የመሬት ቅርምት ለልማት - Ethiopia: A voice for the voiceless
የመሬት ቅርምት ለልማት - Ethiopia: A voice for the voiceless
የመሬት ቅርምት ለልማት - Ethiopia: A voice for the voiceless
Create successful ePaper yourself
Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.
4

ፍኖተ -ነፃነት ጋዜጣ ሐምሌ 2ዐዐ3 ዓ.ም

ተመሠረተ፡፡ ፍኖተ ነፃነት በአንድነት ለዴሞክራሲና

ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ሥር የሚታተም

በፖለቲካዊ፣ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ፣ በወቅታዊ ጉዳዮችና

በመዝናኛ ላይ የሚያተኩር የፓርቲው ጋዜጣ ነው፡፡

ጋዜጣችን እንደ ፓርቲ ልሳን ብቻ

ሳይሆን እንደ አንድ ሚዛናዊ የግል

ጋዜጣ ሆኖ ማገልገል ይፈልጋል

የማንኛዉም ሰዉ ሀሳብና አመለካከት

የሚስተናገድበትና የሚንሸራሸርበት

እንዲሆን እንሻለን ሰፊና ረዝም የሚዲያ

ሽፋን ያለዉ ኢህአዴግም በዚህ ሚዲያ

አቋሙንና ፖሊሲዉን ለማቅረብ ቢፈልግ

ክፍት ነዉ

ዋና አዘጋጅ፡-

አንዳርጌ መሥፍን

አድራሻ፡-

የካ ክ/ከተማ ወረዳ 12

የቤ.ቁ አዲስ

አዘጋጆች፡-

ብዙአየሁ ወንድሙ

ብስራት ወ/ሚካኤል

አምደኞች፡- ዶ/ር ኃይሉ አርዓያ

ኢ/ር ዘለቀ ረዲ

አንዱዓለም አራጌ

ግርማ ሠይፉ

ዳምጠው አለማየሁ

ተስፋዬ ደጉ

በላይ ፍቃደ

ወንድሙ ኢብሳ

ኮምፒውተር ጽሑፍ፡-

የሺ ሃብቴ

ብርቱካን መንገሻ

አከፋፋይ፡-

ነብዩ ሞገስ

አሣታሚው፡-

አንድነት ለዴሞክሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት)

አድራሻ፡- አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 07 የቤ.ቁ አዲስ

አታሚ፡- ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት

አራዳ ክ/ከተማ ቀበሌ 07 የቤ.ቁ 984

የዝግጅት ክፍሉ

ስልክ +251 922 11 17 62

+251 913 05 69 42

+251 118-44 08 40

ፖ.ሳ.ቁ፡ 4222

ኢሜይል፡- udjparty@gmail.com

andinet@andinet.org

ፋክስ ቁጥር፡- +251-111226288

www.andinet.org.et

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 23 2004 ዓ.ም.

ርዕሰ አንቀፅ

ያለማቋረጥ እያደገ ያለው የዋጋ ንረት

መልህቅ ይበጅለት

ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ የሃገራችን የገበያ ሁኔታ ይበልጥ እየተቃወሰና ከቀን ወደ ቀን እየታመሰ

ቀጥሏል፡፡ የሕብረተሰቡ የኑሮ ሁኔታም ከድጡ ወደ ማጡ እየሆነበት መሠረታዊ የሆኑ የዕለት

ፍላጎቶችን ማሟላት እየቸገረው ነው፡፡

በ1997 ዓ.ም 6.8% የነበረው የዋጋ ንረት በተከታዮቹ ሁለት አመታት 12.3 በመቶ እና 15. 8

በመቶ ደረሰ፡፡ ይህም ማለት የንረቱ እድገት መጠን በሁለት ዓመት ውስጥ 132 በመቶ ሆነ ማለት

ነው፡፡ ከ1999 ዓ.ም በኋላ ያሉት አራት ዓመታት አጠቃላይ የዋጋ ንረት መጠንን ስንመለከት

ደግሞ 1999 ላይ 15.8 በመቶ የነበረው በ2003 ዓ.ም 57 በመቶ ደርሷል፡፡ ይህም አጠቃላይ

የአራት ዓመት የዋጋ ንረት እድገቱን 36ዐ.7 ፕርሰንት መድረሱን ያመላክታል፡፡

ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ ያሉትን ስድስት ዓመታት አጠቃላይ የዋጋ ንረት እድገት ስንመለከት

ደግሞ 714% ይሆናል፡፡ ይህም ማለት የገንዘብ የመግዛት አቅም ባለፉት ስድስት ዓመታት በ714

ፕርሰንት ወድቋል ማለት ነው፡፡

በአንፃሩ አማካይ ዓመታዊ ገቢ በ1997 ዓ.ም 165 ዶላር የነበረ ሲሆን አሁን 35ዐ ዶላር

እንደደረሰ የአይኤም ኤፍ ሪፖርት ያመለክታል፡፡ ባለፉት ስድስት ዓመታት አማካይ አመታዊ ገቢ

በ112 በመቶ አድጓል ማለት ነው፡፡

ከላይ ከተመለከቱት መረጃዎች የምንረዳው በስድስት ዓመቱ የገቢ እድገትና የዋጋ ንረት

እድገት መካከል የ602 በመቶ ልዩነት እንዳለ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ

በ1999 ዓ.ም ይኖር የነበረውን ኑሮ ዛሬ ለመኖር እንዲችል የዋጋ ንረቱ ከ14.4 በመቶ መብለጥ

አልነበረበትም ወይም አማካይ አመታዊ ገቢ 1171.5 ዶላር መድረስ ነበረበት፡፡

በሃብታሙና በድሃው ዜጋ መካከል ያለው የሃብት ክፍተት እየሰፋ መሄድ እንዳለ ሆኖ

የኢትዮጵያውያን የድህነት ደረጃ ባለፉት ስድስት ዓመታት በ324.7 በመቶ እንዳደገ መረዳት

ይቻላል፡፡ ይህንን አሰቃቂ ሁኔታ ይበልጥ አስፈሪ የሚያደርገው ገዢው ፓርቲ ችግሩን ለማስወገድ

ቀርቶ ባለበት እንኳን ለማስቆም አለመቻሉ ነው፡፡ እየወሰዳቸው ያሉት ርምጃዎችም አስተውሎት

የጎደላቸው በመሆናቸው ችግሩን የበለጠ ሲያባብሱት እንጂ ሲቀንሱት አልታዩም፡፡

የኢኮኖሚ ኃይሎች (ፍላጎትና አቅርቦት) ገበያውን መምራት ሲሳናቸው መንግሥት ጣልቃ

ገብቶ ማረጋጋት እንዳለበት እምነታችን ነው፡፡ ይህ ሲባል ግን መንግሥት የገበያ ኃይሎችን

መቆጣጠር ወይም መተካት አለበት ማለት አይደለም፡፡ በትክክል መሥራት እንዲችሉ የሚረዱ

የፊስካልና የገንዘብ ፖሊሲዎችን ተግባራዊ በማድረግ የኢኮኖሚውን አቅም ያጠናክራል እንጂ፡፡

በእርግጥ ገዢው ፓርቲ ገበያውን ለማረጋጋት የተለያዩ የፖሊሲና የቀጥተኛ ጣልቃ ገብነት

ርምጃዎችን ወስዷል፡፡ እዚህ ላይ የሚነሳው ዋናው ጥያቄ ታዲያ ለምን የዋጋ ንረቱ የበለጠ

እየተባባሰ ሄዴ? የሚለው ነው፡፡

የኢህአዴግ መሠረታዊ ችግር የችግሩን መነሻ ለይቶ ለማወቅ አለመቻሉ ላይ ነው፡፡ ኢህአዴግ

የዋጋ ንረቱ በተከታታይ እየተመዘገበ ያለው የኢኮኖሚ እድገት የፈጠረው ነው ብሎ ያምናል፡፡

እ.ኤ.አ በ1929 በአሜሪካ የተከሰተው የኢኮኖሚ ዝቅጠትን ተከትሎ የተስፋፋው

የኬንዚያውያን (Keynesian) የምጣኔ ኃብት ባለሙያዎች አስተሳሰብ በምጣኔ ኃብት እድገትና

በዋጋ ንረት መካከል ቀጥተኛ ግንኙነት ስለአለ መንግሥት በከፍተኛ ኢንቨስትመንትና የሥራ

ዕድል ፈጠራ ኢኮኖሚውን ሲያሳድግ የሕዝብ ገቢም አብሮ ያድጋል የሚል ነው፡፡ በመሆኑም

የፍጆታ ወጪ መጠን ይጨምራል፡፡ ይህም የሸቀጦችና የአገልግሎት ዋጋ እንዲንር ያደርጋል የሚል

በመሆኑም ኢኮኖሚው ባደገ ቁጥር የዋጋ ንረቱም ይቀጥላል ማለት ነበር፡፡

ይህ አስተሣሰብ በወቅቱ ትክክለኛ የነበረ ቢሆን በ1970ዎቹ የታየው የስራ አጥነትና የዋጋ

ንረት “Stagflation” በተመሣሣይ ጊዜ በመከሰቱ (Stagflation) ውድቅ እንዲሆን አድርጎታል፡፡

በሃገራችን በአሁኑ ሠዓት እየታየ ያለው ክስተትም ከ1970ዎቹ የምዕራባውያን የኢኮኖሚ ቀውስ

ጋር ተመሣሣይነት አለው፡፡

የዋጋ ንረቱ ሥራ አጥነቱ በእጅጉ እየተባባሱ ናቸው፡፡ ከገቢ አንፃር ሲታይም ከላይ

እንደተገለፀው ባለፉት ስድስት ዓመታት ውስጥ የዋጋ ንረት በ714 በመቶ ሲያድግ ዓመታዊ ገቢ

በ112 ፕርሰንት ብቻ ነው ያደገው፡፡ በመሆኑም በሃገራችን ያለው የዋጋ ንረት የኢኮኖሚው እድገት

የወለደው ነው ሊባል ፈፅሞ አይችልም፡፡

በአንድነት ፓርቲ ዕምነት እይታ የዋጋ ንረቱ መሠረታዊ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፡-

1. መንግሥት ከፍተኛ ብዛት ያላቸው የገንዘብ ኖቶችን አሣትሞ በኢኮኖሚው ውስጥ

መርጨቱ፣

2. የመንግሥት ወጪ መጠን በከፍተኛ ደረጃ እያደገ መምጣቱ፤ ይህም በሃገር ውስጥ

ምርት አቅርቦት እድገት አለመደገፉ፣

3. በውጭ ምርቶች ላይ መሠረቱን የጣለው አቅርቦትና የውጭ አገር ምርቶች ዋጋ

መናሩ፣

4. የብር ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየወደቀ መምጣትና የውጭ ምርት አቅርቦትና ፍላጐት

አለመጣጣም፣

5. የመንግሥት የነዳጅ ድጎማ መነሳት፣

6. የመሠረታዊ ዕቃዎች ፍላጎትና አቅርቦት ከፍተኛ ሁኔታ አለመጣጣም፣

7. መንግሥት የግሉን ዘርፍ ተክቶ አቅርቦትና ሥርጭትን ለመቆጣጠር የሚያደርገው

ጥረት፣

8. በግል ባንኮች ላይ ተጥሎ የነበረው የብድር ጣሪያ የአገር ውስጥ ምርትንና ከውጭ

የሚገቡ ሸቀጦችን አቅርቦት መገደቡ፣

9. በግል ባንኮች ላይ የተጣለው የግምጃ ቤት ሰነድ ግዢ ግዴታ የሃገር ውስጥ ምርትንና

ከውጭ የሚገቡ ሸቀጦች አቅርቦትን የሚገድብ መሆኑ የሚፈጥረው የአቅርቦት እጥረት፣

10. በመሬት ፖሊሲው ምክንያት የመሬትና የገበሬው ምርታማነት መቀነስ፡፡ ይህንንም

ተከትሎ የሃገር ውስጥ ምርት አቅርቦትና ፍላጎት አለመጣጣም፣

11. የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ውስንነትና የዜጎች ከክልል ወደ ክልል ተንቀሳቅሶ የመሥራት

መብት መገደብን ተከትሎ የምርትና የሰው ኃብት እንቅስቃሴ መወሰኑ፡፡ በዚህም ምክንያት የሰው

ኃብትና ምትርት ከፍተኛ አቅርቦት ካለበት አካባቢ ወደ ከፍተኛ ፍላጎት ያለበት ቦታ ለመንቀሳቀስ

አለመቻሉ በሃገራችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ በመምጣት ላይ ላለው የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነት

ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው፡፡

እነዚህን ችግሮች በአንክሮ ስንመለከት የሁሉም ምክንያቶች መነሻ የተዛቡ የመንግሥት

ፖሊሲዎችና አስተውሎት የጎደለው የመንግሥት ጣልቃ ገብነት እንደሆነ እንረዳለን፡፡

በመሆኑም መንግሥት ይህን ውስብስብ ችግር ለመፍታት ቁርጠኝነቱ ካለው በመጀመሪያ

ደረጃ የልማት እስትራቴጂውና ፖሊሲዎቹ ላይ መሠረታዊ ለውጥ ሊያደርግና ከግብታዊ ጣልቃ

ገብነት ሊቆጠብ ይገባል፡፡ ይህን የማያደርግ ከሆነ ግን እየተባባሰ ያለው የኑሮ ውድነትና የዋጋ ንረት

ማቆሚያ የሌለው እንደሚሆንና ካሁኑ የባሰ የተወሳሰበ ሰብአዊና ማሕበራዊ ቀውስ ሊያስከትል

እንደሚችል ልብ ሊል ይገባል፡፡

ነፃ አስተያት

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.10

“ማነው ተው

የሚለኝ?!”

ይድነቃቸው ዐይኔ

አብዛኛዎቻችሁ የዚህን ጽሁፍ ርዕስ ስታዩ የብርሃኑ ተዘራን ማነው

ተው የሚለኝ ማነው? የሚለውን ዘፈን ታስታውሱታላችሁ

ብዬ እገምታለሁ፡፡ ወይም ደግሞ በሰፈራችሁ፣ በአካባቢያችሁ

እና በመንደራችሁ ስፓርታዊ እንቅስቃሴን (በተለይም ክብደት

ማንሳትን) ለፀብ እንጂ ለፀባይ የማይሰሩ በትዕቢት የተሞሉ

ጐረምሶች እና ወጣቶች ማነው ተው የሚለኝ አፍንጫውን

እለዋለሁ፤ የሚለውን አባባል በተደጋጋሚ ስለሚጠቀሙት እነሱ

ትዝ ….. ብለዋችሁ ይሆናል፡፡ እኔ ግን በጽሁፌ ላስታውሳችሁ

የምፈልገው፤ ከሁሉም በላይ አባባሉን በመጠቀም ላይ

ስለሚገኘው እና በተግባር ስለሚያውለው እንዲሁም በዚህ

ድርጊቱ አቻ ስላልተገኘለት አካል ነው፡፡

የመቶ በመቶ የምርጫ ድል (ዘጠና ዘጠኝ ነጥብ ምናምን

የሚለውን ቁጥር ያልተጠቀምኩት አውቄ ነው፡፡ ምክንያቱም ይህ

ገለፃ፤ ምርጫው ሰማንያ በመቶ የማሸነፍ ያህል ያስመስለዋል፡፡

ሥነልቡናዊ ጥቅም አላት፡፡) ከኔ በላይ ለአገሪቱ ተቆርቆሪ ወገን

የለም ብሎ የሚያስብ ገዢ ፓርቲ እና ይህን ሀሳብ የመጨረሻ

እውነት አድርጐ የሚቆጥር የካድሬ ጐርፍ፣ የማያባራ የምሁራን

እና የዜጐች ስደት (ያውም በሬድዮ ጭምር በሚለፍፉ የውጭ አገር

የሥራ ዕድል ማስታወቂያ በሚቀርብበት ሁኔታ ላይ እስክንደርስ፡

፡)፣ በዘፈቀደ የተቀመጠ ግትር ፖሊሲ መቃብራቸውን መማስ፣

የታዋቂ ፖለቲከኞች እና የጋዜጠኞች እስር እና ወከባ እንዲሁም

ተመሳሳይ ሕዝባዊ በደሎች፤ በተጨማሪም የመልካም አስተዳደር

እጦት እና የሙስና መንሰራፋት የተባባሱት እና የተበራከቱት

በሌላ በማንም አይደለም፡፡ ማነው ተው የሚለኝ? ሊጠይቀኝ

የሚችል ከኔ ጋር የተጠጋጋ ኃይል ያለው አካል ከወዴት አለ?

እኔን የሚመጥን ጉልበተኛ ማን አለ? ከኔ በላይ አዋቂ፣ ከኔ በላይ

ብልህ፣ ከኔ በላይ አስተዳዳሪ ለዘበት በሚል መንግስት እንጂ፡፡

ኢሕአዴግ ከጊዜ ወደ ጊዜ ሥር እየሰደደ በመጣው ኃይሉ እና

ባለው የፖለቲካ ሥልጣን ልዕልና በመጠቀም፤ በእያንዳንዱ

እርምጃ እና ድርጊት ያለመጠየቅን ፀጋ ተጐናጽፏል፡፡ ምርጫው

ሙሉ ለሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ማሸነፉን እንደ በጐ

ዴሞክራሲያዊ አካሄድ ማየት፣ የፈለጉትን ሕግ በፓርላማ ማፅደቅ

እና በዚህ ሕግ ሌሎችን ማሸማቀቅ እንዲሁም ማስጨነቅ፣

የሌሎችን ሀሳብ እንደ መናኛ ቆጥሮ የራስን ሀሳብ ብቻ መናገር

እና ማስነገር (የሀገሪቱን ትላልቅ እና ኃይል ያላቸው የመገናኛ

ብዙሀንን ለራስ ብቻ በማዋል የሌሎችን ሀሳብ በመገደብ፡፡)፣

ሌሎችን ባለድርሻ አካላት ሳያማክሩ አገሪቷን አደጋ ላይ ሊጥሉ

የሚችሉ ፖለቲካዊ እና ሥነ ምጣኔያዊ ውሳኔዎችን ማስተላለፍ፤

ተው የሚለኝ ካለ፤ ይሞክረኝ! የሚል ሀላፊነት የጐደለው

መልዕክት ማስተላለፍ እንጂ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል?

በየወንዙ ዳር መቀደስ

የተኛን ሴጣን ለመቀስቀስ

ይህ አባባል በሁለት መስመር ቃላት ብዙ ማለት ከሚችሉ

ኢትዮጵያውያት ሴቶች ከተናገሯቸው አባባሎች አንዱ እንደሆነ

አምናለሁ፡፡ የእምነት ሰው ነኝ፣ የእግዚአብሄርን ስም ከኔ ወዲያ

ማን ያውቃል? ከኔ በላይስ ክርስቲያን አለ? እንደው ከኔ ወዲያ

ቀዳሽ በአገሪቱ ይኖር ይሆን? ብሎ በእምነት ሳይሆን በትዕቢት

አለፍ ሲልም በሞኝነት የተሞላ ሰው የሚያደርገው አድራጐትን

ይገልፃል አባባሉ የዚህ ሁሉ ቅዳሴ እና የእግዚአብሄርን

ስም መጥራት ሰይጣንን ከመቀስቀስ አልፎ አምላክ ዘንድ

እንደማይደርስ ይገልፃል አባባሉ፡፡

ይህንን አባባል ከተናገሩት ቀደምት ሊቃውንት ሁለቱን መስመር

ተውሼ የሰሞኑን የመንግስታችንን ድርጊት ልመዝን፡፡

የፀረ- ሽብርተኝነት ሕግ አዋጁ እና ዘመቻው ሁሉንም ባለድርሻ

አካላት ባግባብ እና ባሳተፈ መልኩ እንዳልተደረገ ለመናገር

ኢትዮጵያዊ መሆን በቂ ነው፡፡ ከዛ ባለፈ የፓርላማን ውሎ

እና ፓርላማው ነገሮችን በምን ፍጥነት አይቶ በምን ፍጥነት

እንደሚያፀድቅ በቴሌቪዥን መስኮት ማየት ይበቃል፡፡

ፓርቲው የሚያቀርበው ሀሳብ በሙሉ የኔ ሀሳብ ነው፡፡ ፓርቲዬ

የሚያቀርበው ሀሳብ በፍፁም እኔን አደጋ ላይ አይጥለኝም፤ በሚል

የራስን ሀሳብ ገሎ በሌሎች ተጨፍልቆ የማሰብ አዙሪት ውስጥ

በገቡ ሰዎች፤ ስንት ማህበራዊ እና ሀገራዊ አደጋን የሚያስከትሉ

ፖሊሲዎች እና አዋጆች ጸድቀዋል?

በኑሮ ውድነት፣ በአንድ ፓርቲ እና በአንድ ሰው የበላይነት

በዴሞክራሲ እና በብልሹ አስተዳደር እንዲሁም ቀጣይነት

በሌላቸው እና ፖለቲካዊ ዓላማቸውን እስካልሳቱ ብቻ በሚጸድቁ

ፖሊሲዎች የተሰላቸው ህዝብ፣ አነሰም በዛም የሚያውቃቸውን

እና የሚያከብራቸውን ከመንግስት በተቃራኒው የቆሙትን

ፓለቲከኞች እና ጋዜጠኞች በሽብርተኝት ታርጋ ከለላ ወደ

እስር ቤት መወርወር፤ ግለሰቦቹን እና ደጋፊዎቻቸውን ብሎም

ጋዜጣችን “ፍኖተ-ነፃነት” ብለናታል፡፡ “ፍኖት” ማለት መንገድ ማለት ሲሆን ከነፃነት ጋር

ሲጣመር “የነፃነት መንገድ” ማለት ነው!! ወደ 7 የዞሯል