Australian citizenship test book - Ahmaric
Australian citizenship test book - Ahmaric
Australian citizenship test book - Ahmaric
Create successful ePaper yourself
Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.
ከአውሮፓ ሰፈታ በኋላ የአገር ተወላጁ ህዝብ

በአውስትራሊያ ውስጥ የአውሮፓ ሰፋሪዎች መምጣት ሲጀምሩ

በግምት ከ750 000 እስከ 1.4 ሚሊዮን የሚሆን የአቦርጂንና

የቶረስ ስትሬት አይላንደር ህዝብ ነበር። ቁጥራቸው እስከ 250

ነብስወከፍ አገሮችንና ከ700 በላይ የቋንቋ ቡድኖችን ያካተተ

ነበር።

በአውስትራሊያ መጀመሪያ ሰፈራ ሲካሄድ በብሪቴን መንግሥትና

በአቦርጂናል ህዝብ መካከል ስምምነት አልተደረገም። የአገሬው

ተወላጅ ህዝብ የራሱ የሆነ ኢኮኖሚ እንዳለውና የጥንት

ግንኙነታቸው ከመሬት ጋር የተያያዘ ነው። መንግሥት ይህንን

ግምት ውስጥ ማስገባት አልቻለም ምክንያቱም በአውሮፓ ውስጥ

የዚህ ዓይነት እምነት ስልት ባለመኖሩ ነው። የአቦርጂናል ህዝብ

ሰብል አያበቅሉም ነበር ወይም እንደ ብሪቴን በአንድ ቦታ

ተረጋግቶ ለመኖር ቤት ስለማይሠሩ፤ ስለዚህ ባለንብረት ስለመሆን

ግድየለሽ እንደሆኑ ይገምታል። መንግሥት መሬቱን ከነሱ

ለመውሰድ የሚሰጋ ነገር የለውም።

አደገኛ ግጭት

ቀደም ሲል የነበረው ገዥ መደብ አቦርጅናልን ላለመጉዳት ይናገር

ነበር፣ ነገር ግን የብሪቴን ሰፋሪዎች አቦርጅናል በሚኖሩበት መሬት

ላይ በመግባት ለብዙ የአቦርጂናል ህዝብ ሞት ምክንያት ሆኗል።

ብዙ ጊዜ ሰፋሪዎች ይህንን ወንጀል ሲፈጽሙ አይቀጡም ነበር።

አንዳንድ የአቦርጅናል ሰዎችና የአውሮፓ ሰፋሪዎች ሰላማዊ በሆነ

አብረው መኖር ይችሉ ነበር። አንዳንድ ሰፋሪዎች በበግን ከብት

እርባታ ሥራ ለአቦርጂናል ይቀጥርራል። ገዢ ማኳሪ/Macquarie

ለአቦርጂናል ህጻናት የሚሆን ትምህርት ቤት ለማሠራት

የራሳቸውን የእርሻ መሬት ለአቦርጂናል አበርክተዋል። ስለዚህ

ጥቂት የአቦርጂናል ሰዎች እንደ ሰፋሪዎች አኗኗር ዘዴ ለመኖር

ይፈልጋሉ። የራሳቸውን ባህልና ልምድ ማጥፋት አይፈልጉም ነበር።

በመሬት ላይ አለመስማማት ጦርነት ምን ያህል የአቦርጂናል

ሰዎች እንደሞቱ አናውቅም፣ ስለዚህ በብዙ መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ

አቦርጂናል እንደተገደሉ ነው። ለአብዛኛው የአቦርጂናል ሞት

መንስሄ በሽታዎች እንደነበሩና እነዚህም በአውሮፓኖች ወደ አገሪቷ

የገቡ በሽታዎች ናቸው። የአቦርጅናል ሕይወት ማለፍ ከፍተኛ ኪሳራ

ነበር። በ1830ዎቹ በቪክቶሪያ ውስጥ የአቦርጂናል ህዝብ ብዛት

ወደ 10 000 ህዝብ ነበር። በ1853 ዓ.ም ውስጥ የአቦርጂናል

ህዝብ ሲቆጠር 1907 ብቻ ነበር።

ታሪካዊ ድርጊቶች

በአገር ውስጥ ጥናት

መጀመሪያ ቅኝ ገዝዎች በኒው ሳውዝ ዌልስ ውስጥ ከባድ ችግር

አጋጥሟቸዋል። በአውስትራሊያ በጣም ጥቂት መሬት ነው ለም

አፈር። አቦርጂናሎች በዚህ አካባቢ ያለውን ሁኔታ ለማስተናገድ

ተምረዋል እንዲሁም በድርቅ ወቅት በጣም ተሰቃይተዋል።

በስይድነይ ሰፋሪዎች ካጋጠማቸው የመጀመሪያ ችግር በ50 ኪ.ሜት

ርቀት ያለን ተራራማ መሬት ወደ ምዕራብ ስይድነይ የሚወስደውን

ብሉ ማውንቴንስ/Blue Mountains ማግኘት ነበር። በ1813

ዓ.ም ሶስት ወንዶች፣ ማለት ብላክስላንድ/Blaxland፣ ወንትዎርዝ/

Wentworth እና ላውሶን/Lawson የተባሉት መጨረሻ ላይ

ተራራዎችን አቋረጡ። በBlue Mountains ማዶ የነበረው

አሁንም መስመሩን የተከተለ መኪና መንገድና ባቡር ሀዲድ

ይገኛል።

በነዚህ ተራራዎች ማዶ ላይ ተማራማሪዎች ለበግና ከብት ማርቢያ

የሚሆን ጥሩ ስክፍት የሆነ የገጠር መሬት እንዳገኙ ነው። ከዚያ

ቀጥሎ የደረሱበት መሬት ደረቅ፣ በርሀማ የገጠር ቦታ ነበር።

ለመኖር ውሀ ማግኘት እንደተቸገሩና በቂ የሆነ ምግብ መሸከም

እንዳልቻሉ ነው። የጀርመን ተወላጅ የሆኑት ተመራማሪ፣ ሉድዊግ

ሌችሀርድት/Ludwig Leichhardt, በ1848 ዓ.ም ከምሥራቅ

ወደ ምእራብ ያለውን አህጉር ለማቋረጥ ሲሞክሩ ጠፍተዋል።

በ1860 ዓ.ም ቡርክ/Burke እና ዊልስ/Wills ከመልበርን

ተነስተው ከደቡብ ወደ ሰሜን አውስትራሊያ ለማቋረጥ እቅድ

አወጡ። ብዙ የጉዞ ቡድኖችን እንደመሩ ሲሆን ነገር ግን

ለማቋረጥ በጣም እንደተቸገሩ ነው። ቡርክ/Burke እና ዊልስ/

Wills የጫካ ኑሮ ልምድስ አልነበሩም። ከአቦርጂናል

ያንድሩዋንድሃ/Yandruwandha ሰዎች የኤክስፐርት እርዳታ

አግንተዋል ነገር ግን ሁለቱም ተማራማሪዎች ሲመለሱ በመንገድ

ላይ ሞተዋል። ምንም እንኳን ቡርክ/Burke እና ዊልስ/Wills

የጉዟቸው ሁኔታ ባይጠናቀቅም ታሪካቸው በስነ-ጥበብና ጽሁፍ

ሲታወስ ይኖራል። የመሬታችን አስቸጋሪነት በዚህ አሳዛኝ ምሳሌ

ይታወቃል።

ቡርክ/Burke እና ዊልስ/Wills በአውስትራሊያ ዙሪያ የአሰሳ ጉዞ፣ 1860 ዓ.ም

58

የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን