Australian citizenship test book - Ahmaric
Australian citizenship test book - Ahmaric
Australian citizenship test book - Ahmaric
You also want an ePaper? Increase the reach of your titles
YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.
በበረዷማ ተራሮች የሀይድሮ ኤሌትሪክ አሰራር

እንደ በራስ መመራት፣ የመድብለ ባህላዊና በሀብት የበለጸገች አገር መሆን ለአውስትራሊያ ማንነት መግለጫ ጠቃሚ ምልክት ነው።

በአውስትራሊያ ውስጥ ይህ ትልቁ የኢንጅነሪንግ ፕሮጀክት ነው። እንዲሁም በዓለም ላይ ካሉት ትላቅ የሀይድሮ-ኤሌትሪክ ሥራ አንደኛው

ይሆናል።

በኒው ሳውዝ ዌልስ እና ቪክቶሪያ ባለ መሬት ላይ የእርሻ ኢንዱስትሪዎች ጠቃሚ የውሀ አቅርቦት በዚህ አሰራር ይቀርባል። እንዲሁም ከመቶ

10 እጅ የሚሆነው የኒው ሳውዝ ዌልስ ኤሌትሪክ ፍጆታ በዚህ ሀይል ማመንጫ ጣቢያዎች ይቀርባል።

የበረዷማ ተራራዎች አሰራር፣ ከመቶ 2 እጅ ብቻ በመሬት ላይ ይታያል። በዚህ አሰራር ላይ 16 ዋና ግድቦች፣ ሰባት የሀይል ማመንጫ

ጣቢያዎች፣ የማጣሪያ ጣቢያና 225 ኪሎ ሜትር መተላለፊያ ቀዳዳዎች፣ የቧንቧ መስመሮችና የውሀ ቧንቧዎች ይካተታሉ።

የአሰራር ዘዴው በ1949 ዓ.ም ጀምሮ በ1974 ዓ.ም አለቀ። ከ30 አገሮች በላይ የመጡና ከ100 000 በላይ ሰዎች በፕሮጀክቱ ላይ

ሠርተዋል። ከነዚህ ሠራተኞች ውስጥ ከመቶ ሰባ እጅ መጤ ስደተኞች ነበሩ። ፕሮጀክቱ ካለቀ በኋላ አብዛኞቹ አውሮፓውያን ሠራተኞች

በአውስትራሊያ ለመኖር እንደቀሩና ለአውስትራሊያ መድብለ ባህላዊ ሕብረሰተስብ ጠቃሚ አስተዋጽኦ እያደረጉ ነው።

የበረዷማ ተራራዎች አሰራር በኒው ሳውዝ ዌልስ፣ በኮስኩዝኮ ብሄራዊ መናፈሻ/Kosciuszko National Park ውስጥ ይገኛል። ፕሮጀክቱ

በአካባቢ ስለሚያስከትለው ችግር በቅርበት ክትትል ይደረጋል። የዚህ አሰራር ጥሩነት በአሁኑ ጊዜ በአንዳንድ ቦታዎች የበረዷማ ወንዝ/

Snowy River ቀደም ሲል ከሚሸከመው ውሀ ከመቶ 1 እጅ ብቻ ይሆናል።

ለጥሩ የአካባቢ ጥበቃ ሲባል ከመቶ 28 እጅ የሚሆነውን የወንዝ ፍሳሽ ለማጠራቀም የቪክቶሪያና የኒው ሳውዝ ዌልስ መንግሥታት

ተስማምተዋል።

በበረዷሟ ተራሮች ሥራ የተሰማሩ ሠራተኞች

68

የአውትራሊያ ዜግነት: የጋራ መተሳሰሪያችን