24.08.2013 Views

የመሬት ቅርምት ለልማት - Ethiopia: A voice for the voiceless

የመሬት ቅርምት ለልማት - Ethiopia: A voice for the voiceless

የመሬት ቅርምት ለልማት - Ethiopia: A voice for the voiceless

SHOW MORE
SHOW LESS

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.10

ከወንድሙ ኢብሣ

ፖለቲካ

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 23 2004 ዓ.ም.

ያለ ታላላቅ ሰዎች አገር ትልቅና

ባለፀጋ ልትሆን አትችልም

በዚህ ርዕስ ሥር ክፍል ሁለትን የቀጠልኩበት ሁለትን

ምክንያቶች ናቸው፡፡ አንደኛ ርዕሱ ሰፊ ስለሆነና በቀድሞ

ጽሑፌ የመጨረሻ ሐረጐችን ትንሽ ለማብራራትና የአገር

አባቶችን የታላቅነት ሚናን ጐላና ረገጥ አድርጌ ለማሳየትና

ስለሱማሌ ሞቃዲሾ ታላላቆች አልቦ ያልኩትን በራሴ

ለማረም አስቤ ነው፡፡

ከሁለተኛው ልጀምር፡፡ እውነትም በዛሬ የዓለም ተጨባጭ

ሁኔታ ከ10 ዓመታት በላይና በእስከ ዛሬም በራሱ ለራሱ

የመንግሥት ሥራ በብቃት በሚከውን መንግሥት አልባ

ወይም ደካማ መንግሥት ያሉት የሞቃደሾ ሱማሌ አገዛዝ

ታላላቆች አጥተው ወይስ የታላላቆቹዋ እርስ በርስ

መታጣጣት ወይንም አለመግባባት ነው የሚለው ጥያቄ

ቢነሳ ተገቢ ነው፡፡

አዎን በቀደም ጽሑፌ እንደገለጽኩት የትኛውም አገር

ታላላቆች አልቦ አትሆንም፡፡ የሱማሌ ሞቃዲሾም አልባ

አትሆንም፡፡ ይመረጣል፡፡ ችግሩ የሞቃዲሾ ሱማሌዎች

ትልልቆች እያሏቸው ትልልቆቹ አንድም ወደ ጐረቤት

አገሮች ለወረራ የሚቅበዘበዙ (በ1969 ዓ.ም የኢትዮጵያን

ወሰን አልፈው ወረዋል፡፡ ይህ እንግዲህ) የፕሮፖጋንዳ

ጦርነት የመንዛት አባዜ ባለቤት ስለሆኑ ነው፡፡

በተጨማሪም ትልልቆች ካልተደማመጡ ትንንሽ፣መናኛና

ደካማ ተደርገው ስለሚታዩ ነው፡፡ ትልልቆች

ይከበራሉ፤ይደመጣሉ፤የሞቃዲሾ ሱማሌ ችግር ይህ ነው፡፡

የአንድ አገር ታላላቆች እርስ በርስ መግባባት

ካልቻሉ፣መከባበር ከዕቃቸው፣መደማመጥ

ከሰለቻቸው፣ችኮና “ጉግማንጉጎች” ይሆናሉ፡፡

ጉግማንጉጎች የበዙበት አገር ጭላንጭልና ተስፋ ይጠፋል፡

፡ ሌላ ቀርቶ ለአንድ አገር ጥሩና ዴሞክራቲክ መንግሥት

ባይፈጠር እንኳ ከመንግሥት አባልነትና ከመግባታችን

አምባገነን አገዛዝ (መንግሥት) ያስፈልጋል ብዬ አምናለሁ፡

፡ በሞቃዲሾ ሱማሌ የጠፋው ይህ ነው፡፡ በዛሬ ጥሩና

መልካም አስተዳደር የመሠረቱ አገሮች አምባገነን የነበሩ

ነበሩ፡፡ በመሆኑም በአንድነት ቆመው አብረው ተባብረው

ሲያበቁ አንባገነን አገዛዝን ወደ ዴሞክራሲያዊ አመራር

ለውጠዋል፡፡

የትላንትናን ደ/አፍሪካ አፓርታይድ አገዛዝን አስቡልኝ፡፡ በሃያ

ዓመታት ውስጥ ሰዎችን ከዘር ከቀለም ተከፋፍለው፣በትም/

ቤት፣በገበያ፣በመንደር አመሠራረት አሰቃቂና ጨካኝ

“የጉግማንጉግ” የሞኝ ፖለቲከኞች ፖለቲካ በፍሬድሬክ

ኤንግልስ (የነጭ የመጨረሻ አፓርታይድ ገዥ) እና በታላቁ

ማንዴላ አርቆ አስተዋይነት የዛሬ ደ/አፍሪካ ከአፍሪካውያን

አንባገነን አገሮች መጨረሻ ተነስታ ዛሬ ከዴሞክራሲያዊ

መንግሥት ቀድማ ተጠቃሽ አገር ናት፡፡ ኢትዮጵያ በዚሁ

ዓመት ከደርግ ተላቀቀች ግን ከደቡብ አፍሪካ ዴሞክራሲዊ

አስተዳደር ጋር አትነፃፀርም፡፡ ሰማይና መድር ናት፡፡ ዛሬ

እኛ ገና አንባገነን ነን፡፡

ስለዚህ ነው አንድ አገር መንግሥት አልባ ከመሆን

አንባገነን መንግሥትም ቢሆን ሊመረጥ የገባል የምለው፡

፡ የሞቃዲሾ ሱማሌ ታላላቆች ጥሩና መልካም አስተዳደር

መመሥረት ቢያቅታቸው “ይህችን ያልተከፋፈለች አገር

ይዘውና ተያይዘው ማቆየት ሲያቅታቸው ስናይ የሱማሌ

(ሞቃዲሾዎች) ታላላቆች የት ገቡ? ከሚለው የሀሳብ

ሙግት የምገጥመው፡፡ ይሁንና ከእኔ የተሻሉ ወዳጆቼም

ሲያወያዩኝ ስህተትን አምኖ መቀበል በእውቀትም ማመን

ነው ብዬ በማሰብ የሞቃዲሾ ሱማሌዎችና ወንድም

እህቶቻችን ታላላቆች አሏቸው፡፡ ነገር ግን ታላቅነት

በመከባበር፣በመተባበር፣በመደማመጥ ወደ ታላቅና ባለፀጋ

አገር መንደርደሪያ አገራዊ የጋራ አገዛዝ (ጥሩም ይሁን

ክፉ) መቆየት ተገቢ ነው ብዬ ነው የማስበው፡፡ መንግሥት

አልቦ መሆን በአውነት ቸነፈር ነው፡፡ መቅሰፍት ነው፡፡

ሶማሌ ሞቃዲሾን ከደካማ መንግሠት ታላቅ የተጠናከረች

ሶማሌንና ለራስዋም ለጐረቤቶቿም ምቹ አገር ትሆን ዘንድ

እየተመኘሁኝ ወደ ተነሳሁበት ርዕሰ ጉዳዬ ልመለስ

አዎን ያለ ታላላቅ ዜጐች ታላቅና የበለፀገች አገር መገንባት

ያስቸግራል ማለት ብቻ ማይሆን የማይቻልም ነው የሚል

ሀሳብ አለኝ፡፡

ከዚህ አንፃር ኢትዮጵያን አገራችን ከጥንት እስከዛሬም

አልፎ አልፎ “ጉግማንጉግ” ክፉ ገዥዎችን ባታጣም (ኮ/ል

መንግሠቱን አስቡልኝ ጭለንጭል አልቦ የዴሞክራሲን

ዘመን) የታላላቆች ሊቃውንት ጠቢባን በየዘርፉ በየሙያውና

በየዘመኑ እንደነበሩ ባለፈው ጽሑፌ ጠቅሻለሁ፡፡ ትልቅነት

በዕድሜም በተግባርም በሥራም ነው፡፡

እነዚህ የኢትዮጵያን ታላላቆች አባቶች ከሁሉም አቅጣጫና

ጐሣ ብሔረሰብና ብሔር የነበሩ፣የተከበሩና የተባበሩ

ለዚህም ከውጭ ለመጣ ጠላት ሁሉ ከጥንት እስከ

ባድሜ በህብረት ክንድ መመከታችን በቂ ማስረጃ ነው፡፡

ይህም ሆኖ ግን ለውስጥ ቅንቅኖቻችን መፍትሄ መስጠት

አልቻልንም፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዛሬ ዘመን ኢትዮጵያዊ ትውልድ

እኔና በእኔ እድሜ ያሉትን ጨምሮ ሺህ ጉዳዮችን፣ሺህ

ማርኪዎችን፣ሺህ አሳዳጆችን፣ሺህ አቁሳዮችን ገዥዎች

ሥርዓት አመራር ከቶ አንሻም፡፡ የወሎ ፈረሶችንና በቆሙ

ሰዎች ዓይነት ሰዎች ውስጣቸው ቀርከሃ የሆኑ ገዥዎችና

መሪዎችም ከዚህም ሆነ ከዚያ ከገዥም ሆነ ከተቃዋሚ

ፓርቲዎች ይህ ትውልድና ዘመኑ በጭራሽ አይፈልግም፡

፡ የዛሬ ኢትዮጵያዊ ትውልድ እንደ ጃፓን ዜጐች ታላቅ

የሞራል እሴት ይፈልጋል፡፡ ዕቃ በየትም ወድቆ ቢያይ

አንስቶ ለፖሊስ ይሰጣል፡፡

ትውልዱ ከድሮ አባቶቻችን ጠንካራ የጋራ ሕዝባዊ

የባህል፣የሞራልና ሥነ-ምግባርን በጥንቃቄና በአክብሮት

ተቀብሎ ራሱንና አገሩንም ማክበር ማስከበር ተገቢ ነው፡፡

ታላላቆች በየዘመኑና በየትውልዱ ይፈጠራሉ ብዬ

አስባለሁ፡፡ ብዙዎቻችሁ እንዲሁ ታስባላችሁ የሚል ቀና

ስሜትና ግምት አለኝ፡፡ ታላላቆች ሁሉ በእምነት በእውነትና

በሃይማኖት የፀኑ ናቸው፡፡ ያለእምነት ያለ እውነትና

ሃይማኖታዊ ሥነ-ምግባር የዓለም ታላላቅ አገሮች ታሪክ

አይታሰብም፡፡ የሃይማኖቶች መለያየት ችግር አይደለም፡፡

ብቻ ሃይማኖት ያለው እምነት ደግሞ ፍቅር ነው፡፡ ፍቅር

በራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ በዚህ መስመር ታላላቆች

ሥራቸው አልፋና ኦሜጋ የሆናል፡፡

ስለሆነም ኢትዮጵያ በእስከ ዛሬና የአሁኑ መንግሥትም

የታሪክ ደረጃና ቦታው ገለልተኛ ታዛቢዎችና ታሪክ

ጸሐፊዎች ተመራማሪዎች ደረጃም ይታወቃል፡፡

የቤተመንግሥት ጸሐፊዎች ታሪክ ግን ተረትና ውሸት ነው፡

፡ የኢትዮጵያ ደረጃም ከፍ ከፍ እያለ መጣ? ወይስ ወጣ

ወጣና ተንከባለለ እንደ ሸንበቆ እየሆን ነው? መልሱን

ለክቡራን አንባብያን እተወዋለሁ፡፡

ትውልዱ ከድሮ አባቶቻችን ጠንካራ የጋራ ሕዝባዊ የባህል፣የሞራልና ሥነ-ምግባርን በጥንቃቄና በአክብሮት

ተቀብሎ ራሱንና አገሩንም ማክበር ማስከበር ተገቢ ነው፡፡

ታላላቆች በየዘመኑና በየትውልዱ ይፈጠራሉ ብዬ አስባለሁ፡፡ ብዙዎቻችሁ እንዲሁ ታስባላችሁ የሚል ቀና

ስሜትና ግምት አለኝ፡፡ ታላላቆች ሁሉ በእምነት በእውነትና በሃይማኖት የፀኑ ናቸው፡፡ ያለእምነት ያለ

እውነትና ሃይማኖታዊ ሥነ-ምግባር የዓለም ታላላቅ አገሮች ታሪክ አይታሰብም፡፡ የሃይማኖቶች መለያየት

ችግር አይደለም፡፡ ብቻ ሃይማኖት ያለው እምነት ደግሞ ፍቅር ነው፡፡ ፍቅር በራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡

በዚህ መስመር ታላላቆች ሥራቸው አልፋና ኦሜጋ የሆናል፡፡

ስለሆነም ኢትዮጵያ በእስከ ዛሬና የአሁኑ መንግሥትም የታሪክ ደረጃና ቦታው ገለልተኛ ታዛቢዎችና ታሪክ

ጸሐፊዎች ተመራማሪዎች ደረጃም ይታወቃል፡፡ የቤተመንግሥት ጸሐፊዎች ታሪክ ግን ተረትና ውሸት ነው፡

፡ የኢትዮጵያ ደረጃም ከፍ ከፍ እያለ መጣ? ወይስ ወጣ ወጣና ተንከባለለ እንደ ሸንበቆ እየሆን ነው?

መልሱን ለክቡራን አንባብያን እተወዋለሁ፡፡

አንድ ነገር ልብ በሉልኝ፡፡ ኢትዮጵያ በአፄ ቴዎድሮስ እጅ

የማትሰጥ አኩሪ አገር፣ አፄ ዮሐንስም ኢትዮጵያ ዳር ድንበር

ሕይወቱን ያልሰሰቱ ታሪክ ሠሪና መሪ ነበሩ፡፡ አፄ ምኒልክም

የአድዋ ድል ጀግና ነበሩ፡፡ ጃንሆይም ከነ ረጅም የሥልጣን

ሱሰኛነታቸው ታላቅ ኢትዮጵያዊና አፍሪካዊ እንደ ነበሩ

5

መካድ ከሀቅ ውጭ ያደርገናል፡፡ ኮ/ል መንግሥቱም ቢሆኑ

የውስጥ ጨፍጫፊነቱና ክፋቱ ወደር አልባ ቢሆንም ቅሉ

ከአፄዎቹ የታሪክ በታኝ ኢትዮጵያ ለመቆየት በ1969

ከሱማሌ ሞቃዲሾ ወረራ ጋር ሙሉ ሕዝብን አስተባብረው

የታላቅነት ድርሻውን ተወጥተዋል፡፡

ከሰሜኑ የአገራችን ወገን ጋር የነበረውን የቅራኔ አያየዝ

አቅምም እውቀትም ስላልነበረው ለዛሬዋ ኢትዮጵያ ክፉ

ሁኔታ የደርግና ኮ/ል መንግሥቱ ድርሻ ብዙ እንዳለበት

መካድ አይቻልም፡፡

ይሁንና ከአፄዎቹ ደርግና በእስከ ዛሬም የተተበተቡ የመፍቻ

ቁልፍ ያልተገኘላቸው የሕግ የበላይነት፣የዴሞክራሲ

ጥያቄ የሀብት አስተዳደር ፈትሃዊነት ጥያቄዎች ከ40 እና

ከ50 ዓመታት ጀምሮ መላ ኢትዮጵያውያን እየታገሉለት

ይገኛሉ፡፡ ከ1936 የወያኔ የቀዳሚ ወያኔ ትግራይ ገበሬዎች

አመፅ፣የባሌ ገበሬዎች (ኢጆሌ ባሌ) እና በጅማ ገበሬዎች

ትግል፣የኢትዮጵያ ተማሪዎች ትግሎች ሁሉ አልሰመሩም

እንጅ የታላቅነት መፍጠሪያ ማጠናከሪያዎች የነበሩ ነበሩ፡፡

በቁጭት መክነው ቀሩ እንጂ፡፡ የኢትዮጵያን ታላላቆች ዛሬ

ዛሬ አንዳንዶች በተሳሳተ ሥሌት ወይም የኢትዮጵያውያንን

የረጅም ዘመቻ የትግል ታሪክ ለመካድና ለማስነሳት

ቢያንስ ቢያንስ (በኢህአዴግ) ዘመን ስለዴሞክራሲ

ስለብዙሃን ፖለቲካ ፓርቲዎች ማሰብ ከጀመርን 19

ዓመታት ቢሆንም ብሎም ሀቁ ግን የእነ ኢህአፓ

ሕወሓት፣ኦነግ፣ኦብነግ፣መኢሶን፣ወዝሊግ አብዮታዊ

ሰደድ ማሌድ፣ኢጭአት ፓርቲዎች ከ1964-1972/3 እና

ከኢሰፓእኮ በኋላም ኢሠፓ ተቀረጣጥፎ እስከተበላበት

ዘመን ድረስ የነበሩትን ትግሎችና በእስከ ዛሬም በተለያዩ

ሁኔታዎች እየተደረጉ ያሉት እልህ አስጨራሽ ትግሎች

የታላቅነት ማሳያ መስታወቶች ነበሩ፡፡ ናቸውም፡፡

እነዚህ ሁሉ ብዙ ሰማዕታት የተገበረባቸው የሙሉ

ኢትዮጵየውያን የትግል መስኮች ተንቋሸውና ዋጋ አጥተው

ስለ ዴሞክራሲ፣ስለ ሕግ የበላይነት፣ስለ ብዙሃን ፖለቲካ

ፓርቲዎች፣ስለ መሬት ስለገዥዎች ሣይሆን መሬት

ለአራሹ፣ስለ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ፣ስለ መልካም አስተዳደር

በጥቅሉ ሁላችንም በእኩልነት የምታስተዳድርና የሁላችን

አቻ አስተናጋጅ አገር ለመገንባት ሲታገሉ የኖሩ እያሉ ያሉት

ሁሉ ታላላቆች ቅቡላንና ቅዱሳን ናቸው ብዬ አስባለሁ፡፡

በተቃራኒው ቅንጣት ያህል ግራም አስተዋጽኦ ሳያበረክቱ

እየተሹለከለኩ ጥቅምና ዝና ፈላጊ ትናንሽ ዜጐችም እንደ

ነበሩንና እንዳሉን አልዘነጋም፡፡ እነዚህም ሰዎች ናቸው፡፡

ትግላችንን ጠመዝማዛና አሜከላ የበዛበት ያደረጉት ብዬ

አስባለሁ፡፡

ዛሬ ዛሬ የተላንቱ ታላላቆቻችን ጥራቶች የዛሬዎች

መስዋዕትነቶችን ለማምከንና ባዶ ለማድረግ ታስቦበት

በእቅድ ለክፋት ስንማር (በተማሪ) በልዩነት (ሲቪል

ሰርቪስ አስቡልኝ የማኛ ካድሬዎች ብቸኛ ት/ቤት በነጥቡ

የማይማርበትን) ተምረን ስንቀጠር (ስትቀጠር) በልዩነት

ዛሬ ማንም ኢትዮጵያዊ አዲስ ለመቀጠር የገዥ ፓርቲ

አበል ደጋፊ ተባባሪ መሆን የቅድሚያ ቅድሚያ በተሰጠበት

አመራር ዘመን፣አስተሳሰባችን፣አነጋገራችን፣አሠራራችን፣እየ

ታወቁና ወደ ትልቅነት ጐዳና እየወሰድን ወይስ በተቃራኒው

እያሰብን መሆኑን ለክቡራን አንባብያን ቢተው ይመረጣል፡

፡ መልሱ ግልጽ አጭር ነውና፡፡

ለማጠቃለል ኢትዮጵያዊ ተላላቆቻችን የተሰውት፣ዕድሜ፣

ጤንነት፣እርጅና ሳያግዳቸው፣ተስፋ ሣያስቆርጣቸው 70

እና 8ዐ ዓመታቸው እየታገሉ ያሉት ከ19 ዓመታት ወዲህ

ቢያንስ ቢያንስ ስለ ዴሞክራሲ ስለ ብዙሃን ፖለቲካ

ፓርቲዎች ማሰብ ጀምርን የሚሉትን ነጭ ውሾች ማጋለጥ

የታላቅነት ማሳያም ነው፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያውያን

ከሁሉም ወገን ታላላቆች በበቂ ነበሩ፤ዛሬም አሉን፡፡ ዋናው

ችግራችን አንደኛ እንደሰዎች፣እንደ ዜጐች፣እንደ አንድ አገር

ልጆች እንከባበር፣መከባበር የቀዳሚ ቀዳሚያችን ይሁን፡

፡ ሁለተኛ የተከባበረ ወገን መደማመጥ አይቸግረውምና

ከአንጅት ከልብ እንደማመጥ፡፡ ሦስተኛ ለሁላችን

የመትሆን መብት፣ሀብት ባንክ ታንክ ያላትን ኢትዮጵያ

ሁላችንም እንደየሙያችን፣እንደችሎታችን ለመገንባት

አዲስ አመለካከት ሊገነባ ይገባል፡፡ አራተኛ ታማኝና

ለፈሪሃ እግዚአብሔር፣ለፈሪሃ ሕዝብ፣ለፈሪሃ ሕግ፣ለፈሪሃ

ሕሊና፣ለፓርቲያችን ዲስፕሊንና መመሪያ እንዲሆን

በአዲሱ አዲስ ዘመንና ዓመት ከገዥው ፓርቲ በጣም ብዙ

ሥራ፤ከተቃዋሚዎችም ቀላል ያልሆነ ቅንነትና ትብብር

ሊፈጥር ትውልድና ዘመኑ ይማፀናል፡፡ ታላላቆችን ሳታጣ

ታላቅነትና ባለ-ፀጋነትን ያጣች ኢትዮጵያ በመከባበር ታላቅ

እናድርግ ባለፀጋም እናደርጋታለን፡፡ ይቻላል፡፡

www.andinet.org.et

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!