታው

የተባለ ወጣት በወቅቱ በርከት ያሉ ወጣቶች አውቶቡስ

ውስጥ ገብተው በተንተን ብለው መቆማቸውን

ያስታውሳል። ከመካከላቸው አንዱ እጅግ ተጫዋችና

ሲበዛ ቀልድ አዋቂ ተሳፋሪዎች በሱ ጫወታ ሲፈዙ

ሌሎቹ ወደ ስራቸው ይሰማራሉ። ‹‹እኔንም የገጠመኝ

ይሄው ነው በልጁ ወሬ ተመስጨ ስፈዝ ለካስ ጓደኛው

ኪሴ ገብቶ 48 ብሩን ሊወስድ ይታገላል። በወቅቱ

ጠበብ ያለ ጅንስ ስለለበስኩ እጁ ሲነካኝ ነቃሁ››

በማለት እንዴት እንደተረፈ የሚገልፀው ችሎታው

አሁን ረቀቅ ያሉ ገፋፊዎች ስለተበራከቱ መጠንቀቅ

አንደሚያሻ ይመክራል።

መልካም አጋጣሚዎች

አንድ ነገር መጥፎ ጎን እንዳለው ሁሉ መልካም

ጎኖችም አይጠፉትም። የከተማ አውቶቡሶችም

እንዲሁ። ስርቆቱ ጾታዊ ትንኮሳውና መሰል ጥሩ

ያልሆኑ አጋጣሚዎች የሚፈጠሩ ቢሆንም መልካም

ነገርም ጎን ለጎን ይኖራል። ስማቸውን መናገር

ያልፈለጉ አንድ ጎልማሳ በአንበሳ አውቶቡስ ውስጥ

ለ17 አመታት አገልግለዋል። ድርጊቱ በተፈፀመበት

እለት ጠዋት ተነስተው በስራ ላይ ተገኝተዋል።

ሲያሸከረክሩ ውለው ከቀኑ ወደ 10 ሰዓት አካባቢ

ድንገት ታመው አውቶቡሱን መንዳት ያቅታቸዋል።

መሀል አስፋልት ላይ መኪናው ቀጥ ብሎ ይቆማል።

‹‹ምን እንደነካኝ ሳላውቅ ራሴን እንደመሳት አደረገኝ።

ምን እንደተፈጠረ አላውቅም ነበር›› የሚሉት እኚህ

ግለሰብ ከዚያም አንድ መስፍን የተባለ ወጣት እሳቸውን

አስነስቶ መሪውን በመጨበጥ ህዝቡን የሚፈልግበት

አድርሶ እርሳቸውንም ሀኪም ቤት ወስዶ ማሳከሙን

ያስታውሳሉ።

ሙሉጌታ የ60 ቁጥር አውቶቡስ ደንበኛ ነው።

ሁሌም ከአዲስ አበባ ደብረዘይት ከደብረዘይት አዲስ

አበባ ለመመላለስ ይህቺ አውቶቡስ ባለውለታው ናት።

ምክንያቱም በዛን ወቅት በአየር ኃይል ውስጥ ሬዲዮ

ኦፕሬተር ሆኖ ይሰራ ስለነበር ሁሌም ጠዋትና ማታ

ተመላላሽ ነው። ከሳምንቱ በአንዱ ቀን ከአየር ሀይል

ግቢ ስራውን አጠናቆ 60 ቁጥር ውስጥ ይገባል።

አውቶቡሱ ተጨናንቆ ስለነበር አንዲት ሴት ቦርሳዋን

እንዲይዝላት ትጠይቀዋለች። ይቀበላልም። ‹‹ቦርሳውን

ስትሰጠኝ መልኳን ልብ ብዬ አላየሁትም በኋላ ግን

ወደ አዲስ አበባ እየቀረብን ስንመጣ እንዴት ቦርሳዋን

አትጠይቀኝም እያልኩ አስብ ጀመር። ምክንያቱም ሰው

መንገድ ላይ እየወረደ አውቶቡሱ ቀለል ብሎ ስለነበር”

ይላል። ይሁን እንጂ አውቶቡሱ ለገሀር ደርሶ ሁሉም

ሰው ሲወርድ የቦርሳው ባለቤት የለችም ግራ ገባው።

‹‹ባለቦርሳ ብዬ እንዳልጠራ አንዷ ተነስታ የኔ ነው

ብትለኝስ ብዬ ዝም አልኩ›› ይላል ሙሉጌታ። እናም

በወቅቱ ቦርሳውን ወደቤቱ ይዞ ይሄድና መፈተሽ

ይጀምራል። በውስጡም ፖስፖርት፣ 5 ሺህ ጥሬ

ብር፣ የ19 ሺህ 500 ብር ቼክ፣ ሌሎች ወረቀቶች፣

የቀበሌ መታወቂያና የእጅ ሰዓት በቦርሳው ውስጥ

መኖሩን ማረጋገጡን ያስታውሳል። ‹‹ከራሴ ጋር

ብዙ ተሟገትኩ። መታወቂያው ላይ ባገኘሁት ስልክ

ልደውል አልደውል በሚል። -ደውልላት የሚለው ሀሳቤ

በማመዘኑ ደወልኩላት›› በማለት የነበረበትን የሀሳብ

አጣብቂኝ ይናገራል። ሙሉጌታ ስልኩን በደወለ ጊዜ

ያነሳው ወንድ ነበር። ስለሁኔታው ሲነግረው ‹‹መልሰን

እንደውል ትንሽ ችግር አጋጥሟት አልተረጋጋችም››

ብሎ አንደመለሰለት ከገለፀ በኋላ በዛን ወቅት

ተንቀሳቃሽ ስልክ ስላልነበረው የእናቱን የቤት ስልክ

ቁጥር መስጠቱን ይናገራል። ‹‹ደወለችልኝ ከዚያም

እናቷ በድንገት ታመው አደጋ ውስጥ እንደነበሩ

ስትሰማ ገና ዱከም ስትደርስ ደንግጣ አንደወረደችና

ፈፅሞ ቦርሳውን እንዳላስታወሰች ነገረችኝ›› ይላል

ሙሉጌታ።

ልክ በአራተኛው ቀን ደውላ ደብረዘይት ከመጣ

እንዲያቀብላት መጠየቋን የሚገልፀው ይህ ወጣት

ቦርሳውን ይዞ ደብረ ዘይት ይሄድና በተቀጣጠሩበት

ቦታ ይገናኛሉ። ቤቷ ይዛው ልትሄድ ብትሞክርም

የስራ ሰዓት በመድረሱ ከስራ ሲወጣ እንደሚያገኛት

ቀጠሮ ይዞ ወደ ስራው ያመራል። ሲወጣም በቀጠሮው

መሠረት ቤቷ ይሄዳል። ዝምድናው ከዚህ ይጀምራል።

አሁን ግን የሴትዮዋን ልጅ አግብቶ ሁለት ልጆችን

በመውለድ ባለቦርሳዋን አያት አድርጓታል። መልካም

አጋጣሚ ይሏል ይህ ነው።

‹‹በባስ ውስጥ እየሄድኩ ነው በቁመት ከእኔ እኩል

የሆነ ወጣት ፊት ለፊቴ ቆሟል አንድ ብረትም

ተጋርተን ይዘናል›› ትላለች ረዘምና ጠየም ያለችው

የ29 ዓመት ወጣት አይናለም ዳርሜለህ። ድንገት

ሳይታሰብ አውቶቡሱ ፍሬን ይዞ በመንገጫገጩ እሷና

ከፊት ለፊቷ የቆመው ወጣት ሚዛናቸውን ስተው

ሲወዛወዙ ከንፈራቸው መገጣጠሙን ትናገራለች።

‹‹እነሆ በዚያች በተቀደሰች አጋጠሚ የተነካካው

ከንፈራችን ዛሬም አልተላቀቀም /ተጋብተናል/ በማለት

አስገራሚውን ገጠመኘዋን ትናገራለች።

የስሜት አንበሶች

አንበሳ አውቶቡስ ውስጥ ተሳፍረው እየተጓዙ

ስሜታቸው አንበሳ ሆኖ ጾታዊ ትንኮሳ የሚያስከትሉትስ

ስንቶቹ ናቸው? መቼም እዚህ ጋዜጣ ላይ ለመፃፍ

ባይበቃም በአውቶቡስ ውስጥ የሚያጋጥሙ አፈንጋጭ

የወሲብ ጥቃቶች በርካቶች ናቸው። እንደውም

ገና የሴት ቀሚስ ሲነካቸው ደርሶ ወንድነታቸው

የሚገነፍል፣ በአይን ብቻ ሴትን ለመተኛት ጥረት

የሚያደርጉ ከዚያም አልፈው ተርፈው ‹‹በማንም

አያየኝም›› ድፍረት አስቀያሚ ድርጊት ሲፈፅሙ

በሆነ አጋጣሚ ለሰዎች እይታ ተጋልጠው ውርደት

የሚከናነቡ፣ ይህም ካልሆነ ጣጣቸውን ሰው ላይ

ለጥፈው እስከመሄድ የሚደርሱ ስንቶቹ ናቸው?

እነሆ ገጠመኝ።

‹‹በአንድ ወቅት በ46 ቁጥር ከገርጂ ወደ ካዛንቺስ

እየተጓዝኩ አንዱ ይተሻሸኛል። እናም እሸሻለሁ።

እርሱ እየተጠጋ ስሜቱን ለማርካት ይጣጣራል››

ትላለች ኤፍራታ አዲሱ የተባለች ወጣት። እንደ

ኤፍራታ ገለፃ ሰውየው ፍፁም ስሜት ውስጥ ስለነበር

ምንም ማስተዋል እንደተሳነው ታስታውሳች። ‹‹ነገሩ

ሲብስብኝ ለምን አታርፍም? የሚል ጥያቄ ሳነሳ

‹አርፈሽ ቁሚ ብዬሻለሁ› በማለት አንዴ በጥፊ

ሲያጮለኝ ጮህኩኝ›› የምትለው ኤፍራታ ሰዎች

ምንድነው ብለው መሀል ሲገቡ እሱ ኃፍረተ-

ስጋውን ከሱሪው ውጭ አድርጎት ነበር›› በማለት

በዕለቱ የደረሰባትን ውርደት አስታውሳ ትስቃለች።

በወቅቱ ሰዎች ባይገላግሉሽ ምን እርምጃ ትወስጂ

ነበር የሚል ጥያቄ አንስተንላት ‹‹ባገኘሁች አጋጣሚ

ከስሩ እንደችግኝ ነቅዬ ነበር በእጁ የምሰጠው››

በማለት ስቃ እኛንም አሳቀችን። በነገራችን ላይ በጣም

የሚያሳዝነው አንድ እናት የ7 ዓመት ሴት ልጃቸውን

አውቶቡስ ውስጥ ወንበር ላይ ለተቀመጠ ትልቅ ሰው

አደራ በማለት እናት ይቆማሉ። ከደቂቃዎች በኋላ

ኅጻኗ አውቶቡሱን በእሪታ ታቀልጠዋለች። ሰውየው

ጭናቸው ላይ አስቀምጠው ደፍረዋታል። ይሄውና

ተፈርዶባቸው ዘብጥያ ወርደው ይገኛሉ። እንዲህና

መሰል ሰቅጣጭ ክስተቶች በአንበሳ አውቶቡስ ውስጥ

ይካሄዳሉ።

አዎ በከተማ አውቶቡስ ውስጥ በርካታ ገመጠኞች

አሉ። አዝናኝም አሳዛኝም፣ አስነዋሪም፣ አስገራሚም።

እርሶ የትኛው አጋጣሚ ደርሶዎት ይሆን? ክፉው

ወይስ ደጉ? እንጃ ብቻ ከቀዶ ጠጋኞቹም ከቡድን

ሰራተኞቹም ከቀፋዮቹም ራስን መጠበቅና መጠንቀቁ

አይከፋም። መልካሙን አጋጣሚ መጠቀምም

ብልህነት ነውና አውቶቡስ ተጠቃሚዎች ሆይ ቸር

ይግጠማችሁ እንላለን።

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 191 ቅዳሜ ጥቅምት 18/ 2004

ማፊያ

በብስራት

ሚና፤ በማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ወይም

በዘመናችን የወንጀል መልክ

እየተለወጠ መጥቷል። ከዚህ

ቀደም ከነበሩ ታላላቅ የተለመዱ

ታዋቂ ማፊያዎች ጎን ለጎን

ሌላ አዲስ የተደራጀ ወንጀል

ብቅ ብሏል። ባለፉት ዓመታት

ጂኦፖለቲካዊ ውጥንቅጥ

ፖለቲካዊ ዘርፎች በተለይ በሕጋዊና ሕገ-ወጥ

ክበብ መሀከል ግልግል ሥራዎችን ለማከናወን

ማፊያዎች ጠቃሚ ሚና ይጫወታሉ። (4)

በክልላዊና ብሔራዊ ደረጃ ከፖለቲካዊ መደብ

(Political Elite) እና ከተቋማት ጋር ያላቸው

ቁርኝት፤ ማፊያ ባለው ትሥሥር ወይም

ግንኙት ምክንያት ወደ አንዳንድ ሕዝብ የኃብት

ምንጮች ወይም ገበያዎች ውስጥ ይገባል።

ውስጥ የተፈጠረውን ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት በዚህም መሰረት በአንዳንድ ሁኔታዎች በሕጋዊ

(Economic Globalization)፣ በዓለም አቀፍ ከለላ በመጠቀም በማኅበረሰቡ ላይ ካለው ተፅዕኖ

የፋይናንስ ዝውውር በመጠቀምና የንግድ አልፎ ለፖለቲካዊ መደቡ ድጋፉን ይለግሳል።

ልውውጥ ውስጥ ራሱን በመሰወር በሰዎች (5) በአንድ ክልል ሥር መሰደድ ወይም ጠንካራ

ከቦታ ቦታ መዘዋወር መፋጠንን በመታገዝ ይዞታ መያዝ፤ አንድ የማፊያ ቡድን በሀገር

እየበለፀገ ይገኛል - የወንጀል ዓለም።

ውስጥና ከሀገር ውጪ በሌሎች አካባቢዎች

እነዚህ አዳዲስ የመጡ ቡድኖች ዕንቅስቃሴ ቢያደርግም ቀድሞ የተመሰረተበትን

ራሳቸውን በፍጥነት በማሳደግና መዋቅራቸውን ቦታ አይለቅም። ሥር ይሰዳል። ለምሳሌ፡-

በመዘርጋት አንዳንዶቹ ቀድሞ በኢጣሊያ፣ ንድራጌታ (Ndrangheta) የተባለ ቡድን በሰሜናዊ

ጃፓን፣ ቻይና፣ ቱርክና በኢጣሎ-አሜሪካን ኢጣሊያ እና በውጭ ሀገራት ዕንቅስቃሴዎችን

በባህላዊ ልማዳቸው፣ በኢኮኖሚ አቅማቸውና ቢያደርግም፣ መጀመሪያ የተቋቋመበትን የካላብር

ከፖለቲካ ጋር ባላቸው ቁርኝት ‹‹ማፊያ›› (Calabre) ክልል ፈጽሞ አልለቀቀም። (6)

የሚለውን መጠሪያ ካገኙት የቀድሞ በድኖች አጠቃላይ የድርጅቱ ኃብት ምንጮች ሕጋዊና

ጋር አቻ የሆነ ሚና በተግባር እስከመጫወት ሕገ-ወጥ ዕንቅስቃሴዎችን አጣምሮ መያዝ፤

ደርሰዋል።

በዓለማችን የማፊያ ቡድንን ወንጀል ከሕግ

በፒራሚዳዊ ቅርጽ በመዋቀር አንጻር ለይተው ያስቀመጡ ሀገራት ከአንዲት

በተፈጠሩበት ሀገር (መጠሪያቸውን የሚያገኙት ሀገር በስተቀር እንደሌሉ ሊሰመርበት ይገባል።

ከዚህ ነው) በደንብ ራሳቸውን አቋቁመው ጣሊያን ካሳለፈችው ታሪካዊ ሁኔታ ይሁን በሌላ

የተወሰኑ የመንግሥት ባለሥልጣናትን በማሞሰን ምክንያት በማፊያ ማኅበር የሚፈፀም ወንጀል

በኢንቨስትመንት ላይ ይሳተፋሉ፤ ኢኮኖማውንም ምን ምን እንደሆነ ከሕግ አንጻር ባግባቡ ለይታ

ይቦጠቡጣሉ። እነዚህ አዳዲስ ቡድኖች የገለፀች ብቸኛ ሀገር ናት።

ዕድሜያቸው አጭር ቢሆንም አደረጃጀታቸው

እነዚህን የማፊያ ማኅብር ዋና

ግን በጣም የቆዩ ያስመስላቸዋል።

ዋና ባህርያት ከተረዳን በኋላ የማፊያ ቡድን

ማፊያ የሚፈጠርበትን ምክንያት ይህ መቼ እንደሚፈጠር እንይ። በአጥኚዎች ገለጻ

ነው ብሎ ለመግለፅ የሚያዳግት ቢሆንም፣ መሠረት ማፊያ የሚፈጠረው ሕዝባዊ ተቋማት

የመንግሥት መዳከም፣ ሥልጣን ርጉዕ በሆነ ፀጥታን ማስከበር ሲሳናቸው ነው። ማፊያ

ፖለቲካዊ ቡድን በምኖፓል ሲያዝ፣ በጎሳ ወይም ከሌሎች ዓይነት የወንጀል ድርጊቶች እና

ጎጠኝነት ላይ የተመሰረተ ማኅበራዊ አደረጃጀት ጥፋቶች ጋር ተጣምሮ ይሄዳል። በመቀጠልም

ወዘተ እንደምክንያት ይጠቀሳሉ።

እንደምንም ኃብት ያካብታል። ማፊያ አመቺ

አንዳንድ የቀድሞ ማፊያ ብዙም ባልሆነ ኢኮኖማያዊ ሁኔታ ውስጥ ሊያቆጠቁጥ

የማያውቃቸው የነበሩ ምዕራባውያን ሀገራት አይችልም። ለምሳሌ በሲሲሊ ውስጥ ኮዛ ኖስትራ

ዛሬ የእነዚህ ዓለም አቀፍ አዳኞች ሰለባ እየሆኑ (Cosa Nostra) የተባ ዕድሜ ጠገብ የማፊያ

ነው። ለምን? የዚህ መነሻው ሁለት ነው። አንድ፡ ቡድን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ላይ ብቅ

- እነዚህ ቡድኖች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየበዙ ያለው በፓሌርሞ አካባቢ የሚገኙ ሰፋፊ የፍራፍሬ

መምጣታቸው። ሁለት፡- ‹‹ኅቡዕ ካፒታሊዝም›› እርሻዎችን በመታከክ በግብርና ኢኮኖሚ ውስጥ

(Clandestine Capitalism) ኢንተርፐርነር ነው። በመጨሻም ማፊያ ከሕዝባዊ ተቋማት

የሆነው የተደራጀ ወንጀል በአዳዲስ ገበያዎች አካላት ጋር ትሥሥር መፍጠር ግድ ይለዋል።

ውስጥ ቋማ ሥፍራ ለማግኘት ስለሚፈልግ ነው። ይህም ሽርክና የሚፈጠረው ወይ እንደ 19ኛው

ለእነዚህ ገበያዎች ምርቶቹንና አገልግሎቶቹን ክ/ዘመን ሲሲሊ በሀገራዊ ሕገመንግሥት ውስጥ

ያቀርባል። ዕጾችን፣ ሴቶችንና የተለያዩ ወንጀል በሚኖር ክፍተት በመጠቀም አሊያም ደግሞ

ነክ ቴክኖሎጂዎችን ማለትም የማጭበርበሪያ ቅርብ ጊዜ ከ1989 እ.አ.አ በኋላ በቀድሞ ሶቭየት

ወይም ማስመሰያ ደረሰኞችን፣ ጭምብሎችን፣ ኅብረት ሪፑብሊክ እንደተከሰተው የአንድን ሀገር

የባንክ ካርዶችን ኮዶች ለማግኘት የሚረዱ ሚኒ መንኮታኮት ተከትሎ ነው።

ካሜራዎችን ወዘተ።

ማፊያ በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ

እስከቅርብ ጊዜ ድረሰ ለመንግሥታት ከቀድሞም የነበረ ሳይሆን በቅርብ ጊዜ በፖለቲካ

ያለመረጋት ምንጮች ተደርገው ይቆጠሩ መዘመን (Political Moderanity) ጋር የመጣ

የነበሩት ሽብርተኝነትና የኢኮኖሚ ድቀት ብቻ ነው። ዘመናዊ ኢኮኖሚ በተገነባበት ሁኔታ ውስጥ

ነበሩ። ዛሬ ዛሬ ግን በዓለም አቀፍ ትብብርና ዴሞክራሲ ሲከስም ወይም ሲቆረቁዝ ለማፊያ

ሕግጋት ክፍተት በመጠቀም ማፊያ ሌላው አመቺ ሁኔታ ይፈጠራል። የመጀመሪያው

ያልታወቀ ያለመረጋጋት መንስኤ እየሆነ ነው። የማፊያ ማኅበር የተፈጠረው በ19ኛው ከፍለ

ይህ ደግሞ በተለይ በክልላችን ዘመን በሲሲሊ ግዛት ነው።

በምሥራቅ አፍሪካ የራሱ መገለጫ አለው።

የማፊያ ቡድን በአንዳንድ ሀገራት ኖሮ

ያንን በዚህ ጽሑፍ በዝርዝር ለማየት በቂ በሌሎች ደግሞ የማይፈጠረው ለምንድነው?

ጥናትና ምርምር ይጠይቃል። ሆኖም ግን ለዚህ ዋናው ምክንያት የጠንካራ ማዕከላዊ

የማፊያ መለያ ባህርያትና ከዴሞክራሲ ዕጦት መንግሥት መኖር ሲሆን፣ ይህም በአንድ

ጋር ያለውን ቁርኝት ጠቅለል ባለ መልኩ ማየቱ መንግሥት ውስጥ የሌላ ኅቡዕ መንግሥት

ጠቃሚ ነው።

(ልክ እንደማፊያ) ሕገ መንግሥት ወይም ደንብ

ለመሆኑ ማፊያ ከሌሎች የወንጀል እንዳይኖር ስለሚከለክል ነው።

ድርጅቶች የሚለየው በምንድነው? በዘርፉ

አንድ የማፊያ ቡድን ቱባ አለቃዎቹ

አጥኚዎች ማብራሪያ መሠረት ማፊያ ስድስት ሲታሰሩበት ይህን ችግር ተቋቁሞ ለማለፍ

መገለጫ ባህርያት አሉት። እነሱም፡-(1) እንዴት ያደርጋል? የማፊያ ቡድን የራሱ

ድርጅታዊ አወቃቀሩ፤ የማፊያ ቡድን አባላት መዋቅር ያለውና በአንድ አካባቢ ሥር የሚሰድ

የጋራ ግዴታ ወይም ውል እና የተወሰነ ኃይል ነው። ዋና አለቃው ሲገደል በተለምዶ

ውስጠ ደንብ አላቸው። (2) ሁከት ወይም ወዲያው አንድ ግለሰብ በቦታው ይተካል። ሆኖም

የኃየል ድርጊት፤ የማፊያ ቡድን ሁከትን ግን ይህ ዕይታ በአግባቡ መመርመር አለበት

ወይም የኃይል ድርጊትን (Violence) አንዳንድ ይላል አንድ የማፊያን ጉዳይ የሚዳኙ ባለሙያ።

ጊዜ ወደ ባለፀጋነት መሰላል ለመውጣት እና አክለውም፣ “ማፊያ” ሰብዓዊ ክስተት ነው። ልክ

በማስፈራራት ድርጅቱን ለመጠበቅ ወይም ጅማሬ (መነሻ) እንዳለው ሁሉ መጨረሻም

ለመከላከል ይጠቀማል። (3) የማፊያ ማኅበራዊ ይኖረዋል” ይላሉ። ይህ አባባል ያለምክንያት

ባሕርያቱና ከዴሞክራሲ

እጦት ጋር ያለው ቁርኝት

የተሰነዘረ አይደለም። በጥሩ መሰረት ላይ

የቆመ የፀረ-ማፊያ ትግል ከተጠናከረ ማፊያ

የማይወገድበት ምክንያት የለምና።

ለመሆኑ የማፊያ ማኅብራት የተፅዕኖ

ክልላቸውን ለማስፋፋት በሉዓላዊነት /

Globalization/ ይጠቀማሉ? አዎ! ከኢኮኖሚያዊ

ዕይታ አንጻር ካፒታላቸውን ወደ ውጭ ሀገር

ይልካሉ፤ መዋዕለ-ንዋያቸውን ያፈሳሉ። ይህም

በሌላ ሀገር በጀት ሥር አመቺ መጠለያ

እንዲያገኙ ይረዳቸዋል። ከሌላ አንጻር ሲታይ

ደግሞ የኢጣሊያ ማፊያ ከ19ኛው መ/ክ/ዘመን

መጨረሻ ጀምሮ በሌሎች ሀገራት ማለትም

በቱኒዚያ፣ አሜሪካና በአውስትራሊያ እግሩን

ለመትከል ስደት (immigration) እንደ አማራጭ

ተጠቅሟል።

እንደማጠቃለያ፤ እነዚህን ሁኔታዎች

ከሀገራችንና ከአካባቢያችን ሁኔታዎች ጋር

አያይዘን መመርመር ያስፈልጋል። በሀገራችን

የገዢው ፓርቲ መሠረት፣ አያያዝና ባህርይ

እንዲሁም የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሁኔታ

እንዴት ነው? ሕዝባዊ ተቋሞቻችንስ ምን

ያህል ፅዱና ጠንካራ ናቸው? የጎረቤታችን

መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ቡድኖችስ

ምን ይመስላሉ? በእኛ ሀገር ተቋማትስ ላይ

ምን ዓይነት ተፅዕኖ ያሳድራሉ?

ከውጭ ሀገር መጥተው መዋዕለ-ንዋያቸውን

የሚያፈሱ ባለኃብቶች ምን ዓይነት ናቸው?

የጀርባ ታሪካቸውን በሚገባ እናውቃለን? ሀገር

ውስጥ ከገቡስ በኋላ ባህሪያቸው እንዴት ነው?

ከሀገራዊ ተቋማት ጋር ያላቸው መስተጋብር

ምን ይመስላል? ሕግ አክባሪ ናቸው? አቋራጭ

መንገድ ይመርጣሉ? ለምን? የእኛስ ዜጎች

ራሳቸው ንብረት ለማፍራት በምን ዓይነት

መንገድ ይሄዳሉ?

በሕጎቻችንና በተለይ

በሕገመንግሥታችን ውስጥ ራሱ ክፍተት አለ

ወይስ የለም? ለምን? ግለሰቦች የሚደርስባቸውን

ችግር ወይም በደል በአግባቡ ለባለሥልጣናት

ወይም ሕግ ፊት ያቀርባሉ? ፍትህስ ያገኛሉ?

ሃሳባቸውን ለመግለጽ በቂ አማራጮች

አሏዋቸው? ለምን ሁነኛ ሀገራዊ ውይይት

ማድረግ ይሳነናል? ለምን በዕርጋታና በሰላም

ግልፅ ውይይት ማድረግ አልቻልንም? ብዙ

ጊዜ የምንለዋወጣቸው ቃላት (በማሕበራዊ

ኑሮ ውስጥ ባልና ሚስት ጎረቤት ለጎረቤት፣

ዐለቃና ምንዝር፣ አግልግሎት ሰጪና ደንበኛ

ወዘተ) በተለይ በኢህአዴግ ዘመን ከችግር

የፀዱ ናቸው? ምንስ ያንፀባርቃሉ? እነዚህንና

የመሳሰሉትን ሁኔታዎች በአግባቡ ማጤን ተገቢ

ነው። ይህንንም ስናጤንና የሚያስፈልጉትን

ማስተካከያዎች ስንከውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ

በአንድ ወቅት ያሉትን - ዛሬ ረስተውት እንደሆነ

አይታወቅም - ‹‹የተሻለ ኅብረተሰብ የመገንባት

ጥማት›› እውን ማድረግ እንችላለን። እንደ’ኔ

እመነት ይህ ደግሞ የሚጀምረው ከአለት

መሰረታዊ ተቋማት ነው - ከቤተሰብ፣ ትምህርት

ቤት እና ከዕምነት ተቋማት።

በገበያ ላይ ውሏል

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

9

ሰላም ለኢትዮጵያ፣

ሰላም ለአፍሪካ!

10

እንደመንደርደሪያ

በሶላር ፊልም ፕሮዳክሽን ተዘጋጅቶ

የቀረበ ፊልም ነው። ዘወትር ማክሰኞ

በ8፣ በ10 እና በ12 ሰዓት በሲኒማ

አምፒር በመታየት ላይ ይገኛል።

የዚህ ፅሑፍ ዳሰሳ አቅራቢ ባለፈው ማክሰኞ

ጥቅምት 14 ቀን 2004 ዓ.ም አመሻሽ 12

ሠዓት በቦታው ታድሞ ነበር። ጥቂት ሰዎች

ወደ አዳራሹ ለመግባት ሰልፍ ይዘዋል።

በፈረንጅኛው ‹‹security›› የሚል ቃል

የተፃፈበት ባለ ሎሚ ከለር የለበሰ ጎረምሳ

ወጣት ሴቶችን እየለየ ከሰልፈኛው ቀድመው

እንዲገቡ ያዛል። ይኼኔ ፊልሙ ‹‹ለማየት

ሳይሆን ለመታየት ለወጡ ወጣት ሴቶች ብቻ

ነው እንዴ የተዘጋጀው?›› ስል ራሴን ጠየቅሁ።

እየገረመኝ የመጨረሻው ታዳሚ ሆኜ ገባሁ።

12 ሰዓት ከ10 ደቂቃ ሆኗል። በሲኒማ

አምፒር ታችኛው አዳራሽ በጣት የሚቆጠሩ

ሰዎች አልፎ አልፎ ተቀምጠዋል። 12 ሰዓት

ከ25 ደቂቃ ተጨማሪ ተመልካች አልገባም።

‹‹ሳታማኻኝ ብላ›› የሚለው ሙዚቃ በአዳራሹ

ውስጥ ይናኛል። ነገሩ እየገረመኝ ታችኛው

አዳራሽ ውስጥ ያለውን ሰው መቁጠ ጀመርኩ።

ከእኔ ጋር 45 ሰው ብቻ ታድሟል። ወዲያው

የአዳራሹ መብራት ጨለመ። ፊቴን ወደ ነጩ

መጋረጃ መለስኩ። ላይኛው መመልከቻ ስፍራ

ስንት ሰው ሊኖር እንደሚችል ለመገመት

እየሞከርኩ ‹‹አልሞትም›› የሚል ርዕስ በነጩ

መጋረጃ ላይ ሲነጠፍ አየሁ። እንዴት ነው

ነገሩ? ሲኒማ አምፒር መግቢያ በር ላይ

በረዥሙ የተሰቀለው የፊልሙ ማስታወቂያ

ላይ ያነበብኩት ‹‹ለአንተ ስል አልሞትም››

የሚል ርዕስ ነው። የርዕሱ ርዝማኔ የሰዎችን

የማየት ፍላጐት የሚያነሳሳ አይደለም እያልኩ

ነበር፡- ለራሴ። የፊልሙ ጅማሬ ላይ የተገለፀልኝ

ርዕስ ግን ‹‹አልሞትም›› ብቻ ነው፡፡ ምክንያቱ

ምንድነው? … ቢሆንም ፊልሙን በትኩረት

መከታተል ቀጠልኩ።

የፊልሙ ጭብጥ

ወደ ሲኒማ አምፒር ለሚገቡ ተመልካቾች

በሚበተነው የፊልሙ ማስታወቂያ በራሪ

ወረቀት ላይ የፊልሙ ዋነኛ ጭብጥ ‹‹ልብ

ለሚነካ ህፃን ልጅ የተከፈለ መስዋዕትነት››

መሆኑ ተገልጿል። ይሁን እንጂ የፊልሙ

ዋነኛ ጭብጥ ከላይ የተገለፀው ነው ብሎ

ለመቀበል ይቸግራል። የህፃኑ ልጅ ጉዳይ

በንዑስ ጭብጥነት ሊገለፅ ይችል ይሆናል።

የሆኖ ሆኖ እኔን እንደገባኝ የፊልሙ ዋንኛ

ጭብጥ ወይም ማጠንጠኛ ነገረ ጉዳይ ወንጀል

ነው። የተደራጀ ወንጀል። እንደው ከአጭርም

በአጭሩ ጠቅለል አድርገን እንግለፀው ካልን

‹‹ማፍያ›› ተብለው የሚታወቁት ወንጀለኞች

ታሪክ ነው ብንል ፊልሙን የበለጠ

ይገልፀዋል።

ለዚህ አባባል መጠነኛ አብነት መጥቀስ

ይቻላል። የፊልም ጥበብ ባለሙያዎች

እንደሚሉት፤ የአንድ ፊልም ሁለንተናዊ

ታሪክ ጭብጥ በሶስት ደቂቃ ውስጥ ተመልካች

እንዲረዳው ማድረግ ያስፈልጋል። ከዚህ

አንፃር ‹‹አልሞትም/ለአንተ ስል አልሞትም››

የተዋጣለት መሆኑን አለመመስከር ንፉግነት

ነው።

ምነው ቢሉ ፊልሙ በታሪኩ ጅማሮ በ1994

ዓ.ም ጅማ ላይ የተፈፀመን የተደራጀ

ወንጀል፣ ከጦርነት ባልተናነሰ ቅልጥ ያለ

ተኩስ ያሳየናል። በቅፅበት እዚያው ጅማ

ውስጥ በ2000ዓ.ም የተፈፀመን ወንጀል

ያስቃኘናል። ከዚያም ግንቦት 2 ቀን 1992

ዓ.ም ወደተፈፀመ ድርጊት ይመልሰናል።

ወዘተ… ከ3 ደቂቃ ባለበለጠ ጊዜ በድርጊት

የታጀበ ሁነት በመመስረት ረገድ ብቃት አለው

የምለው ለዚህ ነው። የታሪኩ ዋነኛ ጭብጥም

ይኸው የተደራጀ ወንጀል መሆኑን የተጠቀሰው

ክፍል በቂ ማሳያ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ፊልሙ

በርካታ ግድፈቶችንም ያስተናገደ ነው። ወደ

ግድፈቶቹ ከመሄዳችን በፊት ግን መልካም

ጐኖችን ማበረታታት ያስፈልጋል።

በዚህ ፊልም ውስጥ ሰለሞን ገብሬ፣ አድያም

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ዓለም፣ ታጠቅ መለሥ፣ ፍሬህይወት

ስዩም፣ ኤደን ሽመልስ፣ ቅዱስ አሰፋ፣

ቢላል እንድሪስ፣ ሰለሞን ነጋሽና ሌሎችም

በተዋንያንነት (Actors) ተሳትፈዋል። ሁሉም

ተዋንያን ማለት ይቻላል፣ በተሰጣቸው ገፀ

ባህሪያት መጠን (የተሰጣቸው ገፀ-ባህሪይ

- ከኢትዮጵያውያን የህይወት ዕውነታ ጋር

የተስማማ ባይሆንም) ኃላፊነታቸውን በሚገባ

ተወጥተዋል። ችሎታቸውንም አሳይተዋል

ማለት ያስደፍራል። በተለይ የህፃኑን ገፀ

ባህሪይ ወርሶ የተጫወተው ታዳጊ ድንቅ ትወና

ማሳየቱን መካድ አይቻልም።

ይህም ብቻ አይደለም። ‹‹ለአንተ ስል

አልሞትም›› ፊልምን የደረሰው ሰለሞን ገብሬ

መሆኑ ከላይ ተጠቅሷል። ነገር ግን ድርሰቱን

ወደ ስክሪፕት ፅሁፍ የለወጡት ብዙአየሁ

እሸቱ እና አንዱዓለም ጌታቸው ናቸው።

ድርሰቱን ወደ ፊልም ፅሁፍነት የቀየሩበት

ስልት ሊደነቅ የሚገባው ነው። ምክንያቱም

ለእያንዳንዱ ገፀ-ባህሪያት በቃለ ተውኔትነት

የተጠቀሙበት አጠርና ቅልብጭ ያለ የቋንቋ

አጠቃቀም ለፊልሙ የተሟላ ህይወት መልካም

ድርሻ ማበርከቱ ይስተዋላል። እንዲያም ሆኖ

ፊልሙ በበርካታ ችግሮች የተዋጠ ነው፡፡

ችግሩ

ፊልሙ ከአገራዊ ፊልም ጥበብ አንፃር

ይመዘን ከተባለ ይህ ነው የሚባል ፋይዳ

ቄሱም ዝም

መጽሀፉም ዝም

ሰውም ዝም

ኑሮውም ዝም

ሁሉም ዝም

ከመዝ …ውአቱ።

ሰላም ለኩልክሙ /ሰላም ለሁላችሁም/ መወድስ

ባናቱ ከነምልዓተ ንባቡ ጋብዣችኋለሁ።

መወድስ

ፀላዕኩ ሰብዐ እምነ-ርዕስየ ዘትርጓሜሁ በቀል

ወዘንባቡ ሀሰት፤

እስመ እምልሳኑ ለሰብዕ አንተ ይበልኦመሬት፤

ለፌትህትና ወለፌ ትዕቢት፤

ይወጽኡ ለስብከት እንዘ በላዕሌሁ ይሔሉ እንተ

ኢይተርፍ ሞት፤

ለዓለም ወለዐለም

ልብየሂ ለዕመጌሠ መንገለ-ሀተታ ገነት፤

ባቲ ዘተጋበዐ ጥበባተ-ሰሎሞን ጽጌያት፤

እሩያነኮኑ በሰምናዊት ሰዐት.

ሰብዕ በዐመፃወእግዚአብሔር በምህረት፤

ትርጉም

ከራሴ ጀምሮ ሰውን ጠላሁ። ከሰው አንደበት

የሚወጣው ነገር

በሙሉ ትርጓሜው በቀል ነው ንባቡም ውሸት

ነው።

በዚህ ውሸት በዛኛው እውነት (ባንድ አፍ ሁለት

ምላስ) ይዘው፣

ለማስተማር ይወጣሉ የማይቀረው ሞት እያለ።

እኔም በተመስጦ የሰለሞን ጥበባት ወደ ተከማቹባት

የገነት ጓሮ ላይ ሆኜ ስመለከት የሰው ልጅና

እግዚብሔር በስምንተኛው ሺህ አንድ ሆኑ

የሰው ልጅ ያጠፋል

እግዚአብሔር ይምራል

(ኤዲያ)

አዱኛው ላይሞላ

ይወደስክ ብላ

በተለምዶ በዘፈኑና በሥነጽሁፉ ባቲ የቆንጆ መዲና

ስትባል እንሰማለን። ስለባቲም ያልተዘፈነ ዘፈን

የለም ብዬ ብናገርም ማጋነን አይሆንብኝም።

ከአራቱ ቅኝቶች መካከልም የባቲ ቅኝት አንዱ

ነው።

1. ትዝታ

2. አምባሰል

3. አንቺ ሆዬ

4. ባቲ

ይህን የምታነቡ በሙሉ ‹‹ባቲ›› ብዬ ስጀመር አገሩን

ነው ወይስ ቅኝቱን? ብላችሁ አስባችሁ ይሆናል።

ያወቃችሁ ደግሞ አውቀችኋል። ባቲ ማለት የግዕዝ

ግስ ሲሆን ትርጉሙም ‘አላት’ ማለት ነው።

ቦ፡- አለ ፤

ቦቱ፡- አለው፤

ባ፡- አላት፤

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 191 ቅዳሜ ጥቅምት 18/ 2004

አለው ማለት አይቻልም። ምነው ቢሉ

የኢትዮጵያውያንን ህይወት፣ የአኗኗር ዘይቤ፣

እምነት፣ አስተሳሰብና ማንነትን የሚያንፀባርቅ

አይደለም። ማንነቱን የማያንፀባርቅ የጥበብ

ስራ ደግሞ የሞተ ነው። ከባህር እንደወጣ አሳ፣

ህይወት አልባ ነው የሚሆነው። የጥበብ ሰው

ደግሞ ያልኖረበትን ዓለም መጠበብ አይችልም።

ባልኖሩበት አለም ልጠበብ ማለት (ጥበበኛ ነኝ)

ማለት ከመቃዠት ተለይቶ አይታይም።

ባቲ፡- አላት፤

የዶሮ እርባታ የማርባቱ አቅም

ባይኖረኝም ባቲ በሚለው የግዕዝ ቃል

እርባታውን አረባላችኋለሁ።

አጽምኡኒ

ስሙኝ

አጽምኡኒ

ስሙኝ

አዱኛው ላይሞላ

እያወደስክ ብላ

ባ…ባተ ለዛቲ ብእሲት እንትን

ለዚያች ሴቲዮ እንትን አላት

አለላት

አለባት

ኖራት ኖረላት ኖረባት

ነበራት ነበረላት ነበረባት

ይኖራታል ይኖርላታል

ይኖርባታል

ይኑራት ይኑርላት ይኑርባት

“ምንድነው ያላት?”

አይ ምንም ነገር የላትም። ዝም ብዬ ግስ

እያረባሁ ነው።

“ሰው ዶሮ ያረባል አንተ ግስ ታረባለህ?

አይደል?”

ተይዟል።

“ምኑ?”

ዶሮው።

“ከብቱስ፣ በጉስ፣ አሳማውስ?”

ዝኒከማሁ (ይህም እንደዚያኛው

ነው) ተይዟል።

p Ç T@

ማፍያዎቹ ፊልመኞች በ‹‹ለአንተ ስል አልሞትም››

የፊልሙ ርዕስ፡- ‹‹ለአንተ ስል አልሞትም››

የፊልሙ ደራሲ፡- ሰለሞን ገብሬ

የፊልሙ ዘውግ፡- አክሽን

የፊልሙ ዳይሬክተር፡- ታጠቅ መለሰ

ፊልሙ የሚፈጀው ጊዜ፡- 1፡40 ሰዓት

በንፍታሌም

በከመ-ይቤ ቅዱስ ኤፍሬም ባለቅኔ

የገዘፈው የፊልሙ ደካማ ጐን

‹‹ለአንተ ስል አልሞትም›› የተሰኘው ይህ

ፊልም ግዙፍ ደካማ ጐን የታሪኩ መዋቅርና

ሁለንተናዊ ይዘት የኢትዮጵያዊያንን ህይወት

የማይወክል መሆኑ ነው ብዬ አምናለሁ።

ምክንያቱም የ‹‹ማፍያ››ዎችን የተደራጀ ወንጀል

ነው የሚያሳየው። በአጠቃላይ የፊልሙ ይዘት

ፊልም ሰሪዎቻችን ‹‹ማፍያዎች›› መሆናቸውን

በገሃድ ያሳዩበት ነው ብል ማጋነን አይሆንም።

አንድ፣ ፊልሙ እንደጣሊያን ሲሲሊያኖች

ማፍያዎች የረቀቀና የተደራጀ ወንጀል መፈፀምና

በዘረፉት ብር ወይም ወርቅ የተነሳ- ግጭት

ውስጥ መግባት ላይ ያጠነጠነ ነው። ፊልሙ

እርስ በእርስ መታኮስ፣ መጠዛጠዝ፣ እርስ በርስ

መሸዋወድ ወዘተ ነው። ፊልሙ በረቀቀ ስልት

ወንጀለኞቹ እርስ በርስ ሲቀጣቀጡና ሲናረቱ..

ወዘተ የሚያሳይ ነው። ከጅማ እስከ አዲስ

አበባ በተዘረጋ የወንጀል መረብ፤ ሰዋራ ቦታ

ላይ፣ ጅምር ህንፃ ስር… ወዘተ መቀጣቀጥና

መታኮስ፣ እንደገና መቀጣቀጥና መታኮስ ብቻ

ነው የሚያሳየው፡፡ መርማሪ ፖሊስን ቤቱ ድረስ

ሄዶ አንገቱን መቀንጠስም ያካትታል። ብላ!

ብላ! ብላ!

ሌሎች ሁኔታዎችን እንጥቀስ ካልን የፊልሙን

ሙሉ ታሪክ መነስነስ ሊሆንብን ነውና

ባቲ

ተውነው። የሆኖ ሆኖ ግን ፊልሙ ከውጭ

አገር የማፍያ ፊልሞች ሙሉ በሙሉ የተኮረጀ

ወይም የተገለበጠ መሆኑን ለመረዳት ነብይ

መሆን አያስፈልግም።

ችግሩ የፊልሙ ታሪክ ወንጀል ላይ

መመስረቱ አይደለም። እንዲህ አይነቱ

በቡድን የተከፈለና ከጦርነት ያልተናነሰ ተኩስ

የሚተኮስበት ለመንግስትም ፈታኝ የሆነ

የወንጀል ተግባር ላይ አገራችን የደረሰች

አይመስለኝም። አልደረሰችምም፡፡ የፈረንጆቹን

ሴራ (በቋንቋ) ለውጥ ብቻ የእኛ አገር

ታሪክ አስመስሎ ማቅረብ ደግሞ ይቅር የማ

ይባል ሃጢያት ነው።

ኩረጃ እና ኮራጅ

ኩረጃ በየትኛውም ዘርፍ የሚነቀፍ አይደለም፡

፡ የኮራጅ ተግባር ነው ኩረጃን ፍፁም ወንጀል

የሚያደርገው። ሁሉንም ነገር ከራስ ፀጉሩ እስከ

እግር ጥፍሩ መኮረጅ ጤንነት አይደለም።

በአንድ ወቅት አንድ አባት ያሉኝ ነገር እዚህች

ላይ ትዝ አለችኝ ‹‹መስረቅ ፍፁም ወንጀል

የሚሆነው፣ ሁሉንም ነገር አግበስብሶ ለመውሰድ

ሲሞከር ነው። የዝርፊያ ጥሩ ባይኖረውም

ከማግበስበስ ይልቅ እንጥፍጣፊውን መውሰድ

ነው የሚሻለው›› ነበር ያሉኝ። የእኛ አገር

የፊልም ጥበብ እንደማፍያዎቹ ሙሉ በሙሉ

የመገልበጥ ያህል መሆኑ ነው የሚያሳዝነው።

ይህም ፊልም ሆኖ፣ ይህም ፊልም ተብሎ፣

ወጣት ሴቶች የፊልም ተመልካቹን ክብር

እየጣሱ ቀድመው ወደ ባዶው አዳራሽ እንዲገቡ

በማድረግ አድልዎ ለመፈፀም መሞከሩ ነው

የሚያሳዝነው፡፡ ሌላው ሌላው ቢዘረዘርማ ችግሩ

የትየለሌ ነው፡፡

(አላት፣ አለላት)

“አይ … ሁሉም ከተያዘ ለምን ሰው

አታረባም?”

የሚረባ ሰው የለም።

“እንዴት?” (መሬት ዐንተ ወትገብዕ

ውስተመሬት)

አፈር ነህና ወደአፈር ትመለሳለህ ስለሚል።

ፍሬ ከርስኪ ነው። ሁሉም ከወሬ የዘለለ ነገር የለውም።

እና … ሁሉም ሰው አይረባም እያልክ ነው?

አዎ ከራሴ ጀምሮ አይረባም።

“አንተስ? ረብተሀል?”

በግሱ ረብቻለሁ፤ በገንዘቡ ግን አረባሁም።

“እስኪ አንድ ነገር ልጠይቅህ፤ አንድ ሰው ይረባል ለማለት

ምን ያስፈልገዋል?”

ያው ገንዘብ ነው። ገንዘብ ካለህ ትረባለህ። ገንዘብ ከሌለህ

ደግሞ አትረባም። አለም ወዳላቸው እንጂ ወደሌላቸው ፊቷን

አታዞርም።

“ገንዘብ ሥትለኝ ያልገባኝ ነገር አለ። ገንዘብ ማለት በእጅ

የሚቆጠረው ወረቀት ማለት ነው?”

እንዴታ! እሱንማ ካልያዝክ ማን እጅ ይነሳሀል? ማንስ

ያከብርሀል? ኧረ ተወኝ ሁሉም ሰው ከቁብም አይቆጥርህ።

“እንዴ ምንድነው የምትለው? የሰው ልጀ ከብር አይበልጥም

እንዴ?”

መብለጥ እንኳን ይበልጣል። የሰው ልጅ ተገዢ ሲሆን ብር

ደግሞ ገዢ ነው። አንድ ብር ላይ ገዢ የሚል ቃል አይተህ

አታውቅም?

“ገዢማ የፈጠረን አምላክ ነው። እንዴት ብር ገዢ

ይሆናል?”

ኤዲያ . . . አምላክንም ገዝቶታል።

“እንዴት አርጎ?”

ለጌታም ጌታ አለው

ገንዘብ ጌታ ሆኖ ጌታን አንገላታው

እና ገንዘብ ይሉሀል ይሄ ነው። ሰላሣ ዲናር ባይኖር አምላክ

ባልተሸጠ፤ ሻጭና ገዢም ባልኖረ። ለዚህ እኮ ነው ባሪያ

ለሁለት ጌቶች መገዛት ይቻለዋልን? ተብሎ ይተፃፈው።

ከር … ከር … ከር ብሎ ሲስቅ፣

ተው አትሳቅ

ለምን?

ሳይኖርህ መሳቅ

ይሆንብሀል መሳቀቅ

አዱኛው ላይሞላ

እያወደስክ ብላ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 191 ቅዳሜ ጥቅምት 18/ 2004

S ´ “ —

መዝናኛ ዜና

ብሌን ፊልም ነገ

ይመረቃል

በኢዮብ ተስፋዬ ተደርሶ በአንተነህ

ሞትባይኖር የተዘጋጀውና ፕሮዲዩስ የተደረገው

ብሌን ፈልም ነገ እና ከነገ ወዲያ በአዲስ አበባና

በክልል ከተሞች በሚገኙ በርካታ ሲኒማ ቤቶች

ይመረቃል። 1፡40 ሰዓት ርዝማኔ ያለውና የፍቅር

ታሪክ ላይ የሚያጠነጥነው ብሌን ፊልም ተሰርቶ

ለመጠናቀቅ 11 ወራትን ወስዷል። በፊልሙ ላይ

ሰላማዊት ብርሀኑ፣ ኢዮብ ተስፋዬ፣ ትዕግስት

ይልማ፣ አንተነህ ሞት ባይኖር፣ ወይሰው አንተነህ፣

አብነት ዳግምና ሌሎችም ተሳትፈውበታል።

እጃቢ ሙዚቃው በአክሊሉ ተዋበ

የተቀናበረውና አማን ተስፋዬና ዮዲት ወርቁ

በድምፅ የተሳተፉት ብሌን ፊልም በአንዲት ወጣት

ዙሪያ የሚደረግ የፍቅርና የጥቅም መስዋዕትነትን

የሚያሳይ ሲሆን ወጣቷ ቤተሰቦቿንና የአይን

ብርሀኗን በአደጋ በማጣቷ የሚያፈቅራት ወጣት

በአስገራሚ ሁኔታ በሚያደርግላት እንክብካቤና

በአክስቷ ልጅና በፍቅር ጓደኛዋ በሚደርስባት በደል

ላይ የሚያጠነጥን እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

በሲ.ኤል.ዲ ፊልም ፕሮዳክሽን የቀረበው

ብሌን ፊልም በዋናነት በአዲስ አበባ ስብሰባ ማዕከል

ከቀኑ በ10 ሰዓት በድምቀት እንደሚመረቅም

ለማወቅ ችለናል።

ምራኤል የስኬት

ት/ቤት በአመለካከት

ለውጥና በስኬት ዙሪያ

ውይይት ያካሂዳል

ምራኤል ኢንተርናሽናል የስኬት ት/ቤት

በአመለካከት ለውጥና በስኬት ዙሪያ በአገር አቀፍና

በግለሰብ ደረጃ እንዴት መተግበር እንደሚቻል

የሚያመላክት ውይይት ዛሬ ረፋዱ ላይ በብሔራዊ

ቴአትር ያካሂዳል። እንደ ድርጅቱ መግለጫ ት/

ቤቱ እስካሁን በግለሰብም ሆነ በአገር አቀፍ ደረጃ

ህብረሰቡ የተዛባን አመለካከት በመለወጥ እንዴት

ወደ ስኬት መድረስ እንደሚችል በማሰልጠንና

በርካታ ስልቶችን በማመላከት እየሰራ መሆኑን

ገልጾ፤ በዛሬው ዕለትም በሚያካሂደው ውይይት ላይ

በዘርፉ ውጤት የሚመጣበትን መንገድ ይፈጥራል

ተብሎ ይጠበቃል።

ምራኤል ኢንተርናሽናል በነገው እለት

ከውይይቱ በተጨማሪ እስከዛሬ ያከናወናቸውን

ፍሬያማ ተግባራት መግለፅ፣ በቅርቡ ሚያስገነባውን

የህንፃ ዲዛይን ማስመረቅ፣ በምራኤል ሰልጥነው

ለውጤት የበቁ ምስክሮችን መስማት፣ የማያቋርጥ

ደስታን መፍጠር የሚያስችሉ 10 ሚስጥሮችን

ማሳወቂያ ስልጠና መስጠት፣ በኢትዮጵያ ላይ

በአስተሳሰብ እና በስራ ፈጠራ ላይ ሰፊ ስራ የሰሩ

ግለቦችን መሸለምና የምራኤል ምርጥ ውጤታማ

ተማሪዎችን መሸለም ከፕሮግራሙ ውስጥ

ተካተዋል። በእለቱ ይህን ውይይት ፍላጎት ያላቸው

እንዲካፈሉበት ምራኤል የጋበዘ ሲሆን በእለቱ ታዋቂ

ሰዎች ጋዜጠኞችና ጥሪ የተደገላቸው የመንግስት

ኃላፊዎችና የምራኤል ት/ቤት ማህበረሰብ በውይይቱ

ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በሬዲዮ ድምፅሽን የሚሰሙ በአካል ሲያገኙሽ

ምን ይሉሻል?

በጣም ነው የሚደነግጡት። ቢሮ

መጥተው እንግዳ መቀበያ ላይ ለተለያየ የስራ

ጉዳይ ስንቀሳቀስ ‹‹ቲጂ የለችም›› ብለው

ይጠይቁኛል። ‹‹እኔ ነኝ›› ስላቸው በፍፁም

አያምኑኝም። የሚያስቡኝ ትልቅ ሴት አድርገው

ነው። እንደምታየኝ ትልቅ ሴት አይደለሁም

አይደል? [ሳቅ] ለሙያው ትንሽ ፈጠን ብያለሁ

መሰለኝ።

አርባ ስንት ዓመትሽ ነው?

[ሳቅ] 27 ዓመቴ ነው።

ህይወትን በስነ-ልቦና አረዳድ እንዴት ታያታለሽ?

እኔ ህይወትን በስነ ልቦና መነፅር

ስመለከታት ይመስለኛል ጥያቄህ…

ትክክል!

ከራሴ እይታ ብናገር ደስ ይለኛል።

እዚህ ህይወት ውስጥ ከገባሁ ጀምሮ የተረዳሁት

ነገር የማትጠብቀውን ነገር ጠብቅ (Expect the

Unexpected) የሚለውን መርህ ነው። በስራ

ላይ እንደ ባህላችሁን ቡና ስንጠጣ ከምንሰማቸው

ወሬዎች በጣም የዘለሉ ጉዳዮች ይመጣሉ። ስለዚህ

ሁሌም ጠዋት ስነሳ የማይጠበቅ፣ ከአቅሜም

በላይ የሆነ ነገር ሊመጣ እንደሚችል ከሙያው

ተረድቻለሁ።

ከአቅምሽ በላይ [በአንቺ የምክር አገልግሎት

ሊያገግሙ የማይችሉ የምትያቸውን] የሆኑ

ችግሮችን ያዘሉ ደንበኞች ሲመጡ ምን

ታደርጊያለሽ?

የስነ-አዕምሮ ሐኪም (ሳይካትሪስት)

የሚያያቸውን ወይም መድኃኒት መጠቀም የደረሱ

ደንበኞችን አንመለከትም። የምንሰራው ከመድኃኒት

ወዲህ ያሉ ሰዎች በቀን ተቀን ኑሯቸው ላይ

የሚያጋጥማቸው ችግሮች ላይ መፍትሄ የማምጣት

ስራ ነው።

ስራው እንዲህ ዘና ብዬ እንደማወራህ

ቀላል አይደለም። በስነ-ልቦና ዓለም የገባኝ ትልቁ

ምስጢር ችግሩ ከባድም ቢሆን ራስን እዚያ ሰው

ጫማ ውስጥ አድርጎ መመልከትን ነው። እኔጋ

ዓለማዊ ወግ

በውሂብ

1

ከያዘ የማይለቅ ሞኝ እና ወረቀት ነው

ይባላል። ከዚሀ በኋላ ግን የኔታም ቢጨመሩበት ደስ

ይለኛል። እና እንዲህ ይባል፡- ከያዘ የማይለቅ የኔታና

ወረቀት ናቸው። አሰለቹኝ። ልንማርበት ከነበረው ዛፍ

ሥር ተነስቸ ወጣሁ።

የግብጽ ጳጳሳትን ሰምተው በዓላትን

ያወጁ ካህናት ትሩፋት የሆኑ ትላልቅ ዛፎች

ቤተክርስቲያኑን ወረውታል። በዓላት ባይኖሩ ኖሮ፣

እንደ ኢትዮጵያውያን ደን የማውደም ፍቅር ይሄኔ

አንድም ዛፍ ባልተገኘ ነበር።

አፍታ

በፋና ኤፍ ኤም 98.1 በሚተላለፉ አዲስ መንገድ እና የእርቅ ማዕድ

በተሰኙ የስነ-ልብዎና ፕሮግራሞች ላይ በምታቀርባቸው ስነ ልቦናዊ

ትንታኔዎች በርካታ አድናቂዎች አሏት። የአስተሳሰብ እና የአዕምሮ

ሂደቶችን ስለሚያጠናው የሳይንስ ዘርፍ (Psychology) እና ስለ ሌሎች

ነጥቦች ‹‹ቲጂ›› አንዳፍታ ቆይታ አድርጋለች፤ ከአቤል ዓለማየሁ ጋር።

‹‹የቤት እንስሳት

ያስባሉ ብዬ አምናለሁ››

ትዕግስት ዋልተ ንጉስ [የስነ-ልቦና ባለሙያ]

በስነ-ልቦና ዓለም የገባኝ ትልቁ

ምስጢር ችግሩ ከባድም ቢሆን ራስን

እዚያ ሰው ጫማ ውስጥ አድርጎ

መመልከትን ነው። እኔጋ የሚመጡ

ሰዎች ‹‹ተበድያለሁ›› ብቻ ሳይሆን

‹‹በድያለሁም›› የሚሉ ናቸው።

ሚስቱን የጎዳ፣ ልጆቹን ያስራበ፣

ወዳጁን በጣም ያስከፋ፣ ገንዘብ

የቀማ ይመጣል።

የሚመጡ ሰዎች ‹‹ተበድያለሁ›› ብቻ ሳይሆን

‹‹በድያለሁም›› የሚሉ ናቸው። ሚስቱን የጎዳ፣

ልጆቹን ያስራበ፣ ወዳጁን በጣም ያስከፋ፣ ገንዘብ

የቀማ ይመጣል። ከውጪ ሆነህ ከተመለከትከው

ርህራሄ የጎደለው ስራ ስለሰራ ሰውዬው ራሱ

ያናድድሀል።

በአዕምሯችን የሚመጡ በጎ እና መጥፎ ሀሳቦች

(Positive & Negative Thoughts) መነሻ ምን

እንደሆነ ልትነግሪኝ ትችያለሽ?

እንደየሰዉ ይለያያል። ይጠቅምህ

እንደሆነ ባላውቅም አንድ መሰረተ ሀሳብ አለ፤

ከቤተክርስቲያኑ ፈንጠር ብሎ ከምጣድ

እንደተፈናጠረ ፈንድሻ ብትንትን ያሉ ጎጆዎች አሉ።

እኒህን ቤቶች ሳይ አንድ ነገር ይታሰበኛል። መቼም

ሀገራችን ብዙ ሥልጣኔዎችን በማምጣት ግንባር

ቀደም እንደሆነች የታወቀ ነው። የዘመናዊ አፓርታማ

እሳቤንም ያመጣችው ሀገራችን ናት። ለዚህም ማሳያው

እኒህ ጎጆዎች እንደሆኑ ይሰማኛል። ብናስጎበኛቸው

ሊያዋጣን ይችላል እያልኩ አስባለሁ።

ሌላ ማረፊያ

ዲያቆን አስማማው ጓደኛዬ ነው። አብረን

እንማራለን። እሱ ግን እየዞሩ ቁራሽ እንደመለመን

ስሜት የሚሰጠው ነገር የለም። ተማር ከሚሉት

ጎጃምን እያካለልክ ቁራሽ ለምን ቢሉት ይዋጣለታል።

በ ገፅ 18

11

ማሰብ፣ ስሜትና ድርጊት የሚል። ‹‹እከሌን

እገለዋለሁ›› የሚል ሰው ነገሩ ሁሉ የሚጀምረው

ከአስተሳሰቡ ነው። ሰባት ቢሊየን የሚሆን የዓለም

ህዝብ ስላለ የዚያን ያህል የተለያየ ስብዕና አለ።

እኔ እና አንተ፣ ቢጫ እና አረንጓዴ የተቀባ ግርግዳ

ብናይ አንተ ቢጫ እኔ ደግሞ አረንጓዴ ሊታየኝ

ይችላል። ነጥቡ የአመለካከት ነው። ተፈጥሯችን

የተለያየ ስለሆነ ነገሮችን የምንተረጉምበት መንገድ

ይለያያል። ዘረ-መል፣ ተፈጥሮ፣ አስተዳደግና

የምትኖርበት ማህበረሰብ በአስተሳሰብህ ላይ ተፅዕኖ

አለው። ጥሩው ነገር ግን ሁሉም መስተካከል

መቻሉ ነው።

ስብሰባ ላይ ተቀምጠን በሚሰጥ አስተያየት

ወይም በዜና ማሰራጫዎች በሰማነው መረጃ ላይ

ተቃርኗዊ አረዳድ/የተለየ አመለካከት ይኖረናል።

ይህ ለምን ይመስልሻል?

ይህ አንተን ብቻ ሳይሆን ሁላችንንም

የሚያስገርም ነገር ነው። በአንድ ወቅት በአንድ

አይነት መንትዮች (Identical Twins) ላይ ጥናት

ተደርጎ ካልተሳሳትኩ 23.8 በመቶ የስብዕና ልዩነት

አላቸው። ስለሆነም ጥያቄውን እኔ ራሴ መመለስ

ያቅተኛል።

እንደማስበው ግን ባህሪ ብቻ ሳይሆን

ተፈጥሮም የምትጫወተው ሚና አላት ብዬ

አስባለሁ። ይዘን የምንወለደው ነገር እንዳለ ሆኖ

አካባቢም ተፅዕኖ አለው። የሰው ልጅ ስብዕና

የሚቀረፀው ከዜሮ እስከ ሰባት ዓመት ነው

ተብሎ ስለሚታመን የአስተሳሰብ ባለሙያዎች

(Behaviorist) ‹‹አንድ የተወለደ ህፃን አምጣልኝ።

ከፈለግክ ሌባ፣ ዶክተር፣ አርክቴክት…

ጎጆው ወስጥ ተኝቷል። ‹‹በሶ ልስጥህ?›› አለ

ከመድረሴ። የበሶ ጭብጦ እየጎመደ ነበር። ትምህርት

ቤት ለምን እንዳልሄደ ስጠይቀው ጭብጦውን በውኃ

አወራረደና፣ ‹‹ለዚች ሀገር ቅስና ሳይሆን ቅድስና

ነው የሚያስፈልጋት›› አለኝ።

በእውነቱ ከሆነ የአስማማውን ፈላስፋነት

ዛሬ ነው ያወቅሁት ማለት ይቻላል።

‹‹ቅስና ትልቀ ነገርማ ቢሆን ኖሮ

የወላጆችህ ትዳር በቄስ ምክንያት ባልደፈረሰ ነበር››

አለ። የምጠላውን የእናቴን ስም እንዳያነሳብኝ ፈራሁ።

ዘነበች . . . ዘነበች . . . አሁን ይህ የሰው ስም

ነው?

‹‹ስለየኔታ የሰማኸው አለ?›› አልኩት።

በ ገፅ 21

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

12

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 191 ቅዳሜ ጥቅምት 18/ 2004

መቆሚያ ያጣው የዋጋ ግሽበት

በሱራፍኤል ግርማ

ከጊዜ ወደ ጊዜ በመሻሻል ፋንታ

በመባባስ ላይ የሚገኘው የዋጋ

ግሽበት፣ ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ

ኤጀንሲ ይፋ ባደረገው መረጃ

መሰረት በመስከረም ወር

2004 ዓ.ም 40.1 በመቶ ሆኖ

ተመዝግቧል። 40.1 በመቶ

የአጠቃላዩ የዋጋ ግሽበት ልኬት

ይሁን እንጂ፣ ለኢትዮጵያውያን

ኑሮን ፈታኝ በማድረግ ቀጣይ

ዕጣ ፈንታቸውን አደጋ ውስጥ

የከተተው የምግብ ዋጋ በተናጥል

የ51.3 ጭማሪ ነው ያሳየው።

በየወሩ በሚያገኙት ቋሚ ገቢ

ብቻ የሚተዳደሩ፣ ጡረተኞች

እንዲሁም በአነስተኛ የዕለት ገቢ

ኑሯቸውን የሚመሩ ላብ አደሮች

በዋጋ ግሽበቱ በተለይም ደግሞ

በምግብ ዋጋ መናር ከፍተኛ ጉዳት

ደርሶባቸዋል፡፡

ምንጩ ምንድን

ነው?

ከ2003 ዓ.ም አጋማሽ አንስቶ

በአስደንጋጭ ሁኔታ ጭማሪ

በማሳየት አሁን ያለበት ደረጃ

ለደረሰው ተከታታይና ባለሁለት

አኃዝ ግሽበት መንግስት የተለያዩ

ምክንያቶችን አስቀምጧል።

አገር ውስጥ ለተከሰተው ግሽበት

በዋና ምክንያትነት በመንግስት

የተፈረጀው በዓለም አቀፍ ገበያ

የተከሰተው የዋጋ ግሽበት ነው።

የዓለም ኢኮኖሚ ከማንሰራራት

ይልቅ ይበልጥ የመቃወስ አቅጣጫን

ይዞ እየተጓዘ ባለበት ወቅት፣

በመካከለኛው ምስራቅ የፈነዳው

‹‹የዓረብ አብዮት›› በነዳጅ ዋጋ

ላይ ጭማሪ እንዲመጣ ማድረጉን

የሚገልፀው መንግስት፣ ‹‹ስለዚህ

የነዳጅ ዋጋ መቀጠልን ተከትሎ

የሌሎች ሸቀጦችም ዋጋ ቀጥሏል››

በማለት ለግሽበቱ ዋና ምንጭ ነው

ያለውን ሁኔታ ይገልፃል።

ምንም እንኳን መንግስት በአገር

ውስጥ ለሚስተዋለው እጅግ

ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ግሽበት

በዋና ምክንያትነት በዓለም አቀፍ

ገበያ የተስተዋለውን የዋጋ ንረት

በመጥቀስ ‹‹እዚህ ያለው ከውጭ

የገባ ግሽበት (imported inflation)

ነው›› ቢልም፣ በዚህ በርካቶች

አይስማሙም።

ፖለቲከኛና የምጣኔ ሐብት

ትምህርት የተከታተሉት አቶ ገብሩ

አስራት አሁን እየተስተዋለ ላለው

የዋጋ ግሽበት ዋና መንስኤው

መንግስት ያለ ገደብ ከብሔራዊ

ባንክ ተበድሮና አሳትሞ ያሰራጨው

የገንዘብ መጠን ከልክ በላይ

መብዛትና የምርት መጠን መቀነስ

መሆኑን በመግለፅ ይሞግታሉ።

ለአጠቃላዩ የዋጋ ግሽበት

መጨመር ከፍተኛውን አስተዋፅዖ

ያበረከተው እዚሁ አገር ውስጥ

የሚመረተው ምግብ መሆኑን

በማስታወስ የመንግስትን ‹‹ከውጭ

የገባ ግሽበት›› መከራከሪያ ውድቅ

የሚያደርጉት አቶ ገብሩ፣ ‹‹የምግብ

ዋጋ የናረው አገር ውስጥ በቂ

ምርት ስለሌለ ነው›› ይላሉ።

የንግድ አስተዳደር ባለሙያ የሆኑት

አቶ ተመስገን ዘውዴ ከመንግስት

በኩል በተደጋጋሚ የሚደመጠውን

‹‹ከውጭ የገባ ግሽበት›› ዕሳቤ፣

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በተዋረድ

ወደታች እንዲወርዱ የሚደረጉ

ቃላትና ፅንሰ-ሐሳቦች አንድ አካል

አድርገው ይወስዱታል። የነዳጅ

ዋጋ መቀጠል የሚያመጣው የዋጋ

መናር እንዳለ ሆኖ፣ የኢትዮጵያ

ኢኮኖሚ በዓለም አቀፍ ገበያ ካለው

እጅግ አነስተኛ ድርሻ የተነሳ ከውጭ

በሚገባ ግሽበት ማመካኘቱ ወደራስ

ለመመልከት ፈቃደኛ ካለመሆን

እንደሚመነጭ የሚያስገነዝቡት

የንግድ አስተዳደር ባለሙያው፣

ችግሩ የመነጨው ከምርት ዕጥረት

መሆኑን የሚናገሩት አስረግጠው

ነው።

የምግብ ዋጋ ግሽበት የተከሰተው

ከምርት እጥረት የተነሳ መሆኑንና

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ገንዘብ ያለገደብ የሚጨመርበት ኢኮኖሚ ለጊዜው ያደገ

እንደሚመስል ፊኛ ነው ‹‹ፊኛ ውስጥ አየር ሲጨመር

የፊኛው መጠን ይተልቃል፤ አየሩ ፊኛው ከሚችለው

በላይ ሲሆን ግን ፊኛው መፈንዳቱ አይቀርም››

አቶ ተመስገን ዘውዴ

ይህ ኹነትም የግብርና ምርት

የ11 በመቶ ዕድገት እንዳስመዘገበ

መንግስት የሰጠውን መግለጫ

ጥያቄ ውስጥ እንደሚከተው

ከገለፁት ሁለቱ ባለሙያዎች

በተጨማሪ ሌሎችም ተመሳሳይ

አስተያየት ሰንዝረዋል።

‹‹ግሽበት›› የሚለው ቃል አሁን

የሚስተዋለውን ኹኔታ በሚገባ

እንደማይገልፀውና ከምርት

እጥረት የተነሳ ለተከሰተው የዋጋ

ግሽበት ያለተቆጣጣሪ የሚያድገው

የሕዝብ ቁጥር አስተዋፅኦ

እንዳለው የሚናገሩት በዓለም

ባንክ ውስጥ በኢኮኖሚስትነት

ያገለገሉት አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ናቸው፡፡ በአገር ውስጥ በአነስተኛ

ደረጃ የሚመረተው ምግብ አሁን

ያለውን ሕዝብ መመገብ እንዳልቻለ

የሚያስረዱት አቶ ቡልቻ፣

የ‹‹የሕዝብ ቁጥር እንዳይጨምር

የመከላከል እርምጃ አልወሰደም››

በሚሉት መንግስት ላይ ሙሉ

ተጠያቂነቱን አሳርፈዋል።

የኢትዮጵያ ገበሬዎች ከግማሽ

ሄክታር በምታንስ ኩርማን መሬት

ላይ እያረሱና የዘመናዊ ቴክኖሎጂ

ተጠቃሚ ባልሆኑበት የምርት

ዕድገት ሊኖር እንደማይችል

የገለፁት አቶ ቡልቻ፣ ቁጥሩ

እየጨመረ የሚሄደውን ሕዝብ

ለመመገብና የምግብ እጥረትን

ለማስወገድ የተጠቀሱትን ችግሮች

መፍታት ግድ እንደሚል አፅንዖት

ይሰጡበታል።

መንግስት፣ ከዓለም አቀፍ

ሁኔታዎች በመቀጠል ለግሽበቱ

በመንስዔነት የሚያቀርበው

የንግድ ሥርዓቱ ቅልጥፍና

የጎደለውና ለልዩ ልዩ ኢ-ፍትሐዊ

አሰራሮች የተጋለጠ መሆኑን

ነው። ይህንንም ችግር ለመፍታት

በመሰረታዊ ሸቀጦች ላይ የዋጋ

ተመን ቢያወጣም መልካም

ውጤት ያላገኘ ሲሆን፣ ግሽበቱን

ለማስወገድና የአቅርቦት እጥረትን

ለመቅረፍ ራሱ ሸቀጦችን በማቅረብ

አዲስ የጅምላ ንግድ ሥርዓት

መዘርጋቱም ይታወቃል።

ሆኖም የግሽበቱ ዋና ምንጮች

ሌሎች ጉዳዮች ሆነው ሳለ ችግሩን

በነጋዴዎች ላይ መንግስት

የሚያሳብበው የፖለቲካ ትርፍ

ለማግኘት በማሰብ መሆኑን

የሚገልፁ ወገኖች አልጠፉም።

ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ሁሌም

ለችግሮች መፍትሔ የሚሰጠው

ከራሱ የፖለቲካ ትርፍ አኳያ

ብቻ መሆኑን የሚያስገነዝቡት

የሕወሓት/ኢህአዴግ አንዱ

መስራች አቶ ገብሩ አስራት፣

ለአጭር ጊዜ ተግባራዊ ተደርጎ

ፉርሽ የሆነው የዋጋ ተመንም

ለፖለቲካ ትርፍ የታለመ መሆኑን

ይናገራሉ።

‹‹የዋጋ ተመኑ ተግባራዊ

የተደረገው በዋጋ መናር የተነሳ

የተማረረው ሕዝብ ቁጣውን

መንግስት ላይ እንዳይገልፅ

ይልቁኑም ነጋዴውን እንዲጠላ

ለማድረግ ነው›› የሚሉት አቶ

ገብሩ፣ ተመኑ የወጣው ‹‹እሳት

አደጋን›› ለማጥፋት በሚመስል

የጥድፊያ እርምጃ እንጂ ዘላቂ

መፍትሔ ለመስጠት ታስቦ

ባለመሆኑ ብዙም ሳይቆይ መነሳቱ

ላይ ያሰምሩበታል።

ከንግድ ሥርዓቱ ጋር በተያያዘ

‹‹ነጋዴዎች ምርቶችን

አላግባብ ደብቀው በማከማቸት

ዋጋ እያናሩ ነው›› የሚለው

ምክንያትም ለአውራምባ

ታይምስ አስተያየታቸውን

በሰጡ ባለሙያዎች ዘንድ

ተቀባይነት አላገኘም። በአገሪቱ

ያሉት ነጋዴዎች ከፍተኛ ምርት

ደብቀው ሊያከማቹበት የሚችል

ግዙፍ መጋዘኖች እንደሌሉ

የሚያስታውሱት ባለሙያዎች፣

‹‹ይሄ እኮ ግልፅ ነው። የምርት

እጥረት መኖሩን ባለማመን

ሕዝቡንና ነጋዴውን ለማጣላት

የሚደረግ ሴራ ነው›› ባይ

ናቸው።

‹‹ምርት ደብቆ በማከማቸት

እጥረት ተከስቶ ዋጋ ሲንር መሸጥ

የሚፈልግ ነጋዴ እውነት የለም?››

የሚል ጥያቄ ከአውራምባ ታይምስ

ለአስተያየት ሰጪዎቹ ቀርቦ

ነበር። እነሱም ምርት የሚደብቁ

ነጋዴዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ

በማመን፣ ‹‹ሆኖም በገበያው ላይ

ወሳኝ ተፅዕኖ ያላቸው ነጋዴዎች

ኢህአዴግና ደጋፊዎቹ ስለሆኑ

ከእነሱ ውጪ ያሉት ቢደብቁም

ያን ያህል ለውጥ አያመጡም።

ለግሽበቱ የገበያው ሥርዓት

በምክንያትነት የሚቀርብ ከሆነም

ተጠያቂዎቹ ኢህአዴግና ደጋፊዎቹ

ነጋዴዎች ናቸው›› የሚል ምላሽ

ሰጥተዋል።

እስካሁን ከተጠቀሱት ምክንያቶች

ባሻገር ለዋጋ ግሽበት ትልቁ

ምክንያት መንግስት ወጪዎቹን

ለመሸፈን ሲል ከብሔራዊ ባንክ

በመበደርና በማሳተም ወደ

ኢኮኖሚው ያፈሰሰው ገንዘብ

ከመጠን በላይ መሆኑን ብዙዎች

የሚስማሙበት ነው።

የገንዘብ አቅርቦት በኢኮኖሚው

ውስጥ መብዛቱ የተጫወተውን

አሉታዊ ሚና በመገንዘብ

የመንግስትን ወጪ ከብሔራዊ

[በመስከረም ወር

ስለተመዘገበው የዋጋ

ግሽበት አንዳንድ ነጥቦች]

ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ

ወር ጋር ሲነፃፀር አብዛኛዎቹ

የምግብ ክፍሎች ጭማሪ

አሳይተዋል

እህል የ61.9 ከመቶ፣

ጥራጥሬ የ89.4 ከመቶ፣

ዘይትና ቅባቶች

የ69.7ከመቶ፣

ድንችና ሌሎች ስራስሮች

የ41.7ከመቶ፣

ያልተቆላ ቡናና ሻይ ቅጠል

የ88.6ከመቶ፣

ቅመማ ቅመሞች የ62.9

ከመቶ

ጭማሪ አሳይተዋል

ምንጭ፦ የኢፌዴሪ ማዕከላዊ

ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ

ባንክ በሚገኝ ብድር ላለመሸፈን

ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያደርግ

(ዘግይቶም ቢሆን) በመግለፅ ላይ

የሚገኘው መንግስት፣ በተያዘው

የበጀት ዓመት ከብሔራዊ ባንክ

ብድር እንደማይወስድ ተናግሯል።

ነገር ግን ይሄንን የመንግስት

ውሳኔ አቶ ገብሩ አስራት

በጥርጣሬ ነው የሚመለከቱት።

መንግስት የጀመራቸውን ግዙፍ

ፕሮጀክቶች ሥራ ለማከናወን

የግድ ከብሔራዊ ባንክ መበደሩ

እንደማይቀር የሚጠቁሙት አቶ

ገብሩ፣ ‹‹አብዛኞቹን ፕሮጀክቶች

ያቀደው ገንዘብ ሳይኖረው ነው።

ስለዚህ እነሱን ለመስራት ሲል

መበደሩ አይቀርም፡፡ ይሄ ደግሞ

ግሽበቱን ያባብሰዋል›› የሚል

መከራከሪያ ያቀርባሉ።

የዋጋ ግሽበት ማለት ሌላ ተዐምር

ሳይሆን በኢኮኖሚው ውስጥ

ጥቂት ምርቶችና በርካታ ገንዘብ

መኖር ማለት መሆኑን ቀለል

ባለ አቀራረብ የሚያስረዱት አቶ

ቡልቻ፣ መንግስት ከብሔራዊ

ባንክ የሚወስደው ብድር

መጠን እንዲታወቅ አለመፈለጉ

ያሳዝናቸዋል። ‹‹መንግስት

ከሚችለው በላይ እየተደበረ

ጥቂት ምርት ባለበት ኢኮኖሚ

ውስጥ ብዙ ገንዘብ አንዲዘዋወር

አድርጓል። በፊት ከብሔራዊ ባንክ

የሚወስደውን የብድር መጠን

የሚወስን ሕግ ነበር። ይሄን

ሕግ ከዓመታት በፊት በፓርላማ

እንዲሻር አድርጓል›› የሚሉት

በዓለም ባንክ በኢኮኖሚስትነት

ያገለገሉት ባለሙያ፣ መንግስት

በፓርላማ የሚሾመውን

ዋና ኦዲተር እንደማያከብር

ይወቅሳሉ።

አቶ ተመስገን ዘውዴም

የመንግስትን አጠቃላይ ዓመታዊ

ሂሳብ መርምሮ ሪፖርቱን ለፓርላማ

በሚያቀርበው ዋና ኦዲተር

መንግስት ደስተኛ እንዳልሆነና

አንዳንዴም ሪፖርቶችን ውድቅ

የሚያደርግበት ሁኔታ መኖሩን

የሚገልፁት በመገረም ነው።

ከጥቂት ዓመታት በፊት የፌደራል

ዋና ኦዲተር ባደረገው ማጣራት

በርካታ ቢሊዮን ብሮች ወደ

ኢኮኖሚው ውስጥ ያላግባብ

ፈሰስ መደረጋቸውን ሪፖርት

ቢያደርግም፣ ጠቅላይ ሚኒስትር

መለስ ዜናዊ ‹‹ተራ የሂሳብ

ሠራተኛ ሊሳሳት የማይችለውን

ስህተት ዋና ኦዲተር ፈፅሟል››

ማለታቸውን ለሚያስታወሱት አቶ

ተመስገን፣ መንግስት ግልፅነት

የጎደለው አካሄድ እየተከተለ

‹‹ግሽበቱን እቆጣጠራለሁ›› ማለቱ

የሚዋጥ አይደለም።

ዕድገት Vs ግሽበት

በአሁኑ ሠዓት የሚስተዋለው

ግሽበት በዕድገት ሂደት

የሚከሰት መሆኑ ከመንግስት

በኩል ይደመጣል። በአንፃሩ

ደግሞ በትክክለኛ ዕድገት ውስጥ

የሚከሰት ግሽበት ከአንድ አሀዝ

እንደማይበልጥ በመግለፅ፣ ‹‹የምር

ግሽበቱ የተከሰተው ከዕድገት ጋር

ተያይዞ ቢሆን ኖሮ ሕዝቡ ለምን

ይቸገራል?›› የሚለው ጥያቄ

የበርካቶች ነው።

ኢኮኖሚ የሚያድገው ብዙ ምርት

ሲኖር እንጂ ከገደብ ባለፈ ገንዘብ

አለመሆኑን የሚያስገነዝቡት

ከአውራምባ ታይምስ ጋር ቆይታ

ያደረጉ ባለሙያ፣ ‹‹11 በመቶ

የኢኮኖሚ እድገት ተመዝግቧል

የሚባለውም ሀሰት ነው፡

፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት

የምግብ እጥረት፣ የዋጋ መናርና

ሌሎች ችግሮች የአስከፊ ድህነት

መገለጫዎች እንጂ የእድገት

አይደሉም›› በማለት ሞግተዋል።

የኢኮኖሚ ዕድገትንና የዋጋ

ግሽበትን በፊኛና ፊኛው ውስጥ

በሚጨመረው አየር የሚመስሉት

የንግድ አስተዳደር ባለሙያ

የሆኑት አቶ ተመስገን ዘውዴ፣

ኢኮኖሚውን ለማሳደግ በሚል

ምክንያት ገንዘብ ያለ ገደብ ወደ

ኢኮኖሚ ማስገባት ከፍተኛ መዘዝ

እንዳለው ያሳስባሉ። ገንዘብ

ያለገደብ የሚጨመርበት ኢኮኖሚ

ለጊዜው ያደገ እንደሚመስል

‹‹ፊኛ ውስጥ አየር ሲጨመር

የፊኛው መጠን ይተልቃል፤ አየሩ

ፊኛው ከሚችለው በላይ ሲሆን

ግን ፊኛው መፈንዳቱ አይቀርም››

በሚል ምሳሌ ነው ያስረዱት።

‹‹ፊኛው›› ውስጥ የሚጨመረውን

‹‹አየር›› መቀነስ የፊኛውን መጠን

ስለመቀነሱ ከአውራምባ ታይምስ

ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ‹‹ኢኮኖሚው

ውስጥ የሚረጨው ገንዘብ ይቀንስ

ማለት እኮ መንግስት የልማት

ሥራዎችን ለማከናወን ሙሉ

በሙሉ ገንዘብ አይጠቀም ማለት

አይደለም፤ በሚያስፈልገው ልክ

ብቻ ይጠቀም ማለት እንጂ›› ነበር

ምላሻቸው።

የተወሰነ የግሽበት መጠን ከኢኮኖሚ

እድገት ጋር ተያይዞ በሚፈጠረው

የገንዘብ ዝውውር የተነሳ ሊስተዋል

ቢችልም፣ ኢትዮጵያ ውስጥ

ያለው አደገኛ ግሽበት (hyper

inflation) ግን የእድገት ሳይሆን

የድቀት ማሳያ መሆኑን የሚገልፁ

ባለሙያዎች ደግሞ በበኩላቸው

ችግሩን ‹‹ከልማታዊ መንግስት››

ፅንሰ-ሀሳብ ጋር ያቆራኙታል።

መንግስት ሊሰራቸው ካቀዳቸው

ግዙፍ ፕሮጀክቶች ውስጥ

የግል ባለኃብቶች ሊሰማሩባቸው

የሚገባቸውን ከዕቅዱ ውስጥ

አውጥቶ ወጪውን በመቀነስ

ግሽበቱን መቆጣጠር እንደሚችል

በመግለፅ የመፍትሄ ሀሳብ

ያቀርባሉ።

መፍትሔው ምንድን

ነው?

ለአውራምባ ታይምስ

አስተያታቸውን የሰጡ ባለሙያዎች

ከተራ ግሽበትነት አልፎ አደገኛ

ደረጃ ላይ ለደረሰው የዋጋ ግሽበት

ዋና መፍትሄው መንግስት ወደ

ኢኮኖሚው ያላግባብ የረጨውን

ገንዘብ መሰብሰብ በመሆኑ ላይ

ያሰምሩበታል።

ገንዘብ ከኢኮኖሚው ውስጥ

ለመሰብሰብ ከተጠቆሙት

የመፍትሄ አቅጣጫዎች መካከል

የመጀመሪያው መንግስት

የብሔራዊ ባንክን ነፃነት በማክበር

ከተገቢው በላይ ብድር መውሰዱን

ማቆሙ ሲሆን፣ የባንክ የወለድ

መጠንን በመጨመር ሰዎች

ገንዘብ ባንክ እንዲያስቀምጡ

ማበረታታትና የተለያዩ ዓይነት

ቦንዶችን በመሸጥ ገንዘብ

መሰብሰብም ሌሎች የተጠቆሙ

አማራጭ መፍትሄዎች ናቸው፡፡

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 191 ቅዳሜ ጥቅምት 18/ 2004

ማ ስ ታ ወ ቂ ያ

13

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

14

መንግሥት በዜጎቹ ላይ

ሬዲዮ የለንም በሬዲዮ መልስ

አይሰጥ ነገር ግራ የገባው ግራ ሆኖብኝ

ነው፡፡ የሬዲዮ ፋና አድማጭ አይደለሁም፡

፡ አብርሃም የሚባል የሬዲዮ ፋና ባልደረባ

ደውሎ በአሸባሪነት አዋጅና በጠቅላይ

ሚኒስትሩ የፓርላማ ውሎ ዙሪያ

የመንግስት ባለስልጣናት የሚገኙበት

የጋራ ውይይት ሰለሚደረግ ፈቃደኝነቴን

ጠየቀኝ፡፡

አኔም ፈቃደኝነቴን ገልጬለት

ቅዳሜ ለሰባት ዕሩብ ጉዳይ ሬዲዮ

ፋና ጣቢያ እንድንገናኛ ቀጠሮ ያዝን፡፡

ጋዜጠኛው ከቀጠሮ ሰዓት ቀደም ብሎ

በአምስት ሰዓት አካባቢ ስልክ ደውሎ

‹‹ሰማኸው አይደል?›› አለኝ። ‹‹ምኑን?››

ስለው ‹‹ማስታወቂያ ለቀናል። ውይይት

እንዳለ አንተም እንደምትገኝ›› አለኝ፤

‹‹ትቀልዳለህ እንዴ? የፋና አድማጭ

አይደለሁም። አሁን ያለሁት ሥራ ላይ

ነው፤ በቀጠሮ ሰዓት ግን እመጣለሁ››

ብዬው በቀልድ ተለያየን።

በእውነትም የሬድዮ ፋና

አድማጭ አይደለሁም። ነገር ግን

እኔ መኪና ውስጥ በአንድ ምክንያት

የተከፈተ ካሴት፣ ሲዲ ወይም ሬዲዮ

ጣቢያ ለሳምንት ምን አልባትም የቴክኒክ

እክል ካልገጠመውና የተሳፋሪ ተቃውሞ

ካልተነሳበት ለወርም ሳይነካ ሊቀጥል

ይችላል። በዚህ ዓይነት ሁኔታ ረቡዕ

በፋና ሬዲዮ ጣቢያ “ተጓዝ ነቃሽ” የተባለ

ፕሮግራም ለመከታተል በቃሁ።

በማግስቱም ዘጠና ደቂቃ

የሚል ፕሮግራም በተመሳሳይ ጉዳይ ላይ

ሲተላለፍ አደመጥኩ። ምቀኝነትን ዜጎች

እርስ በርሳችን በመንግስት ተቋማት

አጋዥነትና በሚዲያ አሟሟቂነት ነብስ

ዘርቶ አገኘሁት፡፡ ዝርዝረሩን ቀጥዬ

አቀርባለሁ።

የፕሮግራሙ ዋና ጭብጥ

በሀገራችን በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ

የመንግስት ቤት ተከራይተው በመንግስት

ቤት አለአግባብ ጥቅም የሚያገኙ፣

ህብረተሰቡን እየበዘበዙ ያሉ ህገወጥ

ሰዎች እንዳሉ፤ እነዚህ ሰዎች ላይም

አስፈላጊው እርምጃ መወሰድ እንዳለበትና

መንግስት እሰከ አሁን ዝም ማለቱ ተገቢ

እንዳልሆነ በተለያየ መንገድ የሚገልፅ

ነው።

ትኩረቱ ቤት ሸንሽነው ለንግድ

ቤትነት የሚያከራዩ ዜጎች ላይ ነው፡፡ ነገሩን

የበለጠ ግልፅ ለማድረግ ከመንግስት ቤት

ተከራይተው ሸንሽነው የሚያከራዩ ሰዎች

ሕገ-ወጥ፣ በዥባዦች፣ ለተፈጠረው

የዋጋ ንረት ተጠያቂዎች ተደርገው የክስ

መዓት ይወርድባቸዋል።

የሚያሳዝነውና እንደመፍትሄ

የቀረበው ደግሞ በሽንሽን ቦታዎች

ላይ ተከራይተው የሚሰሩት ሰዎች

የያዙትን ቦታ ለመውረስና በዝቅተኛ ዋጋ

ተከራይተው እንዲቀጥሉ ያቀረቡት በህግ

ሽፋን የመውረስ ጥያቄ ነው፡፡ ጉዳዩ አቶ

ተፈራ ዋልዋ የአዲስ አበባ መስተዳድር

ከንቲባ እያሉ የነበረውን ዓይነት የተከራይ

አከራይ ድራማ ለመድገም የተጠነሰሰ

ሴራ እንዳለ የሚያመላክት ነገር አለው።

ለማገገም እየሞከረ የነበረውን

በንግድ ማህበረሰብ ውስጥ ያለን ጤናማ

ግንኙነት በድጋሚ እንዲበላሽ የሚያደርግ

ውሳኔ መጠንሰሱን መጠርጠር ደግ

ከመሆኑ በላይ፣ ቤታቸው /የተከራዩትንም

ቢሆን/ ለመወረስ የተዘጋጀ መሆኑን

ሽንሽን ሰርተው በማከራየት ላይ ያሉ

ዜጎች ልብ ሊሉት ይገባል።

በፋና የዋህ አድማጮችና

የሰውን ንብረት ለመውረስ በተዘጋጁ

የሽንሽን ቤት ተከራዮች ከሚቀርቡት

ክሶች ዋነኛ የነበረው “የመንግስትን ቤት

በርካሽ ተከራይተው በውድ እያከራዩ ነው”

የሚለው ነው፡፡ ለመሆኑ የመንግስት

ቤት ማለት ምን ማለት ነው? በመርካቶ

የመንግስት ቤት ማለት የቱ ነው?

መንግስት አንድ ቆርቆሮ ያላለበሰው፣ አንድ

ምስማር ያልመታበት ደርግ የወረሳቸውን

ቤቶች ነው መንግስት “የእኔ ናቸው”

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

በግርማ ሰይፉ

የሚለው፡፡ እንግዲህ ደርግን በመውረሱ

እየኮነነ ደርግ በወረሰው ንብረት ደግሞ

ዜጎችን ለማፈን እየሞከረ ነው።

ሸንሽነው የሚያከራዩ ሰዎች

ግን የሚያከራዩትን ቤት ለገበያ ቦታ

እንዲሆን ገንዘባቸውንና እውቀታቸውን

ገብረውበታል። ከዚያም በላይ ስርዓቱ

የሚጠይቀውን በሽፍንፍን ሙስና፣ በግልፅ

ግን ለግንባታ ማስፈቀጃ ከፍለውበታል።

ጉቦ መክፈላቸው አያስደስተኝም። ከሱ

ጋር የከፈሉት ነፃነታቸው ግን የበለጠ

አንጀቴን ይበላዋል።

ይህን በማድረጋቸው ኢህአዴግን

ሲደግፉ እንደነበረም አውቃለሁ።

የኢህአዴግ ደጋፊ ነጋዴዎች ፎረም

አባል በመሆንም ድጋፍ አድርገዋል።

ኢህአዴግ ግን ዛሬ ከነዚህ ጥቂቶቹ ይልቅ

በሽንሽን ውስጥ ያሉት ብዙኃን የበለጠ

ስለሚያስፈልጉት ነፃነትን ያህል ክብር

የገበሩለት ቢዝነሳቸውን ሊወርስባቸው

ነጋሪት እያስጎሰመ ነው።

ነፃነታችሁን የሸጣችሁ ዕለት

ብዙ ነገር አብሮ እንደተወረሰ ልብ ማለትም

ተገቢ ነበር። አሁን ግን ነፃነታችሁን

የሸጣችሁለት ንብረት ሊወረስ ነው።

የሽንሽን ቤት ወራሾች በናንተ ተራ ገብተው

የናንተን ንብረት ሲወርሱ እነርሱም

በተራቸው ነፃነታቸውን ለማስወረስ

ተዘጋጅተው ብቻ እንዳይመሰላችሁ፤

ለልጆቻቸው ሁሉ የሚነግሩት እውነት

የላቸውም። ዘርፈው እንደሚያወርሷቸው

አይነግሯቸውም።

ሌባ ለልጁ መስረቁን

አይነግርም፤ ልጅ ግን ሁሌም ስለወላጆቹ

የኃብት ምንጭ ያስባል። ልጆቻችንን

ከማሳቀቅ ብንታቀብ ምን ይመስላችኋል?

አንድ ተከራይ ነኝ ያሉ ግለሰብ በብር

ሶስት ሺህ አምስት መቶ እንደተከራዩ

ነገር ግን ስለማያተርፉ ኪራዩን ተበድረው

እንደሚከፍሉ በማሰተዛዘን ገልፀዋል።

ዕውነቱን ለመናገር ኪራይ

በብድር አይከፈልም፤ ዓላማው መንግስት

የዚህን ያህል ኪራይ እንዳያስከፍላቸው፣

ብሎም ከዚህ ጋር ተመጣጣኝ ገቢ መሰረት

አድርጎ የገቢ ግብር እንዳይጠየቁ የዘየዱት

ነው። ከዚህ ባሻገር አከራዩ እንዲከራዩት

አላስገደዳቸውም፤ ምናልባትም ተጫርተው

ነው የተከራዩት፤ እገሌን አስወጣው፤ እኔ

ይህን ያህል እከፍላለሁ ብለው ጭምር

ሊሆን ይችላል።

የኪራይ ቤቶች፣ የሬዲዮ

ጣቢያ አዘጋጆች፣ የተከራዮች ወዘተ …

ምቀኝነት ነብስ ዘርቶ የሚታየው አከራዮቹ

የሚያገኙትን ሂሣብ ሰርተው በምናባቸው

ሲያዩት ነው። ቀደም ሲል እንደገለፅኩት

አንድ ምሰማር ላልመታ መንግስት

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 191 ቅዳሜ ጥቅምት 18/ 2004

ለምን ምቀኛ ይሆናል?

በነገራችን ላይ አንድ የተከራዩትን ቤት ሸንሽነው በውድ እያከራዩ በዘበዙን የምትሉ

ዜጎች እነዚህ ሰዎች ከማከራየት ይልቅ ለብቻቸው ይዘውት እንደአንድ የገበያ ማዕከል

እየሰሩበት ሰራተኛ ቀጥረው ቢሰሩበት ኖሮ ምን ትሉ ይሆን? ከዚህ ይልቅ ግን ሰራተኛ

ቀጥሮ ከማሰተዳደር ሁሉም በነፃነት እንዲሰራ ኃላፊነት እንዲሰማው ማከራየት ይሻላል

ብለው አማራጭ መውሰድ ኃጥያት መደረጉስ ለምንድነው?

የመንግስት ቤት እያሉ የሱ ያልሆነውን

ሲሰጡት፤ የንግድ ሂሣቡን፣ ለተሻለ የገቢ

ምንጭ ብሎ ብዙ ጊዜና ገንዘብ ያወጣውን

ዜጋ ግን በዝባዥ ብለው ያለ ስሙ ስም

ይሰጡታል።

ዜጋ ገንዘብ ሲያገኝ የሚቀና

ምቀኛ ሥርዓትና ይህንን ለማገልገል

የተሰለፉ ሎሌዎች ብዛት ስመለከት

ዕፍረት ይሰማኛል። ጣቢያው በዛው

ዕለት ስለነፃ ኢኮኖሚ ሲሰብክ ብትሰሙት

እንዳይገርማችሁ። ግራ የገባው ግራ

ማለት ይሄኔ ነው። መንግሰት በዘረፋ

የያዘውን ቤትም ቢሆን ዜጎች አከራይተው

ገንዘብ እንደሚያገኙ መረጃ ካለው በንዴት

መብገን ያለበት አይመሰለኝም፤ ተገቢም

አይደለም።።

ዜጎች ባገኙት ገቢ ልክ ግብር

መሰብሰብ ነው ከመንግስት የሚጠበቀው።

የመንግስት ወግ ይህ ነው። ይልቁንም

ተከራዮች በሚከፍሉት ኪራይ ልክ

ግብር እንዳይጠየቁ ኪራይ ተቀንሶ

እንዲነገርላቸው እንደሚማፀኑ ስንቶቻችን

እናውቃለን? እውነቱን ለመነጋገር አከራዩ

ከኪራይ በሚያገኘው ኪራይ ልክ ግብር

አልከፈለም ብለው ሲከሱ የነበሩ ተከራዮች

እስኪ ለኪራይ በከፈሉት ልክ የገቢ ግብር

መክፈላቸውን ይናገሩ። ዓሣ ጎርጓሪ ዘንዶ

ያወጣል ማለት ይህ ይመሰለኛል።

መንግስት ዜጎች ገንዘብ ሲያገኙ

ለምን እንደሚመቀኝ አይገባኝም፡፡ ይህ

ከሶሻሊዝም የወረስነው፤ በአብዮታዊ

ዴሞክራሲ እያዳበርነው ያለነው የመንግስት

ሞግዚትነት አባዜ ውጤት ነው፡፡ ዜጎች

ገንዘብ ሲያገኙ ለተጨማሪ ሥራ ፈጠራ፣

አዳዲስ ቴክኖሎጂ ለማስመጣት፣ ለሀገር

ዕድገት፣ ወዘተ ያውሉታል የሚል ቅን

ልቦናችንን ምን እንደወሰደው መጠየቅ

ያለብን ይመስለኛል።

ሶሻሊዝም በዓለም እንደተወዳዳሪ

ርዕዮት ከተወገደ ከሃያ ዓመት በኋላ

በእኛ ሀገር የሃያና ሃያ አምስት ዓመት

ወጣቶች በዚህ አባዜ ተለክፈው ማየት

ምን እንደሚባል አላውቅም። ከመንግሥት

ይልቅ ግን ዜጎች የሚያገኙትን ገንዘብ

ለተሻለ ሀገራዊ ጥቅም ስለሚያውሉት

መንግሥት ከተወሰኑ መስኮች ውጭ

የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን ለዜጎች መተው

አለበት በሚባልበት ዘመን ላይ ሆነን የእኛ

መንግስት ግን ቤት በማከራየት ሥራ

እንዲሰማራ፣ ሱቅ ሸንሽኖ እንዲያከራየን

እንጠብቃለን።

ዛሬ መንግስት ሱቅ ሸንሸኖ

እንዲያከራየው በሬዲዮ የለመነ ሁሉ

ከዚህ ጋር ተያይዞ መንግስት በነፃነቱ ላይ

የሚያደርሰውን ጫና ለመሸከም ጫንቃውን

ማደንደን ይኖርበታል። መንግስት ከቀበሌ

ቤት እንዳንወጣ፤ ከወጣንም ኮንዶሚኒየም

ውስጥ እንድንገባ የሚፈልገው ስለሚወደን

የሚመሰለው ካለ አይሞኝ። ነፃነታችን

ስለሚያስፈራው ነው። ፋብሪካ ወደ ግል

እንዲዛወር እፈልጋለሁ የሚል መንግስት

ቤት የማከራየት ሥራን ከእጁ ለማውጣት

ወደኋላ የሚለው ለምን ይመሰላችኋል?

አሁንም ቢሆን ከኪራይ ቤቶች

በኪራይ የተያዘን ቤት ሸንሽኖ ማከራየት

ክልክል ከሆነ ይህ በግልፅ ተነግሯቸው

ተከራዮች አማራጭ ሊፈልጉ ይገባል፤

ይህ ሕገ-ወጥ ነው ከተባለም (በእኔ ዕምነት

አይደለም) የንግድ ቦታዎቹን የያዙት ሰዎች

ቦታውን መያዝ ያለባቸው አሁን በያዙት

ዋጋ ሳይሆን በግልፅ ጨረታ በውድድር

አሸንፈው መሆን ይኖርበታል።

የሰው ንብረት ለመውረስ

የቋመጡ የሽንሽን ሱቅ ተከራዮች

ገደባቸውን ሊያልፉ አይገባም። ይህ ውሳኔ

መዘዙ ብዙ ሊሆን እንደሚችል መገመት

አያስቸግርም። የሕይወትና ንብረት

ኪሣራ ሊያስከትል እንደሚችል መንግስት

ተረድቶት ውሣኔውን በጥሞና ሊመረምር

ይገባል።

በነገራችን ላይ አንድ የተከራዩትን

ቤት ሸንሽነው በውድ እያከራዩ በዘበዙን

የምትሉ ዜጎች እነዚህ ሰዎች ከማከራየት

ይልቅ ለብቻቸው ይዘውት እንደአንድ

የገበያ ማዕከል እየሰሩበት ሰራተኛ ቀጥረው

ቢሰሩበት ኖሮ ምን ትሉ ይሆን? ከዚህ

ይልቅ ግን ሰራተኛ ቀጥሮ ከማሰተዳደር

ሁሉም በነፃነት እንዲሰራ ኃላፊነት

እንዲሰማው ማከራየት ይሻላል ብለው

አማራጭ መውሰድ ኃጥያት መደረጉስ

ለምንድነው?

በእኔ ዕምነት የሰው ንብረት

ለመውረስ መንግስትም ካለበት

የተቆጣጣሪነትና በሁሉም ነገር ያገባኛል

ከሚል አባዜ የመጣ ነው የሚል ዕምነት

ነው ያለኝ። ይህ የሰው ንብረት የመውረስ

አባዜ ግን በእኛ ብቻ ሳይሆን ለልጅ

ልጆቻችን የሚተርፍ ጦስ ይዞ ይመጣል።

በጥሞና ልናስብበት ይገባል የሚል ዕምነት

አለኝ። ግለሰብ ከሚበዘብዘኝ፣ መንግስት

ይበዝብዘኝ ነው ምርጫው የሚመሰለው።

የመንግስትን ሚና በቅጡ

ካለመረዳትና ደርግ በቀደደው የመውረስ

መንገድ የተመሰረተ ድርጅት/ኤጀንሲ

ኃላፊ ነን የሚሉ ሰዎችም ወንበራቸው

ጊዜያዊ መሆኑን ተረድተው በማያገባቸው

የሽንሽን ሱቅ የማከራየት ሥራ ባለመግባት

መንግስትን ባያስወቅሱት ደግ ነው።

መንግስት ገቢ ማግኘት አለበት ካሉ

መንግስት ሽንሽን ሱቅ አከራይቶ ሳይሆን

ግብር ሰብሰቦ መሆን ነው ያለበት።

የመንግስት የገቢ ምንጭ መሆን

ያለበት ግብር ነው። በዚህ ፅሁፍ በሽንሽን

ሱቅ ያላችሁ ዜጎች ዛሬ ለጊዜያዊ ጥቅም

የምትወስዱትን አቋም ቆም ብላችሁ

እንድታስቡበት መምከር እወዳለሁ።

ባለፈው ጊዜ መንግስት የፓርኪንግ ሥራ

የጀመሩትን ባለኃብቶች ወርሶ ለፓርኪንግ

ሰጥቶዋል፤ ዛሬ ኪራይ ቤቶች ኤጄንሲ

በተከራይ አከራይ ሰም ሊወርስ ነው፣

ነገ ሌላ ይቀጥላል። እንዲህ እያልን ተራ

በተራ እንወረሳለን ማለት ነው።

/የተከበሩ አቶ ግርማ ሠይፉ

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል ናቸው/

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 191 ቅዳሜ ጥቅምት 18/ 2004

እንዴት ሰነበታችሁ ሰሞነኛ

ወዳጆቼ? …‹‹አላርፍ ያለች

ጣት ለእጇ ካቴና አታጣም››

ይላሉ እኒያ የማላቃቸው

ሴትዮ። የብዕር ወገብ

በጨበጡ ቁጥር ‹‹ተናገር

ተናገር›› ለሚላቸው ብዕር

ለባሾች በጠቅላይ ሚኒስትራችን በኩል

መልዕክት አስተላልፈናል። መቼም መልዕክቱ

እናንተ ጆሮ ሲደርስ ጣሊያንኛ ይሆናል

ብለን አናስብም። ‹‹መልዕክቱን የተቀበለ እሱ

ይድናል›› ይላሉ ያልተፃፈው መፅሐፍ። ሲፃፍ

ደግሞ ብዙ ይላል ብለን ተስፋ እናደርጋለን።

ወዳጆቼ ለእናንተ የሚሆን ወግ

ፍለጋ ከኳስ ሜዳ እስከ ሽሮ ሜዳ፣ ከቦሌ እስከ

ጉለሌ ስዞር ለወግ ማድመቂያ የሚሆን አንዱ

ሹክ ያለኝን ልንገራችሁማ… ማነህ ወዳጄ

ክሬዲቱ ተይዞልሀል። ነገሩ እንዲህ ነው እድሜ

ለጠሀዩ መንግስታችንና ኑሮ እንደ ሮኬት ላይ

በተስፈነጠረበት በዚህ ጊዜ የሰውዬው የቤት

ሠራተኛው በወጣ በገባ ቁጥር ‹‹እንትን አለቀ

እንትንም የለም›› በማለት ስታሳቅቀው ነበርና

አንድ ቀን መልዕክት ልትነግረው ገና ጋሼ

ስትለው ‹‹904 ደሞ ዛሬ ምን አለቀ?›› አላት

አሉ የጉድ አይደለም? ከጉድ ወዲያንዲያ

እንጂ… [እየበላሽ የማታድጊው ስልኬ ትዝ

አልሽኝ]

ቆይ ሳልረሳውማ የእንትን ሰፈር

ልጆች ቴሌ ሰራተኛ አባሮ እንዴት ሊሰራ

ነው? እያላችሁ ስትንሾካሹኩ አልነበር? ይሄው

የኔትወርኩን ምህዳር ‹‹በማስፋት›› ኩም

አደረገልና! በእርግጥ አዲስ አበባ ከሰው ጋር

በስልክ መነጋገር እንደ ዝቋላ ዳገት አስቸጋሪ

እየሆነ ነው። ‹‹ፖለቲከኞች እና ፖለቲካ

ጋዜጣ ላይ የሚሰሩ ጋዜጠኞች ጋር ስንደውል

ኔትወርክ፣ ሀርድ ዎርክ ይሆንብናል። አሁንማ

ከፍቅር ጓደኛችን ጋር ስናወራም…›› የሚሉ

ወቀሳዎች ኢትዮጵያን ከመጪው ዓለም ጋር

‹‹በማቀራረብ›› ላይ ያለው ቴሌያችን ላይ

እየተሰማ ነው። አንድ አሉባልተኛ ወዳጄማ

‹‹ቴሌ የተለወጠው ስሙ ብቻ ነው›› ብሎኝ

በንዴት የሁለት ወር ጉንፋን ለቆብኛል።

ኢትዮ ቴሌኮምዎች አታሰድቡን እንጂ!

‹‹የደወልንላቸውን ደንበኛ አሁን ማግኘት

ካልቻልን›› በቀጠሮ መቼ እንደምናገኛቸው፣

መቼ እንደሚመቻቸው ጠይቃችሁ ንገሩንማ!

እኔ የምወዳችሁ፣ እናንተ የማትነግሩኝ

ወዳጆቼ ደሞ ለወግ? ነፍ ነበር ምን ዋጋ አለው

የታች ሰፈር ልጆች ጢባራቸው አስቸገረን

ወይኔ ነገር ሲጠመዝዙ … አቦ ተውና!

ሰ ሞ ነ ኛ

አንድ የአማርኛ መዝገበ ቃላት ‹‹ሰሞንኛ›› የሚለውን ቃል፣ ‹‹ከዕሁድ እስከ ዕሁድ የሚያገለግል ሰው›› ሲል

ይተረጉመዋል። እኔም የሰማሁትን ላሰማዎ፣ ያየሁትን ላሳይዎ፣ ትጉ ሰሞነኛ አገልጋይዎ መሆንን ወደድሁ።

‹‹ንቦች አሜሪካ ውስጥ አስቸገሩ››

ሬዲዮ ፋና

‹‹ፋና ሆይ ንቦች ያላስቸገሩበት የት አይታችኋል?›› የታች ሰፈር ልጆች

እኔስ ምኔ ፋራ ‹‹እንቆቅልሽ›› አልኳቸው ‹‹ምን እናውቅልህ?››

ሲሉኝ ‹‹ድርቅ እያለ ረሀብ የሌለባት አገር›› ብላቸው እንዴት

ይመልሱት! ማሰቢያ’ኮ የለም፤ ኔፕ ናቸው። ‹‹በቃ ሰፈር ስጡኝ››

ብላቸው ቤተ-መንግስትን አይሰጡኝ መሰልዎ! በስማምዬ! ቤተ-

መንግስት ሆኜ ምን አጥቼ፣ ሁሉ በጄ፣ ሁሉ በደጄ… ስፈልግ

አስሬ፣ ሳልፈልግ ከአገር አባርሬ ምን ነበር ጥያቄው? ጠፋብኝ

መልሱ ግን ኤርትራ ነው።

ብዬ ሃርድ ምናምን ብቦጭቅላቸው ‹‹ሌላስ

የለህም?›› አይሉኝም የሆነ የእንቆቅልሽ ጥያቄ

አስመስለውት። እኔስ ምኔ ፋራ ‹‹እንቆቅልሽ››

አልኳቸው ‹‹ምን እናውቅልህ?›› ሲሉኝ

‹‹ድርቅ እያለ ረሀብ የሌለባት አገር›› ብላቸው

እንዴት ይመልሱት! ማሰቢያ’ኮ የለም፤ ኔፕ

ናቸው። ‹‹በቃ ሰፈር ስጡኝ›› ብላቸው ቤተ-

መንግስትን አይሰጡኝ መሰልዎ! በስማምዬ!

ቤተ-መንግስት ሆኜ ምን አጥቼ፣ ሁሉ በጄ፣

ሁሉ በደጄ… ስፈልግ አስሬ፣ ሳልፈልግ ከአገር

አባርሬ ምን ነበር ጥያቄው? ጠፋብኝ መልሱ

ግን ኤርትራ ነው። [ምነው ሆዴ ጮኸሳ?

ራበኝ እንዴ? (ይቅርታ ለካ ረሀብ አይባልም)

የምግብ እጥረት አጋጠመኝ እንዴ? ወይስ

ሆዴ ደርቆ ይሆን?]

[ውድ አንባብያን አሁን የዜና

ሰዓታችን ስለ ደረሰ ከዜናው በኋላ ተመልሰን

እናወጋለን]

ጤና ይስጥልኝ ዜና እናሰማለን፤

ምክንያቱም ከማን እናንሳለን።

‹‹የዘንድሮው ዓመት ከቀጣዩ ዓመት

በሁሉም ነገር የተሻለ ይሆናል›› ሲሉ ቃሊቲ

ያሉት ጋሼ ታምሩ ኤክስክሉሲቭ ለታች ሰፈር

ልጆች ተንብየዋል። ልጆቹም ‹‹ከሚመጣው

ይህኛው የተሻለ ከሆነ በዚሁ ዓመት

ይውጣልን›› ማለታቸውን የሰሙ መንገደኛ

‹‹ይውጣልን የሚሉት እስር ቤትን ኩፍኝ

ማድረጋቸው ነውን?›› ሳይሉ አልቀረም ብሎ

የጠረጠረው ዳተኛው ዘጋቢ ዜናውን ሳይፅፈው

ቀርቷል።

የውጪ ዜና፡- የስድብ አባት የሆኑት

[ይቅርታ የነበሩት] ሙአመር ጋዳፊ ለስድብ

ሳውንድ ትራክ የሚጠቀሙ ብቸኛው መሪ

እንደነበሩ ሰሞኑን አንድ ቀጣፊ ተናግሯል።

ኰሎኔሉም ትንቢተኛ መሆናቸውን ገልጾ

የዚህ ማሳያው ‹‹አይጥ›› እያሉ የተሳደቡት

በአይጥ ጉሬ መሞታቸውን ለመጠቆም ነው

ብሏል። በሚስጥር የተቀበሩበት ምክንያትም

‹‹ሚስጥር ነው ማን ሰውየውን ያምናል።

ሰማይ ቤትም አረንጓዴውን አብዮት ይሰብኩ

ይሆናል›› ይላል ቶክ.com በጀርባ ገጹ።

እኛ ከዜናው ተመልሰናል ጋዳፊ ግን

ጭረዋል። መልካም ጭረት ይባላል እንዴ?

ኧረ ሳቄ ናልኝ አለች የኛ ሰፈሯ… ‹በህመም

ነው የማይቀለደው እንጂ በሞትማ ቀላል

ይቀለዳል እንዴ? በነገራችን ላይ ‹‹በህመም

ነው የማይቀለደው እንጂ በሞት ይቀለዳል››

የሚለው የትኛው ኢንሳይክሎፒዲያ ነው?

የታች ሰፈሩ ላይ ይሆን?

እውነት ግን አዲስ አበባችን እንኳን

ርሃብ ችግር ራሱ በሰረገላ ቁልፍ ሳይቆለፍበት

አልቀረም እውነቴን ነዋ! ቆይ ግን ችግሩ

ሁሉ ተሰብስቦ የተቆለፈበት እኛ ሰፈር ነው

እንዴ? [እርስዎም ይሄንኑ ሳይሉ አይቀርም

ብለን ጠረጠርን] አዲስ አበቤ ምንድን ነው

የምትሉት? ዳውን ታውን ቡጊ ቡጊ ሲል ነው

የሚጨሰዋ! ሰሞኑን አንድ ሚጢጢ ጥገኛ

ባለ ሀብት ይዞኝ ገባ። መጠጡ አናታቸው

ላይ ሲወጣ ከአንደበታቸው ደግሞ ግጥም

15

ሲወጣ አየሁ። የዜማውን ነገር ተውት አሃ!

የዜማው ቅርፅ እንደ አካሄድ በመሰረተ ሀሳቡ

ያስማማኛል። ሬንጁ ጠባብ ሆኖ የሪትሙ

ትራንስፎርሜሽን ልማታዊ አይደለም። ግጥሙ

ግን እንዲህ ይነበባል፡-

እድገት እድገት ይላል ያላየ

ህልመኛ

ዳቦ ዳቦ ይላል የነገ ተስፈኛ

ሰው በራብ መሞቱን ማን አውቆ

ያለኛ!

እውነቴን ነው መታወቂያ በማሳየት

ልይዛቸው አሰብኩና ነገር ግን በዘፈኑ ልክ

እርምጃ ለመውሰድ እንዲመቸኝ ተውኩት።

ልክ ነኛ! ከዘፈኑ በመለስ [ይሄ መለስ ቀለስ

የሚባልበት ቦታ መቼም…] ‹‹ችግር እስካላመጡ

ማንም ‹‹ጋጠወጥ›› አልደግመውም አፉን

መክፈት ይችላል፤ የአፉ አከፋፈት ሌላ ትርጉም

እስካላሰጠ ድረስ›› ስል የታች ሰፈር ልጆች

ተበድረው አይስቁብኝ መሰልዎ… ጥርሳችሁ

ይርገፍ እንዳልል በቦክስ ጨርሰውታል።

አደገኛ ፍንዳታ ሁላ! [በነገራችን ላይ አደገኛ

ፍንዳታ፣ አደገኛ ቦዘኔ ከሚለው አደገኛ፣ አደጋ

ጣይ ቃል የመጣ ነው።]

እኔ የምለው ሰሞኑን ደግሞ ውሃና

ፍሳሾች ከሰው እኩል ሊያደረጉን ነው። ውሃ

ካለበት አካባቢ ወደ ሌለበት ሊያካፍሉን ነው

ወንዳታ! ግንኮ በነካ እጅ ዳቦ ላጣነውም በርገር

በሊታዎች እንዲያካፍሉን ህግ ይውጣልን!

አንዱ ጠብቆ አዳሪ ‹‹መንግስት የከተማ ግብርና

እያደራጀ እንዳለው ሁሉ ለምን እኛንም በከተማ

እርፍና አያደራጀንም?›› ብሎ አረፈው። አዩ

ግን ልዩነት… አንዱ ባደራጀን፣ ሌላው በክፉ

አይኑ ባላየን፣ ሌላው… ሌላው…

ምን ትዝ አለኝ… ‹‹የእጅ መታጠብ

ቀን›› ሰሞኑን ሲከበር ኢቴቪ ላይ ያፈጠጠው

አያቴ ‹‹የሚበላ ሳይኖር እጅ መታጠብ በራሱ

በሽታ ነው›› ሲል የእህቴ ልጅ አቢቲ እየተኮላተፈ

‹‹እንዴ በአምስት ዓመቱ ትራንስፎርሜሽን

‹‹የእጅ መታጠብ ቀን›› የሚበሉት ላላቸው

ተብሎ ይስተካከላል፣ ለሌላቸው ደግሞ ዳቦ

የማይገኝበት ቀን ይከበራል›› ቢላቸው ደማቸው

ባንዴ እንደ ባንዲራ ላይ አይሰቀል መሰልም።

አሁን ግን ለሀዘን ዝቅ እንደሚደረገው ባንዲራ

ትንሽ ዝቅ ብሏል ወላዲቴን! ግን እስቲ አስቡት

‹‹የሚበሉት ባላቸው ዘንድ የሚከበረው የእጅ

መታጠብ ቀን ለዚህ ጊዜ ያህል ተከብሮ ዋለ››

ሲባል።

ሰሞነኛ ወዳጆቼ ሆይ ቆይማ!

ስልኬን መዝጋት አለብኝ እንዴ? አላዋራ

ያለን ቴሌ ተማረሩ ብሎ ሲፈርድብን ነው

መሰለኝ የማስታወቂያ ጋጋታ ያስልክብኛል።

የጠ/ሚኒስትራችንን የበቀደም የፓርላማ ውሎ

ለታሪክ ላኑረው ብዬ ከዩ ቲዩብ ዳውን ሎድ

ላድርግ ብል መከራ ሆነብኝ። ይህን የነገርኩት

ወዳጄ ‹‹ጀምረኸው ናዝሬት፣ ሀዋሳ ዘመድ

ጠይቀህ ብትመለስ ይቀልሀል›› ብሎ ሙድ

ይዞብኛል። ኧረ! ልማታዊ ዳውን ሎድ ስናደርግ

እንኳን ቴሌያችን እንዴት ነው?

ሰሞኑን አሜሪካ ካሊፎርኒያ ውስጥ

ከጭነት መኪና ያመለጡ ንቦች ፖሊሶችን

ሳይቀር እየነደፉ መሆናቸው አስደንጋጭ

እንደሆነ ሬዲዮ ፋና ደጋግሞ እየዘገበ ነው፡

፡ ይህንን የሰሙ የታች ሰፈር ልጆች ‹‹ወይ

ሬዲዮ ፋና እናንተ የሚታያችሁ የፈረንጅ ንቦች

ብቻ ናቸውን?›› ሲሉ አፊዘዋል፡፡ ‹‹የአገራችን

ንቦች ንድፊያ ለምን አልተወራም›› ነው ነገሩ

መሰለኝ። አንዳንድ አሉባልተኞችማ ‹‹ፋና

ሆይ አንተ የንቦችን ማር እንጂ ንድፊያ የት

አውቀኸው?›› እያሉ ያማሉ አሉ። ሌሎች

ደግሞ ‹‹ንቦች ያላስቸገሩበት የት አለ?›› እያሉ

ያንሾካሽካሉ። ለማንኛውም እኔ የለሁበትም

ብሎ መሰናበት ሳይሻል አይቀርም፤ ስንቱን

ገስፀን እንችላለን? በሁለት ሳምንት ውስጥ

አይቀርላችሁም እንደተባለው ‹‹ፀባይ ካላችሁ

ሁለተኛውንም እናሳልፍላችኋለን›› ካሉን

የሳምንት ሰው ይበለን። ሰላም!!!

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

16

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 191 ቅዳሜ ጥቅምት 18/ 2004

“ሽብርተኝነት ለኢትዮጵያ ባዕድ የሆነ ነገር ነው

…በዚህ ሰበብ ሽብርተኝነትን እንዳናስተምር እሰጋለሁ”

አቶ መለስ ሲናገሩ አቃቤ ሕጎች፣ ዳኞችና ፖሊሶች ይኼንን

ተከትለው ይሄዳሉ ብለው እንኳን አያስቡም

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም

በኤልያስ ገብሩ

የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁን እንዴት ተመለከቱት?

ለእኔ …የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ አሜሪካ እንደዚህ አይነት ሕግ ወጥቷል። ይኼም ሕግ ሲወጣ

በአሜሪካ ውጥ ብዙ ጩኸት ነበር። ‹‹የሰብዓዊ መብቶችን ይነካል›› በሚል ብዙ ችግር ነበር።

እኛ ጋር የሚያሳዝነኝ የዛን መገልበጥ፣ እነሱ የሆኑትን መሆን እና እነሱ የሚፈልጉትን

መሆን መሆናችን ነው። በእኛ በራሳችን፣ በታሪካችን፣ በባህላችንና በመንፈሳዊ ህይወታችን

በኩል ተነስተን ብናየው ሽብር። እንደዚህ አይነት ነገር አናውቅም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ገበያ

ላይ ወጥቶ፣ ትምህርትና ሆስፒታል ሄዶ ቦምብ የሚጥል ሕዝብ አይደለም። በታሪካችን

እንደዚህ አይነት ነገር የለም፤ በፍፁም ባዕድ ነው። እና ይኼን የሌለብንን ነገር ‹‹አለባችሁ››

ብሎ ፈረንጆች ስላሉ ብቻ በራሳቸው ችግር… እነሱ ደግሞ ይኼንን እንዴት እንዳገኙት

እናውቀዋለን። ‹‹እኛም ጋር ይሄ ይመጣል›› ብሎ ወይም ‹‹አለ›› ብሎ እንደዚህ ጠ/ሚ/ሩ

በእርግጠኝነት የሚናሩት ከየት እንደመጣ አላውቅም። የተቃዋሚዎችና የስልጣን ተቀናቃኞች

ችግር ይኖራል። ነገር ግን ይኼ ‹‹ሽብርተኛ›› ተብሎ ከሽብርተኛ ጋር የሚያስፈርጅ ምንም

ነገር የለበትም - ለእኔ፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ በዕድሜዬ ያየሁት ድሮ አንድ ጊዜ ሲኒማ

አምፒር፣ ጊዎንና ዋቢ ሸበሌ ሆቴል እና ማዘጋጃ ቤት ቦንብ ፈንድቶ ነበር። እነዚህን እነማን

እንዳደረጉትም እናውቃቸዋለን። ይኼ ‹‹የኢትዮጵያዊ ስሜት አለበት፤ የለበትም›› ብለን

እንደው በሙሉ ልብ ለመናገር እንችላለን። እኔም እንደምገምተው ይመስለኛል። ክርክሩ

‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ የፀረ-ሽብተኝነት ሕግ ‹ትክክል ነው አይደለም?› እኛ ኢትዮጵያውያን

በእውነቱ የሽብር ታሪክና ባህል አለን ወይ?›› ነው። በዙሪያችን የሽብር ባህል ባላቸው ሀገራት

ተከብበናል። ያ ግን እኛን ሽብርተኞች አያደርገንም - በጭራሽ።

ከዚህ ጋር በተያያዘም፣ ጠ/ሚ/ር መለስ ሕጉን ቃል በቃል ከአሜሪካና ከእንግሊዝ መገልበጡን

ተናግረዋል። አንድ ሕግ ወይም አዋጅ ሲወጣ የሀገሪቷን ነባራዊ ሁኔታ ማገናዘብ አይገባውም?

ቃል በቃል ቀድቶ መገልበጥስ ትክክል ነው ይላሉ?

እሱን እኮ ነው የምልህ! ከዚያ ነው የመጣው ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ የሌሎቹን ችግር…

እንደዚሁ ነው የምናደርገው። በደርግ ጊዜም አንዴ ኮሎኔል መንግስቱ ባለበት ስብሰባ

ላይ የተናገርኩት ነገር ነበር። የምናደርገው ችግርን ከመፅሀፈ ውስጥ እንፈልጋለን፡፡

ለምሳሌ፣ ያን ጊዜ ‹‹ብሔረሰብ›› የተባለው ቃል ተፈጥሮ ነበር። ከመፅሀፍ ‹‹ብሔረሰብ››

የሚለውን ቃል አውጥተን፣ የኢትዮጵያ ችግር አድርገን፣ እንደገናም ከመፅሀፉ ውስጥ

መፍትሄ እንፈልግለታለን። የኢትዮጵያ ሕዝብ ችግር ምን እንደሆነ እሱን ራሱን

እየጠየቁ በመረዳትና ለእዛ መፍትሄ ከማግኘት ፈንታ ከዚህ መፅሀፍ አንድ ችግር

አውጥተን ከሌላ መፅሀፍ ደግሞ የዛን ችግር መፍትሄ እያመጣን የኢትዮጵያን

ሁኔታ ለማሻሻል እንፈልጋለን። ይኼ ግን አይቻልም። ከራሳችን መነሳት

አለብን። እኛው ማሰብ አለብን!። ጠ/ሚ/ሩ ከዛ ነው የገለበጥነው የሚሉት

ነገር… ‹‹መገልበጥ›› ማለት ምን ማለት ነው? እኛ እናስብም? የራሳችንን

ችግር መረዳት አንችልም? የራሳችንን ችግር ለይተን ባህላችንንና የሞራል

ችሎታችንን መመርምርና ማወቅ አንችልም? ይኼ ነገር እነሱ ሀገራቸውም

ውስጥ አለ። ለምሳሌ፣ በቅርቡ ኖርዌይ አንድ ሰው 70 ያህል ወጣቶችን

በጥይት አርከፍክፎ በመጨፍጨፍ ገድሏቸው ነበር። እኛ ሀገር ይኼንን

አይነት በሽታ አለ እንዴ?! የለም። በአሜሪካ አላባማ ግዛት እንደዚሁ

ቦንብ አፈንድቶ ብዙ ሰዎችን ገድሏል። ጠበንጃ ይዘው ወጥተው መንገድ

ላይ ያገኙትን ሰዎች በሙሉ ይጨፈጭፋሉ። በዚህ አይነት በሽታ

የምንጠቃ ሕዝቦች አይደለንም። ግን ሌላ በሽታ የለብንም ማለት

አይደለም። የራሳችን በሽታ አለን። ያንን ለማዳን መሞከር ነው

እንጂ የሌለብን በሽታ ለምን ይሰጡናል።

በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 14፣ 16፣17፣18፣19፣20 እና 29

የዜጎችን ሰብዓዊ መብትና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መደንገጋቸው

ይታወቃል። በዚህም መሠረት ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የመናገር፣

ኃሳብን በነፃ የመግለፅ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ፣ መንግስትን

የመቃወም፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች መስርቶ የመንቀሳቀስ፣

የዋስትና፣ የዳኞች ነፃነት መብት፣ ሰዎች ከታሰሩም በኋላ

በወዳጅ ዘመድ የመጎብኘት… ወዘተ መብቶች አሉ፡፡ ሆኖም

እነዚህን ሁሉ ሊሸረሽር የሚችል የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ

መውጣቱን የሚገልፁ ወገኖች አሉ። ምን ሀሳብ አለዎት?

ከላይ እንደገለፅኩልህ ነው። ይኼ በአሜሪካንም ቢሆን በብዙ

ሰዎች ዘንድ እንደዚሁ አይነት ከሕገ-መንግስቱ ጋር የሰብዓዊ

መብቶችን ‹‹ይቃረናል፤ መብቶችንም አጥብቧል›› የሚል

ክርክር አስነስቷል። በአሜሪካ ክርክሩ አሁንም እየተካሄደ

ነው። በእኛም ሀገር የሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 29 ይመስለኛል

መረጃን እንደፈለክ፣ በፈለከው አይነት ለመቀባበል መብት

ይሰጥሃል። ግን እንደምናየው በኢንተርኔት በምናምን

ያለን የታፈነ ሁኔታ በዚህ ሀገር አለ። ይኼ ስታትስቲክሱን

የሚያሳይ ነው። በአፍሪካ በቅርብ ካሉን ጎረቤት ሀገራት ጋር

ስንወዳደር ለምሳሌ በኬንያ፣ ሞባይል ስልክ ከ1000 ሰዎች

መካከል 500 ያህሉ አላቸው፡፡ በዚህ ሶማሊያና ጅቡቲም

ይበልጡናል። ለምን እንደዚህ ሆነ? ሶማሊያና ጅቡቲ እንዴት

ይበልጡናል? የኢንተርኔት አጠቃቀምንም ከወሰድክ እንደዚሁ ነው፡፡

ያለነው ታች ላይ ነው፡፡ ለምን እንደዚህ ይሆናል፡፡ ይኼ ሁሉ የመታፈን

ሁኔታ እያለ ያንን ሕገ-መንግስቱን ጠቅሶ ‹‹ይኼ ተሻረ… ይኼ ተሻረ››

ማለት እንደው መመፃደቅ ይመስለኛል። ሕገ-መንግስቱ በተለይ በንግግርና

በመፅሀፍ መብት በኩል አንዱ ግልፅ የሆነው ነገር ጠ/ሚ/ሩ ‹‹ማስረጃ

አለን፤ ሰብስበናል›› በማለት ተናግሯል። እንዴ! ያ ማስረጃ ሳይሰበሰብ

ሰዎቹ ለምን ታሰሩ? ሰዎቹን አስሮ ነው ማስረጃ የሚሰበሰበው? ወይስ

መጀመሪያ ማስረጃ ተሰብስቦ ነው ሰዎቹ የሚታሰሩት? ይሄ እኮ በቂ ነው፤

በግልፅ ይታያል። …በእርግጥ ለሽብር የተዘጋጁና ለሽብር የሚዘጋጅ

ሰዎች ካሉ ይኼንን ማን ይፈልጋል? እነዚህን ወንጀለኞች አይያዙ

ብሎ ማን ይከራከራል? ለምን? ..ግን እንደው በጭራሽ [ተግባሩ]

በመንፈሳቸውና በእንደዚህ አይነት ነገር በምንም የማይጠረጠሩ

ሰዎችን ከያዙ በኋላ ‹‹እንመረምራለን፣ ማስረጃ እናሰባስባለን፣

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 191 ቅዳሜ ጥቅምት 18/ 2004

እንዲሁም እንፈልጋለን›› ማለት በሕግ መቀለድ

ነው።

በኢትዮጵያ የፀረ-ሽብርተኝነት ሕግ በትርጓሜ

ደረጃ ሰፊና የተለጠጠ ከመሆኑ ባለፈ እንደወንጀል

የሚቆጥራቸው ከ16-23 የሚሆኑ የሕግ መንግስቱ

አንቀጾችን ጋር የሚጋጭና ‹‹ሽብርተኝነት›› ብሎ

የሚወነጅላቸው ድርጊቶች ግልፅነት የሚጎድላቸው

(vague) መሆናቸው ይገለፃል። እንዲሁም፣

‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ሕጉ የወጣው ለሀገሪቷ በከፍተኛ

ደረጃ ግልፅና ድርስ ወይም (clear and present

danger) የሆነ የሚያሰጋ የሽብርተኝነት ተግባር

በሌለበት ሁኔታ ነው›› እየተባለ ነው። ይኼንን

ከዜጎችን ሰብዓዊ መብቶችና ከፖለቲካ ምህዳር

ማጥበብ አንጻር እንዴት ያዩታል?

እኔ ይኼንን ከዚያ በላይ ነው የማየው። ‹‹ሰብዓዊ

መብቶች›› የሚባሉ ነገሮችን ለብዙ ዓመታት በዚህ

ሀገር አይቻለሁ። ይኼን ያህል የሚነሳ አይደለም።

እኔን በጣም የሚያሰጋኝ ‹‹ሽብርተኛ›› እና ‹‹ሽብር››

የሚባለው ነገር እንዲህ.. እንዲህ እየተባለ ሲነገርና

እያሰፋነው ስንሄድ ሕዝቡን ነገሩን እንዳናስተምረው

ነው። በፀረ-ሽብርተኝነት ሕግና ሰበብ ሽብርተኝነትን

እያስተማርን ነው ወይ? ይኼ ነገር ያሳዝነኛል::

ለወደፊትም ያሰጋኛል፡፡

መንግስት እያንዳንዱን ጥቃቅን ድርጊት ሁሉ

‹‹ሽብርተኝነት›› ብሎ ከተረጎመው በዚህ ሁኔታ

በአሁን ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ ምን አይነት

የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማድረግ ይቻላል? ሲሉ

በጭንቀት የሚጠይቁ ወገኖች አሉ፡፡ በዚህ ላይ ምን

ይላሉ?

የፖለቲካ ትግሉ የተለያየ ፈርጅ ነው። በእርግጥ አንድ

ነገር ማለት እፈልጋለሁ፡፡ አንዳንዴ ጊዜ የሚታዩ

ነገሮች ስላሉ የፖለቲካ ድርጅቶችና ተቀናቃኝ ቡድኖች

ግልፅ ማድረግ አለባቸው፡፡ ‹‹ትግላችን በሠላም

የሆነ እንደሆነ “መልካም”፣ በሠላም ካልሆነ ደግሞ

“እንዴ!? ምናምን” የሚባል ነገር አለ። ሌላ መንገድ

የለም። ለፖለቲካ ትግል ከሠላም ውጪ ሌላ መንገድ

የለም። በዚህም ‹‹በሰላማዊ ትግል ሄደን እናሸንፋለን።

እየገደሉን እንታገላለን። እየደበደቡን እንታገላለን።

እያሰሩን እንታገላለን›› የሚሉ የፖለቲካ ቡድኖች

መነሳትና በግልፅ ይኼንን መናገር አለባቸው።

…‹‹ይኼ የአመራሩ አገዛዝ ልክ አይደለም፤

እንቃወመዋለን። የምንቃመው በሰላማዊ መንገድ

እንጂ ሌላ መንገድ የለንም። ሊገድለን ሲዘጋጅና

ሲገድለንም እንሞትለታለን።›› መባል አለበት፡

፡ ይኼንን በአረቡ ዓለም እያየን አይደለም እንዴ?

ለመሞት መዘጋጀት የሚያቅተው ሰው መግደልን ማን

ያስተምረዋል? መታሰርም ያው ነው። ግን ጥፋቱ

ቆይቶ በማንም ላይ ይደርሳል ነው፡፡ ዛሬ [ቃለምልልሱ

የተደረገው ከትናንት በስትያ ነበር] በአርጀንቲና 12

የጦር ኃይሉ መኮንኖች የዛሬ 30 ዓመት በፈፀሙት

ወንጀል ዕድሜ ልክ ተርዶባቸዋል፡፡ በግብፅ ሁለት

ፖሊሶች ባለፈው ጊዜ አንድ ወጣት ገድለው

ተፈርዶባቸው ነበር። ማምለጥ አይቻልም። በአሁኑ

ጊዜ የዓለም ማሕበረሰብና ዓለም አቀፋዊ ህሊና፤

እንዲሁም ሰዎች መሸሽና ማምለጥ የማይችሉበት

ሁኔታ እየተፈጠረ ነው። ስለዚህ ልናድግና ልንሻሻል

የምንችለው በወንጀል፣ በጠብና በዱላ አይደለም

- በክርክር እንጂ። እንከራከር በቃላትም እንዋጋ

የፖለቲካ ትግል ማለት ያ ነው። ያንን እንልመደው፡፡

‹‹የፖለቲካ ፓርቲዎች ሳያወላውሉ የፖለቲካ ትግልን

መስመር ለመያዝ መታገል አለባቸው›› እላለሁ።

በአንፃሩ በአገዛዙ በኩል ጡንቻና ጉልበት አላቸው።

‹‹በዚህ በጉልበታችን እየተጠቀምን እንገድላለን፣

እናስራለን፣ እንደበድባለን፣ እናስፈራራለን›› ቢሉ

ሽብር ይኼ ነው። ‹‹ያንን ሽብር ደግሞ እኛም

ሳንፈራ እንቀበላለን›› ብሎ ቆርጦ በመንፈሳዊ ኃይል

ለመዋጋት መዘጋጀት ያስፈልጋል።

በአዋጁ መሠረት ፖሊስ ያለምንም የፍ/ቤት ትዕዛዝ

ተጠርጣሪዎችን ማስር የሚችልበት ሁኔታ አለ፡

፡ ካሰረም በኋላ መረጃ ለመሰብሰብ እስከ አራት

ወር ጊዜ ድረስ መጠቀም እንደሚችል ሰፊ መብት

ተሰጥቶታል። በሕገ-መንግስቱ መሠረት ደግሞ

አንድ ሰው በ48 ሰዓታት ውስጥ ፍ/ቤት መቅረብ

አለበት ይላል። ከዚህ አንጻር አንደኛው ህግ መሻሻል

የለበትም ይላሉ፤ወይም ህገመንግስቱ? ወይም

የጸረሽብር ህጉ?

ሕገ-መንግስቱ እነሱ ሲፈልጉ የሚጠቅሱት ነገርና

ሲፈልጉም አንተን ለማጥቂያ የሚጠቀሙበት

መሳሪያ እንጂ ለዜጎች መከላከያና ከለላ እንዲሆን

ማድረግ አልቻሉም። ከላይ እንደተናገርኩት፣ አሁን

ባለንበት ጊዜ አንድን ሰው ይዘኸው መረጃና ማስረጃ

መሰብሰብ ልክ አይደለም። ይኼ እንኳን ኢትዮጵያ

ውስጥ ቀርቶ በዚህ የሽብረተኝነት ጉዳይ በአሜሪካም

እየተደረገ ነው፡፡ ለእነሱ የአሜሪካ ማድረጉ ትልቅ

መስክርነት ነው። …መነሻው ‹‹እኛ ከእነሱ ልንሻል

አንችልም›› ነው። ለምን ልንችል አንችልም?

[እየሳቁ] እነሱ ከተሳሳቱ እኛም መሳሳት አለብን? -

ያውም በታሪክና በባህላችን፤ በማናውቀውና በፍፁም

በሌለብን በሽታ። አሁን መሸሸጊያና መከራከሪያችን

ሕገ-መንግስቱ ብቻ አይደለም፡- የታሪክ፣ የባህላችንና

መንፈሳዊ መሠረታችን ጭምር እንጂ።

የፀረ-ሽብርተኝነት ሕግን በርካታ አገሮች አውጥተዋል።

ለምሳሌ፣ በአፍሪካ ኬኒያንና ናይጄሪያን ብንወስድ ሕጉ

በሰላማዊ መንገድ በሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች

ላይ ተፅዕኖ ሲፈጥር አይታይም። በኢትዮጵያ ግን

ተፅዕኖ እየፈጠረ እንደሚገኝ በተደጋጋሚ ይገለፃል።

የእኛን አዋጅ ከሌሎቹ ጋር እንዴት ያነፃፅሩታል?

በአፍሪካ ብዙ ሀገሮች …ሩቅም ሳንሄድ እዚሁ

ጎረቤታችን ያሉትን እንመልከት፡፡ ለምሳሌ፣ ኬንያ

ከእኛ የበለጠ በሽብርተኞች ተጠቅተዋል፡፡ አሁንም

እየተጠቁ ነው። ነገር ግን፣ በተቻላቸው መጠን

ወጣና ጥልቅ ብለው ሳይገቡበትም ከአሜካኖችና

ምዕራባውያን ጋር በአጠቃላይ ያላቸው ግንኙነት

እንደኛ አይደለም። እኛ ጥልቅ ብለን ነው የገባንበት

-ለምሳሌ በሶማሊያ ስንገባ፡፡ ከዛም በኋላ አሁን

እንደምትለው በሕጉ ላይ የምናሳየው ጠንካራነትና

ኃይለኛነት፡፡ …ሁለት የስዊድናውያን ጋዜጠኞችን

ያለፍቃድ ወደ ሀገር ውስጥ ገብተዋል ተብሎ ይህ

ሁሉ ነገር…እኔ እንደዛ ናቸው ብዬ ለመገመት

ያስቸግረኛል። ምዕራባዊያኖቹ ቀደም ሲል

ለህወሃትም ሲያዝኑ ነበር። ለሻዕቢያም ሲያዝኑና

ሲረዱ ነበር። አሁን እንደዚህ አይነት ነገር እያደረጉ

ይሆናል። ይተዋወቃሉ። ይኼ ይመስለኛል። ነገር

ግን፣ እኛ ከአፍሪካኖች፣ ከአሜሪካኖች፣ ከእንግሊዞች

ጋር የተለያየን ነን። በሽብር በፍፁም ከእነሱ ጋር

አንወዳደርም - ታሪካችንን እንዲህ በትንሹ ያየው

ሰው እንደዚህ አይነት ነገር የለብንም። ይኼ የእኛ

በሽታ አይደለም። ‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብ ነኩኝ፤

መብቴን ነጠቁኝ›› ብሎ ከዛ ካጠቃው ባለጋራው

ጋራ ይጣላል። ነገር ግን፣ ለምሳሌ በሌላ ወንጀልም

ቢሆን የሴቶችን አይን ማውጣትና በአሲድ

ማቃጠል የመሳሰሉ አዲስ በሽታ ሆነው እዚህ ሀገር

መጥተዋል። እንደዚህ አይነት ነገር ነው ሕዝቡን

የምናስተምረው፡፡

‹‹የፀረ ሽብርተኝነት አዋጁ አያስፈልግም፤ ለመሰል

ወንጀለኞች የኢትዮጵያ የወንጀልኛ መቅጫ ሕግ

በቂ ነበር›› የሚሉ ፖለቲከኞች አሉ። በእርስዎ

እምነት የአዋጁ መውጣት ተገቢ ነው?

ለእኔ ሕግ ሲወጣ ችግሩ መጀመሪያ መኖር አለበት።

ያ ሕግ ያስፈልገበት ምክንያት መኖር አለበት።

እኛ ሀገር ‹‹ሽብር›› ከምን ተነስተን ነው? ከላይ

የገለፅኳቸው አንዳንድ የዛሬ ስንት ዓመት አንድ..

ሦስት.. አራት ቦታ የተጣሉ ቦምቦችን ይዘን ነው

ኢትዮጵያ ውስጥ ሽብር አለ ብለን የምንነሳው? ወይስ

ምን ችግር አለ ብለን? እዚህ ስንት ችግር ያለበት

ነው። ለምሳሌ፣ ለችጋርና ችጋርን ለማስወገድ ለምን

እውነተኛና ደንበኛ ሕግ አይወጣም? ሽብርተኝነት

የለብንም በሽታችን አይደለም። በሽታችን ካልሆነ

ለምን ሕግ እናወጣለታለን? አስፈላጊ አይደለም።

‹‹በኢትዮጵያ ውስጥ ሽብር ሳይኖር እንዳለ አድርገን

የምንናገር ከሆነ እውነተኛ ሽብርተኝነት ሊፈጠር

ይችላል›› እያሉኝ ነው?

አዎን፤ አዎን! ‹‹እንዲህ ነው.. እንዲህ ማድረግ…

እንዲህ ማድረግ›› እያልክ በተናገርክ ቁጥር

ማስተማር እኮ ነው።

በዓለም ላይ መንግስታዊ ሽብርተኝነት መኖሩ

ይነገራል። ህወሓትም በትጥቅ ትግሉ ወቅት

የሽብር ድርጊት ይፈፅም እንደነበረ ተገልጾ በዓለም

የሽብርተኝነት ዝርዝር ውስጥ መካተቱን መረጃዎች

ያስረዳሉ። ይኼ አሁን መንግስት ከያዘው አቋም

ጋር አይጣረስም?

ህወሓት ጫካ በነበረበት ጊዜ ያለ ምንም ጥርጥር

ሽብርተኝነትን ፈፅሟል። ጠ/ሚ/ሩ እኮ በአደባባይ

በቴሌቭዥን ባንክ እንደዘረፉ እኮ ነግረውናል። ይኼ

ሽብርተኝነት አይደለም? [እየሳቁ] ይኼ ሽብርተኝነት

ከሚባሉ ነገሮች ውስጥ አንዱ ነው። ግን ከዛ በኋላ

መንግስት ሆነዋል። መልካም! መንግስት ከሆኑ

በኋላ ሌሎች ድርጅቶች ድሮ እነሱ በነበሩበት በትጥቅ

ትግል ‹‹እንታገላለን፤ ስልጣን እንይዛለን›› የሚሉ

ድርጅቶችን ለመቋቋም እነሱ በትጥቅ ትግል በኩል

ስላለፉ ምን ምን እንደሚያስፈልግና ሽብርተኝነትም

እንደሚያስፈልግ ያውቃሉ። ስለዚህ በእነዛ በትጥቅ

ትግል በተዘጋጁት ድርጅቶች ላይ ‹‹እነዚህን ድሮ

ስናደርግ እንደነበረው ያደርጋሉና እናግዳቸው፣

እናፍናቸው፣ እኛም ያደረግነውን እንዳያደርጉ

እናድርጋቸው›› የሚል ስሜት ሊያደርባቸው

ይችላል። ነገር ግን፣ ‹‹በፖለቲካ ትግል ሕጋዊ በሆነ

መንገድ እንታገላለን›› የሚሉትን የፖለቲካ ቡድኖች

እዚህ ውስጥ ማስገባት ተገቢ አይደለም። እንግዲህ

ልዩነቱ ይኼ ነው። በትጥቅ ትግል የሚሄዱትንና

እንሄዳለን የሚሉትን በዚሁ በሽብርተኝነት መክሰስና

መወንጀል ምናልባት ያስኬድ ይሆናል። ግን ‹‹እነዛም

ተቀናቃኝ የፖለቲካ ቡድኖች ናቸው›› ብሎ በትጥቅ

ትግል ያሉትን የፖለቲካ ቡድኖች በሰላማዊ ትግል

ውስጥ ካሉት የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር አንድ

አድርጎ ማየትና መወንጀል በፍፁም የሚያስኬድ

አይደለም። የፖለቲካ ፓርቲዎቹም ‹‹በፖለቲካ

ትግል ነው የምንሄደው፤ በሕጋዊ ስርዓት ነው

የምንታገለው›› ብለው የቆዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች

ይኼንን ግልፅ አድርገው ማሳየት አለባቸው።

ነገር ግን፣ በወላዋይነት አንድ እግራቸውን እዚህ

አንደኛውን ደግሞ እዚያ አንፈራጥጠው የሚሄዱ

ከሆነ ያም አያስኬድም፤ ልክ አይደሉም።

መንግስት ‹‹ሽብርተኛ›› ብሎ የፈጃቸውን የፖለቲካ

ቡድኖች ከኤርትራ መንግስት ጋር ተባብረው

እንደሚሰሩ በተደጋጋሚ ውንጀላውን ያቀርባል፡

፡ የኤርትራን መንግስት ግን ‹‹ሽብርተኛ›› ብሎ

አልፈረጀም። የዚህ አንደምታው ምንድን ነው?

ወንጅሏል እንጂ! ኤርትራን ‹‹የአሸባሪዎች ረዳት

ነች›› ብሏል። በተጨማሪም፣ በአሜሪካና በተባበሩት

መንግስታትም ይኸው ፍዳቸውን እያሳያቸው

ነው። ለእኔም ሆነ ለማንም ሰው ግልፅ የሆነው

አንድም ቦታ ኤርትራ በአሻባሪነት የሚፈርጅበት

ሁኔታ አይታየኝም። የኢትዮጵያ አገዛዝ የኤርትራ

መንግስት ተቀናቃኞችን ይረዳል፤ ያግዛል።

እዚህ እየመጡ ስብሰባ ያደርጉ የለም እንዴ?!

ኤርትራ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስት ተቀናቃኝ

ቡድኖችን ይረዳል። ይኼ አንዱ አንዱን ለመጥለፍ

የሚያደርገው ጥረት እንዴት አድርጎ ‹‹ሽብርተኛ››

እንደሚሆን አላውቅም - ለእኔ።

በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔን መስርተው

በአመራርነት ለረዥም ዓመታት መስራትዎ

ይታወቃል። የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ

እንዴት ያዩታል?

ኢሰመጉ አሁን የለም፤ ጠፍቷል፡፡ ከስሟል

እንዲከስምም አድርገውታል። ስለዚህ የኢትዮጵያ

እሳቸው ሲናገሩ አቃቤ ሕጎች፣ ዳኞችና

ፖሊሶች ይኼንን ተከትለው ሌላ ነገር

ያደርጋሉ ብለው እንኳን አያስቡም። …

ለምሳሌ፣ ከዚህ በፊት እኛ በ1998 ዓ.ም

ልንታሰር ስንል ጥፋታችንን ከነፍርዱ ነበር

የሚናገሩት። ‹‹እንደዚህ አድርገዋል፣

እንደዚህ አጥፍተዋል፣ ይኼንን ያህል

ይፈረድባቸው። እስከ ዕድሜ ልክ

ሊፈረድባቸው ይችላል›› ብለው ነበር።

ዕድሜ ልክም ፈረዱብን።

ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሚባለው ተቋቁሟል። እሱ

ደግሞ ስለ ሰብዓዊ መብቶች ሲናገር አንሰማም። ይኼ

ነው ያለንበት ሁኔታ።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን ለማቋቋም

ለምን የተፈለገ ይመስልዎታል?

ደህና… የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በሌሎች ሀገሮች

አለ። መጥፎው ነገር እሱ መቋቋሙ ሳይሆን የሲቪል

ማሕበረሰቡን እና በግል በራሳቸው የሚያቋቁሙትን

የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶችን ማጥፋቱ ነው።

የራሳቸውን ማቋቋማቸው መጥፎ አይደለም።

በቅርቡ የኮሚሽኑን ኮሚሽነር አምባሳደር ጥሩነህ

ዜናን አነጋግረናቸው ነበር። ኮሚሽነሩ በሽብርተኝነትን

ተጠርጥረው በመጀመሪያ የታሰሩ ጋዜጠኞችን

መኖራቸውን ለሶስት ወራት ያህል አያውቁም ነበር።

ይኼ ተገቢ ነው?

[እየሳቁ] …ይኼንን እንዲከታተሉ አይደለም እኮ

የተቋቋሙት፤ ለምን ይወቁት¡ [ከልባቸው እየሳቁ]

የኢትዮጵያ ሕዝብስ በትክክል ሰብዓዊ መብቱን

ያውቃል? አውቆስ መብቱን ለማስከበር ምን ያህል

ዝግጁ ነው?

መብቱን በደንብ ያውቃል። የኢትዮጵያ ሕዝብ

በሕግ በኩል ምንም የሚጎድለው አይደለም። ድሮ

የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያውቁትን የአንተ ትውልድ

ያልደረሱበትን ነገር አለ። ሕዝቡ ስለ ሕግና ፍትሕ

በደንብ ያውቃል። ማንም መንገደኛ ሰው ዳኛ ነው፡

፡ ምስክር ነው፡፡ ፓሊስ ነው። አንድ ሰው ሲጠቃ

ዝም ብሎ አይሄድም። ቆሞ በነገሩ ውስጥ ገብቶ፣

የሚያዘውን ይዞ ዳኛ ጋር ወስዶ ይሄዳል። አስፈላጊም

ሲሆን የተጣሉትን ሰዎች ኩታና ኩታቸውን ቋጥሮና

አስፈፅሞ ምንም ሳታደርጉ ዳኛ ጋር እንድትሄዱ

ብሎ ዳኛ ጋር ይልካቸዋል። ሰዎቹም በቀጥታ እዛ

ዳኛ ጋር ይሄዳሉ። እንደዚህ አይነት ሕጋዊ ስርዓት

ያለው ሕዝቡ የትም የለም፡፡ ዛሬ ሰው ቢደባደብና

ቢጋደል ማንም ዞር ብሎ የሚያይ የለም፡፡ ቆሞ ግን

ይመለከታል። የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደዚህ አይደለም፡፡

ጥቃት ሲፈፀም ዝም ብሎ አያይም። በጦርነትም ጊዜ

ወታደሩ እሱ ነው። ተነስ ሲባል ተነስቶ ይዘምታል

- በራሱ መሳሪያ፡፡ ስለዚህ መብቱን እንዳይጠቀም

ያደረገው ስርዓቱ ነው?

በአሁን ወቅት የተቃዋሚ ፓርቲዎች መዳከማቸው

ይታያል። በእርስ በርሱ ሽኩቻ ህልውናቸው አደጋ

ላይ የወደቁም አሉ። በዚህ ሂደት ኢህአዴግ ለረዥም

ዓመት ኢትዮጵያን ከመምራት ምን ያግደዋል?

አዎን። ችግር አለ፤ ግልፅ ነው። ቢፈራርሱም እኔ

ለራሴ አላለቅስም። በራሳቸው ችግር ነው። ከአሁን

ወዲያ እውነተኛና ደንበኛ የፖለቲካ ፓርቲዎች

ቢቋቋሙ ከሕዝቡ የሚነሱ ለስልጣን የቋመጡ

ጥቂት ሰዎችን ስብስበው ወይም የፓርላማ ደመወዝ

እየበሉ ለመኖር የሚፈልጉ ሰዎች የሚያቋቁሙት

ፓርቲ ሳይሆን እውነተኛ ትግል ውስጥ መግባት

የሚፈልጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሕዝብ ጋር ሆነው

የሕዝቡን ብሶት/ ሮሮ/ ችግሮች የሚያንፀባርቁ ሰዎች

የሚኖሩበትና የሚመሩት ፓርቲ መምጣት አለበት።

እርግጠኛ ነኝ ይመጣል›› ነገም ከነገ ወዲያም ቀስ

ብሎ እንደዚህ አይነት ፓርቲ ይፈጠራል።

ባሳለፍነው ሳምንት ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ በፓርላማ

ከሽብርተኝነት ጋር በተገናኘ ቁጣ አዘልና ማስጠንቀቂያ

የተቀላቀለበት ንግግሮችን ለተቃዋሚዎችና

ለጋዜጠኞች መናገራቸው ይታወሳል። ይኼንን

እንዴት ተመለከቱት?

አቶ መለስ ማስፈራራታቸው አዲስ ነገር ነው እንዴ?

ሁልጊዜ ይሳደባሉ፣ ያስፈራራሉ፣ እንደልባቸው

ይናገራሉ፡፡ ሌላው ቀርቶ እሳቸው ሲናገሩ አቃቤ

ሕጎች፣ ዳኞችና ፖሊሶች ይኼንን ተከትለው ሌላ ነገር

ያደርጋሉ ብለው እንኳን አያስቡም። …ለምሳሌ፣

ከዚህ በፊት እኛ በ1998 ዓ.ም ልንታሰር ስንል

ጥፋታችንን ከነፍርዱ ነበር የሚናገሩት። ‹‹እንደዚህ

አድርገዋል፣ እንደዚህ አጥፍተዋል፣ ይኼንን ያህል

ይፈረድባቸው። እስከ ዕድሜ ልክ ሊፈረድባቸው

ይችላል›› ብለው ነበር። ዕድሜ ልክም ፈረዱብን።

ይኼ የሚያደርጉት ነው። ‹‹ማስረጃ አለን፤

እየሰበሰብን ነው›› ማለት ምን ማለት ነው? ሕጋዊ

ለሆነ ሰውና ሕጋዊ ስርዓትን ለሚመራ ሰው ይኼ

በፍፁም የሚያስኬድ አባባል አይደለም። ምርመራው

ተደርጎ፣ መረጃዎች ተሰብስበው፣ ማስረጃ ሁሉ

ተዘጋጅቶ ነው ክስ የሚመሰረተው። ንፁውን ሰውዬ

ይዞና አስሮ ብዙ መረጃ ለመሰብሰብ መሯሯጥ

ተገቢ አይደለም። ታስረው ያሉ የሚሰቃዩ ሰዎች፣

ጋዜጠኛችና አንዳንዶቹም የእኛ ጓደኞች በደንብ

የማውቃቸው ሰዎች አሉ። ደበበ እሸቱ በምንም በኩል

በደንብ አውቀዋለሁ። ቃሊቲም አብረን ነበርን። ከዛም

በኋላ እንነጋገራለን፤ እንወያያለን። እንደዚህ አይነት

ነገር በጭራሽ መንፈስ የለም፡፡ ይች ርዕዮትም

የምትባል ልጅ ጥሩ ፀሀፊና ጥሩ ችሎታ ያላት ነች።

ግን እንዴት አድርገው እዚህ ውስጥ እንዳስገቧትና

እንደገባች እኔ አላውቀውም። እስክንድር ነጋም ፊት

ለፊት የሚናገር ሰው ነው። ኃይለኛ ፀሀፊ ነው።

እንደዚሁ እስር ቤት ሲገባና ሲወጣ 20 ዓመቱ ነው።

ስለዚህ መቻቻል አለብን። ሽብርን በምንም አይነት

መንገድ ልንጠራውና ልንለምደው የሚገባን ነገር

አይደለም። ይኼ ሁሉ ጎረምሳ እዚህ ሀገር ጦሙን

እያደረ በሰላም ይሄዳል። አጠገባችንና ጎረቤታችን

ያሉት ሀገራት እኮ እንደዚህ አይደሉም። ይኼንን

መንፈሳዊ መሠረታችንን ይዘነው ብንቆይ? በተለይ

ወጣቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይኼንን ነገር እንዳይማር

ብናደርግ የተሻለ ይመስለኛል።

አቶ መለስ በተደጋጋሚ ‹‹ይኼ የመጨረሻ የስልጣን

ዘመኔ ነው›› ብለዋል። እንዳሉት ቃላቸውን ጠብቀው

ከስልጣን ቢወርዱ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ

ሊለወጥ ይችላል ብለው በሚገምቱ ወገኖች አሉ፡

፡ ይስማማሉ?

በመጀመሪያ እስኪ እሳቸው በምርጫ ተሸንፈውም

ይሁን ከውስጣቸው ለአንዱ የተሻለ ሰው አግኝተው

ስልጣን አስረክበው መደማመጥ የሚቻልበት ሁኔታ

ከተፈጠረ ጥሩ ነው። ላለፉት 20 ዓመታት እኮ

መደማመጥ የለም። አንድ አቅጣጫ ብቻ ነው።

አቶ መለስ ይናገራሉ፤ ከላይ እንካችሁ ይላሉ።

ከእኛ በኩል፣ ከሌላው ከሕዝቡ፣ ከጋዜጣውና ከሌላ

የሚመጣውን ነገር ሰምቶ፣ አዳምጦና አብላልቶ

ለዚያ ተገቢ መልስ የሚሰጥበት ሁኔታ የለም። ‹‹እኔ

ልንገራችሁ እናንተ ስሙኝ። እኔ ትዕዛዝ ልስጣችሁ

እናንተ ፈፅሙ ነው›› ያለው።

በአሁኑ ወቅት ኑሮ በከፍተኛ ሁኔታ እየተወደደ

መጥቷል። የምግብ ዋጋ ግሽበቱም 51.3 በመቶ

ደርሷል። መንግስት ደግሞ ይኼንን የዕድገት አንዱ

ምልክት ነው ይለዋል። በከተማ ውስጥ ሰው በረሃብ

እየሞተ ባለበት ሁኔታ ግሽበት እንዴት የዕድገት

ምልክት ሊሆን ይችላል? ብለው የሚጠይቁ ወገኖች

ተበራክተዋል፡፡ ምን አስተያየት አለዎት?

ስለዚህ በመንግስትም በሌላም ያሉ ኢኮኖሚስቶች

ይናገሩ። …ድሮ ገና በአፄ ኃይለስላሴ ጊዜ በአዋሽ

ተፋሰስ ላይ ባለስልጣን በሚቋቋምበት ጊዜ እድገትን

አስመልክቶ አንድ ፅሁፍ ፅፌ ነበር። በአዋሽ ተፋሰስ

ላይ የወንጂ ስኳር ፋብሪካን ለማቋቋም በእዛ ያሉትን

ከብት አርቢዎችና ዘላኖች ወደ ደረቁ ቦታ ገፍተዋቸው

ለሙን መሬት በሙሉ ለወንጂ ስኳር ፋብሪካ ሸንኮራ

አገዳ ማምረቻ ሰጧቸው። ያን ጊዜ የፃፍኩት ነገር

‹‹ምንድን ነው ዕድገት?›› የሚል ነበር። ለእነዚህ

ለተገፉት ሰዎች ለአፋሮችና ለጂሌ ኦሮሞዎች ዕድገት

ምን ማለት ነው? ሌሎች ሰዎች መጥተው ቤት

ሰርተው፣ ሸንኮራ አገዳ ተክለውና ፋብሪካ አቋቁመው

ሀብታሞች ሲሆኑ ማየትና መመልከት ነው ለእነዚህ

ሰዎች እድገት? ያ ዕድገት እነሱን ይጨምራል ወይ?

እየገፏቸው እንዴት ይጨምራቸዋል? ወደ ውጪና

ወዳልተሻለ ቦታና መሬት እየመሯቸው እንዴት

ያሻሽላቸዋል? ብዬ የዛሬ 45 ወይም 50 ዓመት ፅፌ

ነበር፡፡ አሁንም የማየው እንደዛ ነው። ትልልቅ ፎቅ

ቤቶች ተሰርተዋል። መንገዶች ተሰርተዋል። ግን

ራሳችንን እንጠይቅ አንድ ትልቅ ፎቅ ቤት ሲሰራ

ስንት ቤተሰብ መንገድ ላይ ተጥሏል? አንድ ኪሎ

ሜትር መንገድ ሲሰራ ስንት ቤተሰብ መንገድ ላይ

ተጥሏል? ለእነዛ ሰዎች ልማትና ዕድገት ይኼ

ነው? ለአንዳንዶቹ ግን ነው። እዛ ላይ ደግሞ ብዙ

የማናስበው ነገር አለ። ለጊዜው የምናየው ፎቅ ቤት

መሰራቱን ብቻ ነው። ሰሞኑን በቱርክ በመሬት

መንቀጥቀጥ በጣም በርካታ ቤቶች ድራሻቸው ነው

የጠፋው። በድንገት ዝም ብለው የተሰሩ ትልልቅ

ፎቆች ናቸው። አዋቂዎች ግና የዛሬ 50 ዓመት እዚህ

ሀገር ከአምስት ፎቅ በላይ እንዳይሰራ ተናግረዋል።

ያም መሠረቱ በደንብ ከተሰራ ነው፡፡ ዛሬ ዝም

ብለን ለጠፍ ለጠፍ አድርገን ቤቶች ዝም ተብለው

ይሰራሉ። እነዚህ የሀገር ሀብት ናቸው። እንዲቆዩልን

እንፈልጋለን። ጉዳትም እንዲያመጡም አንፈልግም።

ዕድገት ለሚባለው ነገር እነዚህ ሁሉ ነገሮች አብረው

መታየት አለባቸው፡፡

ኢትዮጵያ በድህነት ውስጥ ትገኛለች። ከእርስዎ

የረዥም ጊዜ የሕይወት ልምድ አኳያ ኢትዮጵያ

በአሁኑ ወቅት ምን ያስፈልጋታል ብለው ያስባሉ።

ለመንግስት፣ ለተቃዋሚዎችና ለሕዝቡ ምን

ይመክራሉ?

በእኛ ሀገር አንድ የጎደለው ትልቁ ነገር መነጋገር

አለመቻላችን ነው። ያለነው ተኳርፈን ነው።

የመንግስት ስልጣን ይዘናል የሚሉት፣ በተለይም

ስለሕዝቡ እናውቃለን፣ የህዝቡን ብሶትና ሮሮ

እንናገር የሚሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ጋዜጠኞችም

ሆኑ በግል ያሉ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች

መንግስት ከሚባሉት ባለስልጣናት ጋር በቅን መንፈስ

ለመነጋገርና ለመወያየት አልቻሉም። ‹‹ልንገርህ/ሽ››

ሳይሆን ‹‹እንነጋገር ወይም እንደማመጥ›› የሚባለው

ነገር ኢትዮጵያ ውስጥ ጎድሏል፡፡

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

17

18

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ሴ ት

ሴበመቅደስ

ፍስሐ

Mekdi745@gmail.com

እኩልም ነሽ፤

እኩልም አይደለሽም

እኩልነት ማለት አለመበላለጥ ነው። በእኩልነት

ስንቶችን እናምናለን? “ሴቶች ከወንዶች እኩል ነን” እንላለን።

አንዳንዴ ይሄንኑ አባባላችንን ራሳችን አባባል ሆኖ እንዲቀር

እናደርገዋለን። አንዳንዶች፣ “ሴቶች ከወንድ ‘እኩል ነን’ ብለው

ካሰቡ እኩል መሆናቸውን ማንሳት በራሱ ምን አስፈለገ?”

(ለምን ያስታውሱናል አይነት ነገር) ሲሉ አንዳንዶች ደግሞ፣

“አይሆንም፤ ሴቶች የራሳቸው ጥንካሬ እንዳላቸው ሁሉ

ከወንዶች የሚያንሱበት መንገድም አለ” ይላሉ። እናንተ በምን

ትስማሙ ይሆን? እርግጥ አንዳንዴ እኩል የማያደርጉን ሰው

ሰራሽና ተፈጥሮአዊ ነገሮች አሉ። ሰው ሰራሹ ራሳችን ሴቶቹ

የፈጠርናቸው ሲሆኑ፣ የተፈጥሮው ደግሞ በተፈጥሮ ደረጃ

በሴቶች ሊሰሩ የማይሞከሩ አንዳንድ ነገሮችን ማለቴ ነው።

አሁን ስለእኩልነት ልሰብክ አይደለም - ብዙ ተብሏልና።

ከዚህ ወጣ እንበልና፤ ወንዶች ከእኛ በምን ይበልጣሉ? እኛስ

በምን እንበልጣቸዋለን? የሚለውን ነገር አስበን እናውቅ ይሆን?

እንዲህ ነው፡- እነሱ በቀላል መንገድ የተቋቋሙት፣

እንደ ተራራ የገዘፈ ነገር ሊኖር ይችላል። እናም፣ ያን የገዘፈ

ሁነት በቀላሉ ተቋቁመውታልና ይበልጡናል። እኛ ሴቶች

ያለፍነው፣ ነገር ግን ወንዶች ከባድ አድርገው የሚወስዱት ነገር፣

ለእኛ “ኢምንት” ሆኖ እናገኘዋለን፣ ወይም ለእነሱ ተራራ ሊሆን

ይችላል። ስለዚህ እዚህ ጋር ልዩነት ሲመጣ እኩል የመሆን ነገሩ

ያከትማል ማለት ነው።

ወንዱ በሴት የሚከወነውን ስራ ሙሉ ቀን ቁጭ

ብለህ ስራ ከምትሉት ሞቱን ይመርጣል። አልወጣውም ብሎ

ስለሚያስብ ብቻም ላይሆን ይችላል። እርግጥ ነው አይወጣውም።

ቢወጣው እንኳ እሷ በተወጣችበት መንገድ ላይሆን ይችላል።

አንድን ሴት ከወንድ እኩል ሙሉውን ጊዜ የጉልበት

ሥራ ስሪ ብንላት የአቅሟ ሁኔታ የሚያስተማምን አይሆንም።

እሷም አትቀበለውም። “ኧረ እኔ ሴት ነኝ! እንዴት እችለዋለሁ?”

የሚል ጥያቄ ልታቀርብ ትችላለች። አይፈረድባትም።

አንዳንዴ ወንዶች ሀዘንን በመቋቋም (ባለማክረር)

ይበልጡናል ብዬ አስባለሁ። “ይሄማ አይሆንም። እነሱ እንደውም

አይቋቋሙም” ያሉኝ ሴቶችም አሉ።

እንደ’ኔ ግን ወንዶች ከእኛ በተሻለ ሁኔታ

ይቋቋሙታል ባይ ነኝ። አንድ ሰው ከእኛ በሞት ሲለይ ማሰብ

ባለብን መጠን ልናስበው ግድ ቢልም፣ ወንዶቹ ለለቅሶው ተብሎ

ከሚባክኑ ወጪዎች አንስቶ “ፍራሽ ዘርግቶ” በመቀመጥ ነገሩን

እየቆሰቆሱ ከማባባስ የፀዱ ናቸው።

በዚህ የማይስማሙ አንዳንዶች፣ “እንበልና ሴቷ

በባሏ ሞት ምክንያት ብቻዋን ብትቀር ሌላ ባል የማግባቷ ጉዳይ

ምናልባትም እዚያ ላይ ሊያበቃ ይችላል፤ ካላበቃ እንኳን ሌላ

የመተካቱ ነገር ይረዝማል። እንዲህ እንዲሆን ያደረገው ደግሞ

ሃዘንን መቋቋም መቻሏ ነው” ይላሉ።

ወንዱስ? ብቸኝነቱንና ሐዘኑን መቋቋም ወዲያው

ይከብደዋል። እሱ፣ ከእሷ በተቃራኒ፣ እሷን የሚያስታውሱትን

ነገሮች ከአጠገቡ አያርቅም። እሱ ግን እሷን ለመርሳት በሌላ

ሊተካት ይፈልጋል - ይተካታልም። ያ ማለት ሃዘኑ ጎድቶታል፣

ጎድቶትም እንዲቀጥል አይፈልግም ይላሉ።

ሌላው የማነሳው ደግሞ ቸኩሎ ውሳኔ በመስጠት

በኩል ሴቶች ረጋ ይላሉ ብል ማድላት አይሆንብኝም። አንድን

ነገር ከመወሰን ይልቅ ከውሳኔ በኋላ ሊኖር የሚችለውን ውጤት

(consequence) በማሰብ በኩል አንደኛ ይመስሉኛል - ሴቶች።

እንዲህ ያለ አስተሳሰብ ያላቸው ወንዶች እንዳሉ አውቃለሁ፤

ብዛታቸው የሴቶችን ያህል አይሆኑም ብዬ በማሰብ እንጂ።

ለዚያም ነው ከውሳኔያቸው በኋላ ሴቶቹን ለመመለስ ለወንዶች

ከባድ የሚሆነው።

ምናልባትም የእሷ ውሳኔ ከዚያ በኋላ ግራ ያጋባህ

ይሆናል። የማታውቃት መስሎ ሊሰማህም ይችላል። ነገር ግን

በእርግጠኝነት የምነገረህ ወደዚህ ውሳኔ ከመምጣቷ በፊት

ደጋግማ አስጠንቅቃሃለች። በዚህ ላይ አንባቢ የራሱን ግምት

ይውሰድ።

ሦስተኛውና የመጨረሻው ነጥቤስ?

አንድን ነገር እየቻልን በራስ መተማመናችን ባዶ

በመሆኑ ምክንያት ብቻ አንድን ኃላፊነት አሳልፈን ለወንድ

የምንሰጥም አለን። ይሄ የእኛ የሴቶች ድክመታችን ነው። ይሄ

የእኛ ልዩነታችን ነው።

የሚገርመው አንድ ሴት ያላትን ጥንካሬ

ተጠቅማ ለውጤት ብትበቃ “ወንድ ነሽ/ናት” የሚል አግባብነት

የሌለው ሙገሳን እንቸራታለን። ራሷን እንደ ወንድ እንድታይ

እናደርጋታለን።

እኔ እንድጽፍ የተሰጠኝ ቦታ አልቆ ተገደብኩ።

ነገር ግን አንቺስ? “እኔን ከወንድ እኩል የማያደርገኝ ተፈጥሮና

ራሴ የፈጠርኩት (ሰው ሰራሽ) ምክንያቶች አሉ” ብለሽ አታምኚ

ይሆን? አዎን። የምትበልጭበትም የምታንሽበትም፣ እንዲሁም

እኩል የሚያደርጉሽም ነጥቦች አሉ ብዬ አስባለሁ። እኩልም ነሽ

እኩልም አይደለሽም።

ከምንም ነገር በላይ ደግሞ በራስ የመተማመን

መንፈሳችን ዝቅተኛ መሆኑ አንዱ ከወንድ እኩል እንዳንሆን

የሚያደርገን መሆኑን ልናጤነው ግድ ይለናል። በቅድሚያ

ለራሳችን ያለን ግንዛቤ ከፍ ሊል ይገባል ባይ ነኝ።

ምክር ቤቱ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 191 ቅዳሜ ጥቅምት 18/ 2004

‹‹የቤት እንስሳት ያስባሉ. . .

አደርገዋለሁ›› ይላሉ። እኔ ግን እነሱ ትንሽ

አበዙት እላለሁ።

ከሰው ልጅ የማይጠበቅ ስህተት/ድርጊት

[በተለምዶ እንስሳዊ የምንለው አይነት]

ፈፅመው የሚገኙን ‹‹ከእንስሳት ታዲያ

በምን ተለየህ? በማሰብህ አልነበረም

እንዴ?›› እንላለን። እንስሳት እንደማያስቡ

ርግጠኛ መሆን ይቻላል? [በርግጥ አንቺ

የሰው ልጅ እንጂ የእንስሳ አዕምሮ ባለሙያ

አይደለሽም]

የሚያስቡ ይመስለኛል። ውሻን

ልትወስድ ትችላለህ። [የውሻ አድናቂ እና

አፍቃሪ ነኝ፤ ቀረቤታውም አለኝ] የሰው

ልጆች ከሚያደርጉት በላይ ያደርጋል።

በርግጥ አመክንዮ አያውቅም። አጥንቱን

ቁጭ አድርጎ ስታልፍ ሊነክስህ ይችላል።

‹‹አጥንቴን ሊወስድብኝ ነው›› ብሎ ስላሰበ

ነው። ምናልባት ‹‹እኔ የነካሁትን አጥንት

የሰው ልጅ አይበላም›› ብሎ ቢያስብ ኖሮ

አይነክስህም ነበር። በተለይ የቤት እንስሳት

በደንብ ያስባሉ ብዬ አምናለሁ። እንደ ሰው

የተወሳሰቡ ነገሮችን ላያስቡ ይችላሉ። [በጣም

እየሳቀች] በርግጥ እስካሁን ያለሁት ሰው ላይ

ነው። ወደፊት ስለ እንስሳት አጠና ይሆናል።

[በቅርቡ አሜሪካ ውስጥ 911 ደውሎ ህመም

ውስጥ የነበረ ጌታውን ውሻው ታድጓል]

ስለ አዕምሮ…

የሰው ልጅ አዕምሮን ለሁለት

ከፍለን ማየት እንችላለን። የግራው

ምክንያታዊ፣ ቀኙ ደግሞ ስሜታዊ ክፍል

ነው። የህፃናት እስከ ሁለት ዓመታቸው ድረስ

75 በመቶ የሚሰራው ቀኙ (ስሜታዊው)

ክፍል ነው። ለዚያ ነው ሲርባቸው፣ ሲናደዱ

ወይም በሌላ ምክንያት የሚያለቅሱት።

የተነሳሽነት፣ የማቀድና ማስፈፀም ስንፈት

ከስነ-ልቦና ችግር ጋር ይያያዛል?

በጣም እንጂ። እኔ ጋር የሚመጡ

የፍቅር፣ የባልና ሚስት ችግሮች ብቻ

አይደሉም። ብር ኖሯቸው ምን መስራት

እንዳለባቸው የማያውቁ እና የሚፈሩም

ይመጣሉ። እንደዚህ አይነት ችግሮች

ሲመጡ የኋላ ታሪካቸውን እናጠናለን።

እንደማምነው 90 በመቶ ያህል የስነ-ልቦና

ችግር የሚመጣው ከልጅነት ችግራችን

ነው። ጉንፋን የያዘው ሰው ያስላል። ሳሉ

ግን ጉንፋን ብቻ ነው ማለት አይቻልም።

ውስጡ መታከም አለበት።

ብዙ ነገሮች ማድረግ እየቻሉ ‹‹እኔ

ብቁ አይደለሁም›› ብለው የሚያስቡ ሰዎች

አሉ። አንዳንድ ሰዎች ማጌጥ የሚፈልጉት

‹‹ይመጥነኛል›› በሚሉት ነገር ነው። አንተ

እጅ ላይ ወርቅ አለ። ያደረግከው ይመጥነኛል

ብለህ ነው። ለአንዳንድ ሰዎች ግን ወርቅ

ብትሰጣቸው ‹‹ሰዎች ወርቁን ሲያዩ እኔ

አንሼ እታያቸዋለሁ›› (ከወርቁ አንሳለሁ)

ብለው ስለሚያስቡ አያደርጉትም። እንዲህ

አይነት ሰዎች ብዙ ጊዜ ‹‹አትችልም››

ተብለው ያደጉ ናቸው።

አዲስ መንገድ እና የእርቅ ማዕድ የተሰኙ

የስነ ልብዎና የሬዳዮ ፕሮግራም አላችሁ።

ማህበረሰቡ ጋር ምን ያህል እንደደረሳችሁ

ዳታው ባይኖረኝም በግላዊ ምልከታዬ

ፍቅረኞች፣ ባለ ትዳሮች፣ ቤተሰብ፣ የፍቅር

ግንኙነታቸው ማደስ የሚፈልጉ እና በኑሮ

ሂደት የትዳር ወይም ቤተሰባዊ ግንኙነታው

የደፈረሰ ለእርቅ እንዲሰናዱ ሊያዳምጧቸው

የሚገቡ ሁለት ፕሮግራሞች ናቸው። ምን

አይነት ግብረ መልስ ታገኛላችሁ?

እኛ በግላችን ስለ ፕሮግራማችን

የሰራነው ጥናት የለንም። ፋና የስርጭት

ማዕከል ከሚሰራው ጥናት ተነስቶ ጥሩ እና

ተደማጭ ፕሮግራም እንደሆነ ይነግረናል።

አነቃቂ ስልጠና (Motivational Training)

ለመስጠት በተለያዩ ቦታዎች ስገኝ

የሚቀበሉኝ በደስታ ነው። ‹‹ወይኔ ታድዬ

ቲጂን አወቅኳት›› እስከ ማለት የሚደርሱ

ያጋጥሙኛል። በሚወዱህ መሀከል መስራት

አስደሳች ነው። ይሄ ለእኛ ትልቁ ሽልማት

ነው።

እግዚአብሔር ይመስገን እጅግ

በጣም ቆንጆ ምላሽ አለን። የስልጠና እና

የማማከር ስራውን ስንጀምር በ400 ብር

ቢሮ ተከራይተን ሲሆን ጠረጴዛ እንኳን

አልነበረንም። እኔም ሆንኩ የድርጅታችን

ሌላው ባለድርሻ (እንዳልካቸው አሰፋ)

ስራ ከቀደመ፣ ገንዘብ እንደሚከተለን

እናውቀዋለን። [ድርጅታቸው በርካታ

ጥንዶችን አስታርቋል።]

ፕሮግራማችሁን ስከታተል ብዙዎች

እንደሚወዱሽ እና እንደሚያደንቁሽ

[ሁለቱም ፆታዎች] ይናገራሉ። በድምፅሽ

እና በአወራር ዘዬሽ የሚሳቡ ያሉ

ይመስለኛል። የፍቅር ጥያቄዎችም

እንደሚቀርብልሽ ሰምቻለሁ።

እንዲህ ወጣ ያለ ጥያቄ ደስ

ይላል። በህይወት ውስጥ የሚያጋጥም ነገር

ነው። ደንበኞቼን በር ከፍቼ ‹‹እንኳን ደህና

መጣችሁ›› ብዬ እቀበላቸዋለሁ። የምክር

አገልግሎት እየሰጠኋቸው ቢያለቅሱ፣

ቢያዝኑ በእጄ እንዲህ (በአመልካች ጣቷ

እየጠቆመች) አልነካቸውም። በጣም ካለቀሱ

ናብኪን አውጥቼ ሰጣቸዋለሁ። ከደንበኞች

ጋር (ወንድም ሆነ ሴት) መገባበዝ

አይፈቀድም። ስጦታ መቀበል ስለማይቻል

መጥቶልኝ መልሼ አውቃለሁ። ይህን

የማደርገው ለእኔም ለደንበኞቼም ደህንነት

ሲባል ነው።

በቀደም ሱሰኝነትን ስለማስወገድ

በሬዲዮ እያወራን ‹‹በድምፅሽ ሱሰኛ ሆኛለሁ››

የሚሉ የፅሁፍ መልዕክቶች ደርሰውኛል።

[እየሳቀች] ሱሰኛ ስላለመሆን እያወራሁ

‹‹ሱስ ሆኖብኛል›› ማለት ጥሩ አይደለም።

ምንም አይነት ነገር ቢመጣ የሙያው

ስነ-ምግባር ገትሮ ይይዝልኛል። እውነት

ለመናገር ስለ ድምፄ አንተ እንዳልከው ያሉኝ

አሉ። ስቱዲዮ ውስጥ በጣም ነፃ ሆኜ፣ ራሴን

ሆኜ ነው የማወራው።

አዎ! ከደንበኞች አንስቶ የፍቅር

ጥያቄ ይገጥመኛል። የፍቅር ጓደኛ አለኝ።

በፕሮግራማችሁ ላይ የምታወሪውን

ትኖሪዋለሽ?

ቆንጆ ጥያቄ ነው።

የማደርጋቸውም፣ የማላደርጋቸውም አሉ።

በግል ህይወቴ ያደረግኳቸው ዋነኛ ለውጦች

አሉ። በጣም ፈሪ፣ ዝምተኛ እና አይናፋር

ነበርኩ። ‹‹ድድ ማስጫ›› ላይ ለሚቀመጡ

ጎረምሶች ‹‹የመጨረሻ ሙድ መያዣ››

ነበርኩ። እናቴ ሬዲዮ ላይ ስትሰማኝ

‹‹የምታወራው እውነት የእኔ ልጅ ናት?››

ብላ ትገረማለች።

አሁን የምሰራው ሰዎች ከእንደዚህ

ያሉ ፍርሃቶች እንዲወጡ ነው። በነፃነት

አልደራደርም፤ እኔ እንደነበርኩበት የሰው

ልጅ በጭንቀት ባርነት ውስጥ እንዲኖር

አልፈልግም።

በብዛት የማወራውን ባደርግም

በጣም በተቀናጀ አካሄድ እና በፕሮግራም

የምመራ አይነት ሰው ግን አይደለሁም።

ማስተካከል ግን ፈልጋለሁ።

ከአንድ ጫፍ ወደ ሌላ ጫፍ

የመጣሁት በራሴ ቢሆንም ዮሐንስ አፈወርቅ

የተባለ ጓደኛዬ እና የስራ ባልደረባዬ እንዳልክ

ብዙ ነገር አደፋፍረውኛል።

አንቺስ አማካሪ እና ቴራፒስት አለሽ?

ሰው እንደመሆኔ መጠን እኔም

ችግር ስላለብኝ መደበኛ አማካሪ አለኝ።

ሲጨንቅሽ ምን ማድረግ ያስደስትሻል?

በጣም ሲጨንቀኝ ልደታ ቤተ

ክርስቲያን ሄዳለሁ። ዛፎቹ ስር መቀመጥ

ደስ ይለኛል። ከጎኔ ካለ ሰው ጋር ማውራት

ደስ ይለኛል። ነገር ስለማያከብድ ከፍቅር

ጓደኛዬ ጋር ማውራትም ያስደስተኛል።

አንዳንዴ ግን ሰዎች አይረዱኝም።

ስንት ኪሎ ነሽ?

52፡፡ ቁመቴ ደግሞ አንድ

ሜትር ከሰባ ነው፤ ረዥም ነኝ። ቅጥነቴን

እወደዋለሁ።

ሁለት ሰከንድ ነው የምሰጥሽ የአዲስ አበባ

ከንቲባ ስም ማን እንደሚባል ንገሪኝ።

‘Oh My God’… [በቁጭት

አንገቷን የተቀመጠችበት ወንበር መደገፊያ

ላይ አኑራ ወደ ጣሪያ እያየች ከትከት ብላ

ሳቀች] በጣም አዝናለሁ አላውቅም። [አንድ

የስነ-ልብዎና ባለሙያ የከተማዋን ከንቲባ

ስም አታውቅም ቢባል ማን ያምናል? አቶ

ኩማ ደመቅሳ መሆናቸውን ነግሬያት እንኳን

ተጠራጥራለች። በሳቅ እየተፍለቀለቀች

‹‹ከፖለቲካ ጉዳዮች ሩቅ ነኝ›› ብላለች።

ይህን ለመመለስ ፖለቲካ የግድ ማወቅ

ያስፈልጋል?]

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 191 ቅዳሜ ጥቅምት 18/ 2004

ዜናዎች

“በሻዕቢያ ነጭ ለባሽነት ሀገር የሚያውቃቸው

የኢህአዴግ መሪዎች ናቸው”

መድረክ

በሱራፍኤል ግርማ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ

አንድነት መድረክ፣ በሻዕቢያ ነጭ ለባሽነት

የሚጠረጠሩትና ሀገር የሚያውቃቸው የኢህአዴግ

መሪዎች ሆነው ሳለ፣ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን

መንግሥት በዚህ መወንጀሉ ግራ የሚያጋባ መሆኑን

አስታወቀ።

ፓርቲው ትናንት ባወጣው መግለጫ፣

“ኢህአዴግ ከሻዕቢያ ጋር ለመታረቅ እየተማፀነ ባለበት

በአሁኑ ጊዜ እንኳን ሳይቀር መድረክ የኢትዮጵያን

ጥቅም በማስጠበቅ ረገድ የአልጀርሱ ስምምነት መሰረዝ

እንዳለበትና የአሰብ ወደብ ባለቤትነት ጉዳይ ድርድርና

ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ሊደረግበት እንደሚገባ የፖለቲካ

በናፍቆት ዮሴፍ

በደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና

ህዝቦች ክልላዊ መንግስት በዳውሮ

ዞን ዋካ ከተማ “ወረዳችን ከቀርጫ

ተነስቶ አማካኝ ቦታ ላይ ይሁንልን”

በሚል ህብረተሰቡ ባነሳው ጥያቄ፣

ህዝቡ እንዲያምፅ የድጋፍ ፊርማ

አሰባስበዋል በሚል ከ30 በላይ ሰዎች መታሰራቸውን

የአካባቢው ነዋሪዎች ለአውራምባ ታይምስ ገለፁ።

እንደነዋሪዎቹ ገለፃ፣ ከዚህ ቀደም የአካባቢው

ወረዳ “ማረቃ” እንደነበር እና ለጊዜያዊነት ወደ ቀርጫ

የተዛወረ መሆኑን ገልፀው፣ ምንም እንኳን በጊዜያዊነት

የተዛወረ ቢሆንም አሁን ግን ቋሚ በመደረጉ ህዝቡ

አቋም የያዘ ፓርቲ ነው” ብሏል።

የሻዕቢያ ተላላኪ ሊሆን ቀርቶ ከሻዕቢያ ጋር

ሊያስማማው የሚችል ባህሪና አቋም እንደሌለው የገለፀው

መድረክ፣ በጋዜጠኞችና በተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ላይ

እየተፈፀመ ያለውን ወከባ አውግዟል። ፕሬዝዳንት

ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ለፓርላማ መክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ

በአባላቱና በሌሎች ጠንካራ ተቃዋሚዎች ላይ ኢህአዴግ

መራሹ መንግስት የሚወስዳቸውን የኃይል እርምጃዎች

ባለመጥቀስ “አንዳንድ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች

በሽብር ተግባር ላይ ተሰማርተዋል” ማለታቸውን

መድረኩ በፅኑ ኮንኗል።

ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተጨማሪ፣

ነፃ ጋዜጠኞችን መንግስት እያሳደደ መሆኑን የገለፀው

መድረክ፣ “ለዚህ ሁሉ መነሻው ኢህአዴግ ሙስናን

ለእንግልት እየተዳረገ መሆኑን አስታውቀዋል።

በዞኑ ከ37 በላይ የቀበሌ ማህበር ነዋሪዎች

መኖራቸውን የገለፁት የአውራምባ ታይምስ ምንጮች፣

ወረዳው ከማረቃ ወደ ቀርጫ ከተዘዋወረ ወዲህ ለፍርድ

ቤት ጉዳይ፣ ለህክምና እና ለመሰል ማህበራዊ ጉዳዮች

ቀርጫ ድረስ መመላለሱ ህዝቡን እያንገላታው በመሆኑና

ጥያቄውንም የዞኑ መስተዳድር ባለመመለሱ፣ እስከ

ክልል አቤት በማለት መፍትሄ ባለማግኘታቸው ህዝቡ

ተሰብስቦ ሰልፍ በመውጣቱ ህዝቡ ለአመፅ እንዲነሳሳ

አስተባብራችኋል በሚል ነበር ከትላንት ወዲያ ለእስር

የተዳረጉት።

በትላንትናው ዕለት በአካባቢው ያሉ ትምህርት

ቤቶች በሙሉ ተዘግተው መዋላቸውንና አስተማሪዎችም

ከቀኑ ስምንት ሰዓት ላይ ለአስቸኳይ ስብሰባ

መዋጋት፣ መልካም አስተዳደርን ማስፈን፣ ሰብዓዊና

ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ማስከበር፣ እንዲሁም የሕግ

የበላይነትን ማስጠበቅ ስላቃተው ነው” የሚል ምክንያት

አስቀምጧል።

ኢህአዴግ ኢትዮጵያ ውስጥ ፍትሕን

ማረጋገጥና የዜጎችን ክብር ማስጠበቅ እንዳቃተው

በመግለፅም የገዢው ፓርቲ ሥርዓተ-መንግስት

በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ሳይውል ሳያድር መተካት

እንዳለበትም አሳስቧል።

በሀገሪቱ ሥር እየሰደደ ላለው ችግር

ተጠያቂው ኢህአዴግ እንጂ ተቃዋሚ ፓርቲዎች

አለመሆናቸውን ያስገነዘበው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ

አንድነት መድረክ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ

በፓርላማ ተገኝተው ባቀረቡት ንግግር ላይም ትችት

በዳውሮ ዞን ዋካ ከተማ ከ30 በላይ ሰዎች ታሰሩ

አጣጥለዋቸዋል። አቶ መለስ በዚህ ወር መጀመሪያ

ከኖርዌዩ አፍተንፖስተን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ-

ምልልስ እነዚህ ስዊድናውያን ጋዜጠኞች “የሽብርተኞች

ግብረ-አበሮች” እና “ጋዜጠኛ ያልሆኑ” መሆናቸውን

ገልፀዋል።

ይህ የአቶ መለስ የፓርላማ አስተያየት

በመንግስት የሚመራው ዕለታዊ ጋዜጣ አዲስ ዘመን

ተዘግቦ የተመለከተው ቴዲ አፍሮ፣ ኢትዮጵያዊውን ነፃ

ለማውጣት አስፈላጊውን ገንዘብ እንደከፈለ ተገምቷል።

እንደ “ሪፖርተር” ዘገባ ከሆነ፣ አስመሮም

ሞት የተፈረደበት ሆን ብሎና አስቦ ሰው ገድሎ ሳይሆን፣

በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ እያለ ባለቤቱን ለመድፈር የመጡ

ግለሰቦችን ለመከላከል በወሰደው እርምጃ ነው።

መረጃው ትክክል ሆኖ ድምፃዊው በጎሳ

መሪዎቹ የተጠየቀውን የ700 ሺህ ብር የነፍስ ካሳ

ሙሉ በሙሉ በመክፈል ኢትዮጵያዊውን ወጣት

ከሞት የሚያተርፈው ከሆነ፣ መንግስት ልጃቸውን

እንዲያድንላቸው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል

ተደጋጋሚ ተማፅኖ ሲያቀርቡ ቆይተው በቂ ምላሽ

ላላገኙት ቤተሰቦቹ እፎይታ እንደሚሆን ተገምቷል።

በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ለአውራምባ

ታይምስ የሰጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል-አቀባይ

ትናንትና የአካባቢው በርካታ ት/ቤቶች ተዘግተው ውለዋል

ሲፒጄ፣ ‘በጋዜጠኞች . . .

ቴዲ አፍሮ በሶማሊያ ሞት ...

በነፃው ሳምንታዊ ጋዜጣ አውራምባ ታይምስ ላይ እጅግ

የሰላ ትችት ባተመ በማግስቱ የተሰነዘረ ሲሆን፤ ይህም

በጋዜጣው ላይና በማኔጂንግ ኤዲተሩ ዳዊት ከበደ ላይ

ከተቀጣጠለ የተራዘመ የስም-ማጥፋት ዘመቻ አንዱ

ነው። በሲፒጄ አማካኝነት ከአማርኛ ወደ እንግሊዝኛ

በተተረጎመው ጽሁፉ አዲስ ዘመን፣ “አመጽ ናፋቂዎችን

መታገስ እስከመቼ?” ሲል ያተመው የአስተያየት ዘገባ

መጠራታቸውን የገለፁት ምንጮች፤ ከተዘጉት ት/ቤቶች

ውስጥ ዋካ መሰናዶ ት/ቤት፣ ኮጀብ መምህራን ኮሌጅ፣

ዋካ አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት፣ ሞዴል

አንደኛ ደረጃ ት/ቤት እና ሌሎችም ተዘግተው ውለዋል።

እንደምንጮቻችን ገለጻ በአካባቢው ያሉ ጋዜጠኞች

የተፈጠረውን ችግር እንዳይዘግቡ ተከልክለዋል።

“ወደ ዋካ ከተማ ከክልል ፖሊሶች ቢመጡም

የዞኑ አስተዳዳሪዎች ግን ጥያቄያችንን የሁለትና የሦስት

ግለሰቦች ጥያቄ እንደሆነ በመግለፅ መፍትሔ እንዳናገኝ

ተከልክለናል” ሲሉ ገልፀዋል። “የዞኑና የወረዳው

አስተዳዳሪዎች በቀርጫ መኖሪያ ቤታቸውን ስለሰሩ

እኛ ወደ ቀድሞ ወረዳችን ማረቃ አሊያም አማካይ ቦታ

ይሁንልን ስንል ‹የመንገድና የወረዳ ጥያቄ የሚያነሳ ገደል

ይግባ› ሲሉ ተሳልቀውብናል›› ያሉት የአካባቢው ሰዎች

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ደግሞ በበኩላቸው መንግስት

ኢትዮጵያዊውን ለማትረፍ ጥረት ሲያደረግ መቆየቱን

ተናግረዋል።

አስመሮም ኃይለሥላሴ ነፍስ ካጠፋና በጎሳ

መሪዎች ውሳኔው ከተላለፈበት አንድ ዓመት እንደሆነው

ያስታወሱት አምባሳደር ዲና፣ “ልጁ እስካሁን ሳይገደል

የቆየው ፑንት ላንድ ያለው ቆንፅላ ጽ/ቤታችን ባደረገው

ጥረት ነው” ብለዋል።

ቤተሰቦቹ ልጃቸውን ለማስለቀቅ

የሚያስፈልገውን ያህል ገንዘብ በዕርዳታ ማግኘታቸውን

የገለፁትን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ፣

ቤተሰቦቹ ገንዘቡን ባያገኙ ኖሮ መንግስት ከፍሎ

ያስለቅቀው እንደነበር ጠይቀናቸው፣ “‘ቢሆን ኖሮ’ ብዬ

መልስ ለመስጠት አልችልም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ስለ ጉዳዩ ድምጻዊ ቴዲ አፍሮን ለመጠየቅ

ወደ ተንቀሳቃሽ ስልኩ ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ

ብናደርግም ስልኩ ዝግ በመሆኑ አስተያየቱን ለማካተት

አልቻልንም።

19

ሰንዝሯል።

“ጠቅላይ ሚኒስትሩና ፓርቲያቸው ኢህአዴግ

በሀገራችን ያለው የፖለቲካ ምህዳር ችግር እንደሌለበትና

የጨዋታ ሕግን ተከትሎ መሄድ ለፈለገ ሁሉ ምቹ

እንደሆነ ለማስረዳት ሞክረዋል፤ ሆኖም በተጨባጭ

የሚታየው ሁኔታ የተገላቢጦሽ ነው” ይላል - የፓርቲው

መግለጫ።

መግለጫው በማከልም፣ ከምርጫ 97

በኋላ ኢህአዴግ ካደረበት ድንጋጤ የተነሳ የሲቪል

ማሕበረሰቡን፣ የግል ጋዜጦችንና የተቃዋሚ ፓርቲዎችን

እንቅስቃሴ የሚገድቡ አዋጆች እንዲፀድቁ ማድረጉን

አስታውሷል።

መንግስት ጉዳዩን ተመልክቶ እልባት ይሰጣቸው ዘንድ

ጥያቄ አቅርበዋል።

ዝግጅት ክፍላችንም የዞኑ የድርጅት ጉዳይ

ኃላፊ ለሆኑት ለአቶ ለማ መሰለ፣ ለዳውሮ ዞን ዋና

አስተዳዳሪ ለአቶ እስራኤል አካሉና በዞኑ የፀጥታ መምሪያ

ኃላፊ ለሆኑት አቶ ተነሣ ብሩ ደውለን ስልካቸውን ያላነሱ

በመሆኑ ምላሻቸውን አያላካተትን ቢሆንም፣ በወረዳው

የህብረት ሥራና ግብይት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ

እስክንድር ተፈራ ችግሩ መፈጠሩን አምነው ወረዳ

ይቀየር በሚል ህዝቡ አድማ እንዲያደርግ የድጋፍ ፊርማ

አሰባስበዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎች መታሰራቸውን

ገልፀው፣ ጉዳዩን ፍርድ ቤት እያየው እንደሚገኝ

ለአውራምባ ታይምስ ገልፀዋል።

የፀጥታ ኃይሎች በአቶ ዳዊት ላይ “እርምጃ እንዲወስዱ”

ወትውቷል-ብሏል ሲፒጄ

ጋዜጣው የሲፒጄ ዓለም አቀፍ የፕሬስ ነፃነት

ሽልማት አሸናፊው ዳዊት ከበደን ከ“ሽብርተኛ ቡድኖች”

ጋር በመስራት ከመወንጀሉም በላይ፣ መንግስት

የ1997ቱን ምርጫ ተከትሎ በግል ሚዲያው ላይ

በወሰደው እርምጃ ከ21 ወራቶች እስር በኋላ በቅድመ-

ሁኔታዊ ይቅርታ የተፈታውን ይህን ጋዜጠኛ ይቅርታውን

በመሻር ዳግመኛ እንዲያስረው ጠይቋል።

እነዚህ የአዲስ ዘመን የቅርብ አስተያየቶች

በአውራምባ ታይምስ ላይ እየተሰነዘሩ ካሉ ተከታታይ

ጽሁፎች መካከል የቅርቦቹ ናቸው። በሀምሌ ወር አቶ

ዳዊት ከበደ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ አቶ

አንተነህ ኃይሉ እና በአታሚው የኢትዮጵያ ፕሬስ

ድርጅት ላይ የስም ማጥፋት ክስ መስርተው እንደነበር

ሲታወስ፣ ክሱም በዳኛው ሙሉቀን ተሻለ ውድቅ

እንደተደረገ የሲፒጄ የጥናት ቡድን አረጋግጧል።

የሲፒጄ የምስራቅ አፍሪካ አማካሪ ቶም

ሮዴስ እንዳብራሩት፣ “ይህ በቅርቡ የተሰማው የጠ/

ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የቁጣ ናዳ በኢትዮጵያ ያሉ ነፃና

ገለልተኛ ጋዜጠኞችን ሽብርተኝነት በሚሉ ውንጀላዎች

ከስራቸው ለመንቀል እየተደረገ ያለው ስልታዊ ዘመቻ

አካል ነው። በመንግስት ሚዲያዎች የሚሰራጨው ስም

የማጥፋት ዘመቻ በአገሪቱ ውስጥ ያለውን የፍርሃት

ድባብ በማባባስ የበኩሉን ሚና ይወጣል። በግል ፕሬሱ

ላይ በተፋፋሙ የማስፈራሪያ እርምጃዎችም ኢትዮጵያ

እንደ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ያላትን ተቀባይነት

እየሰዋች ነው።” ብሏል፡፡

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

20

በኤልያስ ገብሩ

elias.gebru32@gmail.com

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ጤና

ኢትዮጵያ በታህሳስ ወር ለምታዘጋጀው 16ኛው ዓለም አቀፍ የኤድስና አባላዘር በሽታዎች የአፍሪካ ኮንፈረንስ እየተደረገ

ያለው ዝግጅት ምን ደረጃ ላይ ይገኛል?

ዝግጅቱ ሁለት ዘርፍ አለው። አንዱ የፕሮግራም ዝግጅት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የሎጀስቲክ

ነው። ፕሮግራሞቹ ሳይንሳዊ፣ ሕብረተሰባዊና አመራርን የተመለከቱ ናቸው። በሳይንሳዊው

ዙሪያ በርካታ ሥራዎች ተሰርተዋል። ወደ ሦስት ሺህ የሚጠጉ የጥናት ፅሁፎች ቀርበው፣

ከእነዚህም ውስጥ አንድ ሺህዎቹ በዓለም አቀፍ ደረጃ ባሉ ሳይንቲስቶች ተመርጠው በቃልና

በፖስተር ኤግዚብሽን ሊቀርቡ ዝግጁ ሆነዋል። እነዚህን በተመለከተ ጠቅለል ያለ መረጃ

የሚሰጥ መጽሐፍ ተዘጋጅቷል። በአመራር ዘርፍ በርካታ ዝግጅቶች ተደርገዋል። የፖለቲካና

የኃይማኖት መሪዎች፣ የቢዝነስ ዘርፉ፣ ዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች፣ የኤች.አይ.ቪ/ኤ.

አይ.ዲ.ኤስ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ ያለባቸው ሰዎች የግንኙነት መረቦች /ቡድኖች/፣

የማሕበራት መሪዎችን የመሳሰሉት የሚሳተፉባቸው በርካታ ፕሮግራሞች አሉ። የቀድሞ

የሀገር መሪዎች፣ ሚኒስትሮች፣ ቀዳማዊ እመቤቶችና የተባበሩት መንግስታት ዳይሬክተሮች

የሚሳተፉበት ፕሮግራምም አለ።

በሕብረተሰብ በኩል የሕብረተሰብ መሪዎች የሚናገሩባቸው በርካታ ዝግጅቶች ተዘጋጅተዋል።

ሕብረተሰቡም ሊሳተፍበት የሚችል “Community Village” የሚባል ፕሮግራም አለ። እዛ

ውስጥ የተለያዩ የወጣቶች፣ የሴቶችና የሕብረተሰብ ክፍሎች ኤግዚብሽንና ውይይቶች

የሚያደርጉባቸው ፕሮግራሞችና ትርዒቶች ይገኛሉ። ሎጀስቲክን በተመለከተ፤ የሆቴል

መስተንግዶ፣ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ የተለያዩ የመሰብሰቢያ አዳራሾች፣ የቪዛ፣ የደህንነት

ጉዳይና ፕሮቶኮልን የተመለከቱ ዝግጅቶችች እየተከናወኑ ነው። የተለያዩ ኢንፎርሜሽን

ቴክኖሎጂ መሳሪያዎችም ያሉ ሲሆን እነሱን ወደመቋጫ ላይ ነን። ብዙ ነገሮች በጥሩ ሁኔታ

ላይ ነው ያሉት።

ኢትዮጵያ ኮንፈረንሱን ማዘጋጀቷ ፋይዳው ምንድን ነው?

በመጀመሪያ ደረጃ በኤች.አይ.ቪ/ኤ.አይ.ዲ.ኤስ እና በተዛማጅ ችግሮች ዙሪያ አዘጋጁ ሀገር

ጉባዔውን በማዘጋጀቱ ዓለም አቀፍ ግዴታውን መወጣቱን ያስመሰክራል። በአፍሪካም ሆነ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ኤች.አይ.ቪ/ኤ.አይ.ዲ.ኤስን ከመከላከል እና ከመቆጣጠር አኳያ ሀገሪቱ

ዓለም አቀፋዊ ድርሻዋን በትልቁ እንደተወጣች ያስቆጥራል። ሁለተኛ፣ ሀገሪቱ ከዚህ በፊት

በኤ.አይ.ዲ.ኤስ፣ በቲቢ እና ወባን በመሳሰሉት ከፍተኛ ችግሮች ዙሪያ ስትሰራቸው የነበሩትንና

ውጤት ያገኘችባቸውን ሥራዎች የምታሳይበት ነው። ከዚህም ሌላ በቱሪዝም መስክ ከፍተኛ

ቦታ እያገኘ ላለው የኮንፈረንስ ቱሪዝም ጥቅም አለው። በዚህ ከፍተኛ ጥቅም እያገኙ የሚገኙ

የታወቁ ሀገሮች አሉ። በዚህ ከፍተኛ የሥራ መስክም የሚፈጠርበት ሲሆን እየተሰራ ያለው

ከዚህ ቀደም እንደተለመደው የቱሪዝም አይነት ብቻ አይደለም። ከዚህ አንፃር ኢትዮጵያ

በዘርፉ የምትወዳደርበት ይሆናል። ይኼንን ኮንፈረንስ ሀገሪቱ በብቃት ከተወጣች ወደፊት

ተመሳሳይ የሆኑ ኮንፈረንሶች ለማዘጋጀት ያላትን ብቃት ታስመሰክራለች ማለት ነው።

በማስተዋወቅ ደረጃም የተለያዩ ሴክተሮች በዚህ ስብሰባ ይጠቀማሉ - ቀጥተኛ በሆነ የገንዘብ

ጥቅም፣ ከሰዎች ጋር ግንኙነት በማድረግ፣ በቢዝነስና በምርምር ሥራ መረጃ በመለዋወጥ።

ኮንፈረንሱ የሀገሪቱን በጎ ገፅታ ከመገንባት አንፃርም ትልቅ ሚና አለው። እንዲሁም፣ ከፍተኛ

የሆነ የሚዲያ ፍሰት የሚመጣበት ሁኔታም አለ።

በኮንፈረንሱ ላይ ይበልጥ የሚቀርቡት ሳይንሳዊ የምርምር ጥናታዊ ፅሁፎች ናቸው። በተለይ ከሰሃራ በታች በሚገኙት

የአፍሪካ ሀገራት ባለው የበሽታው ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ወደ ተግባር ሥራ የሚያስገቡ ጉዳዮች ላይ

ኮንፈረንሱ ምን ውጤት ይሰጣል?

የጉባዔው የመጨረሻ ውጤት ምንድን ነው ስንል በመጀመሪያ በኤች.አይ.ቪ/ኤ.አይ.ዲ.ኤስ

መከላከል እና መቆጣጠር ዙሪያ ከፍተኛ የሕብረተሰብ እንቅስቃሴ ላይ ያሉ ባለድርሻ አካላትን

የማንቀሳቀስ እና ለጉዳዩ ምላሽ ከፍተኛ ቁርጠኝነት እና ድጋፍ እንዲሰጡ

የማድረግ ነው። እነዚህ ባለድርሻ አካላት የሀገርና የተለያዩ ተቋማት

መሪዎች፣ የዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች፣ ሕብረተሰቡ፣

የቢዝነሱ ዘርፍ፣ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ያሉ የሕብረሰብ

ክፍሎች ናቸው። የኮንፈረንሱ መሪ ቃልም “Own, Scale

up & Sustain” (ባለቤትነት፣ ማስፋትና ቀጣይነት)

የሚል በመሆኑ ባለድርሻ አካላትን በከፍተኛ ደረጃ

የሚያንቀሳቅስ ነው። በሁለተኛ ደረጃ በርካታ ሳይንሳዊ

ፅሁፎች ከመቅረባቸው ባሻገር ሌሎች የተቀመሩ ጥሩ

መልካም ልምዶችም በተለያየ መልኩ ይቀርባሉ።

ይኼም የሚጠቅመው ለኤች.አይ.ቪ/ኤ.አይ.ዲ.ኤስ

ምላሽ በሳይንስ እና በመረጃ ላይ እንዲሆን ለማድረግ

ነው። ስለዚህ ከብዙ የአፍሪካ ሀገራት የመነጩ

ጥናታዊ ፅሁፎችና በጎ ልምዶች፤ ከአፍሪካም ውጪ

ተመሳሳይ ሁኔታ ባለባቸው ደሃ ሀገራት በሽታውን

ከመከላከልና ከመቆጣጠር አንፃር በሕብረተሰብ፣

በመንግሥት ወይም በኃይማኖት ደረጃ የተሰሩ

ሥራዎች ይቀርባል።

ሌላ ከውጤት አንፃር ከኮንፈረንሱ የምንጠብቀው፣

ኤች.አይ.ቪ/ኤ.አይ.ዲ.ኤስን ከመዋጋት አንፃር በመሪዎችና

በአጋሮች ደረጃ ቃልኪዳን ተገብተው የተፈፀመውና

ያልተፈፀሙ የተለያዩ ነገሮች አሉ። እና

እነዚህ የተለያዩ አካላት “ግዴታቸውን

ተወጥተዋል ወይስ

አልተወጡም” ተብለው

የ ሚ ጠ የ ቁ በ ት ና

ው ይ ይ ት

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 191 ቅዳሜ ጥቅምት 18/ 2004

“በኢትዮጵያ የኤች.አይ.ቪ ቫይረስ

ሥርጭት መቀነሱ ሊያዘናጋን አይገባም”

ዶ/ር ይገረሙ አበበ

/የ16ኛው የአይካሳ ኮንፍረንስ ሰብሳቢ/

ዶ/ር ይገረሙ አበበ ኢትዮጵያ በቀጣይ ታህሳስ ወር ላይ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የምታዘጋጀው 16ኛው ዓለም አቀፍ

የኤድስና አባላዘር በሽታዎች የአፍሪካ ኮንፈረንስ (ICASA) ሰብሳቢ ናቸው። ለአራት ቀናት በሚቆየው ዓለም አቀፍ

ጉባዔ ዙሪያ ዶ/ር ይገረሙን የጤና አምድ አዘጋጅ እንዲህ አነጋግሯዋል።

ትክክለኛውን ቁጥር አሁን መጥቀስ

ባልችልም፣ በኢትዮጵያ የበሽታው ወረርሽኝ

በብዛት ያለው በከተማ ነው። ነገር ግን፣

የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ እየቀነሰ

ነው። ይህንን መገንዘብ የምንችለውና

በነፍሰ-ጡሮች ላይ የሚደረገው ክትትል

እንደሚያሳየው፣ በአዲስ አበባ እና በሌሎች

የክልል ከተሞች በአንድ ወቅት ላይ

ስርጭቱ ከ16-17 በመቶ ደርሶ ነበር።

አሁን ግን ስርጭቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ

ከ2-3 በመቶ፣ እንዲሁም በገጠር 0.9

በመቶ የደረሰበት ሁኔታ አለ።

ተደርጎባቸው መልስ የሚገኘበት ነው። በተጨማሪም ሌላ ውጤታማ የሆኑ የተለያዩ

ስትራቴጂዎች፣ ፖሊሲዎችና ፕሮግራሞች ውይይት ላይ ቀርበው ውሳኔ የሚሰጥባቸው

ናቸው። ኃብትን ከማሰባሰብም አንፃር አሁን ብዙ አገልግሎት የሚያገኙ የሕብረተሰብ

ክፍሎች አሉ። በእርግጥ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ያሉ በርካታ በሶስተኛው ዓለም የሚገኙ

የሕብረተሰቡ ክፍሎች ሕክምና እያገኙ ቢሆንም ያላገኙት ይበልጣሉ። ነገር ግን፣ በሽታውን

ስለ መከላከል መረጃ የሚያገኙት ወጣቶች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል። ብዙ የሚቀርም አለ።

ለዚህ ደግሞ መዋዕለ-ንዋይ ያስፈልጋል። ስለዚህ በዚህ ስብሰባ ላይ ከፍተኛ ድጋፍ ሲሰጡ

የኖሩ አካላት ድጋፋቸውን እንዲጨምሩ፤ ድጋፋቸውን ያቆሙ ኃብታም ሀገራትም ድጋፋቸውን

ዳግም እንዲጀምሩ ያደርጋል። በሌላ በኩል እንደ ቻይና፣ ሕንድና ብራዚልን የመሳሰሉ በጣም

በፍጥነት እያደጉ ያሉ ሀገራት ለግሎባል ፈንድ ገንዘብ ማዋጣት ጀምረዋል።

እነዚህ የበለጠ ገንዘብ ማዋጣት እንዳለባቸው ቅስቀሳ የሚደረግበትና ባለፉት ጊዜያት የተዋጡ

መዋዕለ-ንዋዮች በአግባቡ ሥራ ላይ መዋል አለመዋላቸው በኮንፈረንሱ ላይ ውይይት

የሚደረግበት ነው። ጉባዔውም ለአራት ቀናት በመሆኑ በርካታ ጥቅሞች አሉት። ብዙ

መልዕክቶችም ይተላለፋሉ። በአጠቃላይ በአይካሳ ላይ የሚወሰኑት ውሳኔዎች ኢትዮጵያን ብቻ

ብሎ ሳይሆን አጠቃላይ አፍሪካን ጭምር ነው። በተለይም ችግሩ በስፋት ባለበት ከሰሃራ በታች

በሚገኙ ሀገራት ነው። ስለዚህ ኢትዮጵያ ከዚህ ለራሷ የምትወስደው ነገር ሊኖር ይችላል።

ውጤት ሲባል አጠቃላይ የአፍሪካ ወጤት ነው። በኮንፈረንሱ ላይ የሚተላለፉት ውሳኔዎች

ሁሉንም የሚመለከቱ ሆነው ሀገራት የየራሳቸውን ድርሻ ይወስዳሉ።

በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ ያለው የበሽታው ስርጭት ምን ይመስላል?

በአጠቃላይ በዓለም ላይ ከ30 ሚሊዮን በላይ የሚቆጠሩ ሰዎች ከቫይረሱ ጋር ይኖራሉ።

ከዚህም ሌላ በአዲስ መልክ ቫይረሱ የሚተላለፍበት ሁኔታ አለ። በእርግጥ ይሄ እየቀነሰ

መጥቷል። የሞት ቁጥሩም መድኃኒቱ ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ በስፋት እየተሰራጨ በመሆኑ

እየቀነሰ ነው። አሁንም ግን በአፍሪካ በተለይም ከሰሃራ በታች በስተደቡብ ባሉ ሀገራት፣

ከሌሎች ጋር ሲወዳደር፣ በበሽታው በከፍተኛ ደረጃ እየተጎዱ ናቸው። … ለውጦች ቢኖሩም

ገና ብዙ ለውጥ ያስፈልጋል። በአብዛኛው ከ70 በመቶ በላይ የሚሆኑት ቫይረሱ በደማቸው

ያለባቸው ሰዎች የሚኖሩት ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ነው። በአዲስ መልክ

ሕፃናት እና ወጣቶች በቫይረሱ የሚያዙት እና የሚሞቱት በዚሁ አካባቢ ነው። ግን ከላይ

እንደገለፅሁት፣ ገና ቢቀርም፣ የሞት እና የቫይረሱ መተላለፊያዎች ቀንሰዋል።

የበሽታውን ስርጭት ከአፍሪካ ውጪ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስናየው አዳዲስ ወረርሽኞች

በአንዳንድ አካባቢዎች በተለያዩ ምክንያቶች እየተከሰቱ ናቸው። ለምሳሌ፣ በምስራቅ አውሮፓ

ራሺያን ጨምሮ በአንዳንድ የቻይና ክፍሎች በመርፌ በሚሰጥ አደንዛዥ ዕፅ (Injected Drugs)

አማካኝነት ስርጭቱ እየጨመረ ይገኛል። “ከቫይረሱ ነፃ ናቸው” ተብለው ለረዥም ጊዜያት

የተገመቱት የሰሜን አፍሪካና የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ውስጥ፣ አሁንም በመርፌ

በሚሰጥ አደንዛዥ ዕፅና በግብረ-ሰዶማዊነት አማካኝነት ስርጭቱ እየጨመረ ነው። በአጠቃላይ

የበሽታው ስርጭት በዓለም አቀፍ ደረጃ እየቀነሰ ነው። በአፍሪካ ቢቀንስም ችግሩ ሰፊ በመሆኑ

በሌላ አዳዲስ ምክንያቶች እንደወረርሽኝ የሚከሰትባቸው አካባቢዎች አሉ።

ለስርጭቱ መቀነስ ምን ምን ምክንያቶች ይጠቀሳሉ?

ኤች.አይ.ቪ/ኤ.አይ.ዲ.ኤስን ለመቆጣጠር እና ለመከላከል ብዙ ስትራቴጂዎች አሉ። አንዳንዶቹ

አዳዲሶች ናቸው። አንዳንዶቹ ደግሞ ቀድሞ የነበሩ ናቸው። ሁሉም የየራሳቸው ድርሻ አላቸው።

የባህሪ ለውጥ ለማምጣት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ኮንዶም፣ የአባላዘር በሽታዎችን ጉዳይና

ከእናት ወደ ልጅ ቫይረሱ እንዳይተላለፍ የሚደረገው እንቅስቃሴ በከፍተኛ ደረጃ የየራሳቸው

ድርሻ አላቸው። አዳዲሶቹ ደግሞ ስርጭታቸውን በሕክምና አማካኝነት በመከላከልና ይህም

መንገድ በሕብረተሰቡ ውስጥ በሚስፋፋበት ጊዜ የቫይረሱ ስርጭት የመቀነስ ዕድሉ ሰፊ ነው።

ይኼ በግለሰብ ደረጃ አይደለም። ምክንያቱም መድኃኒቱን የጀመሩ ሰዎች የሚመከሩት ደህንነቱ

የተጠበቀ ግንኙነት እንዲፈፀሙ ነው። ያንን ካላደረጉ አሁንም ቫይረሱ የመተላለፍ ዕድል

አለው። ስለዚህ “መድኃኒት የቫይረሱ መተላለፈያን ይቀንሳል” ሲባል በሕብረተሰብ ደረጃ እንጂ

ግለሰቡ፣ “መድኃኒት ጀምሬያለሁና እንደፈለኩ ያለጥንቃቄ ወሲብ እፈፅማለሁ” ቢል ቫይረሱን

ለሌላው ያስተላልፋል። ለራሱም ቢሆን ቫይረሱን የለመዱ መድኃኒቶች ሊያገኙት ይችላሉ።

ስለዚህ ዘዴው በማሕበረሰብ ደረጃ አንዱ የመከላከያ መንገድ ነው። በስፋት መድኃኒቱን

መጠቀም ለሚያስፈልጋቸውና መድኃኒቱን ለሚወስዱት ሰዎች በጥንቃቄ በሀኪም ትዕዛዝ

መሰረት መውሰዱ የቫይረሱን ስርጭት በሕብረተሰቡ ውስጥ እንዲቀንስ ያደርጋል። በተጨማሪም

ሌሎች አዳዲስ የመከላከል ዘዴዎች እየታዩ ነው።

ወደ ሀገራችን እንምጣና፣ የበሽታውን ስርጭት እንዴት ይገልፁታል?

ትክክለኛውን ቁጥር አሁን መጥቀስ ባልችልም፣ በኢትዮጵያ የበሽታው ወረርሽኝ በብዛት ያለው

በከተማ ነው። ነገር ግን፣ የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ እየቀነሰ ነው። ይህንን መገንዘብ

የምንችለውና በነፍሰ-ጡሮች ላይ የሚደረገው ክትትል እንደሚያሳየው፣ በአዲስ አበባ እና

በሌሎች የክልል ከተሞች በአንድ ወቅት ላይ ስርጭቱ ከ16-17 በመቶ ደርሶ ነበር። አሁን ግን

ስርጭቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ2-3 በመቶ፣ እንዲሁም በገጠር 0.9 በመቶ የደረሰበት ሁኔታ

አለ። ይሄ አጠቃላይ ሁኔታ እንዳለ ሆኖ፣ ቫይረሱ እጅግ በጣም የተሰራጨባቸው የምንላቸው

አንዳንድ ቦታዎች አሉ። በእነዚህና በአንዳንድ የሕብረተሰብ ክፍሎች አካባቢ ስርጭቱ ከፍተኛ

እንደሆነና በዚህም ዙሪያ ብዙ ሥራ መሠራት እንዳለበት ነው የሚያሳየው። በመሆኑም

የሥርጭቱ የመቀነስ ሁኔታ ብዙ ሊያዘናጋን አይገባም።

ለኮንፈረንሱ ከኢትዮጵያ ብዙ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበዋል?

አዎን። ደስ የሚለው ጥናታዊ ጽሁፍ በማቅረብ ኢትዮጵያ ከናይጄሪያ ቀጥላ ሁለተኛ ነች።

ይኼ የሚያስመሰግን ነው። ምክንያቱም አንደኛ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሳይንሳዊ ሕብረተሰብ

ብዙ ስራ እየሰራ እንዳለ የሚያሳይ ሲሆን፣ ሁለተኛ ደግሞ በሀገሩ እንደዚህ አይነት ጉባዔ

ሲደረግ በከፍተኛ ደረጃ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኑን ያሳያል።

ጽሑፎች ከመቅረባቸው ባሻገር ተቀባይነት ያገኙና ያላገኙ ጥናቶች አሉ። አብዛኛዎቹ ግን

ተቀባይነት አላገኙም።

ከላይ እንደገለፁልኝ፣ የኮንፈረንሱ አንዱ ትርፍ የኢትዮጵያን በጎ ገጽታ ማሳየት ነው። ነገር ግን፣ በከተሞች በተለይም

በመዲናችን አዲስ አበባ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከተ የመጣው የሴተኛ አዳሪዎችና የመንገድ ላይ የወሲብ ንግድ

የተባለውን በጎ ገፅታ አያሳይም። በዚህ ላይ ምን ታስቧል?

መጀመሪያ ያልከው ነገር “ጨምሯል” ሲባል በደንብ በጥናት

መታወቅ አለበት። ሌላው ነገር ይሄ ማሕበራዊ ችግር

በሁሉም የአፍሪካ ሀገራት ያለ ችግር በመሆኑ የተለየ

ነገር ተደርጎ አይወሰድም። በመሆኑም፣ ስብሰባው

ሲካሄድ የሚደረግ ምንም የተለየ እርምጃ ሊኖር

አይችልም። የተባሉትን ሰዎች ማግለልን የመሳሰሉ

ነገሮች አይደረግም። ምክንያቱም፣ ከዚህም

የባሰ ሁኔታ ላይ የሚገኙ አሉ። በሂደት ሀገሪቱ

እያደገችና ከድህነት እየወጣች በምትሄድበት ጊዜ

ይሄ ሁኔታ እየከሰመ ይሄዳል። ሀገሪቷ እስክታድግ

ድረስ የማይጠበቁና የተባሉትን ሴቶች የሚመለከቱ

ስራዎች እየተሰሩ ነው። በመንግስትና በምግባረ-

ሰናይ ድርጅቶች አማካኝነት የአጭርና የረዥም ጊዜ

ዕቅዶችም አሉ። ሆኖም እነዚህን ሰዎች በኃይል

አስገድዶ ወደ አንድ ቦታ ማስቀመጥ ትክክለኛ አሰራር

አይሆንም። ኮንፈረንሱም ይኼንን አያደርግም።

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 191 ቅዳሜ ጥቅምት 18/ 2004

በታዳሽ የኃይል ምንጮች

የሚከንፉ ዘመናዊ ኦቶሞቢሎች

በአብዱ መሐመድ

ከስኳር ዝቃጭ ኢታኖል

የተባለውን ነዳጅ በማምረትና በኢታኖል

የሚሽከረከሩ ኦቶሞቢሎችን በመፈብረክ

ቴክኖሎጂውን በበላይነት የምትመራው፣

ዓለም በተለይ በእግር ኳሷ የሚያውቃት

ብራዚል ነች።

ኢታኖል፣ ስኳር በማምረት

ሂደት የሚመጣውን ዝቃጭ

‹‹ፈርመንቴሽን›› በተባለው ኬሚካላዊ

ሂደት ‹‹ይስት›› በተባለ በውስጡ ኢንዛይም

በያዘ ባክቴሪያ በማብላላት ለኃይል ፍጆታ

የሚውል ነዳጅ ነው።

ይህንን ነዳጅ እ.አ.አ ከ1982

ጀምሮ እስከ 5.7 ሜጋ ሜትር ኪዩብ

በየዓመቱ በማምረት የኃይል ፍላጎቷን

ማሟላት በጀመረችው ብራዚል እ.አ.አ

ከ2000 ጀምሮ 75 በመቶ የኃይል ፍላጎቷን

የምታሟላውና በጎዳናው ላይ የሚተራመሱ

ኦቶሞቢሎች የሚተራመሱት በኢታኖል

ነው።

የኢነርጂ ጥናት ባለሙያዎች

የብራዚልን ተሞኩሮ መነሻ በማድረግ

ባቀረቡት ጥናት መረጃ በአንድ ሄክታር

በአማካይ 50 ቶን ሸንኮራ አገዳ ማምረት

ይቻላል። ይህንን የሸንኮራ አገዳ ወደ ስኳር

በመለወጥ ሂደት ከስኳር ኢንዱስትሪ

ከሚወጣው ዝቃጭ ከአንድ ቶን ሸንኮራ

በአማካይ 70 ሊትር፤ በአንድ ሄክታር ላይ

ከሚመረት የሸንኮራ አገዳ፣ 3500 ሊትር

ኢታኖል ይወጣል።

ኢታኖልን በሀገራችን

እንደሚሰራበት ከተፈጥሮ ነዳጅ ጋር

ከመቀየጥ ባለፈ በኦቶሞቢል ግንባታ

ከአለማችን ቀዳሚ የሆኑ እንደ ቮልስዋገን፣

ፎርድ፣ ፊያትና ጀነራል ሞተርስ

በብራዚል በሚገኙ ቅርንጫፍ መስሪያ

ቤቶች የሚያመርቷቸው ኦቶሞቢሎች

እንደባለቤቱ ፍላጎት ሲያስፈልግ በተፈጥሮ

ነዳጅ አሊያም በኢታኖል የሚንቀሳቀሱ

ናቸው። ከነዚህ ኦቶሞቢሎች ‘ፍሌክስ’

የተባለው ኦቶሞቢል ከብራዚል አልፎ

በሰለጠነችው አሜሪካ የፈላጊው ቁጥር

ከ20 በመቶ የበለጠ ዕድገት ማስመዝገብ

የጀመረው እ.አ.አ ከ2003 ጀምሮ ነው።

ብራዚል በኢታኖል የኃይል

ፍላጎቷን አሟልታ ከአንድ ሚሊየን

ለሚበልጥ ዜጋዋ የሥራ ዕድል

ከመፍጠሯም በተጨማሪ፣ ቴክኖሎጂውን

በመሸጥ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በማግኘት

በከፍተኛ ርቀት ዓለምን እየመራች ነው።

አሁን በየጊዜው እየነጠፈና ጣራ እየነካ

የመጣውን የነዳጅ ውዝግብ ለመፍታት

እንዲሁም የአካባቢ ብክለትን ለመቀነስ

እተለወጠ በመጣው የቴክኖሎጂ ሽግግር

ከብክለት የፀዱ የኃይል ምንጮች

የሚንቀሳቀሱ ኦቶሞቢሎች እየተፈበረኩና

ወደጎን እየወጡ መሆናቸውን በየጊዜው

የሚደመጥ ዜና ሆኗል።

በየጊዜው እየተመረቱ የሚወጡ

ከብክለት የፀዱ ቴክኖሎጂ የሚጠቀሙ

ኦቶሞቢሎችን በሚያስተዋውቀው

‹‹ካር መጋዚን›› በተባለ መፅሄትና

በየዓመቱ በየዘርፉ ለውድድር ቀዳሚ

ለሆኑት እውቅና በሚሰጠው የጊነስ ቡክ

በተቀመጠው መረጃ አሁን ከፍተኛ ቦታ

የተሰጣቸው የሀይብሪድና የኤሌክትሪክ

ኦቶሞቢሎች ናቸው።

‹‹ሀይብሪድ ካር›› ውሃ

ከተሰራባቸው የኬሚካል ቅንጣቶች

ከሀይድሮጅንና ከኦክሲጅን ሀይድሮጅንን

‹‹ኤሌክትሮሊስስ›› በተባለው የኬሚስትሪ

ዘዴ እየለየ ለኦቶሞቢል ኢንጂን በመቀለብና

ውሀን በተረፈ ምርት በማስወገድ

የሚንቀሳቀሱ ኦቶሞቢሎች ናቸው።

በዚህ ቴክኖሎጂ እንዲንቀሳቀሱና

ከተፈበረኩ ኦቶሞቢሎች በሚያወጣው

ጉልበትና ፍጥነት የአለምን ሪከርድ ሰብሮ

ባለፈው ሳምንት በጊነስ ቡክ የሰፈረው

በእንግሊዝ ሳንታ ሮድ ከተማ በተዘጋጀ

የሀይብሪድ ካር ውድድር አሸናፊ ለመሆን

የቻለው ‹‹ኢንፊኒቲ ኤም 35 ኤች›› የተባለ

ሥያሜ የተሰጠው ኦቶሞቢል ነው።

ዘመናዊ ከሆኑት ከቢኤም

ደብሊው 5 ሲፊየስና ከጃጓር ኤክስ ኤፍ

ዲዛይን ጋር ተመሳስሎ የቀረበው ‹M35H›

3.5 ሊትር ሀይድሮጅን ወደኤሌክትሪክ

በሚቀይሩ በድምሩ 302 የፈረስ ጉልበት

በሚያመነጭ v-6 በተባለ ኢንጂን በሰዓት

105.95 ኪሎ ሜትር በመክነፍ ውድድሩን

ምንም ብክለት በሌላቸው ‹‹ዜሮ ኢሚሽን›› የተባሉ

ከባትሪ የሚያገኙትን ኃይል ወደ ኤሌክትሪክ እየለወጡና

የኤሌክትሪክ ሀይል እየተሞሉ ከሚጓዙ ኦቶሞቢሎች

ሪከርዱን በስማቸው ያስመዘገቡት ለመኪና ውድድር ስፖርት

የተዘጋጀው ‹‹አክሲራይድ›› እና ለሰው መጓጓዣ የተዘጋጀው

‹‹ብላክ ከረንት›› የተባለው ኦቶሞቢል ነው።

ያጠናቀቀው በአማካይ እያንዳንዱን አንድ

አራተኛ ማይል (402.3 ሜትር) በ13.9

ሰከንድ በመክነፍ ነው።

በኢታኖል ከሚከንፉ

ኦቶሞቢሎች ቀዳሚ የሆነው የብራዚሉ

ሥሪት ፍሊክስ ሙሉ በሙሉ ከብክለት

የፀዳ ባለመሆኑ ከብክለት ከፀዱት ጋር

ለውደድር ባይቀርብም የአምሳዮቹን

ሪከርድ የሰበረው በሰዓት 364.6 ኪሎ

ሜትር በተመዘገበ ፍጥነት እንደሆነ የጊነስ

መረጃ ይጠቁማል።

ምንም ብክለት በሌላቸው

‹‹ዜሮ ኢሚሽን›› የተባሉ ከባትሪ

የሚያገኙትን ኃይል ወደ ኤሌክትሪክ

እየለወጡና የኤሌክትሪክ ሀይል እየተሞሉ

ከሚጓዙ ኦቶሞቢሎች ሪከርዱን በስማቸው

ያስመዘገቡት ለመኪና ውድድር ስፖርት

የተዘጋጀው ‹‹አክሲራይድ›› እና ለሰው

መጓጓዣ የተዘጋጀው ‹‹ብላክ ከረንት››

የተባለው ኦቶሞቢል ነው።

በእንግሊዛዊ ወንድማማቾች

በኦሊ እና ሳም ያንግ ለሰው መጓጓዣ

የፈበረኳት ‹‹ብላክ ከረንት›› ጠቅላላ

የውጭና የውስጥ ዲዛይኗ የተወሰደው

እ.አ.አ በ1965 ለመጀመሪያ ጊዜ ጎዳና

ከወጣችው ከቮልስ ዋገን ነው። ይህን

ዲዛይን ተላብሳ በሰኔ 16/2011 በእንግሊዝ

ኖርዝ ሀምብተን በተካሄደ የኤሌክትሪክ

መኪናዎች ውድድር አዲስ ሪከርድ

ያስመዘገበችው ከቆመችበት ተነስታ በሰዓት

96.5 ኪሎ ሜትር እየከነፈች ውድድሩን

በቀዳሚነት ያጠናቀቀችው እያንዳንዳቸው

12 ቮልት የሚያመነጩ 60 የሞተር

ሳይክል ባትሪዎች የተገጠሙላት በመሆኗ

ነው።

ለመኪና ውድድር ስፖርት

ከተዘጋጁ ባትሪን ወደ ኤሌክትሪክ

ኃይል ከሚለውጡ መኪናዎች ወደጃፓን

የማቱሺታ ኤሌክትሪክ ኢንዱስትሪያል

ካምፓና የበኦሳካ ሳንጊዩ ዩኒቨርስቲ

ለውጤት ያበቃችው ‘ኦክስራይድ’ ከባትሪ

ከምታገኘው ኃይል የአምሳያዎቿን

የፍጥነት ወሳን የሰበረችው በሰዓት

105.95 ኪ.ሜ. የመክነፍ ብቃት ተላብሳ

ወደጎንና በመውጣቷ ነው።

በቀጥታ ከኤሌክትሪክ ሀይል

ማመንጫ የኤሌክትሪክ ሀይል የሚሞሉና

ይህን ሀይል አምቀው ከሚያስቀምጡ

ካፓሲተሮች ኃይል እየተመገቡ ከሚከንፉ

መኪናዎች የአለም ክብረወሰን ባለቤት

‹‹ፎርሙሊክ EFOL›› የተባለችው

ኦቶሞቢል ነች።

ፓሪስ በሚገኘው ፎርሙሊክ

ካምፓኒና ከፍተኛ አድናቆትና ውደሳ

የተላበሰችው ፎርሙሊክ ከብክለት

የፀዳች ከመሆኗ በተጨማሪ ኃይልን

በመቆጠብና በፍጥነት በመክነፍ ያላትን

ብቃት በሚተነትነው መረጃ በሰዓት

እስከ 260 ኪ.ሜ. ፍጥነት እያቀያየረች

መጓዝ ትችላለች። ይህ ፍጥነቷ ፎርሙላ

3 ከተባሉ ለመኪና ውድድር ስፖርት

ከተዘጋጁ በተፈጥሮ ነዳጅ ከሚከንፉ

መኪናዎች የሚቀራረብ ከመሆኑ

በተጨማሪ ቀጥ ባሉ ጎዳናዎች ከበካዩቹ

ኦቶሞቢሎች ጋር ለውድድር መቅረብ

የምትችል ናት። አንድ ጊዜ በተሞላቸው

የኤሌክትሪክ ሀይል በምትጓዝበት ጎዳና

ጠመዝማዛነት ወጣ-ገባነት ላይ የተመረኮዘ

ቢሆንም፣ እንደገና የኤሌክትሪክ ቻርጅ

የምትሞላው ያለማቋረጥ ከተጓዘች ከአንድ

እስከ አንድ ሰዓት ተኩል በሚረዝም የጊዜ

ልዩነት ነው።

በዓለማችን የኦቶሞቢል

አምራች ድርጅቶች እየተጠናከረ በመጣው

ከብክለት የፀዱ ኦቶሞቢሎች ግንባታ ገበያ

የሚቀርቡ ኦቶሞቢሎች የሚመዘኑት

በዋጋቸውና ኃይልን በመቆጠብ ብቃታቸው

ነው።

እንደዛሬው ነዳጅ በበርሜል

ከ100 ዶላር በላይ ጣሪያ ነክቶ ባለሀብቶች

ከተራው ሰው ጋር በአውቶቡስና በባቡር

ለመሄድ ከመገደዳቸው በፊት የኦቶሞቢል

ካምፓኒዎች ትኩረት ባለሀብቶችን

ከተራው ሰው ለይተው በጎዳና ላይ

የሚያንደላቅቁ የኦቶሞቢል ዲዛይኖችን

ለገበያ ማቅረብ ነበር። ይህንን መመዘኛ

በመንተራስ ከ1950ዎቹ ወዲህ ከተፈበረኩ

ኦቶሞቢሎች ጣራ በነካ ዋጋ በመሸጥ

እስካሁን ሪከርዱን ይዞ የዘለቀው እ.አ.አ

በ1963 ቼሪስ ኢቫንስ የተባለው እንግሊዛዊ

ባለሀብት በ17,275,00 ዶላር በአሁኑ

የገዛት ፌራሪ 250GT የተባለች ኦቶሞቢል

ናት።

በተመረተ በአንድ ዓመት

ውስጥ ከፍተኛ ሀብት ባስመዘገበ ከፍተኛ

ሽያጭ የዓለማችን ባለሀብቶች በብዛት

ቀዳሚ ሆነው የሸመቱት እ.አ.አ በ1997

እያንዳንዱ በ1,547,620 ዶላር ለገበያ

የቀረበው ‹‹ሜርሴዲስ ቤንዝ CLK/LM

የተባለው ኦቶሞቢል ነው።

ፅሁፋችንን የምንቋጨው

በአብዛኛው የዓለም ህዝብ ጆሮ ያልደረሰውን

ባለፈው ሳምንት ጥቅምት 20/2011 በጊነስ

ቡክ አዲስ የዋጋ ሪከርድ ያስመዘገበውን

ተንቀሳቃሽ የቤት ኦቶሞቢል (Luxury

motorhomes) በማስተዋወቅ ነው።

ባለፈው ሳምንት በኦስትሪያ

ተዘጋጅቶ በከተማዋ ጎዳና በመንፈላሰስ

ለዕይታ የበቃው ‹‹The eleMMent››

ውድ ተንቀሳቃሽ የቤት ኦቶሞቢል

ባለአምስት ኮከብ ሆቴሎች ውስጥ የሚገኙ

መጠጥ ቤቶች የሚሰጡትን አገልግሎትና

ውበት የተላበሰ ተንቀሳቃሽ መኪና ነው።

የተደራረቡ ሁለት ጥንድ መኪናዎች

የሚመስል ገፅታ በተላበሰው በላይኛው

ክፍል አሥራ-ሁለት ሜትር ርዝመት ወደ

ጎን ተዘረጋግቶ የሚጋጠም 30 ስኩየር

ሜትር ስፋት ያለው መኖሪያ ይገኛል።

ከታች ያለው መኪና ከላይ

የተሸከመውን መኖሪያ ይዞና እስከ 20 ቶን

ክብደት ተሸክሞ በሰአት 150 ኪሎ ሜትር

የሚከንፈው 510 የፈረስ ጉልበት ባለው

ሞተር ነው።

ከላይ ወዳለው መኖሪያ

ስትዘልቁ በዋናው መኝታ ቤት በቁሳቁስ

የተሞላ የተንጣለለ አልጋና 40 ኢንች

ስፋት ያለው የሳተላይት ቴሌቭዥን፣

የኢንተርኔት ሞባይልና የቪዲዮ ማሳያ

ዴኮችን ትመለከታላችሁ። መኝታ ቤቱን

በማለፍ ወደ ውስጥ ስትዘልቁ ዘመናዊ

የመታጠቢያ ገንዳ ያለው ክፍልና የመፀዳጃ

ክፍሎችን ታገኛላችሁ። በታችኛው ሹፌሩ

በሚቀመጥበት ክፍል የሹፌሩ ማረፊያ

አልጋ የተዘረጋበት ክፍልና የእንግዳ

መቀመጫ ሳሎን የያዘ ነው። ይህ ዘመናዊ

ኦቶሞቢል እና ተንቀሳቃሽ መኖሪያ ግንባሩ

ላይ በተለጠፈው የፀሐይ ብርሀን ወደ

ኤሌክትሪክ ሀይል ከሚለውጥ መስታወት

በሚያገኘው ሀይልና ነዳጅን በ20 በመቶ

በሚቆጥብ ኢንጂን ነው።

ይህ ብቃት ተላብሶ ለውጤት

የበቃውን ኦቶሞቢል ተንቀሳቃሽ መኖሪያ

ከተሸከሙ ኦቶሞቢሎች በዋጋ ውድነቱ

የጊነስን ሪከርድ የሰበረው ኦቶሞቢሉን

የፈበረከው ማርቺ ሞባይልስ የተባለው

የኦስትሪያ ካምፓኒ የመሸጫ ዋጋው

2.96 ሚሊየን ዶላር ወይም 49 ሚሊየን

ሶስት መቶ ሺህ ብር መሆኑን። ወዳጁ

ባለሀብቶች፣ ይወቁልኝ ማለቱን ተከትሎ

ነው።

ዓለማዊ ወግ...

‹‹የለም፤ ስለየኔታ ሳይሆን ስላንተ

ከየኔታ የሰማሁት ነገር አለ›› አለኝ።

‹‹ምን?››

‹‹አብዷል ብለው ስላንተ

ማበድ ነገሩኝ››

‹‹እኔ! እኔ አብጄ?›› ባጣም

ተደናግጬ ነበር የጠየቅሁት።

‹‹ኋላ እኔ ነኝ ያበድኩት!››

በማለት ሲያሾፍብኝ የኔታ ታላቅ ደባ

እንደሰሩብኝ አወቅሁ። ቅድም ወደ

ትምህርት ስሄድና ስደርስ የተገጠመውን

ግጥም አሰብኩ።

ለምንት አንገለጉ አሕዛብ

ወሕዝብኒ ነበቡ ከንቶ

መቸ በከንቱ ነው ልባቸው

ተነክቶ

የኔታ አበሳጩኝ። እኔ

ወደ ትምህርት ሳልደርስ በፊት እኔን

ሲያሙኝ እንደነበረ ገባኝ። ተማሪዎች

ደግሞ ተታለውላቸዋል። እንዴት

አንድ የቅስና መምህር በቂም በቀል

ተማሪውን ያማል? አስማማውን

አከበርኩት። እውነትም ከቅስና በፊት

ቅድስና መብለጥ አለበት።

‹‹ሌላስ የነገሯችሁ ነገር

አለ?›› አልኩት። ‹‹የለም፤ ሌላ እንኳ

አልሰማሁም።››

ደስ አለኝ። ማን ተማን

ያንሳል። እኔን እንዳሙኝ እኔም

ጉዳቸውን አወጣዋለሁ።

ስለየኔታና ‘ኔ ሁሉንም ነገር

ለአስማማው ነገርኩትና “ታዲያ ምን

እንዳደርግ ትመክረኛለህ?›› አልኩት።

ፈላስፋው ብዙ ጊዜ ወስዶ ሲያስብ ቆየ፤

‹‹እኔ አንተን ብሆን?›› አለና አጓጓኝ።

ምርጥ ሀሳብ እንዳሰበ ስለገመትኩ

በትዕግስት መጠባበቅን መረጥኩ።

‹‹አንድ ነገር ልንገርህ

እንዳለው? ጥፋ!!! እኔም ወደዚያው ነኝ

. . . እዚህ ተምረን ምን ልንፈጥር

ነው? መቸም ስምንተኛው ሺህ ደርሶ

ነው እንጂ መሪጌቶች ሁሉ እንዲህ

ሁነው የተበለሻሹ የጤና አይመስለኝም

‘ና ጥፋ!!!››

‹‹ጠፍቸስ የት እሄዳለሁ?››

‹‹አዲስ አበባ ሂድ፤ እኔም

ወደዚያው ነኝ!››

‹‹እዚያ ሄደህ በምን

ትተዳደራለህ? እኔስ በምን እንድተዳደር

ትመክረኛለህ?››

‹‹ፈራህ እንዴ? እኔ አንዲት

በምስጢር የማዘጋጃት ጉዳይ ስላለችኝ

ነው እንጂ አብረን እንሄድ ነበር። ጥፋ’ና

አንድ ቀን እንገናኛለን፡፡››

አዲስ አበባ ቁራሽ የሚለምን

ሰው ‘ለማኝ’ ነው እንጂ የቆሎ ተማሪ

አይደለም። እኔ ደግሞ በስደት አዲስ አበባ

ገብቸ ግራ ገብቶኛል። የምሰራውም፣

የምበላውም እያጣሁ እግሬ እስኪያጥር

ድረስ ስዞር እውላለሁ። ከሀገሬ እያለሁ

ስለ አዲስ አበባ ብዙ ሲወራ እሰማ ነበር።

“የአዲስ አበባ ውኃ ምግብ ነው” ያሉትን

ሰምቸ እንደመጣሁ ብዙ ውኃ ጠጣሁ።

የተረፈኝ ነገር ቢኖር ግን በየደቂቃው

ሽንቴን በየአጥሩ ጥግ መሽናት ነበር።

መቸም የኔ መጥፊያ ሽንት

ነው። ከሀገሬ የተሰደድኩት በሽንት

የተነሳ ከየኔታ ጋር ተቀያይሜ ነው።

አዲስ አበባ ደግሞ አንድ አጥር

ጥግ እግሬን አንቧትሬ ስሸና አንድ

ወጠምሻ እንደ ድመት ጋማዬን ይዞ

አንጠለጠለኝ።

ሁለት ወይም ሶስት ጊዜ

የካልቾ ድምጽ መስማቴ ትዝ ይለኛል።

ከዚያ ወዲያ እንዴት እንደመታኝ፤

መቸ እንደመታኝ ሳይታወቀኝ ሰውነቴ

ቆሳስሎና ደክሞ ተገኘሁ። አጥሩን

ተደግፌ ለሰባት ትውልድ የሚበቃ እንባ

አፈሰስኩ። አሁን እኔ ሰው ነኝ? ወይስ

የካራቴ መለማመጃ ከረጢት? ማልቀሱ

ሲደክመኝ ማልቀሴን ትቸ በእግሬ

መጓዝ ጀመርኩ።

ብዙ መንገድ በእግሬ

ተጉዤ ቀና ስል የባህል ህክምና የሚል

ማስታወቂያ አየሁ፡፡ በተላላኪነት እንኳ

ቢቀጥሩኝ ብየ ወደዚያው አመራሁ።

እንደውም ሳስበው

21

አስማማው በምስጢር የማዘጋጃት ጉዳይ

ስላለችኝ ነው ያለው ስራ-ስር ሊለቅምና

እዚህ መጥቶ አዋቂ ነኝ ሊል እንደሆነ

ገምቸ ነበር። አዲስ አበባ እንደሆነች

ትንሽ ግዕዝና የገጠር አማርኛ የሚችል

ሁሉ የባህል መድኃኒት እና የድግምት

አዋቂ የሆነባት ከተማ ናት።

የባሕል ሐኪሙ ዘንድ

ደንበኛ የሆኑ ብዙ ሰዎችን አገኘሁ።

ከእነዚህም መካከል ዘፋኞች፣ አትሌቶች፣

አርቲስቶች፣ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣

የፓርላማ ተወካዮች፣ የተለያዩ

ሃይማኖቶች መሪዎች፣ የጥቃቅንና

አነስተኛ ንግድ ባለቤቶች ወዘተ ይገኙበት

ነበር። ሌሎችን የተመለከቱ መረጃዎችን

ሳምንት እንደምነግራችሁ ቃል በመግባት

አሁን ግን ከአንዱ ዘፋኝ ጋር ያደረኩትን

ንግግር ሳልደብቅ ላጫውታችሁ።

አቋሙ ከሲታ ነው። እንደ

እውነቱ ከሆነ ከዚህ ግለሰብ የሚወጣው

ድምጽ ሕዝብን ያዝናናል ከማለት

ይልቅ ያሳቅቃል ብሎ መገመት ያሸልም

ይሆናል። ጉሮሮው ላይ ያለውን ክርክር

የተመለከተ ያዝንለታል እንጂ ዘፍኖ

ያዝናናኛል ብሎ ተስፋ አይጥልበትም።

‹‹ምነው ‘ጓዴ! ምን እግር

ጥሎህ መጣህ?›› ይህ የእኔ ጥያቄ

ነበር።

ሰውየው የዋዛ አልነበረም።

እንደሚከተለው አማረረ፡-

‹‹አንድ አይሉ ሁለት ካሴቶችን

ሰርቻለሁ ግን ከአንድ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር

ሰላሳ ሰው እንኳ አልሰማኝም። ድምጤ

እግዚአብሔር ይመስገነው ደህና ነው!

ያለመደመጤ መንስኤ ምን እንደሆነ

ስላላወቅሁት የሆነ መተት ሰርተውም

ቢሆን አኒህ ቅዱስ አባታችን በቢል-

ቦርድ ላይ ቁጥር አንድ እንዲያደርጉኝ

ለመለመን ነው የመጣሁት። እንዴት

ነው፤ የሚሳካልኝ ይመስልሃል?››

በእውነቱ ይህንን ሲጠይቀኝ

የምመልሰውን አጥቼ ነበር። ይሁንና

ስለያሬዳዊ ዜማ ከሚያወቁት ወገን ነኝና

‹‹ስለ ኢትዮጵያ ቅኝቶች፣ ማለቴ የዜማ

ዓይነቶች ምን ታውቃለህ?›› አልሁት።

ተረጋግቶ እየመለሰልኝ

ነበር፤ ‹‹ስለዜማ ዓይነቶች በማወቅ

እና በመመራመር የሚያህለኝ የለም።

ከፈለግህ የተመኘኸውን ጠይቀኝ›› በማት

በኩራት መለሰ።

‹‹እንግዲያው እየጠየቅሁህ

አይደለምን፤ ስንት የዘፈን፣ ማለቴ የዜማ

አይነቶች አሉ?››

‹‹አራት ናቸው›› ብሎ ሲመልስ

አከበርሁት። ‹‹እስቲ ዘርዝራቸው››

ይህንን የጠየቅሁት ስለ አንባሰል፣

አንች ሆዬ፣ ባቲ እና ትዝታ እውቀት

ስላለኝ ነበር። እርሱ መመለስ ጀመረ፡-

“የኢትዮጵያ ዘፈኖች በአራት ይከፈላሉ።

እነሱም የሀዘን፣ የጦርነት፣ የሥራ እና

የሠርግ ተብለው ነው›› አለ፡፡ ኩም

አልኩ፡፡ /ይቅርታ አሁን ስለተበሳጨሁ

ሌሎችን እንዴት እንዳናገርኋቸው?

መናገር አልችልም፤ ሳምንት ጠብቁኝ።/

የሄድኩበት የባህል ሀኪም

ዓነተ--ብዙ የሆኑ ጥያቄዎችን እየጠየቀ

ሲያውጣጣኝ ቆየ። እኔ ምኔ ሞኝ? አሻፈረኝ

አልሁ! የማውቀው መድኃኒት ቢኖር

እንዴት እንደሚቀመም ሊያውጣጣኝ

አይደል? ምንም ስላልነገርኩት ተበሳጭቶ

የታሰረ ውሻ ፈትቶ ለቀቀብኝ። ሮጬ

አመለጥሁ። ወዲያው ሊታከም ይመጣ

ከነበረ አንድ ወጣት ጋር ግቢው ፊት

ለፊት ተገናኘን።

‹‹የሃኪሙ ቤት እዚህ ነው?››

አለኝ ወጣቱ

‹‹አዎ! ምን ፈልገህ ነው?››

ወጣቱ ገልመጥመጥ ብሎ አካባቢውን

ተመለከተና፣ ‹‹ፍቅር ይዞኝ . . .

መስተፋቅር . . . ››

‹‹ስንት ትከፍላለህ?›› አልኩት

እንዲህ አይነት ትልቅ ሲሳይ ተገኝቶ

ማለፍ ሞኝነት መሰለኝ።

‹‹የተጠየቅሁትን እከፍላለሁ››

አለ ወጣቱ ባለማመን። ‹‹እሺ አንድ ቦታ

ተቀምጠን እናውራ፤ የደረሰብህን ፍቅር

በደንብ አብራተህ ልትነግረኝ ይገባል።››

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

22

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሁለት ዓመት

የስራ ጉዞን እንዴት ይቃኙታል?

ይህ ፌዴሬሽን ብዙ ችግሮች በነበሩበት ጊዜ

የመጣ ስለ ነበር ነገሮችን ስርዓት ለማስያዝ ብዙ ስራ

ሰርቷል። እግር ኳሳችን በውጤት ደረጃ ደካማ በመሆኑ

የህዝቡን ፍላጎት ማሟላት አልቻለም። በዘርፉ ያሉን

ባለሙያዎች በቂ አይደሉም። ባለን አቅም ስራዎችን

ተከፋፍለን ለመስራት ሞክረናል።

በወንዶችም ሆነ በሴቶች በዓለም አቀፍ

ውድድሮች ላይ ተካፋይ ነበርን። የእውነት ነው

የምልህ ሴቶቹ ላይ የቻልነውን ያህል በጣም ብዙ ስራ

ሰርተናል። ያው እንደምታውቀው የሴቶች ኦሎምፒክ

ቡድናችን የለንደን ኦሎምፒክን በር አንኳኩቶ

በመጨረሻው ጨዋታ በደቡብ አፍሪካ በመሸነፉ ሳይገባ

ተመልሷል።

ሴቶች እግር ኳስ ተጨዋቾቹን ፌዴሬሽኑ ሰርቶባቸው

የተገኙ ናቸው ማለት እንችላለን?

ፌዴሬሽኑ ከታች ሰርቶባቸው የመጡ

ባይሆኑም ከመጡ በኋላ ቀባብተን (በአግባቡ በመያዝ)

እንደቀድሞው ጊዜ በሴቶች ለዓለም አቀፍ ውድድር

በራችንን ሳንዘጋ ሰርተንባቸዋል። ረዥም ጊዜ አብረው

እንዲቆዩ በማድረግ፣ የኪስ ገንዘብ፣ ሽልማትና

የሚፈልጉትን ነገር በማሟላት ጥሩ የሚባል ውጤት

ላይ ደርሰዋል። ብዙ ብር ስላፈሰስንባቸው አንፀፀትም።

ምክንያቱም ልጆቹን ክለቦች እየያዟቸው ነው።

በ2004 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ

ቡድኖች የሴት ቡድን መያዝ የግድ እንዳለባቸው

ስትገልፁ ቆይታችሁ ሀሳባችሁን በመቀየር ወደ 2005

ዓ.ም. አምጥታችሁታል። ምክንያታችሁ ምንድን

ነው?

ወደ 2005 ዓ.ም. የተገፋው አንዳንድ

ቡድኖች የመዘጋጃ ጊዜ እንዲኖራቸው ተብሎ ነው።

በዚህ ዓመት በሁለተኛ ወር፣ በአራተኛ ወር ወይም

በአንዱ ወር ቡድን ሊያቋቁሙ ይችላሉ። ይህን

የሚቆጣጠር አካል አለ። በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ

እና ኮንፌዴሬሽን ካፕ ላይ የሚካፈሉ ሁለት ክለቦች

የሴት እና የታዳጊ ቡድን ከሌላቸው በጭራሽ መወዳደር

አይችሉም ተብሏል፤ በካፍ።

እውን ይህ አስገዳጅ ህግ ነው?

በአዲስ አበባ በተካሄደው በ‘Win in Africa

with Africa’ የክለብ አመራሮች ስልጠና ላይ ክለቦች

በ2004 የሴት ቡድን ለማቋቋም ውሳኔ ላይ ደርሰው

ነበር።

ክለቦች ‹‹በዚህ ዓ.ም. የሴት ቡድን ይኖረኛል›› ብለው

ቃል ሊገቡ ይችላሉ። የእኔ ጥያቄ ህጉ አስገዳጅ

ነወይ ነው? እንደዚያ ከሆነ የእንግሊዙ ታላቅ ክለብ

ማን.ዩናይትድን ጨምሮ ያሉ የሴት ቡድን የሌላቸው

ክለቦች ሊታገዱ ነው ማለት ነው?

ማን.ዩናይትድ የሴት ቡድን እንደሌለው

እርግጠኛ ነህ?

በጣም፤ የለውም።

እኔ መረጃው የለኝም። እንዲኖራችሁ ስለተባለ

የተወሰኑ ክለቦች የሴት ቡድን አቋቁመዋል። የተወሰኑ

ክለቦች ደግሞ ‹‹ለከርሞ እንጂ ለዘንድሮ አናዘጋጅም››

ብለዋል። እንደዚህ እየተባለ ከተሄደ በሚቀጥለው

ዓመትም ዋስትና አይሰጥም። በተለየ ይህን ሁኔታ

የሚከታተለው የሊግ ኮሚቴ ነው። እነሱን ብትጠይቅ

የተሻለ መልስ ይሰጡሀል።

2005 ዓ.ም. መጨረሻ የስራ ጊዜያችሁ ስለሚያበቃ

‹‹የሴት ቡድን አቋቁመው ወጡ›› መባልን

ስለምትፈልጉ ገደብ ያላችሁትን እንዳዘዋወራችሁት

የሚናገሩ አሉ። ይስማማሉ?

አንድ ስራ ስትሰራ ግላዊ ሳይሆን ተቋማዊ

በሆነ መልኩ ሊሆን ይገባል። እኔ የጀመርኩትን

ሁሉ ጨርሼ ሄዳለሁ ማለት አይደለም። ሳንሰራው

ለሌላው አስተላልፈን ለመሄድ ብቻም አንሰራም። ብዙ

የሰራናቸው፣ ብዙ የቀሩ ነገሮች አሉ። የቻልነውን

ያህል እንሰራለን።

የአፍሪካ ሴቶች ሻምፒዮና ቅድመ ማጣሪያ በጥር ወር

የመጀመሪያ ሳምንት ይደረጋል። ኢትዮጵያ ከግብፅ

መመደቧ ይታወቃል። ዝግጅት መቼ ለመጀመር

አሰባችሁ? [ወ/ሮ ጥሩወርቅ የብ/ቡድኑ የቡድን መሪ

ናቸው።]

የጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ በተደረገበት ወቅት

ትኩረት ተሰጥቶት የተወያየነው በብሔራዊ ቡድን

ላይ ነው። በግልፅ መስተካከል ያለባቸው ነገሮች

ተቀምጠዋል። ‹‹የብሔራዊ ቡድን መተዳደሪያ

መመሪያ›› ወጥቷል። ይህ ከፀደቀ በኋላ ብ/ቡድን ለስንት

ቀን ልምምድ መስራት እንዳለበት ስለሚገልፅ በዚያ

መሰረት እንወስናለን። እርግጠኛ ባልሆንም ታህሳስ

ውስጥ ልጆቹ ተሰባስበው ልምምድ ይጀምራሉ ብዬ

ገምታለሁ። ከዚያ በፊት ውድድሮች ይኖራቸዋል።

የሴቶች ውድድር በእርግጠኝነት የሚጀመርበት ቀን

ይታወቃል?

ይህን የሚወስነው ሊግ ኮሚቴው ነው። ልጆቹ

በአሁን ሰዓት በየክለባቸው ልምምድ ላይ ናቸው።

[የኢትዮጵያ እና ግብፅ አሸናፊ በሰኔ ወር መጀመሪያ

ከናሚቢያ እና ታንዛኒያ አሸናፊ ጋር የመጀመሪያ ዙር

የማጣሪያ ጨዋታ ታደርጋለች።]

ከቀድሞው ፌዴሬሽን በተለየ የሰራችሁት ነገር እንደሌለ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ስ ፖ ር ት

አቤል ዓለማየሁ

የሚገልፁ አሉ። በሁለት ዓመት የስራ ጊዜያችሁ

በዋናነት ‹‹ሰርተነዋል›› የምትሉት ተጨባጭ ነገር

ምንድን ነው?

የእግር ኳስ ችግራችንን በአንድ የስራ ዘመን

(term) እንፈታዋለን ማለት አይቻልም። ቢያንስ

የቢሮውን አደረጃጀት መለወጥ አለብን። እኛ ስንመጣ

በጣም ጥቂት የነበረው የፅ/ቤት ሠራተኞች ቁጥር

ከማደጉም በላይ ቢሮው በብቃት እየተደራጀ ነው።

ራሱን የቻለ ቢሮ ያለው የዳኞች ኮሚቴ አልነበረንም፤

አሁን ኖሮናል። ፊፋ ይህን አይቶ ‹‹በብዙ አፍሪካ

አገሮች የሌለ ነው›› በማለት መሻሻላችንን አድንቋል።

የቴክኒክ ዳይሬክተር ባይኖረንም በቴክኒክ

ክፍል ውስጥ ብቁ ባለሙያዎችን ቀጥረናል። ስራዎችን

በየዘርፉ በመስጠታችን ለክተን እንደሰጠነው፣ ለክተን

መቀበል እንችላለን። ጉድለቶች ቢኖሩም እነዚህን

እንደ ትልቅ እድገት አያቸዋለሁ።

የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በእግር ኳሱ ላይ

በታሪክ የሚታወስ ስራ አከናውኖ የሚያልፍ

ይመስልዎታል?

ይህንን ካላደረግንማ መምጣትም

አልነበረብንም። ወደ ፌዴሬሽኑ ስመጣ ብዙ ነገር

ፈታለሁ ብዬ ሳይሆን ቢያንስ የተሻለ ነገር ከውናለሁ

በሚል ነው። ይህ ክፍል [ቆይታ ያደረግንበት

የፌዴሬሽኑ የዳኞች ኮሚቴ ቢሮ] በመኖሩ የዳኞችን

የፋይል አደረጃጀት ችግር ፈትቼ አልፋለሁ። ‹‹ዳኛው

ማን ነው? ምን ሰርቷል?›› የሚለውን መረጃ

ከሰበሰብን ማንም መጥቶ ስለ ዳኛው በቂ ነገር ማግኘት

ይችላል።

የዳኞችን ሙሉ መረጃ የሚይዝ ፋይል

ማደራጀታችሁ ጥሩ ስራ ቢሆንም በዳኞች ላይ ስራ

ለመሰራቱ ዋና ማሳያ ይሆናል ብዬ አላምንም።

መለኪያው የዳኞቹ ብቃት እንዲዳብር ምን ተሰራ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 191 ቅዳሜ ጥቅምት 18/ 2004

‹‹ፌዴሬሽኑ ውስጥ የምሰራው

ተመችቶኝ አይደለም››

ወ/ሮ ጥሩወርቅ ብርሃኑ

[የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን - የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል]

ስለ ፌዴሬሽኑ ሁለት የስራ ዓመታት፣ በዳኝነት ዙሪያ ስለሚታዩ ችግሮችና በሴቶች እግር ኳስ ዙሪያ የሚነሱ ጉዳዮችን

አስመልክቶ አቤል ዓለማየሁ ላቀረበላቸው ጥያቄዎች የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል

እና የዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ወ/ሮ ጥሩወርቅ ብርሃኑ ግልፅነት የተሞላው ምላሽ ሰጥተዋል።

አንድ ስራ ስትሰራ ግላዊ ሳይሆን ተቋማዊ በሆነ መልኩ ሊሆን

ይገባል። እኔ የጀመርኩትን ሁሉ ጨርሼ ሄዳለሁ ማለት አይደለም።

ሳንሰራው ለሌላው አስተላልፈን ለመሄድ ብቻም አንሰራም። ብዙ

የሰራናቸው፣ ብዙ የቀሩ ነገሮች አሉ።

የሚለው ነው።

ለምሳሌ ኢንተርናሽናል አርቢትር ባምላክ

ተሰማ ጥሩ ዳኛችን ነው እንበል። ዛሬ ሲያጫውት

ምንም ገላጭ ሰነድ ከሌለው በቀጣይ በአመራርነት

የሚመጣ ሰው ስለ እሱ በአገርም ሆነ በውጪ አገር

ስላጫወታቸው ጨዋታዎችና ሌሎች መረጃዎች

ሊኖሩት አይችሉም። ታዲያ እንዴት የፋይል

አደረጃጀት ዘዴ አያስፈልግም?

ፋይል መደራጀቱንማ አከብራለሁ። ልል

የፈለግኩት የተሻለ ለመሰራቱ ማሳያው የባምላክ

የዳኝነት ብቃት መጎልበት እንጂ የፋይሉ መደራጀት

አይደለም ለማለት ነው።

ያነሳሁልህ እንደ ምሳሌ ነው። እንደ ተቋም

መስራት ያለብን ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ነገሮች

ላይ ነው። ጨዋታን መሸከም የሚችል ብቃት

ያለው ዳኛ በቁጥርም፣ በጥራትም ሳናወጣ በዘርፉ

ለመስራታችን ማሳያ እንደማይሆን እናውቀዋለን።

የፋይል አደረጃጀቱ ግን ስራ ለመሰራቱ አንዱ ማሳያ

ሊሆን ይገባል።

መስከረም 26 እና 27/ 2004 ዓ.ም. በግዮን

ሆቴል በተደረገው የፌዴሬሽኑ የጠቅላላ ጉባዔ

ስብሰባ ላይ ከእርስዎ በ2012 ኢንተርናሽናል ዳኞች

እንደማይኖሩን ሲገለፅ ምናልባት ከንግግር ስህተት

ይሁን ከእኛ የአረዳድ ችግር ባላውቅም በተለያዩ

መገናኛ ብዙሐን ላይ ይሄው መረጃ ተላለፈ።

[ሳምንት እኔም ከጉባዔው በላይ ማንን ልመን ብዬ

ይሄንኑ መረጃ ገልጬ ነበር] ትንሽ የተዛባ ነገር

ያለ መሰለኝ። የሚታወቅበት ጊዜ ገና በመሆኑ

ኢንተርናሽናል ዳኛ ሆነው የሚቀጥሉ እንደሚኖሩ

እየሰማሁ ነው።

አንዳንድ ጊዜ ነገሮች ብድግ ይሉና በጣም

ተጋነው ቀርበው፣ ሰዎችን ወደ ስህተት ይመራሉ።

ካሉን 18 ኢንተርናሽናል ዳኞች ውስጥ [12 ወንድ

እና 6 ሴት] አንዷ ሴት ረዳት ዳኛ እና ሦስት ወንድ

ዋና ዳኞች በአካል ብቃት ፈተና ወድቀዋል። የወደቁት

ማላዊ ለድጋሚ ፈተና ከኪሳቸው ገንዘብ አውጥተው

ሄደው በድጋሚ ወድቀው መጡ። ይህ ማለት ካሉን

ኢንተርናሽናል ዳኞች ውስጥ ቁጥራቸው ያንሳል

እንጂ ምንም ኢንተርናሽናል ዳኛ የለንም ማለት

ከእውነት መራቅ ነው። ካፍ ይቀበለው/አይቀበለው

ባናውቅም 13 ኢንተርናሽናል ዳኖች [4 ዋና እና 9

ረዳት] በ2012ም ሊኖረን ይችላል። በወጡት ቦታም

ሌሎችን እንዲቀበሏቸው ጠይቀናል።

ኢንተርናሽናል ባጅ ያገኙት ዳኞችም ቢሆኑ የውጪ

ጨዋታዎች እንዲያጫውቱ ያን ያህል ሲጠሩ

አይታይም። ትክክል ነው?

በእኛ 2001 ዓ.ም. አንድ ወይም ሁለት

ጨዋታ ብቻ ነው የተጠሩት፣ 2002 ላይ ትንሽ

የተሻለ ነበር። 2003 በጣም የተሻለ ነበር፤ ከሴካፋ

እስከ አፍሪካ ታላላቅ ውድድሮች አጫውተዋል።

አንዳንድ ዳኞች ደግሞ ባጁን ይዘው አንድ ጨዋታ

ሳይዳኙ የሚወርዱ አሉ።

ባጁ የተሰጣቸው ብቁ ናቸው ተብለው ነውና ባጁን

ከማግኘት ባለፈ ተመድበው እንዲሰሩ ከካፍ ጋር

ግንኙነት ታደርጋላችሁ?

በዚህ ረገድ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ

ሳህሉ ገ/ወልድ እንቅስቃሴ በጣም ብዙ ነው። በካፍ

ስብሰባዎች ላይ ሲገኝ እና ኮሚሽነር ሆኖ በሄደበት

ሁሉ የካፍ ሰዎችን ሲያገኝ የእኛ ዳኞች እንዲመደቡ

ጥያቄዎችን ያቀርባል። እንደሚመደቡ ቃል እየገቡልን

ነው። እንዲበረቱ እና የአካል ብቃታቸውን እንዲያሻሽሉ

ይነግሩናል። ሊዲያ እና ትርሃስ በቅርቡ የመላው አፍሪካ

ጨዋታዎችን ላይ መርተው መጥተዋል። በቅርቡም

አራት ሴት ዳኞች ተመድበዋል። ወንዶቹም በቅርቡ

ወጥተው እንዲያጫውቱ ጥሪ መጥቶላቸዋል።

ሜዳ ላይ በግልፅ ብዙ ዳኞች ተሯሩጦ ማጫወት

የሚያስችል የአካል ብቃት ችግር እንዳለባቸው

እየታየ ነው። የፊሽካ ድምጾች በርቀት እየተሰሙ

ነው። ችግሮቹን ለመቅረፍ ምን እያሰባችሁ ነው?

ችግሩ መኖሩንስ ታምናላችሁ?

እሱማ ታየ። ዳኞች ተፈትነው ሲወድቁብህ

ችግሩ መኖሩን ትረዳለህ። ችግሩን ለመፍታት

እንደ ዳኞች ኮሚቴ ማድረግ ያለብን የአካል ብቃት

አሰልጣኞችን መጨመር ነው። በካፍ ሁለት

አሰልጣኞች (ቸርነት አሰፋ እና ኃይለመላክ ተሰማ)

ሰልጥነው መጥተዋል።

ክልል ላይ ተፈትነው የሚመጡ ዳኞች ፈተና

ምናልባት አጥጋቢ ላይሆን ስለሚችል ወደ ውድድር

ከማስገባታችን በፊት እንፈትናቸዋለን። ይህን ፈተና

ማለፍ ካልቻለ አይዳኝም። በዓመት በፊት አንድ የአካል

ብቃት ፈተና ያለፈ ዳኛ ዓመቱን ሙሉ ይዳኝ ነበር።

አሁን ግን ፈተናውን በዓመት አራት ጊዜ እያደረግን

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 191 ቅዳሜ ጥቅምት 18/ 2004

}SdeK¨< Ÿ}c\ ð×” ¾h¨` ¨

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!