የመሬት ቅርምት ለልማት - Ethiopia: A voice for the voiceless
የመሬት ቅርምት ለልማት - Ethiopia: A voice for the voiceless
የመሬት ቅርምት ለልማት - Ethiopia: A voice for the voiceless
You also want an ePaper? Increase the reach of your titles
YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.
6

ግርማ ካሣ

የሕንድ፣ የቻይናና የሳውዲ ኩባንያዎች በአገራችን

ኢትዮጵያ ለእርሻ ሥራዎች ሰፊ መሬት በሊዝ እንደወሰዱ

መሆናቸው በስፋት ተዘግቧል። የገዢው ፓርቲ

ባለስልጣናት «ሰዎች የማይኖሩባቸው ቦታዎችን ነው

ለልማት ስንል ለውጭ አገር ዜጎች የሰጠነው» ይላሉ።

ተቃዋሚዎች በበኩላቸው ያለ ውዴታቸው ዜጎች

እንደተፈናቀሉ ይናገራሉ፡፡ የመሬቱም “ሽያጭ” በርካሽ

ዋጋ፣ እስከ 99 አመታት ላለ ረጅም ጊዜ እንደሆነ

በመግለጽ፣ የገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግን እንቅስቃሴ

ጸረ-ሕዝብና የአገርን ጥቅም የሸጠ እንደሆነ አድርገው

ያቀርባሉ።

አንድ ጊዜ፣ ከአዲስ አበባ የመጣ አፍቃሪ

ኢሕአዴግ የሆነን ሰው «መሬት ለ99 አመታት ለውጭ

አገር ዜጎች ይሸጣል ይባላል። እውነት ነው ወይ?»

ብዬ ጠየኩት። ለ99 አመታት ለውጭ አገር ዜጎች

መሬት በሊዝ እንዳልተሸጠ፣ ቢበዛ ለ25 አመታት ብቻ

ሊሆን እንደሚችል ገለጸልኝ። 25 አመት ለምን ሊሆን

እንደሚችል ሲያስረዳኝ «የተሰጠውን ቦታ ኢንቨስተሮች

መጀመሪያ ማልማት አለባቸው። መንገዶች ይሰራሉ።

ለሰራተኞች የሚሆን በአካባቢው ትምህርት ቤቶች፣

መኖሪያ ቤቶች ይሰራሉ። ይሄ አይነት ቅድመ ትርፍ

ሥራዎች ሁሉ፣ ቢያንስ ከአምስት እስከ አሥር አመት

ይፈጃሉ። ትርፍ ሊያገኙ የሚችሉት ከአሥር አመት በኋላ

ቢሆን ነው። ያን ሁሉ ሰርተው፣ ያን ሁሉ ገንብተው፣

ለእነርሱም ትርፍ የሚያገኙበት ሚዛናዊ የሆነ ተጨማሪ

አሥር አሥራ አምስት አመታት መስጠት ያስፈልጋል።

አለበለዚያ ኢንቨስት ላድርግ ብሎ የሚመጣ አይኖርም»

ነበር ያለኝ። ይህ እንግዲህ የአንድ አፍቃሪ ኢሕአዴግ

ቃል ነው። ያለኝን አለኝ እንጂ ውሎች በርግጥ 25

አመታት ብቻ መሆናቸውን፣ የሚያረጋግጥበት አንዳች

አይነት መረጃ አላቀረበልኝም።

ከዚህ ከኢሕአዴግ ደጋፊም ሆነ ከሌላ ምንጮች፣

ለውጭ አገር ዜጎች የሚሰጠው መሬት በምን ሂሳብ፣

ለምን ያህል ጊዜ እንደሆነ በተጨባጭ በመረጃ

የተገለጸበት ቦታ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ላገኝ

አልቻልኩም ነበር።

ሱልጣን ኢብራሂም አሰብን ለጣሊያኖች እንደ

ሸጠ፣ የአገራችን መሬት፣ እኛ በማናውቀው መንገድ

ለውጭ አገር ዜጎች እየተቸበቸበ ይሆን? ከአመታት

በኋላ ኢትዮጵያ የሕንዶችና የቻይናዎች አገር

ትሆን ይሆን? አይናችን እያየ በልማት ስም ብሄራዊ

ጥቅማችን እየተሸረሸረ ይሆን? ወይንስ ጥቅም ላይ

ያልዋለ መሬቶችን ጥቅም ላይ በማዋል፣ ለዜጎች የሥራ

እድል የሚከፍቱ፣ እህል በአገራችን ገበያዎች በብዛት

እንዲኖሩ የሚያደርጉ፣ የስንዴም የጤፍ የስኳርን ዋጋ

የሚያስቀንሱ፣ ገጠሪቷ ኢትዮጵያን የሚያለሙ፣ ጸረ-

ድህነትና አገር ጠቃሚ ተግባራት ነው እየተሰሩ ያሉት?

በቅርቡ በሰሜን አሜሪካ የሚንቀሳቀስ የአዲሲቷ

ኢትዮጵያ ሶሊዳሪቲ ንቅናቄ የሚባል የሲቪክ ማህበር፣

እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ለብዙ ጊዜ ማወቅ የምፈልገውን፣

ከላይ ለጠቀስኳቸው ጥያቄዎች አንዳንድ ምላሽ

የሚሰጥን መረጃ ይፋ አድርጓል። የአዲሲቷ ኢትዮጵያ

ሶሊዳሪቲ ንቅናቄ አክቲቪስቶች፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ

ሊያውቀው፣ ሊመረምረው፣ መላ ሊፈልግለት

የሚገባውን ይህ አይነቱን ቁልፍ መረጃ አቀናብረው፣

ይፋ ማድረጋቸው በጣም ሊያስመሰግናቸው የሚገባ

ትልቅ ተግባር ነው። እጅግ በጣም ትልቅ ሥራ ነው

የሰሩት።

ያልሆነውን ሆነ በማለት፣ በስሜት በመነዳት ብቻ

መቃወም ሳይሆን፣ ይህ አይነቱን ጥናታዊ፣ በእውነት

ላይ የተመሰረተ፣ ማንም ጥሩ አእምሮ አለኝ የሚል ዜጋን

አእምሮ የሚቆረቁር መረጃዎችን ማሰባሰብና ለሕዝብ

ማሳወቅ፣ ተቃዋሚዎች በዋናነት ሊሰሩት የሚገባ ትልቅ

ተግባር ነው። የአዲሲቷ ኢትዮጵያ ሶሊዳሪቲ ይህንኑ

ነው ያደረገው።

ሶሊዳሪቲ ይፋ ካደረጋቸው መረጃዎች መካከል፣

ምን ያህል መሬት፣ በየትኛው ክልል በሊዝ እንደተሰጠ፣

ለማን እንደተሰጠ፣ በምን ያህል ዋጋ እንደተሰጠ

የሚገልጹ፣ የመንግስት ባለስልጣናት የፈረሙበትና

ማህተማቸውን የመቱበት፣ ሊካዱ የማይችሉ፣

የማያከራክሩ የሕግ ሰነዶች ይገኙበታል።

ለውጭ አገር ዜጎች የተሰጠው መሬት ስፋት

ለኢትዮጵያውያን በሊዝ የተሰጡትን መሬቶች

ለጊዜው ትተናቸው፣ ለውጭ አገር ዜጎች የተሰጡት

www.andinet.org.et

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 23 2004 ዓ.ም.

መሬቶች ብቻ ብንመለከት፣ ለቻይና ኩባንያ 25000

ሄክታር፣ ለሳውዲ ኩባኒያ 10000 ሄክታር፣ ለሕንድ

ስድስት ኩባንያዎች 246,5012 ሄክታር መሬቶች በሊዝ

ታድሏል።

ይህንን አሃዝ አብዛኞቻችን በሚገባን መልኩ

እንደሚከተለው ለማስቀመጥ እሞክራለሁ፡

1. ወደ አራት ሚሊዮን ሕዝብ የሚኖሩባት የአዲስ

አበባ ከተማ ስፋት 54,000 ሄክታር አካባቢ ነው።

በሌላ አባባል የአዲስ አበባን አምስት ጊዜ የሚያህል

መሬት ነው ለውጭ አገር ዜጎች የተሰጠው።

2. በሕንድ በርካታ ፌደራል ክልሎች አሉ። ከነዚህ

ክልሎች መካከል በደቡብ ምዕራብ የምትገኘው፣ ወደ

34 ሚሊዮን ሕዝብ የሚኖርባት የኬራላ ክልልንና

በሰሜን የምትገኛዋ ወደ 26 ሚሊዮን ሕዝብ የሚኖርባት

የሃሪያና ክልል ይገኙበታል። ኬራላ ስፋቷ 3,886,300

ሄክታር ስትሆን ሃሪያና 4,421,200 ሄክታር ትሰፋለች።

ለውጭ አገር ኩባንያዎች የተሰጠውን መሬት

ስንመለከት፣ የኬራላን ስድስት በመቶ የሃሪያናን ደግሞ

5.4 በመቶ የሚሆንን መሬት ያህላል። በኬራላ የሕዝብ

ብዛትን በሄክታር ብናሰላው፣ በአገራችን ለውጭ አገር

ዜጎች የተሰጠውን መሬት በሚያክል የኬራላ ክልል ቦታ

2,147,884 ሕዝብ ይኖራል። በሌላ አባባል 2,147,884

ሊያኖር የሚችልን መሬት ነው ለውጭ አገር ዜጎች

የተሰጠው።

3. ሉክሳምበርግ በአውሮፓ፣ ፈረንሳይን በሰሜን

ምእራብ ሆላንድንና ቤልጅየምን በሰሜን የምታዋስን

አገር ናት። ስፋቷ 258,600 ሄክታር መሬት ነው።

ለውጭ አገር ዜጎች በኢትዮጵያ የተሰጠው መሬት

ሉክሳምበርግን የሚያክል መሬት ነው።

4. በመቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን በከንቱ

ያለቁበት የባድመ ይገባኛል ጦርነት ነው። የባድመ

ከተማ ከዳር እስከ ዳር ከአንድ ኪሎሜትር አትበልጥም።

በመሆኑም ስፋቷ ከ100 ሄክታር ያነሰ ነው ማለት

ይቻላል። እንደሚታወሰው ከ100 ሄክታር በታች ለሆነ

መሬት ነው፣ ያ ሁሉ የንብረት እልቂት የተከሰተው፣ ያ

ሁሉ ደም የፈሰሰው። ለውጭ አገር ዜጎች የተሰጠው

250,012 ሄክታር መሬት በስፋቱ፣ 2,500 ባድማዎች

እንደተሰጡ የሚያስቆጥር ነው። ለአንድ ባድማ ያን

ያህል መስዋእትነት ሲከፈል ለ2,500 ባድማዎች በቀላሉ

መሬቶች ሲሰጡ ማየት እጅግ በጣም የሚያሳዝንና

እያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ ሊያስቆጣ የሚገባ ጉዳይ

ነው።

ለውጭ አገር ዜጎች የተሰጠው መሬት ለምን ያህል

ጊዜ እንደሆነ

የተሰጠው መሬት ብዛት አሳሳቢነት እንደተጠበቀ

ሆኖ፣ ለምን ያህል ጊዜ ነው ሊዙ የተፈረመው የሚለውን

ጥያቄ ስናነሳ ከአዲስ አበባ መጥቶ ያነጋገርኩት አፍቃሪ

ኢኮኖሚ

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.10

የመሬት ቅርምት ለልማት ወይንስ

ለአገር ጉዳት?

የሲ.ኤል.ሲ የሕንድ ኩባንያ ለአምሳ

አመታት መሬቱን ከተጠቀመ በኋላ

የሚከፍለው ጠቅላላ ዋጋ ወደ 2

ሚሊዮን ብር ብቻ ሲሆን፣ ይህም

በአዲስ አበባ 0.02 ካሬ ሜት

ለሚያወጣ መሬት የሚከፈል ዋጋ

ነው። ሌላው ከዋጋው ነገር በተገናኘ

ለማንሳት የምፈልገው ሌላ ነጥብ

አለ።በመሬቱ «ሽያጭ» ስምምነቶች

እንደምናየው ኩባንያዎቹ የሚከፍሉት

በውጭ ምንዛሪ በዶላር ወይንም ዩሮ

ሳይሆን በኢትዮጵያ ብር ነው። የብር

ዋጋ ካሽቆለቆለ እነርሱም የሚከፍሉት

ክፍያ የዚያኑ ያህል ያሽቆለቁላል።

ለምሳሌ አገሬን ለቅቄ ስደት ስጀምር፣

አንድ የአሜሪካን ዶላር በ2.07 ብር

ነበር የሚመነዘረው። አሁን አንድ ዶላር

በ17.5 ብር ይመነዘራል...

ኢሕአዴግ ከነገረኝ ጋር ፈጽሞ የማይሄድ ሆኖ ነው

ያገኘሁት።

ከተሰጡት መሬቶች መካከል 178, 012

(71 በመቶ) ሄክታር መሬት ለአምሳ አመት ነው

የተሰጠው። አሁን ላለው ትውልድ ብቻ ሳይሆን

ለሚቀጥለውም ትውልድ መዘዝ የሚፈጠር ስምምነት

እንደተፈረመ ነው የምናየው።

እንደዚያም ሆኖ ግን በስምምነቶቹ

እንደተቀመጡት የፌዴራል መንግስቱ የተሻለ ሶሲዮ

ኢኮኖሚ ጥቅም ከተገኘ የስድስት ወራት ጊዜ ሰጠቶ

ሊዙን መሰረዝ የሚችልበት ሁኔታ አለ። ለምሳሌ

ከካሩቱሪ የሕንድ ኩባንያ ጋር በተደረገው የስምምነት

ውል አንቀጽ 5.4 “The lessor has exclusive right

to terminate the land lease agreement subject

to at least six months prior notice in written

up on the Federal Government’s decision for

any better socio-economic benefit” ይላል።

ስለዚህ ውሉን በተፈለገ ጊዜ መሰረዝ እስከተሻለ

ድረስ የውሉ ዘመን 25 ሆነ አሥር ሆነ ብዙም ስጋት

ውስጥ የሚከት አይመስለኝም።

ለውጭ አገር ዜጎች የተሰጠው መሬት ዋጋው

ምን እንደሆነ

በአሁኑ ጊዜ አዲስ አበባ ውስጥ እንደ ገርጂ

በመሳሰሉ ብዙ ቦታዎች ወደ 200 ካሬ ሜትር (0.02

ሄክታር) ስፋት ያለው ቤት ከሁለት ሚሊዮን ብር ያነሰ

አይገኝም። አንድ ሄክታር መሬት ወደ 67 ሚሊዮን

ብር ነው የሚያወጣው እንደ ማለት ነው። አስቡት …

መቶ ሺህ ሄክታር መሬት ስድስት ትሪሊየን፣ ስድስት

መቶ ቢሊዮን ብር ይደርሳል።

ሲ.ዔል.ሲ ስፔንቴክስ ለተባለው የሕንድ ኩባንያ

100,000 ሄክታር መሬት ለአምሳ አመት የተሰጠበት

ዋጋ ሃያ ብር ( አንድ ዶላር ከሃያ ሳንቲም) ብቻ ነው።

በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባ በአንድ ተራ ምግብ ቤት፣

ጥቂት ጉርሻ የሚሆን ስጋ ጣል ጣል የተደረገበት አንድ

እንጀራ ወጥ ምግብ ለመመገብ 170 ብር ያወጣል።

የአንድ እንጀራ ምግብ ዋጋ 8.5 ሄክታር ይገዛል።

የሲ.ኤል.ሲ የሕንድ ኩባንያ ለአምሳ አመታት

መሬቱን ከተጠቀመ በኋላ የሚከፍለው ጠቅላላ ዋጋ

ወደ 2 ሚሊዮን ብር ብቻ ሲሆን፣ ይህም በአዲስ

አበባ 0.02 ካሬ ሜት ለሚያወጣ መሬት የሚከፈል

ዋጋ ነው። ሌላው ከዋጋው ነገር በተገናኘ ለማንሳት

የምፈልገው ሌላ ነጥብ አለ።በመሬቱ «ሽያጭ»

ስምምነቶች እንደምናየው ኩባንያዎቹ የሚከፍሉት

በውጭ ምንዛሪ በዶላር ወይንም ዩሮ ሳይሆን

በኢትዮጵያ ብር ነው። የብር ዋጋ ካሽቆለቆለ እነርሱም

የሚከፍሉት ክፍያ የዚያኑ ያህል ያሽቆለቁላል። ለምሳሌ

አገሬን ለቅቄ ስደት ስጀምር፣ አንድ የአሜሪካን ዶላር