24.08.2013 Views

የመሬት ቅርምት ለልማት - Ethiopia: A voice for the voiceless

የመሬት ቅርምት ለልማት - Ethiopia: A voice for the voiceless

የመሬት ቅርምት ለልማት - Ethiopia: A voice for the voiceless

SHOW MORE
SHOW LESS

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.10

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.10

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 23 2004 ዓ.ም.

የመሬት ቅርምት ለልማት

ወይንስ ለአገር ጉዳት? ልጄ በረሃብ

ስለ ፌደራሊዝሙ እኔም የምለው አለኝ

በዚህ ጭብጥ አገባብ ላይ እንዳልነው፣ የጋራ ጥቅም ያላቸው እና በራስ ገዝ እና ክልላዊ የመንግሥት የስልጣን ቁጥጥር የተጠመዱ ልሂቃን፣ ወደ ፓርቲነት

ሲመነዘሩ `የማዕከላዊ ስርዓት` መንስኤን ያሳያል፡፡ ማለትም ባለው የፓርቲ ስርዓት “ኢህአዴግ [ማለት] ህወሓት የበላይ አገር የሆነበት የብሔር ተኮር ፓርቲዎች

ጥምረት ሆኖ በዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ደግሞ አጠቃላይ የፌዴራል ስርዓቱን ይቆጣጠራል፤ እንዲሁም በክልላዊና ንዑስ ክልላዊ መንግስታት አስተዳደር

ውስጥ በስፋት ጣልቃ ይገባል፡፡” ደንበኛ (client) ሆኖ ለመቆየት ብቻ የሚውተረተሩ ፓርቲዎች በክልላዊ ጉዳያቸውም ቢሆን ፓትሮኑን ፓርቲ እስካላስደሰቱ

ድረስ ደህንነት አይሰማቸውም፡፡” ከዚህም መገንዘብ የሚቻለው፣ ፌዳራሊዝም ኮሙኒስት ፓርቲው ጥበቃ ቁጥጥር በመያዙ ላይ መሠረት ያደረገው የሶቭየት

ሞዳል” መሆኑን ፕ/ር መሳይ ይገልፃሉ....

ያለማቋረጥ እያደገ

ያለው የዋጋ ንረት

መልህቅ ይበጅለት

በ1997 ዓ.ም 6.8% የነበረው የዋጋ ንረት

በተከታዮቹ ሁለት አመታት 12.3 በመቶ እና

15. 8 በመቶ ደረሰ፡፡ ይህም ማለት የንረቱ

እድገት መጠን በሁለት ዓመት ውስጥ 132

በመቶ ሆነ ማለት ነው፡፡ ከ1999 ዓ.ም በኋላ

ያሉት አራት ዓመታት አጠቃላይ የዋጋ ንረት

መጠንን ስንመለከት ደግሞ 1999 ላይ 15.8

በመቶ የነበረው በ2003 ዓ.ም 57 በመቶ

ደርሷል፡፡ ይህም አጠቃላይ የአራት ዓመት

የዋጋ ንረት እድገቱን 36ዐ.7 ፕርሰንት

መድረሱን ......

1

ሞተብኝ!

የደረሰብኝን በደል ለመንግስት አሳውቁልኝ ሲሉ

ወ/ሮ አስናቀች ገ/መድህን ዝግጅት ክፍላችንን

ተማፀኑ፡፡ በአዲስ ከተማ ክ/ከ ወረዳ 7 (በቀድሞ

ቀበሌ 16/17) የቤት ቁጥር 750/2 ነዋሪ የሆኑት የቤት

እመቤት እምባቸውን እያረገፉ ሁለት የወረዳው

ባለሥልጣናት በህጋዊ መንገድ የተሰጠኝን ማብሰያ

አፍርሰው ዕቃዬን ውጪ ስለወረወሩብኝ ልጆቼን

አብስዬ የማበላበት ቦታ አጥቼ በመቸገሬ ትንሹ

ልጄም በረሃብ ሞተብኝ” ሲሉ በማያቋርጥ ለቅሶ

ዝግጅት ክፍላችን በመገኘት አንብተዋል፡፡

ወ/ሮ አስናቀች እንደሚሉት “እኔ ከቫይረሱ ጋር

የምኖር ዜጋ ነኝ” ካሉ በኃላ በመቀጠል “ለአዲስ

አበባ ከተማ የባለ አደራ መስተዳድር ከንቲባ ብርሃኑ

ዱሪሳ አመልክቼ የተሰጠኝ ማብሰያ ቤት የወረዳው

መስተዳድሮች ፍጹም ሰብአዊነት በጐደለው ሁኔታ

ቤቱን አፈራርሰው ዕቃዬን ሜዳ ላይ ወረወሩት፡፡

አምስት ልጆች አሉኝ፡፡ ከአምስቱ አንዱ በረሃብ

ሞተብኝ፡፡ መንግስት መድኃኒት በነፃ ይሰጠናል፡፡

ህብረተሰቡ እህል እየሸመተ ያቀርብልናል፡፡ 50

ኪ.ግ የተፈጨ እህል እያለኝ ማብሰያ ቦታ አጥቼ

ልጄን አጣሁ፡፡ መንግስት ምንም አልበደለኝም፡፡

በወረዳ እና በቀበሌ ያሉት ግን ሊያስቀምጡን

ሊያኖሩን አልቻሉም፡፡ ሰውን እንደሰው አያዩም፡፡

ትቢታቸውና እብሪታቸው ያሳዝናል፡፡

መንግስት የሚያስቀምጣቸውን ሰዎች በትክክል

አያውቅቸውም፡፡ ህዝብን በአግባቡ አገልግሎት

እየሰጡ አይደለም መንግስት ይወቅልን ጩኸቴን

ለመንግስት አሰሙልኝ” ሲሉ ብሶታቸውን በመሪሪ

ሐዘን ገልፀዋል፡፡

“ሽብርተኝነትን ለመከላከል” ተብሎ ሽብር ተፈጥሮ ይሆን?

6

13

የምንቃወመው አምባገነናዊነታችሁንና ኢ-ዴሞክራሲያዊ

አሠራራችሁን እንጂ እንናተን አይደለም

የወረደ እና አንድን ርዕሰ ብሔር

ሆኖ አገልግሎ የነበረን ሰው አመናጭቁ

ወይም እነገሌን ሊጠይቅ የመጣ ሰው

በኢትዮጵያዊ ጨዋነት አታገልግሉ የሚባል

አይመስለኝምና ነው፡፡ ምክንያቱም ይህ

ዓይነቱ አሰራር ማንንም አይጠቅምም፡፡

መንግሥት እንደመንግሥት አድርጎት ከሆነ

ተጨማሪ የታሪክ ስህተት እያስመዘገበ

ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ የእኔ ግምት ዶ/ር

ነጋሶን ያላወቁዋቸው ስለመሰለኝ ዶ/ር ነጋሶ

መሆናቸውን ለማስረዳት ሞከርኩ፡፡

4 10

“ማነው ተው

የሚለኝ?!”

የመቶ በመቶ የምርጫ ድል (ዘጠና

ዘጠኝ ነጥብ ምናምን የሚለውን ቁጥር

ያልተጠቀምኩት አውቄ ነው፡፡ ምክንያቱም

ይህ ገለፃ፤ ምርጫው ሰማንያ በመቶ

የማሸነፍ ያህል ያስመስለዋል፡፡ ሥነልቡናዊ

ጥቅም አላት፡፡) ከኔ በላይ ለአገሪቱ ተቆርቆሪ

ወገን የለም ብሎ የሚያስብ ገዢ ፓርቲ እና

ይህን ሀሳብ የመጨረሻ እውነት አድርጐ

4

የሚቆጥር የካድሬ ጐርፍ፣ የማያባራ

የምሁራን....

6

www.andinet.org.et

2

ብዙአየሁ ወንድሙ

www.andinet.org.et

አእምሮው ጤነኛ የሆነ ኢትዮጵያዊ ሽብርተኝነትን

ያወግዛል ብዬ አምናለሁ፡፡ ምክንያቱም የኢትዮጵያዊ

ባህልና ጨዋነት የማይቀበለው በመሆኑ ነው፡፡

ኢትዮጵያኖች ሲወርድ ሲዋረድ በመጣው ባህል ፈርአ

እግዚአብሄር ያደረብን ነን፡፡ በእርግጥ 80 ሚሊዮን

ህዝብ እንደ አንድ ሰው ያስባል ተብሎ አይታሰብም፡፡

ጥንት አባቶቻችን የሚደርስባቸውን በደል ለመከላከልና

የተፈጸመባቸውን ጥቃት ለመበቀል የሚወስዱት ርምጃና

ዱር ቤቴ ብለው ጫካ መግባታቸው ግልጽ ነው፡፡ የአፀፋ

ርምጃቸው ከግለሰብ ንብረት ጋር ነው፡፡ የእህል ክምርና

ቤት ማቃጠል ባለጋራን ወይም የባላጋራን ዘመድ አዝማድ

ፈልጐ መግደል ይከሰታል፡፡ ይህ በአብዛኛው አካባቢ

እየተወገዘና እየተናቀ በኋላ ቀርነቱ ተረት እየሆነ ነው፡፡

በአሁኑ ጊዜ በአንዳንድ ሥፍራዎች አልፎ አልፎ የሚከሰት

ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ በህብረተሰቡ የሚበረታታ አይደለም፡

፡ ድርጊቱን በኋላ ቀር አካሄድነቱ ሲወገዝ ይሰማል፡፡

እንዲህ ዓይነቱ ጥቃቶች በወቅቱም ቢሆን

የሚያተኩሩት ግለሰብ ላይ እንጂ የህዝብና የመንግሥት

የልማት አውታሮች ላይ አልነበረም፡፡ በቅርቡ ሽብርተኝነት

የዓለም ሥጋት እየሆነ መጥቷል፡፡ አብዛኛው የዓለም

ህዝብ ሽብርተኝነትን አምርሮ ይጠላል፡፡ ጉዳቱንም

ተመልክቶታል፡፡ የዛሬ 10 ዓመት በአሜሪካን አገር

የተፈፀመውን ጥቃት ማስታወስ በቂ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ

አገሮች ሽብርተኝነትን የሚዋጉበት ህግ አውጥተዋል፡

፡ ሆኖም ግን አብዛኛው አገሮች ሽብር ይፈፀምብኛል

ብለው የሚሰጉት ከዜጐቻቸው ሳይሆን ከባዕድ ነው፡፡

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 23 2004 ዓ.ም.

በሃይማኖት፣ በድንበር ግጭት፣ በር እዮተዓለም ልዩነት

ወዘተ የራስን ሐሳብ በኃይል ሌላው ላይ ለመጫን የሽብር

ተግባርን እንደውጊያ ሥልት ሲጠቀሙበት ይታያል፡፡ ይህ

በማንኛውም መልኩ የሚደገፍ አይደለም፡፡

የአገራችን የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ 652/2001

መግቢያ “ሕዝቦች በሰላም በነጻነትና በተረጋጋ ሁኔታ

ለመኖር ያላቸው መብት ከሽብርተኝነት አደጋ ሁልጊዜ

መጠበቅ ያለበት በመሆኑ፤ ሽብርተኝነት ለሀገራችን ሰላም፣

ደኅንነትና ዕድገት ፀር እንደሆነ፣ ለአካባቢያችን ለዓለም

ሰላም እና ደህንነትም ከፍተኛ ስጋት እንደሆነ ግንዛቤ

የተወሰደ በመሆኑ፤ በስራ ላይ ያሉት የሀገሪቱ ሕጎች

በበቂ ሁኔታ ሽብርተኝነትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር

የሚያስችሉ ባለመሆናቸው ጠንካራ የሕግ አቅም መፍጠር

በማስፈለጉ፤ ሽብርተኝነትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና

ለማምከን በቂ መረጃዎችንና ማስረጃዎችን ለማሰባሰብና

ለማጠናቀር፣ በሽብርተኝነት የተጠረጠሩ ሰዎችን ወይም

ድርጅቶችን ለሕግ ለማቅረብ የሚያስችሉ የተጠናከሩ

የምርመራና ክስ የማቅረብ አዳዲስ ስልቶችንና ስርዓቶችን

በሕግ መቋቋም አስፈላጊ በመሆኑ፤ ሽብርተኝነትን

በሚገባ ለመዋጋት የፀረ-ሽብርተኝነት ዓላማ ካላቸው

የአካባቢያችን፤ የአሕጉራችንና የሌለው የዓለም ክፍሎች

መንግስታትና ሕዝቦች ጋር መተባበር እና በተለይ

ከተባበሩት መንግሥታትና ከአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራት

ጋር የተደረጉትን ስምምነቶች ስራ ላይ ማዋል አስፈላጊነቱ

የታመነበት በመሆኑ፤ በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ

ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀጽ () መሠረት

ደሰሳ

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.10

“ሽብርተኝነትን ለመከላከል” ተብሎ

ሽብር ተፈጥሮ ይሆን?

...“በሽብር” ተግባር የተጠረጠሩ ሰዎች ሲያዙ እየሰማን ነው፡፡ እውነት በሽብር ተግባር ሲንቀሳቀሱ ተገኝተው ነው? ወይስ በፖለቲካ

አመለካከታቸው ነው? መንግስት “በፖለቲካ አመለካከታቸው አይደለም፡፡ ህጋዊ ፓርቲዎችን ሽፋን አድርገው ከአሸባሪ ቡድን ጋር

ሲንቀሳቀሱ መረጃ አግኝቼ ነው” ብሎናል፡፡ እንዴት እንመነው? ከዚህ ቀደም በርካታ ነገሮች ተዋሽተናል፡፡ ዛሬስ እንዴት ርግጠኛ ሆነን

እንቀበል? እሺ እውነት ነው ብለን እንቀበል፡፡ ተጠርጣሪውን በቀላሉ መያዝ ሲቻል ግርግርና ሽብር ማንሳት ለምን አስፈለገ? እስቲ

ሰሞኑን ከታሰሩት ሰዎች የተወሰኑትን እንመልከት፡፡ ባለን መረጃ ጥቂቶቹ ግርግር ሳይፈጠር ህዝብ ሳይረበሽ የተያዙ አሉ፡፡ ይህ ሞያዊም

ጨዋነትም ነው፡፡ የኦፍዴን ም/ሊቀመንበርና የመድረክ ሥራ አስፈፃሚ የተያዙት “በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በማስተማር ላይ

እንዳሉ ነው” ተብሎአል፡፡ ሥራቸውን ጨርሰው ሲወጡ ቢያዙ አይቻልም ነበር? የመኢዴፓ ዋና ፀሐፊ ዘመኑ ሞላ አያያዝ ለየት ይላል፡

፡ “አንድ ሴት ደውላ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ተማሪ ነኝ፤ በፓርቲዎች ዙሪያ ጥናታዊ ጽሑፍ እያዘጋጀሁ ነኝ ተባበሩኝ” ብላ

ደወለች ይላሉ የትግል አጋሮቻቸው፡፡ አቶ ዘመኑም በሐሳቡ “ተስማምተው ቢሮአቸው ቀጠሯት የተባለችውም ወ/ሪት መጥታ አቶ ዘመኑ

ቢሮ ትገባለች፡፡ ገብታ ከመቀመጧ ስቪል የለበሱ ቀድመው በሩን በርግደው ቆሙ፡፡ መሣሪያ የያዙና ዩኒፎርም የለበሱ ተከታትለው

በመግባት ይዘዋቸው ሄዱ፡፡ ባለጥናቷ በየት መንገድ እንደወጣች በምን ፍጥነት አካባቢውን እንደለቀቀች አላወቅንም” በማለት

ተናግረዋል...

የሚከተለው ታውጇል፡፡” ይላል፡፡ የዚህን አዋጅ ጽንሰ

ሐሳብ በዝርዝር ስንመለከተው ብዙም ልዩነት ላይኖረን

ይችላል፡፡ ምክንያቱም በፀረ ሽብር አቋም ስለምንስማማ

ነው፡፡ ወደ አዋጁ ስንገባ ግን በርካታ ችግሮች ይታዩናል፡

፡ በተራ ወንጀል የሚታዩ ወንጀሎች በፀረ ሽብር አዋጅ

እንዲታዩ ተደርጓል፡፡ የፀረ ሽብሩ አዋጅ በራሱ ዜጐች

ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡ ህጋዊና ሠላማዊ የትግል ሥልትን

እንቅስቃሴ ለመፈረጅ የሚያስችል ክፍተቶች አሉት፡፡

“ማነሳሳት፣ የተገመተ እንደሆነ፣ የታሰበ እንደሆነ ወዘተ”

በሚል ሃረጐች የህግ አተረጓጐሙ የዜጐችን ህገመንግስታዊ

መብቶች ይጋፋሉ፡፡ መጋፋት ብቻ ሳይሆን ለተሳሳተ

ትርጉም አሰጣጥ የተንቦረቀቀ ነው፡፡ ሌሎች ሳይጠቀሱ

የማይታለፉት ነጥቦች አዋጁ መርማሪዎች በተጠርጣሪ

ታሳሪዎች ላይ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት እንዲፈጽሙ በር

መክፈቱ ነው፡፡ አንቀጽ 21 ናሙናዎችን የመስጠት ግዴታ

በሚለው ስር “ፖሊስ በሽብርተኝነት ወንጀል ጉዳይ

የተጠረጠረ ሰው የእጅ ጹሑፉን፣ የጣት አሻራውን፣ ፎቶ

ግራፉን፣ ደሙን፣ ምራቁንና ሌሎች በሰውነቱ የሚገኙ

ፈሳሽ ነገሮችን፣ ናሙናዎችን ለምርመራ እንዲሰጥ ሊያዝ

ይችላል፡፡ በተጨማሪም የህክምና ምርመራ እንዲደረግ

ሊያዝ ይችላል፡፡ ተጠርጣሪው ለምርመራው ፍቃደኛ

ካልሆነ ፖሊስ አስፈላጊውን የሆነ ተመጣጣኝ ሀይል

ተጠቅሞ ከተጠርጣሪው ናሙና ሊወሰድ ይችላል”

ይላል፡፡

የሚወሰደው የኃይል ርምጃው ተመጣጣኝ መሆን

አለመሆኑ መለኪያው ምንድነው? ናሙና ከመስጠት ውጪ

አንድ ተጠርጣሪ ቃሉን ለመስጠት ፍቃደኛ ባይሆንስ

ህገመንግስታዊ መብቱ አይደለምን? አንቀጽ 22 መረጃ

የመስጠት ግዴታ በሚለው አንቀጽ ውስጥ ያለውንም

የሰዎችን ተፈጥሮአዊ መብት በመግፈፍ ለፖሊስ ሥልጣን

የሚሰጥነው፡፡ አንቀጽ 14 መረጃ መሰብሰብ የሚለውንም

ስንመለከት “በሽብርተኝነት የተጠረጠረን ሰው ስልክ፣

ፋክስ፣ ሬዲዮ የኢንተርኔት የኤሌክትሮኒክስ የፖስታና

የመሳሰሉት ግንኙነቶችን ለመጥለፍ ወይም ለመከታተል

ጠለፋውን ለማስፈጸም ወደ ማንኛውም ቤት ውስጥ

በሚስጥር ለመግባት ወይም ይህንኑ ለመፈጸም የሚያስችሉ

መሣሪያዎችን ለማስቀመጥ ወይም ለማንሳት እንደሚችል”

ይዘረዝራል፡፡ አንድ ዜጋ ወንጀል እስካልሰራና ህጋዊ

እስከሆነ ድረስ ያለመረጃ ዓለም አቀፍና ህገመንግሥታዊ

መብት አለው፡፡ ሆኖም በዚህ አዋጅ መሠረት ግን ከሜዳ

ተነስቶ በሽብርተኝነት ጠርጥሬዋለሁ በሚል ሰብአዊና

ዲሞክራሲያዊ መብት እንዲጥስ አዋጁ በር ይከፍታል፡፡

የዚህ ጽሑፍ ዓላማ የአዋጁን ህጸጾች ለመፈለግ አይደለም፡

፡ አዋጁ አዋጅ ሆኖ ወጥቶአል፡፡ በህግ ፍልስፍና አንድ ህግ

ሲወጣ የህግ መስፈርት አሟልቷል የሚባለው አብዛኛውን

ህዝብ ሲያስደስት ነው፡፡ ይህን አዋጅ ስንመለከት ግን

አዋጁ ያስደሰተው ማንን ነው? ህግ አውጪውን ወይስ

ብዙኃኑን ህዝብ? ይህንን አዋጅ የፈራው ሰው ቁጥር ይበል

ወይስ ለደህንነቴ ዋስትና አገኘሁ ብሎ ያለ? ይበልጣል?

ጥያቄውን ለአንባቢው ትቼ ወደ አፈጻጸሙ ልግባ፡፡

“በሽብር” ተግባር የተጠረጠሩ ሰዎች ሲያዙ እየሰማን

ነው፡፡ እውነት በሽብር ተግባር ሲንቀሳቀሱ ተገኝተው

ነው? ወይስ በፖለቲካ አመለካከታቸው ነው? መንግስት

“በፖለቲካ አመለካከታቸው አይደለም፡፡ ህጋዊ ፓርቲዎችን

ሽፋን አድርገው ከአሸባሪ ቡድን ጋር ሲንቀሳቀሱ መረጃ

አግኝቼ ነው” ብሎናል፡፡ እንዴት እንመነው? ከዚህ ቀደም

በርካታ ነገሮች ተዋሽተናል፡፡ ዛሬስ እንዴት ርግጠኛ

ሆነን እንቀበል? እሺ እውነት ነው ብለን እንቀበል፡፡

ተጠርጣሪውን በቀላሉ መያዝ ሲቻል ግርግርና ሽብር

ማንሳት ለምን አስፈለገ? እስቲ ሰሞኑን ከታሰሩት ሰዎች

የተወሰኑትን እንመልከት፡፡ ባለን መረጃ ጥቂቶቹ ግርግር

ሳይፈጠር ህዝብ ሳይረበሽ የተያዙ አሉ፡፡ ይህ ሞያዊም

ጨዋነትም ነው፡፡ የኦፍዴን ም/ሊቀመንበርና የመድረክ

ሥራ አስፈፃሚ የተያዙት “በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ውስጥ

በማስተማር ላይ እንዳሉ ነው” ተብሎአል፡፡ ሥራቸውን

ጨርሰው ሲወጡ ቢያዙ አይቻልም ነበር? የመኢዴፓ ዋና

ፀሐፊ ዘመኑ ሞላ አያያዝ ለየት ይላል፡፡ “አንድ ሴት ደውላ

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ተማሪ ነኝ፤ በፓርቲዎች

ዙሪያ ጥናታዊ ጽሑፍ እያዘጋጀሁ ነኝ ተባበሩኝ” ብላ

ደወለች ይላሉ የትግል አጋሮቻቸው፡፡ አቶ ዘመኑም

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.10

ደሰሳ

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 23 2004 ዓ.ም.

በሐሳቡ “ተስማምተው ቢሮአቸው ቀጠሯት የተባለችውም

ወ/ሪት መጥታ አቶ ዘመኑ ቢሮ ትገባለች፡፡ ገብታ ከመቀመጧ

ስቪል የለበሱ ቀድመው በሩን በርግደው ቆሙ፡፡ መሣሪያ

የያዙና ዩኒፎርም የለበሱ ተከታትለው በመግባት ይዘዋቸው

ሄዱ፡፡ ባለጥናቷ በየት መንገድ እንደወጣች በምን ፍጥነት

አካባቢውን እንደለቀቀች አላወቅንም” በማለት ተናግረዋል፡፡

ጥሩ ዘዴ ነው፡፡

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ/አንድነት/

ብሔራዊ ም/ቤት አባል የሆኑት መ/ር ናትናኤል መኮንን አያያዝ

እንዴት ነበር፡፡ የመምህር ናትናኤል መኮንን የሥራ ባልደረቦች

እንደሚሉት “ከሚያስተምርበት ት/ቤት አብረን ወጥተን የከተማ

አውቶቢስ ተሳፍረን ከመገናኛ ወደ ፒያሳ በመጓዝ ላይ ነበረን፡፡

መንገዱን የፖሊስ መኪና ዘግቶ ቆሞአል፡፡ አውቶቢሱም ቆመ፡፡

ሁላችንም ምን ተፈጠረ ብለን ውጪ ውጪውን እንመለከታለን፡

፡ ናትናኤልም እንደኛው ነበር፡፡ የተሳፈርንበት አውቶቢስ የፊት

በር ተከፈተ፡፡ አንዱ ገብቶ አንተ አንተ ተነስ ብሎ ወሰደው፡፡

ተከትለን ጉዳዩ ለመጠየቅ ስንል በቁጣ እንድንሳፈር አደረጉን፡

፡ በአካባቢው ዙሪያ ፖሊስ ፈሷል፡፡ ይህ ሁሉ ግርግር ለምን

አስፈለገ? ከፈለጉት መኪና ሳይሳፈር ለምን አልያዙትም?

ሲወርድ ጠብቀው ለምን አይዙትም፡፡ በስልክ ቢጠሩትም

የሚሄድ ልጅ አልነበር? ይህ ሁሉ ግርግር ለምን አስፈለገ”?

በማለት ተናግረዋል፡፡ የጓደኞቹን አስተያየት እንተወውና

መምህር ናትናኤል በተፈጥሮው የሁከት የረብሻ ሰው ነውን?

ባለን መረጃ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በአንድነት ፓርቲ ..…

በሚል ርዕስ ጽሑፍ እንዲያቀርብ በተጋበዘበት ዕለት መምህር

ናትናኤል መኮንን በቦታው ተገኝቶ ውይይቱን ተከፍሎአል

ተብሎአል፡፡ በቀረበው ጽሑፍ እና በውይይቱ ርዕስ መሠረት

የራሱን ሐሳብ ማንሸራሸሩ ይነገራል፡፡ ታዲያ መ/ር ናትናኤል

የተያዘው ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ ህገመንግስታዊ መብቱን

ተጠቅሞ በሰጠው አስተያየት ወይስ ከሳሾቹ እንደሚሉት እኛ

የማናውቀው ድብቅ “የሽብር ጥቃት” ለማድረስ ሲንቀሳቀስ?

ሌላው እንዲህ ዓይነት አያያዝ ለምን አስፈለገ ብለን

ለመጠየቅ የምንገደደው የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አያያዝ ነው፡፡

እስክንድር አቋሙንም፣ እምነቱንም፣ ፍላጐቱንም በተደጋጋሚ

ግልጽ አድርጓል፡፡ ሥርዓቱ ለውጥ ያስፈልገዋል፡፡ ህዝብ

ለውጥ ይፈልጋል፡፡ ለውጡ ግን ህጋዊና ሠላማዊ በሆነ መንገድ

መከናወን አለበት የሚል አቋም ያለው ነው፡፡ በቅርቡም

ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ በስልክ ተጠርቶ ሄዶ ቃሉን ሰጥቶ

መመለሱ በተለያየ ሚዲያ መዘገቡ ይታወቃል፡፡ ዛሬ ለምን

በስልክ ተጠርቶ አልታሰረም? ምን የተለየ ነገር ተፈጠረ? ነው

ወይስ ጫወታው አይደምቅም? ባለቤቱ ወ/ሮ ሠርካለም ፋሲል

እንደተናገረችው “የምንኖረው ቤታችንን አከራይተን በአነስተኛ

ኪራይ ሌላ ቤት ተከራይተን ነው፡፡ ዕለቱ የቤት ኪራይ

የሚቀበልበት ዕለት ነው፡፡ የቤቱን ኪራይ ተቀብሎ ልጁን ከት/

ቤት ይዞ ሲመለስ በአስገራሚ ሁኔታ ከበው ያዙት” በማለት

ተናግራለች፡፡ እስክንድር ሲያዝ የነበረውን ሁኔታም በወቅቱ

በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞች ሲናገሩ “አያያዙ የተቀነባበረ

ድራማ ይመስላል” ይላሉ፡፡ እንደ አይን ምስክሮቹ አባባል

“ከበው አስቆሙት፣ ልጁን ከነጠሉ በኋላ ፖሊሶች ከበቡት፡

፡ ልጁ መሬት ላይ ወድቆ ይንፈራፈር ነበር፡፡ እየተንፈራጋጠ

በምሬት ያለቅሳል፡፡ ማንም ሰው ተጠግቶ ልጁን ሊያነሳ ወይም

ጉዳዩንም ለመጠየቅ የደፈረ የለም፡፡ በርቀት ተሰብስቦ ማየት

ብቻ ነበር፡፡ በርካታ ፖሊሶች ከበውታል፡፡ ስቪል የለበሱ አሉ፡

፡ መሣሪያ በየአቅጣጫው ተወድሮአል፡፡ እጁን በሰንሠለት

ያስሩታል፡፡ ቬዲዮ ቀራጮችና ካሜራ የሚያነሱ እየተሯሯጡ

ያነሳሉ፡፡ በግምት አምስትና ስድስት ዓመት የሚሞላው

የእስክንድር ልጅ ተቀምጦ ማልቀሱ እንደማያዋጣው በማወቁ

ተነስቶ አባቱን ከበው እጁን በሰንሰለት የሚያስሩትን እየዘለለ

በርግጫ በካልቾ ይማታ ጀመር፡፡ የሚመለከተው ሰው ግማሹ

ያለቅሳል፡፡ ግማሹ ይስቃል፡፡ ግማሹ ወንድ ወንድ እያሉ

ያላግጣሉ፡፡ ፖሊሶችም እንደማይጐዳቸው በማወቃቸው

ትኩረትም አልሰጡትም፡፡ ልጁም አባቱን የከበቡትን ፖሊሶች

እየዞረ በካልቾ መማታቱን ትቶ ጐትቶ በመወርወር አባቱን

ለማስለቀቅ ይታገላል፡፡ በመጨረሻም እናቱ ደረሰች” በማለት

ይገልጹታል፡፡ ስትደርሺ ልጁን በምን ሁኔታ አገኘሺው በማለት

ስትጠየቅ ወ/ሮ ሠርካለም “አሁን ሳስበው ያስቀኛል፡፡ ልክ እኔን

እንዳየኝ አንዱን ፖሊስ እያሳየኝ ያዢልኝ ያዢልኝ እያለ በካልቾ

ሲመታው ተመልክቼአለሁ፡፡ ያ ፖሊስ አባቱን ምን ሲያደርገው

እንዳየ አላውቅም፡፡ አልቅሶ አልቅሶ ስለወጣለት አባቱን

ያንገላቱትን ደብድቦ እልኩን ለመወጣት ሲወራጭ አይቼአለሁ፡

፡”ትላለች ይህ ልጅ በአሁኑ ጊዜ ወሬው ሁሉ ስለ ፖሊስ ነው፡፡

ፖሊስ እንዲህ አድርጐ እንዲህ ብሎ ይላል፡፡ በጫወታ መካከል

ሰው ሲስቅ ኸረ ዝም በሉ ፖሊስ እንዳይመጣባችሁ ይላል”

በማለት ተናግራለች፡፡

ይህ ህፃን የተወለደው እስር ቤት ነው፡፡ ከምርጫ 97

በኋላ በተፈጠረው ሁኔታ እናትና አባቱ ታስረው ነበር፡፡ እናቱ

ስትታሰር የአንድ ወር ርጉዝ ነበረች፡፡ እዚያው ተገላግላ ወጣች፡

፡ ዛሬ አባቱ በድጋሚ ሲታሰር ቀደም ሲል የዓይን ምስክሮች

እንደሚሉት ድራማውን ተጫወተው፡፡ ምን ይታወቃል፡፡

ዛሬ እንደቀልድ የተዋጣለት ድራማ ነው እያሉ የሚቀለድበት

ገጠመኝ ወደፊት በአንድ ወቅት አንድ አርቲስት በጥሩ ቅንብር

ምርጥ ፊልም ተሰርቶ ልናየው እንችላለን፡፡ ወደ መነሻ ሐሳባችን

ስንመለስ እስክንድርን በስልክ ጠርቶ ማሰር ሲቻል ይህ ሁሉ

ግርግር ለምን አስፈለገ? እስረኞቹስ ከታሠሩ በኋላ ምን ነበር፡

፡ በታሰሩ በማግስቱ ፍ/ቤቱ ይቀርባሉ ተብሎ ጋዜጠኞች

ቤተሰባቸውና የተወሰኑ የትግል አጋሮቻቸው ተገኝተው ነበር፡፡

በሥፍራው የተገኘው ሁሉ ህጋዊና ሠላማዊ በሆነ ሁኔታ ቆሟል፡

፡ ተጠርጣሪ ተከሳሾችን አጅበው የመጡ ፖሊሶች የሚፈጥሩት

ግርግር ለምን አስፈለገ ያሰኛል፡፡ በሥፍራው የተገኘው ሠላማዊ

ዜጋ ጠላት አይደለም፡፡ የሚመናጨቅበት የሚንጓጠጥበት

የሚባረርበት ምክንያት ምን ድነው? ሁከት ለመፍጠር ወይም

ክህግና ሥርዓት ውጪ የሚሆን ካለ በአግባቡ በህግ እንዲጠየቅ

ማድረግ ተገቢ መሆኑ ይታመናል፡፡ ከዚያ ውጪ ሥነ ምግባር

የጐደለው ነገር ማሳየት ከአንድ ፖሊስ የሚጠበቅ አይደለም፡፡

በተለይ አንድ የሲቪል ልብስ የለበሰ /ምናልባትም ፖሊስ የሆነ

ፍ/ቤት በተገኙ ዜጐች ላይ ይፈጽም? የነበረው የትንኮሳ ሥራና

ሥነ ምግባር የጐደለው ፀያፍ ተግባር ርምት የሚያስፈልገው

ነው፡፡ ይህ የፖሊስ ሞያም የፖሊስ ሥነ ምግባርም አይደለም፡፡

የግለሰቡ ድርጊትም ፖሊስን እንደማይወክል ሊታመን ይገባል፡፡

በዕለቱ የቀረቡት ተከሳሾች አምስት ናቸው፡፡ አምስቱ ተከሳሾች

በተናጥል እየመጡ ችሎት ቀርበዋል፡፡

በቅድሚያ የቀረበው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ነው፡፡

እስክንድር ችሎት ሲቀርብ ቤተሰብም ጋዜጠኛውም እንዳይገባ

ፖሊስ ከልክሎአል፡፡ ችሎት ቀርቦ እንደወጣ የፍኖት ነጸነት

ጋዜጠኛ፣ የአሜሪካን ሬዲዮ ጣቢያ /VOA/ እና የሪፖርተር

ጋዜጣ ዘጋቢዎች አስፈቅደው ዳኛው ዘንድ ቀርበው ነበር፡፡

ጋዜጠኛ መሆናቸውን ገልጸው እንዳይዘግቡ መከልከላቸውን

አመለከቱ፡፡ ዳኛውም የጋዜጠኞችን መታወቂያ ተመልክተው

ጋዜጠኛ መሆናቸውን ካረጋገጡ በኃላ፤ መዘገብ መብታቸው

መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ማነው የከለከላችሁ? ሲሉም ጠይቀዋል፡

፡ ፖሊስ እንደሆነ ሲነገራቸው ዳኛውም ፍ/ቤቱ በግልጽ ችሎት

የዳኝነት ተግባሩን የሚያከናውን በመሆኑ ሊከለከል አይችልም፡

፡ ፖሊስም መከልከል አይችልም፡፡ የምትፈልጉትን ጉዳይ

ገብታችሁ መዘገብ ትችላላችሁ ብለው አዘዋል፡፡ ይህ እንደ

በጐ ነገር የሚታይ ነው፡፡ የአገሪቱ ህገመንግሥትም የሚያዘው

ይህንኑ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ የአቶ ዘመኑ ሞላን፣ የአቶ አሳምነው

ብርሃኑን፣ የአቶ ናትናኤል መኮንንና የአቶ አንዱዓለም አራጌን

የችሎት ውሎ ለመከታተል ተችሎአል፡፡ እንደሚታወቀው

3

ህዝብም ሚዛናዊ መረጃ የማግኘት መብት አለውና የነበረውን

የችሎት ውሎ እውነተኛውን መረጃ ማግኘት ችሎአል፡፡

በአብዛኛዎቹ ተከሳሾች ለሚቀርብላቸው ጥያቄ የሚሰጡት

መልስ ተመሳሳይ ነው፡፡ “የተከሰሱበትን ጉዳይ ያውቃሉ?”

ተብሎ ከዳኛው ለሚቀርብላቸው ጥያቄ ፖሊስ “በሽብር ተግባር

ተጠርጥረህ ነው ብሎናል ግን ግልጽ አልሆነልኝም” የሚል

ነው፡፡ በመቀጠልም ፍ/ቤቱ “ፖሊስ አስረዳው” የሚል ትዕዛዝ

ይሰጣል፡፡ ጉዳዩን የያዘው መርማሪ ፖሊስም “ውጪ ከሚገኝ

ሽብርተኛ ድርጅት ጋር በመቀናጀት በቡድን ተደራጅተው

በያዝነው ዓመት ሽብር ለመፍጠር ሁከት ለማስነሳት ሲንቀሳቀሱ

በቂ ማስረጃ በመገኘቱ ነው” የሚል ነው፡፡ ቀጥሎም ከዳኛው

የሚቀርበው ጥያቄ “ፖሊስ የ28 ቀን የምርመራ ጊዜ ጠይቆብሐል

ምን አስተያየት አለህ” የሚል ነው፡፡ ታሳሪዎቹም ሲመልሱ

“ፖሊስ በቂ ማስረጃ አለኝ ካለ ለምን አሁኑኑ ክሱን ለዐቃቢ ህግ

ሰጥቶ ክሱ አይከፈትብንም፤ ለምን የምርመራ ጊዜ ያስፈልገዋል”?

የሚል እንደምታ ያለው ነው፡፡ ፖሊስም ሲመልስ “ሊፈጸም

የነበረው በቡድን በመሆኑና የኢሜልና የስልክ ልውውጦችም

ስለነበሩ ለማስተርጐም ጊዜ ያስፈልገናል” የሚል ነው፡፡ ፍ/

ቤቱም የተጠየቀውን የ28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ሰጥቶአል፡፡

በመጨረሻ ላይ የቀረበው ተጠርጣሪ እስረኛ አቶ

አንዱዓለም አራጌ ነው፡፡ ከላይ እንደገለጹኩት ለአቶ አንዱዓለም

የቀረበው ጥያቄ እንደ መጀመሪያዎቹ “ተጠርጥረው የተያዙበትን

ያውቃሉ” የሚል ነበር፡፡ “ፖሊስ በሽብርተኝነት ተጠርጥረህ

ነው እያሉ ነው ጉዳዩን አላውቅም” በማለት ሲናገሩ ፖሊስም

ለሌሎቹ በሰጠው መልስ መሠረት አስረድቷል፡፡ በመቀጠል

ፍ/ቤቱ አቶ አንዱዓለምን የጠየቀው ጥያቄ ፖሊስ የ28 ቀን

የምርመራ ጊዜ ጠይቆብዎታል አስተያየት አልዎት? የሚል

ነበር፡፡ አቶ አንዱዓለምም ሲመልሱ “ለመጀመሪያና ለመጨረሻ

ጊዜ የምናገረው ነገር አለኝ፡፡ እየተወሰደ ያለው በአገሪቱ ውስጥ

ያለውን ሠላማዊ የፖለቲካ ትግል ለማፈን የሚወሰድ ርምጃ

ነው፡፡ እኔም በዚሁ ስለባ ሆኜአለሁ፡፡ ከእንግዲህ ወዲያ ፍ/

ቤት የፈለገውን ርምጃ ሊወሰድ ይችላል፡፡ ሞትንም ጨምሮ፡

፡ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ” የሚል ነበር፡፡ በመቀጠልም ዳኛው

“በሚናገሩት ርምጃ መውሰድ ይቻላል፡፡ ሆኖም ግን ፍ/ቤቱ

የሚጠይቅዎት የእርስዎንም መብት ለማስከበር ነው፡፡ ፍ/ቤቱን

ሊያከብሩ ይገባል፡፡ ፍ/ቤቱ በነፃ የዳኝነት ሥርዓት ሥራውን

የሚያከናውን ነው” ብለዋል፡፡ በመጨረሻ አቶ አንዱዓለም

“እኔ እንደዚያ ብዬ አላስብም” ሲሉ መልሰዋል፡፡ ዳኛውም

የተጠየቀውን የ28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ በመስጠት ለጥቅምት 2 ቀን

2004 ዓ.ም በ8 ሰዓት ተቀጥሮ የዕለቱ የችሎት ውሎ ተጠናቋል፡

እዚህ ላይ ሳይጠቀስ የማይታለፈው ግን በአቶ አንዱዓለም

አራጌ ላይ፣ በፍ/ቤት ግቢ ውስጥ ይሠራ የነበረው ሁኔታ ነው፡

፡ አቶ አንዱዓለምን እንደማንኛውም እስረኛ አምጥተው ፍ/ቤቱ

ችሎት አደረሱት፡፡ ቤተሰብ የትግል አጋሮች ጋዜጠኞች ችሎት

መቅረቡን እየተጠባበቁ ናቸው፡፡ ዳኛው ይጠብቃሉ፡፡

አቶ አንዱዓለምን ከመኪና አውርደው ወደ ችሎት ከማቅረብ

ይልቅ ያመጣው መኪና ይዞት ተነስቶ ከግቢው ወጣ፡፡ ቤተሰብና

ጓደኞቹ ችሎት ሳያቀርቡት ይዘውት ተመለሱ ብለው መደናገጥን

ፈጠረ፡፡ ይዘውት ከተመለሱ በቃ ወደቤታችን እንሂድ፤ የለም

ሊያመጡት ስለሚችሉ አንሄድም የሚሉ ሐሳቦች ይሰሙ ነበር፡

፡ ዳኛው ደወል ደውለው ይቀርባል የተባለው እስረኛ የታለ?

እስከማለት ደርሰዋል፡፡ በመጨረሻም አቶ አንዱዓለም የያዘችው

መኪና ተመልሳ መጣች፡፡ አንዱዓለም በሰላም ችሎት ቀርበው

ተመልሰዋል፡፡ ፍ/ቤት ግቢ አድርሶ መውጣት መግባት ግቢው

ውስጥ ግርግር መፍጠር ለምን አስፈለገ? የህግ ማስከበሩ አካል

ይሆን? ቤተሰብና የትግል አጋሮች ትግስት ትህትና መረጋጋት

አስፈላጊነቱ የሚደነቅ ነው፡፡ ህግ ማክበር ለህግ ተገዢ መሆን

ምን ጊዜም ጥሩ ነው፡፡

www.andinet.org.et

4

ፍኖተ -ነፃነት ጋዜጣ ሐምሌ 2ዐዐ3 ዓ.ም

ተመሠረተ፡፡ ፍኖተ ነፃነት በአንድነት ለዴሞክራሲና

ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ሥር የሚታተም

በፖለቲካዊ፣ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ፣ በወቅታዊ ጉዳዮችና

በመዝናኛ ላይ የሚያተኩር የፓርቲው ጋዜጣ ነው፡፡

ጋዜጣችን እንደ ፓርቲ ልሳን ብቻ

ሳይሆን እንደ አንድ ሚዛናዊ የግል

ጋዜጣ ሆኖ ማገልገል ይፈልጋል

የማንኛዉም ሰዉ ሀሳብና አመለካከት

የሚስተናገድበትና የሚንሸራሸርበት

እንዲሆን እንሻለን ሰፊና ረዝም የሚዲያ

ሽፋን ያለዉ ኢህአዴግም በዚህ ሚዲያ

አቋሙንና ፖሊሲዉን ለማቅረብ ቢፈልግ

ክፍት ነዉ

ዋና አዘጋጅ፡-

አንዳርጌ መሥፍን

አድራሻ፡-

የካ ክ/ከተማ ወረዳ 12

የቤ.ቁ አዲስ

አዘጋጆች፡-

ብዙአየሁ ወንድሙ

ብስራት ወ/ሚካኤል

አምደኞች፡- ዶ/ር ኃይሉ አርዓያ

ኢ/ር ዘለቀ ረዲ

አንዱዓለም አራጌ

ግርማ ሠይፉ

ዳምጠው አለማየሁ

ተስፋዬ ደጉ

በላይ ፍቃደ

ወንድሙ ኢብሳ

ኮምፒውተር ጽሑፍ፡-

የሺ ሃብቴ

ብርቱካን መንገሻ

አከፋፋይ፡-

ነብዩ ሞገስ

አሣታሚው፡-

አንድነት ለዴሞክሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት)

አድራሻ፡- አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 07 የቤ.ቁ አዲስ

አታሚ፡- ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት

አራዳ ክ/ከተማ ቀበሌ 07 የቤ.ቁ 984

የዝግጅት ክፍሉ

ስልክ +251 922 11 17 62

+251 913 05 69 42

+251 118-44 08 40

ፖ.ሳ.ቁ፡ 4222

ኢሜይል፡- udjparty@gmail.com

andinet@andinet.org

ፋክስ ቁጥር፡- +251-111226288

www.andinet.org.et

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 23 2004 ዓ.ም.

ርዕሰ አንቀፅ

ያለማቋረጥ እያደገ ያለው የዋጋ ንረት

መልህቅ ይበጅለት

ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ የሃገራችን የገበያ ሁኔታ ይበልጥ እየተቃወሰና ከቀን ወደ ቀን እየታመሰ

ቀጥሏል፡፡ የሕብረተሰቡ የኑሮ ሁኔታም ከድጡ ወደ ማጡ እየሆነበት መሠረታዊ የሆኑ የዕለት

ፍላጎቶችን ማሟላት እየቸገረው ነው፡፡

በ1997 ዓ.ም 6.8% የነበረው የዋጋ ንረት በተከታዮቹ ሁለት አመታት 12.3 በመቶ እና 15. 8

በመቶ ደረሰ፡፡ ይህም ማለት የንረቱ እድገት መጠን በሁለት ዓመት ውስጥ 132 በመቶ ሆነ ማለት

ነው፡፡ ከ1999 ዓ.ም በኋላ ያሉት አራት ዓመታት አጠቃላይ የዋጋ ንረት መጠንን ስንመለከት

ደግሞ 1999 ላይ 15.8 በመቶ የነበረው በ2003 ዓ.ም 57 በመቶ ደርሷል፡፡ ይህም አጠቃላይ

የአራት ዓመት የዋጋ ንረት እድገቱን 36ዐ.7 ፕርሰንት መድረሱን ያመላክታል፡፡

ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ ያሉትን ስድስት ዓመታት አጠቃላይ የዋጋ ንረት እድገት ስንመለከት

ደግሞ 714% ይሆናል፡፡ ይህም ማለት የገንዘብ የመግዛት አቅም ባለፉት ስድስት ዓመታት በ714

ፕርሰንት ወድቋል ማለት ነው፡፡

በአንፃሩ አማካይ ዓመታዊ ገቢ በ1997 ዓ.ም 165 ዶላር የነበረ ሲሆን አሁን 35ዐ ዶላር

እንደደረሰ የአይኤም ኤፍ ሪፖርት ያመለክታል፡፡ ባለፉት ስድስት ዓመታት አማካይ አመታዊ ገቢ

በ112 በመቶ አድጓል ማለት ነው፡፡

ከላይ ከተመለከቱት መረጃዎች የምንረዳው በስድስት ዓመቱ የገቢ እድገትና የዋጋ ንረት

እድገት መካከል የ602 በመቶ ልዩነት እንዳለ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ

በ1999 ዓ.ም ይኖር የነበረውን ኑሮ ዛሬ ለመኖር እንዲችል የዋጋ ንረቱ ከ14.4 በመቶ መብለጥ

አልነበረበትም ወይም አማካይ አመታዊ ገቢ 1171.5 ዶላር መድረስ ነበረበት፡፡

በሃብታሙና በድሃው ዜጋ መካከል ያለው የሃብት ክፍተት እየሰፋ መሄድ እንዳለ ሆኖ

የኢትዮጵያውያን የድህነት ደረጃ ባለፉት ስድስት ዓመታት በ324.7 በመቶ እንዳደገ መረዳት

ይቻላል፡፡ ይህንን አሰቃቂ ሁኔታ ይበልጥ አስፈሪ የሚያደርገው ገዢው ፓርቲ ችግሩን ለማስወገድ

ቀርቶ ባለበት እንኳን ለማስቆም አለመቻሉ ነው፡፡ እየወሰዳቸው ያሉት ርምጃዎችም አስተውሎት

የጎደላቸው በመሆናቸው ችግሩን የበለጠ ሲያባብሱት እንጂ ሲቀንሱት አልታዩም፡፡

የኢኮኖሚ ኃይሎች (ፍላጎትና አቅርቦት) ገበያውን መምራት ሲሳናቸው መንግሥት ጣልቃ

ገብቶ ማረጋጋት እንዳለበት እምነታችን ነው፡፡ ይህ ሲባል ግን መንግሥት የገበያ ኃይሎችን

መቆጣጠር ወይም መተካት አለበት ማለት አይደለም፡፡ በትክክል መሥራት እንዲችሉ የሚረዱ

የፊስካልና የገንዘብ ፖሊሲዎችን ተግባራዊ በማድረግ የኢኮኖሚውን አቅም ያጠናክራል እንጂ፡፡

በእርግጥ ገዢው ፓርቲ ገበያውን ለማረጋጋት የተለያዩ የፖሊሲና የቀጥተኛ ጣልቃ ገብነት

ርምጃዎችን ወስዷል፡፡ እዚህ ላይ የሚነሳው ዋናው ጥያቄ ታዲያ ለምን የዋጋ ንረቱ የበለጠ

እየተባባሰ ሄዴ? የሚለው ነው፡፡

የኢህአዴግ መሠረታዊ ችግር የችግሩን መነሻ ለይቶ ለማወቅ አለመቻሉ ላይ ነው፡፡ ኢህአዴግ

የዋጋ ንረቱ በተከታታይ እየተመዘገበ ያለው የኢኮኖሚ እድገት የፈጠረው ነው ብሎ ያምናል፡፡

እ.ኤ.አ በ1929 በአሜሪካ የተከሰተው የኢኮኖሚ ዝቅጠትን ተከትሎ የተስፋፋው

የኬንዚያውያን (Keynesian) የምጣኔ ኃብት ባለሙያዎች አስተሳሰብ በምጣኔ ኃብት እድገትና

በዋጋ ንረት መካከል ቀጥተኛ ግንኙነት ስለአለ መንግሥት በከፍተኛ ኢንቨስትመንትና የሥራ

ዕድል ፈጠራ ኢኮኖሚውን ሲያሳድግ የሕዝብ ገቢም አብሮ ያድጋል የሚል ነው፡፡ በመሆኑም

የፍጆታ ወጪ መጠን ይጨምራል፡፡ ይህም የሸቀጦችና የአገልግሎት ዋጋ እንዲንር ያደርጋል የሚል

በመሆኑም ኢኮኖሚው ባደገ ቁጥር የዋጋ ንረቱም ይቀጥላል ማለት ነበር፡፡

ይህ አስተሣሰብ በወቅቱ ትክክለኛ የነበረ ቢሆን በ1970ዎቹ የታየው የስራ አጥነትና የዋጋ

ንረት “Stagflation” በተመሣሣይ ጊዜ በመከሰቱ (Stagflation) ውድቅ እንዲሆን አድርጎታል፡፡

በሃገራችን በአሁኑ ሠዓት እየታየ ያለው ክስተትም ከ1970ዎቹ የምዕራባውያን የኢኮኖሚ ቀውስ

ጋር ተመሣሣይነት አለው፡፡

የዋጋ ንረቱ ሥራ አጥነቱ በእጅጉ እየተባባሱ ናቸው፡፡ ከገቢ አንፃር ሲታይም ከላይ

እንደተገለፀው ባለፉት ስድስት ዓመታት ውስጥ የዋጋ ንረት በ714 በመቶ ሲያድግ ዓመታዊ ገቢ

በ112 ፕርሰንት ብቻ ነው ያደገው፡፡ በመሆኑም በሃገራችን ያለው የዋጋ ንረት የኢኮኖሚው እድገት

የወለደው ነው ሊባል ፈፅሞ አይችልም፡፡

በአንድነት ፓርቲ ዕምነት እይታ የዋጋ ንረቱ መሠረታዊ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፡-

1. መንግሥት ከፍተኛ ብዛት ያላቸው የገንዘብ ኖቶችን አሣትሞ በኢኮኖሚው ውስጥ

መርጨቱ፣

2. የመንግሥት ወጪ መጠን በከፍተኛ ደረጃ እያደገ መምጣቱ፤ ይህም በሃገር ውስጥ

ምርት አቅርቦት እድገት አለመደገፉ፣

3. በውጭ ምርቶች ላይ መሠረቱን የጣለው አቅርቦትና የውጭ አገር ምርቶች ዋጋ

መናሩ፣

4. የብር ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየወደቀ መምጣትና የውጭ ምርት አቅርቦትና ፍላጐት

አለመጣጣም፣

5. የመንግሥት የነዳጅ ድጎማ መነሳት፣

6. የመሠረታዊ ዕቃዎች ፍላጎትና አቅርቦት ከፍተኛ ሁኔታ አለመጣጣም፣

7. መንግሥት የግሉን ዘርፍ ተክቶ አቅርቦትና ሥርጭትን ለመቆጣጠር የሚያደርገው

ጥረት፣

8. በግል ባንኮች ላይ ተጥሎ የነበረው የብድር ጣሪያ የአገር ውስጥ ምርትንና ከውጭ

የሚገቡ ሸቀጦችን አቅርቦት መገደቡ፣

9. በግል ባንኮች ላይ የተጣለው የግምጃ ቤት ሰነድ ግዢ ግዴታ የሃገር ውስጥ ምርትንና

ከውጭ የሚገቡ ሸቀጦች አቅርቦትን የሚገድብ መሆኑ የሚፈጥረው የአቅርቦት እጥረት፣

10. በመሬት ፖሊሲው ምክንያት የመሬትና የገበሬው ምርታማነት መቀነስ፡፡ ይህንንም

ተከትሎ የሃገር ውስጥ ምርት አቅርቦትና ፍላጎት አለመጣጣም፣

11. የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ውስንነትና የዜጎች ከክልል ወደ ክልል ተንቀሳቅሶ የመሥራት

መብት መገደብን ተከትሎ የምርትና የሰው ኃብት እንቅስቃሴ መወሰኑ፡፡ በዚህም ምክንያት የሰው

ኃብትና ምትርት ከፍተኛ አቅርቦት ካለበት አካባቢ ወደ ከፍተኛ ፍላጎት ያለበት ቦታ ለመንቀሳቀስ

አለመቻሉ በሃገራችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ በመምጣት ላይ ላለው የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነት

ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው፡፡

እነዚህን ችግሮች በአንክሮ ስንመለከት የሁሉም ምክንያቶች መነሻ የተዛቡ የመንግሥት

ፖሊሲዎችና አስተውሎት የጎደለው የመንግሥት ጣልቃ ገብነት እንደሆነ እንረዳለን፡፡

በመሆኑም መንግሥት ይህን ውስብስብ ችግር ለመፍታት ቁርጠኝነቱ ካለው በመጀመሪያ

ደረጃ የልማት እስትራቴጂውና ፖሊሲዎቹ ላይ መሠረታዊ ለውጥ ሊያደርግና ከግብታዊ ጣልቃ

ገብነት ሊቆጠብ ይገባል፡፡ ይህን የማያደርግ ከሆነ ግን እየተባባሰ ያለው የኑሮ ውድነትና የዋጋ ንረት

ማቆሚያ የሌለው እንደሚሆንና ካሁኑ የባሰ የተወሳሰበ ሰብአዊና ማሕበራዊ ቀውስ ሊያስከትል

እንደሚችል ልብ ሊል ይገባል፡፡

ነፃ አስተያት

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.10

“ማነው ተው

የሚለኝ?!”

ይድነቃቸው ዐይኔ

አብዛኛዎቻችሁ የዚህን ጽሁፍ ርዕስ ስታዩ የብርሃኑ ተዘራን ማነው

ተው የሚለኝ ማነው? የሚለውን ዘፈን ታስታውሱታላችሁ

ብዬ እገምታለሁ፡፡ ወይም ደግሞ በሰፈራችሁ፣ በአካባቢያችሁ

እና በመንደራችሁ ስፓርታዊ እንቅስቃሴን (በተለይም ክብደት

ማንሳትን) ለፀብ እንጂ ለፀባይ የማይሰሩ በትዕቢት የተሞሉ

ጐረምሶች እና ወጣቶች ማነው ተው የሚለኝ አፍንጫውን

እለዋለሁ፤ የሚለውን አባባል በተደጋጋሚ ስለሚጠቀሙት እነሱ

ትዝ ….. ብለዋችሁ ይሆናል፡፡ እኔ ግን በጽሁፌ ላስታውሳችሁ

የምፈልገው፤ ከሁሉም በላይ አባባሉን በመጠቀም ላይ

ስለሚገኘው እና በተግባር ስለሚያውለው እንዲሁም በዚህ

ድርጊቱ አቻ ስላልተገኘለት አካል ነው፡፡

የመቶ በመቶ የምርጫ ድል (ዘጠና ዘጠኝ ነጥብ ምናምን

የሚለውን ቁጥር ያልተጠቀምኩት አውቄ ነው፡፡ ምክንያቱም ይህ

ገለፃ፤ ምርጫው ሰማንያ በመቶ የማሸነፍ ያህል ያስመስለዋል፡፡

ሥነልቡናዊ ጥቅም አላት፡፡) ከኔ በላይ ለአገሪቱ ተቆርቆሪ ወገን

የለም ብሎ የሚያስብ ገዢ ፓርቲ እና ይህን ሀሳብ የመጨረሻ

እውነት አድርጐ የሚቆጥር የካድሬ ጐርፍ፣ የማያባራ የምሁራን

እና የዜጐች ስደት (ያውም በሬድዮ ጭምር በሚለፍፉ የውጭ አገር

የሥራ ዕድል ማስታወቂያ በሚቀርብበት ሁኔታ ላይ እስክንደርስ፡

፡)፣ በዘፈቀደ የተቀመጠ ግትር ፖሊሲ መቃብራቸውን መማስ፣

የታዋቂ ፖለቲከኞች እና የጋዜጠኞች እስር እና ወከባ እንዲሁም

ተመሳሳይ ሕዝባዊ በደሎች፤ በተጨማሪም የመልካም አስተዳደር

እጦት እና የሙስና መንሰራፋት የተባባሱት እና የተበራከቱት

በሌላ በማንም አይደለም፡፡ ማነው ተው የሚለኝ? ሊጠይቀኝ

የሚችል ከኔ ጋር የተጠጋጋ ኃይል ያለው አካል ከወዴት አለ?

እኔን የሚመጥን ጉልበተኛ ማን አለ? ከኔ በላይ አዋቂ፣ ከኔ በላይ

ብልህ፣ ከኔ በላይ አስተዳዳሪ ለዘበት በሚል መንግስት እንጂ፡፡

ኢሕአዴግ ከጊዜ ወደ ጊዜ ሥር እየሰደደ በመጣው ኃይሉ እና

ባለው የፖለቲካ ሥልጣን ልዕልና በመጠቀም፤ በእያንዳንዱ

እርምጃ እና ድርጊት ያለመጠየቅን ፀጋ ተጐናጽፏል፡፡ ምርጫው

ሙሉ ለሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ማሸነፉን እንደ በጐ

ዴሞክራሲያዊ አካሄድ ማየት፣ የፈለጉትን ሕግ በፓርላማ ማፅደቅ

እና በዚህ ሕግ ሌሎችን ማሸማቀቅ እንዲሁም ማስጨነቅ፣

የሌሎችን ሀሳብ እንደ መናኛ ቆጥሮ የራስን ሀሳብ ብቻ መናገር

እና ማስነገር (የሀገሪቱን ትላልቅ እና ኃይል ያላቸው የመገናኛ

ብዙሀንን ለራስ ብቻ በማዋል የሌሎችን ሀሳብ በመገደብ፡፡)፣

ሌሎችን ባለድርሻ አካላት ሳያማክሩ አገሪቷን አደጋ ላይ ሊጥሉ

የሚችሉ ፖለቲካዊ እና ሥነ ምጣኔያዊ ውሳኔዎችን ማስተላለፍ፤

ተው የሚለኝ ካለ፤ ይሞክረኝ! የሚል ሀላፊነት የጐደለው

መልዕክት ማስተላለፍ እንጂ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል?

በየወንዙ ዳር መቀደስ

የተኛን ሴጣን ለመቀስቀስ

ይህ አባባል በሁለት መስመር ቃላት ብዙ ማለት ከሚችሉ

ኢትዮጵያውያት ሴቶች ከተናገሯቸው አባባሎች አንዱ እንደሆነ

አምናለሁ፡፡ የእምነት ሰው ነኝ፣ የእግዚአብሄርን ስም ከኔ ወዲያ

ማን ያውቃል? ከኔ በላይስ ክርስቲያን አለ? እንደው ከኔ ወዲያ

ቀዳሽ በአገሪቱ ይኖር ይሆን? ብሎ በእምነት ሳይሆን በትዕቢት

አለፍ ሲልም በሞኝነት የተሞላ ሰው የሚያደርገው አድራጐትን

ይገልፃል አባባሉ የዚህ ሁሉ ቅዳሴ እና የእግዚአብሄርን

ስም መጥራት ሰይጣንን ከመቀስቀስ አልፎ አምላክ ዘንድ

እንደማይደርስ ይገልፃል አባባሉ፡፡

ይህንን አባባል ከተናገሩት ቀደምት ሊቃውንት ሁለቱን መስመር

ተውሼ የሰሞኑን የመንግስታችንን ድርጊት ልመዝን፡፡

የፀረ- ሽብርተኝነት ሕግ አዋጁ እና ዘመቻው ሁሉንም ባለድርሻ

አካላት ባግባብ እና ባሳተፈ መልኩ እንዳልተደረገ ለመናገር

ኢትዮጵያዊ መሆን በቂ ነው፡፡ ከዛ ባለፈ የፓርላማን ውሎ

እና ፓርላማው ነገሮችን በምን ፍጥነት አይቶ በምን ፍጥነት

እንደሚያፀድቅ በቴሌቪዥን መስኮት ማየት ይበቃል፡፡

ፓርቲው የሚያቀርበው ሀሳብ በሙሉ የኔ ሀሳብ ነው፡፡ ፓርቲዬ

የሚያቀርበው ሀሳብ በፍፁም እኔን አደጋ ላይ አይጥለኝም፤ በሚል

የራስን ሀሳብ ገሎ በሌሎች ተጨፍልቆ የማሰብ አዙሪት ውስጥ

በገቡ ሰዎች፤ ስንት ማህበራዊ እና ሀገራዊ አደጋን የሚያስከትሉ

ፖሊሲዎች እና አዋጆች ጸድቀዋል?

በኑሮ ውድነት፣ በአንድ ፓርቲ እና በአንድ ሰው የበላይነት

በዴሞክራሲ እና በብልሹ አስተዳደር እንዲሁም ቀጣይነት

በሌላቸው እና ፖለቲካዊ ዓላማቸውን እስካልሳቱ ብቻ በሚጸድቁ

ፖሊሲዎች የተሰላቸው ህዝብ፣ አነሰም በዛም የሚያውቃቸውን

እና የሚያከብራቸውን ከመንግስት በተቃራኒው የቆሙትን

ፓለቲከኞች እና ጋዜጠኞች በሽብርተኝት ታርጋ ከለላ ወደ

እስር ቤት መወርወር፤ ግለሰቦቹን እና ደጋፊዎቻቸውን ብሎም

ጋዜጣችን “ፍኖተ-ነፃነት” ብለናታል፡፡ “ፍኖት” ማለት መንገድ ማለት ሲሆን ከነፃነት ጋር

ሲጣመር “የነፃነት መንገድ” ማለት ነው!! ወደ 7 የዞሯል

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.10

ከወንድሙ ኢብሣ

ፖለቲካ

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 23 2004 ዓ.ም.

ያለ ታላላቅ ሰዎች አገር ትልቅና

ባለፀጋ ልትሆን አትችልም

በዚህ ርዕስ ሥር ክፍል ሁለትን የቀጠልኩበት ሁለትን

ምክንያቶች ናቸው፡፡ አንደኛ ርዕሱ ሰፊ ስለሆነና በቀድሞ

ጽሑፌ የመጨረሻ ሐረጐችን ትንሽ ለማብራራትና የአገር

አባቶችን የታላቅነት ሚናን ጐላና ረገጥ አድርጌ ለማሳየትና

ስለሱማሌ ሞቃዲሾ ታላላቆች አልቦ ያልኩትን በራሴ

ለማረም አስቤ ነው፡፡

ከሁለተኛው ልጀምር፡፡ እውነትም በዛሬ የዓለም ተጨባጭ

ሁኔታ ከ10 ዓመታት በላይና በእስከ ዛሬም በራሱ ለራሱ

የመንግሥት ሥራ በብቃት በሚከውን መንግሥት አልባ

ወይም ደካማ መንግሥት ያሉት የሞቃደሾ ሱማሌ አገዛዝ

ታላላቆች አጥተው ወይስ የታላላቆቹዋ እርስ በርስ

መታጣጣት ወይንም አለመግባባት ነው የሚለው ጥያቄ

ቢነሳ ተገቢ ነው፡፡

አዎን በቀደም ጽሑፌ እንደገለጽኩት የትኛውም አገር

ታላላቆች አልቦ አትሆንም፡፡ የሱማሌ ሞቃዲሾም አልባ

አትሆንም፡፡ ይመረጣል፡፡ ችግሩ የሞቃዲሾ ሱማሌዎች

ትልልቆች እያሏቸው ትልልቆቹ አንድም ወደ ጐረቤት

አገሮች ለወረራ የሚቅበዘበዙ (በ1969 ዓ.ም የኢትዮጵያን

ወሰን አልፈው ወረዋል፡፡ ይህ እንግዲህ) የፕሮፖጋንዳ

ጦርነት የመንዛት አባዜ ባለቤት ስለሆኑ ነው፡፡

በተጨማሪም ትልልቆች ካልተደማመጡ ትንንሽ፣መናኛና

ደካማ ተደርገው ስለሚታዩ ነው፡፡ ትልልቆች

ይከበራሉ፤ይደመጣሉ፤የሞቃዲሾ ሱማሌ ችግር ይህ ነው፡፡

የአንድ አገር ታላላቆች እርስ በርስ መግባባት

ካልቻሉ፣መከባበር ከዕቃቸው፣መደማመጥ

ከሰለቻቸው፣ችኮና “ጉግማንጉጎች” ይሆናሉ፡፡

ጉግማንጉጎች የበዙበት አገር ጭላንጭልና ተስፋ ይጠፋል፡

፡ ሌላ ቀርቶ ለአንድ አገር ጥሩና ዴሞክራቲክ መንግሥት

ባይፈጠር እንኳ ከመንግሥት አባልነትና ከመግባታችን

አምባገነን አገዛዝ (መንግሥት) ያስፈልጋል ብዬ አምናለሁ፡

፡ በሞቃዲሾ ሱማሌ የጠፋው ይህ ነው፡፡ በዛሬ ጥሩና

መልካም አስተዳደር የመሠረቱ አገሮች አምባገነን የነበሩ

ነበሩ፡፡ በመሆኑም በአንድነት ቆመው አብረው ተባብረው

ሲያበቁ አንባገነን አገዛዝን ወደ ዴሞክራሲያዊ አመራር

ለውጠዋል፡፡

የትላንትናን ደ/አፍሪካ አፓርታይድ አገዛዝን አስቡልኝ፡፡ በሃያ

ዓመታት ውስጥ ሰዎችን ከዘር ከቀለም ተከፋፍለው፣በትም/

ቤት፣በገበያ፣በመንደር አመሠራረት አሰቃቂና ጨካኝ

“የጉግማንጉግ” የሞኝ ፖለቲከኞች ፖለቲካ በፍሬድሬክ

ኤንግልስ (የነጭ የመጨረሻ አፓርታይድ ገዥ) እና በታላቁ

ማንዴላ አርቆ አስተዋይነት የዛሬ ደ/አፍሪካ ከአፍሪካውያን

አንባገነን አገሮች መጨረሻ ተነስታ ዛሬ ከዴሞክራሲያዊ

መንግሥት ቀድማ ተጠቃሽ አገር ናት፡፡ ኢትዮጵያ በዚሁ

ዓመት ከደርግ ተላቀቀች ግን ከደቡብ አፍሪካ ዴሞክራሲዊ

አስተዳደር ጋር አትነፃፀርም፡፡ ሰማይና መድር ናት፡፡ ዛሬ

እኛ ገና አንባገነን ነን፡፡

ስለዚህ ነው አንድ አገር መንግሥት አልባ ከመሆን

አንባገነን መንግሥትም ቢሆን ሊመረጥ የገባል የምለው፡

፡ የሞቃዲሾ ሱማሌ ታላላቆች ጥሩና መልካም አስተዳደር

መመሥረት ቢያቅታቸው “ይህችን ያልተከፋፈለች አገር

ይዘውና ተያይዘው ማቆየት ሲያቅታቸው ስናይ የሱማሌ

(ሞቃዲሾዎች) ታላላቆች የት ገቡ? ከሚለው የሀሳብ

ሙግት የምገጥመው፡፡ ይሁንና ከእኔ የተሻሉ ወዳጆቼም

ሲያወያዩኝ ስህተትን አምኖ መቀበል በእውቀትም ማመን

ነው ብዬ በማሰብ የሞቃዲሾ ሱማሌዎችና ወንድም

እህቶቻችን ታላላቆች አሏቸው፡፡ ነገር ግን ታላቅነት

በመከባበር፣በመተባበር፣በመደማመጥ ወደ ታላቅና ባለፀጋ

አገር መንደርደሪያ አገራዊ የጋራ አገዛዝ (ጥሩም ይሁን

ክፉ) መቆየት ተገቢ ነው ብዬ ነው የማስበው፡፡ መንግሥት

አልቦ መሆን በአውነት ቸነፈር ነው፡፡ መቅሰፍት ነው፡፡

ሶማሌ ሞቃዲሾን ከደካማ መንግሠት ታላቅ የተጠናከረች

ሶማሌንና ለራስዋም ለጐረቤቶቿም ምቹ አገር ትሆን ዘንድ

እየተመኘሁኝ ወደ ተነሳሁበት ርዕሰ ጉዳዬ ልመለስ

አዎን ያለ ታላላቅ ዜጐች ታላቅና የበለፀገች አገር መገንባት

ያስቸግራል ማለት ብቻ ማይሆን የማይቻልም ነው የሚል

ሀሳብ አለኝ፡፡

ከዚህ አንፃር ኢትዮጵያን አገራችን ከጥንት እስከዛሬም

አልፎ አልፎ “ጉግማንጉግ” ክፉ ገዥዎችን ባታጣም (ኮ/ል

መንግሠቱን አስቡልኝ ጭለንጭል አልቦ የዴሞክራሲን

ዘመን) የታላላቆች ሊቃውንት ጠቢባን በየዘርፉ በየሙያውና

በየዘመኑ እንደነበሩ ባለፈው ጽሑፌ ጠቅሻለሁ፡፡ ትልቅነት

በዕድሜም በተግባርም በሥራም ነው፡፡

እነዚህ የኢትዮጵያን ታላላቆች አባቶች ከሁሉም አቅጣጫና

ጐሣ ብሔረሰብና ብሔር የነበሩ፣የተከበሩና የተባበሩ

ለዚህም ከውጭ ለመጣ ጠላት ሁሉ ከጥንት እስከ

ባድሜ በህብረት ክንድ መመከታችን በቂ ማስረጃ ነው፡፡

ይህም ሆኖ ግን ለውስጥ ቅንቅኖቻችን መፍትሄ መስጠት

አልቻልንም፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዛሬ ዘመን ኢትዮጵያዊ ትውልድ

እኔና በእኔ እድሜ ያሉትን ጨምሮ ሺህ ጉዳዮችን፣ሺህ

ማርኪዎችን፣ሺህ አሳዳጆችን፣ሺህ አቁሳዮችን ገዥዎች

ሥርዓት አመራር ከቶ አንሻም፡፡ የወሎ ፈረሶችንና በቆሙ

ሰዎች ዓይነት ሰዎች ውስጣቸው ቀርከሃ የሆኑ ገዥዎችና

መሪዎችም ከዚህም ሆነ ከዚያ ከገዥም ሆነ ከተቃዋሚ

ፓርቲዎች ይህ ትውልድና ዘመኑ በጭራሽ አይፈልግም፡

፡ የዛሬ ኢትዮጵያዊ ትውልድ እንደ ጃፓን ዜጐች ታላቅ

የሞራል እሴት ይፈልጋል፡፡ ዕቃ በየትም ወድቆ ቢያይ

አንስቶ ለፖሊስ ይሰጣል፡፡

ትውልዱ ከድሮ አባቶቻችን ጠንካራ የጋራ ሕዝባዊ

የባህል፣የሞራልና ሥነ-ምግባርን በጥንቃቄና በአክብሮት

ተቀብሎ ራሱንና አገሩንም ማክበር ማስከበር ተገቢ ነው፡፡

ታላላቆች በየዘመኑና በየትውልዱ ይፈጠራሉ ብዬ

አስባለሁ፡፡ ብዙዎቻችሁ እንዲሁ ታስባላችሁ የሚል ቀና

ስሜትና ግምት አለኝ፡፡ ታላላቆች ሁሉ በእምነት በእውነትና

በሃይማኖት የፀኑ ናቸው፡፡ ያለእምነት ያለ እውነትና

ሃይማኖታዊ ሥነ-ምግባር የዓለም ታላላቅ አገሮች ታሪክ

አይታሰብም፡፡ የሃይማኖቶች መለያየት ችግር አይደለም፡፡

ብቻ ሃይማኖት ያለው እምነት ደግሞ ፍቅር ነው፡፡ ፍቅር

በራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ በዚህ መስመር ታላላቆች

ሥራቸው አልፋና ኦሜጋ የሆናል፡፡

ስለሆነም ኢትዮጵያ በእስከ ዛሬና የአሁኑ መንግሥትም

የታሪክ ደረጃና ቦታው ገለልተኛ ታዛቢዎችና ታሪክ

ጸሐፊዎች ተመራማሪዎች ደረጃም ይታወቃል፡፡

የቤተመንግሥት ጸሐፊዎች ታሪክ ግን ተረትና ውሸት ነው፡

፡ የኢትዮጵያ ደረጃም ከፍ ከፍ እያለ መጣ? ወይስ ወጣ

ወጣና ተንከባለለ እንደ ሸንበቆ እየሆን ነው? መልሱን

ለክቡራን አንባብያን እተወዋለሁ፡፡

ትውልዱ ከድሮ አባቶቻችን ጠንካራ የጋራ ሕዝባዊ የባህል፣የሞራልና ሥነ-ምግባርን በጥንቃቄና በአክብሮት

ተቀብሎ ራሱንና አገሩንም ማክበር ማስከበር ተገቢ ነው፡፡

ታላላቆች በየዘመኑና በየትውልዱ ይፈጠራሉ ብዬ አስባለሁ፡፡ ብዙዎቻችሁ እንዲሁ ታስባላችሁ የሚል ቀና

ስሜትና ግምት አለኝ፡፡ ታላላቆች ሁሉ በእምነት በእውነትና በሃይማኖት የፀኑ ናቸው፡፡ ያለእምነት ያለ

እውነትና ሃይማኖታዊ ሥነ-ምግባር የዓለም ታላላቅ አገሮች ታሪክ አይታሰብም፡፡ የሃይማኖቶች መለያየት

ችግር አይደለም፡፡ ብቻ ሃይማኖት ያለው እምነት ደግሞ ፍቅር ነው፡፡ ፍቅር በራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡

በዚህ መስመር ታላላቆች ሥራቸው አልፋና ኦሜጋ የሆናል፡፡

ስለሆነም ኢትዮጵያ በእስከ ዛሬና የአሁኑ መንግሥትም የታሪክ ደረጃና ቦታው ገለልተኛ ታዛቢዎችና ታሪክ

ጸሐፊዎች ተመራማሪዎች ደረጃም ይታወቃል፡፡ የቤተመንግሥት ጸሐፊዎች ታሪክ ግን ተረትና ውሸት ነው፡

፡ የኢትዮጵያ ደረጃም ከፍ ከፍ እያለ መጣ? ወይስ ወጣ ወጣና ተንከባለለ እንደ ሸንበቆ እየሆን ነው?

መልሱን ለክቡራን አንባብያን እተወዋለሁ፡፡

አንድ ነገር ልብ በሉልኝ፡፡ ኢትዮጵያ በአፄ ቴዎድሮስ እጅ

የማትሰጥ አኩሪ አገር፣ አፄ ዮሐንስም ኢትዮጵያ ዳር ድንበር

ሕይወቱን ያልሰሰቱ ታሪክ ሠሪና መሪ ነበሩ፡፡ አፄ ምኒልክም

የአድዋ ድል ጀግና ነበሩ፡፡ ጃንሆይም ከነ ረጅም የሥልጣን

ሱሰኛነታቸው ታላቅ ኢትዮጵያዊና አፍሪካዊ እንደ ነበሩ

5

መካድ ከሀቅ ውጭ ያደርገናል፡፡ ኮ/ል መንግሥቱም ቢሆኑ

የውስጥ ጨፍጫፊነቱና ክፋቱ ወደር አልባ ቢሆንም ቅሉ

ከአፄዎቹ የታሪክ በታኝ ኢትዮጵያ ለመቆየት በ1969

ከሱማሌ ሞቃዲሾ ወረራ ጋር ሙሉ ሕዝብን አስተባብረው

የታላቅነት ድርሻውን ተወጥተዋል፡፡

ከሰሜኑ የአገራችን ወገን ጋር የነበረውን የቅራኔ አያየዝ

አቅምም እውቀትም ስላልነበረው ለዛሬዋ ኢትዮጵያ ክፉ

ሁኔታ የደርግና ኮ/ል መንግሥቱ ድርሻ ብዙ እንዳለበት

መካድ አይቻልም፡፡

ይሁንና ከአፄዎቹ ደርግና በእስከ ዛሬም የተተበተቡ የመፍቻ

ቁልፍ ያልተገኘላቸው የሕግ የበላይነት፣የዴሞክራሲ

ጥያቄ የሀብት አስተዳደር ፈትሃዊነት ጥያቄዎች ከ40 እና

ከ50 ዓመታት ጀምሮ መላ ኢትዮጵያውያን እየታገሉለት

ይገኛሉ፡፡ ከ1936 የወያኔ የቀዳሚ ወያኔ ትግራይ ገበሬዎች

አመፅ፣የባሌ ገበሬዎች (ኢጆሌ ባሌ) እና በጅማ ገበሬዎች

ትግል፣የኢትዮጵያ ተማሪዎች ትግሎች ሁሉ አልሰመሩም

እንጅ የታላቅነት መፍጠሪያ ማጠናከሪያዎች የነበሩ ነበሩ፡፡

በቁጭት መክነው ቀሩ እንጂ፡፡ የኢትዮጵያን ታላላቆች ዛሬ

ዛሬ አንዳንዶች በተሳሳተ ሥሌት ወይም የኢትዮጵያውያንን

የረጅም ዘመቻ የትግል ታሪክ ለመካድና ለማስነሳት

ቢያንስ ቢያንስ (በኢህአዴግ) ዘመን ስለዴሞክራሲ

ስለብዙሃን ፖለቲካ ፓርቲዎች ማሰብ ከጀመርን 19

ዓመታት ቢሆንም ብሎም ሀቁ ግን የእነ ኢህአፓ

ሕወሓት፣ኦነግ፣ኦብነግ፣መኢሶን፣ወዝሊግ አብዮታዊ

ሰደድ ማሌድ፣ኢጭአት ፓርቲዎች ከ1964-1972/3 እና

ከኢሰፓእኮ በኋላም ኢሠፓ ተቀረጣጥፎ እስከተበላበት

ዘመን ድረስ የነበሩትን ትግሎችና በእስከ ዛሬም በተለያዩ

ሁኔታዎች እየተደረጉ ያሉት እልህ አስጨራሽ ትግሎች

የታላቅነት ማሳያ መስታወቶች ነበሩ፡፡ ናቸውም፡፡

እነዚህ ሁሉ ብዙ ሰማዕታት የተገበረባቸው የሙሉ

ኢትዮጵየውያን የትግል መስኮች ተንቋሸውና ዋጋ አጥተው

ስለ ዴሞክራሲ፣ስለ ሕግ የበላይነት፣ስለ ብዙሃን ፖለቲካ

ፓርቲዎች፣ስለ መሬት ስለገዥዎች ሣይሆን መሬት

ለአራሹ፣ስለ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ፣ስለ መልካም አስተዳደር

በጥቅሉ ሁላችንም በእኩልነት የምታስተዳድርና የሁላችን

አቻ አስተናጋጅ አገር ለመገንባት ሲታገሉ የኖሩ እያሉ ያሉት

ሁሉ ታላላቆች ቅቡላንና ቅዱሳን ናቸው ብዬ አስባለሁ፡፡

በተቃራኒው ቅንጣት ያህል ግራም አስተዋጽኦ ሳያበረክቱ

እየተሹለከለኩ ጥቅምና ዝና ፈላጊ ትናንሽ ዜጐችም እንደ

ነበሩንና እንዳሉን አልዘነጋም፡፡ እነዚህም ሰዎች ናቸው፡፡

ትግላችንን ጠመዝማዛና አሜከላ የበዛበት ያደረጉት ብዬ

አስባለሁ፡፡

ዛሬ ዛሬ የተላንቱ ታላላቆቻችን ጥራቶች የዛሬዎች

መስዋዕትነቶችን ለማምከንና ባዶ ለማድረግ ታስቦበት

በእቅድ ለክፋት ስንማር (በተማሪ) በልዩነት (ሲቪል

ሰርቪስ አስቡልኝ የማኛ ካድሬዎች ብቸኛ ት/ቤት በነጥቡ

የማይማርበትን) ተምረን ስንቀጠር (ስትቀጠር) በልዩነት

ዛሬ ማንም ኢትዮጵያዊ አዲስ ለመቀጠር የገዥ ፓርቲ

አበል ደጋፊ ተባባሪ መሆን የቅድሚያ ቅድሚያ በተሰጠበት

አመራር ዘመን፣አስተሳሰባችን፣አነጋገራችን፣አሠራራችን፣እየ

ታወቁና ወደ ትልቅነት ጐዳና እየወሰድን ወይስ በተቃራኒው

እያሰብን መሆኑን ለክቡራን አንባብያን ቢተው ይመረጣል፡

፡ መልሱ ግልጽ አጭር ነውና፡፡

ለማጠቃለል ኢትዮጵያዊ ተላላቆቻችን የተሰውት፣ዕድሜ፣

ጤንነት፣እርጅና ሳያግዳቸው፣ተስፋ ሣያስቆርጣቸው 70

እና 8ዐ ዓመታቸው እየታገሉ ያሉት ከ19 ዓመታት ወዲህ

ቢያንስ ቢያንስ ስለ ዴሞክራሲ ስለ ብዙሃን ፖለቲካ

ፓርቲዎች ማሰብ ጀምርን የሚሉትን ነጭ ውሾች ማጋለጥ

የታላቅነት ማሳያም ነው፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያውያን

ከሁሉም ወገን ታላላቆች በበቂ ነበሩ፤ዛሬም አሉን፡፡ ዋናው

ችግራችን አንደኛ እንደሰዎች፣እንደ ዜጐች፣እንደ አንድ አገር

ልጆች እንከባበር፣መከባበር የቀዳሚ ቀዳሚያችን ይሁን፡

፡ ሁለተኛ የተከባበረ ወገን መደማመጥ አይቸግረውምና

ከአንጅት ከልብ እንደማመጥ፡፡ ሦስተኛ ለሁላችን

የመትሆን መብት፣ሀብት ባንክ ታንክ ያላትን ኢትዮጵያ

ሁላችንም እንደየሙያችን፣እንደችሎታችን ለመገንባት

አዲስ አመለካከት ሊገነባ ይገባል፡፡ አራተኛ ታማኝና

ለፈሪሃ እግዚአብሔር፣ለፈሪሃ ሕዝብ፣ለፈሪሃ ሕግ፣ለፈሪሃ

ሕሊና፣ለፓርቲያችን ዲስፕሊንና መመሪያ እንዲሆን

በአዲሱ አዲስ ዘመንና ዓመት ከገዥው ፓርቲ በጣም ብዙ

ሥራ፤ከተቃዋሚዎችም ቀላል ያልሆነ ቅንነትና ትብብር

ሊፈጥር ትውልድና ዘመኑ ይማፀናል፡፡ ታላላቆችን ሳታጣ

ታላቅነትና ባለ-ፀጋነትን ያጣች ኢትዮጵያ በመከባበር ታላቅ

እናድርግ ባለፀጋም እናደርጋታለን፡፡ ይቻላል፡፡

www.andinet.org.et

6

ግርማ ካሣ

የሕንድ፣ የቻይናና የሳውዲ ኩባንያዎች በአገራችን

ኢትዮጵያ ለእርሻ ሥራዎች ሰፊ መሬት በሊዝ እንደወሰዱ

መሆናቸው በስፋት ተዘግቧል። የገዢው ፓርቲ

ባለስልጣናት «ሰዎች የማይኖሩባቸው ቦታዎችን ነው

ለልማት ስንል ለውጭ አገር ዜጎች የሰጠነው» ይላሉ።

ተቃዋሚዎች በበኩላቸው ያለ ውዴታቸው ዜጎች

እንደተፈናቀሉ ይናገራሉ፡፡ የመሬቱም “ሽያጭ” በርካሽ

ዋጋ፣ እስከ 99 አመታት ላለ ረጅም ጊዜ እንደሆነ

በመግለጽ፣ የገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግን እንቅስቃሴ

ጸረ-ሕዝብና የአገርን ጥቅም የሸጠ እንደሆነ አድርገው

ያቀርባሉ።

አንድ ጊዜ፣ ከአዲስ አበባ የመጣ አፍቃሪ

ኢሕአዴግ የሆነን ሰው «መሬት ለ99 አመታት ለውጭ

አገር ዜጎች ይሸጣል ይባላል። እውነት ነው ወይ?»

ብዬ ጠየኩት። ለ99 አመታት ለውጭ አገር ዜጎች

መሬት በሊዝ እንዳልተሸጠ፣ ቢበዛ ለ25 አመታት ብቻ

ሊሆን እንደሚችል ገለጸልኝ። 25 አመት ለምን ሊሆን

እንደሚችል ሲያስረዳኝ «የተሰጠውን ቦታ ኢንቨስተሮች

መጀመሪያ ማልማት አለባቸው። መንገዶች ይሰራሉ።

ለሰራተኞች የሚሆን በአካባቢው ትምህርት ቤቶች፣

መኖሪያ ቤቶች ይሰራሉ። ይሄ አይነት ቅድመ ትርፍ

ሥራዎች ሁሉ፣ ቢያንስ ከአምስት እስከ አሥር አመት

ይፈጃሉ። ትርፍ ሊያገኙ የሚችሉት ከአሥር አመት በኋላ

ቢሆን ነው። ያን ሁሉ ሰርተው፣ ያን ሁሉ ገንብተው፣

ለእነርሱም ትርፍ የሚያገኙበት ሚዛናዊ የሆነ ተጨማሪ

አሥር አሥራ አምስት አመታት መስጠት ያስፈልጋል።

አለበለዚያ ኢንቨስት ላድርግ ብሎ የሚመጣ አይኖርም»

ነበር ያለኝ። ይህ እንግዲህ የአንድ አፍቃሪ ኢሕአዴግ

ቃል ነው። ያለኝን አለኝ እንጂ ውሎች በርግጥ 25

አመታት ብቻ መሆናቸውን፣ የሚያረጋግጥበት አንዳች

አይነት መረጃ አላቀረበልኝም።

ከዚህ ከኢሕአዴግ ደጋፊም ሆነ ከሌላ ምንጮች፣

ለውጭ አገር ዜጎች የሚሰጠው መሬት በምን ሂሳብ፣

ለምን ያህል ጊዜ እንደሆነ በተጨባጭ በመረጃ

የተገለጸበት ቦታ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ላገኝ

አልቻልኩም ነበር።

ሱልጣን ኢብራሂም አሰብን ለጣሊያኖች እንደ

ሸጠ፣ የአገራችን መሬት፣ እኛ በማናውቀው መንገድ

ለውጭ አገር ዜጎች እየተቸበቸበ ይሆን? ከአመታት

በኋላ ኢትዮጵያ የሕንዶችና የቻይናዎች አገር

ትሆን ይሆን? አይናችን እያየ በልማት ስም ብሄራዊ

ጥቅማችን እየተሸረሸረ ይሆን? ወይንስ ጥቅም ላይ

ያልዋለ መሬቶችን ጥቅም ላይ በማዋል፣ ለዜጎች የሥራ

እድል የሚከፍቱ፣ እህል በአገራችን ገበያዎች በብዛት

እንዲኖሩ የሚያደርጉ፣ የስንዴም የጤፍ የስኳርን ዋጋ

የሚያስቀንሱ፣ ገጠሪቷ ኢትዮጵያን የሚያለሙ፣ ጸረ-

ድህነትና አገር ጠቃሚ ተግባራት ነው እየተሰሩ ያሉት?

በቅርቡ በሰሜን አሜሪካ የሚንቀሳቀስ የአዲሲቷ

ኢትዮጵያ ሶሊዳሪቲ ንቅናቄ የሚባል የሲቪክ ማህበር፣

እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ለብዙ ጊዜ ማወቅ የምፈልገውን፣

ከላይ ለጠቀስኳቸው ጥያቄዎች አንዳንድ ምላሽ

የሚሰጥን መረጃ ይፋ አድርጓል። የአዲሲቷ ኢትዮጵያ

ሶሊዳሪቲ ንቅናቄ አክቲቪስቶች፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ

ሊያውቀው፣ ሊመረምረው፣ መላ ሊፈልግለት

የሚገባውን ይህ አይነቱን ቁልፍ መረጃ አቀናብረው፣

ይፋ ማድረጋቸው በጣም ሊያስመሰግናቸው የሚገባ

ትልቅ ተግባር ነው። እጅግ በጣም ትልቅ ሥራ ነው

የሰሩት።

ያልሆነውን ሆነ በማለት፣ በስሜት በመነዳት ብቻ

መቃወም ሳይሆን፣ ይህ አይነቱን ጥናታዊ፣ በእውነት

ላይ የተመሰረተ፣ ማንም ጥሩ አእምሮ አለኝ የሚል ዜጋን

አእምሮ የሚቆረቁር መረጃዎችን ማሰባሰብና ለሕዝብ

ማሳወቅ፣ ተቃዋሚዎች በዋናነት ሊሰሩት የሚገባ ትልቅ

ተግባር ነው። የአዲሲቷ ኢትዮጵያ ሶሊዳሪቲ ይህንኑ

ነው ያደረገው።

ሶሊዳሪቲ ይፋ ካደረጋቸው መረጃዎች መካከል፣

ምን ያህል መሬት፣ በየትኛው ክልል በሊዝ እንደተሰጠ፣

ለማን እንደተሰጠ፣ በምን ያህል ዋጋ እንደተሰጠ

የሚገልጹ፣ የመንግስት ባለስልጣናት የፈረሙበትና

ማህተማቸውን የመቱበት፣ ሊካዱ የማይችሉ፣

የማያከራክሩ የሕግ ሰነዶች ይገኙበታል።

ለውጭ አገር ዜጎች የተሰጠው መሬት ስፋት

ለኢትዮጵያውያን በሊዝ የተሰጡትን መሬቶች

ለጊዜው ትተናቸው፣ ለውጭ አገር ዜጎች የተሰጡት

www.andinet.org.et

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 23 2004 ዓ.ም.

መሬቶች ብቻ ብንመለከት፣ ለቻይና ኩባንያ 25000

ሄክታር፣ ለሳውዲ ኩባኒያ 10000 ሄክታር፣ ለሕንድ

ስድስት ኩባንያዎች 246,5012 ሄክታር መሬቶች በሊዝ

ታድሏል።

ይህንን አሃዝ አብዛኞቻችን በሚገባን መልኩ

እንደሚከተለው ለማስቀመጥ እሞክራለሁ፡

1. ወደ አራት ሚሊዮን ሕዝብ የሚኖሩባት የአዲስ

አበባ ከተማ ስፋት 54,000 ሄክታር አካባቢ ነው።

በሌላ አባባል የአዲስ አበባን አምስት ጊዜ የሚያህል

መሬት ነው ለውጭ አገር ዜጎች የተሰጠው።

2. በሕንድ በርካታ ፌደራል ክልሎች አሉ። ከነዚህ

ክልሎች መካከል በደቡብ ምዕራብ የምትገኘው፣ ወደ

34 ሚሊዮን ሕዝብ የሚኖርባት የኬራላ ክልልንና

በሰሜን የምትገኛዋ ወደ 26 ሚሊዮን ሕዝብ የሚኖርባት

የሃሪያና ክልል ይገኙበታል። ኬራላ ስፋቷ 3,886,300

ሄክታር ስትሆን ሃሪያና 4,421,200 ሄክታር ትሰፋለች።

ለውጭ አገር ኩባንያዎች የተሰጠውን መሬት

ስንመለከት፣ የኬራላን ስድስት በመቶ የሃሪያናን ደግሞ

5.4 በመቶ የሚሆንን መሬት ያህላል። በኬራላ የሕዝብ

ብዛትን በሄክታር ብናሰላው፣ በአገራችን ለውጭ አገር

ዜጎች የተሰጠውን መሬት በሚያክል የኬራላ ክልል ቦታ

2,147,884 ሕዝብ ይኖራል። በሌላ አባባል 2,147,884

ሊያኖር የሚችልን መሬት ነው ለውጭ አገር ዜጎች

የተሰጠው።

3. ሉክሳምበርግ በአውሮፓ፣ ፈረንሳይን በሰሜን

ምእራብ ሆላንድንና ቤልጅየምን በሰሜን የምታዋስን

አገር ናት። ስፋቷ 258,600 ሄክታር መሬት ነው።

ለውጭ አገር ዜጎች በኢትዮጵያ የተሰጠው መሬት

ሉክሳምበርግን የሚያክል መሬት ነው።

4. በመቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን በከንቱ

ያለቁበት የባድመ ይገባኛል ጦርነት ነው። የባድመ

ከተማ ከዳር እስከ ዳር ከአንድ ኪሎሜትር አትበልጥም።

በመሆኑም ስፋቷ ከ100 ሄክታር ያነሰ ነው ማለት

ይቻላል። እንደሚታወሰው ከ100 ሄክታር በታች ለሆነ

መሬት ነው፣ ያ ሁሉ የንብረት እልቂት የተከሰተው፣ ያ

ሁሉ ደም የፈሰሰው። ለውጭ አገር ዜጎች የተሰጠው

250,012 ሄክታር መሬት በስፋቱ፣ 2,500 ባድማዎች

እንደተሰጡ የሚያስቆጥር ነው። ለአንድ ባድማ ያን

ያህል መስዋእትነት ሲከፈል ለ2,500 ባድማዎች በቀላሉ

መሬቶች ሲሰጡ ማየት እጅግ በጣም የሚያሳዝንና

እያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ ሊያስቆጣ የሚገባ ጉዳይ

ነው።

ለውጭ አገር ዜጎች የተሰጠው መሬት ለምን ያህል

ጊዜ እንደሆነ

የተሰጠው መሬት ብዛት አሳሳቢነት እንደተጠበቀ

ሆኖ፣ ለምን ያህል ጊዜ ነው ሊዙ የተፈረመው የሚለውን

ጥያቄ ስናነሳ ከአዲስ አበባ መጥቶ ያነጋገርኩት አፍቃሪ

ኢኮኖሚ

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.10

የመሬት ቅርምት ለልማት ወይንስ

ለአገር ጉዳት?

የሲ.ኤል.ሲ የሕንድ ኩባንያ ለአምሳ

አመታት መሬቱን ከተጠቀመ በኋላ

የሚከፍለው ጠቅላላ ዋጋ ወደ 2

ሚሊዮን ብር ብቻ ሲሆን፣ ይህም

በአዲስ አበባ 0.02 ካሬ ሜት

ለሚያወጣ መሬት የሚከፈል ዋጋ

ነው። ሌላው ከዋጋው ነገር በተገናኘ

ለማንሳት የምፈልገው ሌላ ነጥብ

አለ።በመሬቱ «ሽያጭ» ስምምነቶች

እንደምናየው ኩባንያዎቹ የሚከፍሉት

በውጭ ምንዛሪ በዶላር ወይንም ዩሮ

ሳይሆን በኢትዮጵያ ብር ነው። የብር

ዋጋ ካሽቆለቆለ እነርሱም የሚከፍሉት

ክፍያ የዚያኑ ያህል ያሽቆለቁላል።

ለምሳሌ አገሬን ለቅቄ ስደት ስጀምር፣

አንድ የአሜሪካን ዶላር በ2.07 ብር

ነበር የሚመነዘረው። አሁን አንድ ዶላር

በ17.5 ብር ይመነዘራል...

ኢሕአዴግ ከነገረኝ ጋር ፈጽሞ የማይሄድ ሆኖ ነው

ያገኘሁት።

ከተሰጡት መሬቶች መካከል 178, 012

(71 በመቶ) ሄክታር መሬት ለአምሳ አመት ነው

የተሰጠው። አሁን ላለው ትውልድ ብቻ ሳይሆን

ለሚቀጥለውም ትውልድ መዘዝ የሚፈጠር ስምምነት

እንደተፈረመ ነው የምናየው።

እንደዚያም ሆኖ ግን በስምምነቶቹ

እንደተቀመጡት የፌዴራል መንግስቱ የተሻለ ሶሲዮ

ኢኮኖሚ ጥቅም ከተገኘ የስድስት ወራት ጊዜ ሰጠቶ

ሊዙን መሰረዝ የሚችልበት ሁኔታ አለ። ለምሳሌ

ከካሩቱሪ የሕንድ ኩባንያ ጋር በተደረገው የስምምነት

ውል አንቀጽ 5.4 “The lessor has exclusive right

to terminate the land lease agreement subject

to at least six months prior notice in written

up on the Federal Government’s decision for

any better socio-economic benefit” ይላል።

ስለዚህ ውሉን በተፈለገ ጊዜ መሰረዝ እስከተሻለ

ድረስ የውሉ ዘመን 25 ሆነ አሥር ሆነ ብዙም ስጋት

ውስጥ የሚከት አይመስለኝም።

ለውጭ አገር ዜጎች የተሰጠው መሬት ዋጋው

ምን እንደሆነ

በአሁኑ ጊዜ አዲስ አበባ ውስጥ እንደ ገርጂ

በመሳሰሉ ብዙ ቦታዎች ወደ 200 ካሬ ሜትር (0.02

ሄክታር) ስፋት ያለው ቤት ከሁለት ሚሊዮን ብር ያነሰ

አይገኝም። አንድ ሄክታር መሬት ወደ 67 ሚሊዮን

ብር ነው የሚያወጣው እንደ ማለት ነው። አስቡት …

መቶ ሺህ ሄክታር መሬት ስድስት ትሪሊየን፣ ስድስት

መቶ ቢሊዮን ብር ይደርሳል።

ሲ.ዔል.ሲ ስፔንቴክስ ለተባለው የሕንድ ኩባንያ

100,000 ሄክታር መሬት ለአምሳ አመት የተሰጠበት

ዋጋ ሃያ ብር ( አንድ ዶላር ከሃያ ሳንቲም) ብቻ ነው።

በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባ በአንድ ተራ ምግብ ቤት፣

ጥቂት ጉርሻ የሚሆን ስጋ ጣል ጣል የተደረገበት አንድ

እንጀራ ወጥ ምግብ ለመመገብ 170 ብር ያወጣል።

የአንድ እንጀራ ምግብ ዋጋ 8.5 ሄክታር ይገዛል።

የሲ.ኤል.ሲ የሕንድ ኩባንያ ለአምሳ አመታት

መሬቱን ከተጠቀመ በኋላ የሚከፍለው ጠቅላላ ዋጋ

ወደ 2 ሚሊዮን ብር ብቻ ሲሆን፣ ይህም በአዲስ

አበባ 0.02 ካሬ ሜት ለሚያወጣ መሬት የሚከፈል

ዋጋ ነው። ሌላው ከዋጋው ነገር በተገናኘ ለማንሳት

የምፈልገው ሌላ ነጥብ አለ።በመሬቱ «ሽያጭ»

ስምምነቶች እንደምናየው ኩባንያዎቹ የሚከፍሉት

በውጭ ምንዛሪ በዶላር ወይንም ዩሮ ሳይሆን

በኢትዮጵያ ብር ነው። የብር ዋጋ ካሽቆለቆለ እነርሱም

የሚከፍሉት ክፍያ የዚያኑ ያህል ያሽቆለቁላል። ለምሳሌ

አገሬን ለቅቄ ስደት ስጀምር፣ አንድ የአሜሪካን ዶላር

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.10

ዜና

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 23 2004 ዓ.ም.

የመኢአድ ሥራ አስፈፃሚ አወዛጋቢ ውሳኔዎች ወሰነ

- ዋና ፀሐፊውን አገደ

- የፕሬዝዳንቱ ጉዳይ ህግና ሥነ ሥርዓት ኮሚቴ

እንዲያው መራ

- ማዕከላዊ ም/ቤቱ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲመራ

ወሰነ

በተደጋጋሚ በመካከሉ አለመግባባት ተፈጥሮ በፍ/ቤት

ክርክርና በድብድብ ሲተራመስ የከረመው መላው ኢትዮጵያ

አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ አዲስ አወዛጋቢ ጉዳዮች

መከሰታቸውን ከፓቲው ጽ/ቤት የመረጃ ምንጮቻችን

ገለጹ፡፡ የመረጃ ምንጮቻችንን መነሻ በማድረግ አስተያየት

እንዲሰጡን የፓርቲውን ሥራ አስፈጻሚ አቶ ማህተመ በኩረን

አነጋግረናቸው ነበር፡፡ አቶ ማህተመ እንደሚሉት “ያገኛችሁት

መረጃ ትክክል ነበር፡፡በ18/01/2004 ዓ.ም የተሰበሰበው

የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ሦስት አብይ ውሳኔዎችን ወስኗል፡

፡ 1. ከመስከረም 18 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ

የፓርቲውን ዋና ፀሐፊ አግዷል፡፡

2. የፓርቲው ፕሬዝዳንት በፈጸሙት ጥፋት

ጉዳያቸው በህግና ሥነ ሥርዓት ኮሚቴ እንዲታይ ተመርቷል

3. የፓርቲው ማዕከላዊ ም/ቤት አስቸኳይ ስብሰባ

ተጠርቶ በተከሰተው ችግርና ለረጅም ጊዜ ሲንከባለል ቆይቶ

ይፋ በሆነው አጠቃላይ ችግር በግልጽ ተወያይቶ ውሳኔ

እንዲሰጥበት ሥራ አስፈጻሚው በአብላጫ ድምጽ ወስኖአል”

ብለዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡን ----- ጠይቀን

በሰጡን መልስ -------- ብለዋል፡፡

ይህንን ለመወሰን ሥራ አስፈጻሚ ሥልጣን አለው ወይ?

“ማነው ተው የሚለኝ ...

የሰላማዊ ትግልን ወዳድ ህብረተሰብ ብቻ የሚጐዳ እና

ተስፋ የሚያስቆርጥ ሊመስል ይችላል፡፡ ይህ የሚመስለው

ግን ከላይ ከላይ ብቻ የታየ እና የታሰበ እንደሆነ ነው፡፡

መንግስት ሰሞኑን የሚወስዳቸውን ከልክ ያለፈ እርምጃዎች

የተኛውን ሴጣን አይቀሰቅስም ብሎ መናገር የሚችል እሱ፤

አንድም የታሪክ መጽሐፍ አያነብም፣ አንባቢ ከሆነም

አላስተዋለም፡፡ ምክንያቱም ትልቁን እውነት ማየት

አልቻለምና፤ ትልቁን ድፍረት ይደፍራል፡፡ ወይም ደግሞ

የነማነው ተው የሚለኝን ፀበል የጠጣና የተጠመቀ ይሆናል

ብለን ከማለፍ ውጭ ምን አማራጭ አለን?

አርጐት ነው!

ብዙዎች የኢትዮጵያ ፖለቲካ ተከታታይ የሆኑ፤

የማይዘነጉት ፖለቲካዊ ክስተት ከሁለት ዓመት በፊት

(በ2001 ዓ.ም፤ በሚያዚያ ወር መጨረሻ) ተፈጥሮ ነበር፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ

ሲሠራር እንደነበር መግለጹ ነበር ክስተቱ፡፡ ከዚህ ጋር

ተያይዞ የተጠረጠሩ ሰዎች የመያዛቸውን ዜና የዓለም

አቀፍ የመገናኛ ብዙሀን እየተቀባበሉ ዘግበውት ነበር፡

፡ ወዲያውም ግን ይህ የመገናኛ ብዙሀን ከፍተኛ ሽፋን

እና ለጉዳዩ የተሰጠው ትኩረት ያልጣመው መንግስት፤

የምንቃወመው ....

እየቀረቡ ነውና ማንም ሥልጣኑን የሚለው በግድ ከሆነ

ወደ ፍቅር መጥቶ በወቅቱ ለሥራው በጎ ነገር እንኳን

ምስጋና ማግኘት ይከብዳል፡፡ ይህም የሚሆነው ከተጣሉና

ከተቋሰሉ በኋላ መሞጋገስ ስለሌለ ነው፡፡ እውነቱን

ለመናገር በህዝብ ትግል የወረዱት ሦስቱም አፍሪካዊ

የዓረብ መንግሥታት ምንም ጥሩ ነገር አላደረጉም ማለት

አይደለም፡፡ ግን ሥልጣናቸውን የለቀቁበት መንገድ

መልካሙን ሥራቸውን ሽፍኖታል፡፡ ለነገሩ መንግሥቱ

ኃ/ማሪያምም ቢሆኑ መልካም ሥራ አልሠሩም ማለት

አይቻልም፡፡ ሆኖም የሰሯቸው መልካም ሥራዎችን

በ2.07 ብር ነበር የሚመነዘረው። አሁን አንድ ዶላር

በ17.5 ብር ይመነዘራል። በአሥራ ዘጠኝ አመት ውስጥ

800% ጨምሯል። የዶላር ዋጋ ወደፊት መጨመሩ

አይቀርም። እንበል በጥቂት አመታት ውስጥ አንድ

ዶላር ሃያ አምስት ብር ቢመነዘር፣ ለአንድ ሄክታር

መሬት፣ 1.2 ዶላር የሚከፈለው ዋጋ ያኔም በሃያ ብር

ስለሚታሰብ፣ የዶላር ዋጋው ሰማኒያ ሳንቲም ብቻ ነው

የሚሆነው።

ለኢትዮጵያውያን ውሉ በብር መሆኑ አያስደንቅም።

ነገር ግን ለውጭ አገር ዜጎች ውሉ በዶላር ከመሆኑ

ይልቅ በብር መሆኑ ከማስገረም አልፎ አሳዛኝ ነው።

በርግጥ ስምምነቱን የፈረሙ ባለስልጣናት ምን ያህል

የኢትዮጵያን ጥቅም እንዳላስቀደሙ ያሳያል።

የስምምነቶቹ ሰነዶች እንደሚገልጹት የፌደራል

መንግስቱ የሊዙን ዋጋ እንደገና ማሻሻል እንደሚችል

በግልጽ ያስቀምጣሉ። በመሆኑም የኢሕአዴግ

የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ቁጥር ስንት ነው? በዚህ ስብሰባ

ላይ ስንት ሰው ተገኘ? ውሳኔውን ለማስፈጸም አቅም

አላችሁ ወይ? ውሳኔው ፓርቲውን ለተጨማሪ ብጥብጥ

አይጋብዘውም ወይ? በማለት የጠየቅናቸው አቶ ማህተመ

በኩረ ሲመልሱ “አንድ ፓርቱ የሚመራው በደንብና

በፕሮግራም ነው፡፡ በዚሁ መሠረት መኢአድም መተዳደሪያ

ደንብ አለው፡፡ ደንቡም በቅርብ በተደረገው ማዕከላዊ ም/

ቤት ስብሰባ ተሻሽሎአል፡፡ የተሻሻለው ደንብ ሥልጣንና

ኃላፊነትን በአግባቡ ከፋፍሎአል፡፡ ሥራ አስፈጻሚው

እያንዳንዱ አመራር ተግባርና ኃላፊነቱ በግልጽ ተቀምጧል፡

፡ ግልጽነትንና ተጠያቂነትን ለይቶ አሳይቷል፡፡ ከዚህ

በፊት በፕሬዝደንቱ እጅ ብቻ የነበረውን ሥልጣን በደረጃ

ከፋፍሎአል፡፡ አሁን እየሠራን ያለነው በዚሁ ደንብ መሠረት

ነው፡፡ በዚህ መሠረት የፓርቲው ፕሬዝዳንት ጠቅላላ

ጉባኤው የሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ አልተወጡም፡፡

ሥራ አስፈጻሚውን በአግባቡ አስተባብረው መደበኛውን

ሳምንታዊ ስብሰባ ሊመሩ አልቻሉም፡፡ በየጊዜው በጽ/ቤት

እየተገኙ ሥራውን በአግባቡ መምራት ሲገባቸው አሉባልታ

እየተቀበሉ ለፓርቲው መከፋፈልና መዳከም መንስዔ እየሆኑ

በመገኘታቸው ዲያስፖራውን ድጋፍ ሰጪ ቻብተሮችን

በአግባቡ ማስተባበር ሲገባቸው ባለማድረጋቸው የፋይናንስ

ገቢና ወጪ በአግባቡ እንዲታወቅ አለማድረጋቸውና የገቢና

የወጪ ሰነድ መዝገብ አለመኖር የፓርቲውን የሦስት ዓመት

ወጪና ገቢ እንዲታወቅ ባለማድረጋቸው፡፡ ዲያስፓራው

ለጻፈው ደብዳቤ መልስ አለመስጠታቸውና ከስብሰባ

በመቅረታቸው፡፡ ጉዳያቸው በህግና ሥነ ሥርዓት ኮሚቴ

ታይቶ ለውሳኔ ለማዕከላዊ ም/ቤት እንዲቀርብ ሥራ

ማስተባበያውን በአቶ በረከት ስሞኦን አማካኝነት

ለመገናኛ ብዙሀን እንዲያቀርብ ተገዷል፡፡ የጉዳዩንም

የትኩረት አቅጣጫ ከመፈንቅለ መንግስት ሥራ ወደ

ማሴር ተለወጠ፡፡ እዚህ ጋ ነው ታዲያ `አክሮባቱ` ለምን

እንዳስፈለገ አይገባኝም፡፡ መዘዙንም ከወዲሁ መገመት

እንዳለበት ተገንዝቧል፡፡ ስለዚህም ጉዳዩን አለሳልሶ

የተፈለጉትን ሰዎች መያዝ የተሻለ እንደሆነ ጥቂት ዘግይቶ

ተገልጦለታል፡፡ በመዘግቱ ግን ዋጋ አልከፈለም ማለት

አላዋቂነት ይሆናል፡፡

በወቅቱ ታዲያ ከሚገርሙኝ ጥያቄ እና መልሶች እንዲሁም

መግለጫዎች አንዱ፤ የግንቦት ሰባት ንቅናቄ (አሁን አሸባሪ

የተባለው) መሪ የሆኑት ዶክተር ብርሀኑ ነጋ የሰጡት መልስ

ነበር፡፡ ስለ መፈንቅለ መንግስት ሴራው እና ተሞክሮ ከሆነ

የሳቸው ደርጅት እንዳልነበረበት ይሁን እንጂ ሆኖ ከሆነ

“አርጐት ነው!” የሚል አስገራሚ መልስ ሰጥተዋል፡፡

ልክ እንደመፈንቅለ መንግስት ዜና እና ያልተሰቡ መዘዞች

መወለድ ሁሉ፤ ከሰሞኑ ድርጊቶች መሰል ነገር አለመኖሩን

እና የትኛው ሴጣን አለመቀስቀሱን እንዲሁም በታሳሪዎቹ

ምክንያት የሚነቃቃው የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች

እንቅስቃሴ እና የግሉ ሚዲያ ዘርፍ ለጉዳዩ የሚሰጠው

ትኩረት ከፍ ማለት በተጨማሪም በነዚህ ምክንያት ሊፈጠሩ

ከገፅ 10 የዞረ

ከገፅ 4 የዞረ

ሥልጣን የለቀቁባቸው መንገዶችና በሥልጣን ላይ እያሉ

ሲሰሯቸው በነበሩት ኢ-ዴሞክራሲያዊ ሥራዎቻቸው

ተሽፍነው ሁል ጊዜ እንደአጥፊ ሲወቀሱ ይኖራሉ፡፡

ኢህአዴግ በዚህ ጊዜ ካልተማረ መቼም ይማራል

ብሎ መገመቱ አዳጋች ነው፡፡ ኢህአዴግ የሙባረክን ያህል

ሊገዛ ዛሬ ላይ 1ዐ ዓመት ብቻ የቀረው ሲሆን ጋዳፊንም

ቢሆን ሊደርስባቸው 21 ዓመት ብቻ ነው የቀረው

እናንተ የኢህአዴግ አባላት ዛሬ ላይ ቆማችሁ ሃሳባችሁን

የተቃወሙትን ሁሉ እናንተን እንደተቃወሙ በመቁጠር

ባለስልጣናት ይሄን ውል እንደገና ማሻሻል አለባቸው

እላለሁ።

ለውጭ አገር ዜጎች ከተሰጠው መሬት

የሚመረተው ምርት ሕዝባችንን አያበላም

ለውጭ ዜጎች ከተሰጡት 250,012 ካሬ ሜትር

ከሚሆነው መካከል 120,000 ሄክታር መሬት (ግማሹ)

ማለት ይቻላል ለሩዝ ምርት የተመደበ ነው።

እንደሚታወቀው ሕንዶችና ቻይናዎች ዋናው

ምግባቸው (ጤፋቸው) ሩዝ ነው። የኢትዮጵያን

መሬት ወስደው የሚያመርቱት ምርት በአገራችን ወዳሉ

ጉሊቶችና መርካቶዎች እንዲሄድ ታስቦ አይደለም።

ነገር ግን ምርቱ በቀጥታ፣ ኢትዮጵያውያን አንዷን

ጥሬ አፋቸው ሳያደርጉ፣ ወደ ሻንሃይና ቦምቤይ ነው

የሚያመራው። ኢትዮጵያውያን ካለባቸው የምግብ

እጥሮት፣ በላያቸው ላይ ከተጫነው የኑሮ ውድነት

አስፈጻሚው በአንድ ድምጽ ተወስኖአል፡፡ ማዕከላዊ ም/ቤቱም

በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጣርቶ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ እንዲሰጥበት

ተስማምተናል” ብለዋል፡፡ በመቀጠልም አቶ ማህተመ ሲገልጹ

የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ ተስፋዬ ታሪኩ የተጣለባችውን

ከፍተኛ የሥራ ኃላፊነት በብቃት፣ በታማኝነት በግልጽነት

ከመወጣት ይልቅ ያልተገባ መስመርን በመከተል የፓቲውን

ሥራ አስፈጻሚ በአሉባልታ በመከፋፈል፣ የተረከቡትን ዕቃ

ሸጠው እንዲያሳገቡ የተሰጣቸውን ገንዘብ ባለማስገባታቸው

ጉዳያቸው በህግና ሥነ ሥርዓት ኮሚቴ እንዲታዩ ሥራ

አስፈጻሚው መስከረም 6 ቀን 2004 ዓ.ም የተወሰነ ቢሆንም

ህግና ሥነ ሥርዓት ኮሚቴ ቀርበው ቃላቸውን ለመስጠት

ፍቃደኛ ባለመሆናቸውና ፓርቲው የገጠመውን ችግሮች ላይ

ሥራ አስፈጻሚው ተሰብስቦ ለመወያየትና ለመወሰን ስብሰባ

ሲጠራ በመቅርታቸው በጥቅሉ ዋና ፀሐፊው የፓርቲውን

ገንዘብ በማባከናቸው፣ የችሎታ ማነስ ደበማሳየታቸውና

አሉባልታ በማናፈስ አመራሩን ለመከፋፈል በመሞከራቸው

ከመስከረም 18 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ ታግደዋል፡፡” ሲሉ

ገልፀዋል፡፡ የሥራ አስፈጻሚው አባላት ስንት ናቸው ስንት

ተገኙ ለሚለው ሲመልሱ “የፓርው ሥራ አስፈጻሚ በደንቡ

መሠረት 19 ቢሆኑም ቀደም ሲል ማዕከላዊ ም/ቤቱ አቶ

ያዕቆብ ልኬ በማገዱ በሥራ ላይ ያለው 18 ነው፡፡ በዕለቱ

10 ሥራ አስፈጻሚዎች ተገኝተው በአንድ ድምጽ ወስነናል፡፡

ውሳኔውን ለምርጫ ቦርድ አሳውቀናል፡፡ ለማስፈጸም አቅም

አላችሁ ወይ ለሚለው እኛ አቅማችን የፓርቲው ደንብ ነው፡

፡ በደንቡ መሠረት እናስፈጽማለን ብለን እናምናለን ካሉ በኋላ

ፓርቲውን ለበለጠ መከፋፈል አያጋልጠውም ወይ ብለህ

ለጠየከኝ አይከፋፍለውም፡፡ ፓርቲው በታሪክ ለመጀመሪያ

ስለሚችሉ ሕዝባዊ ጥያቄዎች እና ቁጣዎች የመቀስቀስ

አዝማሚያ ሊፈጠር አይችልም ማለት ከባድ ነው፡፡

የቱኒዚያ መንግስት እና የመንግስትን ፖሊሲ አስፈፃሚ

አካላት ሙሐመድ ቡአዚዚን ለመፍጠር እና በፈጠሩት

ማዕበል አሁንም ይከብዳል፡፡ እዚህ ጋር የዶክተር ብርሀኑን

አባባል በድጋሚ እንድጠቅስ ይፈቀድልኝና መንግስት

ከላይ የጠቀስኩትን እያደረገ ካለ፤ `አርጐት ነው!` የሚል

ብዙ ሰው መኖሩን መጠራጠር ይቻል ይሆን?

የተዘጋው የመሐከሉ መንገድ

መንግስት በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚወደው እና

ሁሌም ሊሰማው የሚፈልገው ሙዚቃ “ማነው ተው

የሚለኝ ማነው?” የሚለውን ሆኗል፡፡ በዚህም ምክንያት

ማስተዋል የጐደላቸውን እርምጃዎች በሁሉም የህይወት

ዘርፍ ላይ እየወሰደ ይገኛል፡፡ በእርግጥ አሁንም ከነዚህ

አላስፈላጊ እርምጃዎች ጀርባ አንድ መልካም ሁኔታ

እናውጣ ከተባለ `በቅሎ ገመዷን ብትበጥስ …..` የሚለውን

ተረት ቀመስ አባባል ማስታወስ በቂ ነው፡፡

ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከአባላቶቻቸው እና አመራሮቻቸው

ከመታሰራቸው እና ሌሎች አቅምን ከሚፈታተኑ ሁኔታዎች

ጋር ተያይዞ አስቸጋሪ ጊዜን እያሳለፉ እንደሆነ ለሁሉም

ለእናንተ ብቻ እንዲበጅ አድርጋችሁ ባወጣችሁት የፀረ-

ሽብር ህጉ ሠላማዊ ታጋዮችን እያሰራችሁ መሄዱ ታጋዩን

እንጂ ትግሉን እንደማይጎዳው ታውቁት ዘንድ ተገቢ ነው፡፡

በእርግጥ ታጋይን በማሰርና በማዋከብ ትግል እንዳይዳከም

መንገር ልጅ ለእናቷ ምጥ አስተማረች እንደማለት ወይም

ለቀባሪ እንደማርዳት ይቆጠርብኛል፡፡ ምክንየቱም በ17

ዓመት ትግላችሁ ወቅት ታጋዮቻችሁ በደርግ መንግሥት

በመታሰራቸውና በመገደላቸው የእናንተ ትግል ሊቆም

እንዳልቻለ ስለምታውቁት፡፡ እናንተ ሀገሪቱን ከደርግ

ከተረከባችሁ በኋላ መሪ ሳትቀይሩ አሜሪካውያን ቢያንስ

ቀንበር የሚያላቅቅ አይደለም።

በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵጵያ ውስጥ አንድ ኪሎ ምስር

አምሳ ብር ነው የሚሸጠው። 1 ኪሎ የሸኖ ቂቤ 300

ብር ነው። አንድ እንቁላል 2 ብር ነው። ዘይት በአገሩ

የለም። ኢሕአዴግ በዚህ ምክንያት በየቀበሌው ማደል

እንደጀመረም ይነገራል። ሕዝባችን ግራ ገብቶታል።

ህዝባችን በችጋር ውስጥ ውስጡን እያለቀ ነው። የኑሮ

ውድነት እጅግ በጣም አስፈሪ ደረጃ ላይ ደርሷል።

ትላልቅ እርሻና የአባይ ውሃ

ለውጭ አገር ዜጎች በብዛት መሬት የተሰጠው

በቤኔሻንጉልና በጋምቤላ ክልሎች ነው። ኢሕአዴግ

ሊገነባው ያሰበውና አብዛኞቻችን በመርህ ደረጃ

የምንደግፈው የአባይ ግድብ፣ በቤኔሻንጉል እንዲገነባ

ነው፣ በማይታወቅ ሁኔታ የተወሰነው። በቤኔሻንጉልና

በጋምቤላ ለውጭ አገር ዜጎች የተሰጡትን ሰፋፊ

መሬቶችን (በተለይም ሩዝ የሚመረትበት) በመስኖ

7

ጊዜ በደንብ እንዲመራ ያደረገውን ግልጽነትንና ተጠያቂነትን

የፈጠረ ስለሆነ ድርጅቱን የበለጠ ያጠናክረዋል፡፡ ለበለጠ

ትግል ያነሳሳዋል” ሲሉ መልሰዋል፡፡

የመኢአድ ፕሬዝዳንት ኢንጅነር ኃይሉ ሻውል በሰጡን

መልስ “እየተከናወነ ያለው ሥራ ከፓርቲው ህገደንብ ውጪ

ነው፡፡ ስንት ኢትዮጵያዊያን የተሰውለትን ፓርቲ ለማፍረስ

እየሞከሩ ነው፡፡ ከግለሰቦቹ ጀርባ ፓርቲም ያለ ይመስለኛል፡

፡ በፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ ስም ከተሰበሰቡት ውስጥ አቶ

አሰፋ ሀብተወልድ ከአንድ ወር በፊት ድርጅቱን ለቅቄአለሁ

ብሎ ያመለከተ ነው፡፡ መልቀቁን አመልክቶ የወጣ ግለሰብ

በፓርቲው ስም ሊንቀሳቀስ አይችልም፡፡ አቶ ጌታቸው

ባያፈርስ ድርጅቱን ለቆ አንድነት ፓርቲ የገባ ነው፡፡ አባል

ሆኖ ተመዝግቦ ወራዊ ክፍያ የከፈለበት ደረሰኝ በእጃችን

ይገኛል አቶ ማህተመ በኩረ የፓርቲው አስተዳደርና ፋይናንስ

ካልተመደብኩ በማለት የፓርቲውን ማህተም አስረክብ ተብሎ

ቢታዘዝ እንቢተኛ ሆኖ በህገውጥ መንገድ የሚንቀሳቀስ ነው፡

፡ በቃለ ጉባኤው ውስጥ የፈረመች አንድ ሥራ አስፈፃሚ

ባልተረዳሁት ሁኔታ አዋክበው አስፈረሙኝ ብላ አመልክታለች

ስለዚህ ቃለ ጉባኤው ህገውጥ ነው፡፡ በየሆቴሉና በየአልባሌ

ቦታ እየተገናኙ የፈፀሙት አስነዋሪ ሥራ ነው ዋና ፀሐፊውን

የማገድ ሥልጣንም የላቸውም በህገወጥ አካሄድ አዲስ የአዲስ

አበባን ም/ቤት አቋቁመናል ብለዋል፡፡ ይህንን በመቃወም

በርካታ አባላት ፊርማ በማስባሰብ ላይ ናቸው፡፡ ድርጅቱን

ለማፍረስ ከውጪም ከአገር ውስጥ ገንዘብ እንሰጣችኃለን

እያሉ የሚያባቡላቸው እንዳሉ ተረድተናል፡፡ ግን ይህ ሁሉ

ሊሳካላቸው አይችልም፡፡ ድርጊታቸው ግን በእጅጉ የሚያሳዝን

ነው” በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ግልጽ እውነታ ነው፡፡ እንደውም አሁን ያለው አዝማሚያ

ሰላማዊ ትግሉን እና የዴሞክራሲያዊ ሽግግሩን ከመቼውም

ጊዜ በላይ ተስፋ የሚያስቆርጥ ሁኔታ ውስጥ ከቶታል፡፡

በነዚህ በሁለት አካላት መሐል ደግሞ ሕዝቡ አለ፡፡

አሁንም ከድህነት፣ ከርሀብ እና ከስደት አዙሪት መውጣት

የኢትዮጵያ ህዝብ እንዳልቻለ የሚነግሩንን ብዙ ምሳሌዎች

መጥቀስ የሚያቅተው ሰው እንደሌለ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

መንግስት `ማነው ተው የሚለኝ` ከሚል ቅኝት ወጥቶ፣

ተቃዋሚዎች ተጠናክረው ከመንግስት ጋር ለመወያየት

እና ለመደራደር ሲበቁ እና ወደ ውይይት፣ ምክክር እና

ድርድር ማድረግ መቻል የሚያስቀና ሥልጣኔያዊ አካሄድ

እንጂ ሰይጣናዊ ሊሆን እንደማይችል የጋራ መግባባት ላይ

መድረስ ያስፈልጋል፡፡

በተለይ መንግስት `ትከሻ መለካካትን` አቁሞ፤ የመሀከሉ

መንገድ ላይ መጥቶ ከሕዝቡ እና ከተቃዋሚ ፓርቲዎች

ጋር ለመስራት ተነሳሽነትን ሊወስድ ይገባል፡፡ አለዚያ

የሰሞኑ የመንግስት አቋም እና በኮሚኒስታዊ ስልት የተቃኙ

እርምጃዎች (የእስር እና የመፈክሩን ጋጋታ ልብ ይሏል)፤

የኮሚኒስት ሥርዓት አራማጆችን ውድቀት እና ድቀት

በራስ ላይ ከመጋበዝ እና በራስ ላይ ከማሟረት በተለየ

መልኩ እንዳለየው መገመት ይቻላል፡፡

ከአራት ጊዜ በላይ መሪ ቀይረዋል፡፡ እንደኔ እንደኔ እናንተ

በህይወት እያላችሁ ሀገሪቱን ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንግድ

የሥልጣን ሽግግር እንዲኖር ብታደርጉ መልካም ነበር፡፡

ያ ባይሆንና በተለያየ መንገድ ሥልጣን ብትለቁ ከእናንተ

ቀጥሎ ሥልጣን ላይ የሚንጠለጠለው አልወርድም ብሎ

ሙጭጭ ቢል የታሪክ ተወቃሹ እናንተ እንጂ አሁን

አልወርድም ያለው አይመስለኝም፡፡ ስለዚህ ይህ ፀኃፊም

ሃሳባችሁን እንጂ እናንተን አልተቃወመም፡፡ እና “አባት ካለ

አጊጥ ጀምበር ካለ ሩጥ” እንደተባለው ሁሉ ነገር በእጃችሁ

እንዳለ ብታስተካክሉት መልካም ነው፡፡ ቸር ያሰንብተን፡፡

ለማልማት ውሃ ያስፈልጋል። «በእነዚህ ትላልቅ

እርሻዎች ምክንያት የአባይን ውሃ በመስኖ ሊጠቀሙ

ይችላሉ፣ የምናገኘውም የውሃ መጠን ሊቀነስ ይችላል»

የሚል ትልቅ ስጋት ግብጾች እንዳላቸው እየሰማን

ነው።

ኢትዮጵያ ሕዝቧን ለመመገብ፣ ሕዝቧን ለማሳደግ

የአባይን ውሃ ለኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫና ለመስኖ

ስራ የመጠቀም ሙሉ መብት እንዳላት የተረጋገጠ

ነው። የአለም አቀፍ ሕግ አይከለክላትም። ነገር ግን

ከአባይ ወንዝ፣ ውቂያኖስ አልፈው የሚገኙ እንደ

ሕንድና እንደቻይና ያሉ አገሮች ግን የአረንጓዴ ቢጫ

ቀይ ቀለም ያለው ሽፋን ለብሰው፣ የአባይን ውሃ

የመጠቀም ምንም መብት የላቸውም። ሕንድንና

ቻያናን በተዘዋዋሪ መንገድ ለመጥቀም ሲባል ኢትዮጵያ

ከግብጽ ጋር ግብግብ የምትፈጥረበት ምንም ምክንያት

የለም።

www.andinet.org.et

8

www.andinet.org.et

መዝናኛ ከዝናሩ

ሥጦታ

ለአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ ማስታወሻ

ከሰሎሞን አድማሱ

ለሀገር ዘፈነ እያለ ሀገሬ

ኩራት ነበርና ሀገር በቀል ፍሬ፤

“መለያየት ሞት ነው” እያለ ዘፈነ

በመሞት ጥያቄ ለመሞት ወሰነ

ጠግበን ሳንጨርሰው ሲለየን ፈጠነ

ሁሉም ነገር በቃ እንደማይሆን ሆነ፡፡

ያ ዘንባባ ማር ዘንጣፋ ሸበላ

ጥላሁን ስንለው ሲሆን ነበር ጥላ

በሱ ተራ ጊዜ ጥላ አጣ ከለላ

ክፉ ሞት ስትወስደው ከጉያ ነጥላ

የዘፈኑ ንጉስ የዛ አርበኛ ገላ

ካፈር ተቀላቅሎ በምስጦች ተበላ

ለካ ሰው ግብዝ ነው ሞኝ ነው ተላላ

እሱን ሲያመው ጠፋን የማዳኛው መላ፡፡

ከልብ ለማይጠፋው ለቁንጮው ስመ-ጥር

ሁላችን ነበረን ፍፁም ልዩ ክብር

ጥሌ ስለሆነ ያገር ኩራት ፍቅር፤

ድምቀት ስለነበር የልብ ውስጥ አበባ

ስጦታ ይሁንና የወገንህ እንባ፤

ብንወድህ ነበረ ጥላሁነን ያልንህ

መጣላት ፈልገን መች ጥል አሁን አልንህ

ዶክተር የራስክን ነፍስ መልሳት እባክህ

ናና ዝፈንልን ትስማ እስትንፋስህ

በአንድ ላይ ነን ዛሬ አንተን ስንጠብቅህ

ከስተሀል ጠቁረሀል እስቲ ትታይ ወዝህ፡፡

ትዝታውን ትቶ እሱ አፈር ለበሰ

ብርቅዬው ድንቅየው ጥላሁን ገሠሠ፤

ውለታ ሳንከፍለው ስለሄደ ድንገት

ሀዘንና ደስታ ባንጎራጎረበት

ጥበብን በድምፁ ገልፆ ባሰማበት

በጥበቧ አዳራሽ አሁን ባለንበት

ቤተሰብ አድናቂው በተገናኘበት

በድምቀት ይከበር የጥልዬ ልደት፡፡

ምንም ሞት ቢነጥቀን ቢለየን በሥጋ

መቼም መቼም መቼም ጥሌ ነው ከኛ ጋ፤

ሁሉን የሚችለው አምላካችን ቸር ነው

ሞገስ ክብራችንን በገነት ያኑረው፡፡

በዚያ አንታለልም

ሙሉነሽ አበባየሁ

መንገዱን ለመስራት ግንብ ለመደርደር፣

ፋሽስቱ ጣሊያንም የሌለው ነው ወደር፡፡

በዚያ ሳንታለል አምስት ዓመት ታግለን፣

ፋሽስቱ ጣሊያንን አስወጣን አባረን፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የታየው ብልጥነት፣

አሮጌን አፋርሶ አንገትን ማስደፋት፣

የልማት ሲናገር መንገድና ፎቁን በቲቪ ማሣየት፡፡

አቅሙን ተረዳው በዚያ አንታለልም፣

አንተንም በማውረድ ወደኋላ አንልም

ሆዴ ባዶ ሆኖ መላወስ ካቃተኝ፣

የአስፋልቱ ስፋት አረምን ሊበጀኝ

መንፈሴ ታውሮ ሲንጣለል አስፋልቱ፤

ፎቆች ተደራርበው ቢሠሩ በብርቱ፣

ለእኔ የማይሆን ነው ለርሃብ ጥማቱ፡፡

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 23 2004 ዓ.ም.

“ጥሪ አይቀበልም” አዲስ ፊልም

ሊመረቅ ነው!

በሲኒማ ኢትዮጵያ የምሽት የሲኒማ ፕሮግራም ተጀመረ

በአዲስ አበባ ሲኒማ ቤቶች አስተዳደር

በተመልካች ስሜትና ፍላጐት በተመረጡ የአማርኛ

ፊልሞችን ከመስከረም 19 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ

ከምሽቱ 2፡30 ለተመልካች እያቀረበ መሆኑ ገለፀ፡፡

ቁጥሩ እየጨመረ የመጣውና የፊልም ስራ እንዲሁም

የወረፋ መጣበብን ለመቅረፍ ያግዛል ተብሎ የተዘረጋ

መሆኑን ዘወትር አርብ ምሽት “ያንቺው ሌባ”

ቅዳሜ በድጋሚ ቀረፃና በባለሙያዎች አስተያየት

ተስተካክሎ የቀረበው “መፈንቅለ ሴቶች” እሁድ

“መካኒኩ” ፊልሞች ለተከታታይ 2 ወራት የሙከራ

እና እንደሚታዩ የሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ያገኘው

መረጃ ያመለክታል፡፡ ከዚህ ቀደም ባልተለመደ

አሰራር ከፊልሙ ገቢው 60% ፐርሰንት የፊልሙን

ፕሮዲውሰሮች ቀሪ 40% ፐርሰንት ለሲኒማ ቤቶች

መሆኑን ለማወቅ ችለናል፡፡

ባህል፣ ፌስቲቫልና ባዛር ለዕይታ በቃ

የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ከቢ.ቴክ የማስታወቂያ

ስራ ድርጅት ጋር በመተባበር በአይነቱ ለየት ያለ

የባዛርና የባህል ፌስቲቫል መስከረም 19 ቀን 2004

ዓ.ም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ታዋቂ

ግለሰቦች አርቲስቶች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች

በተገኙበት በጥቁር አንብሣ በሚገኘው ድላችን

ሀውልት ሲከፈት ከ50 በላይ አገልግሎት ሰጭ

ተቋማት ተሣትፈዋል፡፡ በዚሁ ባዛርና ፌስቲቫል

ላይ የተለያዩ የሙዚቃ ዝግጅቶች የብሔር

ብሔረሰቦች ጭፈራዎች፣ የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕይ

ቀርበዋል ለተከታታይ ቀናት በቆየው ዝግጅት

ላይ በመዝጊያው ስነ-ስርዓት መስከረም 21 ቀን

2004 ዓ.ም ምሽት 1፡00 ሰዓት ጥሪ የተደረገላቸው

እንግዶች በሐርመኒ ኢንተርናሽናል ሆቴል የባህል

ፋሽን ትርዒት ቀርቧል፡፡ የዘንድሮው በአለም አቀፍ

ደረጃ የተከበረው የቱሪዝም ቀን ምክንያት በማድረግ

ቱሪዝም ያስተሣስራል በሚል መሪ ቃል እንደ

ተዘጋጀ አዘጋጆቹ ለዝግጅት ክፍላችን ገልፀዋል፡፡

ለአለም የምሳሌ ዶክመንተሪ የፊልምና የፎቶ

ኤግዚብሽን ተመረቀ

በእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤትና ወዛም

ኮሙኒኬሽን ኤንድ ቢዝነስ ኃ.የተ.የግ.ማህበር በጋራ

ማዘጋጃ የኢትዮጵያ ታሪክ የሚገልፅ ዶክመንተሪ

ፊልም በተለያዩ ከ6 በላይ ቋንቋዎች በአማርኛ፣

በእንግሊዘኛ፣ በአረብኛ፣ በፈረንሣይና በኦሮሚኛና

በትግረኛ ቋንቋዎች ተሰርተው ቀረቡ፡፡ መስከረም

በሚዲያ ሀውስ ፊልም ፕሮዳክሽን

በደራሲ ዮሊያን ተ/ማርያም በዳሬክተር

ሚሊዮን ስዩም የተሰራው “ጥሪ አይቀበልም”

የተሰኘ በአይነቱ ለየት ያለ አስቂኝ ልብ

አንጠልጣይ ፊልም የፊታችን እሁድ

መስከረም 28 ቀን 2004 ዓ.ም ሁሉም ሲኒማ

ቤቶች በአዲስ አበባ በሚገኙ ያስመርቃል፡፡

በሲኒማ ሴባስትፖል፣ በሲኒማ

ዮፍታሔ፣ በሲኒማ እምቢልታ፣ ሰበታ

ጂም ሲኒማ፣ በደ/ዘይት ህይወት ሲኒማ እና

በናዝሬት ምርምር ሲኒማ በ8፡00፣ በ10፡00

እና በ12፡00 ሰዓት ለህዝብ እይታ ይበቃል፡

፡ በልዩ ፕሮግራም በሲኒማ ዮፍታሔ በ8፡00

ሰዓት አርቲስቶች ታዋቂ ግለሰቦች ጋዜጠኞች

የኪነ-ጥበብ ወዳጆች በተገኙበት በደመቀ ስነ-

ስርዓት ይመረቃል፡፡ በዚህ ፊልም ላይ ታዋቂ

አርቲስቶች ተውነዋል፡፡ ተዋንያን መስፍን ኃ/

እየሱስ (ጠጆ)፣ ሰለሞን ገብሬ፣ ኤልሳቤት

ጌታቸው (ቀጮ)፣ ፈዮሪ ሀይሌ፣ ዳንኤል

ወንድወሰን ሚኪያስ ታምሬ እና ናርዶስ

በርሄ ሌሎችም ከ25 በላይ ወጣትና አንጋፋ

ተዋንያኖች ተውነውበታል፡፡ የፊልሙ

ርዝመት 1፡39 ደቂቃ ሲወስድ ፊልሙን ሰርቶ

ከማጠናቀቅ 1 ዓመት ከ6 ወር ጊዜ ሲወስድ

ከ450.000 /ከአራት መቶ አምሣ ሺህ ብር

በላይ ሲወስድ የፊልሙ ታሪክ በተለያዩ

ምክንያቶች ከስራ ገበታቸው የተፈናቀሉ

ወጣቶች በአቋራጭ ለመበልፀግ የሚያደርጉት

የሕይወት ውጣ ውረድን ያሳያል፡፡

21 ቀን በሚሊኒየም አዳራሽ የሃይማኖት አባቶች

ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣኖች ጥሪ የተደረገላቸው

እንግዶች ሲከፈት ለተከታይ ቀናቶች በሚቆየው

ኤግዚብሽን ታሪካዊ ቦታዎች በፎቶና በምስል የታገዘ

ስለ ሀይማኖቶች እንደተዘጋጀ በመክፈቻው ዕለት

ተገልፆል፡፡

የአደባባይ ምስጢሮች

ጋሻው

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.10

የተገላቢጦሽ

አበው ወደ አንድ ቁም ነገር ወዳለው ጉዳይ ለማምራት

ሲፈልጉ “ወግን ወግ ያንጋጋዋል” ይላሉ፡፡ እኔም የዘመኑ ክፋትና

ጭካኔ ጥላ አጥልቶብኝ እየገረመኝ በጥልቀት ስመለከት የበለጠ

ርቄ በሐሳብ እመሰጣለሁኝ፡፡ ብዙ ጊዜ የሚሆነው ሣይሆን

ሲቀርና የማይሆነው ሲሆን ሣይ ሁሉም ነገር የተገላቢጦሽ

ይሆንብኛል፡፡ በልጅነቴ በተወለድኩበት አካባቢ አዛውንቶች

የማይሆንና ያልጠበቁት ነገር ሲሆን ሲያዩ “የተገላቢጦሽ ! ይሉ

ነበር ሼህ ሙሄ” ሲሉ እሰማ ነበር፡፡ ሸህ ሙሄ በተረት መልክም

ይሁን በምሳሌዊ አነጋገር ብቻ በሆነ አጋጣሚ “ሸህ ሙሄ

እንዲህ ብለው ነበር” እየተባለ ይነገራል፡፡ አለቃ ገ/ሐና፣ ሁሴን

ጂብሪል እንዲህ ተናግረው ነበር፡፡ እየተባሉ እንደሚጠቀሱት

ማለት ነው፡፡ እኔም በትዝታ ልጓም ተስቤ ጊዜ ጎትቶ ወስዶ

እኔ ከነበርኩበት ዘመን አልፌ ከሸህ ሜሄ ዘሌ ዘመን በመግባት

በልጅነቴ እሳቸው ተናገሩት የሚባለው ተረት መሰል ቁምነገር

ትውስታ ውሰጥ ገባሁ፡፡

ሸህ ሙሄ ዘሌ የተባሉ አዛውንት ነበሩ፡፡ እኒህ አዛውንት

በረመዳን ፆም ከሚኖሩበት ራቅ ካለ አገር የቅርብ ዘመዳቸው

የሆነ ይሞትና ከዚያ ቀብር ውለው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ

“ምሳ አቆይኝ” ከተባለ ቦታ ይደርሳሉ፡፡

ምሳ አቆይኝ እንደ እንጨት የቆመ አቀበት ሲሆን ያንን

የገረረ አቀበት ለመውጣት ወገብን አጉብጦ ሰለሚለቅ ከታች

ከቆላው አገር ውለው ወደ ላይ የሚወጡ መንገደኞች ምሳ

አቆይኝ ሲደርሱ ከድካማቸው ጋር ርሃብም ሰለሚይዛቸው

“ምሳ- አቆይኝ!” ብለው የጥንት አባቶች ስም እንዳወጡለት

ይተረካል፡፡ እውነትም የምሳ አቆይኝ ጋራ ጉልበትን የሚፈትን

ነው፡፡ በተለይም በእድሜአቸው ለገፉ አዛውንቶች በቀላሉ

የሚወጡት አይደለም፡፡ ከምሳም አልፎ ራት አቆይኝ

የሚያስብል ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ምሳ አቆይኝ አካባቢ

መንደር የሚባል ስለሌለ ጥቅጥቅ ያለደን በመሆኑ ከመሸ

በኋላ ብቻን ያንን አቀበት ለመውጣት የሚታሰብ አይደለም፡

፡ ጅቦች በየጥጋጥጉ ጉሬቸውን ሠርተው ስላሉ ከመዘነጣጠል

አይመለሱም እየተባለ ይፈራል፡፡ በመሆኑም ሸህ ሙሄ ዘሌ

ከዘመዳቸው ልቅሶ ውለው የማታ ማታ ወደ በመንገድ የደከመ

ጉልበታቸው ከፆም ጋር ተዳምሮ ከስር ሆነው አንጋጠው ያንን

አቀበት ሲመለከቱት አሞታቸው ፍስስ ይላል፡፡

ሸህ ሙሄ ካንድ ዛፍ ስር አረፍ ብለው ያንን የገጠጠ

አቀበት እንዴት እንደሚወጡት ሲያምሰላስሉ አንድ ሐሳብ

ይመጣላቸዋል፡፡ አላህን አጥብቀው ቢማፀኑት ያንን እንደ

እንጨት የቆመ አቀበት አንከብክቦ የሚያ ወጣቸው ሰጋር

በቅሎ እንደሚሰጣቸው! ያምናሉ እናም “ለአላህ ምን

ይገደዋል!” ይሉና በርከክ ብለው፡-

“አላህ አምጣ ግራጫ ያቀበት መውጫ

ዋርዳ በቅሎ አምጣ ይህን አቀበት ይዞ

ሚወጣ! “በማለት በግንባራቸው እየተደፉና

እየተነሱ አላህን ይማፀኑ ጀመር፡፡

አንድ ገበሬ ደግሞ እህል ሸመታ ገበያ ውሎ ባህያውም

ጥርቅ አድርጎ ጭኖ እሱም የተወሰነውን በትከሻው ተሸክሞ

ሲጓዝ አህያውን ከልክ በላይ ጭኖት ስለነበር ይደክምበታል፡

፡ በዚህ ላይ ምሽቱ ይቃረባል፡፡ እንደምንም ያህያውን ቂጥ

እየገፋ፣ አንዳንድ ጊዜም በሽመል እየነረተ አንፏቆ ምሳ አቆይኝ

ይደርሳል፡፡ የምሽቱ ጥላ ጋራውንና የጋራውን ዙሪያ ጥላ

አጥልቶበታል፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ ጅቦች ከያደፈጡበት

ብቅ ብቅ ማለታቸው የማይቀር በመሆኑ እስከነ አህያው

ዝንጥልጥል እንደሚያደርጉት ያውቃል፡፡

“ፈጣሪ የ፤ ፈጥረህ እስከነ አህያዬ ለተራበ ጅብ አትስጠኝ!

ከጉድ አውጣኝ! ቢቻል ጌታ የሌለው ጠብደል አህያ፣ ካልሆነ

ደግሞ የምሳ አቆይኝን ዳገት የሚያወጣኝ አንድ ጠብደል

ጎራዳማን (ወጠምሻ) አምጣልኝ” በማለት እግዚአብሔርን

እየተማፀነ ያህያውን ቂጥ እየገፋ ሸህ ሙሄ ዘሌ ተንበርክከው

ከሚማፀኑበት ይደርሳል፡፡ አህያው በረጅሙ ተነፈሰና ሸህ

ሙሄን ከሽመልና ከጭነት ያድኑኝ የሚል ይመስል ቀጥ ብሎ

ይቆማል፡፡

ሸህ ሙሄ ከኋላቸው ኮቲ ሰምተው መለስ ብለው ሲያዩ

አንድ ሰው አህያ ጭኖ እሱምተሸክሞ ካጠገባቸው ቁሞ ያያሉ፡

፡ ከተንበረከኩበት ይነሱና፡-

“አላህ ሰጋር በቅሎ ስጠኝ ብልህ የተጫነ አህያ

ትሰጠኝ? እንግዲህ ያንተ ስጦታ ከሆነ እቀበላለሁ፤ ይህን

ወደ የዞሯል

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.10

የመጨረሻ ክፍል

ከብሩክ ከበደ

ኪነ ጥበብ

ሣምንት በሃገራችን ታሪክ ቀዳሚ የሚባለውን የፍቅር

ትያትር ስለደረሱት ብላታ ጌታዬ አስፋው የድርሰት ሕይወትና

በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት ስለተለየችው ድምፃዊት ክራር

ተጫዋችና ተዋናይ አስናቀች ወርቁ ለመጀመሪያ ጊዜ በሳዱላ

እድሜዋ በመሪ ገጸ ባሕርይ ስለተወነችው የ”ፍቅርጮራ”

በተመለከተ ያዘጋጀሁትን ማቅረቤ ይታወሳል፡፡ በዛሬው

ጽሑፌ ደግሞ ቀጣዩንንና የመጨረሻውን ክፍል

አስነብባችኋለሁ፡፡

ከዚያ በፊት ግን አቶ አበራ ይርጉ የተባሉ

የጋዜጣው ተከታታይ ሣምንት የወጣውን ጽሑፍ ካነበቡ

በኋላ “ . .. ከፕ/ ግርማ ወ/ጊዬርጊስና ብላታ ጌታዬ አስፋው

ተፈራ ጋር ሌላም ቀደምት በሕይወት የሚገኙ የደራስያን

ማሕበር አባል የነበሩ አሉ፡፡ ስማቸውም ንብረ ዕድ ኤርምያስ

ከበደ የሚባልና ኑሮዋቸውን አሜሪካ ሜሪላንድ ያደረጉ

ይገኙበታል . . .፡፡” ሲሉ ለሰጡን ጥቆማ ከልብ አመሰግናለሁ፡

ባይሆን ለአንዳንድ ወጪዎች መሸፈኛ በሚል ለዛውም

ምናልባት ታሪኩ የሚፃፍለት ግለሰብ ቤተሰቦች የገንዘብ

አቅሙ ካላቸው ይሰጣሉ እንጂ ለፃፍንበት ተብሎ እንዴት

ይጠየቃል፡፡? እንዲህ ከሆነማ ወደፊት የሀገርና ሕዝብን

ታሪክ ማን ሊጽፈው ነው? ሲሉ ሥጋታቸውን ያስቀምጣሉ፡

የክቡር ዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ ታሪክ ለመጻፍ የአማራ

ብ/ክ/ መንግሥት አንድ ሰሞን እንቅስቃሴ ጀምሮ ሥራው

ለደራስያን ማህበር ብቻ ለመስጠት ማሰቡ አግባብ

አይደለም፡፡ ታሪኩ የተዋጣለትና ምሉዕ እንዲሆን ማንኛውም

ግለሰብ፣ተማሪዎች፣ተመራማሪዎች ወ.ዘ.ተ ሁሉ ያላቸውን

እንዲያበረክቱ መደረግ ነው ያለበት፡፡ ታሪክ እጽፋለሁ

የሚለው ነው ወደ ታሪክ መሔድ ያለበት እንጂ ታሪክ ወደ

ፀሐፊው ሊሔድ አይችልም፡፡ አይገባውም፡፡ የሚል ጽኑ

አቋም ብላታ ጌታዬ አስፋው ተፈራ አላቸው፡፡

ታሪክ ፀሐፊ እንዴት ክፈሉኝ ብሎ ይጽፋል የሚለውን

የብላታ ጌታዬን አቋም “አሁን ዱሮ አይደለም! ” የሚሉ

አይጠፉምና ምን ይሉኛል? ስል ጠይቄያቸው የሚከተለውን

መልሰውልኛል፡፡ “. . . እዚህ ውስጥ ብዙም መግባት

አልፈልግም፡፡ በኛ ጊዜ ምሥጋና ግፋ ቢል መጽሐፉ መግቢያ

ብቻ ይሰፍር ነበር፡፡ የዛሬውን አላውቅም “አቦ” እኔም

ያ እየመሠለኝ አንዳንዴ እሣሣታለሁ መሰለኝ ወዳጄ!፡

፡ እኔ እኮ የደጃዝማች ግርማቸው ተ/ሃዋርያትን፣ብላታ

ህሩይ ወ/ሥላሴ፣ቀኝጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ፣ልዑል መኮንን

የመሣሠሉትን ታሪኮች ሁሉ ስጽፍ ገንዘብ ጠይቄ አይደለም፡

፡ ታሪክ ስለሆነ ለትውልድ መተላለፍ አለበት፡፡ አዲስ

ኪዳንን የፃፉት እኮ ይህን ያሸን ያህል ይከፈላችኋል ተብለው

አይደለም፡፡ የትውልድ አደራና ኃላፊነት ስላለባቸው እንጂ፡

የድምፃዊ ዶ/ር ጥላሁን ገሠሠ የሕይወት ታሪክ ጽሑፍን

በተመለከተ ካለኝ መረጃ በመነሣትም ይህን ማለት ፈለኩ፡፡

ድምፃዊ ዶ/ር ጥላሁን ገሠሠ በሕይወት በነበረበት ጊዜ ታሪኩን

ለማፃፍ ደራሲያን ማሕበርን አነጋግሮ ነበር፡፡ ማሕበሩም 147

ሺህ የኢት/ብር እንዲከፈለው ጠይቆ ስምምነቱ ተፈረመ፡፡

ዶ/ር ጥላሁን ገሠሠም መጽሐፉ እንዲወጣ ከነበረው ጉጉት

እ.ኤ.አ በ2001 ስፖንሰር አግኝቶ ክፍያውን ይፈጽማል፡፡

በመሃልም ዶ/ር ጥላሁን ገሠሠ የጓጓለት መጽሐፍ ሳይወጣ

ከዚህ ዓለም በሞት ይለያል፡፡ ታሪክና ፀሐፍትም ይለያያሉ፡

ባለቤቱ ወ/ሮ ሮማን በዙም የተጀመረውን ጉዳይ ያውቁ

ስለነበር ማሕበሩ መጽሐፉን ለሙት ዓመቱ እንዲያደርስ

ይጠይቃሉ፡፡ በጥያቄያቸው መሠረትም ውሉ እንደገና

በሳቸው ስም እንዲሆን ተደርጐ ተጨማሪ የተወሰነ

ገንዘብ ይከፍሉና ጽሑፉ መፃፍ ይጀመራል፡፡ አዲስ ውል

ተዋዋይዋም እባካችሁ እያሉ በማስጨነቅ ባሰቡት ቀን

መጽሐፉ እንዲደርስ ማህበሩን መወጠር ያዙ፡፡ ለመጽሐፉ

ሕትመት የተያዘለት የጊዜ ሠሌዳ በጣም ሲቃረብ ታሪኩን

ያውቃሉ የተባሉ ቃለ-ምልልስ ይደረግላቸው እንደነበር

ሲታወቅም በተባለው ቀን አይደርስ ይሆናል የሚል ሥጋትም

ፈጥሮ ነበር፡፡ ነገር ግን አንድ ሣምንት ሲቀረው “ሻማ ቡክ

አሣታሚ” በብርሃን ፍጥነት ሊባል በሚችል አድርሶታል፡፡

ከመጽሐፍ ሽያጭ ከሚገኘው ገቢ መሀል 1ዐ%

ለባለቤቱ 9ዐ% ወ/ሮ ሮማን ብዙ ለአሣታሚው በሰጡት

አካውንታቸው ባለቤታቸው በሕይወት በነበረበት ጊዜ

ሊያቋቁመው ላስበው የ “ስኳር ሕመምተኞች ማህበር” ገቢ

እንዲሆን ተወስኖ ነበር፡፡ መጽሐፉም ለመጀመሪያ ጊዜ 1ዐ

ሺህ ኮፒ ታተመ፡፡ አልቆም እንደገና የመጀመሪያውን ቁጥር

ያህል ታትሟል፡፡

የቲያትር ጮራዋ አስናቀች ወርቁ

የፍቅር ጮራን ብላታ ጌታዬ አስፋው ተፈራ በ1944

ዓ.ም ለመድረክ ሲያባቁት በጊዜው “you are always my

heart” ከሚባለው ምርጥና ተወዳጅ የእንግሊዘኛ ዘፈን

በመነሣት መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ይኸንን “አንቺ ሁል ጊዜ

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 23 2004 ዓ.ም.

ከ” ኮ”ና “ካ” የፈለቀች አርቲስት

“የፍቅር ጮራ” ደራሲ ማነው?

ብላታ ጌታዬ አስፋው

በልቤነሽ ምንም እንኳን ብንራራቅ” ወደ ሚለው አገርኛ

ግጥም የመጀመሪያውን ስንኝ ተንተርሰው በፃፉት ቲያትር

የዛን ጊዜ ሳዱላ የነበረችው አስናቀች ወርቁ በዋንኛነት

እንድትተውን አድርገዋታል፡፡ ይህ ባለ አምስት ገቢርና 1፡3ዐ

ሰዓት የሚፈጀው ተውኔት ዘመናዊ የፍቅር ቲያትር መሆኑን

የዘርፉ ባለሙያዎች ይስማሙበታል፡፡ የቲያትሩ አዘጋጅም

አቶ ተስፋዬ ተሰማ ነበሩ፡፡

አስናቀች ወርቁ ቲያትሩን ስትተውን የ14 አመት ልጅ

ነበረች፡፡ አዳነች የምትባለው የጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ

ባለቤትም በዚሁ ቲያትር ላይ ተካፍላለች፡፡ ዕድሜዋም 12

ነበር፡፡ ለአስናቀች ወርቁ የበለጠ ቆንጆ ነበረች፡፡ አዳነች

የአስናቀች የአክስቷ ልጅ ናት የሚሉት ደራሲው ሁለቱንም

አለሁ-አለሁ ከሚሉበት ውቤ በረሃ ክለብ ያመጣቸው

ተስፋዬ ተሰማ ነው፡፡ ውቤ በረሃ ከነበሩት ኪዮስኮች (በዚያን

ጊዜ መጠጥ ቤት ወይም ሴት ቤት ማለት እንደ ነውር ነበር

የሚቆጠረው) መሃል ያስናቀች ወርቁ የእናቷ እህት ኪዮስክ

ነበራቸው፡፡ ያመጣናትም ከዚያው ነው፡፡ እኔም ከጉለሌ

እየተመላለስኩ ነበር የማሰለጥናቸው ይላሉ፡፡

እንደገና እንዲሠራ በማዘጋጃ ቤት ተጠይቆ ሲሰራ ብላታ

ጌታዬ እንደ ታዛቢ ያለውን የትያትር ክፍል እንደተወኑና

ከእሳቸው ጋርም ጌታቸው ደባልቄ፣ማዕዛና መኮንን የሚባሉ

ለጊዜው የአባታቸውን ስም የዘነጓቸውን ጨምሮ ሌሎችም

እንደ ተሳተፉበትና የእሳቸውም ዕድሜ 21 እንደ ነበር

ይናገራሉ፡፡

ብላታ ጌታዬ በውቤ በረሃ ልዩ ትዝታ አላቸው፡፡

አካባቢውን የረገጠ ሆለ ለመርገጥ የሚነሣ ሁሉ የደስታና

ፍስሐ መለያ የሆነውን “ኮ” ና “ካ” በሚገባ ያውቀዋል፡፡

አውቆም ይተገብረዋል ይላሉ፡፡ በጊዜው መጠጥ ቤት (ሴት

ቤት )እንሂድ ማለት ከነውርነት አልፎም ተናጋሪውን ክፉኛ

ስለሚያስገምተው አማራጩና ቀላሉ መንገድ “ኮ” ና “ካ”

እንሂድ ማለት ብቻ ነበር፡፡

ስያሜው የተወሰደው አረንቻታ ሆነ አልኮል ነክ መለኪያ

የሚያነሣ ሁሉ ከጐኑ ያለውን ጠጪ የማያውቀው ቢሆን

እንኳን ለ “ጤናችን” ብሎ ማጋጨት እንደ ባሕልና ስርዓት

የሚቆጠር በመሆኑ ሁለቱ የሚጋጩት ቁሶች የሚፈጥሩት

ድምጽን በመውሰድ “ኮ” ና “ካ” የሚል ስያሜ ተሰጠው፡፡

1930 ዓ.ም መጨረሻዎቹ ጀምሮ “ኮ” ና “ካ” የማያውቅ

ከተሜኛ አለ ለማለት በጣም ያስቸግራል፡፡ እንዲያውም

የከተሜኛ መለያ ነበር የሚሉት ብላታ ጌታዬ አስፋው ክቡር

ዘበኛ ከነዩኒፎርሙና ጐፈሩ፣በሬዲዮ የምትሰማቸውና በክብረ

በአላት የምታያቸውን ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና ሲቪል

ባለሥልጣኖች ወደ እነዚህ ክበባት ሲገቡ ልትመለከታቸው

ትችላለህ፡፡

ውቤ በረሃ የሚገባ ሁሉ ለአልኮል መጠጥ ብቻ

አይደለም፡፡ የአቶ ተፈራ ሻረው የመጠጥ ኢንዱስትሪ

የሚያመርተው ዞማ (የፋንታ አይነት መጠጥ) ጨምሮም

እነ አረንቻታን ለመጠጣት ነው፡፡ አልኮልም ካስፈለገ እነ

መሎቲ ኮኛክ፣እናትና ልጅ (ኡዞ) አረቄ የጊዜው ተመራጭ

መጠጦች ነበሩ፡፡ በዋነኛነት ግን አዲስ አበቤው ወደ

ስፍራው የሚያመራው ውበትን አይቶ ለማድነቅና ለመንካት

ነው፡፡ ሴቶቹ በጣም የሚከበሩበት ጊዜ በመሆኑ በሥነ-

ስርዓት ለማግባባት ይሞከራል እንጂ መጐነታተል ሆነ

ፀያፍ ቃላቶችን መናገር እንደ ባለጌ የሚያስቆጥር ነው፡

፡ ተዋናይዋም ከዚህ የፍቅርና የውበት በረሃ ብቻ ሣይሆን

ቸበር ቻቻ መድረክ በመውጣት ወደ ጥበበ መግባቷ ተፈጥሮ

የራሷን እንጂ አርቴፊሺልና ጊዜያዊ ለሆነ ክስተት ቦታ

የማትሰጥ ለመሆኗ አስረጅ ነው፡፡

ፓን-አፍሪካኒዝም

9

ብላታ ጌታዬ አስፋው ተፈራ የትያትርና መጽሐፍ

ደራሲ ብቻ አልነበሩም፡፡ ጥሩ ዲፕሎማትም ነበሩ፡፡ በንጉሱ

ጊዜ ናይጄሪያ በሚገኘው ኤምባሲያችን ቻንስለር እስከ

መሆን ደርሰዋል፡፡ አምባሳደሩም ክቡር ከበደ አበበ ነበሩ፡

፡ ብላታ ጌታዬ ከዲፕሎማትነት ሙያቸው ውጭም በፓን-

አፍሪካኒዝም አቀንቃኝነታቸው ይታወቃሉ፡፡

ፓን-አፍሪካኒስት ለምታየው ጥቁር ቆዳ ክብርና

ነፃነት የሚቆረቆር፣ለንጣት የማይሰግድ በሰው ልጅ

እኩልነት የሚያምን ነው፡፡ አውስትራሊያዊ ከጀርመን

ጋር ከተጋባ ለዘረኞቹ ያው ፋልስ ነው፡፡ ለዚህ ነው

ፓን -አፍሪካኒስት ለአፍሪካውያኖች ብቻ ሣይሆን

ለኤሮፓዊው፣ለኤዢያዊው፣ለላቲናዊው ሁሉ ክብርና ነፃነት

የሚያጎናጽፍ ነው የምንለው፡፡ ከዚህ በመነሣት አንዳንዶቹ

እንደ ሃይማኖት ቢቆጥሩት አይፈረድባቸውም፡፡

እ.አ.አ 196ዐ ዓ.ም ሌጎስ ናይጄሪያ ላይ ከማንዴላ ጋር

ስንገናኝ ቡና እየጠጣን ስለ ነፃነትና ፓን-አፍሪካኒዝም ዙሪያ

ብዙ አውርተናል፡፡ ማንዴላ ናይጄሪያ የመጡት ቀ.ኃ.ሥ

ሌጐስ መግባታቸውን መንስዔ በማድረግ ነበር፡፡ በወቅቱ

ሌጎስ ልክ እንደ አዲስ አበባ የማይመጣ የነፃነት ታጋይ

አልነበረም የሚሉት ፓን-አፍሪካኒስቱ ሎንደን እንዳለሁም

ጃማይካውያኖች ባደረጉልኝ ግብዣ በተገኘሁበት ወቅት

ያገሬን ባንዲራ ከማልበሳቸውም በላይ ንጉሱን የማምለክ

ሥርዓት ሲከውኑ ስመለከት በጣም ነው የተደነቅኩት ይላሉ፡

ሰሜን አፍሪካውያኖች ፓን-አፍሪካኒዝምን ይደግፉ

ይሆን? ስል ጥርጣሬዬን አንስቼላቸው ነበር፡፡ ለዚህ ጥርጣሬ

ብላታ ጌታዬ አስፋው ተፈራ “ . . . እንደ እነ ሰር አቡበከር

ታፌዋ ባሌዋ ያሉ አንተ ጥቁር ነህ እኔ አረብ ነኝ ይሉ ነበር፡፡

ናይጄሪያ ብትሄድ ካኑ የሚባሉ የሰሜኑ ክፍል ሕዝብ ጥቁር

አረብ ነን ይላሉ፡፡ ይህም ዘሬን (ትውልዴን)ከፍ አደርጋለሁ

ከሚል የመጣ ከንቱ አመለካከት ነው፡፡ ሕዝቡንና ሃገሩን

ያልወደደው የሊቢያው አምባገነንም የአፍሪካ ጎሣ መሪዎችን

በየስብሰባ አዳራሹ እየሰበሰበ አንድ አፍሪካ ይለው

የነበረው ስብከት ከልቡ እንዳልሆነ የምታየው ነው፡፡ ፓን-

አፍሪካኒዝም የተረሳ ሃሳብ ነው የሚለው እሳቤም ፓን-

አፍሪካኒስት በአገሩ ጊዜያዊ ችግር የማይፈታና ችግር አይቶ

የሚጠነክር ነው፡፡ ለዚህም ያደረሰው አርቆ አሳቢነቱ ነው

በማለትም ጥንካሬውን ያጐሉለታል፡፡”

ብላታ ጌታዬ አስፋው በአህጉራቸው ዙሪያ በርካታ

ሥራዎችን አበርክተዋል፡፡ ናይጄሪያ እያሉ “African march

to unity” የተሰኘ ባ 25ዐ ገጽ መጽሐፈ በ1961 ዓ.ም እንዲሁም

በቅርቡ 400 ገጽ “Afirca past present and future

development” የሚባል ጽፈዋል፡፡ ሁለቱም መጽሐፎች

የተደረሱት በእንግሊዘኛ ቋንቋ ነው፡፡ በወታደራዊው

ሥርዓትም ርእሱ የአፍሪካ ኢኮኖሚ የሚልና 350 ገጽ

የያዘ 10,000 ኮፒ ቼምበር ማተሚያ ቤት በሕትመት እያለ

ድንገት የመጡት የደህንነት ሰዎች አይናቸው እያየ ቤንዚን

አርከፍክፈው ካቃጠሉት ድርጊት በላይ የሚቆጫቸው

አንድም ኮፒ በእጃቸው ላይ አለመቅረቱን ነው፡፡

የተረካቢ ያለህ

ብላታ ጌታዬ አስፋው ተፈራ ከመስከረም 20 ቀን እስከ

ጥቅምት 5 ቀን 1970 ዓ.ም ድረስ በተካሄደው የአፍሮ ኤዢያ

ደራስያን ማሕበር የተመሠረተበት 20ኛ ክብረ በአል ላይ

ከአቶ አሰፋ ገ/ማርያም ጋር በመሆን ተካፍለዋል፡፡ በዚሁ

በ20 ቀናት ቆይታቸው ያዩትን ሁሉ በግጥም መልክ አካተው

በቅርቡ ለንባብ እንደሚያበቁ እምነት አላቸው፡፡ግጥሙ

ከአዲስ አበባ እስከ ሞስኮና ከሞስኮ በኋላ ሰባት ሰዓት በፈጀ

የአይሮፕላን በረራ ተጉዘው ታሽኬንት ግዛት ደርሰው ያዩትን

ሁሉ የያዘ እንደሚሆን ይናገራሉ፡፡

ስለሶቪየት ስነ-ጽሑፍ ሲያነሱም ሶቪየቶች ከላይ ወደ

ታች ነው የጀመሩት፡፡ እንደምዕራባውያንና አሜሪካውያኖቹ

ከታች ወደ ላይ አይደለም፡፡ ይህ የሆነበትም በሁለተኛው

የዓለም ጦርነት ሁሉ ነገር ለሩስያኖቹ ስለ ተፋለሰባቸው

መሆኑን ይገልፃሉ፡፡

ደራሲው አንድ ቅር የሚያሰኛቸው ጉዳይ ሣይናገሩ

ማለፍ አይፈልጉም፡፡ የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ የኢትዮጵያ

ደራስያን ማሕበር ፕሬዝደንትን አግኝተዋቸው በእጃቸው

ላይ የሚገኙትን የራሳቸውንና የሌሎች አንጋፋ ጸሐፍትን

ሥራዎች ተረከቡኝ ቢሏቸው ደብዳቤ ፃፉልን ሲሉ

የሰጡዋቸው ምላሽን፡፡ አናምንህም ማለታቸው ይሆን?

ሲሉ እራሳቸውን መልሰው ይጠይቃሉ፡፡ ብላታ ጌታዬ

አስፋው ሌላው ቅሬታቸው የሚመነጨው ደግሞ አዲስ

አበባ የአፍሪካ መዲና በመሆኗ በፓን-አፍሪካ ዙሪያ የተፃፉ

መጻሕፍትና ሠነዶች ተረክባችሁኝ አንድ ቤተመጽሐፍት

ክፈቱ ስል ለሚመለከታቸው አቤት ብልም ምላሽ የሚሰጠኝ

አካል አላገኘሁም ይላሉ፡፡

ፈጣሪ ዕድሜ ካልነፈገኝ የፍቅር ጮራን ወደ መድረክ

እመልሰዋለሁ የሚሉት ደራሲ 14 መጽሐፍትን ለተደራስያን

ሲያበረክቱ 10 ሕትመትን የሚጠባበቁ ሥራ እንዳሏቸው

ይናገራሉ፡፡ እኝህ አንጋፋ የስነ-ጽሑፍ ሰው የ80 ዓመት

የእድሜ ባለ ፀጋ ናቸው፡፡

www.andinet.org.et

10

ኢ/ር ዘለቀ ረዲ

www.andinet.org.et

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 23 2004 ዓ.ም.

ወቅታዊ

የምንቃወመው አምባገነናዊነታችሁንና ኢ-ዴሞክራሲያዊ

አሠራራችሁን እንጂ እንናተን አይደለም

ይድረስ ለኢህአዴግ አባላት በሙሉ

በያላችሁበት

ለተከበረው ጤንነታችሁ እንደምን አላችሁ፡፡

በተጨማሪም እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ

እያልኩ ከመልካም ምኞቴ በመቀጠል ለመነሻ

አዶልፍ ፓርለሳክ ጽፎት ተጫነ ጆብሬ መኮንን

ከተረጎመው መጽሐፍ ገጽ 51 ላይ ያለውን ጽሁፍ

እንደመነሻ አድርጌ እጀምራለሁ፡፡ “በደብረ-

ታቦር አካባቢ የመስቀል በዓል የሚከበርበት ቦታ

አለ፡፡ በዚህ ቦታ በወቅቱ ከቀ/ኃ/ሥላሴ ከፍተኛ

ባለ ሥልጣን የነበሩት ልዑል ራስ ካሳ ባሉበት

የተሰበሰበው ህዝብ እየተነሳ ፉከራ ይፎክር

የነበረ ሲሆን በፉከራው ውስጥ በባለስልጣናት

የተበደሉት ፎካሪዎች የበደላቸውን ባለስልጣን

ስም እየጠሩ የበደሉአቸውን በደል እየጠቀሱ

ይፎክሩ ነበር፡፡ ሆኖም በደላቸውን ሲናገሩ በራስ

ካሳ የተበደለውም እንዲሁ የራስ ካሳን ስም እየጠራ

በደሉን እየጠቀሰ እየፎከረ ተናገረ፡፡ ሆኖም በራስ

ካሳ ችሎት ተበድሎም እንደሆነ የተበደሉትን ነገር

በአደባባይ መናገሪያው ብቸኛ ነውና ያለምንም

ፍርሃት እየፎከሩ ይናገሩ ነበር” በዚህም ምንም

እንዳልተባሉ መጽሐፉ ያትታል፡፡

እኔ ከዚህ ጽሁፍ መረዳት እንደቻልኩት እነዚያ

በወቅቱ የነበሩት ሰዎች ይቃወሙ የነበሩት በወቅቱ

የበሩትን ባለስልጣን ሳይሆን የባለስልጣኖቹን

ኢ-ፍትሓዊ አሰራር ነበር፡፡ በዚህም የነበሩት

ባለስልጣናት በወቅቱ እነርሱ በአሰራራቸው

ስለተወቀሱ በተናጋሪዎቹ ላይ እርምጃ መውሰድ

ተባባሪነታቸውን ከመቀነስ ውጭ ሌላ ጥቅም

እንደሌለው በመረዳት አሰራራቸውን እንጂ

እነሱን እንዳልተቃወሞቸው በማወቅ ሲተቿቸው

አብረዋቸው በርካታ መስዋእትነት እንደከፈሉ

ይታወቃል፡፡ ዛሬ በዚህ ጽሁፍ አሰራራችሁን እንጂ

እናንተን አልተቃወምንም በሚል ልጽፍ ያነሳሳኝ

ባለፈው እሁድ በ14/ዐ1/2ዐዐ4 ዓም መንግሥት

በሽብር ተግባር ጠርጥሬያቸዋለሁ ያላቸውን

እስረኞች (እነ አቶ አንዱዓለም አራጌንና እስክንድር

ነጋን) ለመጠየቅ የቀድሞ የኢፌዴሪ መንግሥት

ፕሬዚደንት ከነበሩት ከዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ጋር ወደ

ማዕከላዊ አቀናን፡፡ እዚያም ስንደርስ እንደሌሎቹ

ጠያቂዎች ሁሉ ተራችንን ጠብቀን ለመመዝገብ

ወደ መዝጋቢው ፖሊሲ አመራን፡፡ ሌሎቹ

ተመዝጋቢዎች ተመዝግበው ሲጨርሱ በእድሜም

ይሁን በትምህርት እንዲሁ በምንም ሁኔታ ዶ/ር

ነጋሶ ስለሚበልጡኝ በኢትዮጵያዊ ባህል እርሳቸውን

አስቀድሜ ከኋላ ቆሜ ተራዬን ጠበኩ፡፡ ነገሩ ግን

እንደጠበቅሁትና ከእኛ በፊት ሲመዘገቡ እንደነበሩት

ዓይነት ሳይሆን መዝጋቢው ፖሊስ ማንን

እንደሚፈልጉ ዶ/ሩን ሲጠይቃቸው አንዱዓለም

አራጌን እንደሚፈልጉ ሲናገሩ መዝጋቢዎቹ ፖሊሶች

በተሻለ ትህትና አንዱዓለምን ማግኘት ይቻላል

? ሲሉ አለቃውን ሲጠይቁት አለቃው በቁጣ

ማነው የጠየቀው? አይቻልም ! አይቻልም! ብሎ

መቆጣት ሲጀምር ዶ/ሩ ለምንድነው የማይቻለው?

አሉት፡፡ ሰውየው ግን አይቻልም! ብዬአለሁ

አይቻልም! አለ፡፡ እርሳቸውም ያልተቻለበትን

ምክንያት አስረዳን ሲሉት አላቅልዎትም አላቸው፡

፡ እንደያውም ዞር በል ከቁጣ ወደ ማመናጨቅና

አንተ ወደማለት ዝርጠጣ ገባ፡፡ አሁን አዘንኩ፡

፡ እርሳቸው ግን አሁን አለቃውን ንገረኝና

እጠይቀዋለሁ አሉት፡፡ እርሱ ግን እራስህ እወቀው

አላቸው፡፡ እንዴት ነው ነገሩ የታሰሩትን እስረኞች

መጠየቅ የማይቻልበትን ምክንያት በትእግስት

ማስረዳት እንዴት አይቻልም? በሀገራችን መለመድ

ያልተቻለ ነገር ሲደረግ ቀ/ኃ/ሥላሴን ሲያወርድ

ከፋም ለማም ለሀገራቸው ጥቂት ነገር እንኳን

ሳይሰሩ አልቀሩም፡፡ ቢያንስ የአፍሪካ ህብረት ጽ/

ቤት አ.አ እንዲሆን አድርገዋል፡፡ ግን አልተከበሩም፡

፡ ደርግም እንዲሁ፤ ዶ/ር ነጋሶም እንደዚህ

ሲመናጨቁ ሳይ ነገ በአሁኑ ሰዓት ከፋም ለማም

አምባገነንነቱ እንዳለ ሆኖ ያቅሙን ሲሰራ የነበረው

ኢህአዴግ ቢወርድ እንደዚህ ያለ ነገር ሊገጥመው

ነው ማለት ነው? ዶ/ር ነጋሶ ከጥቂት አመታት በፊት

መንገድ ተዘግቶላቸው የሚያልፉ ባለስልጣን ዛሬ

በሀገራቸው ፖሊስ የረባ መልስ አልተሰጣቸውም፡

፡ የታሰሩም ሰዎች ቢሆኑ እኔ እስከገባኝ ድረስ

የኢህአዴግን አሠራር እንጂ ኢህአዴግ በራሱ

ኢህአዴግ መሆኑን የተቃወሙ አልመሰለኝም፡

፡ ዶ/ር ነጋሶም ቢሆኑ እንደዚያው ነው፡፡ እኔ

በዚያን እለት ማዕከላዊ ያየሁት አስገራሚ ትእይንት

በእርግጥ መንግሥት እንደመንግሥት አዞት ነው

ለማት እቸገራለሁ፡፡ ምክንያቱም እንደዚህ አይነት

የወረደ እና አንድን ርዕሰ ብሔር ሆኖ አገልግሎ

የነበረን ሰው አመናጭቁ ወይም እነገሌን ሊጠይቅ

የመጣ ሰው በኢትዮጵያዊ ጨዋነት አታገልግሉ

የሚባል አይመስለኝምና ነው፡፡ ምክንያቱም ይህ

ዓይነቱ አሰራር ማንንም አይጠቅምም፡፡ መንግሥት

እንደመንግሥት አድርጎት ከሆነ ተጨማሪ የታሪክ

ስህተት እያስመዘገበ ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ የእኔ

ግምት ዶ/ር ነጋሶን ያላወቁዋቸው ስለመሰለኝ ዶ/ር

ነጋሶ መሆናቸውን ለማስረዳት ሞከርኩ፡፡ ነገሩ እኔ

እንዳሰብኩት ሳይሆን አውቃቸዋለሁ እንደዚያ

ማድረጋቸውን ስረዳ በእጅጉ አዘንኩ፡፡ እኔ በበኩሌ

ግምቱ ትክክልም ይሁን አይሁን እንግዲህ ይህንን

ያደረጉ ሰዎች በፍፁም ታዘው አይደለም የሚል

ግምት አለኝ፡፡ የአንድ ወይም የሁለትና ሦስት

መንግሥት አካል ትእዛዝም ቢሆን ከተራ የግለሰብ

አመለካከት አይለይም፡፡ ይህንን በማድረጋቸው

መንግሥት የሚወድላቸው ስለመሰላቸው ብቻ

ነው፡፡ አስተሳሰቤ ትክክል ከሆነ እና ታዘው ካልሆነ

በወቅቱ ይህን ያደረጉ ፖሊሶች ህገ መንግሥቱን

ጥሰው ሰብአዊ መብትን በመርገጣቸው ሊገሰጡ እና

ወደትክክለኛው የምርጫ ትራክ ይገቡ ዘንድ ተገቢ

ይመስለኛል፡፡ ከላይ የጠቀስኩት ፖሊስ ካደረጋቸው

ነገሮች ሁሉ በእጅጉ የገረመኝ ምግብ የሚሰጡ

ሰዎች ሁሉ ለማን እንደሚሰጥና ማን እንደላከ

ይጽፋሉ፡፡ እኔም የእኔን እና የዶ/ር ነጋሶን ስም እና

አንድ ሌላ ጠያቂ ላኪ ብዬ ተቀባይ አንዱዓለም

አራጌ ብዬ ጽፌ ይህንኑ ፖሊስ የትላድርገው፣ ብዬ

ጠየቅሁት፡፡ ወረቀቱን ከእጄ መንጭቆ በመውሰድ

የእኛን ስም ቀዶ ጣለው፤ የሌሎቹ ግን አልቀደደም፡

፡ መቅደድ ካስፈለገ እኛ ከወጣን በኋላ ቀዶ መጣል

እየተቻለ ይህንን ኢ-ዴሞክራሲያዊ አሰራሩን እኛ

እንድናይ ለምን አስፈለገ? ለእኔ እንዲህ ማድረጉ

መንግሥት ፈጽሞ ኢ-ዴሞክራሲያዊ ነው፡፡

እናንተም እምትኖሩት እንዲህ ባለ አገር ውስጥ ነው

የሚል መልእክት ከማስተላለፍ ውጭ ምን ጥቅም

አለው ? በእርግጥም ያስተላለፈው መልክት እኔ

ከላይ የተጠቀስኩት ነው፡፡ እንደኔ እንደኔ እንደነዚህ

አይነት ሰዎች ሰውን ተስፋ በማስቆረጥ ወደ አመጽ

እንዲሄድ መንገድ ጠራጊዎች ይመስሉኛል እና

ቢታዩ መልካም ነው፡፡ ደግሞም ህዝባችሁን

ታዳምጡ ዘንድ ግድ ነው፡፡ ህዝብን የማዳመጥ ነገር

የኢህዴግ ተፈጥሯዊ ባህሪ ባይሆንም ከጐረቤት

አገሮች በጐ በጐውን መኮረጅ ተገቢ ነው፡፡ በቅርቡ

የዛምቢያው ገዢ ፓርቲ በተቀናቃኙ ፓርቲ በ43%

ውጤት ሲሸነፍ ፍርዱን የሰጠው ህዝባቸው ነውና

ገዢው ፓርቲ “ህዝባችን ተናገረ እኛም አዳመጥነው”

ነው ያሉት፡፡ እናንተስ ህዝባችሁን የምታደምጡት

መቼ ይሆን?

በአሁኑ ሰዓት በእርግጥ እናንተ በርካታ

ሠላማዊ ታጋዮችን ሽብርተኞች እያላችሁ ለማሰር

እየተሯሯጣችሁ እንዳለ ግልጽ ነው፡፡ እነዚህ

የማዕከላዊ ፖሊስ አባላት ያደረጉት የዚህ

የኢህአዴግ ሀሳብ ትክክለኛ ቅጂ ይመስለኛል፡፡ ነገር

ግን አንድ ትንሽ ነገር እነግራችሁ ዘንድ አዕምሮዬ

ግድ አለኝ አሁን የተያያዛችሁት ነገር በእጅጉ

እንኳን ለእኛ ለተቃዋሚዎች ነገሩ እየተደረገብን

ላለው ይቅርና ለእናንተም ስራውን እየሰራችሁት

ላላችሁት ግር ሳይላችሁ የሚቀር አይመስለኝም፡፡

አንድ ሥርዓት እንደ ሥርዓት ምንም ነገር ያድርግ

በሰራው ሥራ ላይ ጥሩ ከሰራ ምስጋና ክፉ ከሰራ

ወቀሳ አይቀርለትም፡፡ ከላይ በመግቢያዬ ለመጥቀስ

እንደሞከርኩት፡፡ አሁን እናንተ እንደምታስቡት

የተለያየ በርካታ ሥራዎች ሰርታችሁ ለሀገሪቱ

እድገት ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረጋችሁ እንደሆነ

ይሰማችኋል፡፡ በእርግጥም ሥራ ፈጽሞ አልተሰራም

የሚል ጭፍን አመለካከት የለኝም፡፡ የሠራችሁት

ሥራ ግን መሥራት ሥላለባችሁ እንጂ የተለየ

ነገር ለማበርከት አይደለም፡፡ ማንም ቢሆን አንድ

ነገር ሲሰራ የሚሰራው ሥራ ለራሱ ትክክል እና

ጥሩ እንደሆነ እንደሚሰማው ሁሉ ለእናንተም

ይህ ስሜት ቢሰማችሁ አይደንቅም፡፡ አንድ ሰው

ደግሞ ለራሱ ትክክል ነው ብሎ የሚሰራው ሥራ

በተመልካች እና ሥራው በተሰራለት ሰው ዘንድ

ያለው ግምት የተሰራው ሥራ የታሰበውን ያህል

ግምት ላይሰጠው ይችላል፡፡ በዚህም ሥራችሁ

ትችት ሲቀርብላችሁ ትችቱን የተሰራው ሥራ ላይ

አድርጎ ነገሮች እንዲስተካከሉ ከማድረግ ይልቅ

ትችቱ በእናንተ ላይ እንደተሰነዘረ መቁጠራችሁ

ፈጽሞ ትክክል አይደለም፡፡ በእርግጥ የፌዴራል

ፖሊስ ባልደረባ ያደረገውም ነገር ከዚህ አመለካከት

የመነጨ ይመስለኛል፡፡

የትኛውም የዓለም ሀገር ቢሆን ትውልድ

በትውልድ ይተካ ዘንድ ግድ እንደሆነ ሁሉ

መንግሥትም በሌላ መንግሥት መተካቱ አይቀሬ

ነው፡፡ ይህ የመንግሥት የለውጥ ሂደት ግን

እንደወቅቱ መንግሥት ብስለት ይወስናል፡፡ በሳል

መንግሥት መለወጥ አይቀሬ እንደሆነ አውቆ

በሁኔታዎች ሁሉ ራሱን ለለውጥ ያዘጋጃል፡

፡ በዚህን ጊዜ ዝግጅቱ ስላለ ሠላማዊ የሥልጣን

ሽግግር ስለሚደረግ በትረ ሥልጣኑን ይዞት

የነበረውን መንግሥት በዓለም አቀፍ ህብረተሰብ

ዘንድ ተቀባይነትን ያስገኛል ታሪኩንም በወርቅ

ቀለም ያጽፋል፡፡ እንዲሁም ያስተዳድረው የነበረው

ህዝብ የሚፈልገውን በማግኘቱ ደስተኛ ይሆናል፡፡

ለውጥ አይመጣም ብላችሁ ከሆነ ተሳስታችኋል፡፡

ለውጥ ይመጣ ዘንድ ግድ ነው፡፡ ማንም ማንንም

ቁልፍ በሆነ ቦታ ቢያስቀምጥ ጊዜው ሲደርስ ለውጥ

የሚያመጣው ጊዜው ነውና ማንም ምንም ቦታ

ስለተቀመጠ የሚመጣውን ለውጥ ሊያስቀረው

አይችለም፡፡

አንዳንድ ጊዜ ሁኔታዎች በሠላማዊ መንገድ

እንዲለወጡ ካልተደረገ ትልቅ የታሪክ ስህተት

ይከሰትና ለተሰራው በጎ ነገር እንኳ ምስጋና ሊጠፋ

ይችላል፡፡ እናንተም ሁኔታዎችን ቶሎ አስተካክላችሁ

የጥላቻን ፖለቲካ እስካላጠፋችሁ ድረስ በዶ/ር

ነጋሶ የደረሰው በእኛ አይደርስም ብሎ ማሰቡ

ሞኝነት ነው፡፡ ለውጥ ትልቅ በሆነ ክስተት ወይም

ባልታሰበና ትንሽ በምትባል ነገር ሊመጣ ይችላል፡

፡ ለዚህ ደግሞ በዓረቡ ዓለም የተቀጣጠለው እሳት

የተለኮሰው በቱኒዚያ በደል ይደርስበት የነበረ አንድ

አትክልት ነጋዴ ነው፡፡ ማንም መሮት እመጨረሻው

ጥግ ድረስ ከደረሰ በኋላ መመለስ ፈጽሞ አይቻልም፡

፡ ገንፍሎ የወጣን ነገር እቋቋመዋለሁ ማለት እና

ወድቆ መንፈራገጥ አንድ ናቸው፡፡ ምክንያቱም

ከወደቁ በኋላ መንፈራገጥ መላላጥ ስለሆነ ነው፡

፡ አሁንም የሰላ ሂስ የሚሰጧችሁን ሰዎች ከማሰር

ብትቆጠቡ ጥሩ ነው፡፡ እነዚህ እናንተው ጋር ቁጭ

ብለው በዚሁ እናንተ በምትገዟት ሀገር ሆነው

የሚተቹትን ሰዎች ከማሰር ይልቅ መንከባከብ

የተሻለ ነበር፡፡ እነርሱ ለእናንተ እንደ አብሪ ጥይቶች

ናቸው፡፡ ምክንያቱም ያለባችሁን ችግር ያለፍርሃት

ስለሚነገሯችሁ እንድትስተካከሉ ስለሚረዷችሁ

ነው፡፡ ያም ቢሆን እነሱ ሃሳባችሁን እንጂ እናንተን

አልተቃወሙም፡፡ እናንተን የተቃወሟችሁ

መስሏችሁ ከሆነ ግምታችሁ ትክክል አይደለም፡፡

በተለያየ ጊዜ የቱኒዚያ ህዝብ በሀገሪቱ እየተሰራ

ያለው አሰራር ትክክል እንዳልሆነና የኑሮው

ሁኔታ በእጅጉ ተራርቆ ሀብታሞች ከመጠን ባለፈ

ሀብት ሲንደላቀቁ ድሆች ግን ከመጠን የወረደ

ድህነት ውስጥ ገብተው እንደነበር ለገዢው

መደብ ቢነገረውም ሊሰማ አልቻለም ነበር፡

፡ በመንበረ ሥልጣን ላይ የነበረው መንግሥት

ከመንበሩ ላይ ሆኖ ነገሮችን ማስተካከል እየቻለ

ባለማስተካከሉ ችግሩ ከተፈጠረ በኋላ የተጎዳውን

አንድ ግለስብ ለመጠየቅ ተራ ኪሊኒክ ሁለት ሦስት

ጊዜ መመላለሱ ከምንም ሊያድነው አልቻለም፡

፡ በዚያ በቱኒዚያ ህዝብ ተቃውሞ አምባገነን

መጣል እንደሚቻል ለዓለም ህዝብ አሳዩ፡፡

ይህንን ያዩ ግብፃዊያን በእነርሱም ሀገር ከሦስት

አስርት አመታት ያህል ሲገዛ የነበረውን አምባገነን

መሪያቸውን ከአደባባይ ወጥተው በመቀመጥ

ብቻ ይነካሉ የማይባል የነበሩትን ሆስኒ ሙባረክን

መንበረ ሥልጣን አነቃነቁት፡፡ ሆስኒ ሙባረክ ህዝቡ

ገንፍሎ ከወጣ በኋላ ራሴን ለምርጫ አዘጋጃለሁ

በማለት ሊያግባቡ ሞክረው ነበር፡፡ ህዝቡ ግን

መሪያቸው አለኝ በሚሉት ሚዲያዎቻቸውና ቃል

አቀባዮቻቸው በኩል የአንድ ወር እድሜ ይሰጠኝ፤

የግማሽ ወር ቢሉ ፍፁም ህዝቡ ሊሰማቸው

አልቻለም፡፡ መማፀኑም አልሆነላቸውም፡

፡ ለመጨረሻ ጊዜ ትእግስቱን ጨርሶ የወጣው

ህዝብ ለሙባረክ ሰኮንድ ይሰጣቸው ዘንድ ፍቃደኛ

አልነበረም፡፡ ምክንያቱም ህዝቡ ለሙባረክ

እያሰቡ ያስተዳድሩት ዘንድ ከ3ዐ ዓመት በላይ

ጊዜ ሰጥቷቸው ስላልተጠቀሙበት ሌላ ተጨማሪ

ጊዜ ሊሰጣቸው ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ በፈቃዳቸው

ያልለቀቁትን አምባገነኖች ያለፍቃድ ጎትቶ ማውረድ

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.10

እንደሚችል ሊቢያውያን ከግብፆች አሻግረው ያዩ

የነበሩት ሊቢያውያን አይነኬ የተባሉትን ጋዳፊን

ለመፈንገል መንበሩን ማነቃነቅ ጀመሩ፡፡ ጋዳፊ ግን

የሚነቃነቁ አይመስልም ምክንያቱም ጦሩም ይሁን

ሌሎች ቁልፍ ቦታዎች የተያዙት በልጆቻቸው

እና በዘመድ አዝማድ ስለነበር ከቦታቸው

የሚነቃነቁ ስላልመሰላቸው እንደ ጓድ መንግሥቱ

ኃይለማሪያም አንድ ሰውና አንድ ጥይት እስኪቀር

ድረስ ሥልጣናችንን ላለመልቀቅ እንታገላለን እንጂ

አንለቅም አሉ፡፡ ነገር ግን የተጋጩት ከህዝብ ጋር

ነውና በምንም መልኩ ህዝብን መቋቋም አልቻሉም፡

፡ በአንድ ወቅት አንድ ምሁር ህዝብ ማለት ምን

ማለት እንደሆነሲገልፁ ‹‹ ህዝብ ማለት ቢገድሉት

ቢገድሉት የማያልቅ ነው፡፡›› እንዳሉት ከህዝብ ጋር

በመጣላታቸው ህዝብን ማሸነፍ አልቻሉም፡፡ ያን

ጊዜ በቤተ መንግሥታቸው ቁጭ ብለው በህዝብ

ላይ የሚደነፉት ኮ/ል ጋዳፊ ሆዬ ዛሬ በአይጥ ጎሬ

ውስጥ ለዚያውም የት እንዳሉ በማይታወቅበት

ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ለጋዳፊም ቢሆን የሊቢያ

ህዝብ 41 ዓመት የማሰቢያ ጊዜ ሰጥቷቸው ነበር፡

፡ ነገር ግን አላሰቡበትም፡፡ እንዲያውም ልባቸውን

አደነደኑበት እንጂ፡፡ “እወቅ ያለው ባመቱ አትወቅ

ያለው በአርባ ዓመቱ አያውቅም” ይባል የለ፡፡

እኔ አሁንም ለእናንተ ለወገኖቼ የምናገረው ነገር

ቢኖር የኢትዮጵያ ህዝብ ለኢህአዴግም ቢሆን

2ዐ ዓመት የማሰቢያ ጊዜ ሰጥቶታል፡፡ ኢህአዴግ

እና እናንተም አባላቶቹ ከዓለም አቀፍ ወቅታዊ

ሁኔታ ተሞክሮ መማር ይገባችኋል ባይ ነኝ፡፡

ይህንን ስል ስልጣናችሁን ሃያ ዓመት ሞልቷችኋልና

ልቀቁ ሳይሆን ራሳችሁን ለዴሞክራሲያዊ ምርጫ

አዘጋጅታችሁ ታሪክ ሥሩ ባይ ነኝ፡፡ የታደለው

የዛምቢያ ህዝብ መሪዎቹ እንደሚያደምጡት ሁሉ

እናንተም እኛን ብታዳምጡን መልካም ነበር፡፡

እኔ አንዳንድ ሚዲያዎች ኢህአዴግን

የጠቀሙ እየመሰላቸው እየጎዱት ይመስለኛል፤

ጉዳትና ጥቅሙን ህዝቡ ያውቀዋል፡፡ መራብና

መጥገቡንም እንዲሁ የተራበን ሰው ጠግበሃል

ቢሉት ከመበሳጨት፤ መንግሥትን ከማማረር

ውጭ ጠግበሀል ስለተባለ ላይጠግብ ነገር

የበለጠ ረሀቡን መቀስቀስ ይሆናል፡፡ የለየለት

እብድ የሚባለው ለቅሶ ቤት የሚዘፍን፤ ሰርግ

ቤት የሚያለቅስ ነው ይባላል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ

ኢህአዴግ እንዲያስብበት ያለውን ችግር ፍንትው

አድርጎ መንገር ከጋዜጠኛ ይጠበቃል፡፡ እናንተ

አንዳንድ የግል የህትመትና የግል የኤሌክትሮኒክስ

ሚዲያዎች ነን እያላችሁ ልትሰሩ የምትሞክሩት

የፓርቲውን ልሳን ወክላችሁ ነው፡፡ ፓርቲው

የራሱ ልሳን በሁለቱም ዘርፎች ስላሉት ይበቃዋል

ባይ ነኝ፡፡ ኢህአዴግም የህትመትም ይሁን

የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎችን በተለይ በአሁን

ሰዓት ወደ ኢህአዴግ ልሳንነት እየተቀየሩ ያሉትን

በወጉ አይቶ እረፉ ቢላቸው መልካም ነው፡፡

ያለበለዚያ እንደዚህ አይነቶቹ ሚዲያዎች እውነቱን

ስለማይነገሩ ኢህአዴግን ከህዝብ ጋር ያጣሉታል፡

፡ ምክንያቱም ኢህአዴግ ያልተሰራውን ሰርቷል፡፡

ህዝብ ደግፎታል፡፡ ኢህአዴግን ህዝብ ወዶታል፡፡

በየቦታው ፍትሃዊ ሥራዎች እየሰራ ነው የሚሉ እና

ኢህአዴግ ራሱን እንዳይፈትሽ የሚያደርጉ በርካታ

ካድሬዎች ስላሉት የእናንተ ተጨማሪ ድጋፍ

የሚያሰፈልገው አይመስለኝም፡፡ እኛ ተቃዋሚዎች

ብንሆን የምንቃወመውና እየተቃወምን ያለነው

ኢ-ዴሞክራሲያዊ አሰራራችሁን እንጂ እናንተን

አይደለምና እኛን ነው የተቃወሙን ከሚል ጭፍን

አመለካከት ወጥታችሁ ዴሞክራሲያዊ ብትሆኑ

የበለጠ ተጠቃሚ ትሆናላችሁ፡፡ የአሜሪካው

ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ከአፍሪካ መጀመሪያ

የጐበኙት ጋናን ነው፡፡ በኦሮምኛ ምሳሌያዊ

አነጋገር “ጥንቅሽን በቅጠሉ የማያውቅ፤ ነገር

በአይን አይገባውም” ይባላል፡፡ ነገር አንዳንድ

ጊዜ በምልክትም ይገለፃል፡፡ የአሜሪካው

ፕሬዘዳንት የጐበኙአቸውን የአፍሪካ ሀገራት ስናይ

ዴሞክራሲያዊ የሆኑትን ብቻ ነው፡፡ ዲሞክራሲያዊ

ያልሆኑት አልተጐበኙም ለመጐበኘት ዲሞክራሲያዊ

መሆን ያስፈልጋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት በግድ ተጎትቶ ከመውረድ

ሥልጣንን በገዛፍቃድ በምርጫ መልቀቅ

የበለጠ አስተዋይነት ነው፡፡ ምክንያቱም በግድ

ሥልጣናቸውን የለቀቁ ሁሉ በአሁኑ ወቀት

በህዝባቸው ክስ እየተመሰረተባቸው ፍርድ ቤት

ወደ 7 የዞሯል

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.10

ብሩክ ከበደ

ዜና

ባለፈው ዕሮብ መስከረም 17 ቀን 2004 ዓ.ም

ረፋዱ ላይ ለሁለት ዓመት ብዛታቸው ስድስት ሺህ

የሚደርስ የድምጽ፣ ውዝዋዜና ዘመናዊ ዳንስ ውድድር

ተወዳዳሪዎች የተካፈሉበት የኢትዮጵያ አይዶል

አሸናፊዎቹን በመሸለምና የውጪ የትምህርት ዕድል

በማስገኘት ሲጠናቀቅ ዕለቱንም ለድምፃዊ ዶ/ር ጥላሁን

ገሠሠ የትውልድ ቀን መታሰቢያ ሰይሞታል፡፡

በውድድሩ ዕለትም የየዘርፉ ተወዳዳሪዎች

እናሸንፍበታለን ያሉትን ሥራዎቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን

በዘመናዊ ዳንስ እጅግ መሳጭና ኢትዮጵያዊ እውነቶችን

ያካተተው ሀሁ የዳንስ ቡድን አሸናፊ በመሆን የ35 ሺህ

ብር አሸናፊ ሲሆን፣ ሁለተኛ የወጣው ፍቅር የዳንስ ቡድን

25 ሺህ ብር፣ ኤኬዌስትና አበሾቹ የዳንስ ቡድን በጥምረት

ሦስተኛነትን በመጋራት 20 ሺህ ብር ሲያገኙ 5ኛ የወጣው

ከሚሴ ቦይስ ዳንስ ግሩፕ 15 ሺህ ብር አግኝቷል፡፡ በዚህ

ውድድር 4ተኛ ደረጃን ያገኘ የለም፡፡

በዚሁ ዘመናዊ ዳንስ ውድድር በግል የቀረቡት

አስጨናቂ በቀለና ታምራት ገብሬ እያንዳንዳቸው የ3ሺህ

ብር ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ በባህል ውዝዋዜም አንደኛ

የወጣው ሬንጀርስ 35 ሺህ ብር ሁለትኛ የወጣው

ቻዴት የባህል ቡድን 25 ሺህ ብርና ወክለውት የመጡት

የኮምቦልቻ አስተዳደርና ሌሎች ሸላሚዎች 90 ሺህ

“በሽብርተኝነት ተጠርጥረው” የታሰሩ

እስረኞች በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ

አለማወቃቸውን ቤተሰቦቻቸው

ለዝግጅት ክፍላችን ገለጹ፡፡ እንደ

ቤተሰቦቻቸው ገለጻ ታሳሪዎቹ

ከታሠሩበት ቀን ጀምሮ ምግብ

ከማስገባትና ዕቃ ከመቀበል ባለፈ

ቤተሰቦቻችንን የሚገኙበትን ሁኔታ

ባለማወቃችን አሳስቦናል ሲለ ገልፀዋል፡፡

ቢመስልም (የታሣሪዎችን ልብ መስበር ያስችላል ተብሎ

ቢታሰብም) መዘዙ ብዙ ነው፡፡ በመጀመሪያ ነገር ገዥውን

ፓርቲ የዲሞከራሲ ፀር ተብሎ የሚያስተችና የሚያስወቅስ

ይሆናል፡፡ በመቀጠልም በታሪክም በህሊናም፣ በእምነትም

በህግም ከተጠያቂነት አያድንም፡፡ ጡንቻም እብሪትም ጊዜው

ሲደርስ ይከስማል፡፡

መፍትሄው ቁጭ ብሎ መነጋገር ነው፡፡ ሁላችንም

ኢትዮጵያዊ ነን፡፡ ያለችን አንድ ሀገር ናት፡፡ ሌላ የለንም፡

፡ በአንድ ሀገር የሚኖሩ ሰዎች የተለያየ ፍላጐት ሊኖራቸው

ይችላልና ልዩነትን በሠለጠነ መንገድ መፍታት አስፈላጊ ነው፡፡

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 23 2004 ዓ.ም.

አንድነት ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ ሊጠራ

እንደሆነ ተገለፀ

በድምሩ 115 ሺህ ብር ሲያገኙ ለሦስተኛው አፈንቃሉ 20

ሺህ ብር ጐልደንስቴትና እየሩሣሌም የ15 ና 10 ሺህ ብር

ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በድምፅ በተደረገው ፉክክርም ከከሚሴ የመጣው

ተመስገን አሸናፊ ሆኖ 60 ሺህ ብር ሁለተኛ የወጣው

ማስተዋል እያዩ 40 ሺህ ብር ሦስተኛ ሐሰን አርጋው 30

ሺህ ብር ከመሸላማቸውም በላይ ኢትዮቴሌኮም Nokia

71 ሞባይልና ላፕቶፕ ሸልሞአቸዋል፡፡ አራተኛ የወጣችው

ዮሐና በላይ 20 ሺህ ብር ስታገኝ ይድነቃቸው ገለታ 10

ሺህ ብር ተሸልሟል፡፡

በዚህ የድምፅ ውድድር ኦፔራዊስቷና ብቸኛዋ

አሸናፊና ልዩ ተሸላሚ የሆነችው የ11 ዓመቷ የሐረሯ ሐና

ግርማ 50 ሺህ ብር ተበርክቶላታል፡፡ ከዚህም ውጪ

ሠራዊት መልቲ ሚዲያ 11 ሺህ ብር የአንድ ሬሰቶራንት

ባለቤት 10 ሺህ ብር ሲያበርክቱላት አዲስ ቪው ሆቴል

ኦስትሪያ ቬይና ድረስ ሙሉ ወጪዋን ሸፍኖ በመላክ

በሞዛርት፤ በቤትሆቨን ኦሊያም በሌላ ታዋቂ የሙዚቃ

ት/ቤት ሊያስተምራት ቃል ገብቶላታል፡፡

የኢት/መድን ድርጅትም ኮሌጅ ስትገባ የ30 ሺህ

ብር የትምህርት ኢንዶውመንት ፖሊሲው ተጠቃሚ

እንድትሆን ፈቅዶላታል፡፡ በተጨማሪም ድርጅቱ

ለፍፃሜው ዕለት ለደረሱት ተወዳዳሪዎች በሙሉ ለአንድ

አመት የሚቆይ የመቶ ሺህ ብር የሞት እንዲሁም ለሁለት

አመት የሚቆይ የአካል ጉዳት ዋስትና ገብቶላቸዋል፡፡

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ /አንድነት/

ሁለተኛውን ጠቅላላ ጉባኤ ለመጥራት ቅድመ ዝግጅቱን

ያጠናቀቀ መሆኑ ለዝግጅት ክፍላችን ተገለፀ፡፡ ይህንን

የገለፁት የጠቅላላ ጉባኤው ጠሪ ኮሚቴና የአዲስ አበባ

አንድነት ም/ቤት ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር ንጋት አስፋው

ናቸው፡፡ ዶ/ር ንጋት እንደ ገለጹልን “የፓርቲው ብሔራዊ

ም/ቤት በሦስተኛው ሩብ ዓመት ባደረገው መደበኛ ስብሰባ

ሰባት አባላት ያሉት የጠቅላላ ጉባኤ ጠሪ ኮሚቴ ሰይሟል፡፡

ኃላፊነትና ተግባርም ሰጥቷል” ብለዋል፡፡

የተቋቋመውም ኮሚቴ ሥራውን እንዴት እንደ

ጀመረና ያከናወናቸውን አብይ ተግባራትም ዘርዝረዋል፡፡

“ኮሚቴው የራሱን ሰብሳቢና ፀሐፊ ከሰየመ በኋላ በቅድሚያ

የሚያከናውናቸውን ሥራዎች ስዕላዊ ቅርጽ ማስያዝ

ነበር፡፡ በዚሁ መሠረት የፓርቲውን ደንብና ፕሮግራም

የመፈተሽና የማሻሻል ሥራ፣እጩ ገባኤያተኞችን የመለየት

ሥራ፣የመስተንግዶ ኮሚቴ የመሰየም፣እንዲሁም የሕዝብ

ግንኙነትና የፋይናንስ ጉዳይ መሆናቸውን በመረዳት ሥራውን

ኢትዮጵያ አይዶል ተጠናቀቀ

- ሐና ግርማ አዲስ አበባ ወይስ ቬይና?

ከዚህም ውጪ ታዳጊዋ ሐና ግርማ የብሔራዊ ቲያትሩ

ዝግጅት ከመካሄዱ አንድ ቀን በፊት የአ/አ አስተዳደር

ቃሊቲ በሚገኘው ክራውን ሆቴል ባዘጋጀው የመስቀል

በዐል ልዩ ዝግጅት ተገኝታ ዝግጅቷን ባቀረበችበት

ወቅት የሆቴሉ ባለቤት ወ/ሮ ዘውዲቱ መስፍን ሙሉ

ወጪዋን ችለው ከሐረር በማስመጣት ለማስተማር ቃል

ገብተውለታል፡፡ ሐናም “ዕድሜና ጤና “ይስጥልኝ ስትል

በልጅ አንደበቷ መርቃቸዋለች፡፡ “አዲስ አበባ” የሚለውን

የተስፋዬ ገብሬን ሙዚቃ ከነፉጨቱ በመጫወትም

ከታዳሚው ከፍተኛ አድናቆትን አትርፋለች፡፡

በህዝብ ዘርፍ ተወዳዳሪዎችም ሽልማቱን ያቀረበው

ዩኔስኮ ሲሆን በባህላዊ ውዝዋዜ መቅደላዊት ደምሴ 4

ሺህ፣ ቅዱስ ዘውዱ ዘመናዊ ዳንስ 4 ሺህ ሐና ግርማ

በድምጽ (ኦፔራ) 4ሺህ ብርና ለሦስቱም አሸናፊዎች ዴል

ላብቶፕ አበርክቶላቸዋል፡፡

ይኽ በእንዲህ እንዳለ በድምፅ ያሸነፈው ወጣት

ስሜቱን ለመግለጽ በህይወት የሌሉትን እናቱን

ለማስታወስ ገና ማንሣት ሲጀምር የመድረክ መሪው “በቃ

ተወው” በማለት ማይኩን መቀበሉና እንዲሁም አስሬ

ሰዓት አልቋል እያለ በማጣደፍና በማዋከብ የመጨረሻው

ሥነ- ሥርዓት ዝብርቅርቁ እንደወጣ በማድረግ “ሽልማቱ

የታለ” እስከማለት የደረሰበት ንግግር እጅግ አሣፋሪና

አፀያፊ ነው ሲሉ በዕለቱ የነበሩ ተመልካቶች ቅሬታቸውን

ገልፀዋል፡፡

በጥንቃቄ የሚከናወን ፡፡ መሆኑን ተገዝዝቧል፡፡ በዚሁ

መሠረት ኮሚቴው ሥራውን በአግባቡ በማከናወኑ ዝግጅቱን

እያጠናቀቀ ይገኛል”፡፡ ሲሉ ዶ/ር ንጋት አብራርተዋል፡፡

በመቀጠልም የኮሚቴውን የሥራ ክንውን ዶ/ር ንጋት

ሲያብራሩ “የፓርቲው ደንብና ፕሮግራም የመፈተሽ ሥራ

ግብ ተቀምጦለታል፡፡ በዚሁ መሠረት ዞኖችና የወረዳ አባላት

ሐሳብ እንዲሰጡበት ተደርጓል፡፡ በውጪ አገር በአማርኛ

በሚተላለፍ ሚዲያ ክንውናችንን ገልፀናል፡፡ በአገር ቤት

በሚገኙ ሚዲያዎች በጋዜጣ፣በሬዲዮና በቴሌቪዥን ለመግለጽ

ታቅዷል፡፡ ዲያስፖራው የፓርቲውን አንቅስቃሴ በቅርበት

አንዲከታተለው እየተደረገ ነው፡፡ የፓርቲው መዝሙር

በአዲስ መልክ እየተዘጋጀ ነው፡፡ የፓርቲው የሙዚቃ ባንድ

ይቋቋማል፡፡ በየወረዳውና በየዞኑ ነባርነታቸው፣የትምህርት

ደረጃቸውና ለምዳቸው እንዲሁም የትግል ተነሳሽነታቸው

ግምት ውስጥ ገብቶ የጉባኤ ተሳታፊዎች እየተዘጋጁ ናቸው፡፡

ጉባኤው ሕዳር መጨረሻና ታህሳስ መጀመሪያ ላይ የሆናል፡፡

” በማለት አብራርተዋል፡፡

11

በተጨማሪም ጧት ወደ አዳራሽ ለመግባት የነበረው

የሰዓት ርዝማኔና ያልተቀናጀ መስተንግዶ ፖሊስን

ለእርዳታ እስከ ማስጠራት ያደረሰ ሲሆን የመግቢያ

ካርዱም በየአቅጣጨው እንደልብ በመበተኑ ጥሪ

የተደረገላቸው አባት አርበኞችና የተለያዩ እንግዶች

በመቀመጫ ዕጦት ሲቸገሩ ተሰተውሏል፡፡ በቦታው

የነበሩ ታደሚዎች እንደሚሉት “ይህንን በመስለ ዝግጅት

ላይ ታዳሚን የማይመጥን መድረክ መሪ ማስቀመጥ

ያሳዝናል”፡፡ ሲሉ ተደምጧል፡፡

በሽልማት የገንዘብ መጠንም አንዳንድ ተወዳዳሪዎችና

ተመልካቾች ቅር የተሰኙ ሲሆን ለቅሬታውም በዋንኛነት

የተቀመጠው ትምህርታችንን ሣይቀር ለተስተጓጐለው

ውድድር የወጣው ወጪና ለሽልማት የተሰጠን ገንዘብ

የማይመጥን ነው የሚል ነበር፡፡

የአይዶሉ የመዝጊያ ሥነ-ሥርዓትም መታሰቢያነቱ

ለዶ/ር ጥላሁን ገሠሠ የተሰጠ በመሆኑ ልጁ ሔለን ጥላሁን

በቴዲ ማክ አቀናባሪነት የተዘጋጀውን የአባቷን ደህና

ሰንብች የሚለውን የዘፈን ግጥም “ደህና ሰንብት አበባዬ”

በሚል ቀይራው በክሊፕ ያዘጋጀችውን ሙዚቃ በስክሪን

ለተመልካቹ አሣይታለች፡፡

በመጨረሻም ኢትዮጵያ አይዶል በአሥራ አንድ

የክልል ከተሞች ከ6-80 አመት ዕድሜ ያላቸውን

ተወዳዳሪዎች አካቶ ላለፉት ሁለት አመታት ሲካሔድ

መቆየቱ የሚታወቅ ነው፡፡

“በሽብርተኝነት” ተጠርጥረው የታሰሩ በምን ሁኔታ እንዳሉ

ማወቅ አለመቻላቸውን ቤተሰቦቻቸው ገለጹ

የእስር ዘመቻው ...

በታሰሩት ሰዎች ዙሪያ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ

ፓርቲ /አንድነት/ ምን እያደረገ ነው በማለት የፓርቲውን

ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳን ጠይቀናቸው በሰጡን መልስ

“ስለ ጉዳዩ አሳሳቢነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ ጽፈን

መልሱን እየጠበቅን ነው፡፡ የአውሮፓ ህብረት ዲፕሎማቶች

በጉዳዩ ላይ ከጠ/ሚኒስትሩ ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን

ገልፀውልናል፡፡ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር

አምባሳደር ጥሩነህ ዜና የፓርቲው ደብዳቤ እንደደረሳቸው

ነግረውናል፡፡ በቅርቡም ከበርካታ የሥራ ባልደረቦቻቸው

ከገፅ 15 የዞረ

ሆኖም ግን ከእኛ የባቡር ሀዲድ ውጭ የሚጓዝ ሁሉ አሸባሪ ነው

ብሎ የክስ ዶሴ መምዘዝ ለሰሚው ግራ ነው፡፡ “ፍርድ አያውቅ

ዳኛ ተገን አያውቅ እረኛ” የሚለውን ተረትም ሊያስታውሰን

ይችላል፡፡ በቦርሳው ውስጥ ወረቀትና መፅሐፍ አጭቆ ዘወትር

ከቦታ ወደ ቦታ የሚንቀሳቀሰውን እስክንድር እና መሰሎቹን

በዚህ አደገኛ ወንጀል መክሰስና ለፍርድ ማቅረብ በእውነቱ

ቦግ እልም የሚለውን የነፃውን ፕሬስ ጨርሶ እንዳይጠፋ

መንግሥት ደጋግሞ ቢያስብ ይገባዋል፡፡ የዴሞክራሲ ፋና ወጊ

ማስረጃዎች “ንጉሱ ከስልጣን ከወረዱ ፀሐይ አትጠልቅም”

ይባል ነበር፡፡ የነፃው ፕሬስ ዛሬ ንጉሡ የሉም፡፡ ፀሐይ ግን

ጋር በቡድን በቡድን በመከፋፈል 11 የእስር ቤት ክፍሎችን

መጐብኘታቸውን፤ እሳቸው ያሉበት ቡድን ቀደም ብለው

ከታሠሩት ውስጥ ሦስቱን አግኘተው ማነጋገራቸውን

ገልፀውልናል፡፡ በዚህ በጉብኝታቸው ወቅት አቶ አንዱዓለም

አራጌን፣ አቶ ናትናኤል መኮንን፣ አቶ አሳምነው ብርሃኑ፣

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና ሌሎች የፓርቲ መሪዎችና ጋዜጠኞች

የሚገኙበት ሁኔታ አልታወቀም፡፡ እነዚህን ታሳሪዎች ሌሎች

የሥራ ባልደረቦቻቸው አግኝተዋቸው ከሆነ አጣርተው

እንደሚነግሯቸው ቃል ገብተውልናል” ብለዋል፡፡

ትጠልቃለች፤ መልሳ ትወጣለች፡፡ ደርጎችም ቢሆኑ በራሳቸው

ፕሮፓጋንዳ ናላችንን ሲያዞሩ ቆይተው የታሪክ ትቢያ ሆነው

ቀርተዋል፡፡ የዛሬዎቹ ቅምጥል ገዢዎቻችን ደግሞ እኛ ከሌለን

ቀሪዋ ኢትዮጵያ እንደ ዶሮ ሥጋ ትገነጣጠላለች፣ ልጆቿም

እርስ በርሳቸው ይጣላሉ (ይዋጋሉ) እያሉ ዘወትር ይነግሩናል፡

፡ እነሱን ከምንገምታቸው በስተቀር ይኸም አይሆንም፡፡

ኢትዮጵያ እኮ አፈጣጠሯ ልዩ እና ህብረ ብሔራዊ ሀገር

ናት፡፡ የዛሬዎቹም ሆኑ የትላንትናዎቹ አምባገነን ገዢዎቻችን

ጠፍጥፈው አልሰሯትም፡፡ ለማንኛውም የሚያዋጣው መንገድ

ሆደ ሰፊ በመሆን ወደ ብሄራዊ እርቅ መምጣት ይመስለኛል፡፡

በመቀጠልም ዶ/ር ነጋሶ ሲመልሱ “አምባሳደር ጥሩነህ

በጉብኝታቸው ወቅት እንደተረዳሁት የፀረ- ሽብርተኝነት

ህጉ ለፖሊሶች በሚሰጠው ሥልጣን የምርመራ ጊዜአቸውን

እስኪያጠናቅቁ ድረስ ከጠያቂ ጋር እዳይገናኙ የመከልከል

መብት እንዳላቸው መረዳታቸውን አስረድተውኛል፡፡ እስከ

ጥቅምት 2 ቀን 2004 ዓ.ም ምንም ማድረግ ካልተቻለ

በቀጠሮው ዕለት ፍ/ቤት ተገኝተን በጠበቆች አማካኝነት ህገ

መንግስታዊ መብታቸው እንዲከበርላቸው እንጠይቃለን”

በማለት ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል፡፡

ታሰሩ የተባሉትም ሰዎች በነፃ ፍርድ ቤት ጉዳያቸው መታየት

ይኖርበታል፡፡ ፍ/ቤቱ በስም ብቻ ሳይሆን በተግባር ነፃ ሊሆን

ይገባል፡፡ በችሎቱ ወንበር ላይ የተሰየሙት ዳኞች ለህሊናቸው

ምለው ለተቀበሉት ሞያ ለተረከቡት ችሎት ህግ ብቻ የተገዙ

ሊሆኑ ይገባል፡፡ ዳኝነታቸው በህዝብ እንዲታመኑ ሆነው ሊሰሩ

ይገባል፡፡ ዳኝነቱን በግልጽ ችሎት ማከናወን ይጠበቅባቸዋል፡

፡ “የአይንህ ቀለም አላማረኝም” በማለት ዘብጥያ መወርወር

ለኢትዮጵያ አይበጅም፡፡ እንደውም የኢትዮጵያን የፖለቲካ

አቅጣጫ ከድጡ ወደ ማጡ ሊዶለው ይችላል፡፡ ለማንኛውም

ቸር እንሠንብት አበቃሁ፡፡

www.andinet.org.et

12

www.andinet.org.et

በካይሮ የግብፅ ፖለቲካ መሪዎችና ደጋፊዎቻቸው

ወታደራዊው ገዥው መንግሥትና 13 ፖለቲካ

ፓርቲዎች እሁድ ዕለት በሁለቱም ወገን ውድቅ

ከተደረገው ስብሰባ በኋላ አዲስ ውጤት

የሚያስገኝ ውሳኔ አሳልፈዋል፡፡

ውጥረት የተሞላበት ቅዳሜ ረፋድ ላይ

ከተደረገው ስብሰባ በኋላ በሺዎች የሚቆጠሩ

ሰዎች በማዕከላዊ ካይሮ በሚገኘው ጣሂር

አደባባይ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል፡፡ ይህም

የሆነበት ምክንያት የሃገሪቱ የአደጋ እና መከላከያ

የኢትዮጵያ መንግሥት የፀረ-ሽብር ህጉን በመጠቀም ስድስት

ጋዜጠኞችን አስሯል ሲል በኒዮርክ የሚገኘው ዓለምአቀፍ

የጋዜጠኞች መብት ተማጋች (CPJ) አስታወቀ፡፡

ሁለት የስውድን ጋዜጠኞችን ማርቲን ሽብዬ እና

የካሜራ ባለሙያው ጆሃን ፐርሶን በፀረ-ሽብር ወንጀል ክስ

የተመሰረተባቸው ሲሆን እነኘህም ከሶማሌዋ ፑንት ላንድ

ሐምሌ ላይ ወደ ኢትዮጵያዋ ኦጋዴን ክልል አቋርጠው ሲገቡ

እንደ ሆነ ተገልጿል፡፡ ባለፉት ሁለት ሳምንታት የኢትዮጵያ

ፀጥታ ኃይሎች ሁለት ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች እስክንድር

ነጋ እና ስለሺ ሃጐስን በቁጥጥር ስር አውለዋቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ

መንግሥት ቃል አቀባይ ሽመልስ ከማል በበኩላቸው

ጋዜጠኞቹን “የሽብር ተግባር ሊፈፅሙ ሲል ነው የተያዙት”

በማለት የተነሳውን ቅሬታ አጣጥለዋል፡፡

በክረምት ወቅት ደግሞ መንግሥት በመተቸታቸው ጋዜጠኛ

ውብእሸት ታዬ እና ርዮት ዓለሙ ታስረው በማዕከላዊ

መቆያታቸውና እስከ 20 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት

ለማስቀጣት ክስ እንደተመሰረተባቸው ይታወሳል፡፡

ባለፉት አራት ወራት ብቻ በሽብር ሕግ ስም ታዋቂ ስድስት

ጋዜጠኞች በሀገሪቱ እንደታሰሩ የዓለም አቀፉ ጋዜጠኞች መብት

ተሟጋች የምስራቅ አፍሪካ አማካሪ ቶም ሮድስ ያስታወቁ ሲሆን

“ባለሥልጣኖቹ የታሰሩት ጋዜጠኞች ፈፅመውታል የተባለውን

አሳማኝ የወንጀል ማስረጃ ካለ ለሕዝቡ ይግለፁ አለበለዚያም

በአስቸኳይ ሊፈቱ ይገባል” ሲሉ በድርጅቱ ስም ጠይቀዋል፡

፡ አያይዘውም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋነኛ የነፃው ፕሬስ አፈና

የሚካሄድባት ሀገር ናት ሲሉ ቶም ሮድስ ጠቁመዋል፡፡

ተወዳጇ አዲስ ነገር ጋዜጣ ከተዘጋች ሁለት

ዓመት ሞላት፡፡ ከነፃው ፕሬስ ተርታና ከአዲስ

አበባ ጋዜጣ አዟሪዎች እጅ ብትጠፋም ከብዙዎች

መንፈስና ህሊና ውስጥ ግን አሁንም አለች፡፡

በርካታ አንባቢዎች ዕትሞቿን በሙሉ ጠርዘው

ከማስቀመጣቸውም በላይ፤ አልፎ አልፎ መልሠው

ያነቧታል፡፡ የጋዜጣዋ ህትመት የተቋረጠው

አዘጋጆቿ ከኢትዮጵያ በመሠደዳቸው እንደነበር

ይታወሣል፡፡

በወቅቱ የጋዜጣው አዘጋጆች አገር ጥለው

ለመሠደድ የወሰኑበትን ምክንያት ለተለያዩ

የዓለም አቀፍ ብዙሃን መገናኛዎች በተከታታይ

ገልፀው ነበር፡፡ ያቀርቡት የነበረውም ምክንያት

መንግስት የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁን በመጥቀስ

“በሽብርተኝነት” ሊከሣቸው እየተዘጋጀ መሆኑን

ከመንግስት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

አስተማማኝ መረጃ ስለደረሣቸው እንደነበር

ነግረውናል፡፡ በጊዜው አሳማኝ ምክንያት

ስለነበራቸው፤ መረጃውን ያቀበላቸውን ግለሰብ

ማንነት ሳይነግሩን አልፈው ነበር፡፡ ዛሬ ግን

ዊኪሊክስ ለተባለው የአሜሪካንን መረጃ ጐርጓሪ

ድርጅት ምስጋና ይግባውና የመረጃቸው ምንጭ

አርጋው አሽኔ መሆኑን አወቅን፡፡

በርካታ የአገራችን ጋዜጠኞች በቂ ትኩረት

የማይሰጡት የአካባቢ ጉዳይን ትኩረት ሰጥቶ

ይሰራ የነበረው ጋዜጠኛ አርጋው አሽኔ ዛሬ በስደት

ላይ ይገኛል፡፡ ለተለያዩ ዓለም አቀፍ ብዙሃን

መገናኛዎች ወደ ስደት የገባበትን ምክንያት የገለፀው

ጋዜጠኛው፤ የአዲስ ነገር ጋዜጠኞች “በሽብርተኝነት

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 23 2004 ዓ.ም.

ሰራዊት የያዘውን ሥልጣን በአስቸኳይ

ለፖለቲከኞቹ ማስረከብ አለበት በሚል ነበር፡፡

ከዚህ በተያያዘም በውይይቱም ላይ አነስተኛ

የሚባሉ የአብዮቱ አንቀሳቃሽ ሰዎች

እንዳልተሳተፉና አሁን ያለው ብቸኛው

አማራጭ ወደ ሽግግር መንግሥት አስተዳደር

መሄድ ነው ሲሉ እጩው ፕሬዝዳንት አብዱል

ምኒም አብዱል ፈታህ ተናግረዋል፡፡

የአዲሱ አል አድል ፓርቲ ተወካይ ሙስጠፋ

አል ናጋር በበኩላቸው “ስልጣን ላይ ያለው

የተባበሩት መንግሥታት ሚሽን በደቡብ

ሱዳን፣ብቃት ያላቸው የግል ኮንትራክተሮችን በደቡብ

ሱዳን ሪፕብሊክ ውስጥ ለሚያካሂደው የተባበሩት

መንግሥታት ቢሮዎች የግንባታ ሥራ ማካሄድ

ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዩጋንዳ፣ኬንያ፣ኢትዮጵያ እና

የኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፕብሊክ ዜግነት ያላቸው

ማመልከት ይችላሉ የሚል ማስታወቂያ አውጥቷል፡፡

የሚፈለጉትም ሙያተኞች የሚከተሉት ናቸው፡-

- ሱፕርቫይዘር/የፕሮጀክት ማናጀር

- ግንበኞች

- አናፂዎች

- የቧንቧ ሰራተኞች

- ኤሌክትሪሺያኖች

- የዕቃ ግምጃ ቤት ሠራተኞች

- የከባድ ማሽኖች ኦፕሬተሮች

- የከባድ ማሽኖች ቴክኒሺያኖችና ሙያና ልምዱ

ያላችሁ ዝርዝር ቅጹን በመሙላት በኢ-ሜይል

ወይም በድረጅቱ ፖስታ አድራሻ ማመልከቻቸሁን

ማቅረብ እንደሚችሉ አስታውቋል፡፡

አድራሻውም

E-mail:- unmiss-recruitment-iic @ un.org

ወይም

ዋና ፕርሶኔል ኦፊሰር

የተባበሩት መንግሥታት ደቡብ ሱዳን ተልዕኮ

ፓ.ሣ.ቁ 29

ጁባ 081111

ደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ እንዲያመለክቱ ጠይቋል፡

፡ የማመልከቻውን ቅፅ ከድርጅቱ በኢ.ሜይል

አድራሻ ጠይቆ ማግኘት አንደሚቻልና መጠይቆቹ

በእንግሊዘኛ መሞላት እንዳለባቸው ተጠቁሟል፡፡

ሊከሰሱ” መሆኑን ተጨባጭ ማስረጃ እንዳለው

አዲስ አበባ ከሚገኘው የአሜሪካን ኤምባሲ

ዲፕሎማቶች ጋር በመወያየቱ ነበር፡፡ ይሄን መረጃ

የተቀበሉት ዲፕሎማቶችም ዋሽንግተኝ ዲሲ

ለሚገኘው የአሜሪካን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

በኢንተርኔት ይልካሉ፡፡ መልዕክቱንም ዊኪሊክስ

ጐርጉሮ ያገኘዋል፤ ለህዝብም ይፋ ያደርገዋል፡፡

እዚህ ጋ የአሜሪካን ዲፕሎማቶች ግልፅ

ስህተት ሠርተዋል፡፡ ያገኙትን ይህን ትልቅ

መረጃ ማስተላለፍ ግዴታቸው ቢሆንም፤

የመረጃው ምንጭ አርጋው አሽኔ መሆኑን

ሳይገልፁ ማስተላለፍ ይችሉ ነበር፡፡ ምናልባት

ደህንነቱ የተረጋገጠ የመረጃ መለዋወጫ መስመር

እንዳላቸው በመተማመናቸውም ሊሆን ይችላል፡፡

ዊኪሊክስ ይመጣል ብሎ ማን ጠረጠረ? ጋዜጠኛ

አርጋው ከአገር ወጥቶ የተፈጠረበትን ጫና ነገረን

እንጂ፣ ሌሎች ግለሰቦችም በዊኪሊክስ መረጃ

ላይ በስም ተጠቅሰዋል፡፡ የደረሰባቸውን ወይም

እየደረሰባቸው ያለውን ጫና ገና ስላልነገሩን

ለማወቅ አልቻልንም፡፡ ለምሣሌ የአንድ

መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ባለቤትና መሪ የሆኑ

ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ በአገራችን ስለሚገኙት

የእስር ቤቶች ሁኔታ ለኤምባሲው ዲፕሎማቶች

የሠጡት መረጃ ከነስማቸው ተዘርዝሮ ይገኛል፡፡

የአርጋው አሽኔን መሠደድ ተከትሎ የዓለም አቀፍ

የጋዜጠኞች ተከራካሪ ቡድን (CPJ) ባወጣው

መግለጫ፤ አርጋው አሽኔ ዊኪሊክስ ይፋ ባደረገው

መረጃ ምክንያት የተሰደደ የመጀመሪያው ጋዜጠኛ

መሆኑን ገልፃóል፡፡

ወታደራዊው ኃይል በአስቸኳይ ሥልጣኑን

የሚያስረክብበትን ሂደት ተቃውሞ ላሰሙ

ከፍተኛ የፖለቲካ ፓርቲ ኮሚቴ አባላት

ውሳኔውን ማረጋገጥ ይኖርበታል” ብለዋል፡፡

የኤስ ሲ.ኤ.ኤፍ ፓርቲ አባላት ደግሞ

ወታደራዊው መንግሥት ከየካቲት ጀምሮ

ለሕዝብ የገባውን ቃል አላከበረም፡፡ አሁን ግን

በዚህ ሁለት ሳምንት ውስጥ የመጨረሻ ውሳኔ

ሊያሳውቀን ይገባል ሲሉ አስተያየታቸውን

ሰጥተዋል፡፡ ምክር ቤቱ ከብሔራዊ ዴሞክራሲ

የሁለት ቡድኖች ወግ

የአዲስ ነገር ጋዜጣ አዘጋጆች ከአገር

ከተሰደዱና ጋዜጣዋ ከአዲስ አበባ ጐዳናዎች

የጠፋች ሰሞን ለበርካታ ሰዎች የመነጋገሪያ ርዕስ

ነበረች፡፡ የጋዜጣዋ መዘጋት የማኪያቶ ላይ ጨዋታ

መክፈቻ ከመሆኑም ባሻገር፣ በአገር ውስጥም

በውጭም የሚገኙ የህትመት፣ የኤሌክትሮኒክስና

የድረ -ገጽ ብዙሃን መገናኛዎች ርዕስ ጉዳይ ነበር፡

፡ ከአገር ውጭ የነበሩት አዘጋጆች የአሜሪካን

ድምፅና የጀርመን ድምፅ በመሣሠሉ የሬዲዮ

ጣቢያዎች የተሰደዱበትን ምክንያት ይነግሩን ነበር፡

፡ መንግስት በበኩሉ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የነፃው

ፕሬስን ታሪካዊ ጉዞ የሚተነትን ዘጋቢ ፊልም፣

በስቱዲዮው የተደረገ የፓናል ውይይትና ክቡር

ጠቅላይ ሚንስትሩ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ

ላይም ጭምር ጉዳዩ መነሣቱን አስታውሳለሁ፡፡

የመንግስቱ ልሣን “አዲስ ዘመን” ጋዜጣ በበኩሉ

አዲስ ነገር ከመዘጋቷ ጥቂት ጊዜያት ቀደም ብሎ

“ማስፈራሪያ” የሚመስል ረጅም ፅሁፍ ማውጣቱ

ይታወሣል፡፡ ይህን ፅሁፍም አዲስ ነገር ጋዜጣ

አንድም ቃል ሣታስቀር ከማተሟም በላይ

ለፅሁፉም መልስ ሰጥታለች፡፡ ሁለቱም ፅሁፎች

በተለያዩ ቦታዎች ስለሚገኙ የበለጠ ማወቅ የፈለገ

አንባቢ ለማመሣከር ይችላል፡፡

ከላይ የጠቀስኳቸው የመንግሥት ድምፆች

በሙሉ ሲነግሩን የነበረው፤ አዘጋጆቹን የመክሰስም፣

የማዋከብም፣ የማሰርም…. ድርጊትም ሆነ እቅድ

በመንግስት በኩል እንዳልነበረ ነው፡፡ የአዘጋጆቹንም

የመንግስትን አስተያየቶችን ያዳመጥነው ዜጐች፣

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.10

ዓለም አቀፍ ዜና

የግብፅ ወታደራዊ መንግሥት ቃሉን አልጠበቀም ተባለ

“ኢትዮጵያ በፀረ-ሽብር ሕግ ስም

በመጠቀም ታዋቂ ጋዜጠኞችን

እያፈነች ነው” ሲፒጄ

በተስፋዬ ደጉ

በደቡብ ሱዳን የሥራ ማስታወቂያ ወጣ

ልብ ያለው ልብ ይበል!

ፓርቲ ካለው የሁለት ዓመት የፖለቲካ ተሞክሮ

ተነስተን ሕግን የተከተለ የሚቻለውን ጥናት

እናደርጋለን ሲል ቃል ገብቷል፡፡

የግብፅ ምክር ቤት ከፍተኛ አባለ ሳሚ አናን

በበኩላቸው፡፡ “የፓርቲ ተወካዮች ከዙህ በፊት

የነበረው የምርጫ ህግ ተቃዋሚዎች በነፃነት

እንዲንቀሳቀሱ የማይፈቅደው አንቀፅ መሻሻልና

መሻር የኖርበታል፡፡ ለዚህም የቀድሞ ፖርላማ

አባላት ድጋፍ ያስፈልጋል” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

UNITED NATIONS

United Nations Mission in South Sudan

UNMISS

International Individual Contractors (IIC)

Job Openings

The United Nations Mission in South Sudan (UNMISS) is seeking qualified

candidates to serve as International Individual Contractors to construct UN

accommodation and office blocks countrywide in the Republic of South Sudan.

Nationals from Uganda, Kenya, Ethiopia and the Democratic Republic of Congo

(DRC) with the experience and qualifications in the following occupational groups

are encouraged to apply:

Supervisors/Project Managers

Masons

Carpenters

Plumbers

Electricians

Storekeepers

Heavy Duty Equipment operators

HVAC Technicians

Eligible candidates should indicate their interest by submitting their details by

electronic mail or by hand through the attached Personal History form (P.11) form

quoting the specific occupational group they are applying for.

By email:

All applicants are encouraged to apply by e-mail and MUST include their private

e-mail address in the subject line to: unmiss-recruitment-iic@un.org

By Mail:

Chief Civilian Personnel Officer

United Nations Mission in South Sudan

P.O. Box 29

Juba 081111

Republic of South Sudan

እውነቱ ያለው የቱ ጋ እንደሆነ መለየት ቢያቅተን፤

እንደፍላጐታችንና እንደየእምነታችን ተቀብለን

ኖርን፡፡ አንዳንዶቻችንም ሁለቱንም ወገኖች

ማመን አቅቶን ጥርጣሬ ውስጥ ከረምን፡፡ አሁን ግን

እውነቱ ማን ጋ እንደነበር በዊኪሊክስ ምክንያትና

በአርጋው አሽኔ በኩል ለማወቅ ቻልን፡፡

የኢቲቪ የፓናል ውይይት

ይህ የፓናል ውይይት በጣቢያው ስቱዲዮ

ውስጥ የተደረገ ሲሆን፤ የግል ጋዜጣ ተወካዮች፣

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነት ትምህርት

ክፍል መምህራን፣ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች

ማኀበራት ተወካዮችና ሌሎች ተጋባዦችም

ተሳትፈውበታል፡፡ በዚህ የፓናል ውይይት ላይ

የአዲስ ነገር ጋዜጣ አዘጋጆች ከአገር የተሰደዱበት

ምክንያትም የውይይቱ አካል ነበር፡፡ በውይይቱ

ላይ ተሳትፈው ከነበሩት አብዛኛዎቹ ግለሰቦች

ያቀርቡት የነበረው አስተያየት አዘጋጆቹን የሚኮንን

ነበር፡፡ ይህ ብቻ አልነበረም፡፡ የአዲስ ነገር ጋዜጣ

አዘጋጆች የተሰደዱት በራሣቸው ምክንያት እንጂ፤

መንግስት ምንም ስራቸውን ሊያውክ የሚችል

ጫና እንደማይፈጥርባቸው እየተቀባበሉ ሲነግሩን

አመሹ፡፡

በዚያ ውይይት ሲሰነዘሩ ከነበሩት የአዘጋጆቹ

ስደት ምክንያት ተብለው ቀርበው ከነበሩት ሀሳቦች

መካከል ከማስታውሳቸው አንዳንዶቹን ለመጥቀስ

እሞክራለሁ፡፡ “ሽያጭ ቀንሶባቸው፤ ጋዜጣዋ

የመዘጋት አደጋ ስለገጠማት ነው፡፡”፤ “የሚፅፉበት

ሃሣብ ማምጣት ስላቃታቸው፣ ለዚህም ጋዜጣ

አዟሪዎችን እስከመጠየቅ ደርሰው ነበር፡፡”፣ “ውጭ

ወደ 14 የዞሯል

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.10

ሰለሞን ስዩም

era4st@yahoo.com

ወቅታዊ

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 23 2004 ዓ.ም.

በመስከረም 16 2004 ዓ.ም የወጣችው ፍኖተ

ነፃነት የዶ/ር አይሉ አርአያን “በቅርፅ ፌደራላዊ

በተግባር አሃዳዊ” የሚል ፅሑፍ ይዛ ወጣች፡

፡ ዶ/ር ሀይሉ እንደፈለጉትም ርዕሱ ሀሳብ

ማጫሩ ተሳክቶለት መስከረም 19,2004

ዓ.ም የወጣችው ፍትህ ጋዜጣ የአቶ ቡልቻ

ደመቅሳን” እኔም የምለው አለኝ” የሚል

ፅሑፍ ይዛ ወጣች፡፡ ታዲያ በኔ ላይም ሐሳብ

ጭራ ኑሮ “እኔም ስለ ኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም

የምለው አለኝ” እያልኩ ነው፡፡ ልክ እንደ ዶ/ር

ሀይሉ ሁሉ የኔም ፅሑፍ የውይይት መነሻ

እንጂ የነገሩ መጨረሻ ያለመሆኑን ከወዲህ

ልግለጥ፡፡

በኔ እምነት በኢትዮጵያ ያለው ሰርዓት

እውነተኛ ፌዴራሊዝም ነው አይደለም በሚል

ሀሳብ መሰናዘር ጉንጭ አልፋ ይመስለኛል፡

፡ በመሆኑም ህወሓት /ኢሕአዴግ እንዴት

ለአደባባይ ትችት ሳይጋለጥ የፌዴራል

መንግሥቱን አህዳዊ በማድረግ ጠቀለለ

ለሚለው መልስ ለመስጠት እሞክራለሁ፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም በተግባር አህዳዊ

እንደሆነ የተደረገው ህወሐት ከመጀመሪያው

የብሔር ሥርዓትን ሁን ብሎ በማበረታታቱ

ነው እላለሁ፡፡ ወይም የብሔር ቡድኖቹ

የህወሐት የራሱ እጅ ስራ ከመሆናቸው የተነሳ

በራስ መተማመን ፈፅሞ ማዳበር እንዳይችሉ

ሆነዋል፡፡

በመዳረሻ (end) እየተስማሙ ወደዚያው

በሚወስደው መንገድ (means)

ያለመስማማት የዴሞክራሲያዊና ሳይንሳዊ

አካሄድ ገፅታ ነው፡፡ የብሔር ነፃነትና እኩልነት

መረጋገጥ ድል ነው፡፡ ድል መሆኑ የሚቀረው

ግን ይህንኑ የሚያረጋግጥ እውነተኛ

መንገድ (በዚህ አጋጣሚ ፌዴራሊዝማችን)

በሌለበት፣ የፍትህ፣ ነፃነትና እኩልነት መዳረሻ

(end) መሆኑ ሲሰበክ ማየት ነው፡፡ “ለመሆኑ

ይህ እንዴት ሆነ?” ማለታችን አይቀሬ ነው፡

፡ የብሎርተኝነት አንደኛው ቲዎሪ (theory)

በልሂቃን ስልጣን የመቆጣጠር ትግል ውስጥ

ያለ አንደኛው ወሳኝ አንጓ (variable) ነው

ይላል፡፡ ማለት ኢትዮጵያ እየተከተለች

ያለችው ፌዴራሊዝም ለብሔር ግጭቶች

እና ለካድሬዎች የማያልፉ “የድል ስካር”

ምንጭ ሆኖ ያገለግላል፡፡ ይህ ያለምክንያት

የመጣ አይደለም፡፡ ከዚህ ሴራ ነዳፊ ውጭ

ያሉትን የብሔር ኢሊቶች በተጥሮአዊ በሆነ

መልኩ ከፌዴራል መንግሥቱ ጉዳይ ለማለቅ

የተነደፈ ነው፡፡

ይህን ሀቅ የሚያረጋግጡልን በኦህዮ ደይተን

ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህር የሆኑት ፕ/ር

መሳይ ከበደ ናቸው፡፡ እንደ ፕ/ር መሳይ

“የኢትዮጵያ ስርዓ ከአተገባበሩ ባሻገር

የብሔር ስርዓትን ለማበረታታት ሆንተብሎ

የተመሰረተ የመሆኑ እውነታ ነው፡፡” ይላሉ፡

፡ በምሳሌ ሲያስቀምጡም “እንደ ናይጄሪያ፣

ህንድ ወዘተ… የመሳሰሉት ሌሎች ሀገራት

የብሔር ፌዴራሊዝም ብሔራዊ አንድነትን

ከማጠናከር ይልቅ በሚጎዳ መልኩ የብሔር

ማንነትን ወደ ማጠናከር ያዘምማሉ፡፡”

ይላሉ፡፡

የህወሓት ማጠንጠኛ የአማራ ልሂቃንን

የበላይነት ማብቃት ነበር፡፡ ይህ እንዲሆን

ግን፣ ሀገሪቷ የጭቁን ብሔር ብሔረሰቦች

ማጎሪያ መሆኗን ማስረገጥ ነበረበት፡

ስለ ፌደራሊዝሙ እኔም የምለው አለኝ

፡ ህወሓት ያነሳውን አጀንዳ የሚደግፉ

ብሔር ተኮር ልሂቃኖች፣ በብሔራቸው ላይ

እየተደረገ ያለውን “ጭቆና” በመስበካቸው

ከህወሓት ጋር የጋራ ጥቅም ይኖራቸዋል፡

፡ ነገር ግን ተፎካካሪ በመሆን ከቀደምቱ

ህወሓት ጋር መሄድ አይችሉም፡፡ በዚህ

ጉዳይ ህወሓት የፍላጎታቸው እና ጥያቄያቸው

ቀለዒም ጭምር ነውና፡፡ በመጨረሻም

የክልል ልሂቃኖቹን ትኩረት “በራስ ገዝ (selfrule)

እና ክልላዊ አስተዳደር ቁጥጥር” ላይ

ስለሚያደርግ የፌዴራል መንግሥቱን ጉዳይ

ለቀደምቱ ህወሓት እንዲታው የሚያስገድድ

ተፈጥሮአዊ ሁኔታ ይፈጥራል፡፡

አቶ ቡልቻ እንደገለፁት ህገ መንግሥታዊ

መብቶችና በመሬት ላይ ያለው እውነታ

ተቃርኗዊ መሆናቸው እመን ነው፡፡ ይህ

የዶ/ር ሀይሉም ሀሳብ ነው፡፡ ፕ/ር መሳይ

የዚህን ችግር መንስኤ ሲገልጹ “በንድፈ ሀሳብ

እና በአተገባበር መካከል ስላለው ልዩነት

የተጠናቀረና ሁሉን ያካተተ ምልከታ መስጠት

የሚቻለው ብሔርተኝነት የመንግሥትን

ሥልጣን በልሂቅ ቡድኖች ከመቆጣጠር

ጋር ሲነፃፀር ለዴሞክራሲ የሚሰጠው ቦታ

ያነሰ መሆኑ በታመነ ጊዜብቻ ነው” ይላሉ፡

፡ በኔ እምነት ይህ እውነታ የህወሓትን

ፕራይሞርዲየሊስት (ብሔርተኝነት የራስን

ዕድል በራስ መወሰን አለበት የሚል) መሆን

የሚናገር ነው፡፡ ነገር ግን የፕራይሞርዲያስት

ተፈጥሮ አንድ ክፉ ተቃርኖ አለበት፤

“በትግበራና በንድፈ ሀሳብ መካከል ያለውን

ልዩነት ለማስረዳት ሙሉ በሙሉ ይሳነዋል፡

፡” የተቃርኖም ምንጭም የህወሓት

ፕራይሞርዲያሊስት መሆን ሆኖ ውሳኔዎቹ

ግን የጥቅም ድምር ውጤቶች እንጂ ህወሓት

የተመደበበት ፕራይሞርዲያሊዝም ያለመሆኑ

ነው፡፡ ምክንያቱም የፌዴራሊዝማችን

ውጤት ከህወሓት ፕራይሞርዲያሊዝምነት

የሚመነጭ ቢሆን ኑሮ የህወሓት “ድል”

የትግራይን መገንጠል አሊያም እውነተኛ

በዚህ ጭብጥ አገባብ ላይ እንዳልነው፣ የጋራ ጥቅም ያላቸው እና በራስ ገዝ እና ክልላዊ የመንግሥት የስልጣን

ቁጥጥር የተጠመዱ ልሂቃን፣ ወደ ፓርቲነት ሲመነዘሩ `የማዕከላዊ ስርዓት` መንስኤን ያሳያል፡፡ ማለትም

ባለው የፓርቲ ስርዓት “ኢህአዴግ [ማለት] ህወሓት የበላይ አገር የሆነበት የብሔር ተኮር ፓርቲዎች ጥምረት

ሆኖ በዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ደግሞ አጠቃላይ የፌዴራል ስርዓቱን ይቆጣጠራል፤ እንዲሁም በክልላዊና

ንዑስ ክልላዊ መንግስታት አስተዳደር ውስጥ በስፋት ጣልቃ ይገባል፡፡” ደንበኛ (client) ሆኖ ለመቆየት

ብቻ የሚውተረተሩ ፓርቲዎች በክልላዊ ጉዳያቸውም ቢሆን ፓትሮኑን ፓርቲ እስካላስደሰቱ ድረስ ደህንነት

አይሰማቸውም፡፡” ከዚህም መገንዘብ የሚቻለው፣ ፌዳራሊዝም ኮሙኒስት ፓርቲው ጥበቃ ቁጥጥር በመያዙ ላይ

መሠረት ያደረገው የሶቭየት ሞዳል” መሆኑን ፕ/ር መሳይ ይገልፃሉ፡፡

ፌዴራላዊ እና ራስ ገዝ ሥርዓት እንዲተገበር

በፈቀደ ነበር፡፡

እንደሚታወቀው ከሕወሓት በላይ የኤርትራን

ነፃነት የሚደግፍ የለም፡፡ በታጋይ መለስ

ዜናዊ ከተፃፉት የኤርትራ ህዝብ ትግል

ትኩረት ያደረጉ መፃህፍት በተጨማሪ

የመገንጠሉን ተግባራዊነት በማስፈፀም

ከህወሓት የሚቀድም ኤርትራ ድርጅት አንኳ

ያለ አይመስልም፡፡ ህግሓኤም ቢሆን እላለሁ፡

፡ ነገር ግን ፕራይሞርዲያሊስቱ ህወሓት

እንደ ምን የኤርትራን ነፃነት/ መገንጠል

ሲደግፍ የሶማሌና ኦሮሚያ አካባቢ ተመሳሳይ

ጥያቄዎችን ክፉኛ ጠላ ለማፈን ተንቀሳቀስ?

ይህ ተቃርኖ ግልፅ የሚያደርገው ነገር

ቢኖር-“ የኢትዮጵያ ስርዓት የብሔር ክፍፍልን

የሚያበረታታ ቢሆንም በጣም ማዕከላዊ ሆኖ

መቅረቱን …. ጥቅም” የሚገዛው መሆኑን

ያሳያል፡፡

በዚህ ጭብጥ አገባብ ላይ እንዳልነው፣ የጋራ

ጥቅም ያላቸው እና በራስ ገዝ እና ክልላዊ

የመንግሥት የስልጣን ቁጥጥር የተጠመዱ

ልሂቃን፣ ወደ ፓርቲነት ሲመነዘሩ `የማዕከላዊ

ስርዓት` መንስኤን ያሳያል፡፡ ማለትም

ባለው የፓርቲ ስርዓት “ኢህአዴግ [ማለት]

ህወሓት የበላይ አገር የሆነበት የብሔር ተኮር

ፓርቲዎች ጥምረት ሆኖ በዴሞክራሲያዊ

ማዕከላዊነት ደግሞ አጠቃላይ የፌዴራል

ስርዓቱን ይቆጣጠራል፤ እንዲሁም በክልላዊና

ንዑስ ክልላዊ መንግስታት አስተዳደር ውስጥ

በስፋት ጣልቃ ይገባል፡፡” ደንበኛ (client)

ሆኖ ለመቆየት ብቻ የሚውተረተሩ ፓርቲዎች

በክልላዊ ጉዳያቸውም ቢሆን ፓትሮኑን

ፓርቲ እስካላስደሰቱ ድረስ ደህንነት

አይሰማቸውም፡፡” ከዚህም መገንዘብ

የሚቻለው፣ ፌዳራሊዝም ኮሙኒስት

ፓርቲው ጥበቃ ቁጥጥር በመያዙ ላይ

መሠረት ያደረገው የሶቭየት ሞዳል” መሆኑን

ፕ/ር መሳይ ይገልፃሉ፡፡

ይህ ግን፣ የክልሎች መብት፣ የውስጥ

ጉዳያቸውን በተባለው ልክ ይወስናሉ /

ይቆጣጠራሉ ማለት አይደለም፡፡ ይህ እንዲሆን

ተፈጥሮአቸው አይፈቅድም፡፡ እንደ ፕ/ር

መሳይ አባባል “ይልቁንም መሃል ተቀማጩ

በጥገኛ የአካባቢ ልሂቃን አማካኝነት ቁጥጥሩን

እንደያዘ እንዲቆይ የሚያመቻቹ ደንበኛ

(client) ፓርቲዎችን ስርዓት ይፈጥራል፡

፡” የህወሓት አቋም ይህ እንዲሆን ከሆነ፣

የኤርትራ ከኢትዮጵያ መገንጠል ትክክል ነበር

ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ቫዕቢያ ለህወሓት

ጥገኛ መሆንን መቀበል ቀርቶ ሕወሓት

የእኩልነት ሒሳብ እንኳ አይስማማም፡፡ ይህን

ሐቅ ለማረጋገጥ ብዙ ምንጮችን ማገላበጥ

የሚቻል ቢሆንም የረዳት ፕ/ር መድኃኔ

ታደሰ “የኤርትራና የኢትዮጵያ ጦርነት

የግጭቱ መነሻና መድረሻ” መፅሐፍ ብቻ የላቀ

ትርጉም አለው፡፡ ህወሓት “…… የትኛውንም

ያህል ፖለቲካዊ ብስለትና ወታደራዊ ብቃትን

ቢያስመዘግብ ህወሓት የህግ ሃኤን ክብር

ለማግኘት አልታደለም ነበር” (መድኃኑ

91) “…….. ኤርትራውያን ህወሓት ያሳየውን

ለውጥ ይህን ያክል ክብደት የሚሰጡት

አልነበረም፡፡ ምክንያቱም ህግሃኤ በህወሓት

ላይ የበላይነት ስሜትን ስለሚንፀባርቅ ነበር፡

፡ የፈለገውን ያክል ውጤት ቢያስመዝግቡም

ህግሃኤ የትግራዮችን ብቃት ይለካ የነበረው

በድሮው የተዛባ መሰፈርቱ ነበር” /መድኃኔ

92) የሚሉ ሌሎችም ናቸው፡፡

ስለዚህ ህወሓት በኢትዮጵያ የዘረጋው

ስርዓት እና አተገባበሩ ትርጉም የሚሰጠው

በኤርትራ ላይ የነበረው የመገንጠል አቋሙ

እና በኢትዮጵያ ደግሞ” የአናሳ ብሔር ቡድን

ጥቅሞች” እንዲከበሩ የሚጥር የልሂቃን ቡድን

የበላይነቱና እንዲጠብቅ የሚሊዳ ስርዓት

መዘርጋቱ ስታወቅ ነው፡፡

ለመሆኑ በምርጫ 2002 የነበሩት 95 እና

ከዚያ በላይ የሚሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች

የስርዓቱን ዴሞክራሲዊነት ያረጋግጣሉን? በኔ

እምነት ፍፁም አይችሉም፡፡ ይህ የህወሓት

ፖሊሲ (ስለ) በተዘዋዋሪ ያመጣው የቀውስ

ውጤት ነው፡፡ ማለትም ህወሓት በነበረው

የብሎር ተኮር እንቅስቃሴ ያተኮረው ይህንኑ

ፍላጎት በማንገብ ደንበኛ (client) ለመሆን

የሚነሱ የብሔር ቡድኖች በሽ በሽ እንደሚሆኑ

በማረጋገጡ ነበር፡፡ ይህ ነው ማለት ነው

በተግባር የታየው የ95ቱ ፓቲዎች ጉዳይ፡፡

ህወሓት ፕራሞርዲያሊስት ነው ብዬ ነበር፡፡

ዶ/ር መረራ ጉዲና “Ehtiopia competing

thhnic nationalism and the qyest for

democracy, 1960 -2000” በተባለው

መፅሐፋቸው ኤስማን የተባለ ፀሐፊ ጠቅሰው

እንደፃፉት “ብሔርተኝነት የጋራ ማንነት ነው፤

በመሆኑም ባለፉት ታሪካዊ ክንዋኔዎች ጠልቆ

የሚገባ እይታ ስለሚኖረው የሰዎችን ግንኙነት

በሚመለከት እንደ ነባራዊ /ተፈጥሯዊ/

given) መቀመጥ አለበት የሚል ነው” ይላሉ፡

፡ በመሆኑም የህወሓት ምደባዬ ሙሉ በሙሉ

እንደማይሰራ አሳይቼ ነበር፡፡ በሌላ በኩል

ፕ/ር መሳይ “ብሎርተኝነት እንደ የማንነት

ሀሳባዊ ደግሞ ፈጠራ ተደርጎ ሳይተረጎም

ኢንስትሩሜንታሊዝም (ብሔርተኝነት ልሂቂን

ለመንግሥት ስልጣን በሚያደርጉት ፉክክር

በብሔር ማንነት ስም ህዝብን የሚቀሰቀሱበት

መንገድ መሆኑን የሚናገረው የት/ት እሳቤ

13

የትግራይን የብሔር ምደባ” አያብራራም

ይላሉ፡፡ ትግራይ 3000 ዓመታት ዕድሜ

አለው የሚባለው የኢትዮጵያ (አቢሲኒያ)

ታሪክ አካል ናት፡፡ ህወሓት ትግራይን ነፃ

ሊያወጣ የታገለው፣ ተመሳሳይ የፖለቲካ

ስርዓት እና የባህል ስብጥር ካለው ቡድን ነበር

ከአማራ ልሂቃን /ገዢዎች፡፡ ይህ የታሪካዊ

ሀቆች ድህነት ሕወሓት በቋንቋ ልዩነት ላይ

ብቻ በማተኮር የትግራይ ብሔርተኝነትን

እንዲገነባ አስገደደው፡፡

ኢትዮጵያ ሊሂቃን የፖለቲካ ግባቸውን

ለማሳካት ብሔርተኝነትን መስፈርት

ማድረጋቸው የክበቡን ጥልቅ ተቃርኖ

የሚፈትን ነው፡፡ የኤርትራንና የትግራይን

ጨምሮ አባዛኛዎቹ የብሔር ንቅናቄዎች

መነሻ በጠበቀ ማዕከላዊነት አማራን ባህል

ስነልቡናና ቁሳዊ ጥቅሞችን ማዕከል አድርጎ

ተገበረ ከሞሉት የዘመድ ሥርዓት ጋር

አልነበረምን ታዲያ መፍትሄው በተማከለ

ዴሞክራሲያዊነት የህወሓት የበላይ አጋርነት

የሚታይበት የተማከለ የሥልጣን ሥርዓት

ነው? በራስ ገዝና የቡን መብቶች ላይ ማተኮር

መፍትሄ ነውን? እኔ የፕ/ር መሳይን “….

ኢትዮጵያ ባለብዙ ብሔር ሀገር ለመሆኗ

እውቅና በመስጠት ያተማከለ የሥልጣን

ሥርዓት /decenteralization/” መዘርጋት

መፍትሄ እጋራለሁ፡፡ በመሆኑም በአሁኑ

አሰራር አንድ የማይታየው ሀቅ የብሔር

ቡድኖች የብሔር ብሔረሰቦችን ቦታ የሚተካ

ትርጉም እንዲያገኙ በመደረጉ ቦርጫም

ካድሬዎ፣ መሬት የሚቸበችቡ ካድሬዎች፣ ሀገር

የሚገዙ የሚሸጡ እና የሚወክሉ ካድሬዎች

የተጠበቁ (protected) /ባለመብት/

እንዲሆኑ አድርጓል፡፡ የነዚህ ቡድኖች መነካት

የብሔረሰቦችን መሳካት ሆኖ በመተርጎሙ፡፡

ውጤቱ ደግሞ ብዝሃ ብሔር ላይ የተመሠረተ

ስርዓ ለመገንባት ሲባል ሲቃወሙት የነበረውን

ብሔረ መንግሥት (nationstate) ደገሙ

ማለት ነው፡፡ ኢህአዴግም እንድሜ ዘመኑን

ወደ ከግንባርነት ወደ ውህድ ፓርቲነት

ከማይቀየርባቸው ነገሮች አንዱ የብሔር ኮታ

ያላቸው ሲነኩ የተገኙበት ብሔር እንደተነካ

አድርጎ በማሳየት እራሱን ለመከላከል ነው፡

፡ በአጠቃላይ በዛሬዋ ኢትዮጵያ ትክክለኛና

ዴሞክራሲያዊ የህግ ድንጋጌ የሚደግፈው

ፌዴራሊዝም ባለመኖሩ አሁን በሚተገብረው

የብሔር ፌዴራሊዝም አካሄድ ተጨማሪ

የብሔር ቡድኖች እንደ እንጉዳይ እዚያም

እዚህም እንዲፈሉ ከማስቻሉም በላይ የበለጠ

የአክራሪነት ባህሪ ያሳብሳቸዋል፡፡

በመጨረሻም ለብዙ ጊዜያት ስለ ብሔራዊ

ዕርቅ ተጠይቆ ብዙ ጊዜ የአሉታ መልስ

የሰጠው ኢህአዴግ የመጨረሻውን የእንቢታ

ዲስኩር ያካሄደው በአንደኛ የዚውኑ

ብሔርተኝነትን ባቀነቀነው አቶ ፊዲዋን ሁሴን

በ2001 ዓ.ም የክረምት ወቅት ለመምህኖ

በተደረገው የፕላዝማ ጠመቃ ወቅት ነበር፡፡

በመጨረሻም ሌላው ቀርቶ የህገ-መንግሥቱ

አንቀፅ 32.1 ን በአግባቡ የሚረዳ የለም፡

፡ የክልሎች ሀብት፣ ንብረት እና ቁሳዊ

ቦታው ለክልሉ ተገቢነቱ ቴክኒካዊ አገላለፅ

መሆኑን የሚረሱ አሉ በተለይ በታችኛው

ጥቃቅን አነስተኛ አባላት ዘንድ በፍፁምና

በመውሰዳቸው የዜጎች ከክልል ክልል

በነፃነት የመንቀሳቀስ፣ የመኖር እና ሀብት

ማፍራት እንደሚገደብ ገልጫለሁ፡፡ አሊያም

በኢትዮጵያዊነቱ ብቻ ማግኘት የሚገባውን

ነገር ከብሔር ክልሉ ውጭ በመኖሩ ብቻ

ያጣል፡፡ በኔ አስተሳሰብ በኦሚያ ክልል /

ሌላም ሊሆን ይችላል/ ከ5ኛ ክፍል `ሀ` ብሎ

የሚጀምረው የአማራኛ ት/ት የኦሮሞ ኤሊቶች

በፌዴራል መንግሥት ውስጥ ሊኖራቸው

የሚችለውን ሚና ቀስበቀስ ይቀንሳል፡፡

ቋንቋ መግባቢያ ነው፡፡ አማርኛ የፌዴራል

መንግሥት መግባቢያ ነው፡፡ በመሆኑም

አቋማቸውን መግለፅ የማይችሉ ነገር ግን

በኮታ ቢቻ የሚወክሉ ግዑዝ ፓለቲከኞች

ይሞሏታል፡፡

www.andinet.org.et

14

www.andinet.org.et

ልብ ያለው ልብ ...

አገር ለመሄድ ዕቅድ ስለነበራቸው መንግስት ጫና

ፈጠረብን ያሉት ተቀባይነት ለማግኘት ነው፡፡”

የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ነበሩ፡፡ በውይይቱ ተሣታፊ

ከነበሩት መካከል የአዲስ ፎርቹን ጋዜጣ ማኔጂንግ

ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ታምራት ወ/ጊዮርጊስ

ሚዛናዊ አስተያየት ይሰጡ እንደነበር መግለጽ

ፍርደ ገምድል ከመሆን ያድነኛል፡፡

ከጓዳ ወደ ጓዳ

በ2002 ዓ.ም በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን

የተላለፈው “የነፃው ፕሬስ” ጉዞን በተረከው ዘጋቢ

ፊልም፤ ሂደቱን በሁለት /በሦስት ምዕራፎች ከፋፍሎ

አቅርቦት ነበር፡፡ እስካሁን ከአዕምሮዬ ያልጠፋው

የመክፈያ መንገድ (dividing line) 1997 ዓ.ም

ላይ ማዕከል ያደረገ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡

ቅድመ 97 የነበሩትን ተጨባጭ ያልሆኑ ፅሁፎችን

የሚፅፉ፣ በምርጫው ሰሞን የነበሩት “አክራሪ”

የተቃዋሚዎች ደጋፊና ድህረ 97 የተከሰቱትን

ደግሞ ስህተት ፈላጊና በማጠልሸት ሥራ ላይ

የተጠመዱ በማለት ፈርጇቸዋል፡፡ በሦስተኛው

ምድብ ከተፈረጁት ለናሙናነት የተወሰኑ ጋዜጦችን

ፅሁፎች ያቀረቡ ቢሆንም፤ በዋነኛነት ትኩረት

በመስጠት ጠንካራ ሂስ የተሰነዘረባት አዲስ

ነገር ጋዜጣ ነበረች፡፡ ለዚህ ዓላማም በተለያዩ

ጊዜያትና ርዕስ -ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ህትመቶቿን

ተጠቅመዋል፡፡

የዚያ ዘጋቢ ፊልም መሠረታዊ ስህተት

አዲስ ነገር ጋዜጣን ከሌሎች “የነፃ” ጋዜጦች ጋር

በመደመር “ጭፍን ጥላቻን” የምትፅፍ አድርጐ

የተገላቢጦሽ ...

አቀበት እንደምን ከጭነቱ ላይ ሆኘ ይዞኝ ከወጣ

ከዚያ በኋላ እንደምንም አዝግሜ ከቤቴ እደርሳለሁ፡

፡” ይላሉ

ገበሬው በበኩሉ “አይ ፈጣሪየ፤ ብትችል ጌታ

የሌለው ጠብደል አህያ ወይንም ጎረደማን ሰጠኝ

ነበር ይልኩህ፤ እንግዲህ መቸስ ያንተ ስጦታ ከሆኑ

ምንም ማድረግ አልችልም፡፡ እንደምንም ብለው

ይህንን አቀበት ያህያውን ጭነት ካገዙልኝ ከዚያ

በኋላ አዝግሜም ቢሆን ከቤቴ እደርሳለሁ” አለና

ያህያውን ጭነት ሲፈታ፡- “ተወው ልጄ፤ ብዙም

ክብደት የለኝም፤ ከዚያው ከጭነቱ ላይ እቀመጣለሁ”

ሲሉት ገበሬው በበኩሉ፡- “ሸህ፤ እንኳን እሰዎን

ደርቦ ሊሸከም የተጫነውን ጭነትም ይዞ መዝለቅ

አልቻለም፡፡ ይልቅ ይምጡ ይሸከሙና በጊዜ

አቀበቱን እንውጣ” ሲላቸው “አላህንኮ የለመንኩት

ይህንን አቀበት የምወጣበት ሰጋር በቅሎ እንጂ ያህያ

ጭነት እንድሸከም አይደለም!”

“አባቴ፤ እኔም አላህን የለመንኩት እስከነ አህያየ

ለጅብ አትስጠኝ፤ ሲሆን ጌታ የሌለው ጠብደል

አህያ አለበለዚያም ያህያየን ጭነት ተሸክሞ ይህንን

አቀበት የሚወጣ ጎራደማን እንዲጥልለኝ ነበር፡፡

እንግዲህ እስዎን ከሰጠኝ የሱ ስጦታ ነዎትና ይምጡ

ይሸከሙ” ይላቸዋል፡፡ በዚህ የተነሳ ይሸከሙ

አልሸከምም ከዚያ ዳገት ስር ገላጋይ ከሌለበት ጠብ

ይፈጠርና ያ መጠቅጠቂያ ገበሬ እኒያን በመንግድና

በፆም የተዳከሙ አዛውንት እየተንጠራራ በሽመል

ከወቃቸው በኋላ ያንን ይህያ ጭነት አሸክሞ አህያው

ባፍንጫው ቂጥቂጣቸውን እየጎሸማቸው፣ የምሳ

አቆይኝን አቀበት ትንፋሻቸው ቁርጥ ቁርጥ እያለና

ከላይ ከላይ እየቃተቱ ይዘው ይወጣሉ፡፡

ካፋፉ ብቅ እንዳሉ ገበሬው አስቆማቸውና

“አላህ ይባርከዎት” ብሎ በማሸሟጠጥ አህያውን

ጭኖ መንገዱን ሲቀጥል ሸህ ሙሄ ግን ካላህ ጋር

እልህ በመጋባት ካፋፉ ላይ ተቀመጡና፡-

“አላህ፤ ያቀበት መውጫ ሰጋር በቅሎ

ስጠኝ ብልህ ያህያ ጭነትና ሽመል አዘዝክብኝ?

መጠቅጠቂያ ገበሬ እየተንጠራራ በሽመል ወቃኝ!

አሁንም ለጅብ ስጠኝ እንጂ ከዚህ አልነቃነቅም!”

አሉና ተደላድለው ተቀመጡ፡፡ ከርቀት ቀበሮዎች

ሲጮሁ ይሰማሉ፡፡ ቆይቶ ጅብ መጮሁ አይቀርም፡

፡ ይህ ሁሉ ሸህ ሙሄን አላስጨነቃቸውም፤ በጅብ

ለመበላት ቆርጠዋል፡፡ በዚህ ላይ እንዳሉ አንድ

ሰው ከጥጉ ላይ ካሉት መንደሮች ተነስቶ ሚስቱ

ምጥ ጠንቶባት አዋቂ ፍለጋ እየባከነ ከሸህ ሙሄ

ባጋጣሚ ይደርሳል፡፡ እየተብረከረከ፡-

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 23 2004 ዓ.ም.

ከገፅ 12 የዞረ

ማቅረቡ ነው፡፡ ሁሉም የጋዜጣዋ አንባቢ የነበረ

ሰው በሙሉ እንደሚያስታውሰው፤ ጋዜጣዋ “በነፃ

አስተያየት” አምዷ የገዢው ፓርቲ አባላት ጭምር

የፓርቲያቸውን አቋም ያንፀባርቁበት እንደነበር

ነው፡፡ ለዚህ ሃሳቤም ምሣሌ ለመጥቀስ ያህል

“አብዮታዊ ዲሞክራሲ ለአገራችን አስፈላጊ ነው”

የሚሉ የገዢው ፓርቲ አባላት ደጋፊዎች በአንድ

በኩል “የሊብራሊዝም ፍልስፍና ለኢትዮጵያ

ይበጃል” የሚሉ ፀሃፊያን በሌላ በኩል ለሳምንታት

ሲፃፃፉባት አስታውሳለሁ፡፡ ይህን ታላቅ ዕድል

ፈጥሮ የነበረው አዲስ ነገር ጋዜጣ እንጂ አዲስ

ዘመን አልነበረም፡፡

የሆነው ሆኖ “አዲስ ነገር” ጋዜጣ ከጋዜጠኝነት

ሥነ -ምግባር ባፈነገጠ መልኩ ስትሠራ እንደነበር

ለማስረገጥ በየመሃከሉ አንድ “የጋዜጠኞች ማህበር

መሪ”፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነት

ትምህርት ክፍል መምህራንና ከጋዜጠኝነት ሙያ ጋር

ቀጥተኛ ግንኙነት የነበራቸው ግለሰቦ ሃሣባቸውን

ይሰጡ ነበር፡፡ የሚያሳዝነው አብዛኛዎቹ ይሰጡት

በነበሩት ሃሣቦች ውስጥ ትኩረት ሰጥተውት

የነበረው ጉዳይ “ከኢትኦጲስ እስከ አዲስ ነገር”

ድረስ የታተሙት የግል ጋዜጦች በሙሉ “ለጥፋትና

ገንቢ ላልሆኑ” ዓላማዎች መዋላቸውን ማስረገጥ

ነበር፡፡ በማንኛውም መስፈርት ሁሉንም በአንድ

ቅርጫት ውስጥ ከትቶ መጨፍለቅ አግባብ

አልነበረም፤ አሁንም አይደለም፡፡

በኢቲቪ የፓናል ውይይትም ሆነ በዚያ ዘጋቢ

ፊልም ላይ የጠቀስኩትን አስተያየት የሰጡት

አንዳንዶቹ ግለሰቦች፣ ዛሬ ዛሬ ከቴሌቨዥን ውጭ

ከገፅ 8 የዞረ

“ሸሁ፤ ሚስቴ ምጥ ጠንቶባት ልትሞትብኝ

ነውና አላህ ለርስዎ ቅርብ ስለሆነ ወደ ቤቴ እንሂድ

ይለምኑልኝ” በማለት ይማፀናቸዋል፡፡ እሳቸውም

ካለህ ጋር የበለጠ ግብግብ የሚገጥሙበት አጋጣሚ

በማግኘታቸው ተደስተው “ከሰማኝማ ይሁና”

አሉና ሰውየውን ተከትለው ይሄዳሉ፡፡

ሸህ ሙሄ ከሰውየው ቤት ሲደርሱ እውነትም

የሠፈር ሴቶች ተሰስበው “ማርያም ማርያም መሬም

መሬም” እያሉ ፈጣሪያቸውን ሲማፀኑ አገኟቸው፡፡

ሸህ ሙሄ ምጥ ከተያዘችዋ ሴት አጠገብ በርከክ

አሉና “አላህ አክበር ! አላህ ታላቅ ነው !” በማለት

በቅድሚያ አላህን ካመሰገኑ በኋላ ቀጥለው እየጋሉና

እየተወራጩ “አላህ ይችን ሴት እንዳትገላግላት !

በሽፍን ውሰዳት! ተርትራት! ተርትራት!” እያሉ

ከመሬት እየተደፉና እየተነሱ ሲሰግዱ ከዚያ

የተሰበሰቡት በሙሉ በመደናገጥ፡-

“እንዴ! አባታችን ምነካዎ?! እብድነዎት ጤነኛ

? እንዴት ይተርትራት ! እያሉ አላህን ይማፀናሉ?”

በማለት ይንጫጩባቸዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ሸህ ሙሄ

“አርፋችሁ ዝምበሉ! እናንተ የምታውቁት ነገር

የለም፡፡ እኔና አላህ እንተዋወቃለን፡፡ ነገሩ ሁሉ

የተገላቢጦሽ ሆኖ አግኝቸዋለሁ ! አላህ ይችን ሴት

እንዳትገላግላት!” ሲሉ ወዲያውኑ ወንድ ልጅ ዱብ

ታደርጋለች፡፡ ህፃኑም ወደዚች ዓለም በመምጣቱ

ተከፍቶ ሣይሆን አይቀርም ምርር ብሎ አለቀሰ፡

፡ በዚህ ጊዜ ሸህ ሙሄ ተደስተው፡- “አላህ አክብር

! አላህ አክብር!” በማለት ላላህ ምስጋና አቀረቡና

ከተንበረከኩበት ተነሱ፡፡ ከዚያ የተሰበሰቡት እንደ

ጨካኝና ክፉ ሰው ስላዩዋቸው “ሸሁ፤ በስዎ እልህ

አላህ ከጭንቅ ምጥ ገላገላት፡፡ እስዎማ አትገላግላት

ተርትራት እያሉ ነው የፀለዩት ምን ዓይነት ጨካኝ

ቢሆኑ ነው?” ሲሉ እየተቀባበሉ ይጠይቋቸዋል

“አያችሁ ወገኖች፤ እኔ ጨካኝ አይደለሁም፡፡

ምስጉን ሰው ነኝ፡፡ ተርትራት፣ አትገላግላት እያልኩ

የተማፀንኩት ነገሩ ሁሉ የተገላቢጦሽ ሆኖ ስላገኘሁት

ነው፡፡ ይችን ሴት ገላግላት፣ በምጥ አታስጨንቃት

እያልኩ ብለምነው ኖሮ በምጥ አስጨንቆ ይገላት

ነበር፡፡ የተገላቢጦሹን የተማፀንኩት እናንተ እኔን

ጨካኝ ሰው ናቸው ብላችሁ ገምታችኃል፡፡ እኔ

ግን አይደለሁም” አሉና ከመንገድ የገጠማቸውን

ጉድ ተረኩላቸው፡፡ “አስቡ እንግዲህ ያቀበት

መውጫ ሰጋር በቅሎ ስጠኝ ብዬ ተማፅኘ ሽመልና

ያህያ ጭነት ተሸክሜ የምሳ አቆይኝን አቀበት

እያቃተትኩ ስወጣ ሊሰማኝ የሚችለውን ብርቱ

ሀዘን ገምቱት፡፡ ሁላችሁም ቢሆን እኔን የገጠመኝን

በሆነ ሌላ ጓዳ ውስጥ ሆነው ድምፃቸውን እያሰሙን

ይገኛሉ፡፡ አሁን እየሰጡት ያለው አስተያየት ቀድሞ

ያተኮሩበት ከነበረው ጉዳይ የተለየ ቢሆንም፣

ዓላማው ግን አንድ ነው፡፡ የቀድሞው ዓላማ

የሚመስለው “የነፃው ፕሬስ” ከአጥፊነት በቀር

የገንቢነት ሚና ለመጫወት በተፈጥሮው የማይችል

በመሆኑ፤መንግሥት ጠንከር ያለ የመቆጣጠሪያ

የፕሬስ ህግ ማውጣቱ አግባብ መሆኑን ለማስረገጥ

ነበር፡፡

ዛሬስ? ዛሬማ የዛኔ የነበሩት ግለሰቦች

ኃይላቸውን አስተባብረውና አዳዲስ ሰዎችን

ጨምረው ከአንድ የኤሌክትሮኒስ ሚዲያ መሽገዋል፡

፡ እንደቀድሞው ሁሉ የተለያዩ “ጉዳዮችን” እያነሱ

ይወያያሉ፡፡ በመጨረሻም የጋራ የአቋም መግለጫ

ማውጣታቸውን ባይነግሩንም በተመሳሳይ

አቋም ይለያያሉ፡፡ ቀድሞ “መወያያ” ርዕሣቸው

የነበረውን ነፃው ፕሬስን ብቻ ሳይሆን ሌሎች

ጉዳዮችንም ጨምረውበታል፡፡ እንደ ጋዜጠኛ

እስክንድር ነጋ፣ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ከነጋዜጣው፣

አንድነት ፓርቲ ከፍኖተ ነፃነት ጋር ዋና ዋናዎቹ

ሲሆኑ፤ በአጠቃላይ ግን ገዢው ፓርቲ ላይ የሰላ

ሂስ በሚሰነዝር ማንኛውም ግለሰብ ወይም ቡድን

ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡ ከቀድሞው ዓላማቸው

ጋር ያለው አንድነት ደግሞ ሁለቱም መንግስትን

ለመከላከል በመሞከራቸው ነው፡፡ መንግስት

ስህተት እየሰራ መሆኑን በልባቸው ቢያውቁም

ጋሻው ከመሆን እንደማይመለሱ ለአየር ያበቋቸው

ፕሮግራሞቻቸው ህያው ምስክሮች ናቸው፡፡

የቀድሞውም የዘንድሮውም አስተያየቶች ዓላማ

ዓይነት የክፋት ተግባር ቢገጥማችሁ የተገላቢጦሹን

ከማድረግ እንደማትመለሱ እገምታለሁ፡፡” በማለት

ተረኩላቸው ይባላል፡፡

ውድ ወገኖቼ እኔም አሁን ያለንበት ዘመን ግራ

እያጋባኝና እያደናገረኝ ሁሉንም ነገር ስመለከተው

ሸህ ሙሄ ዘሌ እንዳሉት የተገላቢጦሽ ነው፡፡ ድሮ

አባቶቻችን “ረጋሚ ተረጋሚ ነው” ይሉ ነበር፡፡ በዚህ

ዘመን ደግሞ ርግማን ምርቃት ሆኗል፡፡ በተለይ

የተገላቢጦሽ ከሆነ ከመቅጽበት ይደርሳል፡፡ ይህን

ዘመን በጥንቃቄ አጢናችሁትና ተመልክታችሁት

ከሆነ ነጩ ጥቁር፣ ጨለማው ብርሃን፣ የዔሊ ፍጥነት

ከጥንቸል የሚፈጥንበት ዘመን ነው፡፡ ታዲያ ሁሉም

ነገር በተገላቢጦሹ እንዲህ የሚሆን ከሆነ ምን ችግር

አለው፡፡ አጥብቆ መርገም ነው፡፡

እየተራብን ከጠገብን፣ እየተበጣበጥን

ሰላም ከሰፈነ፣ ድርቅ እየጠበስን የሰሞኑ ዝናብ

በጎርፍ የሚያጥለቀልቀን ከሆነ፣ ጤፍ እያመረትን

በ1300 ብር የምንገዛ ከሆነ፣ ፍቅር ስንል ጥላቻን፣

እምነት ስንል ክህደትን፣ ክብር ስንል ውርደትን፣

እንድንሸከም ፈጣሪ የሚፈርድብን ከሆነ እንደ ሸህ

ሙሄ በተገላቢጦሹ መፀለይና መሥገድ የግድ ሊሆን

ነው፡፡ ፈጣሪ የኛ መሪዎች ደስ ብሏቸው እንዲኖሩ

እኛን ከዚች ኢትዮጵያ ከምትባል ምድር ገላግላቸው?

አጥፋላቸው፤ እኛን ካጠፋህላቸው ቻይናውያን

ቱርኮችን፣ ህንዶችን አስፍረው ከነሱ ጋር የደስታና

የቡረቃ ጊዜን እንዲያሳልፉ እድሉን ሰጣቸው፡፡ ከዚህ

በኋላ ቻይናውያን ይችን የድሆች ሀገር የበለጸገችና

መንታ መንታ ባንድ ጊዜ የሚፈለፈልባት የመንገዱ

ዳር ሁሉ አንዱን ከሌላው ለመለየት የሚያስቸግር

ዝንብ የወረረው ፈልፍላ እንደ ጉድ ይፍላባት፡፡

ከዚህ በኋላ ቅንቡርሱ ሁሉ ምግብ ይሆናል፡፡ ችጋር

የሚባል ነገር ከኢትዮጵያ ምድር ይጠፋል፡፡ ሸኮና

ፍርቅ ሸኮና ድፍን፣ ባላደልጋ ባለጋማ የሚባለው

ሁሉ ይቀርና ሁሉም ነገር ይበላል፡፡ ሁሉም ነገር

ከተበላ ደግሞ በተገላቢጦሹ ጥጋብ ይሆናል፡፡

የባሕር በር እንዲኖረን መመኘትም ከፍተኛ

ርግማን ነው፡፡ በእግዚአብሔር ወይንም ባላህ

ዘንድ የሚያስወቅስ ነው፡፡ የባሕር በር አሳጣን፣

እያሉ መፀለይ ነው፡፡ የቀይ ባህርን ከዚያው

ግመሎቻቸውን ያጠጡበት፤ ጠ/ሚንስትሩን

በክፋት ለመወንጀል በተገላቢጦሹ “ባንዲራን

ጨርቅ አሉ” እያሉ ማብጠልጠል ተገቢ አይደለም፡

፡ ጨውና ስኳር ቋጥረውባት መጥተዋል እያሉም

በተገላቢጦሹ ያሟቸዋል፡፡ እኔ በበኩሌ ለምን

ቡትቶ ጨርቅ አይሏትም፡፡ እንኳን ጨውና

ከኢሕአዴግ ድምፅ በስተቀር ሌሎች ድምፆች

እንዳይሰሙ ማፈን ይመስላል፡፡

የአዲስ ነገር ጋዜጣ አዘጋጆችን ጉዳይ እንደ

ማሳያ አድርጌ ከላይ ያቀረብኩት አብነት አሁን

እየተደረገ ላለው የሚሰራ ይመስለኛል፡፡ ከሁለት

ዓመታት በፊት የጋዜጣዋ አዘጋጆች ከአገር

የተሰደዱት በራሳቸው ውስጣዊ ምክንያት እንጂ

ከመንግስት በተሰነዘረ ውጫዊ ተፅዕኖ እንዳልነበረ

ምክንያታችሁን ደረደራችሁ፡፡ በወቅቱ ያመናችሁ

አመናችሁ፣ ያላመናችሁ አዘጋጆቹን አመነ ወይም

ጥርጣሬውን ይዞ ከረመ፡፡ ዛሬ ግን እውነታው

ታወቀ፡፡ ዛሬ ደግሞ ጓዳ ቀይራችሁ “አንድነት

ህዝባዊ አመፅ ለማስነሣት እየሰራ ያለ ፓርቲ፣

እስክንድር ነጋ ህዝባዊ አመፅ ለማስተባበር

የሚተጋ፣ ፍኖተ-ነፃነት አብዮተኛ ጋዜጣ፣ ዳዊት

ከበደ ………… እገሌ “አሸባሪ” እያለ ይቀጥላል፡፡”

ስትሉ እየሰማን ነው ፡፡

ዘንድሮ ከጓዳችሁ እየነገራችሁን ያለው ነገር

እውነት፣ እውነቱን መሆን አለመሆኑን ለማወቅ

ሁለት ዓመታትን መጠበቅና ሚስጥራችሁን

የሚያወጣ ዊኪሊክስ አያስፈልገንም፡፡

የእስከዛሬዎቹን በማስታወስ እውነቱ የት ጋ እንዳለ

እናውቀዋለን፡፡ በተጨማሪም አደባባይ ወጥታችሁ

እውነቱን ልትነግሩን የማያስችላችሁ ምክንያቶች

ሊኖሩ እንደሚችሉ እገምታለሁ፡፡ ለምሳሌ ፍርሃት፡

፡ ልትፈሩ ትችላላችሁ ቢሆንም ግን ስለምትፈሩ

ሀሰት መናገር ግን ይቅር ሊባል የማይችል ስህተት

ነው፡፡ የፈራ ሰው ዝም ነው የሚለው፡፡ ዝም …

ጭጭ!! እንጂ ሃሰት አይናገርም፡፡

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.10

ጣፋጩን ስኳር ቀርቶ ለምን የሚበጣጥሰውን

አሲድ አይቋጥሩባትም፡፡ ሰው ሥራ ፈት ሆኗል፡፡

እመርቃለሁ ይልና በተገላቢጦሹ ይራገማል፡፡ አሁን

በቅርቡ አንዳንዶች በማያገባቸው ነገር ገብተው

ወጣቱ ጫት ቃሚ ሆኗል ይላሉ፡፡ ለምን የባህር

ዛፍ ቅጠል አያሻምዱም! አንድ ትልቅ ምሁር ክቡር

ጠ/ሚንስትሩን “መተኪያ የሌላቸው ሰው” ሲሉ

አደንቀው ሺ ዓመት ይግዙን ሲሉ እግዚአብሔርን

ተማፅነዋል፡፡ ትክክል ናቸው፡፡ አንዳንዶቻችን

ግን ሳይገባን በተገላቢጦሹ አውግዘናቸዋል፡፡ ይህ

ስህተት ነበር፡፡ አውቀን እንታረም፡፡ እግዚአብሄር

ነፃነት ስንለው ያፈና ሥርዓት የሚሰጠን ከሆነ፤ ሰው

አድርገህ ፈጥረኸናል እንደሰው ባንድ ላይ በፍቅር

መኖር እንፈልጋለን ስንለው አውሬ ይመስል የጎሳ

ሥርዓት ዘርግቶ የሚያስጨንቅንና እርስበርሳችን

የሚያጨፋጭፈን ከሆነ እንደ ሸህ ሙሄ ዘሌ

የተገላቢጦሹን እንዲሰጠን የፈጠረንን አምላክ

መማፀን ግድ ነው፡፡ አይዟችሁ ፈጣሪን ለመለመን

አትፍሩ፡፡ መጠንቀቅ ያለባችሁ በተገላቢጦሹ

መፀለይ እንዳለባችሁ ነው፡፡

እንደ ሸህ ሙሄ ተገቢ ያልሆነ ፀሎት ፀልየንና

ደርግን አውግዘን ቀይ ሽብርንና ነጭ ሽብርን

ረግመን “ረጋሚ ተረጋሚ ነውና” በሰላም አገር

እንደፈራነውና እንደሰጋነው “የፀረ ሽብር ሕግ

አውጥቶ” እግዚአብሄርን የሚቀጣን ከሆነ የሳዳምን

ቀን ይሰጠው! እንደ ሆሴን ሙባረክ፣ እንደ

ብንዓሊን፣ እንደ ጋዳፊ የውርደትን ማቅ ያከናንበው

አንለውም፡፡ ርሃብን ለኛ ጥጋብን ለርሱ፣ ውርደትን

ለኛ ለተዋራጆቹ፣ ክብርና ጥጋብን ለነርሱ ለጥጋበኞች

ይስጥልን!! አሜን በሉ ጎበዝ! ፈጣሪ ተኝተን

እንድንቃዥ፣ እየሠራን እንድንባንን ተረጋግተን

ሥራችንን እንድንሠራ፣ እግዜአብሄር የፀረ ሽብር

ሕግ የሚባል ከሰጠን፣ በአጋጣሚው ሁሉ እየታነቅን

እንደ ሸህ ሙሄ በሽመል እየተዠለጥን እያደፉ ቃልቲ

ወህኒ ቤት የሚያጉሩ ጥጋበኞችን እግዚአብሄር

(አላህ) አታሳጣን! አሜን በሉ ጎበዝ! ኧረ ከልብ

አሜን በሉ ጎበዝ! እንኳን በውናችን በህልማችን

ዓባይ ተገድቦ እናያለን ብለን አሥበን ነበር? በጭራሽ!

ግን የተገላቢጦሽ ሆነና ይኸው በቴሌቪዥን ተገድቦ

እያየን ነው!! ታዲያ ይኸ የሠው ሥራ ነው? በፍፁም

አይደለም፡፡ ያላህ ሥራ ከሆነ አላህን መማፀን ተገቢ

ነው፡፡ ዓባይን የገደበ አምላክ፣ የባንዲራን ክብር

ያጎናፀፈ ፈጣሪ ምን ይሳነዋል፡፡ የተገላቢጦሹ ሁሉ

እንዲደርስ ሁሉንም ነገር ለርሱ እንስጠው፡፡ አሜን

በሉ ጎበዝ!!

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.10

ነፃ አስተያት

ከመ/ር ደረጀ መላኩ

ባሣለፍነው ክረምት ሰኔ ወር ጀምሮ ህዝብ

የሚያውቋቸው ሰዎች ዘብጥያ መውረዳቸውን የዓለም

አቀፍም ሆነ ኢትዮጵያ የዜና ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

በአዲሱ የሽብርተኝነት አዋጅ ህግ መሠረት በመጀመሪያ

ዘብጥያ የተወረወሩት ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ እና በሀገሯ

ጉዳይ ላይ ፊት ለፊት የምትፅፈው ጋዜጠኛና መምህርት

ርእዮት አለሙ ሲሆኑ ቀጥሎም ጋዜጠኛ ስለሺ ሐጐስ

ታስሯል፡፡ ከዚያም እነርሱን ተከትሎ ደግሞ በርካታ

የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች አባላት መታሰራቸው

ፀሐይ የሞቀው መራር እውነት ነው፡፡

የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ጥበቃ ድርጅት

አምንስቲን ኢንተርናሽናል ተወካዮች ኢትዮጵያ

ለጉብኝት መጥተው ጉዳያቸውን ሣይጨርሱ በመጡበት

እግራቸው ከተመለሱ በኋላ ሁለት ከፍተኛ የፖለቲካ

ፓርቲ አመራሮች በተመሣሣይ መልኩ የእስር ገፈት

መቅመሣቸውን ሠምተናል፡፡ እስሩም እንደቀጠለ ነው፡፡

2003 ዓ.ም ሊያበቃ ሲል በወርሃ ጳጉሜ ዝንኛው

የማእከላዊ ምርመራ እስር ቤት ደንበኛውን ጋሼ ደበበ

እሸቱን በእንግድነት ተቀብሎታል፡፡

“ሻፍት ኢን አፍሪካ” በተሰኘው ቆየት ያለ ፊልም

ላይ ተካፍሎ የነበረው፣ የቀድሞው ቅንጅት የቅስቀሳና

ፕሮፓጋንዳ ኃላፊና “የመንፈሴ ፅናት” መፅሐፍ ደራሲ

የ60 አመቱ አዛውንት ደበበ እሸቱን ተከትለው ደግሞ

መስከረም 3/2004 ዓ.ም ሞትን ፊት ለፊት ለመግጠም

የቆረጠው ትንታጉ ብእረኛና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ

ጨቅላ ልጁን ከትምህርት ቤት ወደ ቤቱ በማድረስ ላይ

እያለ እራስ መኮንን ድልድይ አካባቢ ይጠብቁት የነበሩት

ነፍጠኞች እጁ ላይ ካቴና በማጥለቅ ወደ ፈለጉት ቦታ

ወስደውታል፡፡ በዚሁ ዕለት ሌላው የእስር ገፈት ቀማሽ

መንፈሰ ጠንካራው ወጣት የፓርቲ መሪ አቶ አንዱዓለም

አራጌ ነው፡፡ ያሣዝናል! መንፈስንም ይረብሻል! ሕሊናንም

ያደማል! በዚህ እለት የታሰሩት የተጠቀሱት ብቻ

አይደሉም፡፡ በዚች ሀገር ላይ በርካታ የፖለቲካ (ህሊና)

እስረኞች መኖራቸውን ከአለም አቀፍ የሠብአዊ መብት

ጥበቃ ተቋማት መግለጫዎች በየጊዜው ማድመጥ እንግዳ

ነገር መሆኑ እየቀረ ነው፡፡

ለማንኛውም የአገዛዝ ስርዓቱ የያዘው መንገድ

ከእርሱ በፊት የነበሩት ሁለት የአገዛዝ ስርዓቶች

ሞክረው ኢትዮጵያን እንዴት እንዳደሟት እና እነርሱም

መጨረሻቸው እንዴት አሣዛኝ ሊሆን እንደቻለ በወፍ

በረር እንኳን ለማስታወስ ተስኖቸዋል፡፡ ወይም

ሥልጣንና ፍቅረ ንዋይ አሣብዷቸዋል፡፡ ለማንኛውም

እኔ ለማስታወስ እሞክራለሁ፡፡

የ53ቱ መንፈቅለ መንግሥት ጥላ

የ1953ቱ መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ከጨነገፈ በኋላ

ለ13 አመታት አመፁ ተዳፍኖ ቆይቶ ነበር፡፡ በወቅቱ

ማለትም ታህሣስ 5 ቀን 1953 ዓ.ም የአዲስ አበባ ሬዲዮ

ጣቢያ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ በምንም አይነት መልኩ

እስማዋለሁ ብሎ አስቦትና አልሞት የማያውቀውን

ታሪካዊ ዜና ነበር ያስተላለፈው፡፡ ዘጋቢው ጋዜጠኛ

አለም መዝገበ እጅግ ደማቅና ቆራጥ በሆነ ድምፅ የአፄ

ኃይለ ሥላሴ የዘውድ መንግስት በወታደራዊ መፈንቅለ

መንግሥት የተገለበጠ መሆኑን ተናገረ፡፡ የኢትዮጵያ

ሕዝብ ግፍና ጭቆናም በዝርዝር ከገለፀ በኋላ የኢትዮጵያ

ሕዝብ ለመሰረታዊ መብቱ እንዲነሳ ከወቅቱ ወታደራዊ

መፈንቅለ መንግሥት ጥሪ መተላለፉን ደጋግሞ

ማስረዳቱን ከታሪክ ተምረናል፡፡ ሆኖም ግን ይህ የትግል

ጥሪ ፍፃሜ አሣዛኝ ነበር፡፡

ጄኔራል መንግስቱ እና ወንድማቸው እንዲሁም

ሌሎች በአደባባይ ተሰቀሉ፡፡ በነገራችን ላይ ከ1953ቱ

አመፅ በፊትና በኋላ በርካታ የአፄው ተቃዋሚዎች

ታስረዋል፡፡ (ተግዘዋል)፡፡ ይሁን እንጂ ተቃዋሚን ማሰር

እና ማንገላታት የአፄውን እድሜ ዘላለማዊ እንዲሆን

አረዳም፡፡ በአንፃሩ በእጃቸው የጎረሱ ሁሉ ተነሱባቸው፡

፡ ይሄን ተከትሎ ለአያሌ አመታት በፊውዳል አገዛዝ

ሥርዓት ሥር ሲማቅቅ የኖረው የኢትዮጵያ ሕዝብ

ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መብቱን እና ሠብአዊ ክብሩን

ለማስከበር የካቲት 1966 ዓ.ም በህብረት አመፀ፤ ከዳር

እስከዳርም ተንቀሣቀሰ፡፡ በጠቅላላ ወጣቱ አስተማሪውና

ገበሬው ወዛደሩ የመንግስትና የግል ሠራተኞች ሁሉ

ህብረታቸውን አስተባብረውና አጠናክረው በአንድ ድምፅ

ለመሠረታዊ መብቶች ተነሱ፡፡ በተለይ በነፃነትና ለፍትህ

ጮሁ፡፡ የዩኒቨርስቲ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት

ተማሪዎችና አስተማሪዎች እንዲሁም ጠቅላላ ሠራተኛ

ሁሉ ሙሉ ኃይላቸውንና እውቀታቸውን በማስተባበር

ወርቃማ የሆነውን የኢትዮጵያን ጥንታዊ ስልጣኔን አኩሪ

የነፃነት ታሪክ በብዕራቸው አሣምረው በየጋዜጣዎች

አደመቁት፡፡ የፖለቲካ ሂደት ተንታኞች የዚህን ሃያል

የሕዝብ አብዮት የሚመራ ማን ነው ? የሚለውን ወሣኝ

ጥያቄ መልስ ለማወቅ ሩጫቸው ፈጣን ነበር፡፡ ሆኖም ግን

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 23 2004 ዓ.ም.

የእስር ዘመቻው የፖለቲካ አቅጣጫን

ከድጡ ወደ ማጡ…..!!

የህዝብ ፍላጎት ሣይከበር ቀረ፡፡ የኢትዮጵያን ግዛት ወሰን

ለማስከበር በየበረሀው በቀን ሀሩርና በሌሊት ቁር የጦር

ግዳጁን ለመፈፀም ቃል ኪዳን ከገባው ጦር የተውጣጡ

120 ወታደሮች “ደርግ” በሚል ስያሜ የስልጣን አክሊል

ደፋና ስልጣኑን ጨበጡ፡፡ ደርጎቹ ለመድበለ ፓርቲ

ስርዓት እውን መሆን፣ ለሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ

መብቶች መከበር፣ ለነፃ ፕሬስ መሠረት መጣል

ሁኔታዎች መመቻቸት መሥራት ሲገባቸው የተቃራኒውን

መንገድ መረጡ፡፡ በዚህም ኢትዮጵያ በደም አበላ

እንድትታጠብ ግድ ሆነ፡፡ በሀገሪቱ ወታደራዊ ካምፓች

ሣይቀሩ የእስረኞች ማጎሪያ ሆኑ፡፡ እዚህ ላይ የመፃፍ

መብት እስከ 1967 ዓ.ም መጀመሪያ ድረስ እንደነበር

ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የአንድ

የኢትዮጵያ ልጆች እኔ መኢሶን፣ ኢህአፓ ወዝ ሊግ፣

ማሌሬድ ኢጭአት በሠሜን በኩል ያሉት ደግሞ ኢዲዩ፣

ወያኔ፣ ሻቢያ በሚባሉ ድርጅቶች ውስጥ ታቅፈው እርስ

በርስ ተፋጁ፡፡ የብሔራዊ አንድነት ፓርቲ መስርተው

መተባበር ሲገባቸው በራሳቸው መንገድ ተጓዙ፡፡ ደርጎች

ይሄንን ቀዳዳ ተጠቅመው የኢትዮጵያን ወጣቶች ረሸኑ!

ቀሪውንም ሰብስበው አሰሩ፡፡ በተለይ በኢህአፖ ስር

የነበሩት ወጣቶች በአብዛኛው ሰለባ ሆኑ፡፡ ርግጥ ነው

ነጭ ሽብር በሚባለው የመልስ ምት የወታደራዊው

ጁንታ መንግስት ሹሞች እና ደጋፊዎች ወድቀዋል፡፡ ለዚህ

ሁሉ ትርምስ ዋነኛ ተጠያቂው ማእከላዊውን መንግስት

የተቆጣጠረው ቡድን (ደርግ ነው)፡፡ ሰዎቹ የስልጣን

ጥመኞች ባይሆኑ ኑሮ ቢያንስ እርስ በርስ መጠፋፋቱ

ይቀንስ ነበር ባይ ነኝ፡፡ ቁጭ ብሎ በመነጋገር እና ሆደ ሰፊ

በመሆን ኢትዮጵያን ወደ እድገት ጐዳና መውሰድ ሲቻል

ለዚህ ያልታደሉት ከእኔ በላይ ላሳር በማለት የእውር

ድንበር ጉዛአቸውን ቀጠሉ፡፡

በተለይ 60ዎቹ ታላላቅ ሰዎች ርሸና በእግዚአብሄር

ቀጥሎ በሕግ የሚተማመነውን ዜጋ አስደነገጠው፡፡ ፍርድ

ያዋጣኛል የሚለውን የሰዎች እምነት ድምጥማጡን

አጠፋው፡፡ ሰው የሚኖረው በሕግ ተማምኖ ሣይሆን

በደርግ በጎ ፈቃድ መሆኑን ተገነዘበ፡፡ በመሆኑም የቻለ

ማምለጥ ያልቻለ በጭንቀት መኖር ጀመረ፡፡ የጀገነው

ደግሞ ነፍጥ ይዘው ከሚፋለሙት ኃይሎች ተቀላቀለ፡፡

በሕግ ላይ እምነት ጠፋ፡፡ የደህንነት ስሜት ተሟጠጠ፡

፡ በእነኚህና በተለያዩ ምክንያቶች ስርዓቱ እየተሸረሸረ

የነበረው ገና ከጠዋቱ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ “አብዮት

የራሷን ልጆች መልሳ ትባላለች” እንዲሉ ታማኝ

አገልጋዮችን ሣይቀር አስሯል፤ ገሏል፡፡ በጦር ሜዳ

የገጠሙት ተቀናቃኞቹ ድል ሊነሱ ከቻሉበት ዋናው

ምክንያት ደርግ በውሃ ቀጠነ የሠራዊቱን አንዳንድ

አዛዦች (የጦሩን አባላት) በየጊዜው በማሰሩና በመረሸኑ

ነበር፡፡ በሠራዊቱ ፊት ተዋርደው ማእረጋቸው የተገፈፈው

ብርጋዴር ጄኔራል ከበደ ጋሼ እና በሸፍጥ እንዲረሸኑ

የተፈረደባቸው ታሪኩ አይኔ ይጠቀሳሉ፡፡

ግራም ነፈሰ ቀኝ አስራ ሰባት አመት ሙሉ ተቀናቃኞቹን

ሲያስር እና ሲፈታ የነበረው ደርግ ዋነኛ የጦር ተፈላሚዎቹ

በነበሩት ሻቢያና ወያኔ ተገርስሶ ሊወድቅ ችሏል፡፡ ደርግ

የራሱ የሆነ ችግር ቢኖርበትም በአገር ፍቅርና በሉዓላዊነት

ድርድር አልነበረውም፡፡ ለሁለት ዓመት የነበረውን የቀይ

ሽብር ዘመቻ እንዳለ ሆኖ በቀሩት ዓመታት ለህዝብ

የተሻለ ክብር ነበረው፡፡

የደርግ ውድቀት ኢትዮጵያ ለብዙ ሺህ አመታት

ስትጠቀምበት የነበረውን የባህር በሯን አሣጥቷታል፡፡ ይሄ

ከባድ ችግር ይመስለኛል፡፡ በዚህ ምክንያት አሁን ያለው

ትውልድ ዋጋ እየከፈለ ይገኛል፡፡ እንደ ዶክተር ያቆብ ሀ/

ማርያም የጥናት መፅሐፍ ከሆነ ይቺ ደሀ ሀገራችን በቀን 3

ሚሊዮን ዶላር ለወደብ ኪራይ እየከሰከሰች ነው፡፡ ቀደም

ባሉት አመታት ዶሮ ወጥ ሣይቀር እየተሰራ ከድሬደዋ

ይጫንላት የነበረችው ሚጢጢዋ ጅቡቲ እኛን ቁልቁል

ለማየት የበቃችበት አሣፋሪ እና አንገት የሚያስደፋ

ጊዜ ላይ እንገኛለን፡፡ ይህንን ሀቅ የሚክዱ ካሉ እነሱ

ተዋንያኖችና የሥርዓቱ ወንጀለኞች ብቻ ናቸው፡፡

የቀድሞ ሁለት የጦር ሸሪኮች አንደኛው የአስመራን ቤተ

መንግስት በመቆጣጠር አዲስ ሀገር ሲመስርት ሌላው

ደግሞ የምኒልክ ቤተ መንግስትን በመረከብ ቀሪዋን

ኢትዮጵያን መግዛት ጀመረ፡፡

ባለፉት 20 ዓመታት ገዢዎቻችን ምን አዲስ ነገር

አመጡልን ? ምንስ በጐ ነገር አስገኙልን? የፖለቲካ

ተቀናቃኞቻቸው በሠላማዊ እና በህጋዊ መንገድ

እንዲንቀሣቀሱ ከመፍቀድ ጀምሮ ፕሬስ እንዴት

ማስተናገድ ተቻለ? ብለን ስንጠይቅ መልሱ አልጠፋም፤

አለማም፡፡ ሁላችንም እንደምናስታውሰው በወርሀ ግንቦት

1983 በአሜሪካዊው የፖለቲካ ሰው ኸርማን ኮኸን

ቡራኬ ኦነግ የሽግግር መንግስት ከተወሰኑ ድርጅቶች

ጋር በማበር ቢመሠርትም በአጭር ጊዜ ውስጥ የጠብ

ክብሪት በመጫሩ አመራሮቻቸውን በቦሌ ከሸኙ በኋላ

ተራ አባላቶቻቸውን ደግሞ በተለያዩ የጦር ካምፖች

ውስጥ አስሯቸው እንደነበር እናስታውሣለን፡፡ በጣም

አስገራሚው ነገር ግን በኢትዮጵያ ምድር እንቅስቃሴው

አክትሞለታል የተባለው ድርጅት ኦነግ ዛሬ ለብዙዎቹ

ለኦሮሞ ልጆች ሲቃይ ሆኗል፡፡ አባል ነበሩ እየተባሉ ብዙ

ሰዎች መታሰራቸውን ከዜና ምንጮች እናዳምጣለን፡

፡ በእኔ በኩል የኦነግ የፖለቲካ አላማ ለኢትዮጵያ

ይበጃታል ወይንም ይጐዳታል የሚል ክርክር ለማንሣት

ፈልጌ እንዳልሆነ እዚህ ላይ አንባቢን ማስታወስ እሻለሁ፡

፡ ሆኖም ግን አንደኛው የአገዛዝ ከበፊቶቹ አገዛዞች

ስህተቶች መማር አለመቻሉን መመልከት ግን የሚቻል

ይመስለኛል፡፡ እኛ ግን ለምንድን ነው ችግሮቻችን ቁጭ

ብለን መፍታት ያቃተን? እርግማን ይሆን? እስከ መቼ

ነው ሀገሬ ኢትዮጵያ የጉልበተኞች (ጡንቸኞች) እና

የተጨቋኞች ሀገር ሆና የምትቀጥለው? አረ ጎበዝ አለም

ጥሎን ሄደ፡፡ እኛ ዝንተ አለም ሰለ ዲሞክራሲ እና

ሠብአዊ መብቶች ጥበቃ እውን መሆን ስንጮህ ሌላው

አለም የምድርን ሚስጥር በርብሮ ጨርሶ ወደ ሰማይ

ነጎደ፡፡ በእውነት እናሣዝናለን፡፡

ትላንት በቅኝ የተገዙት አፍንጫችን ስር ያሉት ኡጋንዳና

ኬንያ ሣይቀሩ ብዙ ጥለውን ከሄዱ ውለው አድረዋል፡፡

በሩጫው እንኳን በዚህ ዓመቱ የድል ባለቤቶች ሆነዋል፡

፡ እኛ ግን ዛሬም በ21ኛው ክፍለ ዘመን የአሣሪ እና ታሣሪ

ልጆች ሆነናል፡፡ የወያኔ ኢህአዲግ መንግስት በብዙዎች

የሚሞካሽበትና እርሱም ቢሆን የሚመፃደቅበት ቁም ነገር

ቢኖር የመድበለ ፓርቲ ስርአትና የነፃው ፕሬስ እውን

መሆን እንዲችሉ በህግ ሣይቀር ማፅደቁ ይመስለኛል፡፡

ሆኖም ግን ሁለቱም ቢሆኑ ብልጭ ድርግም እያሉ አሁን

የደረሰንበት ጊዜ ላይ ይገኛሉ፡፡ ለማንኛውም ሁለቱም

ያለፉበትን ወጣ ገባ መንገድ በወፍ በረር ላስታውሣችሁ፡

ስርዓቱ የምእራባውያንን ውዳሴ ለማግኘት ሲል

የመድብለ ፓርቲ ስርዓት ቢፈቅድም ገና ከጠዋቱ

ወከባና እስራት ያካሂድ ነበር፡፡ አዛውንቱ ፊት አውራሪ

መኮንን ዶሪ በስርአቱ የፀጥታ ሀይሎች ወከባና እንግልት

ከደረሰባቸው አንዱ እና ዋነኛው ነበሩ፡፡

በጊዮኑ የእርቅ ጉባኤ ለመካፈል ከአውሮፓ ወደ ሀገሩ

የመጣውን ጋሼ አበራ የማነአብን ዛሬ የት እንዳደረሱት

የሚያውቁት አሣሪዎቹ ብቻ ይመስለኛል፡፡ የመጀመሪያው

ኢትዮጵያዊ ቀዶ ህክምና ሐኪም በሙያቸው እናት

አገራቸውን በከፍተኛ ደረጃ በማገልገል ላይ እያሉ የሰዎች

ሠብአዊ መብቶች በመደፈራቸው ለህዝባቸው አንድነትና

ሰብአዊ መከበር በመታገል ህይወታቸውን የሰውት

ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ሌላው የእስር ገፈት ቀማሽ

መሆናቸውን በሀዘን እናስታውሳቸዋለን፡፡

የተፈጥሮ ህግ ነውና የተወለደ ሁሉ ይሞታል፡፡ ሰው

ግን በስራው ህያው ይሆናል፡፡ ከላይ የጠቀስኳቸው እና

ሌሎች ለሀገራቸው ቤዛ የሆኑት እንዲህ አይነት ሰዎች

የነበሩ ናቸው፡፡

በአንድ ወቅት በዚች ሀገር ላይ ጠንካራ የፖለቲካ

ፓርቲ የለም፡፡ (ለምን ይኼ ሆነ) እያሉ የአዞ እንባ

ሲያነቡ የነበሩት ገዢዎቻችን ቅንጅትን የመሰለ መቅሰፍት

አሣያቸው፡፡ እነርሱም ከግንቦት 1997 ዓ.ም የምርጫ

ፌሽታ በፊት ነፃ ሚዲያውን እና በራሣቸው ቁጥጥር ስር

የወደቁትን መገናኛ ብዙሀን ሣይቀር የክርክር መድረክ

እንዲሆኑ ፈቀዱ፡፡ እድሉን ያገኙት ተቃዋሚዎች ደግሞ

ለኢትዮጵያ መፃኢ እድል እጅግ ጠቃሚ ግሩም ሀሣቦችን

ለህዝብ አቀረቡ፡፡ በእውነቱ ለመናገር ከአገዛዙ ሰዎች

ባሻገር ሀገርን በደንብ መምራት የሚችል ጭንቅላት

በተቃዋሚው ጐራ እንደተሰባሰበ ያሣየ ትእይንት ነበር፡

፡ የግንቦት 1997 የምርጫ ውድድር ግን ምን ያደርጋል

ፈረሱም ሜዳው ይሄው ሲሉን የነበሩት ገዢዎቻችን

የምርጫው ውጤት ሙሉ በሙሉ ሳይጠናቀቅ እውነተኛ

ምስላቸውን ለኢትዮጵያ ህዝብ አሣዩት፡፡ ያ በዲሞክራሲና

ሰብአዊ መብቶች እውን መሆን ተስፋ ያደረገ፡፡ እንዲሁም

ጨዋነቱን እና አዋቂነቱን ሚያዚያ 30,1997 ዓ.ም

ለወዳጅም ለጠላትም አሣየ፡፡ ያ ታላቅ ህዝብ ኢትዮጵያ

ሊያልፍላት ነው፡፡ በማለት በደስታ እንባ በእንባ የተራጨ

ህዝብ ድምጹ ተቀማ፡፡ ውጤቱም የተገላቢጦሽ ሆነ፡፡

ያሣዝናል! ማሳዘን ብቻ አይደለም ልብ ያቆስላል፡፡ ህሊናን

ያደማል፤ ሆድንም ይበጠብጣል፡፡

ጨዋታው ፈረሠ ዳቦው (ኬኩ) ተቆረሰ እንዲሉ

ያ ብዙ የተደከመበት ታላቅ ቁም ነገር ውጤቱ ከንቱ

ሆኖ ቀረ፡፡ በተለይ በአገዛዙ እርምጃ የተነሣ ሁላችንም

እንደምናስታውሰው አገዛዙ ከ60 በላይ የቅንጅት

ፓርቲ ከፍተኛ አመራርን ጨምሮ በርካታ የነፃው ፕሬስ

አረበኞችን በዝነኛው የቃሊቲ እስር ቤት ለሁለት አመት

ካቆያቸው በኋላ በዓለም አቀፉ ህብረተሰብ ውትወታ

ውጪ ሀገር በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ያልተቋረጠ ሰላማዊ

ሰልፍ ምክንያት የተነሳ በመጨረሻ ላይ ደግሞ በሽምግልና

ተለቀቁ፡፡ ሰዎቹ ከጨለማ ከወጡ በኋላ ግን የነበራቸው

ህብረትና መንፈሣዊ ጥንካሬ አብሯቸው አልነበረም፡፡

15

በአጭሩ አንድ የነበሩት ብዙ ቦታ ተከፋፈሉና ተዳከሙ፡

፡ እዚህ ላይ መኢአድ አሁን የሚገኝበትን አሳዛኝ ገፅታ

ማስተዋል ተገቢ ነው ባይ ነኝ፡፡

አገዛዙም የልቡ ደርሷልና፡፡ ከበሮውን መደለቅና

መዝፈንም አማረው፡፡ ሆኖም ግን ደስታው በእውነት

ላይ የተመሠረተ ባለመሆኑ ተገኘ የተባለው ውጤት

አሁን አሁን የእንቧይ ካብነቱን እያሣየን ይገኛል፡፡ በሌላ

በኩል በብዙ ሺህ የሚቆጠሩትን የቅንጅት ፓርቲ ደጋፊ

የነበሩትን ሰዎች በተለያዩ ማጎሪያዎች ማሰሩን እዚህ ላይ

ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡ አገዛዙ ብዙ ሺዎችን ቢያስርም

የሰውን መንፈስ ማሰር ባለመቻሉ ዛሬም ቢሆን የሰላማዊ

ትግሉ ሞቶ የተቀበረ አይመስለኝም፡፡

የአገዛዝ ስርዓት ምን ጊዜም ቢሆን ካለፈው ስህተቱ

ወይንም ካለፉት መሰል ስርዓቶች ለመማር ተፈጥሮው

አይፈቅድለትምና ዛሬም በተሣሣተ ጐዳና ላይ ጉዞውን

ቀጥሏል፡፡

ይቅንጅትን አካል ከፋፍዬዋለሁ በማለት ሲኩራራ

የነበረው ስርዓት (በነገራችን ላይ ለቅንጅት መፈረካከስ

ዋነኛው ተጠያቂ መንግስት ብቻ ሳይሆን በውስጡ

የበቀሉ የስልጣን ጥመኞችም ጭምር እንደሆኑ መታወቅ

ይኖርበታል) የሰውን መንፈስ ማሸነፍ ስለማይሆንለት

ዛሬም ቢሆን በሠላማዊ እና በሰለጠነ መንገድ የዲሞክራሲና

የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ለመሆን ከተዘጋጁ ሰዎች ጋር

ፊት ለፊት መግጠም ግድ ሆኖበታል፡፡

ከግንቦት 1997 ዓ.ም ወዲህ ቦግ እልም እያለ የመጣው

የፖለቲካ ፓርቲ አባላትን የማሣደድ ዘመቻው ካለፈው

ሰኔ 2003ዓ.ም ወዲህ አገርሽቶበት ጋዜጠኞች እና ታዋቂ

የፖለቲካ ሰዎችን “አሸባሪ” የሚል ታፔላ በመለጠፍ ሰለባ

እያደረገ ይገኛል፡፡ ይሄ ድርጊት የኢትዮጵያን ፖለቲካ

አቅጣጫ ከድጡ ወደ ማጡ እንዳይዶለው ብዙዎችን

አስግቷል፡፡

የነፃው ፕሬስ ከተወለደ ወዲህ አብዛኛዎቹ ጋዜጠኞች

በደረሰባቸው መንገላታትና እስር ምክንያት ወይ ሀገሪቱን

ጥለውላቸው ሄደዋል አሊያም ብእርቸውን አስቀምጠው

በአርምሞ ላይ ይገኛሉ፡፡

ዛሬ በብእሩ ታአምር ሲሰራ የነበረው ጋሼ ሙሉጌታ

ሉሌ፣ የጦቢያው ፖለቲካ ተንታኝ ሀሰን አብደላ፣ ጋሼ

ክፍሌ ሙላት፣ ከፍያለው ማሞ፣ አንተነህ መርእድ፣

ሲሳይ አጌና ወዘተ…. የሚወዷትን ሀገራቸውን ጥለው

ሲሰደዱ አንጋፋው ጋዜጠኛ ጎሹ ሞገስ፣ አረጋ ወ/ቂርቆስ፣

ታዬ በላቸው ትእግስት አብርሀም ወዘተ ብእራቸውን

አስቀምጠዋል ወይንም በሌላ ሥራ ተሠማርተዋል፡፡ ልበ

ሙሉው እስክንድር ግን ከጋዜጠኝነት ህይወት ውጭ ሌላ

ሕይወት የለኝም በማለት አሁን ድረስ ሀሣቡን በአደባባይ

በመግለጡ ለጨለማ ሕይወትና ብዕር የጨበጠባቸው

እጆቹ ለካቴና ተዳርገዋል፡፡ እዚህ ላይ እስክንድር

የታሰረበት ምክንያት ትክክለኛ ነው አይደለም በማለት

አሣሪውን ክፍል ለመሞገት ብእሬን ያነሣሁ አለመሆኔን

አንባቢ እንዲረዳልኝ፡፡ የአንድን ሀገር ፖለቲካዊ ችግር

ለመፍታት የፖሊስ እስር ችግር ለመፍታት የፖሊስ

እስር መፍትሄ መሆን እንደማይችል ግን መጠቆም

እሻለሁ፡፡ የሚያቀርቡባቸውን ወይም የፖለቲካ ፓርቲ

አመራሮችን (አባላትን) በሰበብ አስባቡ ወደ ወህኒ አምባ

ማስገባት እንደማያዋጣቸው ቀድመው ቢረዱት መልካም

ይመስለኛል፡፡

እንደ መደምደሚያ

በፅሁፌ ውስጥ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት በዚች ሀገር

ላይ መድበለ ፓርቲ ስርዓት እውን እንዲሆን ገዢዎቻችን

መፍቀዳቸው በጎ ተግባር ሆኖ ሣለ አንገታቸውን ቀና

አድርገው ተግባራቸውን እንዳያከናውኑ ጋሬጣዎችን

ማብዛት አሣዛኙ ገፅታ ነው፡፡ አባቶች ስጋ አቅርቦ ቢለዋ

መንሳት ነው የሚሉት?

በእውነቱ ለመናገር አሁን እንደ ትሮይ ፈረስ

የሚጋልቡንን ካለፉት ገዢዎች ጋር ማነፃፀሩ እድለኞች

ይመስሉኛል፡፡ ምክንያቱም እራሳቸውን ለማሻሻል

(ፖሊሲያቸውን ለመከለስ) ብዙ አጋጣሚዎችን ያገኙ

በመሆኑ ነው፡፡

ታላላቅ ሊቃውንት ምርጥ የፖለቲካ ሀያሲና ተንታኞች

እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች (በተለይ በሀገር

ቤት የሚንቀሳቀሱት) በርካታ ምክሮችን ለግሰዋቸው

ነበር፡፡ ሆኖም ግን የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ በማለት እዚህ

ደርሰዋል፡፡ እውን “ውሾቹ ይጮሀሉ ግመሉ ጉዞውን

ይቀጥላል” የሚለው መራር ቀልድ እየተነገረን እና

የፖለቲካ ሂስ ተቺዎችና መካሪዎችን እስር ቤት በመወር

ወር የስልጣን እድሜን ማራዘም የሚቻል አይመስለኝም፡

፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ያለበት ችግር የዳቦ ርሀብ ብቻ

አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ የዲሞክራሲና የሰብአዊ

መብት አከባበር ጥማት አድሮበታል፡፡ ስለሆነም የህዝቡ

ፍላጐት ቢጠና መልካም ነው ባይ ነኝ፡፡ በአንፃሩ

በፖለቲካ ፓርቲ ፊት አውራሪዎችና በተቺ ጋዜጠኞች

ላይ ታፔላ እየለጠፉ ዘብጥያ መወርወር ለጊዜው የጠቀመ

ወደ 11 የዞሯል

www.andinet.org.et

16

www.andinet.org.et

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 23 2004 ዓ.ም.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.10

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!