Australian citizenship test book - Ahmaric
Australian citizenship test book - Ahmaric
Australian citizenship test book - Ahmaric
You also want an ePaper? Increase the reach of your titles
YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.
የመጀመሪያ አውሮፓውያን ወደ

አውስትራሊያ

የመጀመሪያው የአውሮፓ ተዘዋውሮ ማጥናት

በ17ኛው ምእተ ዓመት፣ የፖርቱጉስ/ Portuguese እና የዱትች/

Dutch አሳሾች በደቡብ ክፍል የማይታወቀውን መሬት ‘ተራ

አውስትራሊስ ኢንኮግኒታ/Terra Australis Incognita’ የተባለውን

ተዘዋውረው በማጥናት አግንተዋል። በ1606 ዓ.ም የዱትች ሰው

የሆኑት፣ ዊለም ጃንስዙን/ Willem Janszoon፣ በሰሜናዊ

አውስትራሊያ ጫፍ በምዕራባዊ በኩል ያለን ካፕ ዮርክ ፐኒንሱላ/

Cape York Peninsula ካርታ ሠርተዋል። በዚህን ጊዜ አካባቢ

ሉስ ቫዝ/Luis Vaez de Torres ከፖርቱጋል/ Portugal

በመርከብ አቋርጠው ወደ ሰሜናዊ አህጉር የባህር ወሽመጥ ደርሰዋል።

ከዚያም በኋላ በ1600ዎች ዓመታት፣ የደትች መርከብ ተጓዦች

በምዕራብ አውስትራሊያ ባህር ጠረፍ ያለውን ተዘዋውረው

አጥንተዋል። ደትች ይህንን መሬት ‘ኒው ሆላንድ/New Holland’

የሚል ስም ሰጥተውታል።

በ1642 ዓ.ም አበል ታዝማን/Abel Tasman የተባሉት በባህር

ጠረፍ ላይ አዲስ መሬት እንዳገኙና ስሙንም ‘ቫን ዴመንስ ላንድ/

Van Diemen’s Land’ (የአሁኑ ታዝማኒያ) ብለውታል።

እንዲሁም በሺዎች ማይልስ ርቀት የሚቆጠር የአውስትራሊያን ጠረፍ

በካርታ ላይ አስፍረዋል። የኒው ሆላንድ/New Holland ማፕ/

ካርታን ያላጠናቀቁበት ምክንያት መሬቱ ከስሜናዊ ፓፑ ኒው ጉኒ/

Papua New Guinea ጋር የተገናኘ ስለመሆኑ ለማሳወቅ ነው።

ወንጀለኛን ስለማጓጓዝ

አውስትራሊያን ልዩ የሚያደርጋት ቢኖር የመጀመሪያ

አውሮፓውያን ሰፋሪዎች ወንጀለኞች ስለነበሩ ነው። የተባበሩት

አሜሪካ (USA) ነጻነቷን ካገኘች በኋላ ግሬት ብሪቴን እስረኞቿን

ወደ አሜሪካ መላክ አቆመች። በብሪቴን ያለው እስር ቤት በታም

እንደተጣበበ ነው። በብሪቴን አገር የወንጀለኛ ቁጥር በጣም

ስለጨመረ ለእስረኞች የሚሆን መንግሥት አዲስ ቦታ መፈለግ

አለበት። በ1786 ዓ.ም አዲስ ቅኝ ግዛት ወደሆነችው ኒው ሳውዝ

ዌልስ/New South Wales እስረኞችን ለመላክ ታላቋ ብሪቴን

ወሰነች። ይህ ‘ማጓጓዝ/transportation’ በሚል ይጠራል።

የመጀመሪያ ቅኝ ግዛት

የመጀመሪያ ኒው ሳውዝ ዌልስ/New South Wales ቅኝ ግዛት

ገዥ ካፕቴን አርቱር ፊሊፕ/Captain Arthur Phillip ይባላሉ።

የመጀመሪያውን 11 የጦር መርከቦች ያለችግር ከብሪቴን ወደሌላ

የዓለም ክፍል ያመጡ ሰው ናቸው። ወንጀለኞችን በመቀለብና

ደህንነታቸውን በጣም ይንከባከቡ እንደነበርና በጣም አነስተኛ የሆኑ

በጉዞ ላይ እንደሞቱ ነው።

Captain Phillip የመጀመሪያ የጦር መርከብ አዛዥ ሆነው ወደ

ስይድነይ ባህር ወሽመጥ/Sydney Cove ጥር/January 26

ቀን 1788 ዓ.ም ደረሱ። ይህም በመታሰቢያ በዓላት ውስጥ ያለና

እኛም በየዓመቱ የአውስትራሊያ ቀን በሚል እናከብራለን።

ዊሊአም ዳምፔር/William Dampier የተባሉት በአውስትራሊያ አፈር

ለመጀመሪያ የረገጡ ኢንግሊዛዊ ሰው ነበሩ። በ1684 ዓ.ም በሰሜን

ምዕራብ ጠረፍ ደረሱ። መሬቱ ደረቅና አቧራማ ስለነበር ታዲያ

ለንግድ ወይም ለሰፈራ ይሆናል ብለው ግምት ውስጥ አላስገቡትም።

ካፒቴን ጃመስ ኮክ/Captain James Cook

የምሥራቅ አውስትራሊያ ጠረፍ እንግሊዛዊ የሆኑት ጃመስ ኩክ/

James Cook፣ ‘ኢንዲቮር/Endeavour’ በተባለው መርከባቸው

በ1770 ዓ.ም ከመድረሳቸው በፊት በኢሮፓውያን ተዘዋውሮ ጥናት

እንዳልተደረገ ነው። ኩክ/Cook የደቡባዊ ፓሲፊክን ተዘዋውረው

እንዲያጠኑ በሚል የብሪቲሽ መንግሥት ለረዥም ጉዞ ልኳቸዋል።

በቦታንይ ባህር ወሽመጥ/Botany Bay ላይ በማቆም የምሥራቅ

ጠረፍ ካርታ ሲያነሱ፣ ይህም በዘመናዊ ስይድነይ ደቡባዊ ክፍል

ይገኛል። ጃመስ ኩክ/James Cook ይህንን መሬት ‘New

South Wales’ በሚል እንደሰየሙትና በንጉስ ጂወርጅ/King

George III ተብሎ እንዲጠራ ጠየቁ።

የመጀመሪያ ጦር መርከብ ከብሪቴን ተነስቶ ሲድነይ የባህር ወሽመጥ ላይ በ1788

ዓ.ም ደረሰ

የመጀመሪያዎቹ ዓመታት

የመጀመርያ ዓመታት የሰፈራ ሁኔታ በጣም ከባድ ነበር። ገዥ

ፊሊፕ እራሳቸውንና መኮንኖቻቸው ጨምሮ፣ እያንዳንዱ ሰው

ተመሳሳይ የምግብ መጠን በማግኘት እንዳይራቡ ለማድረግ

ያረጋግጣሉ። በቅኝ ግዛት ያሉትን የመጀመሪያ ዓመታት ችግር

ለመወጣት የርሳቸው ቅን አስተሳሰብና ውሳኔ እረድቷል።

የመጀመሪያዎቹ የሰፈራ ዓመታት ከባድ ሥራዎች በወንጀለኛ

የጉልበት ሀይል ተፈጽሟል። ወንጀለኞቹ በጣም ካልሠሩ ወይም

ክሥራ ካፈገፈጉ ወይም ከሰከሩ ይገረፉ እንደነበር ነው። ከባድ

ወንጀል ከፈጸሙ ወደ በርሀ የሰፈራ ቦታ ይላካሉ ወይንም

ይታነቃሉ። የእስር ጊዚያቸውን ያጠናቀቁ ወንጀለኞች በማህበረሰቡ

ውስጥ ገብተው ለመሥራትና ቤተሰብ ለመመስረት ነጻ ናቸው።

የኒው ሆላንድ አበል ታስማን/Abel Tasman’s ማፕ/ካርታ፣ 1644 ዓ.ም

56

የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን