Neger Ethiopia Issue 2
Neger Ethiopia Issue 2
Neger Ethiopia Issue 2
You also want an ePaper? Increase the reach of your titles
YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.
5 የካቲት 7 ቀን 2006 ዓ.ም. ቅፅ 1 ቁጥር 2 ነገረ-ኢትዮጵያ

ፖለቲካ

‹‹መንግስት›› አሳልፎ የሰጠው

ሉዓላዊነት

ጌታቸው ሺፈራው

ለአንድ አገር ሉዓላዊነት ቁልፍ

ከሚባሉት ጉዳዮች መካከል

ወሰን ዋነኛው መመዘኛ ነው፡፡

የወሰን/የድንበር ጉዳይ ድንበር

ብቻ ሳይሆን ከድንበሩ ጋር

ያለውን ታሪካዊ ሂደትም ይጨምራል፡

፡ ለአንድ መንግስትና ትውልድ የቀደሙ

አባቶች ያኖሩትን ድንበር የመቆጣጠርና

መጠበቅ ታሪካዊ ግዴታቸው ነው፡፡

የውጭ አሊያም ሌላ ሀይል የኖረውን

የአገሪቱን ድንበር የሚደፍር አሊያም

የሚያስቀይር ከሆነ የአገሪቱ ሉዓላዊነት

አደጋ ውስጥ ወድቋል ማለት ነው፡

፡ የአንዲት አገርና ህዝቧ ያለ ድንበር/

ወሰን ሊኖር አይችልም፡፡ አገሪቱ ብቻዋን

መሆን እንደማትችል ሁሉ ክብሯን፣

ታሪኳን፣ የዕለት ተዕለት እንቅስቀቃሴዋ፣

ደህንነቷ ላይ ድንበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ

ይኖረዋል፡፡

የወሰን አለመከበር ወይንም ሌላ ችግር

እኒህን ሁሉ ጉዳዮች የሚያዛባ ይሆናል፡፡

ለዚህም ነው ሌሎች አገራት ከሚሰጡት

እውቅና ይልቅ ድንበር የአንድ አገር

በተጨባጭ /የሚታይ/ ሉዓላዊነት

መገለጫ ነው የሚባለው፡፡ ድንበር

ዋነኛው የሉዓላዊነት አካል ስለመሆኑ

የኢትዮጵያ ህዝብ ሲበድሉት የኖሩት

አገዛዞች ‹‹አገርህ ተደፈረች›› ሲሉት

ለጊዜውም ቢሆን ልዩነቱን ወደጎን ትቶ

ዳር ድንበር ሊያስከበር ሲተም መኖሩ

ትልቅ ማስረጃ ነው፡፡ በተቃራኒው

መንግስታቱ ለሉዓላዊነት የህዝብን ያህል

ቁርጠኛ ሆነው አልተገኙም፡፡ በዚህ በኩል

ደግሞ ኢህአዴግ ሉዓላዊነትን አሳልፎ

በመስጠት ወደር አልረገኘለትም፡፡

አንድ አገር ሉዓላዊ የምትሆነው አሊያም

ይህ ክብር የሚቀጥለው ድንበሯን፣

ታሪኳንና የህዝብን ጥቅም አስጠብቆ

የሚኖር አገር ወዳድ መንግስት ሲኖራት

ብቻ ነው፡፡ በዚህ በኩል የአሁኗ

ኢትዮጵያ አልታደለችም፡፡ የአገርን

ጥቅም፣ በደምና በአጥንት የተገነባን

ታሪክና ድንበር አሳልፎ የሚሰጥ አካል

ባለበት የአገሪቱ ሉዓላዊነት አደጋ

ውስጥ ይገባል፡፡ ሉዓላዊነት የአንዲት

አገር ከሌሎች አገራት ጋር ሲነጻጸር

ያላት እኩል ክብር፣ ህጋዊ ሰውነት

እንደመሆኑ መንግስት የሚባለው አካል

ወሰኗን ባልተገባ መንገድ ለሌሎች

አሳልፎ የሚሰጥ ወይንም የሚወሰድበት

ከሆነ ሉዓላዊነቷ ተደፍሯል ማለት ነው፡

፡ ህወሓት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት

ማስደፈር የጀመረው ገና በርሃ በነበረበት

ወቅት ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ከማንም

ቀድሞ በየጊዜው ሰራዊት ወደ ሶማሊያ

የሚልከው ህወሓት ያኔ ገና በርሃ እያለ

ተስፋፊውን የሶማሊያ መንግስት እስከ

ድሬዳዋ ድረስ መንገድ መምራቱን

እንደ አስግደ ያሉት የቀድሞው የቡድኑ

አባላት እማኝነታቸውን በይቅርታ መልክ

ገልጸዋል፡፡

ህወሓት እንደ ፖለቲካ ቡድን

ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ኤርትራ

የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት እንደሆነችና ነጻ

መውጣት እንዳለባት ሲሰብክ ኖራል፡፡

ህወሓት ‹‹አሸባሪ›› በነበረበት በዛ ወቅት

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ

መለስ ዜናዊ ስለ ኤርትራ ጉዳይ ሁለት

መጽኃፍትን ጽፈዋል፡፡ ‹‹የኤርትራ

ህዝብ ትግል ከየት ወደየት›› በተሰኘው

መጽኃፋቸውም ኤርትራን ከኢትዮጵያ

ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌላት

ነጻ አገር መሆኗን አውጀዋል፡፡ አቶ

መለስና ህወሓት ይህን በሚሉበት ወቅት

በርካታ የኤርትራ ተወላጆች በአገሪቱ

አሁን ህወሓት ለሌሎች የግንባሩ አባል

ፓርቲዎች አሳልፎ የማይሰጣቸው ቁልፍ

ስልጣን እንደነበራቸው አይዘነጋም፡፡

ገና ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ኤርትራን

ከኢትዮጵያ መነጠልን አላማው አድርጎ

የተነሳው ህወሓት ደርግን አሸንፎ ቤተ-

መንግስት ሲገባ የወሰደው እርምጃ

የዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ ኤርትራን

እውቅና እንዲሰጥ ማድረግ ነበር፡፡ ይህም

ኢህአዴግን የዋናዋ አገር ገዥ ሆኖ

የአገሪቱ ክፍልን በፈቃደኝነት ያስገነጠለ

(ሉዓላዊነቷን አሳልፎ የሰጠ) ብቸኛው

ፓርቲ ሳያደርገው አይቀርም፡፡ ኤርትራን

በገዛ እጁ ያስገነጠለው ህወሓት/ኢህአዴግ

ከሻዕቢያ ጋር የነበረው ፍቅር ሲያልቅ

የአገሩ ሉዓላዊነት ተላልፎ የተሰጠበት

የኢትዮጵያ ህዝብ በደሉን ለጊዜው ወደጎን

ትቶ ዳር ድንበሩን ለማስከበር ሲነሳ አገዛዙ

የማይጨነቅለትን ሉዓላዊነት ለማስከበር

እንደማይደክመው አሳይቷል፡፡ ጦርነቱ

በኢትዮጵያ ህዝብ አሸናፊነት ከተጠናቀቀ

በኋላም ቢሆን ህወሓት የለመደውን

ሉዓላዊነት አሳልፎ የመስጠት ልክፍት

ደግሞታል፡፡ ይህ አልበቃው ሲልም

ህዝብ ከእሱ በላይ ለአገሪቱ ሉዓላዊነት

እንደሚጨነቅ ጠንቅቆ ስለሚያውቅም

‹‹ባድመን አግኝተናል!›› በሚል ህዝብን

አሞኝቷል፡፡ ይህም ህወሓት/ኢህአዴግ

ከሉዓላዊነት ጋር ያላውን ተቃርኖ

በጉልህ የሚያሳይ ነው፡፡

የኢህአዴግና የሉዓላዊነት ተቃርኖ

አሁንም ቀጥሏል፡፡ ከስድስትና ሰባት

አመታት ጀምሮ የኢትዮጵያን መሬት

አሳልፎ ለሱዳን ለመስጠት በድብቅ

እየተዋዋለ መሆኑ ሲነገር ቆይቷል፡

፡ በቅርቡ ደግሞ ‹‹ሱዳን ትሪብዩን››

የተባለው የሱዳን ጋዜጣ ‹‹ለም መሬታችን

አገኘን!›› የሚል ዜና ማውጣቱን ተከትሎ

ኢህአዴግ መሬቱን ለመስረከብ መቃረቡን

አመላክቷል፡፡ የአንድ አገር መንግስት

የአገሪቱን ድንበር ማስጠበቅና ማስከበር፣

የዜጎቹን ጥቅም ማስከበር ሲኖርበት

ለራሱ ግላዊ ጥቅም፣ ህጋዊ መሰረት

በሌለው መንገድ የአገሩን ወሰንና ድንበር

አሳልፎ የሚሰጥ ከሆነ በአገር ውስጥ

የሌሎች ወኪል ሆኖ የአገርን ሉዓላዊነት

እየደፈረ ከመሆን ውጭ ሌላ ሊባልለት

አይችልም፡፡

ይህ የ‹‹መንግስት›› ተግባር ልክ ቅኝ

ገዥዎቹ የራሳቸው ታማኞች (ባንዳዎች)

እንደነበሯቸው ማለት ነው፡፡ አንዲት

በመንግስት ስር የምትገኝ አገር ሉዓላዊ

የምትባለው ይህ መንግስት የአገሪቱን

ወሰንና ሌሎች ጥቅሟን በህጋዊ መንገድ

መቆጣጠርና ማስተዳደር ከቻለና

በጥቅምም ይሁን በአቅም ማነስ ለውጭ

ሀይል የአገሪቱን ጥቅም፣ ክብር፣ ወሰን

አሳልፎ የማይሰጥ ከሆነ ብቻ ነው፡፡

አገሪቱን ሁለመናው ነገር ተቆጣጥሮና

እያስተዳደረም ቢሆን በውጭ ሀይል

ተጽዕኖ ውሳኔ የሚያስተላልፍ፣

የአገሪቱን ጥቅም አሳልፎ የሚሰጥ

ከሆነ የአገሪቱ ሉዓላዊነቷ ተደፍሯል፡

፡ የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን አሳልፎ

ለመስጠት እየተደራደረ ያለው ኢህአዴግ

የአገርን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ፣ ለህዝብ

ጥቅም በመቆም ከሚታወቅ ‹‹መንግስት››

ከተባለ አካል ይልቅ በሚገዛት አገር

ውስጥ ለሱዳን ጥቅም የቆመ መሆኑን

አሳይቷል፡፡

አንድ አገር ሉዓላዊ ነው የሚባለው

የአገሪቱን ዜጎች ከውጭ ጥቃት

የሚከላከል አካል (መንግስት) ካለ ብቻ

ቢሆንም የሱዳን ኢትዮጵያ ድንበር

ችግር ከተከሰተ በኋላ በመተማና

አካባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን

ለሱዳን የደህንነት ኃይሎች ተላልፈው

ተሰጥተዋል፡፡ ከስድስትና ሰባት አመት

በፊት ደንብር አካባቢ የነበረው የኢትዮጵያ

ሰራዊት ወደኋላ አፈግፍጎ አርሶ አደሮቹ

ከሱዳን የጸጥታ ሀይሎች ጋር ፊት ለፊት

እንዲጋፈጡ ተፈርዶባቸው እንደነበር

በጊዜው ተዘግቧል፡፡ አሁንም ቢሆን

የሱዳን እስር ቤት ውስጥ የሚማቅቁ፣

ሀብትና ንብረታቸው የሚዘረፍና

በርካታ ሰብዓዊ ጥሰት የሚፈጸምባቸው

መኖራቸው እየተነገረ ነው፡፡ ይህን ሁሉ

የሚያደርገው ከኢትዮጵያ መንግስት

ይሁንታን ያገኘው የሱዳን የደህነነት

ሀይል ነው፡፡ በዚህ ረገድ መንግስት

የመጀመሪያውን ህዝብን ከውጭ ጥቃት

የመከላከል የሉዓላዊነት መርህ አሳልፎ

ሰጥቷል፡፡ የራሱ ህዝብ በውጭ ሃይል

አደጋ እየደረሰበት ዝም ማለት ብቻ

ሳይሆን ሱዳኖች ኢትዮጵያውያንን

እንዲያስለቅቁ የፈቀደው መንግስት

የመጀመሪያው የአገሪቱን ሉዓላዊነት

አሳልፎ የሰጠ አካል ነው፡፡

የዓለም አቀፍ ህግን የጣሰው

ድብቅ ስምምነት

የአንድ መንግስት ዋነኛው

ተግባር አገር ውስጥ ህዝብን

የሚያስተዳድርበትን፣ አገሪቱ ከውጭ

አካላት ጋር የምትገናኝበትንና ጥቅሟን

የምታስከብርበት ህግና አግባብ የአገሪቱን

ጥቅም በሚያስከብር መንገድ መቅረጽ፣

ማስከበርና መተግብር ነው፡፡ ዓለም

አቀፍ ህግ ከእዚህ መካከል አንዱ ነው፡

፡ ኢትዮጵያ ከፈረመቻቸው ዓለም

አቀፍ የድንበር ስምምነቶች መካከል

ደግሞ አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገራት ነጻ

ከወጡ በኋላ የተፈራረሙት ‹‹የካይሮ

ስምምነት›› በአብነት ይጠቀሳል፡፡

አንድ አይነት ቋንቋ የሚናገሩ የአፍሪካ

ህዝቦች ለቅኝ ገዥዎች በሚመችና

ዘፈቀደ ድንበር ተከፋፍለው ተገዝተዋል፡

፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ግልጽ ከሆነው

ይልቅ በየጊዜው የሚቀየሩ የቅኝ ገዥ

አስተዳዳሪዎች፣ እርስ በእርሳቸው

በሚወዳደሩ የምዕራባዊያን አገራት

እንዲሁም የአገር ውስጥ ወኪሎች

(ባንዳዎች) ግራ የሚያጋባ ድንበር መሰረት

ተከፋፋለው ኖረዋል፡፡ ለአብነት ያህል

በሁለትና ሶስት የቅኝ ገዥዎች፣ እነዚህ

አገራትን ወክለው፣ አሊያም ለእነዚህ

አገራት ወኪል ሆነው ለየራሳቸው ጥቅም

ከተሸነሸኑት በርካታ ወሰኖች መካከል

አንዲት አገር በስተመጨረሻ ነጻ ስትወጣ

የያዘችውን ይዛ እንድትቀጥል ነው

የተደረገው፡፡ ይህ ግልጽነት የጎደለው

ድንበር፣ የድንበር ክለላም ለግጭት

መሰረት እንደሚሆን የታመነበት የአፍሪካ

አገራት ነጻ ከመውጣታቸው አስቀድሞ

ነው፡፡ በተለይም የተለያዩ አካላትና

ግለሰቦች የየራሳቸውንና ለራሳቸው

የሚጠቅመውን ድንበር የሚያቀርቡ

መሆኑ ግጭቱን የባሰ እንደሚያደርገው

ታምኖበታል፡፡ ይህም በመሆኑ የአፍሪካ

ህብረት ቻርተር ከጸደቀ ከአመት በኋላ

ይህን ችግር ለመቅረፍ የአፍሪካ አንድነት

ድርጅት በካይሮ ተገኝቶ ቀኝ ገዥዎች

ተክለውት የሄዱትን የድንበር ችግር

ይፈታል ያለውን ስምምነት አጽድቋል፡፡

የዚህ ስምምነት አላማ በቅኝ ግዛት ወቅት

በቅኝ ገዥዎች፣ በግለሰቦች፣ በአገርም

ሆነ በውጭ ቡድኖች አማካኝነት በዘፈቀደ

የተከለሉ ድንበሮች የሚያመጡትን ችግር

ለመቅረፍ የአፍሪካ አገራት ነጻ ሲወጡ

የያዙትን ወሰን ይዘው እንዲቀጥሉ

ማድረግ ነው፡፡ ሌሎች አገራትም

የጎረቤቶቻቸውንም ሆነ የሌሎች ነጻ

ሲወጡ የነበራቸውን ድንበር ማክበር

እንዳለባቸው የሚያሳይ ነው፡፡ ይህ ህግ

እ.ኤ.አ በ1963 በጸደቀው የአፍሪካ ህብረት

ቻርተር ላይም በግልጽ ተቀምጧል፡

፡ የ1963 ቻርተር እንዲሁም በሀምሌ

1964 የተፈረመው ስምምነት “to respect

the frontiers existing on their

achievement of independence”

ወይንም አገራት ነጻ ሲወጡ የነበራቸውን

ወሰን/ድንበር የማክበር ግዴታን አጽንኦት

ሰጥቶ አስቀምጧል፡፡ ይህ ችግር አሁንም

ድረስ ባለመቀረፉ የአሁኑ አዲሱ

የአፍሪካ ህብረት ቻርተርም በአንቀጽ

4(b) ‹‹respect of borders existing

on achievement of independence››

ወይንም አገራት ነጻነት ሲያገኙ

የነበራቸውን ድንበር ማክበርን የሚለውን

መርህ በቀዳሚነት አስቀምጦታል፡፡

የአፍሪካ ህብረት ሚኒስትሮች እ.ኤ.አ

በየካቲት 25 2010 አዲስ አበባ ላይ

‹‹DECLARATION ON THE AF-

RICAN UNION BORDER PRO-

GRAMME AND THE MODALI-

TIES FOR THE PURSUIT AND

ACCELERATION OF ITS IMPLE-

MENTATION›› የሚል ሰነድ በህብረቱ

ስም ተፈራርመዋል፡፡ ሰነዱ ግጭትን

ለመከላከል፣ ህብረትን ለማጠናከር ያለመ

ነው፡፡ ይህ ስምምነት መሰረቱ ያደረገው

‹‹አገራት ነጻ ሲወጡ የያዙትን ድንበር

ይዘው መቀጠል፣ የሌሎቹንም ማክበር

ይኖርባቸዋል›› ከሚለው የካይሮው

ስምምነትን የመነጨ ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት ለሱዳን ይሰጣል የተባለው

መሬትን ስምምነት እ.ኤ.አ በ1902 እና

በ1907 እንደተደረገ ታሪክ ያስረዳል፡

፡ ሆኖም መንግስታቱ መካከል ይህ

በእውን ሳይተገበር መቅረት ብቻ ሳይሆን

ሻለቃ ጉይን የተባለው የእንግሊዝ አዛዥ

መንግስታቱ ከተስማሙበትም ውጭ

ብቻውን ያሰመረው መሆኑ ይታወቃል፡

፡ ያም ሆኖ ሱዳን ነጻ ስትወጣ የያዘችው

ድንበር የዚህን የሻለቃ ድንበር አይደለም፡

፡ የአፍሪካ አንድነት ቻርተር፣ የካይሮ

ስምምነት፣ የአፍሪካ ህብረት ቻርተርና

እዚህን መርሆች መሰረት አድርገው

በየጊዜው በድንበር ጉዳይ የሚወጡ ህጎች

እያሉ በአሁኑ ወቅት እነዚህን ህጎች

በሚጻረር መልኩ ሱዳን ነጻ ስትወጣ

ከነበራት ድንበር ወደ ኢትዮጵያ እስከ

40 ኪሎ ሜትር የሚገባ መሬት ሊሰጣት

መሆኑ ይፋ ሆኗል፡፡

የካይሮን ስምምነት፣ የአፍሪካ ህብረት

ቻርተርና ሌሎችንም ከሁለቱ የሚመነጩ

የድንበር ህጎች በሚጻረር መልኩ

የሚተገበር ተግባር ይበልጡን አስገራሚ

የአንድ መንግስት ዋነኛው ተግባር አገር ውስጥ ህዝብን የሚያስተዳድርበትን፣ አገሪቱ ከውጭ

አካላት ጋር የምትገናኝበትንና ጥቅሟን የምታስከብርበት ህግና አግባብ የአገሪቱን ጥቅም

በሚያስከብር መንገድ መቅረጽ፣ ማስከበርና መተግብር ነው፡፡ ዓለም አቀፍ ህግ ከእዚህ መካከል

አንዱ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከፈረመቻቸው ዓለም አቀፍ የድንበር ስምምነቶች መካከል ደግሞ

አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገራት ነጻ ከወጡ በኋላ የተፈራረሙት ‹‹የካይሮ ስምምነት›› በአብነት

ይጠቀሳል፡፡

የሚሆነው ሌሎቹ ቅኝ ግዛት ስር

በነበሩበት ወቅት የራሷ ወሰን የነበራት

የህብረቱ መስራችና መቀመጫ ኢትዮጵያ

ላይ መሆኑ ነው፡፡ ህግጋቱን ጥሶ

የአገሪቱን መሬት ከድሮው እንደለመደው

መሬትን ብቻ ሳይሆን ‹‹ሉዓላዊነትን››

ለሌሎች በገጸ በረከትነት የሚያስረክበው

ደግሞ ኢትዮጵያን እወክላለሁ በሚለው

‹‹መንግስት›› መሆኑ ኢህአዴግ

ከሉዓላዊነት ጋር ምን ያህል እንደተጣላ

የሚያሳይ ነው፡፡

ሱዳኖችን ጨምሮ መሬቱ ለሱዳን

መሰጠት እንዳለበት ለሚያምነው

ኢህአዴግ ዋነኛው መከራከሪያ

ብሪታኒያና አጼ ምኒልክ በድንበሩ ጉዳይ

ቢዋዋሉም መሬቱ በኢትዮጵያ ቁጥጥር

ስር መቆየቱን ነው የሚያነሱት፡፡ በጉዳዩ

ጥናት ካደረጉት አምስት ኢትዮጵያውያን

መካከል በህይወት የሚገኙት ፕ/ር

መስፍን ወ/ማሪያም ጥር 17/ 2006

ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ ተገኝተው

እንዳስረዱት፤ አሁን በኢትዮጵያና ሱዳን

መካከል አጨቃጫቂ ነው የሚባለውን

ድንበር የከለለው ሻለቃ ጉይን የተባለው

የእንግሊዝ አዛዥ ብቻውን ሆኖ ነበር፡፡

በወቅቱ ኢትዮጵያ ወኪል አልነበራትምና

ስምምነቱ አይገዛትም ማለት ነው፡

፡ ሻለቃው እንዳፈተተው በሚከልልበት

ወቅትም ቢሆን የድንበር ለውጥ

በመደረጉ ድንበሩ ወደ ሱዳን ገባ

ብሎ እንደሚከለል ደብዳቤ ደርሶታል፡

፡ ሆኖም ሻለቃው ከብሪታኒያ ክልል

ካለችው ውጭ ወደ ኢትዮጵያ መሬት

ገብቶ የራሱን ዘፈቀደ ድንበር አስቀምጦ

አልፏል፡፡ ይህ ሆኖ እያለ ኢትዮጵያን

ወክያለሁ የሚለው ኢህአዴግ በዚህ

በተዛባ ህግ፣ አንድ የቅኝ ገዥ መኮነን

ያሰመረውን የተሳሳተና ያልተገባ ድንበር

የሚቀበል ከሆነ ምን አልባትም ለራሱ

ጥቅም ሲል ብቻ ተጠቀመበት እንጂ

ለስልጣን የማይጠቅመው ቢሆን የአባይን

ስምምነትንም መቀበሉ የማይቀር

እንደነበር ነው የሚያሳየው፡፡

አሁን ለሱዳን ይሰጣል የተባለው መሬት

የኢትዮጵያ አካል በነበረበት ወቅት

ሱዳን ገና ነጻ አልወጣችም፡፡ በመሆኑም

ከአፍሪካ አንድነት ቻርተር ጀምሮ፣

በካይሮ ስምምነት፣ በአዲሱ የአፍሪካ

ህብረት ቻርተርና በየጊዜው ድንበርን

በተመለከተ በሚወጡት ህጎች መሰረት

ድንበሩ የኢትዮጵያ እንጂ የሱዳን ሊሆን

አይችልም፡፡ ከመቶ አመት በፊት በአንድ

የቅኝ ገዥ መኮነን የተደረገን የመከለል

ሙከራ እውነት አድርጎ ለሌላኛው አገር

አሳልፎ መስጠት ከአንድ አገር መንግስት

የሚጠበቅ አይደለም፡፡ ኢህአዴግ

ኢትዮጵያ ውስጥ ስልጣን የያዘበት

ጊዜ ዓለም ከጦርነት ይልቅ ወደ ሰላም

የመጣችበትና በህግ የምትመራበት ነው፡

፡ በዚህ ዘመን የአንድ አገርን ሉዓላዊነት

ለማስጠበቅ ፈተናዎች የማይበዙበት

ዘመን ነው፡፡ ከዚህ ይልቅ በርካታ

የኢትዮጵያ መንግስታት የአገሪቱን

ሉዓላዊነት የሚፈታተኑ አጋጣሚዎችን

በጽናት አልፈዋል፡፡

ኢህአዴግ በጣሊያን ወረራም ሆነ በሌሎች

የአገሪቱ ሉዓላዊነት ጥያቄ ውስጥ

በገባበት ወቅት ገዥ ቢሆን ኖሮ ራሱ

ምንዳ እስካገኘ ድረስ ሙሉ በሙሉም

ይሁን የውጭ ሀይሎች በሚፈልጉት

መልኩ አገሪቱን አሳልፎ ይሰጥ እንደነበር

ለመገመት አይከብድም፡፡ በእርግጥ

አሁንም ቢሆን ሉዓላዊነትን አሳልፎ

መስጠቱ ለሱዳን በሚሰጠው መሬት

ይቆማል ተብሎ የሚገመት አይደለም፡

፡ ፕ/ር መስፍን ውይይቱን በመሩበት

ወቅት ለህዝብ መልሰው የጠየቁት

ጥያቄም ‹‹ኢህአዴግ በቀጣይነት አሳልፎ

የሚሰጠው የትኛውን መሬት ይሆን?››

የሚል ነበር፡፡ ከተሳታፊዎችም ‹‹አዲስ

አበባንስ መቼ ያስከልሏት ይሆን?››

የሚል ጥያቄ ተነስቷል፡፡ ይህ እንግዲህ

ኢህአዴግ ምን ያህል ለሉዓላዊነት

የማይጨነቅ መሆኑና በጉዳዩ ታማኝነቱን

ማጣቱን በግልጽ የሚያሳይ ሀቅ ነው፡፡