26.07.2013 Views

መፈንቅለ መንግስት...

መፈንቅለ መንግስት...

መፈንቅለ መንግስት...

SHOW MORE
SHOW LESS

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 184 ቅዳሜ ጳጉሜ 5/ 2003

መልካም

ዓዲስ ዓመት

መልካም ዓዲስ ዓመት

የምንሻው

አጋርነት

በባራክ ኦባማ

/ፕሬዝዳንት/

‹‹በአዲሱ ዓመት ‘አሸባሪ’

ከመባል ይጠብቃችሁ››

ሰሞነኛ ምርቃት

ከታች ሰፈር ልጆች ጋር በኮሪያ- ዴጉ ተካሂዶ የነበረውን የአትሌቲክስ ሻምፒዮና

ፍፃሜ እየተመለከትን እያለ ምነው አትሌቶቻችን ውጤት ራቃቸው ብል እየተቀባበሉ

‹‹የሚወራውን አልሰማህም እንዴ?… ‘እያንጓለለ ካልተፈታ’ ብለው አድማ ላይ እኮ

4ኛ ዓመት ቁጥር 184 ቅዳሜ ጳጉሜ 5 2003 ዋጋ 7፡00 ብር

‹‹በቴሌቪዥን በሚሰሩት ‘ድራማ’ ሀቅ ሊወጣ አይችልም››

ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ

ለቢቢሲ ያወራነው በአደባባይ ነጋ ጠባ ስናወራው የነበረ ነው

የኢቴቪ ዘገባ ላይ የትርጉም ስህተቶች ነበሩ

አባሎቻችሁ ናቸው የተባሉ ሰዎችን አላውቃቸውም

የደርግ ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩትና ኋላ ላይም ስርአቱን በመክዳት ወደ ውጭ ያቀኑት

ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ከሁለት አስርት አመታት በኋላ ሰሞኑን የመጀመሪያ

የሆነውን ይፋዊ ቃለምልልስ ሰጥተዋል። ግንቦት 8 ቀን 1981 ዓ.ም ስለተደረገው

መንፈንቅለ መንግስት፣ደርግን ሥርዓት ለመጣል ይፋለሙ የነበሩትን ሻዕቢያና ህወሀትን

በማግባባት ረገድ ምን ሚና እንደተጫወቱ፣ በወቅታዊው የኢትዮጵያ ፖለቲካና

እስካሁን ይፋ ባልተደረጉ በርካታ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ በዝርዝር ይናገራሉ፡

“የ1981 መፈንቅለ መንግስት

ለማድረግ ከሻዕቢያና ከወያኔ ጋር ተስማምተን ነበር”

በ ገፅ 16

በውስጥ ገፅ በውስጥ ገፅ በውስጥ ገፅ

እንቁጣጣሽ

Vs

ቅዱስ ዮሐንስ

በ ገፅ 20

ደበበ እሸቱ እንዲፈታ አንድነት/መድረክ ጠየቀ

• ‹‹መንግስት ሕዝቡን እያሸበረ ነው››

‹‹ኢህአዴግ ሁለት ሰዎች ድንበር አቋረጡ ብሎ ሊጨነቅ ቀርቶ አገር ገንጥሎ የሚሰጥ ድርጅት ነው››

በሱራፍኤል ግርማ

መንግስት በአሸባሪነት ከፈረጀው ግንቦት ሰባት ጋር ‹‹የሕቡዕ ግንኙነት አለው›› በሚል ምክንያት ለእስር

የተዳረገው አንጋፋው አርቲስትና ፖለቲከኛ ደበበ እሸቱ እንዲፈታ የመድረክ አመራር አባላት ጠየቁ።

ምንም እንኳን የአቶ ደበበን መታሰር አስመልክቶ ለብሉም በርግ አስተያየታቸውን የሰጡት የመንግስት

ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ሽመልስ ከማል ‹‹ከአሸባሪው ግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አለው፤

የሚስ አብዮታዊ ዴሞክራሲ

ልማታዊ ውበት ምስጢር

አንባብያን ሆይ! የተያያዝነውን የሀገር ገፅታ ግንባታ በማስቀጠሉ ረገድ ጉልህ ሚና

እንደሚጫወት የታመነበት ታላቅ ውድድር በቅርቡ መካሄዱ ይታወቃል። በውድድሩም

በታሪካችን ለመጀመሪያ ጊዜ የብሔር ብሔረሰቦችን እኩል ተሳትፎ ባረጋገጠ መልኩ ከተለያዩ

የኅብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጣ የልማታዊ ዳኞች ቡድን፣ የልማታዊ ውበትን እሳቤ የተላበሰች

ቆንጆ መርጦ “ሚስ አብዩታዊት ዴሞክራሲ” ሲል ሰይሟል። ወርቃማው የአሸናፊነት ዘውድ

በክብር ከተጫነላት ወጣት ጋር ልማታዊው ጋዜጠኛችን ቀጣዩን አጭር ቆይታ አድርጓል።

ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ

ናቸው›› አሉኝ። ምን ለማለት ፈልገው እንደሆነ ግን አልገባኝም፡፡

በ ገፅ 9

በ ገፅ 21

በ ገፅ 9

በ ገፅ 7

ማብቂያ የለሹ የኢትዮጵያዊያን ሰቆቃ

በመካከለኛው ምስራቅ?!

አሜሪካ ስለኢትዮጵያ

ምን ታስባለች?

አዳዲስ የዊክሊክስ

መረጃዎች ይናገራሉ

ጠ/ሚኒስትሩ የወታደራዊ ኃይል

የበላዩ ጄኔራል ሳሞራ እና የደህንነት

ክፍሉ ሃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋ

አሜሪካ የኢትዮጵያን የደህንነት

አሳሳቢ ጉዳዮች ጉዳዬ ትላቸው

እንደሆን እምነቱ ተመናምኖባቸዋል

እስከማለት ደርሰዋል። እነዚህ

ሁለቱ ባለሥልጣናት ጦረኛ ነገር

ግን በውጭ ፖሊሲ ጉዳይ ላይ

እጅግ ተፅዕኖ ፈጣሪ የገዢው

ፓርቲ አባላት ናቸው።

5

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

2

የካቲት 2000 ዓ.ም ተመሠረተ

አውራምባ ታይምስ፡- በብሉ

ኤርዝ ጀነራል ቢዝነስ ኃላ/የተ/

የግል/ማህበር ስር የሚታተም፤

በፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ

የሚያተኩር፤ በንግድ ሚኒስቴር

በቁጥር 020/2/6572/2001

የተመዘገበ ሳምንታዊ ጋዜጣ ነው፡፡

T’@Í=”Ó ›?Ç=}`

Ç©ƒ ŸuÅ

ª“ ›²ÒÏ

õì

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 184 ቅዳሜ ጳጉሜ 5/ 2003

መልካም ዓዲስ ዓመት

በባራክ ኦባማ

/ፕሬዝዳንት/

በዚህ የመስከረም

1፣ 1993 የሽብርተኞች ጥቃት

10ኛ ዓመት መታሰቢያ፣ የሽብር

ጥቃቱ በዩናይትድ ስቴትስ

ላይ ብቻ ሳይሆን፣ በዓለም

እንዲሁም በሰብዓዊነት እና

በጋራ ተስፋዎቻችን ላይ የተቃጣ

መሆኑን እናስታውሳለን።

በዚያን ዕለት

ሕይወታቸውን ካጡት ወደ

3ሺህ የሚጠጉ ንፁሀን ሰዎች

ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩት

ከ90 የሚበልጡ አገራት ዜጎች

እንደነበሩም እናስታውሳለን።

በርካታ ዘሮች እና እምነቶች

ያሏቸው ወንዶችና ሴቶች፣

ወጣትና አዛውንትም ነበሩ። በዚህ

የሐዘን መታሰቢያ የእነርሱን

ትውስታ ከቤተሰቦቻቸው እና

ከየአገሮቻቸው ጋር በመሆን

በአክብሮት እንዘክራለን።

የዛሬ አሥር ዓመት

ዓለም እንደ አንድ የተሰባሰበበትን

ሁኔታ ከምስጋና ጋር

እናስታውሰዋለን። በዓለም ዙርያ

ያሉ ከተሞች በሙሉ ለደቂቃ

በሕሊና ፀሎት እረጭ ብለው ነበር።

ሰዎች በአብያተ-ክርስቲያናት፣

በመስጊዶች፣ በምኩራቦችና

የምንሻው

አጋርነት

በሌሎችም የአምልኮ ሥፍራዎች

ፀሎታቸውን አድርሰዋል። እኛም

በዩናይትድ ስቴትስ የምንገኝ፣

በመላው የዓለም ዳርቻ የሚገኙ

ሕዝቦች ባከበሯቸው የሻማ

ምሽቶችና በየኤምባሲዎቻችን

ደጃፎች ባስቀመጧቸው አበቦች

በአንድነት መንፈስ ከጎናችን

መቆማቸውን ያሳዩበትን ሁኔታ

ከቶም አንረሳውም።

ከመስከረም 1፣

1993 በኋላ ባሉት ሳምንታት

እንደ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ

መንቀሳቀሳችንንም እናስታውሳለን።

የመጠነ ሰፊው ጥምረታችን አካል

በሆነ እንቅስቃሴ አል-ቃኢዳን

በአፍጋኒስታን ከሚገኙ የማሰልጠኛ

ሠፈሮቹ አባረነዋል፤ ታሊባንን

ከሥልጣን አስወግደናል፤

እንዲሁም ለአፍጋን ሕዝቦች

ከሽብር ነፃ ሆነው የሚኖሩበትን

ዕድል ሰጥተናቸዋል። ነገር

ግን ቀጣዮቹ ዓመታት ቀላል

አልነበሩም፤ በመስከረም 1፣ 1993

ማግስት ተጋርተነው የነበረው

የዓለም አቀፍ አጋርነት መንፈስም

ፈተና ገጥሞት ነበር።

እንደ አሜሪካ

ፕሬዝዳንትነቴ፣ የተጋረጡብንን

ዓለማቀፋዊ ተግዳሮቶች

ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ለመቋቋም

የሚያስፈልገንን ዓለምአቀፋዊ

ትብብር ለማደስ የሚያስችሉ

ተግባራትን አከናውኛለሁ። አብሮ

የመሥራት አዲስ ዘመንን ይፋ

በማድረግ፣ ከአገራትና ከሕዝቦች

ጋር በጋራ ፍላጎትና በመከባበር

ላይ የተመሠረተ አጋርነትን

መሥርተናል።

እንደ ዓለም አቀፍ

ማኅበረሰብ፣ ሽብርተኞች ከዜጎቻችን

ጋር የሚነጻጸር ጥንካሬና ፅናት

እንደሌላቸው አሳይተናል።

ዩናይትድ ስቴትስ ከኢስላም ጋር

ጦርነት ውስጥ እንዳልሆነችና

ወደፊትም እንደማትሆን ግልጽ

አድርጌአለሁ። ከዚያ ይልቅ፣

CITY TECH TRADING

New Arrival Surveying Equipment

Leica Total Stations

Sokkia Totalstation

Sokkia Automatic Level

Come and Visit Our Shop to Get All

Surveying Equipment with Affordable Price

Address:-Bole DH Geda Tower 1st floor, No 1-09

Tell: +251911 229906 ,+251 16628452 +251 16628052

ከተባባሪዎቻችንና ከአጋሮቻችን ጋር

አል-ቃኢዳን ለመዋጋት በአንድነት

ቆመናል። አል-ቃኢዳ በበርካታ

አገራት በፈፀማቸው ጥቃቶች

በአሥር ሺህዎች የሚቆጠሩ

ንፁኃን ወንዶች፣ ሴቶችና ሕፃናትን

የገደለ ሲኾን፣ ከሰለባዎቹ ውስጥ

እጅግ የሚበዙት ሙስሊሞች

ናቸው። እናም በዚህ ሳምንት፣

ከመካከለኛው ምስራቅ እስከ

አውሮፓ፣ ከአፍሪካ እስከ ኢሲያ

ሁሉንም የአል-ቃኢዳ ሰለባዎች፣

እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውና

ዜጎቻቸው በፈታኝ ሁኔታዎች

ውስጥ ለማለፍ ያሳዩትን ድፍረትና

ፅናት እናስታውሳለን።

በጋራ በመንቀሳቀሳችን

የአል-ቃኢዳ ሴራዎችን አክሽፈናል፤

ኦሳማ ቢን ላደንንና ብዙዎቹን

የአመራሩ አባላት አስወግደናል፤

እናም አል-ቃኢዳን በሽንፈት

ጎዳና ላይ እንዲጓዝ ዳርገነዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ፣ በመካከለኛው

ምስራቅና በሰሜን አፍሪካ

የሚገኙ ሕዝቦች ፍትኅና ሰብዓዊ

ክብርን ለመቀዳጀት የሚያበቃው

እርግጠኛ መንገድ፣ አዕምሮ-አልቦ

ሽብርተኝነትና ነውጥ ሳይሆን፣

ከነውጥ አልባነት የሚመነጭ

የሞራል ኃይል (የበላይነት)

መሆኑን እያሳዩ ይገኛሉ። ይህ

ሁኔታ ነውጠኛ ጽንፈኞች

ሰሚ እያጡ መምጣታቸውንና

መጪው ዘመን የእነዚያ ለማፍረስ

የሚተጉት ሽብርተኞች ሳይሆን

መገንባትን ለሚሹት መሆኑን

በግልጽ አመላክቷል።

የሰላምና የብልጽግና

መጻዒ ዘመንን ለሚሹ አገራትና

ሕዝቦች - ዩናይትድ ስቴትስ

ከእነርሱ ጋር በአጋርነት

ትቆማለች። በአገር ውስጥ

ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶች እያሉብን

እንኳ፣ ዩናይትድ ስቴትስ በዓለም

ላይ የተለየ የአመራር ሚና

መጫወቷን ትቀጥላለች። ከኢራቅ

ቀሪ ወታደሮቻችንን ስናስወጣና

በአፍጋኒስታንም ፀጥታ የማስከበር

ኃላፊነቱን ስናስተላልፍ፣

ኢራቃውያንና አፍጋኖች

የሕዝቦቻቸውን ደኅንነት ለማስከበር

እና የዕድሎች ተጠቃሚነትን

ለማረጋገጥ የሚያደርጉትን

ጥረት መደገፋችንን እንቀጥላለን።

በአረቡ ዓለምና ከዚያም ባሻገር፣

ለመላው የሰው ልጆች ክብር እና

ሁለንተናዊ መብቶች መከበር

በጽናት እንቆማለን።

በዓለም ዙርያ ሰላምን

ለማስፈን፣ ሕዝቦችን ከድህነት

የሚያወጡ የልማት ተግባራትን

ለማገዝ፣ እንዲሁም የምግብ

ዋስትናን፣ ጤናንና የዜጎችና

የኅብረተሰብን እምቅ አቅም ጥቅም

ላይ ለማዋል የሚያስችለውን

መልካም አስተዳደር ለማራመድ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

3

የሚጠይቀውን ከባድ ሥራ

መስራታችንን እንቀጥላለን።

ከዚሁ ጎን ለጎን፣

በአገር ውስጥ እሴቶቻችንን

ጠብቀን ለመኖር የራሳችንን

ቃል-ኪዳን እናድሳለን፡፡ ዩናይትድ

ስቴትስ የስደተኞች አገር

እንደመሆኗ ከየትኛውም አገርና

ባህል የሚመጡ ሕዝቦችን እጆቿን

ዘርግታ ትቀበላለች። እኒህ አዳዲስ

አሜሪካውያን - የዛሬ አሥር ዓመት

እንዳጣናቸው ንፁኃን የሽብር

ሰለባዎች ሁሉ - የቱንም ያህል

የዘር ወይም የጎሳ፣ የአስተዳደግ

ወይም የእምነት ልዩነቶች

ቢኖሩን እንኳ ሁላችንም ይህችን

ዓለም ለዛሬውም ሆነ ለመጪው

ትውልድ የተሻለች የመኖርያ

ስፍራ ለማድረግ እንችላለን

በሚል የጋራ ተስፋ የተሳሰርን

መሆናችንን ያስታውሱናል።

እነዚያን ያጣናቸውን ሰዎችም

ከዚህ ታላቅ እሴት ጋር ልናስባቸው

ግድ ይለናል።

እነዚያ መስከረም 1

ቀን 1993 ጥቃት የፈፀሙብን

ሰዎች በዩናይትድ ስቴትስ እና

በተቀረው ዓለም መካከል የጥላቻ

ንፋስ እንዲነፍስ ፈልገው ነበር።

አልተሳካላቸውም። እነሆ በጥቃቱ

የአሥረኛ ዓመት መታሰቢያ

ከወዳጆቻችንና ከአጋሮቻችን ጋር

በአንድነት ቆመን እነዚያን በዚህ

ትግል ውስጥ ያጣናቸውን በሙሉ

እናስታውሳለን። እነርሱንም

በማስታወስ፣ ሕዝቦች ሁሉ

በክብር፣ በነፃነትና በሰላም

የሚኖሩባትን ዓለም ዕውን

ለማድረግ የሚያስፈልገንን

የአጋርነትና የመከባበር መንፈስ

ዳግም እናረጋግጣለን።

/ባራክ ኦባማ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ፕሬዝዳንት ናቸው።

ይህ ጽሑፍ፣ የመስከረም አንዱ የሽብርተኞች ጥቃት 10ኛ ዓመት

መታሰቢያን አስመልክተው ያስተላለፉት መልእክት ሲሆን አዲስ አበባ

በሚገኘው የአሜሪካን ኤምባሲ በኩል ለዝግጅት ክፍላችን የተላከ ነው።/

4

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ፊ ቸ ር

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 184 ቅዳሜ ጳጉሜ 5/ 2003

መልካም ዓዲስ ዓመት

ማብቂያ የለሹ የኢትዮጵያዊያን ሰቆቃ

በመካከለኛው ምስራቅ?!

ኢትዮጵያዊያን ወደ መካከለኛው ምስራቅ የሚያደርጉት ስደት እና የሚደርስባቸው ኢ-ሰብዓዊ ጥቃት የጭንቅ ዜና አብሳሪነቱ ቀጥሏል። አቤል ዓለማየሁ እና

ሱራፍኤል ግርማ ባሰናዱት ቀጣይ ሀተታዊ ፅሁፋቸው የህግ ባለሙያዎች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ በጉዳዩ ላይ ሰፊ ጥናት ያካሄዱ ኢትዮጵያዊያንንና

ዕድሜያቸው በ60ዎቹ መባቻ ላይ የሚገመተው

ወ/ሮ ኩሪ ወልዱ በትካዜ ተውጠው ዕንባቸው መንታ

መንታ ሆኖ ይወርዳል። በጎረቤቶቻቸውና በንስሐ

አባታቸው ጭምር ቢለመኑ፣ ቢገዘቱ ማንባታቸውን

ማቆም አልቻሉም። ስለልጃቸው መልካም ፀባይና ቅን

አሳቢነት ሳይታክቱ ደግመው ደጋግመው በማያባራው

እንባቸው በመታጀብ ይናገራሉ። ‹‹ልጄን የማጎርስበት

አቅም እንኳን የለኝም፤ እንዲያሳክምልኝ መንግስትን

እና የኢትዮጵያን ሕዝብ እለምናለሁ›› የሚል

ተማፅኗቸውን ያቀርባሉ። አዛውንቷ ወ/ሮ በሞሐመድ

ጋዳፊ ቤተሰብ ኢ-ሰብዓዊ ጥቃት የደረሰባት የሸዋዬ

ሞላ እናት ናቸው።

ሊቢያን ለ42 ዓመታት እንደግል ድርጅታቸው

ባሻቸው መንገድ ሲዘውሯት እንደኖሩና የአምባገነኖች

አርአያ መሆናቸው ከሚነገርላቸው ጋዳፊ ልጆች

አንዱ የሆነው ሐኒባል ጋዳፊ ሚስት የሆነችው

አሊያን፤ እንጀራ ፍለጋ በተሰደደችው ሸዋዬ ሞላ

ላይ ያደረሰችው ዘግናኝ ድርጊት ልብ አድሚም፣

አነጋጋሪም ሆኗል። አሊያን ‹‹ያለ ምግብና ውኃ ለሶስት

ቀናት እንድትቆዪ የሰጠኹሽን ትዕዛዝ ተላልፈሻል››

በሚል ምክንያት የወጣቷን እጅና እግር በሌሎች

የቤት ሠራተኞች አሳስራ የፈላ ውኃ በጭንቅላቷ

ላይ በማፍሰስ ከባድ ጉዳት ከማድረሷ በላይ፣ ወጣቷ

ሕክምና እና በቂ ምግብና ውኃ እንዳታገኝ በጠባብ

ከፍል ውስጥ ለወራት ዘግታባት መቆየቷ የጥቃቱን

ከፍተኛነት አጉልቶታል።

የሚመለከታቸው የመንግስት ባለስልጣናትን በማነጋገር ‹‹ይህ ችግር ማብቂያው መቼ ይሆን?›› ሲሉ ይጠይቃሉ።

ኃላፊ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ሴቶችም ሆኑ ወንዶች

እድላቸውን ለመሞከር በዓለም አቀፍ መድረክ ሙከራ

ማድረጋቸውን (መጓዛቸውን) እንደ ችግር መውሰድ

እንደሌለበት ጠቁመው ‹‹ግን›› ይላሉ፣ ‹‹ግን ዜጎች

በሄዱበት የዜግነት ክብራቸው እንዳይነካ መንግስት

ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል። መንግስት ያለውም ዜጎች

ጥቅም ለማስጠበቅ ነውና›› ይላሉ።

‹‹እዚህ አገር ያለው አማራጭ ውስጥ ስለሆነ ዜጎች

በሕገ-ወጥ መንገድ ከአገር ወጥተዋል ብሎ በቸልታ

ሊታዩ አይገባም። ራስን ለመለወጥ እንደሚደረግ

ሰዋዊ ባህሪ ማየት ይገባል። ስለሁሉም ኢትዮጵያዊ

ዜጋ ኃላፊነት አለበት›› በማለት ፕሮፌሰር በየነ

ጴጥሮስ ለሁሉም ዜጎች ከለላ መሆን እንዳለበት

መንግስትን ያሳስባሉ።

የኢትዮጵያ መንግስት

ለዜጎቹ ከለላ እየሆነ ነውን?

የደነደነ ልብ ያለውን ሰው እንኳን ስሜት

የሚሰብረው መካከለኛው ምስራቅ እና አንዳንድ

የአፍሪካ አገራት የሚጓዙ ኢትዮጵያውያን ሴቶች

መብት ጥሰት የዘወትር ጩኸት ቢሆንም የሸዋዬ

ሞላ ጉዳት የሲ.ኤን.ኤን፣ አልጀዚራና አል አረቢያ

በግርድፉም ቢሆን የሌሎች ብዙዎች የሚከታተሏቸው

መገናኛ ብዙሐንን ከወትሮው የተለየ ትኩረት ስላገኘ

ዓለም አቀፍ መነጋገሪያ ሆኗል። አጋጣሚውን በአረብ

አገራቱ ላሉ ዜጎች መታደግ የሚቻልበት ጊዜ ‹‹አሁን››

መሆኑን ይበልጥ ስለመጠቆሙ እየተገለፀ ነው።

ሸዋዬ ላይ የተፈፀመው በደል በሊቢያ ከተፈጠረው

አመፅ ተንተርሶ በጋዳፊ ቤተሰብ መሆኑ ዓለም አቀፍ

ትኩረትን ስቦ ለመነጋገሪያነት በቃ እንጂ፣ በሌሎች

አረብ አሰሪዎቻቸው ከፍተኛ ስቃይ የሚደርስባቸው

አያሌ ‹‹ሸዋዬዎች›› መኖራቸው የዘወትር ሐቅ ነው።

‹‹የአረብ አገር ሕይወት መሯት ራሷን ከፎቅ ወርውራ

ሞተች››፣ ‹‹መርዝ በመጠጣት ራሷን የማጥፋት

ሙከራ አደረገች›› እንዲሁም ‹‹አሰሪዋን ገደለች››

የሚሉ ዜናዎች ለኢትዮጵያውያን አዲስ አይደሉም።

‹‹የሸዋዬ ጉዳይ የሚዲያዎችን ሰፊ ትኩረት

ስላገኘ አረቦች ደንግጠዋል። መንግስታቱም የዜጎችን

መብት ያከብሩ ዘንድ ከዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብት

ጠባቂዎች ወቀሳ ለማምለጥ የተቻላቸውን ያህል

የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ያደርጋሉ የሚል እምነት

አለኝ›› የሚለው ነብዩ ሲራክ አጋጣሚው (የሸዋዬ

ጉዳት) አሳዛኝ ቢሆንም ችግሩ እንዲጎላና ዓለማቀፋዊ

እውቅና እንዲኖረው የሚያደርግ መልካም አጋጣሚ

መፈጠሩን ያምናል። አምባሳደር ዲና ሙፍቲም

ክስተቱ ንቃትን እንደሚጨምር ይስማማሉ።

‹‹በየኤምባሲው ያሉ ሰዎች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ

መወጣት አለባቸው። በትክክል ውጪ የሚገኙ

ኢትዮጵያውያን ለሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች ተገቢውን

ምላሽ ሊሰጥ ይገባል›› ይላሉ።

ተቀድቶ ‹‹በማያልቅ›› የነዳጅ ሀብት አቅማቸው

ወደዳበሩት የአረብ አገራት ከቤት ሰራተኝነት ብቻ

ሳይሆን በተለያየ የሙያ መስኮች ሥራ ፈላጊዎች

ይተማሉ። በቤት ሰራተኝነት ወደ አገራቱ ከሚደርሱ

ዜጎች መካከል የሩቅ ምስራቅ አገሮች ቁጥራቸው

ያይላል፤ ኢንዶኔዥያ፣ ስሪላንካ፣ ፊሊፒንስ፣

ሕንድ፣ ፓኪስታን፣ ባንግላዴሽ…። የኢትዮጵያውያኑ

ቁጥርም ከፍተኛ ሲሆን በተለይ የቅርብ መረጃዎች

እንደሚያሳዩት ከሆነ እንደ አትሌቲክሱ ሁሉ በቤት

ሠራተኝነት ፍልሰትም የኢትዮጵያውያኑ ቁጥር

በልጠው ኬኒያዊያን በአገራቱ እየተነሰነሱ ነው፡፡

ሸዋዬ ሞላ፣

ዜጎች ለምን ይፈልሳሉ?

የኢትዮጵያ ሕገ-መንግስት፣ አንቀጽ 32 የመዘዋወር

ነፃነት በሚል ርዕስ ንዑስ አንቀፅ አንድ እና ሁለት

ላይ በሰፈረው መሠረት፣ ‹‹ማንኛውም ኢትዮጵያዊ

በሕጋዊ መንገድ የመዘዋወር፣ በፈለገው ጊዜ ከአገር

የመውጣት ነፃነት እና ወደ አገሩ የመመለስ መብት

እንዳለው ይደነግጋል።

ብዙ ዜጎች ግን ይህን መብት በመጠቀም ወደ

ሌላ አገር የሚሻገሩት በሰራተኛና ማሕበራዊ ጉዳይ

ሚኒስቴር አማካኝነት ዋስትና ተገብቶላቸው እና

ዓለም አቀፋዊ ሕግጋትን በተከተለ ሁኔታ አይደለም።

በዋነኛነት ችግር የሚያጋጥማቸውም ሕገ-ወጥ

ተጓዦቹ መሆኑን የውጪ ጉዳይ ቃል አቀባይ

የሆኑት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ይገልፃሉ። ‹‹ትልቅ

ይህቺ ኢንዶኔዥያዊት የቤት ሠራተኛ በ50ዎቹ የእድሜ ክልል በሚገኙ አሰሪዋ በተፈፀመባት

ችግር የሚያጋጥማቸው በሕገ-ወጥ ደላላ አማካኝነት

ከባድ ድብደባ ከሸዋዬ የማይተናነስ ጉዳት ደርሶባት መዲና ውስጥ በሚገኝ ፍ/ቤት ቀርባ

ባዶ ተስፋ ተሞልተው የሚሄዱ ናቸው። አሰሪዎቹም

አሰሪዋ ላይ ፍርድ ከመሰጠቱም በላይ የኢንዶኔዥያ እና የሳውዲ አረቢያ የሠራተኛ አቅርቦት

ምንም ዋስትና እንደሌላቸው ስለሚያውቁ እጃቸው

ስምምነት እንዲቋረጥ አንዱ ምክንያት ሆኗል። አገራችን ከዚህ ምን ትማራለች?

ለገባው ኢትዮጵያዊ ደህንነት አይጨነቁም›› ሲሉ

ሕጋዊ ጉዞ አለመኖሩ ችግሩን እንደሚያጎላው

ከአሰራር ጋር በሚፈጠር አለመግባባት የሰብዓዊ

ቢያሰምሩበትም ከቦታው የሚወጡ መረጃዎች

ተልዕኮውን በደንብ ያልተረዳ ነው›› ይላሉ።

መብት ጥሰቶች በሁሉም አገር ሰራተኞች ላይ

የሚጠቁሙት በሕጋዊ ኤጀንሲ በኩል በሰራተኛ እና

በተለያየ ወቅት እንደ አሜሪካ ያሉ የበለፀጉ አገራት

የሚፈፀም ቢሆንም ሌሎች አገራት ለዜጎቻቸው

ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ‹‹ታውቀው›› ድንበር

በሌላ አገር የሚገኙ ዜጎቻቸው በጥፋት ተሳታፊ ቢሆኑ

ከለላ እንደሚቆሙ በምርመራ ጋዜጠኝነት መረጃ

የሚሻገሩትም ከጣጣ ነፃ አለመሆናቸውን ነው።

እንኳን ሰብዓዊ መብታቸው እንዳይደፈር እንቅልፍ

የሰበሰበው የጀርመን ድምፅ ዘጋቢ ነብዩ ሲራክ

ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ይህ ችግር መኖሩን በሳውዲ

አለመተኛታቸው አርያነት ያደርጋቸዋል። [ሕግን

ያስረዳል። ‹‹የተጠቀሱት አገር ዜጎች ችግር

አረቢያ ታዝቧል። ‹‹በሥራ እና አሰሪ ኤጀንሲዎች

የተላለፈ ኢ-ሰብዓዊ አያያዝ እንዲኖረው የሚደነግግ

ከመፈጠሩ አስቀድሞም ሆነ ከተፈጠረ በኋላ

የሚላኩ የኮንትራት ሰራተኞች ተቀባይ አጥተው

ሕግ ስለሌለ] በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ በውጪ

በመንግስት ተወካዮቻቸው አማካኝነት ክትትልና

ለሳምንታት ሲንገላቱ ተመልክቻለሁ። አሰሪዎቻቸውን

አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ደህንነት እና ዋስትና

ጥበቃ ይደረግላቸዋል። ሲበደሉ ይብዛም ይነስ ፍትህን

አግኝተው ወደ ሥራ የተሰማሩትም በምግብ አቅርቦት፣

እንዲረጋገጥ የኢትዮጵያ መንግስት የተቻለውን

ሳያገኙ የሚቀሩበት አጋጣሚ አናሳ ነው›› የሚለው

በሥራ ብዛትና ለተመሳሳይ ችግሮች በመዳረጋቸው

ማድረግ እንዳለበት የሚጠቅሱት ዶ/ር ሼክስፒር

ጋዜጠኛው በቅርቡ አንዲት ኢንዶኔዥያዊት የቤት

አሁን ድረስ ስልክ እየደወሉ የሚገልፁልኝ እህቶች

የአሜሪካን ተሞክሮ በመጥቀስ መንግስት እንዲነቃ

ሰራተኛ በ50ዎቹ የእድሜ ክልል በሚገኙ አሰሪዋ

አጋጥመውኛል›› የሚለው ነብዩ የቅርብ ጊዜ

ይጠይቃሉ። ‹‹በአሜሪካ ሴናተሮች እና የኮንግረስ

በተፈፀመባት ከባድ ድብደባ ከሸዋዬ የማይተናነስ

ተሞክሮው ይህን ሀቅ ፍንትው አድርጎ እንደሚገልፅ

አባላት የዜጎች መብቶች፣ ደህንነትና ዋስትናን

ጉዳት ደርሶባት እንደነበር ገልጾ፣ ‹‹ጉዳዩ መዲና

ማሳያውን ይዘረዝራል። ‹‹ከጥቂት ሳምንታት በፊት

ለማረጋገጥ ከሌላ አገር ጋር አብረው በመስራት

ውስጥ በሚገኝ ፍ/ቤት ቀርቦ አሰሪዋ ላይ ፍርድ

ያነጋገርኳት እህት ሳውዲ አረቢያ ጅዳ ለአንድ ሳምንት

ንቁ ተሳትፎ ያደረጋሉ። ይህንንም በተደጋጋሚ

ከመሰጠቱም በላይ የኢንዶኔዥያ እና የሳውዲ

በማቆያ/ እስር ቤት ሆና አሰሪዎቿን ስትጠባበቅ

ተመልክተናል። በእህቶቻችን ላይ የደረሰው በአንድ

አረቢያ የሰራተኛ አቅርቦት ስምምነት እንዲቋረጥ

ብርድ መትቷት የከፋ የጤና መታወክ ገጥሟታል።

አሜሪካዊ ዜጋ ላይ ተፈፅሞ ከሆነ፣ የአሜሪካ

ምክንያት ከሆኑ ጉዳዩች መካከል አንዱ ሆኗል›› ሲል

አሰሪዎቿም መጥተው ቢወስዷትም ግማሽ ጎኗ

መንግስት ጉዳቱን በቀላሉ አይመለከተውም። ለዜጋው

በምሳሌነት በሳውዲ አረቢያ መገናኛ ብዙሃን ሳይቀር

‹‹ሽባ›› የመሆን የጤና እክል እንዳጋጠማት በተማፅኖ

ፍትህን ለማሰጠት የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል።››

ስለተዘገበው ጉዳይ ተናግሯል፤ ጉዳዩ ኢትዮጵያውያን

ገልፃልኛለች። ከእሷ ባገኘሁት አድራሻ መሠረት

ላይ ሲያጠነጥን ግን ትኩረቱ የተገላቢጦሽ እንደሆነ

አዲስ አበባ ወደሚገኘው ያመጣት የሥራ አገናኝ

የዲፕሎማቶች ግንዛቤ ሲመዘን

በመጠቆም።

ኤጀንሲ በተደጋጋሚ ብደውልም ስልኩ አይመልስም።

የኢትዮጵያ መንግስት በአረቡ ዓለም ላሉት ዜጎቹ

ነዋሪነታቸውን በአሜሪካ ሲያትል ከተማ ያደረጉት

ወደ አገሬ የምገባበትን መንገድ ፈልጉልኝ ስትል

ከለላና ጥበቃ ስለማድረጉ ችግሮች በተነሱ ቁጥር

የሕግ ባለሙያው ዶ/ር ሼክስፒር ፈይሳም የኢትዮጵያ

የድረሱልኝ ጥሪዋን ማሰማቷን በጀርመን ሬዲዮ ላይ

ሁሌም ጥያቄ ያጭራል። በመካከለኛው ምስራቅ

መንግስት ከፍተኛ ትኩረት የሚያሻው ጉዳይ ላይ

አቅርቤዋለሁ›› ይላል።

የጀርመን ድምፅ ሬዲዮ ዘጋቢ የሆነው ነቢዩ ሲራክ

ቸልታ እንደመረጠ ከሚያምኑት ውስጥ ናቸው።

ዜጎች በሕጋዊ መንገድ በሠራተኛ እና አሰሪዎች

ጉዳዩን አስመልክቶ ለአውራምባ ታይምስ በሰጠው

መንግስት አስቀድሞ ዲፕሎማሲያዊ፣ ፖለቲካዊና

አማካኝነት ስራ አግኘተው ወደ አገራቱ ቢላኩም

ምስክርነት፣ በአካባቢው ያሉ የኢትዮጵያ መንግስት

ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶቹን ስለሚያስብ በቸልታ

ችግር ሲደርስባቸው የሚያማክሯቸውን የኤምባሲ

ተወካይ ዲፕሎማቶች የዜጎችን መብት ለማስከበር

ለመዋጡ በምክንያትነት ያቀርቡታል። ‹‹መንግስት

እና ቆንስላ መስሪያ ቤቶች እንዳይገናኙ ያደርጓቸዋል።

እርባና ያለው ሥራ ባለመሥራታቸው እንደሚወቀሱ

ለዜጎቹ የጥበቃና የመቆርቆር ሚናውን ከተወጣ

እንደውም የአሰሪዎች የሴራ ትብታብ የሚጀምረው

ያረጋግጣል።

ያለውን የጠቀስኳቸውን ግንኙነቶች ማጣትን

ኤምባሲ እና ቆንስላ መ/ቤቶችን እንዳያውቁ በማድረግ

‹‹በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ባሉባቸው አረብ

ያስከትልበታል። ለዚህም ነው በተደጋጋሚ ጊዜ ዜጎቹ

ነው፤ በተለይ ሕገ-ወጥ ተጓዦችን።

ሀገራት የሚላኩት በጣት የሚቆጠሩ ዲፕሎማቶች

ሰብዓዊ ባልሆኑ በችግር ውስጥ ሲሰቃዩ ዝምታን

ሴቶቹ በሥራ ቦታ ላይ መድረሳቸውን ‹‹ሃሎ››

በዲፕሎማሲ የጠለቀ ዕውቀት የሌላቸውና

የሚመርጠው›› ይላሉ።

ይበሉ እንጂ ስለ አሰሪዎቻቸው ፀባይ፣ የስራቸው

የሚላኩባቸውን ሐገራት ህግና ስርዓቶች ከራሳቸው

የኢትዮጵያን ልማት፣ ዴሞክራሲና ሰላም ሊደግፉ

አይነት፣ ተገቢ መጠለያ እና ሕክምና ስለማግኘታቸው

ጋር በቶሎ አዋህደው መሥራት ስለሚከብዳቸው

የሚችሉ ስራዎችን መስራት፣ ኢንቨስትመንት እና

በወል አይታወቅም። ይህንን መሰል የችግሮች መነባበር

የዜጎችን መብት ማስከበርም ሆነ ችግሮች ሲከሰቱ

ቱሪዝም መሳብ፣ የውጪ ገበያ ማፈላለግ ብቻ

የተሰላቹ ሰራተኞች በተስፋ መቁረጥ ወንጀል ውስጥ

በአፋጣኝ ለመፍታት ይቸገራሉ›› የሚለው ነቢዩ፣

ሳይሆን የዜጎችን መብት ማስጠበቅም የውጪ ጉዳይ

ተዘፍቀው ይታያሉ። የዜጎች መብት ጠባቂው፤

ያስተዋላቸውን ችግሮች ዘርዝሯል።

ሚኒስቴር በኤምባሲዎች አማካኝነት የሚከውነው

መንግስት ተቀዳሚ ግዴታውን መወጣት ያለበት ይህ

በቅርቡ በኩዌት ከ400 በላይ የኮንትራንት

ተልዕኮ እንደሆነ የሚናገሩት አምባሳደር ዲና

ሁሉ ከመከሰቱ በፊት መሆኑን ዶ/ር ሼክስፒር ፈይሳ

ሠራተኞች በአሠሪዎቻቸው የሚደርስባቸውን

ሙፍቲ፣ ‹‹ዋነኛው የስራችን ትኩረት ኢኮኖሚክ

ያሰምሩበታል።

ድብደባና በቂ ምግብ አለመኖር፣ ለአንድ ሥራ ሄደው

ዲፕሎማሲ ነው። ይህ ለማሳካት ውጪ የሚገኙ

ዓለም ለሁሉም ዓለማቀፋዊ ቤት መሆኗ

በተለያዩ ቤቶች እንዲሠሩ በመደረጉ የተፈጠረባቸውን

ኢትዮጵያውያንን መብት ማስከበር የግድ ነው።

ተፈጥሯዊ ሂደት የፈጠረው መሆኑን የሚገልፁት ‹የኢትዮጵያን መንግስት ኃላፊነት እየተወጣ ነው›

ባለበት አገር ሆኖ ‘እዚህ ያለሁት ኢንቨስተር ለመሳብ

የመድረክ ምክትል ሊቀ መንበር እና የህዝብ ግንኙነት ተብሎ የሚሞካሸው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ

ብቻ ነው’ የሚል ዲፕሎማት ካለ ‹‹ያልገባው እና

በ ገፅ 22

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 184 ቅዳሜ ጳጉሜ 5/ 2003

መልካም ዓዲስ ዓመት

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

5

6 ኮመንትሪ

በታዲዎስ ጌታሁን

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

“እኚህ ነበሩ”

... የሰው ልጅ

የሚሞተው፣ ዕድሜው

ሲንዘላዘል አብሮ የሚዝረከረክ

እንቅስቃሴውን ሥርዓት ለማስያዝ

የሚደክሙ ወዳጅ ዘዶቹን ሥራ

አስፈትቶ (ያልቀናቸው) በረሀብ

እንዳይገላቸው ‹‹ይመስለኛል››።

አንድ ሰው ወይም

ደግሞ እኔ ብሞት ይህቺ ሀገር

የሚጎድልባት ገፀ-በረከት አለ

ብዬ አላምንም። ይኸን ስሜት

የማይሰጥ ጉዳይ ከማመን ይልቅ፣

የአንድ ግለሰብ ቦርጭ ተደርምሶ/

ፈንድቶ አንዲት ቀበሌን አጥለቀለቀ

የሚል “ስጥ እንግዲህ” ወሬ ባምን

ይቀለኛል።

በእርግጥ አልጋ

ላይ ሲውሉ ቀርቶ ሲያስነጥሱ

እንኳን ክፉ እንዳይገጥማቸው

የምንንሰፈሰፍላቸው አያሌ የሰው

ሰው ኢትዮጵያውያን አሉ።

ሰዎች፣ መቼ

እንደሚሞቱ አይወቁ እንጂ

ከሚያውቋቸው ቀናት በአንዱ

እንደሚሞቱ ያውቃሉ።

እንደሚሞቱ የሚያውቁ ብዙዎች

(ሁሉም) ሲሆኑ፣ “ሞታቸውን”

ጠቀም ላለ ጉዳይ (ለሀገር እና

ለወገን) የሚያውሉ ግን በጣም

ጥቂት ናቸው።

ሙቅ ሲጠጣ ‘ትን’

ብሎት የሞተም ሆነ ለነፃነት

(፬)

/መጠቅለያ/

ሰላም ለእናንተ ለአንባቢዎቼ!

ለሶሰት ሳምንታት የዛሬው

ርዕሳችን መቆያ ሆኖን ሰንብቷል።

ዛሬ መጠቅለያ ያክል ይህንን

እፀፋለሁ።

ውድ አንባቢያን በሁለተኛው

ክፍል ጽሑፍ እንዳልኩት ይህ

ጽሑፍ እንደተናጋሪ እንጅ እንደ

አጥኚ አለዚያም እንደተመራማሪ

የሰራሁት አይደለም። በሌላ

አባባል እንደ አንድ ፀሐፊ

እያየሁና እየሰማሁ ከታዘብኳቸው

ነገሮች እናንተም ከምታዩአቸውና

ከምትሰሟቸው ተነስቼ ነው

የፃፍኩት።

መሰንበቻዬን ሕፃን፣ ወጣት፣

ምሁር፣ ካህን፣ መሪ፣ ሰራተኛ

እያልኩ በርዕስ እየከፋፈልኩ

በአንድ የሞራል ኪሳራ መገለጫው

በሆነ ሰው የሚታዩ ባህሪያትን

ገልጫለሁ። ለመሆኑ ግን ለዚህ

ሁሉ የሞራል ዝቅጠት ተጠያቂው

ማነው? እኔ እንዲህ ይማሰኛል።

ሰዎች በጎ አእምሯዊ

አስተሳሰብን ማዳበር ይችሉ ዘንድ

ትልቁን ሚና የሚወስደው መማር

ነው። መማር ደግሞ ደብተር

ይዞ ትምህርት ቤት መመላለስን

ብቻ ሳይሆን የሚገልፀው፣

ከሃይማኖት /ከእምነት ተቋም/

ከሰፈር፣ ከቤተሰብ፣ ከአካባቢ፣

ሲፋለም የሞተ አንድ ዓይነት

ስም ነው የሚሰጠው - ‘ሞተ’

የሚል። ነገር ግን፣ ሞቱን

ለአንድ ብር ገመድ አሳልፎ

የሰጠ ሰውና ለማኅበረሰብ ነፃነት

የሰጠ፣ በታሪክም ሆነ በትውልድ፣

በሰማይም ሆነ በምድር ‘እኩል’

ክብር አያገኝም።

… ሰዎች፣ ኑሮ

የሚያቀርብላቸውን ጥያቄ

ለመመለስ ብዙ ቦታዎች ይገባሉ

- መሥሪያ ቤቶችን ጨምሮ።

አንድ ሰው ወይም ባለጉዳይ

ከመንግሥትም ሆነ ከግል

መሥሪያ ቤቶች የሚሰጠው

ምላሽ የማያሳምነው ከሆነ

‘ለምን?’ ብሎ መጠየቅ አለበት።

አለበለዚያ በተጠያቂነትና በግል

ፅናት የመገልገል (የመስተናገድ)

መብቱን በገዛ ፈቃዱ አሳልፎ

እንደሰጠ ይቆጠራል።

ሁሉም የየራሱን

መብትና ነፃነት በራሱ ጉልበትና

ወዝ ማስከበር አለበት። ተጠያቂነት

በጎደለው አሰራር መብቱን የተቀማ

ኢትዮጵያዊ፣ የተነጠቀውን ነፃነት

አልያም መብት የሚያስመልስለት

የፈረንሳይ ፓርላማ ሳይሆን ራሱ

ኢትዮጵያዊው ባለጉዳይ ነው።

እያንዳንዱ ሰው የየራሱ

ነፃ አውጪ መሆን አለበት። ለእኔ

ነፃነት ወይም እኔ ነፃ እንድወጣ፣

በዬትም ሀገር ያለፈው ትውልድ ድል የተቀዳጀበትን ስልት አሊያም ተነሳሽነት ይሔ

ትውልድ መድገም ካቃተው ቀስ በቀስ የታሪክ ሞት ይከሰታል። የአንድ ተራ ሰው ሞት፣

ከቤተሰቡና ወዳጆቹ አልፎ ለብሔራዊ ሐዘን የሚበቃበት ጉልበት የለውም። የታሪክ ሞት

ግን ከሀገር አልፎ ጎረቤት ሀገሮችን ጨምር ለሐዘን ይዳርጋል።

በደሳለኝ ስዩም

ከባህል፣ ከኑሮ፣ ከስልጣኔ ደረጃ

ወዘተ የሚገኙ ትምህርቶችንም

ይገልፃል።

እንግዲህ ትምህርት የንቃተ-

ኅሊና እና የበጎ አስተሳሰብ ምንጭ

መሆኑን ከተስማማን፣ የትምህርት

ምንጭም ከላይ የዘረዘርነው ሁሉ

መሆኑን ከተስማማን ነገራችን

ያለው “ከትምህርት” ይሆናል

ማለት ነው።

፩. ባሕላዊ ትምህርት

በመሠረቱ ባህላዊ ትምህርት ስል

የየባህሉ፣ የየሚዛኑ፣ የየሰፈሩ፣

የየሃይማኖቱ ወዘተ ታሪኮች፣

አፈ-ታሪኮች፣ እንቆቅልሾች፣

የልጆች ጨዋታዎች፣ አለባበሶች፣

ሰላምታዎች፣ እንቅስቃሴዎች፣

ዜማዎች ወዘተ ሁሉ

ያጠቃልላል።

አንድ ዜጋ በስብዕና ደረጃ

የተሟላና በአወንታዊነት

የበለፀገ ሞራል መላበስ ይችል

ዘንድ ከመነጨበት ማኅበረሰብ

ውስጥ ያሉ ባህላዊ ትምህርቶች

ያስፈልጉታል። ያለዚያ የማንነት

ቀውሱ ከዚሁ ከልጅነቱ ጀምሮ

ይጠናወታል።

በእያንዳንዱ ባህላዊ ትምህርት

ውስጥ እንዴት መልካም ስብዕናን

ማጎልበት እንደሚችል በቀጥታም

ይሁን በተዘዋዋሪ ትምህርቶችን

ያገኛል።

እነዚህን ባህላዊ ትምህርቶች

በነፃነት አግኝቶ የማደግ አጋጣሚው

በጠበበ ቁጥር ማን ነህ? ከየት

የሌላ (ሀገር) ሰው ደም የሚፈስ

አሊያም ጥይት የሚፈነዳ ከሆነ

የነፃነት ጣዕም ሳይገባኝ ነው

የምኖረው።

በራሴ ፍላጎትና

ተነሳሽነት ነፃነቴን እና መብቴን

ካልጨበጥኩ፣ ሌላ ወገን

ያስጨበጠኝን ነፃነት በቀላሉ

ለማንም አሳልፌ የምሰጥ ተራ

ሰው እሆናለሁ። ምክንያቱም፣

ለነፃነቴ ዋጋም ሆነ ግብር

አልከፈልኩበትምና።

ሌሎች በልካቸው

አስጠብበው የሚሰጡንን

የነፃነት ካባ መልበስ፣ ሕይወት

በምትፈቅደው አቅጣጫ ሁሉ

አለመንቀሳቀስ ማለት ነው።

የቻይና የነፃነት ካባ፣ ለኢትዮጵያ

ይጠባታል ወይም ያጥራታል

አሊያም ይሰፋታል። ስለዚህ ካባው

የተመጣጠነ እንዲሆን ሲንጀሩ

(ፍላጎቱና ተነሳሽነቱ) የራስ መሆን

አለበት።

ዜጎች፣ ራሳቸውን

ነፃ ማውጣት እንደሚችሉ

ካመኑ፣ ለታመነው የነፃነት

መጀመሪያ የራሳቸውን ፊሽካ

ይነፋሉ፤ አሊያም ነፃነታቸውን

ለቀሙት ገዢዎቻቸው ወደው

ሳይሆን ተገደው (ተረግጠው)፣

ለማያምኑበት ሕግ ታምነው

ይኖራሉ።

የነፃነት ፀሐይ እንደ

ተፈጥሮ ፀሐይ በምስራቅ በኩል

ብቻ አትገኝም። የሰው ልጆች

ባሉበት በአራቱም አቅጣጫዎች

አለች። ነፃ መሆን የሚፈልጉ

ሰዎች ፀሐይቱን የማያወጧት

ከሆነ፣ ለረዥም ዘመናት በጨለማ

ውስጥ ለመኖር በራሳቸው ላይ

እንደፈረዱ ማወቅ አለባቸው።

ተፈጥሮ በነፃ

የሰጠችውን ነፃነቱንና መብቱን

በየስርቻው ለማርመጥመጥ

ነህ? ወዴት ነህ? ወዘተ ለሚሉ

ጥያቄዎች ቀጥተኛና አወንታዊ

መልስ መስጠት የማይችል ብኩን

ዜጋ እየበረከተ ይመጣል።

በዚህ ደረጃ የምስራቅ ሀገራት

/ቻይና፣ ጃፓን፣ ህንድ/ በጎ

ምሳሌ መሆን የሚችሉ

ይመስለኛል። ዘመናቸው

እየረቀቀ፣ ቴክኖሎጂያቸው

እየመጠቀ ቢመጣም እንኳ ባህላዊ

ትምህርቶቻቸው እንደ ተጠበቁ

የልጆች ማሳደጊያ ናቸው።

ሰላምታ፣ አለባበስ፣ አመጋገብ፣

ስፖርታዊ እንቅስቃሴአቸው ሁሉ

ለዚህ ማሳያ ሊሆን ይችላል።

ባንፃሩ ገና ታድጋለች ብለን

በመንጠብቃት ሀገራችን ግብረ-ወጥ

የሆኑ የሰለጠኑ የሚመስሉ ግን

የሰየጠኑ ልማዶች እንደፋሽስት

ወረዋት ባህላዊ ትምህርቶቿ

የአላዋቂነት መገለጫ ሆነው

መቆጠር ጀምረዋል።

እስኪ አዲስ አበባ ውስጥ ለልጆቹ

ኢትዮጵያዊ ተረት እየነገረ ባህሉን

እያስተማረ ልጀቹን የሚያሳድግ

ወላጅ ምንያክል ይሆናል?

መሠረታዊ እና ታላቁ የሞራል

ቀውስ ከዚህ ይጀምራል።

፪. ዘመናዊ ትምህርት

ባለንበት የሉላዊነት ዘመን /

ዘመነ ግሎባላይዜሽን የዘመናዊ

ትምህርት መስፋፋት የስልጣኔና

የሳይንስ ምንጭ ተደርጎ

ይወሰዳል። በመሆኑም ይህንን

ዘመናዊ ትምህርት ለማስፋፋት

ብዙ ጥረት ይደረጋል።

ዘመናዊ ትምህርት ብዙ አማራጭ

የኑሮ ዘዴዎችን፣ አቋርጭ የኑሮ

መስመሮችን ውበትንና ስልትን

የተላበሱ የአኗኗር ልማዶችን

ለማበጀት ይጠቅማል።

“ሰው ማኅበራዊ እንስሳ ነው”

የሚለውን ፍቱንነቱ ያልተረጋገጠ

አባባል ውድቅ ሊያደርጉ የሚችሉ

ፍቱን ስልጣኔዎችን ያመጣል -

ዘመናዊ ትምህርት።

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 184 ቅዳሜ ጳጉሜ 5/ 2003

መልካም ዓዲስ ዓመት

የሚነሳሳበትን ኃይል በመመከት

ራሱን በራሱ ነፃ ማውጣት አለበት

- ማንኛውም ዜጋ።

አንድ ኢትዮጵያዊ

ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ ያገኘውን

መብትና ነፃነት ማስከበር ያለበት

በኢትዮጵያ መፈክር እንጂ በራስ

ወዳዶች የጥቀመኝ ልጥቀምህ

ፖሊሲ አይደለም።

ኢትዮጵያውያን፣ በሰበብ

አስባቡ በፖለቲካ ደዌ የሚገመት

ነፃነታቸውን የሚያክሙላቸው

የባንኮክ ስፔሻሊስቶች አይደሉም።

የስኳር ታማሚ ወደ ታይላንድ

ሊላክ ይችላል። የነፃነት በሽተኛ

(በቂ ነፃነት የሌለው) ኢትዮጵያዊ

ሪፈር የሚያደረገው ግን ወደ

አድዋ ተራራ ነው።

በተራራው ስር

የተከናወነው የነፃነት ተጋድሎ

የልብ ልብ ስለሚሰጥ፣ ዛሬ

ነፃነት የጎደላቸው ወይም

ነፃነታቸውን የተቀሙ ዜጎች

ያለፈው ታሪካቸውን ሊጠቀሙበት

ይችላሉ። የትላንት የድል ታሪኮች

ተመዝግበው የሚቀመጡት የዛሬ

ሰዎች ከሚደነቀርባቸው ፈተናዎች

የሚያመልጡበትን መንገድ

ለማመላከት ጭምር ነው።

ሰዎች ነፃነት አልባ

የሚሆኑት፣ ፖለቲካ ጨጓራ

በሽታ የሚሸመትበት የህመም ገበያ

ሲሆን ነው። የገዢዎች የፖለቲካ

አካሔድ መዳረሻውና ዓላማው

ሀገርን ወደተሻለ አንድነትና

ዕድገት ማድረስ ከሆነ ማንም ሰው

ፈሪ አይሆንም። ደግሞም ፖለቲካ

ሀገርን ከማልማት ውጭ ሌላ

ዓላማ ሊኖረው አይገባም።

አንዳንድ ጊዜ፣

የፖለቲካ ትርጉም ያልገባው

ፖለቲከኛ በልጅነቱ የመታውን

ጉልቤ ዛሬ አስታውሶ ለማሰር፣

ሥልጣኑን ተጠቅሞ አፈንጋጭ

ባንፃሩ ቅደም ተከተሉ ተጠብቆ

አለማና ግቡ ተለይቶ ግልፅና

ሊዳሰስ የሚችል ሆኖ ትምህርቱ

መስፋፋት ካልቻለ በተቀራኒው

ኪሳራን ውድቀትን ሊያመጣ

እንደሚችል የታመነ ነው።

በትምህርት ስርአት ውስጥ

የመጀሪያም የመጨረሻም አላማና

ግብ ቢኖር የሰውን ልጅ አእምሮ

ማልማት እንጂ ቁስ አካላዊነትን

ማስፋፋት አይደለም።

የዘመናዊ ትምህርት አላማ ሊሆን

የሚገባው በጎ ስብዕና መላበስን

ሰብአዊነትን ርህራሄን አሳቢነትን

ቅንነትን በጠቅላላው በሞራል

መበልፀግን ማስቻል ነው።

ገንዘብ ማግኘት መኪና መግዛት

ቤት መስራት ጠፈር ላይ

መዝናናት ወዘተ በተደራቢነት

ማለትም የሞራል ግንባታው

እየተካሄደ ሞራሉ የበለፀገ ሰው

የሚሰራው እንጂ እንደመጀመሪያ

አላማ ተደርጎ በዘመናዊ ትምህርት

ውስጥ ከተቀመጠ ጥፋቱ ብዙ

ነው።

ቁጥር መደመር መቀነስ የጦር

ስትራቴጅ መቀየስ የንድፈ ሐሳቦችን

ሽኩቻ መቀላቀል ገንዘብን ማጋበስ

ቅድሚያ አለማዎቹ ከሆኑ ዘመናዊ

ትምህርት የሚያፈራው ሞራሉ

የዘቀጠ ዜጋ ብቻ ይሆናል። ራስ

ወዳድነት ጨካኝነት የሀገር ፍቅር

ማጣት ወዘተ ይነግሳሉ።

በመሆኑም ከእያንዳንዱ የሳይንስና

የቁጥር ትምህርት በቅድሚያ

ግብረ-ገባዊነት (ኤቲካል) ሥነ-

ልቦናዊ /ሳይኮሎጂካል/ ትህርቶች

ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባል።

፫. ሃይማኖታዊ

ትምህርቶች

የሰው ልጅ በተፈጥሮው

የአማኝነት ባህርይን የታለበሰ

ነው። በዚህ ማመኑ ውስጥ ያሉ

ስርዓቶችን ህገ ደንቦችን እና

የአኗኗር ዘይቤዎችን ማክበር

ህግ የሚያወጣ ይመስለኛል።

አንዲት ሀገር ያለ

በቂ ነፃነት መኖር ትችላለች

የሚል ፖለቲከኛ በተዘዋዋሪ፣

ያለ ፓራሹት ከአውሮፕላን ላይ

መዝለል እችላለሁ እያለ መሆኑን

ማወቅ አለበት።

በተለይ፣ ባለፉት

ዘመናት ለነፃነትና ለመብት ትልቅ

ቦታ ይሰጡ የነበሩ ህዝቦች፣ ዛሬ

ዛሬ ነፃነታቸው አጣብቂኝ ውስጥ

ሲገባ ‹ዝም› ካሉ ከታሪካቸው

ጋር እየተጣሉ ነው ማለት ነው።

አሊያም የነፃነታቸውን ታሪክ

በገዛ ፈቃዳቸው ገንዘብ ለመቅበር

እየተዘጋጁ ነው።

በዬትም ሀገር ያለፈው

ትውልድ ድል የተቀዳጀበትን ስልት

አሊያም ተነሳሽነት ይሔ ትውልድ

መድገም ካቃተው ቀስ በቀስ የታሪክ

ሞት ይከሰታል። የአንድ ተራ ሰው

ሞት፣ ከቤተሰቡና ወዳጆቹ አልፎ

ለብሔራዊ ሐዘን የሚበቃበት

ጉልበት የለውም። የታሪክ ሞት

ግን ከሀገር አልፎ ጎረቤት ሀገሮችን

ጨምር ለሐዘን ይዳርጋል።

ምክንያቱም ብዙ ሀገሮች ነፃነት

ያገኙት ከጎረቤቶቻቸው የነፃነት

ታሪክና እንቅስቃሴ ልምድ ወስደው

ነው።

ዜጎች፣ በየወቅቱ

ለሚያስመዘግቡት የነፃነት ድል

ሻማ ሲያበሩ ደስ ይላል። ነገር

ግን ነፃ መሆን አቅቷቸው ያለፈው

ወገናቸው ያስመዘገበውን ድል

ለመዘከር ‹ብቻ› ሻማ የሚያበሩ

ከሆነ ደስ አይልም።

አንድ ትውልድ በገነባው

የታሪክና የድል ማማ ላይ ሰላሳና

አርባ ትውልድ እየወጣ ሊሸልልና

ሊምነሸነሽ አይገባም። ሁሉም

ትውልድ የየራሱን ታሪክና ድል

ማስመዝገብ አለበት። ያለበለዚያ

‹‹የድል ታሪክ ማስመዝገብ

ያቃታቸው ትውልዶች እኚህ

ነበሩ›› ከሚል ጥቅስና የፎቶ

ኤግዚቢሽን የሚያመልጥ ሰው

አይኖርም።

የድል ታሪክ፣ መኪና

በመንዳትና ትላልቅ ቤቶችን

በመስራት የሚከሰት /የሚመዘገብ

የሚመስላቸው ደሀ ሰዎች፣ ሽሮ

እየበሉ ጮማ ታሪክ ማስመዝገብ

እንደሚችሉ ሊያውቁና ሊያምኑ

ይገባል።

ለሞራል ዝቅጠት ተጠያቂው ማን ነው?

መንግስት ወይም መንግስታዊ አሰራር በባህላዊና በሃይማኖታዊ

ጉዳዮች መደናገሩ ቀርቶ ይልቁንም ዘመናዊ ትምህርትን ሊሆን

በሚገባው መልኩ ማስፋፋት ከተቻለ ሁሉም ሰላም ይሆናል

ደግሞ ያስደስተዋል።

በዓለም ያሉ ሃይማኖቶች

በዝርዝር ጉዳዮችና በአንዳንድ

መሰረታዊ ነጥቦች ይለያዩ እንጂ

የጋራ መገለጫዎቻቸው የሆኑ ብዙ

ነጥቦች አሉ። ከእነዚህም ውስጥ

ሰላማዊ መሆን፣ ፍቅር መሰጠት፣

ግብረ-ገባዊ መሆን፣ ለደንቦች

መገዛት ወዘተ ይጠቀሳሉ።

የአንድ ዜጋ ሞራል የበለፀገ

ይሆን ዘንደ አስተሳሰቡም

በአወንታዊነት የተቃኘ ይሆን

ዘንድ ሃይማኖታዊ ትምህርቶች

ታላቅ አስተዋጽኦ አላቸው። አንድ

ሀገር፣ የአንድ ሀገር ህዝብ ወይም

የአንድ ሀገር መንግስት ከአንድ

ዜጋ የሚፈልጉትን አስተዋፅኦ

ሊያገኙ የሚችሉት ዜጋው

ከመሠረቱ በተስተካከለ የሞራል

መሠረት ላይ የቆመ ሲሆን ነው።

ባንፃሩ ሃይማኖቶች ለእውነታዊነት

ይህንን ያክል ተፅኖ ያላቸው

የመሆናቸውን ያክል ለጥፋትም

ይህንኑ ያክል ተፅኖ ይኖራቸዋል።

መከፋፈልን፣ ዘረኝነትን፣

ወገናዊነትን፣ ግላዊነትን መስበክ

የየሃይማኖቶች የዕለት ከዕለት

ተግባር ከሆነ የዜጎች የሞራል

ኪሳራ ቃላት የማይገልጠው

ይሆናል።

በእርግጥ የአንድ ሀገር ዜጎች

የሞራል ግንባታ ሥርዓቱን ሁሉ

በእጁ የያዘው መንግስት ላይ

ይንጠልጠል እንጂ አስተዋጽኦው

የሁሉም ነው።

በመሆኑም መንግስት ወይም

መንግስታዊ አሰራር በባህላዊና

በሃይማኖታዊ ጉዳዮች መደናገሩ

ቀርቶ ይልቁንም ዘመናዊ

ትምህርትን ሊሆን በሚገባው

መልኩ ማስፋፋት ከተቻለ ሁሉም

ሰላም ይሆናል።

ሰላም ለእናንተ!

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 184 ቅዳሜ ጳጉሜ 5/ 2003

መልካም ዓዲስ ዓመት

በአናንያ ሶሪ

በአብርሃም ተስፋዬ

ከቀደመው ዘመን አንስቶ

እስካሁን ስለግሪክ ፍልስፍናዎች

ይነገራል። የግሪክ ህዝቦች በክርክርና

በውይይት ከፍተኛ እምነት

እንደነበራቸው ይወሳል። ለዚህም

ይመስላል በርካታ ፍልስፍናዎች

ከምድረ-ግሪክ መነሳታቸው።

የፍልስፍናዎቹ መነሻ ደግሞ እኒሁ

የአመለካከት ልዩነቶች እንደሆኑ

ይታመናል። ናቸውም። በልዩነቶች

ውስጥ የሚፋጭ እውነት ይኖራል።

በልዩነቶች ውስጥ ማመንና ማሳመን

ይኖራል። በልዩነቶች ውስጥ

የሚወጡ የሚወርዱ ጉዳዮች

ይኖራሉ። በዚህ መሀከል ደግሞ

የበሰለ ነገር ይገኛል።

በግሪክ የነበሩ ፈላስፎችም

ታዲያ በአመለካከቶቻቸው ዙሪያ

ይወያዩ ይከራከሩ እንደነበር ይነገራል።

በተለይም ህዝብ ወደተሰበሰበበት

ቦታ በመሄድ አመለካከቶቻቸውን

ያንጸባርቃሉ። እነዚህ አመለካከቶች

በደንብ ይብላላሉ። ህዝቡም

የወደደውን፣ ያመነበትን ይቀበላል።

ለነገሩ እነዚህ

የአመለካከት “አባቶች” ስላመኑበት

አተያይ በአደባባይ በድንጋይ

ተወግረዋል፤ ስለእምነታቸው

በአደባባይ ተሰቅለዋል፤ ተገቢ ነው

ላሉት ምልከታ ከህዝብ መሀከል

እንደ ባዕድ ተቆጥረዋል፤ “የለም!

እንዲህ ነው” ብለው ለማሳመን በጣሩ

“አብደዋል፣ አቅላቸውን ስተዋል”

ተብለዋል፤ ስለአመለካከታቸው

የሚደርስባቸውን አሜን ብለው

ተቀብለዋል።

ትናንት ከትናንት ወዲያ

የተገፉትን የአመለካከት ባለቤቶች፤

ዛሬ የመርህ ሁሉ መነሻ፤ የተግባር

ሁሉ መዳረሻ እነርሱ እንደሆኑ

እናነሳለን። ዓለምም ያወድሳቸዋል።

“እከሌ እንዳለው” እያልን ያን ጊዜ

ህዝቡ ያልተቀበለውን አመለካከት

ለእራሳችን እምነት ማስኬጃ

እንደመጀመሪያ ምዕራፍ አድርገን

እንነሳለን። ዛሬ ላይ ስለበርካቶቹ

ስናነሳም “ከጊዜያቸው ቀድመው

የተፈጠሩ” እስከማለት እንደርሳለን።

ስለኢትዮጵያ ስናነሳ ስለአጼ

ቴዎድሮስ እንደምናነሳው ሁሉ።

እኔ ግን በዚህ

አልስማማም። ማንም ፍጡር

ወደዚህ ምድር በጊዜው ይመጣል።

ለዛውም መምጣት ባለበት ጊዜ።

ባይሆን ኖሮ የግሪክ ፈላስፎችንም፤

ኢትዮጵያውያኑንም ጀግኖች

አናያቸውም ነበር። ለነገሩ

ስለፍልስፍናዎቹ መነሻ ሲነሳ

የፈላስፎቹ አመለካከት ይነሳል።

ክርክራቸው ልዩ ነው። እርስበእርስ

ለመተማመን የማይፈነቅሉት

ድንጋይ የለም። ነገር ሲመረምሩ

ይከርማሉ። ብዙም ነገር ይፈትሻሉ።

ምክንያቱን ለህዝቡ የሚያቀብሉትን

ነገር በቅድሚያ ሊያምኑበት

እንደሚገባ ጠንቅቀው ያውቃሉ።

ይህንን ሳያደርጉ ወደህዝብ /

መድረክ/ ብቅ ማለት የማይታሰብ፣

እንደውርደትም ተደርጎ የሚቆጠር

ነገር ነው። ስለሆነም ከባድ ኃላፊነት

እንዳለባች ያስባሉ። ከዚህ ሁሉ

ዝግጅት በ|ላ ታዲያ የሚሆነው

እንዲሆን ከመድረኩ ብቅ ይላሉ

- የአቴና የድሮ ልጆች። ክብbን

ዳግም ለዘመናት እያስጠሩ ይኸው

ዛሬም ድረስ በየመዛግብቱ ሰፍረው

ይታያሉ። በርካታ ፍልስፍናዎች

ከዚህች የአመለካከት ልዩነቶች

ሲስተናገዱባት ከነበረች ምድር ከተፍ

ብለዋል።

በኢትዮጵያም በርካቶች

ስለአመለካከታቸው ብዙ ዋጋ

ከፍለዋል። ቀድሞ በተማሪዎች

ንቅናቄ ውስጥ ከፍተኛ እንቅስቃሴ

የነበራቸው፤ የዚያ ዘመን ሰዎች

ስማቸው ዛሬም ይጠቀሳል። በርካቶቹ

ዛሬ ላይ ሆነን ትንቢት ተናጋሪ አይነት

እንደነበሩ መገመት አያቅተንም።

ግን ብዙዎችን አጥተናል። እንዲህ

ያሉትን ትንቢተኞች በማጣታችን

ደግሞ እነርሱ ስለአመለካከታቸው

ከከፈሉት ዋጋ በላቀ፣ ኢትዮጵያ

እነርሱን ስላጣች የከፈለችው

እንደሚብስ እሙን ነው።

እንደኢትዮጵያ ባለ ሀገር

ደግሞ የአመለካከት ልዩነቶች ሊኖሩ

ግድ ነው። ይህንን ማስተናገድ

ኮመንትሪ

አሜሪካ ስለኢትዮጵያ ምን ታስባለች?

የአሜሪካ መንግስት ስለኢትዮጵያ

እና ስለገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ምን

ያስባል? በፀረ ሽብርተኝነት ዘመቻው

ውስጥ ኢትዮጵያን በምስራቅ አፍሪካ

ያለች እውነተኛና አስተማማኝ

አጋር አድርጎስ ያያታል? አልያስ

ከኤርትራ፣ ሱዳን፣ ሶማሊያና

ጅቡቲ ጋር ሲነፃፀር የተሻለ ወዳጅ

ኢትዮጵያ ናት ከሚል የአቅርቦት

እጥረት የተነሳ ሻል ካለው ጋር

የመቀጠል አዝማሚያ ይሆን? ዋርካ

በሌለበት አንቧጮ አድባር ይሆናል!

እንዲል ተረቱ። የአሜሪካ መንግስት

ብሔራዊ ጥቅሙን ከማስጠበቅ

አንፃርስ የጠ/ሚኒስትር መለስን

አብዮታዊ ዲሞክራሲ እንዴት

ይቃኘዋል? በተለይ ደግሞ ኢህአዴግ

እከተለዋለሁ ከሚለው የቻይና ፈለግ

እና ተዛማጅ የመንግስት ጣልቃ-

ገብ ፖሊሲዎቹ አኳያ፣ እንዲሁም

የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ

ውስጥ ያለጨረታ እና ተፎካካሪ

በ‹‹ድርድር›› ስለሚያገኙት ከፍተኛ

የወታደራዊና የንግድ አትራፊ

ሥራዎች አሜሪካ ምን ታስባለች?

በዛሬው የዊክሊክስ ገመና አጋላጭ

ጽሁፍ ውስጥ የተዘረዘሩት ጉዳዮች

በዋናነት የሚያጠነጥኑት የአሜሪካ

ኤምባሲና የአሜሪካ መንግስት

ስለኢትዮጵያ፣ ኢህአዴግ፣ እና

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ያላቸው

አመለካከት ምን እንደሚመስል

በጥቂቱም ቢሆን ለመቃኘት

በሚያስችል መልኩ ሲሆን ትንሽ

ግርም የሚያሰኘው ነገር ቢኖር ግን ይህ

ለአደባባይ የበቃ ገመና ስለኢትዮጵያና

ገዢዎቿ ከሚናገረውም በላይ

ወይም እኩል ስለአሜሪካ መንግስት

መንታ አካሄዶች እና የተሰላ ጥበባዊ

አቀራረብ በመስመሮቹ መሐል

ማንበብ ለሚችል ሁሉ የሚገልፀው

አያሌ ምስጢራት ይዟል።

አዎ እነዚህን ሁሉ ጉዳዮች በቅርበት

እየተከታተለ ዋሽንግተን ለሚገኘው

ነጩ ቤተመንግስት (White House)

ሪፖርት የሚያደርገው በኢትዮጵያ

ያለው የአሜሪካ ኤምባሲ ሲሆን

አብዛኞቻችን የማንገምተውን

ነገር ግን ውስጥ ውስጡን ሲነገሩ

የምንሰማቸውን የአደባባይ

ሹክሹክታዎች የአሜሪካ ኤምባሲም

ጭምር የሚጋራቸው የዲፕሎማሲክ

ማህበረሰቡ የኮሪዶር ላይ ወጎች

እንደሆኑ ስንቶቻችን እናውቅ

ይሆን? ታዲያ እነዚህን የአሜሪካ

ኤምባሲ አመለካከቶች፣ ትዝብቶች፣

ምልከታዎች እና ግንዛቤዎች ለህዝብ

ይፋ በማድረግ የሚታወቀው የድረ-

ገፅ ገመና አጋላጭ ዊክሊክስ ሰሞኑን

ባሰራጫቸው ቱባ ቱባ ሰነዶቹ

የኢትዮጵያን መንግስት እብድ

የጠ/ሚ/መለስን ያልተስተካከሉ እይታዎች ማረም ብንችልም፤

እንዲሁም በሰብዓዊ መብት ሪፖርቱ ዙሪያ ለመወያየትና የታዩት

ችግሮችን ለማረም ጥረት እያደረግን እንደሆነ ብናስታውቃቸውም፤

አሁንም እየቀጠለ ያለው የእነዚህ ጉዳዮች መነሳት የጠ/ሚኒስትሩንና

የመንግስታቸውን ጭንቀት ያመለክታል።

አዳዲስ የዊክሊክስ መረጃዎች ይናገራሉ

እብድ የሚያካክሉ ሚስጥራት ፀሐይ

አስመትቷቸዋል።

አሜሪካ የአቶ መለስን

ልማት ‹‹ገድላዊ የኢኮኖሚ

ዕድገት›› በማለት

ገልፃዋለች

ከሴናተር ኢንሆፍ እና ልዑካኖቹ

ጋር በApril 7 ከተደረገ አጭር ስብሰባ

በኋላ ጠ/ሚ መለስ አምባሳደሩን

ነጠል አርገው ወደ ጎን ወሰዱና

በግል ሦስት ጉዳዮችን አነሱላቸው።

1ኛ) በስህተቶች የተሞላ ነው

ብለው የሚያምኑበትን የስቴት

ዲፓርትመንት የሰብዓዊ መብቶች

ሪፖርት ‹‹ማሻሻል›› ስለማስፈለጉ

2ኛ) የአሜሪካ ኤምባሲ

የኢትዮጵያን ረቂቅ የፀረ-ሽብርተኝነት

ህግ ለሂውማን ራይትስ ዎች አሳልፎ

ሰጥቷል ስለሚባለው ውንጀላ እና

3ኛ) የተፈጠሩትን አለመግባባቶች

ለመፍታት እና የኢትዮ-አሜሪካ

ግንኙነትን ለማዳበር በከፍተኛ ደረጃ

ባለው እርከን የሁለትዮሽ ስብሰባዎች

መካሄድ ስለማስፈለጉ ነበር።

ከቅርብ ወራት ወዲህ የሚስተዋሉና

የአሜሪካ መንግስት እርምጃዎችን

ተከትለው እየባሰባቸው የመጡ

መረር ያሉ የአቶ መለስ ምላሾች

በርግጠኝነት የሚመነጩት የኦባማ

አስተዳደር ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን

ግንኙነቱን በምን መልኩ ይቃኘው

ይሆን? ከሚል የመንግስታቸው

ጭንቀት ነው።

ከዚሁ ጋር በተጓዳኝ የጠቅላይ

ሚኒስትሩ ምክንያተ-ቢስ ግትርነት

የሚንፀባረቅባቸው የብርቱካን

ጉዳይ፣ የመ.ያ.ድ.ዎች ህግ፣ ገድላዊ

የኢኮኖሚ ዕድገትና የኢትዮጵያ

የሰብዓዊ መብት አያያዞች ከብዙ

በጥቂቱ ለመጥቀስ መንግስታቸው

አገሪቱን በአሁን ሰዓት እያለፈችባቸው

ባሉ ጉዳዮች ላይ ከአሜሪካ ፖለቲካ

እና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች እንዲሁም

እሴቶች በተፃራሪ የቆመን የመከላከያ

ስለአመለካከት ልዩነት

የሚከፈል ዋጋ እስከምን?

የውዴታ ግዴታ ይሆናል። ተወደደም

ተጠላ እንደብዛታችን ልዩነታችንን

ተረድቶ አስተሳሰባችንንም

እንድናራምድ የሚፈቅድ አይነት

ምህዳር ያስፈልጋል። ከምንም ነገር

በላይ በአንድ እሳቤ ከመታጠር

የተሻለ እንደሆነም ይታየኛል።

ዛሬ ግን ይህንን

የሚያበረታታ ነገር መመልከት ከባድ

እንደሆነ ይሰማኛል። ስለበርካታ

ጉዳዮች ለመወያያትም የሚሻ ማግኘት

ከባድ እየሆነ ነው። በመሠረቱ

በዚህ ረገድ የትምህርት ማዕከላት

የሚጫወቱት ሚና ከምንምና

ከማንም ይልቃል። ልዩነቶች

እንዲስተናገዱ እድሉንና መንገዱን

ሁሉ ማመቻቸት፣ በልዩነቶቹ

ውስጥ የሚንቀለቀሉ እሳቤዎችን

እንዲፋፋሙ፣ ሌሎችም ያሻቸውን

እንዲመርጡና እንዲቀበሉ። የሀሳብ

አቅራቢዎቹም ምልከታ በተደራጀ

መልኩ እንዲቀመጥ ማስቻል

ይጠበቅባቸዋል - የትምህርት

አምባዎቻችን።

እንዲህ ያሉ ሀሳባቸውን

እንዳሻቸው መግለጽ የሚችሉና

የሚፈልጉ፣ ብሎም የሚደፍሩ

ዜጎችን ለማፍራት ደግሞ ተsማቱ

መድረኮችን መፍጠር ይኖርባቸዋል።

መድረኩን ከመፍጠርም ባሻገር

እንዲህ ያሉትን ዜጎች /ግለሰቦች/

ማወደስ ያስፈልጋል። ዕውቅናም

ሊቸራቸው ግድ ነው። ጠቃሚና

አሳማኝ አጀንዳ ይዞ ለሚመጣ

ማንኛውም ዜጋ በአንድም ይሁን

በሌላ፣ ብቻ ማኅበረሰቡን የሚጠቅም

ነገር እስከሆነ ድረስ፤ ማኅበረሰቡ

በአንድ አይነት አጀንዳ ላይ ብቻ

ማተኮር አለበት ከሚል ብሒል

ተላቀን፣ የሌሎችንም ምልከታ

ጠቀሜታ ሊኖረው ይችላል ብሎ

ማሰብ በጣም ጠቃሚ ይመስለኛል።

በማንኛውም ነገር

ላይ የሚነሱ ሀሳቦች በምሁራን

ውይይቶች ቢዳብሩ፤ ሀገራዊ የሆኑ

አጀንዳዎች ላይም ልዩነቶች ቢኖሩ

እንኳን የልዩነቶቹን መነሻ ለህዝቡ

በደንብ በማሳየት ህዝቡም እንዲወያይ

ግንብ እየገነባ እንደሆነ አመላካች

ነው። በመሆኑም ልክ የአፍሪካ

ጉዳዮች ረዳት ፀሐፊ እንደተመደበ

በከፍተኛ ደረጃ ባለው እርከን (senior

level) የሁለትዮሽ ስብሰባዎች

እንዲካሄዱ አሁንም እናሳስባለን።

ይህ እርምጃ የኢትዮጵያን ጭንቀቶች

ጋብ ለማድረግ ከመርዳቱም በላይ

ያሳሰቡንን ጉዳዮች አፅንኦት ለመስጠት

እና ለግንኙነቱ የምንሰጠውን ድጋፍ

ለማጠናከር ይረዳል።

አሜሪካ ኢትዮጵያን

እንደአስፈላጊ አጋር

አታያት ይሆን?

የጠ/ሚ/መለስን ያልተስተካከሉ

እይታዎች ማረም ብንችልም፤

እንዲሁም በሰብዓዊ መብት ሪፖርቱ

ዙሪያ ለመወያየትና የታዩት

ችግሮችን ለማረም ጥረት እያደረግን

እንደሆነ ብናስታውቃቸውም፤

አሁንም እየቀጠለ ያለው የእነዚህ

ጉዳዮች መነሳት የጠ/ሚኒስትሩንና

የመንግስታቸውን ጭንቀት

ያመለክታል። ይህም አሜሪካ

በኢትዮጵያ ላይ ያላት አቋም

እየጠነከረና እየባሰ ይሄድ ይሆን?

ከሚል እና አሜሪካ ከእንግዲህ

ኢትዮጵያን በቀጠናው እንዳለ ወሳኝ

አጋሯ አድርጋ ላታያት ትችል

ይሆናል ከሚል ጭንቀት የሚመነጭ

ነው።

አቶ መለስ ከዚህ የተሻሉ

መልካም ግንኙነቶችን እንደሚሹ

ግልፅ ቢሆንም እነዚህ የሁለትዮሽ

ግንኙነቶች ግን በርሳቸው መርህዎች

እንዲመሠረቱና ኢትዮጵያ የሰብዓዊ

መብቶችን፣ ዴሞክራሲን ብሎም

የኢኮኖሚ ልማትን በራሷ የፖሊሲ

ግቦች ተመስርታ በምታካሂድበት

ወቅት አሜሪካ ለአገራቸው

የመተናፈሻ እና የመፈናፈኛ ቦታ

እንድትሰጣት ይፈልጋሉ።

ማድረግ ተገቢ ነው።

መንግስትም ቢሆን

እንዲህ ላለው ነገር ትኩረት ሊሰጥ

ግድ ነው። ሁሌም አንድ ዓይነት

አስተሳሰብና አመለካከት ይዘን

እስከመቼ፤ እንዴትስ እንÕዛለን?

የነገዋን ኢትዮጵያ የሚረከበው ዜጋ

ዛሬ ላይ ባላንሸራሸረው አስተሳሰቡ

ነገን ማየት ይቻለዋልን? እውነት

ኢትዮጵያስ ህዳሴዋ እንዲሰምር

አማራጮች አያሿትም? እና ሌሎችም

ጥያቄዎች በውስጤ ይመላለሳሉ።

ምንም እንኳን እንደ

ግሪኮቹ ህዝብ ሰብስበን የምንወያይበት

ቦታ ባይኖርም፣ ሁኔታዎችን ግን

ማመቻቸት ተገቢም አስፈላጊም

ነው። ብዙ ጊዜ እንደውም ከዚሁ

የራስን አመለካከት በነጻነት ከመግለጽ

ጋር በተያያዘ በተለይም ከመንግሥት

ወገን ነን የሚሉት ግለሰቦች ቃላቸው

አንድ አይነት እየሆነ አግራሞት

ይፈጥርብኛል። ከላይ በመንግሥት

የሥልጣን መዋቅር ውስጥ ያሉት

ምናልባትም በውይይት ወቅት

ልዩነቶቻቸውን እያነሱ ይማEገቱ

ይሆናል። ይሆናል ነው ያልኩት።

ከዚህ ባለፈ የማስፈጸም ጉዳይ

እያነሱ ምላሽ ይሰጡ ይሆናል።

ሌላውን “ወገን ነኝ” ባይ ግን ምን

ይሉታል?

መግባባት እየቻልን

አይደለም። መደማመጥ አቁመናል።

የምናነሳውን ሀሳብ ለማስረዳት

ሳይሆን ለማዘዝ ይቀናናል። የተለየ

ነገር ለመቀበል ዝግጅቱ ያንሰናል።

ለነገሩ ልዩነት ያለው ነገር

የሚያመጣም ከጠፋ ሰንበት እያለ

ነው። ለዚህ ደግሞ በልዩነት መÕዝ

አለመቻላችን ወይም አለመፈለጋችን

በምክንያትነት ሊጠቀስ ይችላል።

በእርግጥም ልዩነቶችን

ያለማስተናገዳችን ነገር ዋጋ

እያስከፈለን ነው። “የተለየ ሀሳብ

አለን” ያሉ ዜጎችም በየዘመኑ

አጥተናቸዋል። መሪዎቻችንም

እንደልዩ ፍጡር እያዩዋቸው ዳግም

እንዳይደርሱባቸው አርቀዋቸዋል።

ትንቢት ተናጋሪ ምርጥ ዜጎች

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

7

አቶ መለስ የአሜሪካ

ፖሊሲ እንዲቀየር

ተፅዕኖ ለመፍጠር

ሞከሩ

ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ በFebruary 25

አምባሳደሩን ጠርተው በኢትዮጵያ

እይታ አሜሪካ ከጋራ ዓላማቸው

ውስጥ ከተካተቱት ከክልላዊ

መረጋጋት፣ ፀረ ሽብርተኝነት እና

ከልማት ጉዳዮች ይልቅ ለሰብዓዊ

መብቶች የበለጠ ትኩረት በመስጠት

ጠንከር ያለ የፖሊሲ ለውጥ

እያደረገች እንደሆነ እንደሚሰማቸው

ገለፁ። ይህ አባባል የውጭ ጉዳይ

ሚኒስትር አቶ ስዩም በ February

20 ለአምባሳደሩ የተናገሩትን

የቃላት ተቃውሞ የሚያጠናክር

ነበር። አቶ ስዩም የአሜሪካ ኮንግረስ

ኢትዮጵያን ልማትና መሰል እርዳታ

ከማግኘታቸው በፊት የኮንግረሱን

ማስገንዘቢያ ከሚፈልጉ እንደሱዳን፣

ዚምባቡዌ፣ እና ኢራን ያሉ 20

አገራት ዝርዝር ውስጥ ማካተቱን

አጥብቀው ተቃውመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲናገሩ

‹‹ኢትዮጵያ በሁለትዮሽ ግንኙነቱ

ውስጥ ከወዲሁ የሚታወቅ አካሄድን

(predictability) እና ኢትዮጵያ

ለአሜሪካ ምን ዓይነት ስፍራ ላይ

የቆመች አገር መሆኗን በግልፅ

ማስቀመጥ እንደሚያስፈልግ››

ገልፀዋል። እንደውም ጠ/ሚኒስትሩ

የወታደራዊ ኃይል የበላዩ ጄኔራል

ሳሞራ እና የደህንነት ክፍሉ

ሃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋ አሜሪካ

የኢትዮጵያን የደህንነት አሳሳቢ

ጉዳዮች ጉዳዬ ትላቸው እንደሆን

እምነቱ ተመናምኖባቸዋል

እስከማለት ደርሰዋል። እነዚህ ሁለቱ

ባለሥልጣናት ጦረኛ ነገር ግን

በውጭ ፖሊሲ ጉዳይ ላይ እጅግ

በ ገፅ 23

የነበራት/ያላት ኢትዮጵያ ብርታት

በሌላቸው ምክንያቶች ለዘመናት

ልጆቿን አጥታለች። ምናልባትም

ዛሬ ላይ ለጠፋው አመለካከትን

ጥርት አድርጎ ለማቅረብ ያለመቻል

ችግር በእነዚህ ዜጎች ላይ የተወሰደው

አሰቃቂና አሳዛኝ ግፍ የተሞላበት

እርምጃ እንደ ምክንያትነት ሊጠቀስ

ይችል ይሆናል።

በያለንበት አጋጣሚዎች

እንደሚፈጠሩበት ብርቱ

የምክንያታዊነት ጥያቄዎች ምላሽ

የሌለን ብዙዎች ነን። ለምን ብሎ

መጠየቅ እንደወንጀል የሚቆጠርብንም

እልፎች። በጣም አሳዛኙ ነገር

ኢትዮጵያ ላጣቻቸው ምርጥ ልጆቿ

መጥፋት ወይም መሸሽ ምክንያቱ

አሳማኝ አይደለም። ሞትን የተቀበሉ

በርካታ ኢትዮጵያውያን ነበሩ።

ልዩነቶችን እንደጦር

ከመፍራት ይልቅ፣ አቅርቦ

ማዳመጥና መመርመር ለመንግሥት

ኃላፊነትም ጭምር ነው። በዚህ

ረገድ ከመንግሥት ወዲያ ማን

የአንበሳውን ድርሻ መውሰድ

ይቻለዋል? ዜጎችም ከተጫናቸው

ፍርሃት ተላቀው አመለካከቶቻቸውን

በነጻነት የሚያንጸባርቁበትን ዘመን

ከመናፈቅ ይልቅ፣ ጊዜው አሁን

ነው ማለት ይገባቸዋል። መድረኩን

ማመቻቸት ደግሞ የሁላችንም

ድርሻ ነው። ለኢትዮጵያ ከእኛ

ወዲህ ማን እንዲመጣላት እንሻለን?

ለዘመናትስ ከዜጎቿ ይልቅ ሌሎች

ሲንሰፈሰፉላት ይታያል እየተባለች

እስከመቼ? አመለካከቶቻችንስ

ሳናወጣቸው ለመቼ? ፍርሃታችንስ

የሚለቀን፤ ስለአመለካከቶቻችንስ

የምንከፍለው ዋጋ እስከምን

ይደርሳል? እስከምንስ መድረስ

ይኖርበታል?

እኒያ የግሪክ ሰዎች

ብዙ ከፍለዋል። ስማቸውም ዛሬ

ድረስ ይወሳል። ኢትዮጵያውያኑም

በሚገባቸውም ደረጃ ባይሆንም

አንዳንድ ጊዜ ይነሳሉ። ልንዘክራቸው

ግድ ይላል። ምናልባትም ስለእነርሱ

ብርታት ማንሳታችን ሌሎች

ጀግኖች ይፈጥርልን ይሆናል።

እነርሱ ስለምልከታቸው የከፈሉትን

ዋጋ እያነሳን ማወደሳችን ሌሎች

እንደነሱ ላሉቱ ብርታት ይሆናል።

ስለሆነም “እናንተ ስለሀገራችሁ

ብላችሁ በቅን ልቡና ያነሳች|ቸው

አመለካከቶቻችሁ ዋጋ ያስከፈላDችሁ

ኢትዮጵያውያን ሆይ! ሰላማችሁ

ይብዛ፤ ጽናታችሁን በአሁኗ

ኢትዮጵያ ላለነው ያውርሰን”

እላለሁ።

8

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 184 ቅዳሜ ጳጉሜ 5/ 2003

መልካም ዓዲስ ዓመት

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 184 ቅዳሜ ጳጉሜ 5/ 2003

መልካም ዓዲስ ዓመት

‹‹በአዲሱ ዓመት ‘አሸባሪ’

ከመባል ይጠብቃችሁ››

በወጋየሁ ታምራት

ጤና ይስጥልኝ! እንዴት ናችሁሳ? ዓመቷን

እንደቀልድ ፉት አልናትም አይደል?። በርግጥ ዓመቱ

ማለቂያው ደረሰ እንጂ ማለቁን እርግጠኛ መሆን

አይቻልም። እንዴ! መንግስታችን ጳጉሜ ከተመቸው

ዓመቱ ይራዘም ቢልስ? ‹‹ሽብርተኛ›› በመያዝም እኮ

በዚህ ወር ስኬታማ ሆኗል…አይደል እንዴ?

አርቲስት ደበበ እሸቱም ‹‹ከአሸባሪው የግንቦት 7

አመራሮች ጋር በህቡ ሲያሴር በመገኘቱ ታሰረ››

መባሉን ሰምተናል። ‹‹ኧረ ደቤ ህብር መፍጠር እንጂ

ሽብር አያውቅም!›› ሲሉ አንዳንድ ተቆርቋሪዎችን

ብሰማ ‹‹እናንተ ውሳኔውን ለነፃው ፍ/ቤት ስጡ››

በማለት ገስጫቸዋለሁ። የተከሰሰ ፖለቲከኛ ሁሉ

ጥፋተኛ ሳይባል በነጣ መለቀቅ እኛ አገር እንብዛም

ስላልተለመደ ነው መሰል ሰዉ እስር ሲመጣ ይሰጋል።

‹‹ደግሞ እወቁ እኛ ማንንም ተቃወመን ብለን በፖለቲካ

አቋሙ የምናስር ሰዎች አይደለንም!›› የሚለውን

የትምህርት አይነት ሰሞኑን በደንብ እያስጠኑን ስለሆነ

በቀጣይ ጊዜ በደንብ አድርገን ለጠርጣሪዎች ለማስረዳት

ዝግጁ ነን። ግን ጥያቄ ያለው አለ?

ዓመቱ ለእርስዎ እንዴት ነበር? በዓመቱ ምን

ያላየነው አለ? እንደ ኑሮ ውድነት እደግመዋለሁ እንደ

ኑሮ ውድነት ኮሜዲ እና ትራጄዲ ፊልም የሰራብን

ግን አልነበረም። [ለነገሩ ማን ያልቀለደብን አለ?]

ዓመቱን እንደ ሩጫ ማቋረጥ የሚቻል ቢሆን እንደ

ገ/እግዚአብሄር የዴጉ ውሎ 38 ደቂቃ ድረስስ ማን

ይሮጥ ነበር? ያው እንግዲህ እየተደረቡም ቢሆን የኑሮ

ሩጫውን መቀጠል ነውና ይበርቱ የአገር ሰው!!!

እኔ ሰሞነኛ አገልጋይዎ የወግ ማዕዴ የፍስክ ወግ

ብትሉ፣ የጾም በየአይነቱ እዚህ ድረስ ነው ስላችሁ

[በአውራ ጣቴ አገጬን ነክቻለሁ።] ይሄውላችሁማ

አንዱ ፍንዳታ ብጤ… ‹‹የሚሰራውን የማያውቅ እብድ

ነው›› አለኝ። በጄ! አልኩት ቀጠለናም ‹‹መንግስታችንም

እኮ የሚሰራውን አያውቅም፡፡ ‘ቁርጥ የዋጋ ተመን’ አለ

አልተሳካለትም፣ ‘የታክሲ ስምሪት’ አለ ችግሩ ያው

ነው…›› ሲል ትክን ብዬ እና መንግስታችን እብድ ነው

ልትል ነው? ብለው አስቀያሚ ሳቅ ከሳቀ በኋላ ‹‹ያው

ነው…›› ብሎ ወሬውን ሊቀጥል ሲል በግልምጫ

ሰማይ አድርሼ ብመልሰው ቱር ብሎ ከአጠገቤ

ጠፋ፡፡ [የማትፈልጉት ነገር ሁሉ እንዲህ ቱር ብሎ

ከአጠገባችሁ ይጥፋላችሁ፤ አሜን! በሉ]

ግራ የገባው ሁሌም ቀኙ አይታየውም፡፡ እውነቴን

ነዋ! ለዚህ የሆዱን አውርቶ ቱር ብሎ ጠፊ የሚታየው

የተገነባው ዴሞክራሲ፣ መንገድና ህንፃ ሳይሆን ቤቱ

የፈረሰበት ብሶተኛ፣ ‹‹ምህረት›› የተደረገለት ሳይሆን

ግብር የተጫነበት ምላሰኛ ነው። እንደዚህ አይነቶቹን

ይዘን አገሪቱን እንዴት ለአቅመ አገር ማብቃት

ይቻላል?

ሌላ ወዳጄን አገኘሁትና ስለ እዚህ ቱር ብሎ ጠፊ

እና ንግግሩ ከአወራሁት በኋላ ለእርስዎ ከላይ

እንዳጫወትኮት እንደዚህ አይነቶቹን ይዘን አገሪቱን

እንዴት ለአቅመ አገር ማብቃት ይቻላል? ብለው ወደ

እኔ ዞሮ ቁጭ አለ። ‹‹አንተ እና መሰል ካድሬዎች

የምትናገሩትን የማታውቁ፤ በቀቀኖች፣ ህሊና እና

ሞራላችሁን የቀበራችሁ፣ ኢትዮጵያ በቀዳዳ ወንፊት

እያነፈሰች የአብዮታዊ ዴሞክራሲን ጠበል ካልጋትን

በኃይለየሱስ ካሳ

ልማታዊ ጋዜጠኛ (ል.ጋ)

ፉክክሩ በተመሳሳይ ሂደት ውስጥ ያለፉ እንስቶችን

ብቻ ቢመለከትም፣ ፍትሐዊና ዓለም አቀፍ

መለኪያዎችን ያሟላ እንደነበር የአፍሪካ ኅብረት

ታዛቢዎች ማረጋገጫ ሰጥተዋል። አንቺስ ማሸነፌ

ተገቢ ነው ትያለሽ?

ልማታዊ ቆንጆ (ል.ቆ)

ያለ ጥርጥር። ኦልሞስት ሁሉም ዳኞች ድምፃቸውን

ሰጥተውኛል። ወሳኞቹ እነሱ ናቸው። ባልፈልግም

እንኳ ምርጫቸውን የመቀበል አብዩታዊ ግዴታ

አለብኝ። በእርግጥ ለዚህ በመብቃቴ ደስታዬ አንድና

አንድ የለውም። ለህዳሴው መሳለጥ ማበርከት

የምችለውን አስተዋጽኦ ሳስብ ሀሴት ያናውጠኛል።

ል.ጋ

ባለድል መሆንሽ እንደማይቀር የውድድሩ አዘጋጆች

አስቀድመው ሲተነብዩ ነበር። የትንቢቱ መስመር

በእቅድና ጥናት ላይ ተመስርተው መንቀሳቀሳቸውን

አመላካች ነው። ተተኪ የልማት አርበኛ የመኮትኮት

ዓላማቸውንም በአንቺ አሳክተዋል። እስኪ እስካሁን

የመጣሽበትን ጎዳናና የወደፊት አቅጣጫሽን

ግለጪልን?

ል.ቆ

ሲጀመር መድረኩ የተዘጋጀው ማንም እንዳሻው

እየገባ እንዲፈነጭበት አይደለም። በጭራሽ። ይህ

ለድርድር አይቀርብም። ረጅም ርቀት ተጉዘን

የሚፈለግብንን ያሟላን ጥቂቶች ነን ለእጩነት

የደረስነው። “የተመረጡ ምርጦች” ይሉናል። ክበቡን

ለመቀላቀል ብዙ ትጋት ይጠይቃል። ጥቂት ጥቅም

ትላላችሁ፡፡ አሁን አንተ የምርጫ ሰሞን ስብሰባ፣

ስብሰባ ትል ነበር፡፡ ያኔ ትንሽ ግንባርህ ወዝቶ ነበር፡

፡ አሁን ግን እንዳለቀ የውሃ እቃ የሚፈልግህ አለ?››

ብሎ በጥያቄ ሀሳቡን ሲቋጭ እንደዚህ አይነቱን ሰው

እንዴት መመልከት እንዳለብን ከፓርቲዬ በተነገረኝ

መሰረት ‹‹አላዋቂ ነህ›› በሚመስል እና በሀዘኔታ

አስተያየት ‹‹ዝም ብለህ አትንጫጫ ሳይኖርህ

ማሳለጫ›› አላልኩት መሰሎት። ኤጭ! አሉ እኒያ

የማላውቃቸው ሴትዮ… ስንቱን እንዲህ ብዬ

እንደምችለው ግን አልገባኝም፡፡ ሰዉ እኮ እህ ብለው

ካዳመጡት ተበድሮ ያወራል።

ከእሱ ይልቅ የገረመኝ ይሄ IMF የሚባው ሰውዬ

ይሁን ሴትዮ ይቅርታ ዳታው ለጊዜው ቢጠፋብኝም

ግን… ለምን ከራሳችን ላይ አይወርድም? ‹‹የማክሮ

ኢኮኖሚያችሁ ሚዛኑ የተዛባ ነው። ነጋዴውም

እምነት እያጣ ነው›› የሚለው ማን ንገረን አለው?

ንገሩኝ ባይ! በእርግጥ ለትራንስፎርሜሽናችን ሩጫ

ላይ በመሆናችን ሻይ ቡና አላልነውም። በዚህም ደንፉ

(ንዴት) ጋማ ሲለው ጊዜ ‹‹ሚዛኑ የተዛባ ነው›› አላ!

እኔምለው ሚዛኑ በሻይና ቡና ነውንዴ የሚሰራው

ብል ታች ሰፈር ያለው አደገኛ ቦዘኔ አደገኛ ቃላት

ወረወረብኝ፡፡ ቀላል ይናገራልንዴ? ‹‹ለችግራችን ፔስ

ሜከር እየሆናችሁ ረሀብ ራሱ ሀትሪክ ሰርቶብናል…

ምዕራባውያኑ ጓዳችን ፈትሸው ለዓለም ሲያወሩ

እውነቱ አልጥማችሁ እያለ ለ‘አይናችሁን ጨፍኑ’

ጨዋታችሁ ቀይ ካርድ የሚመዝ አጥተናል …››

ቢለኝ ጀርባውን ሳላስጠና ምንም መናገር አያስፈልግም

ብዬ ዝቅ ብዬ አሳለፍኩት ልክ ነኛ! እንዲህ አይነት

ሰው ወይ ሽብርተኛ፣ ወይ ፅንፈኛ፣ ወይ ጨለምተኛ

ወይ ሌላ በ ‹‹ኛ›› የሚያልቅ ነገር እንደሆነ እኛ መች

እናጣዋለን?

እህሳ! ይች ክረምት ትንሽ ከበድ አለች አይደል?

‹‹ሊነጋ ሲል ይጨልማል›› እንዲሉ ነዋ! እኛም

አውቃንበታል ድህነታችንን ቀቅለን እየበላን፣

ቴሌቪዥን ላይ እናፈጣለን። እዚያ ደግሞ ጥጋብ ስላለ

ሚሊየነር ገበሬዎችን እያየሁ ‹‹ተመስገን›› ስል የሰማኝ

መንግስትን ማመስገን አላርጂክ የሆነበት አንድ ወዳጄ

‹‹ፓ! ወገኛ ነህ የታለ ስኳር ድንች? የት እንደጠፋ

ታውቃለህ? አታውቅም ምርጥ ምርጡን ለፈረንጆች

ሲባል አልሰማህም? እኛ ሳንጠግብ ኤክስፖርት

አድርገውታል›› ቢለኝ እንዴት በ‹‹አድርገውታል››

ይገደባል? ‹‹አድርጋችሁታል›› ባለማለቱ እኔን እንደ

ነጭ ለባሽ ነው እንዴ የሚያየኝ? ብዬ በገደምዳሜ

በጭላንጭል አይተው የተከተሉን ድንኳን ሰባሪዎች

ተንጠባጥበው ቀርተዋል። አካሄዳቸው ኪራይ

ሰብሳቢነት ነበርና። በበኩሌ ነፍስ ካወቅሁበት ጊዜ

አንስቶ ተሳትፎዬ ተስተጓጉሎ አያውቅም። ካምፓስ

ሳለሁ የተማሪዎች ህዋስ መሪ ሆኜ አገልግያለሁ።

ተመርቄ ከወጣሁ በኋላ ደግሞ የሴቶች ሊግ

ሊቀመንበር፣ የወጣቶች ፎረም ጸሐፊና ያላገቡ

ወጣት ሴቶች ፌዴሬሽን አቃቤ ነዋይ ነኝ። የሀገሪቱ

ታሪክ ተስተካክሎ እንዲፃፍ የተዋቀረው ኮሚቴ

ውስጥ በአባልነት አለሁበት። የምጣኔ ኃብታችንን

ምጥቀት የሚያስተነትኑ ቁጥሮች በተንኳሾች

ተዛብተው እንዳይዘገቡ ጠንክሬ እከታተላለሁ።

ከዚህም በላይ በቻይናዋ ዋንግ ዡ ከተማ የሶስት

ወር ሥልጠና ወስጃለሁ። “ወ/ሪት ልማት” መባል

ከማኩራትም ባለፈ በቀላሉ የማይገኝ ዕድል ነው።

እርሱን ተጠቅሜ የምሰራቸው ተግባራት ይኖራሉ።

ለአብነት ያህል ታዳጊዎች ምን ማሰብ እና እንዴት

ማሰብ እንዳለባቸው የሚነግር ተቋም ለመክፈት ጫፍ

ደርሻለሁ። በተጨማሪም “ኃይማኖት ለልማት” በሚል

ማዕቀፍ ላከናውነው የምሻው ውጥን አለኝ። አንተም

በሚገባ እንደምትረዳው በፈጣሪ ማመን ያን ያህልም

የሚያስፈልግ ጉዳይ አይደለም። የእኛ መንፈሳዊ

መጽሐፍ ትግላችን ያስገኘለን አምላክ-አካል ግለሰቦች

ቃላት ናቸው። እነርሱን ጠንቅቆ ማወቅና ማነብነቡ

ይበቃል። ሆኖም የእምነት ተቋማትን ልንገለገልባቸው

እንችላለን ብዬ አምናለሁ። በተረፈ የዘወትር ምኞቴ

ሁሌም የማልማትን ታላቋን ሀገር ሰሜን ኮሪያን

መጎብኘት ነው። እንደሚሳካ አልጠራጠርም። ዋነኛ

ሥራው ንግድን መቆጣጠርና ነጋዴዎችን ማውገዝ

የሆነ ቡድን አለ። የእሱ አካል መሆን ከቻልኩ

እርካታዬ የትየሌሌ ይሆናል።

ል.ጋ

የኢራንና የኩባ ተመራማሪዎች እንደደረሱበት

ሰሞነኛ ምርቃት

ከታች ሰፈር ልጆች ጋር በኮሪያ- ዴጉ ተካሂዶ የነበረውን የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ፍፃሜ እየተመለከትን እያለ

ምነው አትሌቶቻችን ውጤት ራቃቸው ብል እየተቀባበሉ ‹‹የሚወራውን አልሰማህም እንዴ?… ‘እያንጓለለ

ካልተፈታ’ ብለው አድማ ላይ እኮ ናቸው›› አሉኝ። ምን ለማለት ፈልገው እንደሆነ ግን አልገባኝም፡፡

ብነግረው ‹‹ምርጥ ምርጡ ጉዳይ ለትልልቆቹ ዓሳዎች

እንጂ ለትንንሾቹ በሰሚ ሰሚ ካልሆነ መረጃውን

ስለማይነግሯችሁ ከእኛ እኩል ናችሁ ብዬ ነው››

በማለት የሆዴን ስለነገረኝ በፀጥ ማርሽ ኩምሽሽ

አደረገኝ እላችኋለሁ። እኔንማ ሲጠራኝ ‹‹አትርሱኝ››

እያለ ነው፤ አትርሱኝ ካላልካቸው በቀር ለምርጫ

ሰሞን ካልሆነ እንዳንተ ያለው ካድሬ ትዝ አይላቸውም

ለማለት ነው።

[ውድ አንባብያን አሁን የዜና ሰዓታችን ስለደረሰ

ከዜናው በኋላ እንደገና እናወጋን]

ጤና ይስጥልኝ ዜና እናሰማለን ምክንያቱም ከማን

እናንሳለን፡፡

ሁሉም በኢህአዴግ ፊት እኩል ነው የሚለውን

‘እውነታ’ ሽሮ ‹‹አይደለም ታጋይ እና አባል የሚሉ

ልዩነቶች አሉ›› በማለት በቅምቀማ ቤት ሲያወራ

የተገኘው እንደልቡ ባሻዬ የተባለ ግለሰብ እንዲህ

ሊያናግረው የቻለው ምን ጠጥቶ ነው፣ ምንስ ተመግቦ

ነበር በሚል ሊካሄድ የነበረው ጥናት ትክክለኛ ቀኑ

ባይገለፅም ለሚቀጥለው ዓመት ጠዋት ተላልፏል

ተብሎ በየመሸታው ቤት እየተወራ ነው።

የውጪ ዜና፡- ትሪፖሊን በሚስጥር ለቀው አልጀሪያ

የገቡት የጋዳፊ ባለቤት ሰሞኑን በሚስጥር ቅኔ አዘል

ነጠላ ዚማ መልቀቃቸውን ከአልጀርስ ሰምተናል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት አቶ ኦባማም ይህን ቅኔ

ለፈታ ኢትዮጵያዊ እስረኛ(ሰው) ከስራቱ ይፈታል

[አሜሪካ ይሄዳል ለማለት ከሆነ አገራችንን መዘባበቻ

ማድረጋቸው ያሳዝናል] ሲሉ ሀሳብ ሰንዝረዋል

በማለት የዘገበው ነቆራ.com ነው አዝማቹ እንዲህ

ይነበባል።

አሻግሬ ሳየው ከማዶ ከጎራው

በዝናር ያጌጠው እሱ ነው ያ ጀግናው

ከዜናው ተመልሰናል ስራችንን እንቀጥል። ወግም ስራ

ሆነንዴ? ይላሉ የታች ሰፈር ልጆች። አልቀረባችሁም

እላቸዋለኋ! ስራ ስል ምን ትዝ አለኝ መሰላችሁ ሁለት

የቀድሞ ወዳጆቻችን አግኝቼ ምን እየሰራችሁ ነው?

ብላቸው ‹‹ስፖርት›› አሉኛ! ኧረ ሳቄ ናልኝ ካልኩ

በኋላ ሌላውን ከተመረቀ ሁለት ዓመት ያለፈውን ልጅ

አንተስ ምንድን ነው የምትሰራው? ብለው ጨዋና

ታታሪ የሚባሉትን የላይ ሰፈር ልጆች ጠርቶ ‹‹እነሱ

እንኳን አልያዙም›› ሲል በሾርኒ ዋልጌነቱን ነገረኝ።

በራሱ የሚያሽሟጥጥም አለ ለካ!

እኔምለው! ኮሌጅ ማስበጠሱ ብቻ ምን ዋጋ አለው?

የበጠሱትን መልሰው መቋጠር ካልቻሉ ኮሌጅ እንደ

በኒዩሊበራል ሀገራት ውበት ሴቶችን የመጨቆኛና

ወንዶችን የማሽመድመጃ ሴራ አካል ነው። ሥርዓቱም

እየተንኮታኮተ ከመሆኑ አንፃር በልማታዊ አስተሳሰብ

ውበት እንዴት ይገለፃል?

ል.ቆ

ዋናው ነገር የገላ መለምለም ወይም የመልክ ስልክክ

ማለት አይደለም። ከሁሉ በላይ በማንነት መኩራት

ያሻል። ኩራትህን ለመግለፅ ደግሞ መግደርደር

የለብህም። ለእኔ ፈታኝ የነበረው አጋጣሚ በደሜ

ውስጥ የበርካታ ዘሮች ጠብታ መኖሩ ነው። የምልህ

ገብቶሃል? የትኛውን ብሔር መወከል እንዳለብኝ

እርግጠኛ አልነበርኩም። አለባበሱ፣ ጭፈራው፣ ታሪክ

ነገራው አምታታኝ። የአባቴ አባት ወገኖቼ የእናቴን

እናት ወገኖች መጨቆናቸውን፣ የአባቴ እናት ወገኖች

ከእናቴ አባት ወገኖች ጋር መፋለማቸውን ተረዳሁ።

ግን ልማታዊነት ከጭቁኖች ጎን መቆም መሆኑን

አልዘነጋሁም። ያደረግሁትም ያንን ነው። ቁንጅና

ዝም ብሎ አይን ከማማለል ባለፈ የራሱ ግብና ፋይዳ

አለው። እርሱን ለመገንዘብ በቅድሚያ ሚናን መለየት

ግድ ነው። ዓለም ጥቁርና ነጭ ነች። ወይ ከጥቁሩ

ጋር ሁን ወይም ከነጩ ጋር ሁን። ልማታዊ ውበትን

ከተጎናፀፍክ የሚሉህን ትሰማለህ። የሰማኸውን

ታሰማለህ። በተቀደደልህ ቦይ ትፈሳለህ። በተመተረልህ

መንገድ ትነጉዳለህ። ዞር ዞር ብለህ ዙሪያህን መቃኘት

የለብህም። ጥያቄዎችን በማሰላሰልና በመሰንዘር

አትቸገርም። በእውነቱ አስደሳች ነው።

ል.ጋ

አንዳንድ የአዲስ አበባ ከተማ ኗሪዎች ውድድሩን

ማሸነፍሽ ከምስራቅ አፍሪካ መረጋጋት ጋር ቀጥተኛ

ተዛምዶ እንዳለው የገለፁበት ሁኔታ ነው ያለው።

ፊታቸውን ቅጭም አድርገውም ቢሆን ደስታቸውን

በሰላማዊ ሰልፍ ሊያሳዩ እየተሰናዱ ናቸው።

ሞባይል ካርድ መሸጫ ሱቅ መፍላቱ በእርግጥ

እንደ አካሄድ ከአገር ገፅታ ግንባታ አንፃር ሙድ

አለው። በየመንደሩ፣ በየኩሽናው፣ መከፈቱ ቁልፍ

ጥንካሬያችንን ያሳያል፡፡ [ሳቄ መጣብኝ፡፡ እናንተዬ

የብርድ ሳቅ ለካ ስትራፖ አለው።] ለማንኛውም ከሳቁ

ተመልሻለሁ።

ጠቅላይ ሚኒስትራችን አልናፈቁዎትም? ፈቃዱን

የሰጣቸው መድረክ ወይም ቅንጅት ይመስል ‹‹እነዚህ

የሠርተፍኬት መሸጫ ሱቆች…›› እያሉ በራሳቸው

እና በእኛ ላይ ፓርላማው ተከፍቶ ሲቀልዱ ማየት

ነው ያማረኝ። ይህን የትምህርት ‹‹አብዮት››

እና የሠርተፍኬት መሸጫ ሱቆች ሰሞኑን አይን

በዝቶባቸዋል። መንግስት እንደ ምርጫ ፈተና ኮሌጆቹን

ሀ፣ ለ፣ ሐ 1 እና 2 እያለ መክፈል ጀመረ አሉ።

በቀይ ካርድ የተባረሩም አሉ። ኢንቨስት ካደረጉ በኋላ

ከማባረር ቀድሞ ነበር እንጂ መደቆስ አትሉም?

መንጌን የሚያስታውሰን ነገር… የጠ/ሚኒስትራችን

ፎቶ በየቢሮው እና በአደባባዩ መሰቀል ከተጀመረ

ከራርሟል አይደለም? አንድ ወዳጄ ይህን ሲያነሳብኝ

‹‹እወደድ ባዩ ሰቀለው እንጂ እሳቸው ይህንን

አልደግፍምም፣ አላየሁም፣ አልሰማሁም፣ ብለዋል

አራት ነጥብ›› ብለው ‹‹በየሚኒስትሮቻችሁ፣

በየኮሚሽነሮቻችሁ ቢሮ ፎቶው ተሰቅሏል። ሰዎቹ

ወይ አይሰሙም፣ ወይ አይታዘዙም ማለት ነው።

የማይታዘዝ ደግሞ ነገ…›› ብሎ ሳይጨርስ እኔም

ቱር ብዬ ጠፋሁ፡፡ የቀረውን አሞራ ትጨርስላችሁ።

በሞቴ ሳልረሳው ልንገራችሁማ ኢቴቪ በሰከንድ

የማስታወቂያውን ክፍያ ጣራ ላይ ሰቀለውኮ

አሃ! ለእኛም ይታሰብልና ማስታወቂያ ባናሰራም

ማስታወቂያ እናያለና! ልክ ነኛ! በማስታወቂያው

ካልተዝናናን ታዲያ በምኑ ልንዝናና ነው…[በርግጥ

ማስታወቂያ ሰሪዎቹ ሁለት ብቻ መስለዋል፡፡ እነሱም

ጣሪያ ወጥተው ሲወርዱ አልቆባቸዋል እያሉ ታች

ሰፈር ያወራሉ] እኛ ሰፈር ቴሌቪዥን ድምፅ ተቀንሶ

ይከፈታል። ማስታወቂያ ሲመጣ ‹‹ከፍ አድርገው

ይባላል›› ሲያልፍ ይቀነሳል እንዲህ ነው ኢቴቪ ጋር

ተስማምተን የምንኖረዋ! ምን ላድርግ ታዲያ ከታች

ሰፈሮች ጋር ሲኖሩ ተስማምቶ ካልሆነ ስለማይቻል

ችያቸዋለሁ።

መቼም የእኔ ነገር አንዱን ጥዬ አንዱን አንጠልጥዬ

ሆነብኝ እንጂ ኢቴቪ ‹‹በኤሌክትሪክ የሚሰራ ባስ

ደብረ ማርቆስ ሊገጣጣም ነው። በቅርቡ ለሙከራ

ከጊዮርጊስ አዲሱ ገበያ ይጀምራል›› ብሎ ካስደሰተን

ይኸው ፀሀይዋ ስንት ጊዜ ገብታ ወጣች መሰላችሁ፡፡

‹‹ከምን ደረሰ ብለው አጣርተዋል?›› አሃ! ከማስደሰት

የገፅታ ግንባታ አንፃር ከሆነማ ይሄ የባቡር ዝርጋታው

ጉዳይስ እንዴት ነው?

ከታች ሰፈር ልጆች ጋር በኮሪያ- ዴጉ ተካሂዶ

የነበረውን የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ፍፃሜ እየተመለከትን

እያለ ምነው አትሌቶቻችን ውጤት ራቃቸው ብል

እየተቀባበሉ ‹‹የሚወራውን አልሰማህም እንዴ?…

‘እያንጓለለ ካልተፈታ’ ብለው አድማ ላይ እኮ

ናቸው›› አሉኝ። ምን ለማለት ፈልገው እንደሆነ ግን

አልገባኝም፡፡ ለማንኛውም ሳምንት በሰላም እንገናኝ

ዘንድ ከስንብቴ በፊት ከተማ ውስጥ የሚወራውን

ሰሞነኛ ምርቃት ቱቱ ብዬ ላድርስዎ። ‹‹በአዲሱ

ዓመት ‘አሸባሪ’ ከመባል ይጠብቅዎ!›› ሰላም!!!

የሚስ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ልማታዊ ውበት ምስጢር

አንባብያን ሆይ! የተያያዝነውን የሀገር ገፅታ ግንባታ በማስቀጠሉ ረገድ ጉልህ ሚና እንደሚጫወት የታመነበት ታላቅ ውድድር በቅርቡ መካሄዱ ይታወቃል። በውድድሩም በታሪካችን

ለመጀመሪያ ጊዜ የብሔር ብሔረሰቦችን እኩል ተሳትፎ ባረጋገጠ መልኩ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጣ የልማታዊ ዳኞች ቡድን፣ የልማታዊ ውበትን እሳቤ የተላበሰች ቆንጆ

መርጦ “ሚስ አብዩታዊት ዴሞክራሲ” ሲል ሰይሟል። ወርቃማው የአሸናፊነት ዘውድ በክብር ከተጫነላት ወጣት ጋር ልማታዊው ጋዜጠኛችን ቀጣዩን አጭር ቆይታ አድርጓል።

ለአድናቂዎችሽ ምን መልዕክት ታስተላልፊያለሽ?

ል.ቆ

ምልክታችሁ እሆን ዘንድ ስለፈቀዳችሁ

አመሰግናለሁ። ይህ ለእኔ የኮንትራት ውል ነው።

ስሜን በተግባር ካላስከበርኩ ህዝቡ ውሉን ያለማደስ

መብቱ ተከብሮለታል። አልፈልግሽም ብሎ ቀይ

ካርድ ሊመዝብኝ ይችላል። ስለዚህ አሁን የምለው

እኔ ለልማት ተግቻለሁ፣ ከጎኔ ቁሙና እጅ ለእጅ

ተያይዘን የአምስት ዓመቱ - አራት ሆነ’ንዴ? -

የእድገት ትራንስሚውቴሽን እቅድ ... ማለቴ እድገትና

ተራንስፊክሴሽን ... ኤጭ! ምን ዕዳ ነው’ቴ ...

የአምስት ዓመቱ የእድገትና ትራንስግሬሽን . . .

ል.ጋ

ትራንስፎርሜሽን

ለ.ቆ

አዎ። እርሱ እንዲሳካ የበኩላችንን እንወጣ።

ል.ጋ

በጣም ጥሩ። በመጨረሻ ከየወረዳ ኃላፊዎች

የሰበሰብኩት ዳታ አለ። ቁጥራቸው እዚህ ግቡ

ማይባልና ግራፉ እንደሚያሳየን ቁልቁል እየወረደ ያለ

ነቃፊዎች አላጣሽም። ምን ትያቸዋለሽ?

ል.ቁ

ወየውላችሁ!

ል.ጋ

አመሰግናለሁ ሚስ አብዮታዊት ዴሞክራሲ። ልማታዊ

ስኬትና አብዮታዊ ደስታ እንዲገጥምሽ እመኛለሁ።

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

9

10

በንፍታሌም

የመፅሐፉ ርዕሥ፡- ፒያሳ (መሐሙድ ጋ ጠብቂኝ)

የመፅሐፉ ደራሲ፡- መሐመድ ሰልማን

የመፅሐፉ አይነት፡- ወግ፣ መጣጠፍ እና የጉዞ

ማስታወሻ

የገፅ ብዛት፡- 181 ገፅ

የመፅሐፉ ዋጋ፡- 29 ብር

ፒያሳን የትውልድ መንደሬ ያህል

አብጠርጥሬ አውቃታለሁ። ለድፍን 15 ዓመታት

በውስጧ ተመላልሼባታሁ። ከእግር እስከ ራሷ ልቅም

አድርጌ አይቻታለሁ ብዬ አምናለሁ። በመሀመድ

ሙዚቃ ቤት ወረድ ብዬ ተረት ሰፈር ውስጥ ወግ

ሰልቄአለሁ። ሸቅብ ተመልሼ በዶሮ ማነቂያ ጉራንጉር

ተሹለክልኬአለሁ። ሰራተኛ ሰፈርን በቀን በለሊትም

ቃኝቻለሁ። ውቤ በረሃን፣ ገዳም ሰፈርን፣ አትክልት

ተራን ወዘተ በየተራ ውዬባቸዋለሁ፤አምሽቼባዋለሁ።

ሁሉንም የፒያሳ ‹‹መዳረሻ››ዎች እስኪበቃኝ ድረስ

አዳርሻቸዋለሁ። እንዲያው በአጭሩ፣ ከአጭሩም

በአጭሩ አውቃቸዋለሁ ባይ ነኝ።

ግን ደግሞ ከእኔ በላይ ፒያሳን የሚያሳየኝ

ሲገኝ ገረመኝ። ምን መገረም ብቻ? ደነቀኝ። ዕለት

በዕለት የምጎበኛትን ፒያሳ እንደ አዲስ በአይነ

ህሊናዬ እየቃኘሁ ሳቅኩ። አንድም በራሴ፣ አንድም

በሁላችንም፣ አንድም በማንነታችን እየሳቅሁ ከራሴ

ጋር ሙግት ገጠምኩ። እየሳቅኩ አዘንኩ። ‹‹እያነቡ

እስክስታ›› እንዲሉ።

እንዲህ ያለ ጥልቅና መንታ ሥሜት

ውስጥ የከተተኝ በቅርቡ ለአንባቢያን የቀረበውና

‹‹ፒያሳ›› የሚል ርዕስ የተሰጠው መፅሐፍ ነው።

‹‹ፒያሳ›› ከሚል ጉልህ ርዕሥ ሥር ‹‹ማሕሙድ

ጋር ጠብቂኝ›› የሚል ንዑስ ርዕሥ በድራቢነት

ተሰጥቶታል። ደራሲው ደግሞ መሐመድ ሰልማን

ይባላል።

ደራሲው መሐመድ ሰልማን ‹‹ፒያሳ››

(መሐሙድ ጋ ጠብቂኝ) የሚል ርዕሥ የሰጠው

ይህ መፅሐፍ ወጎችን፣ መጣጥፎችን እና የጉዞ

ማስታወሻዎችን በአንድነት አጣምሮ ይዟል። በ14

ክፍሎች (ርዕሶች) የተሰደሩት የመሐመድ ሰልማን

በረከቶች በፒያሳ ‹‹ምህዳር›› ብቻ የተከበቡ ይደሉም።

የሀገርን ዳር የሚያካልሉ፣ የሀገርን ሁለንተና ቁልጭ

አድርገው የሚያሳዩ የብዕር ትሩፋቶች ናቸው። በሌላ

አነጋገር የሀገር ዕውነት፣ የሐገር እብደት፣ የሐገር

ንቅዘት፣ የሀገር ዝቅጠት፣ የሀገር እምነት ወዘተ

እንደዘበት የታቀኙባቸው ናቸው። እንደገና በሌላ

አነጋገር የእኛ ማንነት፣ የእኛ ምንነት፣ የእኛ ዕምነት፣

የእኛ ሥነ ምግባር ልኬት ወዘተ በሚጥም ቋንቋ

የተመዘነበት ድንቅ የሥነ ፅሁፍ በረከት ነው።

ለዚህም ይመስለኛል የቀድሞው አዲስ

ነገር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ መስፍን ነጋሽ ፣ ካለበት

ከሀገረ- ስዊድን የሚከተለውን አስተያየት በመፅሐፉ

መቅድም እንዲህ ሲል ያሰፈረው፡-

‹‹በፀሐፊው እይታ ፖለቲካ/ፖሊሲ፣ ባህል፣

ኢኮኖሚና ጊዜ ተጣምረው የሰሩትን ኢትዮጰያዊ

ህይወት፣ አኗኗር፣ ህልም፣ ብሶት ወዘተ በጋዜጠኛ

አይን ከትቦልናል። ፅሁፎቹ የግለሰቦችንና የቡድኖችን

የቀን ተቀን አኗኗርና ትዝብት የሚያንፀባርቁ

እንደመሆናቸው የዘመኑ ‹ዜና መዋዕል› አካል

ተደርገው ሊታዩ የሚገባቸው ናቸው።…››

ይህ አስተያየት የመፅሐፉን ይዘት ብቻ

ሳይሆን፣ የደራሲውን ላቅ ያለ ችሎታ የሚጠቁም

ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ የሥነ ፅሁፍ አጥኚዎች

(ተመራማሪዎች) አንድ ደራሲ የድርሰቱ ምንጭ

የሆነውን ማህበረሰብ በሚገባ ማወቅ እንዳለበት

ነው ለደራሲነት ክህሎት ቅድሚያ የሚሰጡት።

ደራሲ ማህበረሰቡን የኑሮ ገፅታ፣ የኢኮኖሚውን፣

የፖለቲካውን፣ የማህበራዊ ህይወቱን ሁኔታ፣

ከእነዚህ ጋር ተያያዥ የሆኑ ታሪካዊ ክስተቶችን

ልቅም አድርጎ ማወቅ አለበት ይላሉ። ምክንያቱም

‹‹በሥነ ፅሁፍና በማህበረሰብ መካከል ጥብቅ ትስስር

አለ፤ ትስስሩና የእውኑ ህይወት ገፅታዎች የድርሰቱ

መሠረቶች ናቸውና›› ሲሉ ያሰምሩበታል።

የ‹‹ፒያሳ›› (መሐሙድ ጋ ጠብቂኝ) ደራሲ

መሐመድ ሰልማን፣ ይህንን የማህበረሰብን እና የሥነ-

ፅሁፍን ጥልቅ ትስስር በድንቅ ብቃትና ክህሎት ነው

ያስመሰከረው። ‹‹ዐደይ መቀሌ››፣ ‹‹በኤርትራ ሙዚቃ

የምትደንስ ከተማ››፣ ‹‹የመመረቂያ ፅሁፎች ጥቁር

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ፒያሳ

በ‹‹ ››

ገበያ››፣ ‹‹ሼ መንደፈር በመርካቶ››፣ ‹‹ከአዲግራት

እስከ ዛል አንበሳ›› ወዘተ በተሰኙ ርዕሶች ያቀረበልን

ታሪኮች ለዚህ አባባል አይነተኛ ማሳያዎች ናቸው።

በነገራችን ላይ በመፅሐፉ ውስጥ

ከተካተቱት ትረካዎች ስምንት ያህሉ በቀድሞዋ

‹‹አዲስ ነገር›› ጋዜጣ ለንባብ የበቁ ናቸው። ቢሆኑስ?

ዛሬም እንደ አዲስ እየተገረምን፣ እየተደመምን፣

በራሳችን እያዘንን እና እየተከዝን እናነባቸዋለን።

ራሳችንን እንፈትሽባቸዋለን። የት እንዳለንና ወዴት

እየሄድን እንደሆነ እናይባቸዋለን። ለማንኛውም ወደ

ዋና ጉዳይ እንመለስ። ወደ ደራሲው።

በ‹‹ፒያሳ›› መፅሐፍ የምናስተውለው

የደራሲውን የላቀ ችሎታ ነው፡፡ ደራሲው መሐመድ

ሰልማን በመማር ብቻ ሳይሆን፣ በተፈጥሮ

የተጎናፀፈው ድንቅ ችሎታ አለው ብንል ማጋነን

አይሆንም። መሐመድ በእርግጥ ይፅፋል። ይፅፋል

ብቻ ሳይሆን በቃላት መሳልን ተክኖበታል። በቃላቶች

ህብረ ነገሮችን አጉልቶ ያሳየናል። አንድን ነገር

በአንባቢያን ልቦናና አዕምሮ ውስጥ ለመቅረፅ ብዙም

አይጨነቅም። በቀላል ቋንቋ፣ በአጭርና በቁጥብ

ዓረፍተ ነገር፣ በተዋበ ስልትና ፍሰት መጥኖ በቀላሉ

ይገልፅልናል።

አገላለፁ ልክ እንደ ልጅነት ልብና አዕምሮ

ንፁህ ነው። ለዚህ አባባል አስረጂ ይሆን ዘንድ

የሚከተለውን መጥቀስ እንችላለን፡-

‹‹ትልቁ የአገራችን የህዝብ ሽንት ቤት

‹ማህሙድ ሙዚቃ ቤት› ማዶ ነው። ግርማዊነታቸው

የፈረንሳይ ህንፃ ባለሙያዎች አስመጥተው ነው

ይህንን የህዝብ ሽንት ቤት ያሰሩት። እውነቴን ነው።

ካላመንክ አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ የጻፉትን ‹የፒያሳ ልጅ›

መፅሐፍ አንብብ…›› (ገፅ 7)

መሐመድ ሰልማን አስረጅ ከማቅረቡ

በፊት ‹‹እመነኝ›› ይላል። ‹‹‹ከላማንክ እነ እከሌን

ጠይቅ፣ የእከሌን መፅሐፍ አንብብ›› ይልና ወደ ሌላ

ጉዳይ ያመራል። ህፃን ሆናችሁ ‹‹ካላመንክ እከሌን

እንጠይቅ›› ያላችሁበት የዕውቀት ማስረገጫ እማኝ

የጠራችሁበትን የቅንነት ዘመን አስታወሳችሁ?።

መሐመድ ሰልማን የተከተለው የአተራረክ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 184 ቅዳሜ ጳጉሜ 5/ 2003

መልካም ዓዲስ ዓመት

p Ç T@

ሽንቁር ሀገር ሲመተር

ስልትና ዘይቤ መራሩን የሚያጣፍጥ፣ ጠፋጩን

የሚያመር ነውና የአንባቢያንን ስሜት ሰቅዞ የመያዝ

ኃይል ደርቧል፡፡

‹‹ፒያሳ ፎቅ አልባ ናት ካልን ‹ገመናዋን

ማን ሸፈነላት?› የሚለው ጥያቄ ይከተላል።

በፒያሳ ወርቅ ወርቁን ስታይ ከጀርባ ምን እንዳለ

ትረሳለህ። በፒያሳ ቆንጆ ኮረዶች ሽው እልም ሲሉ

ስታይ ማሰቢያህ ይሰለባል። ደፈር ብለህ አንዷን

የፒያሳ ቆንጆ ዳሌዋን እያየህ በ‹ብሪቲሽ ካውንስል›

ወይ በ‹አምፒር› ወይ በ‹ሰራተኛ ሠፈር› በኩል ባለ

ቀጭን ቅያስ ውስጥ ትገባለች። መጨረሻዋን ልይ

ብለህ አሁንም ትከተላለህ። እስከ ውስጥ። ድንገት

ትሰለብብሃለች። በዚህ ቅፅበት ምን ሰወራት ብለህ

ለራስህ ስታንሾካሹክ ከጭርንቁስ ቤቷ በመስኮት

ወጥታ ‹ምን አልክ› ልትልህ ትችላለች። ስለዚህ

የፒያሳ ልጅ አትከተል። ከተከተልክም እጇን ይዘህ

ተከተላት፡፡…›› (ገፅ 10)

ይኼኔ ነው የዘይቤን ምንነት ማጠየቅ

የሚገባው። ዘይቤ የአንድን ሀሳብ፣ ድርጊት፣ የአንድን

ነገር ቅርፅ ወይም ሁኔታ፤ እንዲሁም የሰውን ባህርይ

ስሜትና መልክ አጉልቶና አድምቆ ለተመልካችም ሆነ

ለሰሚው ፍስሃ በመስጠት የሚቀርብ የአነጋገር ስልት

መሆኑን ነው የዘርፉ ምሁራን የሚያስረዱት።

ይህ ስልት ግዑዙ ነፍስ እንዲዘራ፣ ደብዛዛው

ብሩህ እንዲሆን፣ ረቂቁ እንዲገዝፍ ከመርዳቱም

በላይ ተገላጩ የስሜት ህዋሳትን ነክቶ ብሩህ ምስል

በመፍጠር በዓይነ ህሊና እንዲታይ፣ በእዝነ ህሊና

እንዲሰማ፣ ጣዕምና ለዛው እንዲታወቅ የማድረግ

ኅይል እንዳለው ነው ምሁራኑ የሚያስረግጡት።

ከዚህ አንፃር መሀመድ ሰልማን በሚያስገርም

ሁኔታ ተሳክቶለታል። ከላይ ለአብነት የጠቀስናትን

የፒያሳ ቆንጆ ታሪክ ልብ በሉ፡፡ የሚከተላትን

ወጣት ሹክሹክታ ብቻ ሰምታ ‹ምን አልክ› ስትል

ትታያችሁ። ያ ቤት በጭቃ ግድግዳ ነው የተሰራው

ወይስ በካርቱን? በካርቱንስ ቢሆን ሹክሹክታን እንዴት

ያሰማል? አይታያችሁም በመሐመድ ብዕር ውስጥ

የዚያች ቆንጆ ልጅ ሰፈር ጉስቁልና? ቤቶች እንዴት

ችምችም ብለው እንደተሰሩ?

ይህ ብቻ አይደለም፤ መለመድ በእያንዳንዱ

ታሪክ ውሰጥ በስላቁ ያስቀናል። እያሳቀን ስቃይና

ሰቆቃን ያሳየናል። እናም ከራሳችን ጋር እንዋቀሳለን።

ከአስተሳሰባችን ንቅዘት ጋር እንብሰለሰላለን። በትካዜና

በቁጭት እንትከነከናለን። የወደፊት ህይወታችንን

በሥጋት እናስተውላለን።

መሀመድ ሰልማን በትረካው ከሚያሳየን

ዕውነታ ውጪ ለማንም ለምንም አይወግንም።

እንዲያም ይበል እንጂ በፍፁም ቅንነትና ጨዋነት

ለኢትዮጵያዊነትና ለመልካም እሴቶቿ ከመወገን

ወደኋለ አይልም። ግን ደግሞ ውግንናው ንፅህናውን

የጠበቀ ነው። ‹‹ሼ መንደፈር በመርካቶ››ን ሊነቅሱ

ይችሏል። እነሆ፡-

‹‹… በየአጋጣሚው የማነባቸው አዳዲስ

መንፈሳዊ መፅሐፍትም ስለፍቅር የሚሰብኩት

ቃላት ጎድለውባቸዋል። ይልቁንም መጪው ዘመን

በኃይማኖቴ ላይ አደጋ የሚያንዣብብበት እንደሚሆን

የሚተነብዩና ነቅቼ እንድጠብቅም የሚያስጠነቅቁ

ናቸው። በተቀራኒው ጎራ የሚፃፉ መፅህፍትም

በተመሳሳይ መልኩ ተናዳፊ ናቸው።… ከቤተ ሙከራው

ሲወጡም ብዙ አማኝን የሚያስቀይም ውጤት ይዘው

እኛን ብቻ ስሙ ሲሉ ይንጎራደዳሉ። ያንኑ በመፅሐፍ፣

በሲዲ፣ በቲ-ሸርት ካልታተመልን ይላሉ። የእኔዋ

የአሁኗ መርካቶ በዚህ ሁሉ ተቃርኖ የተሞላች ናት።

በዚህ ዓመት በጋራ የተጀመሩት የፍልሰታና የረመዳን

ጾሞች ደግሞ ተቃርኖውን አጉልተው እያሳዩኝ ነው።

በመርካቶው ሼ መንደፈር።…›› (ገፅ 146)

መሐመድ ሳልማን ከኃይማኖት ሥነ

ምግባር አልባነት እስከ ትምህርት ጥራት ውድቀት፣

ከፖለቲካ ግራ መጋባት እስከ ማህበራዊ ህይወት

ዝቅጠት፣ ወዘተ ያልዳሰሰው ጉዳይ የለም። በዚህ

ትረካው ስለ ትግራይ ህዝብ ታዝናላችሁ። ስለ

አዲግራት ታዝናላችሁ። ስለ ትግራይ እናቶች

ታለቅሳላችሁ።

‹‹…በአዲግራት የሰማሁት የአፈሣ

ታሪክ አስደንቆልኛል። ለምሳሌ ሰርግ ላይ የነበሩ

ወንድማማቾች ከታደሙበት ሰርግ ድንኳን ታፍሰው

ተወስደዋል። ታላቅ በጦርነቱ ህይወቱ ሲያልፍ፣

ታናሽ ህይወቱ ተርፏል። ይህንን ታሪክ የነገሩኝን

ወዳጆቼን ይህ የሆነው በደርግ ጊዜ ነው? እያልኩ

ሞግቻቸዋለሁ። አይደለም። … መቀሌ ላይ ደግሞ

ዘወትር ማለዳ የቀበሌ ወታደር መልማዮች በየስርቻው

በየመንደሩ ይዞሩ ነበር፡፡ ያገኙትን ኮበሌ ቀብ

አድርገው ስልጠና ያስገቡታል። በየጎዳናው ወጣት

ሲጠፋ ደግሞ ቤት ለቤት አሰሳና አፈሳ ተጀመረ። …

እናቶች ልጆቻቸውን ለመሸሸግ ተገደዱ። ይህ ታሪክ

የደርግ አይደለም። … ‹ደብሪ›ን (ጎተራ) በጦርነቱ ጊዜ

እናቶች ልጆቻቸውን ለመደበቅ ተጠቅመውበታል…››

(ገፅ 167)

መሐመድ ስልማን መራሩን የህይወት

ዕውነታ በቀላል አገላለፅ ቁልጭ አድርገን እንድንጋት

ግድ ይለናል። ያላየነውን የቅንጦት የሚመስል የዘቀጠ

እና መረን የለቀቀን ብልግና እያሳየን እንድንጠየፍ

ያደርገናል። ‹‹የጀሚላ መዳፎች›› (ከገፅ 119-129)

ለዚህ ከበቂ በላይ አስረጅ ናቸው። ውቦቹ የጀሚላ

መዳፎች ፀያፍ ተግባራት የማህበረሰባችንን ብልሹነት

ለመግለፅ በእርግጥም ከበቂ በላይ ናቸው።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሶሲዮሎጂ

ዲፓርትመንት ሌክቸረር የሆኑት አቶ ደረሰ ጌታቸው

በመፅሐፉ መግቢያ ‹‹መሿለኪያ›› በሚል ርዕሥ

ባሰፈሩት አስተያየት የሚከተለውን ያሉት ለዚህ

ይመስለኛል።

‹‹አዲስ አበባን ሰንገው የያዙ ችግሮችንም

መሐመድ በሰላ ፅሁፉ ነቅሶ አውጥቷቸዋል።

ሥራ አጥነት፣ የኑሮ ውድነት፣ ሴተኛ አዳሪነትን

የመሳሰሉትን የኑሮ ችግሮች ላይ የራሱን ቁዘማ

(ሪፍሌክሽን) ያስነብበናል። አዲስ አበባን ሲያስስ

የከተማ አውቶብስ አይቀረውም። ከዚያ ወጣ ብሎም

የደረሰባቸውን የሀገሪቱ ክፍሎች በከተሜ ዕይታ

ታዝቧቸዋል። ‹ገጠርን ማዕከል ባደረገ› የልማት

ስትራቴጂና የሰው ኃይል ስብስብ የሚታወቀው

መንግስትና የከተማው ባለስልጣኖች ይህን መፅሐፍ

ቢያነቡት ጥሩ ነው…››

ምን ባሥልጣናት ብቻ? የሀገሪቷ

ህዝብ በሙሉ ቢያነበው ጥሩ ነው እንጂ። መቼም

ባለሥልጣናቱ ያነበንባሉ እንጂ አያነቡም። ህዝቡ ነው

ማንበብ ያለበት። ምክንያቱም ‹‹ፒያሳ›› (መሀሙድ

ጋ ጠብቂኝ) መፅሐፍ ውስጥ የሁሉም ህይወት አለ።

በጥበብና በጥበበኛ ብዕር የተኳለ። ያ ብዕር የመሐመድ

ሠልማን ብዕር ነው። የምናየውን ዕውነት፣ ባላየነው

መንገድና ዕይታ አሳምሮ፣ እንደዋዛ አዋዝቶ ልክ

ልካችንን የሚነግረን ድንቅ ብዕር። አቦ! ‹‹እጅ በነክ››

ብዬ ባሳርግ ነው የሚሻለው። እጅ በነክ!!!

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 184 ቅዳሜ ጳጉሜ 5/ 2003

መልካም ዓዲስ ዓመት

S ´ “ —

‹‹አሰብ የማን ናት?››

መፅሐፍ ለንባብ በቃ

አለም አቀፍ የህግ ባለሙያ የሆኑት እና በኢትዮጵያ ፖለቲካ

ውስጥ ጉልህ ሚና የነበራቸው ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም

አሰብ የማን ናት? በሚል ርዕስ መፅሐፍ ፃፉ፡፡ ዶ/ር ያዕቆብ

የመፅሐፉን ዋና አላማ ሲገልፁም ታሪክን፣ አለም አቀፍ ሕግን፤

የቀይ ባህር አፋሮች አንድነትና መብትን ከግንዛቤ አግብቶ የአሰብ

ወደብ ሕጋዊ ባለቤት ኤርትራ ወይስ ኢትዮጵያ ነች ለሚለው

ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት መሞከር እንደሆነ ነው፡፡ በተለያዩ

ዘመናት አሰብን ለማስመለስ የተደረጉ ትግሎችን፤ ስለ አልጀርሱ

ስምምነት እንዲሁም የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን አስተያየት

ከመያዙም በተጨማሪ ወደብ ለአንድ አገር ያለውን ኢኮኖሚያዊ

ፋይዳም አካቶ ይዟል፡፡

መፅሐፉ በ13 ምዕራፎች የተከፋፈለ ሲሆን 260 ገፆች አሉት፡

፡ በመፅሐፉ የተወሰነ ገፅ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ያቀረቡ ሲሆን

ይህንንም በመግቢያቸው አሰብን ወደ ኢትዮጵያ ለማስመለስ

የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ ስለሚያስፈልግ ለእነሱ መጠነኛ

ግንዛቤ ለማስጨበጥ እንደተዘጋጀ ገልፀዋል፡፡

መፅሐፉ በ45 ብር በመሸጥ ላይ ሲሆን ከሽያጩ የሚገኘው

ገቢ ለበጐ አድራጐት ድርጅቶች እንደሚውልና መታሰቢያነቱን

ለዴሞክራሲ፤ ለፍትህና ለአንድነት ሲታገሉ ለወደቁ

ኢትዮጵያዊያን አድርገዋል፡፡

በኳንተም ፊዚክስ ላይ

ውይይት ተካሄደ

በዶክተር አቡሽ አያሌው በተፃፈው ‹‹አልፋና ኦሜጋ››

መፅሀፍና በውስጡ ስለተገለፃው ‹‹ኳንተም ፊዚክስ›› ምንነትና

አጠቃላይ ሀሳብ ላይ ውይይት ተካሄደ። ውይይቱ የተካሄደው

ባለፈው ሳምንት እሁድ ረፋድ ላይ በጥቁር አንበሳ ት/ቤት

የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን የእኛና የዩኒቨርስ ማንነት

በኳንተም ፊዚክስ መነጽር ሲታይ ምን ገጽታ እንዳለው፣

ሳይንሱ በህይወታችን ስኬታማነት፣ ሰላምና ፍቅር እንዲሁም

ም ብልፅግና በኩል የሚጫወተውን ሚና እና ተያያዥ ነገሮች

ለህብረተሰቡ ግልፅ ለማድረግ ውይይቱ መካሄድን የመፀሀፉ

ደራሲና አዘጋጅ ዶ/ር አቡሽ አያሌው ገልጿል። የሳይንሱን

ትክክለኛነት በህዝቡ አስተሳሰብ ውስጥ ለማስረፅ ተከታታይ

ውይይቶች እንደሚካሄዱም ነው የተገለፀው።

“የትሮይ ፈረስ” እና ‹‹ገንዘብና

ፍቅር›› ፊልሞች ተመረቁ

በአስቴር ፊልም ፕሮዳክሽን የተዘጋጀውና 1 ሰዓት ከ40 ደቂቃ

የሚፈጀው ‹‹የትሮይ ፈረስ›› ፊልም ባለፈው ሰኞ ነሐሴ 30 ቀን

2003 ዓ.ም በብሔራዊ ቲያትር አዳራሽ በይፋ ተመረቀ።

በቤተሰብ ተፅዕኖ ምክንያት ወንድ ቀርባ የማታውቅ አንዲት

ቆንጆን ለመርታት በሚደረግ ጥረት ላይ የታሪኩን ጨብጥ

የመሠረተው ይህ ፊልም፣ በ1994 ዓ.ም ለህትመት ከበቃው

‹‹የትሮይ ፈረስና ሎሎች አጫጭር ታሪኮች›› ከተሰኘ መፅሐፍ

መነሻ ሀሳቡ የተወሰደ መሆኑ በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ወቅት

ተገልጿል። ይህም የሀገራችንን የአጫጭር ልብ ወለድ ደራሲዎች

ሥራ በማግዘፍ፣ ደራሲዎችን ሊያበረታታ ይችላል ተብሏል።

የፊልሙ ደራሲ አሳምነው ባርጋ ሲሆን፣ ዳይሬክተሩ ደግሞ

አርቲስት ቢንያም ወርቁ ነው።

አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ፣ ጌታሁን ሰለሞን፣ ሸዋፈራሁ

ደሳለኝ፣ ይገረም ደጀኔ፣ እፀህይወት አበበና ሎሎች ታዋቂና

አዳዲስ ተዋናዮችም ተሳትፈውበተል። ፊልሙን ሰርቶ

ለማጠናቀቅም 580 ሺህ ብር ወጪ መጠየቁም ታውቋል።

እንዲሁም በኤሊያስ ወርቅነህ ፕሮዲዩስ ተደርጎ በጋላክሲ

ፊልም ፕሮዳክሽን የቀረበው ‹‹ገንዘብና ፍቅር›› ፊልም ሀሙስ

በ8፡00 ሰዓት በሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት የኪነ-ጥበብ አፍቃሪያን

ታዋቂ ሰዎችና ጥሪ የተደረገላቸው አንግዶች በተገኙበት

ተመርቋል። አስቂኝ የሆነው ይህ የፍቅር ፊልም 1፡40 ሰዓት

ርዝመት ያለው ሲሆን በርካታ ተዋንያን እንደተሳተፉበትም

ተገልጿል።

‹‹ንቃት›› ፊልም ዛሬ ይመረቃል

በደራሲና አዘጋጅ ዮናስ ጌታቸው ተሰርቶ በሰርድ አይ ፊልም

ፕሮዳክሽን የቀረበው ‹‹ንቃት›› ፊልም ዛሬ በአዲስ አበባ ቴአትርና

ባህል አዳራሽ ይመረቃል። ፊልሙን ሰርቶ ለማጠናቀቅ ከአንድ

ሚሊዮን ብርና ከሁለት አመት በላይ መፍጀቱን አዘጋጆች

ለአውራምባ ታይምስ በላኩት መግለጫ አስታውቀዋል። ልብ

አንጠልጣይ የፍቅር ፊልም እንደሆነ የተነገረው ‹‹ንቃት›› ህዝቡ

ስለ ኤች. አይ. ቪ ግንዛቤ ቢኖረውም ችግሩ ባለመቀረፉ ላይ

እንደሚያጠነጥን እንዲሁም ሙሉ በሙሉ በአሜሪካ አገር

መሠራቱን ጨምረው ገልፀዋል።

ፋንቱ ማንዶዬ 60ኛ የልደትና

44ኛ የሞያ ቆይታውን አከበረ

አንጋፋው የጥበብ ሰው አርቲስት ፋንቱ ማንዶዬ 60ኛ

የልደት በአሉንና 44ኛ የኪነ-ጥበብ ቆይታውን ባለፈው ማክሰኞ

በደማቅ ሁኔታ አከበረ። ጳጉሜ 1 ቀን በአዲስ አበባ ቲያትርና

ባህል አዳራሽ ከቀኑ 8ሰዓት ጀምሮ በተዘጋጀው በዚህ ፕሮግራም

ላይ እጅግ በርካታ የሙያ አጋሮቹ ተገኝተው እንኳን አደሰረህ

ብለውታል። በእለቱ በአርቲስት ተስፋዬ አበበ (ፋዘር) የተፃፈ

‹‹እሱ ማን ነው›› የተሰኘ ህብረ ዝማሬ በተስፋዬ ቲያትር

ማደራጃ አባላት የቀረበ ሲሆን የተለያዩ ስጦታዎችና ሽልማቶች

ለአርቲስት ፋንቱ ተበርክተውለታል። በኪ- ጥበብ ቆይታው

33 የመድረክ ቴአትሮችን፣ 11 የቴሌቪዥን እንዲሁም ሁለት

ተከታታይ የሬዲዮ ድራማዎችን መስራቱ ተገልጿል።

ጥበብ ሀበሻ በልዩ ፕሮግራም

በአሉን ሊያከብር ነው

በሀበሻ ሚዲያና ፕሮሞሽን ሰርቪስ የሚቀርበው ‹‹ጥበብ

ሀበሻ›› የሬዲዮ ፕሮግራም አውድ አመቱን አስመልክቶ ልዩ

የኪነ-ጥበብ ፕሮግራም አዘጋጀ። ዘወትር አርብ ከ9-11 ሰዓት

እና ዘወትር እሁድ ከ6-8 ሰዓት በኪነ-ጥበብ፣ በቤተሰብና በፍቅር

ዙሪያ የመረጃ ፕሮግራሞችን በ96.3 ኤፍ ኤም የሚያቀርበው

ጥበብ ሀበሻ በበዓሉ ዋዜማ ምሽት ከ3-6 ሰዓት የተለያዩ ታዋቂ

ሰዎችን፣ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችንና አዝማሪዎችን በመጋበዝ

በቀጥታ ሥርጭት እንደሚያስተላልፍ የፕሮግራሙ አዘጋጅ

አብርሀም ግዛው ገልጿል።

እንኳን አደረሰህ ግዛቸው!

እንኳን አብሮ አደረሰን! ሰላም ነው?

በአሉን ለመቀበል ምን ምን ዝግጅቶች እያደረክ ነው?

እርግጥ ብዙ ዝግጅት አላደርግም። ግን ያው

እንደማንኛውም ሰው ማድረግ የሚገባኝን

አደርጋለሁ።

ዘመን መለወጫ ሲመጣ ምን ምን የምታስታውሰው ነገር አለህ?

አዲስ ዓመት ሲመጣ ከሌሎቹ በአላት ለየት

የሚልበት የራሱ ድባብ አለው፡፡ በውስጥሽ

የአዲስነትና የተስፋ ስሜት ያጭራል፡፡ እንደገና

ደግሞ በዓሉ በየትኛውም በሳምንቱ ቀናት ሊሆን

ይችላል። እስከዛሬ ለዋዜማው ስንሰራ ኢቭ እሁድ

ቀን ውሎ አላስታውስም። የዘንድሮው ኢቭ እሁድ

መሆኑ በራሱ ደስ ይላል። አመት በዓል ሲመጣ

ቤት ውስጥ የሚደረገው ሽርጉድ ድባቡ ሁሌም

ይታወሰኛል። ከዛ በተረፈ የተለየ የማስታውሰው

ነገር የለም። በእያንዳንዱ አመት እቅዶች ስላሉኝ

እነሱን አስታውሳለሁ።

በ2003 ምን አቅደህ ምን ተሳካልህ?

የተወሰኑ ነገሮች አቅጀ ነበር። በእቅዴ ያልተካተቱ

በርካታ ነገሮችም ተሳክተውልኛል። ራሴን አንደ

እድለኛ እቆጥራለሁ። ይሄ ነው ያ ነው ከማለት

ተቆጥቤያለሁ። ይህ የእግዚአብሔር ስራ ነውና።

ለበዓል በግ የመግዛት ልማድ አለህ?

አዎ። እገዛለሁ።

ለዚህ በዓል በግ ገዝተህ ቢጠፋ፣ ቢሞት፤ አሊያም በመኪና ቢገጭ

ደግመህ ትገዛለህ ወይስ ለእኔ ባይለው ነው ብለህ ትተወዋለህ?

[በጣም እየሳቀ] ይሄ ከባድ ጥያቅ ነው፡፡ ግን በጉ

ባልሽው መንገድ አደጋ ቢደርስበት ከእኔም ሆነ

ከቤተሰቦቼ ደስታ አይበልጥምና ደግሜ እገዛለሁ

እንጂ አይገርመኝም። ዋናው እኔ ደህና ልሁን

እንጂ ምናባቱ።

ኃብታም ነኝ ለማለት ነው?

እንደዛ ሳይሆን የበጉ መሞት ወይም መጥፋት

ከደስታዬ አይበልጥም ለማለት እንጂ ዋጋው ቀላል

ነው ለማለት አይደለም።

ዶሮ መገነጣጠል ትችላለህ?

እኔ ኧረ አልችልም! እንዴት አይነት ነገር ነው

ባካችሁ?! ምን መሰለሽ፤ በአል ሲሆን ቄጤማው፣

የቡና ስነ-ስርዓቱ፣ ሬዲዩው የሚዘፍነው የበዓል

ዘፈን . . . ሁሉ ነገር ደስ ስለሚለኝ እቤት ዶሮ

ሲሰራ፣ ሲገነጣጠል አያለሁ፤ አብሬም እሆናለሁ፡፡

ግን ዶሮ መገነጣጠልን አስቤው አላውቅም።

በበዓል ብዙ ምግብ በልተህ ታውከህ ታውቃለህ?

የባሠ አታምጣ! [ረዥም ሳቅ] በመጀመሪያ ደረጃ

የምግብ ፍላጎቴ ጥርቅም ብሎ የሚዘጋው በበዓል

ጊዜ ነው። እንኳን ብዙ በልቼ ልታወክ ይቅርና።

በልጅነትህ አበባ ስለህ እየዞርክ ትሰጥ ነበር?

አዎ በጣም! አበባ ስዬ መስጠት ብቻ ሳይሆን

ከየህፃናቱ በ10 ሳንቲም እየገዛሁ እኔ በ15ና

በ25 ሳንቲም የመሸጥ ቢዝነስ ጀምሬ አትራፊ

የነበርኩበትን ጊዜ አስታውሳለሁ። ይሄ እንደውም

ለዚህ በዓል መታሰቢያ ይሁንልኝ፡፡ የሚገርምሽ

አበባ በመሳልም በኩል የሚስተካከለኝ አልነበረም።

ዲዛይነር ነበርኩ ማለት ይቻላል።

የምትስላቸውን ነገሮች ታስታውሳለህ?

አደይ አበባ፣ የሚካኤልን ሥዕል፣ አደይ አበባ ላይ

መስቀል በመሳል መልካም አዲስ ዓመት የሚል

እፅፍና አመተ-ምህረቱን ከጎኑ አድርጌ እስል ነበር።

ቀለም የምገዛው ወይዘሮ ማሚቱ ከሚባሉ የልብስ

ቀለም ከሚሸጡ ሴትዮ ነበር። ቀጨኔ የታወቁ

የልብስ ቀለም ሻጭ ነበሩ። [ቀጨኔ የሽመና ሥራ

የሚካሄድበት አካባቢ መሆኑን ልብ ይሏል።]

ቀለሙን ከገዛሁ በኋላ መጀመሪያ ሸንበቆ እፈልግና

እዛ ላይ ጥጥ እጠመጥማለሁ። ከዛም መቀባት ነው

አልኩሽ።

ስኬች ያደረከው ላይ ማለት ነው?

እንዴ! ተይ እንጂ! ሀበሽኛ አድርጊው እንጂ።

‘ዲዛይን ያደረግከው ላይ’ ለማለት ነው። [‘ዲዛይን’ም

እኮ ግን . . . ???]

1

አፍታ

“እኔ ጋር ሥራ እንጂ ውበት

የሚባል ነገር የለም”

ድምፃዊ ግዛቸው ተሾመ

በባህል ዘፈኖቹ በዙዎች ጎጃም ተወልዶ እንዳደገ ቢገመቱም እሱ ግን የአዲስ አበባ ልጅ መሆኑን ይገልፃል። ከተለያዩ ድምፃውን ጋር በጋራ አልበም በማውጣት ወደሙዚቃው ጠልቆ የገባ ሲሆን

በ2001 ዓ.ም ‹‹ይሁና›› የሚል የራሱን አልበም በመልቀቅ ተደማጭነትን አግኝቷል። ውበቴ ሥራዬ ነው ከሚለው ድምፃዊ ግዛቸው ተሾመ ጋር ናፍቆት ዮሴፍ አዝናኝ ቆይታ አድርጋለች።

እሺ ‘ዲዛይን’ ያደረከው [የነደፍከው]ላይ? ሂሴን ውጫለሁ

እና እልሻለሁ አበባ ገዝቶ በመሸጥም በመሳልም

አንደኛ ነበርኩ።

የሠርግ ሥራ ሽቀላው እንዴት ይዞሀል?

ኧረ በጣም አሪፍ ነው! በነገራችን ላይ ከሽቀላ አንፃር

ብቻ አትይው፡፡ በተለይ ሰዎች በሠርጋቸው እለት

ሲደሰቱ ማየት ምን ያህል እንደሚያረካ ልነግርሽ

አልችልም። ሽቀላው እንዳለ ሆኖ ማለት ነው። እናም

እኔ ራሱ የሠርግ ካሴት ሰርቼ አጠናቅቄያለሁ።

ከ2004 እቅዴ አንዱ እሱን ማሳካት ነው።

ቢሰራም ባይሰራም በአዲስ አመት ዕቅዶች ይታቀዳሉ። ከካሴቱ ውጭ

ምን ያቀድከው ነገር አለ?

ከላይ የለገፅኩት የሰርጉን ካሴት ለአድማጭ ማድረስ

አንዱ ነው። ሌላው በ2004 ካቀድኩት ውስጥ የራሴን

ባንድ አቋቁሜ በራሴ ባንድ ሰርግ መስራት ነው።

የእግዚአብሔር ፈቃዱ ይሁን።

አንዳንድ ሰዎች መጠጥ የማይወዱ ቢሆኑም እንኳን በአል ሲመጣ

ከተለያዩ መጠጦች ይቀማምሳሉ። ከቢራውም፣ ከጠጁም፣

ከጠላውም፣ ከውስኪውም . . . ። አንተ በበአል ምን መጠጣት

ያስደስትሀል?

እኔ የማልዋሽሽ ነገር፣ እናቴ ቤት ሁሌም በበአል ጠጅ

አለ። ጠጁ ልስልስ ያለና ለተማሪ የሚሰራ አይነት

ነው። ወደ ብርዝ የሚያደላ ማለት ነው። እናቴ ቤት

እሱን ቁጭ ብዬ ስጠጣ ትክክለኛ የአመት በአል

ስሜት ይሰማኛል። በተረፈ ከዚህ በላይ ለመጠጥ ብዙ

ፍላጎት የለኝም።

እንጉርጉሮህን የሰሙ ብዙዎች ግዛቸው ጎጃሜ ነው እንደሚሉ

ታውቃለህ?

በመጀመሪያ እኔ ጎጃሜ ብሆን ደስ ነው የሚለኝ።

ከዛ በላይ ግን ኢትዮጵያዊ ነኝ። ይህ ደግሞ በጣም

ያኮራኛል፡፡ እንደዛም ሆኖ ተወልጄ ያደግኩት

አዲስ አበባ ውስጥ ቀጨኔ መድኃኒያለም

አካባቢ ነው።

ከመልክና ከቁመና ጋር በተያያዘ የግዛቸው ውበቱ

አንገቱ ነው ይባላል፡፡ ትስማማለህ?

የእኔ ውበቴ ወንድነቴ ነው።

ወንድነቴ ስትል?

ወንድ መሆኔ ነዋ!

የአንገትህንስ ነገር ብዙ አትስማማበትም?

እኔ አላውቅውም። እኔ ጋር ውበት

የሚባል ነገር የለም። ሥራ ብቻ ነው።

፡ ግን በጉ ባልሽው መንገድ አደጋ

ቢደርስበት ከእኔም ሆነ ከቤተሰቦቼ ደስታ

አይበልጥምና ደግሜ እገዛለሁ

እንጂ አይገርመኝም።

ዋናው እኔ ደህና

ልሁን እንጂ

ምናባቱ።

በመጀመሪያ ወንድነቴ ነው ውበቴ ያልከኝ ወንድነት ብቻውን

ውበት ነው ማለትህ ነው?

ወዴት ወዴት! እኔ እንደዚህ ወጣኝ? ወንድ

አሁን ቆንጆ ሆነ አልሆነ ለእኔ ግድ የለኝም።

ሴት ልጅ ግን ውበትን በመቀባባትና በተለያዩ

ዘዴዎች ታመጣዋለች። እኔ በግሌ ግን ቆንጆ

ሆንኩ አልሆንኩ ግድ የለኝም። አላስበውምም።

ስራ ላይ ነው ትኩረቴ።

እናስ ቆንጆ ነኝ ብለህ ታምናለህ?

ቆይ በናትሽ . . . ይሄ የሚያስጠላ ጥያቄ

አይመስልሽም? [መመለስ አልፈለገም።]

እስከዛሬ ፊት ለፊት ያላገኘኸው ግን ደግሞ የምታደንቀውና

በዚህ አጋጣሚ እንኳን አደረሰህ ማለት የምትፈልገው ካለ?

እኔ በጣም ደስ የሚሉኝና በጣም የማደንቃቸው

ጠቅላይ ሚኒስትሩን ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር

መለስ ዜናዊን፣ “እንኳን ለ2004 ዓ.ም አዲስ

አመት ከነቤተሰብዎ በሰላም አደረሰዎት! አመቱ

የጤና፣ የሰላምና መልካም የአመራር ጊዜ

እንዲሆንልዎ እመኝልዎታለሁ!” በይልኝ።

ለኢትዮጵያ ህዝብ የትኛውን ዘፈንህን ልጋብዝልህ?

በመጀመሪያ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን

ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ በይልኝ። ከዛም

‹‹አውዳመቱ›› የተሰኘውን ዘፈን ጋብዣቸዋለሁ።

አመሰግናለሁ።

11

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

12

በኤልያስ ገብሩ

ከተቋቋመ ሦስት ዓመታትን ያስቆጠረው

ጃካራንዳ ኢንተግሬትድ አግሮ ኢንዱስትሪ

አ.ማ በተለያዩ ጊዜያቶች ለሀገር ውስጥ

መገናኛ ብዙሃን የሚያዘጋጃቸውን የመስክ

ጉብኝቶች መሠረት በማድረግ የአውራምባ

ታይምስ ዝግጅት ክፍል እሁድ ነሐሴ

29/2003 ዓ.ም ድርጅቱ ተግባራዊ ሥራውን

እያከናወነ በሚገኝበት በአዋሽ መልካሳ

የግብርና መስክ ላይ ከቀትር ጀምሮ ተገኝቶ

ነበር፡፡ ምንም እንኳን ያለነው በክረምት ወራት

መገባደጃ ላይ ቢሆንም፣ በወቅቱ በአዋሽ

መልካሳ የከረረ ፀሀይ ሳይኖር የሙቀት ወበቁ

ግን ከላይ የተደረበ ልብስን የማስወለቅ አቅም

ነበረው፡፡

አዋሽ መልካሳ ደርሰን ከናዝሬት ወደ አሰላ

በሚወስደው ዋና መንገድ በስተቀኝ በኩል

በሚገኝ ኮረኮንጅ መንገድ ወደ ውስጥ ጥቂት

መቶ ሜትሮች በመኪና ከገባን በኋላ አንድ

አነስተኛ ድልድይ ጋር ደርሰን በመቆም

ከመኪና ወረድን። ቀጥሎም፣ ለመስክ ጉብኝቱ

በስፍራው ለነበርነው ለዚህ ፅሁፍ አቅራቢና

ለአውራምባ ታይምስ ማኔጂንግ ኤዲተር

ዳዊት ከበደ፣ የአክሲዮን ማሕበሩ የቦርድ

ሊቀመንበርና ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት

አቶ ደምመላሽ ወጋየሁ ገለፃ ያደርጉልን

ጀመር

ጥናትን መሠረት

ያደረገ የውኃ ጠለፋ

በጠባቧ ድልድይ ሥር 400 ኩንታል

ክብደት ያለው ኮንክሪት ድንጋይ ተቀብሯል፡

- ወደ ወንጂ ስኳር ፋብሪካ የሚሄዱ ከባድ

ተሽከርካሪዎችን መሸከም እንዲችል ታስቦ፡፡

ከድልድዩ በስተቀኝ የተወሰኑ ሜትሮች ራቅ

ብሎ የአዋሽ ወንዝ እንደደፈረሰ በእርጋታ

ተፈጥሯዊ ጉዞውን ሲያደርግ ይታያል፡፡

የውሃ ሥራዎች ዲዛይንና ቁጥጥር ባለስልጣን

መ/ቤት በወንዙ ላይ በቂ ጥናት አድርጎ

ጃካራንዳ ኢንተግሬትድ አግሮ ኢንዱስትሪ

አ.ማ እያካሄደ ለሚገኘው የልማት ሥራ

አገልግሎት እንዲሰጥ ሁለት ኪሎ ሜትር

የውሃ መስመር ጠለፋና የቦይ ግንባታ

መሥራቱን አቶ ደምመላሽ ይናገራሉ፡፡

በሚፈልገው አቅም ውሃ እንዲያመጣ ተደርጎ

በግንብ በተሰራው ቦይ ውስጥ የሚያልፈው

ውሃ በተገቢ የውሃ ፍሰት ቀመር የተስተካከለ

በመሆኑ በአካባቢው የሚገኙትን የሕብረተሰብ

የግብርና ማሳዎች ከጎርፍ ለመከላከል ትልቅ

ድጋፍ ይሰጣል።

በተፈጥሮ የስበት ኃይል አማካኝነት

አንድ ኪሎ ሜትር ያህል የሚጓዘው ይኼ

የተጠለፈው ውሃ ጃካራንዳ በሰራው መጠነኛ

ግድብ ውስጥ ለመጠራጠም ይገደዳል።

[ሌላው አንድ ኪሎ ሜትር በግፊት ኃይል

የሚንቀሳቀስ ነው] በውሃው መሄጃ ግራና

ቀኝ፣ በተለይም በስተግራ በኩል ያሉት

እንደ ዝግባ፣ ግራርና ባህር ዛፍን የመሳሰሉ

ዛፎች፣ ቁጥቋጦዎችና ሳሮች ከሌላው በተለየ

መልኩ ለምልመው ይታያሉ። …‹‹እነዚህ

በፊት ውሃ በአጠገባቸው በማያልፍበት ጊዜ

የመቅላትና የመድረቅ ባህሪ ነበራቸው››

በማለት ስለሁኔታው በንፅፅሮሽ የገለፁት አቶ

ደምመላሽ፣ በጥናት ተመርኩዞ የተካሄደው

የውሃ ጠለፍ ሥራ በአካባቢው ሥነ-ምህዳር

ላይ አዎንታዊ ለውጥ ማምጣቱን በአፅንዎት

ይናገራሉ። በእርግጥም ለዚህ ጥሩ ምስክር

የሚሆን ነገር ወዲያው ተመለከትን፡፡

በግድቡ አጠገብ ቅርንጫፎቻቸው ተንዥርግጎ

አንገታቸውን ወደ መሬት ዳፋ ባደረጉት

የግራር ዛፎች ላይ በሕብረ-ቀለማት ያሸበረቁ

ወፎች ጎጇቸውን ቀልሰው በነፃነት እየዘመሩ

ነበር።

ጥቅመ- ብዙዋ ትንሿ ግድብ

በአጠቃላይ 300 ሜትር ርዝመትና 10

ሜትር የጎን ስፋት ያላት ትንሿ ግድብ ከጥቂት

ወራቶች በኋላ ለመስኖ ልማት፣ ለከብቶችና

ፍየሎች መጠጥ ውሃና ለሌሎች አገልግሎቶች

ጥቅም ለመስጠት ተዘጋጅታለች። በግድቢ

ውስጥም 11 ሺህ አሳዎች በመርባት ላይ

ሲገኙ ከእነዚህም መካከል አንድ ሺህ ያህሉ

ለቻይናዊያኖች ተሽጠዋል፡፡ በቀጣዩ ዓመት

መስከረም ወር ደግሞ የሚረቡት አሳዎች

ቁጥር 40 ሺህ እንደሚደርስ የሚናገሩት

አቶ ደምመላሽ፣ ይህንን በተመለከተ የሰበታ

አሳ ምርምር ድርጅት ተመራማሪዎች ጥናት

ማካሄዳቸውን ይገልፃሉ። ከግድቡም በላይ

ትንሽ ሞልቶ የሚፈስሰው ውሃ ተመሳሳይ

መንገድን ተከትሎ ወደ ሌላኛው የአካባቢ ስፍራ

በአነስተኛ መጠን ሲጓዝ ይታያል፡፡ ሆኖም

ግን፣ እንደ አክስዮን ማህበሩ ኃላፊ ንግግር

ከሆነ ጃካራንዳ ይኼንን የውሃ መስመር 300

ሜትር ያህል አስተካክሎ በማዘጋጀት ሌላ

ተመሳሳይ የአሳ ማርቢያ ግድብ ለመስራት

የአጭር ጊዜ ዕቅድ ነድፏል።

ከግድቡ ጎን ከፍ ብሎ ደግሞ አዲስ

የተሰራ የውሃ መሳቢያ ፓምፕ የሞተር

ክፍል የሚገኝ ሲሆን፣ በኤሌክትሪክ ኃይል

የሚሰራው ይኼ ፓምፕ 90 ኪሎ ዋት

ኃይል ሲኖረው በሰኮንድ 75 ሊትር ውሃ

የመሳብ አቅመ አለው። ይኼም በ45 ሜትር

ርቀት ላይ ተሰርቶ ሙሉ በሙሉ ሊጠናቀቅ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ለተቃረበውና ሲያልቅ አምስት ሺህ ኪውቢክ

ሊትር ውሃ የመያዝ አቅም ላለው የውሃ

ማጠራቀሚያ ገንዳ (Reservoir) ውሃን

በፍጥነት ያቀብላል። አንዴ በገንዳው ውስጥ

የሚጠራቀመው ውሃ ለአንድ ሳምንት

ያህል ለካምፓኒው የተለያዩ ስራዎች

አገልግሎት በቂ እንደሆነ የተናገሩት አቶ

ደምመላሽ፣ የውሃ መስመሮች ተዘርግተው

መጠናቀቃቸውንና የኤሌክትሪክ ኃይል

አቅርቦት ለማግኘት ደግሞ ትራንስፎርመር

በጥሩ ሁኔታ መተከሉን ያስረዳሉ፡፡

ሕብረተሰብን ያማከለ ልማት

እስከ ግድቡ ድረስ ባሉት መሬቶች ግራና

ቀኝ ከሚገኙት ቦታዎች መካከል ሁለት

ሁለት ሜትር ብቻ ለጃካራንዳ የሥራና

የመንገድ አገልግሎት በመተው በቁጥቋጦ

በተለይም፣ በቁልቋል የተሸፈኑትን መሬቶች

በመመንጠር በአካባቢው ለሚገኙ 500 ያህል

ወጣቶች ለግብርና ልማት እንዲጠቀሙበት

በዕቅድ ተነድፎ ወደ ሥራ እየተገባ ያለበት

ሁኔታ መኖሩን ኃላፊው ይገልፃሉ። በጉዳዩ

ዙሪያም፣ ከፌዴራል መንግስት የኦሮሚያ

ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት ም/ኮሚሽነር

አቶ ሳሙኤል ገዳ ጋር በአካል ተገናኝቶ

በመምከርና አካባቢውን በማስጎብኘት ጥሩ

መግባባት ላይ ተደርሶ ይሁንታ ሊገኝበት

ችሏል። ለወጣቶቹም የተለያዩ የአትክልት

ችግኞችን፣ ዘሮችንና የውሃ አቅርቦትን

የሚሰጣቸው ጃካራንዳ ነው፡፡ ‹‹በአሁን

ወቅት የአካባቢው ሕብረተሰብ ለድርጅታችን

ያለው አመለካከት በጣም መልካም ነው፡

፡ ሕብረተሰብን ያላማከለ ልማት ውጤታማ

አይሆንም፡፡ ከሥራችን ጎን ለጎን ሕብረተሰቡ

ተጠቃሚ እንዲሆን እንፈልጋለን›› ሲሉ

የገለፁልን አቶ ደምመላሽ፣ ከዚህ ቀደም

ተሰርቆባቸው የነበረውን የውሃ መሳቢያ

ፓምፕ ሕብረተሰቡ ተከታትሎ ማስመለሱን

በመልካም አርያነት ያስታውሱታል፡፡

እንደመሬቱ አመቺነት መስራት

የጃካራንዳ ኢንተግሬትድ አግሮ ኢንዱስትሪ

አ.ማ ለሥራ የተሰጠው አብዛኛው መሬት

ለግብርና ልማት በጣም የማያመች መሆኑ

ይገለፃል፡፡ በዓይን አይቶ ምስክርነት

ለመስጠትም ቀላል ነው። አክሲዩን ማሕበሩን

በመጀመሪያዎቹ ወራት ከገጠሙት ችግሮች

መካከል ተፈጥሯዊ የሆኑት ተጠቃሽ ናቸው።

አካባቢው ቀደም ብሎ በቁጥቋጦ ተሸፍኖ

የነበረ ሲሆን የአካባቢው ቀደምት ‹ነዋሪዎች›

የነበሩትን ጅብ፣ ዘንዶ፣ ጊንጥ፣ እና እባብን

ለማባረር ፈታኝ መሆኑ ይታወሳል።

ነገር ግን፣ ቁጥቋጦዎቹ እየተመነጠሩ፣

አካባቢውን የተቆጣጠሩት የእሳት ጎመራ

ውጤት ድንጋዮች ተለቅመው እየተቆሩ

ለግንባታ፣ ለሽያጭና ለቋሚ አትክልትና

ፍራፍሬ ተክሎች ምርት አካባቢው ምቹ

ወደመሆን እየመጣ ነው - ባላሰለሰ የሥራ

ጥረትና ትጋት። ይኼንንም አስመልክቶ

አቶ ደምመላሽ እንዲህ ሲሉ ይገልፃሉ፡

- ‹‹እንደሥራው አመቺነት ሳይሆን እንደ

መሬቱ አመቺነት እየተሰራ ነው።››

አትክልትና ፍራፍሬዎችና

ችግኝ ጣቢያ

ከጃካራንዳ ሳይት አቅራቢያ በኢትዮጵያ

ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የመልካሳ

ግብርና ምርምር ማዕከል ይገኛል። የማዕከሉ

ተመራማሪዎች በሙያ ነክ ጉዳዩች ዙሪያ

የጃካራንዳ አጋሮች ናቸው። ለዚህም ነው

የተሻለ ምርት ሊሰጡ የሚችሉ የቋሚ

አትክልትና ፍራፍሬ ዝርያዎችን ማዕከሉ

ለጃካራንዳ ሰጥቶ በማዳቀል የተወሰኑ

ፍራፍሬዎች በጥሩ ሁኔታ አፍርተው ማየት

የተቻለው።

ቀደም ሲል በ2500 ካሬ ሜትር መሬት

ላይ 250 እግር ማንጎዎች ተተክለው ነበር።

በአሁን ወቅት እነዚህ በግንዶቻቸው ላይ

በርካታ ፍሬዎችን አፍርተዋል። እንዲሁም

ተጨማሪ 750 እግር ያህል ማንጎዎች በቅርቡ

የተተከሉ ሲሆን፣ በአጠቃላይ የሚተከሉት

ማንጎዎች ለአምስት ዓመታት ያህል

በጥራትና በብቃት ተመርተው እንደሚለቀሙ

የአቶ ደምመላሽ ሀሳብ ነው። አቦካዶና ሙዝን

የመሳሰሉ የፍራፍሬ ተክሎችም የጃካራንዳ

ሌሎች የልማቱ ፍሬዎች ናቸው።

በሌላ በኩል ደግሞ፣ 150 ሜትር ርዝመትና

መጠነኛ የጎን ስፋት ባላት አነስተኛ ችግኝ

ጣቢያ (Nursery) ውስጥ ፓፓዬ 200 ሺህ፣

አቦካዶ አንድ ሺህና ማንጎ 400 እግር

ያህል ችግኞች በመፍላት ላይ ይገኛሉ።

የችግኝ ጣቢያው ዋና ዓላማም የከብቶች

ፍግና ተረፈ ምርቶችን (Waste product)

በተፈጥሮ ማዳበሪያነት በመጠቀም ለችግኞቹ

አመቺ ሁኔታን በመፍጠር በቅድሚያ

ለድርጅቱ ልማት፣ ሲተርፍ ደግሞ ለሌሎች

አልሚዎችና ገበሬዎች ችግኞችን መሸጥ

መሆኑን ኃላፊው ይገልፃሉ።

ከብቶች፣ ፍየሎችና ዛፎች

አክስዩን ማሕበሩ ከዚህ ቀደም

እንደሚያደርገው ሁሉ የሚደልቡ ከብቶችን

ከቦረናና ሞያሌ ገዝቶ በማምጣት ሰንጋዎቹ

ተገቢው ክብደት ላይ ሲደርሱ ከነቁማቸው

ወደ ውጭ ሀገራት (ግብፅና አረብ ሀገራት)

ለሽያጭ ይቀርባሉ። በጥር ወር 2003

ዓ.ም ላይ ይኼንን አስመልክቶ አውራምባ

ታይምስ በሰራው ዘገባ ላይ ሰንጋዎቹ ወደ

ማደለቢያው ጣቢያው ሲገቡ ክብደታቸው

ከ270 ኪ.ግ እንደማይበልጥ፣ ለሶስት

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 184 ቅዳሜ ጳጉሜ 5/ 2003

መልካም ዓዲስ ዓመት

እንደ ስሙ በማበብ ላይ ያለው

ጃካራንዳ

ወራት በየቀኑ አስር ሊትር ውሃ እየተቀለቡ

ለሽያጭ ብቁ እንደሚሆኑና ክብደታቸው

እስከ 400 ኪ.ግ እንደሚመዝን፣ እንዲሁም

እነዚህን ለውጭ ገቢያ ብቁ ለማድረግ ሶስት

ወራት እንደሚፈጅ አስፍሯል። በዕለቱ

ያገኘናት የሥራ ተቆጣጣሪም ደልበው

ወደ ውጪ ሃገራት የሚሸጡት ሰንጋዎች

ዋጋቸው ከ6500-8000 ብር ድረስ መሆኑን

ነግራናለች። በመስክ ጉብኝቱ ወቅት በቁጥር

430 ያህል ሰንጋዎችና 213 ያህል ፍየሎች

ነበሩ። የበረቶቹ ቁጥርም ከአራት ወደ ስድስት

ከፍ ብሏል።

በተጨማሪም፣ ድርጅቱ ከአዳማ ወረዳ

ግብርና ፅ/ቤት ጋር በመመካከር የአካባቢውን

የአግሮ-ኢኮሎጂካል ሥነ-ምህዳር ለመጠበቅና

የሙቀቱን መጠን ለመቀነስ በማሰብ

2800 ያህል የጃካራንዳና የድሬዳዋ ዛፎችን

አሰበጣጥሮ በመትከል እየተንከባከቡ

እንደሚገኙ አቶ ደምመላሽ ያስረዳሉ።

ቀጣይ ዕቅዶችና ትግበራዎች

አምስት ሺህ ኪውቢክ ሊትር ውሃ የመያዝ

አቅም ካለው የውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳ

በስተቀኝ በኩል አምስት ሄክታር ቦታ ላይ

መሬቱን አመቺ በማድረግ የዶሮ እርባታ

በቀጣይ ወራት ለመጀመር መታቀዱን

የአክስዮን ማሕበሩ የቴክኒክ ክፍል ኃላፊ

የሆነው ወጣት ይስሃቅ ገ/እግዚያብሔር

ገልፀዋል። እንዲሁም ማሕበሩ አሁን ከያዘው

38 ሔክታር መሬት ውጪ ተጨማሪ 15

ሔክታር መሬትን ለመጨመር ተገቢውን

ነገር በማድረግ ከሚመለከተው የመንግስት

አካልና የሕብረተሰብ ክፍል ጋር ተነጋግሮ

የግል ይዞታው አድርጓል፡- በመሬቱ ላይ

የተተከሉ አትክልትና ፍራፍሬ እና የተዘሩ

ሰብሎች እስኪነሱ ከመጠበቅ ውጪ። የከብት

ሥጋ እርድና ማቀነባበሪያ ሥራ ግንባታም

የቀጣይ ዕቅዶች አንዱ አካል ነው።

በግማሽ ቀን የነበረንን የመስክ ጉብኝት

አጠናቅቀን በአካባቢው የነበረውን ሁኔታ

በእርጋታ ስንመለከት ጃካራንዳ በእርግጥም

በለውጥ ጎዳና ላይ መሆኑን በቀላሉ መገንዘብ

ችለናል። የአክሲዮን ማሕበሩ የቦርድ

ሊቀመንበርና ዋና ሥራ አስኪያጅ በሆኑት

አቶ ደምመላሽ ላይ የተመለከትነው ጠንካራ

የሥራ ፍላጎትና፣ ተነሳሽነትና የለውጥ ራዕይ

ትልቅ ስሜትን የሚፈጥር ነበር። በመጨረሻም

አቶ ደምመላሽ በአጋጣሚ ፈገግ የሚያደርግ

ንግግርን ተናገሩ። የዚህ ፅሁፍ አቅራቢ

የግብርና ባለሙያ እንደነበረ ሰሙና ትንሽ

ኮስተርና ሳቅ በማለት፣‹‹ በጋዜጠኝነት ሙያ

ወሬ እየፈለክ ወረቀት ከምትቀዳድ ይልቅ

በሙያህ ገበሬ ሆነህ ብትሰራ ይሻልሃል፣

የሚያዋጣው እሱ ነው።›› ሲሉ ተናገሩ።

ቀደም ሲል በ2500 ካሬ ሜትር

መሬት ላይ 250 እግር ማንጎዎች

ተተክለው ነበር። በአሁን ወቅት

እነዚህ በግንዶቻቸው ላይ በርካታ

ፍሬዎችን አፍርተዋል። እንዲሁም

ተጨማሪ 750 እግር ያህል

ማንጎዎች በቅርቡ የተተከሉ ሲሆን፣

በአጠቃላይ የሚተከሉት ማንጎዎች

ለአምስት ዓመታት ያህል በጥራትና

በብቃት ተመርተው እንደሚለቀሙ

የአቶ ደምመላሽ ሀሳብ ነው።

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 184 ቅዳሜ ጳጉሜ 5/ 2003

መልካም ዓዲስ ዓመት

13

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

14

በዓለም አቀፍ ሕግ በውጭ ሀገራት ለሚገኙ ዜጎች ሚኒስቴር መ/ቤቱ

የሚያደርገው ከለላ ምንድን ነው?

ወደ ዓለም አቀፍ ሕግ ከመሄዳችን በፊት የውጭ

ጉዳይ ሚኒስቴር ካሉት የውጭ ተልዕኮዎች መካከል

አንዱና ዋንኛው በውጭ ያሉ ዜጎችን መጠበቅ ነው።

በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያንን መጠበቅ ሲባል ብዙ

ጉዳዮች አብረው ይነሳሉ። አንደኛ እዛ ያሉ ዜጎች

የሚፈልጓቸውን ሕጋዊ ሰነዶች ማዘጋጀትና ችግር

ሲገጥማቸው ማገዝ ነው።

ወደ ዓለም አቀፍ ሕጉ ስንመጣ፤ እያንዳንዱ ሕግ

ከዓለም አቀፍ ሕግጋት እና ድንጋጌዎች ጋር ተጣጥሞ

ነው መስራት ያለበት። ስለዚህ በዓለም አቀፍ ደረጃ

ለሚንቀሳቀሱ ሰዎች የሚሰጡ ከለላዎች አሉ።

ለምሳሌ ለስደተኞች የሚሰጥ መብት አለ። የተባበሩት

መንግስታት ድርጅት ስለስደተኞች ያፀደቀው ድንጋጌ

አለ። የእኛ ሕግጋትም ከእዛ ጋር የሚጣጣሙ ናቸው።

ስለዚህ ዞሮ ዞሮ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ተልዕኮዎች

ውስጥ አንዱ በውጭ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከለላ

መስጠት ነው።

ተግባራዊነቱስ ምን ያክል ነው? ምክንያቱም ‹‹ችግር በገጠመን ጊዜ

የሚሰማን የለም›› የሚሉ ቅሬታዎች አረብ ሀገራት ከሚገኙ ዜጎች

ዘንድ በስፋት ይደመጣልና።

እንግዲህ በተቻለ መጠን በውጭ በርካታ ኤምባሲዎችና

ቆንፅላ ጽ/ቤቶች አሉ፡፡ አንዱም የችግሩ ምንጭ

የሚመስለኝ [ከለላ ላለማግኘታቸው] ኤምባሲዎቻችን

በሌሉባቸው ሀገራት ያሉ ዜጎቻችን ጉዳይ ነው።

ይሄ መዋቅራዊ ችግር ነው። አቅም ስንገነባ

ሊቀረፍ የሚችል ነው። ሁለተኛው የችግሩ ምንጭ

ዜጎች ራሳቸው መከተል የሚገባቸውን አካሄዶች

ስለማይከተሉ ነው። ለምሳሌ ኤምባሲዎች ባሉባቸው

ሀገራት ያሉት ኤምባሲ ሄደው አይመዘገቡም።

አድራሻቸውን አለማሳወቅና ችግር ሲከሰት ብቻ ወደ

ኤምባሲ የመሄድ ነገር አለ።

ዜጎችን እየወቀስኩ አይደለም፤ እነሱ ጋር የሚስተዋለው

ችግር የሚመነጨው ምናልባት ከግንዛቤ እጥረት

ይሆናል፤ አሊያም ኤምባሲ ሄዶ የመመዝገብን ጥቅም

አሳንሶ ከማየት የመነጨ ይመስለኛል።

ሶስተኛው አንተም እንዳልከው … እንግዲህ

ኤምባሲዎች ውስጥ የሚሰሩት ሰዎች ናቸውና

ከእነሱም ስህተት አይጠፋም። ከኤምባሲው ፖሊሲ

በተቃራኒ እዛ የሚሠሩ ግለሰቦች ለዜጎች ተገቢውን

ምላሽ ላይሰጡ ይችላሉ።

በጋዳፊ ቤተሰቦች አስከፊ ጥቃት የደረሰባትን የሸዋዬ ጉዳይ መንግስት

እንዴት አየው?

ይሄ በጣም አሰቃቂ ነው። ማንም መንግስት

በዜጋው ላይ እንዲህ ዓይነት ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት

አንዲፈፀም አይፈልግም። መረጃው እንደደረሰንም

ፈጥነን የልጅቱን ቤተሰቦች አነጋግረናል። ስለማንነቷ

እና ስለአካሄዷ መረጃዎችን ተቀብለናል። ከዛም

በዚህ ጉዳይ ላይ ተባብረን ልንሰራ የምንችላቸውን

ወገኖች አነጋግረናል። አዲስ አበባ በሚገኘው የሊቢያ

ኤምባሲ ካሉት አምባሳደር ጋርም ተነጋግረናል።

አሁን የደረስንበት ውጤት ልጅቱ የተሻለ ሕክምና

የምታገኝበት ሁኔታ መመቻቸት እንዳለበት ነው።

በዚህ ረገድ የተያዙ አማራጮች አሉ፤ አንደኛው፣

የማልታ መንግስት የሕክምና ወጪዋን ችሎ

እንደሚያሳክማት እየገለፀ ነው። ሁለተኛው፣

እንግሊዝና አሜሪካ ለማሳከም ጥያቄ አቅርበዋል።

የትኛውን አማራጭ እንደምትጠቀም ልጅቷ ነች

የምትወስነው። ሌላው የጉዞ ሰነድ በእጇ ስለሌለ

የሚያስፈልጓት ሰነዶች እየተዘጋጁላት ነው።

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ለሽግግር መንግስቱ ኢትዮጵያ ዕውቅና እንደመስጠቷ መጠን የጋዳፊን

ቤተሰቦች ለመክሰስ መንግስት አስቧል?

እንዳልከው ለሽግግር ካውንስሉ ዕውቅና ከሰጡ

የአፍሪካ አገሮች አንዷ ኢትዮጵያ ነች። ጦርነቱ ገና

አልተጠናቀቀም፣ የተረጋጋ ሁኔታም አልተፈጠረም።

እንግዲህ ሁሉም ነገር ሲረጋጋ ነው ይሄን ጉዳይ

ማንሳት የሚቻለው። ጉዳዩ በጣም ትኩረት የሚሰጠው

ነው። ልጅቷ/ቤተሰቦቿ ካሳ የጠየቁበት ሁኔታ አለ ግን

በመንግስት ደረጃ ይሄን ለማድረግ መረጋጋት የግድ

ነው።

እዚህ ካለው የሊቢያ ኤምባሲ ጋር ‹‹ተነጋግረናል›› ብላችኋል …

እነሱ ጉዳዩን እንዴት ነው ያዩት?

በጣም ነው ያዘኑት። ሰውየውና ቤተሰቦቹ [ጋዳፊ]

እንኳንና በሌላ ሀገር ዜጋ ቀርቶ በራሳቸው ዜጎች

ላይም ከእዚህ የበለጠ ግፍ የሚፈፅሙ መሆናቸውን

በመግለፅ አፅናንተውናል።

በሌሎች አረብ ሀገራትም ያሉ ኢትዮጵያውያን ተመሳሳይ ወይም

ከዚህ የባሰ ጥቃት ይፈፀምባቸዋል፤ ለዚህ ምክንያቱ ምንድን ነው?

በተደጋጋሚ የምንናገረው ነገር አለ። አንደኛ፣

ከአካሄዳቸው ጀምሮ ሊታዩ የሚገቡ ጉዳዮች አሉ።

በሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካኝነት

ዋስትና ተይዞላቸው የሥራው ሁኔታ ታውቆ፣

ሰብዓዊነት በተከተለና ዓለም አቀፍ ሕግጋትን

በተከተለ ሁኔታ ብዙዎች ሲሄዱ አይስተዋልም።

ለዚህ ነው እንግዲህ በሕገ-ወጥ ደላላ አማካኝነት

ያልሆነ ባዶ ተስፋ ተሞልተው የሚሄዱትና ትልቅ

ችግር የሚያጋጥማቸው። አሰሪዎቹም በሕገ-ወጥ

መንገድ የሚሄዱት ምንም ዋስትና እንደሌላቸው

ስለሚያውቁ እጃቸው ለገባው ኢትዮጵያዊ ደህንነት

አይጨነቁም።

አረብ ሀገራት ያሉ ኢትዮጵያውያን ችግር ደርሶባቸው ለኤምባሲ

በሚያመለክቱበት ጊዜ ‹‹ዞር በል፤ እኛ የመጣነው ኢንቨስተር

ለመሳብ እንጂ ለአሽከር አይደለም›› የሚል መልስ እንደሚሰጣቸው

ይገልፃሉ። በሌላ በኩል ደግሞ የኤምባሲዎች ዋና ዓላማ የኢህአዴግ

ደጋፊ ዳያስፖራዎችን ማሰባሰብ መሆኑን የሚገልጹ አሉ … ዋና

ተልዕኳቸው ምንድን ነው?

በነገራችን ላይ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተሰጠው

ተልዕኮ በውጭ የሚተገበረው በኤምባሲዎች

አማካኝነት ነው። ለመ/ቤቱ ከተሰጠው ተልዕኮ

አንዱ የኢትዮጵያን ልማት፣ ዴሞክራሲ እና ሰላም

ሊደግፉ የሚችሉ ሥራዎችን በውጭ መስራት ነው።

እነዚህም ኢንቨስትመንትን መሳብ፣ የውጭ ገበያ

ማፈላለግና ጎብኚዎችን መሳብ ናቸው፡፡ ነገር ግን

የዜጎችን መብቶች ማስጠበቅም ከዚሁ እኩል ትኩረት

ተሰጥቶት የሚሰራ ነው።

ስለዚህ ‹‹እኔ እዚህ ያለሁት ኢንቨስተር ለመሳብ ብቻ

ነው›› የሚል ዲፕሎማት ካለ ያልገባው ነገር አለ ማለት

ነው። ተልዕኮውን በደንብ አልተረዳም ማለት ነው።

በእርግጥ የሥራችን ዋንኛው ትኩረት ኢኮኖሚያዊ

ዲፕሎማሲ ነው። ሆኖም ኢኮኖሚያዊ ዲፕሎማሲን

በደንብ ለማሳካት ውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን

መብቶች ማስከበር የግድ ነው። ለሚሺነሪዎቻችንም

በየጊዜው ስለተልዕኳቸው ሥልጠናዎች የሚሰጠው

ለዚህ ነው።

እዚህ ጋር አንድ ጥያቄ ላንሳ … አሁን ባለው ሁኔታ በውጭ የሚገኙ

ኢትዮጵያውያን መብቶች አጥጋቢ በሆነ ደረጃ ተከብረዋል?

ቅድም ባነሳናቸው ምክንያቶች ክፍተቶች የግድ

ይኖራሉ። ወደ ኤምባሲ ሄዶ መመዝገብ አነስተኛ

ግምት ስለተሰጠው ዜጎች ሄደው የመመዝገባቸው

ሁኔታ በጣም አነስተኛ ነው። እንዲሁም በአቅም

ውስንነት የተነሳ ኤምባሲ ባልከፈትንባቸው ሀገራት

ያሉ ዜጎችን መብቶች ማስጠበቅ አዳጋች ነው።

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 184 ቅዳሜ ጳጉሜ 5/ 2003

መልካም ዓዲስ ዓመት

‹‹ከተፈፀመ ቆይቷል ግን ሲ.ኤን.ኤን እስኪዘግበው ድረስ

እኛም ቤተሰቦቿም ምንም መረጃ አልነበረንም››

ሸዋዬ ሞላ በተባለች ኢትዮጵያዊት ላይ በጋዳፊ ቤተሰቦች

የተፈጸመው ኢ-ሰብዐዊ ጥቃት አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ ሱራፍኤል ግርማ

ለወጣቷ እየተደረገ ስላለው ድጋፍና በአጠቃላይ በአረብ አገራት

ስላሉ ኢትዮጵያዊያን ሁኔታ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ

የሆኑትን አምባሳደር ዲና ሙፍቲን አነጋግሯል፡፡

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

በመሠረቱ ከሆነ አንድ ሥራ መቶ በመቶ ይከናወናል

ብሎ መጠበቅ አዳጋች ነው። የዳያስፖራ ፖሊሲ

ተዘጋጅቶ በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር

ቤት መጥተው በልማት እንዲሳተፉ አንዳንድ ጥቅማ

ጥቅሞችን በመስጠት ሁሉ እየጣርን ነው።

‹‹ዳያስፖራ›› ሲባል የትኛው ዳያስፖራ ነው?

በሁሉም ሀገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች

አንድ ዓይነት ሁኔታ ላይ አይደለም ያሉት። ለምሳሌ

ሰሜን አሜሪካና አውሮፓ ያሉ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ

ያሉበትን ሀገር ዜግነት ይወስዳሉ። ስለዚህ እነዚህ

ኢትዮጵያውያን ሳይሆኑ ‹‹ትውልደ ኢትዮጵያውያን››

ነው የሚባሉት። ለእነሱ የሚሰጠው ድጋፍ እንደ

ዜጋ አይደለም። ሌላው በአፍሪካ እና በኢሲያ ያሉ

ዳያስፖራዎች ያሉበትን ሀገር ዜግነት ስለማያገኙ

ኢትዮጵያውያን ናቸው። የሚያገኙት ጥቅምም

እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነው። ስለዚህ ፖሊሲው

ሁለቱንም የሚመለከት ነው።

የቆንፅላ ጽቤቶች ሥራ ምንድን ነው?

የቆንፅላ ጽ/ቤቶች ከኤምባሲ ዝቅ ያሉ ሲሆን፣ ኤምባሲ

በሌለበት ሀገር ውስጥ ሥራዎችን የሚያከናውኑ

አካላት ናቸው፤ በተለይም ሕጋዊ ሰነዶችን ማዘጋጀትና

ማረጋገጫ መስጠት። በነገራችን ላይ የኤምባሲና

ቆንፅላ ጽ/ቤት አከፋፈት እንደየሀገራት ሁኔታ

ይለያያል። የበለፀጉት ሀገራት በመላው ዓለም በሚገኙ

ሀገራት ኤምባሲዎች ሊኖራቸው ይችላል። በእኛ ደረጃ

ግን ‹‹ወሳኝ›› ተብለው በሚታመኑ ሀገራት ብቻ ነው

ኤምባሲ የሚያስፈልገው። የመን አሁን ኤምባሲ ነው

ያለን። ሳዑዲ አረቢያ ጅዳ ቆንፅላ ጽ/ቤት ነው ያለው።

ዱባይና ቤይሩት ቆንፅላ ነው ያለው።

የሸዋዬ ጉዳይ የማንቂያ ደወል ነውና ከዚህ በኋላ ወደ አረብ ሀገራት

የሚሄዱ ኢትዮጵያውያን ምን ከለላ ይደረግላቸዋል?

‹‹ማንቂያ ደወል›› ያልከው በጣም ትክክለኛ ቃል

ነው። ይሄ ነገር ከተፈፀመ ቆይቷል ግን ሲ.ኤን.ኤን

እስኪዘግበው ድረስ እኛም ቤተሰቦቿም ምንም መረጃ

አልነበረንም። ሌሎች ከዚህ መማር ያለባቸው ነገር

በየሄዱባቸው ሀገራት ሄደው መመዝገብ ያለባቸው

መሆኑን ነው። አካሄደቸውን ሕጋዊ ማድረግ

አለባቸው። የጉዳዩ ትልቁ ባለቤት ተጓዦች ናቸው።

ስለዚህ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው።

ጥሩ . . . ወደ ውጭ የሚሄዱት የጠቀሷቸውን ቅድመ-ሁኔታዎች

ማሟላት አለባቸው። መንግሥትስ ከዚህ በኋላ ለዜጎቹ እንዴት ነው

ከለላ የሚያደርገው?

በየኤምባሲው ያሉ ሰዎች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ

መወጣት አለባቸው። ውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን

ለሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች ትክክለኛና ተገቢው ምላሽ

ሊሰጣቸው ይገባል።

በተለያዩ እስር ቤቶች ውስጥም የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን አሉ፤

ለምን አስፈትታችኋቸው ወደ ሀገር ቤት እንዲመጡ አታደርጉም?

የተመዘገቡ ስላልሆኑ የመረጃ ዕጥረት አለ።

የሚደርሱን መረጃዎች የግምት ናቸው። ‹‹የት

እስር ቤት? ብዛታቸውስ?›› የሚለውን ነገር በደንብ

የሚመልስ አይደለም። የሚመጡ ሰዎችም የሚሰጡን

መረጃ አጥጋቢ አይደለም።

የአረቡ ዓለም አብዮት በተቀሰቀሰበት ወቅት ኢትዮጵያውያንን ወደ

ሀገር ቤት የመመለስ ሥራ በመንግስትና በዓለም አቀፍ ተቋማት በኩል

ይከናወን ነበር። በአንፃሩ ደግሞ ወደዛው የሚሄዱ ሰዎች ነበሩ።

ለምንድን ነው ዝም የሚባለው?

ትክክል። ከየመን ሸሽተው የሚመጡትን ለመቀበል

አየር ማረፊያ ቆመን ወደ የመን የሚሄዱ ሰዎችን

ተመልክተናል። ‹‹ይኸው እነዚህ የሚመለሱት እዛ

ችግር ሆኖ ነው፤ ለምን ትሄዳላችሁ?›› ስንላቸው

ሊሰሙን ፈቃደኞች አልነበሩም። በዚህ ላይ ማንም

ሰው ወደ ፈለገበት ቦታ የመሄድ ሕገ-መንግስታዊ

ነፃነት አለው። ያንን ጥሰን ማስቆም አንችልም።

ግን ከሄዱስ በኋላ ከለላ ማድረግ አይቻልም?

ከሄዱ በኋላ ሌላ ሀገር ነው ያሉት። በሄዱበት ሀገር

ሕግ መሰረት ነው የሚተዳደሩት። መንግስት ጣልቃ

መግባት የሚችለው ችግር ሲደርስ ነው። ችግሮች

ሲከሰቱ ከዛ ሀገር መንግስት ጋር በመነጋገር ለጉዳዩ

ዕልባት ይሻል እንጂ ለእያንዳንዱ እንቅስቃሴ ከለላ

መስጠት አይችልም።

በርካታ ኢትዮጵያውያን ከሚገኙባት ኳታር ጋር ዲፕሎማሲያዊ

ግንኙነት ተቋርጧል። እዛ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ጉዳይ እንዴት ነው

የምትከታተሉት?

እስካሁን ድረስ ያጋጠመ ችግር የለም። ግን እንደ

ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት [IOM] እና በተባበሩት

መንግስታት ድርጅት [UNHCR] ባሉ ዓለም አቀፍ

ተቋማት በኩል መብቶቻቸውን ማስጠበቅ ይቻላል።

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 184 ቅዳሜ ጳጉሜ 5/ 2003

መልካም ዓዲስ ዓመት

15

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

16

ደርግ ወደ ሥልጣን ሲመጣ እርስዎ የትና በምን

ኃላፊነት ላይ ነበሩ?

ደርግ ወደ ስልጣን ሲመጣ እኔ አሜሪካን

ሀገር ትምህርት ላይ ነበርኩ። ከዚያ

እንማንኛውም በዘመኑ እንደነበሩ ወጣት

ተማሪዎች ለውጡን ደግፌ ተሰለፍኩ።

በነገራችን ላይ ከዚያ በፊት ከውትድርናው

ዓለም ወጥቼ ነበር። የለውጡ እንቅስቃሴ

ሲጀመር ነው እንደገና ወደ ወታደርነት

የተመለስኩት። እናም ለውጡን የበለጠ

ለማንቀሳቀስ ከሌሎች መኮንኖች ጋር

ተባብሬ ተሰለፍኩ፡፡ በደርግ ውስጥ

በሰራሁባቸው ዓመታት ውስጥ የሚቻለንን

ያህል በኢትዮጵያ እውነተኛና መሠረታዊ

ለውጥ ለማምጣት፣ ከድህነት ወደ

ዕድገት፣ ከጦርነት ወደ ሰላም መሸጋገር

የምንችልበትን መንገድ ለመቀየስ

ሞክረናል።

ወደ አሜሪካ ለትምህርት ከመውጣትዎ በፊት የት

ነበር የሚሰሩት?

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ትምህርት ላይ

ነበርኩ። የመጀመሪያ ዲግሪዬን ያገኘሁትም

እዛው ነው። ከዛ በኋላ ወደ አሜሪካ አገር

ወጥቼ ኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ትምህርት

ጀመርኩ። ኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ስማር

የሻለቅነት ማዕረግ ማግኘት የምችልበት

ወቅት ነበር። በዚህ የተነሳ ወደ ሀገር

ቤት ስመለስ የሻለቅነት ማዕረግ ሰጡኝ።

ቢሆንም በሻለቅነት ማዕረግ ብዙ ጊዜ

አልሰራሁበትም።

በሐረር ጦር አካዳሚ 2ኛ ኮርስ ሰልጣኝ ነበሩ።

2ኛ ኮርስ መኮንኖች ደግሞ እስከ ጀኔራል ማዕረግ

ደርሰዋል። እርስዎ ታዲያ ለምን እስከ ጄኔራል ማዕረግ

ማግኘት አልቻሉም?

ወደ ወታደርነት ሥራ አልተመለስኩም።

አብዮቱን እንደተቀላቀልኩ በሲቪልነት

ነው ያገለገልኩት።

ከአሜሪካ ወደ አገርዎ የተመለሱት ደርግ ሥልጣን

ከያዘ ከስንት ጊዜ በኋላ ነው?

ንጉሱ መስከረም 2 ቀን ከሥልጣን ወረዱ

ሲባል፣ እኔና ኒውዮርክ አካባቢ የምንገኝ

ሰዎች ወዲያው ነው ጓዛችንን ጠቅልለን

ወደ ሀገር ቤት የገባነው፡፡ በዚያው

በመስከረም ወር ማለት ነው።

መልካም። ለህትመት ባበቁት አንድ መፅሐፍ፣

እርስዎ የሐረር ጦር አካዳሚ፣ ኮ/ል መንግስቱ

ደግሞ የሆለታ ጦር አካዳሚ ሰልጣኝ እንደነበራችሁ፣

ሁለታችሁም በማዕረግ ደረጃ አቻ እንደሆናችሁ

ጠቅሰው፣ ሀገር ቤት እንደገቡ ኮ/ል መንግስቱን

ለማነጋገር ወደ ቤተመንግስት በሄዱ ጊዜ ‹‹አንተ ብዬ

ነው የማነጋግረው›› ብለው ፣ ‹‹ወዲያው ሳላስበው

አንቱ ማለት ጀመርኩ›› ሲሉ የተረኩት ክፍል አለ።

እስቲ ይህ ሊሆን የቻለበትን ሁኔታ መለስ ብለው

ያጫውቱኝ?

ተፈሪ መኮንን ትምህርቴን ከጨረስኩ

በኋላ ወደ ሐረር ጦር አካዳሚ የገባሁት

በግል ፍላጎቴ አይደለም። ተመልምለን ነው

የግድ ወደ ጦር ት/ቤት የተላክነው። እና

የ2ኛ ኮርስ ሰልጣኝ ነኝ። ሐረር ሚሊቴር

አካዳሚ፣ የታወቀ ሚሊተሪ አካዳሚ ነው።

ህንዶች ያቋቋሙት ነው። እዚያ 3 ዓመት

ሰልጥኛለሁ። በእነዚያ ሶስት ዓመታት

በየቀኑ የምንማረው፣ የምንዘጋጀው እና

አዕምሮአችንን የምናሰለጥነው ከራስ

በላይ ሀገርን (ኢትዮጵያን) ማስቀደምን

ነው። ከራስ በፊት ሀገር፣ ከራስ በፊት

ሀገር፣ ከራስ በፊት ሀገር በሚል መርህ

ተኮትኩተን ነው የሰለጠንነው።

ከስልጠና በኋላ አየር ወለድ ገባሁ። የኛ

ኮርስ ሁለተኛው ቡድን ነበር ወደ አየር

ወለድ ሲገባ። ከዚያ ኤርትራ ሄድኩ።

በኤርትራ ለሰራዊቱ የተለያየ ስልጠና

በመስጠት ለብዙ ዓመታት አገለገልኩ።

ከዚያ ደግሞ በአሜሪካን ሀገር (አድቫንስ)

ከፍተኛ የእግረኛ ወታራዊ ትምህርት

ሥልጠና ለ11 ወራት ተማርኩ። እንደገና

ደግሞ ወደ አገር ቤት ተመልሼ ወደ

ምድብ ሥራዬ ኤርትራ አቆናሁ። ውጊያ

ላይ ቆሰልኩ። በመቁሰሌ ምክንያት

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ከወታደር ቤት ተሰናበትኩና አዲስ አበባ

ዩኒቨርስቲ ገባሁ።

በእነዚህ ወቅቶች ሁሉ እኔ መንግስቱ

ኃ/ማርያምን አላውቀውም። እሱ ግን

ኤርትራ መጥቶ በነበረበት ጊዜ አይቶኛል፤

ያስታውሰኛል። እሱ ከሆለታ ጦር ት/ቤት

ነው የወጣው። የእኔ ሲኒየር ነው። ከአሜሪካ

ለውጡን ደግፈን ወደ ሀገር ቤት ስንመለስ

መንግስቱ የደርግ ምክትል ሊቀመንበር

ነበር። በወቅቱ ማንኛውም መኮንን እንደ

ጓድ “አንተ” ነበር የምንባባለው። እንደ

ጓደኛ ነበር የምንነጋገረው።

እና አሁን አንተ የጠየቅከኝ ፍርሀትና

“አንቱታ” የተፈጠረው በአንድ ጊዜ

ሳይሆን ቀስ በቀስ ነው። መጀመሪያ

“አንቱ” በሉ ተባልን። ማለት ጀመርን።

ከዚያ እጃችሁን ኪሳችሁ ውስጥ አትክተቱ

ተባልን፣ እጃችንን ከኪሳችን ማውጣት

ጀመርን። ከዚያ ቀረብ ብሎ ማነጋገር

ቀረ። በመጨረሻ የምንነጋገረው በ20

ሜትር ርቀት ሆነ። እንዲህ እንዲህ እያለ

ሰውየው የሚያስፈራ ድባብ ፈጠረ። ከዚያ

ትጥቅ ፈትተን እንድንገባ ተደረገ። ያ

ሁኔታ ፍርሃት አሳደረብን። ክብር ሳይሆን

ፍርሀት። እነዚህ ሁኔታዎች ተደምረው

ነው በመፅሐፉ ያልኩት የሆነው።

በነገራችን ላይ ይህንን ሁኔታ የፃፉት ከሀገር ከወጡና

ከደርግ ከተለዩ በኋላ ቢሆንም፣አተራረክ ግን ኮሎኔል

መንግስቱን ያደንቋቸው እንደነበር የሚያሳይ ነው

የሆነብኝ። መፅሐፍዎን ሳነብ እንደተረዳሁት፣ ኮ/ል

መንግስቱን ለማነጋገር ወደ ቤተ መንግስት ሲገቡ ተራ

ሰው ጠብቀው በአስተሳሰቡ ላቅ ያለ ሰው እንዳገኙ

አድርገው ነው የገለፁት። ይህ አገላለፅዎ አሁን

ከሚናገሩት ጋር አይጋጭም?

የፍርሃት ስሜት ከየትና እንዴት እንደመጣ

ነው ቀደም ብዬ የነገርኩህ። እንጂ መቼም

ጊዜ ቢሆን ብናገረው የማላፍርበት፣ ከደረግ

ጋር መስራት ከጀመርኩበት ጊዜ አንስቱ

ለተወሰነ ጊዜ ያህል ለኮ/ል መንግስቱ

ታላቅ አክብሮት ነበረኝ።

አብዮቱ ሲጀመር ያየሁበት የኢትዮጵያዊነት

ስሜት ከምጠብቀው በላይ ነው የሆነብኝ።

የመናገር ችሎታው፤ የማዳመጥ

ችሎታው፣ የመምራት ችሎታው በጣም

ነበር ያስደነቀኝ። ትዝ ይለኛል ያኔ እኔ

የዕድገት በህብረት ምክትል አዝማች

ነበርኩ። በእሱ ፊት ዘማች ተማሪዎችን

አሰልፈን ‹‹ቪቫ መንግስቱ›› እያልን

ስናልፍ፣ እኔ ነበርኩ የመጀመሪያው

‹‹ቪቫ መንግስቱ›› ባይ። ከተፈሪ ባንቲ እና

አጥናፉ አባተ እሱን ለይተን ነበር ‹‹ቪቫ››

ስንል የነበረው።

በዚያ ጊዜ የነበረውን ሁኔታ መለስ ብለህ

ከተመለከትከው በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ

ስንል ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ሳይሆን፣

ህብረተሰባዊ (የህብረተሰብ) ለውጥ ነው።

ፊውዳሊዝምን የማጥፋትና አዲሲቱን

ኢትዮጵያ የመገንባት ህልም ነበርን።

እና የመንግስቱ ኃ/ማርያም ከአናሳ

ብሔረሰብ የመምጣቱ ጉዳይ፣ ከበታች

መኮንንነት የመምጣቱ ጉዳይ፣ ባህርይው፣

ከጀርባውም ሆነ ከፊቱ ያለው ሌላ ሌላ

ነገር ተደማምሮ እንደለውጥ ተምሳሌት

ተወሰደ። በጠቅላላው እሱ የሚያሳው

የለውጥ ምልክት ነበር የኢትዮጵያን

ለውጥ ያሳያል በሚል ደገፍነው፡ ከዚህ

በተጨማሪ በጣም ጎበዝ አርበኛ ነበር።

ሲናገር፣ ሲያሳምን፣ ሲያዳምጥ በጣም

አደንቀው ነበር። በዚያን ጊዜ ያለ ምንም

ማመንታት እሱን ደግፌአለሁ። ለተወሰነ

ጊዜም አመራሩን ተቀብያለሁ።

በደርግ ውስጥ በየትኛው የኃላፊነት ሥልጣን ላይ ነው

የሰሩት?

በመጀመሪያ የዕድገት በህብረት ምክትል

አዝማች ሆኜ ነው የሰራሁት። ዋና

አዝማቹ ኪሮስ አለማየሁ ይባል ነበር።

በኢትዮጵያውያን ዘንድ በስፋት የታቅሁት

ያኔ ነው። ምንም እንኳን ዘመቻውን

መንግስት የኋላ ኋላ ለሌላ ነገር

ቢጠቀምበትም በኢትዮጵያ አዲስ ዕይታን፣

አዲስ ዕውቀትን የፈነጠቀ ነበር። ዓላማው

ጥሩ ነበር።

ከዚያ በኋላ የዕርዳታ ማስተባበሪያና

ማቋቋሚያ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር

ነው የሆንኩት። በወቅቱ በኢትዮጵያ

ከፍተኛ ድርቅ ችግር ነበር። ያ ድርቅ

ለደርግ ውድቀት እንደ አንድ ምክንያት

ነው።

የሆነ ሆኖ በረሃብ ለተጎዳው ኢትዮጵያዊ

የተቻለኝን ድጋፍ ለመስጠት ዕድል

ያገኘሁበትም ነው። ከዚያ በኋላ ውጭ

ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት ምክትል

ሚኒስትር ሆኜ ተሾምኩ። ኮ/ል ፈለቀ ወ/

ጊዎርጊስ ሚኒስትር፣ እኔ ምክትል ሆኜ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 184 ቅዳሜ ጳጉሜ 5/ 2003

መልካም ዓዲስ ዓመት

“የ1981 መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ

ከሻዕቢያና ከወያኔ ጋር ተስማምተን ነበር”

ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ

ግንቦት 8 ቀን 1981 ዓ.ም በኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማርያም ላይ የተቃጣው መንፈንቅለ መንግስት የከሸፈበት ዕለት መሆኑ በኢትዮጵያውያን ዘንድ የሚረሳ አይደለም። የዛሬ 22 ዓመት የተካሄደው ያ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ሀገሪቷ በረዥም

ዓመታት ያፈራቻቸውን ምርጥ የጦር ባለሟሎች ያጣችበት ነውና። ኮሎኔል መንግስቱ ወደ ምሥራቅ ጀርመን ለጉብኝት መጓዛቸውን ተከትሎ የተሞከረውና የከሸፈው የግንቦት 8ቱ መፈንቅለ መንግስት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ ሰፊ ዝግጅት

የተደረገበት፣ በዚያ ወቅት የደርግን ሥርዓት ለመጣል የትጥቅ ትግል ሲያካሂዱ ከነበሩት ሻዕቢያና ህወሀት ጋር ሥምምነት የተደረሰበት ነበር ይላሉ፡- ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዎርጊስ። ሻለቃ ዳዊት፣ በሀገር ውስጥ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ያደረጉትን

ጄኔራል መኮንኖችንና የደርግ ጦር አዛዦችን፣ እንዲሁም የደርግን ሥርዓት ለመጣል ይፋለሙ የነበሩትን ሻዕቢያና ህወሀትን በማግባባት ወሳኝ ሚና መጫወታቸውን በተመለከተ በይፋ ቃለምልልስ ሰጥተዋል። ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዎርጊስ ሥርዓቱን

ከድተው የወጡ የመጀመሪያው የደርግ ከፍተኛ ባለሥልጣን መሆናቸው ይታወቃል። ከእሳቸው ቀጥሎ ደርግን ከድተው ከሀገር የወጡት ኮ/ል ጎሹ ወልዴ ናቸው። እነዚህ ሁለት ከፍተኛ የደርግ ሹማምንቶች የሐረር ጦር አካዳሚ ምሩቆችም ነበሩ።

ሁለቱም፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን የያዙት ከአሜሪካን ሀገር የል ዩኒቨርስቲ እና ኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ነው። ከድተው ከሀገር የወጡት እነዚህ ሁለት የሥርዓቱ ባለሥልጣናት አገዛዙን ለመጣል ውጭ ሀገር ሆነው ሲታገሉ፣ ሌሎቹ የደርግ ጄኔራሎች ደግሞ

በሀገር ውስጥ መፈንቅለ መንግሥት ለማካሄድ ተስማምተው የግንቦት 8ቱ ሙከራን መታቀዱን ሻለቃ ዳዊት ይተርኩልናል። ኮ/ል መንግስቱ ያንን የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ይሻገሩ እንጂ፣ ከዚያ በኋላ በሥልጣናቸው ላይ የቆዩት ለሁለት ዓመት

ከ5 ቀናት ብቻ ነበር። ይሁን እንጂ ሻለቃ ዳዊት፣ ከግንቦት 8ቱ በኋላም በኮሎኔሉ ላይ መፈንቅለ መንግስት ታቅዶ ነበር ሲሉም አስገራሚ ቃለምልልስ ሰጥተዋል። በአሁኑ ወቅት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ በመስራት ላይ የሚገኙት ሻለቃ

ዳዊት ወ/ጊዎርጊስ፣ ሰሞኑን ወደዋሽንግተን ዲሲ ለሥራ ብቅ ባሉበት ወቅት ለአንጋፋው ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና የሰጡት ቃለ-ምልልስ እስካሁን ያልተሰሙና ተደብቀው የቆዩ ታሪኮችን የያዘ ሆኖ አግኝተነዋል። ስለዚህም ለአንባቢዎቻችን ግንዛቤ ይረዳ

ዘንድ፣ የሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስን ቃለምልልስ እንደሚከተለው አቅርበነዋል።

ለ3 ዓመት አገለገልኩ።

ውጭ ጉዳይ ም/ሚኒስትር የሆንኩት

በመጥፎ ጊዜ ነበር። የሱማሌ ወረራ

ነበር በወቅቱ። ያኔ የኢትዮጵያ ድንበር

እንደተደፈረ፣ ህልውናዋ እንደተነካ

በየክፍለ ዓለማቱ እየተዘዋወሩ ለማሳማን

የደከምንበትና ከፍተኛ ትግል የገጠምንበት

ወቅት ነበር።

በዚያ ጊዜ ኢትዮጵያ ማርክስሲት ርዕዮትን

እየተከተለች እንደገና ደግሞ ወደ ምዕራቡ

አገር ሄዳ ዕርዳታና ድጋፍ ለመጠየቅ

የተገደደችበት ወቅት ነበር። በአንድ

በኩል በድርቅ ለተጎዳው ህዝባችን ዕርዳታ

ሰጡን፣ በሌላ በኩል ግሞ ሀገራችን

ስለተወረረች የፖለቲካ ድጋፍ ስጡን

ብሎ ዓለምን መጠየቅና የፈለግነውን ነገር

ማግኘት ቀላል ነገር አልነበረም። ያንን

ሁኔታ አስታርቆና ሚዛን ጠብቆ ተጠቃሚ

መሆን መቻል ፈታኝ ነበር፡፡

ከዚያ በኋላ ደግሞ የኤርትራ ዋና ተጠሪ

ሆኜ ተሾምኩ። ኤርትራን የማስተዳደር

ኃላፊነት የኔ ነበር። በመስክ ያለው ወታደራዊ

ጉዳይ የኔ ኃላፊነት አልነበረም። ህዝቡን

ማስተዳደርን፣ ፀጥታውን ማስጠበቅ፣

የኤርትራ ህዝብ በኢትዮጵያዊነቱ ፀንቶ

እንዲቆይ ማድረግ የእኔ ኃላፊነት ነበር።

ኤርትራ በአስተዳደሪነት 3 ዓመት

ሰርቻለሁ። በጣም ደስተኛ የሆንኩበትን

ፍሬያማ ሥራ አከናውኛለሁ። በወቅቱ

የኤርትራ ህዝብ ሁሉ የሚመሰክረው

ተግባር ተወጥቻለሁ።

እርስዎ በቀይ ኮከብ ዘመቻ ጊዜ የኤርትራ አስተዳዳሪ

ነበሩ?

አዎ! ከ74-76 ዓ.ም ማለት ነው። በዓሉ

ግርማ ኦሮማይን ሲፅፍ ማለት ነው።

አብረን ኤርትራ ነበርን።

ለህትመት ካበቋቸው መፅሐፎች የአንዱን ገቢ

‹‹ለኤርትራና ኢትዮጵያ ህዝቦች ወዳጅነት

ማህበር›› መስጠትዎን አንብቤአለሁ። ከዚህ በኋላ

የኤርትራና የኢትዮጵያ ህዝብ እንደገና አብሮ ይኖራል

የሚል ተስፋ አለዎት ማለት ነው? የመፅሐፍዎን

ሽያጭ የለገሱት ማህበር ዓላማስ ምንድን ነው? ምንስ

እየሰራ ነው?

ምን መሰለህ? አሁን ኤርትራን መገንጠል

የመጀመሪያው አማራጭ ከሆነ፣ ቀጥሎ

መምጣት ያለት አማራጭ የኢትዮጵያ እና

የኤርትራ ህዝብ አንድ መሆን ይገባዋል

የሚል መሆን አለበት። ህዝቡ በጠላትነት

መተያየት የለበትም። ሁለቱ ህዝቦች

ሰላማቸው፣ ኢኮኖሚያቸው፣ አኗኗራቸው

ወዘተ አንድ አይነት ነው። ሁሉም ነገር

የሚያገናኛቸው ናቸው። ኤርትራ ላይ

የመጣ ነገር ኢትዮጵያንም ይነካል።

ኢትዮጰያ ላይ የመጣ ነገር ሁሉ ኤርትራን

ይነካል።

ባለፉት 150 ዓመታት በኢትዮጵያ ወደ

90 ያህል ጦርነቶች ተደርገዋል። ከእነዚህ

ጦርነቶች ውስጥ 95 በመቶ ያህሉ

የመጣው በኤርትራ ባህር በኩል ነው።

አሁንም የእስልምና አክራሪነት ቢከሰት፣

የሶማሌ ጦርነት ቢመጣ፣ የኢኮኖሚ

ችግር ወዘተ ቢፈጠር፣ የሚመጣው

በኤርትራ በኩል ነው። ልክ እንደዚያው

ሁሉ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጠር

ችግር ሁሉ ኤርትራ ውስጥ ይሰማል።

ስለዚህ አብረን መኖር የሚገባን ህዝቦች

ነን። በሁሉም ነገር ተሳስረን ያለን እና

የምንኖር ነን። ይህንን ዕውነታ በፖለቲካ

ማሰር ባይቻልም፣ አብረን በሰላም መኖር

አለብን በሚል መርህ ነው ማህበሩን

የመሰረትነው።ማህበሩ በሁለቱ ሕዝቦች

መሀከል ያለውን የጋራ ትስስርና ታሪክ

የሚያጎላ፣ ህዝቡን የሚያነቃቃ ስለሆነ

ነው የመፅሀፌን ገቢ ያበረከትኩት።

ማህበሩን የመሠረታችሁት ኢትዮጵያውያንና

ኤርትራውያን በጋራ ሆናችሁ ነው?

አዎ! በመሀሉ ግን እኔ የማህበር ሥራ

መስራት አልቻልኩም። አሁን በአሜሪካ

ሳንሆዜ ያሉ ሌሎች ድርጅቶች ናቸው

ዓላማውን የሚያራምዱት።

እርስዎ ግን ኢትዮጵያና ኤርትራ አንድ ቀን

በኮንፌዴሬሽንም ሆነ በሌላ መልክ አብረው መኖር

ይችላሉ ብለው ይገምታሉ?

አዎ ይችላሉ። ግን በመጀመሪያ ደረጃ

መሠረቱ አሁን መጣል አለበት።

መልካም። እርስዎ የእርዳታ ማስተባበሪያ ኮሚሽን

ኮሚሽነር በነበሩበት ጊዜ ስለተከሰተው ረሃብና

ስለሆነው ነገር በጥቂቱ ሊነግሩኝ ይችላሉ?

እ.አ.አ ከ82-85 ዓ.ም ማለት ነው

እኔ በእርዳታ ኮሚሽን ኮሚሽነርንት

ያገለገልኩት። ያኔ ኢትዮጵያ ውስጥ

የተከሰተውን ከባድ የድርቅ ችግር

ለመታደግ ዓለም በሙሉ የተንቀሳቀሰበት

ዘመን ነው።

አሁን በሶማሌ፣ በኢትዮጵያና በኬንያ

የተፈጠረውን የድርቅ ችግር ከዚያ ዘመን

ጋር ይወዳደራል የሚሉ አሉ። ቢሆንም፣

ያኔ የተከሰተው የድርቅ ችግር ግን እጅግ

የከፋ ነበር። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት

ወዲህ መላውን ዓለም ያስተባበረ የድርቅ

ችግር ነበር የተከሰተው።

የአጋጣሚ ነገር ሆኖ፣ ያኔ የደርግ

መንግስት የፖለቲካ አሰላለፍ ከምስራቁ

ዓለም ጋር ነበር። ዕርዳታ ለመስጠት

የተዘጋጀው ደግሞ ምዕራቡ ዓለም ነው።

ይህንን ሁለቱን ጉዳይ ማስታረቅ ከባድ

ፈተና ነበር። ከዚህ ሌላ የደርግ መንግስት

10ኛውን የአብዮት በዓል አከብራለሁ

ብሎ የተነሳበት ነበርና ድርቅ አለ ብሎ

ማመን አልፈለገም። ኢትዮጵያ በሀብት

በለፀገች፣ አደገች፣ በሀብት ተጥለጠለቀች

ተብሎ ፕሮፓጋንዳ የሚነዛበት ወቅት

ነበር። ዕውነታው አፍጥጦ የሚታይ

ነበር። ምዕራቡ ዓለም ዕርዳታ ለመስጠት

ቢዘጋጅም፣ ደርግ መቀበል አልፈለገም።

‹‹ችግር የለም፤ ድርቅ የለም፤ ችግሩን

የፈጠራችሁት እናንተ ናችሁ›› ባይ

ነው። ይህንን ማስታርቆ ህዝቡን ከችግር

መታደግ ለእኔ እጅግ ከባድ ፈተና ነበር።

ያም ሆነ ይህ፣ የዓለም ዕውቅ አርቲስቶች

‹‹We are the World›› የተሰኘ ኮንሰርት

አዘጋጁ። ያንን ዘፈን ሲያዘጋጁ አማክረን

ብለው ወደ አሜሪካ ጠርተውኝ ነበር።

በ ገፅ 18

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 184 ቅዳሜ ጳጉሜ 5/ 2003

መልካም ዓዲስ ዓመት

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

17

18

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ሴ ት

ሴበመቅደስ

ፍስሐ

tigi.vip@gmail.com

ኪራይ ሰብሳቢዎቹ

በ2002 ዓ.ም ለ2003 መባቻ፣ ‹‹አዲስ›› ብለን ልንቀበለው

የጥቂት ቀናት ልዩነት ሲቀረን፣ በዚሁ ዓምድ

ያቀረብነው አንድ ጽሁፍ ነበር - ኪራይ ሰብሳቢ ሕፃናትን

በማስመልከት።

ለማስታወስ ያህል፡-

ሴቶቹ፣ በአዲስ ዓመት ወቅት የሚጨፍሩበት መንገድና

ወንዶቹ የሚጨፍሩበት መንገድ አንድ እንዳልሆነ ያወዳደርንበት ሁኔታ

ነበር። ባህል እየተበረዘ ነው (ኧረ እንደውም እየጠፋ ነው!) ብለን ነበር።

ልክ ነው። ባህል አጥፊዎቹ ራሳቸው ባህልን ናፋቂዎቹ ሆነው ተቸገርን

እንጂ።

የወንዶቹ ማስጠንቀቂያ አይሉት ‹‹ሆያ-ሆዬ›› አስቂኝም፣

አሳቃቂም ነው። እስቲ በደጅዎ የቆሙ ታዳጊ ሆያ-ሆዬ ጨፋሪ ህፃናት

ሲጨፍሩ እንዳልሰሙአቸው ሆነው ዝም ይበሏቸው፤ ድካማቸው ከንቱ

እንዳይሆን የሰጉት ህፃናት፣ ‹‹ኧረ በቃ በቃ ጉሮሮአችን ነቃ›› ብለው

ሊገስፁዎት ይሞክራሉ። ‹‹እምቢኝ›› ካሉም ወንዶቹ ለእርስዎ የሚሆን

የስድብ ግጥም አያጡም።

አንዳንዴም እነሱ በምን ገንዘብ እንደሚያገኙ ይገባቸዋልና

እንዲገጥምላቸው ብቻ የሚጠቀሙት ንግግርም አጀብ ያሰኛል። የሰማንያ

ዓመቱን ሽማግሌ ‹‹የኔ’ማ አባባ ኢትዮጵያዊው ሩኒ›› ሊሉም ይችላሉ -

ታዲያ ይሄን ምን ይሉታል?

የሴቶቹም ከዚህ በብዙ ይለያል ማለት አይደለም። ነገር ግን

‘የአለማመን’ ዘይቤአቸው ይለያል። የእነሱ እንደወንዶቹ ትዕዛዛዊና

ሽንገላዊ አይደለም። ልምምጥ ነው። ሌላውን ሰው የሚያሳዝን፣

የሚያራራና ሆድ የሚያባባ አይነት ነው። ሴቶቹ እንደወንዶች ‹‹ኧረ

በቃ በቃ ጉሮሮአችን ነቃ›› ላይልዎት ይችላሉ።

የሴቶቹ የጭፈራ ስርዓት ልምምጥንና የሌላውን ሰው

ሩሁሩነት መፈለግ መሆኑን በዚህ ማረጋገጥ እንችላለን፡-

‹‹ . . . እንኳን ቤትና የለኝም አጥር፣

እደጅ አድራለሁ ኮከብ ስቆጥር።

ኮከብ ቆጥሬ ስገባ ቤቴ፣

ትቆጣኛለች የእንጀራ እናቴ።››

በማለት እርስዎ የማያገባዎትን፣ ነገር ግን እነርሱ የእርስዎን ልብ

ያራራል ያሉበትን መንገድ ይጠቀማሉ።

የሴቶቹ ምርቃት ከወንዶቹ ይለያል። ወንዶቹ፡-

‹‹…ክበር በስንዴ ክበር በጤፍ፣

ምቀኛ ይርገፍ፣ እንደቆላ ጤፍ።››

ሊልዎት ይችላሉ። በስንዴና በጤፍ መክበር እንደሚቻል ያገናዘቡ

የሚመስሉት ህፃናቱ፣ ለጭፈራቸው ክፍያ ያበረከቱት ሽልማት በስንዴ

የተጋገረ ዳቦ ቢሆን ይሄ ምርቃት ላይደርስዎም ይችላል።

ሴቶቹ፡- የዛሬ ባለውለታቸውን ለዛሬ ዓመትም እንዲያገኙት

በመመኘት፡-

‹‹ከብረው ይቆዩኝ ከብረው፣

ባ’መት ወንድ ልጅ ወልደው፣

ሰላሳ ጥጆች አስረው።›› ብለው መልካም ምኞትን

ይገለፃሉ።

አንዳንዴ በወንዶች የ‹‹ሆያ-ሆዬ›› በዓል ሴቶች እንደ ወንድ

ሲጨፍሩ ገጥሞዎት ያውቃል? ለምን ይሆን? የሚል ጥያቄ ውስጤ

ያጭራል። እንደ ወንድ መሆን የመመኘት ሀሳቡ የመጣው ከምን

ይሆን? እኔ መልስ የለኝም።

ነጥቡ ከላይ ለትውስታ ያነሳነው ነገር ብቻም አይደለም።

ከዓመት ዓመት ይሄው ጉዳይ እየተቀየረና በሚገርም ሁኔታ ከትክክለኛ

ባህሉ እያፈነገጠ መሆኑ እንጂ። ጠያቂዎቹ ህፃናት እንዳሉ ሆነው

ሰጪዎቹ ምን ነካቸው የሚያስብል ነው።

‹‹ዮንዜና ዮንዜ ሳቢሳ፣ ጠላትህ ይበሳ እንደ አሮጌ ጣሳ።›› .

. . የተባለው አባወራ ምናልባትም ፀበኛ ጎረቤት ካለው የልቡ ደርሷልና

ግጥም አድርጎ ይሸልም ይሆናል። ነገር ግን መሆን ያለበት ያ አልነበረም።

እኛ እንዲህ እያደረግን ተመልሰን ደግሞ ‹‹ወይ ጊዜ!›› ብንል ምን ዋጋ

ይኖረዋል። ባህል ስለመበላሸቱ ተጠያቂው ተረካቢው ትውልድ ሳይሆን

አስረካቢው ትውልድም እንደሆነ ልብ ይሏል። እናስብበት።

ወደአዲስ ዓመት ስንመጣስ? እንዲህ ነው፡- ‹‹አዲስ›› ብለን

አንድ ነገር ስንገዛ ቀድሞ የነበረንን አሮጌ ነገር በአግባቡ ተጠቅመንበት

ሲያልቅ (ተጠቅመንበታል ብለን ስናስብ) ነው። በዚህ ሊያልቅ የቀናት

ልዩነት በቀረው ‹‹አሮጌ›› ዓመት የፈፀምነውን በጎ ተግባር ብቻ በማሰብ

ዓመቱን በጥሩ ሁኔታ ተጠቅመንበታል ብለን የምናስብ ከሆነ ስህተት

ሰርተናል።

ከወንዶቹ በመቀጠል ዓመቱን በመልካም ምኞት ያስጀመሩን

ሴት ህፃናት ለእነሱ የተሳካ ላይሆን ይችላል።

‹ከብረው ይቆዩኝ› ብለው የመረቁዎትና መልካም ምኛታቸውን

የገለፁልዎ ሴት ህፃናት በዓመቱ ያለ እድሜያቸው ወልደው የኃላፊነት

ሸክም ተከምሮባቸው ያገኙዋቸውም ይሆናል። አሊያም ያለአቅማቸው

በተሰጣቸው የስራ ኃላፊነት ላይ ሲዳክሩ፤ አሊያም የትምህርት እድል

ተነፍጓቸው ቤት ውስጥ ቁጭ ብለው … ይህ ሁሉ የሚሆነውና

የሚለወጠው በእርስዎ ነው። ያኔ - ‹‹አዲስ›› አስተሳሰብ ያመጡ ቀን -

ሁሌም ለእርስዎ ዓመቱ አዲስ ይሆናል።

ከብረው ይቆዩኝ!

መልካም አዲስ ዓመት!

የአፍሪካ ዜናዎች

እነ ማይክል ጃክሰን፣ እነ ሊየንል

ሪቼ ወዘተ ሁሉ አግኝቼ

አነጋገርኳቸው። የዘፈኑን ግጥም

ሁሉ አየሁ። ሙዚቃውን ሰሩት።

ብዙ የዕርዳታ ገንዘብ አሰባሰቡ።

ከዛ በኋላ ደግሞ ኢትዮጵያ መጡ።

አክብረን ተቀበልናቸው። ቦብ

ጊልዶፍ ደግሞ ከእንግሊዘ አንዲሁ

ለዕርዳታ ተነሳሳ። ላይቭ ኤይድ

አደረገ። በአሜሪካ ፊያደልፊያ

በተካሄደው ‹‹ባንድ ኤይድ›› ላይ

ብርሃነ ደሬሳ ምክትል ኮሚሽነር

ስለነበር በስፍራው ተገኝቶ ነበር።

እንዲህ እንዲህ ባለ ሁኔታ

በታቻለ መጠን እርዳታ እንዲገባ

አድርገናል።

ነገር ግን ጥረታችንን ከምስራቁ

ዓለም ፖለቲካ ጋር ሊታረቅ

አልቻለም። ‹‹ኮሚኒዝም ተበረዘ፤

በዕርዳታ ሰበብ ምዕራቦች ሰርገው

እየገቡ ነው፤ አብዮቱ ተቀለበሰ››

ተባለ። ያኔ የኢትዮጰያን ገፅታ

በማሳየት ረገድ ፊት ለፊት

የነበርኩት እኔ ስለሆንኩ ክፉኛ

እወቀስ ጀመር።

መወቀስ ማለት? ዕርዳታ ለምን ገባ ነው?

አዎ! ለምን ችግር አለ ብላችሁ

ኢትዮጵያን አጋለጣችሁ ነው

የተባለው። ወቅቱ 10ኛው

አብዮት በአል የሚከበርበት ነው።

መንግስቱ ኃ/ማርያም 6 ሰዓት

ሙሉ ንግግር አደረገ።6 ሰዓት

ሙሉ ንግግር ሲያደርግ የአንጎላው

ፕ/ት ዶ ሳንቶስ፣ የዛምቢያ ፕ/ት

ኬኔት ካውንዳ፣ የዚምባቡዌው

ሙጋቤ፣ የደቡብ የመኑ ፕ/ት እና

ሌሎችም እዚያው አዳራሽ ውስጥ

ነበሩ። በስድስት ሰዓት ንግግሩ

ስለዚያ አስከፊ ድርቅ አንድ

ገፅ አልተናገረም። ብቻ ግን፣

ዕርዳታ እንዲገባ እኔ ምዕራቡን

አለም ስለወተወትኩ ‹‹የሲ.

አይ. ኤ ኤጀንት ነው፤ አብዮቱን

ለማስቀልበስ የተቀጠረ ነው››

ስባል ለህይወቴ ፈራሁ። ያኔ

ጠፋሁ፤ አሜሪካ ገባሁ።

አወጣጥዎ ለሥራ ነበር?

አዎ! ለሥራ ነው የወጣሁት።

ምክንያቱም በግልፅ ነው

የተወገዝኩት። ፖሊት ቢሮ

ተጠርቼ ‹‹የኢትዮጵያን አብዮት

ለመቀልበስ ሞክረሀል፤ በዕርዳታ

ሰበብ የኃይማኖት ሰዎች እየገቡ

አይዲዮሎጂውን እንዲበርዙ

አድርገሀል፤ የምዕራባውያን

ወኪሎች ገብተው በኢትዮጵያ ላይ

ሳቦታጅ እንዲፈፅሙ ተባብረሃል።

ከምሥራቁ ዓለም ጋር እንድንጣላ

አድርገሀል››… ወዘተ ተባልኩ።

ለማንኛውም ዛቻ ሲበዛብኝ ከአገር

እንደወጣሁ ቀረሁ።

በዚያ ረሀብ የተነሳ ምን ያህል ሰው እንደሞተ

ይታወቃል? የተገኘውስ ዕርዳታ ህይወት

በማትረፍ ረገድ ምን ያህል አግዟል?

በእውነቱ መገመት በጣም

አስቸጋሪ ነው። የቁጥር ነገር

አስቸጋሪ ይመስለኛል። በእኔ

ግምት 2 ሚለየን ሕዝብ በረሃብ

ህይወቱን አጥቷል። በወቅቱ

ቤት ይቁጠረው ነው ያልነው።

የውጭው ዓለም ዕርዳታ ባይደርስ

ኖሮ ከዚያም በከፋ መጠን ሕዝብ

ያልቅ ነበር። የእኛ መ/ቤት እና

ሌሎች ምግባረ ሰናይ ድርጅቶች

በመተባበር ነው ዕርዳታ እንዲገኝ

ያደረገው። በእውነቱ እኔ በወቅቱ

ሕዝብን ለመታደግ ብርቱ ጥረት

አድርጌያለሁ። ይህንን ጥረቴ

ደግሞ በዚያ ወቅት የተ.መ.ድ

ባለስልጣን የነበሩ ሰው ለሕትመት

ባበቁት መፅሐፍ ‹‹ዳዊት ወ/

ጊዎርጊስ ብርቱ ጥረት ባያደርግ

ኖሮ ከ1 ሚሊዮን የበለጠ ህዝብን

ህይወት ማትረፍ አይቻልም

ነበር›› ሲሉ ምስክርነታቸውን

ሰጥተውበታል። ማዘር ቴሬዛም

እንዲሁ።

ግን እንደው በሚሊየን የሚቆጠር ሕዝብ

ለዕልቂት ከመዳረጉ በፊት መርዳት

አይቻልም ነበር?

በዚያ ወቅት ደርግ በትግራይ

ከወያኔ፣ በኤርትራ ከሻዕቢያ ጋር

ጦርነት ላይ ነበር። እና የደርግ

መንግስት የጦርነቱን ቀጠና ክፍት

አድርጎ ሕዝቡ ይረዳ ማለት

በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሽምቅ

ተዋጊዎችን መርዳት ነው በሚል

አልተቀበለውም። ሕዝቡን ነጥሎ

መርዳት ደግሞ አይቻልም።

የከፋው ረሀብ ያለው ደግሞ

በጦርነቱ ቀጠና ያለው ሕዝብ

ነው። ይሁን እንጂ የእኛ መ/ቤትና

ሌሎች ምግባረ ሰናይ ድርጅቶች

ከሰብዓዊነት አንፃር ሕዝቡ መረዳት

አለበት የሚል ዕምነት ነበረን።

የደርግ መግስት ጭራሽ ረሃብን

መኖሩንም ለመቀበል ፈቃደኛ

ሊሆን አልቻለም። ረሐብ መኖሩን

ቢያምን ይከበራል እንጂ አይናቅም

ነበር። ባለማመሪ የበለጠ ተናቀ።

ሕዝብን ያስጨረሰ መንግስት

የሚል ስም አተረፈ።

እናንተ ያለውን ሁኔታ ለመንግስት ማስረዳት

አትችሉም ነበር?

እኛማ ተናገርን። እኔ ራሴ በግሌ

ችግሩን ዘርዝሬ ገልጬ ነበር።

‹‹የለም፤ መንግስት በአቅሙ

ይረዳል፤ የውጭው ዓለም

አይስማ›› የሚል ምላሽ ነው

ያገኘሁት። እንዲያም ሆኖ ማይክል

በርግ እና መሀመድ ዓሊ (ጋዜጠኛ)

ኮረም ገብተው ሁኔታውን

በፊልም እንዲቀርፁ አደረግን።

ያ ፊልም በቢ.ቢ.ሲ 24 ደቂቃ፣

በአሜሪካው ቢ.ኤን.ሲ ቴሌቪዥን

ደግሞ 4 ደቂቃ ታየ። ዓለም

በሙሉ ለእርዳታ ተንቀሳቀሰ።

የብዙ ሰዎችንም ህይወት ማትረፍ

ተቻለ።

እርስዎ ህይወትዎን ለማትረፍ ከሀገር

እንደወጡ ቢናገሩም፣ በአሜሪካ የተደላደለ

ህይወት እንደገጠመዎት ነው በወቅቱ

ሲነገር የነበረው። ይህ ሁኔታ ደግሞ የደርግ

መንግስት ‹‹ዳዊት የሲ.አይ.ኤ ኤጀንት

ነው›› ሲል ያወጣውን መግለጫ ተዓማኒ

ያደርገዋል የሚሉ አሉ። በዚህ ጉዳይ ላይ

የእርስዎ አስተያየት ምንድነው? ለመሆኑ

አሜሪካ እንደደረሱ ወዴት ሄዱ? ምንስ

አደረጉ?

እንዳልከው ደርግ ‹‹ዘርፎ ከሀገር

ወጣ፤ የሲአይኤ ኤጀንት ነው››

ወዘተ የሚል የሥም ማጥፋት

ዘመቻ አካሂዶብኛል። እኔ ግን

እንደማንኛውም ሰው አሜሪካ

እንደገባሁ የፖለቲካ ጥገኝነት

ነው የጠየቅሁት። በዚያ ወቅት

በዕርዳታ ሰጪ ድርጅቶችና

በውጪ መንግስታት ዘንድ

ዕውቅና ስለነበረኝ ብዙም ችግር

አልገጠመኝም።

አሜሪካ ከገባሁ በኋላ ወዲያውኑ

ለደርግ መንግስት ሶስት ደብዳቤ

አከታትዬ ፃፍኩ። እነዚያን

ደብዳቤዎች ደበበ እሸቱ አፈላልጎ

በመፅሐፉ ውስጥ አትሞታል።

ደብዳቤዎቹ በፖለቲካውም ሆነ

በኢኮኖሚው መስክ ደርግ ምን

ማድረግ እንደሚገባው የሚመክሩና

መንግስትን የሚያቃኑ ነበሩ። እኔ

የደርግን መንግስት በይፋ መኮነን

እና መውገዝ የጀመርኩት የሥም

ማጥፋት ዘመቻ ከተከፈተብኝ

በኋላ ነው። በዚያው ወደ ፖለቲካ

ትግል ገባሁ። ፖለቲካ ውስጥ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 184 ቅዳሜ ጳጉሜ 5/ 2003

መልካም ዓዲስ ዓመት

አወዛጋቢው የዙማ ተሿሚ

ስለአስገድዶ መድፈር እንዲሁም በተመሳሳይ ጾታዎች መካከል

ስለሚደረግ ወሲባዊ ግንኙነት ወይም ግብረ-ሰዶማዊነት በተመለከተ

በሚሰነዝሯቸው አነጋጋሪ አስተያየቶች ይታወቃሉ - ሞጎንግ ሞጎንግ።

እኝህን ግለሰብ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ ዋና ዳኛ (ቺፍ

ጀስቲስ) አድረገው በቅርቡ መሾማቸው ጠንካራ ትችት እያስሰነዘረባቸው

ይገኛል።

ከሹመቱ አስቀድሞ የሀገሪቱ ቀንደኛ የሚባሉ ጎትጓች

ቡድኖች ጃኮብ ዙማ ዳኛ ሞጎንግን ዋና ዳኛ አድርገው እንዳይሾሟቸው

ቢጎተጉቷቸውም የሚሰማ ጆሮ አላገኙም። ለጉትጎታቸው ዋነኛ ምክንያት

ብለው የሚያነሱት ተሿሚው በአስገድዶ ደፋሪዎች ላይ ያላቸው አቋም

ጠንካራ አይደለም የሚል ነው።

ውንጀላውን በፍጹም የማይቀበሉት ዋና ዳኛ ሞጎንግ፣ ፈጣሪ

ዋና ዳኛ እንዲሆኑ እንደሚፈልግ መግለፃቸውን ባለፈው ሳምንት ቢቢሲ

ዘግቦ ነበር። ከ2009 አንስቶ በሀገሪቱ ሕገመንግሥታዊ ፍርድ ቤት

ያገለገሉት ዳኛ ሞጎንግ፣ ከዚህ ቀደምም በሀገሪቱ ‹‹ኖርዝ ዌስት›› ግዛት

መፈንቅለ መንግስት...

በሚገኝ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው አገልግለዋል።

ታዋቂ የደቡብ አፍሪካ የሕግ ባለሙያዎች፣ የሰብዓዊ መብት

ተሟጋች ቡድኖች እና የደቡብ አፍሪካ የሰራተኞች ማኅበር፣ ሹመቱን በይፋ

ከተቃወሙ አካላት መካከል ይጠቀሳሉ። ከዚህም በተጨማሪ፣ የኖቤል የሰላም

ሎሬቶችን - የኢራኗ ሽሪን ኢባዲ፣ የአየርላንዷ ሜይሪድ ማጉዌር እና

አሜሪካዊቷ ጆዲ ዊሊያምስ - ያቀፈው ሴት የኖቤል ተሸላሚዎች ቡድን (The

Nobel Women’s Initiative) ዋና ዳኛ ሞጎንግን በመቃወም በደተረገው ዘመቻ

ድጋፋቸውን ለግሰዋል።

‹‹እንደዚህ አይነት ኃለፊት ሲመጣ፣ ሳልፀልይና ኃላፊቱንም

እንድወስድ እግዚአብሔር መፈለጉን ውስጤ ሳያረጋግጥ አልቀበለውም››

ያሉት አዲሱ ተሿሚ ዋና ዳኛ ሞጎንግ ናቸው። ጃኮብ ዙማም በአዲሱ ተሿሚ

ኃላፊነት ሥር የፍትህ ሥርዓቱ በአስተማማኝ መዳፎች ውስጥ እንደሆን

ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።

በ2004 ውስጥ ዳኛ ሞጎንግ አንድ የሰባት ዓመት ሴት አስገድዶ

የደፈረ ግለሰብ የተፈረደበትን የዕድሜ ልክ እስራት ወደ 18 ዓመት ዝቅ እንዲል

ከገባህ ደግሞ ጠንካራ ቆዳ

ሊኖርህ ይገባል። እኔም ጠንካራ

ቆዳ ያለኝ ነኝና ከትግል ወደ ኋላ

አላልኩም።

አሜሪካ እንደተራ ስደተኛ ነው የገባሁት

እያሉኝ ነው?

አዎ እንደማንኛውም ተራ ስደተኛ

ነው የገባሁት።

እሺ፤ መቼ ነው የተባበሩት መንግስታት

ድርጅት ውስጥ ሥራ የጀመሩት?

ወያኔ አዲስ አበባ ከገባ በኋላ

ነው።

ከተሰደዱ በኋላ ወደ ፖለቲካው ትግል

የገቡት እንዴት ነው? ምንስ አደረጉ?

እንደነገርኩህ ደርግን በፅሁፍ

በማጋለጥ ነው የፖለቲካ ትግል

የጀመርኩት። ከዚያ በኋላ ደርግን

ከሥልጣን ለመጣል መጠቀም

የሚገባን አማራጭ ጦርነት

ሳይሆን፣ በውስጡ ባሉ ኃይሎች

መፈንቀል ነው በሚል ከጓደኞቼ

ጋር ‹‹ነፃ የወታደሮች ንቅናቄ››ን

አቋቋምን። እናም ተራማጅ በሆኑ፣

ለፍትህ በቆሙና በደርግ ውስጥ

ባሉ ከፍተኛ መኮንንኖች መፈንቅለ

መንግስት ለማድረግ ሞከርን።

የ1981 ዓ.ምን ማለት ነው።በዚያ

መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ውስጥ

ከሀገር ውጪ ያለውን ሁኔታ

የምናስተባብረው እኔ እና ጓደኞቼ

ነበርን። ያንን ያደረግነው ደርግን

በመፈንቅለ መንግስት አስወግዶ፣

በኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የሽግግር

መንግስት ማቋቋም አለብን በሚል

ነው።በዚህ መሰረት ከሻዕቢያ ጋር

ብዙ ከተወያየን በኋላ ሥምምነት

ላይ ደርሰን ተፈራረምን።

ምን የሚል ሥምምነት ላይ ደርሳችሁ

ተፈራረማችሁ?

በመፈንቅለ መንግስት ደርግ

ከስልጣን ከተወገደ፣ ሻዕቢያ

ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የሽግግር

መንግስቱ አባል ሆኖ፣ ስለኤርትራ

ሁኔታ ይወያያል የሚል ስምምነት

ላይ ደርሰን ነው የተወዳደርነው።

የት ተገናኝታችሁ ነው የተወያያችሁት?

ኤርትራ መሬት። እኔ ራሴ ናቅፋ

ገብቼ ነው የተፈራረምነው።

ፊርማው ከመፈንቅል መንግስቱ ሙከራ

ቀደም ብሎ ነው የተከናወነው?

አዎ። የመፈንቅለ መንግስቱ

ዋነኛ ዓላማ ጦርነቱን ማቆም

ነው። ጦርነት የማይቆም ከሆነ

መፈንቅለ መንግስት ማድረግ

ጥቅም የለውም። በጥቅሉ ጦርነት

እናቆማለን፤ ሠላም እንፈጥራለን፤

ከዚያ ሁሉን አቀፍ የሽግግር

መንግስት እንመሰርታለን የሚል

ነው ስምምነቱ። ለዚህ ሁኔታ

መሳካት ደግሞ በቅድሚያ

ከሻዕቢያና ህወሀት፣ ከኢህአፓ፣

ከኦነግ ጋር መስማማት ያስፈልግ

ነበር።

ከህወሀት ጋር የት ተነጋገራችሁ?

ዋሽንተን ውስጥም ተነጋግረናል።

በዋናነት ከህወሀትጋር

የተነጋገርነው ግን በሻዕቢያ በኩል

ነው።

ከሁሉም ተቃዋሚዎች ጋር በእኩልነት

የሽግግር መንግስት ለመመስረት ማለት

ነው?

እንደዛ ነበር የተስማማነው።

ከዚያስ?

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ መፈንቅለ

መንግስት ለማካሄድ በከፍተኛ

መኮንኖችና ባለሥልጣናት

መሀከል ሙሉ ስምምነት ተደርጎ

አያውቅም። ሀገር ውስጥ በሁሉም

ደረጃ ያሉ፣ ሁሉም መኮንኖች

በሃሳቡ ተስማሙ። የፖሊስ፣ የጦር

ሰራዊት፣ የአየር ኃይል፣ የባሕር

ኃይል አዛዦች፣ ምክትል አዛዦች

በሙሉ ጉዳዩን ተስማምተውበት

ነው እዚያ ደረጃ የደረሱት። ችግር

መሆን የነበረበት እዚያ ስምምነት

ላይ መድረስ ነበር። እንጂ መፈንቅለ

መንግሱትን ማካሄድ ችግር መሆን

አልነበረበትም።

እርስዎ ሁሉም ተስማሙ ቢሉም

ሜ/ጄ/ል ኃብተጊዎርጊስ ሀብተማሪያም

ባለመስማማታቸው እኮ ነው በመፈንቅለ

መንግስት አድራጊዎቹ እንደተገደሉ

የሚታወቀው። እና…

ሁሉም ተስማሙ ስልህ፣ እዚያ

ጉዳይ ውስጥ መታቀፍ የሌለባቸው

መጀመያውኑም አልተነገራቸውም።

ለደርግ ሙሉ ድጋፍ የነበራቸው

እነ ጄ/ል ኃብተጊዎርጊስ ኃ/ማሪያም

አልተነገራቸውም። ሌሎቹ ግን

ተነግሯቸዋል። ለምሳሌ ጄኔራል

መርዕድን ውሰድ። የታወቁ የጦር

መኮንን ናቸው፤ ኮንጎና ኮርያ

የዘመቱ ትልቅ ዕውቀት የነበራቸው

የጦር ሰው ናቸው። ጄ/ል ደምሴ

ቡልቶ ለኢትዮጵያ ጦር ከፍተኛ

አስተዋጽኦ ያደረጉ ናቸው። የባህር

ኃይል አዛዥ ኮሞደር ተስፋዬም

እንዲሁ። እነዚህ ሁሉ ከፍተኛ

የጦር አዛዦች የተስማሙበት

መፈንቅለ መንግስት ነው

የተካሄደው።

እነዚህ ምርጥ የጦር መኮንኖች በእናንተ

ስምምነት መሰረት የሽግግር መንግስት

በመመስረቱ ጉዳይ ላይ ተስማምተው ነበር?

መፈንቅለ መንግስቱ ቢሳካ እንኳ፣ እነሱ

እርስ በርስ ለሥልጣን ሊሻኮቱ ይችላሉ

የሚል ሥጋት የነበራቸው ብዙ ሰዎች አሉ።

ያ ሁኔታ ላለመከሰቱ ምን ማስተማመኛ

ነበራችሁ?

በዋናነት መፈንቅለ መንግስቱ

ከተደረገ በኋላ በ15 ቀን ወይም

3 ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ

የሽግግር መንግሰት ይቋቋማል

የሚል ስምምነት ነው የደረስነው።

ሀገር ቤት የጦሩ ኃላፊነት ያቺን

መፈንቅለ መንግስት ማካሄድ ብቻ

ነበር። ሻዕቢያ፣ ህወሀት፣ ኦነግ፣

ኢህአፓ ወዘተ ወዲያው ሀገር

ቤት ገብተው 15 ቀን ባልሞላ

ጊዜ ውስጥ ሽግግር መንግስት

ለመመስረት ተስማምተው ነበር።

እዚያ አዲስ አበባ መፈንቅለ

መንግስት ማድረግ የተስማሙት

ሰዎች ሌላ ዓላማ ይኑራቸው

አይኑራቸው አላውቅም። ነገር ግን

ከእኛ ጋር የተደረገው ስምምነትና

ዝግጅት እንደነገርኩህ ነው።

ግን የሽግግር መንግስቱን ለማካሄድ የሆነ

ኮማቴ መኖር አለበት። ኮሚቴ ካለ፣ ያንን

ኮሚቴ ማን እንደሚመራው ይታወቃል?

እኔ በውጭ ሀገር በኩል ያለውን

ሁኔታ ነው የማውቀው። ሀገር

ውስጥ እስከመጨረሻዋ ደረጃ

ድረስ የሆነውን የሰማሁት ልክ

እንደእናንተው ነው። እኛ አርብ

ዕለት ካርቱም ገባን። ስምምነት

ላይ ደረስን። ማክሰኞ መፈንቅለ

መንግስት ይደረጋል አሉን።

ማክሰኞ ዕለት ይሳካል ብለን

ለተባበሩት መንግሰታት አንዳንድ

ነገር ስናደርግ መፈንቅለ መንግስቱ

ከሸፈ ተባለ። ሌላውን ነገር እኔ

አላውቅም። የሚያውቁት ሀገር

ውስጥ የነበሩት ናቸው። እኔ

‹‹አሉ››ን ነው የምሰማው።

መፈንቅለ መንግስቱ ከከሸፈ በኋላ፣ እናንተ

የመሠረታችሁት ነፃ የወታደሮች ንቅናቄ

ተበተነ ወይስ?

አይ… ሌላ ሁተኛና ሶስተኛ

የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ

ለማድግ ሞክረናል።

(ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ ለዚህና ለሌሎች

አነጋጋሪ ጥያቄዎች የሰጡትን ምላሽ

በሚቀጥለው ሳምንት ይዘን እንቀርባለን።

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 184 ቅዳሜ ጳጉሜ 5/ 2003

መልካም ዓዲስ ዓመት

አድርገው ነበር። ከዓመት በኋላም የሰባት ዓመት ዕድሜ

ሴትን ለመድፈር ሙከራ ያደረገ ግለሰብ የተፈረደበትን

የአምስት ዓመት እስራት ወደ ሁለት ዓመት ዝቅ አድርገው

ወስነዋል። በሌላ ውሳኔያቸው ደግሞ ለአንድ ባለቤቱን/

ሚስቱን ለደፈረ ባል ይቅረታቸውን አጎናፅፈውታል።

የተዘገበው ምክንያታቸውም በወቅቱ ባለቤቱ የምሽት ልብስ

እና የውስጥ ሱሪ ለብሰው የነበረ መሆኑ ነው።

በባልና በሚስት መሀከል የሚደረግ ወሲባዊ

ግንኙነትን እንደ አስገድዶ ደፈራ እንደማይቆጥሩ

በሶስየትድ ፕሬስ የተዘገበላቸው ዋና ዳኛ ሞጎንግ ግን

ይህ ሁሉ ተቃውሞ ቢሰነዘርባቸውም፣ የደቡብ አፍሪካን

ሕገመንግሥት እንደሚያስፈጽሙ እና በሀገሪቱም ላዕላይ

ሕግ መሰረት እንደሚገዙ በመግለጽ ሹመቱን በጸጋ

ተቀብለዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የአስገድዶ ደፈራ ወንጀሎች

በተደጋጋሚ ከሚፈፀሙባቸው ሀገራት መካከል ደቡብ

አፍሪካ ከቀዳሚ ተሰላፊዎች መካከል ግንባር ቀደሟ

ናት። በኢንተርፖል መረጃ መሰረት፣ በደቡብ አፍሪካ

በየ17 ሰከንዶች ውስጥ አንድ የአስገድዶ ደፈራ ወንጀል

ይፈፀማል።

/ምንጭ - ቢ.ቢ.ሲ/

በኤልያስ ገብሩ

ከታህሳስ 1953 ዓ.ም. ጀምሮ የኢትዮጵያ

ሕዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት ለመሆን የጀመረው

ሁሉን አቀፍ ትግል ሳይሳካ ሃምሳ ዓመታት

እንደሞላው በመጥቀስ፣ ‹‹ቀጣዩ ዓመት የጨለማ

ጊዜ ሆኖ መቀጠል የለበትም›› ሲል አንድነት

ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ትናንት

መግለጫ አወጣ።

ቀጣዩ 2004 ዓ.ም. ለሁለንተናዊ ነፃነት

ሁሉን አቀፍ የነፃነት ትግል የሚደረግበት ዓመት

ሊሆን እንደሚገባ የገለፀው አንድነት ‹‹የሚደረገው

የነፃነት ትግልም ለኢትዮጵያውያን ሁሉ ለኢህአዴግ

አባላትም ጭምር ነፃነትን የሚያጎናፅፍ ሊሆን

ይገባዋል። ትግሉ ከዘረኝነት ከበቀልና ከቁርሾ የፀዳ

ሁላችንንም ኢትዮጵያውያንን ከሊቅ -እስከ ደቂቅ

በደቡብ ምስራቃዊ አፍሪካ የምትገኘው ማላዊ መሪ የሆኑት ፕሬዝዳንት ቢንጉ

ዋ ሙታሪካ፣ ባቤታቸውን የመንግሥታቸው የሥራ አስፈፃሚ አካል አባል

ማድረጋቸው፣ እና እንዲሁም ወንድማቸውን በፊት ከነበሩበት መንግሥታዊ

ሥልጣን አንስተው ከፍ ላለ ኃላፊነት መሾማቸው አነጋጋሪ አድርጓቸዋል።

ባለፈው ረቡዕ ነበር ባለቤታቸውን ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እና የሴቶች ጉዳዮች ሚኒስትር

አድርገው የሾሟቸው። ባለፈው ሀምሌ ወር ውስጥ በመንግሥታቸው ላይ በተካሄደ

የተቃውሞ ሰልፍ በተፈጠረ ግጭት 19 ሰዎች ከሞቱ በኋላ በተከተለው የካቢኒ

ብፕወዛ፣ ከባለቤታቸው ካሊስታ ሹመት በተጨማሪ ወንድማቸው ፒተር ሙታሪካ

በሚኒስትርነት ማዕረግ ወደ ሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ተዘዋውረዋል።

የዚያ የሰው ህይወት የጠፋበት ሰልፍ አደራጆች ለፕሬዝዳንት ሙታሪካ አንድ

ጠንካራና ቆራጥ የተባለ ቀነ-ገደብ አስቀምጠውላቸዋል - እስከ መስከረም 21 ድረስ

መንግሥታዊ ማሻሻያዎችን እንዲወስዱ።

ያም ሆኖ፣ ቀነ-ገደቡ ተከበረም አልተከበረም፣ ሚር. ሙታሪካ የሚመሩትን

መንግሥት የቤተ-ዘመድ መሰብሰቢያ አድርገዋል የሚል ውንጀላ በይፋ ከመሰንዘሩ

በፊት ሚስታቸውንና ወንድማቸውን የካቢኔ አባል ለማድረጋቸው አሳማኝ ምክንያት

ማቅረብ እንደሚጠብቅባቸው ማሳሰቢያ ያስተላፉት የአገሪቱ ተቃዋሚ የፖለቲካ

ድርጅት - የማላዊ ኮንግሬስ ፓርቲ - መሪ ጆን ቴምቦ ናቸው።

እንቅስቃሴዎቹንም በቅርበት ስንከታተል ቆይተናል››

ቢሉም የመድረክ አመራሮች ውድቅ አድርገውታል።

መድረኩ ትናንት በሰጠው ጋዜጣዊ

መግለጫ ላይ ‹‹የደበበ እሸቱን መታሰር መድረክ

በተለይም አንድነት ፓርቲ እንዴት ያየዋል?›› የሚል

ጥያቄ ከአውራምባ ታይምስ ቀርቦ የነበረ ሲሆን፣ ባለው

የፖለቲካ አቋም የተነሳ በኢህአዴግ እንደማይወደድ

ያስታወሱት የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ

ጊዳዳ፣ ‹‹እንደ አንድ የኢትዮጵያ ታጋይ እንዲለቀቅ

አንድነትና መድረክ ይጠይቃሉ›› ብለዋል። የፓርቲው

ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ አንዷለም አራጌም

ደበበ እሸቱን በደንብ እንደሚያውቁትና ‹‹በሽብር

ተግባር ይሰማራል›› የሚል ዕምነት እንደሌላቸው

ተናግረዋል።

የቀድሞው ቅንጅት የላዕላይ ም/ቤት

አባልና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረው አርቲስት

ደበበ፣ ምርጫ 97ን ተከትሎ ከሌሎች የቅንጅት

አመራር አባላት ጋር የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት

ዜናዎች

ፕሬዝዳንቱ ሚስታቸውን ሾሙ

የአፍሪካ ዜናዎች

እንደተንታኞች እይታ ከሆነ፣ ፕሬዝዳንቱ ወንድማቸውን የሾሙበት ዋነኛ ዓላማ

እየተንገዳገደች ላለችው ሀገር ‹‹አዲስ›› መሪ (ወይም ወራሻቸውን) አስቀድመው ለማዘጋጀት

እና በዚህም መንገድ የዓለማቀፋዊ ግንኙቶች ተሞክሮአቸውን ማዳበር ነው።

በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት መግቢያ አካባቢ የሙታሪካ መንግሥት በሙስና ተጨማልቋል፣

ኢኮኖሚውን አመሳቅሏል በሚሉ ዋነኛ ምክንያቶች ዮናይትድ ኪንግደም ለማላዊ ትሰጥ

የነበረውን እርዳታ ማቋረጧ ይታወሳል።

ይህ የኢኮኖሚ ጉዳይ ባለፈው ወር ለተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ተጠቃሽ ምክንያት ነበር -

በሀገሪቱ ተቃዋሚዎች። ተቃዋሚዎቹ እንደሚሉት፣ ማላዊ ከእንግሊዝ የ73 ዓመታት የቅኝ

አገዛዝ በኋላ በሀምሌ 6/1964 (እ.አ.አ) ነፃነቷን ከተቀዳጀች በኋላ ካጋጠሟት ኢኮኖሚያዊ

ቀውሶች መካከል ይሄኛው በአስከፊነቱ ቀዳሚው ነው።

ከፍተኛ የነዳጅ፣ የኤሌክትሪክ ኃይል እና የውጭ የመገበያያ ገንዘብ እጥረት በአሁኑ ወቅተ

ሀገሪቱን እያመሷት ይገኛሉ። ባለፈው ወር የፕሬዝዳንት ሙታሪካ መንግሥት የሀገሪቱ

የመገበያያ ገንዘብ (‘ዋቻ’) ከዶላር (የአሜሪካ) ጋር ያለውን የምንዛሬ ተመን/ዋጋ ዋጋ ዝቅ

ለማድረግ ተገዶ ነበር።

ከዓለም እጅግ ደሃ ሀገራት ተርታ የምትሰለፈው ማላዊ፣ 75 በመቶ የሚሆነው ሕዝቧ በቀን

ከአንድ ዶላር ባነሰ ገቢ ነው የሚኖረው፤ መኖር ከተባለ።

/ምንጭ - ቢ.ቢ.ሲ/

ሲፒጄ፣ መንግስት በጋዜጠኞች ላይ

ያቀረበው ክስ ፍሬ ቢስ መሆኑን ገለፀ

በሱራፍኤል ግርማ

ማድረጋቸውን ላይወድ ይችላል። ግን ጋዜጠኞቹ ርምጃ ነው›› ያለው ጋዜጠኛ ዳዊት፣ መንግስት ጋዜጠኞች በተመሳሳይ ሁኔታ የሽብርተኝነት ክስ

ከሥራቸው ፀባይ አኳያ ሁሉንም ወገኖች ማግኘት ጋዜጠኞችን ‹‹በሽብር ተጠርጥረዋል›› እያለ ማሰሩ ተመስርቶባቸዋል።

ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬና ርዕዮት ዓለሙን ግድ ይላቸዋል›› ሲል የመንግስትን ‹‹ከአሸባሪዎች የመንግስት ጥገኛ ያልሆኑና ተቺ የሚዲያ ተቋማትን

ብሉምበርግ በድረ ገፁ፣ የመንግስት

ጨምሮ በሽብርተኝነት ክስ የቀረበባቸውን የስዊዲን

ጋዜጠኞች መንግስት በአፋጣኝ እንዲፈታ የጋዜጠኞች

መብቶች ተሟጋች የሆነው ሲፒጄ ጠየቀ። ባወጣው

መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት የፀረ ሽብርተኝነት

ሕጉን ለነፃ ፕሬስ ማፈኛነት እየተጠቀመበት መሆኑን

ያስታወቀ ሲሆን፣ ‹‹መንግስት ይሄን ፍሬ ቢስ ክሱን

በመተው ጋዜጠኞቹን ሊፈታ ይገባል›› ብሏል።

የሲፒጄ በአፍሪካ አስተባባሪ የሆነው

ሞሐመድ ኪየታም ‹‹የኢትዮጵያ መንግስት ‹ሽብርተኛ›

ብሎ ከፈረጃቸው ወገኖች ጋር ጋዜጠኞቹ ግንኙነት

ጋር ንክኪ አላቸው›› የሚል ክስ ውድቅ አድርጓል።

የአውራምባ ታይምስ ም/ዋና አዘጋጅ

በአሸባሪነት መከስስን አስመልክቶ ለተለያዩ ዓለም

አቀፍ የሚዲያ ተቋማት አስተያየቱን የሰጠው

የአውራምባ ታይምስ ማኔጂንግ ኤዲተር ዳዊት ከበደም

በባልደረባው ላይ የቀረበውን ክስ እንደማይቀበል

አስታውቋል።

ለአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ የእንግሊዘኛ

አገልግሎት ዘጋቢ ፒተር ሄንሌ በስልክ በሰጠው ቃለ

መጠይቅ ‹‹ይህ ክስ ነፃውን ፕሬስ ለማሸማቀቅ የተወሰደ

ለማጥፋት የተቀነባበረ ሴራ መሆኑን ተናግሯል።

የመንግስትን ፖሊሲዎች መተቸት

በአሸባሪነት እየተተረጎመ መሆኑን ያስገነዘበው

የአውራምባ ታይምስ ማኔጅንግ ኤዲተር፣ ለብሉም

በርግ የዜና አውታርም ‹‹የባልደረባችን በሽብር መከሰስ

ጋዜጣው ላይ ተፅዕኖ የማሳረፊያ አንዱ መንገድ ነው››

ሲል ሁኔታውን አብራርቷል።

በሌላ በኩል ከወራት በፊት ፓርላማ

በአሸባሪነት ከፈረጀው ኦብነግ ታጣቂዎች ጋር

ጂጂጋ ከተማ አካባቢ የተያዙት ስዊዲናያዊያን

ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር ዲኤታ አቶ

ሽመልስ ከማል ‹‹ግለሰቦቹ ወደ አገር ውስጥ የገቡት

በሕገ ወጥ መንገድ ነው፡፡ ከጋዜጠኝነት ሥራ ውጪ

የጦር መሳሪያ አጠቃቀም ስልጠና ወስደዋል፤ የጦር

መሳሪያ ይዘው የሚያሳይ የቪዲዮ ቴፕም አቃቤ ሕግ

አለው›› ማለታቸውን አስነብቧል።

ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬና ርዕዮት ዓለሙ

ክስ ከተመሰረተባቸው በኋላ በፖሊስ ምርመራ ላይ

ከነበሩበት ‹‹ማዕከላዊ›› ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት

የተዛወሩ ሲሆን፣ ለጥቅምት ዘጠኝ ቀን 2004ዓ.ም

ተቀጥረዋል።

‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብ የተነጠቀው ነፃነቱን ለመቀዳጀት ዛሬውኑ ለትግል ይነሳ››

አንድነት ፓርቲ

የሚያስተባብር አንድነታችንን ከመቼውም ጊዜ በላይ

ጎልቶ የሚወጣበት ሊሆን ይገባዋል።›› ብሏል።

የነፃነት ትግሉም መጀመሪያ ፍርሃትን

ድል መንሳት መሆኑን በመጥቀስም፣ በአሁኑ ወቅት

በአረቡ ዓለም እየተካሄደ ያለው የነፃነት ትግልና

ውጤቱም ተግባራዊ ተሞክሮውን ማጠናከሩን፣

ሕዝቡ ነፃ አውጪዎችን ቁጭ ብሎ የሚጠብቅበት

ጊዜ ማብቃቱንና እያንዳንዱ የኢትዮጵያ ሕዝብም

የነፃነቱ ባለቤት ለመሆን አበክሮ ሊታገል እንደሚገባው

መግለጫው አትቷል።

‹‹የወደፊቷን የበለፀገችና ዴሞክራሲያዊት

ኢትዮጵያን መፍጠር ላለበት ኢትዮጵያዊ ወጣት ግን

አምባገነን አገዛዝን ተሸክሞ መኖር ፈፅሞ አማራጭ

ሊሆን አይችልም። በመሆኑም የነፃነት ህልምን እውን

ለማድረግ በ2004 ዓ.ም. የመጀመሪያው እርምጃ

ፍርሃትን ድል መንሳት ነው›› በማለት ፓርቲው

ለኢትዮጵያዊ ወጣት ጥሪውን አስተላልፏል።

ደበበ እሸቱ እንዲፈታ አንድነት...

እንዲሁም በገዥው ፓርቲ ቡራኬ

የሚተዳደሩና ለገዥው ፓርቲ የጭቆና አገዛዝ

ድጋፋቸውን ቀጥተኛ በሆነና ባልሆነ መንገድ እየሰጡ

የሚገኙ “ተቃዋሚ ፓርቲዎች” ሳይረፍድ ከሕዝብ ጎን

እንዲቆሙ አንድነት ሀሳቡን ሰንዝሯል።

የኢትዮጵያ ዲያስፖራም ትኩረቱ የነፃነት

ጥያቄ ላይ መሆን ስለሚገባው ለጥያቄው ተጠናክኖና

ተደራጅቶ መውጣት እንደሚገባው፣ ዓለም አቀፍ

ማሕበረሰብም የኢትዮጵያ ሕዝብ አሁን ካለበት

የጭቆናና የችጋር አዘቅት ራሱን ነፃ ለማውጣት

ለሚያደርገው ትግል ከመቼውም ጊዜ በላቀ መልኩ

ድጋፍ እንዲሰጥ ፓርቲው ጠይቋል።

በመጨረሻም ለኢህአዴግ ጥሪውን

ያስተላለፈው አንድነት፣ አገዛዙ ለሕዝብ ሰላማዊ

የለውጥ እንቅስቃሴ ሰላማዊ ምላሽ ቢሰጥ ከምንም

በላይ ለራሱ፣ ለሕዝብ፣ ለሀገርና ለትውልድ ጠቃሚና

ክቡር ውጤት ማስመዝገብ ይችላል ብሎ እንደሚያምን

በይቅርታ መፈታቱና ከእስር ከተፈታ በኋላ

በመስራችነት ባቋቋመው አንድነት ለዴሞክራሲና

ለፍትሕ ፓርቲ ውስጥ በተፈጠረው የሀሳብ ልዩነት

የተነሳ ‹‹መርህ ይከበር›› በሚል አቋሙ ከፓርቲው

መሰናበቱ ይታወሳል።

ከፖለቲካዊ እንቅስቃሴው በተጨማሪ

በተለያዩ ኪነ-ጥበባዊና ማህበራዊ ክንዋኔዎች ላይ

ተሳታፊ የነበረው አርቲስት ደበበ፣ በሸገር ኤፍ.ኤም

ላይ የመጽሀፍት ትረካ ሲያቀርብ ቆይቷል።

ከመታሰሩ ጥቂት ሠዓታትን ቀደም ብሎ

ለፍትሕ ጋዜጣ የአዲስ ዓመት መልካም ምኞቱን

የሚገልፅ ፅሁፍ ያስገባው ደበበ እሸቱ፣‹‹አዲሱ ዓመት

ከሰቀቀን ኑሮ ተላቀን እፎይ የምንልበት፣በፍራቻ

ሳይሆን በመምረጥ የምንኖርበት እንዲሆን እመኛለሁ››

ብሎ ነበር።

‹‹ረሐብን ማጋለጥ በሽብርተኝነት

ሊያስወነጅል አይገባም›› በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ

ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ በሰጠው

ከመታሰሩ ጥቂት ሠዓታትን ቀደም ብሎ ለፍትሕ ጋዜጣ የአዲስ

ዓመት መልካም ምኞቱን የሚገልፅ ፅሁፍ ያስገባው ደበበ እሸቱ፣‹‹አዲሱ

ዓመት ከሰቀቀን ኑሮ ተላቀን እፎይ የምንልበት፣በፍራቻ ሳይሆን

በመምረጥ የምንኖርበት እንዲሆን እመኛለሁ›› ብሎ ነበር።

19

ገልጿል።

በተያያዘ ዜናም ነሐሴ 29 ቀን 2003

ዓ.ም በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከዜና እወጃ በኋላ ፕ/ር

በየነ ጴጥሮስ በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተውን ድርቅ

ምክንያት በማድረግ ተዘጋጅቶ የነበረውን አንድ

የማስተባበያ ፕሮግራም አንድነት ተችቶታል። በዚህ

ፕሮግራም ላይ ቀርበው ከተናገሩት ሰዎች መካከል

በተለይ ሁለቱ ‹‹የመድረክ አባላት ነን›› በማለት

ያቀረቡት አስተያየት የተሳሳተ መሆኑ በመጥቀስ፣

አንደኛ አቶ አበበ ታምራት ከሀምሌ 13/2003 ዓ.ም

ጀምሮ በሥነ-ምግባር ችግር ምክንያት ከፓርቲው

መታገዳቸውን ተገልጿል። ሁለተኛ አቶ አጥናፉ

የተባለው ግለሰብ ደግሞ በሥነ-ምግባር ብልሹነት

የሚታወቅና የመድረክ አባል አለመሆኑን መድረክ

ትናንት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

መግለጫ ዋና ርዕሰ ጉዳይ የነበረው በቅርቡ የታሰሩት

የመድረክ አመራር አባላት ጉዳይ ነበር። ለአቶ በቀለ

ገርባ አና ለአቶ ኦልባና ሌሊሳ መታሰር መንግስት

‹‹ከኦነግ ጋር ሲያሴሩ ነበር›› የሚል ምክንያት

ቢያቀርብም፣ መድረኩ ይህን ውድቅ አድርጎታል፡፡

በመግለጫው መሠረት ለሁለቱ ግለሰቦች

መታሰር ዋንኛው ምክንያት በኢትዮጵያ ስላለው

አጠቃላይ ሁኔታ ለአምንስቲ ኢንተርናሽናል መረጃ

በመስጠታቸውና የኢህአዴግ መንግስት የእርዳታ

እህልን ለፖለቲካ መሳሪያነት እያዋለው መሆኑን

ለዘገቡት የቢቢሲ ጋዜጠኞች ጥቆማ በመስጠታቸው

ነው።

ፖለቲከኞቹ የምር የኦነግ አባላት ቢሆኑ

ኖሮ ከኦነግ የሚፃረር የፖለቲካ ፕሮግራም ባለው

መድረክ ውስጥ አባል ከመሆን ይልቅ መገንጠልን

በሚደግፈው ኢህአዴግ ውስጥ መታቀፍ ይችሉ

እንደነበር አቶ ጥላሁን እንዳሻው የተባሉ የመድረክ

አመራር አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ደሞክራሲያዊ

አንድነት መድረክ ሽብርተኝነትን በምንም መልኩ

እንደማይደግፍ አፅንኦት የሰጡት አቶ ገብሩ አስራት

ደግሞ በበኩላቸው፣ ኢህአዴግ ተቃዋሚዎቹንና

ተቺዎቹን በማሰር አጠቃላይ ሕዝቡን እያሸበረ

መሆኑን ገልፀዋል።

በሽብርተኝነት ክስ ስለተመሰረተባቸው

ስዊዲናዊያን ጋዜጠኞች ጉዳይም በመግለጫው ላይ

ተነስቷል። ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ‹‹ሁለቱ ጋዜጠኞች

በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ በመግባት

ሉዓላዊነታችን መደፈሩን እንዴት ያዩታል?›› የሚል

ጥያቄ ለአቶ አንዷለም አራጌ ቀርቦ የነበረ ሲሆን፣

አቶ አንዷለምም ‹‹ኢህአዴግ ሁለት ሰዎች ድንበር

አቋረጡ ብሎ ሊጨነቅ ይቅርና አገር ገንጥሎ የሚሰጥ

ድርጅት ነው›› የሚል መልስ ሰጥተዋል።

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

20

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 184 ቅዳሜ ጳጉሜ 5/ 2003

መልካም ዓዲስ ዓመት

‹‹በቴሌቪዥን በሚሰሩት ‘ድራማ’

ሀቅ ሊወጣ አይችልም››

ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ

/የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ሊቀ-መንበር እና የመድረክ ምክትል ሊቀ-መንበር/

በአንድ ወር በፊት ቢቢሲ ኒውስ ናይት በተሰኘው ፕሮግራሙ ላይ የኢትዮጵያ መንግስት የሚሰጠውን እርዳታ ለፖለቲካ ፍጆታ እንደሚያውለው፣ የተደበቀ

ረሀብ በኢትዮጵያ እንደሚገኝና ሌሎች ሀሳቦችን የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን እና ቦታው ድረስ ተገኝቶ ተጎጂ ያላቸውን ዜጎች በማነጋገር ዘገባ

ካቀረበ በኋላ የኢትዮጵያ መንግስት በተለያየ መንገድ ዘገባው የተሳሳተ መሆኑን መግለፁ ይታወሳል። ባለፈው እሁድ ምሽት በኢትዮጵያ ፈርስት ድረ-ገጽ

ኤዲተር ቢኒያም ከበደ ተዘጋጅቶ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የቀረበው ‹‹ዶክመንተሪ›› ፊልምም በዋነኛነት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ላይ ባጠነጠነ መልኩ

ለቢቢሲ የሰጡት አስተያየት እውነትነት እንደሌለው የገለፀ ነበር። በዚህና በመሰል ጉዳዮች ዙሪያ የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ሊቀ-መንበር፣

የመድረክ ምክትል ሊቀ-መንበርና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስን አቤል ዓለማየሁ አነጋግሯቸዋል።

ኒውስ ናይት በተሰኘው የቢቢሲ ፕሮግራም ላይ መንግስት አገር ውስጥ የሚገባ የእርዳታ እህልን ለፖለቲካ ጥቅም እያዋለው እንደሆነ፣ የሚረዱትም

የኢህአዴግ አባላት (ደጋፊዎች) መሆናቸውን ገልፀዋል። ይህን ሀሳብ የሰነዘሩት ከምን ተነስተው ነው?

ኢህአዴግ አባላቱ በሆኑና ‹‹ተቃዋሚ›› በሚላቸው መሀከል አድሎ እንደሚያደርግ ባለፈው 20 ዓመት ስንናገረው የነበረ

ነው። አሁን እነሱን ለምን እንዲህ እንዳርበተበታቸው እኔ’ንጃ። ጉዳዩ ለንደን ደርሶ በቢቢሲ በኩል ተመልሶ ስለመጣ ነው?

በየቀኑ ለጋዜጠኛ ጋዜጣዊ መግለጫ ስንሰጥ የምንናገረው ነው።

በተራቡት ዜጎች ላይ ሞራል የሚነካ ሥራ እንደሚሠራ በአደባባይ ነጋ ጠባ ስናወራው የነበረ ነው። ፓርላማ ውስጥ

በነበርንበት ጊዜም ስንገልፀው የኖርነው ነው። ስም ዝርዝር ሰብስበን ለእርዳታ ለጋሾች ሰጥተን እናውቃለን። ለኢፒጂ

(Ethiopian Partners Group)፣ ዓለም ባንክና ለሌሎችም ሰጥተናል።

ስም ዝርዝራቸው የተገለፀው ሰዎች ምንድን ናቸው?

በምርጫ ሰሞን ባለ ሽኩቻ ሰዎች ማንን እንደሚደግፉ በሚያደረጉት እንቅስቃሴ ወረዳ አመራሮች ተለይተው ይታወቃሉ።

የተቃዋሚ ደጋፊዎችን ምርጫው እንዳለቀ ከሴፍቲ ኔት ዝርዝር ያስወጧቸዋል። እውነታውን ለመደበቅ የሚጠቀሙበት

ቃል ‹‹እናንተ ጨርሳችኋል›› የሚል ነው። የእነዚህ ሰዎች ስም እና የቦታቸውን ስም ዝርዝር ለጠቀስኳቸው ድርጅቶች

ሰጥተናል።

ይህ ችግር በቀድሞ ጊዜም ሆነ አሁን ድረስ አለ ነው የሚሉት?

ይሄ ችግር ድሮም ሆነ አሁንም ያለ ነው። ኢህአዴግ በበቂ መረጃ ማስተባበል የቻለበትን ሁኔታ እስከዛሬ አልተመለከትኩም።

ይህንን አድበስብሶ ማለፍ አይቻልም። የተራበውን ህዝብ [በተለይ የእኛ ደጋፊውን] ‹‹ይህ የመጣው ለኢህአዴግ አባላት

እና ደጋፊዎች ነው። ለእናንተ በየነ ጴጥሮስ ሲያመጣ ትበላላችሁ›› ይሏቸዋል። ይህ የተለመደ አባባል ነው። ጨዋታው

ያለው እነሱ ካምፕ ነው። ለሁሉም እየሰጡ መሆኑን በተግባር ካየን እኛም ወቀሳችንን እናቆማለን። በቴሌቪዥን

በሚሰሩት ድራማ ሀቅ ሊወጣ አይችልም።

‹‹ኢህአዴግ እርዳታን ለፖለቲካ ጥቅም ያውለዋል›› ሲሉ እውን ፖለቲካ ልዩነትን ከማንፀባረቅ በፀዳ መልኩ ነው?

በምርጫ ሰሞን በከባድ መኪና የእርዳታ እህል ሞልቶ የምግብ እጥረት አለ ወደሚባልበት ቦታ መሄዱ ሲሄዱ ለማን

ድምፅ መስጠት እንዳለባቸውም መመሪያ ይሰጧቸዋል።

ዳቦ በጆንያ ይዘው አድለው ከጨረሱ በኋላ ‹‹አባል ሁኑ›› የሚሉበት ሁኔታ መኖሩን እናውቃለን። ሩቅ ሳትሄድ እዚህ

አዲስ አበባ ለኢህአዴግ ድምፅ ይሰጣል ለተባለ ጎረምሳ ሁሉ ሰላሳ እና ሃምሳ ብር ሲያድሉ ይውሉ አልነበር እንዴ?

አድልዎ ማለት ይሄ ነው፤ በገንዘብ ድምፅ መግዛት።

የትም ቀበሌ ያለ ወጣት ሥራቸውን ይንቃል። ገንዘቧን ግን ‹‹እፈልጋታለሁ›› ብሎ ይወስዳል። ይህን የሚያደርጉት የቀን

የውሎ አበል የሚከፈላቸው ካድሬዎቻቸው ናቸው። በአንድ የምርጫ ክልል ብቻ ሰዎች [የእኛ ደጋፊዎች] ‹‹እህላችን

ሳይደርስ ቀርቶ እርዳታ ብንጠይቅም ተገለልን እናም ተቸግረናል›› ብለው ፅፈው ፈርመው የላኩልን መረጃዎች እጃችን

ላይ አሉ።

ይህ ከሆነ እርዳታ ለጋሾች ሊያውቁ አይችሉም ብለው ያስባሉ?

እርዳታ ሰጪዎች ‹‹እርዳታ የሚገባው ለእነዚህ ነው›› የሚል ሚና የላቸውም። ከወረዳ/ከቀበሌ ተጣርቶ በተላለፈላቸው

ስም ዝርዝር መሰረት ይሰጣሉ። ተመርጠው የመጡት ሰዎች የኢህዴግ ሰዎች ይሁኑ/አይሁኑ የሚያውቁት ነገር

የለም።

መድልዎ እየፈፀመ ያለው ስም ዝርዝር የሚሰጠው አካል ነው። የእኛ አባላት ‹‹በሴፍቲ ኔት አንታቀፍም፣ እርዳታ

ሲመጣ ስም ዝርዝራችን የለም›› ይሉናል። እንደውም መታወቂያ ሁሉ እየታደለ ነው። ለእኛ ሰዎች ግን ያንን መታወቂያ

እሺ ብለው አይሰጡም። እኛ መረጃ ሳይኖረን ዝም ብለን አንናገርም።

ቢቢሲ ዘገባውን ካስተናገደ በኋላ መንግስት ላይ ተቺ ሀሳብ የሰነዘራችሁ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን በምርጫ ድምፅ ህዝብ ስለቀጣችሁና ተስፋ ስለቆረጣችሁ

ባገኛችሁት አጋጣሚ ውሸትን (ጥላቻን) እንደምትሰብኩ በመንግስት መገናኛ ብዙሐን ላይ ስሞታ ቀርቦባችኋል። ይስማማሉ?

ይህ በራሱ በጣም ሰፊ አወያይ ርዕስ ነው። መድረክ ከምርጫው በኋላ ‹‹ኢህአዴግ አዳፍኖት ለማለፍ ያቀደው የአገራችን

የዴሞክራሲ ሂደት ግንባታ በህዝባችን ሰላማዊ ሂደት ይከሽፋል›› የሚል መግለጫ መስጠቱ ይታወሳል። እዚያ ላይ

የነበሩትን ችግሮች ዘርዝረናቸዋል። ‹‹ምርጫው ድራማ እንጂ ፍትሃዊ አልነበረም፣ የምር’ኮ ውጤት ነው›› ብለናል።

እኔ ከማንም በላይ ፓርላማ የቆየሁ ሰው ነኝ፤ ከሽግግሩ ወቅት ጀምሮ። ያኔ ሁሉ የምናቀርበው ክስ ነው። በምርጫ

ባሸነፍኩባቸው ጊዜያት ‹‹በየነ ጴጥሮስን መርጣችሁ ምን አገኛችሁ? እሱ ያመጣውን እርዳታ ብሉ›› እያሉ ይዘባበቱባቸው

ነበር። ይሄ እውነታ እንጂ ከምርጫ መሸነፍና ማሸነፍ ጋር የሚያያዝ አይደለም።

ለምሳሌ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ወደሃድያ አካባቢ፤ ሆሳዕና ድረስ ስንት ጊዜ ሄዱ? ድሮ የትኛው ቦታ ሄደው ያውቁ

ነበር? ጨርሶ ታይተው አይታወቁም። በምርጫ ስለተሸነፉ ግን ተመላለሱ። በተወሰነ መንገድ ተሳክቶላቸዋል። የህዝቡን

ልብ ግን መቼም አያገኙትም። ሰዉ በተወሰነ መልኩ ዲፕሎማት ሆኗል። በቀጥታ መቃወም ትቷል። እኔ ብሄድ ግን

‹‹ሆ›› ብሎ እንደሚቀበለኝ አውቃለሁ። የገለፅኳቸው ነገሮች ሁሉ ያሉና የማምንባቸው ናቸው።

ቢቢሲ ላይ የእናንተ ሀሳብ (ክስ) መስተናገዱን ማጣጣል ላይ መሰረት ያደረገ ‹‹ዶክመንተሪ›› ፊልም ባለፈው እሁድ ምሽት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን

ቀርቧል። እንደተመለከቱት ነግረውኛልና በዚህ ዙሪያ ምን ይላሉ? አዘጋጁ በእርስዎ የትውልድ መንደር ባደዋቾ ድረስ ሄዶ…

እኔ የተናገርኩት በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የተደበቀ ረሃብ እንጂ ስለተወለድኩበት አካባቢ የተለየ ሁኔታ

ያነሳሁት ነገር የለም። እንዳለኝ መረጃም ከሆነ የቢቢሲ ዘጋቢዎች እኔ የተወለድኩበት አካባቢም አልሄዱም። እነሱ

በጠቋሚዎቻቸው አማካኝነት ማየት የፈለጉት ኢትዮጵያ ውስጥ የተደበቀ ረሃብ እንዳለ፣ ርዳታ የፖለቲካ አንድምታ

ስላለው በፍትሃዊነት እንደማይዳረስ መረጃ ይዘው ነው የመጡት።

ያወራነው ዋሻ ውስጥ ሳይሆን የሚታወቅ ሆቴል ውስጥ ነው። የአቶ ቢኒያም (የዶክመንተሪው አዘጋጅ እና ኢትዮጵያ

ፈርስት ድረ-ገጽ ኤዲተር) አካሄድ ነገር ፍለጋ እንጂ የሚገናኝም ነገር የለውም፤ ‹‹ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ›› ዓይነት

ነው። እኔ በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ነገር እያወራሁ እኔ አካባቢ መሄድ ምን ማለት ነው? የእሱን (የቢኒያምን) ጥበት

ነው የሚያሳየው። የፈለገው እኔን በአካባቢዬ ብቻ ሊገድበኝ ነው። [ሳቅ እያሉ] የእኔ የመረጃ ምንጮች በመላው ኢትዮጵያ

ይገኛሉ። ኃላፊነቴም በዚያው ያህል ነው።

እንደዚህ ዓይነት ነገር ውስጥ የሚገባው ቅጥረኛ ሰው ነው። እውነት እና ሀቅ ፈላጊ ቢሆን ‹‹አንተ የምርጫ ጣቢያ

(የትውልድ አካባቢ) እየሄድኩ ስለሆነ የማናግራቸውን ሰዎች ስጠኝ›› ማለት ነበረበት። ቢቢሲ ቢያናድደውም ስለ ቢቢሲ

የሚታመን የመረጃ አካል መሆንና/አለመሆን እሱ ክሬዲት የመስጠት አቅም ያለው አይመስለኝም። ‹‹የአገራችንን ስም

አጎደፉ›› የሚል ‹‹አርበኛ ነኝ›› ባይ ነው። ምክንያታዊ ሆኖ ‹‹አርበኛ›› ቢሆን እኔ ችግር የለብኝም። ‹‹ጋዜጠኛ (መረጃ

ሰብሳቢ ነኝ)›› ካለ አካሄዱ ጤናማ/ሚዛናዊ አልነበረም። የሄደው ለአንድ ወገን የሚሆን መረጃ ይዞ ለመምጣት ብቻ ነው።

ነገር የማይገባው የዋህ ነው።

ያነጋገራቸው ሰዎች የኢህአዴግ ጥቅም ተካፋዮች ይሆናሉ ብሎ ሳይጠረጥር ቀርቶ ነው? ያነጋገራቸው በአጋጣሚ ደርሶ

ያገኛቸውን ሰዎች ናቸው? [እየሳቁ] አይደለም። የማውቀው የወረዳ ሊቀ-መንበር የቆመበት መሀከል ነው ሲያዋራቸው

የነበረው። እናስ ‹‹ረሃብ፣ ችግር፣ አድሎ አለ›› እንዲሉ ይጠብቃል?

የእርስዎ አጎት ሚስት በግብዓትነት ቀርበው ክስዎ ውሸት መሆኑን ‹‹መንግስት ለተቃዋሚ/ለደጋፊ ብሎ ለያይቶ እርዳታ እንደማያከፋፍል ተናግረዋል።

ይህስ ማረጋገጫ መሆን አይችልም?

በ ገፅ 23

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 184 ቅዳሜ ጳጉሜ 5/ 2003

መልካም ዓዲስ ዓመት

በናፍቆት ዮሴፍ

የዘመን መለወጫ

( እ ን ቁ ጣ ጣ ሽ )

በ ሀ ገ ራ ች ን

ከሚከበሩ ሀገራዊና

ሀ ይ ማ ኖ ታ ዊ

በዓላት አንዱ

ከመሆኑም ሌላ

ከሌሎች በዓላት

የሚለይበት በርካታ ገጽታዎች

አሉት።

አሮጌው አልፎ አዲስ ዓመት

ሲተካ ብዙዎች የአዲስነት

ስሜት የሚላበሱበት፤ በአሮጌው

አመት ያላሳኩትን ለመከወን

የሚያቅዱበት፤ ሱሰኞች ከሱስ

ነፃ ለመውጣት፣ ብቸኞች በጋብቻ

ለመጣመር፣ ሌሎች ለመማር

(ከስህተትም ሆነ የቀለም

ትምህርት) የሚያቅዱበት፤

በአጠቃላይ ብሩህ ተስፋ

የሚሰነቅበት በዓል ነው።

በበዓሉ መቃረቢያ ልጃገረዶች

‹‹እንቁጣጣሽ እንኳን መጣሽ››

እያሉ ሲጨፍሩ ልጅነት

የሚታወስበትም ነው - የዘመን

መለወጫ። ከዚያም አልፎ በዓመት

አንድ ጊዜ ብቻ የሚበቅለው ደማቅ

ቢጫ አደይ አበባ የሚታይበትም

ስለሆነ በዓሉ ልዩ ስሜትን

ያላብሳል።

‹‹እንቁጣጣሽ›› ማለት?

በዓሉ ሁለት መጠሪያዎች

እንዳሉት - ‹‹እንቁጣጣሽ›› እና

‹‹ቅዱስ ዮሀንስ››። በዚህ ፅሁፍ

በዓሉ ለምን ቅዱስ ዮሀንስና

እንቁጣጣሽ እንደተባለና ታሪካዊ

ዳራውን ለማስቃኘት ወደናል።

ቅዱስ ዩሀንስ

ሀመር መፅሄት በመስከረም

1996 ዓ.ም እትሙ፣ የአይሁድ

ንጉስ የነበረው ንጉስ ሄሮድስ

የወንድሙ የፊልጶስ ሚስት

የሆነችውንና ‹‹ሄሮዲያደን››

የተባለችውን ሴት ባገባ ጊዜ

መጥምቁ ዮሀንስ ‹‹የወንድምህ

ሚስት ለአንተ እንድትሆን

አልተፈቀደም›› ብሎ በማስተማሩ

ጳጉሜ አንድ ቀን ታስሮ መስከረም

ሁለት ቀን አንገቱ በሰይፍ ተቀልቶ

ሞተ። ይህ ቅዱስ የህግ አዲስ

ካህን፣ ነቢይና ሐዋሪያ በመሆኑ

መታሰቢያው የአዲስ ዘመን

መባቻ ተደርጎ በእስክንድሪያና

በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር

በዓላት የሚከበሩበት፣ እንዲሁም

አፅዋማት የሚገቡበት ተደርጎ

መወሰዱን፣ እናም ቀኑም በስሙ

ቅዱስ ዮሀንስ ተብሎ መሰየሙን

ይገልፃል። ዘመኑም በዚሁ እለት

ይታደሳል፣ ይለወጣል።

መፅሄቱ ሁለት ዮሐንሶች እንዳሉ

ይገልፃል፡- መጥምቀ መለኮት

ቅዱስ ዮሐንስ እና ሐዋሪያውና

ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሀንስ። ዘመኑ

የተሰየመው አራተኛውን ወንጌል

በፃፈው በዮሀንስ ወልደ-ነጎድጓድ

ሲሆን፣ ቃለ-ነቢይ ልዑል ዮሀንስ

መስከረም አንድ ቀን በ1979 ዓ.ም

ለኢትዮጵያ ሬዲዮ የሰጡትን ቃለ-

ምልልስ ጠቅሶ ዘግቧል።

መፅሄቱ፣ ዘመኑ በስሙ

ስለተሰየመለት ቅዱስ ዮሀንስ

ሌላም ተጨማሪ መረጃ

አጣቅሷል።

‹‹ዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ

የመሸጋገሪያው ዕለት በየአመቱ

ቅዱስ ዮሀንስ እየተባለ ይጠራል።

ይህም የነቢዩ የዘካሪያስ ልጅ

መጥምቁ ዮሀንስ ነው፡፡ በዘመነ-

ብሉይ መጨረሻና በዘመነ

ሀዲስ መጀመሪያ ላይ ተነስቶ

‹መንግስተ-ሰማያት ቀርባለችና

ንስሀ ግቡ› እያለ ስለክርስቶስ

አዳኝነት ስላስተማረ በየአመቱ

የዘመን መጀመሪያ በእርሱ ሥም

እንዲጠራ ተደርጓል›› ሲሉ ቀሊኃ

ልሳኑ በዛብህ ‹‹ልሳነ-ተዋህዶ ዘ

ኦርቶዶክስ” በተሰኘ፣ በ1987

ዓ.ም በቁጥር ሰባት መፅሀፍ

መፃፋቸውን ያትታል።

ልዩ ቅኝት

እንቁጣጣሽ

Vs

ቅዱስ ዮሐንስ

‹‹እንቁጣጣሽ››

አንዳንዶች ስለ እንቁጣጣሽ በቃል

የተነገረ አንጂ በፅሁፍ የሰፈረ ነገር

አንደሌለ ሲናገሩ፣ ሌሎች ደግሞ

የተጻፈ ታሪካዊ ዳራ እንዳለው

ይከራከራሉ። ሆኖም ከዘመን

ዘመን ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ

ከግዕዝ የተወሰደ ቃል አንደሆነ

መዛግብት ያስረዳሉ። ‹‹እንቁ›

የግዕዝ ቃል ሆኖ ለነጠላ ቁጥር

የሚያገለግል ሲሆን፣ ‹‹አዕናቁ››

የሚለው ለብዙ ቁጥር ያለግላል።

‹‹ጣጣሽ›› የሚለው ‹‹ፃዕፃዕ››

ከሚለው የግዕዝ ቃል የተወረሰ

እንደሆነና የአማርኛ ትርጓሜውም

ጣጣ፣ መባዕ፣ ግብር፣ መፍቀድ፣

ገፀ-በረከት (በረከተ-ገፅ) ማለት

አንደሆነ ከላይ በገለፅነው ዓ.ም

ለንባብ የበቃው ሀመር የተባለው

መንፈሳዊ መፅሄት መረጃዎችን

ጠቅሶ አስፍሯል። በአጠቃላይ

እንቁጣጣሽ ማለት የእንቁጣጣሽ

ግብር፣ የእንቁጣጣሽ ገፀ-በረከት

ማለት እንደሆነ የታሪክ ድርሳናት

ያስረዳሉ። በመፅሀፍ ብሉያትም

ቢሆን ለመባዕ የሚገባውን ግብር

‹‹ፃዕፃዕ›› ይሉት እንደነበር ነው

መረጃዎች የሚጠቁሙት።

መነን መፅሄት በ1965 ዓ.ም

‹‹እንቁጣጣሽ ምንድን ነው›› በሚል

ርዕስ እንዳስነበበው፣ በሀገራችን

ለመጀመሪያ ጊዜ እንቁጣጣሽ (ገፀ-

በረከት) የተበረከተው ለቀዳማዊ

ምኒልክ እናት ለንግስት ማክዳ

እንደነበርና ንግስቲቱ ምኒልክን

በወለደች ጊዜ ህዝቡ ንጉስ

ተወለደ ብሎ እልል በማለት

የአበባ እንቁጣጣሽ ለንግስት ማክዳ

አበረከተ።

ታዲያ እንቁጣጣሽ የተባለው

በመጀመሪያ ለንግስቲቱ ስለተበረከተ

እንጂ ለንጉሱ ተበርክቶ ቢሆን

ኖሮ ‹‹ዕንቁ ፃፃሁ›› ይባል ነበር።

ከዚህም በተጨማሪ ንጉስ ሰለሞን

ከደስታው ብዛት ለንግስቲቱ

ለጣትሽ መታሰቢያ ይሁንሽ ሲል

የዕንቁ ቀለበት ሰጥቷት እንደነበር

ሊቃውንት ያስረዳሉ።

በ1951 ዓ.ም ብርሀንና ሰላም

ጋዜጣ ላይ በዓሉን አስመልክቶ

‹‹ርዕሰ አውደ ዓመት›› በሚል ርዕስ

የሰፈረው ጽሁፍ ንግስት አዜብ

ለንጉስ ሰለሞን ‹‹ተንካራ›› የተሰኘ

እንቁ ወስዳ ገፀ-በረከት በሰጠችው

ጊዜ ‹‹እንቁጣጣሽ ይሁን›› ብሏት

እንደነበር ያስረዳል።

ጋዜጣው ጨምሮ እንደገለፀው፣

በኢትዮጵያ ስለ ሕግ የተሰበከው

በንግስት አዜብ በምኒልክ እናት

በመሆኑ ሲታሰብ እንደሚኖር፣

በዚህም ቀን የቅድስ ዮሀንስ

መጥምቅ በዓል እንደሚከበር ነው፡፡

ታዲያ የኢትዮጵያ ሴቶች ለምለም

ሳርና አበባ በእጃቸው ይዘው

በዓሉን የሚያከብሩት ለምለም

ሳርና አበባው በኖህ ጊዜ ‹‹ማየ

አይህ›› (የጥፋት ውሀ) መጉደሉን

ለማብሰር እርግብ በአፏ ቅጠል

ይዛ ታይታ ስለነበር ነው። ምንም

እንኳን ‹‹ማየ አይህ›› የጥፋት

ቢሆንም፣ ክረምት አለፈ የሚለውን

ሀሳብ እንደሚወክል ብርሀንና

ሰላም ጋዜጣ ከላይ በገለፅነው ዓ.ም

እትሙ አስፍሮታል።

በሌላ በኩል ስለ ዘመን መለወጫ

(እንቁጣጣሽ በዓል) አለቃ አያሌው

ታምሩ በ1953 ዓ.ም ባሳተሙት

‹‹የኢትዮጵያ እምነት በሶስቱ

ህግጋት›› በተሰኘው መፅሀፋቸው

የዘመን መለወጫ በሶስት መንገድ

መታወቁን አስፍረዋል። አንደኛ፣

እስራኤላውያን በብሉይ ኪዳን

ያከብሩት የነበረው ሚያዚያ 1

ቀን፤ ሁለተኛ፣ የአለም ክርስቲያን

የክርስቶስን ልደት ተቀዳሚ

በማድረግ የሚያከብሩት ጥር 1

ቀን፤ ሶስተኛ፣ ኢትዮጵያ ከጥንት

መሠረት አውቃ የምታከብረው

መስከረም 1 ቀን ናቸው።

እስራኤላውያን የዘመን መለወጫ

በአልን ሚያዚያ 1 ቀን ማድረጋቸው

በዚሁ ወር ከግብፅ ባርነት ነፃ

በመውጣተቸው፣ እንዲሁም

እግዚአብሔር ይህንን የነፃነት በአል

በየአመቱ እዲያከብሩ ስላዘዛቸውና

የአለም ክርስቲያን ጥር 1 ቀን

ማክበራቸው የክርስቶስን ልደት

ምክንያት በማድረግ መሆኑ ግልፅ

ነው፡፡ የኢትዮጵያ መስከረም 1 ቀን

አውድ አመት (ዘመን መለወጫ)

ስላደረገችበት ጥቂት እንበል።

ኢትዮጵያ ይህንን በዓል

የተቀበለችው ከ‹‹ካም›› ነው፡

፡ የተጀመረበትም ካም እና ልጁ

ኩሣ ወደ ኢትዮጵያ የገቡበትና

አኩስም (አክሱም) በኩሳ ስም

የተመሰረተችበት ጊዜ ነው።

ዘመኑም በኢትዮጵያ ከ4900

ዓመት በላይ ሲሆን፣ ጊዜውም

ከጥፋት ውሀ በኋላ መሆኑን

የአለቃ አያሌው መጽሀፍ ያስረዳል፡

ስለ ዘመን መለወጫ ስያሜዎች

ማለትም ስለ ቅዱስ ዮሀንስና

እንቁጣጣሽ አለቃ አያሌው

ታምሩ በ2001 ዓ.ም ባሳተሙት

‹‹ትምህርተ-ሀይማኖት›› በተሰኘ

መጽሐፋቸው ‹‹እንቁጣጣሽ››

የሚለው ቃል ከግብር፣ ከመባዕ፣

ከገፀ-በረከት ጋር የተቆራኘ ትርጓሜ

በየዘመኑ የመጡ ምሁራን

ያመጡት እንጂ እውነታው ወዲህ

ነው ይላሉ። ይሁን እንጂ ‹‹ቅዱስ

ዮሀንስ›› ስለተባለው የዘመን

መለወጫ ስያሜ እላይ ከሰፈረው

ጋር ብዙ የሚያመሳስለው ነገር

አለ።

‹‹ቅዱስ ዮሀንስ› አለቃ

አያሌው እንደገለፁት

አለቃ አያሌው ታምሩ ዘመኑ

በአራቱ ወንጌላውያን የተሰየመ

ነው ይላሉ። የዘመን መለወጫው

‹‹ቅዱስ ዮሐንስ›› የሚባልበትንም

ምክንያት ሲያስረዱ፣ ወንጌልን

የሚቀበሉ ሁሉ በአራቱ

ወንጌላዊያን (በዩሀንስ፣ በማቲዎስ፣

በማርቆስና በሉቃስ) የዘመን ቁጥር

መስመራቸውን እንደሚያሳርፉ

ገልጸው፣ ኢትዮጵያ ዘመን

መለወጫን ‹‹ቅዱስ ዮሃንስ››

የምትልበት ሁለት ዋና ዋና

ምክንያቶች አንዳሏት ያብራራሉ፡

፡ አንደኛ፣ ቅዱስ ዮሀንስ ወንጌላዊ

ወንጌሉን የጀመረው በዜና

ፍጥረት መሆኑን እንደሚከተለው

ገልጾታል፡-

‹‹ቃል ቀዳማዊ፣ ቃል

በእግዚአብሔር ዘንድ ነበር።

እግዚአብሔር ቃል ነበር፣ እርሱ

በእግዚአብሔር ዘንድ ነበር። ሁሉ

በእርሱ ሆነ›› ብሎ ሙሴ ‹‹ቀዳማዊ

ገብረእግዛብሔር ሰማየ ወምድረ

(እግዚአብሔር መጀመሪያ ሰማይና

ምድርን ፈጠረ ሲል በቀዳማዊ

ቃሉ በኢየሱስ ክርስቶስ አለሙን

መፍጠሩን ያስረዳ በመሆኑና

ቅዱስ ዮሀንስም የወንጌልን

ትምህርት ከሙሴ ስብከት ጋር፣

የወንጌልን ፅህፈት ከሙሴ አፃፃፍ

ጋር እንዲሁም የወንጌልን ጥንት

ከሙሴ አነሳስ ጋር በማስተባበር

(ቃል ቀዳማዊ ነው) ሁሉ በእርሱ

ሆነ) በማለት ስላጠናቀቀው፣

ቤተክርስቲያንም በቅዱስ ዮሀንስ

ወንጌል መሠረት እለቱን ‹‹ቅዱስ

ዮሀንስ›› ብላ ትጠራለች” ካሉ

በኋላ በተጨማሪም በቁጥር

ስርአት አንድ ጊዜ ወደ ፊት

አንድ ጊዜ ወደኋላ ነው ብለን

ካመንን ዘንድ ወደኋላ ተመልሰን

አሁን ባለው በአራቱ ወንጌላውያን

መስፈሪያ ያለውን ዘመን ስንለካ

ስነ-ፍጥረት ጥንተ-ፍጥረት በዘመነ

ዮሀንስ ሆኖ ይገኛል። እናም ከቃሉ

አፃፃፍ ጋር ተስማምቶ ስላገኘችው

ቤተ-ክርስቲያን ቅዱስ ዮሀንስ ብላ

ትጠራለች።

ሁለተኛው ደግሞ ‹‹ወንጌላውያን

ሁሉ የተባበሩት በቅዱስ ዮሀንስ

መጥምቅ ዜና ነው። ወንጌላውያን

ሁሉ ወንጌልን የጀመሩት በቅዱስ

ዮሀንስ ስብከት ነው፡፡ ይህም

ማቴዎስ ምዕራፍ 3፣ ማርቆስ

መዕራፍ1፣ ሉቃስ ምዕራፍ 3፣

ቅዱስ ዮሀንስ በምዕራፍ 1 ሁሉም

ለወንጌል ትምህርት መሠረት

መግቢያ ያደረጉት የቅዱስ ዮሀንስን

መጥምቅ ትምህርት ነው›› ሲሉ

አስፍረዋል።

አለቃ አያሌው በመፅሀፋቸው

‹‹ከዚህም ጋር ቅዱስ ዮሀንስ

በንጉስ ሄሮድስ ትዕዛዝ ጳጉሜ

1 ቀን ታስሮ መስከረም 2 ቀን

በሰማዕትነት ሞቷል›› ሲሉ

አስፍረዋል።

እንቁጣጣሽ በአለቃ አያሌው ገለፃ

አለቃ አያሌው የእንቁጣጣሽን

ትርጉሜ በተመለከተ እዳሰፈሩት

የቃሉ ትርጓሜና ታሪኩ ከምድርና

ከኢትዮጵያ አመሰራረት ጋር

የተያያዘ እንደሆነ ገልፀው

‹‹እግዚአብሄር ፍጥረትን መፍጠር

በጀመረ በሶስተኛው ቀን ‹ምድር

ሳርም ቡቃያም ታውጣ›› ብሎ

ሲናገር ሰማዩን በከዋክብት

ከማስጌጡ አስቀድሞ ምድርን

በአበባ አስጊጧል›› ሲሉ በመፅሀፉ

ያሰፈሩት ሲሆን በዚህም ምክንያት

“ምድር ተንቆጠቆጠች ማለት

እንቁጣጣሽ መሰለች፣ አበበች፣

ለመለመች አጌጠች ለማለት

ነው። እንቁጣጣሽ የሚባለው

በአሁኑ ጊዜ በየአመቱ መጀመሪያ

ላይ ከሌሎች አበቦች አስቀድሞ

የሚታየው በአማርኛ ቋንቋ ‹‹አደይ

አበባ›› የተባለው ቢጫ አበባ ነው።

ይሄ ነው እንቁጣጣሽ ያሰኘው”

ሲሉ በትምህርተ-ሃይማኖት

መጽሃፋቸው ላይ አስፍረውታል።

አለቃ አያሌው እንደፃፉት፣

ስለእንቁጣጣሽ ተራኪዎች የተለያየ

ቋንቋ እንደሰጡት ጠቁመው

በተለይም ‹‹የሠለሞንን ዘር

መመኪያ እናደርጋለን የሚሉ

ተራኪዎች›› ያሏቸው ንጉስ

ሰለሞን ከንግስት ሳባ ጋር በተገናኘ

ጊዜ ስለክብሯ አንቁጣጣሽ ብሎ

የዕንቁ ቀለበት ሰጥቷት ነበር።

ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ነው እንቁጣጣሽ

የተባለው” ብለው ይተርካሉ። ግን

“ትክክለኛ ታሪክ አይደለም›› ሲሉ

ያጣጥሉታል፡፡

የሆነ ሆኖ እንደ ግዕዙ ቃል

እንቁጣጣሽ ‹‹ጣጣ›› ከሚለው ቃል

መጥቶ ግብር፣ ገፀ-በረከት፣ ጣጣ

የሚለውን ትርጉሜ አግኝቶም

ከሆነ በአሉ በርካታ ግብርን

(ወጪን) የሚጠይቅ በመሆኑ

ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡

› እንደአለቃ አያሌው ገለፃ ምድር

ለመለመች፣ አጌጠች፣ አበበች

ማለትም ከሆነ ለሀገራችን አሜን

ያድርግለን፡፡ ስለዘመን መለወጫ

ካነሳን አይቀር በዚሁ አጋጣሚ ስለ

ጳጉሜም ትንሽ እንበል።

ይህቺ የሀገራችን 13ኛ ወር

(ጳጉሜ) ትርጓሜዋ ‹‹ጭማሪ››

ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ጭማሪ

ወጪም ትሆናለችና ልብ ልንላት

ይገባል፤ ዘንድሮ ደግሞ ስድስት

ቀን ሆና ትውላለችና።

መልካም ቅዱስ ዮሀንስ! መልካም

የእንቁጣጣሽ በዓል!

21

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

22

በኤልያስ ገብሩ

በአዲስ

elias.gebru32@gmail.com

ዓመት አዲስ መንፈስ

ኢትዮጵያኖች የፊታችን

ሰኞ አዲስ ዓመትን

የ ም ን ጀ ም ር በ ት

ዕለት ነው። አዲስ

ዓመት ብዙዎቻችን

አዲስ እንዲሆንልን

እ ና ስ ባ ለ ን ፣

እንመኛለን። በአዲስ ዓመት ለውጥ

ለማየትና ስኬትን ለመቀዳጀት ዕቅድ

ነድፈውና ለራሳቸው ቃል ገብተው በአዲስ

የመንፈስ ሀይል ለመንቀሳቀስ የሚሹና

እንዳሰቡትም የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችና

አካሎች መኖራቸው እሙን ነው። በአንፃሩ

ደግሞ፣ አዲስ ዓመት ስለመጣ ብቻ አዲስ

ነገር ማድረግ እንዳለባቸው በማሰብ

ስሜታዊ ሃሳብ ላይ በመመርኮዝ እርጋታ

የጎደለው ስሜታዊ ዕቅድን ይነድፋሉ።

እነዚህም በአዲሱ ዓመት ብዙም

ሳይጓዙ ከእቅዳቸው ውጪ እንደሚሆኑ

አያጠራጥርም። ለማንኛውም…… አዲስ

ዓመት እንዴት ነው የምናከብረው?

እንዲሁ በቀላሉ እቤት ውስጥ በመቀመጥ

እና ዓመቱን አቅልሎ በመመልከት? ብዙ

ሕዝብ በዓሉን ለማክበር በተሰበሰበበት

ቦታ በመገኘት ወይስ ወዳልለመድነው ቦታ

በመጓዝ? የበዓሉስ አከባበር የጠበቅነውን

ያህል ይሆንልን ይሆን?

ጠቃሚ ነገሮች ላይ

የፀባይ ውሳኔዎች ላይ ነው። በሕይወት

ውስጥ የሚገኙ የፀባይ ውሳኔዎች የሰዎችን

ስኬት ይወስኑታል። የሚፈልጉትን

ወይም ማድረግ የሚሹትን ለማሟላት

ሰዎች ለራሳቸው ሕይወት ተጠያቂዎች

መሆናቸው ይገለፃል።

የተለየ ነገር ምን

እናድርግ?

የቢዝነስ ባለቤቶች፣ የድርጅት ማናጀሮች

ወይም አስፈፃሚዎች የራሳቸውን የሥራ

ዕቅድ የማስፈፀም ኃላፊነት እንዳለባቸው

ሁሉ ሠራተኞቻቸውም የሚጠበቅባቸውን

ነገሮች ማሳካት እንዲችሉ የመደገፍ

ኃላፊነት ሊኖራቸው ይገባል፡፡

በአሜሪካ ሀገር በአዲስ ዓመት መግቢያ

ሰሞን በአንድ ትምህርት ቤት መግቢያ

በር ላይ እንዲህ የሚል መርህ ቃል

ተፅፎ በትልቁ ተለጥፏል፡- ‹‹High

Expectation = High Achievement››

(ከፍተኛ ግምት = ከፍተኛ ውጤት)፡፡

በዚህም በአካባቢው ለሚገኙ መምህራን

እንዲደርስ ታስቦ መዘጋጀቱን የሚገልፀው

መረጃው፣ መምህራኖች ከተማሪዎቻቸው

ከፍተኛ ውጤት የሚጠብቁ ከሆነ እነሱም

ከራሳቸው የሚጠብቁት ነገር ከፍ ያለ

ይሆናል። መምህራኖች ከራሳቸው የላቀ

ነገር እንደሚጠበቅ ሲያስቡ ደግሞ

ተማሪዎቻቸውን በዕውቀትና በሥነ-ምግባር

ሊያሳድግ የሚችል ጥራት ያለው ትምህርት

ለመስጠት ያስችላቸዋል፡፡ ይኼንንም

ተከትሎ ተማሪዎች የሚጠበቅባቸው

ደረጃ ላይ ይገኛሉ። ‹‹የቢዝነስ ባለቤቶች፣

የድርጅት ማናጀሮች ወይም አስፈፃሚዎች

ራሳቸውን እንደአስተማሪ፣ ሰራተኞቻቸውን

ደግሞ እንደተማሪ ሊያስቧቸው ይገባል።››

በማለት በአሜሪካን ሀገር የወጣ አንድ

መረጃ ዘግቧል፡፡

አዲስ ዓመት በመጣ ቁጥር አዲስ

የባህሪ ውሳኔ ለማድረግ ከፍተኛ እድልን

ይፈጥራል። ሽግግሩ ሥነ-አዕምሯዊ

ለውጥን ለማድረግ በጣም ቀላል

የሚያደርግ ሲሆን፣ ሰብኮንሺየስ የሆነው

የሠው የአንጎል ክፍል አዲሱን ውሳኔ

በቀላሉ ይቀበላል። ምን አይነት አዲስ

የፀባይ ለውጥ ውሳኔ ማድረግ አለብን?

በዋነኝነት እርስ በእርስ በመተባበር ትስስር

እና ቁርኝትን መፍጠር ነው። ለምሳሌ፣

በቢዝነስ ሥራ ውስጥ የሚጠበቀውን

ውስጣዊና ውጫዊ ስኬቶችን ለመጎናፀፍ

አዲስ የፀባይ ለውጥ ውሳኔ ለማድረግ

ሚናው የጎላ ነው። እንዲሁም አንድ

ሰው በውስጡና ከእሱ ውጪ እንዲሆኑ

የሚጠብቃቸው ነገሮች እንዲለወጡ ድጋፍ

ይሰጣል። በቢዝነስ ዓለምም አንድ ድርጅት

በአዲስ ዓመት ከእሱ ውጭ ካሉ ሸሪኮች

ጋር ለውጤት የሚያበቃ ስትራቴጂን

በመንደፍ ሕብረት መፍጠር አለበት፡

፡ ቅድሚያ ግን፣ ለካምፓኒው/ ለድርጅቱ

ስኬት አጋር መሆን የሚችሉ ሸሪኮችን

መምረጥ ተገቢ ነው።

የድርጅቱን ምርጥ

ታሪክ መምረጥ

በካምፓኒው ወይንም በድርጅቱ ውስጥ

ስላለው መልካም ነገር ሰራተኞች አዎንታዊ

አመለካከትን ይዘው የባለቤትነት ስሜት

እንዲሰማቸው አዲስ ስትራቴጂን መንደፍ

ወሳኝነት እንዳለው መረጃዎች ያስረዳሉ።

የድርጅት ባለቤቶች ወይንም የተቋም

ኃላፊዎች ደግሞ ለሥራቸው እድገት

ዕውቀትና ጥበብን ያማከለ ኃላፊነትንና

የተጠና ሪስክን ሊወስዱ ይገባቸዋል።

ሰራተኞች ከድርጅቱ ራዕይ ጋር ራሳቸውን

ማስማማት እንዲችሉ የድርጅቱን ያለፈ

ታሪክ እንዲያውቁ ማድረግ ብልህነት

ነው፡፡ በድርጅቱ ታሪክ ውስጥም ጥሩ

የሚባለውን መርጦ በመለየት በሰራተኞቹ

እንዲደገም ደጋግሞ መናገር የባለቤቶች

ወይም የኃላፊዎች ድርሻ ሲሆን

ሰራተኞችም በዚህ ተገቢውን የፀባይ ለውጥ

ውሳኔ እንዲያመጡ ማድረግ ያስፈልጋል።

ትኩረት ማድረግ

በአዲስ ዓመት ከግዢ ጋር ለተገናኙ

የተለያዩ ነገሮች ይበልጥ ትኩረት ሰጥቶ

ከማክበር ይልቅ በአዲስ ዓመት ለራስና

ከራስ ውጪ ትልቅ ለውጥ ሊያመጡ

በሚችሉ ቅድመ-ዕቅዶች ላይ የላቀ ትኩረት

የኢትዮጵያዊያን ሰቆቃ...

መስጠቱ በጣም ጠቀሜታ እንዳለው

መረጃዎች ያስረዳሉ። ለምሳሌ በብዙ

የአዲስ ዓመት ወቅቶች ላይ፣ ሁሌም

ለማለት በሚያስችል መልኩ በርካታ

ሕፃናት ልጆች፣ ታዳጊዎችና ወጣቶች

ከቤተሰቦቻቸው አዳዲስ አልባሳትና

ጫማዎች ተገዝተው እንዲበረከትላቸው

ይፈልጋሉ፣ ይጠብቃሉም። ብዙዎች

እንዳሰቡት ሆኖ ሊያገኙት ይችላሉ። ነገር

ግን፣ በአጋጣሚም ይሁን በሌላ [ቤተሰብ

በብር እጥረት ምክንያት መግዛት ካልቻለ]

በየዓመቱ ለልጆች ያስለመዳቸውን ነገር

በሚያስቀርበት ጊዜ አዳዲስ አልባሳትና

ጫማዎችን ይጠብቁ የነበሩ ሕፃናት፣

ታዳጊና ወጣት ልጆች ራሳቸውን

ከጓደኞቻቸው/ ከጎረቤት ልጆች ጋር

በማነፃፀር መከፋታቸውና መበሳጨታቸው

አይቀሩ ነው፡- የቤተሰብን ችግር በበቂ

ምክንያት ካለተረዱት በስተቀር።

አለበለዚያ ያ የአዲስ ዓመት ትውስታ

ሁሌም በአዕምሯቸው ውስጥ ተቀምጦ

ይረብሻቸዋል። በአሉታዊ መንገድ

የተቀረፀው ትዝታ ልጆቹን ማንቀሳቀስ

ካልቻለ ደግሞ ትዝታው አሁንም ድረስ

በውስጣቸው መኖሩን ጠቋሚ ምልክት ነው።

ይኼ ከላይ ልጆችን መሠረት በማድረግ

የተጠቀሰው ምሳሌ በአዋቂ ሰዎች፣

በድርጅቶች፣ በአካባቢዎችና በዝግጅቶች

ላይ የሚሰራ መሆኑ ይገለፃል። በአዲስ

ዓመት የሆነ ነገር እንደሚደረግላቸው

የሚጠብቁ ሰዎችም ሆኑ ድርጅቶች

የሚጠብቁት ነገር ካልተደረገላቸው በቀላሉ

ስሜታቸው ሊነካ፣ የመስራት አቅማቸው

ሊቀንስ፣ ብሎም ለውድቀት ሊዳረጉ

እንደሚችሉ በጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረጉ

ምሁራን ያስረዳሉ። የሚጠበቀው ነገር

አንዳንዴ እውነት ላይሆን እንደሚችልም

ጠቁመዋል። በአጠቃላይ ሕፃናት፣

አዋቂዎች፣ ድርጅቶች…አዲስ ዓመት

በመጣ ቁጥር የሆነ ጥቅም ነክ-ነገር ከሰዎች

ወይም ከሌላ አካል እንዲደረግላቸው

አብዝቶ ከመፈለግ ይልቅ በሕይወታቸው

ላይ በመሰረታዊ ሁኔታ ትልቅ ሊያመጡ

በሚችሉ እውነተኛ ዕቅዶች ላይ ትኩረት

ማድረግ እንደሚገባቸው አፅንዎት

ሰጥተውታል፡- የዘርፉ ተመራማሪዎች።

ያልተሟላ የፍላጎት ስሜታችንን

ወደ ውስጣችን እንዲገባ ከፈቀድንለት

ሕይወታችንን ውስብስብ የማድረግ አቅም

አለው። ፍላጎታችን ካልሟላ ሕይወት

ይበልጥ አስቸጋሪ ትሆናለች። ከእኛነታችን

ውጪ የምንጠብቀው ነገር በተለያየ

መልኩ ይመጣል። በገንዘብና በቢዝነስ፣

በሥራ፣ በትምህርት፣ በፍቅርና በትዳር

ሕይወት፣ በመንፈሳዊ ሕይወት …

እነዚህን ነገሮች ለማግኘት የቁጥጥር ስራ

ወሳኝ ነው። ይኼንን መስራት ካልተቻለ

ደግሞ ብዙ ኃይልን ውጤት በማያመጣ

ነገር ላይ ማዋሉ ተገቢ አለመሆኑን

በዘርፉ የምርምር ጥናት ያደረጉ ምሁራን

ይናገራሉ። ቁጥጥሩ የሚደረገው በሰዎች

የሥራ ጫና መቋቋም አቅቷቸው የሸሹ ኢትዮጵያውያን በድብቅ እንዳነጋገሩት

የሚያስታውሰው ነቢዩ፤ በሊባኖስ፣ በባሕሬን፣ በዱባይና አቡዳቢ ዜጎች በተመሳሳይ

ሁኔታ ለችግር ቢዳረጉም በመንግስት ተወካዮች ምንም ዓይነት የመብት ጥበቃ

እንዳልተደረገላቸው አረጋግጧል።

በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ሰቆቃ የተለያዩ መገናኛ ዘዴዎችን

በመጠቀም ይፋ በማድረጉ ‹‹መንግስት ሊሰራ ይገባ የነበረውን ሥራ እየከወነ ነው››

ተብሎ የሚሞካሸው ይህ ጋዜጠኛ በአካባቢው ያሉ ዲፕሎማቶች የኢትዮጵያውያንን

ጩኸት ሰምቶ ምላሽ ለመስጠት ለምን እንደከበዳቸው ጥያቄ ማቅረቡ አልቀረም።

ቀደም ሲል የጅዳ ቆንፅላ ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩት አምባሳደር ተክለአብ ከበደና

ሌሎች ሠራተኞች ሲሰጡት የቆየው መልስ ‹‹የበጀትና የሰው ኃየል ዕጥረት አለብን››

የሚል ነበር፡፡ ሆኖም ፕሬዝደንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ጅዳ በሄዱ ጊዜ ተመሳሳዩን

ጥያቄ አቅርቦላቸው ‹‹የበጀትና የሰው ኃይል እጥረት ስለመኖሩ ጥያቄ አልቀረበልንም፡

፡ ሲቀርብልን ምላሽ እንሰጥበታለን›› ማለታቸው ችግሩ የቅንጅትና የበሰለ አመራር

እጥረት እንደሆነ መመስከሩን ያስታውሳል።

‹‹አለ›› የተባለውን የገንዘብና የሰው ኃይል ዕጥረት ለመቅረፍ ከልብ ስላልታሰበበት

እንጂ የጅዳው ቆንፅላ ጽ/ቤት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ፓስፖርት በማደስና

የውክልና ወረቀት በመስጠት በሚያስገባው ከፍተኛ ገቢ ችግሩን ማቃለል

እንደሚቻልም መረጃዎች ይጠቁማሉ። በውጭ አገራት በተለይም በአረብ አገራት

የሚገኙ ዲፕሎማሲያዊ ሚሲዮኖች በስፍራው የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ችግር

ከመፍታት ይልቅ የኢህአዴግ ደጋፊ ዲያስፖራዎችን በማሰባሰቡ ላይ እንደሚያተኩሩ

የሚያስገነዝቡ ወቀሳዎች ሲቀርቡ ይስተዋላል።

ካለፈው አራት ዓመት ወዲህ በጅዳና አካባቢው ያሉ ኢትዮጵያውያንን እንዲያገለግሉ

ተመድበው በነበሩት አቶ ሙክታር መሐመድ ላይም ተመሳሳይ ትችት ተሰንዝሯል።

ምንም እንኳን የዲፕሎማቱ ዋና ተልዕኮ ለኢትዮጵያውያን አንገብጋቢ ጥያቄዎች

ምላሽ መስጠት ቢሆንም እሳቸው ግን ብሔር ተኮር ‹‹የልማት ማህበሮችን››

በማደራጀት ላይ ተጠምደው የሥራ ጊዜያቸውን እንዳገባደዱ ምንጮች ለአውራምባ

ታይምስ ገልፀዋል።

በየዕለቱ በርካታ ኢትዮጵያውያን በሚጎርፉባት የመን ያሉ ኢትዮጰያውያንም እዚያ

ያለው ኤምባሲ ጩኸታቸውን ለመስማት ፈቃደኛ አለመሆኑን ሲገልጹ ቆይተዋል።

በተለይም የዘመናት ብሶት የወለደው የዓረብ አብዮት በየመንም መቀጣጠሉን ተከትሎ

ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደነበሩ በአንድ ወቅት ግሩም ተ/ኃይማኖት

የተባሉ ስደተኛ አውራምባ ታይምስ ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ መግለፃቸው አይዘነጋም።

ምንም እንኳን የኢትዮጵያ መንግስት /የመን የሚገኘው ኤምባሲ/ ከ IOM ጋር

በመተባበር በየመን ሊቀሰቀስ በሚችለው ጦርነት ዜጎች እንዳይጎዱ ኢትዮጵያውያንን

ወደ ኢትዮጵያ ሲመልስ የነበረ ቢሆንም፣ ‹‹የመን ባለው ኤምባሲ አንተማመንም››

ያሉት ኢትዮጵያውያን በርካታ ናቸው።

ግፍ ተፈፅሞባቸው ወደ ኤምባሲው በመሄድ ጥያቄ የሚያቀርቡ ወገኖችን

‹‹እኛ ለገረድ አልመጣንም›› በሚል ዲፕሎማቶቹ ሲገፏቸው እንደነበር አቶ

ግሩም በፅሁፋቸው ከማስታወሳቸው ባሻገር፣ በመንግስትና በIOM አማካኝነት ወደ

ሐገራቸው የተመለሱትም ለአውራምባ ታይምስ ይህንኑ ተናግረዋል። በወቅቱ

ተመላሾቹ በሰው ሀገር ከደረሰባቸው ግፍና መከራ የተነሳ እንባ እየተናነቃቸው

‹‹ኤምባሲው ከሰውም አይቆጥረንም። እንደምንም ገንዘብ አግኝተን ስልክ ስንደውል

‹ጠግበህ ነው የመጣኸው፤ ይበልህ የራስህ ጉዳይ ነው› ይሉናል›› ሲሉ ነበር በአረብ

አገራት የሚገኙ ኤምባሲዎች ከኢትዮጵያውያን ጋር ሆድና ጀርባ መሆናቸውን

ያመለከቱት።

ከአውራምባ ታይምስ ጋር ቆይታ ያደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ ‹‹መቼም ኤምባሲዎች ውስጥ የሚሠሩት ሰዎች ናቸውና

ከኤምባሲዎች ፖሊሲ በተጻራሪ ስህተት መሥራታቸው አይቀርም›› በማለት

አቤቱታውን በከፊል ቢጋሩትም መንግስት በውጭ አገራት ለሚገኙ ዜጎች ከለላ

በማድረግ ላይ መሆኑን በመግለጽ በፅኑ ሞግተዋል፡፡

‹‹ልጆቻችን እና እህቶቻችን ላይ የሚደርስ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት አገራችንንም ሆነ

የሚመሩትን ሰዎች የሚያስከብር ካለመሆኑም በላይ የዲፕሎማቲክ እንቅስቃሴ

ውድቀት ማሳያ ነው›› የሚሉት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ‹‹ኤምባሲው ከመኖር

መዝለል አለበት›› ሲሉ ይወቅሳሉ።

ዲና ሙፍቲ በአቅም ውስንነት የተነሳ ኤምባሲ ባልተከፈተባቸው አገራት ያሉ

ዜጎች መብት ማስጠበቅ አዳጋች ነው ቢሉም በየነ በዚህ አይስማሙም። ‹‹ሁሉ አገር

ኤምባሲና ቆንስላ አይኖርም። በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና በሌሎች አገሮች

በኩል የቅርብ የጎንዮሽ ክትትል ያደርጋሉ›› ሲሉ የኤምባሲ እና ቆንስላ አለመኖር

ሁሌ እንደ ችግር መታየት እንደሌለበት ጠቁመዋል።

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

ጤ ና

አዲስ ዓመት በመጣ ቁጥር አዲስ የባህሪ ውሳኔ ለማድረግ ከፍተኛ እድልን ይፈጥራል። ሽግግሩ ሥነ-አዕምሯዊ ለውጥን

ለማድረግ በጣም ቀላል የሚያደርግ ሲሆን፣ ሰብኮንሺየስ የሆነው የሠው የአንጎል ክፍል አዲሱን ውሳኔ በቀላሉ ይቀበላል

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 184 ቅዳሜ ጳጉሜ 5/ 2003

መልካም ዓዲስ ዓመት

አንድን ድርጅት ስኬታማ ወደሆነ የሥራ

ባህል መውሰድ ጊዜ ስለሚጠይቅ በተቻለ

መጠን ትግስተኛ መሆን ይመከራል፡፡

ለዚህ ምን ማድረግ ያስፈልጋል?

ከአሮጌው ዓመት ራስን መነጠል

አንድ ድርጅት በአዲስ ዓመት ስኬታማ

ለመሆን የተሻሉ ሰራተኞችን መምረጥ

መቻል ወሳኝና ቁልፍ ተግባሩ ማድረግ

አለበት፡፡ አንድ የሥራ ኃላፊ ከራሱ

ጋር በውስጡ የሚነጋገረው ነገር በፀባይ

ለውጥ ውሳኔዎች ላይ ጫና የመፍጠር

አቅም አለው። ከእሱ በሚጠበቀው ነገር

ላይ ውጤታማ ለመሆን ኃላፊው ግለሰባዊ

ባህሪውን በመጀመሪያ መቆጣጠር አለበት።

በአካላዊ ሰውነቱ ላይ የኬሚካል ወይንም

የሆርሞኖች አለመመጣጠት ካልኖረ

በስተቀር ፀባዩን መቆጣጠር ይችላል።

ግለሰቡ የሥነ-አዕምሮ ችግር ካለ ደግሞ

የሕክምና ባለሙያ ጋር በመሄድ ሕክምና

መውሰድ እና ስላለበት ችግር በዙሪያው

ላሉት ሰዎችና የሥራ ባልደረቦቹ ማሳወቁ

መልካም መሆኑን መረጃዎች ያስረዳሉ።

በዚህ ወቅት ሰራተኞች ለኃላፊው በጣም

ቅን ሊያስቡለት፣ በቀላሉ ሊረዱትና እና

ትዕግስተኛ ሊሆኑለት የሚችሉበት ዕድል

ከፍተኛ ነው፡፡ … የሆነ ሆኖ፣ በተቻለ

መጠን ስላለፈው አሮጌ ዓመት ከማሰብ

መታቀብ ብልህነት መሆኑ ይገለፃል።

ስለዚህ ሰዎች ለስኬታማ ሥራቸውና

ሕይወታቸው ያላቸውን ሙሉ ኃይል

እና አቅም በአዲሱ ዓመት ላይ ማድረግ

እንደሚገባቸው በዘርፉ ጥናት ያደረጉ

ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡ ይኼም ማለት

ብዙ ጊዜን ለእውነተኛ ዕቅድ በመስጠት

ስኬት ላይ ማነጣጠር ሲሆን ባለፈ ጊዜ

ውድቀት እና ስኬት አልባነት ላይ እያሰቡ

ጊዜ ማባከኑ ዋጋ የለውም።

መልካም አዲስና የጤና ዓመት

ይሁንላችሁ!

ተስፋ እና ስጋት

ከወራት በፊት ም/ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ኃ/ማርያም

ደሳለኝ ሳዑዲ አረቢያን ከጎበኙ በኋላ፣ ሳዑዲ አረቢያ ወደ 30 ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያዊ

የኮንትራት ሠራተኞችን እንደምትፈልግ ይፋ ማድረጋቸውን ተከትሎ ከ15 ሺህ በላይ

የሚገመቱ ዜጎች ወደ ሳዑዲ መግባታቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

30 ሺህ ሠራተኞች በሳዑዲ አረቢያ መፈለጋቸው አገር ውስጥ በሥራ አጥነትና

በድህነት ለሚማቅቀው ወጣት አስደሳች ዜና ቢሆንም ስጋቶችም አብረው መከሰታቸው

አልቀረም። ለዚህ ሐተታዊ ፅሁፍ ሰፊና በማስረጃ የተደገፉ ማብራሪያዎችን በመስጠት

ተባባሪ የሆነው ጋዜጠኛ ነቢዩ ሲራክ፣ ስጋቱ የሚመነጨው በሁለቱ ሀገራት መካከል

ስለተደረገው ስምምነት የተፈረመ ሰነድ ይፋ ካለመደረጉ መሆኑን ያስገነዝባል።

በኮንትራት ስለሚሄዱ ሠራተኞች ደመወዝ፣ የሥራ ሠዓት ህክምናና ተዛማጅ

መብቶችን በሚመለከት የሚነሱ ጥያቄዎችን መመለስ የሚችል ሰነድ ይፋ አለመሆኑ

ኢትዮጵያውያንን ለብዝበዛ ሊዳርግ እንደሚችል በመግለፅ ትዝብቱን አካፍሏል።

በአዲሱ የሥራ ዕድል ‹‹ተጠቃሚ›› ሆነው ሳዑዲ አረቢያ ከገቡ ኢትዮጵያውያን

መካከል አንዳንዶች ተቀባይ አጥተው ሲንገላቱ መመልከቱን ለአውራምባ ታይምስ

የገለፀው የመካከኛው ምስራቅ የጀርመን ሬዲዮ ዘጋቢ፣ አሠሪዎቻቸውን አግኝተው

ወደ ሥራ የተሰማሩትም በምግብ እጦትና በሥራ ብዛት ለከፋ ችግር መዳረጋቸውን

አልሸሸገም።

ይህንንም ችግር ለመቅረፍ ያሉት አማራጮች ለሠራተኛና አሠሪ አገናኝ ኤጀንሲዎች

ፍቃድ በሚሰጠው የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርና በየሀገሩ በሚገኙት

ዲፕሎማቲክ መሥሪያ ቤቶች መካከል ያለውን የመረጃ ክፍተት ማጥበብና ዜጎችን

ወደ ባዕድ አገር ከላኩ በኋላ ችግር ሲደርስ ዝም የሚሉ ሥራ አገናኝ ኤጀንሲዎች ላይ

ጥብቅ ቁጥጥር የማያደርግ መሆኑን የሚያስገነዝቡ አሉ። ‹‹ውል ገብተው እስከላኩ

ድረስ ሠራተኞችን በሚመለከት ማናቸውም ጉዳይ ከኃላፊነትና ከተጠያቂነት ማምለጥ

እንደማይችሉ መንግስት እርምጃ በመውሰድ ትምህርት ሊሰጥ ይገባል›› በማለት

ሀሳቡን ያጠናክራል፤ ነብዩ።

ሸዋዬ - የማንቂያ ደወል?

‹‹ዘመናዊ ባርነትን ለማስፋፋት የሚሯሯጡትን ጥጋጥግ ላይ ያሉትን ሕገ-ወጥ

ደላሎች ተከታትሎ መቆጣጠር መንግስት አቅቶት ነውን?›› ሲሉ የሚጠይቁት

ፕሮፌሰር በየነ መረጃው ጠፍቶት ሳይሆን ኃላፊነት ያለመስማት ችግር ነው ካሉ

በኋላ ይህን ችግር መቅረፍ የችግሩን ግማሽ ያህል መቅረፍ መሆኑን ይስማማሉ።

‹‹ሸዋዬ ሞላ ለደረሰባት ጉዳቶች፣ ሕመምና ስቃይ ካሳ ይገባታል›› የሚል አመለካከት

አለኝ›› የሚሉት ዶ/ር ሼክስፒር ፈይሳ ‹‹የደረሱባት ከባድ ጉዳቶች በቀጥታ ከጋዳፊ

ቤተሰብ እርምጃዎች የመነጩ ናቸውና ጋዳፊንና ቀንደኛ ጋሻግሬዎቻውን በፍትሐ

ብሔርም ብቻ ሳይሆን በወንጀል ሕግም ተጠያቂ ሊያደርጋቸው ስለሚችል ካሳ

ለማስከፈል የኢትዮጵያ መንግስትን ትጋት ይሻል›› ይላሉ።

በሸዋዬ ሞላ ላይ የተፈፀመው ድርጊት እጅግ አስከፊና በኢትዮጰያዊነት ብሔራዊ ኩራት

ላይ የተቃጣ ቢሆንም፣ የተገለፁትን ችግሮች ለመቅረፍ እንደማንቂያ ደወል ሊወሰድ

እንደሚገባ እየተገለፀ ነው። ወጣቷ የተሻለ ኑሮ ፍለጋን ሲንከራተቱ በየበረኻውና

በየባሕሩ ድምፃቸው ዳግም ላይሰማ ጠፍቶ የቀረ እንዲሁም በአሠሪዎቻቸው ግፍ

ለሚፈፀምባቸው ሌሎች የአገሯ ልጆች ሁሉ ማሳያ ተደርጋ እየተወሰደች ነው። የወጣቷ

ጉዳይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሰፊ ሽፋን ተሰጥቶት በመዘገቡ የተነሳ የእርዳታ እጆች

እንዲዘረጉ የተማፅኖ ጥሪዎች እየቀረቡ ሲሆን፣ በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ

ኢትዮጵያውያን ዕልፍ አዕላፍ መሆናቸውን በመግለፅ ‹‹እነሱንም እንታደጋቸው››

የሚሉ ድምጾች ሊበረክቱ እንደሚገባ የሚወተውቱ ወገኖች መደመጥ ጀምረዋል።

ሌሎች ደግሞ ይህ ወቅት የኢትዮጵያ መንግስት መፈተኛው መሆኑን

በመግለፅ ላይ ናቸው። ‹‹መንግስት የድርጊቱን ፈፃሚዎች በዓለም አቀፍ ፍ/

ቤት በመክሰስ ተመጣጣኙን ቅጣት ሊያስወስንባቸው ይገባል›› የሚሉት እነዚህ

ወገኖች፣ ኢትዮጵያውያን በርክተው ከሚገኙባቸው የአረብ አገራት መንግስታት ጋር

የዜጎቹን ሁኔታ አስመልክቶ ከእስካሁኑ ‹‹ኮስተር›› ባለ መልኩ ሊነጋገር እንደሚገባ

አስገንዝበዋል።

‹‹‘የማንቂያ ደወል’ የሚለው አገላለፅ ትክክለኛ ነው›› የሚሉት አምባሳደር ዲና

ሙፍቲ ደግሞ በበኩላቸው፣ ከዚህ በኋላ ወደ አረብ ሐገራት ለመጓዝ የሚያስቡ

አካሄዳቸውን ሕጋዊ በማድረግና በአቅራቢያቸው ወዳለ ኤምባሲ አሊያም ቆንጽላ

ጽ/ቤት ሄደው በመመዝገብ ለራሳቸው ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚኖርባቸው

አስገንዝበዋል፡፡

ዞሮ ዞሮ በአረብ ሐገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን መብት ስለማስከበር ሲነሳ

ዓይኖች ወደ ኤምባሲዎች ማነጣጠራቸው አይቀርምና ወደ አካባቢው የሚላኩት

ዲፕሎማቶች ከፖለቲካ ታማኝነታቸው ባለፈ በሰብዓዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸው በቂ

የሥራ ልምድና ፍላጎት ግምት ውስጥ ሊገባ እንደሚገባ የበርካቶች መስማሚያ ነጥብ

ነው።

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 184 ቅዳሜ ጳጉሜ 5/ 2003

መልካም ዓዲስ ዓመት

}SdeK¨< Ÿ}c\ ð×” ¾h¨` ¨

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!