24.08.2013 Views

የመሬት ቅርምት ለልማት - Ethiopia: A voice for the voiceless

የመሬት ቅርምት ለልማት - Ethiopia: A voice for the voiceless

የመሬት ቅርምት ለልማት - Ethiopia: A voice for the voiceless

SHOW MORE
SHOW LESS

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.10

የመጨረሻ ክፍል

ከብሩክ ከበደ

ኪነ ጥበብ

ሣምንት በሃገራችን ታሪክ ቀዳሚ የሚባለውን የፍቅር

ትያትር ስለደረሱት ብላታ ጌታዬ አስፋው የድርሰት ሕይወትና

በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት ስለተለየችው ድምፃዊት ክራር

ተጫዋችና ተዋናይ አስናቀች ወርቁ ለመጀመሪያ ጊዜ በሳዱላ

እድሜዋ በመሪ ገጸ ባሕርይ ስለተወነችው የ”ፍቅርጮራ”

በተመለከተ ያዘጋጀሁትን ማቅረቤ ይታወሳል፡፡ በዛሬው

ጽሑፌ ደግሞ ቀጣዩንንና የመጨረሻውን ክፍል

አስነብባችኋለሁ፡፡

ከዚያ በፊት ግን አቶ አበራ ይርጉ የተባሉ

የጋዜጣው ተከታታይ ሣምንት የወጣውን ጽሑፍ ካነበቡ

በኋላ “ . .. ከፕ/ ግርማ ወ/ጊዬርጊስና ብላታ ጌታዬ አስፋው

ተፈራ ጋር ሌላም ቀደምት በሕይወት የሚገኙ የደራስያን

ማሕበር አባል የነበሩ አሉ፡፡ ስማቸውም ንብረ ዕድ ኤርምያስ

ከበደ የሚባልና ኑሮዋቸውን አሜሪካ ሜሪላንድ ያደረጉ

ይገኙበታል . . .፡፡” ሲሉ ለሰጡን ጥቆማ ከልብ አመሰግናለሁ፡

ባይሆን ለአንዳንድ ወጪዎች መሸፈኛ በሚል ለዛውም

ምናልባት ታሪኩ የሚፃፍለት ግለሰብ ቤተሰቦች የገንዘብ

አቅሙ ካላቸው ይሰጣሉ እንጂ ለፃፍንበት ተብሎ እንዴት

ይጠየቃል፡፡? እንዲህ ከሆነማ ወደፊት የሀገርና ሕዝብን

ታሪክ ማን ሊጽፈው ነው? ሲሉ ሥጋታቸውን ያስቀምጣሉ፡

የክቡር ዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ ታሪክ ለመጻፍ የአማራ

ብ/ክ/ መንግሥት አንድ ሰሞን እንቅስቃሴ ጀምሮ ሥራው

ለደራስያን ማህበር ብቻ ለመስጠት ማሰቡ አግባብ

አይደለም፡፡ ታሪኩ የተዋጣለትና ምሉዕ እንዲሆን ማንኛውም

ግለሰብ፣ተማሪዎች፣ተመራማሪዎች ወ.ዘ.ተ ሁሉ ያላቸውን

እንዲያበረክቱ መደረግ ነው ያለበት፡፡ ታሪክ እጽፋለሁ

የሚለው ነው ወደ ታሪክ መሔድ ያለበት እንጂ ታሪክ ወደ

ፀሐፊው ሊሔድ አይችልም፡፡ አይገባውም፡፡ የሚል ጽኑ

አቋም ብላታ ጌታዬ አስፋው ተፈራ አላቸው፡፡

ታሪክ ፀሐፊ እንዴት ክፈሉኝ ብሎ ይጽፋል የሚለውን

የብላታ ጌታዬን አቋም “አሁን ዱሮ አይደለም! ” የሚሉ

አይጠፉምና ምን ይሉኛል? ስል ጠይቄያቸው የሚከተለውን

መልሰውልኛል፡፡ “. . . እዚህ ውስጥ ብዙም መግባት

አልፈልግም፡፡ በኛ ጊዜ ምሥጋና ግፋ ቢል መጽሐፉ መግቢያ

ብቻ ይሰፍር ነበር፡፡ የዛሬውን አላውቅም “አቦ” እኔም

ያ እየመሠለኝ አንዳንዴ እሣሣታለሁ መሰለኝ ወዳጄ!፡

፡ እኔ እኮ የደጃዝማች ግርማቸው ተ/ሃዋርያትን፣ብላታ

ህሩይ ወ/ሥላሴ፣ቀኝጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ፣ልዑል መኮንን

የመሣሠሉትን ታሪኮች ሁሉ ስጽፍ ገንዘብ ጠይቄ አይደለም፡

፡ ታሪክ ስለሆነ ለትውልድ መተላለፍ አለበት፡፡ አዲስ

ኪዳንን የፃፉት እኮ ይህን ያሸን ያህል ይከፈላችኋል ተብለው

አይደለም፡፡ የትውልድ አደራና ኃላፊነት ስላለባቸው እንጂ፡

የድምፃዊ ዶ/ር ጥላሁን ገሠሠ የሕይወት ታሪክ ጽሑፍን

በተመለከተ ካለኝ መረጃ በመነሣትም ይህን ማለት ፈለኩ፡፡

ድምፃዊ ዶ/ር ጥላሁን ገሠሠ በሕይወት በነበረበት ጊዜ ታሪኩን

ለማፃፍ ደራሲያን ማሕበርን አነጋግሮ ነበር፡፡ ማሕበሩም 147

ሺህ የኢት/ብር እንዲከፈለው ጠይቆ ስምምነቱ ተፈረመ፡፡

ዶ/ር ጥላሁን ገሠሠም መጽሐፉ እንዲወጣ ከነበረው ጉጉት

እ.ኤ.አ በ2001 ስፖንሰር አግኝቶ ክፍያውን ይፈጽማል፡፡

በመሃልም ዶ/ር ጥላሁን ገሠሠ የጓጓለት መጽሐፍ ሳይወጣ

ከዚህ ዓለም በሞት ይለያል፡፡ ታሪክና ፀሐፍትም ይለያያሉ፡

ባለቤቱ ወ/ሮ ሮማን በዙም የተጀመረውን ጉዳይ ያውቁ

ስለነበር ማሕበሩ መጽሐፉን ለሙት ዓመቱ እንዲያደርስ

ይጠይቃሉ፡፡ በጥያቄያቸው መሠረትም ውሉ እንደገና

በሳቸው ስም እንዲሆን ተደርጐ ተጨማሪ የተወሰነ

ገንዘብ ይከፍሉና ጽሑፉ መፃፍ ይጀመራል፡፡ አዲስ ውል

ተዋዋይዋም እባካችሁ እያሉ በማስጨነቅ ባሰቡት ቀን

መጽሐፉ እንዲደርስ ማህበሩን መወጠር ያዙ፡፡ ለመጽሐፉ

ሕትመት የተያዘለት የጊዜ ሠሌዳ በጣም ሲቃረብ ታሪኩን

ያውቃሉ የተባሉ ቃለ-ምልልስ ይደረግላቸው እንደነበር

ሲታወቅም በተባለው ቀን አይደርስ ይሆናል የሚል ሥጋትም

ፈጥሮ ነበር፡፡ ነገር ግን አንድ ሣምንት ሲቀረው “ሻማ ቡክ

አሣታሚ” በብርሃን ፍጥነት ሊባል በሚችል አድርሶታል፡፡

ከመጽሐፍ ሽያጭ ከሚገኘው ገቢ መሀል 1ዐ%

ለባለቤቱ 9ዐ% ወ/ሮ ሮማን ብዙ ለአሣታሚው በሰጡት

አካውንታቸው ባለቤታቸው በሕይወት በነበረበት ጊዜ

ሊያቋቁመው ላስበው የ “ስኳር ሕመምተኞች ማህበር” ገቢ

እንዲሆን ተወስኖ ነበር፡፡ መጽሐፉም ለመጀመሪያ ጊዜ 1ዐ

ሺህ ኮፒ ታተመ፡፡ አልቆም እንደገና የመጀመሪያውን ቁጥር

ያህል ታትሟል፡፡

የቲያትር ጮራዋ አስናቀች ወርቁ

የፍቅር ጮራን ብላታ ጌታዬ አስፋው ተፈራ በ1944

ዓ.ም ለመድረክ ሲያባቁት በጊዜው “you are always my

heart” ከሚባለው ምርጥና ተወዳጅ የእንግሊዘኛ ዘፈን

በመነሣት መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ይኸንን “አንቺ ሁል ጊዜ

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 23 2004 ዓ.ም.

ከ” ኮ”ና “ካ” የፈለቀች አርቲስት

“የፍቅር ጮራ” ደራሲ ማነው?

ብላታ ጌታዬ አስፋው

በልቤነሽ ምንም እንኳን ብንራራቅ” ወደ ሚለው አገርኛ

ግጥም የመጀመሪያውን ስንኝ ተንተርሰው በፃፉት ቲያትር

የዛን ጊዜ ሳዱላ የነበረችው አስናቀች ወርቁ በዋንኛነት

እንድትተውን አድርገዋታል፡፡ ይህ ባለ አምስት ገቢርና 1፡3ዐ

ሰዓት የሚፈጀው ተውኔት ዘመናዊ የፍቅር ቲያትር መሆኑን

የዘርፉ ባለሙያዎች ይስማሙበታል፡፡ የቲያትሩ አዘጋጅም

አቶ ተስፋዬ ተሰማ ነበሩ፡፡

አስናቀች ወርቁ ቲያትሩን ስትተውን የ14 አመት ልጅ

ነበረች፡፡ አዳነች የምትባለው የጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ

ባለቤትም በዚሁ ቲያትር ላይ ተካፍላለች፡፡ ዕድሜዋም 12

ነበር፡፡ ለአስናቀች ወርቁ የበለጠ ቆንጆ ነበረች፡፡ አዳነች

የአስናቀች የአክስቷ ልጅ ናት የሚሉት ደራሲው ሁለቱንም

አለሁ-አለሁ ከሚሉበት ውቤ በረሃ ክለብ ያመጣቸው

ተስፋዬ ተሰማ ነው፡፡ ውቤ በረሃ ከነበሩት ኪዮስኮች (በዚያን

ጊዜ መጠጥ ቤት ወይም ሴት ቤት ማለት እንደ ነውር ነበር

የሚቆጠረው) መሃል ያስናቀች ወርቁ የእናቷ እህት ኪዮስክ

ነበራቸው፡፡ ያመጣናትም ከዚያው ነው፡፡ እኔም ከጉለሌ

እየተመላለስኩ ነበር የማሰለጥናቸው ይላሉ፡፡

እንደገና እንዲሠራ በማዘጋጃ ቤት ተጠይቆ ሲሰራ ብላታ

ጌታዬ እንደ ታዛቢ ያለውን የትያትር ክፍል እንደተወኑና

ከእሳቸው ጋርም ጌታቸው ደባልቄ፣ማዕዛና መኮንን የሚባሉ

ለጊዜው የአባታቸውን ስም የዘነጓቸውን ጨምሮ ሌሎችም

እንደ ተሳተፉበትና የእሳቸውም ዕድሜ 21 እንደ ነበር

ይናገራሉ፡፡

ብላታ ጌታዬ በውቤ በረሃ ልዩ ትዝታ አላቸው፡፡

አካባቢውን የረገጠ ሆለ ለመርገጥ የሚነሣ ሁሉ የደስታና

ፍስሐ መለያ የሆነውን “ኮ” ና “ካ” በሚገባ ያውቀዋል፡፡

አውቆም ይተገብረዋል ይላሉ፡፡ በጊዜው መጠጥ ቤት (ሴት

ቤት )እንሂድ ማለት ከነውርነት አልፎም ተናጋሪውን ክፉኛ

ስለሚያስገምተው አማራጩና ቀላሉ መንገድ “ኮ” ና “ካ”

እንሂድ ማለት ብቻ ነበር፡፡

ስያሜው የተወሰደው አረንቻታ ሆነ አልኮል ነክ መለኪያ

የሚያነሣ ሁሉ ከጐኑ ያለውን ጠጪ የማያውቀው ቢሆን

እንኳን ለ “ጤናችን” ብሎ ማጋጨት እንደ ባሕልና ስርዓት

የሚቆጠር በመሆኑ ሁለቱ የሚጋጩት ቁሶች የሚፈጥሩት

ድምጽን በመውሰድ “ኮ” ና “ካ” የሚል ስያሜ ተሰጠው፡፡

1930 ዓ.ም መጨረሻዎቹ ጀምሮ “ኮ” ና “ካ” የማያውቅ

ከተሜኛ አለ ለማለት በጣም ያስቸግራል፡፡ እንዲያውም

የከተሜኛ መለያ ነበር የሚሉት ብላታ ጌታዬ አስፋው ክቡር

ዘበኛ ከነዩኒፎርሙና ጐፈሩ፣በሬዲዮ የምትሰማቸውና በክብረ

በአላት የምታያቸውን ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና ሲቪል

ባለሥልጣኖች ወደ እነዚህ ክበባት ሲገቡ ልትመለከታቸው

ትችላለህ፡፡

ውቤ በረሃ የሚገባ ሁሉ ለአልኮል መጠጥ ብቻ

አይደለም፡፡ የአቶ ተፈራ ሻረው የመጠጥ ኢንዱስትሪ

የሚያመርተው ዞማ (የፋንታ አይነት መጠጥ) ጨምሮም

እነ አረንቻታን ለመጠጣት ነው፡፡ አልኮልም ካስፈለገ እነ

መሎቲ ኮኛክ፣እናትና ልጅ (ኡዞ) አረቄ የጊዜው ተመራጭ

መጠጦች ነበሩ፡፡ በዋነኛነት ግን አዲስ አበቤው ወደ

ስፍራው የሚያመራው ውበትን አይቶ ለማድነቅና ለመንካት

ነው፡፡ ሴቶቹ በጣም የሚከበሩበት ጊዜ በመሆኑ በሥነ-

ስርዓት ለማግባባት ይሞከራል እንጂ መጐነታተል ሆነ

ፀያፍ ቃላቶችን መናገር እንደ ባለጌ የሚያስቆጥር ነው፡

፡ ተዋናይዋም ከዚህ የፍቅርና የውበት በረሃ ብቻ ሣይሆን

ቸበር ቻቻ መድረክ በመውጣት ወደ ጥበበ መግባቷ ተፈጥሮ

የራሷን እንጂ አርቴፊሺልና ጊዜያዊ ለሆነ ክስተት ቦታ

የማትሰጥ ለመሆኗ አስረጅ ነው፡፡

ፓን-አፍሪካኒዝም

9

ብላታ ጌታዬ አስፋው ተፈራ የትያትርና መጽሐፍ

ደራሲ ብቻ አልነበሩም፡፡ ጥሩ ዲፕሎማትም ነበሩ፡፡ በንጉሱ

ጊዜ ናይጄሪያ በሚገኘው ኤምባሲያችን ቻንስለር እስከ

መሆን ደርሰዋል፡፡ አምባሳደሩም ክቡር ከበደ አበበ ነበሩ፡

፡ ብላታ ጌታዬ ከዲፕሎማትነት ሙያቸው ውጭም በፓን-

አፍሪካኒዝም አቀንቃኝነታቸው ይታወቃሉ፡፡

ፓን-አፍሪካኒስት ለምታየው ጥቁር ቆዳ ክብርና

ነፃነት የሚቆረቆር፣ለንጣት የማይሰግድ በሰው ልጅ

እኩልነት የሚያምን ነው፡፡ አውስትራሊያዊ ከጀርመን

ጋር ከተጋባ ለዘረኞቹ ያው ፋልስ ነው፡፡ ለዚህ ነው

ፓን -አፍሪካኒስት ለአፍሪካውያኖች ብቻ ሣይሆን

ለኤሮፓዊው፣ለኤዢያዊው፣ለላቲናዊው ሁሉ ክብርና ነፃነት

የሚያጎናጽፍ ነው የምንለው፡፡ ከዚህ በመነሣት አንዳንዶቹ

እንደ ሃይማኖት ቢቆጥሩት አይፈረድባቸውም፡፡

እ.አ.አ 196ዐ ዓ.ም ሌጎስ ናይጄሪያ ላይ ከማንዴላ ጋር

ስንገናኝ ቡና እየጠጣን ስለ ነፃነትና ፓን-አፍሪካኒዝም ዙሪያ

ብዙ አውርተናል፡፡ ማንዴላ ናይጄሪያ የመጡት ቀ.ኃ.ሥ

ሌጐስ መግባታቸውን መንስዔ በማድረግ ነበር፡፡ በወቅቱ

ሌጎስ ልክ እንደ አዲስ አበባ የማይመጣ የነፃነት ታጋይ

አልነበረም የሚሉት ፓን-አፍሪካኒስቱ ሎንደን እንዳለሁም

ጃማይካውያኖች ባደረጉልኝ ግብዣ በተገኘሁበት ወቅት

ያገሬን ባንዲራ ከማልበሳቸውም በላይ ንጉሱን የማምለክ

ሥርዓት ሲከውኑ ስመለከት በጣም ነው የተደነቅኩት ይላሉ፡

ሰሜን አፍሪካውያኖች ፓን-አፍሪካኒዝምን ይደግፉ

ይሆን? ስል ጥርጣሬዬን አንስቼላቸው ነበር፡፡ ለዚህ ጥርጣሬ

ብላታ ጌታዬ አስፋው ተፈራ “ . . . እንደ እነ ሰር አቡበከር

ታፌዋ ባሌዋ ያሉ አንተ ጥቁር ነህ እኔ አረብ ነኝ ይሉ ነበር፡፡

ናይጄሪያ ብትሄድ ካኑ የሚባሉ የሰሜኑ ክፍል ሕዝብ ጥቁር

አረብ ነን ይላሉ፡፡ ይህም ዘሬን (ትውልዴን)ከፍ አደርጋለሁ

ከሚል የመጣ ከንቱ አመለካከት ነው፡፡ ሕዝቡንና ሃገሩን

ያልወደደው የሊቢያው አምባገነንም የአፍሪካ ጎሣ መሪዎችን

በየስብሰባ አዳራሹ እየሰበሰበ አንድ አፍሪካ ይለው

የነበረው ስብከት ከልቡ እንዳልሆነ የምታየው ነው፡፡ ፓን-

አፍሪካኒዝም የተረሳ ሃሳብ ነው የሚለው እሳቤም ፓን-

አፍሪካኒስት በአገሩ ጊዜያዊ ችግር የማይፈታና ችግር አይቶ

የሚጠነክር ነው፡፡ ለዚህም ያደረሰው አርቆ አሳቢነቱ ነው

በማለትም ጥንካሬውን ያጐሉለታል፡፡”

ብላታ ጌታዬ አስፋው በአህጉራቸው ዙሪያ በርካታ

ሥራዎችን አበርክተዋል፡፡ ናይጄሪያ እያሉ “African march

to unity” የተሰኘ ባ 25ዐ ገጽ መጽሐፈ በ1961 ዓ.ም እንዲሁም

በቅርቡ 400 ገጽ “Afirca past present and future

development” የሚባል ጽፈዋል፡፡ ሁለቱም መጽሐፎች

የተደረሱት በእንግሊዘኛ ቋንቋ ነው፡፡ በወታደራዊው

ሥርዓትም ርእሱ የአፍሪካ ኢኮኖሚ የሚልና 350 ገጽ

የያዘ 10,000 ኮፒ ቼምበር ማተሚያ ቤት በሕትመት እያለ

ድንገት የመጡት የደህንነት ሰዎች አይናቸው እያየ ቤንዚን

አርከፍክፈው ካቃጠሉት ድርጊት በላይ የሚቆጫቸው

አንድም ኮፒ በእጃቸው ላይ አለመቅረቱን ነው፡፡

የተረካቢ ያለህ

ብላታ ጌታዬ አስፋው ተፈራ ከመስከረም 20 ቀን እስከ

ጥቅምት 5 ቀን 1970 ዓ.ም ድረስ በተካሄደው የአፍሮ ኤዢያ

ደራስያን ማሕበር የተመሠረተበት 20ኛ ክብረ በአል ላይ

ከአቶ አሰፋ ገ/ማርያም ጋር በመሆን ተካፍለዋል፡፡ በዚሁ

በ20 ቀናት ቆይታቸው ያዩትን ሁሉ በግጥም መልክ አካተው

በቅርቡ ለንባብ እንደሚያበቁ እምነት አላቸው፡፡ግጥሙ

ከአዲስ አበባ እስከ ሞስኮና ከሞስኮ በኋላ ሰባት ሰዓት በፈጀ

የአይሮፕላን በረራ ተጉዘው ታሽኬንት ግዛት ደርሰው ያዩትን

ሁሉ የያዘ እንደሚሆን ይናገራሉ፡፡

ስለሶቪየት ስነ-ጽሑፍ ሲያነሱም ሶቪየቶች ከላይ ወደ

ታች ነው የጀመሩት፡፡ እንደምዕራባውያንና አሜሪካውያኖቹ

ከታች ወደ ላይ አይደለም፡፡ ይህ የሆነበትም በሁለተኛው

የዓለም ጦርነት ሁሉ ነገር ለሩስያኖቹ ስለ ተፋለሰባቸው

መሆኑን ይገልፃሉ፡፡

ደራሲው አንድ ቅር የሚያሰኛቸው ጉዳይ ሣይናገሩ

ማለፍ አይፈልጉም፡፡ የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ የኢትዮጵያ

ደራስያን ማሕበር ፕሬዝደንትን አግኝተዋቸው በእጃቸው

ላይ የሚገኙትን የራሳቸውንና የሌሎች አንጋፋ ጸሐፍትን

ሥራዎች ተረከቡኝ ቢሏቸው ደብዳቤ ፃፉልን ሲሉ

የሰጡዋቸው ምላሽን፡፡ አናምንህም ማለታቸው ይሆን?

ሲሉ እራሳቸውን መልሰው ይጠይቃሉ፡፡ ብላታ ጌታዬ

አስፋው ሌላው ቅሬታቸው የሚመነጨው ደግሞ አዲስ

አበባ የአፍሪካ መዲና በመሆኗ በፓን-አፍሪካ ዙሪያ የተፃፉ

መጻሕፍትና ሠነዶች ተረክባችሁኝ አንድ ቤተመጽሐፍት

ክፈቱ ስል ለሚመለከታቸው አቤት ብልም ምላሽ የሚሰጠኝ

አካል አላገኘሁም ይላሉ፡፡

ፈጣሪ ዕድሜ ካልነፈገኝ የፍቅር ጮራን ወደ መድረክ

እመልሰዋለሁ የሚሉት ደራሲ 14 መጽሐፍትን ለተደራስያን

ሲያበረክቱ 10 ሕትመትን የሚጠባበቁ ሥራ እንዳሏቸው

ይናገራሉ፡፡ እኝህ አንጋፋ የስነ-ጽሑፍ ሰው የ80 ዓመት

የእድሜ ባለ ፀጋ ናቸው፡፡

www.andinet.org.et

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!