24.07.2013 Views

ምንጭ - Ethiopia: A voice for the voiceless

ምንጭ - Ethiopia: A voice for the voiceless

ምንጭ - Ethiopia: A voice for the voiceless

SHOW MORE
SHOW LESS

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.15

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ ጥቅምት 28 ቀን 2004 ዓ.ም.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.15

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ ጥቅምት 28 ቀን 2004 ዓ.ም.

ዋጋ 5:00

“ቻይናውያን ሕገ-መንግሥታችሁንም

የአዋጅ ሕጋችሁንም አናውቅም ብለዋል” 6

አቶ ኩራባቸው ፍቅሩ ገ/ማርያም የዋልዳ ሆጀቶታ ዳንዲ ደራርቱ አርሲ

“ከሲኦል ያመለጡ” ወጣቶች በግልፅ ይናገራሉ፡፡ ከእስር እንደተፈታ ሰው ነው ራሳቸውን

የሚቆጥሩት፡፡ በየአደባባዩም “እንኳን ደስ ያለህ/ያለሽ!” ሲባባሉ ይሰማል፡፡ በተለይም

በየወሩ ከደመወዛቸው የሚቆረጠው ገንዘብ፣የጋዜጣና የመፅሄት ክፍያ በአባላቱ ቋንቋ

“የማይደርስ ዕቁብ” የሚሉት የድርጅቱ ክፍያ፣የልማት (....) መቶ ፕርሰንት መዋጮ እና . . .

9

አንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ም/ቤት መደበኛ

ስብሰባውን አካሄደ

የደብረብርሃን ከንቲባና

ባለሥልጣናት በሙስና

ተጠርጥረው

መታሰራቸው ተገለፀ

የዞኑ ደን ልማት ሽያጭ መነጋገሪያ ሆኖአል::

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን

ሸዋ ዞን ዋና ከተማ የሆነችው ደብረ ብርሃን

ከተማ ከንቲባ የሆኑት “አቶ ስዩም ተፈራና

በመሬት አስተዳደርና በልዩ ልዩ የሥራ ኃላፊነት

ላይ የነበሩት የዞኑ ከፍተኛ ባለሥልጣናት

ከሙስና ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በእስር ላይ

እንደሚገኙ...

11

ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ነፃ የሞያ

ማህበራት ያስፈልጋሉ!

የኢንዱስትሪ ሰላምን በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ ጊዜያዊ ሠላምና ዘላቂ ሠላም ናቸው፡፡ ጊዜያዊ

የኢንዱስትሪ ሠላም የማስመሰያ /አሳሳች/ ሠላም ነው፡፡ የሠራተኛውን ልብ ያልገዛ /የሠራተኛውን ጥቅም

ያልጠበቀ/፣አስተማማኝና ዘላቂ ልማትን የማያመጣ ሠላም ነው፡፡ የመፍጠር ችሎታን የማያበረታታና

ምርታማነትን የማያሳድግ ሠላም ነው፡፡ ዘላቂ የኢንዱስትሪ ሠላም ግን የሠራተኛውን ጥቅምና መብትን

የሚያስከብር፣በሠራተኛው ውስጥ በራስ መተማመንንና መረጋጋትን የሚፈጥር፣የሠራተኛውን የኃላፊነት

ስሜት የሚያስከብር ነው፡፡ ሊኖር የሚገባው ጊዜያዊ ሳይሆን ዘላቂ የኢንዱስትሪ ሠላም ነው፡፡ በሀቅ ላይ

የተመሠረተ ከሆነ የኢንዱስትሪ ሠላም ጥሩ ነው፡፡ ሠላም የሕይወትና የንብረት ዋስትና ይሰጣል፡፡ ሠላም

ካለ ልማትና እድገት አለ፡፡ ሠላም ካለ ቤተሰብ በሰላም ወጥቶ ሠርቶ ይገባል፡፡ ሠላም ከሌለ ሁሉም

የለም፡፡ ዛሬ ያለው ሰላም ግን ምን ዓይነት ሠላም ነው? መብትና ጥቅምን የገፈፈ ሠላም፤የታፈነ ሠላም፤

በቁጭትና በዝምታ የታጀበ ሠላም፤ በፍርሃት የታጨቀ ሠላም፤አደጋን ያረገዘ ሠላም! እንዲህ ዓይነት ሠላም

ውጤቱ የከፋ ስለሚሆን አደጋ ነው፡፡ ጊዜውን ጠብቆ የሚፈነዳ ሠላም አንሻም፡፡ ጥፋትን በውስጡ አምቆ

የያዘ “ሠላም” አያሻንም...

4

በጂማ ከተማ የተቃጠለው ውሃ ልማትና ዐቃቤ

ህግ ጽ/ቤት አነጋጋሪ መሆኑ ተገለፀ

11

15

1

የሠራተኞችን ደሞዝ

ለመቀማት ሲል 3ሰው ገድሎ

2 ሰው ያቆሰለው ፖሊስ

በቁጥጥር ሥር ዋለ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን

የምትገኝኘው የያያ ወረዳ አስተዳደር ሠራተኞች

የጥቅምት ወር ደሞዝ ለመዝረፍ ሦስት ሰው

ገሎ ሁለት ሰው ያቆሰለው የወረዳው ፖሊስ

በቁጥጥር ሥር መዋሉን የዜና ምንጮቻችን

በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ገለጹ፡፡ እንደ

ዜና ምንጮቻችን ገለጻ ከሆነ “ጥቅምት 20

ቀን 2004 ዓ.ም አንድ ሚሊዮን ብር ይሆናል

የሚባለውን የወረዳውን የመንግስት ሠራተኖች

ደሞዝ ለማምጣት ከወረዳው ፍቼ ከተማ ንግድ

ባንክ ይመጣሉ፡፡ ግንዘቡን ለማምጣት የመጡት

ሦስት ሠራተኞች አንድ ፖሊስና አንድ ሹፌር

በጠቅላላ አምስት ሰዎች ....

11

www.andinet.org.et

2

www.andinet.org.et

የሙስና መስፋፋት

በአንድ አገር ውስጥ በጥቅም ላይ

ሊውል የሚገባውን መዋዕለ-ንዋይ

(Investment) ይሸረሽረዋል። የውጭ

አገር ከበርቴዎችንም ቢሆን በዚያ አገር

የመዋዕለ-ንዋይ (Foreign Investment)

ተግባር እንዳይሳተፉ ተጽዕኖ ያሳድራል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ጥናቶች ያደረጉ

ተመራማሪዎች ሲገልጹ “አንዳንድ

ባለሃብቶች ወደ አንዳንድ አገሮች፤

በተለይም ወደ አፍሪካ አገሮች ውስጥ

ከሚያስገቡት የውጭ ምንዛሬና መዋዕለ-

ንዋይ ይልቅ ከነዚህ አገሮች ወደ ሀብታም

አገሮች በስርቆት መልክ የሚወጣው

የውጭ ምንዛሬ ይበልጣል” ይላሉ።

(ለምሳሌ በቅርቡ የአለም ባንክ ያወጣው

ጥናታዊ ጽሁፍ ከኢትዮጵያ ተመዝብሮ

ወደ ውጭ ሀገር እንዲሸሽ የተደረገው

ሀብት/ገንዘብ እስከ 11 ቢሊዮን ዶላር

እንደሚደርስ አሳይቷል። የተባበሩት

መንግሥታትም እንደጎርጎረሳውያን

አቆጣጠር ከ1990 ዓ/ም ጀምሮ

ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ ሀገሮች ተዘርፎ

የጎረፈው ሀብት ከ8.3 ቢሊልዮን ዶላር

እንደማያንስ አሳይቷል።) አንዳንድ

አበዳሪዎችም በተመሳሳይ ሁኔታ “ያገር

መሪዎች የሃገራቸውን ሃብት ወደውጭ

የሚያሸሹ ከሆነ እኛ ምን ቸግሮን ነው

ወደነዚህ አገሮች መዋዕለ-ንዋያችንን

የምናስገባው?” የሚል ጥያቄ ያነሳሉ።

ለአብነት ለመጥቀስ ያህል በ1997

ዓ/ም በኢትዮጵያ የተካሄደው ምርጫ

በህወሓት/ኢሕአዴግ ከከሸፈ በኋላ

ከኢትዮጵያ ወደ እንግሊዝ አገር የጎረፉት

ሃብቶች በጣም በዝተው እንደነበር

አንዳንድ የእንግሊዝ የዜና ማሰራጫዎች

አጋልጠዋል። በዚያው ሰሞን ሰሚ ያጡ

አቤቱታዎች ከተለያዩ አቅጣጫዎች

መነሳታቸው አልቀረም። ለምሳሌ እ.ኤ.አ.

በ1997 World Development Report

በተባለው መጽሄት ታትሞ የወጣው

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ ጥቅምት 28 ቀን 2004 ዓ.ም.

ጥናት ሲያመለክት እንደ ኢትዮጵያ

በሙስና የተዘፈቁትና ሙስና ያላጠቃቸው

አገሮች ሲወዳደሩ ሙስና ያጠቃቸው

አገሮች በእድገት ወደ ኋላ መቅረታቸውን

ዘግቧል፡፡ እንዲሁም በዚሁ አመት

(National Bureau of Economic

Research) ተብሎ በሚጠራው ጥናታዊ

መጽሄት ያወጣው ጥናት እንደዘገበው

ይህ ሁኔታ በሩቅ ምስራቅ የእስያ አገሮች

እንደተከሰተ ዘግቧል።

ሙስና እንደ ተጨማሪ

ታክስም ስለሆነ የግል ተቋሞችና

ኩባንያዎች እንዳያድጉ ያደርጋል።ሙስና

በግል ተቋማትና በግለሰቦች መካከል

መኖር የሚገባውን ጠቃሚ ውድድር

ይቀንሳል፤ያጫጫል።

ሙስና በጣት የሚቆጠሩ

ሰዎች ብቻ ካለመጠን እንዲከብሩ

ያደርግና በሃብታምና በድሆች መካከል

ልዩነቶችና ቅራኔዎች ያስነሳል። ቅራኔው

ሲገፋም ሀብታሞች ሕጋዊ ባልሆነ መልክ

ያካበቷቸውን ሃብቶች ወደ ሌላ አገር

እንዲያሸሹ ይገፋፋል። ይኸው ድርጊት

በበኩሉ አገር ያራቁታል። ለምሳሌ የዛዬሩ/

የኮንጎው ሞቡቱ ሴሴኮና የፊሊፒኑ

ፈርድናንድ ማርቆስ በሥልጣን ላይ

በነበሩበት ወቅት ያካበቷቸውና በውጭ

አገር ባንኮች ያስቀመጧቸው ንብረቶች

በብዙ ቢሊዮን ዶላር ይቆጠሩ ስለነበር

ዛዬርም/ኮንጎም ሆነች ፊሊፒንስ ለብዙ

ዓመታት የተከማቸባቸውን የውጭ

ብድር በገዛ መሪዎቻቸው የተሰረቀው

ገንዘብ ብድራቸውን ሁሉ ከፍሎ ከዕዳ ነጻ

ሊያደርጋቸው እንደሚችል ተዘግቧል።

ሙስና በአንዲት አገር ውስጥ

የሚገኝን ሕጋዊና ትክክለኛ የንግድ ተግባር

ያዛባል። የፍጆታ ዕቃዎች ትክክለኛ

ዋጋ በተስተካከለ መልክ እንዳይተመን

ያደርጋል። የሸቀጥ እቃዎች እንዲያንሱ

ወይም እንዲጠፉ፤ ብሎም በጓዳ በር

እንዲሸጡ መንገድ ይከፍታል። ዋጋቸው

እንዲንር ያደርጋል፤ ቀስ በቀስም የፍጆታ

ዕቃዎች ዋጋ በጣም ከፍ ይልና ህዝብን

ያስቆጣል። በመንግስትና በነጋዴዎች

መካከል አስፈላጊ ያልሆነ ጠብ እንዲፈጠር

ያደርጋል። ባገራችንም ሆነ በሌሎች

አገሮች እንደተከሰተው፤ መንግስት ነኝ ባዩ

የራሱ መመሪያና ተግባር በፈጠረው ችግር

ነጋዴዎች እንዲከሰሱና እንዲቀጡም

ያደርጋል። በዚህ ምክንያት እንግልት፣

እስርና ግድያ ሊከተል ይችላል። የፍጆታ

ዕቃዎች ዋጋዎች ከፍ ሲሉ የፍጆታ

ዕቃዎቹን ሊያገኙ የሚችሉ ሃብታሞችና

ከነሱ ጋር ግንኙነት ያላቸው እንዲሁም

ከሻጮች ጋር ዝምድና ያላቸው ብቻ

ናቸው። ለዘመድና ለጓደኛ ብቻ መሸጥ

ይመጣል። ሻጮች ዋጋ ከፍ አድርገው

ለዘመዶቻቸውና ለጓደኞቻቸው ብቻ

የመሸጣቸው ምክንያትም ለመንግስት

አያጋልጡንም በሚል አስተሳሰብ

ነው። ተራው ዜጋ በተለይም ድሀው

የሕብረተሰብ ክፍል ግን ቁሳቁሶቹን

እንዳያገኝ የገንዘብ አቅሙ የማይፈቅድለት

በመሆኑ እንዲሁም ከሀብታሙም ሆነ

ከሻጩ የሕብረተሰብ ከፍል ጋር የጠበቀ

ግንኙነት ስለማይኖረው ሁሌም ተጎጂ

ነው። እኒህን ዓይነት የሙስና ገጽታዎች

በኢትዮጵያችን በጣም የተንሠራፉ

ስለሆኑ ባንዳንድ ሰዎች አገላለጽ “በአገሪቱ

ውስጥ ዛሬ የሚካሄደው ንግድ ከማፍያ

ድርጊት የማይተናነስ ነው” ብለው

እንደነ ሪፖርተር ያሉ ጋዜጦች ጭምር

ያስገነዝባሉ። በማፍያ መልክ የሚሰራው

ወንጀላዊ የንግድ አሠራር ከመብዛቱም

የተነሣ በድብቅ መነገድና የጥቂቶች ብቻ

መጠቃቀም ባህል ይሆናል፤ ኮንትሮባንድ

ይስፋፋል፤ ዝርፊያ ይጧጧፋል፤

ወንበዴዎች ይፈጠራሉ፤ ይባስ ብለውም

ወንበዴዎች የራሣቸውን ኬላ ይፈጥራሉ፤

እንዳሻቸው ይዘርፋሉ። የሚያሳዝነው ግን

እነዚህን የመሰሉ ክስተቶች በአገራችን

በሰፊው እየታዩ መሆናቸው ነው።

ዳሰሳ

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.15

የሙስና መስፋፋት በኢኮኖሚ፤በፖለቲካና በማህበራዊ ኑሮ

ፕሮፌሰር ሰይድ ሐሰን

መሪ ስቴት ዩኒቨርስቲ (አሜሪካ)

ካለፈው የቀጠለ

ዘርፍ የሚያስከትለው ችግር

ሙስና ሰዎች በትጋት ሰርተው

ሃብታቸውን እንዳያዳብሩ፤ ቤታቸውን

እንዳያቀኑና አገራቸውን እንዳይገነቡ፤

ባንፃሩ ግን ባቋራጭ የመክበር

ፍላጎታቸው እንዲያድግ ያደርጋል። ዜጎች

ለምርት ያላቸውን ዝግጁነት ይቀንሳል

(It distorts incentives)። ይህ

የሚሆንበት ምክንያቱ ብዙ ነው። ለምሳሌ

በበርካታ አገሮች ውስጥ እንደታየውና

እንደተከሰተው፤ ከሙስና ጋር የተሳሰሩ

ድርጅቶችና የንግድ ተቋማት በመልካም

መንገድ ሰርቶ መክበር አይችሉም።

ሁሌም በሙስና መክበርን የሚመርጡ

ናቸውና። ይህ ደግሞ ባኳያው በትክክልና

በመልካም መንገድ ሥራቸውንና

ሃብታቸውን ለማቃናት የሚጥሩትን ተስፋ

ያስቆርጣል። ቀስ በቀስም በመልካም

መንገድ የሚያካሂዱትን ሥራቸውን

ለቀው ወደመጥፎ ጎዳና እንዲገፉ

ይገደዳሉ፤ ብሎም እነሱም እንደሌሎቹ

ጥቂት ገፋፊዎች በሙስናው እንዲሳተፉ

ይገፋፋሉ። ይህ የስነ-ልቦና ለውጥ እያደር

ለእንያንዳንዱ ዜጋ ይደርሰውና ቀስ በቀስ

አገርና ዜጎች በሙስና ይጠመዳሉ።

ቀደም ሲል ለመጠቆም

እንደተሞከረው በታዳጊ አገሮች ብዙ

መዋዕለ ንዋይ የለም፤ ይባስ ብሎ ያሉትም

ሲዘረፉ ደግሞ አገሮቹ ለበለጠ ድህነት

ይዳረጋሉ። ያገሮቹ ጥቂት ሃብቶች

ወደተወስኑ ግለሰቦችና ድርጅቶች

ወይም ቡድኖች ሲገቡ ደግሞ ያላግባብ

በከበሩ ቡድኖችና በተራው ዜጋ መካከል

መቃቃር ከመከተሉም በላይ የሀብቱ

ልዩነት ይራራቅና ለግጭትና ለብጥብጥ

ይዳርጋል። ይህ ሲሆን በሙስናና

በብልጣብልጥነት የከበሩት አላግባብ

መክበራቸውን ስለሚያውቁ አንደኛ

ሃብታቸውን ሁለተኛ ራሳቸውንም

ወደ ውጭ ማሸሽ ይከተላል። ይህ

ተግባር በብዙ አገሮች ውስጥ የተከሰተና

በኢትዮጵያችንም እያቆጠቆጠ ያለ አስፈሪ

ክስተት ነው፤ መባባሱም አያጠራጥርም።

በስልጣን የሚባልጉ

ባለስልጣናትና የሙስና ተባባሪዎቻቸው

ሃብት የሚያካብቱት ባቋራጭና በፍጥነት

ስለሆነ፤ በፋሲካ የተዳረች ሁሌም ፋሲካ

ይመስላታል ነውና፤ ሃብት ሁሉ በዚሁ

መልክ የሚገኝና ምንጊዜም ሊተካ የሚችል

አድርገው ስለሚቆጥሩ በፈጠነ መልክ

ሃብታቸውን እንዲያባክኑ ይገፋፋሉ፤

ይታለላሉ። ባጭር ጊዜ ውስጥ ያገር

ሃብት የሚወድምበት አጋጣሚ ተፈጥሮም

ሃገርና ዜጋ ያለረዳት ይቀራሉ።

ብዙውን ጊዜ በሙስና

የተበከሉ ሰዎች በሕገ-ወጥ መልክ

ያካበቱትን ሀብት የሚያውሉት በድሎትና

በቅምጥል (luxury) ዕቃዎች ላይ ነው።

ከሚገዟቸው ቁሳቁሶች መካከልም፤

ውድ የሆኑ መኪኖች፤ ጌጣጌጦች፤

የቤት ማስጌጫዎች፤ መጠጥና ልብሶች

ተጠቃሾች ናቸው። እንደነዚህ ያሉ

እቃዎችም ባንድ በኩል አላቂና ግላዊ

ስለሆኑ ላገር የሚያስገኙት ጥቅም እጅጉን

ውሱን ነው። የቁሳቁሶቹ ዋጋ ከሌሎች

ቁሳቁሶች ጋር ሲወዳደር ከፍ ስለሚልም

የተገዙበት ንዋይ ተቀማጭ ወይም ታሳሪ

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.15

ዳሰሳ

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ ጥቅምት 28 ቀን 2004 ዓ.ም.

እንጂ ተንቀሳቃሽ ወይም በሃገር ኢኮኖሚ

ውስጥ ተዘዋውሮ ተነግዶበት ለትርፍ

የሚያበቃ አይደለም። በሌላ በኩል ይህ

የተወሰነው የሙስና ተሳታፊ የህብረተሰብ

ከፍል ብዙውን ጊዜ በውድ ቁሳቁሶችና

ጌጣጌጦች በማሸብረቅ ፉክክር ተጠምዶ

ስለሚቀር ለአጓጉል ባህል መጸነስ ምንጭ

መሆንም ይንጸባረቅበታል።

በርከት ያሉ ጥናቶች

እንዳመለከቱትም ቀልጣፋ ያልሆኑትንና

ውጤታማ ያልሆኑትን (inefficient)

ድርጅቶችን፤ አምራቾችንና ግለሰቦችን

የበላይነት እንዲኖራቸው በማድረግ አገር

ወደ ኋላ እንድትጎተት ያደርጋል።

ሙስና የሕብረተሰብን ንብረት

ወስዶ ለግለሰቦች ያስረክባል። ይህንን

በማድረግም ከሁሉም ይበልጥ የድሀውን

የህብረተሰብ ክፍል በበለጠ ይጎዳል።

ከመንግስት ባለስልጣኖች ጋር ግንኙነት

ያላቸው በሙስና የተዘፈቁት ግለሰቦች

የሕዝቡን ሀብት ለግላቸው ሲያውሉት

የትምህርት ቤት ተቋማትን ለማቋቋም፤

የጤና ጥበቃ ጣቢያዎችን ለመመስረት፤

ለአዉራ ጎዳናና መንገድ ሥራው ሥራዎች፤

ለዉሃ ልማቶች፤ ወ.ዘ.ተ. ሊዉል የሚገባው

ሀብት እንዲባክን ያደርጋል።

ሙስና ከዉጭ አገር

የሚገኘውን እርዳታ ውጤተ-ቢስ

እንዲሆንና እንዲባክን ያደርጋል። ምንም

እንኳ እርዳታው የሚላከው ለድሆች

እንዲደርስ ቢሆንም፤ እርዳታው ለድሆች

እንዳይደርስ፤ በርዳታው ገንዘብ እንዲሰሩ

የተፈለጉት ተቋሞች እንዳይሰሩ ወይም

ብልሹ በሆነ መልክ እንዲሰሩ ያደርጋል።

እኔ እራሴ እንደተገነዘብኩትም፤ በገባያ ላይ

እንዳይሸጡ የተከለከሉ የርዳታ እቃዎች

ሕገ-ወጥ በሆነ መልክ እንዲሸጡ ያደርጋል።

ለዚህ ዋቢም ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ

የሚላከውን የምግብ ዘይት መጥቀስ

ይበቃል።

ፖለቲካንና መንግስታዊ አስተዳደርን

በሚመለከት (በከፊል)፤

ሙስና እየገነነ ሲመጣ በሃገር

ዕድገት መስክ ጉልህ ሚና የሌላቸው በጣም

ጥቂቶች እየከበሩ ይመጡና የመንግስትና

የሕዝብ መገልገያ በሆኑ መሥሪያ ቤቶች

በመስራት ብዙ ልምድ ያካበቱና ታማኝ

የሆኑ፤ እንዲሁም ብቃት ያላቸው

የቢሮ ሰራቶኞችን ሥራቸውን ለቀው

እንዲወጡና ቀስ በቀስ ብቃት የሌላቸው

በቦታው እንዲተኩ በር ይከፍታል።

ይህም በሕዝብ መሥሪያ ቤቶች ውስጥ

መልካም ባህርይና ችሎታ ያላቸው መሪዎች

እንዳይበቅሉ ያደርጋል፤ የሃገርን የብቁ ዜጋ

ቋት ያራቁታል። መድረሻ የለንም የሚሉ

ቢኖሩም፡፡

ሙስና ላገራቸውና

ለህዝባቸው ተግተው የሚሰሩ ዜጎችንና

ከፍተኛ የሙያ ትምህርት የቀሰሙ

ሊሂቃንን ለሀገራቸው የሚያደርጉትን

የአገልግሎት ፍላጎት የሚቀንስ ነው።

ሙስናው እየበረታ ሲሄድም የመንግስት

ሥራን እየለቀቁ፤ ለትምህርታቸው

የከፈለላችውን ህዝብ እንደማገልገል

ፋንታ፤የግል ባለህብቶችን/ኩባንያዎችን

ለማገልገል ወይም የራሳቸውን የግል ንግድ

እንዲፈጥሩ ይገፋፋል፤ያስገዳዳልም።

ብዙዎች ባልሰለጠኑበት ሙያ እንዲሰማሩ

እንደሚያስገድድም በብዙ አገሮች ውስጥ

ታይቷል። በኢትዮጵያም እንደዚሁ ባስከፊ

ሁኔታ እየተከሰተ ነው። እያደር ተስፋቸው

እየተሟጠጠ አገራቸውን ጥለው እንዲሄዱ/

እንዲሸሹ የሚገፉ ብዙዎች ለመሆናቸውም

ጥርጥር የለውም። ይህ እየበረከተ ሲሄድ

ደግሞ አገር ምሁር አልባ፤ አዕምሮ አልባ

ትሆናለች። ብዙ ሃብት ጠፍቶ የሰለጠኑ

ምሁራን ለሀብታም አገሮች ሲሳይ (braindrain)

ይሆናሉ። ድሃ አገሮች ደክመውና

ከፍለው ያሰለጠኑት አዕምሮ እየሸሻቸው፤

ያሳደጉትን መሳም ያልቻሉ ደካሞች ሆነው

እንዲታዩም ምክንያት ይሆናል። በአፍሪካ

አህጉር ኢትዮጵያና ጋና በዚህ ረገድ ቀዳሚ

ተጠቃሽ ናቸው። ቀጥተኛ የሆነ የፖለቲካ

ችግር ተጨምሮበት አገራችን ዛሬ ማቆሚያ

በሌለው መልክ የሰለጠነ የአእምሮ ሃብቷ

እየተራቆተ ነው።

በሌላ በኩል በሙስና ምክንያት

ችሎታና ብቃት ያላቸው ባለሙያዎች

ከመንግስታዊ መዋቅሮች ሲለቁ ቦታው ብቁ

ችሎታ በሌላቸው ሰዎች እንዲሞላ ግድ

ይሆናል። ይህም እየቆየ የመንግስት መሥሪያ

ቤቶች እንዲጠሉ ያደርግና ቀስ በቀስ

የመንግስት ትእዛዞች እንዳይከብሩ፤ ብሎም

መንግስት ራሱ እንዲጠላ የራሱን አሉታዊ

ሚና ይጫወታል። በህዝብ የሚጠላ

መንግስት ደግሞ ሕዝባዊ ችግሮችን ሊፈታ

የሚችል አይሆንም።

በሙስና ምክንያት ሌብነት

በዝቶ ድህነት ሲስፋፋ እያደር ዴሞክራሲም

ደብዛው ይጠፋል። ዴሞክራሲ ሲጠፋም

በኤኮኖሚ የማደግ እድል ይቀንሳል፣

በሌላ በኩል በሙስና ምክንያት ችሎታና ብቃት ያላቸው

ባለሙያዎች ከመንግስታዊ መዋቅሮች ሲለቁ ቦታው ብቁ ችሎታ

በሌላቸው ሰዎች እንዲሞላ ግድ ይሆናል። ይህም እየቆየ የመንግስት

መሥሪያ ቤቶች እንዲጠሉ ያደርግና ቀስ በቀስ የመንግስት ትእዛዞች

እንዳይከብሩ፤ ብሎም መንግስት ራሱ እንዲጠላ የራሱን አሉታዊ

ሚና ይጫወታል። በህዝብ የሚጠላ መንግስት ደግሞ ሕዝባዊ

ችግሮችን ሊፈታ የሚችል አይሆንም።

ድህነትንም ያንሰራፋል። የሰብዓዊና

ሌሎችም ዴሞክራሲዊ መብቶች መታጣት

በበኩሉ ለእርስ በርስ ጥልና ንክሻ

ምክንያት ይሆናል። ይህ የሚንጸባረቅበት

ህብረተሰብ ችግርና መከራ እንደ አዙሪት

እየተሽከረከሩበት (vicious circle)

ለመኖር ይገደዳል። ካዙሪቱም መውጣት

አስቸጋሪ ይሆናል።

ሙስና ሲስፋፋ በሥልጣን

ላይ ያሉ ግለሰቦች በሙስናው ይሰክሩና

ያጋልጡናል ብለው የሚፈሯቸውን

ለምሳሌ እንደ ነፃ ፕሬስና ሌሎችም

የሕዝብ መገናኛ ዘዴዎች ባለሙያዎችን

እንዲሁም ንቁ የህብረተሰብ ክፍሎችን

ማፈንና ማሳደድን ስራዬ ብለው ይይዛሉ።

አፋኝ የሆኑ አዳዲስ ሕጎችን እያወጡ ነጻ

አሰራሮችን ያግዳሉ፤ ጋዜጠኞችን ያስራሉ፤

ያሰቃያሉ፤ ያዋክባሉ። በዚህም የተነሳ ነጻው

ፕሬስና የሕዝብ መገናኛው መድረክ ሁሉ

እያደር እየተዳከመ የተልፈሰፈሰ ይሆናል።

ተልፈስፋሽ እንዲሆንም ፍላጎታቸውም፤

ተግባራቸውም ነው። ይኸው ድርጊት

ጠቅላላው ሕብረተሰብ እንዳያውቅ

እንዳይማርና እንዳይጠይቅ ሆኖ የሰጡትን

ብቻ ተቀባይና መስማት የተሳነው እንዲሆን

ያደርጋል። በኢትዮጵያችን ይህ እየሆነ ያለ

ክስተት ይሁን እንጂ ህዝቡ ይባስ ብሎ

ከመንግሥት ለሚተላለፉ መመሪያዎችም

ሆነ ዜናዎች ጆሮ ዳባ ልበስ ካለ ዓመታት

ተቆጥረዋል። ይልቁንም ዕውነትን

ፍለጋ በውጭ መገናኛ ብዙሃን ዘርፎች

ለመጠቀም ተገዷል። ሕዝቡ መንግሥት

ተብዬው ለሚያወጣቸው መመሪያዎች

ቁብ የለውም፤ እንዲለግም የተገደደበት

ሁኔታ ነው የሚታየው። በዚህ ዓይነትም

ፖሊሲዎች በወረቀት ላይ ብቻ ይሆናሉ።

ሕዝብና መንግስትም ሆድና ጀርባ እንደሆኑ

ይቀራሉ።

ማህበረሰባዊ ኑሮን በሚመለከት

(በከፊል)፤

ተደጋግሞ እንደተገለጸው

ሙስና እጅጉን ሲስፋፋ በመንግስት

መዋቅሮች ውስጥ የሚሰሩ በተለይም

በንቃት ሃገራቸውን ሊያገለግሉ የተዘጋጁና

ለስልጠናቸው ብዙ የተደከመባቸው

ወገኖች አእምሯቸው እንዲላሽቅ

ይደረጋል።

ሙስና በትምህርት፤ በሥራ

ልምድና በታታሪነት ኑሮን ከማዳበር

ይልቅ፤ በጓዳና ባቋራጭ መንገድ የመክበር

ፍላጎትንና፡ ስግብግብነትን የሚያበረታታ

ስለሆነ ተጎጂው ሁሌም ንቁና ሀገሩን ወዳዱ

ክፍል ነው። ሙስና ሁሉም ሊከብርና

ኑሮውን ሊያቃና የሚችልበት ሳይሆን

ጥቂቶች ያላግባብ የሚበለጽጉበት በመሆኑ

“እድሉ” ያላጋጠመው አብዛኛው ሁሌም

ብስጭት ላይ ይወድቃል። ኑሮውን

ያማርራል፤ ተስፋ የቆረጠ የህብረተሰብ

አባልን ያበረክታል። ተስፋ በቆረጠ ዜጋ

ሀገር ሊያድግ ከቶውንም አይችልም።

ሙስና በተለይ ድሆችን ጎጂ

ነው፤ ድሆች እንኳን ጉቦ የሚከፍሉት

ሊኖራቸው ቀርቶ ለራሳቸውም የሚበቃ

ሃብት የላቸውምና!

በሃይማኖት በኩልም ቢሆን፤

ሙስና ከኃጢዓት (መቅሰፍት) የሚቆጠር

እንጂ የሚያበረታታ አይደለም። በጉቦ

የተለከፈ ሕብረተሰብ ብርቱ ሞራልና

የወደፊት የረጅም ጊዜ የኑሮ ዕቅድ

የለውም፤የዛሬን የከብሮ ማደር ብቻ ቀዳሚ

ዓላማው ነውና። በሙስና የተጠመዱ ሰዎች

አእምሯቸው ሁሌም የተረበሸና በጥቅም

የተበረዘ በመሆኑ ቀስ በቀስ እንደተላላፊ

በሽታ ሌሎቹንም የሚበክሉ ናቸው።

ለዚህም ነው ሙስና እኩይ ወጥመድ

ነው የሚባለው። በሙስና የተለከፉ ዜጎች

ርህራሄ የጎደላቸውና ከምንም በላይ

ጥቅማቸውን የሚያስቀድሙ በመሆናቸው

የጋራ ሃገር ዕድገት እንቅፋቶች ናቸው።

በሙስና የተጠመዱ ሰዎች ሁሉንም

ለማግበስበስ በሚያደርጉት ሩጫ በተለይ

ድሃው የህበረተሰብ ክፍል በመንግስት

የዕለት ተዕለት አገልግሎቶች እንኳ ሳይቀር

ተጠቃሚ እንዳይሆን የሚያደርጉ ጨካኞች

ናቸው። ሙስና ራሱ ሃጢዓተኛ ነው

የሚባለውም ለዚህ ነው።

ሙስና የህብረተሰብ የእድገት

መስኮችን ሁሉ ገቺና ወደፊት የማያራምድ

ማነቆ ነው። ዕድገትን ሳይሆን ዝቅጠትን

የሚያስከትል አደገኛ የህዝብና የሃገር ነቀርሳ

ነው።

ሙስና ወንጀለኞችን

ያበራክታል፤ ብዙ ጊዜም ድሃ ዜጎች

በሕይወታቸው ደስተኝነትን በማጣት

ሳቢያ ህይወታቸውን እንዲያጠፉ ጭምር

የሚገፋፋ ነው።

3

ሙስና በሰፈነበት አገር

የኢኮኖምም፤ የፖለቲካም የማህበራዊ

ኑሮም አዳዲስ ግኝቶችና ሀሳቦች ማፍለቅ

የሚበረታታበት መድረክ ጎልቶ አይታይም።

ስለሆነም ሙስና የማህበረሰባዊ ዕድገት

ጠንቅ ነው።

ሐ) መደምደሚያና ማጠቃለያ፤

ዉድ ወገኖች፤ ሙስና የአንዲት

አገር ኤኮኖሚን አቆርቋዥ፤ ባህልንና

ሕብረተሰባዊ ትብብርን አኮላሽ፤ መንገሥት

ለሕዝብና ለሃገር ሊያደርግ የሚገባውን

አገልግሎት ቀናሽ ሥለሆነ ሁላችንም

ልንዋጋው ይገባል።

ሙስናን የሚያራምዱ በባህላቸው

የዘቀጡና የባህል ድህነት ያጠቃቸው፤

በተንኮለኝነት አስተሣሰብ የተዘፈቁ፤

በሌብነትና በቀማኛነት የተለከፉ፤ የጥሩ

ሥነ-ምግባር ድሃ የሆኑ፤ የሕብረተሰብንና

ያገር ንብረትን አባካኝ/አጥፊ የሆኑ፤ፀረ-

ሕዝብ ግለሰቦች ናቸው። በሙስና ወረርሽኝ

የተለከፉ ግለሰቦች ከሕብረተሰቡ ጋር

ያላቸው ንክኪም በጣም የበረከተ ስለሆነ

በሽታውን ለጠቅላላው ሕብረተሰብ

የማስፋፋትና የማስለከፍ ችሎታቸው

ከፍተኛ ስለሆነም ከሥልጣናቸው መወገድ

አለባቸው።

በሙስና የተዘፍቁ አግሮች በኢኮኖሚም

ሆነ በባሕል ወደ ኋላ የቀሩ መሆናቸው

በብዙ ጥናቶች የተረጋገጠ ስለሆነ ይህ

ችግር በኢትዮጵያችን በሚያስፈራ መልክ

እያንሠራራ ስለሆነ ይህንን የነቀርሳ

በሽታ ለመዋጋትና መንግሎ ለማውጣት

መተባብር ያስፈልገናል። ከብዙ አገሮች

የተገኘው ልምድ እንደሚያመለክተው ሁሉ

ሙስናን ለመዋጋት በሙስና የተለከፉትን

ግለሰቦች ማጋለጥና መንግሥት ሙስናን

ለመዋጋት የማይተባበር ከሆነም፤ በሕቡዕ

በመደራጀትና በመተባበር መዋጋትን፤

በሙስና የተዘፈቁትንም በምስጢራዊ

ሰነድ አዘጋጅቶ እንደአስፈላጊነቱ ማጋለጥ።

እንደዚህ ያለው አስተዋፅዖና መልካም

ምግባር፤ ለሙስናው መሥፋፋት

ምክንያት የሆነው የአስተዳደር ብልሹነት

እንዲፍረከረክ ያደርገዋል። ተጎጅው

ሕዝብንም እስትንፋስ ይሰጠዋል።

እንደሚታወቀው ባገራችን በኢትዮጵያ

(በየክፍለ ሃገሩ፤ በየከተማው፤ በየንመደሩ፤

በልዩ ልዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች፤

ዱሮ በመንግስት ሥር በነበሩት አሁን ግን

“ለግል ባለ ሀብቶች” በርካሽ በተቸረቸሩት

ተቋማት መካከል፤በግል ሀብቶች መስክ፤

….ወዘተ) ከሙስና ጋር የተያያዘው ችግርና

የሚደረገው ደባ ተዘርዝሮ አያልቅም።

ሙስናው የወረርሽኝ በሽታ ስለሆነ

ከዘራፊዎቹ በስተቀር ሁሉንም ሰው

ይጎዳል። ስለዚህ “የኔ ጉዳይ አይደለም”

ተብሎ የሚተው መሆን የለበትም።

እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ ሕዝብና

በሀገሪቷ ላይ አሁንም እየተፈፀሙ ያሉትን

በደሎችን ብሔራዊ ወንጀሎችን በቀጣይነት

መመዝገብና ማጋለጥ አለብን። የዜግነትና

የሰው ልጅነት ግዴታችንን እንድንወጣ አላህ

(እግዚአብሔር) እንዲረዳን እማፀናለሁ!

በመጨረሻም ሙስና ከሰው ጋር

ያልተፈጠረ ክስተት ስለሆነ ያለጥርጥር

እናሸንፈዋለን! በሙስና የተበከሉ

ግለሰቦች፤ ቡድኖችና የመንግሥት

ባለስልጣኖች የድሃውን ወገናችንን ደም

መጣጭ መዥገሮች ናቸውና መወገድ

አለባቸው!የሁለተኛው የሙስና ክፍል፤

ማለት፤ የመንግሥቱን የሥልጣን አውታር፤

አስተዳደሩን፤ ህጎቹን፤ ወ.ዘ.ተ. በመማረክ

የሚገለፁ የሙስና ጠባዮች (state

capture) በሌላ ጊዜ እስከማቀርብ ድረስ፤

እስከዚያው አላህ ቸር ይበለን።

www.andinet.org.et

4

ፍኖተ -ነፃነት ጋዜጣ ሐምሌ 2ዐዐ3 ዓ.ም

ተመሠረተ፡፡ ፍኖተ ነፃነት በአንድነት ለዴሞክራሲና

ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ሥር የሚታተም

በፖለቲካዊ፣ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ፣ በወቅታዊ ጉዳዮችና

በመዝናኛ ላይ የሚያተኩር የፓርቲው ጋዜጣ ነው፡፡

ጋዜጣችን እንደ ፓርቲ ልሳን ብቻ

ሳይሆን እንደ አንድ ሚዛናዊ የግል

ጋዜጣ ሆኖ ማገልገል ይፈልጋል

የማንኛዉም ሰዉ ሀሳብና አመለካከት

የሚስተናገድበትና የሚንሸራሸርበት

እንዲሆን እንሻለን ሰፊ የሚዲያ

ሽፋን ያለዉ ኢህአዴግም በዚህ ሚዲያ

አቋሙንና ፖሊሲዉን ለማቅረብ ቢፈልግ

ክፍት ነዉ

ዋና አዘጋጅ፡-

አንዳርጌ መሥፍን

አድራሻ፡-

የካ ክ/ከተማ ወረዳ 12

የቤ.ቁ አዲስ

አዘጋጆች፡-

ብዙአየሁ ወንድሙ

ብስራት ወ/ሚካኤል

አምደኞች፡- ዶ/ር ኃይሉ አርዓያ

ኢ/ር ዘለቀ ረዲ

አንዱዓለም አራጌ

ግርማ ሠይፉ

ዳምጠው አለማየሁ

ተስፋዬ ደጉ

በላይ ፍቃደ

ወንድሙ ኢብሳ

ስለሞን ስዩም

ኮምፒውተር ጽሑፍ፡-

የሺ ሃብቴ

ብርቱካን መንገሻ

አከፋፋይ፡-

ነብዩ ሞገስ

አሣታሚው፡-

አንድነት ለዴሞክሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት)

አድራሻ፡- አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 07 የቤ.ቁ አዲስ

አታሚ፡- ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት

አራዳ ክ/ከተማ ቀበሌ 07 የቤ.ቁ 984

የዝግጅት ክፍሉ

ስልክ +251 922 11 17 62

+251 913 05 69 42

+251 118-44 08 40

+251 923 11 93 74

ፖ.ሳ.ቁ፡ 4222

ኢሜይል፡- udjparty@gmail.com

andinet@andinet.org

ፋክስ ቁጥር፡- +251-111226288

www.andinet.org.et

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ ጥቅምት 28 ቀን 2004 ዓ.ም.

ርዕሰ አንቀፅ

ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ

ነፃ የሞያ ማህበራት ያስፈልጋሉ!

አገራችን የመድበለ ፓርቲ ሥርዓትን ተቀብላ በሕገ-መንግሥትዋ ካፀደቀች 17 ዓመት ሞላት፡፡ ተግባራዊነቱና

ዕድገቱን ስንመለከት ግን የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት መጀመሩም አጠያያቂ ነው፡፡ ሕገ-መንግሥቱ በተለያየ

ጊዜ በአዋጆች እየተሸረሸረ ነው፡፡ ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰት ይፈፀማል፡፡ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት

መገንቢያ ተቋማት ከማስመሰያነት አልዘለሉም፡፡ ዛሬ በአገራችን ነፃ የሲቪክ ድርጅቶች እና ነፃ የሞያ ማህበራት

አሉ ማለት አይቻልም፡፡

በአገራችን ረጅም ታሪክ ያለው የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማሕበር ነበር፡፡ ዛሬ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማሕበር

ኮንፌዴሬሽንም አለ፡፡ ግን ጥርስ የሌለው አንበሳ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ለረጅም ጊዜ የኢትዮጵያ መምህራን ማሕበር

ነበር፡፡ ዛሬም ለስሙ የመምህራን ማሕበር አለ፡፡ ቀደም ሲል ከ30 ዓመት በፊት የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማሕበር

ነበር፡፡ ዛሬም በቁጥር መብዛት ከሄድን አምስት የጋዜጠኞች ማሕበራት አሉ፡፡ የወጣቶች፣የሴቶች፣የመንፈሳዊ

ድርጅቶች፣የተማሪ ማሕበሮች፣የሰብአዊ መብት ድርጅቶች፣ወ.ዘ.ተ. ነበሩ፡፡ ዛሬም አሉ፡፡ በስም ብቻ መኖራቸው

ግን ፋይዳ የለውም፡፡

ወደ ኋላ መለስ ብለን የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበርን በጥቂቱ እናስታውሰው፡፡ በእነ አበራ ገሙ መሪነት

የሠራተኛውን መብትና ጥቅም ለማስከበር ያደረገው እንቅስቃሴ ለዛሬው ኢሠማኮ መፈጠር መሠረት ነው፡፡

የምድር ባቡር ሠራተኞች ማህበር የትግል ታሪክን መጥቀስ ይቻላል፡፡ የሠራተኛውን መብት ለማስከበር ታግለዋል፡

፡ ከነበረው የፊውዳሉ ሥርዓት ጋር ሠላማዊ ትግል አድርገዋል፡፡ መደራጀት መብት መሆኑን አረጋግጠዋል፡

፡ ደርግ ሥልጣን እንደያዘ አካባቢም ቢሆን ቀላል የማይባል መስዋዕትነት ከፍለዋል፡፡ ደርግ ይከተለው

በነበረው ወታደራዊ አመራር የሠራተኛው ተወካዮችና ግንባር ቀደም ተሟጋቾች የቀይ ሽብር ሠለባ ሆነዋል፡፡

መስዋትነታቸው ለሠራተኛው መብትና ጥቅም ሲሉ ቢሆንም ለዛሬው ለመደራጀትም አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡

ደርግ ሥርዓቱን ከተቆጣጠረ በኋላ የሠራተኛ ማህበሩን እንደ አንድ የመንግስት ተቋም እንዲያገለግል

አድርጐታል፡፡ ኢህአዴግ አገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላም ማህበሩን በአዲስ መልክ ለማደራጀት ጥረት ተደርጐ

ነበር፡፡ በዚሁ መሠረት በዘጠኝ ፌዴሬሽኖች የተደራጀው ማህበር የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበር ኮንፌዴሬሽን /

ኢሠማኮ/ መሠረተ፡፡ ኢሠማኮ እንደተመሠረተ አካባቢ የሠራተኛውን መብትና ጥቅም የሚያስጠብቁ ጥያቄዎችን

ማንሳት ሲጀምር፡፡ ኢህአዴግ ነፃ ማህበራት እንዳይኖሩ ርምጃ ወሰደ፡፡

እነዚህ ድርጅቶች እያንዳንዳቸው ያሉት እንደ አንድ ነፃ የሲቪክ ድርጅት ወይም እንደ አንድ ነፃ የሞያ ማሕበር

ወይስ እንደ አንድ የመንግሥት ተቋም እያገለገሉ ነው? ብለን ብንጠይቅ መልሱ አጭርና ግልፅ ነው፡፡ እንደ

አንድ መንግሥት ተቋም ሆነው እያገለገሉ ነው ብለን እናምናለን፡፡ ኢመማ ወይም ሌሎች የሞያ ማህበራትንም

ብንመለከት መልሱ ተመሳሳይ ነው፡፡ ምክንያቱም የማሕበሩን አባላት መብትና ጥቅም የሚያስከብር፣በነፃ ምርጫ

በማሕበሩ አባላት ተመርጠው ወደ አመራር በሚመጡ አመራሮች የሚመራ ሳይሆን በድርጅታዊ አሠራርና

ተጽዕኖ ባለበት ምርጫ የሚቋቋሙ አመራሮች ያሉበት ተቋም ሆኖ ይገኛል፡፡ ሥራ አፈጻጸሙም የማሕበሩ አባላት

የሚያነሱዋቸውን ጥያቄዎች በማፈን የሚቆጣጠር ዋና ኃይል ሆኖ የሚያገለግል ነው፡፡ አመራሮቹም ለሞያቸው

ክብር የሚሰጡ፣ለወከሉት ሠራተኛ የቆሙ ሳይሆኑ በአፍቃሬ ኢህአዴግነት ለኢህአዴግ ታማኝ በመሆናቸው

ክብር የሚሰማቸው ናቸው፡፡

የሥርዓቱ ገዢዎች በተደጋጋሚ ሲናገሩ እንደምንሰማው የሠራተኛውን መብትና ጥቅም ለማፈን “ኢንዱስትሪ

ሰላም ነው” ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ የማሕበራት ተወካዮችም ይህንኑ ቃል በተደጋጋሚ ያስተጋባሉ፡፡ “የኢንዱስትሪ

ሠላም” ምን ዓይነት ነው? የሠራተኛውን መብትና ጥቅም ወደ ጐን ትቶ የአሠሪውን ጥቅም ብቻ ያስከበረና

የገዢውን የሥልጣን ጥቅም ለማስጠበቅ የታለመ ነው ወይንስ የሠራተኛውን መብትና ጥቅም የሚያስከብር?

መልሱ ሠራተኛው የሥራ ዋስትና አጥቶ ሲበተን የህብረት ስምምነቱ እየተጣሰ መብቱና ጥቅሙ ሲነፈግ፤ ፍትህ

አገኛለሁ ብሎ በየፍ/ቤቱ ሲጉላላ ማህበሩ ዝምታን መርጧል:: በመሆኑም የኢሕአዴግ የእድሜ ክር ቀጣይ እንጂ

የሠራተኛውን መብትና ጥቅም የሚጠብቅ አይደለም፡፡ የይስሙላ “የኢንዱስትሪ ሰላም ነው”

የኢንዱስትሪ ሰላምን በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ ጊዜያዊ ሠላምና ዘላቂ ሠላም ናቸው፡፡ ጊዜያዊ

የኢንዱስትሪ ሠላም የማስመሰያ /አሳሳች/ ሠላም ነው፡፡ የሠራተኛውን ልብ ያልገዛ /የሠራተኛውን ጥቅም

ያልጠበቀ/፣አስተማማኝና ዘላቂ ልማትን የማያመጣ ሠላም ነው፡፡ የመፍጠር ችሎታን የማያበረታታና

ምርታማነትን የማያሳድግ ሠላም ነው፡፡ ዘላቂ የኢንዱስትሪ ሠላም ግን የሠራተኛውን ጥቅምና መብትን

የሚያስከብር፣በሠራተኛው ውስጥ በራስ መተማመንንና መረጋጋትን የሚፈጥር፣የሠራተኛውን የኃላፊነት ስሜት

የሚያስከብር ነው፡፡ ሊኖር የሚገባው ጊዜያዊ ሳይሆን ዘላቂ የኢንዱስትሪ ሠላም ነው፡፡ በሀቅ ላይ የተመሠረተ

ከሆነ የኢንዱስትሪ ሠላም ጥሩ ነው፡፡ ሠላም የሕይወትና የንብረት ዋስትና ይሰጣል፡፡ ሠላም ካለ ልማትና እድገት

አለ፡፡ ሠላም ካለ ቤተሰብ በሰላም ወጥቶ ሠርቶ ይገባል፡፡ ሠላም ከሌለ ሁሉም የለም፡፡ ዛሬ ያለው ሰላም ግን ምን

ዓይነት ሠላም ነው? መብትና ጥቅምን የገፈፈ ሠላም፤የታፈነ ሠላም፤ በቁጭትና በዝምታ የታጀበ ሠላም፤ በፍርሃት

የታጨቀ ሠላም፤አደጋን ያረገዘ ሠላም! እንዲህ ዓይነት ሠላም ውጤቱ የከፋ ስለሚሆን አደጋ ነው፡፡ ጊዜውን

ጠብቆ የሚፈነዳ ሠላም አንሻም፡፡ ጥፋትን በውስጡ አምቆ የያዘ “ሠላም” አያሻንም!

የሚያስፈልገን ሠላም ክፋትንና ጭንቀትን ያስወገደ፣ የዜጐችን መብትና ጥቅም ያስከበረ ሠላም ነው፡፡

የሠራተኛውንና የባለሀብቱን መብትና ጥቅም ፍትሐዊ ያደረገ ሠላም እንሻለን፡፡ የሞያ ማሕበራት የመንግሥት

ጣልቃ ገብነትና ተጽዕኖ የሌለባቸው፣የሥራ ብቻ ሣይሆን ነፃ የምርምር ተቋማት መሆን አለባቸው፡፡ ማህበራት

በነጻነት መደራጀት መቻል አለባቸው፡፡ ይህ እስካልሆነና የማሕብራቱን አባላት መብት እስካላስጠበቀ ድረስ

ኢህአዴግ የሚፈልገው የኢንዱስትሪ ሠላምና የሚመኘው ዕድገት ዘላቂነት አይኖረውም፡፡

የተደራጁት ማሕበራት የአባሎቻቸውን መብት ማስከበር መቻል አለባቸው፡፡ መብታቸውንና ጥቅማቸውን

በመጠየቃቸው አሠሪው ኃይልና መንግሥት በጋራ ሆነው ሠራተኛው ላይ የበቀል ጥቃት ማድረስ መቆም አለበት

ብለን እናምናለን፡፡ ለዚህ ምሳሌ የሚሆነን በዋልዳ ሆጀቶታ ዳንዲ ደራርቱ አርሲ (W H D D A) የቻይና

ሠራተኞች ማሕበር ሠራተኞችና የማሕበሩ አመራሮች ላይ የተወሰደውን ሠራተኞችን ማሰቃየትና የማኅበሩን

የአመራር አባላት የሠራተኛውን መብት እንዳይጠይቁና እንዳያስከብሩ ከሥራቸው በማፈናቀል የተወሰደውን

እርምጃ በጥብቅ እናወግዛለን፡፡ በሌላ በኩልም ጥቃቱም እንዲቆም እንጠይቃለን፡፡ ለደረሰባቸው ጥቃት ካሳ

እንዲከፈላቸው፣ሕክምና እንዲያገኙና መብትና ጥቅማቸው እንዲከበር የሚመለከተው ሁሉ እንዲረባረብ

ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ እንዲሁም የመደራጀት ጥያቄ አቅርበው የተከለከሉ 120 ሺ መምህራን ጥያቄአቸው

በአግባቡ ሊመለስላቸው ይገባል፡፡

የኢህአዴግ መንግሥት እጁን ከማሕበራት ላይ ያንሳ፡፡ ማሕበራት የመጨቆኛና የማፈኛ ተቋማት መሆን

የለባቸውም ብለን እናምናለን፡፡ በአገሪቱ አስተማማኝ የኢንዱስትሪ ሠላም ኢንዲመጣ ከተፈለገ ሞያ ማህበራት

በነጻነት መደራጀት አለባቸው፡፡ ማህበራት የሠራተኛውን መብትና ጥቅም የማስጠበቅ አቅም ሊኖራቸው

ይገባል፡፡ ጥቅማ ጥቅሞቻቸው መጠበቅ አለባቸው፡፡ የሠራተኛው ሞያዊ አቅምና ሥነልቦና መገንባት አለበት፡

፡ ጠንካራ የሠራተኛ ተወካዮችን ከሥራ ገበታቸው ላይ ማፈናቀልና ለጥቃት መዳረግ የለባቸውም፡፡ ይህ አይነቱ

ሠይጣናዊ ርምጃ በአስቸኳይ መቆም አለበት፡፡ ካልቻለ ግን እንደ አንድነት በአጅጉ ያሳስበናል፡፡ የሞያ ማህበራት

የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ መሠረት ናቸው ብለን እናምናለን፡፡ የሞያ ማህበራት በአገሪቱ ፖለቲካዊ

ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል፡፡ የማሕበር አባሎቻቸውን መብትና ጥቅም

አሳልፈው ሰጥተው የመጨቆኛ መሳሪያ፤ የሰብዓዊና የዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰት ተባባሪ መሆን የለባቸውም፡

፡ የተቋቋሙለትን ዓላማ በተቃራኒው መፈፀም ነው ብለን እናምናለን፡፡ በመጨረሻም ለመድበለ ፓርቲ ሥርዓትና

ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ መጠናከር ነፃ የሞያ ማህበራት በእጅጉ ስለሚያስፈልጉ እነዚህ ማኅበራት

ከኢሕአዴግ የተፅዕኖ ቀንበር ነፃ እንዲወጡ አብረን እንታገል፡፡

ጋዜጣችን “ፍኖተ-ነፃነት” ብለናታል፡፡ “ፍኖት” ማለት መንገድ ማለት ሲሆን ከነፃነት ጋር

ሲጣመር “የነፃነት መንገድ” ማለት ነው!!

ነፃ አስተየት

ታደሰ ፍስሐ

ለማን አቤት

እንበል?

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.15

ኢትዮጵያውያን ብዙ ጮኽን ያዳመጠን ግን የለም፡

፡ ለሰው ጩኽን፤ ለፈጣሪ ጩኽን፤ ለመሬትም ጮህን፤

አንዳች ምላሽ በመሻት፤ ጩኽታችን ግን ለሠማይና

ለምድርም ጮህን፤ ጩኸታችን ግን የቁራ ጩኽት ሆኖ ቀረ፡፡

የተፈረደብን የመከራ ዘመን ከማለቅ ወይ ከመገባደድ ይልቅ

እየጨመረ ሄደ፡፡

በግልፅ የሚታየውን ችግራችንን፣ ከፊታችን ሳይቀር

የሚነበበው ጉስቁልናችን፣ ሚሊዮኖችን ምርኮኝ ያደረገ

ርሃባችን፣ ፀሐይ የሞቀው የርስበርስ ፍጅታችንን ደመናን

ቀርቶ የጎጇችንን ጣሪያ ማለፍ የተሳነው ምህላና ፀሎታችን

ብዙዎች በየቀኑ ሽቅብ የምንረጨው እንባችን፤ ሁሉም

በማንም ዘንድ ተሰሚነት አላገኘም፡፡ አሁንም ለቅሶና

ዋይታችን ተባብሶ እንደቀጠለ ነው፡፡

ተንኮለኞች ያጠመዱትን ወጥመድ የደገሱልን መከራና

የሰቆቃ ድግስ ከዘመናት በፊት በሴራ መክረው ያወጁብን

የጥፋት ዘመን በብሄርና በጎሳ ከፋፍለው የኢትዮጵያን

አንድነት ለመነጣጠል በመካከላችን የከተቱብን የተኩላ

መንጋ ሁሉም እንዳሰቡት ሆኖ ትንቢታቸው ሲይዝላቸውና

ምኞታቸው ሲሳካላቸው በስቃያችን ይደሰታሉ፡፡ በቁስላችን

የጋለ ብረት እየሰደዱ ለቅሷችንን እንደ ጥጋብ፣ ጭንቀት

ጥበታችንን እንደ ደስታ፣ ጦርነታችንን እንደ መዝናኛ፣

መባዘናችንን እንደ በረከት፣ የርስ በርስ እልቂታችንን

እንደሰላም በመቁጠር ያላግጡብናል፡፡ እውነቱን የማያውቁ

ይመስል የላኳቸውን እንደራሴዎች የሚሰሩትን የማይረዱ

ይመስል፡፡ የእኛን መከራና ችግር እንደማያውቁ ሆነው

በመቆለል በጣት የሚቆጠሩ የተሻለ ኑሮ የሚኖሩ በገጠር

በግብርና የሚተዳደሩትን ከተማ ያሉ ሃብታችን በመመልከት

ብቻ ጥሩ ኑሮ ላይ ነን ይላሉ፡፡ እነዚያም ተቀብለው

“ይኽ መቸ አነሳችሁ፤ ጥሩ ኑሮ እየኖራችሁ ነው” በማለት

ይሳለቁብናል፡፡

ጥቂት የምትባል የመናገር፣ የመፃፍ ግድብ (ዴሞክራሲ)

መብት በማየት ብቻ ዴሞክራሲያችን እዚህ ደርሷል

በማለት አዎንታዊ አብነት ወስደው ከእኛ አልፈው

ለሌሎች አገሮች ማስተማሪያ ሊሆን እንደሚገባ ይሰብካሉ፡

፡ ይህ ድርጊታቸው በዴሞክራሲ ላይ ብቻ ሳይሆን በሰው

ልጆችም ላይ እንደማፌዝ የሚቆጠር ከመሆኑም በተጨማሪ

ለይስሙላ ያህል በውሸት በሚያመልኩት በእግዚአብሄርም

ዘንድ በእጅጉ አስነዋሪና ሃጢያት መሆኑን ሊገነዘቡት

ይገባቸው ነበር፡፡ ፈጣሪ የሰውን ልጅ በቀለምና በዘር

በስልጣኔና በመልካም ምድር ልዩነት እየፈጠራችሁ ተፋጁ

(አፋጁ) አላለም፡፡ ከዚህ ነጥብ አኳያ ተምረዋል የተባሉት

አማረዋል፡፡ እነዚህ ወገኖች እየሰሩት ያለው ግፍና በደል

ሲጤን መሰልጠናቸው ሳይሆን መስይጤናቸውንና ፀረ

ሰውም፣ ፀረ ፈጣሪም መሆናቸውን የሚያሳይ ነው፡፡

ሀገራዊም ሆነ አለም አቀፋዊ ሁኔታዎች ለእኛ

ለኢትዮጵያውያን የሚመቹ ባለመሆናቸው ተናግረን

የምንደመጥበት፣ አኩርፈን የምንጠጋበት፣ ፍትህን

የምናገኝበት አንድም አለኝታ የለንም፡፡ ሁሉም ነገር

ያዘነበለው ወደ ገዢዎቻችን በመሆኑ የችግራችን መጠን

ስፋትና ጥልቀት ተነግሮ አያልቅም፡፡ ፈጣሪ ጭምር አስጨናቂ

ዘመን እንድንገፋ የፈረደብን ይመስላል፡፡ ከታሰርንበት

የኑሮ ሰንሰለት ከገባንበት ምድራዊ ሲኦል ነበልባላዊ እቶን

የሚታደገን ከቶ ማነው? ዳዊት በመዝሙሩ አቤቱ ጌታ ሆይ

እስከመቼ ነው የምትተወኝ ያለው ወዶ አይደለም፡፡ እንደኛ

ክፉኛ ቢጨንቀው እንጂ፡፡ በርግጥ መከራ ሲበዛ ያነሆልላል፤

ስቃይ ሲበዛ መፈጠርን ያስረግማል፤ ግፍና በደል ከአንድ

ሰው የመሸከም አቅም ሲያልፍ ራስን ብቻ ሳይሆን ፍጣሪን

ድረስ ሊያስክድ ይደርሳል፡፡

ምንም እንኳን “እረኛ ቢያኮርፍ ምሳው እራት ይሆነዋል”

እንዲሉ አኩራፊ ቢያኮርፍ ከራሱ በላይ የሚጎዳው

ባይኖርም የችግሩ ክረት ፈጣሪን እስከ መውቀስ ቢያደርሰው

ቢያንስ ሊያስነውረው የሚገባ አይመስለኝም፡፡ በክርስቲያኑ

ህይወት እንግልትና የቁም ስቅልን የሚያሳይ አሳር ሲገጥም

በመፅናናት የሚጠቀስ አንድ መፅሐፍ ቅዱሳዊ ምሳሌ ነው፡

፡ የኢዮብ ስቃይ ከእኛ ከኢትዮጵያውያን ስቃይ ማወዳደር

የሚቻል አይመስለኝም፡፡ ለዘመንም ሆነ ከሌሎች መሰል

ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ ችግሮች አንፃር የኢዮብን ከእኛ

አስቸጋሪ ህይወት ላነፃፅር አልችልም፡፡

የመከራ ዶፍ የወረደበት ኢዮብ በደረሰበት ስቃይ

ሰማይ ምድሩ ተደፍቶበት ጭንቅ ውስጥ በነበረበት ወቅት

ከተናገረው ጥቂት እናስታውስና እኛ ከተዘፈቅንበት የችግር

ማጥ አኳያ ብሶት ምን ያህል እንደሚያናግር እንመልከት፡፡

ከችግርና ከረሃብ ብዛት የተነሳ በለሊት ተነስተው ወደ

በረሃ እየሄዱ

ስራ ስሮችን ያኝኩ ነበር፡፡

ጨው ጨው የሚል የበርሃ ቅጠላ ቅጠሎን ይለቅሙ

ነበር፡፡

ሰዎች ሌቦችን እየጮሁ እንደሚያባርሩ

እነርሱም ከህብረተሰቡ መካከል ያባርሯቸው ነበር፡፡

መኖሪያቸውም በየዋሻውና በየገደሉ ስር በተቆፈረ

ጉድጓድ ውስጥ ነበር፡፡

ወደ 10 ዞሯል

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.15

ፖለቲካ

ግርማ ሞገስ

(girmamoges1@gmail.com)

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ ጥቅምት 28 ቀን 2004 ዓ.ም.

የዚህ ጽሑፍ ግብ የሰላም ትግል

ለውጥ ማምጫ መንገዶች (Mechanisms

of change) በኢትዮጵያ እንዴት ህዝብን

የመንግስት ስልጣን ባለቤት ሊያደርጉ

እንደሚችሉ በማጥናት በኢትዮጵያ የፖለቲካ

ትግል እና የመንግስት ሽግግር ለማድረግ

ሰላማዊ ትግል ማደረግ እንደሚቻል እና

ተመራጩ የትግል ስልትም እሱ መሆኑን

ማሳየት ነው።

የሰላም ትግላችን ግብ ህዝብን የመንግስት

ስልጣን ባለቤት ማድረግ ነው። ህዝብን

የመንግስት ስልጣን ባለቤት ለማድረግ የሰላም

ትግል በህዝብ እና በአምባገነን መንግስት

መካከል የሚገኘውን የፖለቲካ ኃይል ሚዛን

ግንኙነት ወደ ህዝብ እንዲያደላ ማድረግ

አለበት። የሰላም ትግል ይኽን አስፈላጊ

የሆነ የፖለቲካ ኃይል ሚዛን ግንኙነት

ሽግሽግ (ለውጥ) ተፈጻሚ የሚያደርገው

በአራት መንገዶች እንደሆነ ጅን ሻርፕ

(Gene Sharp) አጥንቶ ለአለም የዲሞክራሲ

ኃይሎች እና ተመራማሪዎች ካበረከተ

ውሎ አድሯል። እነሱም፥ (1ኛ) የመቀየር/

የመለወጥ (Peaceful conversion)፣ (2ኛ)

የመቻቻል (accommodation)፣ (3ኛ)

ሰላማዊ አስገዳጅነት (Peaceful coercion)

እና (4ኛ) ሰላማዊ መፈረካከስ/መበታተን

(Peaceful disintegration) የተባሉት

ናቸው። እነዚህ ሰላማዊ ለውጥ ማምጫ

መንገዶች ከሰላም ትግል መሳሪያዎች ጋር

ዝምድና አላቸው። የሰላም ትግል መሳሪያዎች

ሶስቱ አብይ ክፍሎች (1ኛ) ተቃውሞ እና

ማግባባት (Protest and Persuasion)

እስከዚኽ ድረስ እንዳየነው መቀየር/መለወጥ (Peaceful

conversion) የተባለውን የለውጥ ማምጫ መንገድ ፕላን ቀይሰን

በአግባብ እና በቀጣይነት ከተጠቀምንበት የዲሞክራሲ ትግልን በህብረተሰቡ ውስጥ

ለማስፋፋት እና የህብረተሰቡን የሰላማዊ ትግል አቅምን ለመገንባት ይጠቅማል።

ነገር ግን ይኽ ለውጥ የማምጫ ሰላማዊ መንገድ በአምባገነኖች የፖለቲካ ኃይል

ምንጮች ላይ የሚያደርሰው ቀጥተኛ ጥቃት የለም። ጥቃቱ ተዘዋዋሪ ነው። ለጥቀን

መቻቻል የተባለውን ለውጥ ማምጫ መንገድ እንመልከት።

የሠላም ትግል ለውጥ ማምጫ አማራጭ

መንገዶች በኢትዮጵያ

፣ (2ኛ) ትብብር መንፈግ (noncooperation)

፣ (3ኛ) ጣልቃ መግባት

(intervention) እንደሆኑ እና ዝርዝራቸው

ወደ 200 ግድም እንደሚደርስ በፍኖተ ነፃነት

ቁጥር 13 “የሰላም ትግል መሳሪያዎች” በሚል

ርዕስ ቀርቧል። እነዚኽ አራት ለውጥ ማምጫ

መንገዶች ከሰላማዊ ትግል አቅም ግንባታ

አንስቶ እስከ መንግስት ሽግግር ፍጻሜ ድረስ

እንዴት አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ ባጭር

ባጭሩ እንመልከት።

(1ኛ) መቀየር/መለወጥ (Peaceful

conversion)

የዲሞክራሲ ኃይሎች ያቀረቡትን የለውጥ

አሳብ ወይንም የለውጥ ጥያቄ መንግስት

ቢቀበል እሱም ተጠቃሚ ሊሆን እንደሚችል

መንግስትን ማሳመን (መቀየር/መለወጥ)

የሚቻልበት ሁኔታዎች (መንገዶች) ሊኖሩ

ይችላሉ። ይኽን በማድረግ የዲሞክራሲ

ኃይሎች ከሚያገኙዋቸው ፋይዳዎች ውስጥ

ጥቂቱ፥ በህዝብ እና በመንግስት ዘንድ

የተቃዋሚ መሪዎችን ህጋዊነት ከፍ ማድረግ፣

ከመንግስት ጋር ሊደረጉ የሚችሉ ግጭቶችን

መቀነስ፣ የሰላማዊ ትግልን የሰው እና የቁሳቁስ

አቅም በረባ ባልረባው ሁሉ እንዳይባክን

ማድረግ ናቸው።

ርግጥ ይኽ መንገድ በመንግስት ላይ

የሚያሳድረው ጫና (ክብደት) በጣም

ዝቅተኛ በመሆኑ የሚያስገኘው ጠቀሜታ

እዚህ ግባ የማይባል ሊሆን ይችላል።

ያም ሆኖ ግን የተመረጠው የለውጥ ጥያቄ

የአምባገነኖችን ስልጣን አደጋ ላይ የማይጥል

እና የጥያቄው አቀራረብ ብልህ እስከሆነ

ድረስ አልፎ አልፎም ቢሆን ጠቃሚ

ውጤት አይገኝም ማለት ያስቸግራል።

ለውጥ የተገኘበት ጊዜ አለ። ምሳሌ፥ እንደ

አውሮፓ አቆጣጠር በ1962 ዓመተ ምህረት

ቀድሞ የእንግሊዝ ቅኝ አገር በነበረችው

በርማ ውስጥ በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን

ላይ የወጣው ወታደራዊ አምባገነን ቡድን

መጀመሪያ ከያዘው አቅዋም ከጊዜ በኋላ

እንዴት እንደተለወጠ እንመልከት።

ስልጣን እንደጨበጠ፣ የእንግሊዘኛ

ቋንቋ ትምህርት በአንደኛ ደረጃ እንዳይሰጥ

አደረገ። በዩንቨርስቲ ደረጃም የሚሰጥ

የእንግሊዘኛ ቋንቋ ዝቅ እንዲል አደረገ።

ወታደራዊው መንግስት ለህዝብ የሰጠው

ሃሰተኛ ምክንያት “እንግሊዘኛ ቋንቋ የቅኝ

ግዛት ዘመን ውርደታችን ማስታወሻ በመሆኑ

መወገድ አለበት” የሚል ሲሆን ሃቀኛው

ምክንያት ግን በመምህርነት ስራ የተሰማሩትን

እና ኗሪ እንግሊዞችን ከአገር በማስወጣት

የበርማን ህዝብ ከውጪው አለም ፖለቲካ

ተጽእኖ ለማፈን (Censorship) ነበር። ይኽ

ፖሊሲ የበርማ ተማሪዎችም ወደ ምዕራቡ

አለም እንደቀድሞው እንደልብ እየወጡ

ከፍተኛ ትምህርት ለመማር በቅድሚያ

ማለፍ ያለባቸውን የእንግሊዘኛ ቋንቋ ፈተና

ማለፍ እንዳይችሉ ማድረግ ጀመረ። በበርማ

እንግሊዘኛ ቋንቋ መናገር የሚችሉ ተወላጅ

የቢሮ አስተዳዳሪዎች ማግኘት አስቸጋሪ

መሆን በመጀመሩ የውጭ አገር ኢንቨስተሮች

ወደ በርማ መምጣት አቆሙ። የአገሪቱ

ኢኮኖሚ ተንኮታኮተ። በዚኽ አይነት

ለስልጣኑ መጠናከር ሲል ለ20 አመቶች

ያህል አለም አቀፍ የቢዝነስ እና የንግድ

ቋንቋ በበርማ እንዲዳከም ካደረገ በኋላ ይኽ

ፖሊሲ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ያስከተለው

አሉታዊ ተጽእኖ ለአምባገነኖቹ ገዢዎች

ወለል ብሎ ይታያቸው ጀመረ። የበርማ

የንግዱ ማህበረሰብ እና የዲሞክራሲ ኃይሎች

በእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርት ላይ የተጣለው

ገደብ እንዲነሳ ያቀርቡት የነበረውን የለውጥ

ጥያቄ የበርማ አምባገነን መንግስት ተቀበለ።

አምባገነኑ የበርማ መንግስት የለውጡን

ጥያቄ የተቀበለው ለውጥ ቢያደርግ ተጠቃሚ

መሆኑን በመገንዘቡ ነበር።

የሰላም ትግል የመንግስት ባለስልጣኖችን

ብቻ ሳይሆን ህዝብንም በመቀየር/በመለወጥ

ለዲሞክራሲ ትግል መስፋፋት እና አቅም

ግንባታ ጥቅም ይሰጣል። መንግስት በህዝብ

ላይ የሚፈጽማቸው በደሎች፣ ዲሞክራሲ

የሚሰጠው ጠቀሜታ እና ዛሬ በአለም ውስጥ

እየተደረገ ስላለው የለውጥ እንቅስቃሴ

እና ስለመሳሰሉት በሰፊው ማሰራጨት

ህዝብ ለመለውጥ ያግዛል። በአለም ውስጥ

ስለሚሆነው እና በአገር ስለሚፈጸም ሰላማዊ

ሰልፎች፣ ተቃውሞዎች፣ ህዝባዊ ውይይቶች

እና ተመሳሳይ የሰላማዊ ትግል ዜናዎች

የህዝብን ዝንባሌ እንደሚቀይሩ እና ከፍራቻ

ነፃ ለመውጣት እንደሚያግዙ መረሳት

የለበትም። በዚህ ረገድ ድረ ገጾች፣ የህትምት

እና የኤሌክትሮኒክ ሚዲያዎች ከፍተኛ

ሚና አላቸው። ለዚህም ነው አምባገነኖች

የሚያፍኗቸው።

አምባገነኖች በሰላም ትግል ታጋዮች ላይ

የሚፈጽሙት ግፍ እና የሰላም ትግል ታጋዮች

የሚያሳዩት ጀግንነት ህዝብን በመለወጥ

የዲሞክራሲ ትግሉን ያጠናክራል። በዚህ

ረገድ በህዝብ ዘንድ ጀግንነት ተደርገው

የሚወሰዱ ርምጃዎች ሌላውን የመለወጥ

አቅም እንዳላቸውም መረሳት የለበትም።

ምሳሌ፥ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር

በ1950 ዎቹ እና 1960ዎቹ አፍሪካ

አሜሪካውያን መንግስት በሚለቅባቸው

ተናካሽ ውሻዎች መነከሳቸው፣ በእሳት አደጋ

መኪናዎች በሚረጭ ውሃ መደብደባቸው፣

ማታ ማታ በሰላም ትግል መሪዎች ቤቶች

ላይ ይደርስ የነበረው ቃጠሎ፣ የሰላም

ትግል ሰራዊት በሚሰበሰብባቸው ቤተ

ክርስቲያኖች ላይ ይደርስ የነበረው ፈንጂ እና

ቃጠሎ ሳይገታቸው በጀግንነት ለእኩለንት

ያደረጉዋቸው ትግሎች ህዝባቸው ብቻ

ሳይሆን ነጭ አሜሪካውያንን እና የቀረውን

አለም ህዝብ በመለወጥ ከአፍሪካውያን

አሜሪካውያን ጎን እንዲቆም አድርጓል።

ሌላ ምሳሌ፥ ግብጾች መንግስት ሳያስፈቅዱ

በነፃነት አደባባይ መስፈራቸው እና

ነፃነታቸውን ማወጃቸው ብዙ ግብጻውያንን

እንደለወጠ እና ሰላማዊ ትግሉን እንዲቀላቀሉ

እንዳደረገ የምናውቀው ትኩስ ዜና ነው።

እንዲሁም በድስፕሊን የታነጸ የሰላም

ትግል ሰራዊት በአምባገነኖች እየተዋከበ፣

ሳያስር እየታሰረ እና እየተገደለ፤ በጀግንነት

ሰላማዊ ትግሉን በቀጣይነት ሲያኪያሂድ

ሲያዩ የጨቋኙ መንግስት አባላት (የጦር

መኮንኖች፣ ሚንስትሮች፣ ዲፕሎማቶች፣

ወ.ዘ.ተ.) እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት፣

የምዕራቡ አለም መሪዎች፣ የመብት ተሟጋች

ድርጅቶች ወ.ዘ.ተ. ሳይቀሩ እየተለወጡ

ሰላማዊ ትግሉን ይቀላቀላሉ። ለምሳሌ

የሊቢያው ጋዳፊ በሰላማዊ መንገድ አደባባይ

ወጥቶ ነፃነቱን በጠየቀ ህዝብ ላይ አረመኒያዊ

ጦርነት ሲያውጅ በጋዳፊ መንግስት ውስጥ

በአገር ውስጥ የነበሩ ባለስልጣኖች እና

ዲፕሎማቶች ሰላማዊ ትግሉን ተቀላቅለዋል።

በየመንም አምባገነኑ የሳላህ መንግስት በሰንዓ

(ለውጥ አደባባይ) እና በታኤዝ ከተሞች

በሰፈረው ሰላማዊ ታጋይ ላይ ግድያ በፈጸመ

ቁጥር ተመሳሳይ ሁኔታዎች ተፈጥረዋል።

እስከዚኽ ድረስ እንዳየነው መቀየር/

መለወጥ (Peaceful conversion)

የተባለውን የለውጥ ማምጫ መንገድ

ፕላን ቀይሰን በአግባብ እና በቀጣይነት

ከተጠቀምንበት የዲሞክራሲ ትግልን

በህብረተሰቡ ውስጥ ለማስፋፋት እና

የህብረተሰቡን የሰላማዊ ትግል አቅምን

ለመገንባት ይጠቅማል። ነገር ግን ይኽ ለውጥ

የማምጫ ሰላማዊ መንገድ በአምባገነኖች

የፖለቲካ ኃይል ምንጮች ላይ የሚያደርሰው

ቀጥተኛ ጥቃት የለም። ጥቃቱ ተዘዋዋሪ

ነው። ለጥቀን መቻቻል የተባለውን ለውጥ

ማምጫ መንገድ እንመልከት።

(2ኛ) መቻቻል (Peaceful

accommodation)

አንዳንድ ጊዜ አምባገነናዊ መንግስቶች

በዜጎች ዘንድ ላገር አሳቢ መስሎ ለመታየት፣

በውጭ መንግስታት ዘንድ ተቀባይነት

ለማግኘት ወይንም የገጠማቸውን የለውጥ

ጥያቄ ውጥረት ለማርገብ ሲሉ የዲሞክራሲ

ኃይሎችን ጥያቄዎች ይቀበላሉ። ይኽን

የሚያደርጉት መብት አክባሪ እና ትሁት

በመሆናቸው ሳይሆን ለተቃዋሚዎች የለውጥ

ጥያቄ የመቻቻል መፍትሄ ብንሰጥ ስልጣናችን

አይነጠቅም፣ አቅማችንም አይዳከምም ነገር

ግን ከጭቅጭቅ እንድናለን ከሚል እምነት

ነው። ይሁን እንጂ አንድ አምባገነን መንግስት

መቻቻልን እንደመፍትሄ ከወሰደ በስልጣን

ላይ የነበረው ፍጹም የሆነ ቁጥጥር ተቀንሷል

ማለት ነው። በህዝብ እና በአምባገነኖች

መካከል በነበረው የኃይል ሚዛን ግንኙነት

ላይ የተወሰነ ሽግሽግ ተደርጓል ማለት ነው።

ለምሳሌ የስራ ማቆም አድማዎችም ቆመው

ሰራተኞች ወደ ስራ የሚመለሱት በአሰሪና

በሰራተኞች መካከል በሚደረግ መቻቻል

ነው።

5

በአገሮች መካከልም መቻቻል ይደረጋል።

የቻይና መንግስት ጥቂት የፖለቲካ እስረኛ

በመፍታት በምዕራቡ አለም የሚቀርብበትን

የሰብዓዊ መብት ማሻሻል ጥያቄ ለማርገብ

ሲሞክር እናያለን። ምዕራቡም ለጊዜው ዝም

ይላል። በምዕራቡ እና በቻይና መንግስት

መካከል መቻቻል ተደረገ ማለት ነው።

የቻይና መንግስት ይኽን የሚያደርገው

በምዕራቡ አለም ተገዶ (Coerced ሆኖ)

ሳይሆን የቀረበው የመብት ጥያቄ ከምዕራቡ

አለም ጋር ካለው የንግድ እና ሌሎች ጉዳዮች

ጋር እየተወሳሰበ እንደልብ አላራምድ

ስለሚለው ነው። ስለዚኽ ለምዕራቡ ጥያቄ

የመቻቻል ምላሽ በመስጠት ንግዱን እና

ሌሎች የሚጠቅሙትን ነገሮች ያደርጋል።

ምርጫም መቻቻል ነው። በየአምስት

ወይንም አራት አመቶች የሚደረግ ምርጫ

ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለሚያቀርቡት የፖለቲካ

ለውጥ ጥያቄ አምባገነን መንግስቶች

የሚሰጡት የመቻቻል መልስ ነው። ይሁን

እንጂ ከተመክሮ ማነስ የተነሳ የተቃዋሚ

ፓርቲ መሪዎች ምርጫው ነፃ እና ፍትሃዊ

ይሆናል፣ ከምርጫው ጋር በተያያዘ

መንግስት የሚፈጽመውን ወከባ ህዝቡ

መቋቋም ይችላል ወይንም አለም አቀፍ

ታዛቢዎች የምርጫውን ድምጽ ቆጠራ

እንዳይሰረቅ ያደርጋሉ ብለው ይገምታሉ።

ይኽ የዋህነት ነው። አምባገነኖች ነጻ ምርጫ

ተደርጎ ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው ይለቃሉ

ብሎ መገመት ስህተት ነው። ሳይገደዱ

በፈቃደኛነት ስልጣን ማስረከብ የአምባገነኖች

ጸባይ አይደለም። አምባገነኖች ዲሞክራቶች

አይደሉም። አምባገነኖች ስልጣን ላይ

የሚወጡት በግድያ እና በሽብር ነው።

በስልጣን ለመቆየትም መንግስታዊ ሽብር

ይፈጽማሉ። ምርጫም ከሆነ የሚያግዳቸው

ኃይል ከሌለ ድምጽ ይሰርቃሉ። እንደ

አውሮፓ አቆጣጠር በ2000 ዓመተ ምህረት

በሰርቢያ እና በ2002 ዓመተ ምህረት

በዝንባቡዌ የተደረጉት ምርጫዎች በንፅፅር

ማየት ይጠቅማል። ሁለቱም ምርጫዎች

በስልጣን ላይ በነበሩት አምባገነኖች

ተሰርቀው ነበር። ይሁን እንጂ በሰርቢያ

የህዝብን ድምጽ ማስከበር ሲቻል በዝንባቡዌ

ግን ያን ማድረግ ሳይቻል ቀርቷል። ስለዚኽ

የሁለቱ ምርጫዎች የመጨረሻ ውጤት

ሊለያይ ቻለ። እንመልከት።

በሰርቢያ ተቃዋሚው በመላ አገሪቱ

የምርጫ ታዛቢዎች አሰልጥኖ አሰማራ።

ህዝቡ ንቅል ብሎ ወጥቶ ድምጹን እንዲሰጥ

የሚያነሳሳ እና የሚቀሰቅስ የሰላማዊ የምርጫ

ሰራዊት አሰልጥኖ በመላ አገሪቱ አዘመተ።

መንግስት ድምጽ ቢሰርቅስ ብሎ ቀደም ብሎ

በማሰብ ተቃዋሚው ድምጽ “ለማስከበር

ፕላን ለ” (Plan B) አዘጋጅቶ ነበር። አንድ

መንግስት የህዝብ ድምጽ አላከብርም ካለ

ህዝቡም በበኩሉ ለመንግስት የለገሰውን

የገዢነት ክብር እና ህጋዊነት የመንፈግ መብት

አለው። ስለዚኽ “ፕላን ለ” (Plan B) ድምጽ

ለማስከበር የሚደረግ የፖለቲካ እምቢታ፣

ትብብር የመንፈግ እና የጣልቃ መግባት

የሰላም ትግል መሳሪያዎችን የሚጠቀም

ሰላማዊ ትግል ነው። በየምርጫ ጣቢያው

የተመደቡ የተቃዋሚ ታዛቢዎች በድምጽ

ቆጠራው ላይ በመሳተፍ ቆጠራው እንዳለቀ

በዚያው ምሽት ውጤት በየጣቢያው ይፋ

እንዲሆን አደረጉ። በመጨረሻ በሞሊሶቪች

ይመራ የነበረው አምባገናንዊ መንግስት

የምርጫው ውጤት እንደፈለገው ሳይሆን

በመቅረቱ አይኑን በጨው አጥቦ አሸንፌያለሁ

ቢልም በምርጫው እለት ምሽት በየምርጫ

ጣቢያው ድምጽ ይፋ ተደርጎ ስለነበር ህዝቡ

“ድምጽ ይከበር” አለው። ተቃዋሚው ቀደም

ብሎ ያዘጋጀውን በሚሊዮኖች የሚቆጠር

ወደ 13 ይዞሯል

www.andinet.org.et

6

www.andinet.org.et

በማህበራችሁና በቻይና ኩባንያ በሚሰሩ ዜጐቻችን ላይ ከፍተኛ

በደልና ግፍ እየተፈፀመ ነው ይባላል፡፡ እውነት ነው፡፡ ካለስ

የሚፈፀመው በደል ምንድነው?

- እውነት ነው፡፡ እጅግ አሰቃቂ ግፍ እየተፈጸመብን ነው፡፡

ዋናው ጉዳይ ቻይናውያን በእኛ ሕግ ተዳደሩ ይሉናል፡፡ እኛ

ደግሞ የለም፤ በአገራችን ሕገ-መንግሥትና በአዋጅ 377/96

ሕግ መሠረት እንተዳደር እንላለን፡፡ ሕገ መንግሥቱ አንቀጽ

55/ን/አ/3 የተሰጠን የዜግነት መብት ይከበርልን እንላለን፡

፡ ቻይናውያን ሕገ-መንግሥታችሁንም የአዋጅ ሕጋችሁንም

አናውቅም ብለው በገዛ አገራችን እንደ ዕቃ እየተጫወቱብን

ነው፡፡ በጉልበታችን፤ በጊዜአችንና በሞራላችን ላይ ብቻ ሳይሆን

የሰብአዊና የዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰት፣የአካል ጉዳትና በሴት

እህቶቻችን ላይ የፆታ ጥቃት እየተፈፀመ ነው፡፡

የውል ስምምነት የላችሁም? ከሌላችሁስ እንዲኖራችሁ

አልሞከራችሁም?

- በአገራችን ካለው የሥራ እጦት መጀመሪያ ስንቀጠር ሠርተን

እንብላ እያልን ተቀጠርን፡፡ መብታችን አልከበር ሲል፤ጥቃት

ሲደርስብን፤በማህበር ተደራጅተን መብታችንን ለማስከበር

ሞክረን፡፡ የሰራተኛው ብዛት 720 /ሰባት መቶ ሃያ/ ነው፡፡ 3 ጊዜ

ማሕበሩን ለማፍረስ ተሞከረ፡፡ ሆኖም ግን አልቻሉም፡፡ ቀጥሎ

እየነጣጠሉ ማጥቃት ጀመሩ፡፡

የማሕበሩ አመራር በመሆኑ የደረሰ የተለየ የሚባል ጥቃት አለ?

በማስረጃ ሊገልጹልኝ ይችላሉ?

- አዎ፡፡ የማሕበራችን መስራች የሆነው አቶ አረጋኸኝ ተፈሪ

የሚባል የ24 ዓመት ወጣት አለ፡፡ ማሕበሩን ለምን አቋቋምክ?

ለምን አታፈርስም? ብለው ቢያዙት እንቢ በማለቱ የተወሰደበትን

ጥቃት ልንገርህ፡፡ ሚስተር ማ የሚባል ቻይናዊ ከአንድ ሺ

ኪ.ግ በላይ የሆነ የስሚንቶ ማቡኪያ በሃፍቼ ፔን ማሽን ብድግ

ካደረገ በኋላ ከሥር ሆነህ ስሚንቶውን ፈቅፍቅልኝ አለው፡

፡ ይህ ሠራተኛ በታዘዘው መሠረት ከሥር ገብቶ ስሚንቶውን

መፈቅፈቅ ጀመረ፡፡ ማሽኑን አውርዶ አስቀመጠበት፡፡ አረጋኸኝ

ከሥር ሆኖ በሲቃ ሲጮህ ለ49 ደቂቃ በላዩ ላይ አስቀመጠበት፡

፡ አረጋኸኝ ከዚያ ሲወጣ ከሰውነቱ ሦስት አጥንት ወጥቷል፡፡

ሽንቱን መቆጣጠር አልቻለም፡፡ ዛሬ አይነምድሩን እናቱ በጓንት

ያፀዳዱለታል፡፡ የህክምና ፋይሉ ዮርዳኖስ ሆስፒታል ይገኛል፡

፡ ዮርዳኖስ ሆስፒታል 15 ቀን ካስተኙት በኋላ አውጥተው

እንዲሞት ተፈልጐ በአንድ ሆቴል ለ3 ቀን አስተኙት፡፡ ሆኖም

ግን በቤተሰብ ጥረት ተረፈ፡፡ ማህበራችንን ከመሠረቱት ሰባት

ሰዎች አንዱ ነው፡፡ በማህበሩ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ከሚያደርጉ

መካከል አረጋኸኝ ተፈራ ግንባር ቀደም ነበር፡፡ ዛሬ አረጋኸኝ

ሽንቱን መቆጣጠር አይችልም፡፡ የአልጋ ቁራኛ ሆኗል፡፡ ይህ

የደረሰበት ሰው ነኝ፤ አገር አለኝ፤ መብቴን በሕገ-መንግሥቱና

በአዋጁ መሠረት መብቴን አስከብራለሁ፤ መንግሥትም ከጐኔ

ይቆምልኛል ብሎ በማመኑ ነበር፡፡ ነገር ግን አልሆነም፡፡

ወንድሞቹን ያስተምር ነበር እናቱን የሚጦር እሱ ነው፡፡ በአሁኑ

ጊዜ ከ6ቱ ወንድሞቹ አራቱ ትምህርታቸውን አቋርጠው ልመና

ገብተዋል፡፡ ለአረጋኸኝ ምግብ ያስፈልገዋል፡፡ አረጋኸኝን

ለሚያስታምሙ እናቱም ምግብ ያስፈልጋታቸዋል፡፡ የቀረነውን

አመራሮች የሚያድን ኃይል ተመድቦብን ሕይወታችን አደጋ

ውስጥ ወድቋል፡፡ በገዛ አገራችን መብታችንን በመጠየቃችን

የሕይወት ዋስትና አጥተን ዛሬ የምንኖረው ተሸሽገን ነው፡

፡ እኛ የጠየቅነው ሕገ መንግሥቱ ይከበር! ሕገ መንግሥስቱ

የሰጠን መብት ይከበርልን ነው፡፡ ሕገ መንግሥቱን ቻይናውያን

አንቀበልም ሲሉ የመንግሥት አካላትም በተገላቢጦሽ እኛን

እንደወንጀለኛ አይተው እያሳደዱን ነው፡፡ እያሳደዱን ያሉት

ሠራዊት ሕጋዊ ሠራዊት መሆኑን እየተጠራጠርን ነው፡፡ በማን

መዋቅር የተደራጀ ሠራዊት በማን እንደሚታዘዝም አልገባንም፡

፡ በዚህ አጋጣሚ የተደቀነብን የሕይወት አደጋ ለሚመለከተው

ሁሉ አሳውቃችሁልን ሕይወታችንን አትርፍልን፡፡

በሌላ አመራር ወይም አባል ላይ እንደዚህ ዓይነት የደረሰ ጉልህ

በደል ይኖር ይሆን?

- 17 አባሎቻችን ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው ለእንግልትና

ለሥቃይ ተዳርገዋል፡፡ ህክምና አጥተው አካላቸው ተበላሽቶ

በቁስል እየተሰቃዩ ናቸው፡፡ ለምን እንዴት ብሎ የሚጠይቅ

ሠራተኛ ካለ በሎደር አፈር ይደፋበታል፡፡ በየዕለቱ በሴት

እህቶቻችን ላይ አስገድዶ መድፈር ይፈፀምባቸዋል፡፡

ለየትኛውም የመንግሥት አካል ብታመለክት መልስ አታገኝም፡፡

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ ጥቅምት 28 ቀን 2004 ዓ.ም.

ቆይታ

- “ቻይናውያን ሕገ-መንግሥታችሁንም የአዋጅ

ሕጋችሁንም አናውቅም ብለዋል”

አፍህን ሰብስበህ ሥራህን ሥራ እንባላለን፡፡ ለቻይና እስከሰራችሁ

ድረስ፤ ቻይና ደሞዝ እስከፈለጋችሁ ድረስ፤ በቻይና ሕግ

መተዳደር አለባችሁ ይሉናል፡፡ በቻይና ሕግ ማህበር ማቋቋም

ክልክል ነው፡፡ በቻይና ሕግ ሐሳብን በነጻነት መናገር አይቻልም፡

፡ መሰብሰብ ወንጀል ነው፡፡ ሐሳብን በነጻነት መናገር አይቻልም፡

፡ ጋሻው ጣሰው የተባለ አንድ አባላችን ጥር 7 ቀን 2003 ዓ.ም

በሰርግ ሚስት አገባ፡፡ ጥር 8 ቀን 2004 ዓ.ም አስጠርተው

በሰርግህ ዕለት አንድ ቻይና የሚለብሰው ነጭ ተመሳሳይ ጃኬት

ለምን ለበስክ ብለው ደብድበው የዘር ፍሬውን አበላሽተውታል፡

፡ የዚህን ሠራተኛ የዘር ፍሬ ለማበላሸት የፈፀሙበት ስቃይ

እነዚህ ሰዎች እንደ ሰው የሚያስቡ ናቸው የሚያስኝ ነው? ይህ

ሰራተኛችን አሁንም በአካል አለ፡፡ ልታነጋግሩት ትችላላችሁ፡፡

ከአካል ጉዳትና ከሴቶች መደፈር ሌላስ የሚጠቀስ ጥቃት

ይኖራል?

- እየተፈፀመ ያለው ጥቃት ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም፡፡

የብሔራዊና የሃይማኖት በዓላትን እንዳናከብር ተከልክለናል፡፡

በዚሁ ምክንያት 5 የክርስትና፣3 የእስልምና በዓላትን፣የአድዋና

የሜዴይ በዓላትን እንዳናከብር ተከለከልን፡፡ የራሳችንን

ብሔራዊ በዓላት ተከልክለን በአገራችን ተቀምጠን የቻይናን

የጐማ በዓል ተገደን አንድናከብር እየተደረገ ነው፡፡

ይህ ሁሉ በደል ሲፈፀም የት የት አመለከታችሁ? ምን መልስ

ተሰጣችሁ?

- መጀመሪያ አካባቢ የነበረን ግንዛቤ ቻይናውያን

በኢትዮጵያውያን ላይ ለሚያደርሱብን ጥቃት አቤቱታ አቅርበን

ከአንዳንድ የመንግሥት ባለሥልጣናት ፍትህ ስናጣ የመሰለን

የባለሥልጣናት የሙስና ውጤት ነው፤እያልን እሱን ትተን

ወደ ሚቀጥለው ባለሥልጣን እናመለክት ነበር፡፡ በመጨረሻ

ላይ ግን እንደምናየው የመንግሥት አቋም ነው፡፡ መንግሥት

ከቻይናውያን ጥቅም እስካገኘ ድረስ በዜጐች ላይ ምንም

ጥቃት ቢደርስ የፈለገው ግፍ ቢፈጸም ማየትም መስማትም

አለመፈለጋቸውን ነው የተረዳነው፡፡

እንደዚህ ለማለት የሚያበቃችሁ ምንድነው? በቀጥታ ቀርባችሁ

ለመጨረሻ ጊዜ ያነጋገራችሁት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣን

ማነው? ምንስ መልስ ሰጡዋችሁ?

- ሌላውን ልተወውና ሁለት ቦታዎችን ብቻ ልግለጽልህ፡፡ ለህዝብ

ተወካዮች ም/ቤት ሕግና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

አመለከትን፡፡ የፓርላማ አባል የሆኑት የተከበሩ አቶ ብርሃኑ

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.15

አቶ ኩራባቸው ፍቅሩ ገ/ማርያም የዋልዳ ሆጀቶታ ዳንዲ ደራርቱ አርሲ (W H D D A) የቻይና ሠራተኞች ማህበር ሊቀመንበር ናቸው፡፡

የቻይና ኩባንያዎች በማሕበራቸውና በዜጐቻችን ላይ እያደረሰ ነው በሚባለው ጉዳይ ላይ ባልደረባችን ብዙአየሁ ወንድሙ አነጋግሮአቸዋል፡፡

አበበ ሥፍራው ድረስ ሄደው ተመልክተዋል፡፡ ሠራተኛው

የደረሰበትን ነገር ሁሉ አስረድቷቸዋል፡፡ ተመልሰው ከሄዱ

በኋላ ትልቅ መፍትሔ እናገኛለን ብለን ተስፋ አድርገን ነበር፡፡

ምንም መልስ አላገኘንም፡፡ ለጠ/ሚኒስትሩ ጽ/ቤት አመልክትን፡

፡ መፍትሄ ስንጠብቅ ያገኘነው ውጤት በተገኘንበት ቦታ ሁሉ

እያሳደዱ እርምጃ መውሰድ ጀመሩ፡፡ ቀይ ሽብራዊ ግርፍ

ተፈጽሞብናል፡፡ ታስረን ተገልብጠን ተገርፈናል፡፡ ሱሪንና

ቡታንታን አስወልቀው እጅና እግርን አስረው ገልብጠው

ሰቅለው መጫወቻ አደረጉን፡፡

እንዲህ ተሰቅላችሁ የተገረፋችሁት የት ነው?

በአርሲ ጮሌ ወረዳ ማኛ ላይ የፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ ነው ይህንን የፈፀመብን፡

፡ 51 አባሎቻችን ቀይ ሽብር ግርፍ ተፈጽሞብናል፡፡ በ7 አባሎቻችን ላይ

ደግሞ ለምርመራ ተብለው ተወስደው በራሳቸው ላይ እንዲመሰክሩ

አሰቃይተዋቸዋል፡፡ ኬሚካል ረጭተውባቸዋል፡፡ አእምሮአቸውን እንዲሰቱ

አድርገዋቸዋል፡፡ ጥር 8 ቀን 2003 ዓ.ም ከፍተኛ ተኩስ ተከፍቶብን ሊፈጁን

ሲሉ የሼክ አብዱራህማን ጉቺ የሚባል የእምነት ሥፍራ ያለ ህዝብ ወጥቶ

ነው ያዳነን፡፡

ይህ የተጋነነ ወይም ማስረጃ የሌለው ነገር ነው ማለት አይቻልም?

- ይኸውልህ ከወረዳው መስተዳድር ደብዳቤ አጽፈን በእጃችን

ይገኛል፡፡ ለተፈፀመብን ጥቃት በጠቅላላ የሲዲና የጽሑፍ

ሰነዶቻችን ይኽውልህ፡፡ ሁሉንም አይተህ ማረጋገጥ ትችላለህ፡፡

ሌሎች ሠራተኞችንም አነጋግር፡፡

ቻይናዊያን ይህንን ግፍ ለምን የሚፈጽሙ ይመስልሃል?

ቻይናዊያን እንደሚታወቀው በሰብአዊ መብት ጥሰት በዓለም ላይ የታወቁ

ናቸው፡፡ በተለይ ኢትዮጵያ ከመጡ በኃላ ባለቤትና ከልካይ የሌለው ዜጋ

አገኙ፡፡ እጅግ አድርገው ናቁን፡፡ የዜግንነትና ሉዓላዊ ክብር የሚነካ ስድብ

ይሰድቡናል፡፡ ለመናገር የማይቻል ፀያፍ ስድብ ይሰድቡናል፡፡ በሥራ

ምክንያት ለሚደርስ የአካል ጉዳት ህክምናና ካሳ አገልግሎት መክፈል የለብንም

ብለው ያምናሉ፡፡ በሠራተኛ ማህበር ተደራጅቶ መብትን መጠየቅ ትልቅ

ወንጀል አድርገው ያያሉ፡፡ በሴቶች ላይ የሚፈጽሙትን አስገድዶ መድፈር

እንደመብታቸው ይቆጥሩታል፡፡ በኢትዮጵያ ህግ አንተዳደርም ብለው

አምነዋል፡፡ ከመንግሥት ጋር ያላቸውን ውል አናውቅም፡፡ በአዋጅ 377/96

ተከሰን ለአንድ ሠራተኛ አንድ ሺ ብር ከምንከፍል ለአንድ ባለሥልጣን አንድ

ሚሊዮን ዶላር ሰጥተን ጉዳዩን ብንጨርስ ይሻላል ይላሉ፡፡ ምክንያቱን

ሲገልጹ ለዘላቂ ጥቅም ለወደፊት ዓላማችን ይበጀናል ብለው ያምናሉ፡፡ እረፉ

የሚላቸው ህግም ባለሥልጣንም ባለመኖሩ አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በቻይናዊያንና በኢትዮጵያኖች መካከል

የሚነሳ አለመግባባቶችን በህግ ለመዳኘት ችግሩ ምንድነው

ይላሉ?

ይህ መንግሥት ካለበት ውጫዊና ውስጣዊ ችግር ምክንያት ይመስለኛል፡፡

መንግስት ከምዕራባዊያንና ከአሜሪካውያን ፊት ስላጣ ሙሉ በሙሉ በሚባል

መልኩ ግንኙነቱን ወደ ቻይና አድርጓል፡፡ ቻይናን እንደ ከለላ መያዣ የፈለገ

ይመስለኛል፡፡ ስለዚህ በምንም መልኩ የቻይናን ኩባንያ በአገሬ ላይ በዜጐች

ላይ ይህንን አትፈጽሙ ለማለት ሞራል አላገኘም፡፡ እንዲያውም ከቻይና ጋር

ግንኙነቱን ካረጋገጠና ካጠናከረ ጀምሮ ራሱ የእኛ መንግሥት በአገሪቱ ውስጥ

ያለው የሰብአዊ መብት ጥሰት በእጅጉ ተጠናክሮ ቀጥሎአል፡፡ ልክ እንደቻይና

ገዢው ፓርቲ ከሚያራምደው አመለካከትና ሐሳብ ውጪ አማራጭ

ሐሳብን ማራመድ ከባድ ውንጀል እየሆነ ነው፡፡ ሚዲያውም የተለየ ሐሳብ

እንዲያንሽራሽር አይፈልግም፡፡ በተጨማሪ ካለብን ድህነት ችግር በዜጐች

ላይ የሚፈጸመውን ግፍና በደል አፍኖ እርዳታና ብድር ማግኘትን መርጧል፡

፡ መንግስት ከዜጐች ይልቅ ገንዘብን የመረጠ ይመስላል፡፡ ምናልባትም የተለየ

ውልና ስምምነትም ሊኖራቸው ይችላል፡፡

በመጨረሻም ያልጠቀስኩት ነገር አለ ካሉ አጠር አድርገው

መግለጽ የሚፈልጉት ሐሳብ ይኖራል?

በመጀመሪያ አሁንም እንደትላንትናው ደግመን ደጋግመን የምንጠይቀው

መንግስት ኃላፊነቱን ይወጣ ነው፡፡ የአገሪቱን ህገመንግስትና ያወጣቸውን

አዋጆች ያስከብር፡፡ የዜጐችን በደልና ግፍ ያድምጥ፡፡ መፍትሄ ይሰጠን

እንላለን፡፡ በሁለተኛ ደረጃ የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች ነን፤ የፆታ ጥቃትን

እንታገላለን፤ የሚሉ ሁሉ ጩኽታችንን ሰምተው ከጐናችን እንዲቆሙ

በሠራተኛው ስም ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡ በገዛ አገራችን እየተፈፀመብን ያለውን

እጅግ ዘግናኝ ግፍና ሰቆቃ በገለልተኛ አካል ተጣርቶ እርምጃ እንዲወሰድ

እንዲደረግልን፤ ህክምና ምግብ አጥተው በስቃይ ላይ ላሉ የጥቃት ሰለባዎች

እርዳታ ድርጅቶችም ሆኑ የመርዳት አቅም ያላቸው ሁሉ እጃቸውን

እንዲዘረጉልን፤ አሁንም በሠራተኛ ማሕበሩ ስም እማፀናለሁ፡፡ በመጨረሻም

መላው ኢትዮጵያውያን ሁሉ በአገሩ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ግፍ ይረዳልን

ማለት እውዳለሁ፡፡

እርማት

በፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ 2ኛ ዓመት ቅጽ 2 ቁጥር 14 ረቡዕ ጥቅምት 22 ቀን 2004ዓ.ም በወጣው እትም ዝግጅት ክፍላችን ከተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ ጋር ቆይታ ማድረጉ

ይታወቃል፡፡ በገጽ 6 አራተኛው አንቀጽ በስምንተኛው ስንኝ ላይ በሰጡት መልስ “የኢሰፓ አባል ነበርኩ” የሚለው በመቅረፀ ድምጽ ጥራት የተፈጠረ ችግር ስለሆነ

“የኢሠፓ አባል አልነበርኩም” ተብሎ እንዲታረም እየገለጽን ለተፈጠረው ስህተት አንባቢያችንንና የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉን ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.15

በተስፋዬ ደጉ

ወቅታዊ

ሐሙስ ጥቅምት 2 ቀን 2004 ዓ.ም ከጠዋቱ አራት

ሰዓት ላይ በመድረክ ጽ/ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ

እየተሰጠ ነው፡፡ በስድስት የተቃዋሚ የፖለቲካ

ፓርቲዎች የተመሰረተው መድረክ፣ ከቅንጅትነት

ወደ ግንባርነት መሸጋገሩን ለማብሰር፡፡ የየፓርቲዎቹ

አመራሮች ጋዜጣዊ መግለጫውን ለመስጠት

መድረኩን ይዘዋል፡፡ የአገር ውስጥም የውጭ አገርም

በርካታ ጋዜጠኞች ሁኔታውን ለመዘገብ በቦታው

ተገኝተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም ካሜራዎቹን

ደቅኖ ከአንድ ሰዓት በላይ የተካሄደውን ጋዜጣዊ

መግለጫ እየቀረፀው ይታያል፡፡ መግለጫው ተነበበ፡

፡ መድረኩ ለጋዜጠኞች ክፍት ተደረገ፣ ለአመራሮቹ

ጥያቄ እንዲያቀርቡ፡፡

የመጀመሪያዎቹ ሦስት ጥያቄዎች ከጋዜጠኞቹ

ከተሰበሰቡ በኋላ፣ ለጥያቄዎቹ መልሶች መድረኩ ላይ

ያሉት ዶ/ር መረራ ጉዲና መልስ መስጠት ጀምረዋል፡

፡ ለመጀመሪያዎቹ ሁለት ጥያቄዎች በእርጋታ መልስ

ሰጡ፡፡ ሦስተኛውን ጥያቄ ሲመልሱ ግን የተቆጡ

መሰሉ፡፡ “እናንተ የኢሕአዴግ ካድሬዎች ግን

መቼ ነው ፕሮፓጋዳችሁን መንዛት የምታቆሙት?

መቼ ነው የምትተውን?” በማለት ጥያቄውን

ወደ ጠየቃቸው ጋዜጠኛ እንደዋዛ እየተመለከቱ

ጥያቄያቸውን ሰነዘሩ፡፡ ጋዜጠኛውም “ከኢሕአዴግ

ቢሮ አልመጣሁም፡፡ የሬዲዮ ፋና ጋዜጠኛ ነኝ፡

፡” ብሎ ጥያቄቸውን መለሰ፡፡ ዶ/ር መረራም

ሃሳባቸውን ቀጠሉ፡፡ “ጋዜጠኛ ብትሆኑማ ጥሩ ነበር፡

፡ የኢሕአዴግ ካድሬ እየሆናችሁ አስቸገራችሁን

እንጂ፡፡” የሚል ምላሽ ከፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት

ለመጣው ጋዜጠኛ ሰጡ፡፡

ከፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት የመጣው ጋዜጠኛ

የጠየቀው ጥያቄ ያጠነጠነው የመድረክ “ግንባርን”

የፈጠሩት ስድስቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያላቸውን

የአይዲዮሎጂ ልዩነትን የተመለከተ ነው፡፡ ጋዜጠኛው

ስድስቱ ፓርቲዎች ያላቸው ተቃራኒ ሊባል የሚችል

የአይድዮሎጂ ልዩነት “ግንባር” ለመፍጠር

እንደማያስችላቸው ጠቃቅሶ፣ በመካከላቸው ያለውን

የአይዲዮሎጂ ልዩነት የት እንዳደረሱት የሚሞግት

ዓይነት ነበር፡፡

ከመለስተኛዋ መመላለስ በኋላ ዶ/ር መረራ ጉዲና

ለተጠየቀው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በዚህም

ምላሻቸውም አገራችን ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት

ዘርፈ ብዙ ችግሮች፤ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓቱ

መገታቱ፣ የኢሕአዴግ አምባገነን ፓርቲ እየሆነ

መሄድ፣ የዜጐች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች

መታፈን፤ የገዢው ፓርቲ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና

የመገናኛ ብዙሃንን ሙሉ በሙሉ በራሱ ቁጥጥር

ሥር ማዋሉና አገራችን ያለችበት አጠቃላይ ቀውስ

በተሰባሰቡት ወቅት በተቃዋሚዎች መካከል

ያለውን የአዲዮሎጂ ልዩነትን በሁለተኛ ደረጃ ላይ

እንዳስቀመጠው ገልፀዋል፡፡ አክለውም መድረክ

በመለስተኛ ፕሮግራሙ ያስቀመጣቸው ነጥቦችም

የጋራ መታገያቸው መሆናቸውን ገልፀው፤ የመድረክ

ዓይነት ግንባር በመፍጠር በጋራ አገር መምራትም

በሰለጠኑት አገራትም ጭምር የተለመደ አካሄድ

መሆኑን የጀርመንና የእስራኤልን ተሞክሮን ዋቢ

አድርገው አብራርተዋል፡፡

ማታ በሁለት ሰዓቱ የአማርኛ ዜና ላይ የመድረክ

ከቅንጅት ወደ ግንባር መሸጋገሩን ከደቂቃዎች

በላይ ባልፈጀ ዜና የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተናገረ፡፡

ሬዲዮ ፋናም በድረ ገጹ ላይ ባንድ መስመር ዜናውን

አስፍሮት ተስተዋለ፡፡

የመገናኛ ብዙሃንና ነፃነት

በማንኛውም አገር ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን

ለመመስረት መገናኛ ብዙሃን የሚያበረክቱት

አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ መገናኛ

ብዙሃንም ሊያበረክቱት የሚችሉት አስተዋፅኦም

ባላቸው የነፃነት መጠን ላይ ተንጠልጥሎ ይገኛል፡

፡ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ስንልም የሃሣቦች ብዝሃነት

(plurality of ideas) ዋነኛው አምድ መሆኑን

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ ጥቅምት 28 ቀን 2004 ዓ.ም.

የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን በሕገ-መንግሥቱ እውቅና የተሰጣቸውን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትንና የተለያዩ አስተሳሰቦችን ማስተናገድ ግዴታ እንዳለባቸው ተደንግጓል፡

፡ ዴሞክራሲና መገናኛ ብዙሃን በጣም የተቆራኙ በመሆናቸው፤ አንዱን ከአንዱ ለይቶ ለማየት እስኪያስቸግር ድረስ ተደጋጋፊ ናቸው፡፡ የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ደግሞ

ከየትኛውም የአገራችን የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት በበለጠ፤ ለሕዝብ ዓይንና ጆሮ በመሆን ሕገ-መንግሥቱ በተለያዩ ምክንያቶች ሲጣስ ለሕዝብ የማሳወቅ ግዴታ አለባቸው፡፡

የሕዝብን ፍላጐት ግምት ውስጥ በማስገባት ምላሽ መሰጠት የሚችሉ ፕሮግራሞችን ማዘጋጀትም ሌላው ኃላፊነታቸው ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ላይ መጠነኛ የዳሰሳ

ጥናት ያደረገው ተስፋዬ ደጉ ይሄን ለማድረግ እስካሁ ያልቻሉት “ከገዢው ፓርቲ በኩል የሚሰነዘር ጫና” በመኖሩ መሆኑን ሊያሳየን ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሮልናል፡፡

ኢሕአዴግና መገናኛ ብዙሃን

ካሰብን ደግሞ ከኢ-ዴምራሲያዊ ጣልቃ ገብነትና

ተፅዕኖ ነፃ በሆነ መልኩ መደራጀታቸውና ስራቸውን

ማከናወናቸው፤ ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱን በአጭር

ጊዜ ለመመስረት የሚያስችል የማይተካ ሚና

እንዳላቸው መረዳት ይቻላል፡፡

መገናኛ ብዙሃን ላይ የተሰሩ በርካታ ጥናቶች

እንደሚያሳዩት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመመሥረት

በመንገድ ላይ ያሉት በርካታ የአፍሪካ አገሮች

ከመድበለ ፓርቲ ይልቅ ወደ አንድ ፓርቲ አገዛዝ

እየሄዱ መሆኑን ያሳያል፡፡ በየአገራቱ መንግሥት

የሚያስተዳድራቸው ብዙሃን መገናኛዎች በስልጣን

ላይ ያለውን ገዢ ቡድን እንጂ የተለየ ድምፅ

ለማሰማት በራቸውን ዘግተው ተቀምጠዋል፡

፡ በመሆኑም በእነዚህ አገራት የዴሞክራሲያዊ

ሥርዓት ግንባታ ሂደቱ ፈተና ላይ የወደቀው የአንድ

ፓርቲ አገዛዝ ሥርዓት በመመስረቱ ብቻ ሳይሆን

የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ከገዢው ፓርቲ ሃሳቦች

በስተቀር ለሌሎቹ ወይም ለተቃዋሚዎቹ ዕድል

አለመስጠታቸው ነው፡፡ ሲከፋም አሉታዊ ይዘት

ያላቸውን ዘገባዎችን ማቅረብና “የስም ማጥፋት”

ዘመቻዎችም ሲቀርብባቸው ይስተዋላል፡፡ እዚህ

ጋ የዜናዎቹ /የዘገባዎቹ ሚዛናዊነት፣ ትክክለኛነት

ወይም እውነተኛነት የመሳሰሉት የጋዜጠኝነት ስነ-

ምግባር የሚጠይቃቸው እሴቶች አስታዋሽ ያላቸው

አይመስሉም፡፡ እነዚህ ሆን ተብሎ የሚዘነጉ እሴቶች

ደግሞ ለሃሳብ ብዝሃነት (plurality of ideas)

ዋስትና፣ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ደግሞ

መሠረት ናቸው፡፡

ሮኒንግ ሄልግ “The Role of Media in Democracy”

በተባለው መጽሐፍ እንዳስረዱት መገናኛ

ብዙሃን ከመንግስት ወይም ከገዢ ፓርቲ ቀጥተኛ

ጣልቃ ገብነት ነፃ ሆነው መደራጀታቸው በጣም

አስፈላጊ የሚሆነው፤ መንግስት ስልጣኑን አላአግባብ

እንዳይጠቀም ለመከላከል መሆኑን ያስረዳሉ፡፡

ምናልባት የመንግሥትን ስልጣንን የያዙ ግለሰቦች

ስልጣናቸውን ለራሳቸው ግላዊ ጥቅም ቢያውሉት

የህዝብ ዓይንና ጆሮ ሆነው የሚያገለግሉት መገናኛ

ብዙሃን “ስህተቱን” ለሕዝብ ያሳውቃሉ፡፡ መረጃው

የደረሰው ሕዝብም፤ ያጠፉት ወኪሎቹን ማብራሪያ

ከመጠየቅ ጀምሮ ውክልናውን እስከማንሳት የደረሰ

እርምጃ ሊወሰድባቸው ይችላል፡፡ ይህ ሊሆን

የሚችለው ግን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በመሰረቱት

እንደ አሜሪካና በምዕራብ አውሮፓ ባሉ አገራት

ነው፡፡ በኢትዮጵያስ?

ሁለቱ ወንበሮች

ወንደስን አለሙ (ስሙ ለዚህ ፅሑፍ ተቀይሯል) እንደ

ፖለቲካል ሳይንስ ተማሪነቱ የገዢው ፓርቲን ሁለት

ወንበሮች ለመለየት እንደሚቸግረው ይናገራል፡፡

እንደ ፓርቲ ስለየትኛውም ፖለቲካዊ ጉዳዮች የራሱን

አቋም መያዝ መብቱ መሆኑን የሚቀበለው ቢሆንም፤

የፓርቲውን አቋም ህገ-መንግሥቱን በመጣስ ጭምር

በመንግሥታዊ ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ መግባቱን ግን

አምርሮ እንደሚቃወመው ይናገራል፡፡

የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ዶ/ር

ኃይሉ አርአያ “መድበለ ፓርቲ በኢትዮጵያ የወደፊት

ዕጣፋንታ” በሚለው ጥናታቸው ላይ እንደገለፁት

“ከምርጫ 2002 በኋላ ኢሕአዴግ አምባገነናዊ

አውራ ፓርቲ ሆኖ ወጥቷል፡፡ ወደዚህ የደረሰበት

መንገድም ከምርጫ 97 በኋላ በወስዳቸው

ኢ-ዴሞክራሲያዊ እርምጃዎች ነው፡፡” ይላሉ፡

፡ ዝርዝራቸውን ለመቁጠር ወደ ጣቶቻቸው

እየተመለከቱ፡፡ “የመጀመሪያው ነፃው ፕሬስን

ለማዳከም የወጣው የሚዲያ አዋጅ፣ ሲቪክ

ማህበራትን ተሳትፎ ለመቀነስ የወጣው አዋጅ፣

የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ደካማ ለማድረግ የወጣው

አዋጅና የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ” መሆናቸውን

ይገልፃሉ፡፡

ይሄው የዶ/ር ኃይሉ ተመሳሳይ ጥናት

እንደሚያስረዳው ኢሕአዴግ አውራ ፓርቲ ሆኖ

ለመውጣት የቻለው “ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን

በማፈንና ነፃና ፍትሃዊ ባልነበረ ምርጫ በ2002

በማሸነፉ” ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ኢሕአዴግ

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ “አምባገነናዊ አውራ

ፓርቲ” እንጂ፣ “አውራ ፓርቲ” እንዳልሆነ

ይደመድማሉ፡፡ ሃሳባቸውን በመቀጠልም

“አምባገነናዊ አውራ ፓርቲዎች ባሉበት አገራት

ገዢው ፓርቲንና መንግሥትን መለየት አለመቻል፣

ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ መሰረት

የሆኑ ነፃ የሚዲያ፣ የፍትህ፣ ሲቪክ ማኅበራትና

የምርጫ አስፈፃሚ አካላት አለመኖር፤ ዋና ዋናዎቹ

መገለጫዎቹ” መሆናቸውን አስታውሰው፤

የአገራችን ነባራዊ እውነታም ይሄንኑ እንደሚያሳይ

አስረድተዋል፡፡

የገዢው ፓርቲ ይፋዊ ህትመቶች እንደሚያትቱት

ደግሞ መንግሥት (ኢሕአዴግ ለማለት ነው) የግሉን

የመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ፤ “ሊቆጣጠረው” የሚገባው

የአሁኑ ታዳጊ ዴሞክራሲያችን “እንዳይቀለበስ”

ለመጠበቅ ነው፡፡ እነዚህ ይፋዊ ህትመቶችና አልፎ

አልፎም የፓርቲው ሹማምንት እንደሚያስረዱት

“ኢሕአዴግ የጀመረው የዴሞክራሲያዊ ስርዓት

ግንባታ ሊቀለበስ በማይችልበት ደረጃ ላይ

ገና አለመድረሱን ነው፡፡ ለዚህም ክርክራቸው

የሚያቀርቡት ማስረጃም በምርጫ 97 ጊዜ ነፃው

ፕሬስ ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጐን

“መሰለፉ” የሚያሳየው ሐቅ ቢኖር፣ “ነፃው ፕሬስ”

ከ “ኢ-ዴሞክራሲያዊ” ኃይሎች ጋር በማበር

“ዴሞክራሲውን” አደጋ ላይ የመጣል አቅም

እንዳለው ማሳየቱን የፓርቲው ህትመቶች ይገልፃሉ፡፡

የዶ/ር ኃይሉ ጥናት የሚያሳየው ግን በሚድያ ህጉ

እንደታየው የኢሕአዴግ ዓላማ ዴሞክራሲያዊ

ስርዓቱን ለማፈን እንጂ ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱን

ለመጠበቅ የተሰራ አለመሆኑን ነው፡፡ የምሁሩ ጥናት

እንዲማሳየው የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት በኢትዮጵያ

ለወደፊት የሚኖረውን ዕጣ ፈንታን በተነተኑበት

ፅሁፋቸው እንደደመደሙት ኢህአዴግ በሥልጣን

ላይ እስካለ ድረስ የመነመነ ነው፡፡ እኚህ የአንድነት

ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ከፍተኛ

አመራር እዚህ መደምደሚያ ላይ ያደረሳቸውን

ምክንያት ሲገልፁ ገዢው ፓርቲ ከምርጫ 97

ያልጠበቀው ሽንፈት ወዲህ ያፀደቃቸውን አፋኝ

አዋጆችን ነው፡፡ አዋጆቹም የመገናኛ ብዙሃን

አዋጅ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ማቋቋሚያ አዋጅ፣

የሲቪክ ማኅበራት አዋጅና የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ

መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡ የምሁሩ ጥናታዊ ፅሁፍ

እንደተነተነው እነዚህ አራት አዋጆች በአገራችን

የዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ለማጐልበት እንዲረዱ

በማሰብ ሳይሆን የፀደቁት፣ ይልቁንም ኢህአዴግ

አምባገነናዊ አውራ ፓርቲ ሆኖ እንዲቀጥል፣

ተቺዎቹንና ተቃዋሚዎቹን ከፖለቲካው ጨዋታ

ውጭ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ያሰምሩበታል፡፡

ዶ/ር ነጋሶና አንቀፅ 29

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የአንድነት ለዴሞክራሲና

ለፍትህ (አንድነት) ፓርቲ ሊቀመንበር ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ህገ-መንግሥት ከያዛቸው ከመቶ በላይ

አንቀፆች መካከል አንቀጥ 29ን የበለጠ የሚወዷት

ያስመስልባቸዋል፡፡ ፓርቲያቸውን ወክለው

በተገኙበት ቦታ ሁሉ፣ በጋዜጠኞች ቃለ-መጠይቅ

ሲደረግላቸው….. ሁልጊዜም አንቀጽ 29 ሳያነሷት

አያልፉም፡፡

ዶ/ር ነጋሶ “ሃሰብን በነፃነት የመግለጽ መብት ” የህገ-

መንግሥት አርቃቂ ኮሚሽን ውስጥ በነበሩበት ወቅት

የፀደቀ አንቀጽ ነው፡፡ሕገ-መንግስቱም በ1987 ዓ.ም

በርሳቸው የመጨረሻ ፊርማ ፀደቀ፡፡ ፕሬዚዳንት

ስለነበሩ፡፡ ትዝታቸውንና ተስፋቸውን ወደኋላ

ተመልሰው ሲያስታውሱ “ዜጐች የተቃውሞም

ይሁን የድጋፍ ሃሳባቸውን በነፃነት እንዲገልፁ

ዋስትና እንዲሆናቸውና፤ የመንግስት መገናኛ

7

ብዙሃንን ጭምር ተጠቅመው ለሕዝብ ማድረስ

ዕድል ይሰጣቸዋል” በሚል እንደነበር ይናገራሉ፡፡

ሕገ-መንግሥቱ ሥራ ላይ ከዋለ አስራ አምስትና

አስራ ስድስት ዓመታት በኋላና ከኢሕአዴግ የፓርቲ

አባልነት ራሳቸውን ካገለሉ አስር ዓመታት በኋላ

ግን፤ ተስፋቸው አይናቸው እያየ እንደጉም መትነኑን

ይናገራሉ፡፡ ገዢው ፓርቲ ወደለየለት አምባገነንነት

የገባው በዋናነት ከ1993 ወዲህ ሲሆን፣ በተለይ

ግን ከምርጫ 97 ወዲህ መሆኑን ያስምሩበታል፡፡

ለዚህ መከራከሪያም የሚያቀርቡት ማስረጃም ህገ-

መንግሥቱንና የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁን በማነፃፀር

ነው፡፡ “የህገ-መንግሥቱ አንቀጽ 29 ሃሳብን በነፃነት

መግለፅን የሚያበረታታ ሲሆን፣ የፀረ-ሽብርተኝነት

አዋጁ ግን ወንጀል የሚያደርግ ነው፡፡” ይላሉ፡

፡ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲዊ ሥርዓት ለመመሥረት

እነዚህ ሁለት ህጐች ሊያበረክቱት የሚችለውን

አስተዋፅኦ ሲያነፃፅሩት ደግሞ “አንቀጽ 29

የሚያበረታታና ገንቢ ነው፡፡ አዋጁ ግን የሚገታ ብቻ

ሳይሆን ዜጐች በፍርሃት እንዲኖሩ የሚያስገድድ

ነው፡፡” በማለት ተናገሩ ፡፡ “የሚያሳዝነው

ደግሞ አዋጁን እየጠቀሱ፤ አንቀጽ 29ን ሲጥሱ

መመልከታችን ነው፡፡ የአንዱዓለም አራጌና

የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋም እስር የዚህ ውጤት

ነው፡፡ ሁላችሁም በነበራችሁበት፣ በዚሁ መድረክ

ላይ ሁለቱም ያሉት በአዲሱ ዓመት በ2004 ዓ.ም

በአገራችን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመመሥረት

በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ለመታገል እንዘጋጅ

ነው፡፡ ይህ በህገ-መንግሥቱ የተረጋገጠ መብት

ነው፡፡ ወንጀል አይደለም፡፡ ወንጀል የሚደረገው

በኢሕአዴግ ነው፡፡” በእጃቸው መድረኩን እያሳዩ

ንግግራቸውን ጨረሱ፡፡

እንደምን አመሻችሁ ዲሽ የሌላችሁ

ከአራት ኪሎ ተነስተው ፒያሳ እንደገቡ ቀዝቀዝ

ያለ አየር በሚነፍስበት ጥግ ቀዝቀዝ ያለ ገበያ

ያላቸው ሁለት ሱቆች ይታያሉ። የመጀመሪያው

ሱቅ ስም አልባ ቢሆንም በመስታወቱ ወደ ውስጥ

ዘልቆ አተኩሮ ለተመለከተ የኤሌትሪክ ዕቃዎች

መሸጫ መሆኑን መለየት ይቻላል። ሁለተኛው ሱቅ

አጠገብ ያለው ደግሞ ለብዙ ዓመታት መስታወቱ

ላይ በለጠፈውና የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ድርጅት

ለሚሰጠው አገልግሎት ከደንበኞቹ ክፍያ መቀበያ

መሆኑን የሚገልፀው ማስታወቂያ ያለበት ቢሮ ነው።

ዛሬ ግን አዲስ የሚመስል ነጭ ባነር ላይ “የቴሌቪዥን

ባለቤትነት ማረጋገጫና የቴሌቪዥን አገልግሎት

ክፍያ መሰብሰቢያ” መሆኑን የሚገልፅ ፅሁፍ ሻተሩ

ላይ እንደነገሩ ተንጠልጥሎ ይታያል። በሩ ክፍት

ነው። ሰው ሲገባም ሆነ ሲወጣ አይታይም። ክፍሉ

ውስጥ የሚታየው ደብዘዝ ያለ ብርሃን ክፍሉን

ህይወት አልባና ፈዛዛ ድባብ አላብሶታል። ፒያሳ

ውስጥ ያለ አይመስልም።

በ1957 ዓ.ም የተመሠረተው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን

ዛሬም ድረስ ብቸኛውና በመንግስት ቁጥጥር

ስር ያለ ጣቢያ ነው። ኢሕአዴግ ወደ ስልጣን

እንደመጣ ነፃ ፕሬስ እንዲቋቋም ቢፈቅድም

የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያውን ግን ለግል ባለሃብቶች

እንደማይፈቅድ በተደጋጋሚ ሲገልፅ መሰንበቱ

ይታወሳል። ፓርቲው እዚህ አቋም ላይ የደረሰበትን

ምክንያት ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች በባህሪያቸው

ሰፋ ላለው የህብረተሰብ ክፍል በቀላሉ መድረስ

የሚችሉ በመሆናቸው እነሱን ተጠቅሞ የሚደረግ

“ቅስቀሳ” አገሪትዋን ወደ መተላለቅና ወደ መበታተን

ሊያደርሳት መቻሉን ነው። ነፃው ፕሬስስ ? እሱማ

በከተሞች አካባቢና በተማረው የህብረተሰብ

ክፍል ብቻ ተደራሽ በመሆኑ ያን የሚያህል

አቅም አይኖረውም ተብሎ በመታሰቡ ነው።

ይህ የተጠቀሰው የፓርቲው መሠረታዊ ፍልስፍና

ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የተቀየረው ከ1997ቱ

ምርጫ በኋላ ይመስላል።

ወደ 14 ይዞሯል

www.andinet.org.et

8

ከመ/ር ደረጀ መላኩ

www.andinet.org.et

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ ጥቅምት 28 ቀን 2004 ዓ.ም.

ኢትዮጵያውያን ሁሉ ኡኡ!

ሪፖርተር ጋዜጣ ጥቅምት

5, 2004 ቅፅ 16.ቁ.5/1197

ግንባር ቀደም ዜናው ላይ

ካራቱሪ የህንድ ገበሬዎችን ሊያሠፍር

ነው በሚል ርእስ ስር ለኢትዮጵያ ህዝብ

መርዶ አሰምቷል፡፡ አስደንጋጩ መርዶ

የሚከተለውን ይመስላል፡፡

ካራቱሬ አዲስ ባወጣው ህግ 20 ሺ

ሄክታር መሬት ላይ የሕንድ ገበሬዎችን

ለማሠራት ወስኗል፡፡ “ከገበሬዎቹ ቀና ምላሽ

አግኝተናል፡፡ መሬቱን እውቀቱ ባላቸው

ገበሬዎች እናለማለን” ሲሉ የኩባንያው ሃላፊ

ገልፀዋል::

“የገቢ ትርፋችን 65 በመቶ ለ35 በመቶ

ሆኖ ከገበሬዎቹ ጋር ገቢውን እንጋራለን”

ሲሉ ለህንዱ ቢዝነስ ስታንዳርድ ጋዜጣ

ገልፀዋል፡፡ ገበሬዎችን ወደ ኢትዮጵያ

የማምጣት ሂደት የሚቀጥል ሲሆን

በሁለተኛው ዙር 50 ሺህ ሄክታር መሬት

ላይ ተጨማሪ ገበሬዎችን እንደሚያስፍሩ

ሀላፊው ተናግረዋል፡፡

የኩባንያው እቅድ እንዳልገባቸው

የጋምቤላ ምክትል ፕሬዜዳንት አቶ ጋነርየር

ሲናገሩ “እኛ የምናውቀው ካራቱሪን

እንጂ የሕንድ ገበሬዎችን አይደለም” ሲሉ

አዲሱ እቅድ ግር እንዳሰኛቸው ገልፀዋል፡

፡ በሌላ በኩል አገዛዙ በፌዴራል ግብርና

ቢሮ ግብርና ኢንቨስትመንት ድጋፍ ሰጭ

ዳይሮክቶሬት ዳይሪክተር በሚል ማዕረግ

የሾማቸውን ግለሰብ ስማቸው አቶ ኢሳያስ

ከበደ ይመስሉኛል አስተያየታቸውን

ለማካተት የጋዜጣው ሪፖርተር ጥረት

አድርጎ እንዳልተሣካለትም አስነብቦናል፡

፡ ከቶ ለመሆኑ ይሄን ትልቅ ሀገራዊ ጉዳይ

በተመለከተ የመአከላዊውን መንግስት አቋም

የሚነግሩን ውጪ ሀገር ለስራ ጉዳይ የሄዱት

ተሻóሚ ብቻ ናቸው? አይሠማም እየተባለ

ነው? ግራም ነፈሰ ቀኝ በኢኮኖሚ ጉዳዮች

ላይ የምታጠነጥ ነው ፎርቹን የእንግሊዝኞ

ጋዜጣ ጥቅምት 5,2004 ዓ.ም እትሟ

ላይ ስለዚሁ አሣሣቢ ጉዳይ ሰፊ ሽፋን

ሰጥታ አስነብባናለች፡፡ አዎ የጋዜጠኞች

ዋነኛ ሥራ እውነተኛ የዜና ምንጭ መሆን

አይደል? በእውነቱ ለመናገር የሁለቱም

ጋዜጦች አዘጋጆች አገራዊ ግዴታቸውን

በመወጣታቸው ሊመሠገኑ ይገባል፡፡

ይሄን ካልኩ ቀጥታ ወደ ተነሣሁበት ነጥብ

ልውሰዳችሁ::

እንደ ሥነ ህዝብ ጠበብት ከፍተኛ

ስጋትና ጥናት ከሆነ ሀገሬ ኢትዮጵያ እጅግ

በአጭር ግዜ ውስጥ ከ200 ሚሊዮን በላይ

ህዝብ ይኖርባታል፡፡ አሁን 90 ሚሊዮን

ደርሰናል፡፡ ዛሬ በወጣትነት እድሜ

የሚገኙና ህፃናቶች ወደ እማይቀረው

አለም ከመሄዳቸው በፊት ነው በኢትዮጵያ

መሬት ላይ ከላይ የተጠቀሰው ህዝብ

የሚኖርባት:: ለነገሩ የኢትዮጵያ መሬት

ከተሠራበትና በሀገር ፍቅር ስሜት የነደደ

እንዲሁም የተማረ እና በስልጣን ፍቅር

ያለበደ መሪ ብታገኝ ከ40 ሚሊዮን በላይ

ህዝብ እንደምት መግብ ብዙ ጠበብቶች

የመሠከሩት ጉዳይ ይመስለኛል፡፡ ለዚህ

አልታደልንም:: እና ዝንተ አለም ተመፅዋች

ሆነን ቀርተናል፡፡ ያሳዝናል:: ሌላው ቀርቶ

የሩቁን ትተን የቅርብ ጊዜውን ታሪካችንን

ብንፈትሸው አንገት የሚያስደፋ ነው፡

፡ ቀድሞ በየ አስርተ አመቱ (ከዚያ በላይ)

እየመጣ የሚቀጣን ድርቅና ጠኔ ዛሬ

“የዴሞክራሲ ስርዓት ጀማሪዎች ነን” እያሉ

ሌት ተቀን በተቆጣጠሩት የኤሌክትሮኒክስ

እና የህትመት መሣሪያዎቻቸው ዘወትር

የሚወተውቱት ገዢዎቻችን ቃል እና ተግባር

ያልተገናኙበት ጊዜና ሰዓት ላይ ደርሶናል፡፡

እንደ አሰልቺ ዲስኩራቸው ቢሆን

ኖሮ ሀገሬ ኢትዮጵያ ያልፍላት ነበር፡፡

ከራሷ ልጆች አልፋ ለሌሎች ለተቸገሩ ቀን

ለጨለመባቸው አለም ህዝቦች በደረሰች

ማለት ይገባናል

ነበር፡፡ ይህ ግን ከቶውንም ሲሆን አላየንም

(አልሠማንም)፡፡

በአንፃሩ ዜጎች “የዳቦ ያለህ” እያሉ

ይጠይቃሉ፡፡ ወይንም ፈጣሪያቸውን

ይማፀናሉ፡፡ “ምን አይነት ዘመን መጣን”

በማለት በእውነቱ ለመናገር ካለፉት

20 አመታት ጀምሮ እንደ ትሮይ ፈረስ

የሚጋልቡን የደደቢት በርሃ ጨካኞችና

ጋሻ ጃግሬዎቻቸው ለኢትዮጵያ ህዝብ

ደረቅ ዳቦ እንኳን በስዓቱ ሊያቀርቡለት

አልተቻላቸውም፡፡ ወይንም የስራ ጀግና

የሆኑ ኢትዮጵያውያን በነፃነት ተንቀሳቅሰው

ሊሰሩ የሚችሉበትን ሁኔታ ማመቻቸት

አልቻሉም (አልፈለጉም)፡፡ ኢትዮጵያ እኮ

የወላድ መካን አይደለችም፡፡ ብዙ ምርጥ

ልጆች ሞልተዋታል፡፡

በቅርቡ እንኳን ለአለም አዳጊ አገር

ገበሬዎች መድህን የሆነ የአእምሮ ጭማቂ

ከኢትዮጵያዊው ሣይንቲስት ፕሮፌሰር

እጀታ ጋቢሳ እንደተገኘ አለም ሁሉ

የሚያውቀው እውነት ይመስለኛል፡፡

ኢትዮጵያ ግን ዛሬም ሊያልፍላት አልቻለም፡

፡ ከቶ ለምን ይሆን? የፕሮፌሰሩ የትውልድ

ቦታ ሣይቀር (ሆለታ) ሞልቶ የተረፈው

አይደለም፡፡ መቀመጫቸውን ዴንማርክ

ያደረጉት ፕሮፌሰር ማሞ ሙጬ በቅርቡ

ስለ ኮምፒዮተር እና ኢንተርኔት አስፈላጊነት

በጀርመን ድምፅ ተክሌ ይኋላ ጋር ቃለ

ምልልስ አድርገዋል፡፡ ከቃለ ምልልሱ

ለመረዳት እንደቻልኩት በ21ኛው ክፍለ

ዘመን ያለ ኮምፒዩተር እና ኢንተርኔት

እድገት ፈፅሞ አይታሰብም፡፡ ፕሮፌሰሩ

ያላቸውን ጥልቅ እውቀት ለሀገራቸው

እድገት ማዋል ባለመቻላቸው በሀዘን

ሲናገሩም አድምጫለሁ፡፡ (የተጠቀሰውን

ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ ለማስፋፋት

ሁኔታው አመቺ ባለመሆኑ ለማት ነው)

የደስታ እና አባ ሠንጋ በሽታ ክትባት ግኝት

ባለቤት ፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ የት ገቡ?

ከ30 ሚሊዮን በላይ የቀንድ ከብት ከ50

ሚሊዮን በላይ ዶሮዎች …. ወዘተ ባለቤት

የነበረችው ኢትዮጵያ ዛሬ ያ ሀብቷ አለን?

በቦረና በሌሎች አካባቢዎች በድርቅ

ምክንያት በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ እንስሶች

ወደ ትቢያነት ሲቀየሩ አልሰማንም?

አፍንጫችን ሥር ያለችው ኬንያ ከኢትዮጵያ

ጋር በእንሥሳት ብዛት መወዳደር ቀርቶ

የምትደርስባት አይመስለኝም፡፡ ሆኖም ግን

በአለም ገበያ ላይ ጥራት እና ከፍተኛ ክብደት

ያለው ስጋ እና የሥጋ ውጤቶች (ከኢትዮጵያ

በብዙ የሚልቅ ማለቴ ነው) በየጊዜው

ትልካለች፡፡ ዛዲያ ለምን ለእማማ ኢትዮጵያ

ቀኑ ጨለመባት? ያለ ሥሟ ያለ ምግባሯ

የድሆች ደሀ ብለው ስም አወጡላት?

እንደሚመስለኝ ፕሮፌሰር ጥላሁን እና ሌሎች

ኢትዮጵያውያን ሀገር ቤት እውቀታቸውን

በተግባር እንዳያውሉ በሩ ስለተዘገባቸው

ነው፡፡ በአለምም ሆነ በአፍሪካ ደረጃ በንብ

አንቢነት ከሚተወቁት ሀገራት ኢትዮጵያ

ግንባር ቀደም ሀገር ነበረች፡፡ እውን ዛሬ

ታዲያ ልጆቿ የማር ተጠቃሚዎች ሆነዋል?

መልሱን ለአንባቢ ትቼዋለሁ፡፡ ኬንያ

ከኢትዮጵያ በተሻለ ሁኔታ የተማሩ ዜጎቿን

በማቅረቧ (በመያዟ) ከኢትዮጵያ የተሻለ

እድገት አሣየች፡፡ እኛ ግን ዛሬም እየዳከርን

እንገኛለን፡፡ ታሪክ እንደሚያስተምረን

በንጉሱ ዘመን ብዙ የተማሩ ኢትዮጵያውያን

ሀገራቸውን ለማግለገል ፍላጐት ነበራቸው፣

በደርግ ዘመን ፖለቲካውን ሣይተቹ

በሙያቸው የቀጠሉ መስራት የተከለከሉ

አይመስለኝም፡፡ በእርግጥ የደርግን መጥፎ

ድርጊት በመቃወም ስፍር ቁጥር የሌላቸው

ልጆቿ እንደ ጨው ዘር በአለም ተበትነው

ቀርተዋል፡፡ ዛሬ ደግሞ የጎሣ ፖለቲካ

ተጨምሮበት ከዚህ በፊት ታይቶ ተሠምቶ

በማይታወቅ ሁኔታ ብዙ ምኹራን ሀገር

ለቀው ሄደዋል፡፡ ኢትዮጵያን ከምኹራን

ፍልሰት ለመታደግ ዘላቂ መፍትሄ የተገኘ

አይመስለኝም፡፡ እንዲያውም ጉዳዩን

የሚያባብስ ድርጊት ተፈፅሟል፡፡ ከ1985ቱ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አመፅ

በኋላ ከ45 በላይ የዩኒቨርስቲው ነባር

እና ምርጥ መምህራን መባረራቸውን ልብ

ይሏል፡፡

ዛሬ ከሰውነት ደረጃ ዝቅ ብለን እንደ

እንስሳ ዝርያ እየፈለግን መቧደናችን

አሣዛኝም አሣፋሪም ነው፡፡ ከ1983ቱ

የደርግ ውድቀት ወዲህ በእያንዳንዳችን

አእምሮ ውስጥ የተዘራው የጎሳ ፖለቲካ

ውጤት እየታየ ነው፡፡ በወቅቱ 20 አመት

እድሜ የነበረን ዛሬ 40 አመት ሞልቶናል፡

፡ 40 እና ከዚያ በላይ እድሜ የነበራችሁ

ኢትዮጵያውያን የእድሜ ባለ ጸጎች 60

እና ከዚያ በላይ ሆኗችኋል፡፡ ከቶ ምን

ይሰማችሁ ይሆን? ያቺ የወተት እና የማር

ሀገር እንዲህ ስትራብ ስትጠማ? ፍሪምባ

ከቁርጥ አማርጣችሁ የተመገባችሁ እናንተ

ኢትዮጵያውያን፣ በ25 ሣንቲም ክትፎ

የበላችሁ የሀገሩ ሰዎች በእውን ኢትዮጵያ

እንዲህ ነበረች ብሎ ለሚጠይቃችሁ

የአሁኑ ጨለማና አሣፋሪ ጊዜ ሣይሆን

ያኔ ! ጥንት በጃንሜዳ በጥምቀት እለት

የሚደረገው የአንድነትና የፍቅር ዜማ ትዝ

ይላቹህ ይሆን? በደርግ ዘመን እንኳን

የ1975 ዓ.ም አካባቢ ጃንሜዳ ኢዲዩ ቤት

የሚባል ምግብ ቤት ነበር፡፡ ዛሬ ስለመኖሩ

አላውቅም፡፡ ክትፎ ላይ የተጨመረው ቅቤ

አነሰኝ ለሚል ደምበኛ ቅቤ በማንቆርቆሪያ

እየዞረ የሚጨምር እንደነበር በአይኔ

በብረቱ አይቻለሁ፡፡ ለዛውም ንፁህ የሸኖ

ቅቤ፤ ዋጋው ቢበዛ 10 አሊያም ከ15 ብር

አይበልጥም ነበር፡፡ ኢትዮጵያ ሀገራችን

የባህር በሯን በማጣቷ የጂኦ ፖለቲካዊ

ጠቀሜታዋ ከላይዋ ላይ ከተገፈፈ በኋላ

የተፈጠራችሁ ደግሞ 20 አመት እድሜ ላይ

የደረሳችሁ እናንት ሦታ ወጣቶች እኔ ማን

ነኝ? የሚለውን ጥያቄ ለራሳችሁ አቅርባቹሁ

ታውቁ ይሆን? አዎ እናንተ የባለ ታሪክ

ኢትዮጵያ ልጆች መሆናችሁን ለአፍታም

ቢሆን መዘንጋት የለባችሁም፡፡ የጎሳ ፖለቲካ

ሊያጠምቃችሁ የሚፈልገውን እኔ ሰው

ነኝ በማለት መከራከር ይገባችኋል፡፡ በጎስ

ሥርዓት ውስጥ የተፈጠራችሁ በመሆናችሁ

ጎሰኝነት ሊጣባችሁ ይችል ይሆናል፡፡ ግን

ራሳችሁን በራሳችሁ ከቶባችሁ ከጎሳ በሽታ

ተላቀቁ፡፡ የብሮዝ ቲቶ ሀገር የነበረችው

ይጎዝላቪያና የብሬዥኔቭ ሦቬየት ህብረት

እንዴት (ለምን) እንደተፈረካከሱ ታሪክን

መመርመር ተገቢ ነው፡፡ (ታሪክን መርምሩ)

ታላቁ የአፍሪካ ልጅ ኒልሰን ማንዴላ ለምን

አለም አቀፍ እውቅና እና ክብር ተሰጣቸው

ብላችሁ ጠይቁ፡፡

ስማቸውን በወርቅ ቀለም ያፃፉት

የሠላማዊ ትግል አስተማሪዎች የሆኑትን

ማህተም ጋንዲና ማርቲን ሉተር ኪንግን

የህይወት ታሪክ አንብቡ፡፡ እነ ወጣት

አቢቹ፣ ደጃች በላይ ዘለቀ፣ ኮሎኔል አብዲሳ

አጋ፣ ጄኔራል ተሾመ መተኪያ የሌላቸውን

ወድ ህይወታቸውን ለምን ለኢትዮጵያ

ሰውላት ብላችሁ ተመራመሩ፡፡ ጠይቁ?

የትናቷ ኢትዮጵያ ማር ወተት ቅቤ ነበረች፤

ጮማ ነበረች፤ ለዚች ቅዱስ ሀገር ነበር አፄ

ቴዎድሮስ ሽጉጥ ጠጥተው ለክብሯ ሱሉ

ሕይወታቸውን ያሳለፉላት፡፡ የሳቸውን

ፈለግ ተከትለው ሌሎቹም የሚሰውላት

በመሆኑም ይህ ትውልድም የሀገሩ ባለቤት

ለመሆን ራሱን መጠየቅ አለበት፡፡ አለበለዚያ

ጎሰኞች በጀመሩት ዕቅድ የሚገፉበት ከሆነ

(ከመግፋትም አይመለሱም) ከጥቂት

ዓመታት በኋላ የሕንድንና የቻይናን

ቱጃር እያሰፈሩ አገር አልባ አድርገው

እንደሚያስቀሩን ቅንጣት አትጠራጠሩ፡፡

በመሆኑም ጎሳ ሳንለይ እጅ ለእጅ እንያያዝ፡፡

ሰላማዊ ድምፃችንን በኡኡታ! እናሰማ፡፡

የአደባባይ ምስጢሮች

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.15

“ነፃ የሚያወጣኝ

መድረክ ነው

መሰለኝ”

“ኦነግን ሳላውቅ የኦነግ አባል የሆንኩ መሰለኝ” የሚለውን

ቃል የተናገሩት ከዛሬ ዘጠኝ ዓመት በፊት አንድ የዩኒቨርስቲ

መምህር ናቸው፡፡ በ1994 ዓ.ም ክረምት ላይ ጠ/

ሚኒስትር መለስ ዜናዊና አቶ ተፈራ ዋልዋ የከፍተኛ ትምህረት

ተቋም መምህራንን ረዘም ላሉቀናት ያወያዩ ነበር፡፡ አንድ

የዩኒቨርስቲ መምህር የኢህአዴግን የፍረጃ ፖሊሲ ለመግለጽ

ሲሉ የተጠቀሙበት ቃል ነበር፡፡ “እኔ የማንም ድርጅት አባል

አይደለሁም፡፡” አሉ መምህሩ ሲናገሩ “የማንም ድርጅት

አባል ለመሆን እቅድም የለኝም፡፡ ሐሳቤን በነፃነት እሰጣለሁ፡፡

የማላምንበት ነገር በነፃነት እከራከራለሁ፡፡ ኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ

ብቻ በመሆኔ የኢህአዴግ አባላት “የኦነግ አባል የኦነግ አባል!

እያሉ አሉኝ፡፡ ኦነግን እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ እንጂ በቅርብ

አላውቀውም፡፡ ኦነግ የእኔን ሐሳብ የሚያራምድ ድርጅት ነው?

ብዬ እንዳስብ እድርጐኛል፡፡ ኦነግን ሳላውቀው የኦነግ አባል

ሆንኩኝ እያልኩ አሰላስላለሁ” በማለት ጠ/ሚኒስትሩ ባሉበት

መናገራቸውን አስታውሳለሁ፡፡

ዛሬ ይህ ትዝ ያለኝ በተለያየ ጊዜ የተለያየ ስም እየተሰጣቸው

ተከሰው በነፃ ስለሚወጡ ሰዎች ሳስብና እንዲሁም ጐንደር

ላይ የገጠመኝ አንድ ገጠመኝ ትዝ ብሎኝ ነው፡፡ ኢህአዴግ

ሥልጣን እንደያዘ አካባቢ አምርረው ኢህአዴግን የተቃወሙ

ደርግ ኢሠፓ ቀይ ሽብር እየተባሉ ወህኒ ወረዱ፡፡ በአንድ ወቅት

ደግሞ መአህድ ሌላ ጊዜ ሌላ ስም እየተሰጠ ይታሰራሉ፡፡ አልፎ

አልፎ የህሊና ዳኛ ሲገጥማቸውም በነጻ ሲለቀቁ እሰማለሁ፡

፡ ዛሬ ደግሞ ጊዜው መድረክ ሆኖአል፡፡ በአንድ ወቅት ደቡብ

ጐንደር ደብረታቦር ከተማ የሰማሁትን ገጠመኝ ላካፍላችሁ፡፡

ከአካባቢው ገጠራማ ቦታ የመጡ አንድ አርሶ አደር አግኝቼ

ተግባባንና ጫወታ ጀመርን፡፡ ስለ ወቅቱ ዝናብ፣ ስለሰብሉ፣

ስለማዳበሪያው ዋጋ ሌላው ሌላውንም አንስተን በመጨረሻው

ወደ ፖለቲካው ገባን፡፡

“ካድሬው አላስቀምጥ አላሰራ አለን፡፡ “አዲሱ እረኛ

ከብትም አያስተኛ” እንደሚባለው አንዱን አውርደው አንዱ

ሲሾም ጥዋት ማታ ሰብስባ ወሬ ጭቅጭቅ ነው፡፡ የተስፋ ወሬ

ነው፡፡ የማዳበሪያው ዋጋ ሰማይ ወጣ ምንም የሚበጀን ነገር

አላገኘንም፡፡ ቅንጅት ይመጣል ብለን ስንጠብቅ በዚያው ቀረ፡

፡ ሰሞኑን ደግሞ መድረክ እየተባለ ነው፡፡ ምናልባት እንግዲህ

መድረክ ነፃ ያወጣን እንደሆነ በተስፋ እየጠበቅን ነው፡፡

አሉኝ እኔም ተገርሜ መድረክ እዚህ አለ እንዴ? አልኳቸው

“ኽረ የለም” ሲሉ መለሱልኝ፡፡ ለእናንተ የሚበጅ ወይም

የማይበጅ መሆኑን እንዴት አወቃችሁ አልኳቸው “ወያኔ ራሷ

ትነግረናለች” አሉኝ፡፡ እንዴት አልኳቸው “ወያኔ ከመጣችበት

ዘመን ጀምሮ የተረፈን ወሬዋ እና ውሸቷ ነው፡፡ የተረፈን፡፡

ያገኘነው፡፡ ድህነትና ውርደት ነው፡፡ ሁሉም ነገር ተወደደ፤

ገንዘብ አምጡ አምጡ ነው፡፡ ሰለቸን፤ የሚያሽንፋቸውና

ለእኛ የሚበጀን ድርጅት ብቅ ሲል ሬዲዮኑም ካድሬውም

ጥዋት ማታ ስም እየጠራ ይሳደባል፡፡ ተጠንቀቁ መጣባችሁ!

ሊያጠፋችሁ ነው! እያለ እንደ ልጅ ሊያታልለን ይሞክራል

ቅንጅት በነበረ ወቅት ቅንጅትን አውሬ አስመስሎ ሲነገረን ነበር፡

፡ ኋላ ላይ ስንሰማ እንዲያ የጠሉት የእኛን ጥያቄ ስለሚያነሳ

ነው አሉ፡፡ አሁን ደግሞ መድረክን እያሉን ነው፡፡ ታዲያ እኛም

ሰማን ሰማንና ጐበዝ ይኽ መድረክ የሚሉት ደግሞ እኛን ነፃ

የሚያወጣን ይሆናል ብለን አመንን፡፡ ለዚህ ነው መድረክ ጥሩ

ነው ያልኩህ” ሲሉ አጫወቱኝ፡፡ “እነሱ ከጠሉት የእኛ ነው

ማለት ነው፡፡” ሲሉ በለሆሳስ ነገሩኝ፡፡

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.15

ከአሸናፊ ደስታ ወንድም አገኘሁ

ወቅታዊ

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ ጥቅምት 28 ቀን 2004 ዓ.ም.

ሕወሓት ከደደቢት በረሀ መርሾ

ማሃል አገር ገብቶ ዙፋን ላይ ከተቀመጠበት ጊዜ

ጀምሮ በኢትዮጽያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ብዙ

ፍንዳታዎች ፈንድተው በብዙ ሚሊዮን ብር

የሚገመት የኢትዮጵያ ሕዝብ ንብረት ወድሟል፡

፡ በሰው ሕይወት ላይም እንዲሁ ብዙ ጉዳት

ደርሷል፡፡

ምንም እንኳን በዩኒበርሲቲው ላይ

የሳት ቃጠሎ ባይደርስበትም፣ “የአገሩን ሠርዶ

በአገሩ በሬ” በሚለው የአበው አባባል፣ባዕዳን

መምህራንን ተክተው ሲያስተምሩ የነበሩ

አንቱ የተባሉ አያሌ እውቅ ፕሮፌሰሮች ከሥራ

ገበታቸው ተባረዋል፡፡ ይህም በራሱ በወቅቱ

በትጉ መምህራን ሽብርና መቅሰፍት ነበር፡፡ በዚያን

ወቅት በዩኒቨርስቲው ውስጥ የተወሰደው ርምጃ

የመንፈስ ስብራት ዛሬም ድረስ ሊቃና አልቻለም፡፡

ያወቅት በጣም አስጊ እና አደጋ

የበዛበት ወቅት ስለነበር፣በወቅቱ የተባበሩት

መንግሥታት ዋና ጸሐፊ የነበሩት የግብፅ ተወላጅ

ቡትሮስ ቡትሮስ ጋሊን ለጉብኝት ወደ አዲስ አበባ

መምጣት ተቃውሞው ሰላማዊ ሰለፍ በወጡ

ተማሪዎች ላይ የጥይት በረዶ ተርከፍክሮባቸው

ተገድለዋል፡፡ ተማሪዎቹ ሰላማዊ ሰልፍ የወጡበት

ምክንያት ግልጽ ስለሆነ፣ከመናገር ተቆጥበን

አልፈነዋል፡፡

ወደ ተነሳሁበት ዋና ነገር ልመለስና

የመጀመሪያው የአዲስ አበባ ነዋሪ ሕዝብ

በሽብር ያናወጠው፣ማቄን ጨርቄን ሳይል

ቤቱን ሳይዘጋ የሌሊት ልብሱን እንደለበሰ፣ቀበሮ

እንደ ገባበት የበግ መንጋ ወደ እየአቅጣጫው

ያስፈረጠጠው፣ከባድ፣እጅግ በጣም ከባድ ፈንዳታ

ነፋስ ስልክ አካባቢ የፈነዳው ፍንዳታ ነበር፡፡

በዚያ አደጋ በተጋለጠ ስፈራ ላይ ያ

ፈንዳታ እንዲፈነዳ የተደረገው በዐፄ ኃ/ሥላሴ

ዘመነ መንግሥት ተገንብቶ አገልግሎት በመስጠት

ላይ የነበረን የሥንቅና ትጥቅ ዴፖ ለማውደም

ሲሆን አጋጣሚ ሆኖ በዚያ አካባቢ ይኖሩ በነበሩ

ነዋሪዎች ላይም በርካታ ቤቶች ተደርምሰዋል፡፡

በቃጠሎ ወድመዋል፡፡ ይህ ነው የማይባል ንብረት

ወድሟል፡፡ የሰው ሕይወት ሳይጠፋ አንዳልቀረም

ተገምቷል፡፡

ከላይ አንብበን እንደመጣነው

ያ ወቅት በሳልና ጠሬውን ለመለየት ወይንም

ማን ምን እንደሆነ ለይቶ ለማወቅ አስቸጋሪ

የሆነበት ወቅት ስለነበር በፈንዳታው ፍንጣሪዎች

ቤቶቻቸው የተደረመሱባቸው፣የተቃጠሉባቸውና

ንብረቶቻቸው የወደሙባቸው አባወራዎችና

እማወራዎች ዋይታ ሲያሰሙና ሲያነቡ

የሚታዩበት ወቅት ነበር፡፡

ስውር ደባ

እነ አጅሬም ፍንዳታው በደረሰበትና

በፍንዳታው በተደረመሱና በቃጠሎው

በነደዱ ቤቶች ዙሪያ ወይም አካባቢ ቁምጣ

ሱሪዎቻቸውን ታጥቀው፣ነጠላ ጫማዎቻቸውን

ተጫምተው አንዳንዶቹ ፎጣቸውን ከአንገታቸው

ላይ ጠምጥመው አንዳንዶቹ ደግሞ ፎጣቸውን

ከራሳቸው ላይ ጠምጥመውና ጠብመንጃቻቸውን

አንግበው፣የዚያን ከባድ ፍንዳታ ውጤት

ለማየት ይርመሰመስ የነበረውን ሕዝብ “ወደዚያ

ሂድ፣ወደዚህ አትጠጋ፣ወደዚህ አትቅረብ” እያሉ

ይገረምሙ ነበር፡፡

ከዚህበላይ ነግረን እንዳመጣነው፣ያ

በከባድ ፈንዳታ የጋየ የሥንቅና ትጥቅ ዴፖ በዐፄ

ኃ/ሥላሴ ዘመን መንግሥት የተገነባ፣ለሠራዊቱ

ሥንቅ እንዲሆን ተዘጋጅተው የተቀመጡ ልዩ

ልዩ የምግብ ዓይነቶች፣ልዩ ልዩ ጥይቶችና ልዩ ልዩ

የጦር መሣሪያዎች የተከማቹበት

ዴፖ ነበር፡፡ ይህም የዚች ሀገር ሀብት እንጂ

የንጉሱ ወይንም የደርግ የግል ሀብት አልነበረም፡

፡ ግን አጋጣሚውን ተጠቅሞ ሰርጎ የገባ

ወይንም ከሕወሓት ጋር ተቀላቅሎ የመጣ ጠላት

አቃጠለው፡፡ መጠነ ሰፊ የሕዝብ ንብረትም

ወደመ፡፡ ይህም በዚያን ጊዜ የከፋና አስደንጋጭ

ሽብር ነበር፡፡

በኢትዮጵያዊነቱ ለሚያምንና

የተከማቸን ብረትን ማውደም፣የአገር ቁርስን

ማውደም መሆኑን ለሚያውቅና ለአገሩ

ተቆርቋሪ ለሆነ ዜጋ፣የዚያ ሁሉ ንብረት

መውደም፣ሳይቆጨውና ሳያንገበግበው

እንደማይቀር ርግጠኛ ሆኖ መናገር ይቻላል፡

፡ ይሁንና፣የፈሰሰ አልታፈሰ ነውና ከሚንቀለቀል

እሣት ውስጥ እንደ ተጣለ ጅማት አሮ ተኮማትሮ

ዝም ከማለት በስቀተር ሌላ መንም ለማድረግ

ስለማይቻል እንደ ጅማቱ አረን ተቀብለነዋል፡፡ ዛሬ

አገራችን ለኛ ባእድ እየሆነች ነው፡፡

እንደሚታወቀው የነፋስ ስልክ አካባቢ

ለአደጋ የተጋለጡ የነዳጅ ማደያዎች፣የእህል

ጐተራዎች፣ከዕለት ጉርሳቸው በስተቀር ሌላ ቋሚ

ንብረት የሌላቸው ባለብዙ ቤተሰብ አባውራዎች

የሚኖሩበትና የኤሌክትሪክ መሥመር የተዘረጋበት

በቀር ወረቀት አያሌ ሕፃናት የሚኖሩበት ት/

ቤቶች ያሉበት በመሆኑ ለሽብር የተጋለጠ ነው፡፡

ስለሆነም ነው የጦር መሣሪያ የተከማቸበት ዴፖ

እንዲቃጠል የተደረገው፡፡

ይህ ሁሉ ሆኖ አልፏል፡

፡ የፈነዳ ፈንድቷል፤የወደመ ንብረትም

ወድሟል፤የተቃጠለም ተቃጥሏል፡፡ የሞተ

ሙቷል፣ግድ የለም፡፡ “በጊዜ ለኩሉ እንዳለው

ቅዱስ ዳዊት” ለሁሉም ጊዜ ስላለው ጊዜው ሲደርስ

የሚጠየቀው አጥፊ ይጠየቃል፡፡ ቢያንስ በታሪክ

እንዲቀመጥ ይደረጋል፡፡ ደባውን ትውልድ

እንዲያውቀው ተጽፎ ይቀመጣል፡፡

ሁለተኛው ከባድ ፍንዳታ በሽሮሜዳ

አካባቢ በአንድ የልዩ ልዩ ቁሣቁሦች ማከማቻ

የፈነዳው ፍንዳታ ነበር፡፡ ምክንያቱ ከመጋዘኑ

ውስጥ የነበሩ ልዩ ልዩ ፈንጂዎችና ሌሎች ልዩ ልዩ

መሣሪያዎች ፈንድተው የአያሌ ሰዎች ሕይወትና

ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሶ አልፏል፡፡

ይህም በዚያን ወቅት የከፋ ሽብር ነበር፡፡

ሦስተኛው ፍንደታ በለደታ

ቤተክርስቲያን ማዶ ከባለወልድ ቤተክርስቲያን

ዝቅ ብሎ ባሉት ቤቶች ውስጥ ከዐፄ ኃ/ሥላሴ

ዘመነ መንግሥት ጀምሮ ጥይት ይከማችባቸው

ስለነበር ያ ሁሉ ጥይት እንዲፈነዳና በአካባቢው

ነዋሪ ሕዝብ ላይ ጉዳት እንዲያደርስ ሆነ ተብሎ

እሳት በመለኮሱና በጥይቶቹና ሌሎች ፈንጂዎችም

በመፈንዳታቸው የጥይቶቹ አረሮችና የሌሉች

ፈንጀዎች ፈንጣሪዎች በሰው ሕይወትና በንብረት

ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ ይህም አሳፋሪ

ሽብር ነበር፡፡

ሌላውና አራተኛው ፍንዳታ የደረሰው

ፒያሣ አካባቢ መብራት ኃይል መሥሪያ ቤት በስተ

ጀርባ ትግራይ ሆቴል እየተባለ ይጠራ በነበረውና

የትግሬዎች ዋና መናሐሪያ በነበረው ሆቴል

ውስጥ የፈነዳ ቦመብ ሲሆን፣ሆቴሉ ከምድር

ቤቱ አንስቶ ፎቆ ድረስ በቃጠሎ ወድሟል፡

፡ በዚያ ወቅትም በሆቴሉ ውስጥ ይዝናኑ የነበሩ

በርካታ ዜጎች ሞተዋል፤እንዲሁም ከፎቁ ላይ

ተኝተው በነበረው ከምድር ቤቱ ውስጥ ሲጠጡ

በነበሩትና በአሰላፊዎቹ ላይ ቃጠሎና የሞት

አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡ ቤቱም በጣም ወድሞ

ስለነበር፣አሁን ከቦታው ላይ ሌላ ትልቅ ፎቅ

ተሠርቶ ከሆቴል ቤትነት ወደ ሌላ ሸቀጣሸቀጥ

ንግድ ቤትነት ተለውጦ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡

በጣም የሚያስገርምና በጣም

የሚያሳዝነው በዚያ ግዙፍ ሆቴል ላይ ያ ሁሉ

ቃጠሎ ሲደርስ፣ያ ሁሉ ንብረት ሲወድምና በሰው

ሕይወት ላይ የሞት አደጋ ሲደርስ ምክንያቱ ምን

እንደሆነ አይታወቅም፡፡ አለመታወቁ ብቻ ሣይሆን

ለማወቅም ጠረት አለመደረጉ አስገራሚ ድራማ

ነው፡፡ ምኒልክ ዐደባባይ የሚገኘው በእሳት አደጋ

ጣቢያ በወቅቱ ደርሶ ቃጠሎውን ለማጥፋትና

የሰው ሕይወትና ንብረት ለማዳን፣አልሞከረም፡

፡ ከጥፋቶቹ ብርቱ ክንድ ከበስተ ጀርባ እንዳለ

በቂ ማሣያ ነው፡፡ አጥፊው አለመታወቁም በራሱ

ሽብር ነው፡፡

9

ሌላው በጣም አሳዛኝ ወይም ሳይወሳ መታለፍ

የሌለበት አንገብጋቢ ጉዳይ ትምህርቷን ጨርሳ

የመመረቂያ ጊዜዋ ደርሶ ወላጆቿን ጠይቃ

ለመመለስ ወደ ቦሌ በመጓዝ ላይ እንዳለች ውጭ

ጉዳይ ሚኒስቴር ዝቅ ብሎ ቤተ መንግሥት አካባቢ

ስትደርስ ከሚኒባሱ ውስጥ ተጠምዶ የነበረ ቦምብ

ፈንድቶ ካሉት ተሳፋሪዎች ጋር አብራ የተቀሰፈችው

ልጃ ገረድ ናት፡፡ ሌሎችንም፣አሷንም፣ልዑል

እገዚአብሔር ነፍሳቸውን ይማር እንላለን፡፡ ይኸም

በወቅቱ አሣፋሪ ሽብር ነበር፡፡ ብቻ ኢህአዴግ

በሥልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ ከጥፋትና ከሽብር

ወጥተን አናውቅም፡፡ መሸም ነጋም ሽብር ነው፡፡

ዛሬም ከሽብር አልወጣንም፡፡ ነገር፣ኪነጋ ወዲያም

አንወጣም፡፡

ሌላው ሳይወሳ ተዘሎ መታለፍ

የሌለበት ታሪካዊ ጉዳይ በሰማይ ነፈሳቸውን

ይማረውና የመላው አማራ ድርጅት የተባለ

የፖለቲካ ፓርቲ አቋቁመው ባያተርፉት ኖሮ

የብሔርን ትርጉም ጠንቅቀው የማያውቁ ጐሰኞች

የቀበሌ መታወቂያ ላይ “ብሔር አማራ” የሚል

ቅጽል የተሰጠው የኢትዮጵያ ዜጋ መጨረሻው ምን

ይሆን ነበር? የሚል ጥያቄ ማስከተሉ አይቀርም፡፡

በ1984 ዓ.ም የተባለው ድርጅት

ተቋቁሞ የብዙ ንጹሐን ዜጐች ሕይወት

እስከታደገበት ጊዜ ድረስ አያሌ ንጹሐን ዜጐች

ተገድለዋል፤ወደ ገደል ተጥለዋል፤አሰቦት የተባለ

ገዳም ተቃጥሏል፤ገዳሙን ሲያገለግሉ የነበሩ

መነኮሳትም ተገድለዋል፡፡ ይህም በታሪክ ልንረሳው

የማንችለው ክፉ የዘር ሽብር ነበር፡፡ በአማራ

ሕዝብ ላይ የተፈፀመ ሁለገብ ዘመቻ ትውልድ

በክፋቱ ሲያወሳው የሚኖር ከሽብሮች ሁሉ

የከፋው ሽብር ነበር፡፡

በመሠረቱ ሕወሓት አዲስ አበባን

ከረገጠበት ወቅት አንስቶ የተለያዩ ሽብሮች

ተካሒደዋል፡፡ ለነዚያ አያሌ የሰው ሕይወትና

የንብረት ውድመት ለደረሱት ሽብሮች ኃላፊነትን

የወሰደ ግለሰብ፣ቡድን ወይም ድርጅት ግን

እስካሁን ድረስ አልተገኘም፡፡

ስለዚህ ክቡር የሰው ሕይወትና ንብረት እንደ

ወደመ ታፍኖ ይቅር የሚል ሕግ ስለሌለ የሕግ

ልዕልና የሚያከብርና ሐቅን የሚከተል አካል እስከ

ሚገኝ ድረስ ወይም በሌላ አነጋገር ኢህአዴግ

በሥልጣን ላይ እስካለ ድረስ ታፍኖ ይቆያል፡፡

እስከዚያው ግን ከሽብር ማጥ ውስጥ መውጣት

አንችልም፡፡ በመሆኑም ልዑል እግዚአብሔር

እንዲገላግለን እሱን መማፀን ተገቢ ነው፡፡

ከሲኦል ያመለጡ የኢህአዴግ አባላት

ከመ/ር ቀለሙ ሁነኛው

በአንድ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ

ዜናዊ “የኢህአዴግ ስልጣን ዛፍ ላይ ወጥቶ እንደ

ማንቀላፋት ነው ይሉና ፍሬውን ለቅመው ይወርዳሉ”

ሲሉ በተሻDሚዎቻችው ላይ አፊዘው እንደነበር

ሰምቻለሁ፡፡ መዳፈር አይሁንብኝና በራሳቸውም ላይ

ያፌዙ ይመስለኛል፡፡ ፍሬውን የለቀሙት ግን እነማን

ናቸው? በአርግጥም የዛፍ አናት ላይ ቁጢጥ ያሉት

ለበሰለው ፍሬ እጅግ የቀረቡ በመሆናቸው እንዳሻቸው

እጃቸውን እየዘረጉ ለቅመዋል፤እየለቀሙም ነው፡

፡ ከታች ያሉት ተሻሚዎች ደግሞ ከጌቶቻቸው

የተራረፈውን ለመቃረምም ይሁን ከቅንነት በመነጨ

አመለካከት የኢህአዴግን ልማታዊ መንግሥትነት

ለመደስኮር እንደ ክልፍልፍ ውሻ ነጋ ጠባ በየመንደሩ

ሲዘሩ ያተረፉት ቢኖር “ዘመናዊ ቆራሊዮ”የሚል

ስያሜ ነው፡፡ አሁንማ በየወረዳው የተሾሙ

ካቢኔዎችና ግንባር ቀደም ካድሬዎች ውሎአቸው

በየመንደሩ መሆኑ ክፉኛ አማሯቸዋል፡፡ ከዚህ

አንፃር በግምገማም ይሁን በተገኘው ቀዳዳ ሾልከው

መውጣትን ይሻሉ፡፡ በብዛትም እየወጡ ናቸው፡፡

በቅርቡ ከአመራርም ሆነ ከአባልነት የተሰናበቱና

ወደ ቀድሞ ሥራቸው የተመለሱ “ከሲኦል ያመለጡ”

ወጣቶች በግልፅ ይናገራሉ፡፡ ከእስር እንደተፈታ ሰው

ነው ራሳቸውን የሚቆጥሩት፡፡ በየአደባባዩም “እንኳን

ደስ ያለህ/ያለሽ!” ሲባባሉ ይሰማል፡፡ በተለይም በየወሩ

ከደመወዛቸው የሚቆረጠው ገንዘብ፣የጋዜጣና

የመፅሄት ክፍያ በአባላቱ ቋንቋ” የማይደርስ ዕቁብ”

የሚሉት የድርጅቱ ክፍያ፣የሕዳሴው ግድብ መቶ

ፕርሰንት መዋጮ . . . /የሕዳሴው ግድብ መዋጮ

ከኛም ደመወዝ በግዴታ መወሰዱ ሳይዘነጋ/

ኑሮአቸውን ከማቃወሱ ባሻገር በገንዘባቸው ላይ

ማዘዝ የማይችሉ እንደነበረ በምሬት ይገልፃሉ፡

፡ ይበልጥ ደግሞ ፋታ የማይሰጠው የኢህአዴግ

ግምገማ ከሰውነት ተራ አውጥቷቸዋል፡፡ የወጣትነት

ሞራላቸውን ያላሸቀ ግምገማ እጅግ አድርጎ

ከርፍቷቸዋል፡፡ በራስ የመተማመን ስሜታቸውን

ክፉኛ ጎድቶታል፡፡ የዚህ አስተያየት ፀሐፊ እነዚህ

ወጣቶች የስነ ልቡና ሀኪም እንደሚያስፈልጋቸው

ያምናል፡፡

ከሲኦል ካመለጡ ወጣቶች አንዳንዶቹ ካወጉልኝ

ገጠመኞቻቸው መሀከል ባንድ ወቅት የኢህአዴግን

የፖለቲካ መስመር ለመስበክ በየመንደሩ እየዞሩ

በር ሲያንኳኩ አንዲት እማወራ “ኽረ ውሾቹ

እንዳይነክሷቸው” ሲሉ አባወራው ቀበል አድርገው

“ምንነካሽ?! ውሾቹ ከእኛ ይልቅ የሚያውቁት እነሱን

አይአለም እንዴ?!” ያሏቸው ከልብ አስደንቆኛል፡፡

በ2002 ምርጫ ወቅት ጠቅላይ ሚንስትሩ

ሳይቀሩ የኢህአዴግ አባላት ቁጥር ሰባት ሚሊዮን

እንደሚደርስ በኩራት ሲናገሩ ነበር፡፡ “ውስጡን

ለቄስ” እንዲሉ፡፡ አሁን አሁን ግን ይህንን አሀዝ

በእርግጠኝነት ደፍሮ የሚናገር የለም፡፡ የድርጅቱ

ገመና በራሱ የድርጅቱ አባላት ገሀድ እየወጣ ነው፡

፡ በራሱም ጊዜ መፈራረስ ጀምሯል፡፡ “እከሊትን ያየ

በእሳት አይጫወትም” እንዲሉ ከሲኦል ያመለጡትን

የኢህአዴግ አባላት የሞራል ድቀትና ምሬት ያስተዋለ

እንኳን አባልና ደጋፊ ሊሆን አይፈልግም፡፡

የዚህ አስተያየት ፀሀፊ ለዚህ አንድ መረጃ አለው፡

፡ በዚህ ወር እንኳን ከየወረዳው በተባረሩ አመራሮች

መትክ ተረኛ ተዋራጆችን ለመመደብ ድርጅቱ

ያደረገው ጥረት ከንቱ ልፋት ሆኗል፡፡ በየመስሪያ ቤቱ

የሚገኙ አባላቱ በተደጋጋሚ ቢለመኑም አሻፈረን

ብለዋል፡፡

ኢህአዴግ መቼም “አልሞት ባይ ተጋዳይ” ነው፤

አንድ ቀን ጥርስ የሌለው አንበሳ መሆኑ ባይቀርም

/አባባሉ ጋዳፊንም ያስተውሏል/፡፡ ጥቅምት 18

ቀን 2004 ዓ.ም በመዲናችን አዲስ አበባ በሚገኙ

ፕላዝማ ቴሌቪዥን በተዘረጋባቸው ት/ቤቶች

በየወረዳው የሚገኙ አባላትን ለመሰብሰብ ተሞክሮ

ነበር፡፡ የምክትል ከንቲባውና የሌሎች የአዲስ አበባ

መስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ከሥልጣናቸው

መባረር በመጠኑም ቢሆን ኢህአዴግን ያሳስበዋል፡፡

የእያንዳንዳቸው የግንኙነት ሰንሰለት እስከ ወረዳዎች

ወርዶ ተራ አባላትንም ስለሚያካትት የአኩራፊዎቹ

ቁጥር ማሻቀቡ አይቀርም፡፡

በጣም የሚያስገርመው ግን ከመስከረም

15/2004 ጀምሮ የትምህርት ሥርጭት ይጀምራል

የተባለው የፕላዝማ ቴሌቪዥን አስታዋሽና ባለቤት

አጥቶ እስከ ጠቅምት 18/2004 ባልጀመረበት

ሁኔታና የቴክኒክ ችግር እንዳጋጠመ ሲነገር እንዳልቆየ

የኢህአዴግን አባላት ለማወያየት ግን መፍትሄ

ተገኘለት፡፡ በሰበቡም የፕላዝማው ትምህርት

ተጀመረ፡፡ የትምህርት ጥራት ይሏችኋል ይሄ ነው፡፡

ሀሳቤን የምቋጨው በስብከት ነው፡፡ ስብከቱ

ግን ቤተ እምነቶችን አይመለከትም፡፡ በሲኦል ያሉ

ቤተ-ኢህአዴጎችን አይመለከትም-በሲኦል ያሉ

ቤተ-ኢህአዴጎችን እንጂ ሰባኪው እንዲህ ይላል፡፡

“የመዳን ቀን አሁን ነው! በሕይወት ሳሉ እንጂ ከሞት

በኋላ ከሲኦል ማምለጥ አይቻልም፡፡ ቢጤዎቻችሁ

በኢህአዴግ የግምገማ መድረኮች ለራሳቸው የደረጃ

ውጤት “ር” እየሰጡ ከሲኦል አምልጠው ከኢትዮጵያ

ሕዝብ ጋር በንሰሐ እንደተቀላቀሉ ሁሉ መንታ

መንገድ ላይ የቆማችሁ የድርጅቱ አባላትም ጊዜ

አተባክኑ! ፍጠኑ! መዳን ይሆንላችሁ ዘንድ አትፍሩ!

አትፍሩ! “ር” ውጤት ማስመዝገብ የሚያሳፍረው

ለዩኒቨርሲቲ ትምህርት ነው፡፡ በኢህአዴግ ግምገማ

“ር” ማስመዝገብ ግን ጀግንነት ነው፤ “F” ማስመዝገብ

ደግሞ ከጀግንነትም በላይ ጀግንነት ነው!!

ፈጣሪ አምላክ ኢትዮጵያን ይባርክ!

www.andinet.org.et

10

ከብሩክ ከበደ

www.andinet.org.et

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ ጥቅምት 28 ቀን 2004 ዓ.ም.

“ ነጋ-እንዴና የግብሩ አብዮት”

ከላይ የተቀመጠውን ርዕስ የተጠቀምኩት

ለቀጣይ ፅሁፌ አንድም ሁለትም

ትርጉም እንዲሰጥልኝ በማሰብ ነው፡

፡ አንደኛው መጠይቂያዊ ወይም ቃል

አጋኖአዊ ትርጓሜ የያዘው የቃላቱ

ዘርፍ ሌሊቱ አልፏአል፣ ነግቷል፣ ፀሐይ ወታለች የሚል

ጥያቄ አዝሎ በመንጋቱ የሚቆጭም፣ የሚደነግጥም፣

የሚደሰትም ሲመስል፤ በሌላ በኩል ደግሞ ነግቷል

ፈጥኜ ለሥራ ጀንበሯን ልቀላቀል የሚል መልህክት

ይይዛል፡፡

ሌላውና ዋነኛው ከዚህ ጋር የተያያዘው

ደግሞ በላቡና ጥረቱ ብቻ ለማደግ የሚጣጣረው

የነጋዴ ክፍል ንጋትን በናፍቆት እንደሚጠብቃት

የታወቀ በመሆኑ አዲስ የሽያጭ ዕቃ ለማስገባት፣

አዲስ ትርፍ ለማግኘት፣ አዲስ ዘርፍ ለመክፈት ካለው

ጉጉት በመነሣት የንጋት ጥያቄና ነጋዴ የሚነጣጠሉ

አይደሉም፡፡ ለዚህም ነው ሳድሶችን በማስወገድ ራሱን

የቻለ ትርጉም የሚሰጥ “ነጋዴ” የሚለውን ሥርወ /ቃል

እንዲያነግስ ያመቻቸሁት፡፡

ይህስ ሆነ ቃሉን ግን እንዲህ ለመሰነጣጠቅ

መልሶም ለማዛመድ ያበቃህ ምንድነው? የሚል ጥያቄ

ሊነሣ ይችላል፡፡ ቢነሣም ተገቢ ነው፡፡ ምክንያቱም

የሰኔ ሰማይ ማጉረምረም ሲጀምር ሁለቱ የቴሌቮዥን

መስመሮች፣ ዋናውን ሬዲዮ ጨምሮ የተለያዩ ኤፍ

ኤም ጣቢያዎች፣ በመንግስት የሥራና በውጭ ቋንቋ

የሚታተሙ የህትመት ውጤቶች፣ በያደባባዩ፣ በተለያዩ

ህዝባዊና መንግስታዊ ተቋማት ደጃፍ የሚሰቀሉ

መፈክሮችና ጥቅሶች ወዘተ ግብር መክፈል ግዴታ

ብቻ ሳይሆን የዜግነት ድርሻ እንደሆነ በሚያስገነዝቡና

በሚያስተምሩ ጽሁፎች ይጥለቀለቃሉ፡፡

በተለይ ዘንድሮ ከመቼውም በተለየ መልኩ

ግብር፣ ክፍያውንና ሂደቱን በተመለከተ ከከፍተኛ

የስራ አላፊዎች እስከመምሪያና ክፍል አለቆች ተራ

ሠራተኞች እስከ አንዳንድ የከተማ ነዋሪዎች ተብለው

እስከሚጠቀሱት ድረስ በየመገናኛ ብዙኃኑ እየቀረቡ

በተቀነባበሩ ቃለምልልሶችና የውይይት መድረኮች

የተነገራቸውን በሰፊው ለማስረዳት ሲጨነቁና

ሲውተረተሩ መመልከት የዘወትር ጸሎት ያህል

የሚደጋገም ነበር፡፡

ግማሹ የመንግስት ተቀጣሪ ሠራተኛ

በአንዳንዱ ነጋዴ ላይ በተጣለው (በተወረወረው)

ከፍተኛ ግብር ባያምንበትም ስራው ደሞዝ

የሚያገኝበት ብቻ በመሆኑ ለከፋዩ ያንያህል ግብር

ለምን እንደተጣለበት ለማሳወቅ በቂ ግንዛቤ ይሁን

በቂ ማብራሪያ መስጠት የተሳነውና እየተውለፈለፈ

ለማን አቤት እንበል...

በየጫካው እየዞሩ እንደዱር አውሬ ይጮሁ ነበር::

በየቁጥቋጦው ስር ተጠግተው ይኖሩ ነበር፡፡

አሁን ግን ልጆቻቸው እየሰደቡኝ ይዘባበቱብኛል::

ተፀይፈውኝ ከእኔ ይርቃሉ

ማምለጫና ኡፎይ የምታሰኘውን “የመንግስት መመሪያ

ነው” የምትለውን ቃል በመሰንዘር የዜጎችን መብትና

ግዴታ እንደግዴታ ብቻ ቆጥሮ “አበቃሁ ጨርሻለሁ”

የሚል ሲቪልሰርቫንት (የመንግስት ተቀጣሪ )

መመልከት ሆነ ሊያጋጥም የሚችለው ይኽችው ሰኔ

ስትመጣ ነው፡፡

ጉዳዩ ይመለከተናል፣ ያገባናል የሚሉት

ተቋማትና ግለሰቦች የሚናገሩትን፣ በማስታወቂያና

ማስጠንቀቂያ ብዛት የሚያጨናንቁትን የግብር

ክፍያ ከተወሰነው በቀር ቁብ ሰቶት የሚከታተላቸው

እምብዛም ነው፡፡ ለምን ቢባል ስር የሰደደው

አንዳንዴም ያልተጠናው እና ያልታሰበበት መልሶም

የሚዘነጋው ጨርሶም ትቼዋለሁ ሊባል የሚችለው ክፍያ

ቀድሞ ግዴታውን የተወጣውን ሲጐዳ እንጂ ሲጠቅም

አለመመልከቱ በህይወት ልምድና ኑሮ ሲያልፍበት

የቆየውነው፡፡ ለዚህም በ1997 ዓ.ም ተፈጥሮ የነበረውን

እና መልሶ የከሰመውን የግብር አብዮት ግብረኛው

በሚገባ የሚያውቀው ብቻ ሳይሆን የተቀጣበትም

ነውና፡፡

ከዚህ ከደነደነ የግብር አከፋፈል ትከሻው

ልምዱ በመነሳት “ደግሞ ይሔ ግብር መጣ !” እያለ

ከመዘባበትና ጊዜው ሳያልቅ ክፈሉ የሚለውን

ማስጠንቀቂያ ችላ በማለት የተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ

ሊያልቅ ሁለት አልያም አንድ ቀን ሲቀረው ከሚደርሰው

መጨናነቅ የዘለለ አዲስ ነገር አይጠበቅም፡፡ ዘንድሮ

ግን ይህን አካሄድ በመጠኑ የሚገለባብጠው አስጨናቂ

ጉዳይ ተፈጥሮ ግብረኛው ማማረር ብቻ ሳይሆን ከፈለጉ

ያሸጉት ሲልም በንግድ ቤቱ ላይ የፈረደበት ይመስላል፡፡

ግብር አስከፋዩን በየጊዜው ገማቾች

የገመቱት ነው በሚለውና አንዳንዴም የተጠና

የማይመስለውን ግብር በከፋዩ ላይ ሲከምረው ከፋዩ

እንዴት እንዲህ ሊሆን ይችላል አስረዱኝ? በሚልበት

ጊዜም መጀመሪያ የተጣለብህን ግማሹን ክፈልና

አቤቱታህን ማቅረብ ትችላለህ የሚል አገር ያለህዝብ

ባዶ መሆኗን ያልቃኘ ምላሽ ይቀርብለታል፡፡ ይህንንም

የሚጠናክርሎት ምላሽ ገንዘብንና ገንዘብን ብቻ ያማከለ

አሰራር እንዲሰሩ የተዋቀሩት የየክፍለ ከተማው ገቢዎች

ሰራተኞች በሚገባዎት ቋንቋ ያስረዳዎታል፡፡ እነዚሁ

በአንዳንድ ክፍለ ከተማ በአንድ ወንበር ላይ ሁለትና

ሦስት ሠራተኞች ሆነው ተደራርበው ሲተረማመሱ

ለሚመለከት ታዛቢ ግብር አስከፋዩ ገንዘብን ብቻ

መሰብሰብ የሚል መመሪያ የሚከተልና ከሰው በፊት

ገንዘብ እንዲቀድም የሚፈልግ ይህንኑም በትጋት

የሚሰብክ ቢመስለው አይፈረድበትም፡፡

እነኚህ በየክፍ ከተማው ያሉ የፋይናንሱ

የስራ ኃላፊዎችና ተራ ሠራተኞች በርካታ ሚሊዮኖችን

ሰብስበው በከፍተኛ የሥራ አለቆቻቸው ለመመስገን

ከገፅ 4 የዞረ

ያለ አንዳች ፍርሃት እፊቴ ምራቃቸውን ይተፋሉ

እግዚአብሄር ሃይሌን አድክሞ ስላዋረደኝ እነርሱም

ልጓሙ እንደወቀለት ፈረስ በላዬ ይፈነጩብኛል፡፡

የኛ ሲቃይም ከላይ ከተጠቀሰው ከኢዮብ

የሰመጉ ጥሪ

ብሎም ዋንጫና የምስክር ወረቀት ከግብር ከፋዩ

በሚሰበሰበው ገንዘብ ድል ያለ ድግስ ደግሰው

ለመቀበልና ለመሸላለም በሚያደርጉት ነፍስ ውጪ ነፍስ

ግቢ አካሄድ ግብር ከፋዩን ህብረተሰብ እስከ ማማረር

የሚደርስ ነው፡፡ በተጨማሪም በተመሣሣይ ስራና ሙያ

ላይ ያለው የግብር አከፋፈል እና አወሳሰን አንዱ ክፍለ

ከተማ ከአንዱ የሚለያይበት አጋጣሚ ስለሚፈጠርም

እርስ በእርሱ የሚነጋገረው ነጋዴ በልዩነቱ ላይ አጥብቆ

ሲማረር ይደመጣል፡፡

ግብርን በወቅቱ ሰብስበን ለመሠረተ ልማት፣

ለዳንድበር ጥበቃ፣ ለደን ልማት ወዘተ እያለ ግብር

አስከፋዩ ተቋም በየጊዜው ቢወተውትም ግብር ከፋዩ

ሕዝብ ግን የሚከፍለው ግብር ለአላስፈላጊ የመንግስት

ተቋማት ልዩ ልዩ ወጪዎች እየዋለ ነው የሚለው

ምክንያት እልባት እስካልተገኘለት ወይም እስካልተሻሻለ

ድረስ ግብርን በትጋት ለመክፈል የሚያበረታታ

አይመስልም፡፡ ይህን አባባል በምሣሌ ለማስረዳት

ካስፈለገም አንድ የገጠር የውስጥ ለውስጥ ጥርጊያ

መንገድን አሊያም ንፁህ የመጠጥ ውሃን ወይንም

አንደኛ ደረጃ ት/ቤትን ለመመረቅ የሚጠሩ እንግዶች

በተናጥል እያግተለተሉ ይዘዋቸው የሚነግዱትን

በሚሊዮኖች የሚቆጠር ግንዘብ የፈሰሰባቸውን

ተሽከርካሪዎች መመልከት ይበቃል፡፡ ጭርሱንማ አሁን

አሁን ያአንዳንድ መስሪያ ቤት ሹመኞች V-8(ቪ-ኤይት)

የተባለውንና ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣውን

ተሽከርካሪ ካልተገዛልን እያሉ ነው የሚል ጭምጭምታ

እየተሰማ ነው፡፡ ከነሱ የቀደሙትና በእጃቸው ያስገቡት

ግን በከተማችን ውስጥ ሲፈሱበት እየተመለከትናቸው

ነው፡፡

ከዚህ ውጪ ለአዲስ እና ለተጀመሩ

ፕሮጀክቶች ማስፈጽሚያ፣ ለዕቃ ግዢ ወዘተ. እየተባለ

የሚባክነው እና የሚወድመው አንሶ የ----------- መ/

ቤት የስራ ኃላፊ፣ ገንዘብ ያዥ፣ ዕቃ ግዥ----------

ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ይዞ ተሰወረ፡፡ የ--------

ክፍለ ከተማ የመሬት አስተዳደር ባለሥልጣን ከሁለት

ሚሊዮን ብር በላይ መዘበሩ፡፡ ወዘተ የሚሉና የመሳሰሉ

ዜናዎች መደጋገሙ አገር ብቻ ሳይሆን ግለሰቦችም

የሚለሙት ባንተ ኪስ ነው እየተባለ በተዘዋዋሪ

የሚነገረው ግብር ከፋይ በተለይ ደግሞ ታታሪውና

ሀቀኛው ነጋዴ “ገንዘቤ የበላተኛ ሲሳይ ሆኗአል” እያለ

ዘወትር ቢቆጭና ስለግብር የምሰማበት ጆሮ የለኝም ቢል

ማን ይፈርድበታል?፡፡

ከዚህ ውጪ ሕዝብ ግብር በመክፈሉ፣

ግዴታውን በመወጣቱ የሚደረግለት ተመጣጣኝ

ነገር ባለመኖሩም ቀበሌ ሆነ እስታዲዮም፣ ሆስፒታል

ሆነ አውቶብስ ተራ የሚያጋጥመውን ሰልፍ፣ ጡጫና

ልምጭ፤ በየፖሊስ ጣቢያው፣ ፈርድ ቤት ሕክምና

ወደ 13 ዞሯል

ሲቃይና መከራ ቢበልጥ እንጂ አያንስም ችግራችን

በዝቷል፤ ሸክማችን ከብዷል፤ እንዲቀልልን ለማን

አቤት እንበል?

የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ) በቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉበኤ /

ኢሰመጉ/ የቆመው ለህግ ልዕልና፣ ለዲሞክራሲና ለሰብአዊ መብቶች መከበር ነው፡፡ የሰመጉ

አባል ይሁኑ፡፡ ዓላማውን ለማስፈጽም ይችል ዘንድ በገንዘብ ይደግፉ፡፡

ስልክ 011 551-44089/011 551-77-04

አድራሻ ሣህለ ሥላሴ ሕንፃ 8ኛ ፎቅ ከአዲስ አበባ ስታዲየም ፊት ለፊት

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.15

የሰመጉ ይግባኝ በፌዴራል

ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት

ሊታይ ነው

በቀድሞ አጠራር የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ

(ኢሰመጉ) በአሁኑ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ)

በበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ያለአግባብ

የባንክ አካውንቴ ታግዶአል በማለት ከፍቶት የነበረው

ክስ በፌደራል በከፍተኛ ፍ/ቤት ውድቅ በመደረጉ

ለፌደራሉ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት ይግባኝ ጠይቋል፡

፡ ጉዳዩ “በይግባኝ ያሳቀርባል ወይስ አያስቀርብም

በማለት የተመለከተው ሠበር ችሎት ያስቀርባል ወይስ

አያስቀርብም በማለት የተመለከተው ሠበር ችሎት

ያስቀርባል ተብሎ ብይን መስጠቱን” ከሰመጉ ያገኘነው

መረጃ ይገልጻል፡፡

በዚሁ መሠረት በከፍተኛ ፍ/ቤት የተፈጠረውን የህግ

ጥሰት በማንሳት በሰበር ችሎት ለመከራከር ሰመጉ ዝግጅት

እያደረገ መሆኑን” ገልጸዋል፡፡ ከሠመጉ ባገኘነው መረጃ

መሠረት “የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ(ሰመጉ)፣ በቀድሞ

አጠራር የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ)

መንግስታዊ ያልሆነ፤ ከየትኛውም ፖለቲካ ድርጅት

ጋር ያልወገነ ነፃ ድርጅት ነው፡፡ ጉባኤው የቆመው

ለሕግ ልዕልና፤ ለዴሞክራሲ እና ሰብአዊ መብቶች

መከበር ነው፡፡ በቅርቡ ባጋጠመው ችግር ምክንያት

ሥራ እንቅስቃሴው በመድከሙ ጨርሶ ሥራውን ያቆመ

የመሰላቸው በርካታ ሰዎች እንዳሉ ተገንዘበናል፡፡ ሆኖም

ለአላማው ፅኑ እምነት ባላቸው አባላቱ እና ጥቂት

ሠራተኞቹ እየታገዘ አሁንም በመንቀሳቀስ ላይ እንደሆነ

ለደጋፊዎቹ ሁሉ ለማሳወቅ እንፈልጋለን፡፡

ቀደም ሲል ጉባኤው በአብዛኛው ድጋፍ ያገኝ የነበረው

ከውጭ አገር ለጋሾች እንደነበር ይታወሳል፡፡ ሆኖም

አዋጅ 621/2001 በሰብአዊ መብቶች ማስከበር

አኳያ የሚንቀሳቀሱ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች

ከአመታዊ ገቢያቸው ዘጠና በመቶ ማግኘት ያለባቸው

ከአገር ውስጥ ምንጮች መሆን እንዳለበት በመደንገጉ

ገቢው በእጅጉ ቀንሷል፡፡ ከአባላት ሊሰበሰብ የቻለው

ገቢ አነስተኛ ከመሆኑም ሌላ ጉባኤው ለመቋቋሚያ

ብሎ አሥራ ስምንት ዓመታት ሙሉ በማጠራቀም

በባንክ ያስቀመጠው ገንዘብ በበጎ አድራጎት ድርጅቶች

እና ማህበራት ኤጀንሲ ታግዶበት ለማስለቀቅ በክስ ላይ

ይገኛል፡፡

`ሰመጉ` ላለፉት 20 ዓመታት በ12 ቅርንጫፎች እና

ለሰብዓዊ መብት ዴሞክራሲ እና የህግ የበላይነት

መስፈን ፅኑ ፍላጎት ባላቸው ሠራተኞቹ የሰብአዊ

መብት ተጠቂዎች ለጉዳታቸው ድምፅ እንዲያገኙ እና

አጥፊዎቹም እንዲታረሙ በሰፊው ተንቀሳቅሷል፡፡ ከላይ

የተጠቀሰው አዋጅ እስከወጣበት ጊዜም `ሰመጉ` 58

ሠራተመፐች 3 የሥራ ሂደቶች እና 8 ንዑስ የሥራ ሂደቶች

የነበሩት ሲሆን በ2001 ብቻ በ16 የሰብአዊ መብት ጥሰት

መርማሪዎች እና በ12 ቅርንጫፎቹ በመንቀሳቀስ 1723

የሰብአዊ መብት ምርመራዎችን አድርጓል፤ 3 መደበኛ

ሪፖርቶችን እና 6 ልዩ መግለጫዎችን አሳትሟል፡፡

አዋጅ 621/2001 ከወጣ ጊዜ ጀምሮም በተከተለው

አሉታዊ ተጽዕኖ ምክንያት አቅሙ በመዳከሙ ዘጠኝ

ቅርንጫፎቹን ለመዝጋት የተገደደ ሲሆን 85%

ሠራተኞቹንም አጥቷል፡፡ ይህም `ሰመጉ`በመላው

ኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ተጎጂዎችን ጩኽት

በማሰማት እና ከጎናቸው በመቆም ሲያደርግ የነበረውን

የማይተካ ሚና ያስተጓጎለበት ከመሆኑም በተጨማሪ

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግሥት ማንኛውም ሰው

ለማንኛውም ዓላማ ማህበር የማደራጀት መብት አለው

የሚለው ድንጋጌ ከማጠናከር ይልቅ ውጤት አልባ

የሚያደርግ ነው፡፡ በተለይም የኢትዮጵያ ህዝብ ድምፁን

ከማጠናከር ይልቅ ውጤት አልባ የሚያደርግ ነው፡

፡ በተለይም የኢትዮጵያ ህዝብ ድምፁን ሲያሰማበት

የነበረውን `ሰመጉ`ን በማዳከም ዋናው የህጉ ተጎጅ

`ሰመጉ` ሳይሆን ሲያገለግለው እና ድምፁን ሲያሰማለት

የነበረው ህዝቡ ነው፡፡ ምንም እንኳን ይህ ሁኔታ

ከፍተኛ ጫና ያሣደረብን ቢሆንም ሰመጉ በሰብአዊ

መብት፣ ዲሞክራሲ እና በህግ የበላይነት ፅኑ እምነት

ባላቸው ኢትዮጵያውያን በመታገዝ ሥራዎቹን ቀጥሏል

ለወደፊትም ይቀጥላል፡፡ አሁንም ባሉት ሠራተኞ

በመታገዝ 5 ልዩ መግለጫዎችን እና 1 መደበኛ ሪፖርት

አውጥቷል፡፡

ጉባኤያችን እስካአሁን ሲታገል የቆየው ለህዝብ መብቶች

መከበር እንደመሆኑ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ሊደግፉት

ይገባል የሚል እምነት አለን ስለሆነም ገቢ ለመሰብሰብ

በምናደርገው ጥረት ሁሉ ተካፋይ እንድትሆኑ ከአደራ

ጭምር እናሳስባለን፡፡” ብለዋል፡፡

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.15

ዜና

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ ጥቅምት 28 ቀን 2004 ዓ.ም.

የሠራተኞችን ደሞዝ ለመቀማት ሲል 3ሰው ገድሎ

2 ሰው ያቆሰለው ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ዋለ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን

የምትገኝኘው የያያ ወረዳ አስተዳደር ሠራተኞች

የጥቅምት ወር ደሞዝ ለመዝረፍ ሦስት ሰው ገሎ

ሁለት ሰው ያቆሰለው የወረዳው ፖሊስ በቁጥጥር

ሥር መዋሉን የዜና ምንጮቻችን በተለይ ለፍኖተ

ነፃነት ጋዜጣ ገለጹ፡፡ እንደ ዜና ምንጮቻችን

ገለጻ ከሆነ “ጥቅምት 20 ቀን 2004 ዓ.ም አንድ

ሚሊዮን ብር ይሆናል የሚባለውን የወረዳውን

የመንግስት ሠራተኖች ደሞዝ ለማምጣት ከወረዳው

ፍቼ ከተማ ንግድ ባንክ ይመጣሉ፡፡ ግንዘቡን

ለማምጣት የመጡት ሦስት ሠራተኞች አንድ

ፖሊስና አንድ ሹፌር በጠቅላላ አምስት ሰዎች

ነበሩ፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዷ ሠራተኛ ነፍሰጡር

ነበረች፡፡ ለጊዜው በባንክ ያለው 12ሺ ብር ብቻ ነው

ባንክ ውስጥ ያለው ተብለው ያንን እንደተሰጣቸው”

ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡

በመቀጠልም የዜና ምንጮቻችን እንደሚሉት

“የተሰጣቸውን ብር 12ሺ ይዘው ወደ ወረዳቸው

ሊንቀሳቀሱ ሲሉ አንድ ሌላ የወረዳው ፖሊስ

ይዛችሁኝ ሂዱ ብሎ ትብብር ይጠይቃቸዋል፡፡

እነሱም እሺ ብለው አሳፈሩት ጉዞ ጀምረው ገጠር

ሲደርሱ ያ በልመና የተሳፈረው ፖሊስ “ሽንት

ሰለያዘኝ አንዴ ሽንቴን ልሽና” ብሎ ጠየቃቸው፡

፡ አሁንም እሺ ብለው መኪና አቆሙለት፡

፡ ከወረደ በኃላ መሣሪያውን አውቶማቲክ ላይ

አድርጐ በቅድሚያ ፖሊሱን ከመታው በኋላ ከዚያ

በተሳፈሩት ላይ በጠቅላላ ጥይት አርከፈከፈባቸው፡

፡ ሁለት ወዲያውኑ ሲሞቱ ሌሎቹ ቆሰሉ፡፡ ገንዘቡን

አንስቶ ለማምለጥ ሞከረ፡፡ ጥይት ጨርሶ ስለነበር

የአካባቢው አርሶ አደሮች ከበው በዱላ ቀጥቅጠው

ከያዙት በኋላ ወዲያውኑ ለፖሊስ አስረክበውታል፡፡

የቆሰሉት ሦስቱ አዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል

እንደደረሱ ፖሊሱ በጠና ተጐድቶ ስለነበር

ወዲያውኑ ሲሞት፤ አንዱ ተሽሎት ከሆስፒታል

ሲወጣ ነፍሰጡሯ እስከ አሁን ሆስፒታል በከፍተኛ

ጉዳት ላይ ትገናለች፡፡” ብለዋል፡፡ ስለጉዳዩ መረጃ

እንዲሰጡን የፍቼ ከተማ ዞን ፖሊስ ጠይቀን

ስማቸውን ለመጥቀስ ያልፈለጉ ሰው “የተሟላ መረጃ

ሊነግሩአችሁ የሚችሉት ህዝብ ግንኙነቶች ናቸው፡

፡ እነሱ በአሁኑ ጊዜ የሉም፡፡ ለጊዜው ልሰጣችሁ

ይምችለው መረጃው ተጠናቅሮ ለኦሮሚያ ፖሊስ

ተላልፏል” በማለት መልስ ሰጥተውናል፡፡ በተያያዘ

ዜና በዚህ ዕለት ማለትም ጥቅምት 20 ቀን 2004

ዓ.ም በዚሁ በፍቼ ቆላማው አካባቢ ልዩ ቦታው

ግራር አዲስ ጌ ቀበሌ ገ/ማህበር ውስጥ “አንድ

ታጣቂ ህዝቡን ሰብሰባ ውጡ እያለ በየቤቱ እየዞረ

በዱላ ሲደባደብ በጥይት ተገድሏል” ሲሉ የዜና

ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡ እንደ ዜና ምንጮቻችን

ገለጻ “በግድያ ተጠርጣሪው ነው የተባለው ግለሰብ

ከሦስት ቀን በኋላ ለመንግስት እጁን ሰጥቷል”

ብለዋል፡፡ በዚህም ጉዳይ ያነጋገርናቸው የዞኑ ፖሊስ

“ግጭቱ የተፈጠረው በሁለት ታጣቂዎች መካከል

ነው፡፡ በአካባቢው ማህበራዊ ፍ/ቤት ተካሰው ነበር፡

፡ ተይዞ እንዲቀርብ የተወሰነበት ታጣቂ ቤቱን ዘግቶ

እንቢተኛ በመሆኑ ለማስወጣት ሲሞክሩ ከቤት

ውስጥ በተተኮሰ ጥይት አንድ ታጣቂ ሞቷል፡፡ ቤት

ውስጥ የነበረው ታጣቂ ለጊዜው የተሰወረ ቢሆንም

በህዝብ ትብብርና በፖሊስ ጥረት ተጠርጣሪው

በቁጥጥር ሥር ውሎአል፡፡ ጉዳዩ በምርመራ ላይ

ነው” በማለት መልስ ሰጥተውናል፡፡

የደብረብርሃን ከንቲባና ባለሥልጣናት በሙስና ተጠርጥረው መታሰራቸው ተገለፀ

የዞኑ ደን ልማት ሽያጭ መነጋገሪያ ሆኖአል

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ

ዞን ዋና ከተማ የሆነችው ደብረ ብርሃን ከተማ ከንቲባ

የሆኑት “አቶ ስዩም ተፈራና በመሬት አስተዳደርና

በልዩ ልዩ የሥራ ኃላፊነት ላይ የነበሩት የዞኑ ከፍተኛ

ባለሥልጣናት ከሙስና ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው

በእስር ላይ እንደሚገኙ” የዜና ምንጮቻችን

በተለይ ለፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ ገለጹ፡፡ እንደ መረጃ

ምንጮቻችን ገለጻ ከሆነ “የዞኑ ነዋሪዎች በተለያየ

ጊዜ በመልካም አስተዳደር እጦት ለተለያዩ አካላት

አቤቱታ ቢቀርብም ፍትህ ማግኘት አይቻልም ነበር፡፡

በጂማ ከተማ የተቃጠለው ውሃ ልማትና ዐቃቤ ህግ ጽ/ቤት

አነጋጋሪ መሆኑ ተገለፀ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ጂማ ዞን ዋና ከተማ

በሆነችው ጂማ ከተማ ውስጥ ልዩ ቦታው “ውሃ

ልማት” በሚባል አካባቢ ኖክ ማደያ ፊት ለፊትና

ከፍ/ቤት ጐን የሚገኙት የውሃ ልማትና የዐቃቢ

ህግ ጽ/ቤቶች ሰሞኑን ሙሉ በሙሉ በእሳት ቃጠሎ

መውደማቸው በከተማው አነጋጋሪ ጉዳይ መሆኑን

የዜና ምንጮቻችን ገለጹ፡፡ እንደ ዜና ምንጮቻችን

ገለጻ በ2003 ዓ.ም ለምዕራብ ኦሮሚያ (ጂማ፣ ምዕራብ

ወለጋ፣ ምስራቅ ወለጋና፣ ኢሊባቦር ዞኖች…) በገጠራማ

ሥፍራዎች ለውሃ ቁፋሮ ከፌዴራል መንግስት

ህጋዊ የሆኑ ይዞታዎችን እየነጠቁ ለሚፈልጉት እየሰጡ

ዜጐችን ሲያንከራትቱ፣ ምሪት ቦታዎችን እንዳሻቸው

ለፈለጉት ሲሰጡ ከልካይ አልነበራቸውም፡፡ፍትህ

ሲያዛቡ ጠያቂም አልነበራቸውም፡፡ የአካባቢው

ህዝብ አድማጭ አልነበረውም፡፡ የሚቃወማቸውንና

ልክ አይደለችሁም የሚላቸውን ተለጣፊ ስም እየሰጡ

እያሳሰሩና ከኑሮው እያፈናቀሉ ቆይተዋል፡፡ ዛሬ

ለገዢዎች ባልተመቿቸው ወቅት ጠብቀው ማሰራቸው

የዘገየ እርምጃ ነው” ሲሉ በቁጭትና በሐዘን ገልፀዋል፡፡

በተያያዘ ዜና “ከጣርማ በር መዘዞ ባሽ የሚገኘው

ከተመደበው በጀት ውስጥ 13 ሚሊዮን ብር ጉድለት

በማሳየቱ በባለሥልጣኖች ላይ ክስ ተከፍቶ ጉዳዩን

የፌዴራል ዋናው ኦዲተር መ/ቤት ካሸገው በኋላ ክሱን

የከፈተው የዐቃቢ ህግ ጽ/ቤት ኦዲት ሊደረግ የነበረው

የውሃ ልማት ጽ/ቤት በአንድ ቀንና ሰዓት መቃጠላቸው

እያነጋገር ነው” ሲሉ አብራርተዋል፡፡

የመረጃ ምንጫችን እንደሚሉት “የእሳት

ቃጠሎው ርብርብ አድርጐ ንብረትን፣ ገንዘብንና

ሰነዶችን ማትረፍ ሲቻል ተቃጥሎ እንዲወድም

የተፈለገበት ምክንያት ግልጽ አይደለም፡፡ ካሉ በኋላ

ሰፊ የባህር ዛፍና የጥድ ደን ግልጽነት በጐደለው

ሽያጭ ተሸጦ እየተጨፈጨፈ ነው” ሲሉ አንዳንድ

የአካባቢው ነዋሪዎች ለዝግጅት ክፍላችን ገለጹ፡፡ እንደ

ነዋሪዎቹ ገለጻ “ከጣርማ በር መዘዞ ከመዘዞ መካከል

ባሽ የሚገኘው የሌባ መስቀያ የሚባለው ደን ብቻውን

በእግር ሁለት ሰዓት ያስኬዳል፡፡ ከጣርማ በር እስከ ባሽ

ድረስ በመኪና የአንድ ሰዓት መንገድ ነው፡፡ ይህንን

በ10 ሚሊዮኖች የሚቆጠረውን ደን እንደ ተራ እቃ

በስውር መሸጥ እና ጭፍጨፋ መጀመር አነጋጋሪ ነው”

ሲሉ ያብራራሉ፡፡

ምናልባት ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣን እጅ

ሳይኖርበት አይቀርም” በማለት ጥርጣሬአቸውን

ገልፀዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡን የጂማ ከተማ

ፖሊስ ደውለን ነበር፡፡ ስማቸውን ለመጥቀስ ያልፈለጉ

አንድ ግለሰብ ጥያቄያችንን ካዳመጡ በኋላ “ጉዳዩ

በምርመራ ላይ ያለ በመሆኑ አስተያየት ልንሰጣችሁ

አንችልም” በማለታቸው ዜናውን ሚዛናዊ ማድረግ

አልቻልንም፡፡

አርቲስት ደበበ እሸቱ ተጨማሪ ቀነ

ቀጠሮ ተጠየቀበት

በ ”ሽብር” ተጠርጥሮ ማዕከላዊ እስር ቤት የሚገኘው አርቲስት ደበበ እሸቱ ጥቅምት

24 ቀን 2004 ዓ.ም አራዳ ምድብ ችሎት ተቀጥሮ እንደነበር ይታወሳል፡፡

አርቲስት ደበበ በቀጠሮው ቀን ከማዕከላዊ እስር ቤት ወደ ችሎት ቀርቧል፡፡

ችሎቱን ለመከታተልም የተጠርጣሪው ቤተሰብም ሆነ ጋዜጠኞች እንዳይገቡ የተከለከለ

ሲሆን ተጨማሪ የ28 ቀን ቀነ ቀጠሮ ተጠይቆበታል ሲሉ ጠበቃው በተለይም ለዝግጅት

ክፍላችን ገልፀዋል፡፡

ተጠርጣሪውም ጥቅምት 24 ቀን 2004 ዓ.ም ችሎት እስከቀረቡበት ጊዜ

ድረስ በማዕከለዊ እስር ቤት ከጠበቃቸው ጋር እንዲገናኙ ባለመፈቀዱ ጠበቃው ችሎት

ፊት ከደንበኛቸው ጋር እንዲመክሩ በጠየቁት መሠረት ተፈቅዶላቸዋል ሲሉ ምንጮቻችን

ጠቁመዋል፡፡ በዚህም ክቡር ፍ/ቤቱ ተጠርጣሪው ከጠበቃቸው ጋር የመገናኘት ሕገ

መራግሥታዊ መብታቸው መሆኑንና ሊከለከሉ እንደማይገባ ለመርማሪው ፖሊስ

በማሳሰባቸው ጠበቃቸውም ተግባራዊ መሆኑን ለማረጋገጥ ዛሬ ወይም ነገ ማዕከላዊ

እስር ቤት ሄደው ደንበኛቸው አርቲስት ደበበ እሸቱን ለማነጋገር መወሰናቸውን በተለይም

ለዝግጅት ክፍላችን ገልፀዋል፡፡

11

በናይጄሪያ 150 ሰዎች

በአጥፍቶ ጠፊዎች

መገደላቸው ተገለፀ

በሰሜን ናይጄሪያ ደማቱሩ ከተማ 150 ሰዎች

በአጥፍቶ ጠፊዎች ቦምብና በጠብመንጃ በተፈጠረው

ተኩስ ጥቃት ያለፈው ቅዳሜ መገደላቸው ተገለፀ፡፡ ለጥቃቱ

“ይሄነስ” የተባለው እስላማዊ ቡድን እጅ አለበት ብለዋል”

ሲሉ የሀገሪቱን ባለሥልጣናትን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ይህንንም አስመልክቶ የፕሬዘዳንት ጉድላክ

ጆናታን ቃል አቀባይ ሩበን አባቲ ጥቃቱ የተፈፀመው

ከ5 በማያንሱ አጥፋቶ ጠፊዎች እንደሆነና ጉዳዩንም

የሚመለከተው አካል እያጣራ እንዳለ አስታውቀዋል፡

፡ ቃል አቀባዩ አያይዘውም አሁን በአካባቢው ምንም

የፀጥታ ችግር እንደሌለና ጥቃቱን አስተባብረዋል ተብለው

የተጠረጠሩትም በእስር ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል

ሲሉ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኋን ዘግበዋል፡፡

በኬንያ ቱሪስት መዳረሻ

ኬንያዊ ሾፌር ሲገደል

ስዊዘርላንዳዊ ጐብኚ መቁሰሏ ተገለፀ

በኬንያ ምስራቃዊ ክፍል “ጌም ፓርክ” በተባለው የቱሪስት

መዳረሻ ስዊዘርላንዳዊ ጐብኚዎችን ይዞ የነበረው ኬንያዊ

ሾፌር ባልታወቁ ታጣቂዎች ሲገደል አንድ ስዊዘርላንዳዊት

ጐብኝ መቁሰሏን የፈረንሳይዩ የዜና ወኪል ኤ ኤፍ ፒ

ዘግቧል፡፡

ባለፈው አርብ በተፈፀመ ጥቃት በከፍተኛ ደረጃ የቆሰለችው

ስዊዘርላንዳዊት ቱሪስት ወደ አቅራቢያ ሆስፒታል ሄዳ

የሕክምና እርዳታ እየተደረገላት እንደሆነና አብሯት

የነበረው ስዊዘርላንዳዊ የመቁሰል አደጋ እንዳልገጠመው

የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ስቴፈን ቮን

ቢሎው አስታውቀዋል፡፡

ኬንያ በቱሪዝም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የምታገኝ

ሀገር ስትሆን ከዚህ በፊት በመስከረም ወር እንግሊዛዊ

ጐብኚ ሲገደል ባለቤቱ ታግታ አንደነበር ይታወሳል፡

፡ በተመሳሳይም በጥቅምት ወር አንድ ፈረንሳያዊት እና

ሁለት ስፔይናዊ ዜጐች ጥቃት እንደደረሰባቸው ተዘግቧል፡

፡ ይህንንም አስመልክቶ ኬንያ ከቱሪስት የምታገኛቸው

ገቢዎች እንዳይቀንስ ስጋት የፈጠረ ሲሆን የሀገሪቱ

መንግሥት በበኩሉ ድርጊቱን የሚፈፅሙ ያልታወቁ

ታጣቂዎችን በቅርቡ በቁጥጥር ሥር እንደሚያውል

ገልጿል፡፡

ዓለም አቀፉ የገንዘብ

ድርጅት ለኮትዲቯር

616 ሚሊዮን ዶላር ብድር አፀደቀ

ኮትዲቯር ካለፈው ዓመት ምርጫ ውጤት ጋር

በተያያዘ በተፈጠረ ችግር ከፍተኛ የምጣኔ ሃብት

ውድቀት ተከስቶ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ይህ ምጣኔ

ሃብት እንዲያንሰራራ ፕሬዘዳንት ኦታራ ዓለም አቀፍ

አበዳሪ ተቋማትን የተማፀኑ ሲሆን በዚህም መሠረት

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት 616 ሚሊዮን ዶላር ብድር

ያለፈው አርብ ዕለት ማፅደቁ ተጠቁሟል፡፡

በተያያዘ ዜና ባለፈው የኮትዲቯር ምርጫ ተሸንፈው

የነበሩት ሎረንት ባግቦ “ስልጣን አልለቅም” በሚል

በተፈጠረው አለመግባባት 3ሺህ ሰዎች መገደላቸውን

አስመልክቶ በወቅቱ ጥቂት የሀገሪቱ አመራሮች ላይ

የኦታራ መንግስት ክስ መስርቷል፡፡

ከተከሳሾችም መካከል የቀድሞ ፕሬዘዳንት ሎረንት

ባግቦ፣ 24 ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናት

እና 57 የሀገሪቱ ወታደራዊ አመራሮች ይገኙበታል ሲል

የፈረንሣዩ የዜና ወኪል ዘግቧል፡፡

www.andinet.org.et

12

ከዳምጠው አለማየሁ

www.andinet.org.et

“ወይ ቶሎ ግደለኝ ወይ እድሌን ባርከው”

“ሊቀደድ ነው ሆዴ ሲርበኝ የማከው”

ድምፃዊ ባሕሩ ቃኘው

“ድህነት ባጭሩ ሲተረጎም የሚበሉትን

ማጣት ወይም መታረዝ ወይም መጠለያ

ማጣት ብቻ ሊመስል ይችላል፡፡ ድህነት

ከሁሉም ይበልጥ ተስፋ ማጣት ነው፣ ክብር

ማጣት ነው፣ በሰዎች መካከል እየተመላለሱ

አለመታየትና መረሳት ነው፡፡ ድህነት

በእያንዳንዱ ቀን ነገን እየፈሩ መኖር ነው፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ በኢህአዴግ ልማታዊ

መንግስትነት ከላይ በተገለፀው ሁኔታ

ውስጥ የማይኖር ከሆነ ፍርዱ የራሱ ነው፡

፡ ስለሆነም በእኛ ግንዛቤ ዛሬ በኢትዮጵያ

ኢትዮጵያውያንን የሚጠቅም ሰባዊ ልማት

የለም፡፡ ኢኮኖሚው አስርና አስራ አንድ

በመቶ አደገ አላደገ ለሕዝቡ ግን “ያው በገሌ”

እንደተባለው መሆኑን ልብ ይላል፡፡ ይህን

ህዝብ ይፍረድ!!” ከብርሀን ፓርቲ የምርጫ

ቅስቀሳ ሰነድ የተወሰደ፡፡

ሰሞኑን “ድርቅ እንጂ ርሀብ

የለም” በማለት ጠቅላይ ሚኒሰትሩና

ሹማምንቶቻቸው እየተቀባበሉና እየደጋገሙ

ሲናገሩ የምንሰማው እውን በዚህ ሀገር ያለ

ሀቅ ነው?

እንደ እውነቱ ከሆነ ኮሚኒስቶች

ብዙ ጊዜ መፈክሮቻቸውም ሆነ

ዕቅዶቻቸው፤ ህልሞቻቸውም ሆነ የድርጊት

ፕሮግራሞቻቸው ግልፅነት የጎደላቸው

ስለሆኑ ተደናግረው ማደናገር ይወዳሉ፡፡

ረሀብ ትርጉሙ ካልጠፋን በስተቀር

የሚላስ የሚቀመስ ማጣት ብቻ ሳይሆን

በየለቱ በሚቀመሰው ምግብ ውስጥ አማካኝ

የካሎሪ መጠን ማጣት ጭምር መሆኑ

መዘንጋት የለበትም፡፡

ሕወሓት በሽፍትነት ዘመኑ የተከሰተው

ዐይነት ርሀብና የሙት እናቱን ጡት

እየጠባ እነደታየው ህፃን ሰቆቃ፣ “ዋይ ዋይ

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ ጥቅምት 28 ቀን 2004 ዓ.ም.

ሲሉ” የሚደመጥ የልጆች እሮሮ ዛሬም ከ

አርባ አመታት በኋላም የምንጠብቅ ከሆነ

የተዋቀርንበት ስርዓት ሰብዓዊ ስርአት መሆኑ

ይቀርና በደመ-ነፍስ የተሰባሰቡ የዓራዊት

ዱለታ ያስመስለዋል፡፡

የሀገራችን ድርቅ እያሰለሰና አብዛኛውን

ጊዜ በየአስር አመቱ የሚመላለስ ክስተት መሆኑ

ባይካድም ረሀብና መራብ ግን የአብዛኛው

ህዝብ የእለት በእለት ኑሮና ቋሚ ህይወት

ነው፡፡ በአስከፊ ድህነት ውስጥ ከሚኖረው

የአብዛኛውን ገበሬ ህይወት እንለፈውና

በመካከለኛ ደረጃ ውስጥ የሚኖረውን ገበሬ

ህይወት እንመርምር፡፡ እንደሚታወቀው

የሀገራችን ገበሬ ተበልቶ ባለቀና በተበጣጠሰ

አነስተኛ ማሳ የሚያመርታት ምርት እጅግ

አነስተኛ ከመሆኑም በላይ በአማካኝ ከአምስት

እስከ ሰባት የሚደርሱ ቤተሰቦቹን ከመመገብ

ጀምሮ ካመረታት ምርት ውስጥ ግማሽ ያህሉን

ይሸጥና…………

1. ግብር ይከፍልበታል

2. የማዳበርያ እዳ ይከፍልበታል

3. ለራሱ ለልጆቹና ለቤተሰቡ

የዓመት ልብስና መጫሚያ እነደአቅሙ

ይገዛል

4. ለልማት መዋጮ እና ለገዢው

ፓርቲ ማጠናከሪያ የግድ ይከፍላል

5. የሚታደሱና ያለቁ የእርሻ

መሳሪያዎችን ይገዛል ለምግብ ማጣፈጫ

ጨው፣በርበሬ፣ዘይት፣ሽሮ፣ስኳር፣ቡና……

ወዘተ ይገዛበታል

6. ማገዶና ሳሙና ወዘተ

የሚያሟላው ከዚሁ ገንዘብ ነው፡፡

በዚህ ሁኔታ በግድ መሟላት

የሚገባቸውን ሸቀጦች ለመግዛት ሲል ወደ

ጎተራው ከገባችው ሰብል የተረፈችው

ምን ያህል ወራት መመገብ እንደምትችል

መገመት አያዳግትም፡፡ በዚህም ምክንያት

የተረፈችው ሰብል ያለጥርጥር ከስድስት

ወራት በላይ ሊመገቧት አይቻላቸውም፡፡

በዚህ አይነት የድህነት አዙሪት ቀለበት ውስጥ

የሚኖረው አብዛኛው የሀገራችን ገበሬ በቂ

ዝናብ ባለባቸው ወቅቶችም እንኳን ከስድስት

ወራት በላይ ሊመግበው የሚያስችለው

ምርት ከቶም ሊያመርት አይችልም፡

፡ ቀሪዎቹ ስድስት ወራት የረሀብ ወራት

ናቸው፡፡ ምክንያቱም እጅግ ኋላ ቀር በሆነ

የአስተራረስ ዘዴ እና ምርታማነቱ ተሟጦ

ባለቀ የተበጣጠሰ አነስተኛ ማሳ ግማሽ ዓመት

የሚመግበው ሰብል ማምረት የሚችል ገበሬ

እጅግ አነስተኛ ሊሆን ይችላል፡፡ በመሆኑም

ረሃብ በአገራችን በማናቸውም ጊዜ በየዓመቱ

ህዝብ እንዲሰደድና እንዲፈናቀል እንዲሁም

ከተሞችን በስራ አጦች ከማጨናነቅ ለማዳን

አልተቻለም፡፡

እንግዲህ ይህ ተጨባጭ የሀገራችን

ሀቅ ረሀብ፣ስደት፣መፈናቀልና ሞት እጣ

ፈንታችን ሆኖ አብሮን የኖረ ነው፡፡ በቅርቡ

በመካከለኛው ምስራቅ ከሊብያ ወደ

አውሮፓ እንዲሁም ከመቋዲሾ ወደ የመን፤

በሶማሌ ላንድ የታገቱና ሞትን ንቀው በስደት

የሚንገላቱ የኢትዮጵያውያን ህይወት ዘግናኝና

አሳዛኝ ነው፡፡ በይበልጥ የሚያሳዝነው ከነዚህ

ውስጥ ከፊሎቹ በጀልባ ሲያቋርጡ የባህር

አውሬ ቀለብ የሆኑ ወገኖቻችን ኢትዮጵያ

ምን ያህል ከሞትም በታች እንደሆነች

የሚያመለክት ነው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ አንድ አለምአቀፍ

የጥናት ማእከል በቅርቡ ይፋ ባደረገው መረጃ

መሰረት ከኢትዮጵያ ህጻናት ግማሽ ያህሉ

በምግብ እጥረት ምክንያት አካላዊ መቀጨጭ

የደረሰባቸው ናቸው፡፡ ይህ ሁኔታ የአእምሮ

መቀጨጭንም ስለሚያስከትል ለማህበራዊ

ልማት ዋና ጉዳይ የሆነው ትምህርትን

የመቀበል አቅማቸውን ከማዳከሙም በላይ

ትውልድ ገዳይ ከሆነው ስርዓተ-ትምህርት

ጋር ተደምረው የኢትዮጵያን ሰብዓዊ ልማት

መካን ያደርገዋል፡፡

በ 1996 ዓ.ም መ.ኢ.አ.ድ. ስለህዝብ

አደረጃጀት ጉዳይ በጎጃም፣ በጎንደርና

በወሎ ታላቅ ፖለቲካዊ ጉዞ መድረጉን

አስታውሳለሁ፡፡ እንዳጋጣሚ ሆኖ ከአዲስ

አበባ የተጓዝን በመሆናችን የገጠሩን

ህዝባችንን ብስቁልና ስንመለከት ሁላችንም

መረበሻችን ትዝ ይለኛል፡፡ በዚያን ግዜ

በደብረታቦር ከተማ ለሚደረገው ታላቅ

ህዝባዊ ስብሰባ ቅድመ ዝግጅት ሲባል

ከተመረጡ አረጋውያንና የአካባቢው

ፖለቲከኞች ጋር የዋዜማው ዕለት አመሻሽ

ላይ በተደረገ ውይይት የመክፈቻ ንግግር

እንዲያደርጉ የተጋበዙት ኢንጂነር ኃይሉ

ሻውል ነበሩ፡፡ ኢንጂነሩም ንግግራቸውን

ከመጀመራቸው ሳግ እየተናነቃቸውና

ንግግራቸውንም እያደናቃቀፈባቸው ያነቡት

እንባ በብርበራ ሰበብ ፊልሙ ካልተዘረፈ

በስተቀር በቪዲዮ ካሜራ የተቀዳ መሆኑ

አይረሳም፡፡ በማግስቱ የዞኑ ህዝብና ከፊል

ፈረሰኛ በቴዎድሮስ አደባባይ ወደሚካሄደው

ህዝባዊ ስብሰባ ከመታደማችን በፊት የዚህ

ጽሁፍ አቅራቢ በማለዳ በመነሳትና በመኝታ

ቤታቸው በመገኘት ትላንትና ማታ ለምን

እንዳለቀሱ ጠየኳቸው፡፡ እርሳቸውም

እስከዛሬ የማይረሳኝንና ጥልቅ ስሜታቸውን

የተገነዘብኩበትን ሃሳባቸውን ገለጹልኝ

እንዲህ በማለት “የወልድያ ወረታ መንገድ

የቻይና ኩባንያ በሚሰራበት ዘመን እኔ

የአውራ ጎዳና ስራአስኪያጅ ነበርኩና መንገዱ

በተሰጠው ንድፍና ደረጃ እየተሰራ መሆኑን

ለመቆጣጠር በተደጋጋሚ እመላለስበት

ነበር፡፡ በዚያን ግዜም በደብረታቦር የነበረ

የሰው ዘር ቁመናው ያማረ፣ ሸበላና መለሎ

ትውልድ አልቆ ትቢያ የመሰለ የደቀቀና

ድውይ ህዝብ ተሰብስቦ ስመለከት ራሴን

መቆጣጠር ተሳነኝ፡፡ ይህንን የተራቆተ መሬት

መልሰን እንዲያገግም ማድረግ እንችላለን፡

፡ ነገር ግን ያለቀውን ዝርያችንንና ወገናችንን

ከየት እናገኘዋለን?” ካሉ በኋላ በመቀጠልም

’’የሰሜን ሸዋን ህዝብ ቢቀጠቅጡት ምኒልክን

የተበቀሉ መስሎአቸው ነው፡፡ የደብረታቦር

ህዝብ ግን ምን አደረጋቸው’’?ማለታቸው

የሚረሳ አይደለም፡፡

ለነገሩማ በአፄ ቴዎድሮስ

“አንድ ሀገር አንድ ንጉሰ ነገስት” የተባለው

የዘመናዊው የኢትዮጵያ አንድነት ታሪክ

ጠንካራ አምድ የተተከለው፤ በፀረ-

ኢምፒሪያሊዝምና በፀረ-ቅኝ አገዛዝ የታነፁና

የአድዋን ጦርነት አይቀሬነት ቀድሞ የተገነዘቡ

ጠንካራዋ የአለማችን የመጀመሪያዋ ሴት

እቴጌ ጣይቱ የተገኙበትና እንዲሁም

በኢትዮጵያ እንደ ቀዳሚ ኢንዱስትሪ አባዮት

የተቆጠረውና ያልዘለቀው ጋፋት የጦር

መሳሪያ ፋብሪካ ማዕከላት ደብረታቦር እና

ጎንደር መሆኑ መቼ ሚረሳ ሆነና ብዬ በልቤ

አሰብኩ፡፡ ደብረታቦርም በፀረ-ኢትዮጵያ

ኃይሎች ኢላማ ውስጥ መግባቱ እንደምን

ያጠራጥራል?

አዲሱ የከተማ ውስጥ ርሃብ!

ድርቅ፣ አስከፊ ድህነትና ኋላ ቀር

ያስተራረስ ዘዴ ያስከትል የነበረው ርሃብና

ሞት በገጠሪቱ ኢትዮጵያ እንደነበረ

አይዘነጋም፡፡ ይሁንና ዛሬዛሬ ርሃብ ባጠቃላይ

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.15

ዕውን በኢትዮጵያ ውስጥ “ድርቅ እንጂ

በዚህ ረገድ እጅግ የሚያሳዝኑ ህፃናት አሉ፡፡ አንዳንዶቹ

ህፃናት ትምህርት ቤት መሄድ እድል ቢያጋጥማቸውም

ምሳ ለመቋጠር ያልታደሉ ወላጆች ስላሉዋቸው ባንዳንድ

የመንግስት ትምህርት ቤቶች ጠኔ የሚጥላቸው ልጆች

መታየት አዲስ ክስተት ነው፡፡ ይህ አስጨናቂ ሀላፊነት

የወደቀው ደግሞ በመምህራንና በየትምህርት ቤቱ

ማህበረሰብ ትከሻ ላይ ነው፡፡ በመሆኑም በአንዳንድ

ትምህርት ቤቶች ጊዜያዊ የመመገቢያ ስፍራዎች

እየተደራጁ ነው፡፡ ቀድሞውኑም ቢሆን ጥቂት የማይባሉ

ህፃናት ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ፣ አልባሳትና

ጥሬ የምግብ ሰብሎች የሚሰጡዋቸው ግብረ ሰናይ

ድርጅቶች አሉ፡፡ በመረጃ አቀራረብ ረገድ መተላለፊያው

ጠባብ ባይሆን ኖሮ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ እርዳታ

ፈላጊዎች እንደሚኖሩ መገመት አያዳግትም፡፡ በዚህ

አይነት ሰቆቃ በእያንዳንዱ ድሃ ጎጆ ተደፍተው ሚያድሩ

ረሃብተኛ ህፃናት አንጀት የሚበሉ ናቸው፡፡ የዚህ ሀገር

መሪ መሆን እንደመርግ የሚከብድ አበሳ ለመሸከም

ዝግጁ መሆንን እንጂ በመሬት ላይ ካለው ሃቅ ሸሽቶ

’’ድርቅ እንጂ ርሃብ የለም’’ ማለት ይገባል??

ርሃብ የለም ?”

ኢኮኖሚ

በኢትዮጵያ ከተሞችና በተለይ ደግሞ በአዲስ

አበባ ከተማ አዲስ ማህበራዊ ቀውስና

ክስተት ሆንዋል፡፡ የጦር ቁስለኞች፣የኤድስ

ህሙማን፣ጧሪ የሌላቸው አረጋውያን፣

ወላጅ አልባ ህጻናት፣ ቤት አልባና ጎዳና

ተዳዳሪዎች፣ በልመና የሚተዳደሩ ድሆች፣

ስራአጥ ወጣቶች ከግብርናና ከኢንዱስትሪ

ስራ የተገለሉ በርካታ ዜጎች ………ወዘተ

ከተማይቱን በማጨናነቅ ላይ ያሉ ርሃብተኞች

ናቸው፡፡ እነዚህ ሁሉ የአዲሱ የከተማ ውስጥ

ርሃብ ሰለባዎች ናቸው፡፡

በዚህ ረገድ እጅግ የሚያሳዝኑ ህፃናት

አሉ፡፡ አንዳንዶቹ ህፃናት ትምህርት ቤት

መሄድ እድል ቢያጋጥማቸውም ምሳ

ለመቋጠር ያልታደሉ ወላጆች ስላሉዋቸው

ባንዳንድ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ጠኔ

የሚጥላቸው ልጆች መታየት አዲስ ክስተት

ነው፡፡ ይህ አስጨናቂ ሀላፊነት የወደቀው

ደግሞ በመምህራንና በየትምህርት ቤቱ

ማህበረሰብ ትከሻ ላይ ነው፡፡ በመሆኑም

በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች ጊዜያዊ

የመመገቢያ ስፍራዎች እየተደራጁ ነው፡፡

ቀድሞውኑም ቢሆን ጥቂት የማይባሉ ህፃናት

ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ፣ አልባሳትና

ጥሬ የምግብ ሰብሎች የሚሰጡዋቸው ግብረ

ሰናይ ድርጅቶች አሉ፡፡ በመረጃ አቀራረብ

ረገድ መተላለፊያው ጠባብ ባይሆን ኖሮ

በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ እርዳታ ፈላጊዎች

እንደሚኖሩ መገመት አያዳግትም፡፡ በዚህ

አይነት ሰቆቃ በእያንዳንዱ ድሃ ጎጆ ተደፍተው

ሚያድሩ ረሃብተኛ ህፃናት አንጀት የሚበሉ

ናቸው፡፡ የዚህ ሀገር መሪ መሆን እንደመርግ

የሚከብድ አበሳ ለመሸከም ዝግጁ መሆንን

እንጂ በመሬት ላይ ካለው ሃቅ ሸሽቶ ’’ድርቅ

እንጂ ርሃብ የለም’’ ማለት ይገባል??

ውድ አንባቢያን!

ኢትዮጵያ ያላት ዋና ሀብት መሬት፣ውሃና

ታታሪ ህዝቧ ነው፡፡ ይህንን አቀናጅቶ

በመስራት ሀገራችን ከወደቀችበት አረንቋ

መንጭቆ በማውጣት ድህነትና ርሃብን

መሰናበት ይቻላል፡፡ ተደጋግሞ እንደሚነገረው

በውሃ ሊለማ የሚችል ድንግል መሬት አለን፡

፡ በተለይ በሰባቱ ታላለቅ ተፋሰሶቻችን

ውስጥ ያለው በሚሊዮን ሄክታር የሚቆጠር

ለም መሬት ለማረስና ለማልማት የሚያስችል

በቂ የገንዘብ አቅም እንዳለ ይታወቃል፡

፡ የኢህአዴግ መንግስት በያአመቱ ከአራት

ቢሊዮን ዶላር በላይ በይፋ እርዳታ የሚያገኝ

ከመሆኑም በላይ ይፋ ባልሆነ መንገድ

የዚህን ሶስት እጥፍ እንደሚያገኝ የኢኮኖሚ

ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡ ይህ ሁሉ ለልማት

የተትረፍረፈ ሀብት እያለ የሀገሩን ህዝብ

ጩኸት እና ዋይታ ከማዳመጥ ይልቅ ላለም

አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ጆሮ መስጠት

ቀዳሚ አጀንዳ ሆኖዋል ይልቁንም ገንዘብ

ካለን ሸምተን እንበላለን ማለት ይቀናቸዋል፡

፡ በዛሬው አለም የምግብ እህል ዋጋ

መናር አያስጨንቀንም፡፡ እንደ እውነቱ

ከሆነ ኢትዮጵያ ያላትን ለም መሬትና ውሃ

ተጠቅማ ብታርስ የአለምን የምግብ ዋጋ

መናር በማረጋጋት እረገድ የራስዋን ድርሻ

ልታዋጣ ከመቻልዋም በላይ በመቶ ሺህዎች

የሚቆጠሩ የእርሻ ሰራተኞችን በማሰማራት

ይልቁንም ርሃብና ድህነትን ከማስወገድ

ጀምሮ ወደ ብልፅግና በመረማመድ የሀገሪቱን

ገፅታ መለወጥ ይቻላል፡፡ የህንድ ገበሬዎችን

ለማስፈር የመሬት ቅርምትን ከማስፋፋት

ይልቅ የሀገራችንን ህዝብ ችግር እንፍታ፡

፡ በባዶ ፕሮፖጋንዳ የሀገር ገፅታ ግንባታ

አይኖርም!፡፡

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.15

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ ጥቅምት 28 ቀን 2004 ዓ.ም.

“ ነጋ-እንዴና የግብሩ ...

መስጫ ተቋማት የሚጠየቀውን ጉቦ የሚያስጥለው

ባለመኖሩ ስለ ግብር አከፋፈል ዝቅተኛ እውቀት

ብቻ ሳይሆን ጭርሱንም ላለመክፈል የሚያደርገውን

ድብብቆሽ የሚያባብስበት እንጂ የሚመልስለት

እንደማይሆን እሙን ነው፡፡

ግብር ከፋዩ ዛሬ ግብሩን ከፍሎ ነገ ወደ

አንድ ሕክምና መስጫ ማዕከል ጐራ ቢል ከጎንት

(ግላቭ) ጨምሮ የተለያዩ የህክምና መድኃኒቶችን

በጓሮ በር እያወጡ ለሚቸረችሩ ጥቅመኞች ቀድመው

የተጋለጡ በመሆናቸው ሚስቱ ወይም ልጁ

በግላቭ ወይም ጓንት እጦት ህይወታቸው ሲያልፍ

እየተመለከተና እያዳመጠ ግብር ጠቀሜታው ላንተነው

የሚለውን ፕሮፓጋንዳ እንዴት ሊያዳምጥ ይችላል?

እንዲያዳምጥስ ይጠበቃልን ?፡፡

ታታሪው ግብረኛ አመታዊውን ዜግናታዊ

ግዴታ ተወቶና እፎይ ግብሬን ከፈልኩ ብሎ ለሌላ

ጉዳይ ወደ ሌላ ቢሮ ሲገባ ለመሀንዲስ ትራንሰፖርት

አቅርብ፣ ለልዩ ልዩ ጉዳዮች ማስፈጸሚያ ለምሣሌ እንደ

የሰላም ትግል...

ሰላማዊ የምርጫ ሰራዊት አንቀሳቀሰ። ይኽ ሰላማዊ

ሰልፈኛ “ድምጽ ይከበር” በማለት ፓርላማውን

ያዘ። ወታደሩ እና የፖሊስ ኃይል በምርጫ ፖለቲካ

እንዳይገባ ተቃዋሚው ቀደም ብሎ ህጋዊ ስራ

በመሰራቱ ጣልቃ ከመግባት ተቆጠቡ። የመንግስት

ስልጣን ወደ አሸናፊ ፓርቲዎች ግንባር ተላለፈ።

ይኽ ግንባር በውስጡ 16 ያህል ተቃዋሚ ፓርቲዎች

ነበሩበት። እስቲ የዝንባቡዌን ሁኔታ እንመልከት።

በዝንባቡዌ ተቃዋሚው ፓርቲ ደጋፊዎቹ

በብዛት ወጥተው እንዲመርጡ በማድረግ እንዲሁም

ምርጫው ነፃ እና ፍትሃዊ እንዲሆን አለም አቀፍ

ህብረተሰብ በሙጋቤ አምባገነን መንግስት ላይ ጫና

እንዲያሳርፍ በማድረግ ረገድ ጥሩ ዝግጅት አድርጎ

ነበር። ምርጫውን ከሙጋቤ መንግስት ስርቆት

የሚያድን “ፕላን ለ” (Plan B) ግን ቸል ተብሉ ነበር።

የሙጋቤ መንግስት በምርጫ ሽንፈት ቢደርስበት

ስልጣን እንደማይለቅ የሚጠቁሙ ምልክቶች ቀደም

ብለው ይታዩ ነበር። በምረጡኝ ዘመቻ ወቅት

በተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎች እና ፓርቲ ሰራተኞች

ላይ ወከባዎች፣ ድብደባዎች፣ ግድያ፣ ማሳደድ

እና እስር ቤት የማጎር ተግባራት ይፈጸሙ ነበር።

በምርጫው ቀን ሳይቀር አለም አቀፍ ታዛቢዮች

እየተመለከቱ ድምጽ ለመስጠት የተሰለፉ ዜጎች

ይደበደቡ ነበር። ፖሊስ፣ ደህንነት፣ የጦር ኃይል፣

ካድሬ፣ ሚሊሺያ፣ እና በገንዘብ የተገዙ ቦዘኔዎች

ሳይቀሩ በተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎች ላይ አረመኔያዊ

ተግባሮች ፈጸሙ። ተቃዋሚ ፓርቲ የመረጡ ብዙ

ዜጎች ለህይወታቸው በመፍራት መኖሪያቸውን ለቀው

ተሰደዱ። አገር ለቀው ወደ ደቡብ አፍሪካ የጎረፉት

ጥቂት አልነበሩም። ምርጫ ለመታዘብ ከአውሮፓ

ተጋብዘው ከመጡት ውስጥ ምርጫው ሳያልቅ አገር

ለቀው እንዲወጡ የተደረጉ ነበሩ። ባጭሩ ምርጫው

ተሰረቀ። የዝምባቡዌው ሙጋቤ እንደሰርቢያው

ሞሊሶቪች አይኑን በጨው አጥቦ በምርጫው አሸናፊ

መሆኑን አወጀ። የሞሊሶቪች አዋጅ ተቀባይ እንዳጣ

አይተናል። የሙጋቤ አዋጅ ግን ተቀባይ አላጣም።

ምክንያቱም ተቃዋሚው ፓርቲ ምርጫውን ከሙጋቤ

ስርቆት ማዳን ባለመቻሉ። ተቃዋሚው ድምጽ

ለማስከበር የሚያስችል ዝርዝር ፕላን እና የሰላም

ትግል አቅም ስላልነበረው “ምርጫው ነፃ አይደለም፣

ድምጽ ይጣራ፣ ሌላ ምርጫ ይደረግ” የሚሉ ፋይዳ

ቢስ ጩኸቶች ከማሰማት፣ የሙጋቤን መንግስት

በጎ ፈቃደኛነት ከመጠየቅ እና የምዕራቡን አለም

ከመማጸን ባሻገር ምንም ማድረግ ሳይችል ቀረ።

የዝንባቡዌው ተቃዋሚ ፓርቲ እንደ ሰርቢያ “ፕላን

ለ” (Plan B) ያስፈልገው ነበር !!

በምርጫ ሽንፈትን መቀበል ማለት ለገዢው ፓርቲ

በአገር ውስጥ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ህጋዊነትን

ማጣት ስለሚሆን በስልጣን ላይ ያሉ አምባገነን

መንግስቶች ሽንፈትን ለመቀበል ዝግጁ አይደሉም።

ተቃዋሚ የዲሞክራሲ ኃይሎችም በምርጫ ያገኙትን

አሸናፊነት ማስከበር ካልቻሉ በአገር ውስጥ እና

በአለም አቀፍ ደረጃ የገዢነት እውቅናን እና ህጋዊነትን

ማግኘት አይችሉም ! ህዝብን የመንግስት ስልጣን

ባለቤት ማድረግ ዋዛ አይደለም።

መታወቂያ ለመሳሰለው ይሄን ያህል ክፈል እየተባለ

በሚጠየቅበት እና በሚከፍለው ግብር ልክ እንኳን

ባይሆን እጅግ አናሳ አገልግሎቶች እንዲያጣ እየተደረገ

ከዓመታት በኃላ ታገኛቸዋለህ ሲለሚባለው ትልልቅ

ፕሮጀክቶች እንዲያስብ ለማድረግ መሞከር በእጅጉ

አስቸጋሪ ነው የሚሆነው፡፡

ከሁሉ በላይ ደግሞ ግብር የሚከፍለውም ሆነ

ማይከፍለው፣ ህገውጡና ወንጀለኛው ነጋዴ ከንፁህና

ታታሪው ነጋዴ ጋር ተደበላልቆ ለትንሹም ለትልቁም

ጉዳይ እኩል ከተጉላላና አንዳንዴም ቅድሚያው

ለህገወጡ ለወንጀለኛው ነጋዴ ሲሰጠው ከታየ ግብር

በመክፈል የሚመጣውን ለውጥና ልዩነት መለፈፉ

ነገሩን ከፈረሱ ጋሪውን ማስቀደም ያስመስላል፡፡

ባለፈው ክረምት ውስጥ የከተማችን ከንቲባ

በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ብለው ግንባራቸውን እንደዛ

ከስክሰው ስለግብር ሲያስረዱ ለተመለከተ ግብር

በዜጐች ቀና አመለካከትና ፈቃደኝነት ፍፁም ለአገርና

ሕዝብ እድገት ተገዢ በመሆን የሚከፈል የንፁህ ነፍስ

ከገፅ 5 የዞረ

የሆነው ሆኖ መቀየር/መለወጥ (Peaceful

conversion) እና መቻቻል (Peaceful

accommodation) የተባሉት ለውጥ ማምጫ

መንገዶች ለገዢው ቡድን ከተቃዋሚዎች የቀረበለትን

ጥያቄ የመቀበል እና ያለመቀበል ምርጫ ይሰጣሉ።

ገዢውን ቡድን ማስገደድ አይችሉም። ሰላማዊ

ማስገደድ (Peaceful coercion) የተባለው ለውጥ

ማምጫ መንገድ ግን ገዢው ቡድን የቀረበለትን

የለውጥ ጥያቄ እንዲቀበል ማስገደድ ይችላል።

እንመልከት።

(3ኛ) ሰላማዊ ማስገደድ (Peaceful coercion)

ሰላማዊው ትግል ማስገደድን ተፈጻሚ ማድረግ

ከሚችልበት ደረጃ ከደረሰ በስልጣን ላይ ያለው

አምባገነናዊ መንግስት አቅም እጅግ ዝቅ ብሏል ማለት

ነው። በአንጻሩ የዲሞክራሲ ኃይሎች የፖለቲካ ኃይል

ከፍ ብሏል ማለት ነው። ጉልህ የፖለቲካ ኃይል ሚዛን

ግንኙነት ሽግሽግ ተደርጓል ማለት ነው። የሆነው ሆኖ

የገዢውን ቡድን ህልውና ላይ ስጋት የሚያሳድሩ

አስገዳጅ ጥያቄዎች ከመቅረባቸው በፊት ግን

ተቃዋሚው ጥንቃቄ የተሞላበት ፕላን መቀየስ እና

ሰፊ የአቅም ዝግጅት ማድረግ ይኖርበታል። ተፈጻሚ

ሊሆኑ የማይችሉ አስገዳጅ ጥያቄዎች ማቅረብ በህዝብ

ዘንድ ተዓማኒነት ያሳጣል። የፕላን አለመጠናቀቅ

ወይንም የትግል አቅም ማነስ ካለ አስገዳጅ ጥያቄዎችን

ከማቅረብ መቆጠብ ወይንም አኪያሄድን ማስተካከል

ይመረጣል። በስልጣን ላይ ያለው አምባገነን መንግስት

የቀረበለትን አስገዳጅ የለውጥ ጥያቄ ፈቃደኛ ሳይሆን

ተገዶ ከተቀበለ ማስገደድ ተሳካ ሊባል ይችላል።

የሰርቢያን እና የዝምባቡዌን ሁኔታዎች እንመልከት።

(4ኛ) (Peaceful disintegration)

ከፍ ብለን እንዳየነው ተቃዋሚው በስልጣን

ላይ ያለውን መንግስት ማስገደድ ከቻለ በገዢው

ቡድንና በህዝብ መካከክል ተጨባጭ የሆነ የስልጣን

ሽግሽግ ተደርጓል ማለት ነው። የፖለቲካ ኃይል ሚዛን

ግንኙነት ወደ ተቃዋሚ ማድላቱ በእርግጠኛነት

ከታወቀ የፖለቲካ እምቢተኛነት (Political defiance)

ትብብር መንፈግ (Non-cooperation) እና ጣልቃ

መግባት (Intervention) የተባሉትን የሰላም ትግል

መሳሪያዎች በመጠቀም ስርዓቱን በበርካታ ግንባሮች

ማጥቃት ይቻላል። ይኽ ጥቃት ቀጣይነት ካለው

የፖለቲካ ኃይል ምንጮች እንደሚደርቁ እና መንግስት

ተርቦ እንደሚፈረካከስ መገመት አያዳግትም።

በመጨረሻ በኢትዮጵያ ሰላማዊ ትግል ህዝብን

የመንግስት ስልጣን ባለቤት ማድረግ እንደሚችል

በመተንተን ጥናታችንን እንፈጽማለን። በኢትዮጵያ

ህዝብን የመንግስት ስልጣን ባለቤት ማድረግ

የሚችልባቸው ሁለት አማራጭ ቀዳዳዎች አሉ ማለት

ይቻላል። እነሱም፡-

(1) አንደኛው አማራጭ በሰሜን አፍሪካ እና

በመካከለኛው ምስራቅ የአረቡ ህዝብ የመረጠው

መንገድ ነው። ህዝብ ለመንግስት የሰጠውን የገዢነት

መብት እና ክብር በመንፈግ ህጋዊነቱን ገፍፎ ከስልጣን

ማውረድ ይችላል። ህዝብ በፈለገው ጊዜ የመንግስት

ለውጥ የማድረግ መብት እንዳለው የታወቀ ነው።

የግብጹ ፕሬዘዳንት ሙባረክ የተመረጠበትን የአራት

ከገፅ 10 የዞረ

ስርዓት መገለጫ ሳይሆን ክተት የተዋጀበት ጦርነት

አስመስለው ማቅረባቸው አሁንም ግብርን በተመለከተ

ገዢው ፓርቲ ለራሱ በራሱ ያልገባው ስነልቦናዊ

አመለካከት እንዳለ አስረጂ ነው፡፡ ይህንንም ስል ግብር

መብትም ግዴታም እንደሆነ በሙሉ ልቤ ስለማምንበት

ብቻ ሳይሆን እንደ ሃይማኖታዊ ትዕዛዝ የተቀበልኩት

መሆኔንም ጭምር ለማሳወቅ ነው፡፡

አለመታደል ሆኖ እንጂ ለጉዳይ በምንሄድባቸው

የተለያዩ ህዝባዊ ሆነ መንግሥታዊ ተቋማት፣ ለምርጫ

በቀረብንባቸው የምርጫ ጣቢያዎች፣ ፓርላማ፣

ሆስፒታል ወዘተ ልባችን ሞልተን፣ ደረታችን ነፍተን

እኔእኮ ግብር ከፋይ ነኝ! ያንተን ደሞዝ የምከፍልህ

እኔነኝ ለማለት ቅንጣት ፍርሀትና የዛኛው ወገን አሉታዊ

ምላሽ የምንፈራ ባልሆን ነበር፡፡ ይህን ግን አልሆነም

ለዚህም አልታደልንም ግብር እንዲህ በትንሹ ነገርግን

ትልልቅ ጉዳዮችን ተሸክሞ ባልጠራበት ሁኔታ እየተጓዘ

ገዢው ፓርቲ የኢህአዴግ ደጋፊ ነጋዴዎች ፎረም

የሚል ስያሜ ነጋዴው ላይ በመለጠፍ ነጋዴው እርስ

ወይንም የአምስት አመት የስልጣን ዘመኑን ሳይጨርስ

ከስልጣን እንደተወገደ እናስታውሳለን። ባጭሩ ህዝብ

እምቢ አልገዛም ካለ መንግስት ሊኖር አይችልም።

የኢትዮጵያ ህዝብ ይኽን አማራጭ ከመረጠ የትግሉ

ባለቤት እራሱ ህዝቡ ነው የሚሆነው። የተቃዋሚ

ፓርቲዎች ሚና ከህዝብ ጎን መቆም ነው የሚሆነው።

(2) ሁለተኛው አማራጭ “ለድምጽ ስርቆት

የማይች ምርጫ ማድረግ” ወይንም በአጭሩ

“የማይሰረቅ ምርጫ” ብለን የምንጠራው ነው።

የኢትዮጵያ ህገ መንግስት በምርጫ ሰላማዊ የመንግስት

ሽግግርን ይፈቅዳል። ይኽ ህገ መንግስታዊ ድንጋጌ

ቢያንስ በወረቀት ላይ ለመንግስት ለውጥ ጥያቄ

ያመቻቻል መልስ ይሰጣል። ነገር ግን በኢትዮጵያ

በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በፈጠራቸው የምርጫ

ቦርድ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ ካድሬዎች እና

ሲያስፈልግ ፖሊስ በመጠቀም ምርጫ ስለሚሰርቅ

የኢትዮጵያን ህዝብ የመንግስት ስልጣን ባለቤት

እንዳይሆን ያደርጋል። ይኽን ምርጫ የመስረቅ

ችግር መቋቋም ከተቻለ በህገ መንግስት የተደነገገው

ይመቻቻል መፍትሄው የከፈተውን ቀዳዳ መጠቀም

እንደሚቻል ግልጽ ነው። የመንግስትን ምርጫ

መስረቅ ለመከላከል “ነፃ አውጭ” የተባለ ተቃዋሚ

ቡድን ጫካ ገብቶ የእርስ በርስ ጦርነት መጀመር

የለበትም። ከዚኽ በኋላ የኢትዮጵያ ህዝብ የአዞ እንባ

ረጪ ነፃ አውጪዎች አያስፈልጉትም። ህዝቡ ራሱን

ነፃ ማውጣት አለበት። አብረውት እየኖሩ የሚታገሉ

የሰላማዊ ትግል መሪዎች በሚለግሱት እገዛ ብቻ ራሱ

ህዝቡ የሚያስፈልገውን መስዋዕት በመክፈል ድምጹን

ከስርቆት ተከላክሎ የመንግስት ስልጣን ባለቤት

መሆን ይችላል። ዛሬ ዲሞክራሲ በሆኑ አብዛኛዎቹ

አገሮች ህዝቡ ነው እራሱን በሰላማዊ ትግል ነፃ

ያወጣው። ለዲሞክራሲ ሽግግር አስተማማኙ

መንገድም ይኸው ህዝቡ የተሳተፈበት ሰላማዊው

መንገድ ነው። የኢህአዴግ መንግስት የኢትዮጵያን

ህዝብ ድምጽ አላከብርም ካለ የኢትዮጵያም

ህዝብ በበኩሉ አልገዛልህም ማለት አለበት። ህዝብ

የኢትዮጵያ ህዝብ ድምጹ እንዳይሰረቅ የመጠበቅ

መብትም አለው። ድምጽህን እኛ እንጠብቅልሃለን

የሚሉ የአዞ እንባ ረጪ ካድሬዎችንም ያለማመን እና

በድምጽ አሰጣጥ እና በድምጽ ቆጠራ ላይ በተወካዮቹ

አማካኝነት የመሳተፍ መብትም አለው።

የሆነው ሆኖ የኢትዮጵያ ህዝብ በህገ መንግስቱ

ውስጥ የተጠቀሰውን የምርጫ (መቻቻል) ድንጋጌ

ከ“ፕላን ለ” ጋር አዳቅሎ መጠቀምን ከመረጠ ከህዝቡ

ጋር አብረው የሚኖሩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ብዙ

ስራ ይጠበቅባቸዋል። በኢትዮጵያ የምርጫ ቦርድ

እና የምርጫ አስፈጻሚዎች ገለልተኛ እንዲሆኑ እና

አለም አቀፍ ምርጫ ታዛቢዎች በብዛት እንዲሰማሩ

ከመደራደር አንስቶ ህዝቡ ድምጹን ከስርቆት

እንዲጠብቅ የማዘጋጀት ኃላፊነት አለባቸው። የሰላም

ትግል ሰራዊት መገንባት ይኖርባቸዋል።

ከፍ ብለው የተመለከቱት ሁለቱም አማራጮች

የሰላም ትግል ሰራዊት ይሻሉ። ለመሆኑ የሰላም ትግል

ሰራዊት ማን ነው? ኢንጅነሮች፣ መምህራን፣ የህግ

ባለሙያዎች፣ የህክምና ባለሙያዎች፣ ተማሪዎች፣

13

በርስ የጎሪጥ እንዲተያይ በአሜት እንዲበላላ መንገድ

ከፍቶለት ይገኛል፡፡

አመታዊውን የሕዝብ ምንዳቸውን በተገቢው መልክ

የሚከፍሉ ሕዝቤና አገሬ አድገው አያቸዋለሁ የሚሉ

እንዳሉ ሁሉ ከባለሥልጣን ጋር በመሞዳሞድ፣ በዘር፣

በቋንቋ፣ በቡድን፣ በኃይማኖት በመጠላላለፍ እና

በመሳሳብ ከሕገወጡ ከኮንትሮባንድ ንግድ ጀምሮ

ሰነድ እስከመደለዝና ማዘጋጀት አልፎ የሕዝብ ንብረት

የሆኑ እንደ መሬት ማምረቻና ማከፋፈያ ተቋማትን

ወደ እራሳቸውን ግብረ አበሮቻቸው የሚያዘዋውሩ

ጥቂት አይደሉም፡፡ የሚያሳዝነው ደግሞ ይህን አደገኛ

አካሄድ የሚቀላቀሉ ግለሰቦች ቁጥር ከእለት ወደ እለት

በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መምጣቱ ሌላው አደገኛ እና

አሳሳቢ ሁኔታ ነው፡፡ አሁንም የዘንድሮ የግብር ዓመቱ

ጥቅምት 30/2004 ዓ.ም እንደሚገባደድ የታወቀ ነው፡፡

ቢሆንም ግን ምን ያህሉ ከጨዋታ ውጪ እንደሚሆንና

ምን ያህሉም ተፍገምግሞ ምን ያህሉም ተዝናንቶ

እንደሚቀጥል ይለይለታል፡፡

ኢኮኖሚስቶች፣ የባንክ ሰራተኞች፣ የቴሌ፣ የመብራት

ኃይልና የውሃ ሀብት ሠራተኞች አርቲስቶች፣ ታክሲ

ነጂዎች፣ ግንበኞች፣ ሱቅ ነጋዴዎች፣ እናቶች፣

አባቶች፣ የከተማ እና የገጠር ኗሪ ባጠቃላይ የሀገሪቱ

ለውጥ ፈላጊ ዜጎች ሁሉ ሰላማዊ የዲሞክራሲ ኃይል

ናቸው። የሰላም ትግል ሰራዊት አባላት ስራቸውን

ሲጨርሱ ወደ መደበኛ ስራቸው የሚመለሱ ዜጎች

ናቸው። አምባገነን መንግስትን ከስልጣን ለማስወገድ

የሚደረግ ቀጣይነት ያለው የትጥቅ ትግል የሰለጠነና

የተደራጀ መደበኛ የጦር ኃይል ሊኖረው እንደሚገባ

ሁሉ የህዝብ ድምጽ እንዳይሰረቅ ለማድረግም ሆነ

የህዝብ ድምጽ አላከብርም ያለ አምባገነን መንግስትን

በሰላማዊ ትግል ከስልጣን ለማስወገድ የሚደረግ

የሰላም ትግልም የሰለጠነ፣ የተደራጀ እና በድስፕሊን

የታነጸ የሰላም ትግል ሰራዊት ያስፈልገዋል። የሰላም

ትግል ሰራዊት ራሱን ከመንግስት ወሬ አቀባዮች

(informers) እና ከመንግስት መልክተኛ ቆስቋሾች

በመጠበቅ ረገድም የሰለጠነ ነው። በመኪና ነዳጅ

ውስጥ ውሃ መቀላቀል የመኪና ነዳጅን እንደሚበክል

ሁሉ የሰላም ትግል በካዮችም እንዳሉ የሚያውቅ እና

በጥንቃቄ የሚጓዝ ኃይል ነው። የሰላም ትግል ሰራዊት

ከገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች ጋር ግጭት ቀርቶ ክፉ ቃል

መቀያየር እንደማያስፈልግ ያውቃል። የሰላም ትግል

ሰራዊት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የሰለጠኑ አባሎች

ስለሚያሳትፍ የተወሰኑ መሪዎች ቢታሰሩም ትግሉ

ይቀጥላል። አምባገነኖች የአገሪቱን ህዝብ በሙሉ

የሚያስሩበት እስር ቤት የላቸውም።

በፍኖተ ነፃነት ቁጥር 4 በአክሱም ዘመን የነበረው

የመንግስት ሽግግር ባህላችን አስከፊ እንደነበር

ተመልክቷል። ከዘመነ አክሱም ወዲህ ኢህአዴግ

ስልጣን እስከጨበጠበት ድረስም ቢሆን የመንግስት

ሽግግር ታሪካችን ይበልጥ አስከፊ እየሆነ እና ኋላቀር

እያደረገን እንጂ ወደፊት እንድንራመድ አንዲት

ጋት አልረዳንም። በእርስ በርስ ጦርነት የሚደረግ

የመንግስት ሽግግር ቢትዮጵያ ላይ ያደረሰው ኪሳራ

በፍኖተ ነፃነት ቁጥር 12 ቀርቧል። በእርስ በርስ

መገዳደል የሚፈጸም የመንግስት ስልጣን ሽግግር

በኢትዮጵያ መቆም አለበት። ኢትዮጵያ ህዝብ

የመንግስት ስልጣን ባለቤት የሚሆንበት ዘመናዊ

የመንግስት ሽግግር ባህልን ተቀብላ በዘመናዊ

መንግስት መመራት መጀመር አለባት። ለዚህ

አስተማማኙ የፖለቲካ ትግል መንገድ ሰላማዊ ትግል

ነው። ከፍ ብለን ያየናቸው ሁለት አማራጮች የሰላም

ትግል መንገዶች ናቸው። ለዲሞክራሲ የሚደረግ

ትግል በየትም አገር ቢሆን ቀላል ሆኖ አያውቅም።

ይሁን እንጂ ከገዢ አምባገነኖች አቅም ጨቁነው

የሚገዙት ህዝብ አቅም ሚሊዮን ጊዜ እንደሚበልጥ

ላፍታ መዘንጋት የለብንም። ስለዚኽ በረጅሙ

አስፈላጊው ጥናት እና ዝግጅት ከተደረገ፣ አቅም

ከተገነባ፣ ስትራተጂዎች እና ፕላኖች በጥንቃቄ ከተሰሉ

በኢትዮጵያ የሰላም ትግል መስራት ብቻ ሳይሆን

ለኢትዮጵያ ተመራጩ የፖለቲካ እና የመንግስት

ሽግግር ባህል እሱ ብቻ ነው በማለት ጥናታችንን

እንደመድማለን።

www.andinet.org.et

14

ኢሕአዴግና መገናኛ ...

www.andinet.org.et

የግሉን ሚዲያ በተመለከተ ምርጫ 97 ለኢትዮጵያ

ያመጣው መልካምም መጥፎ ነገሮችም አሉ።

የኢትዮጵያ ሚዲያ ላይ ከፍተኛ ጥናት ያደረጉና

ስማቸው እንዳይገለፅ የጠየቁ ምሁር እንደሚሉት

“መልካም ነገር የምለው በአገር ውስጥና በዓለም

ዓቀፍ ጫናዎች ምክንያት ኢሕአዴግ በጭራሽ

ፍቃድ ሊሰጠው የማይፈልገው የነበረውን የሬዲዮ

ፍቃድ መስጠቱ ነው። በእርግጥ ፍቃድ አሰጣጡ

ጥንቃቄ ያልተለየው መሆኑ የሚያስታውቀው፣

የኤፍ.ኤም ሬዲዮ መስመሮች መሆናቸውና ለሦስት

ድርጅቶች ብቻ መፈቀዱ ነው።” ይላሉ። እነዚህ

ሶስት በስራ ላይ ያሉት የኤፍ.ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች

ዛሚ FM 90.7፣ ፋና FM 98.1 እና ሸገር FM 102.1

ናቸው።

በ1999 ዓ.ም የፀደቀው ስለብሮድካስት አገልግሎት

የወጣው አዋጅ በአንቀጽ 23(3) ላይ “የፖለቲካ

ድርጅት ወይም የፖለቲካ ደርጅት ባለአክስዮን

የሆነበት ወይም የፖለቲካ ድረጅት የበላይ አመራር

አባል ባለአክስዮን ወይም በማንኛውም ደረጃ

የአመራር አባል የሆነበት ድርጅት” የብሮድካስት

ፍቃድ እንደማይሰጠው ያውጃል፡፡በኢትዮጵያ

የመገናኛ ብዙሃን ላይ እንደሚያሳየው ዛሬ

በኢትዮጵያ አንድ ሙሉ በሙሉ በመንግሥት

ቁጥጥር ስር ያሉ የቴሌቪዥን ጣቢያና አስር የሬዲዮ

ጣቢያዎች እንዳሉ ይገልፃል፡፡ ይህ ጥናት በግልፅ

እንዳስቀመጠው ስምንቱ ክልላዊ ሽፋን (FM)

ሲኖራቸው፤ ሁለቱ ደግሞ በክልል ደረጃም በአገር

አቀፍ ደረጃም ስርጭት ያስተላልፋሉ፡፡

ምሁሩ ድህረ 97 የተጋረጠ ከባድ ፈተና የሚሉት

ዸግሞ በአጠቃላይ የሚዲያ ተቋማትን የተመለከተ

ቢሆንም፤ እጅግ የከበደው ፈተና ግን ወደ ነፃው

ፕሬስ ማድላቱን ያሰምሩበታል። “ኢሕአዴግ

ከምርጫ 97 በፊት የነፃው ፕሬስ ተፅዕኖ ከቁጥጥሩ

እንደማይወጣ የነበረው እምነት ስህተት መሆኑን

የተረዳው በምርጫው ጊዜ ነበር። ስልጣኑን

ጭምር ሊያሳጡት የሚያስችል አቅማቸውን

በማየቱ ከምርጫው በኋላ በወሰዳቸውና አሁንም

ከሚወስዳቸው እርምጃዎች በቀላሉ ለመረዳት

ይቻላል።” ይላሉ። ለዚህ አባባላቸውም ማስረጃ

አድርገው የሚያቀርቧቸው ዋና ዋናዎቹ የገዢው

ፓርቲ እርምጃዎች በ2001 ዓ.ም የወጣው

የማያላውሰው የሚዲያ ህግንና የአዲስ ነገር ጋዜጣን

እጣ ፈንታ ነው።

የ42 ዓመቱ ሸምሱ ኢቲቪ 3 አልጠራ ብሎት

የቴሌቪዥኑን የውስጥ አንቴና አንዴ ቴሌቪዥኑ

ላይ ይሰካዋል፣ አንዴ ግድግዳው ላይ ይሰካዋል፣

አንዴ ገመድ ቀጥሎበት ከቤቱ ውጭ አጣና አቁሞ

ቢሰቀለውም፤ ጥርት ያለ ምስልና ድምፅ ማግኘት

አልቻለም። ይህን ሁሉ ድካም የሚያይበት ምክንያት

“ኢቴቪ አንድና ሁለት ልዩነት ስለሌላቸው፣ ኢቴቪ

ሦስት የተለየ ነገር ይኖረዋል።” በሚል ተስፋ

መሆኑን ይናገራል። የመስሪያም የመኖሪያም

ስፍራው በሆነችው ትንሿ “ሻይ ቤት” ውስጥ ቀኑን

ሙሉ ተከፍቶ የሚውለው ቴሌቪዥኑ፤ ከኢትዮጵያ

ቴሌቪዥን በስተቀር የሳተላይት ቴሌቪዥን

ፕሮግራሞችን ለመሳብ የሚያስችል መቀበያ ሳህን

ስለሌለው መሆኑን ያስረዳል።

ትንሿ ሻይ ቤቱ በደንበኞች የምትጨናነቀው

በምሳ ሰዓትና በእራት ሰዓታት ነው። በመጠነኛ

ዋጋ የሚሸጣቸው ከሻይ ጀምሮ ያሉት ሌሎች

ምግቦቹን ከኢቴቪ በሚተላለፉት የሰባት ሰዓትና

የምሽት ሁለት ሰዓት ዜናዎች አጅቦ ያቀርባቸዋል።

አብዛኛዎቹ ደንበኞቹ መገናኛ አካባቢ የህንፃ መሳሪያ

በሚሸጥባቸው መደዳ ሱቆች ውስጥ የጉልበት ስራ

የሚሰሩ ሰራተኞች ናቸው። ሲሚንቶና የአርማታ

ብረት የመሳሰሉትን ከመኪና ወደ ሱቆቹ፣ ከሱቆቹ

ወደ መኪና ይጭናሉ፣ ያወርዳሉ። ደንበኞቹን

በከፍተኛ ክብካቤ የሚያስተናግደው ሸምሱ፣

ደንበኞቹ በሁለት ነገሮች ቀልድ እንደማውቁ

ይናገራል። በምግባቸውና በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን።

“አድካሚ የጉልበት ሥራ ስለሚሰሩ፣ ምግባቸውን

በጥራት ብቻ ሳይሆን በፍጥነትም ማቅረብ አለብህ”

ይላል። ከተቀመጠበት እንደነገሩ ወደ ተቀመጠው

ቴሌቪዥን እያማተረ። በምሳና በእራት ሰዓታት

ደምበኞቹ ከምግባቸው ጋር እንዲቀርብላቸው

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንን የቀትር የሰባት ሰዓትንና

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ ጥቅምት 28 ቀን 2004 ዓ.ም.

ከገፅ 7 የዞረ

የምሽት ሁለት ሰዓት ዜናን ነው። ከዜናውም

የስፖርት ዜናውን። የምግብ ቤቷ ደንበኞች፤ የስራ

ልብሳቸውን እንኳን ሳይቀይሩ፣ ሲሚንቶ የጠጣውን

ፀጉራቸውን ሳያራግፉ ቶሎ ምሳቸውን በልተው ወደ

ሥራቸው ለመመለስ ሲጣደፉ ይታያሉ። አንዳንዶቹ

ከላይ ካደረጉት ካኪ ቱታ ሥር የአርሰናል፣ የቼልሲና

የማንቸስተር ዩናይትድ እግር ኳስ ቡድኖች

ማሊያዎችን /ቲ-ሸርቶች/ ማድረጋቸው ይታያል።

ሰባት ሰዓት ሞልቶ የኢቴቪ የዕለቱ ዜና መቅረብ

ቢጀምርም፤ ተመጋቢዎቹ ግድ የሰጣቸው

አይመስልም። ፕሬዝዳንት ግርማ ለሁለቱ ምክር

ቤቶች “በአሜሪካ የተከሰተውን የኢኮኖሚ …..”

ቢልም ዜና አንባቢው ግድ የሰጣቸው አይመስልም።

በየከበቡት ጠረጴዛና እጃቸውን በየሚሰዱበት

ትሪ ላይ አፍጥጠው፣ አልፎ አልፎ ገልመጥ እያሉ

የተከፈተውን ቴሌቪዥን እየቃኙ የራሳቸው

“ወግ” ይጠርቃሉ። ዜና አቅራቢው “አሁን ለሰዓቱ

ወደያዝናቸው የስፖርት …….” የጀመረውን ዓረፍተ

ነገር ከመጨረሱ በፊት “ስፖርት” የሚለውን ቃል

ሲጠራው፤ ከየጠረጴዛው “ዝም በሉ እስፖርት

እንስማ” የሚሉ ድምፆች መውጣት ጀመሩ።

የቴሌቪዥኑ ድምፅ ከፍ እንዲል ተጠየቀ። ታዛዡ

ሸምሱ ድምፁን ጨመረ።

የአገር ውስጥ የስፖርት ክንውኖች ቀረቡ። የውጭ

አገር ስፖርታዊ ክንውኖች በተለይም እ.ኤ.አ የ2012

የአውሮፓ ዋንጫ ማጣሪያ ግጥሚያዎች በምስል

ተደግፈው በጥሩ ትንታኔ በቴሌቪዥኑ መስኮት

ታዩ። የስፖርት ዜናው አብቅቶ ወደ ዋና ዋና ዜናዎች

መመለሱን ዜና አቅራቢው ከመናገሩ በጫጫታ

ተሞላች። “ፈረንሳይ አለፈች፣ የናስሪን ፔናሊቲ

አመታት አየኸው?”፣ “የክርስቲያኖ ሮናልዶን ጐል

ተመለከትህ?”፣ “ፓርቹጋል መሸነፏ ያሳዝናል።”

ሌላም ሌላም የኳስ ትንታኔም አስተያየትም

እየተሰጣጡ ሻይ ቤቷን ጥለው ወጡ። ምሳቸውን

ከኢቴቪ የስፖርት ዜና ጋር አጣጥመው፣ ለራታቸው

የሚሆን ገንዘብ ለማግኘት ወደ ሥራቸው ተመለሱ።

ሸምሱንና ቴሌቪዥኑን ለብቻቸው ትተው።

ሸምሱም አንዴ የቴሌቪዥኑን የርቀት መቆጣጠሪያ፤

አንዴ ውጭ አጣና ላይ የሰቀለውን አንቴናን

መነካካት ይጀምራል። የኢቴቪ ሦስትን የጠራ

ድምፅና ምስል ለማግኘት። ፍለጋውን ይቀጥላል

እስኪሳካለት ድረስ። ወይም ደምበኞቹ ሁለት ሰዓት

መሙላቱን እስኪነግሩት ድረስ።

ኢሣት ያመጣው ጣጣ

ሰለሞን ቻላቸው በህይወቱ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንን

እንደመመልከት የሚጠላው ነገር ያለ አይመስልም፡

፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሲባል መንገሽገሽ

ይጀምራል፡፡ ቤተሰቡ ውስጥ በአማርኛ ዜና

መመልከት የሚፈልግ ሰው በመኖሩ ግን ዘወትር

ማታ ቴሌቪዥኑ ፊት ማፍጠጥ ግድ ሆኖበታል፡

፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሁለትም ሆነ ሦስት

ወይም አራት ግድ እንደሌለው ይናገራል፡፡ በፊት

በፊት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እንዳይከፈት ነበር

ከቤተሰቡ ጋር ሲከራከር የከረመው፡፡ ቀድሞ የሱን

ሃሳብ ደጋፊ የነበረችው ታናሽ እህቱ በእሱ አገላለፅ

“ሌላውን ዓይነት ኢቴቪ” ካልተመለከትኩ እያለች

ታስቸግረዋለች፡፡

ሰለሞን እንደሚለው EBS የተባለውን በዲሽ

የሚተላለፈውን ጣቢያ የኮሌጅ ተማሪ የሆነችው

እህቱ ካላየን ብላ ታስቸግረዋለች፡፡ እንደ ዕምነቱ

EBS የተከፈተው ESAT ጣቢያን ለማስቀየስ ነው፡

፡ በፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ንቁ ተሣታፊ መሆኑን

የሚገልፀው ሰለሞን “መንግሥት በፈጠራት በዚች

ትንሽ መሸወጃ” እህቱን ጨምሮ ብዙ ሰዎች ሲሸወዱ

መመልከቱ እንደሚያናድደው እጁን እያወናጨፈ

ይናገራል፡፡አማራጭ ሲያጣ ሸገር ኤፍ ኤምን

ለመስማት መኝታ ቤቱ መደበቅ ብቸኛ መፍትሄው

መሆኑን ያስረዳል ፡፡

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲና ብቸኛው

የተቃዋሚ ፓርቲ የምክር ቤት አባል የሆኑት

የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ ደግሞ የተለየ ሃሳብ

አላቸው፡፡ “ኢቴቪን ለማየት ምንም የሚያጓጓ

ነገር የለውም፡፡ እንደ ህዝብ ተወካይነታቸው ግን

የመንግሥትን ወቅታዊ አቋሞችና ሃሳቦችን ለማወቅ

ብቻ የሚከታተሉት መሆኑን ገልፀዋል፡፡” አቶ

ግርማ ከዚያ ይልቅ በጣም የሚገርማቸው ጠቅላይ

ሚንስተሩን ጭምር ጠይቀው መልስ ያላገኙለት

ጥያቄ ኢቴቪ አንድ ሆኖ በብቃት መስራት ሳይችል

ሁለትና ሶስት የመሆኑ ሚስጥር ነው፡፡

የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ሚዛናዊነት

አቶ ሰለሞን ኃይለ ማርያም “Transforming State

Broadcasting in to Public Service Broadcasting

in Ethiopia” በሚለው ከ1997 ዓ.ም በፊት

በተሰራው ጥናታቸው እንዳሳዩት የኢትዮጵያ ሬዲዮ

ድርጅት አየር ላይ ካዋላቸው የሁለት ሰዓት ዜናዎች

ውስጥ 74.8% የሚሆኑት ይሰሩ የነበሩት በጣቢያው

ጋዜጠኞች ሳይሆን በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት

እንደነበር ያስረዳሉ፡፡ ጣቢያው በሁለት ሰዓቱ

የማታ የዜና ክፍለ ጊዜው ያሰራጫቸውን ዜናዎች

በመውሰድ የተደረገው ይህ ጥናት እንደሚያሳየው

የዜናው አንባቢዎች ብቻ ሳይሆኑ፤ የዜና አራሚዎቹ

ጭምር የዜናውን ሚዛናዊነት፣ ትክክለኛነትና ነፃ

መሆን ማረጋገጥ እንደማይችሉ ይገልፃል፡፡

ይኸው ተመሳሳይ ጥናት የደረሰበት ድምዳሜ

እንደሚያሳየው ባለስልጣናት በቃል በሚሰጡት

ትዕዛዝ ምክንያት፣ የጣቢያው ጋዜጠኞች

የተዛባ፣ ትክክል ያልሆነና ሚዛናዊ ያልሆኑ

ዘገባዎችን እንዲያስተላልፉ እንደሚገደዱ ፅፏል፡

፡ በተጨማሪም ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው፣

በመንግሥት ላይ ሂስ የሚሰነዝሩ ዜናዎች በጣቢያው

ጋዜጠኞች ቢዘጋጁም፤ ብዙ ጊዜ ዕጣ ፈንታቸው

ውድቅ መደረግና ከኢዜአ ወይም ከዋልታ በመጡ

ሌሎች ዜናዎች መተካት እንደነበር አስፍርውታል፡፡

ሌላው የአቶ ሰለሞን ጥናት የደረሰበት ድምዳሜ

እንደሚያሳየው ለአንድ ወር ገደማ የሰበሰባቸውና

የተነተናቸው የኢትዮጵያ ሬዲዮ ዜናዎች

በማጠቃለያቸው ውስጥ እንዳስቀመጡት የተቃዋሚ

የፖለቲካ ፓርቲዎችን በተመለከተ የተሰሩት ዜናዎች

በሙሉ አሉታዊና ሚዛናዊ ያልሆኑ ሲሆኑ ገዢውን

ፓርቲ የተመለከቱት ደግሞ አዎንታዊ ነበሩ፡፡

በመሆኑም አቶ ሰለሞን ሲደመድሙም የተጠቀሰው

ግኝት የሚያደርሰን መደምደሚያ ገዢው ፓርቲ

በቁጥጥሩ ሥር ያሉትን የመንግሥት መገናኛ

ብዙሃንን ፣ሕገ-መንግሥቱን፣ ሌሎች ድንጋጌዎችንና

የዴሞክራሲን መሠረታዊ መርህ በሚጥስ መልክ

እየተጠቀመበት መሆኑን ነው፡፡ መሠረታዊ መርህ

ብለው የጠቀሱትም የተለያዩ ሃሳቦችን ማስተናገድ

(plurality of opinion) መሆኑን ነው፡፡

አቶ ሰለሞን ኃይለማርያም የጥናታቸው ግኝትን

መሠረት በማድረግ የመፍትሄ ሃሳቦችን በመጠቆም

ጥናታቸውን አጠናቀዋል፡፡ ካስቀመጧቸው

የመፍትሄ ሃሳቦችም መካከልም የህገ-መንግሥቱን

አንቀፅ 29(2) መንፈስ የያዘ አዲስ ህግ በፓርላማው

ማውጣት የመንግሥት መገናኛ ብዙሃንን

ወደ Public service Broadcasting ማዞር ፤

የመንግስት መገናኛ ብዙሃን የቦርድ አባላትን ግልፅ

በሆነ መንገድ መሾም፤የመንግሥትን ጣልቃ ገብነት

በህግ መገደብ፤ሚዲያውን ለህዝብ ክፍት ማድረግና

ሙያዊ ጣልቃ ገብነትን ማስወገድ ጋዜጠኞቹ ሙያዊ

ነፃነት እንዲኖራቸው ማድረግ የሚሉ አሉበት፡፡

ኢሕአዴግ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የግንባሩን

አቋም በሚያንፀባርቁት ይፋዊ ህትመቶቹ ውስጥ

በግልፅ እንዳስቀመጠው፣ መገናኛ ብዙሃን

ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ሊያበረክቱት

የሚችሉትን ሚና ከፍተኛ መሆኑን እውቅና

ይሰጣሉ፡፡ ይህ እውቅና ግን “ለማጥፋትም” ትልቅ

አቅም እንዳላቸው ከመግለፅም ባለፈ መልኩ

መንግሥት ሊቆጣጠራቸው እንደሚገባ አፅንኦት

ይሰጣል፡፡ ለዚህም መከራከሪያው በተደጋጋሚ

የሚያነሳው ምሳሌም በምርጫ 97 ወቅት “ነፃው

ፕሬስ” ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር “በመወገን”

በመንግስት፣ በሕዝብና በአገር አንድነትና ፀጥታ ላይ

ሊያደርሱት የነበሩትን “አደጋዎችን” ነው፡፡ ለዚህም

ምክንያቱን ሲገልፅ “የዴሞክራሲያችን ታዳጊነትና

ውስንነት” መሆኑን ይገልፃል፡፡ ይፋዊ ህትመቶቹም

መፍትሄ ብለው የሚሰነዝሩት፣ አሁን በአገራችን

የሌለው የነቃ ሊብራል መካከለኛ መደብ የመገናኛ

ብዙሃን አካሄድን መስመር ማስያዝ የሚችለው

እስኪፈጠር ድረስ በአንድ በኩል የመንግሥት

ቁጥጥር ተገቢ መሆኑን ያሰምርበታል፡፡ በሌላ በኩል

“ታዳጊ ዴሞክራሲያችን” እንዲጐለብት መንግሥት

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.15

የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታው ሂደት ላይ

ርብርብ ማድረግ ለመቀጠል ቁርጠኛ መሆኑን

ይገልፃል፡፡

ሸክሙ የማነው ?

ምርጫ 97 ውጤትን ተከትሎ በኢሕአዴግና

በቅንጅት መካከል ተፈጥሮ በነበረው ውዝግብ

እንደታየው፣ ሁለቱም ፓርቲዎች የተለያዩ የመገናኛ

ብዙሃንን በመጠቀም ከህዝብ ጋር ይገናኙ እንደነበር

ይታወሳል፡፡ ሂዩማን ራይትስ ዎች አውጥቶት

የነበረው አንድ ዘገባ እንደሚያሳየው፤ በምርጫ 97

ሰሞን በኢትዮጵያ ታይቶ የነበረው የነፃው ፕሬስ

በነፃነት ያሰራውን ከባቢ መፈጠሩ በኢትዮጵያ ታሪክ

ተከስቶ እንደማያውቅ ነው፡፡ ይኸው ተመሳሳይ ዘገባ

እንደሚያትተው ከድህረ-ምርጫ 97 በመንግሥት

የተወሰዱ እንደ ጋዜጠኞችን ማሰርና ብዙም

የማያላውስ አዲስ የሚዲያ ሕግ ማውጣት ፕሬሱን

መቀመቅ እንደከተተው ይደመድማል፡፡

ፖለቲካ ፓርቲዎች ውጤት ለማምጣት የመገናኛ

ብዙሃንን እድሎችን አሟጦ መጠቀም፣ ከየፓርቲዎቹ

የቀን ተቀን ስራ እኩል (ምናልባትም የበለጠ?)

ትኩረት እንደሚያስፈልገው ከኢሕአዴግና

ከቀድሞው ቅንጅት በስተቀር በደንብ የተረዳው

ያለ አይመስልም፡፡ የቀድሞው ቅንጅት ምክር ቤት

ለመግባት ወይም ላለመግባት ረጅምና ተከታታይ

ስብሰባዎች አድርጐ፣ በመጨረሻ ላይ የደረሰበት

ውሳኔ የማመቻቸት (Compromise) ነበር፡

፡ ፓርቲው ምርጫ 97 ነፃና ፍትሃዊ ያልነበረ

መሆኑን ቢያምን፣ ለኢሕአዴግ “ስምንት ነጥቦችን”

አቅርቦ ገዢው ፓርቲ ከተቀበለው ምክር ቤት

ሊገባ እንደሚችል መግለጹ ይታወሳል፡፡ ከስምንቱ

ጥያቄዎች ውስጥም የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን

ከገዢው ፓርቲ ቁጥጥር ተላቀው፣ ራሳቸውን ችለው

ነፃ ሆነው እንዲቋቋሙ የሚጠይቀው አንዱ ነው፡፡

በሌላ በኩል ኢሕአዴግ በመንግሥት ቁጥጥር

ሥር ያሉትን መገናኛ ብዙሃንን ለሚቃሙ ወገኖች

ለማጋራት ፍቃደኛ አይመስልም፡፡ ይህ ብቻ

አይደለም፡፡ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች “በራቸው

ክፍት ነው” ተብለው የሚገመቱ የመገናኛ ብዙሃንን

ከማዳከምም የሚመለስ አይመስልም፡፡ ነፃውን

ፕሬስ ጠንከር ባለ አዋጅ፤ ኢሳትን፣ የአሜሪካንና

የጀርመን ድምፅን በማፈን ይህንን አቁዋሙን

አሳይቱአል፡፡

በምርጫ 2002 ሰሞን እንዳስተዋልነው፤ የአሜሪካን

ድምፅ ሬዲዮን ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይሰማ

ለማድረግ መንግሥታቸው እንደሚያፍነው

ጠቅላይ ሚንስትር መለስ በግልፅ መናገራቸው

አንድ ማሳያ ተደርጐ ሊወሰድ ይችላል፡፡ በእርግጥ

ኢሳት (ESAT) የተባለውን ከኢትዮጵያ ውጭ

የሚሰራጨውን የሳተላይት ቴሌቪዥንን ኢትዮጵያ

ውስጥ እንዳይደርስ የተደረገው የመንግሥታቸው

እጅ ስለገባበት እንደሆነ ተጠይቀው፤ በጉዳዩ ላይ

አስተያየት መስጠት እንደማይፈልጉ በመግለጽ ፣

ጥያቄውን አለመመለሳቸው ይታወቃል፡፡ የዚህ

ዓይነት መልስ ግን የቴሌቪዥን ፕሮግራሞቻቸው

ኢትዮጵያ ውስጥ ሊታዩ ያልቻሉት ኢሕአዴግ

ስርጭታቸው ላይ እየፈጠረ ባለው ማስተጓጐል

ምክንያት መሆኑን ለሚከሱት የኢሳት ጣቢያ

ኃላፊዎች፣ በቂ መልስ መስጠት የቻለ አይመስልም፡

፡አሁንም ክሳቸውን ቀጥለዋልና ፡፡

አጠቃላዩ የአገራችን የመገናኛ ብዙሃን ነባራዊ

እውነታ፣ በፍፁማዊ የበላይነት በሚያስብል

ደረጃ ኢሕአዴግ ለብቻው ተቆጣጥሮት ባለበት

ሁኔታ ሌሎች ድምፆች የመስተናገዳቸው ዕድል

በጣም ጠባብ ይመስላል፡፡ መድረክ ወደ “ግንባር”

መሸጋገሩን ለማብሰር መድረክ ላይ የወጡት ዶ/ር

መረራም፣ ኢቲቪ አንድና ሁለት ሰልችተውት ኢቲቪ

ሦስትን ሲፈልግ የሚውለው ሸምሱም፣ ኢሳትን

ለመከታተል ያልቻለውና ኢቲቪን ሸሽቶ ማምለጥ

ያቃተው ሰለሞንም የልባቸው በቅርቡ የሚደርስ

አይመስልም፡፡ የምርጫ 97 ውጤት የሆነው

የሸገር ኤፍ.ኤም ሬዲዮ አይነት የቴሌቪዥን ጣቢያ

እንዲመጣ መመኘታቸው አልቀረም፡፡ ምኞታቸው

መቼ እውን እንደሚሆን ግን መገመት እንኳን

አልቻሉም፡፡

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.15

መግለጫ ተያት

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ ጥቅምት 28 ቀን 2004 ዓ.ም.

ትግሉ መራራ ቢሆንም በፅናት ለድል እንበቃለን!

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ የተነሳለትን ዓላማ

ለማሳካት የአምባገነኖችን አፈና እየተቋቋመ አባላቱ የህይወትና የንብረት መስዋዕትነት እየከፈሉ

እስከዛሬ ቀን ደርሰዋል፡፡ ዛሬም ገዢው ፓርቲ በአዋጅ በመደገፍ በአካሄደው መንግስታዊ

የጥቃት ዘመቻ ከፍተኛ የፓርቲው አመራሮች፡- (1ኛ) ምክትል ሊቀመንበርና የሕዝብ ግንኙነት

አላፊ አቶ አንዱዓለም አራጌ፣ (2ኛ) የብሔራዊ ምክር ቤት አባል አቶ ናትናኤል መኮንን፣ (3ኛ)

የብሔራዊ ምክር ቤት አባል አቶ ብርሃኑ አሳምነው የማያባራው የግፍ ጥቃት ሰለባ ሆነዋል፡፡

በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ባደረጉት ንግግር በተቃዋሚው ጎራ በተለይ

በአንድነት ፓርቲ ላይ የሚደረገው አፈና ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡ ከጥቃት ዘመቻው

በተጨማሪም የፍርድ ቤቱን በትር በህግ ሽፋን እንደሚጠቀሙ በአደባባይ ያለምንም ይሉኝታ

አረጋግጠውልናል፡፡ መንግስት አንድነትን በህግ ሽፋን ስም በጉልበት ለማዳከም መዘጋጀቱን

ያለጥርጥር አረጋግጠውልናል፡፡

ይህ አደገኛ መንግስታዊ ሽብር በፓርቲያችን ላይ እየተፈፀመ ባለበት በአሁኑ ወቅት

የፓርቲያችን ከፍተኛ የስልጣን አካል የሆነው ብሔራዊ ምክር ቤታችን ከጥቅምት 25-

26/2004 ዓ.ም. የአንደኛውን ዙር የመጨረሻ የሥራ ዘመኑን ስብሰባ በታላቅ ቁጭትና ወኔ

ታጅቦ ጉባኤውን አከናውንዋል፡፡

ጉባኤው መንግስት ሕገ-መንግቱን በመጣስ በአባሎቻችን ላይ እየፈፀመ ያለውን የእብሪት

እርምጃ አውግዝዋል፡፡ እንዲሉ በሽብርተኝነት ስም በግፍ

አፍኖ ከማንም ጋር እንዳይገናኙ ሸብቦ ያስራቸው አባሎቶቻችን በአስቸካይ እንዲፈቱ ምክር

ቤቱ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ምክር ቤቱ በቀረበለት አጀንዳ ላይ ለሁለት ቀናት ሰፊና ጥልቀት ያለው ውይይት በማድረግ

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለነጻነትና ለዴሞክራሲ የሚያደረገውን ሰላማዊ ትግል ወደ ፊት ለማራመድ

የሚያስችሉ ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን አስተላፏል፡፡ በተለይም የፓርቲውን የ2003 ዓ.ም. የሥራ

አፈፃፀምን በተመለከተ ሰፊ ሪፖርት ቀርቦ ደካማና ጠንካራ ጎኖች ተገምግመዋል፡፡

ምክር ቤቱ ከአምስት ወር በፊት ያቋቋመው የጠቅላላ ጉባኤ ጠሪ ኮሚቴ ከአንድ

ወር በኋላ የፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ የስራ ዘመኑን የጨረሰውን ይህን ምክር ቤት

በክብር ያሰናብተዋል፡፡ የሁለተኛው ዙር አዲስ ምክር ቤት በጠቅላላ ጉባኤው በሚደረግ ነፃና

ዴሞክራሳያዊ ምርጫ አዲስ ብሔራዊ ምክር ቤት በመምረጥና የስልጣን ርክክብ ለማድረግ

አንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ም/ቤት መደበኛ ስብሰባውን አካሄደ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ /አንድነት/

ብሔራዊ ም/ቤት የመጀመሪያ ዙር የመጨረሻውን የሥራ

ዘመን ጥቅምት 25 እና 26 ቀን 2004 ዓ.ም በጽ/ቤቱ

አዳራሽ መደበኛ ስብሰባውን አካሄደ፡፡

በስብሰባውም በዋነኛነት አራት አጀንዳዎች

ለውይይት የቀረቡ ሲሆን እነኝህም 1ኛ የብሔራዊ ሥራ

አስፈፃሚ ኮሚቴ የሥራ ሪፖርት ማዳመጥ 2ኛ የጠቅላላ

ጉባዔ ጠሪ ኮሚቴ የሥራ ሪፖርት ማዳመጥ 3ኛ የአምስት

ዓመት እቅድና ስትራቴጂ መሠረት በማድረግ የ2004

ዓ.ም በጀት ዕቅድን ማጽደቅ እና 4ኛ ያለፉትን ስብሰባዎች

ቃለ ጉባዔ ማፅደቅ በሚሉ አጀንዳዎች ዙሪያ ነበር፡፡

ብሔራዊ ምክር ቤቱ በአጀንዳዎቹ ላይ

ሰፊ ውይይት በማድረግ አጀንዳዎችን ያፀደቀ ሲሆን

በተለይም በብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የሥራ

ሪፖርት በፓርቲው ሊቀመንበር በዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ

ቀርቧል፡፡

በሪፖርቱ ላይ በእቅዱ መሠረት የተሰሩና

ያልተሰሩ ሥራዎችን መለየት ተችሏል ሲሉ አባላቱ

ገልፀዋል፡፡ በእቅዱ መሠረት ከተሰሩት ውስጥ የፓርቲው

ልሳን “ፍኖተ ነፃነት” ጋዜጣ በየሳምንቱ አሳትሞ

የፓርቲውን እንቅስቃሴ ወቅታዊ የሆኑ ሀገር አቀፍና ዓለም

አቀፍ መረጃዎችን ለሕዝቡ ማድረስ፣በሀገራዊ ወቅታዊ

ጉዳይ ላይ የተለያዩ ምሁራንን ከውጭና ከሀገር ውስጥ

በመጋበዝ ውይይት ማድረግ፣የፓርቲው መመሪያና ደንብ

በሚፈቅደው መሠረት ከመድረክ አቻ ፓርቲዎች ጋር

ሰፊና ጥልቅ ውይይት በማድረግ መድረክን ከቅንጅት

ወደ ግንባር የማሸጋገር ሂደት፣ከብርሃን ለአንድነትና

ለዴሞክራሲ ፓርቲ ጋር ውህደት የመፍጠር ሂደት

ከተሳኩ ተግባራቶች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው ተብሏል፡፡

ሌላው ፓርቲው መዋቅሩን በመላው

ሀገሪቱ የማስፋፋትና አሰራሩንም እስከ ወረዳ ድረስ

በመዘርጋት የፓርቲው አባላት በአቅራቢያቸው

እንዲደራጁ ተደርጓል፡፡ ይሁን እንጂ ይህንና ሌላሎች

እቅዶች ሙሉ በሙሉ ተፈፃሚ እንዳይሆኑ የተለያዩ

እንቅፋቶች ተፈጥረው ነበር፡፡ ከችግሮቹም መካከል

ኢህአዴግ የፖለቲካ ምህዳሩን ማጥበብ፣የፓርቲ አባላትን

ማስፈራራት፣ማሰርና መግደል ዋነኞቹ ችግሮች እንደሆኑ

በም/ቤቱ ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም ፓርቲው በሰው

ኃይል፣በአቅምና በገንዘብ ማነስ ምክንያት በእቅዱ መሠረት

የሚጠበቅበትን አልሰራም ሲሉ ያለፈው ዓመት ስራ

አፈፃፀም ሪፖርትን ም/ቤቱ ገምግሟል ሲል የፓርቲው

ጽ/ቤት ገልጿል፡፡

ለእቅዱ መሳካት ሌሎች ችግሮችም

ተነስተዋል፡፡ እንደ ችግር ከተነሱት መካከል በቂ የገንዘብ

የታሰበውን ያህል ያለማግኘት፣በቂ የሰው ኃይል ያለመኖር

ተጠቅሰዋል፡፡

ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮችን ለመቅረፍ

በ2004 ዓ.ም የተለያዩ የመፍትሄ አቅጣጫዎች የተነሱ

ሲሆን ከነዚህም መካከል በዕውቀትና በቁርጠኝነት

ላይ የተመሰረተ የሰው ኃይል ወደ ፓርቲው እንዲመጣ

መጋበዝ፣ደጋፊዎች ከእውቀትና ከጉልበት በተጨማሪ

በገንዘብም ድጋፍ ማድረግ እንዲችሉ ሕጋዊ የሆኑ

የተለያዩ ስልቶችን መቀየስና ለሕዝቡ ይፋ ማድረግ፣

የሚመጣውም አዲሱ ም/ቤት አባላት በዕውቀትና

በቁርጠኝነት ላይ መሠረት ማድረግ እንዳለበትም ም/ቤቱ

ጠቁሟል፡፡

አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ

አካባቢ ያሉ ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙ የፓርቲው

አባላትንና ሌሎች የፖለቲካና የሕሊና እስረኞችን ጉዳይ

የሚከታተል ልዩ ግብረ ኃይል እንደተቋቋመና ሥራውን

እያከናወነ እንዳለም በሪፖርቱ ገልጿል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከ13 ቀናት በፊት

የፓርቲው አባል አቶ ገዛኸኝ ምትኩ በሽብር ተጠርጥሮ

ከሚኖርበት ቂርቆስ ክ/ከተማ በመውሰድ ማዕከላዊ እስር

ቤት እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡ ባለፈው መስከረም 4 ቀን

2004 ዓ.ም ተጠርጥረው ከታሰሩት መካከል የአንድነት

ፓርቲ ም/ሊቀመንበርና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ

አንዱዓለም አራጌ ታመው ሆስፒታል ሄደው የሕክምና

እርዳታ እንደተደረገላቸው በሪፖርቱ ላይ የፓርቲው

ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ገልፀዋል፡፡

በስብሰባው ላይ በቀረቡት አጀንዳዎች ዙሪያ ሰፊ

ውይይት ካደረገ በኋላ በአባላቱ ፀድቆ የመጨረሻው

የሥራ ዘመን ጥቅምት 26 ቀን 2004 ዓ.ም ተጠናቋል

ሲል የአንድት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ /አንድነት/

ብሔራዊ ም/ቤት በተለይም ለዝግጅት ክፍላችን ገልጿል፡

፡ይህ በእንዲህ እንዳለ የጉበኤ ጠሪ ኮሚቴ የተሻሻለ

ፕሮግራምና ደንብ ለምክር ቤቱ አቅርቧል፡፡ በአንድነት

15

ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ለምክር ቤቱ አብስሮዋል፡፡ ብሔራዊ ምክር ቤቱ የአንድነት ጠቅላላ

ጉባኤ ህዳር 30 እና ታህሳስ 1/2004 እንዲካሄድ ወስኗል፡፡

ይህንን ተከትሎ ለጠቅላላ ጉባኤ ቀርበው የሚፀድቁትን ልዩ ልዩ የፓርቲው የመታገያ

ሠነዶች ለምክር ቤቱ ቀርበው ከተመረመሩ በኋላ ጠቅላላ ጉባኤው መርምሮ እንዲያፀድቃቸው

ወስኗል፡፡ የፓርቲያችን አዲሱ ሊቀመንበር ከሁሉም አባላት በውድድር በዕጩነት ቀርበው

በጠቅላላ ጉባኤው ፊት አባላት ቀጥተኛ የድምፅ አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት እንዲመረጡ

ወስኗዋል፡፡

አንድነት በአለፉት ሦስት ዓመታት ከአጋጠሙት መሰናክሎች ትምህርት ወስዶ የራሱን

የትግል ስትራቴጂና የአምስት አመት እቅድ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ የተቀየሰውን

ስትራቴጂ ለመተግበር የሚያስችል አቅም ለመፍጠር ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው፡፡

በአዲሱ ዓመት ዜጎች ያለፍርሃት፣ ሳይሸማቀቁ በነፃነት የሚኖሩባት፣ በግል ጥረታቸው

ያፈሩትን ሃብትና ንብረት በግፍ የማይነጠቁባት፤ የዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶች

የተከበረባት ኢትዮጵያን ለመፍጠር በሚደረገው ትግል ኢትዮጵያዊያን ሁሉ እጅ ለእጅ

ተያይዘን በፅናት እንድንታገል ብሔራዊ ምክር ቤታችን ጥሪውን ያቀርባል፡፡

መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሕገወጦችን አውግዞና፣ ጊዜው የለውጥ መሆኑን ተገንዝቦ

ፓርቲያችን የሰነቀውን ሀገራዊ ራዕይ ደግፎ በዕውቀት ላይ የተመሠረተና የሰለጠነ የመቻቻል

የፖለቲካ መርሆችን ተከትሎ ለነፃነቱ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት የአንድነት ፓርቲ

ብሔራዊ ምክር ቤት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

የፖለቲካና የህሊና እስረኞች በአስቸኳያ ይፈቱ!!

ሠላማዊ ትግል ያሸንፋል!!

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት

ጥቅምት 26/2004 ዓ.ም.

አዲስ አበባ

የስብሰባው ተካፋዮች በከፊል

ፕሮግራም ውስጥ እንዲካተቱ ከተደረጉ ጉዳዮች

መካከል አሸባሪነትን በተመለከተና የመሬት ወረራ

ጉዳይን ያካትታል፡፡ ምክር ቤቱ የፓርቲው ፕሮግራም

ውስጥ እንደ አዲስ የተካተቱትን ጉዳዮች በጥልቀት

ተወያይቶበቷል ሲል ምክር ቤቱ ጠቁሟል፡፡

የተሻሻለው የፓርቲው ህገ-ደንብ እንደሚያስረዳው

የፓርቲው ሊቀመንበር በጠቅላላ ጉባኤ የሚመረጥ ሲሆን፣

ሊቀመንበሩ ሌሎች የስራ አስፈፃሚ አባላትን መልምሎ

በዕጩነት ለብሔራዊ ምክር ቤት አቅርቦ ያፀድቃል፡

፡ የፓርቲው መሪ መሆን የሚፈልጉና የተቀመጠውን

መስፈርት የሚያሟሉ አባላት የጠቅላላ ጉባኤ አባላትን

ድጋፍ እንዲያደርጉ በመቀስቀስ መወዳደር እንደሚችሉ

ተገልጿል፡፡ በተመሳሳይም የስራ አስፈፃሚ አባለት ቁጥር

ከ18 ወደ 11 እንዲወርድ ተደርጓል፡፡

ብሔራዊ ምክር ቤቱም የፓርቲውን ጠቅላላ ጉባኤ

በህዳር 30 እና ታህሳስ 01 ቀን 2004 ዓ.ም. እንዲካሄድ

መወሰኑን ምክር ቤቱ በተለይም ለዝግጅት ክፍሉ

ገልጿል፡፡

www.andinet.org.et

16

www.andinet.org.et

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ ጥቅምት 28 ቀን 2004 ዓ.ም.

E-mail: udjparty@gmail.com

andinet@andinet.org

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.15

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!