Neger Ethiopia Issue 2
Neger Ethiopia Issue 2
Neger Ethiopia Issue 2
You also want an ePaper? Increase the reach of your titles
YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.
3 የካቲት 7 ቀን 2006 ዓ.ም. ቅፅ 1 ቁጥር 2 ነገረ-ኢትዮጵያ

ልብ አድርጉ

ውህደት ወይስ ትብብር?

በላይ ማናዬ

ሀገር አቀፉ ምርጫ 2007 እየደረሰ ነው፤

ምርጫን ተከትሎ የሚስተዋለው የፖለቲካ

ግለትም በትንሹም ቢሆን ከወዲሁ ለብ

ማለት የጀመረ ይመስላል፤ የት መሽገው

እንደከረሙ ጠፍተውብን የነበሩ የፖለቲካ

ፓርቲዎችም አንገታቸውን ብቅ ለማድረግ

እየሞከሩ እንደሆነ መታዘብ ይቻላል፡፡

በሀገራችን በፓርቲዎች የቁጥር ብዛት ረገድ

ችግር የለም ማለት ይቻላል፡፡ ባለፈው

ምርጫ 2002 እንኳ ወደ 90 የሚጠጉ

ፓርቲዎች እንደነበሩ ይታወቃል፡፡

በእርግጥም አሁን ላይ ኢትዮጵያ

ውስጥ በቁጥር በጣም ብዙ የፖለቲካ

ፓርቲዎች ተመዝግበው ይገኛሉ፤

(በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚንቀሳቀሱትን

ህብረ-ብሄር ፓርቲዎችም፣ ጎሳን ወይም

አንድን ብሄረሰብ ማዕከል አድርገው

የሚንቀሳቀሱትንም ማለቴ ነው)፡፡ ለአብነት

በሁለተኛው ረድፍ ላይ ከሚመደቡት እንኳ

ብናይ ለኦሮሞ ህዝብ እንታገላለን የሚሉት

ከ10 በላይ፣ ጉራጌ 5፣ አርጎባ 3፣ ሀረሪ

3 እና ሌሎችም በተመሳሳይ በርካቶች

አሉ፡፡ በዚህም ከአጠቃላይ የፓርቲዎች

ቁጥር አብላጫውን ሀገር አቀፍ ያልሆኑት

ፓርቲዎች ይዘው ይገኛሉ፡፡ (የምዝገባ

ፍቃዱን ወስዶ ዳናው የሚጠፋውም ጥቂት

የሚባል አይደለም፡፡)

ይህ ቁጥሩ የበዛ የፓርቲዎች እንቅስቃሴ

ያለው ደግሞ በተቃውሞው ጎራ በኩል

ነው፡፡ እንዲህ አይነቱ የፓርቲዎች አካሄድ

ማንን እንደሚጠቅም ሳይታለም የተፈታ

ነው፡፡ በምርጫ ወቅት የህዝብን ድምጽ

በመከፋፈል የትኛውም ተቃዋሚ ፓርቲ

አብላጫ ድምጽ በቀላሉ እንዳያገኝ በማድረግ

ለገዥው ፓርቲ በተዘዋዋሪ ይጠቅመዋል፡

፡ ስለሆነም እንዲህ ባለ ወቅት ተቃዋሚ

ፓርቲዎች በሁለት አማራጮች ላይ

ይንጠለጠላሉ፤ አንድም በቁጥር የበዙትን

ፓርቲዎች ወደ አንድ ኃይል ማምጣት

ላይ፣ አሊያም በተናጠልም ቢሆን በሀገር

አቀፍ ደረጃ ጎልቶ ለመውጣት የሚያስችልን

አቅም ፈጥሮ ገዥው ፓርቲንም ሆነ

ሌሎች ተወዳዳሪዎችን ተፎካክሮ ለማሸነፍ

የሚያስችልን እንቅስቃሴ ማድረግ፡፡

በተግባር እንቅስቃሴ ላይ ያሉትን የተለያዩ

ፓርቲዎች ወደ አንድ ኃይል አምጥቶ

ወደ ምርጫ መግባት በባለፉት የምርጫ

ተሞክሮዎቻችን ላይ አይተናል፤ (ቅንጅትን

በ97፣ መድረክን በ2002 መጥቀስ ይቻላል፡፡

) ያለፉት ሂደቶችና ተሞክሮዎች የራሳቸው

ጥንካሬና ድክመት እንደነበረባቸው መካድ

አይቻልም፡፡ ያም ሆነ ይህ ግን አሁን

ሌላ የታሪክ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን፡

፡ ቀደም ብዬ እንደጠቀስኩት ምርጫ

2007 እየደረሰ ነው፡፡ ስለሆነም አሁን

ፓርቲዎች የበለጠ ለስራ የሚነሱበት ጊዜ

ነው፤ በተናጠልም፣ በትብብርም፡፡ ከዚህ

ጋር ተያይዞ በዚህ ሰሞን ስለ ፓርቲዎች

ውህደትም የሚያነሱት በዝተዋል፡፡ ይህን

የውህደት ጉዳይ እንደሚከተለው ለማየት

እንሞከራለን፡፡

ውህደት እንዴት?

በአጭሩ ውህደት አንድ መሆን ማለት

ነው፡፡ ከውህደት በፊት ያለው የተናጠል

ህጋዊ ህልውና አክትሞ አዲስ ፓርቲ

በአንድ ላይ መመስረት ነው ውህደት፡

፡ አንድ ለመሆን ደግሞ፣ አንድ ለመሆን

የሚያስችሉ ሁኔታዎች መኖር አለባቸው፡

፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለመዋህድ የፖለቲካ

ፕሮግራማቸው መመሳሰልና መቀራረብ

ይኖርበታል፡፡ ከዚህም በላይ ግን ፓርቲዎቹ

ለመዋህድ ፍላጎት ማሳየት የግድ ነው፤

በውህደቱ ሂደትና ከውህደት በኋላ

ስለሚኖረው እንቅስቃሴም የተሻለ መስራት

እንደሚችሉ ሊያምኑበት ይገባል፡፡ በዚህም

ማን ከማን ጋር መዋህድ እንደሚችል

ካላቸው የፖለቲካ ፕሮግራም፣ የውህደት

ፍላጎትና በመዋህዳቸው ሊያመጡት

የሚችሉትን ውጤት ገምግመው፣ ወይ

ወደ ውህደት ይገባሉ አሊያም በራሳቸው

መስመር ጠንክረው ለመስራት ውሳኔ

ያስተላልፋሉ፡፡

ከሰሞኑ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት

ድርጅት (መኢአድ) እና አንድነት

ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት)

በአስቸኳይ ለመዋህድ እየሰሩ እንደሆነ

ገልጸዋል፡፡ ፓርቲዎቹ ጥር 25 ቀን 2006

ዓ.ም መአህድ/መኢአድ የተመሰረተበትን

22ኛ አመት በዓል በጽ/ቤቱ ባከበረበት ወቅት

እንደገለጹት፣ ሁለቱ ፓርቲዎች በፍጥነት

ወደ ውህደት ለመምጣት መወሰናቸውን

በይፋ በመሪዎቻቸው በኩል ግልጽ

አድርገዋል፡፡ የመኢአድ ፓርቲ ፕሬዚዳንት

አቶ አበባው መሐሪ ፓርቲያቸው መኢአድ

ከአንድነት ፓርቲ ጋር መዋሃድ ፍላጎቱ

መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ በቀድሞ ፓርቲያቸው 22ኛ

አመት ክብረ በዓል ላይ የተገኙት የአንድነት

ፓርቲ ፕሬዚዳንት ኢ/ር ግዛቸው ሺፈራው

በበኩላቸው ፓርቲያቸው ከመኢአድ ጋር

መዋሃድ ፍላጎቱ መሆኑን ገልጸው፣

በ15 ቀናት ውስጥ ውህደቱ እውን ሊሆን

እንደሚችልም ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡

ፓርቲዎቹ ይህን ይበሉ እንጂ (በዕለቱ

በነበረው የመድረክ ሞቅታ እንዳይሆን

እሰጋለሁ) በዚህ ፍጥነት ሊዋሀዱ

የሚችሉበት ሁኔታ ውስጥ እንዳልሆኑ

ጠቋሚ ምልክቶች መኖራቸውን መካድ

አይቻልም፡፡

ውህደት መቼ?

ውህደት ምርጫ ስለቀረበ የሚከናወን

የይድረስ ይድረስ ስራ እንዳልሆነ እሙን

ነው፡፡ በተቃራኒው ግን በሀገራችን የነበሩ፤

ያሉ ፓርቲዎች ውህደት የሚታያቸው

ምርጫ ሲቃረብ መሆኑ አለመታደል ነው፡፡

አንዳንዶቹ ሂደቱን ቀድመው ቢጀምሩትም

ሲያጓትቱ ሲያጓትቱ እስከ ምርጫ መቃረቢያ

ድረስ ያደርሱታል፡፡ የመኢአድና የአንድነት

ውህደት እውን ቢሆን የሚወድ ብዙ ነው፡

፡ ዳሩ ግን ውህደቱ መሆን የነበረበት

(በእውነት ኢ/ር ግዛቸው እንዳሉት በ15

ቀናት ውስጥ የሚከናወን ከሆነ ወይም

ቢሆን ኖሮ) እንዲህ በሩጫ አሁን ላይ

አይደለም፤ (በ15 ቀናት ውስጥ የሚደረግ

ውህደት የፖለቲካ ፓርቲዎች ሳይሆን….)፡

፡ ይህ ውህደት ከምርጫ 2002 ማግስት

ቢሆን በተገባ ነበር፡፡

ውህደት በተናጠል በውጠ-ፓርቲ ትግል

ፈተና ውስጥ የገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች

መሪዎች ከቀውስ ማምለጫ ወይም አጀንዳ

ማስቀየሻ ሊሆን አይገባም፡፡ በተጨማሪም

አንድ ፓርቲ ከገጠመው የገንዘብ እጥረት

አሊያም የቢሮ ኪራይ ችግር ለመውጣት

ዘው ብሎ የሚገባበት ጉዳይ መሆን

አይኖርበትም፡፡ በሩጫ የሚደረግ ውህደት

ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል ለማንም

የተሰወረ አይሆንም፡፡

እናም ውህደት በቂ ጊዜ ወስዶ መጤን

ያለበት ትልቅ የፖለቲካ ስራ ነው፡፡

እርግጥ ነው ህዝቡ ፓርቲዎቹ እንዲዋህዱ

ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በላይ ግን አብዛኛው

ህዝብ ፓርቲዎች ተዋህደው እንዲዘልቁና

ለውጥ እንዲያመጡ እንደሚሻ ግልጽ ነው፡

፡ ለዚህ ደግሞ ከጅምሩ የሰከነ የውህደት

ሂደት መኖሩ ግድ ይላል፡፡

የውህደት ፈተናዎች

የፖለቲካ ፓርቲዎችን ወደ ውህደት

ማምጣት፣ ከውህደት በኋላም ተስማምቶ

መቀጠል ትልቅ ፈተና አለው፡፡ በተለይም

እንዲህ በአጭር ጊዜ ውህደትን እናመጣለን

ብለው ሰርጋቸውን ከሚያፋጥኑ ሰዎች

ወደ ፊት የሚሆነውን በስጋት መመልከት

ግርምትን የሚፈጥር ጉዳይ አይሆንም፡

፡ በተዋሃጆቹም በኩል የእነቶሎ ቶሎ

ቤት…እንዳይሆን መጠንቀቁ የሚበጅ ነው፡

፡ ምርጫ ስለደረሰ ብቻ በፍጥነት ውህደትን

ማከናወን ሊኖረው የሚችለውን ፈተና

ሊያስረሳን አይገባም፡፡ ሰርገኛ መጣ በርበሬ

ቀንጥስ እንዳይሆን መጠንቀቁ የብልሆች

ምርጫ ነው፡፡

በእርግጥም ውህደት የጥቂት ግለሰቦች

ወይም የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎች

ፍላጎትና ተግባር ብቻ አይደለም፡፡ ከዚያ

ይልቅ የሚዋሃዱት ፓርቲዎች አባላት

(ጠቅላላ ጉባኤ በሚገባ ተወያይቶበት

ውሳኔ ማሳለፍን ይጠይቃል፤) በየደረጃው

ሰፊ ጊዜ ሰጥተው ጉዳዩን ሊወያዩበትና

ሊያጤኑት ግድ ይላል፡፡ ይህን ለማድረግ

የሚያስችላቸው ጊዜም ሊሰጣቸው

እንደሚገባ እሙን ነው፡፡ በሌላ አነጋገር

ውህደቱ ከጅምሩ እሰከ ፍጻሜው አባላትንም

ማዕከል ያደረገ መሆን ይኖርበታል፡፡ ይህ

ሳይሆን ቀርቶ ውህደቱ የጥቂቶች ስራ

ከሆነ፣ አንድም ውህደቱ እውን አይሆንም፣

እውን ከሆነም ዘላቂነቱ አጠራጣሪ ከመሆን

አይድንም፡፡

የውህድ ፓርቲው መሪ

ሌላው ፈተና ውህደቱ ከተፈጸመ በኋላ

የውህድ ፓርቲው (አዲሱ ፓርቲ) መሪ

ማን ይሁን የሚለው ጉዳይ ነው፡፡ የዚህ

ፈተና ምንጭ ውህደቱን ከመሰረቱት

ፓርቲዎች ወገን ሁሉም የቀድሞ ፓርቲው

መሪ፣ የአዲሱ ውህድ ፓርቲ መሪም

ሆኖ እንዲዘልቅለትና ቡድናዊ ጥቅሙን

እንዲያስከብርለት የመፈለጉ ጫና ነው፡፡

በዚህም ሁሉም የየራሱን የቀደመ የትግል

ታሪክና የአደረጃጀት ስፋት እያነሳ ስልጣኑ

እንደሚገባው መሞገቱ ስለማይቀር ነው፡፡

እንዲህ አይነቱ ጉዳይ ደግሞ ማን የተሻለ

መምራት ይችላል ሳይሆን፣ ማን የውህድ

ፓርቲው መሪነት ይገባዋል ወደሚል

ሰንካላ ምክንያት ይገፋናል፡፡

በተመሳሳይ ውህደቱ ከሚከናወንበት

ወቅት አንስቶ፣ ውህደቱ ሊያመጣባቸው

የሚችለውን ከጥቅማ ጥቅምና ስልጣን

ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ማጣት በማጤን

ቅሬታ የሚሰማቸው ግለሰቦችም ሌላኛዎቹ

ፈተናዎች መሆናቸው የማይቀር ነው፡

፡ ከሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ

ፓርቲዎች ወደ አንድ ሲመጡ፣ ቀድሞ

በተናጠል የነበረውን የስራ አስፈጻሚ ያህል

ቁጥር ሊያካትት አይችልም፡፡ በዚህ ጊዜ

ተቀናሾች መኖራቸው ግድ ነው፤ እዚህ

ጋር የሚነሳው ጉዳይ የመቀነሻ መስፈርቶቹ

ናቸው፡፡ ያም ሆነ ይህ በአዲሱ ፓርቲ

የሚደረገው የስልጣን ሽግሽግ በውህደት

ወቅትና ከውህደት በኋላ ከሚገጥሙ

ፈተናዎች መካከል መሆኑ የማይቀር ነው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ከውህደት በኋላም፣

ከግል የስልጣን ጥማቸው ጋር በተገናኘ

በስልጣን ተዋረድ ውስጥ ሁለተኛ ሰው

ሆነው ለመስራት የማይፈልጉና ሁሌም ከኔ

በላይ ላሳር ባዮች አይጠፉም፡፡ በዚህም፣

እንዲህ አይነት ግለሰቦች አንዴ ከፖለቲካ

ሲርቁ፣ ሌላ ጊዜ ያችኑ የመሪነት ቦታ

ሲሰጣቸው ወደ መድረኩ ብቅ የሚሉ

ናቸው፡፡ የእነዚህ ግለሰቦች የስልጣን ጥም

የመሪነት ቦታ የነፈጋቸውን ፓርቲ ለቅቀው

ወደ ሌላ ፓርቲ እስከመሄድ የሚያደርሳቸው

ነው፡፡ ስለሆነም እነዚህን መሰል ግለሰቦች

ዛሬ ስለውህደት አብዝተው ቢሰብኩም

ያችኑ የመሪነት ቦታ የሚያሳጣቸው ጉዳይ

ሲመጣ ሲያቀነቅኑት የነበረውን ዓላማ

ረስተው የውህደቱ እንቅፋት ከመሆን

ላይመለሱ ይችላሉ፡፡

ደካማ የቀደመ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውህደት

ተሞክሮ ያለን ከመሆኑ ጋር ተያይዞ

(በቅንጅቱ መፍረስ የተፈጠረ መንፈስን

ማስታወስ ይበቃል፤) በህዝቡ ዘንድ ያለው

ተስፋ የመቁረጥ ስሜትም እንደ አንድ ሌላ

ፈተና ሊወሰድ የሚችል ነው፡፡ ፈጥኖ ወደ

ውህደት የመግባትን ያህል ከውህደት በኋላ

ተስማምቶ የመቀጠሉ ፈተናም ከባድ ነው፡

፡ ስለሆነም መዋሃዱ መልካም ሆኖ፣ ነገር

ግን አሁንም ከውህደት በፊት መሰራት

ያለባቸው የቤት ስራዎች በጊዜ ከተከናወኑ

በኋላ ቢሆን የተሻለ ውጤት ይኖረዋል፡፡

አሁን ላይ ውህደት ወይስ ትብብር?

ቀደም ብሎ እንደተጠቀሰው ውህደትን

ለማከናወን የተዋሃጅ ፓርቲዎች ፕሮግራም

ተመሳሳይ ወይም ተቀራራቢ መሆን

ይኖርበታል፡፡ በዚህም አንድ ፓርቲ ከሌላው

ጋር ለመዋሃድ መሰሉን ወይም ቢጤውን

መፈለግ ግድ ይለዋል፤ ይህም የሚሆነው

የሌላኛው ፓርቲ ፍላጎት ሲጨመርበት

ነው፡፡ እናም ውህደት አግላይ ጎንም

እንዳለው መገንዘብ ይቻላል፡፡ ለአብነትም

የመኢአድ ሊቀመንበር አቶ አበባው መሐሪ

የፓርቲያቸውን አቋም በሚከተለው መልኩ

ገልጸውታል፡፡

‹‹መኢአድ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ

ከማያምኑ የብሄር (የጎሳ) የፖለቲካ

ድርጅቶች፣ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ

አልደራደርም በማለት፣ በውህደት ደረጃ

አብሮ ለመስራት እቸገራለሁ የሚለው በቂ

ምክንያት ስላለው ነው፡፡›› (አንድነት ከአረና

ትግራይ ጋር ለመዋሀድ ንግግር መጀመሩ

የሚታወቅ ነው፡፡ ታዲያ መኢአድ በአንድነት

በኩል የመጣውን አረና ትግራይን እንዴት

ሊያደርገው ይሆን?) ያም ሆነ ይህ ጉዳዩ

የሚያሳየን የውህደትን አግላይነት ነው፡፡

ከመኢአድ አቋም ለመረዳት እንደሚቻለው

ፓርቲው ለውህደት በሩን የሚከፍተው

ጠንካራ ጥበቃዎችን ከፊት አቁሞ ነው፡

፡ ስለሆነም ውህደት የራሱ ጠንካራ ጎኖች

እንዳሉት ሆኖ፣ እንደ አሸን የፈሉትን

የፖለቲካ ድርጅቶች በጋራ አስተባብሮ ወደ

አንድ የማምጣቱ ነገር ውስን መሆኑን

ነው፡፡

በአብዛኛው የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች

የጋራ የሆነ የሚታገሉት ኃይል አላቸው፤

እሱም ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ነው፡

፡ እነዚህ ፓርቲዎች የየራሳቸው የተለያየ

ዓላማን አንግበው የሚንቀሳቀሱ ቢሆኑም

የወል ጉዳይ እስካላቸው ድረስ ግን መተባበር

ወደ ገፅ 6 ይዞራል