Australian citizenship test book - Ahmaric
Australian citizenship test book - Ahmaric
Australian citizenship test book - Ahmaric
Create successful ePaper yourself
Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.
ታላቅ የኢኮኖሚ ውድቀት፡ 1929 – 1932

ይህ ለአውስትራሊያ ህዝብ ከባድ ችግር የተከሰተበት ጊዜ ነበር። የኒው ዮርክ/New York የሽያጭ ገበያ ሲወድቅ በተመሳሳይ ጊዜ

አብሮ የጀመረ ሲሆን ነገር ግን ለዚህ የኢኮኖሚ ማሽቆልቆል ሌሎች ምክንያቶች ነበሩ። እነዚህም የኤክስፖርት ዋጋና ሽያጭ መቀነስ፣

በውጭ አገር ብድርና ለህንጻ የሚወጣ ብጀት ብበንግሥት መቀነስን ያካትታል። በ1932 ዓ.ም አጋማሽ ላይ ከመቶ 32 እጅ የሚሆነው

አውስትራሊያዊ ሥራ አልነበረውም።

በኢኮኖሚ ውድቀት ምክንያት የአውስትራሊያ ሕብረተሰብ በጣም

አውድሞት ነበር። ብዙ ሰዎች ያለሥራና ያለ ቋሚ ገቢ መጠን

ቤታቸውን እንዳጡ ነው። የጤንነት ሁኔታ ባልተጠበቀ ወይም

ማሞቂያ በለለበት ጊዚያዊ መጠለያ እንዲኖሩ ተገደዋል። አንዳንድ

አባቶች ቤተሰባቸውን ትተው ወጥተዋል ወይም ወደ አልኮሆል ተገዥ

ሆነዋል። ህጻናት ለሥራ ሲሉ ትምህርት ቤት በ13 ወይም 14

ዓመት እድሜ አቁመዋል። ብዙ ስቶች መሰረታዊ በሆኑ ሥራዎች

ላይ ተሳትፈዋል እንዲሁም ልጆችንና ቤታቸውን በርሳቸው

ተንከባክበዋል።

በአውስትራሊያ የኢኮኖሚ ውድቀት በሚከሰትበት ጊዜ መንግሥት

ማእከላዊ የሆነ የሥራ አጥ ፕሮግራም አልነበረውም። እርዳታ

ከሚያደርጉ ድርጅቶች ባሻገር አንዳንድ የግል ድርጅቶች፣

ድሀ የሆኑ ሰዎች በሥራና ሰራተኛ ፕሮጀክቶችና በህዝባዊ ሥራ

ፕሮጀክቶች ላይ ይመኩ ነበር።

በ1932 ዓ.ም ኢኮኖሚው በብዙ መልኩ ሲሻሻል ነገር ግን

የቤተሰብ ጉዳት ሊያገግም አልቻለም። በታላቁ የኢኮኖሚ ውድቀት

ጊዜ የአውስትራሊያ በጎ አድራጊ ድርጅቶችና በፈቃደኛ ሠራተኞች

የተደረገ ጠቃሚ ድርሻ የሚደነቅ ነበር።

በኢኮኖሚ ውጥረት ጊዜ በኩሽና ሾርባ

ሰር ቻርለስ ኪንግስፎርድ ስሚዝ/Sir Charles Kingsford Smith (1897 – 1935)

ሰር ቻርልስ ኪንግስፎርድ ስሚዝ የተባሉት ደፋር አይሮፕላን አብራሪ፣ የበረራ አሳሽና የአውስትራሊያ

ጀግና ሰው ነበሩ።

በአንደኛ ዓለም ጦርነት ቻርልስ ኪንግስፎርድ ስሚዝ በጋሊፖሊ የተዋጉ እና ከብሪቴን የሮያል በራሪ

ብርጌድ ጋር ሆነው በረራ አካሂደዋል።

ከካሊፎርኒያ ተነስተው የፓስፊክ ውቂያኖስን አቋርጠው ኩዊንስላንድ በ1928 ዓ.ም መድረስ የመጀመሪያ

ታላቁ ስኬታማ ኣብራሪ ነበር። አይሮፕላናቸው ደቡባዊ ክልልን በማቋረጥ አውስትራሊያ ውስጥ ሲደርሱ

አንጠረኛ የሆኑ ጀግናቸውን በእልልታ ለመቀበል 25 000 ታማኝ ህዝብ ተገንቷል። በ1932 ዓ.ም በበረራ

አሳሽ ስይንስ የተመሰገኑ አገልጋይ ነበሩ።

በ1935 ዓ.ም ሳይታሰብ ከኢንግላንድ ወደ አውስትራሊያ ሲበሩ አይሮፕላናቸው እንደወደቀና እንዳልተገኙ

ነው።

ሰር ቻርልስ ኪንግስፎርድ ስሚዝ የዓለም ታላቁ የበረራ ሊቅ ይባሉ እንደነበርና በኢኮኖሚ ውጥረት ጊዜ ለህዝብ በመስጠት ትክክለኛ

የአውስትራሊያ ጀግና በመሆናቸው ሲታወሱ ይኖራሉ።

ክፍል 5 – የአውስትራሊያችን ታሪክ 65