የመሬት ቅርምት ለልማት - Ethiopia: A voice for the voiceless
የመሬት ቅርምት ለልማት - Ethiopia: A voice for the voiceless
የመሬት ቅርምት ለልማት - Ethiopia: A voice for the voiceless
Create successful ePaper yourself
Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.
8

www.andinet.org.et

መዝናኛ ከዝናሩ

ሥጦታ

ለአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ ማስታወሻ

ከሰሎሞን አድማሱ

ለሀገር ዘፈነ እያለ ሀገሬ

ኩራት ነበርና ሀገር በቀል ፍሬ፤

“መለያየት ሞት ነው” እያለ ዘፈነ

በመሞት ጥያቄ ለመሞት ወሰነ

ጠግበን ሳንጨርሰው ሲለየን ፈጠነ

ሁሉም ነገር በቃ እንደማይሆን ሆነ፡፡

ያ ዘንባባ ማር ዘንጣፋ ሸበላ

ጥላሁን ስንለው ሲሆን ነበር ጥላ

በሱ ተራ ጊዜ ጥላ አጣ ከለላ

ክፉ ሞት ስትወስደው ከጉያ ነጥላ

የዘፈኑ ንጉስ የዛ አርበኛ ገላ

ካፈር ተቀላቅሎ በምስጦች ተበላ

ለካ ሰው ግብዝ ነው ሞኝ ነው ተላላ

እሱን ሲያመው ጠፋን የማዳኛው መላ፡፡

ከልብ ለማይጠፋው ለቁንጮው ስመ-ጥር

ሁላችን ነበረን ፍፁም ልዩ ክብር

ጥሌ ስለሆነ ያገር ኩራት ፍቅር፤

ድምቀት ስለነበር የልብ ውስጥ አበባ

ስጦታ ይሁንና የወገንህ እንባ፤

ብንወድህ ነበረ ጥላሁነን ያልንህ

መጣላት ፈልገን መች ጥል አሁን አልንህ

ዶክተር የራስክን ነፍስ መልሳት እባክህ

ናና ዝፈንልን ትስማ እስትንፋስህ

በአንድ ላይ ነን ዛሬ አንተን ስንጠብቅህ

ከስተሀል ጠቁረሀል እስቲ ትታይ ወዝህ፡፡

ትዝታውን ትቶ እሱ አፈር ለበሰ

ብርቅዬው ድንቅየው ጥላሁን ገሠሠ፤

ውለታ ሳንከፍለው ስለሄደ ድንገት

ሀዘንና ደስታ ባንጎራጎረበት

ጥበብን በድምፁ ገልፆ ባሰማበት

በጥበቧ አዳራሽ አሁን ባለንበት

ቤተሰብ አድናቂው በተገናኘበት

በድምቀት ይከበር የጥልዬ ልደት፡፡

ምንም ሞት ቢነጥቀን ቢለየን በሥጋ

መቼም መቼም መቼም ጥሌ ነው ከኛ ጋ፤

ሁሉን የሚችለው አምላካችን ቸር ነው

ሞገስ ክብራችንን በገነት ያኑረው፡፡

በዚያ አንታለልም

ሙሉነሽ አበባየሁ

መንገዱን ለመስራት ግንብ ለመደርደር፣

ፋሽስቱ ጣሊያንም የሌለው ነው ወደር፡፡

በዚያ ሳንታለል አምስት ዓመት ታግለን፣

ፋሽስቱ ጣሊያንን አስወጣን አባረን፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የታየው ብልጥነት፣

አሮጌን አፋርሶ አንገትን ማስደፋት፣

የልማት ሲናገር መንገድና ፎቁን በቲቪ ማሣየት፡፡

አቅሙን ተረዳው በዚያ አንታለልም፣

አንተንም በማውረድ ወደኋላ አንልም

ሆዴ ባዶ ሆኖ መላወስ ካቃተኝ፣

የአስፋልቱ ስፋት አረምን ሊበጀኝ

መንፈሴ ታውሮ ሲንጣለል አስፋልቱ፤

ፎቆች ተደራርበው ቢሠሩ በብርቱ፣

ለእኔ የማይሆን ነው ለርሃብ ጥማቱ፡፡

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 23 2004 ዓ.ም.

“ጥሪ አይቀበልም” አዲስ ፊልም

ሊመረቅ ነው!

በሲኒማ ኢትዮጵያ የምሽት የሲኒማ ፕሮግራም ተጀመረ

በአዲስ አበባ ሲኒማ ቤቶች አስተዳደር

በተመልካች ስሜትና ፍላጐት በተመረጡ የአማርኛ

ፊልሞችን ከመስከረም 19 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ

ከምሽቱ 2፡30 ለተመልካች እያቀረበ መሆኑ ገለፀ፡፡

ቁጥሩ እየጨመረ የመጣውና የፊልም ስራ እንዲሁም

የወረፋ መጣበብን ለመቅረፍ ያግዛል ተብሎ የተዘረጋ

መሆኑን ዘወትር አርብ ምሽት “ያንቺው ሌባ”

ቅዳሜ በድጋሚ ቀረፃና በባለሙያዎች አስተያየት

ተስተካክሎ የቀረበው “መፈንቅለ ሴቶች” እሁድ

“መካኒኩ” ፊልሞች ለተከታታይ 2 ወራት የሙከራ

እና እንደሚታዩ የሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ያገኘው

መረጃ ያመለክታል፡፡ ከዚህ ቀደም ባልተለመደ

አሰራር ከፊልሙ ገቢው 60% ፐርሰንት የፊልሙን

ፕሮዲውሰሮች ቀሪ 40% ፐርሰንት ለሲኒማ ቤቶች

መሆኑን ለማወቅ ችለናል፡፡

ባህል፣ ፌስቲቫልና ባዛር ለዕይታ በቃ

የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ከቢ.ቴክ የማስታወቂያ

ስራ ድርጅት ጋር በመተባበር በአይነቱ ለየት ያለ

የባዛርና የባህል ፌስቲቫል መስከረም 19 ቀን 2004

ዓ.ም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ታዋቂ

ግለሰቦች አርቲስቶች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች

በተገኙበት በጥቁር አንብሣ በሚገኘው ድላችን

ሀውልት ሲከፈት ከ50 በላይ አገልግሎት ሰጭ

ተቋማት ተሣትፈዋል፡፡ በዚሁ ባዛርና ፌስቲቫል

ላይ የተለያዩ የሙዚቃ ዝግጅቶች የብሔር

ብሔረሰቦች ጭፈራዎች፣ የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕይ

ቀርበዋል ለተከታታይ ቀናት በቆየው ዝግጅት

ላይ በመዝጊያው ስነ-ስርዓት መስከረም 21 ቀን

2004 ዓ.ም ምሽት 1፡00 ሰዓት ጥሪ የተደረገላቸው

እንግዶች በሐርመኒ ኢንተርናሽናል ሆቴል የባህል

ፋሽን ትርዒት ቀርቧል፡፡ የዘንድሮው በአለም አቀፍ

ደረጃ የተከበረው የቱሪዝም ቀን ምክንያት በማድረግ

ቱሪዝም ያስተሣስራል በሚል መሪ ቃል እንደ

ተዘጋጀ አዘጋጆቹ ለዝግጅት ክፍላችን ገልፀዋል፡፡

ለአለም የምሳሌ ዶክመንተሪ የፊልምና የፎቶ

ኤግዚብሽን ተመረቀ

በእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤትና ወዛም

ኮሙኒኬሽን ኤንድ ቢዝነስ ኃ.የተ.የግ.ማህበር በጋራ

ማዘጋጃ የኢትዮጵያ ታሪክ የሚገልፅ ዶክመንተሪ

ፊልም በተለያዩ ከ6 በላይ ቋንቋዎች በአማርኛ፣

በእንግሊዘኛ፣ በአረብኛ፣ በፈረንሣይና በኦሮሚኛና

በትግረኛ ቋንቋዎች ተሰርተው ቀረቡ፡፡ መስከረም

በሚዲያ ሀውስ ፊልም ፕሮዳክሽን

በደራሲ ዮሊያን ተ/ማርያም በዳሬክተር

ሚሊዮን ስዩም የተሰራው “ጥሪ አይቀበልም”

የተሰኘ በአይነቱ ለየት ያለ አስቂኝ ልብ

አንጠልጣይ ፊልም የፊታችን እሁድ

መስከረም 28 ቀን 2004 ዓ.ም ሁሉም ሲኒማ

ቤቶች በአዲስ አበባ በሚገኙ ያስመርቃል፡፡

በሲኒማ ሴባስትፖል፣ በሲኒማ

ዮፍታሔ፣ በሲኒማ እምቢልታ፣ ሰበታ

ጂም ሲኒማ፣ በደ/ዘይት ህይወት ሲኒማ እና

በናዝሬት ምርምር ሲኒማ በ8፡00፣ በ10፡00

እና በ12፡00 ሰዓት ለህዝብ እይታ ይበቃል፡

፡ በልዩ ፕሮግራም በሲኒማ ዮፍታሔ በ8፡00

ሰዓት አርቲስቶች ታዋቂ ግለሰቦች ጋዜጠኞች

የኪነ-ጥበብ ወዳጆች በተገኙበት በደመቀ ስነ-

ስርዓት ይመረቃል፡፡ በዚህ ፊልም ላይ ታዋቂ

አርቲስቶች ተውነዋል፡፡ ተዋንያን መስፍን ኃ/

እየሱስ (ጠጆ)፣ ሰለሞን ገብሬ፣ ኤልሳቤት

ጌታቸው (ቀጮ)፣ ፈዮሪ ሀይሌ፣ ዳንኤል

ወንድወሰን ሚኪያስ ታምሬ እና ናርዶስ

በርሄ ሌሎችም ከ25 በላይ ወጣትና አንጋፋ

ተዋንያኖች ተውነውበታል፡፡ የፊልሙ

ርዝመት 1፡39 ደቂቃ ሲወስድ ፊልሙን ሰርቶ

ከማጠናቀቅ 1 ዓመት ከ6 ወር ጊዜ ሲወስድ

ከ450.000 /ከአራት መቶ አምሣ ሺህ ብር

በላይ ሲወስድ የፊልሙ ታሪክ በተለያዩ

ምክንያቶች ከስራ ገበታቸው የተፈናቀሉ

ወጣቶች በአቋራጭ ለመበልፀግ የሚያደርጉት

የሕይወት ውጣ ውረድን ያሳያል፡፡

21 ቀን በሚሊኒየም አዳራሽ የሃይማኖት አባቶች

ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣኖች ጥሪ የተደረገላቸው

እንግዶች ሲከፈት ለተከታይ ቀናቶች በሚቆየው

ኤግዚብሽን ታሪካዊ ቦታዎች በፎቶና በምስል የታገዘ

ስለ ሀይማኖቶች እንደተዘጋጀ በመክፈቻው ዕለት

ተገልፆል፡፡

የአደባባይ ምስጢሮች

ጋሻው

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.10

የተገላቢጦሽ

አበው ወደ አንድ ቁም ነገር ወዳለው ጉዳይ ለማምራት

ሲፈልጉ “ወግን ወግ ያንጋጋዋል” ይላሉ፡፡ እኔም የዘመኑ ክፋትና

ጭካኔ ጥላ አጥልቶብኝ እየገረመኝ በጥልቀት ስመለከት የበለጠ

ርቄ በሐሳብ እመሰጣለሁኝ፡፡ ብዙ ጊዜ የሚሆነው ሣይሆን

ሲቀርና የማይሆነው ሲሆን ሣይ ሁሉም ነገር የተገላቢጦሽ

ይሆንብኛል፡፡ በልጅነቴ በተወለድኩበት አካባቢ አዛውንቶች

የማይሆንና ያልጠበቁት ነገር ሲሆን ሲያዩ “የተገላቢጦሽ ! ይሉ

ነበር ሼህ ሙሄ” ሲሉ እሰማ ነበር፡፡ ሸህ ሙሄ በተረት መልክም

ይሁን በምሳሌዊ አነጋገር ብቻ በሆነ አጋጣሚ “ሸህ ሙሄ

እንዲህ ብለው ነበር” እየተባለ ይነገራል፡፡ አለቃ ገ/ሐና፣ ሁሴን

ጂብሪል እንዲህ ተናግረው ነበር፡፡ እየተባሉ እንደሚጠቀሱት

ማለት ነው፡፡ እኔም በትዝታ ልጓም ተስቤ ጊዜ ጎትቶ ወስዶ

እኔ ከነበርኩበት ዘመን አልፌ ከሸህ ሜሄ ዘሌ ዘመን በመግባት

በልጅነቴ እሳቸው ተናገሩት የሚባለው ተረት መሰል ቁምነገር

ትውስታ ውሰጥ ገባሁ፡፡

ሸህ ሙሄ ዘሌ የተባሉ አዛውንት ነበሩ፡፡ እኒህ አዛውንት

በረመዳን ፆም ከሚኖሩበት ራቅ ካለ አገር የቅርብ ዘመዳቸው

የሆነ ይሞትና ከዚያ ቀብር ውለው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ

“ምሳ አቆይኝ” ከተባለ ቦታ ይደርሳሉ፡፡

ምሳ አቆይኝ እንደ እንጨት የቆመ አቀበት ሲሆን ያንን

የገረረ አቀበት ለመውጣት ወገብን አጉብጦ ሰለሚለቅ ከታች

ከቆላው አገር ውለው ወደ ላይ የሚወጡ መንገደኞች ምሳ

አቆይኝ ሲደርሱ ከድካማቸው ጋር ርሃብም ሰለሚይዛቸው

“ምሳ- አቆይኝ!” ብለው የጥንት አባቶች ስም እንዳወጡለት

ይተረካል፡፡ እውነትም የምሳ አቆይኝ ጋራ ጉልበትን የሚፈትን

ነው፡፡ በተለይም በእድሜአቸው ለገፉ አዛውንቶች በቀላሉ

የሚወጡት አይደለም፡፡ ከምሳም አልፎ ራት አቆይኝ

የሚያስብል ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ምሳ አቆይኝ አካባቢ

መንደር የሚባል ስለሌለ ጥቅጥቅ ያለደን በመሆኑ ከመሸ

በኋላ ብቻን ያንን አቀበት ለመውጣት የሚታሰብ አይደለም፡

፡ ጅቦች በየጥጋጥጉ ጉሬቸውን ሠርተው ስላሉ ከመዘነጣጠል

አይመለሱም እየተባለ ይፈራል፡፡ በመሆኑም ሸህ ሙሄ ዘሌ

ከዘመዳቸው ልቅሶ ውለው የማታ ማታ ወደ በመንገድ የደከመ

ጉልበታቸው ከፆም ጋር ተዳምሮ ከስር ሆነው አንጋጠው ያንን

አቀበት ሲመለከቱት አሞታቸው ፍስስ ይላል፡፡

ሸህ ሙሄ ካንድ ዛፍ ስር አረፍ ብለው ያንን የገጠጠ

አቀበት እንዴት እንደሚወጡት ሲያምሰላስሉ አንድ ሐሳብ

ይመጣላቸዋል፡፡ አላህን አጥብቀው ቢማፀኑት ያንን እንደ

እንጨት የቆመ አቀበት አንከብክቦ የሚያ ወጣቸው ሰጋር

በቅሎ እንደሚሰጣቸው! ያምናሉ እናም “ለአላህ ምን

ይገደዋል!” ይሉና በርከክ ብለው፡-

“አላህ አምጣ ግራጫ ያቀበት መውጫ

ዋርዳ በቅሎ አምጣ ይህን አቀበት ይዞ

ሚወጣ! “በማለት በግንባራቸው እየተደፉና

እየተነሱ አላህን ይማፀኑ ጀመር፡፡

አንድ ገበሬ ደግሞ እህል ሸመታ ገበያ ውሎ ባህያውም

ጥርቅ አድርጎ ጭኖ እሱም የተወሰነውን በትከሻው ተሸክሞ

ሲጓዝ አህያውን ከልክ በላይ ጭኖት ስለነበር ይደክምበታል፡

፡ በዚህ ላይ ምሽቱ ይቃረባል፡፡ እንደምንም ያህያውን ቂጥ

እየገፋ፣ አንዳንድ ጊዜም በሽመል እየነረተ አንፏቆ ምሳ አቆይኝ

ይደርሳል፡፡ የምሽቱ ጥላ ጋራውንና የጋራውን ዙሪያ ጥላ

አጥልቶበታል፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ ጅቦች ከያደፈጡበት

ብቅ ብቅ ማለታቸው የማይቀር በመሆኑ እስከነ አህያው

ዝንጥልጥል እንደሚያደርጉት ያውቃል፡፡

“ፈጣሪ የ፤ ፈጥረህ እስከነ አህያዬ ለተራበ ጅብ አትስጠኝ!

ከጉድ አውጣኝ! ቢቻል ጌታ የሌለው ጠብደል አህያ፣ ካልሆነ

ደግሞ የምሳ አቆይኝን ዳገት የሚያወጣኝ አንድ ጠብደል

ጎራዳማን (ወጠምሻ) አምጣልኝ” በማለት እግዚአብሔርን

እየተማፀነ ያህያውን ቂጥ እየገፋ ሸህ ሙሄ ዘሌ ተንበርክከው

ከሚማፀኑበት ይደርሳል፡፡ አህያው በረጅሙ ተነፈሰና ሸህ

ሙሄን ከሽመልና ከጭነት ያድኑኝ የሚል ይመስል ቀጥ ብሎ

ይቆማል፡፡

ሸህ ሙሄ ከኋላቸው ኮቲ ሰምተው መለስ ብለው ሲያዩ

አንድ ሰው አህያ ጭኖ እሱምተሸክሞ ካጠገባቸው ቁሞ ያያሉ፡

፡ ከተንበረከኩበት ይነሱና፡-

“አላህ ሰጋር በቅሎ ስጠኝ ብልህ የተጫነ አህያ

ትሰጠኝ? እንግዲህ ያንተ ስጦታ ከሆነ እቀበላለሁ፤ ይህን

ወደ የዞሯል