Neger Ethiopia Issue 2
Neger Ethiopia Issue 2
Neger Ethiopia Issue 2
You also want an ePaper? Increase the reach of your titles
YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.
1 የካቲት 7 ቀን 2006 ዓ.ም. ቅፅ 1 ቁጥር 2 ነገረ-ኢትዮጵያ

ነገረ-ኢትዮጵያ

ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን እንናገራለን!

ቅፅ 1 ቁጥር 2 አርብ የካቲት 7 2006 ዓ.ም. ዋጋ 8.00

ማርቆስ ሀጎሶች እና

ዳሮ ነጋሾች ዛሬም

ያስፈልጉናል!

‹‹መንግስት›› አሳልፎ

የሰጠው ሉዓላዊነት

12 5

መሬት

ያስቆረሱት

የመለስና

ተከታዮቹ እኩይ

ስምምነቶች

7

ውህደት ወይስ ትብብር?

3

ውህደት በተናጠል በውጠ-ፓርቲ ትግል ፈተና ውስጥ የገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎች ከቀውስ ማምለጫ ወይም አጀንዳ

ማስቀየሻ ሊሆን አይገባም፡፡ በተጨማሪም አንድ ፓርቲ ከገጠመው የገንዘብ እጥረት አሊያም የቢሮ ኪራይ ችግር ለመውጣት

ዘው ብሎ የሚገባበት ጉዳይ መሆን አይኖርበትም፡፡ በሩጫ የሚደረግ ውህደት ውጤቱ ...

ሰማያዊ ፓርቲ ‹የካቲት 12›ን በሰማዕታቱ

ሐውልት በመገኘት ሊዘክር ነው

አዲስ አበባ:- ሰማያዊ ፓርቲ

በዳግም የጣሊያን ወረራ ወቅት

በፋሽስት ግራዚያኒ ትዕዛዝ

በአዲስ አበባ ብቻ ከ30,000 በላይ

ንጹሃን በግፍ የተጨፈጨፉበትን

የየካቲት 12 ሰማዕታት ቀን

በተለያዩ ፕሮግራሞች ሊዘክር

መሆኑን አስታወቀ፡፡

የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት

ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ

እንዳስታወቁት፣ ሰማያዊ ፓርቲ

የየካቲት 12 ሰማዕታት ቀንን

ምክንያት በማድረግ በጽ/ቤቱ

የፓናል ውይይት ያካሂዳል፤

በተጨማሪም ስድስት ኪሎ

በሚገኘው የሰማዕታት መታሰቢያ

ሐውልት በዕለቱ በመገኘት

ሰማዕታቱን የመዘከርና የአበባ

ጉንጉን የማስቀመጥ ስነ-ስርዓት

ያከናውናል፡፡

እንደ አቶ ብርሃኑ ገለጻ፣

ፓርቲው ፕሮግራሞችን

ያዘጋጀበት ዋና ዓላማ ሰማዕታቱ

የተሰውት ለሀገር አንድነትና

ሉዓላዊነት ሲሉ ከመሆኑ ጋር

በተገናኘ ሰማዕትነታቸውን

ለትውልድ ለማስተላለፍ ነው፡፡

ቀኑ በአብዛኛው በጥንታዊት

ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች

ብቻ የተወሰነ እየሆነ መምጣቱን

ያወሱት አቶ ብርሃኑ፣

የሰማዕታት ቀን በመላው ህዝብ

ዘንድ የሚታወስ ታላቅ ቀን

ወደ ገፅ 6 ይዞራል

በጎንደር በተካሄደው ሰልፍ የተሳተፉ ወከባ

እየደረሰባቸው መሆኑን አስታወቁ

ሰማያዊ ፓርቲ ጥር 25 ቀን 2006

ዓ.ም ‹የኢትዮጵያ መንግስት መሬት

በድብቅ ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት

እየተዘጋጀ መሆኑን› ተከትሎ

የጠራውን ሰላማዊ የተቃውሞ

ሰልፍ ያስተባበሩና በሰልፉ የተሳተፉ

ወጣቶች ከሰልፉ በኋላም በደህንነት

አካላት ወከባ እየደረሰባቸው መሆኑን

ለነገረ-ኢትዮጵያ አስታውቀዋል፡፡

በሰልፉ ወቅት ህዝብ ወደ ሰልፉ

እንዳይቀላቀል ከመከልከል ባለፈ ፎቶ

ግራፍ በማንሳትና ክትትል በማድረግ

ሲያስፈራሩ የዋሉት የደህንነት አባላት

ሰልፉ ከተጠናቀቀ በኋላ የተሳታፊ

ወጣቶችን የቀበሌ መታወቂያ

የቀሟቸው ሲሆን ወጣቶቹ ጥር

26 መታወቂያቸውን ለመቀበል

ወደ ቀበሌ ባቀኑበት ወቅትም

በድጋሚ በመንግስት ላይ የተጠራ

ሰልፍ እንዳይሳተፉ ማስፈራሪያ

እንደደረሰባቸው ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ በጎንደር ሰልፉን

ወደ ገፅ 6 ይዞራል

መመረጥ በሌላው

ድክመት

ኢህአዴግ ተሸንፏል!

(የጉዞ ማስታወሻ)

13

ሳይሆን በራስ ጥንካሬ

16
ነገረ-ኢትዮጵያ ቅፅ 1 ቁጥር 2 የካቲት 7 ቀን 2006 ዓ.ም. 2

ርዕሰ አንቀጽ

ስለ ሀገርና ወገን የሚታገሉትን ማዋከቡ ይቁም!

ከዚህ በፊት በተለያዩ ጊዜያት ለሀገርና ለወገን

ተቆርቁረው ጥቅማችንን ለማስጠበቅና

ድምጻችንን ለማሰማት በተነሱ ወገኖች ላይ

ከመንግስት የተሰጠው ምላሽ ያልተጠበቀ

እንደነበርና ይህንንም በተለያዬ ጊዜ ብዙዎች

በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ መግለጻቸው ይታወቃል፡፡

በእርግጥም በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያገባኛል ብሎ የመሰለውንና

ለሀገር ይጠቅማል ያለውን አቋም በአደባባይ በሚገልጽ

ማንኛውም አካል ላይ የተወሰደው እና እየተወሰደ ያለው

እርምጃ አደናጋሪም አሳፋሪም ነበር፤ ነውም፡፡

ለአብነትም ሰማያዊ ፓርቲ በ2005 ዓ.ም ጣሊያኖች

በወገኖቻችን ላይ ከፍተኛ በደል የፈጸመውን ሮዶልፍ

ግራዚያኒ በትውልድ ከተማው ‹የጀግና› ሐውልት በማቆም

ዕውቅና መስጠታቸውን በመቃወም ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ

በአዲስ አበባ መጥራቱ የሚታወስ ነው፡፡ ሆኖም ግን መንግስት

ከፋሽስቱ ግራዚያኒ ታሪክ ጎን የቆመ በሚያስመስለው መልኩ

ለተቃውሞ ሰልፍ የወጡትን ሰዎች ለቃቅሞ አስሯቸው ነበር፡

፡ ድብደባና እንግልትም አድርሶባቸዋል፡፡

እንዲሁ በሌላ ጊዜ የሳውዲ አረቢያ መንግስት እንጀራ

ፍለጋ ከሀገራቸው የተሰደዱትን ኢትዮጵያዊያን በአስቸኳይ

ሳውዲን ለቀው እንዲወጡ ማድረጉንና ሂደቱም ሰብዓዊነት

በጎደለው ሁኔታ መከናወኑን በመቃወም በዚህ በሀገር ቤት

ስለ ወገኖቻቸው እንግልት ጥብቅና በመቆም ተቃውሞ ባሰሙ

የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እና መላ ሀገርና ወገንን ብለው ሰልፍ

የወጡ ዜጎቻችንን በአዲስ አበባ የሳወዲ ኤምባሲ አካባቢ

መንግስት የወሰደባቸው የድብደባና የእንግልት እርምጃ

የሚያሳፍር ሆኖ አልፏል፡፡

ይህም ብቻ ሳይሆን አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ

(አንድነት) የሚሊዮኖች ድምጽ ለፍትህና ለነጻነት በሚል

መርህ ፀረ-ሽብር ህጉ አፋኝና የማጥቂያ መሳሪያ ነው፣

ስለዚህም መሻሻል አሊያም መሰረዝ ይገባዋል ብሎ የድጋፍ

ፊርማ በሚያሰባስብበት ወቅት በአባላቱ ላይ የተለያዩ

እንግልቶች ሲፈጸምባቸው እንደነበር በተደጋጋሚ ገልጾዋል፡፡

በተጨማሪም የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች ይፈቱ ብለው

በተለያየ መልኩ ህጋዊና ሰላማዊ ጥያቄ ባነሱና ለዚህም

ተግባራዊነት በተንቀሳቀሱ ሀገርና ወገን ወዳዶች ላይ

የሚደርሰው ጫና አሌ የማይባል ነው፡፡

ይህ ሁሉ እንዳለ ሆኖ ደግሞ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ሰማያዊ

ፓርቲ የኢትዮ-ሱዳን የድንበር መሬትን አስመልክቶ ያለው

የመንግስት አካሄድ ግልጽና ተጠያቂነት የሰፈነበት መሆን

እንደሚገባውና ሂደቱንም ዜጎች በየጊዜው እንዲያውቁ

እንዲህም ተብሏል

‹‹መኳንንቶች ሲሻሩ ህዝብ ይሆናሉ፡፡››

አለቃ ዘነብ፣ የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ ጸሐፊ ትዕዛዝ፤

‹‹ሀገር የጋራ ነው፤ ሀይማኖት የግል ነው፡፡››

ቀዳማዊ አጼ ኃ/ስላሴ፤

መደረግ እንዳለበት በተለያየ መንገድ መጠየቁን ተከትሎ፣

በአባላቱ ላይ ሰፊ የእመቃና የእስር ዘመቻ ተክፍቶባቸው

አይተናል፡፡ ፓርቲው የድንበር መሬቱን ጉዳይ አስመልክቶ

በጎንደር ከተማ ባካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ በተሳተፉ

ሀገር ወዳድ ዜጎችና በፓርቲው አባላት ላይ የተወሰደው

የማሳደድ እርምጃ ዛሬም እንደትናንቱ አሳፋሪነቱ ጎልቶ

ታይቷል፡፡ ገና ሰልፉን በተመለከተ ለከተማዋ ህዝብ የቅስቀሳ

ስራ በወጡ የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎቹ ላይ የተጀመረው

ግልጽ የማደናቀፍ ስራ እስከ ሰልፉ ማጠናቀቂያ ቀን ድረስ

የቀጠለ እንደነበር ለመመልከት ችለናል፡፡

ማንም ሰው በቀላሉ ሊረዳው እንደሚችለው በሰላማዊ

የተቃውሞ ሰልፉ ላይ የተነሳው ጉዳይ የሀገር ጉዳይ ነው፡፡

ቢሆን ቢሆን በሀገር ጉዳይ ላይ የፖለቲካ ልዩነታችን ተወግዶ

ወይም ለጊዜው ልዩነቱን ወደ ጎን ገፍተን በአንድነት ብንቆም

እሰየው ነበር፡፡ በዚህም የኢህአዴግ አባላትና ደጋፊዎቻቸው

ሳይቀር በበላይ አለቃዎቻቸው ዘንድ በስውር እየተካሄደ

ነው ስለሚባለው የሀገርን ጥቅም አሳልፎ የመስጠት እኩይ

ተግባር ላይ ግልጽነት እንዲፈጠርና የህዝብ ይሁንታን በተጋፋ

መልኩ እንዳይካሄድ ለመጠየቅ ሰማያዊ ፓርቲ የተጠራውን

የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ በተቀላቀሉ ነበር፡፡

ይህ ካልሆነ ግን ስለሀገር ብለው ድምጻቸውን ከፍ አድርገው

በሚያሰሙ ሰላማዊ ኢትዮጵያዊያን ላይ ያልተገባና ህገ-ወጥ

ተግባር መፈጸምና ከመሬት ቆራሾች ጋር ማበር አሊያም

በዝምታ ማለፍ ነገ በህግ ዛሬ በህሊና ከመጠየቅ እንደማያድን

ልብ ማለት ይገባል፡፡

ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ የማካሄድም ሆነ በተደራጀ

መልኩ የተለያዩ ጥያቄዎችን የማሰማት እንዲሁም ሀሳብን

በነጻነት የማራመድ መብት በህገ-መንግስቱ ተደንግጎ እያለ

በማናለብኝነት ህግን ጥሶ ዜጎችን ማንገላታት ከመንግስት

ማናቸውም አካላት ፈጽሞ የማይጠበቅ ድርጊት መሆኑን

ደጋግመን ማስታወስ እንወዳለን፡፡ አሁን መንግስት የማዋከብና

የማሳደድ እርምጃ እየወሰደባቸው ያሉ አያሌ ኢትዮጵያዊያን

እያነሷቸው ያሉት ጉዳዮች ተራ የፖለቲካ ፍጆታ ከማጋበስ

ጋር የማይገናኙ፣ በአንጻሩ ግን የሀገርና የህዝብ ተቆርቋሪነትን

የሚያሳዩ እንቅስቃሴዎች እንደሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ስለ ሀገርና

ወገን የሚታገሉትን መሸለም እንጂ ማዋከብ የማይገባና

ኢ-ዴሞክራሲያዊነት ነው፡፡

በእርግጥም ከህዝብና ከሀገር ጥቅም ጋር ተጋጭቶ ዜጎችን

ማሳደድ አምባገነንነትና ግዴለሽነት ነው፡፡ ስለሆነም እንዲህ

አይነቱ የመንግስት አካሄድ ሀገር ያለ ተቆርቋሪና ሃይ ባይ

እንድትቀርና ዜጎች በሀገራቸው እና በወገኖቻቸው ላይ

በሚደርስ ማናቸውም አይነት ጥቃት ግዴለሽ እንዲሆኑ

የሚገፋ ኃላፊነት የጎደለው ድርጊት በመሆኑ በአስቸኳይ

ሊቆም ይገባዋል እንላለን፡፡

‹‹ከጠላትህ ጋር ሰላም ለመፍጠር ከፈለክ፣ ከጠላትህ ጋር መስራት ይኖርብሃል፤ ይህንን ጊዜ አጋርህ ይሆናል፡፡››

ኔልሰን ማንዴላ፤

‹‹ከትልቅ ወይም ከትንሽ መወለድ ሙያ አይደለም፤ ራስን ለታላቅ ታሪክ መውለድ ግን ሙያ ነው፡፡››

ዳግማዊ አጤ ምኒልክ (እምዬ)፤

‹‹እኛ ኢትዮጵያዊያን ሁለት ቃል አንወድም፡፡ ለወዳጅነት የፈለጉኝን እፈልጋቸዋለሁ፤ እንዲያቃልሉኝ ግን ፈጽሞ አልፈቅድም፡

ሻምበል አብዲሳ አጋ፣ ስመጥር አርበኛ፤

አንደኛ ዓመት ቅጽ 1. ቁጥር 2

ነገረ-ኢትዮጵያ ጋዜጣ ጥር 2006 ዓ.ም

ተመሰረተች፡፡ ነገረ-ኢትዮጵያ በሰማያዊ

ፓርቲ አሳታሚነት የምትታተም

ፖለቲካዊ፣ ወቅታዊ፣ ማህበራዊና

ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን የምትዳስስ

በየሳምንቱ አርብ የምትወጣ ጋዜጣ ናት፡፡

ጋዜጣዋ ሚዛናዊና ነጻ ሆና የማገልገል

መርህ አላት፤ ማንኛውም ሀሳብ በነጻነት

የሚስተናገድባትና የሚንሸራሸርባት

እንድትሆን እንፈልጋለን፡፡ ገዥው

ፓርቲም ቢሆን አቋሙንና ፖሊሲውን

ለመግለጽ ቢፈልግ የሰፊ ሚዲያ ባለቤት

ነው ብለን ዕድሉን አንነፍገውም፤ በራችን

ለሁሉም ክፍት ነው፡፡

የአሳታሚ አድራሻ:- የካ ክ/ከተማ ቀበሌ 09/10

ቤት ቁ.460

E-mail:- info@semayawiparty.org

P.O.Box: 180298

ዋና አዘጋጅ

ጌታቸው ሺፈራው

የካ ክ/ከተማ ቀበሌ 01/02

ቤት ቁ. 07/859/14

E-mail:-gecholink@gmail.com

ስልክ ቁጥር:- 09-10-45-99-32

ምክትል ዋና አዘጋጅ

በላይ ማናዬ

የካ ክ/ከተማ ቀበሌ 01/02

ቤት ቁ.099

E-mail:- belaymb@gmail.com

ስልክ ቁጥር:-09-20-19-09-72

አምደኞች

ፕ/ር አለማየሁ ገ/ማርያም

ታዴዎስ ታንቱ

ታምራት ታረቀኝ

አፈወርቅ በደዊ

እያስፔድ ተስፋዬ
3 የካቲት 7 ቀን 2006 ዓ.ም. ቅፅ 1 ቁጥር 2 ነገረ-ኢትዮጵያ

ልብ አድርጉ

ውህደት ወይስ ትብብር?

በላይ ማናዬ

ሀገር አቀፉ ምርጫ 2007 እየደረሰ ነው፤

ምርጫን ተከትሎ የሚስተዋለው የፖለቲካ

ግለትም በትንሹም ቢሆን ከወዲሁ ለብ

ማለት የጀመረ ይመስላል፤ የት መሽገው

እንደከረሙ ጠፍተውብን የነበሩ የፖለቲካ

ፓርቲዎችም አንገታቸውን ብቅ ለማድረግ

እየሞከሩ እንደሆነ መታዘብ ይቻላል፡፡

በሀገራችን በፓርቲዎች የቁጥር ብዛት ረገድ

ችግር የለም ማለት ይቻላል፡፡ ባለፈው

ምርጫ 2002 እንኳ ወደ 90 የሚጠጉ

ፓርቲዎች እንደነበሩ ይታወቃል፡፡

በእርግጥም አሁን ላይ ኢትዮጵያ

ውስጥ በቁጥር በጣም ብዙ የፖለቲካ

ፓርቲዎች ተመዝግበው ይገኛሉ፤

(በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚንቀሳቀሱትን

ህብረ-ብሄር ፓርቲዎችም፣ ጎሳን ወይም

አንድን ብሄረሰብ ማዕከል አድርገው

የሚንቀሳቀሱትንም ማለቴ ነው)፡፡ ለአብነት

በሁለተኛው ረድፍ ላይ ከሚመደቡት እንኳ

ብናይ ለኦሮሞ ህዝብ እንታገላለን የሚሉት

ከ10 በላይ፣ ጉራጌ 5፣ አርጎባ 3፣ ሀረሪ

3 እና ሌሎችም በተመሳሳይ በርካቶች

አሉ፡፡ በዚህም ከአጠቃላይ የፓርቲዎች

ቁጥር አብላጫውን ሀገር አቀፍ ያልሆኑት

ፓርቲዎች ይዘው ይገኛሉ፡፡ (የምዝገባ

ፍቃዱን ወስዶ ዳናው የሚጠፋውም ጥቂት

የሚባል አይደለም፡፡)

ይህ ቁጥሩ የበዛ የፓርቲዎች እንቅስቃሴ

ያለው ደግሞ በተቃውሞው ጎራ በኩል

ነው፡፡ እንዲህ አይነቱ የፓርቲዎች አካሄድ

ማንን እንደሚጠቅም ሳይታለም የተፈታ

ነው፡፡ በምርጫ ወቅት የህዝብን ድምጽ

በመከፋፈል የትኛውም ተቃዋሚ ፓርቲ

አብላጫ ድምጽ በቀላሉ እንዳያገኝ በማድረግ

ለገዥው ፓርቲ በተዘዋዋሪ ይጠቅመዋል፡

፡ ስለሆነም እንዲህ ባለ ወቅት ተቃዋሚ

ፓርቲዎች በሁለት አማራጮች ላይ

ይንጠለጠላሉ፤ አንድም በቁጥር የበዙትን

ፓርቲዎች ወደ አንድ ኃይል ማምጣት

ላይ፣ አሊያም በተናጠልም ቢሆን በሀገር

አቀፍ ደረጃ ጎልቶ ለመውጣት የሚያስችልን

አቅም ፈጥሮ ገዥው ፓርቲንም ሆነ

ሌሎች ተወዳዳሪዎችን ተፎካክሮ ለማሸነፍ

የሚያስችልን እንቅስቃሴ ማድረግ፡፡

በተግባር እንቅስቃሴ ላይ ያሉትን የተለያዩ

ፓርቲዎች ወደ አንድ ኃይል አምጥቶ

ወደ ምርጫ መግባት በባለፉት የምርጫ

ተሞክሮዎቻችን ላይ አይተናል፤ (ቅንጅትን

በ97፣ መድረክን በ2002 መጥቀስ ይቻላል፡፡

) ያለፉት ሂደቶችና ተሞክሮዎች የራሳቸው

ጥንካሬና ድክመት እንደነበረባቸው መካድ

አይቻልም፡፡ ያም ሆነ ይህ ግን አሁን

ሌላ የታሪክ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን፡

፡ ቀደም ብዬ እንደጠቀስኩት ምርጫ

2007 እየደረሰ ነው፡፡ ስለሆነም አሁን

ፓርቲዎች የበለጠ ለስራ የሚነሱበት ጊዜ

ነው፤ በተናጠልም፣ በትብብርም፡፡ ከዚህ

ጋር ተያይዞ በዚህ ሰሞን ስለ ፓርቲዎች

ውህደትም የሚያነሱት በዝተዋል፡፡ ይህን

የውህደት ጉዳይ እንደሚከተለው ለማየት

እንሞከራለን፡፡

ውህደት እንዴት?

በአጭሩ ውህደት አንድ መሆን ማለት

ነው፡፡ ከውህደት በፊት ያለው የተናጠል

ህጋዊ ህልውና አክትሞ አዲስ ፓርቲ

በአንድ ላይ መመስረት ነው ውህደት፡

፡ አንድ ለመሆን ደግሞ፣ አንድ ለመሆን

የሚያስችሉ ሁኔታዎች መኖር አለባቸው፡

፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለመዋህድ የፖለቲካ

ፕሮግራማቸው መመሳሰልና መቀራረብ

ይኖርበታል፡፡ ከዚህም በላይ ግን ፓርቲዎቹ

ለመዋህድ ፍላጎት ማሳየት የግድ ነው፤

በውህደቱ ሂደትና ከውህደት በኋላ

ስለሚኖረው እንቅስቃሴም የተሻለ መስራት

እንደሚችሉ ሊያምኑበት ይገባል፡፡ በዚህም

ማን ከማን ጋር መዋህድ እንደሚችል

ካላቸው የፖለቲካ ፕሮግራም፣ የውህደት

ፍላጎትና በመዋህዳቸው ሊያመጡት

የሚችሉትን ውጤት ገምግመው፣ ወይ

ወደ ውህደት ይገባሉ አሊያም በራሳቸው

መስመር ጠንክረው ለመስራት ውሳኔ

ያስተላልፋሉ፡፡

ከሰሞኑ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት

ድርጅት (መኢአድ) እና አንድነት

ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት)

በአስቸኳይ ለመዋህድ እየሰሩ እንደሆነ

ገልጸዋል፡፡ ፓርቲዎቹ ጥር 25 ቀን 2006

ዓ.ም መአህድ/መኢአድ የተመሰረተበትን

22ኛ አመት በዓል በጽ/ቤቱ ባከበረበት ወቅት

እንደገለጹት፣ ሁለቱ ፓርቲዎች በፍጥነት

ወደ ውህደት ለመምጣት መወሰናቸውን

በይፋ በመሪዎቻቸው በኩል ግልጽ

አድርገዋል፡፡ የመኢአድ ፓርቲ ፕሬዚዳንት

አቶ አበባው መሐሪ ፓርቲያቸው መኢአድ

ከአንድነት ፓርቲ ጋር መዋሃድ ፍላጎቱ

መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ በቀድሞ ፓርቲያቸው 22ኛ

አመት ክብረ በዓል ላይ የተገኙት የአንድነት

ፓርቲ ፕሬዚዳንት ኢ/ር ግዛቸው ሺፈራው

በበኩላቸው ፓርቲያቸው ከመኢአድ ጋር

መዋሃድ ፍላጎቱ መሆኑን ገልጸው፣

በ15 ቀናት ውስጥ ውህደቱ እውን ሊሆን

እንደሚችልም ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡

ፓርቲዎቹ ይህን ይበሉ እንጂ (በዕለቱ

በነበረው የመድረክ ሞቅታ እንዳይሆን

እሰጋለሁ) በዚህ ፍጥነት ሊዋሀዱ

የሚችሉበት ሁኔታ ውስጥ እንዳልሆኑ

ጠቋሚ ምልክቶች መኖራቸውን መካድ

አይቻልም፡፡

ውህደት መቼ?

ውህደት ምርጫ ስለቀረበ የሚከናወን

የይድረስ ይድረስ ስራ እንዳልሆነ እሙን

ነው፡፡ በተቃራኒው ግን በሀገራችን የነበሩ፤

ያሉ ፓርቲዎች ውህደት የሚታያቸው

ምርጫ ሲቃረብ መሆኑ አለመታደል ነው፡፡

አንዳንዶቹ ሂደቱን ቀድመው ቢጀምሩትም

ሲያጓትቱ ሲያጓትቱ እስከ ምርጫ መቃረቢያ

ድረስ ያደርሱታል፡፡ የመኢአድና የአንድነት

ውህደት እውን ቢሆን የሚወድ ብዙ ነው፡

፡ ዳሩ ግን ውህደቱ መሆን የነበረበት

(በእውነት ኢ/ር ግዛቸው እንዳሉት በ15

ቀናት ውስጥ የሚከናወን ከሆነ ወይም

ቢሆን ኖሮ) እንዲህ በሩጫ አሁን ላይ

አይደለም፤ (በ15 ቀናት ውስጥ የሚደረግ

ውህደት የፖለቲካ ፓርቲዎች ሳይሆን….)፡

፡ ይህ ውህደት ከምርጫ 2002 ማግስት

ቢሆን በተገባ ነበር፡፡

ውህደት በተናጠል በውጠ-ፓርቲ ትግል

ፈተና ውስጥ የገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች

መሪዎች ከቀውስ ማምለጫ ወይም አጀንዳ

ማስቀየሻ ሊሆን አይገባም፡፡ በተጨማሪም

አንድ ፓርቲ ከገጠመው የገንዘብ እጥረት

አሊያም የቢሮ ኪራይ ችግር ለመውጣት

ዘው ብሎ የሚገባበት ጉዳይ መሆን

አይኖርበትም፡፡ በሩጫ የሚደረግ ውህደት

ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል ለማንም

የተሰወረ አይሆንም፡፡

እናም ውህደት በቂ ጊዜ ወስዶ መጤን

ያለበት ትልቅ የፖለቲካ ስራ ነው፡፡

እርግጥ ነው ህዝቡ ፓርቲዎቹ እንዲዋህዱ

ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በላይ ግን አብዛኛው

ህዝብ ፓርቲዎች ተዋህደው እንዲዘልቁና

ለውጥ እንዲያመጡ እንደሚሻ ግልጽ ነው፡

፡ ለዚህ ደግሞ ከጅምሩ የሰከነ የውህደት

ሂደት መኖሩ ግድ ይላል፡፡

የውህደት ፈተናዎች

የፖለቲካ ፓርቲዎችን ወደ ውህደት

ማምጣት፣ ከውህደት በኋላም ተስማምቶ

መቀጠል ትልቅ ፈተና አለው፡፡ በተለይም

እንዲህ በአጭር ጊዜ ውህደትን እናመጣለን

ብለው ሰርጋቸውን ከሚያፋጥኑ ሰዎች

ወደ ፊት የሚሆነውን በስጋት መመልከት

ግርምትን የሚፈጥር ጉዳይ አይሆንም፡

፡ በተዋሃጆቹም በኩል የእነቶሎ ቶሎ

ቤት…እንዳይሆን መጠንቀቁ የሚበጅ ነው፡

፡ ምርጫ ስለደረሰ ብቻ በፍጥነት ውህደትን

ማከናወን ሊኖረው የሚችለውን ፈተና

ሊያስረሳን አይገባም፡፡ ሰርገኛ መጣ በርበሬ

ቀንጥስ እንዳይሆን መጠንቀቁ የብልሆች

ምርጫ ነው፡፡

በእርግጥም ውህደት የጥቂት ግለሰቦች

ወይም የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎች

ፍላጎትና ተግባር ብቻ አይደለም፡፡ ከዚያ

ይልቅ የሚዋሃዱት ፓርቲዎች አባላት

(ጠቅላላ ጉባኤ በሚገባ ተወያይቶበት

ውሳኔ ማሳለፍን ይጠይቃል፤) በየደረጃው

ሰፊ ጊዜ ሰጥተው ጉዳዩን ሊወያዩበትና

ሊያጤኑት ግድ ይላል፡፡ ይህን ለማድረግ

የሚያስችላቸው ጊዜም ሊሰጣቸው

እንደሚገባ እሙን ነው፡፡ በሌላ አነጋገር

ውህደቱ ከጅምሩ እሰከ ፍጻሜው አባላትንም

ማዕከል ያደረገ መሆን ይኖርበታል፡፡ ይህ

ሳይሆን ቀርቶ ውህደቱ የጥቂቶች ስራ

ከሆነ፣ አንድም ውህደቱ እውን አይሆንም፣

እውን ከሆነም ዘላቂነቱ አጠራጣሪ ከመሆን

አይድንም፡፡

የውህድ ፓርቲው መሪ

ሌላው ፈተና ውህደቱ ከተፈጸመ በኋላ

የውህድ ፓርቲው (አዲሱ ፓርቲ) መሪ

ማን ይሁን የሚለው ጉዳይ ነው፡፡ የዚህ

ፈተና ምንጭ ውህደቱን ከመሰረቱት

ፓርቲዎች ወገን ሁሉም የቀድሞ ፓርቲው

መሪ፣ የአዲሱ ውህድ ፓርቲ መሪም

ሆኖ እንዲዘልቅለትና ቡድናዊ ጥቅሙን

እንዲያስከብርለት የመፈለጉ ጫና ነው፡፡

በዚህም ሁሉም የየራሱን የቀደመ የትግል

ታሪክና የአደረጃጀት ስፋት እያነሳ ስልጣኑ

እንደሚገባው መሞገቱ ስለማይቀር ነው፡፡

እንዲህ አይነቱ ጉዳይ ደግሞ ማን የተሻለ

መምራት ይችላል ሳይሆን፣ ማን የውህድ

ፓርቲው መሪነት ይገባዋል ወደሚል

ሰንካላ ምክንያት ይገፋናል፡፡

በተመሳሳይ ውህደቱ ከሚከናወንበት

ወቅት አንስቶ፣ ውህደቱ ሊያመጣባቸው

የሚችለውን ከጥቅማ ጥቅምና ስልጣን

ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ማጣት በማጤን

ቅሬታ የሚሰማቸው ግለሰቦችም ሌላኛዎቹ

ፈተናዎች መሆናቸው የማይቀር ነው፡

፡ ከሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ

ፓርቲዎች ወደ አንድ ሲመጡ፣ ቀድሞ

በተናጠል የነበረውን የስራ አስፈጻሚ ያህል

ቁጥር ሊያካትት አይችልም፡፡ በዚህ ጊዜ

ተቀናሾች መኖራቸው ግድ ነው፤ እዚህ

ጋር የሚነሳው ጉዳይ የመቀነሻ መስፈርቶቹ

ናቸው፡፡ ያም ሆነ ይህ በአዲሱ ፓርቲ

የሚደረገው የስልጣን ሽግሽግ በውህደት

ወቅትና ከውህደት በኋላ ከሚገጥሙ

ፈተናዎች መካከል መሆኑ የማይቀር ነው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ከውህደት በኋላም፣

ከግል የስልጣን ጥማቸው ጋር በተገናኘ

በስልጣን ተዋረድ ውስጥ ሁለተኛ ሰው

ሆነው ለመስራት የማይፈልጉና ሁሌም ከኔ

በላይ ላሳር ባዮች አይጠፉም፡፡ በዚህም፣

እንዲህ አይነት ግለሰቦች አንዴ ከፖለቲካ

ሲርቁ፣ ሌላ ጊዜ ያችኑ የመሪነት ቦታ

ሲሰጣቸው ወደ መድረኩ ብቅ የሚሉ

ናቸው፡፡ የእነዚህ ግለሰቦች የስልጣን ጥም

የመሪነት ቦታ የነፈጋቸውን ፓርቲ ለቅቀው

ወደ ሌላ ፓርቲ እስከመሄድ የሚያደርሳቸው

ነው፡፡ ስለሆነም እነዚህን መሰል ግለሰቦች

ዛሬ ስለውህደት አብዝተው ቢሰብኩም

ያችኑ የመሪነት ቦታ የሚያሳጣቸው ጉዳይ

ሲመጣ ሲያቀነቅኑት የነበረውን ዓላማ

ረስተው የውህደቱ እንቅፋት ከመሆን

ላይመለሱ ይችላሉ፡፡

ደካማ የቀደመ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውህደት

ተሞክሮ ያለን ከመሆኑ ጋር ተያይዞ

(በቅንጅቱ መፍረስ የተፈጠረ መንፈስን

ማስታወስ ይበቃል፤) በህዝቡ ዘንድ ያለው

ተስፋ የመቁረጥ ስሜትም እንደ አንድ ሌላ

ፈተና ሊወሰድ የሚችል ነው፡፡ ፈጥኖ ወደ

ውህደት የመግባትን ያህል ከውህደት በኋላ

ተስማምቶ የመቀጠሉ ፈተናም ከባድ ነው፡

፡ ስለሆነም መዋሃዱ መልካም ሆኖ፣ ነገር

ግን አሁንም ከውህደት በፊት መሰራት

ያለባቸው የቤት ስራዎች በጊዜ ከተከናወኑ

በኋላ ቢሆን የተሻለ ውጤት ይኖረዋል፡፡

አሁን ላይ ውህደት ወይስ ትብብር?

ቀደም ብሎ እንደተጠቀሰው ውህደትን

ለማከናወን የተዋሃጅ ፓርቲዎች ፕሮግራም

ተመሳሳይ ወይም ተቀራራቢ መሆን

ይኖርበታል፡፡ በዚህም አንድ ፓርቲ ከሌላው

ጋር ለመዋሃድ መሰሉን ወይም ቢጤውን

መፈለግ ግድ ይለዋል፤ ይህም የሚሆነው

የሌላኛው ፓርቲ ፍላጎት ሲጨመርበት

ነው፡፡ እናም ውህደት አግላይ ጎንም

እንዳለው መገንዘብ ይቻላል፡፡ ለአብነትም

የመኢአድ ሊቀመንበር አቶ አበባው መሐሪ

የፓርቲያቸውን አቋም በሚከተለው መልኩ

ገልጸውታል፡፡

‹‹መኢአድ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ

ከማያምኑ የብሄር (የጎሳ) የፖለቲካ

ድርጅቶች፣ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ

አልደራደርም በማለት፣ በውህደት ደረጃ

አብሮ ለመስራት እቸገራለሁ የሚለው በቂ

ምክንያት ስላለው ነው፡፡›› (አንድነት ከአረና

ትግራይ ጋር ለመዋሀድ ንግግር መጀመሩ

የሚታወቅ ነው፡፡ ታዲያ መኢአድ በአንድነት

በኩል የመጣውን አረና ትግራይን እንዴት

ሊያደርገው ይሆን?) ያም ሆነ ይህ ጉዳዩ

የሚያሳየን የውህደትን አግላይነት ነው፡፡

ከመኢአድ አቋም ለመረዳት እንደሚቻለው

ፓርቲው ለውህደት በሩን የሚከፍተው

ጠንካራ ጥበቃዎችን ከፊት አቁሞ ነው፡

፡ ስለሆነም ውህደት የራሱ ጠንካራ ጎኖች

እንዳሉት ሆኖ፣ እንደ አሸን የፈሉትን

የፖለቲካ ድርጅቶች በጋራ አስተባብሮ ወደ

አንድ የማምጣቱ ነገር ውስን መሆኑን

ነው፡፡

በአብዛኛው የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች

የጋራ የሆነ የሚታገሉት ኃይል አላቸው፤

እሱም ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ነው፡

፡ እነዚህ ፓርቲዎች የየራሳቸው የተለያየ

ዓላማን አንግበው የሚንቀሳቀሱ ቢሆኑም

የወል ጉዳይ እስካላቸው ድረስ ግን መተባበር

ወደ ገፅ 6 ይዞራል
ነገረ-ኢትዮጵያ ቅፅ 1 ቁጥር 2 የካቲት 7 ቀን 2006 ዓ.ም. 4

ከዚህ በታች የቀረበው ጽሑፍ የሰማያዊ ፓርቲ ፕሬዚዳንት ኢ/ር ይልቃል

ጌትነት ፓርቲያቸው ጥር 25 ቀን 2006 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ባካሄደው

ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ያደረጉት ንግግር ነው፡፡

‹‹አገርን ከመቁረስ በላይ ምንም ነገር

ሊመጣብን አይችልም››

በዚህ ትውልድ እዚህ

ደረጃ ላይ ባለ ነገር

መነጋገራችን አሳፋሪና

አዋራጅ ነው፡፡ ሰው

ከአባቱ የተሻለ ነገር

እየሰራ፣ የነበረውን

እያሻሻለ፣ አገሩን

እያሻሻለ መሄድ ሲገባው

በአሁኑ ወቅት አገሩን እየቆረሰ የሚሸጥ

ጉደኛ መንግስት መጥቶብናል፡፡ እንዲህ

ያለውን ነገር በአንድ ላይ ቆመን፣

ተባብረን፣ መልክ ካላስያዝነው በስተቀር

አምባገነን ለስልጣኑ ሲል የማይሰጠው

ነገር ስለሌለ፤ ከዚህ በኋላ በፍርሃት፣

በመሸማቀቅ፣ ከስራዬ እሰናበታለሁ

በሚል፣ አምስት ለአንድ ይህን

ያደርገኛል እየተባለ የሚፈራ ከሆነ

በአገር ላይም የማንኖርበት ደረጃ ላይ

እንደርሳለን፡፡

ስለዚህ እነሱ የሚሉትን ከሰማን

ዘላለም ሊገዙን ይሞክራሉ፤ ክብራችን

ጨምሮ ሁሉን ነገራችንን አሳልፈን

እንድንሰጣቸው ይፈልጋሉ፤ ቅዳሜ

(ጥር 24) ቀንና ሌሊቱን ሙሉ የእኛን

ጓደኞች አስረዋቸዋል፡፡ ጥር 22ትም

ከቀኑ አምስት ሰዓት እስከ ምሽቱ

አስራ ሁለት ሰዓት አስረዋቸው፡፡ ነገር

ግን የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና

አባላት ከዓላማቸው፣በከሃሳባቸውና

እውነት ይዘው ከተነሱበት መንገድ

አንድም ፈቀቅ አይሉም፡፡ ምን ጊዜም

ቢሆን የኢትዮጵያ ጉዳይ ትልቅ ስራ

እያለ፣ የተለያየ የኑሮ ሁኔታ እያለ

ሁሉንም ነገር ተቋቁመው የሰማያዊ

ፓርቲ ወጣቶች ከረዕቡ ዕለት ጀምረው

በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የደህንነቶችን

ወከባ፣ ያለውን አፈና እየተቋቋሙ

ለሰላማዊ ሰልፉ ስላበቁን በሰማያዊ

ፓርቲ ስም ከልብ አመሰግናለሁ፡፡

ለኢትዮጵያ ወጣቶች ሁሌም የምናገረው

ነገር ቢኖር አምባገነን መንግስት

ያስረኛል፣ ይህን ያደርገኛል፣ ከዚህ

ስሄድ ይህኛው ነገር ይመጣብኛል

ከተባለ ትግል ሊኖር እንደማይችል

ነው፡፡ ትግል ከተባለ የሚመጣውን

ሁሉ ዋጋ እየተከፈለ ነው፡፡ የቋረኛው

ቴዎድሮስ ልጅ ስንሆን እኮ፤ እሱ

ክብሬን አላስደፍርም ብሎ ሽጉጡን

ጠጥቶ የተሰዋ ሰው አለ እያልን

ነው በየ ዘፈኑ የምናነሳው፡፡ ታዲያ

ይህንን ክብር የነበረው ሰው መሬቱና

ዳር ድንበሩ ሲወሰድበት፣ ዝም ብሎ

የሚያይ ከሆነ ይህ ትውልድ በታሪክ

ይጠየቃል፡፡ የምንጠየቀው ደግሞ የዚህ

ትውልድ አባላት ብቻ አይደለንም፡

፡ እነዛን አጥንታቸውን ከስክሰው፣

ደማቸውን አፍስሰው አገራችን

ያቆዩዋትን ታሪክ ብኩርናም መሸጥ

ነው፡፡ እነዚህን አባቶቻችንም መክዳት

ነው፡፡ በዚህ ዘመን የእኛን ትውልድ

አሳልፈን መስጠታችንም እራሳችን

መክዳት ነው፡፡ የወደፊቱን ትውልድ

ሃላፊነትም መካድ ነው፡፡ ስለዚህ አሁን

እኛ የምናደርገው ለድንበራችን መከበር

ጠንክረን ከሰራን የአባቶቻችን ታሪክ

እናስጠብቃለን፡፡ የእኛንም የወደፊት

ታሪክ እናስጠብቃለን፡፡ ወደፊት

የሚመጡትን ልጆችም በሙሉ ልብ

እንዲኖሩ እናደርጋለን፡፡

አሁን ግን ዝም ብለን ይህን ሁሉ

ነገር ካለፍን ስለ ቴዎድሮስ መዝፈን

አይቻልም፤ ከዚህ በኋላ ስለ አጼ

ዮሃንስ መዝፈን አይቻልም፡፡ መዝፈን

የምንችለው የእነሱን ክብር የሚያስጠብቅ

ትውልድ መሆን ከቻልን ብቻ ነው፡

፡ ይህንን የማያደርግ ትውልድ ከሆነ

አፋራም ትውልድ ነው፣ ብኩርናውን

ሽጧል፣ አባቶቻችን አዋርዷል፣ራሱንም

አዋርዷል፣ ቀጣዩ ትውልድም በእሱ

ምክንያት አንገቱን ደፍቶ እንዲኖር

አድርጓል ማለት ነው፡፡

ስለዚህ ይህ የአገር ጉዳይ ቀላል ጉዳይ

አይደለም፡፡ አባቶቻችን የደሙበት ነው፡

፡ አጥንት የተከሰከሰበት ነው፡፡ ክብራችን

ብለን ለነጻነት የቆምንበት ነው፡፡ ለዚህ

የሚደረገው ትግል እንደማንኛውም

ትግል በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡

፡ ለእኔ ዴሞክራሲና መልካም

አስተዳደር ቅንጦት ነው፡፡ አገርን

ከመቁረስ በላይ ግን ሌላ ምንም ነገር

ሊመጣብን አይችልም፡፡ ይህንን ጉዳይ

ዝም ብለን የምናይ ከሆነ አሁን ያለው

የኢትዮጵያ ትውልድ በታሪክ ፊት

እንዳፈረ ይኖራል፡፡ ስለሆነም ወገኖቼ!

አምባገነኖች ይሄዳሉ፣ ትውልድ

ይሄዳል፣ አገርና ህዝብ ግን ዘላለም

ይኖራል፡፡ በዚህ ለዘላለም በሚኖር

አገርና ህዝብ ክብራችን ጠብቀን መኖር

አለብን፡፡

የኢትዮጵያ ልጆች ሁሉ ለአፍሪካም

ሆነ ለዓለም የነጻነት ምሳሌ ነን፡፡

አባቶቻችን የነጻነት ምሳሌዎች ናቸው፡

፡ እኛም በየትኛውም ዓለም ልባችንን

ሞልተንና ቀና ብለን የምንሄደው

አባቶቻችን በከፈሉት መስዕዋትነት

ነው፡፡ ይህንን ብኩርናችንን፣

ነጻነታችንን፣ ተምሳሌትነታችንን

አሳልፈን እንዳንሰጥ የሚሆነውን ሁሉ

በንቃት እንድንከታተል አሳስባለሁ፡

፡ ስልጣን ላይ ያሉት ሰዎች ለአንድ

ሰሞን ስልጣን፣ ለአንድ ሰሞን ገንዘብና

ለሚያልፍ ነገር ብለው ይህን ሁሉ

በደል ከመፈጸምና ራሳቸውን ከታሪክ

ተጠያቂነት ጠብቀው፣ ቆም ብለው

ጉዳዩን ሃላፊነት በተሞላበት መንገድ

እንዲያዩትና ከህዝብ ጋር ግልጽ

ውይይት አድርገው የህዝብን ታሪክና

አንድነት ሳያናጉ የኢትዮጵያን ብሄራዊ

ጥቅም አስከብረው ከማፈርና ከውርደት

እንዲድኑ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ!!

መመረጥ በሌላው ድክመት...

አጠናክሮ የፕሮፓጋንዳ ብቻ ሳይሆን የተግባር

ታጋይ ሆኖ ለመውጣት የሚያስችል ሥራ

በየፓርዎቹ በተግባር መታየት መቻል አለበት፡

፡ የፓርቲ መሪዎች ቢመረጡ በተሻለ ሀገር

የመምራት አቅሙም እውቀቱም ያላቸው

መሆኑን ፓርቲ ውስጥ በሚሰጡት አመራርና

በሚያስመዘግቡት ለውጥ ማሳየት መቻል

ይኖርባቸዋል፡፡

በሕዝቡ የተባበሩ ጥያቄ በተለያዩ ግዜያት

የተፈጠሩ መተባበሮች የእንቧይ ካብ እየሆኑ

ወይ ኀብረት ሳናይ ወይ አንድና ሁለት ጠንካራ

ፓርቲ ሳናይ 21 ዓመታትን ቆጠርን፡፡ ምርጫ

2002 ያስተባበራቸው የምርጫ 97ን ውጤት

መናዳቸው አስቆጭቶአቸው በምርጫ 2007

የተሻለ ነገር ለመስራት የሚያስችል ዝግጅት

ሊያደርጉ በሚገባቸው ወቅት ስለምርጫ

እያሰቡ መሆናቸውን እንኳን የሚጠቁም ነገር

አይታይም፡፡ ይህም በራስ ብቃት ተወዳዳሪ

መሆንን ያለሙ አለመሆናቸውን ያሳያል፡፡

የአመለካከት ጥራት፣ ድርጃታዊ ብቃት፣

ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው አሰራር

የውይይት ባህል የዳበረበት ዴሞክራሲያዊ

አሰራር የሚስተዋልበት ጠንካራ የህዝብን

ይሁንታ ያተረፈ ፓርቲ መፍጠር ብዙ ዋጋ

የሚያስከፍል ከባድ ስራ ነው፡፡ የሌላውን

ጉድለት እያወሩ የሕዝብን ብሶት እየነካኩ

ለመመረጥ ማሰብ ግን ቀላል ግን ተፈላጊውን

ውጤት የማያስገኝ መንገድ ነው፡፡ በመተባበር

ካባ ተሸፍኖ መቅረብም እንዲሁ፡፡

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በተዋቂ ግለሰብነት

በመሰረቱትና ኋላም የአንድነት ሊቀመንበር

በመሆናቸው በነበራቸው የመድረክ ተሳትፎ

ከተገነዘቡት ተነስተው «….በአሁኑ ሁኔታ

ከተጠቀሱት ድርጅቶች ለመዋሀድ በጣም ከባድ

ነው ያስቸግራል፡፡ ወደ ውህደት ለመምጣት

ብዙ ውይይቶች ብሎም አብሮ መስራ

ያስፈልጋል፤ መተዋወቅ አለብን፡፡ የድሮው

ቁስሎች መረሳት አለባቸው፡፡» (ኢትዮ ምህዳር

ታህሣሥ 30/2006) በማለት የተናገሩት

በተግባር ካዩት ተነስተውና እውነትነቱ

የሚያጠያይቅ አይደለም፡፡ ስለሆነም በውህደት

ካርድ ለመጫወት የሚያስቡ ፖለቲከኞች

በርግጥ ለውጥ አልመው ለዛም የሚያበቃ

ድርጅታዊ ብቃት ፈጥረው ሳይሆን በእድሜ

ከ ገፅ 13 የዞረ

ማራዘሚያነት ለመጠቀም ነውና ለመርጫ

2007 የሚፈይደው የለም፡፡

ስለሆነም በርግጥ ለለውጥ የሚታገሉና

ተቀዋሚ እየተባሉ በዚህም የሚገኘውን

እየቀማመሱ መኖርን የመረጡ ይለዩ፡፡

የመጀመሪያዎቹ ሰላማዊ ትግል ያለምርጫ

ምርጫ ያለብቃት እንደማይሳካ የለውጥ

መገኛው መንገድም ምርጫ መሆኑን አምነው

ምርጫ 2007 ከተበላሸ በህዝቡ ዘንድ ሊፈጠር

የሚችለውን የመጨረሻ ተስፋ መቁረጥ

ከወዲሁ ገምተው ሕዝብ ተስፋ በቆረጠበት

ሀገር ሰላማዊ ትግል ፋይዳ እንደማይኖረውም

ተገንዝበው ሌላ ሌላውን ጨዋታቸውን

ሁሉ አቁመው በ2007 ምርጫ ውጤት

ለማምጣት ምን እናድርግ የሚል ምክክር

ሊጀምሩና በምርጫው ውጤት ለማስመዝገብ

የሚያበቃቸውን አቅም በተናጠልም ሆነ

በጋራ ለመገንባት መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡

መመረጥ የሚቻለው የመራጩን ቀልብ መሳብ

የሚችል ብቃት ላይ ሲገኙ ነውና፡፡

ጊዜ ቆሞ አይጠብቅም ምርጫ 2007

እየቀረበ ነው፡፡ ኢህአዴግ ለምርጫ መስራት

የጀመረው 99.6 በመቶ ባሸነፈበት ምርጫ

ማግስት ነው፡፡ ከተቃውሞው ሰፈር የሚሰማ

ነገር የለም፣ ሕዝቡ ሁሉንም በትዝብትና

በአረምሞ በዝምታ እያስተዋለ ነው፡፡ ለጽሁፌ

ማሳረጊያነት ሎሬት ጸጋየ ገብረ መድህን

ከምርጫ 97 በፊት የካቲት 1/97 ከታተመችው

ጦቢያ መጽሔት ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ

ከተናገረው ልዋስ (አንቱ ያላልኩበት

ምክንያት ለአንባቢያን ግልጽ ይመስለኛል፡፡)

{የሕዝብን እውነት በልብ ሳይቋጥሩ ሕዝብ

ግንባር ፊት መቆም እንደ ወያኔ ድፍረት

ሕዝብን ማርከስ ነው፡፡ መተባበር ያቃተው

‹ኀብረትና ቅንጅት› ደግሞ ሕዝብን

ሊያስተባብር አይችልም፡፡ አለንልህ የሚሉት

ፖለቲከኞች ርስ በርሳቸው ሲጠላለፉ እያየ

ሕዝቡ በመራራ ትዝብት ያስተውላቸዋል፡፡

አይቆስሉ ቁስለት ማለት የኢትዮጵያ ሕዝብ

ቁስለት ነው፡፡ አይችሉ መቻል ማለትም

የኢትዮጵያ ሕዝብ መቻል ነው፡፡ ‹‹በላይ እሳት

በታች እሳት› እንደ ድፎ ዳቦ እየነደደ በፅናቱ

ብቻ ሳይሆን ሕዝቡ በትእዝብቱም ቀድሞናል፡

፡} ነፍሱን ይማረውና ሎሬት ዛሬ ቢኖር ምን

ይል ነበር!
5 የካቲት 7 ቀን 2006 ዓ.ም. ቅፅ 1 ቁጥር 2 ነገረ-ኢትዮጵያ

ፖለቲካ

‹‹መንግስት›› አሳልፎ የሰጠው

ሉዓላዊነት

ጌታቸው ሺፈራው

ለአንድ አገር ሉዓላዊነት ቁልፍ

ከሚባሉት ጉዳዮች መካከል

ወሰን ዋነኛው መመዘኛ ነው፡፡

የወሰን/የድንበር ጉዳይ ድንበር

ብቻ ሳይሆን ከድንበሩ ጋር

ያለውን ታሪካዊ ሂደትም ይጨምራል፡

፡ ለአንድ መንግስትና ትውልድ የቀደሙ

አባቶች ያኖሩትን ድንበር የመቆጣጠርና

መጠበቅ ታሪካዊ ግዴታቸው ነው፡፡

የውጭ አሊያም ሌላ ሀይል የኖረውን

የአገሪቱን ድንበር የሚደፍር አሊያም

የሚያስቀይር ከሆነ የአገሪቱ ሉዓላዊነት

አደጋ ውስጥ ወድቋል ማለት ነው፡

፡ የአንዲት አገርና ህዝቧ ያለ ድንበር/

ወሰን ሊኖር አይችልም፡፡ አገሪቱ ብቻዋን

መሆን እንደማትችል ሁሉ ክብሯን፣

ታሪኳን፣ የዕለት ተዕለት እንቅስቀቃሴዋ፣

ደህንነቷ ላይ ድንበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ

ይኖረዋል፡፡

የወሰን አለመከበር ወይንም ሌላ ችግር

እኒህን ሁሉ ጉዳዮች የሚያዛባ ይሆናል፡፡

ለዚህም ነው ሌሎች አገራት ከሚሰጡት

እውቅና ይልቅ ድንበር የአንድ አገር

በተጨባጭ /የሚታይ/ ሉዓላዊነት

መገለጫ ነው የሚባለው፡፡ ድንበር

ዋነኛው የሉዓላዊነት አካል ስለመሆኑ

የኢትዮጵያ ህዝብ ሲበድሉት የኖሩት

አገዛዞች ‹‹አገርህ ተደፈረች›› ሲሉት

ለጊዜውም ቢሆን ልዩነቱን ወደጎን ትቶ

ዳር ድንበር ሊያስከበር ሲተም መኖሩ

ትልቅ ማስረጃ ነው፡፡ በተቃራኒው

መንግስታቱ ለሉዓላዊነት የህዝብን ያህል

ቁርጠኛ ሆነው አልተገኙም፡፡ በዚህ በኩል

ደግሞ ኢህአዴግ ሉዓላዊነትን አሳልፎ

በመስጠት ወደር አልረገኘለትም፡፡

አንድ አገር ሉዓላዊ የምትሆነው አሊያም

ይህ ክብር የሚቀጥለው ድንበሯን፣

ታሪኳንና የህዝብን ጥቅም አስጠብቆ

የሚኖር አገር ወዳድ መንግስት ሲኖራት

ብቻ ነው፡፡ በዚህ በኩል የአሁኗ

ኢትዮጵያ አልታደለችም፡፡ የአገርን

ጥቅም፣ በደምና በአጥንት የተገነባን

ታሪክና ድንበር አሳልፎ የሚሰጥ አካል

ባለበት የአገሪቱ ሉዓላዊነት አደጋ

ውስጥ ይገባል፡፡ ሉዓላዊነት የአንዲት

አገር ከሌሎች አገራት ጋር ሲነጻጸር

ያላት እኩል ክብር፣ ህጋዊ ሰውነት

እንደመሆኑ መንግስት የሚባለው አካል

ወሰኗን ባልተገባ መንገድ ለሌሎች

አሳልፎ የሚሰጥ ወይንም የሚወሰድበት

ከሆነ ሉዓላዊነቷ ተደፍሯል ማለት ነው፡

፡ ህወሓት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት

ማስደፈር የጀመረው ገና በርሃ በነበረበት

ወቅት ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ከማንም

ቀድሞ በየጊዜው ሰራዊት ወደ ሶማሊያ

የሚልከው ህወሓት ያኔ ገና በርሃ እያለ

ተስፋፊውን የሶማሊያ መንግስት እስከ

ድሬዳዋ ድረስ መንገድ መምራቱን

እንደ አስግደ ያሉት የቀድሞው የቡድኑ

አባላት እማኝነታቸውን በይቅርታ መልክ

ገልጸዋል፡፡

ህወሓት እንደ ፖለቲካ ቡድን

ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ኤርትራ

የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት እንደሆነችና ነጻ

መውጣት እንዳለባት ሲሰብክ ኖራል፡፡

ህወሓት ‹‹አሸባሪ›› በነበረበት በዛ ወቅት

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ

መለስ ዜናዊ ስለ ኤርትራ ጉዳይ ሁለት

መጽኃፍትን ጽፈዋል፡፡ ‹‹የኤርትራ

ህዝብ ትግል ከየት ወደየት›› በተሰኘው

መጽኃፋቸውም ኤርትራን ከኢትዮጵያ

ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌላት

ነጻ አገር መሆኗን አውጀዋል፡፡ አቶ

መለስና ህወሓት ይህን በሚሉበት ወቅት

በርካታ የኤርትራ ተወላጆች በአገሪቱ

አሁን ህወሓት ለሌሎች የግንባሩ አባል

ፓርቲዎች አሳልፎ የማይሰጣቸው ቁልፍ

ስልጣን እንደነበራቸው አይዘነጋም፡፡

ገና ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ኤርትራን

ከኢትዮጵያ መነጠልን አላማው አድርጎ

የተነሳው ህወሓት ደርግን አሸንፎ ቤተ-

መንግስት ሲገባ የወሰደው እርምጃ

የዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ ኤርትራን

እውቅና እንዲሰጥ ማድረግ ነበር፡፡ ይህም

ኢህአዴግን የዋናዋ አገር ገዥ ሆኖ

የአገሪቱ ክፍልን በፈቃደኝነት ያስገነጠለ

(ሉዓላዊነቷን አሳልፎ የሰጠ) ብቸኛው

ፓርቲ ሳያደርገው አይቀርም፡፡ ኤርትራን

በገዛ እጁ ያስገነጠለው ህወሓት/ኢህአዴግ

ከሻዕቢያ ጋር የነበረው ፍቅር ሲያልቅ

የአገሩ ሉዓላዊነት ተላልፎ የተሰጠበት

የኢትዮጵያ ህዝብ በደሉን ለጊዜው ወደጎን

ትቶ ዳር ድንበሩን ለማስከበር ሲነሳ አገዛዙ

የማይጨነቅለትን ሉዓላዊነት ለማስከበር

እንደማይደክመው አሳይቷል፡፡ ጦርነቱ

በኢትዮጵያ ህዝብ አሸናፊነት ከተጠናቀቀ

በኋላም ቢሆን ህወሓት የለመደውን

ሉዓላዊነት አሳልፎ የመስጠት ልክፍት

ደግሞታል፡፡ ይህ አልበቃው ሲልም

ህዝብ ከእሱ በላይ ለአገሪቱ ሉዓላዊነት

እንደሚጨነቅ ጠንቅቆ ስለሚያውቅም

‹‹ባድመን አግኝተናል!›› በሚል ህዝብን

አሞኝቷል፡፡ ይህም ህወሓት/ኢህአዴግ

ከሉዓላዊነት ጋር ያላውን ተቃርኖ

በጉልህ የሚያሳይ ነው፡፡

የኢህአዴግና የሉዓላዊነት ተቃርኖ

አሁንም ቀጥሏል፡፡ ከስድስትና ሰባት

አመታት ጀምሮ የኢትዮጵያን መሬት

አሳልፎ ለሱዳን ለመስጠት በድብቅ

እየተዋዋለ መሆኑ ሲነገር ቆይቷል፡

፡ በቅርቡ ደግሞ ‹‹ሱዳን ትሪብዩን››

የተባለው የሱዳን ጋዜጣ ‹‹ለም መሬታችን

አገኘን!›› የሚል ዜና ማውጣቱን ተከትሎ

ኢህአዴግ መሬቱን ለመስረከብ መቃረቡን

አመላክቷል፡፡ የአንድ አገር መንግስት

የአገሪቱን ድንበር ማስጠበቅና ማስከበር፣

የዜጎቹን ጥቅም ማስከበር ሲኖርበት

ለራሱ ግላዊ ጥቅም፣ ህጋዊ መሰረት

በሌለው መንገድ የአገሩን ወሰንና ድንበር

አሳልፎ የሚሰጥ ከሆነ በአገር ውስጥ

የሌሎች ወኪል ሆኖ የአገርን ሉዓላዊነት

እየደፈረ ከመሆን ውጭ ሌላ ሊባልለት

አይችልም፡፡

ይህ የ‹‹መንግስት›› ተግባር ልክ ቅኝ

ገዥዎቹ የራሳቸው ታማኞች (ባንዳዎች)

እንደነበሯቸው ማለት ነው፡፡ አንዲት

በመንግስት ስር የምትገኝ አገር ሉዓላዊ

የምትባለው ይህ መንግስት የአገሪቱን

ወሰንና ሌሎች ጥቅሟን በህጋዊ መንገድ

መቆጣጠርና ማስተዳደር ከቻለና

በጥቅምም ይሁን በአቅም ማነስ ለውጭ

ሀይል የአገሪቱን ጥቅም፣ ክብር፣ ወሰን

አሳልፎ የማይሰጥ ከሆነ ብቻ ነው፡፡

አገሪቱን ሁለመናው ነገር ተቆጣጥሮና

እያስተዳደረም ቢሆን በውጭ ሀይል

ተጽዕኖ ውሳኔ የሚያስተላልፍ፣

የአገሪቱን ጥቅም አሳልፎ የሚሰጥ

ከሆነ የአገሪቱ ሉዓላዊነቷ ተደፍሯል፡

፡ የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን አሳልፎ

ለመስጠት እየተደራደረ ያለው ኢህአዴግ

የአገርን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ፣ ለህዝብ

ጥቅም በመቆም ከሚታወቅ ‹‹መንግስት››

ከተባለ አካል ይልቅ በሚገዛት አገር

ውስጥ ለሱዳን ጥቅም የቆመ መሆኑን

አሳይቷል፡፡

አንድ አገር ሉዓላዊ ነው የሚባለው

የአገሪቱን ዜጎች ከውጭ ጥቃት

የሚከላከል አካል (መንግስት) ካለ ብቻ

ቢሆንም የሱዳን ኢትዮጵያ ድንበር

ችግር ከተከሰተ በኋላ በመተማና

አካባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን

ለሱዳን የደህንነት ኃይሎች ተላልፈው

ተሰጥተዋል፡፡ ከስድስትና ሰባት አመት

በፊት ደንብር አካባቢ የነበረው የኢትዮጵያ

ሰራዊት ወደኋላ አፈግፍጎ አርሶ አደሮቹ

ከሱዳን የጸጥታ ሀይሎች ጋር ፊት ለፊት

እንዲጋፈጡ ተፈርዶባቸው እንደነበር

በጊዜው ተዘግቧል፡፡ አሁንም ቢሆን

የሱዳን እስር ቤት ውስጥ የሚማቅቁ፣

ሀብትና ንብረታቸው የሚዘረፍና

በርካታ ሰብዓዊ ጥሰት የሚፈጸምባቸው

መኖራቸው እየተነገረ ነው፡፡ ይህን ሁሉ

የሚያደርገው ከኢትዮጵያ መንግስት

ይሁንታን ያገኘው የሱዳን የደህነነት

ሀይል ነው፡፡ በዚህ ረገድ መንግስት

የመጀመሪያውን ህዝብን ከውጭ ጥቃት

የመከላከል የሉዓላዊነት መርህ አሳልፎ

ሰጥቷል፡፡ የራሱ ህዝብ በውጭ ሃይል

አደጋ እየደረሰበት ዝም ማለት ብቻ

ሳይሆን ሱዳኖች ኢትዮጵያውያንን

እንዲያስለቅቁ የፈቀደው መንግስት

የመጀመሪያው የአገሪቱን ሉዓላዊነት

አሳልፎ የሰጠ አካል ነው፡፡

የዓለም አቀፍ ህግን የጣሰው

ድብቅ ስምምነት

የአንድ መንግስት ዋነኛው

ተግባር አገር ውስጥ ህዝብን

የሚያስተዳድርበትን፣ አገሪቱ ከውጭ

አካላት ጋር የምትገናኝበትንና ጥቅሟን

የምታስከብርበት ህግና አግባብ የአገሪቱን

ጥቅም በሚያስከብር መንገድ መቅረጽ፣

ማስከበርና መተግብር ነው፡፡ ዓለም

አቀፍ ህግ ከእዚህ መካከል አንዱ ነው፡

፡ ኢትዮጵያ ከፈረመቻቸው ዓለም

አቀፍ የድንበር ስምምነቶች መካከል

ደግሞ አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገራት ነጻ

ከወጡ በኋላ የተፈራረሙት ‹‹የካይሮ

ስምምነት›› በአብነት ይጠቀሳል፡፡

አንድ አይነት ቋንቋ የሚናገሩ የአፍሪካ

ህዝቦች ለቅኝ ገዥዎች በሚመችና

ዘፈቀደ ድንበር ተከፋፍለው ተገዝተዋል፡

፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ግልጽ ከሆነው

ይልቅ በየጊዜው የሚቀየሩ የቅኝ ገዥ

አስተዳዳሪዎች፣ እርስ በእርሳቸው

በሚወዳደሩ የምዕራባዊያን አገራት

እንዲሁም የአገር ውስጥ ወኪሎች

(ባንዳዎች) ግራ የሚያጋባ ድንበር መሰረት

ተከፋፋለው ኖረዋል፡፡ ለአብነት ያህል

በሁለትና ሶስት የቅኝ ገዥዎች፣ እነዚህ

አገራትን ወክለው፣ አሊያም ለእነዚህ

አገራት ወኪል ሆነው ለየራሳቸው ጥቅም

ከተሸነሸኑት በርካታ ወሰኖች መካከል

አንዲት አገር በስተመጨረሻ ነጻ ስትወጣ

የያዘችውን ይዛ እንድትቀጥል ነው

የተደረገው፡፡ ይህ ግልጽነት የጎደለው

ድንበር፣ የድንበር ክለላም ለግጭት

መሰረት እንደሚሆን የታመነበት የአፍሪካ

አገራት ነጻ ከመውጣታቸው አስቀድሞ

ነው፡፡ በተለይም የተለያዩ አካላትና

ግለሰቦች የየራሳቸውንና ለራሳቸው

የሚጠቅመውን ድንበር የሚያቀርቡ

መሆኑ ግጭቱን የባሰ እንደሚያደርገው

ታምኖበታል፡፡ ይህም በመሆኑ የአፍሪካ

ህብረት ቻርተር ከጸደቀ ከአመት በኋላ

ይህን ችግር ለመቅረፍ የአፍሪካ አንድነት

ድርጅት በካይሮ ተገኝቶ ቀኝ ገዥዎች

ተክለውት የሄዱትን የድንበር ችግር

ይፈታል ያለውን ስምምነት አጽድቋል፡፡

የዚህ ስምምነት አላማ በቅኝ ግዛት ወቅት

በቅኝ ገዥዎች፣ በግለሰቦች፣ በአገርም

ሆነ በውጭ ቡድኖች አማካኝነት በዘፈቀደ

የተከለሉ ድንበሮች የሚያመጡትን ችግር

ለመቅረፍ የአፍሪካ አገራት ነጻ ሲወጡ

የያዙትን ወሰን ይዘው እንዲቀጥሉ

ማድረግ ነው፡፡ ሌሎች አገራትም

የጎረቤቶቻቸውንም ሆነ የሌሎች ነጻ

ሲወጡ የነበራቸውን ድንበር ማክበር

እንዳለባቸው የሚያሳይ ነው፡፡ ይህ ህግ

እ.ኤ.አ በ1963 በጸደቀው የአፍሪካ ህብረት

ቻርተር ላይም በግልጽ ተቀምጧል፡

፡ የ1963 ቻርተር እንዲሁም በሀምሌ

1964 የተፈረመው ስምምነት “to respect

the frontiers existing on their

achievement of independence”

ወይንም አገራት ነጻ ሲወጡ የነበራቸውን

ወሰን/ድንበር የማክበር ግዴታን አጽንኦት

ሰጥቶ አስቀምጧል፡፡ ይህ ችግር አሁንም

ድረስ ባለመቀረፉ የአሁኑ አዲሱ

የአፍሪካ ህብረት ቻርተርም በአንቀጽ

4(b) ‹‹respect of borders existing

on achievement of independence››

ወይንም አገራት ነጻነት ሲያገኙ

የነበራቸውን ድንበር ማክበርን የሚለውን

መርህ በቀዳሚነት አስቀምጦታል፡፡

የአፍሪካ ህብረት ሚኒስትሮች እ.ኤ.አ

በየካቲት 25 2010 አዲስ አበባ ላይ

‹‹DECLARATION ON THE AF-

RICAN UNION BORDER PRO-

GRAMME AND THE MODALI-

TIES FOR THE PURSUIT AND

ACCELERATION OF ITS IMPLE-

MENTATION›› የሚል ሰነድ በህብረቱ

ስም ተፈራርመዋል፡፡ ሰነዱ ግጭትን

ለመከላከል፣ ህብረትን ለማጠናከር ያለመ

ነው፡፡ ይህ ስምምነት መሰረቱ ያደረገው

‹‹አገራት ነጻ ሲወጡ የያዙትን ድንበር

ይዘው መቀጠል፣ የሌሎቹንም ማክበር

ይኖርባቸዋል›› ከሚለው የካይሮው

ስምምነትን የመነጨ ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት ለሱዳን ይሰጣል የተባለው

መሬትን ስምምነት እ.ኤ.አ በ1902 እና

በ1907 እንደተደረገ ታሪክ ያስረዳል፡

፡ ሆኖም መንግስታቱ መካከል ይህ

በእውን ሳይተገበር መቅረት ብቻ ሳይሆን

ሻለቃ ጉይን የተባለው የእንግሊዝ አዛዥ

መንግስታቱ ከተስማሙበትም ውጭ

ብቻውን ያሰመረው መሆኑ ይታወቃል፡

፡ ያም ሆኖ ሱዳን ነጻ ስትወጣ የያዘችው

ድንበር የዚህን የሻለቃ ድንበር አይደለም፡

፡ የአፍሪካ አንድነት ቻርተር፣ የካይሮ

ስምምነት፣ የአፍሪካ ህብረት ቻርተርና

እዚህን መርሆች መሰረት አድርገው

በየጊዜው በድንበር ጉዳይ የሚወጡ ህጎች

እያሉ በአሁኑ ወቅት እነዚህን ህጎች

በሚጻረር መልኩ ሱዳን ነጻ ስትወጣ

ከነበራት ድንበር ወደ ኢትዮጵያ እስከ

40 ኪሎ ሜትር የሚገባ መሬት ሊሰጣት

መሆኑ ይፋ ሆኗል፡፡

የካይሮን ስምምነት፣ የአፍሪካ ህብረት

ቻርተርና ሌሎችንም ከሁለቱ የሚመነጩ

የድንበር ህጎች በሚጻረር መልኩ

የሚተገበር ተግባር ይበልጡን አስገራሚ

የአንድ መንግስት ዋነኛው ተግባር አገር ውስጥ ህዝብን የሚያስተዳድርበትን፣ አገሪቱ ከውጭ

አካላት ጋር የምትገናኝበትንና ጥቅሟን የምታስከብርበት ህግና አግባብ የአገሪቱን ጥቅም

በሚያስከብር መንገድ መቅረጽ፣ ማስከበርና መተግብር ነው፡፡ ዓለም አቀፍ ህግ ከእዚህ መካከል

አንዱ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከፈረመቻቸው ዓለም አቀፍ የድንበር ስምምነቶች መካከል ደግሞ

አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገራት ነጻ ከወጡ በኋላ የተፈራረሙት ‹‹የካይሮ ስምምነት›› በአብነት

ይጠቀሳል፡፡

የሚሆነው ሌሎቹ ቅኝ ግዛት ስር

በነበሩበት ወቅት የራሷ ወሰን የነበራት

የህብረቱ መስራችና መቀመጫ ኢትዮጵያ

ላይ መሆኑ ነው፡፡ ህግጋቱን ጥሶ

የአገሪቱን መሬት ከድሮው እንደለመደው

መሬትን ብቻ ሳይሆን ‹‹ሉዓላዊነትን››

ለሌሎች በገጸ በረከትነት የሚያስረክበው

ደግሞ ኢትዮጵያን እወክላለሁ በሚለው

‹‹መንግስት›› መሆኑ ኢህአዴግ

ከሉዓላዊነት ጋር ምን ያህል እንደተጣላ

የሚያሳይ ነው፡፡

ሱዳኖችን ጨምሮ መሬቱ ለሱዳን

መሰጠት እንዳለበት ለሚያምነው

ኢህአዴግ ዋነኛው መከራከሪያ

ብሪታኒያና አጼ ምኒልክ በድንበሩ ጉዳይ

ቢዋዋሉም መሬቱ በኢትዮጵያ ቁጥጥር

ስር መቆየቱን ነው የሚያነሱት፡፡ በጉዳዩ

ጥናት ካደረጉት አምስት ኢትዮጵያውያን

መካከል በህይወት የሚገኙት ፕ/ር

መስፍን ወ/ማሪያም ጥር 17/ 2006

ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ ተገኝተው

እንዳስረዱት፤ አሁን በኢትዮጵያና ሱዳን

መካከል አጨቃጫቂ ነው የሚባለውን

ድንበር የከለለው ሻለቃ ጉይን የተባለው

የእንግሊዝ አዛዥ ብቻውን ሆኖ ነበር፡፡

በወቅቱ ኢትዮጵያ ወኪል አልነበራትምና

ስምምነቱ አይገዛትም ማለት ነው፡

፡ ሻለቃው እንዳፈተተው በሚከልልበት

ወቅትም ቢሆን የድንበር ለውጥ

በመደረጉ ድንበሩ ወደ ሱዳን ገባ

ብሎ እንደሚከለል ደብዳቤ ደርሶታል፡

፡ ሆኖም ሻለቃው ከብሪታኒያ ክልል

ካለችው ውጭ ወደ ኢትዮጵያ መሬት

ገብቶ የራሱን ዘፈቀደ ድንበር አስቀምጦ

አልፏል፡፡ ይህ ሆኖ እያለ ኢትዮጵያን

ወክያለሁ የሚለው ኢህአዴግ በዚህ

በተዛባ ህግ፣ አንድ የቅኝ ገዥ መኮነን

ያሰመረውን የተሳሳተና ያልተገባ ድንበር

የሚቀበል ከሆነ ምን አልባትም ለራሱ

ጥቅም ሲል ብቻ ተጠቀመበት እንጂ

ለስልጣን የማይጠቅመው ቢሆን የአባይን

ስምምነትንም መቀበሉ የማይቀር

እንደነበር ነው የሚያሳየው፡፡

አሁን ለሱዳን ይሰጣል የተባለው መሬት

የኢትዮጵያ አካል በነበረበት ወቅት

ሱዳን ገና ነጻ አልወጣችም፡፡ በመሆኑም

ከአፍሪካ አንድነት ቻርተር ጀምሮ፣

በካይሮ ስምምነት፣ በአዲሱ የአፍሪካ

ህብረት ቻርተርና በየጊዜው ድንበርን

በተመለከተ በሚወጡት ህጎች መሰረት

ድንበሩ የኢትዮጵያ እንጂ የሱዳን ሊሆን

አይችልም፡፡ ከመቶ አመት በፊት በአንድ

የቅኝ ገዥ መኮነን የተደረገን የመከለል

ሙከራ እውነት አድርጎ ለሌላኛው አገር

አሳልፎ መስጠት ከአንድ አገር መንግስት

የሚጠበቅ አይደለም፡፡ ኢህአዴግ

ኢትዮጵያ ውስጥ ስልጣን የያዘበት

ጊዜ ዓለም ከጦርነት ይልቅ ወደ ሰላም

የመጣችበትና በህግ የምትመራበት ነው፡

፡ በዚህ ዘመን የአንድ አገርን ሉዓላዊነት

ለማስጠበቅ ፈተናዎች የማይበዙበት

ዘመን ነው፡፡ ከዚህ ይልቅ በርካታ

የኢትዮጵያ መንግስታት የአገሪቱን

ሉዓላዊነት የሚፈታተኑ አጋጣሚዎችን

በጽናት አልፈዋል፡፡

ኢህአዴግ በጣሊያን ወረራም ሆነ በሌሎች

የአገሪቱ ሉዓላዊነት ጥያቄ ውስጥ

በገባበት ወቅት ገዥ ቢሆን ኖሮ ራሱ

ምንዳ እስካገኘ ድረስ ሙሉ በሙሉም

ይሁን የውጭ ሀይሎች በሚፈልጉት

መልኩ አገሪቱን አሳልፎ ይሰጥ እንደነበር

ለመገመት አይከብድም፡፡ በእርግጥ

አሁንም ቢሆን ሉዓላዊነትን አሳልፎ

መስጠቱ ለሱዳን በሚሰጠው መሬት

ይቆማል ተብሎ የሚገመት አይደለም፡

፡ ፕ/ር መስፍን ውይይቱን በመሩበት

ወቅት ለህዝብ መልሰው የጠየቁት

ጥያቄም ‹‹ኢህአዴግ በቀጣይነት አሳልፎ

የሚሰጠው የትኛውን መሬት ይሆን?››

የሚል ነበር፡፡ ከተሳታፊዎችም ‹‹አዲስ

አበባንስ መቼ ያስከልሏት ይሆን?››

የሚል ጥያቄ ተነስቷል፡፡ ይህ እንግዲህ

ኢህአዴግ ምን ያህል ለሉዓላዊነት

የማይጨነቅ መሆኑና በጉዳዩ ታማኝነቱን

ማጣቱን በግልጽ የሚያሳይ ሀቅ ነው፡፡
ነገረ-ኢትዮጵያ ቅፅ 1 ቁጥር 2 የካቲት 7 ቀን 2006 ዓ.ም. 6

ውህደት ወይስ ትብብር...

ይችላሉ ማለት ነው፡፡ ትብብር አቃፊ

ነው፡፡ የጎሳ ፓርቲውም ሆነ ህብረ-

ብሄራዊው ፓርቲ በጋራ ጉዳዮች ላይ

ተባብረው ከመስራት የሚያግዳቸው

ነገር ሊኖር አይችልም፡፡

በዚህ ረገድ ሰማያዊ ፓርቲ ከማናቸውም

ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ጋር በትብብር

ለመስራት ፍላጎቱ እንደሆነ ሲገልጽ

ይደመጣል፡፡ ፓርቲው እንደሚለው፣

ከውህደት በፊት የሚቀድሙ የቤት

ስራዎችን መስራት ተገቢ ነው፤

ለዚህም ትብብር ከውህደት ይቀድማል

የሚል አቋም አለው፡፡

በእርግጥም አሁን ላይ የፖለቲካ

ፓርቲዎች ተቀራርበው በበለጠ

በትብብር በመስራት ኃይላቸውን

ማጠናከር ይገባቸዋል፡፡ ይህ አሁን ላይ

በትብብር የሚጀምሩት ግንኙነትም

ቀስ በቀስ ወደ ውህደት ሊያመራቸው

ይችላል፤ ለውህደት የሚያደርሱ

ስራዎችንም በዚያው ደረጃ በደረጃ

እያከናወኑ መሄድ ይቻላል፡፡ በዚህ

መልኩ የሚመጣ ውህደትም ዘላቂ

እንደሚሆን መገመት ይቻላል፡፡ ያም

ካልሆነ ደግሞ በትብብር መስራትን

በመቀጠል አቅምን አጎልብቶ ወደ

መሪነት መሸጋገር ትክክለኛ አካሄድ

ይሆናል፡፡

ከ ገፅ 3 የዞረ

ከጅጋ ቋሪት ያለው የትራንፖርት ችግር

ተገልጋዮችን ለስቃይ መዳረጉ ተገለፀ

ጅጋ:- በምዕራብ ጎጃም ዞን ከጅጋ ከተማ

እስከ ቋሪት ያለው የትራንስፖርት

አገልግሎት ችግር ህዝቡን እያሰቃየ

ነው ሲሉ ተሳፋሪዎች ገለጹ፡፡

አራትና አምስት እጥፍ ክፍያ

እንድንከፍል እንገደዳለን ያሉት

ተሳፋሪዎች ‹በህገ-ወጥነት ተመዘበርን መንግስት

ስርዓት ሊያስይዝልን ይገባል› የሚል ጥያቄ ስንጠይቅ

ካልፈለጋችሁ አለመሳፈር ትችላላችሁ የሚል መልስ

ከመንግስት አካላት ይሰጠናል ሲሉ ቅሬታቸውን

ገልጸዋል፡፡

24 ሰው የመጫን አቅም ያላቸው የአረጁና የወላለቁ

መኪኖች እስከ 104 ሰው ድረስ ሲጭኑ ለህዝብ

ህይወት በመቆርቆር እርምጃ የሚወስድ የመንግስት

አካል አለመኖሩ እጅግ አሳዛኝ ነው ያሉት ተሳፋሪዎቹ፣

የዚህን ህዝብ ሰቆቃና እንግልት ለማን አቤት እንደምንል

አናውቅም ብለዋል፡፡

መንግስት የመደባቸው ትራፊክ ፖሊሶች እንዲሁም

የመንገድና ትራንስፖርት ሠራተኞች ተሳፋሪው

ምንም አይነት መብት እንደሌለው ጫና ከማሳደርና

የተሳፋሪውን ሰቆቃ ከማራዘም ውጭ በምንም ዓይነት

ሁኔታ ግዴታቸውን ሲወጡ አናይም ብለዋል፡፡

ጥቂት የወላለቁና ከጥቅም ውጭ የሆኑ መኪኖች

የተመደቡለት ይህ መስመር መንግስት የዘነጋውና

አመቱን ሙሉ ተሳፋሪ ህዝብ የሚንገላታበት ቦታ ሆኗል

ሲሉ ያነጋገርናቸው ተሳፋሪዎች ጨምረው ገልፀዋል፡፡

ፋሽስት ገዳይ ባየር...

ታውቋል! ቀጥሏል! ቀጥሏል! ቀጥሏል! ወራሪው

በማንአህሎኝነት መንፈስ ተረጋግቶ ተቀምጧል!

ጀግናው ተሰማ እርገጤ አሁን ከወራሪው

ኃይል ሰፈር በጣም ተጠግቷል! ብዙም ሳይቆይ

ተኩስ ከፈተበት! ወራሪው ኃይል የሚይዘውና

የሚጨብጠውን አጥቷል! ሆኖም ለጥቂት

ደቂቃዎች ተታኩሷል! ወዲያው ግን ፈርጥጧል!

ከጨለንቆ ደብረ ሲና ገብቷል! የጀግናው አርበኛ

ተሰማ እርገጤ ድል አድራጊነት አሁንም

ተረጋገጠ! ይህ በታሪካችን የጥንታዊት ኢትዮጵያ

የጀግኖች አርበኞች የትግልና ድል ቀጥታ ድምጽ

ነው! ከሸዋ ጠቅላይ ግዛት ጨለንቆ ከተባለ

የውጊያ ሜዳ! መስከረም 19 ቀን 1929 ዓ.ም!

ይህ ለዛሬው ወር ተረኛ ትውልድ የተላለፈ

የጀግኖች አርበኞች ኢትዮጵያን የማዳን ተጋድሎ

ታሪክ ቀጥታ ድምጽ ነው! ከአርበኝነት ገድላችን

የተወሰደ!

መስከረም አልቋል፡፡ ጥቅምትም አልፏል! አሁን

በህዳር ወር ውስጥ መሆናችን ይመዝገብልን!

ጀግናው አርበኛ ተሰማ እርገጤ አሁን ጉደ

በረት ወረዳ የፋሽስት ወራሪ ኃይል የመሸገበትን

ቦታ በመስክ መረጃ ለይቷል! ወራሪው ኃይል

ከመሸገበት መንደር ደረሷል! አርበኞች ምድብ

የውጊያ መስመራቸውን ይዘዋል! ከጥቂት

ጊዜያት በኋላ እሳት ይዘንባል! አርበኞች ወደ

ምሽጉ ተጠግተዋል! በጣም ቀርበዋል! ጊዜ

አላጠፉም! የቅድሚያ ተነሳሽነት ወስደዋል!

ወዲያው ጦርነቱ ተጋግሎ ቀጠለ! ጀግናው አርበኛ

ተሰማ እርገጤ በርካታ የፋሽስት ኢጣሊያ ወራሪ

ኢትዮጵያ ለምን ...

ለማጣፈጥ ሲባል አዲስ ሰበካ ተጀምሯል። እኛ

የምናካሂደው ትጥቅ ትግል የማንዴላ አይነት

ትጥቅ ትግል ነው የሚል ማጭበርበሪያ። ጦርነት

ጦርነት ነው። ይህን አባባል የሚያስተጋባው

ቡድን በአንድ በኩል ተከታዮቹ መከተላቸውን

እንዲቀጥሉ ለማድረግ ሲሆን በሌላ በኩል

ደግሞ ሰላማዊ ትግል ካደረሰበት ትኩሳት

ለጊዜው እረፍት ለማግኘት በሰላማዊ ትግል

ንድፈ አሳብ ተማሪዎች እና ደጋፋዊዎች ላይ

የከፈተው የማሸማቀቅ የስነ ልቦና ጦርነት ነው።

መለስ ዜናዊ በምርጫ 97 የተቃሚው አሳብ

የህዝብ ድጋፍ እያገኘ መሄዱን ሲያስተውል

ደጋፊዎቹን ለማረጋጋት እና ተቃዋሚውን

ለማሸማቀቅ ኢንተርሃምዌይ እስከማለት ደረሶ

እንደነበር አስታውሳለሁ። አምባገነኖች ብዙ

ከ ገፅ 8 የዞረ

ኃይል ተዋጊዎችን በጥቂት ጊዜያት ከአፈር ጋር

አዋህዷቸዋል! ታላቅ ጦርነት ሆነ! ከኢትዮጵያ

ጀግኖች አስራ ሁለት አርበኞች በዚሁ ጦርነት

ተሰውተዋል፡፡ በጀግንነት ወደ ታሪክ ወርደዋል!

ጦርነቱ ቀኑን ሙሉ ቀጥሎ ውሏል! በዚህ

ጦርነት ጀግናው ተሰማ እርገጤ በትከሻው ላይ

በሁለት ጥይት ተመትቶ ቆስሏል፡፡ ብዙ ደምም

ፈስሶታል! ጀግናው ተሰማ እርገጤ እስከ ጦርነቱ

ፍጻሜ ዘጠኝ ጊዜ መቁሰሉ ታውቋል! የጉደ በረት

ጦርነት እስከ ሌሊት ድረስ ቀጥሏል! በዚሁ

ጦርነት ሰባ አምስት የፋሽስት ኢጣሊያ ወራሪ

ኃይል መኮንኖችና ወታደሮች ተገድለዋል!

ቆራጡ አርበኛ ተሰማ እርገጤ በአምስቱ

የፋሽስት ኢጣሊያ ወረራ ዓመታት የተዋጋባቸው

የጦር ሜዳዎች በጣም ብዙ ናቸው! በዚህም

መሰረት ጥር ወር በ1929 ዓ.ም ባደረገው ውጊያ

በርካታ የወራሪው ተዋጊዎችን በሞት ቀንሷል!

እንዲሁም በየካቲት ወር 1929 ዓ.ም በሞፈር

ውሃ ላይ በተደረገው ጦርነት ብዙ ፋስስቶችን

ገድሏል! በዚህ ብቻም አላበቃም! በመጋቢት ወር

1929 ዓ.ም ገዘት በተባለ ቦታ ጦርነት አድርጎ

በርካታ የወራሪው ኃይል አባላትን ደምስሷል!

አሁንም በመቀጠል በሚያዚያ ወር 1929

ዓ.ም በመንዝ ውስጥ ወይራ ገበያ በተባለ ቦታ

የተደራጀውን የወራሪውን ኃይል ተዋጊ ድባቅ

መትቷል! የጦር መሳሪያም ማርኳል! ጀግናው

አርበኛ ተሰማ እርገጤ አሁንም በጽኑ የውጊያ

ስነ-ልቦና ይስተዋላል! ቀጥሏል! ግንባሩን ሳያጥፍ

ቀን ከሌት ይዋጋል! በዚህ ሂደት ሐምሌ 18

ከ ገፅ 9 የዞረ

ይላሉ። የሚሉት ሁሉ ግን ከአጭር ጊዜ

መፍትሄነት ባሻገር አይረዳቸውም። ይሄም ያን

አይነት የስነ ልቦና ጦርነት ነው። የአለም ህዝብ

ለማንዴላ ክብር የለገሰው ጠበንጃ በማንሳቱ

አይደለም። በሃውልቱም ላይ የሚጻፈው ጦረኛ

መሆኑ አይደለም።

ቤተሰቡም እስከ ልጅ ልጆቹ ድረስ በአደባባይ

ስለማንዴላ የሚሰብኩት ሰላማዊነቱን እና

በሰላማዊ መንገድ አፓርታይድን እንዳፈረሰ

ነው። አፓርታይድ የፈረሰው በትጥቅ ትግል

አይደለም። የደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያው

ጥቁር ፕሬዘዳንት ሊሆን የቻለው በትጥቅ

ትግል አይደለም። ጥቁር እና ነጭ ደቡብ

አፍሪካውያን በህብረት ያደረጉት ሰላማዊ

ትግል መዘንጋት የለበትም። ታዋቂ ጥቁር እና

እና 22 ቀን 1929 ዓ.ም ግንደ በረት ላይ ክልቤ

በተባለ ቦታ ተዋግቶ ድል ማድረጉን የአርበኝነት

ታሪኩ ያመለክታል፡፡ በመቀጠልም ሺኖ በተባለ

ቦታ ተዋግቶ አኩሪ ውጤት አስመዝግቧል!

ቆፍጣናው አርበኛ ተሰማ እርገጤ በመቀጠልም

በሰላሌ አውራጃ ውስጥ ኩዩ ጊዮርጊስ በተባለ

ቦታ ከወራሪው ኃይል ጋር ተዋግቶ ድል

አስመዝግቧል! ለሁለት ቀናት በተካሄደው በዚሁ

ጦርነት በርካታ የወራሪው ኃይል ተዋጊዎቹን

መግደሉ ታውቋል! እንዲሁም መስከረም 12

ቀን 1930 ዓ.ም ተዋግቶ ወራሪው ኃይል

እንዲፈረጥጥ አድርጓል! በተመሳሳይ መልኩ

መስከረም 15 ቀን 1930 ዓ.ም ተዋግቶ ድል

ተቀዳጅቷል!

ጅግናው አርበኛ ተሰማ እርገጤ እስከ ጦርነቱ

ፍጻሜ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ውስጥ በወራሜ

በላሎ ምድር በአይት በተጉለት ወረዳ አምባ

ሞሻ፣ በከሴ ቆላ አቦ ጉር ህዳባይ፣ በላሎ

ምድር ኪደር በምሐይና በአንጉቦላ ቀበሌዎች

እየተዘዋወረ ከፍተኛ ጀብዱ ፈጽመዋል!

የታወቀው ጀግና ተሰማ እርገጤ ከድል በኋላ

የአምስት ዓመት የአርበኝነት ኒሻን ባለአምስት

ዘንባባ ተሸልሟል! እንዲሁም የድል ኮከብ

ሜዳይ አግኝቷል! በተመሳሳይ መልኩ የቅዱስ

ጊዮርጊስ ሜዳይ ባለሁለት ዘንባባ ተሸልሟል፡፡

ጀግናው የኢትዮጵያ ልጅ ተሰማ እርገጤ ከአባቱ

ከባሻ እርገጤ ሀብተ-ገብርኤልና ከእናቱ ወይዘሮ

ወለተ አረጋይ ጨድድ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት

በይፋት ውስጥ ሐር አምባ በተባለ ቀበሌ በ1888

ነጭ ደቡብ አፍሪካውያን አርቲስቶች የአለምን

ህዝብ በአፓርታይድ ላይ ለማስተባበር

ያደረጉት ቀጣይነት ያለው አለም አቀፍ

ሰላማዊ ዘመቻቸው መዘንጋት የለበትም።

ማንዴላን ለማስፈታት እና አፓርታይድን

ለማስፈታት የአለም ህዝብ ያደረገው ሰላማዊ

ትግል መዘንጋት የለበትም። በማንዴላ

ሃውልት ላይ የሚጻፈው የጦር አበጋዝነቱ እና

የገደለው ሰው ቁጥር ሳይሆን ማንዴላ ከእስር

ቤት ከወጣ በኋላ የፈጸመው ነው።

በመጨረሻ ወደ ኢትዮጵያ ልመለስ እና

ጽሁፌን ልደምድም። ሰላማዊ ትግል ሰላማዊ

ሰልፍ ማድረግ ብቻ አይደለም። ሰላማዊ

ትግል በምርጫ መሳተፍ ብቻ አይደለም።

ሰላማዊ ትግል በአደባባይ ወጥቶ መቃወም

ዓ.ም ተወለደ፡፡ በልጅነቱ አማርኛ ተምሯል፡

፡ ማይጨው ዘምቷል! ግዳጁን ተወጥቷል!

ከማይጨው መልስ የይፋትን ህዝብ ለጦርነት

አስተባብሯል! ቆፍጣናው ጀግና ተሰማ እርገጤ

ሰኔ 23 ቀን 1964 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት

ተለይቷል፡፡ ጀግናው ተሰማ እርገጤ በህይወት

ዘመኑ ሰባት ልጆችን አፍርቷል፡፡ ጀግናው

አርበኛ ተሰማ እርገጤ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለይ

ባህላዊ ወታደራዊ ማዕረጉ ደጃዝማች እንደነበር

ታውቋል!

ውድ የኢትዮጵያ ወጣት ሆይ በቀደምት

የኢትዮጵያ ጀግኖች መስዋዕትነት ታፍራና

ተከብራ የኖረችው ሀገራችን ተዋርዳለች! ሀገር

ለመሸጥ ደላላ ኮሚሽን ተቋቁሟል! ስለዚህ

ወጣቱ ትውልድ የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ

ጠንቅቆ በማወቅ ህሊናዊ ሁኔታዎችን ለማሳደግ

ሊነሳ ይገባል! እርግጥ ነው ሀገርን ጠብቆ

በክብር ለመጪው ትውልድ ማስረከብ የዜጎች

ሁሉ ግዴታ ይሆናል፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያን

ከጠቅላላ ውድቀት ለማዳን በቁርጠኝነትና በዓላማ

ጽናት በተግባር እንነሳ! ክብር ለቆራጡ አርበኛ

ለደጃዝማች ተሰማ እርገጤ! ክብር በአምስቱ

የፋሽስት ኢጣሊያ ወረራ ዓመታት በዱር

በገደሉ ለወደቁ ጀግኖች! ክብር ዛሬም ከዕለታዊ

ጥቅምና ጊዜያዊ ተድላ ርቀው ለኢትዮጵያ ነጻነት

በመታገል ላይ ለሚገኙ ቆራጦች! ኢትዮጵያዊ

ብሄርተኝነት ያሸንፋል!

ብቻ አይደለም። ሰላማዊ ትግል እነዚህን ሁሉ

ማድረግ ነው። በተጨማሪ ሰላማዊ ትግል

ህዝብን የራሱ ነፃ አውጭ በማድረግ (1)

በስልጣን ላይ የሚገኝን አምባገነን መንግስት

አስወግዶ ህዝብን የመንግስት ስልጣን ባለቤት

ማድረግን፣ (2) መፈንቅለ መንግስት ቢነሳ

ትብብር መንፈግ፣ (3) እንደ ህውሃት/

ኢህአዴግ ከጫካ ወይንም ከጎረቤት አገር

(ኤርትራን ጨምሮ) ተነስቶ ልውረርህ የሚል

ቡድን ቢመጣ ህዝባዊ መከላከል (Civil Resistance)

ማድረግን ያካትታል። ሰላማዊ

ትግልን በሚመለከት ግንዝቤያችን ሰፋ ያለ

መሆን አለበት። የቀድሞው የመንግስት

ሽግግር ባህላችን ደደብ ነው። ብልህ ሰዎች

አይከተሉትም።

እንዲሆን በማሰብ ፓርቲው ቀኑን መዘከር አስፈላጊ

መሆኑን ያምናል ብለዋል፡፡ በዕለቱ በሁለቱም

ፕሮግራሞች ላይ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ እንዲሳተፍ

አቶ ብርሃኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ በ2005 ዓ.ም ጣሊያኖች በወገኖቻችን

ላይ ከፍተኛ በደል የፈጸመውን ሮዶልፍ ግራዚያኒ

በትውልድ ከተማው ‹የጀግና› ሐውልት በማቆም

ዕውቅና መስጠታቸውን በመቃወም ሰላማዊ የተቃውሞ

ሰልፍ በአዲስ አበባ መጥራቱን ተከትሎ በቦታው የተገኙ

አባላቱ ለእስር መዳረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡

በጎንደር በተካሄደው...

ከ ገፅ 1 የዞረ

ያስተባበሩት የአካባቢው የፓርቲው መዋቅር አካላት

ደህንነቶች ለቤተሰቦቻቸው ደውለው እያስፈራሩዋቸው

መሆኑን የፓርቲው የዞን ሰብሳቢ አቶ አግባው ሰጠኝ

ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል፡፡

ፓርቲው ጥር 25 በጎንደር ከተማ መስቀል አደባባይ

በጠራው ሰልፍ፣ የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ማካለል

ሂደትን በተመለከተ መንግስት ለህዝብ ጉዳዩን ግልጽ

እንዲያደርግና ሉዓላዊነትን እንዲያከብርና እንዲያስከብፈር

መጠየቁ ይታወሳል፡፡
7 የካቲት 7 ቀን 2006 ዓ.ም. ቅፅ 1 ቁጥር 2 ነገረ-ኢትዮጵያ

መሬት ያስቆረሱት የመለስና ተከታዮቹ

እኩይ ስምምነቶች

አለማየሁ ገ/ማርያም (ፕ/ር)

የአሁኑ አስገራሚ ጊዜ ሸክስፒር፣ ‹ጁሊየስ

ቄሳር› በሚለው ፅሁፉ ላይ ለተናገረው አነጋገር

ልዩ ትርጉም ይሰጠዋል፣ “ሰዎች የሰሩት ተንኮል

ከመቃበራቸው በላይ ህያው ሆኖ ይኖራል” ብሎ

ነበር ሸክስፒር፡፡ በአሁኑ ጊዜ አቶ መለስ ዜናዊ

በህይወት በነበሩበት ጊዜ ከሰሩት ተንኮሎችና

ጭራቃዊነት የሞላው አስቀያሚ ተግባር ውርስ

ጋር ፊት ለፊት ተፋጥጠን እንገኛለን፡፡ የኢትዮጵያ

ሉዓላዊ የግዛት አካል ተቆርሶ እንደገና ለሽያጭ

ለሱዳን ቀርቧል፡፡ ይህንንም ጭራቃዊነት ተንኮል

የቀበሮ ባህታውያኑ “የድንበር ማካለል“ ብለው

ይጠሩታል፡፡ እኔ ደግሞ ድንበር መቁረስ፣

መቆራረስ፣ መሽረፍ እና መሸራረፍ ብዬ

እጠራዋለሁ፡፡ ባጭሩ ኢትዮጵያን ለቅርጫ

ማቅረብ እለዋለሁ… ደግሞ ለሰላሳ ቁርጥራጭ

የመዳብ ዲናሮች! እ.ኤ.አ በ2008 “የኢትዮጵያ

ጋሻ“ ተብሎ በሚጠራው የሰሜን አሜሪካ የሲቪል

ማህበረሰብ ስብስብ ጉባኤ ላይ በመገኘት የእናት

አገር ኢትዮጵያን ሉዓላዊነት መጠበቅ በሚል

ርዕስ ስሜትን የሚቀሰቅስ ንግግር አድርጌ ነበር፡፡

አቶ መለስ የአሰብን ወደብ አሳልፈው በሰጡበት

ወቅት ዝምታን በመምረጣችን ወደብ አልባ

የመሆንን ዋጋ ከፍለናል፡፡ እ.ኤ.አ በ1998 ባድመ

ተወረረች፣ እናም የ80,000 ኢትዮጵያውያን

ህይወትን የበላ መስዋዕትነት ተከፍሎ

ጠላቶቻችን ከግዛታችን እንዲወጡ ተደረገ፡

፡ ሆኖም ግን አቶ መለስ በብርሃን ፍጥነት

ተገልብጠው የኢትዮጵያን አንጸባራቂ የጦር

ሜዳ ድል ቀልብሰው የዲፕሎማሲያዊ ሽንፈትን

በመጋት በእርቅ ሰበብ ስም ባድመን ለወራሪው

ኃይል አሳልፈው ለመስጠት ስምምነት አደረጉ…

(ዛሬ) በምዕራብ ኢትዮጵያ የሚኖሩ ወገኖቻችን

በግልጽ እንደነገሩን የአያት ቅድመአያቶቻቸውን

መሬት እና መኖሪያ ቤታቸውን ሳይቀር አቶ

መለስ ለሱዳኑ አምባገነን [በዓለም አቀፉ

የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በወንጀል ለሚፈለጉት

እና ከፍትህ ለማምለጥ እራሳቸውን በመደበቅ

ተወሽቀው ላሉት] መሪ ኦማር አልባሽር

አሳልፈው ለመስጠት በሚስጥር ስምምነት

ፈጽመዋል…ያንን ንግግር ካደረግሁ ከስድስት

ዓመታት በኋላ እንኳን በሚያሳዝን ሁኔታ እናት

አገራችንን ለመበታተን አቶ መለስ ከበረሃ ውስጥ

ነድፈው ያመጡትን ጭራቃዊ ዕቅድ እኩይ

ምግባር ለመቀልበስ ባለመቻላችን አዝናለሁ፡፡

አቶ መለስ አሁን በህይወት የሉም፣ ሆኖም ግን

እኛን እንዲያጠፋ ጥለውት ከሄዱት ተንኮላቸው

ስራቸው ጋር ፊት ለፊት ተጋትረናል፡፡ “መልካም

ሰዎች ዝም ስላሉና ምንም ባላማድረ ጋቸው

ይሆን ተንኮል የሚበረታው” የሚለው አባባል

እውነታነት አለውን? በመጨረሻም ተንኮልና

ጭራቃዊነት ድል ተጎናጽፏልን?

ኢትዮጵያ በአቶ መለስ ዜናዊ ቅርጫ መግባት

እ.ኤ.አ ዴሴምበር 2013 የሱዳን የውጭ ጉዳይ

ሚኒስትር የሆኑት ዓሊ ካርቲ የኢትዮጵያ

እና የሱዳን ገዥ አካላቶች “ፋሻጋ እየተባለ

በሚጠራው አካባቢ የነበረውን የድንበር

አለመግባባት እና በሌሎች አካቢዎችም ያሉትን

የድንበር ማካለል ስራዎችንም በሰላማዊ

መንገድ ለማጠናቀቅ ስምምነት አድርገናል“

በማለት በግልጽ ተናግረዋል፡፡ ስለሁለቱ አገር

መሪዎች አስመልክቶ ካርቲ እንዲህ ብለዋል፣

“የመጨረሻውን የማካለል ስራ ለመተግበር

ታሪካዊ ስምምነት አድርገናል፡፡“ የሱዳን የውጭ

ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በኢትዮጵያ እና

በሱዳን መካከል ያሉትን “የድንበር ውዝግቦች”

በማስመልከት ለሚቀርቡ አስተያየቶች ሁሉ

ምንም ዓይነት ሀሳብ እንደማይቀበል ጠቅሶ

ሲናገር፣ “በጠረፉ በተወሰኑ የወሰን ድንበር ነጥብ

ቦታዎች ላይ“ በጣም ቀላል የሆኑ አለመግባባቶች

ከመኖር በስተቀር ሌላ ችግር እንደሌለ አስረግጠው

ተናግረዋል፡፡ ባለፉት ሳምንታት የኢትዮጵያ

የውጭ ግንኙነት መምሪያ እንደ ዔሌ አንገቱን

ብቅ ጥልቅ እያደረገ በድብቅነት እና ማደናገር

በተላበሰ ስልት/strategy “የድንበር ማካለሉን

ጉዳይ“ እና “መጠነ-ሰፊ ጠቀሜታ“ አላቸው እያለ

ከበሮ የሚደልቅላቸውን “የደህንነት ትብብር

ስምምነት፣ የኢኮኖሚ፣ የግብርና፣ የትምህርት

እና የባህል“ “የስትራቴጅክ ስምምነት ማዕቀፍ“

በማለት በሚጠራቸው ጉዳዮች ላይ እምነት

እንዲያድርብን የፕሮፓጋንዳ ዘመቻዎችን

በመሰለቅ ጊዜውን በከንቱ አሳልፏል፡፡

እ.ኤ.አ በ2001 “ለድንበር ውዝግቡ” ይሰጡ

የነበሩት ምክንያቶች አሁን እየተሰጡ ካሉት

ምክንያቶች ፍጹም የተለዩ ነበሩ፡፡ በዚያን ጊዜ

የሱዳን ገዥ አካል እንደገለጸው የድንበር ማካለሉ

ስራ አስፈላጊነቱ “የአልቃዳሪፍን ግዛት በሰሜን

ኢትዮጵያ ከሚገኘው የትግራይ ግዛት ጋር

‘ለማልማት እና ለማቆራኘት‘ የሚል ነበር…

ሁለቱ አካባቢዎች በጣም ለም የነበሩ ሲሆኑ፣

ከዚህም በላይ አልቃዳሪፍ ለሱዳን የዳቦ ቅርጫት

ተደርጎ የሚቆጠር ነበር… ከአልቃዳሪፍ እስከ

መቀሌ ያለው የመኪና መንገድ…እየተጠገነ እና

ደረጃው ከፍ እየተደረገ ነው… የትግራይ ግዛት

ከዚህ በመነሳት በዚህ በኩል ወደ ቀይ ባህር

የሚያሸጋግረው ዕድል ስለሚያገኝ እና አልቃዳሪፍ

ደግሞ ከፖርት ሱዳን ጋር የሚያገናኘው ስለሆነ

ተቃሚ ይሆናል፡፡ በዚህም መሰረት ፖርት ሱዳን

ለመቀሌ በኤርትራ ግዛት ከሚገኘው የአሰብ

ወደብ እና በሶማሌ ግዛት ከሚገኘው የበርበራ

ወደብ የበለጠ ቅርብ ትሆናለች…“ የሚል ነበር፡፡

እ.ኤ.አ በ2008 አቶ መለስ ዜናዊ ከሱዳን ጋር

የተደረገውን “ስምምነት” አስመልክቶ በውሸት

ባህር ውስጥ እየተንቦጫረቁ የጭቃ ጅራፋቸውን

ማጮህ ጀመሩ፡፡ በዚያው ዓመት በግንቦት ወር

ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው

ሙልጭ አድርጎ በመካድ ለመጀመሪያ ጊዜ

አንድም ጋት የሚሆን የኢትዮጵያን መሬት

ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት የተደረገ ስምምነት

የለም የሚል መግለጫ ሰጠ፡፡ ያ መግለጫ

በውጭ የሚገኙትን “የዜና አውታሮች” እና

“ኃላፊነት የማይሰማቸው” በበሬ ወለደ የፈጠራ

ወሬ የተሰማሩ ሽብር እና ፍርሀትን በህብረተሰቡ

ዘንድ የሚነዙ አሸባሪዎች ናቸው በማለት

ከሷቸው ነበር፡፡ የሱዳን ባለስልጣኖች ግን ያንን

መግለጫ በሚጻረር መልኩ “ከኢትዮጵያ መሬት

እንዳገኙ“ በይፋ በአደባባይ ተናግረዋል፡፡ በግንቦት

አጋማሽ አቶ መለስ እና አጫፋሪዎቻቸው

የመሬት ማደሉን ሚስጥር ደብቀው ማቆየት

ባለመቻላቸው ወደ ቀድሞው ታሪካቸው

ለመመለስ ተገደዋል፡፡ በድንበር ማካለሉ ወቅት

አንዳንድ የቅድመ ስራ እንቅስቃሴዎች ብቻ

እንደተከናወኑ፣ እናም የተጠናቀቀ ነገር የለም

በማለት በግልጽ ተናግረዋል፡፡ በቀናት ጊዜ

ውስጥ አቶ መለስ እና አጫፋሪዎቻቸው ሌላ

አዲስ ቅጥፈትን ፈብርከው ብቅ አሉ፡፡ የሆነው

“ቀደም ሲል በንጉሱ እና በደርግ ዘመን ከሱዳን

ጋር የተደረጉ ስምምነቶችን ተግባራዊ አደረግን”

ብለው ጭራ ቀረሽ ዉሸት ፈጠሩ፡፡

የኢትዮ ሱዳን የድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ጉዳዩን

በግልጽ ሲያቀርበው እና በተጨባጭ በድንበሩ

ባሉ አካባቢዎች ላይ ምን እየተደረገ እንዳለ ይፋ

ሲያደርግ እስከ አፍ ጢሙ ተቀብትቶ/ሞልቶ

የነበረው የውሸት ጎተራ መፈረካከስ ጀመረ፡፡

በአቶ መለስ ለሱዳን መሬት ዕደላ ፖሊሲ

ምክንያት የተጎዱ ዜጎቻችን ለአሜሪካ ድምጽ

የአማርኛው አገልግሎት እና ለሌሎች ዓለም

አቀፍ ብዙሃን መገናኛ ተቋማት ቃለመጠይቅ

መስጠት ጀመሩ፡፡ በመሬት ዕደላው ምክንያት

ቀጥተኛ ተጎጅ የሆኑ ወገኖቻችን አያት ቅደመ

አያቶቻቸው ጠብቀው ያቆዩት መሬት በሱዳን

ኃይሎች እየተወረረ ይዞታቸው ሲወሰድባቸው

እና ከቀያቸው እና እትብቶቻቸው ከተቀበሩባቸው

ቦታዎች ሲባረሩ የነበረውን ሁኔታ በመረረ

አኳኋን የተሰማቸውን ቅሬታ በሰፊው ማሰማት

ጀመሩ፡፡ የእርሻ መሳሪያዎቻቸው እና የመገልገያ

ቁሳቁሶች በሱዳን ወራሪ ኃይሎች መወረሱን

ገለፁ:: እንዲሁም በርካታ ኢትዮጵያውያን

በሱዳን እስር ቤቶችም ታስረው እንዲማቅቁ

አስታወቁ፡፡ በዚያን ጊዜ አቶ መለስ ምንም

ምርጫ አልነበራቸውም፣ በግዴታ ሳይወዱ

መሬት ለመስጠት ከሱዳን ጋር መፈራረማቸውን

ለማመን ተገደዋል፡፡ እ.ኤ.አ በሜይ 2008

አቶ መለስ ከኦማር አልባሽር ጋር ያደረጉትን

ስምምነት እንዲህ በማለት ይፋ አድርገዋል፣ “እኛ

ኢትዮጵያውያን እና የሱዳን መንግስት የድንበር

ማካለሉ ስራ በሚሰራበት ወቅት ከሁሉቱም

ወገን አንድም ዜጋ እንዳይፈናቀል ለማድረግ

ስምምነት ተፈራርመናል… በ1996 የወሰድነውን

መሬት መልሰን ለሱዳን ሰጥተናል፣ ይህ መሬት

ከ1996 ዓ.ም በፊት የሱዳን ገበሬዎች ይዞታ

ነበር፡፡ አንዳንድ የብዙሃን መገናኛ ተቋማት

እንደሚያናፍሱት ሳይሆን በድንበሩ ዙሪያ አካባቢ

አንድም የተፈናቀለ ዜጋ የለም፡፡” እ.ኤ.አ በ2008

በዊክሊስ (የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ አመራር

ሚስጥር ሰነድ) ሌላ ወሳኝ የሆኑ መረጃዎች

ይፋ ተደርገዋል፡፡ “የቀድሞው የህዝባዊ ወያኔ

ሃርነት ትግራይ ማዕከለዊ ኮሚቴ አባል እና

የቀድሞው የመከላከያ ሚኒስትር የነበሩት አቶ

ስዬ አብርሃ እንዲህ በማለት ተናግረዋል፣ ‘አቶ

መለስ በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ተፈጥሮ

የነበረውን የድንበር ውዝግብ ውጥረት ለማርገብ

ጥረት በሚያደርጉበት ወቅት “ለአማራ ክልል

ትልቅ ዋጋ ሊያስከፍል የሚችል ግዙፍ መሬት“

አቶ መለስ ለሱዳን ሰጥተዋል፡፡ እናም የአቶ

መለስ አገዛዝ “በድብቅ ይዞ ለማቆየት ሞክሯል”

አሉ አቶ ስዬ አብርሃ::

ቀደም ሲል አቶ መለስ፣ አሁን ደግሞ የዕኩይ

ምግባር ውርስ አጫፋሪዎቻቸው ያንን ስምምነት

“በድብቅ ይዘው ለማቆየት” በመውተርተር እና

በመዳከር ላይ ይገኛሉ፡፡ ሆኖም ግን እ.ኤ.አ

በ2008 አቶ መለስ ከኦማር አልባሽር ጋር

ባደረጉት ስምምነት ላይ የሰጡት መግለጫ

አንዳንድ ጠቃሚ ምልክቶችን ይሰጣል፡፡

እራሳቸው አቶ መለስ ባመኑት እ.ኤ.አ በግንቦት

2008 በእርሳቸው እና በኦማር አልባሽር መካከል

በተደረገው “የመሬት መስጠት ስምምነት”

ዝርዝር የስምምነቱን ሁኔታ የሚያመላክት

መሆኑ የሚያጣያይቅ አይደለም፡፡ “የስምምነቱን”

ሁኔታ ስናጠናው አቶ መለስ በስምምነት መዝገቡ

ላይ በርካታ ጠቃሚ ማስረጃዎችን አስቀምጠዋል፡

፡ “ስምምነቱ” 1ኛ) መሬቱ በሚሰጥባቸው

አካባቢዎች ሰዎችን ሊያፈናቅል የሚችል ጥያቄ

መነሳት እንደሌለበት 2ኛ) ከድንበር ማካለሉ

ጉዳይ ጋር በተያያዘ መልኩ ከማካለል ስራው

ጋር ተያይዞ ጉዳት የሚደርስባቸውን ሰዎች

ጥቅሞች የማስጠበቅ ሁኔታ መኖር እንዳለበት

3ኛ) በኢትጵያውያን ገበሬዎች በህገወጥነት

መልክ ተይዞ የነበረ የተባለውን መሬት ለሱዳን

ገበሬዎች የባለቤትነት መብትን ማስጠበቅ 4ኛ)

በ1996 ዓ.ም በህገወጥ መልክ በኢትዮጵያውያን

ተይዞ የነበረውን መሬት ለሱዳናውያን መመለስ

የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

በአቶ መለስ ፈቃድ እና አዛዥነት በእራሳቸው እና

በኦማር አልባሽር የተፈረመው መሬት የመስጠት

ስምምነት “የ1902 የግዌን መስመር/Gwen

Line of 1902” (የ1902 የአንግሊዝ-ኢትዮጵያ

ስምምነት) እየተባለ የሚጠራው “በኢትዮጵያ

እና በሱዳን መካከል ያለውን ድንበር” መስመር

ማስያዝ ከሚለው ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት

እንደሌለው መገንዘብ ሊሰመርበት የሚገባ ጉዳይ

ነው፡፡ እንደዚሁም እ.ኤ.አ ከ1974 በፊት በንጉሱ

ዘመን እና በደርግ ዘመን ከ1995 እስከ 1991

ድረስ የተረቀቁ እና የተፈረሙ የድንበር መካለል

ወይም ደግሞ መፍትሄ መስጠት ስምምነቶች ካሉ

ከዚህ ስምምነት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት

የላቸውም፡፡ እ.ኤ.አ ከ1996 መጀመሪያ አካባቢ

ጀምሮ አቶ መለስ በእራሳቸው ፈቃድ ከድንበር

እና ተመሳሳይ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ መልኩ

ያደረጉት “ስምምነት” በአቶ መለስ ግላዊ አተያይ

የሱዳን መሬት በኢትዮጵያውያን በኃይል የተቀማ

ነው በማለት በግላቸው ያደረጉት ህገወጥ እርምጃ

እንጅ ሌላ ምንም ዓይነት ማስረጃ የሌለው

እርባናቢሰ ስብከት መሆኑ በውል ሊጤን ይገባል፡

የኢትዮጵያን “ግዙፍ መሬቶች” በድብቅ እና

ለህዝብ ይፋ ሳያደርጉ በሚስጥር ለሱዳን

የሚሰጡበት፡፡

ምንድን ነው?

የድንበር “ስምምነት” ምክንያቱ

አቶ መለስ እና አቶ ኃይለማርያም በአጠቃላይ

“በድንበር ስምምነቱ” ዙሪያ እያቀረቡት የነበረው

እና ያለው የውሸት ፍብረካ ድሪቶ ሪፖርት

እውነታውን ለመደበቅ ከሚሽመደመደው ድሁር

አስተሳሰባቸው ያለፈ ፋይዳ አይኖረዎም፡

፡ እውነተኛው የድንበር መስጠት ስምምነት

እ.ኤ.አ በ2008 ተጠናቁአል፡፡ በምንም ዓይነት

መልኩ ቢሆን አቶ መለስ “ግዙፍ የሆነ

መሬት ከአማራ ክልል” ቆርሰው ፈርመው፣

አትመው እና አሽገው ለሱዳን መስጠታቸውና

በድብቅ “በድብቅ ተይዞ እንዲቆይ” መጣራቸው

የሚያጠያየቅ ጉዳይ አይደለም፡፡ እ.ኤ.አ በ2014

የኢትዮጵያ የይስሙላው ጠቅላይ ሚኒስትር

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የአቶ መለስን የበከተ

ውሸት እንደተለመደው “በሀሰት መጋረጃ

ደብቀው” ለዘላለም ለማቆየት በማሰብ ሌላ ዘርዘር

ያለ ፖለቲካዊ ድራማ ለመተወን በመውተርተር

ላይ ይገኛሉ፡፡ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እና

ጌቶቻቸው የኢትዮጵያን ህዝብ ሊያታልሉ፣

ሊያጭበረብሩ እና በውሸት ሊደልሉ የሚችሉ

ይመስላቸዋል፡፡ እነዚህ የዕኩይ ምግባር ባለቤቶች

መሬትን ያህል ነገር በድብቅ ሸፍኖ የመስጠት

ጨዋታቸውን ኢትዮጵያውያን የማያውቁ እና

የማይገነዘቡ ሞኞች አድርገው ይቆጥራሉ፡

፡ እነርሱ ይህን የሞኝነት ጨዋታቸውን

እንደፈለጉ መጫወት ይችላሉ፣ ሆኖም ግን

አቶ ኃይለማርያም አንድ ጥያቄ እንዲመልሱልኝ

እፈልጋለሁ፣ ይኸውም “ ‘ከአማራ ክልል ግዙፍ

መሬቶችን ቆርሰው የሰጡት’ “ድብቅ የሚስጥር

ስምምነቶችን የት እንዳስቀመጧቸው ሊያሳዩኝ

ይችላሉን? አቶ መለስ እ.ኤ.አ በ2008 እና

አሁን ደግሞ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እና

የዕኩይ ምግባር አጋሮችዎ የድብቅ ስምምነቶችን

ከህዝብ ፊት ደብቃችሁ ከፊታችሁ ላይ የውሸት

መጋረጃ በማድረግ ለመዝለቅ የምትፈልጉት

ለምንድን ነው?” ከአገር መሬት ቆርሳችሁ

ለባዕድ አገር ስትሰጡ በአገሪቱ ህገመንግስት

ስልጣን ለተሰጠው ፓርላማ (ለተወካዮች ምክር

ቤት) ተብዬው ለይስሙላ እንኳን ቢሆን መቅረብ

የለበትምን“? ህገመንግስቱ የሚለው ሌላ የስርዓቱ

ቁንጮዎች የሚያደርጉት ሌላ! አራምባ እና ቆቦ!

ከላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች መልሱ ቀላል ነው፣

እ.ኤ.አ 2008 አቶ መለስ የተናገሩለት “የሚስጥር

ስምምነት“ እና አሁን ደግሞ አቶ ኃይለማርያም

እያነበነቡት እንዳለው አይደለም እውነታው፡፡

ህዝብ ግብር እየከፈለ በሚያስተዳድራቸው መገናኛ

ብዙሀን ብቅ እያሉ በእብሪት የሚያሰራጩት

ነጭ ውሸት ነው፡፡ በእርግጥ አቶ መለስ ይዋሻሉ

ማለት “መለስ ወይስ መቀልበስ” መጠሪያ

ስማቸው ነው፡፡ ሁሉም አፍጥጠዉ ይዋሻሉ፡

፡ አቶ መለስ እና አቶ ኃይለማርያም ከኦማር

አልባሽር ጋር በስምምነቶች ላይ ያስቀመጧቸው

ቃላት፣ ሀረጎች እና ዓረፍተ ነገሮች ወደ እውነት

ተግባርነት የሚሸጋገሩ ከሆነ ከዚህ ጋር ተያይዘው

የሚመጡ አደጋዎች ምን ሊሆኑ ይችላሉ?

በእውነት እነዚህ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ የግዛት

አንድነት በመዳፈር መሬቱን እየቆረሱ ለመስጠት

ተፅፈው ተፈረመው የተደበቁ ስምምነቶች የአቶ

መለስን እና የአቶ ኃይለማርያምን ቀጣፊነት

ወደ ገፅ 15 ይዞራል
ነገረ-ኢትዮጵያ ቅፅ 1 ቁጥር 2 የካቲት 7 ቀን 2006 ዓ.ም. 8

ዝክረ ታሪክ

ፋሽስት ገዳይ ባየር በራሪ፣

ድንግል ጠብመንጃ በደም ነካሪ

ከፉከራ ስነ-ቃል የተወሰደ

ታዴዎስ ታንቱ

የመ.ሣ.ቁጥር 43414

የኢትዮጵያ ሰራዊት በታላቅ ጀግንነት

ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍሏል!

ከአውሮፕላን የዘነበውን የመርዝ

ጭስ መቋቋም ግን ሳይችል ቀርቷል፡

፡ በምክንያቱ ምክንያት የፋሽስት

ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል የበላይነትን

ተቀዳጅቷል፡፡ በአሸናፊነት ስነ-ልቦና

ታይቷል፡፡ የማይጨው ጊዜያዊ ድል

ፈጽሞ እንደማይቀለበስ ተስፋ ሰንቋል!

የአድዋ ጀግኖች ቀጥታ ተወላጆች

መሆናችንን ማስታወስ እንኳን

ተስኖታል፡፡ በዕብሪት የኢትዮጵያን

መሬት ረግጧል፡፡ ወደ አዲስ አበባ

ይገሰግሳል! ይገሰግሳል! ይገሰግሳል!

ይገሰግሳል! አሁን ደሴ ገብቷል! ቀዳማዊ

ኃይለ ስላሴ መሰደዳቸውን ሰምቷል፡

፡ ዋና ከተማችንን በቶሎ ለመያዝ

ቋምጧል! ከፊቱ ሊቆም የሚችል

ጀግና ከቶም ሊኖር እንደማይችል

ገምቷል! ጊዜአዊ ድል ዘላለማዊ

አሸናፊነትን እንደማይወክል ለመገንዘብ

አስተውሎት ጎድሎታል! የማን

አህሎኝነት መንፈስ ለብሷል! ባሁኑ

ሰዓት ሮቤ ደርሷል፡፡ ይግተለተላል!

ይግተለተላል! ይግተለተላል! እንዲህ

በቀላሉ ኢትዮጵያን ቅኝ ግዛት ማድረግ

የሚችል መስሎታል፡፡ እርግጥ ነው!

ከማይጨው ጦርነት ወዲህ የከፋ ነገር

ሳያጋጥመው መጥቷል፡፡ ይህ ሁኔታ

ሊቀጥል እንደማይችል ግን በጥቂት

ጊዜያት ውስጥ ይታያል! ማን ለማን

ይገዛል? የጀግኖች መሬት የፋሽስቶች

መቃብር ይሆናል! የማይቀር እውነት

በተግባር ይረጋገጣል! የጥንታዊት

ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች በመንገዱ

ግራና ቀኝ ተነጥፈዋል፡፡ በነፍስ ወከፍ

ጦር መሳሪያ ቆርጠው ተነስተዋል!

ድም! ድም! ድም! ዱዋ! ዱዋ! ዱዋ!

የኢትዮጵያ አርበኞች የቅድሚያ

ተነሳሽነት ወስደዋል! አከታትለው

ተኩሰዋል! ቆራጡ የኢትዮጵያ ጀግና

ተሰማ እርገጤ ክንዱን ሳይንተራስ

የፋሽስት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል

በኢትዮጵያ ምድር ተረጋግቶ ሊኖር

እንደማይችል ከአቋም ተነስቶ ወደ

ተግባር ገብቷል! የጦረኛ ዘር የጀግና

ልጅ እሱ ማንን ይፈራል? ጦርነቱ

አሁን ተጋግሏል! ከክብሩ ይልቅ

ሆዱን የሚወድድ ከእንሰሳ ይመደባል!

ከማንም ህይወት የሀገር ህልውና

ይቀድማል! የነጻነትን ትርጉም

የሚያውቅ ለነፍሱ አይሰስትም!

ለጀግና ሞት ሰርጉ ነው! የጥንታዊት

ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች

ቆርጠዋል! በደፈጣ ውጊያ የበላይነትን

ጨብጠዋል! የፋሽስት ኢጣሊያ ወራሪ

ኃይል ተዋጊዎች ተረፍርፈዋል!

በማያውቁት መንገድ አውቀው

መጥተዋል! መጥተውም አልቀዋል!

የሰውን ፈላጊ የራሱን ያጣል! ጦርነቱ

ሌሊትም ቀጥሏል! ጀግና መች ሞት

ይፈራል! ጦርነቱ ተጋግሏል! የፋሽስት

ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል ተዋጊዎች

ተጠቅተዋል! የእሳት ራት ሆነዋል!

አሁንም ግን በመፍጨርጨር ሂደት

ገፍተዋል! የኢትዮጵያ ጀግኖች ደግሞ

ከማሸነፍ ያነሰ ውጤት ላለማስመዝገብ

ወስነዋል! ሰባት መኪና ሙሉ የነበረው

የፋሽስት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል አሁን

በጣም መንምኗል! ታሪክ ይመሰክራል!

የወገን ትግል በድል ተጠናቅቋል!

ጀግናው አርበኛ ተሰማ እርገጤ ወገንን

አኮራ! ይህ በታሪካችን የጥንታዊት

ኢትዮጵያ የጀግኖች አርበኞች የትግልና

ድል ቀጥታ ድምጽ ነው! ከሸዋ ጠቅላይ

ግዛት ከደብረ ሲና ጦር ሜዳ! ግንቦት

23 ቀን 1928 ዓ.ም፡፡

ቆፍጣናው የኢትዮጵያ አንበሳ ተሰማ

እርገጤ አሁንም በከፍተኛ የውጊያ

ስነ-ልቦና ይስተዋላል! ጀግናው አርበኛ

ተሰማ እርገጤ ከውስን የውጊያ

ሜዳ መልስ ረግቶ የሚቀመጥ ሰው

አልነበረም፡፡ የፋሽስት ኢጣሊያ ወራሪ

ኃይል ለአንዴና ለዘለዓለም ኢትዮጵያን

ለቅቆ እነዲወጣ ለማድረግ ጽኑ የግዳጅ

አቋም ይዟል፡፡ የተፈለገው መስዋዕትነት

ሁሉ ይከፈላል! ጀግና ከነጻነት

ያነሰ ነገር አይፈልግም! ለዓላማው

ደግሞ እስከ ህይወት መስዋዕትነት

ይዘልቃል፡፡ ቆራጡ የጦር ሰው ተሰማ

እርገጤ አሁን በተጠንቀቅ ቆሟል!

ከመስክ ስምሪት የተገኙ መረጃዎችን

ይተነትናል፡፡ ከኢትዮጵያ የቁርጥ

ቀን ጀግኖች ጋር በስፋት የሀሳብ

ልውውጥ አድርጓል! በጥቂት ጊዜያት

ውስጥ ተጨባጭ ተኩስ ይከፈታል!

የኢትዮጵያ አርበኞች ወደ ወራሪው

ኃይል በቀጥታ ተጠግተዋል! ወራሪው

ኃይል በቀጥታ ወደ አዲስ አበባ

ሲተምም ይታያል! ለጊዜው በውጊያ

ስነ-ልቦና ላይ እንዳልነበረ ታውቋል!

ጀግኖቹ የኢትዮጵያ አርበኞች አሁን

ለወራሪው ኃይል የጉዞ መስመር

በጣም ቀርበዋል! ድም! ድም! ድም!

ዱዋ! ዱዋ! ዱዋ! ጀግኖቹ የኢትዮጵያ

አርበኞች ቅድሚያ ተነሳሽነቱን

በተግባር ወስደዋል፡፡ የፋሽስት ኢጣሊያ

ወራሪ ኃይል ተደነባብሯል! ሆኖም

የአጸፋ ተኩስ ለማሰማት የደቂቃ

ክፍልፋይ ጊዜ በቅቶት ተገኝቷል፡፡

ማይጨው ላይ የነበረው የኢትዮጵያ

ሰራዊት በሙሉ የመጣበት ያህል

ደንግጧል! ሳያስበው አስቦ ያደፈጠ

ጀግና አጋጥሞታል! ተኩሱ ቀልጧል!

እንደ ፈንድሻ ይንጣጣል፡፡ ለሰዓታት

ቀጥሏል! የፋሽስት ኢጣሊያ ወራሪ

ኃይል ድባቅ ተመትቷል! ድል በትግል

ተመዝግቧል! ታሪክ ይናገራል! ይህ

በታሪካችን የጥንታዊት ኢትዮጵያ

የጀግኖች አርበኞች የጦርነትና የድል

ቀጥታ ድምጽ ነው! ከሸዋ ጠቅላይ

ግዛት ከጣርማ በር የጦር ሜዳ! ሐምሌ

5 ቀን 1928 ዓ.ም፡፡

ውድ የኢትዮጵያ ጀግና ተሰማ እርገጤ

ከፍልሚያ በኋላ አሁንም ሌላ ፍልሚያ

ይጠብቀዋል! ወሳኙን ድል ለማምጣት

ቆርጦ ተነስቷል! በየቀኑ በፍቃደኝነት

ወደ አርበኝነት የገቡ ወጣቶች

የጦር መሳሪያ እንዲታጠቁ ጥረት

ያደርጋል! ወራሪው ኃይል ዘመናዊ

የጦር መሳሪያ ታጥቋል! ከኢትዮጵያ

አርበኞች አንዳንዶቹ ጠብመንጃ

እንዳልነበራቸው ታውቋል! ብሄራዊ

ስሜት የህሊና እረፍት ነስቷቸው

ቤታቸውን አቃጥለው በሬዎቻቸውን

ሸጠው፣ እርሻቸውን ትተው ከጀግኖች

ጋር ተቀላቅለዋል! ጦር፣ ጋሻና ጎራዴ

ብቻ የያዙም ተስተውለዋል! የተቃጠለ

ብሄራዊ ስሜት ደግሞ ከጦር መሳሪያም

ይልቃል! እርግጥ ነው! የማያቅማማ

ልብ ፈጠነም ዘገየ ለድል ያበቃል!

ጀግናው አርበኛ ተሰማ እርገጤ አሁን

ከመስክ ስምሪት ወታደራዊ መረጃ

ደርሶታል! የፋሽስት ኢጣሊያ ወራሪ

ኃይል ተዋጊዎች በቅርብ የሰፈሩበትን

ቦታ ለይቶ አውቆታል! ጀግና ለፋሽስት

ጊዜ አይሰጥም! ቆራጡ አርበኛ

ወራሪው ኃይል ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ታጥቋል! ከኢትዮጵያ አርበኞች አንዳንዶቹ ጠብመንጃ

እንዳልነበራቸው ታውቋል! ብሄራዊ ስሜት የህሊና እረፍት ነስቷቸው ቤታቸውን አቃጥለው

በሬዎቻቸውን ሸጠው፣ እርሻቸውን ትተው ከጀግኖች ጋር ተቀላቅለዋል! ጦር፣ ጋሻና ጎራዴ ብቻ

የያዙም ተስተውለዋል! የተቃጠለ ብሄራዊ ስሜት ደግሞ ከጦር መሳሪያም ይልቃል! እርግጥ

ነው! የማያቅማማ ልብ ፈጠነም ዘገየ ለድል ያበቃል!

ተሰማ እርገጤ አሁን ተንቀሳቅሷል፡

፡ አርበኞች ምድብ መስመራቸውን

ይዘዋል! ተጠጋግቶ መጓዝ ክልክል

ነው! ተፈነጣጥሮ በቅርብ ርቀት

እየተጠባበቁ መጓዝ የግድ ይላል፡

፡ ሁሉም በየምድብ መስመራቸው

ጉዟቸውን ቀጥለዋል!

ጀግናው ተሰማ እርገጤ ከጥቂት

አርበኞች ጋር ወራሪው ኃይል

ከሰፈረበት ግራ አቅጣጫውን ይዟል!

አርበኞች የነፍስ ወከፍ የጦር

መሳሪያቸውን ታጥቀዋል! ጀግናው

ተሰማ እርገጤ ዘወትር በጥቂት

መስዋዕትነት ታላቅ ድል ለማስመዝገብ

በቁርጠኝነትና በዓላማ ጽናት ይዋጋል!

የተቃጠለ ብሄራዊ ስሜት ተላብሷል!

ማቅማማት አያውቅም! መስዋዕት

መሆን ወይም ድል! አርበኛ ሲሰዋ

በእልህ የውጊያ ዝግጁነት መንፈሱ

ይነሳሳል! የፋሽስት ኢጣሊያ ወራሪ

ኃይል የኢትዮጵያን መሬት ለቅቆ

እስካልወጣ ለአፍታም ጦርነቱን

ላለማቆም ቆርጧል! ጥቁር በነጭ

እንዴት ይገዛል? የአድዋ ጀግኖች

አጥንት እሾህ ሆኖ ይውጋን! ለጣሊያን

ፈጽሞ አንገዛም! ይህ የአርበኞች ድምጽ

ነው! ኢትዮጵያ ጀግና ነበራት! ነበራት!

ነበራት! አሁን ቆራጦቹ የጥንታዊት

ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች የፋሽስት

ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል ተዋጊ ከሰፈረበት

ቦታ ደርሰዋል! ሁሉም በምድብ

መስመራቸው ከተኩስ ቦታቸው ላይ

ተገኝተዋል፡፡ የወራሪውን ኃይል ሰፈር

ከብበዋል! ለተኩስ ዝግጁ! ለግድያ

ዝግጁ! ለምርኮ ዝግጁ! የኢትዮጵያ

ጀግና መቼ ፈርቶ ያውቃል? ድም!

ድም! ድም! ዱዋ! ዱዋ! ዱዋ!

ጦርነቱ በኢትዮጵያ ጀግኖች ቅድሚያ

ተነሳሽነት ተከፍቷል! ወራሪው

ኀይል የአጸፋ ተኩስ ከፍቷል! አሁን

መከበባቸውን አውቀዋል፡፡ የተፋፋመ

ተኩስ ቀጥሏል! እሳት ይዘንባል!

ጀግና ለክብሩ ቆርጧል! የፋሽስት

ወራሪ ኃይል ለማምለጥ ይተኩሳል!

የኢትዮጵያ አርበኞች ደግሞ የወራሪው

ኃይል ተዋጊዎችን በነበሩበት ከአፈር

ጋር ለማዋሀድ በተግባር ተነስተዋል!

ጦርነቱ በተከፈተ በጥቂት ጊዜያት

ውስጥ በወራሪው ኃይል ላይ ከፍተኛ

ጉዳት ደርሷል! የኢትዮጵያ አርበኞች

የበላይነት ይዘዋል! ተኩሱ ቀጥሏል!

ይህ የታሪክ ድምጽ ነው! በአሁኑ

ሰዓት በኢትዮጵያ ታሪክ በሸዋ ጠቅላይ

ግዛት ውስጥ በልበላ በተባለ ቦታ

ከጀግኖች አርበኞች ጋር በተፋፋመ

ጦርነት መካከል ቆመናል!

በርካታ የፋሽስት ወራሪ ኃይል

ተዋጊዎች ተደምስሰዋል! አንዳንዶች

ተሾሎክልከው አምልጠዋል፡፡ የነበሩበት

ድንኳን ነድዷል! ሬሳ ተዝረክርኮ

ይታያል! በማያጠራጥር መልኩ

አርበኞች ድልን ተጎናጽፈዋል! ቆራጡ

አርበኞ ተሰማ እርገጤ እንደ አንበሳ

ይጎማለላል! ባሁኑ ሰዓት በየቦታው

የተዝረከረከውን የወራሪው ፋሽስት

ሬሳ በየአቅጣጫው ያስተውላል!

ቆራጡ የህዝብ ባለአደራና የሀገር

ባለውለታ ተሰማ እርገጤ በዚሁ

በበልበላ ጦርነት ጣሊያኖችን የገደለ

ከመሆኑም በላይ በርካታ የፋሽስት

ተዋጊ ባንዳዎችን እንደ ገብስ አጭዷል!

የጦር መሳሪያዎችንም ማርኳል!

ድል አድራጊው የኢትዮጵያ አርበኛ

አሁን ወራሪው ኃይል ሲፈረጥጥ

ያዝረከረከውን የጦር መሳሪያ

በመሰብሰብ ሂደት ላይ ይታያል!

አንዳንድ አርበኞች ከወራሪው ኃይል

ተዋጊዎች ሬሳ ወገብ ላይ ዝናር ሲፈቱ

ይስተዋላል! ይህ የታሪክ ድምጽ ነው!

የኢትዮጵያ አርበኞች ከፋሽስቶች

ሬሳ ላይ የጦር መሳሪያ ከመፍታት

በስተቀር ልብስ ፈጽሞ አይገፍፉም!

ነውር ነው! ይህ በታሪካችን

ለአንድነታቸው፣ ለሉዓላዊነታቸው፣

እንዲሁም ለሐይማኖታቸው ቀናዒ

የነበሩ የጥንታዊት ኢትዮጵያ የጀግኖች

አርበኞች የጦርነትና የድል ድምጽ

ነው! ከሸዋ ጠቅላይ ግዛት ከበልበላ

ጦር ሜዳ! ጳጉሜ 2 ቀን 1928 ዓ.ም!

ቆፍጣናው አርበኛ ተሰማ እርገጤ

አሁን በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ውስጥ

ግፋይታ በተባለ መንድር ድርጅታዊ

አቅሙን በማጎልበት ስራ ተጠምዷል!

ወጣቶች ወደ አርበኝነት እንዲገቡ

በተከታታይ ይቀሰቅሳል! በምስጢር

የጦር መሳሪያ ይሸምታል! በከፍተኛ

ደረጃ በውጊያ ስነ-ልቦና ላይ ይስተዋላል!

የፋሽስት ወራሪ ኃይል ግን ጀግናው

ተሰማ እርገጤ የነበረበትን ቦታ

ለይቶ አውቋል! ባንዳ ሹክ ብሎታል!

በዚህን ጊዜ ወራሪው ኃይል ጀግናውን

ተሰማ እርገጤን ለመግደል ቆርጦ

መነሳቱ ተሰማ! ቆፍጣናው ተዋጊ

ተሰማ እርገጤ መረጃው ደርሶታል!

ታዲያ ምን ሊያደር ይችላል?

ቆፍጣናው ተዋጊ ተሰማ እርገጤ

ማድረግ የነበረበትን መቼ አጣ?

በቅድሚያ ገዥ መሬት ይዞ ጠበቀው!

ወራሪው ኃይል አሁን እየትግተለተለ

መጥቶዋል! አርበኛው ተሰማ እርገጤ

ዳቦ በማር ይገምጣል! ወራሪው ኃይል

ተጠግቷል! የኢትዮጵያ አርበኞች ከሳር

ጋር ሳር መስለዋል! ወራሪው በአሰራር

ቀድሟል! ባንዳ ቀድሟል! ጣሊያኖች

ወደ ኋላ ቀርተዋል! መገናኛ መሳሪያ

ይዘዋል! ከጦር መሳሪያ ደግሞ ሽጉጥ

ብቻ ታጥቀዋል! የወራሪው ኃይል

ተዋጊዎች በአሰራር አሁንም ወደ

ፊት ሲጠጉ ይስተዋላል! ድም! ድም!

ድም! ዱዋ! ዱዋ! ዱዋ! የወራሪውን

ኃይል ተዋጊዎች በአሰራር ጉዞ

ከርቀት ዒላማቸው ውስጥ አስገብተው

ይጠባበቁ የነበሩት ጀግኖቹ የኢትዮጵያ

አርበኞች በቅድሚያ ተነሳሽነት ተኩስ

ከፍተዋል! ከፊት የነበሩ ባንዳዎችን

መትተው ጥለዋል! ከወራሪው ኃይል

የአጸፋ ተኩስ በኋላ ጦርነቱ ወዲያው

ተጋግሏል! ነገር ግን ረጅም ሰዓት

አልፈጅም! ቆራጦቹ የኢትዮጵያ

አርበኞች ወዲያው አጥቅተው

የበላይነትን ጨብጠዋል! ጀግናው

አርበኛ ተሰማ እርገጤ የፈረጠጠውን

ባንዳ እያሳደደ ከአፈር ጋር ያዋህድ

ገባ! በርካታ የነፍስ ወከፍ የጦር

መሳሪያዎችንም ማርኳል! ጦርነቱ

በኢትዮጵያ ጀግኖች ድል አድራጊነት

ተጠናቀቀ! ይህ የጥንታዊት ኢትዮጵያ

ጀግኖች አርበኞች ቀጥታ የታሪክ

ድምጽ ነው! ከሸዋ ጠቅላይ ግዛት

ግፋይታ ከተባለ ውጊያ መስክ በቀጥታ

ለዛሬው ተረኛ ትውልድ የሚተላለፍ

የታሪክ ድምጽ ነው! መስከረም 15

ቀን 1929 ዓ.ም!

ቆራጡ የጦር ሰው ተሰማ እርገጤ

ፈጽሞ ሊበገር አልቻለም! በዚህ

ምክንያት የፋሽስት ኢጣሊያ ወራሪ

ኃይል በጣም ተበሳጨ! ተበሳጭቶ

ግን ዝም አላለም! ጀግናውን አርበኛ

ተሰማ እርገጤን ይዞ ለሚያቀርብለት

ከፍተኛ ሹመት እንደሚሰጠው አወጀ!

በተጓዳኝም የአርበኛውን ዘመዶች

ከየቦታው ለቃቅሞ አሰራቸው!

አርበኛው ተሰማ እርገጤ ግን ከአቋሙ

ፍንክች ሳይል ቀርቷል! በሀገር ፍቅር

የተቃጠለው ጀግናው አርበኛ ተሰማ

እርገጤ ከአንድ ድል በኋላ ፋታ

ሳያገኝ ወዲያው ለጦርነት ይዘጋጃል!

ወራሪው ኃይል የግድ ኢትዮጵያን

ለቅቆ መውጣት አለበት፡፡ መፍትሔው

ደግሞ ጦርነት ብቻ መሆኑን አጥብቆ

ያምናል! ይህ የኢትዮጵያ አርበኞች

የማይቀለበስ ውሳኔ ነው! ቆራጡ

አርበኛ ተሰማ እርገጤ አሁን ጨለንቆ

በተባለው ቦታ የሰፈረውን የፋሽሰት

ወራሪ ለመደምሰስ በጉዞ ላይ መሆኑ

ወደ ገፅ 6 ይዞራል
9 የካቲት 7 ቀን 2006 ዓ.ም. ቅፅ 1 ቁጥር 2 ነገረ-ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ለምን ኋላ ቀረች?

ክፍል ሁለት

ግርማ ሞገስ

●የኢትዮጵያ የመንግስት ስልጣን

ሽግግር ባህሏ

ለዘጠኝ መቶ አመቶች ላላነሰ ጊዜ

ኢትዮጵያ በዘመናዊ (Secular)

ትምህርት እና ትምህርቱን ተከትሎ

ለሚመጣ ዘመናዊነት እና ስልጣኔ

ጀርባዋን መስጠቷ ለኋላ መቅረቷ

አንዱ አውራ ምክንያት እንደነበር

ባለፈው አንብበናል። በእንቅርት ላይ

ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ደግሞ ቢያንስ

ቢያንስ ከአክሱም ስልጣኔ መውደቅ

ወዲህ ጀምሮ አምባገነኑ ህውሃት/

ኢህአዴግ በ1983 ዓ.ም. ስልጣን

እስከጨበጠበት ጊዜ ድረስ በእርስ

በርስ ጦርነት ይፈጸም የነበረው

የመንግስት ሽግግር ባህሏ ኢትዮጵያን

እጅ እና እግሯን ተብትቦ ስለስልጣኔ

የምታስብበት መተንፈሻ ጊዜ እንኳን

እንዳይኖራት አድርጓት ነበር። ስለዚህ

ኢትዮጵያ ከውጭ ወረራ ረጅም

የነፃነት ዘመን ቢኖራትም በስልጣኔ

እንዳትገፋ ያደረጋት ሁለተኛው

አውራ ምክንያት በእርስ በርስ ጦርነት

የሚፈጸመው የመንግስት ሽግግር

ባህሏ ነበር ማለት ይቻላል። በዚህ

ጉዳይ ላይ ተክለ ፃዲክ መኩሪያ፣

ባህሩ ዘውዴ፣ ሃሮልድ ማርኪውስ

እና ፓንክረስት የመሳሰሉ የታሪክ

ምሑራን ብዙ ጽፈውታል።

የመንግስት ሽግግር ባህሏም በበኩሉ

ከስልጣኔ እንድትርቅ አድርጓል።

ለምን ያህል ጊዜ (ስንት አመቶች)?

ግምት መስጠት እንችላለን?

እንሞክር! በኢትዮጵያ ሲደረግ

የነበረው የመንግስት ሽግግር

ታሪካችን ሁለት አኪያሄዶች ነበሩት።

አንደኛው አኪያሄድ ከአንድ ዝርያ

ወደ ሌላ ዝርያ የሚደረግ የመንግስት

ሽግግር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ

በአንድ ዝርያ ውስጥ ከአባት ወደ

ልጅ የሚፈጸም የመንግስት ስልጣን

ሽግግር ነበር። ሁለቱም አይነት

የመንግስት ሽግግሮች ከጦርነት ነፃ

አልነበሩም። በጦርነቶቹ መካከል

ልዩነት ካለም የጦርነቱ አስከፊነት

መጠነ እና የጦርነቱ እድሜ ብቻ

ነበር።

ለጥናት እንዲያመቸን ካፄ ኢዛና

(321 ዓ.ም.) በፊት ለመንግስት

ሽግግር (ለስልጣን) የተደረጉትን

የእርስ በርስ ጦርነቶች በሙሉ

ከግምት አናስገባም። ጥናታችንን

ይበልጥ ቀላል ለማድረግ ስንል ካፄ

ኢዛና ወዲህ ተሞክረው ያልተሳኩትን

ቁጥር ስፍር የሌላቸው ለመንግስት

ሽግግር የተደረጉ የእርስ በርስ

ጦርነቶች በሙሉ ወደጎን እንተዋለን።

ጥናታችን ካፄ ኢዛና ወዲህ በተደረጉት

የተሳኩ የመንግስት ሽግግሮች ላይ

ያተኩራል። ስለዚህ በ321 ዓ.ም.

በስልጣን ላይ ከነበረው ካፄ ኢዛና

ዘመነ መንግስት ጀምረን እስከ በ1983

ዓ.ም. በእርስ በርስ ጦርነት ስልጣን

የጨበጠው አምባገነኑ የህውሃት/

ኢህአዴግ መንግስት ድረስ ከነበሩት

1662 አመቶች ውስጥ የመንግስት

ሽግግር ባህሏ ስንት አመቶች እጅ

እና እግሯን ተብትቦ በማሰር ስልጣኔ

ከውስጥም እንዳታበቅል እንዳደረጋት

አጠቃላይ ግምት ለመስጠት

እንሞክራለን። እያንዳንዱ የመንግስት

ሽግግር ባህላችን ጦርነት የፈጀው

ጊዜ በዝርዝር ተጽፎ የተላለፈልን

መረጃ የለንም። ለግዜው ማድረግ

የምንችለው እነ ተክለ ፃዲቅ ጽፈው

ካወረሱን ትረካ ግምት ለመውሰድ

መሞከር ነው። እያንዳንዱ የተሳካውም

ያልተሳካውም የመንግስት ሽግግር

የፈጀውን ጊዜ አመት በአመት

የማስላቱን ስራ ለመጪው ትውልድ

ታሪክ ተመራማሪዎች እንተዋለን።

ካፄ ኢዛና (321 ዓ.ም.) ወዲህ

የተደረጉትን ዋናዎቹን የመንግስት

ሽግግሮች

እንደሚከተለው

መከፋፈል እንችላለን፣ (1) ከኢዛና

ዝርያዎች ወደ ንግስት ዮዲት (ቤተ

እስራኤሎች) ዝርያዎች፣ (2) ከቤተ

እስራኤሎች ወደ ላስታው መራ ተክለ

ሃይማኖት (ዛጉዌ ስረወ መንግስት)

ዝርያዎች፣ (3) በ1262 ከላስታ

አገዎች ወደ ሸዋው ይኩኖ አምላክ

ዝርያዎች፣ (4) በ1523 ዓ.ም. ያፄ

ይኩኖ አምላክ ዝርያ ከነበረው ልብነ

ድንግል ወደ ይማም አህመድ (ግራኝ

በሚል የሚታወቁት እና በአባታቸው

የኦጋዴ በእናታቸው ደግሞ የሐረር

ተወላጅ የሆኑት)፣ (4) በጎንደር ካፄ

ገላውዲዎስ 1533-1552) እስከ ዐፄ

እዮዋስ (1747-1761) (በአባት የቋራ

አማራ በእናት ደግሞ የየጁ ኦሮሞ)፣

(5) ከራስ ስሑል እስከ የየጁው

ትንሹ ራስ ዐሊ (ዘመነ መሳፍንት)፣

(5) ካፄ ቴዎድሮስ (1847-1860)

እስከ ሰቆጣው ዐፄ ተክለ ጊዮርጊስ

(1860-1864) ከዚያ ወደ ተምቤኑ

ዐፄ ዮሐንስ (1864-1881) ከዚያ

ወደ ሸዋው ምኒልክ (1882-1906)፣

(6) ከምንሊክ ወደ ልጅ ልጃቸው

ልጅ እያሱ ከዚያ ወደ ምኒልክ ሴት

ልጅ ዘውዲቱ ከዚያ ወደ ኃይለስላሴ

ከዚያ ወደ ደርግ ከዚያ ወደ ህውሃት/

ኢህአዴግ። እነዚህ የመንግስት

ሽግግሮች በሙሉ የተጠናቀቁት

በእርስ በርስ ጦርነት እና ሽብር

ነበር።

ከአባት ወደ ልጅ የተደረጉ የመንግስት

ሽግግሮችም ከሁከት እና ከእርስ በርስ

ጦርነቶች የጸዱ ስላልነበሩ ሁከቱን

እና ጦርነቱን ለመቀነስ ነገስታቱ

ልጆቻቸውን በጠባቂ በሚከተሉት

እስርቤቶች ሆነው የንጉስነት

ተራቸውን (እድላቸውን) እንዲጠብቁ

አድርገዋል። (1) ደብረ ዳሞ አምባ

እስር ቤት፥ በአክሱም ዘመነ መንግስት

በዙፋን ላይ የሚገኘው ንጉሱ ታመመ

በተባለ ቁጥር በቤተ ዘመድ ውስጥ

“ዙፋን ይገባኛል” “ተረኛው እኔ

ነኝ” የሚሉ ሁከቶች እና ጦርነቶች

ይነሱ ነበር። ስለዚህ ይኽን ሁከት

እና የርስ በርስ ጦርነት ለማስወገድ

ነገስታቱ ልጆቻቸውን እና በቅርብ

ከሚዛመዱዋቸው የሚወለዱትን

ጨምረው በትግራይ ከአዲግራት

በስተ ምዕራብ በሚገኘው ደብረ ዳሞ

አምባ ጠባቂ ተደርጎላቸው የንግስና

ተራቸውን እንዲጠብቁ ይደረግ

እንደነበር ተክለ ፃዲቅ መኩሪያ

ይገልጻል።

ከሠርፀ ዘድንግል ወደ ፋሲል አባት (ዐፄ ሱስነየስ) የተደረገው የመንግስት ሽግግር በቀጣይነት የርስ በርስ

ጦርነት ዘመን ነበር። ሠርፀ ሲሞት ለትንሽ ልጁ አቆብ (1590-1595) አወረሰ። የአጎቱ ልጆች ዙፋን

ለኛ ይገባል የሚል ጦርነት ከፍተው ዙፋኑ ከአቆብ ወደ ዘድንግል (1595-1596) ከዚያ ከዘድንግል

እንደገና ወደ ያእቆብ (1596-1598) ከዚያ በመጨረሻ ወደ ፋሲል አባት ሱስነየስ

(1598-1625) የተሸጋገረው በድምሩ 10 አመቶች የርስ በርስ ጦርነት ከተደረገ ቧላ ነበር።

(2) ግሸን አምባ እስር ቤት፣

የአክሱም ነገስታትን ልማድ

በመከተል የላስታዎቹ ነገስታትም

ተመሳሳይ ችግር ለማስወገድ ከደሴ

በስተምዕራብ ግሸን አምባ ይባል

የነበረውን ተራራማ ቦታ ለእስር ቤት

ተጠቅመውበታል። (3) ግሸን አምባ

እስር ቤት (እንደገና)፣ የአክሱምን

እና የላስታን ነገስታት ልማድ

በመከተል እስከ ልብነ ድንግል ድረስ

የነበሩት የሸዋ ነገስታትም ይህንኑ

ግሸን አምባን እንደ እስር ቤት

ተጠቅመዋል። በግሸን አምባ የነበሩት

የነገስታት ዝርያዎች በሙሉ

በእስር ላይ ሳሉ በልብነ ድንግል

እና በይማም አህመድ መካከል

የተካሄደው እንደፈጃቸው ተክለ

ፃዲቅ መኩሪያ እና የውጭ ታሪክ

ጸሐፊዎች ጽፈዋል። (4) ወህኒ

ተራራ እስር ቤት፣ በጎንደር ዘመነ

መንግስት ደግሞ ካፄ ፋሲል ጀምሮ

ከጎንደር በስተ ምዕራብ የሚገኘውን

ወህኒ ተራራን ለተመሳሳይ ተግባር

ነገስታቱ ተጠቅመዋል።

ለጥቀን ከኢዛና ዘመነ መንግስት

(321 ዓ.ም.) እስከ ህውሃት/ኢህአዴግ

ስልጣን እስከጨበጠበት 1883

ዓ.ም. ድረስ ከተደረጉት የመንግስት

ሽግግሮች ውስጥ አለፍ አለፍ እያልን

ጥቂት ምሳሌዎች እንመለከታለን፣

(1) ወደኋላ መለስ ብለን የንግስት

ዮዲትን ዘመን ብናይ ከመንግስት

ስልጣን በፊት 50 አመቶች ግድም

እና በስልጣን ዘመኗ ደግሞ 40

አመቶች በድምሩ 90 አመቶች

የጦርነት ዘመን እንደነበሩ ተጽፎ

እናያለን።

(2) በቱርክ እና ግብጽ የታገዙት

የይማም አህመድ ዘመንንም

ብንወስድ በቱርክ ወታደራዊ

የበላይነትን ከማግኘታቸው በፊት

እና ወታደራዊ የበላይነትን የያዙበት

አመቶች እንዲሁም ፖርቱጋሎች

ክርስቲያኖችን አግዘው የተዋጉበት

አመቶች በድምሩ ከ30 አመቶች

በላይ ይሆናል።

(3) ከሠርፀ ዘድንግል ወደ ፋሲል

አባት (ዐፄ ሱስነየስ) የተደረገው

የመንግስት ሽግግር በቀጣይነት የርስ

በርስ ጦርነት ዘመን ነበር። ሠርፀ

ሲሞት ለትንሽ ልጁ አቆብ (1590-

1595) አወረሰ። የአጎቱ ልጆች ዙፋን

ለኛ ይገባል የሚል ጦርነት ከፍተው

ዙፋኑ ከአቆብ ወደ ዘድንግል (1595-

1596) ከዚያ ከዘድንግል እንደገና

ወደ ያእቆብ (1596-1598) ከዚያ

በመጨረሻ ወደ ፋሲል አባት ሱስነየስ

(1598-1625) የተሸጋገረው በድምሩ

10 አመቶች የርስ በርስ ጦርነት

ከተደረገ ቧላ ነበር። ምናልባትም

ለዚህ ነበር ፋሲል ዮሐንስ ከተባለው

ልጁ በስተቀር የቀሩትን ልጆቹን እና

ሌሎች ዘመዶቹን ወደ ተራራ ወህኒን

የላከው።

(4) ታላቁ እያሱ ከተገደለበት (1698)

ጊዜ ጀምሮ ባባቱ ቋራ በእናቱ የጁ

የሆነው ዐፄ እዮአስ እስከተገደለበት

1761 ዓ.ም. ድረስ የነበሩት 63

አመቶች የማያቋርጥ የእርስ በርስ

ጦርነት አመቶች ነበሩ።

(5) በ1761 ዓ.ም. ዘመነ መሳፍንት

ከተነሳ ወዲህ እስከ ወደቀበት 1847

ዓ.ም. ድረስ 86 አመቶች ሲኖሩ ከዚያ

ውስጥ የየጁው ራስ ጉግሳ በገዙበት

ዘመን ከነበረው ትንሽ መረጋጋት

በስተቀር ሰላም አልነበረም።

(6) ከዚያም ያፄ ቴዎድሮስ ዘመን

(1847-1860) ማለቂያ ባልነበረው

የማስገበር ዘመቻ ተጠምዶ ስለነበር

እስከ ፍጻሜያቸው ድረስ የነበሩት 13

አመቶች የመንግስት ሽግግር የእርስ

በርስ ጦርነት አመቶች ነበሩ።

(7) ያፄ ተክለ ጊዮርጊስ 4 አመቶችም

የጦርነት ዘመን ነበሩ።

(8) ያፄ ዮሐንስ ዘመን (1864-1881)

በግብጾች እና በቅኝ ገዢዋ ኢጣሊያ

ጦርነቶች ከመጠመዱ ባሻገር

ለስልጣን ከውስጥ የሚያፈነግጠው

ጥቂጥት አልነበረም። በዚህ የተነሳ

ዮሐንስ መጨረሻ መተማ ላይ

እስከሞቱበት ጊዜ ድረስ በቤተ

መንግስታቸው ያደሩባቸው ቀኖች

በጣም ጥቂት ነበሩ።

(9) ከምኒሊክ ዘመነ መንግስት

(1882/9-1906/13) እስከ ምኒልክ

ፍጻሜ (1906/13) ድረስ የተወሰነ

የሰላም ጊዜ ቢኖርም ከዚያ እስከ

ኃይለስላሴ ንጉሰ ነገስት (1922/30-

1967/75) ያልተቋረጠ የመንግስት

ሽግግር ጦርነቶች ተካሂደዋል።

የምኒልክን ዙፋን ወራሽ የልጅ

እያሱ ዘመን (1906/13-1919/27)

ከመንግስት የተፈነቀለው በብዙ

የርስ በርስ ደም መፋሰስ ነበር።

ከዚያም ወደ ኃይለስላሴ ንግስና

በተደረገው የመንግስት ሽግግር

ሂደት የልጅ እያሱን ደጋፊዎች፣

የንግስት ዘውዲቱን (1919/27-

1922/30) ደጋፊዎች፣ የምኒልክን

ባለቤት የእቴጌ ጣይቱን ደጋፊዎች

የማጽዳት በርካታ የርስ በርስ ጦርነት

ተፈጽሟል።

የኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ከርካሳ

አውሮፕላን የመጀመሪያ ስራ

ለመንግስት ሽግግር በጎንደር

ተቃዋሚዎች ላይ ቦንብ መጣል

እንደነበር እና የኢትዮጵያ

የመጀመሪያው ታንክም በአዲስ አበባ

ለተመሳሳይ ጉዳይ ስራ ላይ ውለው

እንደነበር ባህሩ ዘውዴ ያመለክታል።

የኃይለስላሴን የመጨረሻዎቹ አመቶች

የእርስ በርስ ጦርነቶች ብንጨምር

ከምኒልክ ዘመነ መንግስት ጅማሬ

እስከ ኃይለስላሴ ዘመነ መንግስት

ፍጻሜ ድረስ በግምት 16+4=20

አመቶች የጦርነት አመቶች ብሎ

መውሰድ ይቻላል)

(10) የደርግ 17 አመቶች ከዘመነ

መሳፍንት በባሰ ደረጃ ከ7 በላይ

የሚሆኑ ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች

እርስ በርስ ተዋግተዋል።

ስለዚህ ካፄ ኢዛና ከነገሰበት ከ321

ዓ.ም. እስከ በ1983 ዓ.ም. ድረስ

ከነበሩት 1662 አመቶች ውስጥ

የተሳኩት የመንግስት ሽግግሮች

በግምት ከ360 እስከ 400 አመቶች

ያህል ጊዜው ወስደዋል ብንል ስህተት

አይመስለኝም።

በ400 አመቶች ላይ ያልተሳኩት

የመንግስት ሽግግሮች የወሰዱት ጊዜ

ቢጨመርስ? በዚያ ላይ ኢትዮጵያ

ከቱርኮች እና ከኢጣሊያ ጋር

ያደረገቻቸው ጦርነቶች የወሰዱት

ጊዜ ቢጨመርስ?

እንደ እኔ ከሆነ በአጠቃላይ በትንሹ

ከ500 አመቶች ላላነሰ ጊዜ ኢትዮጵያ

እጅ እና እግሯ በጦርነት ተተብትቦ

ከአገር ውስጥ ስልጣኔ እንዳይበቅል

ተደርጓል። ትንሽ የሰላም ጊዜ

እና ጥሩ መሪ ሲገኝ የሚደረገው

እድገትም ለጥቀው በሚካሄዱ

ጦርነቶች ይወድማሉ። አገሪቱ ወደ

ኋላ ትሄዳለች። ይህን የእርስ በርስ

ጦርነት አውዳሚነት እና ጎታችነት

ጸባይ አስመልክቶ ተክለ ፃዲቅ

መኩሪያ ካፄ ልብነ ድንግል እስከ

ዐፄ ቴዎድሮስ በሚለው መጽሐፉ

የታላቁ እያሱን ዘመን እንደ ምሳሌ

በመውሰድ በታላቁ እያሱ በዘመን

የገነባው በሙሉ ከታላቁ እያሱ በኋላ

በመጡት የርስ በርስ ጦርነቶች

መውደማቸውን ይተርካል።

የመንግስት ሽግግር እርስ በርስ

ጦርነት ታሪካችን ኢትዮጵያችንን

ወደ ኋላ የማስቀረት እንጂ ወደ

ስልጣኔ የማራመድ ሚና ተጫውቶ

እንደማያውቅ ግልጽ ይመስለኛል።

የመንግስት ሽግግር ባህላችን ብዙ

ጊዜ አቃጥሏል ኢትዮጵያ ወደፊት

እንዳትራመድ በማድረግ። ከዚህ በኋላ

ኢትዮጵያ በስልጣኔ ብዙ እርቀዋት

የሄዱትን አገሮች ለመድረስ የርቀት

ቅነሳ ስራ ላይ በትጋት መሰማራት

አለባት። ወደ ስልጣኔ መንደር

የሚያደርሱ ብዙ ስራዎች በትጋት

መስራት ይጠበቅባታል። ለመንግስት

ሽግግር የሚደረግ የ’እርስ በርስ

ጦርነት ግን አንዱ አይደለም።

በቅርቡ ደግሞ ትጥቅ ትግል

ወደ ገፅ 6 ይዞራል
ነገረ-ኢትዮጵያ

ቅፅ 1 ቁጥር 2

የካቲት 7 ቀን 2006 ዓ.ም.

10

የአስር ሳንቲም ኢኮኖሚ ወፖለቲካ

አ በላይ ማናዬ

ያስር በምዕራብ ጎጃም ዞን ባህር ዳር ዙሪያ

ወረዳ ነዋሪ ነበር፤ አሁን ጠቅልሎ የከተማ

ነዋሪ ሆኗል፣ ባህር ዳር፡፡ አሁን ላይ ያስር

እኔ ነኝ ያለ የናጠጠ ሃብታም ነጋዴ ነው፡

፡ ያስር የሚለው ስሙም ተቀይሯል፡፡

ለዚህ ጽሑፍ ብቻ የድሮ ስሙን ተጠቅመን

እንቀጥላለን፡፡

ያስር የሚለውን ስም ያወጡለት

በተወለደባት ትንሽ የገጠር ከተማ ከልጅነት

ጊዜው ጀምሮ ይሰራው ከነበረው የንግድ

(ችርቻሮ) ስራ ጋር በተያያዘ ነበር፤ አንዱን

ጥሎ አንዱን ያነሳበት ከነበረው የችርቻሮ

ገበያው፡፡ በለጋነቱ፣ ገና የችርቻሮ ንግድን

‹ሀ› ብሎ ሲጀምር ወላጅ እናቱን (አባቱ

በህይወት የሉም) የጠየቃት ሀምሳ ሳንቲም

ብቻ እንደነበር ያስር ዛሬ ላይ በትውስታ

ይናገራል፡፡ ብላቴናው ያስር ከዕናቱ ባገኛት

ሀምሳ ሳንቲም ትንንሽ የዕለት ከዕለት

የህብረተሰቡ መገልገያዎችን እና የህጻናትን

ጥያቄዎች ‹ማስቀየሻ› ጣፋጭ ነገሮችን

እያዞረ በገበያ ግርግር መሐል ይሸጥ ጀመር፡

፡ በተለይም መርፌ፣ ከረሚላ፣ ማስቲካ፣

ምላጭ፣ ክር፣ መርፌቁልፍ፣ አዝራር እና

የመሳሰሉትን ሸቀጣ ሸቀጦች ለገበያተኛው

እዚያው ባለበት ቦታ ይዞ ከተፍ በማለት

ታወቀ፡፡ ትንሽ ጊዜ ሲዘዋወር ካልታዬ

እንኳ ‹ያስር የት ሄደ› ባዩ ይበረክታል፡፡

ይህ ፈጣንና ፍልቅልቅ ብላቴና ያለችውን

ትንሽ ሳንቲም በፍጥነት እየተገለገለ

መጠኗ ከዕለት ወደ ዕለት እንድትጨምር

አደረጋት፡፡ በተለይ ቅዳሜ ዕለት ለያስር

የሞት የሽረት ቀኑ ነበረች፤ ሞቅ ባለው

ገበያ ውሰጥ እየተሹለከለከ ችርቻሮውን

የሚያቀላጥፍባት ቀን ቅዳሜ ናት፡፡ ወዲያው

ከአንድ ደንበኛው ሱቅ ሸቀጦችን ይገዛል፤

ወዲያው በገበያተኛው መሀል እየተሹለከለከ

ያጣራል፡፡ ማንም ይግዛው ማን፣ ምንም

ይሽጥ ምን ያስር ጋር ያለው ዋጋ ያው

አስር ሳንቲም ብቻ ነበር፤ መርፌ ባስር

ሁለት ገዝቶ ከሆነ ባስር አንድ ይሸጣል፡፡

በቃ ይህ የያስር ገበያ ነው፡፡ ለያስር ከአስር

ሳንቲም በላይ ወጭ አውጥቶ ዕቃ መግዛት

ኪሳራ ነው፤ ምክንያቱም ሰዎች ካስር

ሳንቲም ውጭ ባለ ዋጋ አይገዙትም ነበር፡፡

እንዲህ እንዲህ እያለ ያስር ከአስር

ሳንቲም ጋር ጋብቻ መሰረተ፤ ጋብቻውም

ተመቸው፤ ብዙ ትርፍ ይዞለትም መጣ፡

፡ የገንዘብ ትርፍ ብቻ ሳይሆን ያላሰበውን

ዕውቅናም አተረፈለት፤ ይህም እናቱ

ያወጣችለትን ስም እንኳ አስቀየረው፡

፡ ሁሉም ሰው ከዕሱ ዕቃ ሲገዛ ባስር

ሳንቲም ብቻ በመሆኑ የብላቴናውን ስም

ያስር አሉት፣ ገበያተኞቹ፡፡ እሱም ስሙ

ተመቸው፤ ድንገት ገበያተኛውን ጠጋ

እያለ ‹ያስር!...ያስር!...ያስር አለ!› ይል

ጀመር፡፡ ገበያተኛውም ‹ያስር መርፌ›፣

‹ያስር ከረሚላ›፣ ‹ያስር አዝራር›፣ ‹ያስር

መርፌቁልፍ›…እያለ ይሸምተው ነበር፡

፡ ስሙ ያስር፣ የሚሸጣቸው ነገሮች

ዋጋቸው አስር ሳንቲም፤ መልካምና ለያስር

የተመቼው ስምሙ ጋብቻ ሆነ፡፡

አሁን ያስርን በቀድሞ ስሙ የሚጠራው

ሰው ጠፋ፤ ምናልባት እናቱም ብትሆን

ከዚህ ሁሉ በላይ ግን ያጣነው ትልቅ ጸጋ አለ፤ መብትን አሳልፎ

መስጠት፤ (የአስር ሳንቲም ፖለቲካ ልንለው እንችላለን)፡፡

ይህ ከገንዘቡም በላይ ነው፡፡ ባለታክሲዎች (ረዳቶች) በራሳቸው

ጊዜ የታክሲን ታሪፍ 2 ብር ከ90 የነበረውን ዋጋ 3 ብር

አድርገውታል፡፡ ከስንት አንድ ሰው መልስ ሲጠይቃቸው እንኳ

ይገላምጡታል፤ በተጨማሪም ሳንቲሙን ያለአግባብና ስርዓት

በጎደለው መልኩ ሲወረውሩለት ይታያል፡፡ ለምን ተጠየኩ

እንደማለት! ይህም መጀመሪያ እኛው ራሳችን ያስለመድናቸው

ነገር በመሆኑ ነው፤ ‹ቀድሞ ነበር እንጂ…› የሚሉት ብሂል

መሆኑ ነው፡፡

የምታስታውሰው አትመስልም፤ ‹ያስር›

የሉታል ‹አቤት!› ይላል፡፡ ያስር ኑሮው፣

ገቢው ተሻሻለ፡፡ ከራሱ የትምህር ቤት ወጭ

አልፎ ለእናቱ ደራሽ ሆነ፤ ከነበሩበት የከፋ

ድህነት ውስጥ አውጥቶ ማገገሚያ ክፍል

ውስጥ ጨመራቸው፡፡ ቀስ በቀስ የያስር

ግብይት ከአስር ሳንቲም ከፍ እያለ መሄዱ

አልቀረም ነበር፤ ቢሆንም ግን ስሙ፣

መጠሪያው አሁንም ያው ያስር ነበር፡፡

ያስር በዚህ ስም እየተጠራ፣ ንግዱን ግን

እያስፋፋ ለዓመታት ዘለቀ፤ በዓዕምሮም

ሆነ በአካል እያደገና እየጎለበተም መጣ፤

ገቢውም ደረጀ፡፡

የያስር ህይወት ከአስር ሳንቲም ጋር

የተቆራኘች ሆና የዘለቀችው ለአጭር

ጊዜ ብቻ አይደለም፤ ዛሬም ያስር እና

አስር ሳንቲም ቁርኝታቸው ጥብቅ ነው፡

፡ የዛሬው የናጠጠ ነጋዴነት፣ የዛሬው

የተትረፈረፈ ሃብትና ንብረት ባለቤትነት፣

የዛሬው ክብርና ሞገስ፣ የዛሬው በተደላደለ

ሁኔታ ህይወትን ቤተሰብን መምራት

መሰረታቸው አስር ሳንቲም ናት፡፡ በአስር

ሳንቲም ነግዶ አትርፏል፤ በአስር ሳንቲም

ዕውቅናን አግኝቷል፡፡ የሚገርመው ያስር

በደንበኞቹ ዘንድ ታማኝና ቅን ነበር፤ ዛሬም

ድረስ እንዲያ እንደሆነ ይነገርለታል፡፡

በተተመነው ዋጋ ነግዶ ከማትረፍ ውጭ

በሌላ ነገር አይታማም ይሉታል ደንበኞች፡፡

አሁን ላይ ያስር ሀብታምና በርካታ

ካፒታል የሚያንቀሳቅስ ነጋዴ ነው፤ ከዚህ

ያደረሰችውን አስር ሳንቲም ግን አይንቃትም፡

፡ አስር ሳንቲም ለማትረፍ ትናንት ብቻ

ሳይሆን ዛሬም ከመነገድ ወደ ኋላ አይልም፡

፡ አውቆ ካልሆነ በቀር አስር ሳንቲምን

ንቆ መልስ ከመቀበል አይመለስም፤

ምክንያቱም ዋጋዋን ያውቃታል፡፡ ‹‹አስር

ሳንቲም ትንሽ መስላ የምትታዬን ዋጋዋን

በሚገባ ካልተረዳንና ህይወትን የመለወጥ

አቅሟን ካላወቅን ነው፤ እኔ በአስር ሳንቲም

በምሸጠው መርፌ አይደለም እንዴ የተቀደደ

ልብስህን ሰፍተህ ገመናህን የምትሸፍነው?

ባስር ሳንቲም በገዛኸው መርፌ አይደለም

እንዴ ለስቃይ የዳረገህን እሾህ ከእግርህ

ነቅሰህ የምታወጣው? ታዲያ አስር ሳንቲም

ዋጋዋ ትልቅ አይደለም ወይ?›› በማለት

ይጠይቃል ያስር፡፡

ብዙዎቻችን ወደ አዲስ አበባ ታክሲዎች

ዘው ብለን ገብተን የአስር ሳንቲምን ዋጋና

ከሳንቲሟ ጋራ እያጣን ያለነውን ውድ

ጸጋ ካየን ግን ያስር ለአስር ሳንቲም ካለው

ግንዛቤ በእጅጉ የተለዬ ሆኖ እናገኘዋልን፡

፡ በየጊዜው ዋጋው እየተከለሰ የሚገኘው

የታክሲ የአንድ ፌርማታ ጉዞ ክፍያ ወይም

ታሪፍ ብዙ ነገሮችን እያሳየን ይገኛል፡

፡ ላለፉት ሁለት ወራት ስራ ላይ ባለው

ታሪፍ መሰረት የሁለት ፌርማታ ዋጋ 2

ብር ከ90 ሳንቲም ነው፡፡ ለሶስት ብር አስር

ሳንቲም የጎደለው ማለት ነው፡፡ ይህቺ አስር

ሳንቲም ናት እንግዲህ መነጋገሪያችን፡፡

ብዙ ተሳፋሪዎች 3 ብር ከፍለው መልስ

አይቀበሉም፤ መልሳቸው ደግሞ አስር

ሳንቲም ናት፡፡ ብዙ የታክሲ ረዳቶች

(ወያላዎች) 3 ብር ተቀብለው መልስ

አይሰጡም፤ መልሱ ደግሞ አስር

ሳንቲም ናት፡፡ ግን ለምን? በጥናት ላይ

የተመሰረተም ባይሆን ብዙዎቹ ተሳፋሪዎች

አስር ሳንቲምን ከመናቅ የመነጨ ሊሆን

ይችላል መልሳቸውን የማይጠይቁት፡፡ ብዙ

የታክሲ ረዳቶች አስር ሳንቲምን ለማስቀረት

ካላቸው ፍላጎት (በቀን ምን ያህል ገንዘብ

ማስቀረት እንደሚችሉ ያውቃሉና) አሊያም

ጠያቂ ከሌለ በማለት ሊሆን ይችላል መልስ

የማይሰጡት፡፡ ሁለቱም ወገኖች ግን ተገቢ

ያልሆነ አረዳድ ውስጥ የገቡ ናቸው፡፡ አስር

ሳንቲም ዋጋ አላት፤ አስር ሳንቲም ገንዘብ

ናት፡፡

ቀደም ብለን ያነሳነው ያስር በአስር

ሳንቲም ትልቅ ደቋና ደፍኖባታል፤ ትልቅ

ቁምነገር ከውኖባታል፡፡ ስለዚህም አስር

ሳንቲም ትንሽ አይደለችም፡፡ ተሳፋሪዎች

ንቀዋትም ሆነ በሌላ ምክንያት ታክሲ

ውስጥ ትተዋት የሚወርዱት አስር

ሳንቲም ተጠራቅማ የጎጆን ቀዳዳ መድፈን

ይቻላታል፤ ቢነግዱባት አትርፋ ቤት

ለመስራት ትበቃለች (የያስርን እውነታ ልብ

ይሏል)፡፡ አንድ ተሳፋሪ በቀን 20 ሳንቲም

ታክሲ ውስጥ ትቶ ቢወርድ በወር ውስጥ

6 ብር ያጣል ማለት ነው፡፡ ይህ ስድስት

ብር ለአንድ የኔ ቢጤ አራት ዳቦ ሊገዛለት

የሚችል ገንዘብ ነው፡፡ ለተቸገሩት ወገኖች

የሚውልን (ከእጅ ላይ ያለችን ሳንቲም

መስጠት ታክሲ ላይ ጥሎ እንደመውረድ

ባይቀልም) ገንዘብ እንዲሁ መተው አጓጉል

መቀናጣት ሊሆን ይችላል፡፡

ከዚህ ሁሉ በላይ ግን ያጣነው ትልቅ ጸጋ

አለ፤ መብትን አሳልፎ መስጠት፤ (የአስር

ሳንቲም ፖለቲካ ልንለው እንችላለን)፡፡

ይህ ከገንዘቡም በላይ ነው፡፡ ባለታክሲዎች

(ረዳቶች) በራሳቸው ጊዜ የታክሲን ታሪፍ

2 ብር ከ90 የነበረውን ዋጋ 3 ብር

አድርገውታል፡፡ ከስንት አንድ ሰው መልስ

ሲጠይቃቸው እንኳ ይገላምጡታል፤

በተጨማሪም ሳንቲሙን ያለአግባብና

ስርዓት በጎደለው መልኩ ሲወረውሩለት

ይታያል፡፡ ለምን ተጠየኩ እንደማለት! ይህም

መጀመሪያ እኛው ራሳችን ያስለመድናቸው

ነገር በመሆኑ ነው፤ ‹ቀድሞ ነበር እንጂ…›

የሚሉት ብሂል መሆኑ ነው፡፡

በእጃችን ያለን ነገር መልቀቅ በኋላ

እንደማስመለስ ቀላል አይደለም፡፡ አሁን

ላይ ንቀን የምንተዋት እያንዳንዷ ነገር

ዘግይታ ብዙ ዋጋ ታስከፍለናለች፡፡

ካለመጠየቅ ደጃዝማችነት ይቀራል እንዲሉ

አበው ስለመብታችን የመቆርቆር ንቃት፣

መብታችንን ማስከበር ላይ ድክመት

ይታይብናል፡፡ ከተነጠቅን ወዲያ መጮህ

ብቻ ሳይሆን ቀድሞውንም አሳልፎ

ላለመስጠት መጣር ተገቢ ነው፡፡ ዛሬ አስር

ሳንቲም የወሰደብን ሰው ነገ ቤታችንም

ለመውሰድ ወደ ኋላ ሊል አይችልም፡

፡ ይህ የአስር ሳንቲም ጉዳይ አይደለም፤

ይህ የክብር ጉዳይ ነው፡፡ ግለሰቦችም ሆነ

መንግስታት በማናለብኝነት የሚነጥቁን

የእኛ የሆኑ ነገሮች ሁሉ መነሻቸው

የእኛ አለመጠየቅና ለመብታችን ጥብቅና

አለመቆም ነው፡፡

ዛሬ ቀበሌ ላይ የመናገር መብትህን የነፈገህ

የቀበሌ አስተዳዳሪ ዝም ከተባለ የሐገር

መሪም ሆኖ ጨቋኝና የለየለት አምባገነን

መሆኑ የታወቀ ነው፤ ዛሬ ጨቋኝነቱን

ቀበሌ ላይ የነገርነውና የታገልነው ሰው ሀገር

የመምራት ዕድሉን አግኝቶ ስልጣን ላይ

ቢወጣ የህዝብን ጉልበት የተረዳ ለመሆኑ

ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ነው፡፡ እናም፣

የእኛ ለመብቶቻችንና ለገንዘባችን ቸልተኛ

መሆን አምባገነንና ስግብግብ መሪዎችን

ለመፍጠራችን እማኝ ነው፡፡ የመብት ትንሽ

የለውም፤ መብት የክበር ጉዳይም ነው፡፡

ስንደፈር በትንሹ ነው፣ በትልቁ ነው ልንል

አንችልም፡፡ ጭብጡ ያለው መርሁ ላይ

ነው፡፡ መብቱን በእንዝላልነት አሳልፎ የሰጠ

ሰው መልሶ ሲጠይቅም አያምርበትም፡፡
11የካቲት 7 ቀን 2006 ዓ.ም. ቅፅ 1 ቁጥር 2

የኔ-ሐሳብ

ነገረ-ኢትዮጵያ

እንደሀገር መግባባት የተሳነን ‹ባቢሎናውያን›

ትሁን ተስፋ

ባቢሎናውያን በስልጣኔ ከመራቀቃቸው

የተነሳ ወደ ሰማይ ህንጻ በመገንባት

አምላካቸው ጋር መድረስ ፈለጉ፡፡ ይህ

ስራቸው ያላስደሰተው አምላክም ይግባቡበት

የነበረውን ቋንቋቸውን ደበላለቀባቸው፡

፡ ከቋንቋቸው መደበላለቅ የተነሳ መግባባት

ተስኗቸው አካፋ የተጠየቀው ዶማ፣ ድንጋይ

የተጠየቀው ጭቃ፣ ሚስማር የተጠየቀው

አጠና እያቀረበ መግባባት ባለመቻላቸው

የገነቡት ሰማይ ጠቀስ ህንጻ ከግቡ ሳይደርስ

ሊፈርስ ችሏል፡፡

ሁሌም ይህን ታሪክ ሳስታውስ የሀገሬ

ልጆች መግባባት አለመቻል ይታወሰኝና

ምን አልባት ቋንቋችን ተደበላልቆ ይሆን

እንድል ያስገድደኛል፡፡ በብሄራዊ ደረጃ

መግባባት ከማይችሉ ሀገራት መካከል

ኢትዮጵያ በቀዳሚነት ትጠቀሳለች ብል

ማጋነን አይሆንም፡፡ ኢትዮጵያውያን እንደ

ሀገር ከምንግባባባቸው ነገሮች ይልቅ

የማንግባባባቸው ጉዳዮቻችን ብልጫውን

ይወስዳሉ፡፡ በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ

ያለመግባባታችን ጥግ መራራቅ ነው፡፡ ከዚህ

ያለመግባባት ችግራችን የተነሳ የተጣባን

ልዩነትን በጉልበትና በጠብ-መንጃ የመፍታት

አባዜ ያለመግባባታችንን ወደ ጫፍ

በመለጠጥ ወደ መጠፋፋት ሲገፋን ኑሯል፡

፡ በጠረጴዛ ዙሪያ ማለቅ የሚገባው ልዩነት

የተራዘመ ብጥብጥና ግድያ ካስከተለ በኋላ

አንዱ ጉልበታም በሌላ ጉልበታም እየተተካ

እዚህ ደርሰናል፡፡ ዓለም አንድ መንደር እየሆነ

በመጣበት በዚህ ጊዜ የእኛ መንደሮች ግን

የዓለም ጥግ ላይ ያሉ የምድር ዋልታዎችን

ያክል ተራርቀዋል፡፡

ቀጥዬ ለምን መግባባት ተሳነን፣

ላለመግባባታችን ተጠያቂው ማን ነው፣

የማንግባባባቸው ጉዳዮች የትኞቹ ናቸው?

እና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በማሳያዎች

ለመዳሰስ እሞክራለሁ፡፡

ማሳያ አንድ፡- ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት

የሀገራችን የፖለቲካ ልሂቃን ኢትዮጵያና

ኢትዮጵያዊነትን የሚያዩበት መነጽር

የተንሸዋረረ መሆኑ ላለመግባባታችን እንደ

ምክንያት ሆኖ ይነሳል፡፡ አንዳንድ ምሁራን

ኢትዮጵያዊነትን የሀበሻነት (አማርኛና

ትግርኛ ተናጋሪዎች) መገለጫ ብቻ

አድርገው ይወስዱታል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ

የሚመጣው የኢትዮጵያ ታሪክ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ታሪክ በአንዳንዶቹ አምስት ሺህ

ዘመን ድረስ ሲለጠጥ በሌሎቹ ደግሞ ወደ

መቶ አመት ይኮማተራል፡፡ የአምስት ሺህ

ዘመን ታሪክ ተብሎ የሚጠቀሰው የኖህ ልጅ

ካም ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ጋር ተያይዞ

ያለው ሲሆን፣ በዚህም ኢትዮጵያ ተብላ

በመጽሀፍ ቅዱስም ሆነ በሌሎች መጽሀፍት

የምትጠቀሰው ሀገር ከግብጽ በታች ያለውን

የአፍሪካ ምድር ትይዛለች፡፡

በበተቃራኒው ደግሞ የመቶ አመት ታሪክ

ባለቤት የሚያደርጓት አሉ፡፡ ለመቶ አመቱ

ክርክር የሚጠቀሰው የቀድሞው ጠቅላይ

ሚንስትር የአቶ መለስ ትርክት ነው፡፡ አቶ

መለስ ጫካ መነበሩበት ዘመን ”የኤርትራ

ህዝብ ትግል ከየት ወዴት” በሚል

ርዕስ ያሳተሙት መጽሀፍ ‹‹ኢትዮጵያ

የመቶ አመት ታሪክ ነው ያላት›› ይልና

የኢትዮጵያ ፈጣሪ ንጉስ ምኒልክ እንደሆኑ

ለማስረዳት ያጣጥራል፡፡ መከራከሪያቸውን

ያጠናክርላቸው ዘንድም ‹‹የአክሱም ሀውልት

ለወላይታው ምኑ ነው?›› ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡

ዳሩ ግን የአክሱም ሀውልት ሲገነባ ወላይታው

አስተዋጽኦ ማድረጉን ዘንግተውት አይደለም፤

‹ኢትዮጵያ ቅኝ ገዥ ነች› ወደሚል ሀላፊነት

የጎደለው መከራከሪያ ለመግፋት እንጂ፡፡ ከዚህ

ጋር በተያያዘ አንዳንድ የኦሮሞ ልሂቃን ቅኝ

ተገዝተናል እንገነጠላለን የሚሉት ሌላው

ኢትዮጵያዊነት ላይ የተደነቀረ ሳንካ ነው፡፡

በነዚህ ምሁራን ትርክት መሰረት ኢትዮጵያ

ቅኝ ገዥ ነች፤ ኢትዮጵያዊነትም በግድ

የተጫነብን ቀንበር ስለሆነ አንቀበለውም

ወደሚል ጫፍ ይለጠጣል፡፡ ይህንን

የኢትዮጵያን ቅኝ ገዥነት ለማስረዳትም

ጎሰኝነትን አጥብቆ በማጓን ኢትዮጵያዊነትን

መገዳደር መገለጫው ያደርጉታል፡፡ ብቻ

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት የተወሰነው

ህዝብ ፍላጎት ብቻ በማስመሰል እውነቱን

ለማድበስበስና አውቆ ላለመግባባት የቆረጥን

እንመስላለን፡፡

አንዳንድ የስልጣን ጥም የተጣባቸው ግለሰቦች

ልክ እንደ ኤርትራው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ

“ባርነት ወይስ ነጻነት” በሚል የማወናበጃ

ምርጫ ትንንሽ ግዛቶችን መፍጠር ይፈልጋሉ፡

፡ በዚህም የተነሳ ሳንግባባ እንደወንድማማች

ሳንተያይ የጎሪጥ እንደተዳባን እዚህ ደርሰናል፡

፡ እዚህ ላይ መሰመር ያለበት ያለመግባባቱ

ጉዳይ የፖለቲካ ልሂቅ ነኝ በሚለው እንጅ

በሌላው ህዝብ ዘንድ የሌለ መሆኑን ነው፡

፡ ብቻ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት እንዲህ

ሳያግባባን አለን፡፡

ማሳያ ሁለት፡- ወደብና የባህር በር

ኢትዮጵያ ለብዙ ዘመን ጠላት ሲያፈራባትና

ሲያዋጋት የኖረው የባህር በሯ መሆኑ

ይታወቃል፡፡ ይህን የባህር በር ለመያዝ

በተደረገው ተጋድሎ አባቶቻችን ብዙ

ጀብዱ ፈጽመዋል፡፡ ይህን የዘነጋው አቶ

መለስ ዜናዊ ግን አሰብን አሳልፎ ሰጥቷል፡

፡ ስለጉዳዩ ሲጠየቅም፣ “የባህር በር

የተስፋፊወችና የጦርነት ናፋቂወች ወሬ

ነው፤ አንድ ሀገር ለማደግ የግድ የባህር

በር አያስፈልጋትም፤ ኢሳያስ አፈወርቂ

ከፈለገ ግመሎቹን ያጠጣበት”፡፡ ጠቅላይ

ሚንስትሩ ይህን ቢሉም ወደባችን አሳልፈን

በመስጠታችን ብቻ ለጅቡቲ በቀን ከሶስት

ሚሊዮን ዶላር በላይ እንደምንከፍል

አጥተውት አይደለም፡፡ ከምንከፍለው ዶላር

በተጨማሪ የራሳችን ሚስጥር የሚባል ነገር

ሊኖረን አይችልም፤ በተለይ የጦር መሳሪያን

በተመለከተ፡፡ በነገራችን ላይ ለጂቡቲ ወደብ

የምንከፍለው ዶላር አባይን ለመገደብ ቢውል

በአመት ከስድስት ወር ውስጥ የሚወጣው

ብቻ ይበቃን ነበር፡፡ አሁንም ልብ ማለት

የምንችለው ኢህአዴጎች ይህን ቢሉም አሰብን

አንጋጦ የሚያይ ዜጋ መኖሩ እሙን ነው፡

፡ በመሆኑም የወደብ ጥያቄ ላለመግባባታችን

አንዱ ምክንያት ነው፡፡

ማሳያ ሦስት፡- የአድዋ ድል

የአድዋ ድል ለጥቁር የሰው ዘር ሁሉ የነጻነት

ተምሳሌት መሆኑ የሚዘነጋ አይደለም፡፡ እነ

አብርሃም ሊንከን እነ ማልኮን ኤክስን ጨምሮ

ብዙ ለጥቁር ህዝቦች ነጻነት የታገሉ ሰዎች

ጥቁር ነጭን ሊያሸንፍ እንደሚችል ትምህርት

ያገኙት ከአድዋ መሆኑ ጸሀይ የሞቀው ሀቅ

ነው፡፡ ይህ የጥቁሮች የመብት እንቅስቃሴ

ኢትዮጵያኒዝም ተብሎም ይጠራል፡

፡ ኢትዮጵያ አድዋ ላይ ድል ማድረጓን

ተከትሎ እንደ ታላቋ ጽዮናዊት ኢየሩሳሌም

ወደ ኢትዮጵያ ሀይማኖታዊ ጉዞ የሚያደርጉ

ጥቁሮች ተበራከቱ፡፡ የሀይቲው ቤኒቶ

ሲልቪያን እና የምዕራብ ኢንዲያው ጆሴፍ

ቪታሊየን ወደ ተስፋይቱ ምድር ኢትዮጵያ

ጉዞ ያደረጉ የመጀመሪያቹ ጥቁሮች ናቸው፡፡

እነሱን በመከተል እንደ ቡከር ቲ.ዋሽንግተን፣

አይዳ ቢ.ዌልስ፣ ደብሊዩ ኢ.ቢ ዱበይሰን

የመሳሰሉ ታዋቂ ጥቁር አፍሪካውያን ስለ

አድዋ እና የኢትዮጵያ የነጻነት ተምሳሌትነት

በስፋት ማውራት ጀመሩ፡፡

ከተወሰኑ ትውልዶች በኋላ “በራስ

ተፈሪያን” ስያሜ የሚደረገው ጉዞም የአድዋ

ተጽዕኖ ውጤት ነው፡፡ አድዋ ሲነሳ አብሮ

የሚነሳ ሀገራዊ አንድነታችን ነው፡፡ ይህ

የጥቁሮች ሁሉ መኩሪያ የሆነ ድል ግን

እኛን ባለቤቶቹን ሊያግባባን አልቻለም፡

፡ አድዋ ኢትዮጵያንም በአለም ብቸኛዋ

በነጭ ቅኝ ያልተገዛች ሀገር ያደርጋታል፡፡

እዚህ ላይ በታሪክ ቅኝ ያልተገዙ የአፍሪካ

ሀገራት እየተባሉ ሲጠቀሱ የምንሰማቸው

ላይቤሪያንና ኢትዮጵያን ቢሆንም የላይቤሪያ

ቅኝ አለመገዛት ግን ብዙም የሚያከራክር

አይደለም፡፡ ምክንያቱም ላይቤሪያ ተብሎ

የሚጠራው ሀገር ከአሜሪካ በተመለሱ

‹ባሪያዎች› የተገነባች ሀገር ስለሆነች እንደ

ነጻ ሀገር ለመጥቀስም የሚያስኬድ ስላልሆ

ነው፡፡ ይህ ልንኮራበት የሚገባን ታሪካችን

እንደውም ለኤርትራውያን ተገንጣዮች

የሚያሳፍር ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ ምኒልክ

አድዋ ላይ ተመልሰው ኤርትራን ለጣልያን

አሳልፈው ሰጡብን የሚለው ትርክት ለእነዚህ

ተገንጣዮች እንደ መልካም የመጫወቻ ካርድ

አገልግሎአቸዋል፡፡ ሻቢያና ህወሓት ጫካ

በነበሩበት ወቅት ወታደር ለመመልመል

“የአድዋን ታሪክ ትቀበላለህ አትቀበልም”

የሚል መስፈርት እንደነበራቸው የትናንት

ትዝታ ነው፡፡ ለማነኛውም የአድዋ ድል

ሌላኛው ያለመግባባታችን ምንጭ መሆኑ

አልቀረም፡፡

ማሳያ አራት፡- ሰንደቅ አላማ

ሰንደቁ አላማ አንዱ የአንድ ሀገር መለያ

ነው፡፡ ኢትዮጵያ በዚህ የታደለች ነበረች፡

፡ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ሰንደቃችን

የነጻነታችን ምልክት የአንድነታችን

ተምሳሌት ሆኖ ለብዙ ዘመን ኖሯል፡፡

ነገር ግን በየጊዜው የሚነሱት አምባገነኖች

የራሳቸውን ምልክት ሲለጥፉበትና ህዝቡም

አርማውን በግድ እንዲቀበል ሲገፉት መኖሩ

ሀቅ ነው፡፡ የቅርብ ጊዜዎቹን ብንወስድ እንኳ

ንጉሱ የይሁዳ አንበሳ ምልክት ሲለጥፉበት፣

ደርግ በበኩሉ የማያውቀውን የሶሻሊዝም

መዶሻ ለብዶበት ነበር፡፡ ቀጥሎም ኢህአዴግ

ታጋይ መሪው ‹‹ባንዲራ ጨርቅ ነው›› ብሎ

በቀደደለት ክፍተት ተጠቅሞ የበሶ መቋጠሪያ

አድርጎት አዲስ አበባ እንደገባ ትናንት

የነበሩት ይመሰክራሉ፡፡

ባንዲራ ጨርቅ ነው የሚለው የአቶ መለስ

አባባልም ኢህአዴግን ምን ያክል ዋጋ

እንዳስከፈለው የሚታወስ ነው፡፡ ኢህአዴግም

ጨርቅ ባለው ባንዲራው ላይ ኮከብ መሀሉ

ላይ ሰፍቶ የእኩልነትና የመከባበር ምልክት

ነው እያለን ነው፡፡ መቸም ኮከብ በምን

መልኩ የአንድነትና የመከባበር ምልክት

እንደሚሆን ኢህአዴግም ሊያውቀው

አይችልም፡፡ ለማንኛውም ይህ ሰንደቁ መሀል

ላይ የተሰፋው ሰማያዊ ኮከብ ለልዩነታችን

እንደ ምክንያት ሆኖ አገልግሏል፡፡ ባለኮከብ

ሰንደቅ አንቀበልም ያሉ ኢትዮጵያውያን

በተለያየ ክብረ በአላት ላይ ኮከብ የሌለውን

ባንዲራ መጠቀማቸው ያሳሰበው ኢህአዴግ

የባንዲራ አጠቃቀም አዋጅ እስከማውጣት

ድረስ ተገዷል፡፡ የሰንደቅ አላማ ቀንም ማክበር

ሰንደቁ አላማ አንዱ የአንድ ሀገር መለያ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በዚህ የታደለች ነበረች፡፡

አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ሰንደቃችን የነጻነታችን ምልክት የአንድነታችን ተምሳሌት ሆኖ

ለብዙ ዘመን ኖሯል፡፡ ነገር ግን በየጊዜው የሚነሱት አምባገነኖች የራሳቸውን ምልክት

ሲለጥፉበትና ህዝቡም አርማውን በግድ እንዲቀበል ሲገፉት መኖሩ ሀቅ ነው፡፡ የቅርብ

ጊዜዎቹን ብንወስድ እንኳ ንጉሱ የይሁዳ አንበሳ ምልክት ሲለጥፉበት፣ ደርግ በበኩሉ

የማያውቀውን የሶሻሊዝም መዶሻ ለብዶበት ነበር፡፡ ቀጥሎም ኢህአዴግ ታጋይ መሪው

‹‹ባንዲራ ጨርቅ ነው›› ብሎ በቀደደለት ክፍተት ተጠቅሞ የበሶ መቋጠሪያ

አድርጎት አዲስ አበባ እንደገባ ትናንት የነበሩት ይመሰክራሉ፡፡

ጀምሯል፡፡ ይህ አዋጅ ሰንደቅ አላማውን

በመኪና ላይ ማውለብለብ የሚችለው

ጠቅላይ ሚንስትር፣ የሀገሪቱ ርዕሰ ብሄርና

አምባሳደሮች እንደሆኑ ቢጠቅስም በዘልማድ

የሚታየው ግን አፈር ጫኝ መኪና ሳይቀር

ሲያንጠለጥለው ነው፡፡ የሚገርመው እኛ

ሰንደቅ አላማችንን ላለመግባባት ይህን ያክል

ስንለጥጠው አብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሀገራት

ግን አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ሰንደቁን በተለያየ

መልክ ሲጠቀሙበት እናያለን፡፡ ምክንያቱ

ደግሞ እኛ እንደ ሀገር ሊያግባባን የሚችል

ባንዲራ የለንም የሚል ነው፡፡

ማሳያ አምስት፡- ህገ-መንግስት

የአንድ ሀገር መንግስት ህዝቦቹን

ያስተዳድርበት ዘንድ ህገ መንግስት

ያስፈልገዋል፡፡ በዚህ ህገ መንግስት ውስጥ

ህዝቦች ያላቸው መብትና ግዴታወች

እንዲሁም መንግስት ያለው ስልጣን በህግ

ተገድቦ ይሰጠዋል፡፡ ይህ የሚሆንበት

ምክንያት የመንግስትን ፈላጭ ቆራጭነት

ሚና ለመገደብ ሲባል ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ

መሪወች የስልጣን እድሜያቸውን ለማራዘም

ሲሉ እንደፈለጉ እንዳይሆኑ ሲባል በህገ

መንግስት ይታሰራሉ፡፡ በሀገራችን የህገ-

መንግስት ታሪክ ውስጥ እስከ አሁን

ከተቀረጹት ህገ መንግስቶች ሁሉ የተሻለ

የሰብአዊም ይሁን የዴሞክራሲያዊ መብቶችን

በማካተት የ1987 ዓ.ምቱ ህገ መንግስት

የተሻለ ነው፡፡ ይህ ማለት ግን ህገ መንግስቱ

እንከን አልባ ነው ማለት አይደለም፡፡

በተለይም አንዳንድ ድንጋጌዎች የልዩነት

መፈጠሪያ ሁነው እናገኛቸዋለን፡፡ ለምሳሌ

የህገ-መንግስቱ አንቀጽ 39 ለሀገር አንድነት

እንቅፋት ነው፣ ስለዚህ ህገ መንግስቱ

በሚፈቅደው መሰረት ይሻሻል የሚል ጥያቄ

ማንሳት በሀገር ክህደት ሊያስከስስ ይችላል፡

፡ ይህ እንኳን ባይሆን የአድሃሪነት ታርጋ

ሊያስለጥፍ ይችላል፡፡

ሌላው የመሬት ባለቤትነት መብትን

የሚያትተው አንቀጽ ነው፡፡ መሬት

የመንግስት ነው፤ ሊሽጥም ሆነ ሊለወጥ

አይችልም የሚለው የኢህአዴግ ግትር

አቋም፣ መሬት የህዝብ መሆን አለበት

ከሚለው የተቃራኒ አቋም ጋር መላተሙ

በህገ-መንግስቱ ላይ ያለውን ልዩነት ሰማይ

እንዲነካ ያደርገዋል፡፡ መሬት የሚሸጠውና

የሚለወጠው በኢህአዴግ መቃብር ላይ ነው

የሚለውን የኢህአዴግ ትንታኔ ነቃፊዎች

የመሬት መሸጥንና መለወጥን ሃሳብ

ለማንበር የግድ ኢህአዴግን መቃብር ውስጥ

መጨመር ግድ ነው ብለው ሊገፉ ይችላሉ፡

፡ በዚህም ህገ መንግስታችን የልዩነት ሰበብ

ከመሆን አልተረፈም፡፡

ማሳያ ስድስት፡- የፍትህና የጸጥታ ተቋማት

አብዛኛውን ጊዜ የሀገራችን የፍትህ

ተቋማት ሁሉንም ሊያስማማ የሚችል

ስራ ሲሰሩ አይታዩም፡፡ እነዚህን የፍትህና

የጸጥታ ተቋማት ስራ በምንዳስስበት ወቅት

የምናገኘው እውነት በጣም አስደንጋጭ ነው፡

፡ ለምሳሌ የሀገር ደህንነትና መረጃ ማዕከል

ስራው የሀገሩን ህልውና መጠበቅ ሆኖ ሳለ

የሚሰራው ስራ ግን ከአንድ የህዝብ ድርጅት

የሚጠበቅ አይደለም፡፡ የኢህአዴግን ህልውና

ለመጠበቅ የተቋቋመ በሚመስል መልኩ

ለኢህአዴግ ያሰጋሉ ያላቸውን ግለሰቦችና

ድርጅቶች እየተከታተለ ማደንና ማስፈራራት

ግፋ ሲልም አፍኖ በመውሰድ አሳፋሪ

ተግባርና እርምጃ ያለ ምንም ፍርድ በራሱ

ሲወስድ ስናይ ተቋሙ የኢህአዴግ የግል

ንብረት ነው እንዴ ያስብላል፡፡

በተጨማሪም ፖሊሶች በተለያየ ወቅት

የወሰዱትን እርምጃ በመንተራስ ስራቸው

ግብር እየከፈለ የቀጠራቸውን ምስኪን ድሀ

መደብደብ ነው እንዴ ብለን እስክንጠይቅ

ያደርሰናል፡፡ ለምሳሌ ያክል በ97 ምርጫ

የተነሳውን አለመግባባት ተከትሎ በመለስ

ዜናዊ ቀጭን ትዕዛዝ መከላከያችንና የፖሊስ

ሀይሉ የወሰደው የእመቃ እርምጃ ከህዝቡ

ጋር እንዲቃቃር አድርጎታል፡፡ በዚህ የተነሳ

ወደ ገፅ 15 ይዞራል
ነገረ-ኢትዮጵያ

ቅፅ 1 ቁጥር 2

ማርቆስ ሀጎሶች እና ዳሮ ነጋሾች ዛሬም

የካቲት 7 ቀን 2006 ዓ.ም.

ያስፈልጉናል!

-የመንግስት ሰራተኛው እና መምህሩ የደሞዝ ጭማሪ ያስፈልገዋል!

12

እያስፔድ ተስፋዬ

ዓለም አቀፍ ደረጃ የሰራተኛ

ማህበራት እንዴት፣ መቼና ለምን

ተመሰረቱ? ስለምን ታገሉ? ምንስ

አስገኙ? የሚለውን ታሪክ ለመዳሰስ

ቦታውም ጊዜውም አይበቃንም፡፡

የእነዚህ ማህበራት መፈጠር በዓለም

አቀፍ ደረጃ አድካሚ የነበረው የስራ

ሰዓት ወደ 8 ሰዓት ዝቅ እንዲል

መደረግን ጨምሮ ብዙ ለውጦች

አምጥቷል፡፡ የዛሬው ትኩረታችን

ግን የሚሆነው በሀገራችን ከኢሰአማ

አንስቶ እስከ ኢሰማኮ ያለውን

የሰራተኛ ማህበር የመብት ትግል

ታሪክና ዘንድሮም ያላከተመውን

የሰራተኛውን ክፍል (በተለይ

የመንግስት ሰራተኞች) ሰቆቃ እና

ስቃይ በአጭሩ መዳሰስ ነው፡፡

በኃይለስላሴ ዘመን

በሀገራችን ኢትዮጵያ የሰራተኛ

ማህበራት ለመጀመሪያ ጊዜ

የተመሰረቱት በአፄ ኃይለስላሴ

ዘመነ መንግስት ነው፡፡ የታሪክ

ሰነዶች እንደሚጠቁሙት

የመጀመሪያው የሰራተኛ ማህበር

ተብሎ ሊጠቀስ የሚችለው በ1939

የተመሰረተው የኢትዮጵያ ባቡር

ጣቢያ ሰራተኞች ማህበር ነው፡፡

ከዚህ በኋላ ለመመስረት የተሞከሩ

የሰራተኛ ማህበራት በስርአቱ

ከፍተኛ አፈና ይካሄድባቸው የነበሩ

ሲሆን የሰራተኛው መሪዎችም

እስር እና ግድያ ይፈፀምባቸው

ነበር፡፡ የኋላ ኋላም ቢሆን የአፄው

ስርአት ለሰራተኛ ማህበራት

እውቅና በመስጠት ኢሰአማ

(የኢትዮጵያ ሰራተኞች አንድነት

ማህበር) እንዲመሰረት ቢያደርግም፤

የኢሰአማን የበላይ አመራር

የኃይለስላሴ መንግስትና የአሜሪካ

መንግስት (በሲ.አይ.ኤ) አማካኝነት

በቁጥጥራቸው ስር አድርገውት

ነበር፡፡

እናም የልባቸው ያልሞላው የበታች

ሰራተኞች እና ማህበራት የመጀመሪያ

ትግላቸው እነዚህ የአገዛዙ ቀኝ

እጅ የነበሩትን አመራሮች (በየነ

ሰለሞን- ፕሬዝዳንት፣ አለም አብዲ-

ም/ክ ፕሬዝዳንት እና ፍስሀፂዮን-

ፀሀፊ) ማስወገድና በእውነተኛ

የሰራተኛው መሪዎች መተካት ነበር፡

፡ በተጨማሪም የስራው ሁኔታ እና

የመነሻ ደሞዝ እንዲሻሻል የሚሉ

ጥያቄዎችን አንግበው ይታገሉ

ነበር፡፡ በስተመጨረሻም የሰራተኛው

መሪዎች በወቅቱ ከኃይለስላሴ አገዛዝ

ጋር የሞት የሽረት ትንቅንቅ ውስጥ

ከነበሩት ተማሪዎች ጋር ግንኑነትን

ፈጥረው ለስርአቱ ፈታኝ ሆነው

እንደነበር ታሪክ ያስረዳል፡፡

በወቅቱ የሰራተኞች ቁጥር

እንደዛሬው የትየለሌ አይሁን እንጂ

ጥቂቶችም ቢሆኑ ለመብታቸው

እና ለአላማቸው ቆራጦች ነበሩ፡

፡ አብዮቱ በፈነዳበት በ1966 ዓ.ም

አካባቢ በኢሰአማ ስር ተመዝግበው

ይገኙ የነበሩ ሰራተኞች ቁጥር ወደ

100 ሺህ ይደርስ ነበር፡፡ አፈናው

እና ጭቆናው ሊያስቀረው ያልቻለው

አብዮት እንዲነሳ የሰራተኛ ማህበሩ

ያደረገው አስተዋፅኦም በቀላሉ

የሚገመት አይደለም፡፡

በ”ጊዜያዊ” ወታደራዊ መንግስት

ደርግ ዘመን

ከኃይለስላሴ መውረድ እና

“ጊዜያዊ” ወታደራዊው መንግስት

ወደ ስልጣን መምጣት በኋላም

ቢሆን የሰራተኛውን መብት

ለማስከበር ከሚደረጉ ትግሎች

በተጨማሪ በይፋ ጊዜያዊ ህዝባዊ

መንግስት እንዲመሰረት የሚጠይቁ

መግለጫዎችንና የዴሞክራሲያዊ

መብቶች መከበርን የሚደግፉ

መግለጫዎችን በማውጣት

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ ውስጥ

ጉልህ ሚና ተጫውቷል፡፡

የሰራተኛ ማህበሩ የጊዜያዊ ህዝባዊ

መንግስት ይመስረት ጥያቄን

ማንሳት ያልተዋጠለት ደርግ

እንደ ኃይለስላሴ ሁሉ የሰራተኛ

መሪዎችን ማሰርንና መግደልን

ስራዬ ብሎ ተያያዘው፡፡ በተለይም

ኢሰአማ (የሰራተኛው ማህበር)

ከመስከረም 8 እስከ 11 ባደረገው

የሶስት ቀናት ጉባኤ መንግስት

የሰራተኞች መሪዎችንና ሌሎች

የፖለቲካ እስረኞችን እንዲፈታ፣

በዴሞክራሲያዊ መብት ላይ

የተጫነው ገደብ እንዲነሳ፣ ጊዜያዊ

ህዝባዊ መንግስት እንዲመሰረት

የሚጠይቅ መግለጫ ማውጣቱን

ተከትሎ መስከረም 16 ቀን

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች

ማህበር አባላት የጉባኤውን ውሳኔ

ለሰራተኞች በሚያድሉበት ጊዜ

ወታደሮች በወሰዱባቸው የማጥቃት

እርምጃ 8 ሰዎች መግደላቸው

እና በ20ዎች ማቁሰላቸው የሚረሳ

አይደለም፡፡ ደርግም “በኢትዮጵያ

አየር መንገድ መስሪያ ቤት ውስጥ

ፀረ አብዮት ፅሁፍ ሲበትን የነበረ ሰው

እንዳያዝ በማወካቸው ወታደሮች

ተኩስ ለመክፈት ተገደዱ” በማለት

በይፋ ለማስተባበል ሞክሮ ነበር፡፡

ማርቆስ ሀጎስ

ማርቆስ የደርግ ሰለባ ከሆኑት

የሰራተኛው ግንባር ቀደም መሪዎች

አንዱ ነበር፡፡ ከኃይለስላሴ ዘመን

ጀምሮ ለሰራተኛው መብት እና

ለኢትዮጵያ ህዝብ መብት ሲታገል

የቆየው ማርቆስ እሱ በሃላፊነት

የሚመራው የሰራተኛ ማህበር

ለደርጉ በስልጣን ላይ ተደላድሎ

መቀመጥ አመቺ ሆኖ ስላልተገኘ

ገና በጠዋቱ ነበር ለእስር የተዳረገው፡

፡ በእስርም እያለ ከፍተኛ ስቃይ

ከተቀበሉ የሰራተኛው መሪዎች

አንዱ ነው፡፡ አንዳንዴም ከድብደባው

የተነሳ ብዙ ደም ይፈሰው ስለነበር

የወቅቱ የደህንነት ሹም ዳንኤል

አስፋው ማርቆስን ወንበር

እንዳታበላሽ መሬት ላይ ቁጭ በል

ሲል ያዘው ነበር፡፡ አንዳንዴም ደም

በደም ከሆነ በኋላ በእስረኞች መሀል

እያዞሩት ይሄ ነው ንጉስ የሚሆነው

እያሉ ያፌዙበት ነበር፡፡ በመጨረሻም

ማርቆስ ሰማዕት ሆኖ ከመሞቱ

በፊት እጅግ አስቀያሚ እንደሆነ

ወደሚነገርለት ወደ ማይጨው ጦር

ሰፈር እስር ቤት ተዘዋውሮ ነበር፡፡

የሰራተኛው መሪዎችን በማሰርና

በመግደል ያልተመለሰው ደርግ

የሰራተኛው ማህበርን በነፃነት

እንዳይንቀሳቀስ ስላደረገው

ሰራተኛው በግልፅ መደራጀቱን

በመተው በህዕቡ የላባደር ማህበርን

(ኢላማ) በመመስረት ለሰራተኛው

መብት መከበር የሚደረገውን ትግል

አጧጧፈው፡፡

ዳሮ ነጋሽ

ዳሮ ነጋሽ የደርጉን አፈና ለመቋቋም

ሲባል በህቡዕ የተደራጀው

የኢትዮጵያ ላብአደሮች ማህበር

መሪዎች መካከል አንዷ ነበረች፡፡

የብርሀንና ሰላም ማተሚያ መስሪያ

ቤት ሰራተኛ የነበረችው ዳሮ ነጋሽ

የ5 ልጆች እናት የነበረች ቢሆንም

ለሰራተኛው መብት መከበር

ከመታገል ግን ወደ ኋላ ሊያስቀራት

አልቻለም ነበር፡፡ ቤቷን ሳይቀር

ለህቡዕ ስብሰባዎች ማካሄጃነት ክፍት

ያደረገችው ዳሮ ቆራጥ እና በአላማዋ

ፅኑ ሴት ነበረች፡፡ የዜጎች መደራጀት

ያስበረግገው የነበረው ደርግም የ 9

ወር እርጉዝ እና የ 5 ልጆች እናት

የነበረችውን ዳሮ ነጋሽን ያለ ምንም

ርህራሄ በጥይት ደብድቦ ገደላት፡፡

ዳሮ ነጋሽ ለሰራተኛው እና ለሰፊው

ህዝብ መብት ሰማዕት የሆነች ጀግና

ነበረች፡፡

ደርግ እንዲህ ያሉ አሰቃቂ

እርምጃዎችን በማህበራቱ እና

በማህበራቱ መሪዎች ላይ ይውሰድ

እንጂ ሰራተኛው ለመብቱ

የሚያደርገውን ትግል ሊያስቆመው

አልቻለም፡፡

በተለያዩ ወቅቶች የስራ ማቆም

አድማ፣ የስራ ማለዘብ (ማቀዝቀዝ)፣

የማሺን መስበር ወዘተ ያሉ

የትግል ስልቶችን በመጠቀም

ሰራተኞች መብታቸውን ለማስከበር

እስከመጨረሻው ታግለዋል፡፡

በህወሓት/ኢህአዴግ ዘመን

በዘመነ ደርግ ለመብታቸው መከበር

ከፍተኛ ተጋድሎ ያደርጉ የነበሩት

ማህበራት በዘመነ ህወሓት/ኢህአዴግ

ዘመንም ቢሆን የትግላቸውን ፍሬ፤

የመብታቸውን መከበር ሊጎናፀፉ

አልቻሉም፡፡ እስርና ስደትና ግድያው

አሁንም ቀጠለ፡፡

ዳዊ ኢብራሂም (የሰራተኛ ማህበር

ፕሬዝዳንት የነበረ)

ህወሓት/ኢህአዴግ ስልጣን

እንደያዘ እንዳለፉት ስርአቶች

ሁሉ የሰራተኛ ማህበሩን በራሱ

ቁጥጥር ስር ለማድረግ ቢፈልግም

በወቅቱ የሰራተኛ ማህበሩ መሪዎች

የነበሩት በተለይም ፕሬዝዳንቱ ዳዊ

ኢብራሂም የሚቀመሱ አልሆኑም፡

፡ ስለዚህም አመራሮቹን ከማሰር

እና ከማስፈራራት አልፎ የተለያዩ

አሻጥሮችን መስራቱ የቅርብ ጊዜ

ትውስታ ነው፡፡ በመጨረሻም ጫናው

የበዛባቸው የማህበሩ ፕሬዝዳንት

ዳዊ ኢብራሂም በሞያሌ በኬንያ

አድርገው ሊሰደዱ በቅተዋል፡፡

አሰፋ ማሩ (የመምህራን ማህበር

ፕሬዝዳንት የነበረ)

ህወሓት/ኢህአዴግ ያመጣውን

የትምህርት ፖሊሲ በግልፅ

የተቃወመው የመምህራን ማህበርም

የደረሰው እጣ ፋንታ ያለፉት

ስርአቶች ያደርጉ ከነበረው የተለየ

አይደለም፡፡ የመምህራን ማህበር

ነፃነት ለድርድር እንደማይቀርብ

ግልፅ ያደረገው አመራርም

የተወገደበት መንገድ አነጋጋሪና

ጊዜ የሚፈታው ጉዳይ ነው፡፡

የመምህራን ማህበሩ ፕሬዝዳንት

የነበረው አሰፋ ማሩ ከቤቱ ወጥቶ

በእግሩ በሚጓዝበት ወቅት በቀን

በአደባባይ በጥይት ተገድሏል፡፡

አሁንስ? ኢሰማኮ?

አሁን ያለው የሰራተኛ ማህበር

ለሰራተኛው መብት መከበር

የሚታገል ነፃ ማህበር ነው

ወይስ የህወሓት/ኢህአዴግን

ፖሊሲ እንደወረደ የሚያስፈፅም

የስርአቱ ቀኝ እጅ? በኃይለስላሴ

ዘመን የሰራተኛ ማህበሩ የመነሻ

ደሞዝ ይስተካከል ሲል ያቀረበው

ጥያቄ ዛሬስ ቢሆን ተሻሽሏል???

በመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ

በዲግሪ ተመርቆ የሚቀጠር ሰራተኛ

የመነሻ ደሞዙ 1499 ብር ብቻ

ነው፡፡ በ800 ብሩ ቤት ተከራየ

ብንል...ለትራንስፖርት 300 ብር

አወጣ ብንል በቀረችው ብር ወሩን

የሚዘልቀው እንዴት ነው? ምንስ

እየተመገበ ነው የሚዘልቀው? ይህ

ሰው ቤተሰብ ያለው ከሆነ ደግሞ

የልጆች ቀለብ የልጆች ት/ቤት

ወዘተ ይጠብቀዋል፡፡ ይህ የመነሻ

ደሞዝ ለአመታት ሳይጨምር

ሲቆይ የሰራተኛ ማህበሩ አንዳችም

ተቃውሞ አሰምቶ አያውቅም!

በዚህም ማህበሩ የስርአቱ ቀኝ

እጅ እንጂ ሰራተኛውን የሚወክል

እንዳልሆነ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡

ምን ይደረግ?

ሰራተኛው አሁን ያለው ማህበር

እንደማይወክለው ካወቀና

አይወክለኝም ብሎ ካለ ህጉ

በሚፈቅድለት መሰረት ሌላ የሰራተኛ

ማህበር ማቋቋም ይችላል፡፡ ህጉ

በአንድ መስሪያ ቤት ውስጥ ከአንድ

በላይ የሆኑ ማህበሮችን ማቋቋም

እንደሚቻል በግልፅ ቢያስቀምጥም

በአንድ በኩል ከፍርሀት በሌላ

በኩል ደግሞ ካለው አፈና እና ጫና

የተነሳ በአንድ መስሪያ ቤት ውስጥ

ከተለመደው ማህበር ውጪ ሌላ

ማህበር ለማቋቋም ጥረት ሲደረግ

አይታይም፡፡ ሰራተኛው በተናጠል

የሚደረግ መብትን የማስከበር

ስራ የትም እንደማያደርስ አውቆ

ባመቸው መንገድ ሊደራጅ ይገባል፡፡

በግልፅ ተደራጅቼ መብቴን

ለማስከበር ያለው ሁኔታ አመቺ ነው

ብሎ ካመነ በግልፅ ሊደራጅ አሊያም

በግልፅ ለመደራጀት የሚያስችል

ነፃና አመቺ ሁኔታ የለም ካለ ደግሞ

ልክ ነው ባለው መንገድ ተደራጅቶ

መብቱን ማስከበር የሰራተኛው

ሀላፊነት ነው፡፡ ሁሉም በቤቱ

ተቀምጦ ቢያጉረመርም በአንድ

ላይ ተደራጅቶ እስካልተነሳ ድረስ

የሚያመጣው ለውጥ አይኖርም!

ሰራተኛው ተደራጅቶ ምን ያድርግ፣

የተባለ እንደሆነ መብቱን ለማስከበር

ሲል የስራ ማቆም አድማ! ያ

ያልተሳካ እንደሆነ እንኳን የስራ

ማለዘብ (ማቀዝቀዝ) ወዘተ ያሉ

የትግል ስልቶችን በመጠቀም ቆራጥ

እርምጃን መውሰድ ይኖርበታል፡፡

የዘመናችን ማርቆስ ሀጎስ ሆይ ተነሳ!

የዘመናችን ዳሮ ነጋሽ ሆይ ተነሺ!!!

ሁልጊዜም ቢሆን ትግል ከፊት ሆነው

የሚመሩ ቆራጦችን ይጠይቃል!

ዛሬም ከልጆቿ በፊት የሰራተኛውን

እና የሰፊውን ህዝብ መብት መከበር

ቅድሚያ የምትሰጥ ጀግና ደፋር

ዳሮ ነጋሽ ታስፈልገናለች፡፡ ዛሬም

ለሰራተኛው መብት መከበር እና

ለሰፊው ህዝብ ጥቅም ሲል ህይወቱን

ሊሰጥ የቆረጠ ጀግና ደፋር ማርቆስ

ሀጎስ ያስፈልገናል፡፡ አንቺ/አንተ

እንዳትሆኚ/ን ምን ይከለክልሻል/

ሃል?
13የካቲት 7 ቀን 2006 ዓ.ም. ቅፅ 1 ቁጥር 2

ነገረ-ኢትዮጵያ

መመረጥ በሌላው ድክመት

ሳይሆን በራስ ጥንካሬ

ታምራት ታረቀኝ

ፓርቲ የሚመሰረተው ለሀገር ይበጃሉ

ተብሎ የታመነባቸው ፖለቲካዊ፣

ኢኮኖሚዊና ማህበራዊ ዓላማዎች

ተቀርጸውና እቅድ ተዘጋጅቶ

የአፈጻጸም ስልትም ተነደፎ ነው፡፡

አንድ ፓርቲ የሚኖሩት ሁለት ዋንኛ

ሰነዶች ፕሮግራምና መተዳደሪያ

ደንብም የሚያሳዩት ይህንኑ

ነው፡፡ ፕሮግራሙ ዓላማውን

መተዳደሪያ ደንቡ የአሰራር ሥልቱን

ያመለክታሉ፡፡ ፓርቲው በፕሮግራሙ

የሰፈረውን ዓላማውን ገቢራዊ

ማድረግ የሚችለው የመንግሥትነት

ሥልጣን ሲያገኝ ነው፡፡ ስለዚህም

ነው የፖለቲካ ፓርቲ ዋንኛ ትግል

የሥልጣን ጥያቄ የሚሆነው፡፡

ለዓላማው ከግብ መድረስ

የሚታገልበትን መንገድ ሠላማዊ

ያደረገ ፓርቲ የሥልጣን ጥያቄውን

ለማሳካት የሚጠቀምበት አንድና

ብቸኛ መንገድ ደግሞ ምርጫ ነው፡

፡ ነጻ ትክክለኛና ወቅታዊ ምርጫ፡

፡ ይህ ዓይነቱ ምርጫ እውን

ሊሆን የሚችለውም ዴሞክራሲያዊ

ሥርዓት በአስተማማኝ መገንባት

ሲቻል፣ አልያም በሥልጣን

ላይ ያለው መንግስት አጠቃላይ

ሁኔታዎችን ተገንዝቦ ራሱን

በመለወጥ ወይንም በውስጥና

በውጪ ተጽእኖ ተንበርክኮ ዓለም

አቀፍ መስፈርቶችን የሚያሟላ

ምርጫ ለማካሄድና ውጤቱንም

በጸጋ ለመቀበል ሲዘጋጅ ነው፡፡

ስለሆነም አንድ ፓርቲ ዓላማውን

ተፈጻሚ ለማድረግ የሚያስፈልገውን

ሥልጣን በትክክልና በአስተማማኝ

ሁኔታ ለመጨበጥ በሀገሪቱ

አስተማማኝ የዴሞክራሲያዊ

ሥርዓት መሰረት እንዲጣል ይህ

ካልሆነም ነጻና ፍትሀዊ ምርጫ

ለማካሄድ የሚያሰችሉ ሁኔታዎች

እንዲሟሉ መታገል ቀዳሚ ተግባሩ

ይሆናል፡፡

በምርጫው ማግሥት ውጤቱ

በአሳዛኝ ሁኔታ ቢበላሽም ቅንጅት

ከዚህ አንጻር በየታሪክ ወቅቶች

የሚነሳ ተግባር አከናውኗል፡፡

ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት አልነበረም፣

ምርጫ ቦርድ አልተለወጠም፣

የፖለቲካ ምህዳሩ ጠቧልና

ከኢህአዴግ ጋር ካላተደራደርን ብሎ

ልመናም ሆነ ምልጃ አላቀረበም፡፡

በአጭር ግዜ እንቅስቃሴ መታመንን

አተረፈና የሠላማዊ ትግሉ ዋንኛ

ኃይል የሆነውን ሕዝብ በአንድ

መንፈስ በቁርጠኝነት ለማሰለፍ

ቻለ፣ እናም ያንን በዚህ ትውልድ

ድጋሜ ስለመታየቱ ማንም ርግጠኛ

ሆኖ ሊናገር የማይችለውን ዓለምን

«….ኢህአዴግ መስተጋብሩን

ጠብቆ በማያቋርጥ ሁኔታ እያሸነፈ

መቀጠል ያለበት ድርጅት ነው፤

መስተጋብሩን ጠብቆ በማያቋርጥ

ሁኔታ የህዝቡን ልብ ይዞ፣ የህዝብ

ልብ የሚያዘው በማያቋርጥ የልማት

እንቅስቃሴ፣ በማያቋርጥ የህዝቡን

ፍላጎት የማርካት እንቅስቃሴ፣

በማያቋረጥ መልካም አስተዳደርን

የመገንባት እንቅስቃሴዎች ነው፣

ከዚህ ውጪ የሚመጣ አይደለም፣

በታሪክ ማሸነፍ አይቻልም፣ ማሸነፍ

የሚቻለው በተጨባጭ ተግባር ብቻ

ነው፣ ምርጫን በታሪክ ማሸነፍ

አይቻልም…» በማለት የተናገሩት

የኢህአዴግ የእለት ተእለት

እንቅስቃሴ ምርጫን መሰረት ያደረገ

መሆኑን ያሳያል፡፡

በአንጻሩ አብዛኛዎቹ ተቀዋሚዎች

ለመመረጥ ኢህአዴግ ሕዛባዊ

ተቀባይነት ስለሌለው ነጻ ምርጫ

ከተካሄደ ሕዝቡ ተቀዋሚዎችን ነው

የሚመርጠው በማለት የራሳቸውን

ጥንካሬ ገንብተውና አስተማማኝ

አማራጭ ሆነው በመቅረብ ሳይሆን

በኢህአዴግ ድክመት እንመረጣለን

ብለው የሚያስቡ በመሆናቸው

ምርጫ የሚታሰባቸው ምርጫ ቦርድ

የግዜ ሰሌዳ ሲያወጣ ነው፡፡ በዛች

አጭር ግዜ በሚደረግ ዝግጅት ወደ

ምርጫ መግባት ደግሞ ውጤት

አያመጣም፡፡ የተሸነፍነው ምርጫው

ተጭበርብሮ ነው ምርጫ ቦርድ

ገለልተኛ ባለመሆኑ ነው በደል

ተፈጽሞብን ነው ወዘተ የሚሉ

ክሶችም ከባዶ ጩኸትነት ሊያልፉ

አይችሉም፡፡ አንደ ፕ/ር መድሀኔ

ታደሰ አባባል ምርጫ ሁለት

ዓመትም ሲቀረው ይጨበረበራልና

ስለ ምርጫ የሚሰራው የቀደመው

ምርጫ በተካሄደ ማግስት ጀምሮ

መሆን አለበት፡፡ ይህ ጉዳይ ሲነሳ

ቅንጅት በስድስት ወር ግዜ አይደለም

ወይ ለማሸነፍ የበቃው የሚል

መከራከሪያ ለማቅረብ የሚዳዳቸው

አሉ፡፡ ይህን የሚሉ ፖለቲከኞች፣

1. ከላይ የጠቀስኳቸው አፈ

ጉባኤ አባዱላ ገመዳ እንዳሉት

ምርጫን በተጨባጭ ተግባር እንጂ

በታሪክ ማሸነፍ ማይቻል መሆኑን፣

2. ቅንጅትን ለአሸናፊነት

ያበቁትን መንገዶች ሁሉ ኢህአዴግ

ከምርጫው ማግስት ጀምሮ

የዘጋቸው መሆኑን፣

3. በቅንጅት ምስረታና

በምርጫ 97 መካከል የነበረው

ግዜ ስድስት ወራት ብቻ ቢሆኑም

ቅንጅትን የመሰረቱት በተለይ

መኢአድና ኢዴፓ በረዥም ግዜ ሰፊ

የምርጫ ስራ የሰሩና በቂ ዝግጅት

ያደረጉ መሆኑን የዘነጉ ናቸው፡፡

በምርጫ ውጤታማ ተወዳዳሪ

ለመሆን የሚያስብ ፓርቲ በቅድሚያ

በራሱ ጥንካሬ ለመመረጥ አልሞ

የእለት ተእለት እንቀስቃሴው

በመራጩ ልብ ውስጥ የሚገባና

መታመንን የሚያስገኝለት እንዲሆን

መስራት አለበት፡፡ ስለሆነም

ሀገራዊና ዓለም ዓቀፋዊ ተጨባጭ

ሁኔታዎችን ከፕሮግራሙ ጋር

በማገናዘብ የአጭርና የረዥም ጊዜ

እቅድ አዘጋጅቶ ለአፈጻጸሙም

ግልጽ የሆነ የአሰራር ስልት ነድፎ

የሚታይና የሚታመን እንቅሰቃሴ

ማድረግ ይኖርበታል፡፡ በቢሮ

ከትሞ፣ ከመግለጫ የዘለለ ተግባር

ሳያሳዩ ከርሞ ሰዉ በኢህአዴግ

አገዛዝ ተሰላችቷል ለውጥ ይፈልጋል

በመሆኑም ተቀዋሚዎችን

ይመርጣል በሚል እሳቤ ብቻ

በምርጫ ሰሞን ብቅ በማለት ወንዝ

በሌለበት ድልድይ አሰራለሁ አይነት

ቅስቀሳ ማካሄድና ከእኔ በላይ ለሀገር

አሳቢ ለህዝብ ሰሪ አይርኖም የሚል

ፕሮፓጋንዳም እንበለው የምርጫ

ቅሰቀሳ ማካሄድ ባዶ ጩኸት ነው

የሚሆነው፡፡

በየደረጃው የሚገኙት የፓርቲው

መሪዎችና አባላት ማንነትና

የተግባር እንዴትነት ብሎም

በዕጩነት የሚያቀርባቸው

ተወዳዳሪዎች ማንነት በምርጫው

ውጤት ለማምጣት ወሳኝ ናቸው፡

፡ እስከ መስዋዕትነት በሚጠይቀው

ሠላማዊ ትግል ውስጥ የትወልድ

ድርሻቸውን ሊያበረክቱ በበጎ

ፈቃደኝነት የተሰለፉ አባላቱ የጠበቀ

የዓላማ ትስሰርና የመንፈስ አንድነት

አንዲሁም መተማመን ሲኖራቸው፣

በመኖሪያ አካባቢያቸውም ሆነ

በሥራ ቦታቸው በሥነ ምግባራቸው

የተከበሩ በስራቸውም የተወደዱ

ሲሆኑ የመራጩን ሕዝብ ቀልብ

በመሳብ ፓርውን ለውጤት

ያበቁታል፡፡ ይህ ሳይሆን ተቀዋሚ

በመሆን ብቻ እንመረጣለን ብሎ

ማሰብ ምርቻን በታሪክ ማሸነፍ

እንደማይቻል ያለመገንዘብ ነውና

ምርጫ 2007 እንደ ምርጫ 2007

እንዳይሆን ያሰጋል፡፡

ፓርቲዎች በየግል ተጠናክረው

በጋራ ተማምነው በስፋት መክረውን

በረዥሙ አቅደው ሳይሆን ተባብረን

ከታየን ሕዝቡ ይመርጠናል በሚል

ብቻ በምርጫ ሰሞን የሚካሄድ

የመተባበር ሆይ ሆይታም ጥንካሬ

ፈጥሮ አስተማማኝ አማራጭ

ሆኖ ከመቅረብ የሚነሳ ባለመሆኑ

ለውጤት አያበቃም፡፡ እንደምንም

ተደጋግፈን ከፊት ለፊታችን ያለውን

ግዙፍ ተራራ መናድ የሚለው

የኋላ መሰረት የዛሬ ጥንካሬ የፊት

ራዕይ የሌለው ሥልጣንን ብቻ

አስቦ የሚነሳ መደጋገፍ ፈጥረው

ለምርጫ ቢቀርቡም የሚፈጥሩት

መጎነታተል(በቅንጅትም

በመድረክም የታየ ነው) ደካማ

አቅማቸውን ይበልጥ ያዳክመውና

ለኢህአዴግ አሸናፊነት ምቹ ሁኔታ

ይፈጥሩለታል፡፡

ዛሬ ትናንት አይደለም ነገሮች ተለዋውጠዋል፣ ጠንክሮ በመገኘት

እንጂ በሌላው ድክመት ለመመረጥ ማለም ግዜ አልፎበታል፡

፡ ኢህአዴግን ደካማ አድርጎ ማሰብም በራሱ ትልቅ ድክመት

ይመስለኛል፡፡ በደቂቃ ውስጥ መረጃ ለሚሊዮኖች በሚደርስበት

ዘመን በተግባር ሆኖ ሳይሆን በፕሮፓጋንዳ መስሎ በመቅረብ

ለውጤት መብቃት የሚቻል አይደለም፡፡

በየግላቸው ድርጅታዊ ብቃት

ሳይፈጥሩ በጋራም በቅጡ

መክረው የጋራ እቅድ ሳይነድፉና

ሆነው ሳይሆን መስለው ለምርጫ

በመቅረብ በጥረታቸው ሳይሆን

በሕዝቡ ለውጥ ፈላጊነትና ታሪክ

ሰሪነት ለአሸናፊነት ቢበቁ ውጤቱን

አሰጠብቀው በስምምነት የሥልጣን

ክፍፍል አድርገው በምርጫ ያገኙትን

ውጤት ወደ ተግባር በመለወጥ

ሕዝቡ በድምጹ የሰጣቸውን ኃላፊነት

መወጣት መቻላቸው ያጠራጥራል፡

፡ ምክንያቱም ወደ ምርጫ የገቡት

ጥንካሬ ፈጥረው የህዝብን አመኔታ

አትርፈው ሳይሆን በመተባበር ሽፋን

በመሆኑ ነው፡፡

አንድነቱ የጠነከረ፣ በሚያራምደው

ዓላማ በእኩል ደረጃ እምነት

ያለው፣ በፓርቲ ዲስፕሊንና በንጹህ

ሰብአዊ ፍቅር የተሳሰረ፣ እሰከ

መስዋእትነት አብሮ ለመዝለቅ

የተማመነ ከአባለቱም ሆነ ከመራጩ

ሕዝብ አመኔታን ያተረፈ አመራር

እንዲሁም በዓላማው የጸና ሞራሉ

የተገነባና በመንፈስ የጠነከረ አባል

መኖር ለአንድ ፓርቲ ዓላማ

መሳካትም ሆነ ተባብሮ በምርጫ

ለመሰለፍ በእጅጉ ወሳኝ ናቸው፡

፡ ይህ በምርጫ ለማሸነፍ ወሳኝ

የሆነ የፓርቲ ጥንካሬ ማሳያ በአንድ

ሰሞን የሚገነባ አለመሆኑ ምርጫን

የረዥም ግዜ ስራ ከሚያደርጉት

ምክንያቶች አንዱ ይሆናል፡፡

በተለይ የፓርቲው አመራር በአደባባይ

ስለ ፍቅር እየሰበከ በፓርቲው

ውስጥ ጥላቻን የሚያነግስ ከሆነ፣

ስለ አንድነት እያዜመ ተለያይቶ

የሚቆም ከሆነ፣ ሥልጣን ላይ ካለው

ፓርቲ ጋር መነጋገር እሻለሁ እያለ

በሀሳብ ከሚለዩ የአመራር አባላትም

ሆነ ጥያቄ ከሚያነሱ አባላት ጋር

ለመነጋገር የማይደፍር ከሆነ፣

ዘመናት ላስቆጠረው የሀገራችን

ችግር ዋናው መፍትሄ ብሔራዊ

እርቅ ነው ብሎ በፕሮግራሙ አስፍሮ

ይህንኑ በአደባባይ እየተናገረና

ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር

የሚያስችል ጉባኤ አሰፈላጊነትን

እየጠየቀ፣ በፓርቲው ውስጥ

የሚፈጠሩ ጥቃቅን ልዩነቶችን

በውይይት መፍታትና በእርቅ

ማድረቅ የማይችል ከሆነ ወ.ዘ.ተ

እንኳን በመራጩ ሕዝብ ዘንድ

በአባላቱም መታመንና መከበርን

ሊያተርፍ አይችልም፡፡ አመራሩ

ካልታመነ ደግሞ ፓርቲው ሊታመን

አይችልም፡፡ የማይታመን ደግሞ

አይመረጥም፡፡

ዛሬ ትናንት አይደለም ነገሮች

ተለዋውጠዋል፣ ጠንክሮ በመገኘት

እንጂ በሌላው ድክመት ለመመረጥ

ማለም ግዜ አልፎበታል፡፡

ኢህአዴግን ደካማ አድርጎ ማሰብም

በራሱ ትልቅ ድክመት ይመስለኛል፡

፡ በደቂቃ ውስጥ መረጃ ለሚሊዮኖች

በሚደርስበት ዘመን በተግባር ሆኖ

ሳይሆን በፕሮፓጋንዳ መስሎ

በመቅረብ ለውጤት መብቃት

የሚቻል አይደለም፡፡

ፖለቲከኞቹ ከደረሰባቸውም

ካደረሱትም መማር ባይችሉም

ሕዝቡ ከሁሉም አቅጣጫ ከደረሰበትና

ከሚደርስበት ችግር፣ በየጊዜውም

ከሚያይና ከሚሰማው እንዲሁም

21 ዓመታት ለውጥ ካላመጣውና

መስዋዕትነቱ ግን ካልተቋረጠው

ትግል ብዙ ተምሯል፡፡ ተፎካካሪ

ፓርቲዎች ትግላቸው ለውጤት

ባያበቃውም ዳፋቸው እያዳፋው ብዙ

መከራ አይቷል፣ ስለሆነም ምንም

ማድረግ ባይችል በሚታወቅበት

ዝምታው ይሸኛል፡፡

በመሆኑም ሕዝብን የሠላማዊ

ትግሉ ተሳታፊ ብቻ ሳይሆን

ባለቤት ለማድረግና በምርጫ 2007

ለውጥ ለማምጣት ራስን አጥርቶና

ወደ ገፅ 15 ይዞራል
ነገረ-ኢትዮጵያ

ሰማያዊ

ቅፅ 1 ቁጥር 2

የካቲት 7 ቀን 2006 ዓ.ም.

ይህ ገጽ በሰማያዊ ፓርቲ አዘጋጅነት የሚቀርብ ሲሆን፣ ፓርቲው ፕሮግራሙንና

አላማውን ለአባላትና ደጋፊዎቹ የሚያደርስበት ነው፡፡

14

መንደርደሪያ

ሰማያዊ ፓርቲ በዘር፣ በሃይማኖት በቋንቋ በፆታና በሌሎች

ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መመዘኛዎች በዜጎች መካከል

ልዩነት ሳያደርግ በማደራጀት የኢትዮጵያን ህዝቡ የሥልጣን

ባለቤትነት ለማረጋገጥ ይታገላል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ለምን

ተመሰረተ?

ሀገራችን ኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ አኩሪ ታሪክ፣ ቀደምት

የሥልጣኔ ባለቤትና ከ3000 ዘመን በላይ የመንግስትነት

ታሪክ ያላት ታላቅ ሀገር ናት፡፡ የሰው ልጅ ዛሬ ለደረሰበት

የዕድገትና የስልጣኔ ደረጃ መሰረት የሆኑ ቁሳዊና መንፈሳዊ

ትውፊቶችን በማበርከት ለዓለም ስልጣኔ ታላቅ አስተዋፅዖ

አበርክታለች፡፡ በየዘመናቱ ነፃነቷን ለማጥፋት የወረሯትን

የውጭ ተስፋፊዎችና ቅኝ ገዥዎች በተደጋጋሚ ጊዜ ድል

በማድረግ ነፃነቷንና ሉዓላዊነቷንም አስከብራ ኖራለች፡

፡ ሀገራችንን በእብሪት ለመውረር የመጣውን የኢጣሊያን

ወራሪ በመደምሰስ በዓለም ለመጀመሪ ጊዜ ጥቁር የሰው ልጅ

ዘር ነጭ ወራሪዎችን ማሸነፍ እንደሚችል በአድዋ ታሪካዊ

ድል ያስመሰከረች ብቸኛ የጥቁር ሰው ዘር መኩሪያና

መመኪያ ሃገር ነች፡፡

ቅኝ ገዥዎችና ኢምፔሪያሊስቶች አፍሪካን ለመቀራመትና

የተፈጥሮ ሃብቷን ለመዝረፍ ያደረጉትን ስምምነት ተከትሎ

አፍሪካን በቅኝ ግዛት ስር ለማዋል በተደረገው ወረራ

ተስፋፊዎችን በመመከት በቅኝ ገዥዎች ሥር ያልወደቀችና

ለመላዉ ጥቁር ሕዝብ የነፃነት ተምሳሌት ሐገር ነች፡፡

አብዛኛዎቹ አፍሪካዊ ሀገሮች ድንበሮቻቸውና ማንነታቸው

በቅኝ ገዥዎች ፍላጎት እንዲወሰን ሲደረግ ሀገራችን

ወራሪዎችን በመቋቋም የራሷን የድንበር ወሰንና ማንነት

በራሷ መወሰን የቻለች ብቸኛዋ አፍሪካዊ ሀገር ናት፡፡

ሀገራችን የበርካታ ገፀ ምድርና ከርሰ ምድር ኃብት፣ አስደናቂ

የተፈጥሮ ውበትና የሰው ልጅ ቀደምት ስልጣኔ መገለጫ

የሆኑ ቅርሶች ባለቤት፣ ሰፊ መሬትና የሰው ኃይል ያሏት

ታላቅ ሐገር ናት፡፡ ሀገራችን የተለያዩ የአየር ፀባያት ባለቤት

ስትሆን ለሰው ልጅ መኖሪያና ለአዝርዕት መብቀያ ተስማሚ

ተፈጥሮ በሰፊው የተለገሳት ሀገር ናት፡፡ በርካታ በጥቅም

ላይ የዋሉና ገና ያልተነኩ የተፈጥሮ ስጦታየፈሰሰባትም

ምድር ናት፡፡

ሆኖም የዚህ አኩሪ ታሪክ፤ ባህልና የተፈጥሮ ሃብት

ባለቤት የሆነች ሃገራችን ዛሬ በቀሪው የዓለም ሕዝብ ፊት

የምትታወቀው በርሃብተኝነት፣ በተመፅዋችነት፣ በስደትና

በእርስ በእርስ ጦርነት ባለቤትነቷ ነው፡፡ የሰው ልጅ ዛሬ

ከረደሰበት የአስተዳደርና የኢኮኖሚ እድገት ደረጃ እንዳንደርስ

ያደረገን በሃገራችን ተንሰራፈተው በቆዩና አሁንም ባሉ

የአስተዳደርና የፖለቲካ ሥርዓት ብልሹነቶች ምክንያት

ነው ብለን እናምናለን፡፡ ዛሬ ኢትዮጵያ በፖለቲካ እድገት

ብቻ ሳይሆን በኢኮኖሚና በማህበራዊ እድገትም የዓለም

ሃገራት የመጨረሻዎቹ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ ሕዝቧ የዘር፣

የሃይማኖት፣ የቋንቋና የባህል ልዩነቶችን ተቀብሎ ለበርካታ

ዘምናት ተቻችሎ የኖረ ቢሆንም ዛሬ እርስ በእርስ በጥርጣሬ

እንዲተያይና አንድነቱ እንዲላላ እየተደረገ ነው፡፡ ሃገራችን

በተቀበለቻቸውና ባፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ህጎች እንዲሁም

በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት እውቅና ያገኙ ሰብአዊና

ዲሞክራሲያዊ መብቶች የሚያከብራቸውና የሚጠብቃቸው

ባለቤት አጥተዋል፡፡ የኢኮኖሚ መርሃችንም በጥናትና

በአስተማማኝ መሠረት ላይ ያልተጣለ በመሆኑ ካለንበት

የድሕነት አዘቅት ሊያወጣን አልቻለም፡፡ ፍትኃዊ የንብረት

ስርጭትና የሥራ እድል ባለመኖሩ በኢትዮጵያውያን መካከል

ያለው የኑሮ ደረጃ እጅግ እየተራራቀ መጥቷል፡፡ ዜጎችም

የዜግነት እኩልነት ክብራችን ተነፍገን አብዛኛዎቻችን

በሃገራችን ጉዳይ ባይተዋር ሆነናል፡፡

ዛሬ የዚህ ትውልድ አካል የሆንን ዜጎች ይህንን የተዛባ

አካሄድ የመቀየርና ሃገራችንን የተሻለች ሃገር የማድረግ

ኃላፊነት አለብን ብለን እናምናለን፡፡ በመሆኑም የሰማያዊ

ፓርቲያችን ራዕይ፣ ተልዕኮና ዓላማ ለሃገራችን ካለን ጥልቅ

ፍቅር፣ለፍትሃዊ አስተዳደር መስፈን ካለን ፅኑዕ እምነትና

ከሰው ልጅ ምክንታዊ አስተሳሰብ ይመነጫሉ፡፡ ፍትሕ

እንዲሰፍን የምንፈልግ ሃገራችንንም በእውነት የምንወድ

ከሆነና በሰው ልጅ ምክንያታዊ አስተሳሰብ የምንገዛ ከሆነ

ችግሮቻችን በሰላማዊ መንገድ፣ በመነጋገር፣ በመደማመጥና

በመግባባት ብሔራዊ እርቅና መከባበርን በመፍጠር የሚፈቱ

ናቸው ብለን እናምናለን፡፡

ፓርቲያችን በሃገሪቱ ህገ-መንግስት መሠረት በሰላማዊ

መንገድ የፖለቲካ ትግል በማድረግ የኢትዮጵያ ሕዝብ

ከውስብስብና ፈርጀ ብዙ ችግሮች ተላቆ እያንዳንዱ ዜጋ

በነፃነት ሃሳቡን የመግለፅ፣ የመደራጀት፣ የፈለገውን

የመደገፍና የመቃወም፣ በፈለገው ሙያና የሥራ መስክ

የመሰማራት፣ ሃብት የማፍራትና የሃብቱ ባለቤት የመሆን

እንዲሁም የግል ስብዕናውን የማሳደግ መብቱ የተረጋገጠ

እንዲሆን እንታገላለን፡፡ ሐገራችን ከድህነትና ከጦርነት

የተላቀቀች፣ ፍትሕና ሰላም የሰፈነባት እንድትሆን የፖለቲካ

ሥልጣን በመያዝ የዜግነት ድርሻችንን ለመወጣትና

ራዕያችንን እውን ለማድረግ ሰማያዊ ፓርቲያችንን

መስርተናል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ራዕዩን እውን ለማድረግ፤

ሀ. ፓርቲያችን የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መርሆችን

ይከተላል፡፡

ለ. በሰማያዊ ፓርቲ ፕሮግራም ውስጥ ለተካተቱ

አንዳንድ ጉዳዮች ተፈፃሚነት የሕገ-መንግሥቱ አንዳንድ

ድንጋጌዎችን ህገ-መንግስቱ ባስቀመጠው የህገ-መንግስት

ማሻሻያ መርሆች መሰረት ማሻሻል አስፈላጊ መሆኑን ታሳቢ

ተደርጓል፡፡

መ. ዓላም ዛሬ ከደረሰችበት የሥልጣኔ ደረጃና ከሰው

ልጅ ምክንያታዊ አስተሳሰብ በመነሳት ከሰላማዊ ትግል

ውጭ በሃገራችን የተረጋጋ የፖለቲካ ሥርዓትን መገንባት

አይቻልም ብለን እናምናለን፡፡ ስለዚህ ፓርቲያችን በሰላማዊ

የትግል ስልት የፖለቲካ ሥልጣን ለመያዝ ይታገላል፡፡

የፖርቲው ስያሜና ትርጓሜ፤

የፓርቲው ስያሜ “ሰማያዊ ፓርቲ” በአህፅዕሮት “ሰማያዊ”

በእንግሊዝኛው አጠራር “BLUE PARTY” ሲሆን

ትርጓሜውም ሰማያዊ ቀለም የሰላም፣ የተስፋና የአንድነት

መገለጫ በመሆኑና ፓርቲያቸንም ሰላም ተስፋና አንድነት

በሃገራችን እንዲሰፍን ያለውን የፀና እምነት መግለፅ ነው፡፡

የፓርቲው ዓርማ፡-

ከመሃል በጠባብ ክብ የሚጀምርና ሌሎች እየሰፉ

የሚሄዱ ክቦቹ ሲኖሩት በደማቅ ሰማያዊና ውሃ ሰማያዊ

ቀለሞች በመፈራረቅ የሚቀባ በጨርቅ ወይም በሌላ ቁስ

ላይ የሚያርፍ ምልክት ይሆናል፡፡ የዓርማው ቀለማት

የፓርቲያችንን ስያሜና ትርጉም የሚያሳዩ ሲሆን ከትንሽ

ጀምሮ እየሰፉ የሚሄዱት ክብ ምልክቶች ደግሞ ጥቂት

ሆነን ጀምረን እየበዛን እንደምንሄድ ለማሳየት ነው፡፡

የፓርቲው ሀገራዊ ዕይታ

ሀ. ኢትዮጵያ ሀገራችን በኢትዮጵያ ህዝብ ሙሉ

ገዥነት ስር የሚገኘውን መሬት፣ ውሃ፣ የአየር ክልል፣

በከርሰ ምድርና በከርሰ ውኃ የሚገኘው ሃብት፣ በአየር

ክልሉ ያለው የድምፅና የምስል ሞገድ ባለቤት ሉዓላዊ ሀገር

ናት፡፡

ለ. የኢትዮጵያ ያልተመለሱ የድንበርና የይገባኛል

ጥያቄዎች መኖራቸው እንደተጠበቀ ሆኖ የኢትዮጵያ

ሉዓላዊ የአስተዳደር ወሰን አሁን በኢትዮጵያ መንግስት ሥር

የሚገኘውና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተመዘገበዉ

ክልል ነው፡፡

ሐ. በኢትዮጵያ ውስጥና በውጭ ሃገራት የሚኖሩ

ኢትዮጵያውያን በአንድነት የኢትዮጵያ ሕዝብ ናቸው፡፡

መ. የኢትዮጵያ ሕዝብም በኢትዮጵያ ጉዳይ ባለሙሉ

የሥልጣን ባለቤት ነው፡፡ ሃገሪቱን የማስተዳደር ሥልጣን

ከሕዝብ ይመነጫል፡፡

ሠ. የኢትዮጵያ አንድነትም ሆነ ሉዓላዊነት

አይነጣጠሉም፤ለሌላም አይለቀቁም፡፡

ረ. ኢትዮጵያውያን በግል ያላቸው የዜግነት መብትም

ሆነ በወል የሚጋሩት የህግ፣ የፖለቲካ የማህበራዊና

የባህል መብት የአንድነታቸው ዓይነተኛ መሰረት ነው፡፡

ሰ. ኢትዮጵያ ሀገራችን የረጅም ጊዜ አኩሪ ታሪክ፣

የበርካታ ገፀ-ምድርና ከርሰ-ምድር ሃብት ባለቤት፣ አስደናቂ

የተፈጥሮ ውበትና የሰው ልጅ ቀደምት ሥልጣኔ መገለጫ

የሆኑ ቅርሶች ያሏት ታላቅ ሃገር ናት፡፡

ሸ. ሃገራችን ኢትዮጵያ በተለያዩ ባህል፣ ሃይማኖት፣

ቋንቋ፣ ወግና ሥርዓት አሸብርቃ የኖረች፣ በብዙ ዓይነት

ሃረጎች ተሳስረውና በታሪክ ተቆራኝተው የጋራ አመለካከትና

ኢትዮጵያዊ ማንነትን በማዳበር ለዘመናት ተቻችለውና

ተከባብረው በአንድነት የኖሩ ዜጎች ሃገር ናት፡፡ እነዚህ

ዜጎች በየዘመናቱ የተለያዩ አስተዳደራዊ በደልና ጭቆና

ደርሶባቸዋል፡፡ ዛሬም ቢሆን የዜጎች የአስተዳደርና

የፍትህ ጥያቄ በአግባቡ አልተፈታም ወይም መብታቸው

አልተከበረም፡፡ በመሆኑም ሁሉም ዜጎች የዜግነት

መብታቸው እንዲከበርና በሃገር ጉዳይ ላይ ተገቢው ድርሻና

ተሳትፎ እንዲኖራቸው አሁንም ፅኑዕ ትግል የሚያስፈልጋት

ሃገር ናት፡፡

ራዕይ

የዜጎች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ሙሉ በሙሉ

የተከበሩባት፤ ለሕዝብ ፍላጎት መሟላት በኃላፊነትና

በተጠያቂነት መንፈስ የሚሰራ መልካም አስተዳደርና የህግ

የበላይነት የተረጋገጠባት፤ የኢኮኖሚና ማሕበራዊ ብልፅግና

የሰፈነባት፤ ለዜጎቿ ሁሉ አለኝታና መኩሪያ የሆነች፤ለዓለም

ሕዝብ መልካም ግንኙነት የበኩሏን አስተዋፅዖ የምታደርግ

ኢትዮጵያን ማየት ነው፡፡

ዓላማ

ሀ. የዜጎች ዲሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶች

እንዲከበሩና ተፈፃሚም ኢንዲሆኑ በጽናት መቆም፡፡

ለ. ለዜጎች አስተማማኝ የማሕበራዊ ደህንነት

ዋስትና አገልግሎት ማቅረብ፡፡

ሐ. የፖለቲካ ፓርቲዎችና ግለሰቦች ነፃ፣ ፍትሃዊና

ትክክለኛ በሆነ መንገድ ተወዳድረው የፖለቲካ ሥልጣን

የሚይዙበት የምርጫ ሥርዓት መመስረት፡፡

መ. ራዕዩን ተግባራዊ ለማድረግ በነፃና ፍትኃዊ

ምርጫ በህዝብ ድምፅ የፖለቲካ ሥልጣንመያዝ

ሠ. ሀቀኛ፣ ብቃትና ተጠያቂነት ባለው አመራር

አማካኝነት ታታሪና የፈጠራ ችሎታ ያላቸው ዜጎች

መፍጠር፡፡

ረ. የሕብረተሰቡን የፖለቲካ ግንዛቤ በማሳደግ ዜጎች

በሃገራቸው ጉዳይ በንቃት እንዲሳተፉ፣ ግዴታቸውንና

ኃላፊነታቸውንም እንዲወጡ ማድረግ፡፡

ሰ. የእያንዳንዱን ዜጋ ችሎታ በማሳደግ በሃገርና

በዓለም ደረጃ ብቁ ተወዳዳሪ ለመሆን ያለውን ምኞት

ማሳካት፡፡

ሸ. ከሀገራቸው ውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሰብዓዊና

ቁሳዊ አቅማቸውን ለሃገራቸው ልማት እንዲያውሉና

ለሕዝብም ቁሳዊና መንፈሳዊ ሕይወት መሻሻል የበኩላቸውን

አስተዋፅዖ ማበርከት የሚችሉበት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና

የማሕበራዊ ሥርዓት መመስረት፡፡

ቀ. ዓለምን ለመረዳትም ሆነ የዓለም ሕብረተሰብ

በአግባቡ እንዲረዳው ማድረግ የሚችልና በነፃነት የሚያስብ

ሕብረተሰብ መመስረት፡፡

በ. የኢትዮጵያ ወጣት ትውልድ በራሱና በወረሰው

መልካም ነገር እንዲኮራና በሕይወቱ ውስጥ ተስፋ

እንዲኖረውና ለከፍተኛ ግብ እንዲሰራ ማደፋፈር፡፡

ተልዕኮ

ተልዕኮአችን ዓላማችንን ማሳካት ሆኖ በተለይ በሀገራችን

ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲሰፍንና የሕግ የበላይነት

እንዲረጋገጥ ዋስትና የሚሰጥ ከሕዝብ፣ በሕዝብ፣ ለሕዝብ

የቆመ መንግስት በሰላማዊ መንገድ መመስረት ነው፡፡

ርዕዮተ ዓለም

እጅግ ውድ የሆነው የሰው ልጅ ሃብት ነፃነቱ በመሆኑ

ሰማያዊ ፓርቲ ለግለሰብ ነፃነት ቅድሚያ ይሰጣል፡፡ ዜጎች

በቡድን ሊያከናዉኗቸው የሚፈልጓቸው እንደ ሃይማኖት፣

ልማዶች፣ ቋንቋ፣ ማህበሮች እና የመሳሰሉት የጋራ

መብቶች የግለሰብን በነፃነት የመወሰን መብት ሳይሸረሽሩ

እንዲከበሩ የህግ ጥበቃ እንደሚያስፈልጋቸው ያምናል፡፡

በመሆኑም ሰማያዊ ፓርቲ በለዘብተኛ ሊብራል ዲሞክራሲ

መሰረታዊ መርሆች ይመራል፡፡

ትኩረት

ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮጵያ ውስጥ 51% ያህል ቁጥር

ያላቸውን ሴቶች ወደ ፖለቲካው መድረክ እንዲመጡ

ቅድሚያ በመስጠት ይሠራል፡፡ በተጨማሪም እድሜው ከ35

ዓመት በታች የሆነውና 70% የሚሆነውን የኢትዮጵያን

ህዝብ ቁጥር የያዘው ወጣቱ ትውልድ የኢትዮጵያን ፖለቲካ

ወደፊት ለማራመድ ከፍተኛ አሰተዋፅኦ አለው ብሎ

ፓርቲያችን ያምናል፡፡ ከፍተኛ ተኩረትም ለወጣቱ ትውልድ

ይሰጣል፡፡ ይህንንም በተግባር ለማሣየት የፓርቲው

አብዛኛው አማራሮች የዚህ ትውልድ አካል ናቸው ፡፡

ዋና ዋና እንቅስቃሴዎች

1. ሰማያዊ ፓርቲ በምርጫ ቦርድ የተነፈገውን

የምስክር ወረቀት በህግና በትግሉ ከቦርዱ ወረቀት በፊት

ራሱን ህጋዊ አካል አድርጓል

2. ፓርቲው ራሱን ከህዝብና ከደጋፊዎቹ

ለማስተዋወቅ በርካታ የውይይት መርሃ ግብሮችን አካሂዷል፡

3. ለፓርቲው ድጋፍ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ያዘጋጀው

የራት ግብዣ ፕሮግራም በመንግስት ካድሬዎች ጫና

ተስተጓጉሏል፡፡

4. “ውይይትና መነጋገርን እንለማመድ” በሚል

ርዕስ “መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ” በተሰኘው የፕ/ሮ

መስፍን ወልደማርም መፅሀፍ ላይ ውይይት እንዲደረግ

በብሔራዊ ቲአትር ባዘጋጀው ዝግጅት ከሁለት ሺህ በላይ

ተገኝቶ እንዲወያይ እድል ፈጥሯል፡፡

5. ለፋሽስቱ ግራዚኒ ሐውልትና የመታሰቢያ

መናፈሻ ቦታ እንዲሰራለት መደረጉን በመቃወም ሰላማዊ

ሰልፍ በማድረጉ አባላቱን አመራሮቹ ወደ አስር ቤት

እንዲወረወሩ ተደርገዋል፡፡

6. በሚናገሩት ቋንቋ መለየት ምክንያት በቤኔሻንጉል

ለዘመናት ከኖሩበት የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን እቦታቸው

ድረስ በመሔድ ጎብኝቷል፤ አወያይቷል፡፡

7. በሐገራችን የሰፈነውን አምባገነንት፣ የሰብዓዊና

ዲሞክራሲያዊ መብት ጥሰት፣ የዜጎችን መፈናቀልና

የመንግስትን በሐይማኖት ጣልቃ መግባት በመቃወም

ለስምንት አመታት የተነፈገውን የሰላማዊ ሰልፍ መብት

በመመለስ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ አድርጓል፡፡

ለበለጠ መረጃ የፓርቲያችንን ድ-ገፅ www.Semayawiparty.org

ይጎብኙ፡፡ ወይም Facebook BluePartyEthiopia

ላይክ ፔጅ semayawiparty ይከታተሉ፡፡

አድራሻ፡- ሰማያዊ ፓርቲ

ቁጥር፡ C/A619

ፖ.ሳ. ቁ 180298

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ስልክ +251116514240

አቢሲኒያ ባንክ ተንቀሳቃሽ ሂሳብ
15የካቲት 7 ቀን 2006 ዓ.ም. ቅፅ 1 ቁጥር 2

ነገረ-ኢትዮጵያ

እንደሀገር መግባባት ...

ከ ገፅ 11 የዞረ

የጸጥታ ሀይሉ ከህዝብ ተነጥሎ የኢህአዴግ

የግል ንብረት እስኪመስል ድረስ ተለያይቷል፡

ሌላው ደግሞ የፍትህ ተቋማት የምንላቸው

ድርጅቶቻችን ናቸው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ

በሀገራችን የታዩ የፍርድ ሂደቶች የተመሩት

በነጻ የዳኝነት ሂደት ሳይሆን በአለቃዎቻቸው

በጎ ፈቃድ መሆኑ ጸሐይ የሞቀው ሀቅ ነው፡

፡ ይህን መከራከሪያችን የሚያጠናክርልን

የ1997 የቅንጅት አመራሮችና አባላት ላይ

የተበየነው የእስር ፍርድ ነው፡፡ ጠቅላይ

ሚንስትር መለስ ዜናዊ በፓርላማ ቀርበው

እስከሞት ፍርድ ሊያስቀጣ የሚችል ወንጀል

አግኝተንባቸዋል ብለው ተናግረው ነበር፡

፡ ይህንን ተከትሎ ፍርድ ቤት መመላለሱ

የሰለቻት ዳኛ ብርቱካን ሚዴቅሳ እንዲህ ስትል

ተናግራ ነበር፡፡ “ለምን ታመላልሱናላችሁ፤

መለስ ዜናዊ የሞት ፍርድ ፈርዶብን አይደል

እንዴ!? ወስዳችሁ ግደሉን እንጂ፡፡” በቅርብ

እነ እስክንድር ነጋን ጨምሮ በአንዱዓለም

አራጌ፣ በሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ

ኮሚቴወች ላይ የተወሰደው የጥፋተኝነት

ውሳኔም ከቀድሞው የተለየ አይደለም፡

፡ በዚህም ምክንያት በሀገራችን የፍትህ

ተቋማት ላይ መግባባት ሆድና ጀርባ ሆኗል፡፡

ማሳያ ሰባት፡- ዘውግ ተኮር ፌደራሊዝም

የህገ መንግስቱ አንቀጽ 39 እንዲህ ይላል፤

‹‹የራስን እድል በራስ መወሰን እስከ

መገንጠል››፡፡ በዚህ አንቀጽ መሰረት ክልሎች

እራሳቸውን በራሳቸው ያስተዳድራሉ፤

ከፈለጉም መገንጠል መብታቸው ነው፡

፡ በግሌ ‹እስከ መገንጠል› ብሎ መብት

ምን እንደሆነ ባይገባኝም የፌደራል ስርዓት

መኖሩን ግን አጥብቄ እፈልገዋለሁ፡፡ ‹እስከ

መገንጠል› የሚለው ሀረግ መግባቱ ግን

ላለመግባባታችን አንዱ ማሳያ ነው፡፡

ማሳያ ስምንት፡- ምርጫና የምርጫ ቦርድ

ለአንድ ሀገር በዴሞክራሲ መበልጸግ

የምርጫ ቦርድ ገለልተኛነት ወሳኝ ሚና

አለው፡፡ የምርጫ ቦርድ ሃላፊነቱን በአግባቡ

ከተወጣ አጭበርባሪዎችና ኮረጆ ገልባጮች

ቦታ የላቸውም፡፡ ይህን አሰራር በሀገራችን

ለማስፈን ጅምሩ እንኳን የለም ለማለት

ያስደፍራል፡፡ የምርጫ ቦርድ አመራሮችም

ሹመታቸው በቀጥታ ከመንግስት መሆኑ

ለገዥው ተባባሪነታቸው መንገድ ከፋች ነው፡

፡ ምርጫ ቦርድ የገዥውን ፓርቲ የሙቀት

ልክ እየለካ የሚሰራ መሆኑ የታየ እውነት

ነው፡፡ በዚህ የተባባሪነት አመሉ ገዥው

ኮረጆ ሲገለብጥ ምርጫ ቦርድ የምርጫ

ውጤት ተቀበሉ በሚል ተቃዋሚዎችን

ያባብላል፤ ካልተሳካት ደግሞ ያስፈራራል፡፡

ስለሆነም ምርጫ ቦርድ ሌላኛው እንደ ሀገር

ያለመግባባታችን ምክንያት ሆኖ ሊጠቀስ

ይችላል፡፡

በአጠቃላይ ሀገሬ ኢትዮጵያ የዚህ ክፍለ

ዘመን ዳግማዊ ባቢሎን እየሆነች ነው፡

፡ ይህን በቋፍ ላይ ያለ አለመግባባት በጊዜ

ካልፈታን እጣ ፋንታችን እንደ ባቢሎን ህንጻ

መፈራረስ ከመሆን አያልፍም፡፡ አምላክ

አያድርገው እላለሁ!

እውነትና ህዝብ ያሸንፋል! ኢትዮጵያ

ለዘላለም በክብር ትኑር!!!

ኢህአዴግ ተሸንፏል...

ከ ገፅ 16 የዞረ

እንደተለመደው ወዲያውኑ ኢንተርኔትና

ስልክ እንዲጠፋ ተደረገ፡፡

አሁን ሰላማዊ ሰልፉ እየተቃረበ እንደመሆኑ

የከተማውን አስተዳደር ይበልጡን ፈርቷል፡

፡ ሰልፉ እንደማይቀር ከሰማያዊ ወጣቶች

ድፍረትና ቆራጥነት ተረድተዋል፡፡

በመሆኑም የከተማውን ነዋሪ በመሰብሰብ

ማስፈራራት ነበረባቸው፡፡ ለዚህም ሰማያዊ

ፓርቲን ስም እየለጠፉ ህዝቡን ለማራቅ

ከመሞከር ባለፈ ‹‹ልጆቻችን ሰላማዊ ሰልፉ

ላይ ቢሳተፉ በጥይት ይመታሉ!›› ብለው

እስከማስፈራራት ደርሰዋል፡፡ የተሸናፊዎቹ

አቅም ይህ ነው፡፡ ሰላማዊ ሰልፉ ሊደረግ

10 ደቂቃ ሲቀረው ደግሞ በየ መግቢያው

የተደረደሩት ፖሊሶች ህዝብን ወደ መስቀል

አደባባይ እንዳይሄድ ሲያግዱ ተስተውለዋል፡

፡ በሰላማዊ ሰልፉ ወቅትም የቀበሌ ካድሬዎች

ከሰልፉ በኋላ በመሆን ህዝቡን በመቅረጽ

ለማስፈራራት ሞክረዋል፡፡ በእርግጥ ከዚህ

አልፈው ሰላማዊ ሰልፉ ከተጠናቀቀ በኋላ

እርምጃ እየወሰዱ መሆናቸውም ተሰምቷል፡

፡ ሰላማዊ ሰልፉ ካበቃ በኋላ በቅርብ

እርቀት ሲከታተሉ የነበሩት ካድሬዎች

በሰልፉ ላይ የተሳተፉትን ወጣቶች የቀበሌ

መታወቂያ ቀምተዋል፡፡ ወደ ቀበሌ ሄደው

መታወቂያቸውን በተቀበሉበት ወቅትም

ዳግመኛ ሰማያዊም ሆነ ሌሎች ፓርቲዎች

በሚጠሩት ሰልፍ እንዳይሳተፉ ማስጠንቀቂያ

ተሰጥቷቸዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ሰልፉን

ያስተባበሩት የጎንደር የፓርቲው አባላትና

ቤተሰቦቻቸው ላይ ደህንነቶች እየደወሉ

ሲያስፈራሩዋቸው ሰንብተዋል፡፡

ሰላማዊ ሰልፉ ተደርጎም ቢሆን ማዋከቡ እንደማይቆም ቀድመው የተገነዘቡት የፓርቲው

አመራሮች ጎንደርን ቶሎ መልቀቅን እንዳለባቸው አምነዋል፡፡ እናም ሰላማዊ ሰልፉ

ከተጠናቀቀ ከሁለት ሰዓት በኋላ ጉዞ ወደ አዲስ አበባ ተጀመረ፡፡ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች

መሬቱን ለማስመለስ የተደረገውን ግፊት ቢያደንቁም ሰማያዊ በመመለሱ ከመጠን በላይ

የሚቆራረጠው የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ጋብ እንደሚል በግልጽ ይናገሩ ነበር፡

፡ ሰላማዊ ሰልፉ በሰላም መካሄዱ ያናደደው የሚመስለው ገዥው ፓርቲ ግን ከጎንደርም

ውጭም እየተከተለ መተንኮሱን አላቆመም፡፡ አዲስ አበባ ለመድረስ ጥቂት ኪሎ ሜትሮች

ሲቀሩንም ቢሆን ‹‹ከበላይ አካል›› ትዕዛዝ የተላለፈላቸው የሚመስሉት የትራፊክ

ፖሊሶች ደብረ ጽጌ ላይ በመሳሪያ አስቆሙን፣ አስጸያፊ ስድብምና ማስፈራራትም

ተጨመረበት፡፡

ሆኖም በሰልፉ የተገኙት ወጣቶችም ይህን

የአካባቢው ቅርንጫፍ በደረሰባቸው ወከባ

አለመደናገጣቸውን ደውለው ነግረውኛል፡፡

ለሰላማዊ ሰልፉ በሄድንበት ወቅት ጎንደር

ውስጥ ካገኘኋቸው የኢህአዴግ አባላት

መካከል አብዛኛዎቹ መሬቱ ለባዕድ ተላልፎ

መሰጠቱን ከመቃወም አልፈው በጉዳዩ

ከተቃዋሚዎች ጋር አብረው ለመስራት

ፍላጎት እንዳላቸው ተረድቻለሁ፡፡ ደብድቡ

ተብለው የተላኩት ፖሊሶችና የከተማው

አስተዳደርም እንደ ፌደራል መንግስቱ

ግትር አቋም አለመውሰዱ የሽንፈቱ አንድ

አካል ነው ማለት ይቻላል፡፡

ወደ አዲስ አበባ

ጉዞ

ሰላማዊ ሰልፉ ተደርጎም ቢሆን ማዋከቡ

እንደማይቆም ቀድመው የተገነዘቡት

የፓርቲው አመራሮች ጎንደርን ቶሎ

መልቀቅን እንዳለባቸው አምነዋል፡፡ እናም

ሰላማዊ ሰልፉ ከተጠናቀቀ ከሁለት ሰዓት

በኋላ ጉዞ ወደ አዲስ አበባ ተጀመረ፡

፡ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች መሬቱን

ለማስመለስ የተደረገውን ግፊት ቢያደንቁም

ሰማያዊ በመመለሱ ከመጠን በላይ

የሚቆራረጠው የስልክና የኢንተርኔት

አገልግሎት ጋብ እንደሚል በግልጽ ይናገሩ

ነበር፡፡ ሰላማዊ ሰልፉ በሰላም መካሄዱ

ያናደደው የሚመስለው ገዥው ፓርቲ ግን

ከጎንደርም ውጭም እየተከተለ መተንኮሱን

አላቆመም፡፡ አዲስ አበባ ለመድረስ ጥቂት

ኪሎ ሜትሮች ሲቀሩንም ቢሆን ‹‹ከበላይ

አካል›› ትዕዛዝ የተላለፈላቸው የሚመስሉት

የትራፊክ ፖሊሶች ደብረ ጽጌ ላይ

በመሳሪያ አስቆሙን፣ አስጸያፊ ስድብምና

ማስፈራራትም ተጨመረበት፡፡

ይህ ሁሉ ወከባ ግን ልዑካኑን አላስደነገጠም፡

፡ ወደ ጎንደር ጉዞ ከጀመሩበት ወቅት አንስቶ

ወጣቶቹ በድፍረት ከተሸናፊው መንግስት

ጋር ፊት ለፊት ተጋፍጠዋል፡፡ ደብረ ጽጌ

ላይም ያደረጉት ተመሳሳይ ነው፡፡ ትራፊክ

ፖሊሶች መኪናውን ወደ ጣቢያ እንዲወስድ

ሲወተውቱት የሰነበተውና ከልዑካኑ ጋር

ሁለቱንም ቀን የታሰረው ሾፌር ደብረ ጽጌ

ላይም ልክ እንደ ሰማያዊ ወጣቶች መብቱን

አሳልፎ ላለመስጠት ያለውን ቁርጠኝነት

አሳየ፡፡ የልዑካኑ አባላት መሳሪያ አውጥቶ

‹‹እበትንሃለሁ!›› ላለው ፖሊስ ደረታቸውን

ሰጡ፤ አጸያፊ ስድብ የተሳደበውን

አፋጠጡት! አሁን ልዑካኑን ለማስቆም

የጣሩት ፖሊሶች እንደገና መደናገጥ

ጀምረዋል፡፡ የከተማው ህዝብ ወጣቶቹና

የትራፊክ ፖሊስ የሚያደርጉትን ክርክር

እየተመለከተ ተስብስቧል፡፡

የሰማያዊ ወጣቶች ዋናው ሰላማዊ ሰልፍ

ከመደረጉ በፊት መስቀል አደባባይና አዘዞ

ላይ ፖሊስ ሲያስቆማቸው ሲይዛቸው

በመዘመር፣ ህጉን በማስረዳት ህዝብን

ሰብስበዋል፡፡ በጽናታቸውና በድፍረታቸው

ፖሊሶቹን ሳይቀር አስገርመዋል፡፡ ደብረ

ጽጌ ላይ በመሳሪያ ለማስቆም ሲጥርም

ሌላ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል፣ ህዝብን

ሰብስበው ስለመብቱ አስተምረዋል፡

፡ ከፖሊስ ጋር እየተከራከሩ፣ ህዝብን

ሰብስበው እያስተማሩም ለቀሪው ህዝብ

በስልክና በማህበራዊ ድህረ ገጾች ትዕይንቱን

ማካፈላቸውን ቀጥለዋል፡፡ በተለይ በፌስ

ቡክ ዜናው በስፋት መዳረስ ጀምሯል፡፡

ይህን ሁሉ ያልጠበቁት ትራፊክ ፖሊሶችን

የላኩት የበላይ አካላትም ይሁኑ የከተማው

ካድሬዎች ወጣቶቹን ለመልቀቅ ተገድደዋል፡

፡ ለኢህአዴግ ሌላ ሽንፈት! ለሰማያዊ

ወጣቶች ሌላ ድል! ከድል በኋላም የድል

መዝሙር!

ተከብረሽ የኖርሽው በአባቶቻችን ደም፣

በአባቶቻችን ደም፣

እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም

ያስደፈረሽ ይውደም፣

‹‹የትግል ጉዞ ታሪካዊ፣

ዓላማው ፍጹም ህዝባዊ፣

ራዕያችንም ኢትዮጵያዊ…››

መሬት ያስቆረሱት...

ከ ገፅ 7 የዞረ

የሚያስረዱ መረጃዎች ሊሆኑ አይችሉምን?

ድብቅነት በኢትዮጵያ በመግዛት ላይ ላለው

ገዥው አካል ዋና መለያ ባህሪው ነው፡፡ ነገሮችን

ደብቆ በመያዝ እያንዳንዱን በማሞኘት ላይ

ይገኛሉ፡፡ አቶ መለስ በህይወት በነበሩበት ጊዜ

እና በአሁኑ ጊዜ ያሉት ሎሌዎቻቸው ደግሞ

የቅብብሎሽ ዱላውን ከጌታቸው ራዕይ በመቀበል

በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እያሳዩ ያሉት ንቀት

የህዝቡን ምንነት ሳይገመግሙ እና ሳይረዱ

በራቁት ገላው ላይ ሱፍ እየጎተቱ መሆኑን

በውል ሊያጤኑት ይገባል፡፡ አቶ መለስ እና

ጋሻጃግሬዎቻቸው አሰብን እና ባድመን በቤሣ

ቁርጥራጮች ካስረከቡ በኋላ ዝምታ ብቻ

መልስ ስላገኙ ከዚያ ነገር አንድ ቁም ነገር

ተምረዋል፡፡ ይኸውም ኢትዮጵያውያንን እና

የኢትዮጵያን ግዛት የእነርሱ የግል እንደፈለጉ

የሚለውጧት፣ የሚሸጧት የህግ ተጠያቂነት

የሌለበት የግል ንብረታቸው መሆኗን አረጋገጡ፡

፡በመለስ/ኃይለማርያም ከምዕራብ ኢትዮጵያ

የግዛት አንድነት መሬት በመቁረስ ለሱዳን

ለመስጠት የሚደረግ ማንኛውም “ስምምነት”

ህገመንግስታዊ አይደለም፡፡ እ.ኤ.አ. ወደ 2008

መለስ ብለን ስናይ አቶ መለስ የኢትዮጵያን

መሬት ቆርሰው ለሱዳን ወይም ደግሞ ለማንም

ቢሆን ለመስጠት ህጋዊ ስልጣን የላቸውም ብዬ

ተከራክሬ ነበር፡፡

ዛሬም ቢሆን አቶ ኃይለማርያም የኢትዮጵያን

መሬት ቆርሰው ለሱዳን የመስጠት ህጋዊ

መብትም ሆነ ስልጣን የላቸውም፡፡ ይህንን ካልኩ

ዘንድ አቶ መለስ “ከአማራ ክልል ግዙፍ የሆነ

መሬት” ቆርሰው ለሱዳን ለመስጠት “ስምምነት”

እንደተፈራረሙ አጠያያቂ ነገር አይደለም፡

፡ አቶ ኃይለማርያም እና ጌቶቻቸው ይህን

ህገወጥ የመሬት ዕደላ ዕኩይ ተግባራቸውን

“የስልታዊ/ስትራቴጂክ ስምምነት ማዕቀፍ”

በማለት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በመክፈት ጣፋጭ

በማስመሰል በማር የተለወሰ መርዛቸውን

ሊግቱን ይፈልጋሉ፡፡ እውነታው ግን በአሁኑ

ጊዜ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለው ገዥ አካል

ምንም ዓይነት የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳንም

ሆነ ለማንም ሌላ አገር አሳልፎ የመስጠት ህገ

መንግስታዊም ሆነ ዓለም አቀፋዊ መብትም

ስልጣንም የለዉም፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ

ሊታይ የሚችለው ይህ የተካሄደው የድብቅ

ስምምነት የኢትዮጵያን ህገ መንግስት አንቀጽ

12 የሚጻረር ስለሆነ የህገ መንግስት ጥያቄን

ያስነሳል፡፡ አቶ መለስ በህይወት በነበሩበት ጊዜ

እና እርሳቸውን ተክተው በመስራት ላይ ያሉት

የአሁኖቹ ገዥዎቻችን ከኢትዮጵያ ህዝብ እና

ከተወካዮች ምክር ቤት በሸፍጥ ደብቀው ከኦማር

አልባሽር ጋር ያደረጉትን የሚስጥር “ስምምነት”

እየተባለ የሚጠራውን ተግባራዊ ለማድረግ

ይፍጨረጨራሉ፡፡ በኢትዮጵያ ህገ መንግስት

አንቀጽ 12 ስር (“የመንግስት የስራ ድርሻ

እና ተጠያቂነት“) እንዲህ ይላል፣ “መንግስት

ተጣያቂነት እና ለህዝብ ግልጽነት ባለበት ሁኔታ

ስራውን ይሰራል… ማንም የህዝብ ባለስልጣን

ወይም ተመራጭ በህግ የተሰጠውን ስልጣን

በህግ አግባብ ካልተጠቀመ ተጠያቂ ይሆናል፡

፡” አቶ መለስ እና ተኪዎቻቸው “የህዝብ

ባለስልጣን” እንደመሆናቸው መጠን ግልጽነት

እና ተጠያቂነት ባለበት ሁኔታ ስራቸውን

ለማከናወን ህገ መንግስታዊ ግዴታ አለባቸው፡

፡ ለህዝብ ሳይቀርብ እና የስምምነቱ ሁኔታም

በዝርዝር ምን እንደሆነ ሳይታወቅ እንዲሁም

ህጋዊ ስልጣን የተሰጠው የተወካዮች ምክር

ቤት ሳያጸድቀው የአገርን የግዛት አንድነት

በመጣስ መሬት ቆርሶ ለሌላ አገር ለመስጠት

በእራስ ፈቃድ የሚደረግ የሚስጥር ስምምነት

የህገመንግስቱን አንቀጽ 12 ይጻረራል፣ ሙሉ

በሙሉም ህገ መንግስቱን ይደፈጥጣል፡፡

ኢትዮጵያ ለዘላለም በክብር ትኑር!

(ሳምንት ይቀጥላል…)
ነገረ-ኢትዮጵያ

ቅፅ 1 ቁጥር 2

የካቲት 7 ቀን 2006 ዓ.ም.

16

ኢህአዴግ ተሸንፏል!

(የጉዞ ማስታወሻ)

ጌታቸው ሺፈራው

ዛሬ የማወራው በምርጫ ስለመሸነፍ

አይደለም፡፡ በምርጫ መሸነፍማ ወግ

ነው፡፡ በተለይ ምርጫን ፍትሃዊና

ዋነኛው የስልጣን ምንጭ አድርጎ

ሽንፈቱን በጸጋ ለተቀበለ ‹‹ሽንፈቱ››

አሸናፊነት በሆነ ነበር፡፡ ኢህአዴግ

ይህኛውን ወግ አላገኘውም፡

፡ እንዲያውም አስከፊው ሽንፈት

ሳያውቁት፣ በግድ መሸነፍ ሳይሆን

አይቀርም፡፡ አዎ ኢህአዴግ ይህን

ሽንፈት ተከናንቦታል፡፡ ኢህአዴግ

ይህንን ሽንፈቱን ለመሸፈን ለ23

አመታት በግድ መግዛትን መርጧል፡፡

ከ1997 በኋላ ተቃዋሚዎች

ቢዳከሙም፣ ህዝብ በፖለቲካው ተስፋ

ቆርጦ ‹‹ዝም ብሎ ለመገዛት›› የቆረጠ

ቢመስልም ኢህአዴግ ግን ሽንፈቱን

ይደብቅልኛል ያለውን ወከባና ጥርነፋ

አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ባለፉት ጥቂት

ወራት ደግሞ በፖለቲካው መስክ

መነቃቃቶች እየታዩ ነው፡፡ ይህኛው

‹‹ዝም›› ያለው ህዝብ ኢህአዴግን

እንደማይፈልግ፣ ኢህአዴግ ምንም

ያህል የመጨቆንና የማታለል አቅም

ቢኖረውም የህዝብን ልብ መግዛት

አለመቻሉንና መሸነፉን የሚያሳይ

ነው፡፡ ኢህአዴግ ለመሸነፉ እጅግ

በርካታ ማሳያዎችን ማንሳት ይቻላል፡

፡ አሁን ግን ለሱዳን አሳልፎ ከሰጠው

መሬት ጋር በተያያዘ ያለው ጉዳይ

ላይ ብቻ ማተኮር ወደድኩ!

ፓርቲ የጎንደር ጉዞ

የሰማያዊ

ሰማያዊ ፓርቲ ወደ ጎንደር ከማቅናቱ

በፊት በጽ/ቤቱ በድንበሩ ጉዳይ ጥናት

ካደረጉት መካከል ብቸኛው የሆኑትን

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያምን

በመጋበዝ ህዝብን አወያይቶ ነበር፡፡

በዚህ ውይይት ወቅት ፕሮፌሰሩን

ጨምሮ ተሰብሳቢዎቹ ‹‹ኢህአዴግ

አገር ሻጭ›› መሆኑን ተናግረዋል፡

፡ ሁሉም እንደ መንግስት ሳይሆን

የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት አሳልፎ

ለመስጠት የተነሳ አንዳች ባዕድ

ሀይል እንደሆነ ተግባብቶበታል፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች

ደግሞ ይህን የፕሮፌሰር መስፍንና

የሌሎችን ጥናት እንዲሁም

መረጃዎች በግብዓትነት ወስደው

ሉዓላዊነታቸውን ለማስከበር ወደ

ጎንደር ለማቅናት በዝግጅት ላይ

ነበሩ፡፡

ሰማያዊ ወደ ጎንደር ሲያቀናም

ኢህአዴግ መሸነፉን በጉልህ

ተመልክቻለሁ፡፡ አድርባይ ደህንነትና

ፖሊስ የማይፈሩት ወጣቶች

ወደሚታሰሩበት፣ ወደሚደበደቡበትና

መስዕዋትነት ወደሚያስከፍል ተልዕኮ

ሳይሆን ለሰርግ አሊያም ለሌላ

ቅንጦች የሚጓዙ ያህል ደስተኞች

ነበሩ፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ በሚወገዝበት

ስርዓት አብዛኛዎቹ ወጣቶች ‹‹እኔ

አልቀርም!›› በማለት የፓርቲውን

አመራሮች ሲለምኑ፣ በመቅረታቸው

ቅር መሰኘታቸው ስርዓቱ

ሊያስገባቸው ከሚፈልገው የፍርሃት

አዙሪት ሰብረው መውጣታቸውን

የሚያሳይ ነው፡፡

ወከባ

የተሸናፊው

የተሸነፈ የሚወስደው እርምጃ

ግብታዊ ነው፡፡ ተረጋግቶ መፍትሄ

ከመስጠት ይልቅ ማዋከብ፣ መደናበር

ልዩ ባህሪው ነው፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ

ልዑካን ወደ ጎንደር አቅንተው

እንደገና አዲስ አበባ እስኪመለሱ

ያጋጠማቸውም ይህ የተሸናፊዎች

እርምጃ ነው፡፡ ወከባው የጀመረው

የጎጃሟ ሉማሜ ከተማ ላይ ነው፡

፡ ከአዲስ አበባ ጀምሮ በርካታ

የትራፊክ ፖሊሶች እየገላመጡ

ቢያሳልፉንም ከላይ አንዳች

ትዕዛዝ የተሰጣት የምትመስለዋ

የሉማሜዋ የትራፊክ ፖሊስ ግን

በቀላሉ የምታሳልፈን አልነበረችም፡

፡ መውጫው የምትቆዩበትን ቀን

በግልጽ አላስቀመጠም በሚል ሰንካላ

ምክንያት መኪናችን አስቆመች፡

፡ ካልተቀጣችሁ አትሄዱም በማለቷ

ላለመዘግየት ‹‹ቅጣታችን›› ቶሎ

መክፈልን ወሰንን፡፡ ምን አልባትም

ከ‹‹በላይ አካል›› ትዕዛዙ የመጣላት

የምትመስለው የትራፊክ ፖሊስ

ውሳኔ ግን ቢሮ ውስጥ የነበረውን

አለቃዋንም ያስገረመ ነበር፡፡

ለመክፈል ወደ አለቃዋ ቢሮ ያቀኑት

የልዑካኑ አባላት እንዳረጋገጡልን

የትራፊክ ፖሊሷ ያቀረበችው ሰንካላ

ምክንያት ለማስቀጣት ይቅርና

ለተግሳጽ የሚያበቃ አልነበረም፡፡

መስዋትነት ወደሚያስከፍል

ተልዕኮ ሳይሆን ወደ አንዳች ደስታ

ቦታ የሚያቀኑ የሚመስሉት

የልዑካኑ አባላት መንገዱን በሙሉ

የአገራቸውንና የፓርቲያቸውን

መዝሙር በመዘመር፣ እንዲሁም

በመቀላለድና በመሳሳቅ ጉዟቸውን

ቀጥለዋል፡፡ ይህን ደስታቸውን

ከጥቂት አመታት በፊት በርካታ

ወጭ ፈሶበት በጥቂት አመት ውስጥ

የፈረሰው ቻይና ሰራሽ መንገድ እንኳ

አላቀዘቀዘውም፡፡ ሆኖም የመኪናችንን

ፍጥነት በእጅጉ ቀንሶታል፡፡ በዚህም

ምክንያት በጊዜ መግባት ሲገባን

ግማሹን ሌሊት ሁሉ ለመጓዝ

ተገደናል፡፡

አይደለም ሰማያዊን የግንባሩን አባላት

የማያምነው ኢህአዴግ የልዑካኑንና

ከልዑካኑ ጋር የሚገናኙትን አካላት

በቅርብ እርቀት መከታተሉ የሚጠበቅ

ነው፡፡ ስለሆነም የት እንደደረስን፣

መቼ ጎንደር እንደምንገባና

ሌሎች መረጃዎችን ለአገሪቱ

ሳይሆን ለስልጣን ማራዘሚያ

በሚጠቀምባቸው የደህንነት

ተቋማቱ ሊያዳምጥ እንደሚችል

ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ ይህን

እያወቅንም ቢሆን እኛ እንደልባችን

እናወራለን፡፡ የት እንደደረስን፣ መቼ

እንደምንገባና ሌሎች መረጃዎችንንም

በነጻነት እንለዋወጣለን፡፡ በተለይ

ጎንደር ከሚገኘው የፓርቲው

ቅርንጫፍና ቀድመው ወደ ጎንደር

ካቀኑት የፓርቲው አመራሮች ጋር

እነዚህን መረጃዎች በተከታታይ

ተለዋውጠናል፡፡

ጎንደር ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ላይ

ደረስን፡፡ እነዚህን መረጃዎች

ሲያዳምጥ የነበረው ገዥው ፓርቲ

የተሸናፊ እርምጃ ሊወስድ እንደነበር

የሰማነው ግን በነጋታው ጠዋት ላይ

ነው፡፡ እንፍራንዝ የተባለችውን ከተማ

እኛ ያለፍናት ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት

አካባቢ ነው፡፡ ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት

አካባቢ ‹‹ሰማያዊ ነው!›› ተብሎ

መኪና መዘረፉን የነገረን በአካባቢው

የሚገኝ አንድ የሰማያዊ ፓርቲ ደጋፊ

ነው፡፡ አዎ የተሸነፈ የሚወስደውን

እርምጃ አያውቅም፡፡ ለማመዛዘን

ጊዜም ሆነ ብቃት አይኖረውም፡፡

ወከባው ጎንደር ከደረስን በኋላም

ቢሆን አላቆመም፡፡ ካድሬዎች

ያረፍንበትን ሆቴል ማጨናነቅ ዋነኛ

ስራቸው ሆነ፡፡ ከዚህም አልፈው

‹‹እነዚህን ሰዎች አስወጡልን!››

እስከማለት መድረሳቸውን በግልጽ

ሰምተናል፡፡ በሌላ በኩል የሰላማዊ

ሰልፉ እንዲካሄድ ባለመፈለጋቸው

አንቀበልም ከማለትም አልፈው

ሲደበቁ የሰነበቱት የጎንደር ከተማ

አስተዳደር ባለስልጣናት የሰማያዊ

ወጣቶች ገፍተው ከገቡበት እውነት

ጋር መፋጠጥ የግድ ሆኖባቸዋል፡፡

ሀሙስ ጥር 22 ስድስት ሰዓት ላይ

ሰው የሚበዛባት አራዳ ለቅስቀሳ

ተመርጣለች፡፡ ከየት እንደመጡ

ያልታወቁት የሰማያዊ ወጣቶች

በፍጥነት ወረቀቶችን ለህዝብ

ማድረስ ጀመሩ፡፡ መኪና ላይ ሆነው

መሬቱን አሳልፈው እንደማይሰጡ

ህዝብን ቀሰቀሱ፡፡ ቅስቀሳውን ከአራዳ

እስከ መስቀል አደባባይ በፍጥነት

አከናወኑ፡፡ ምን አልባት እስራት

ካለ ህዝብ በስፋት ከሚያይበት

የመስቀል አደባባይ ላይ መታሰሩ

አዋጭ እንደሚሆን ታምኖበታል፡

፡ እንደተገመተው የተደናገጡት

የከተማው ባለስልጣናት መስቀል

አደባባይ ላይ እየቀሰቀሱ የነበሩትን

ወጣቶች ለማስቆም ጥረት አደረጉ፡

፡ ማስቆም የፈለጉበት መንገድ ግን

የሚያስገርም ነበር፡፡

ልክ ሉማሜ ላይ እንዳደረጉት

የላኩት የትራፊክ ፖሊስ ነው፡፡ ምን

አልባትም መኪናቸውን ከተቀሙ

እንቅስቃሴው ይገታል ከሚል እሳቤ

ሳይሆን አይቀርም፡፡ ጎንደር ላይ ግን

በቀላሉ የሚሳካ አልነበረም፡፡ ሲቪል

የለበሱ የትራፊክ ፖሊሶች ሳይቀሩ

ለወጣቶቹና ተሸናፊዎች ላስደፈሩት

ሉዓላዊነት ዘብ ቆመው ታይተዋል፡

፡ ቅስቀሳውን እንዲያስቆሙ

የተላኩት ፖሊሶች መኪናው ምን

እንዳጠፋ ንገሩን ሲባሉ ምክንያት

አልነበራቸውም፡፡ ግን ‹‹ከበላይ

አካል›› ይዛችኋቸው ኑ መባላቸውን

ብቻ ነው በተደጋጋሚ የሚገልጹት፡፡

ቅስቀሳ ላይ የነበሩት ወጣቶች ከታሰሩ በኋላ የኢትዮጵያ ፖሊስ የሚታወቅበትን ድብደባና ዘለፋ አልፈጸመም፡

፡ ይህ ግን የፖሊሶቹ ደግነት ብቻ አልነበረም፡፡ የከተማ አስተዳደሩ አንዳች ቅርቃር ውስጥ መግባቱን ራሱ

አስመስክሯል፡፡ ወጣቶቹ እስር ቤት እያሉ ከቀናት በፊት የማሳወቂያ ደብዳቤውን አልቀበልም ያሉት አካላት

አመናጭቀው የመለሷቸውን ሰዎች አስጠርተው ተለማምጠዋል፡፡

የሰማያዊ ወጣቶች ደግሞ ጥፋታችንን

ካልነገራችሁን ቅስቀሳውን አናቆምም

ካለንበትም አንንቀሳቀስም አሉ፡፡

ቅስቀሳውን የደገፈው ህዝብም ቢሆን

ተመሳሳይ አቋም ያዘ፡፡ ቅስቀሳውን

ሲከታተል ከነበረው ህዝብ ‹‹ከህዝብ

ጋር እንዳትቀያየሙ›› የሚል

ምክር የተሰጣቸውና ወትሮውንም

ያላመኑበት የትራፊክ ፖሊሶች

መለሳለስ ጀመሩ፡፡ ትንሽ ቆይተው

የወጣቶቹን ቅስቀሳና ከፖሊስ ጋር

የሚያደርጉትን ትዕይንት እንደ ህዝብ

ታድመዋል፡፡

የከተማው አስተዳደር ግን ቅስቀሳው

መቆም እንዳለበት ቆርጧል፡፡

በመሆኑም የትራፊክ ፖሊሶችን ተክቶ

ፖሊስ ተላከ፡፡ ኢህአዴግ ከምንም

በላይ የሚፈራው መረጃን ነው፡

፡ በመሆኑም የፖሊሶች የመጀመሪያ

ኢላማ የሆነው ፎቶ ግራፍ

የሚያነሳው ወጣት ነበር፡፡ ካሜራውን

ለመንጠቅ ሲሞክሩ ግን ከሰማያዊ

ልጆች ከፍተኛ ትግል ገጠማቸው፡

፡ ፖሊስና ወጣቶቹ ተናነቁ፡፡ ህዝብ

ተሰበሰበ፡፡ ወጣቶቹ ህግ አያከብርም

የሚሉት ኢህአዴግ የላካቸውን

ፖሊሶች እየተፋለሙ ‹‹በህግ አምላክ!

በህግ አምላክ!›› ይላሉ፡፡ በህግ ሳይሆን

በጉልበት ቅስቀሳውን እንዲያስቆሙ

የተላኩት ፖሊሶች ግን ከዚህ በላይ

መታገል አልፈለጉም፡፡ አዎ! ከበላይ

አካል ከተሰጣቸው ይልቅ ‹‹በህግ

አምላክ›› ሲባሉ ተደናግጠው ቆሙ፡

፡ ጎንደር ላይ በህግ አምላክ ተከበረ፡

፡ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች በቀላሉ

እጅ የሚሰጡ አልነበሩም፡፡ እናም

አምነውበት ሳይሆን ከበላይ አካል

የተላኩት ፖሊሶች ያለ ግድ በውድ

ለሰማያዊ ወጣቶች ካሜራውን ለቀቁ፡፡

አሁን ኢህአዴግ ተሸንፏል፡፡ ወጣቶቹ

ደግሞ በአሸናፊነት ይዘምራሉ፡፡

ተከብረሽ የኖርሽው በአባቶቻችን

ደም፣

በአባቶቻችን ደም፣

እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም

ያስደፈረሽ ይውደም፣

‹‹የትግል ጉዞ ታሪካዊ፣

ዓላማው ፍጹም ህዝባዊ፣

ራዕያችንም ኢትዮጵያዊ…››

ያም ሆኖ ፖሊሶቹ ‹‹ይዛችኋቸው

ኑ!›› የተባሉትን ትዕዛዝ አልረሱም፡፡

ወጣቶቹ በመኪና ተጫኑ፡፡ ከፖሊሶቹ

ጋር ሆነው ግን ወረቀት ከመበተን፣

በሞንታርቮ ከመቀስቀስ ያገዳቸው

አካል አልነበረም፡፡ እንዲያውም ወደ

ፖሊስ ጣቢያው የሚያደርሰውን

ረዥም መንገድ ይዘው ሲጓዙ

ፖሊሶቹ ሰላማዊ ሰልፉ እንዲካሄድ

ፍላጎት እንደነበራቸው ያሳያል፡፡

ቅስቀሳ ላይ የነበሩት ወጣቶች

ከታሰሩ በኋላ የኢትዮጵያ ፖሊስ

የሚታወቅበትን ድብደባና ዘለፋ

አልፈጸመም፡፡ ይህ ግን የፖሊሶቹ

ደግነት ብቻ አልነበረም፡፡ የከተማ

አስተዳደሩ አንዳች ቅርቃር ውስጥ

መግባቱን ራሱ አስመስክሯል፡፡

ወጣቶቹ እስር ቤት እያሉ ከቀናት

በፊት የማሳወቂያ ደብዳቤውን

አልቀበልም ያሉት አካላት

አመናጭቀው የመለሷቸውን ሰዎች

አስጠርተው ተለማምጠዋል፡፡

በአንድ በኩል ተርበትብተው መደራደር

የሚፈልጉት የጎንደር አስተዳደር

ሰዎች በሌላ በኩል ማዋከባቸውን

ግን አላቆሙም፡፡ የታሰሩት ቢፈቱም

ቅስቀሳውን ለማሰናከል መሳሪያዎቹ

በፖሊስ እንደተያዙ ቆይተዋል፡፡

የመቀስቀሻ መሳሪያዎቹ በፖሊስ

እጅ በመውደቃቸውና ለአንዳንድ

ጥንቃቄዎች ሲባል አርብ ጥር 23

ወረቀት መበተንና ሌሎች ግልጽ

ቅስቀሳዎች አልነበሩም፡፡ ይህም

በስጋት የተዋጡት የከተማው

አስተዳደር አካላትን አስጨንቋል፡

፡ እናም በተቀላቀለ ስሜት ደውለው

‹‹ምነው ጠፋችሁ!›› እስከማለት

ደርሰዋል፡፡ ቅዳሜ ጥር 24 ኮሌጅና

አዘዞ ለቅስቀሳ ተመርጠዋል፡፡

ለቅስቀሳ የወጡት ወጣቶች ኮሌጅና

ዩኒቨርሲቲው አካባቢን በፍጥነት

ከቀሰቀሱ በኋላ ወደ አዘዞ ሲደርሱ

ፖሊስ አስቁሟቸዋል፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ ልዑካን ወደ ጎንደር

ካቀኑበት ጊዜ ጀምሮ ከወትሮው በተለየ

መልኩ ኢንተርኔትና ስልክ ተቋርጦ

ለረዥም ሰዓት መቆየት ጀምሯል፡

፡ ከዚህ ባሻገር ከሆቴሉ ጎን የሚገኝ

ቤት በእሳት ተያያዘ ተብሎ ጥይት

በመተኮስ ጫጫታ ለመፍጠርና

መብራት በማጥፋት ለማደናገጥም

ተሞክሯል፡፡ ተቃጠለ የተባለው

ቤት ከሆቴሉ ጎን ቢሆንም ምንም

አይነት ጭስ፣ የእሳት ምልክትና ሽታ

አልነበረውም፡፡ ወዲያውኑ ደግሞ

ጠፋ ተባለ! በቅስቀሳ ላይ የነበሩት

ወጣቶች አዘዞ ላይ በተያዙበት ወቅት

ወደ ገፅ 15 ይዞራል