ምንጭ - Ethiopia: A voice for the voiceless
ምንጭ - Ethiopia: A voice for the voiceless
ምንጭ - Ethiopia: A voice for the voiceless
Create successful ePaper yourself
Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.
2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.15

ፖለቲካ

ግርማ ሞገስ

(girmamoges1@gmail.com)

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ ጥቅምት 28 ቀን 2004 ዓ.ም.

የዚህ ጽሑፍ ግብ የሰላም ትግል

ለውጥ ማምጫ መንገዶች (Mechanisms

of change) በኢትዮጵያ እንዴት ህዝብን

የመንግስት ስልጣን ባለቤት ሊያደርጉ

እንደሚችሉ በማጥናት በኢትዮጵያ የፖለቲካ

ትግል እና የመንግስት ሽግግር ለማድረግ

ሰላማዊ ትግል ማደረግ እንደሚቻል እና

ተመራጩ የትግል ስልትም እሱ መሆኑን

ማሳየት ነው።

የሰላም ትግላችን ግብ ህዝብን የመንግስት

ስልጣን ባለቤት ማድረግ ነው። ህዝብን

የመንግስት ስልጣን ባለቤት ለማድረግ የሰላም

ትግል በህዝብ እና በአምባገነን መንግስት

መካከል የሚገኘውን የፖለቲካ ኃይል ሚዛን

ግንኙነት ወደ ህዝብ እንዲያደላ ማድረግ

አለበት። የሰላም ትግል ይኽን አስፈላጊ

የሆነ የፖለቲካ ኃይል ሚዛን ግንኙነት

ሽግሽግ (ለውጥ) ተፈጻሚ የሚያደርገው

በአራት መንገዶች እንደሆነ ጅን ሻርፕ

(Gene Sharp) አጥንቶ ለአለም የዲሞክራሲ

ኃይሎች እና ተመራማሪዎች ካበረከተ

ውሎ አድሯል። እነሱም፥ (1ኛ) የመቀየር/

የመለወጥ (Peaceful conversion)፣ (2ኛ)

የመቻቻል (accommodation)፣ (3ኛ)

ሰላማዊ አስገዳጅነት (Peaceful coercion)

እና (4ኛ) ሰላማዊ መፈረካከስ/መበታተን

(Peaceful disintegration) የተባሉት

ናቸው። እነዚህ ሰላማዊ ለውጥ ማምጫ

መንገዶች ከሰላም ትግል መሳሪያዎች ጋር

ዝምድና አላቸው። የሰላም ትግል መሳሪያዎች

ሶስቱ አብይ ክፍሎች (1ኛ) ተቃውሞ እና

ማግባባት (Protest and Persuasion)

እስከዚኽ ድረስ እንዳየነው መቀየር/መለወጥ (Peaceful

conversion) የተባለውን የለውጥ ማምጫ መንገድ ፕላን ቀይሰን

በአግባብ እና በቀጣይነት ከተጠቀምንበት የዲሞክራሲ ትግልን በህብረተሰቡ ውስጥ

ለማስፋፋት እና የህብረተሰቡን የሰላማዊ ትግል አቅምን ለመገንባት ይጠቅማል።

ነገር ግን ይኽ ለውጥ የማምጫ ሰላማዊ መንገድ በአምባገነኖች የፖለቲካ ኃይል

ምንጮች ላይ የሚያደርሰው ቀጥተኛ ጥቃት የለም። ጥቃቱ ተዘዋዋሪ ነው። ለጥቀን

መቻቻል የተባለውን ለውጥ ማምጫ መንገድ እንመልከት።

የሠላም ትግል ለውጥ ማምጫ አማራጭ

መንገዶች በኢትዮጵያ

፣ (2ኛ) ትብብር መንፈግ (noncooperation)

፣ (3ኛ) ጣልቃ መግባት

(intervention) እንደሆኑ እና ዝርዝራቸው

ወደ 200 ግድም እንደሚደርስ በፍኖተ ነፃነት

ቁጥር 13 “የሰላም ትግል መሳሪያዎች” በሚል

ርዕስ ቀርቧል። እነዚኽ አራት ለውጥ ማምጫ

መንገዶች ከሰላማዊ ትግል አቅም ግንባታ

አንስቶ እስከ መንግስት ሽግግር ፍጻሜ ድረስ

እንዴት አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ ባጭር

ባጭሩ እንመልከት።

(1ኛ) መቀየር/መለወጥ (Peaceful

conversion)

የዲሞክራሲ ኃይሎች ያቀረቡትን የለውጥ

አሳብ ወይንም የለውጥ ጥያቄ መንግስት

ቢቀበል እሱም ተጠቃሚ ሊሆን እንደሚችል

መንግስትን ማሳመን (መቀየር/መለወጥ)

የሚቻልበት ሁኔታዎች (መንገዶች) ሊኖሩ

ይችላሉ። ይኽን በማድረግ የዲሞክራሲ

ኃይሎች ከሚያገኙዋቸው ፋይዳዎች ውስጥ

ጥቂቱ፥ በህዝብ እና በመንግስት ዘንድ

የተቃዋሚ መሪዎችን ህጋዊነት ከፍ ማድረግ፣

ከመንግስት ጋር ሊደረጉ የሚችሉ ግጭቶችን

መቀነስ፣ የሰላማዊ ትግልን የሰው እና የቁሳቁስ

አቅም በረባ ባልረባው ሁሉ እንዳይባክን

ማድረግ ናቸው።

ርግጥ ይኽ መንገድ በመንግስት ላይ

የሚያሳድረው ጫና (ክብደት) በጣም

ዝቅተኛ በመሆኑ የሚያስገኘው ጠቀሜታ

እዚህ ግባ የማይባል ሊሆን ይችላል።

ያም ሆኖ ግን የተመረጠው የለውጥ ጥያቄ

የአምባገነኖችን ስልጣን አደጋ ላይ የማይጥል

እና የጥያቄው አቀራረብ ብልህ እስከሆነ

ድረስ አልፎ አልፎም ቢሆን ጠቃሚ

ውጤት አይገኝም ማለት ያስቸግራል።

ለውጥ የተገኘበት ጊዜ አለ። ምሳሌ፥ እንደ

አውሮፓ አቆጣጠር በ1962 ዓመተ ምህረት

ቀድሞ የእንግሊዝ ቅኝ አገር በነበረችው

በርማ ውስጥ በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን

ላይ የወጣው ወታደራዊ አምባገነን ቡድን

መጀመሪያ ከያዘው አቅዋም ከጊዜ በኋላ

እንዴት እንደተለወጠ እንመልከት።

ስልጣን እንደጨበጠ፣ የእንግሊዘኛ

ቋንቋ ትምህርት በአንደኛ ደረጃ እንዳይሰጥ

አደረገ። በዩንቨርስቲ ደረጃም የሚሰጥ

የእንግሊዘኛ ቋንቋ ዝቅ እንዲል አደረገ።

ወታደራዊው መንግስት ለህዝብ የሰጠው

ሃሰተኛ ምክንያት “እንግሊዘኛ ቋንቋ የቅኝ

ግዛት ዘመን ውርደታችን ማስታወሻ በመሆኑ

መወገድ አለበት” የሚል ሲሆን ሃቀኛው

ምክንያት ግን በመምህርነት ስራ የተሰማሩትን

እና ኗሪ እንግሊዞችን ከአገር በማስወጣት

የበርማን ህዝብ ከውጪው አለም ፖለቲካ

ተጽእኖ ለማፈን (Censorship) ነበር። ይኽ

ፖሊሲ የበርማ ተማሪዎችም ወደ ምዕራቡ

አለም እንደቀድሞው እንደልብ እየወጡ

ከፍተኛ ትምህርት ለመማር በቅድሚያ

ማለፍ ያለባቸውን የእንግሊዘኛ ቋንቋ ፈተና

ማለፍ እንዳይችሉ ማድረግ ጀመረ። በበርማ

እንግሊዘኛ ቋንቋ መናገር የሚችሉ ተወላጅ

የቢሮ አስተዳዳሪዎች ማግኘት አስቸጋሪ

መሆን በመጀመሩ የውጭ አገር ኢንቨስተሮች

ወደ በርማ መምጣት አቆሙ። የአገሪቱ

ኢኮኖሚ ተንኮታኮተ። በዚኽ አይነት

ለስልጣኑ መጠናከር ሲል ለ20 አመቶች

ያህል አለም አቀፍ የቢዝነስ እና የንግድ

ቋንቋ በበርማ እንዲዳከም ካደረገ በኋላ ይኽ

ፖሊሲ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ያስከተለው

አሉታዊ ተጽእኖ ለአምባገነኖቹ ገዢዎች

ወለል ብሎ ይታያቸው ጀመረ። የበርማ

የንግዱ ማህበረሰብ እና የዲሞክራሲ ኃይሎች

በእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርት ላይ የተጣለው

ገደብ እንዲነሳ ያቀርቡት የነበረውን የለውጥ

ጥያቄ የበርማ አምባገነን መንግስት ተቀበለ።

አምባገነኑ የበርማ መንግስት የለውጡን

ጥያቄ የተቀበለው ለውጥ ቢያደርግ ተጠቃሚ

መሆኑን በመገንዘቡ ነበር።

የሰላም ትግል የመንግስት ባለስልጣኖችን

ብቻ ሳይሆን ህዝብንም በመቀየር/በመለወጥ

ለዲሞክራሲ ትግል መስፋፋት እና አቅም

ግንባታ ጥቅም ይሰጣል። መንግስት በህዝብ

ላይ የሚፈጽማቸው በደሎች፣ ዲሞክራሲ

የሚሰጠው ጠቀሜታ እና ዛሬ በአለም ውስጥ

እየተደረገ ስላለው የለውጥ እንቅስቃሴ

እና ስለመሳሰሉት በሰፊው ማሰራጨት

ህዝብ ለመለውጥ ያግዛል። በአለም ውስጥ

ስለሚሆነው እና በአገር ስለሚፈጸም ሰላማዊ

ሰልፎች፣ ተቃውሞዎች፣ ህዝባዊ ውይይቶች

እና ተመሳሳይ የሰላማዊ ትግል ዜናዎች

የህዝብን ዝንባሌ እንደሚቀይሩ እና ከፍራቻ

ነፃ ለመውጣት እንደሚያግዙ መረሳት

የለበትም። በዚህ ረገድ ድረ ገጾች፣ የህትምት

እና የኤሌክትሮኒክ ሚዲያዎች ከፍተኛ

ሚና አላቸው። ለዚህም ነው አምባገነኖች

የሚያፍኗቸው።

አምባገነኖች በሰላም ትግል ታጋዮች ላይ

የሚፈጽሙት ግፍ እና የሰላም ትግል ታጋዮች

የሚያሳዩት ጀግንነት ህዝብን በመለወጥ

የዲሞክራሲ ትግሉን ያጠናክራል። በዚህ

ረገድ በህዝብ ዘንድ ጀግንነት ተደርገው

የሚወሰዱ ርምጃዎች ሌላውን የመለወጥ

አቅም እንዳላቸውም መረሳት የለበትም።

ምሳሌ፥ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር

በ1950 ዎቹ እና 1960ዎቹ አፍሪካ

አሜሪካውያን መንግስት በሚለቅባቸው

ተናካሽ ውሻዎች መነከሳቸው፣ በእሳት አደጋ

መኪናዎች በሚረጭ ውሃ መደብደባቸው፣

ማታ ማታ በሰላም ትግል መሪዎች ቤቶች

ላይ ይደርስ የነበረው ቃጠሎ፣ የሰላም

ትግል ሰራዊት በሚሰበሰብባቸው ቤተ

ክርስቲያኖች ላይ ይደርስ የነበረው ፈንጂ እና

ቃጠሎ ሳይገታቸው በጀግንነት ለእኩለንት

ያደረጉዋቸው ትግሎች ህዝባቸው ብቻ

ሳይሆን ነጭ አሜሪካውያንን እና የቀረውን

አለም ህዝብ በመለወጥ ከአፍሪካውያን

አሜሪካውያን ጎን እንዲቆም አድርጓል።

ሌላ ምሳሌ፥ ግብጾች መንግስት ሳያስፈቅዱ

በነፃነት አደባባይ መስፈራቸው እና

ነፃነታቸውን ማወጃቸው ብዙ ግብጻውያንን

እንደለወጠ እና ሰላማዊ ትግሉን እንዲቀላቀሉ

እንዳደረገ የምናውቀው ትኩስ ዜና ነው።

እንዲሁም በድስፕሊን የታነጸ የሰላም

ትግል ሰራዊት በአምባገነኖች እየተዋከበ፣

ሳያስር እየታሰረ እና እየተገደለ፤ በጀግንነት

ሰላማዊ ትግሉን በቀጣይነት ሲያኪያሂድ

ሲያዩ የጨቋኙ መንግስት አባላት (የጦር

መኮንኖች፣ ሚንስትሮች፣ ዲፕሎማቶች፣

ወ.ዘ.ተ.) እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት፣

የምዕራቡ አለም መሪዎች፣ የመብት ተሟጋች

ድርጅቶች ወ.ዘ.ተ. ሳይቀሩ እየተለወጡ

ሰላማዊ ትግሉን ይቀላቀላሉ። ለምሳሌ

የሊቢያው ጋዳፊ በሰላማዊ መንገድ አደባባይ

ወጥቶ ነፃነቱን በጠየቀ ህዝብ ላይ አረመኒያዊ

ጦርነት ሲያውጅ በጋዳፊ መንግስት ውስጥ

በአገር ውስጥ የነበሩ ባለስልጣኖች እና

ዲፕሎማቶች ሰላማዊ ትግሉን ተቀላቅለዋል።

በየመንም አምባገነኑ የሳላህ መንግስት በሰንዓ

(ለውጥ አደባባይ) እና በታኤዝ ከተሞች

በሰፈረው ሰላማዊ ታጋይ ላይ ግድያ በፈጸመ

ቁጥር ተመሳሳይ ሁኔታዎች ተፈጥረዋል።

እስከዚኽ ድረስ እንዳየነው መቀየር/

መለወጥ (Peaceful conversion)

የተባለውን የለውጥ ማምጫ መንገድ

ፕላን ቀይሰን በአግባብ እና በቀጣይነት

ከተጠቀምንበት የዲሞክራሲ ትግልን

በህብረተሰቡ ውስጥ ለማስፋፋት እና

የህብረተሰቡን የሰላማዊ ትግል አቅምን

ለመገንባት ይጠቅማል። ነገር ግን ይኽ ለውጥ

የማምጫ ሰላማዊ መንገድ በአምባገነኖች

የፖለቲካ ኃይል ምንጮች ላይ የሚያደርሰው

ቀጥተኛ ጥቃት የለም። ጥቃቱ ተዘዋዋሪ

ነው። ለጥቀን መቻቻል የተባለውን ለውጥ

ማምጫ መንገድ እንመልከት።

(2ኛ) መቻቻል (Peaceful

accommodation)

አንዳንድ ጊዜ አምባገነናዊ መንግስቶች

በዜጎች ዘንድ ላገር አሳቢ መስሎ ለመታየት፣

በውጭ መንግስታት ዘንድ ተቀባይነት

ለማግኘት ወይንም የገጠማቸውን የለውጥ

ጥያቄ ውጥረት ለማርገብ ሲሉ የዲሞክራሲ

ኃይሎችን ጥያቄዎች ይቀበላሉ። ይኽን

የሚያደርጉት መብት አክባሪ እና ትሁት

በመሆናቸው ሳይሆን ለተቃዋሚዎች የለውጥ

ጥያቄ የመቻቻል መፍትሄ ብንሰጥ ስልጣናችን

አይነጠቅም፣ አቅማችንም አይዳከምም ነገር

ግን ከጭቅጭቅ እንድናለን ከሚል እምነት

ነው። ይሁን እንጂ አንድ አምባገነን መንግስት

መቻቻልን እንደመፍትሄ ከወሰደ በስልጣን

ላይ የነበረው ፍጹም የሆነ ቁጥጥር ተቀንሷል

ማለት ነው። በህዝብ እና በአምባገነኖች

መካከል በነበረው የኃይል ሚዛን ግንኙነት

ላይ የተወሰነ ሽግሽግ ተደርጓል ማለት ነው።

ለምሳሌ የስራ ማቆም አድማዎችም ቆመው

ሰራተኞች ወደ ስራ የሚመለሱት በአሰሪና

በሰራተኞች መካከል በሚደረግ መቻቻል

ነው።

5

በአገሮች መካከልም መቻቻል ይደረጋል።

የቻይና መንግስት ጥቂት የፖለቲካ እስረኛ

በመፍታት በምዕራቡ አለም የሚቀርብበትን

የሰብዓዊ መብት ማሻሻል ጥያቄ ለማርገብ

ሲሞክር እናያለን። ምዕራቡም ለጊዜው ዝም

ይላል። በምዕራቡ እና በቻይና መንግስት

መካከል መቻቻል ተደረገ ማለት ነው።

የቻይና መንግስት ይኽን የሚያደርገው

በምዕራቡ አለም ተገዶ (Coerced ሆኖ)

ሳይሆን የቀረበው የመብት ጥያቄ ከምዕራቡ

አለም ጋር ካለው የንግድ እና ሌሎች ጉዳዮች

ጋር እየተወሳሰበ እንደልብ አላራምድ

ስለሚለው ነው። ስለዚኽ ለምዕራቡ ጥያቄ

የመቻቻል ምላሽ በመስጠት ንግዱን እና

ሌሎች የሚጠቅሙትን ነገሮች ያደርጋል።

ምርጫም መቻቻል ነው። በየአምስት

ወይንም አራት አመቶች የሚደረግ ምርጫ

ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለሚያቀርቡት የፖለቲካ

ለውጥ ጥያቄ አምባገነን መንግስቶች

የሚሰጡት የመቻቻል መልስ ነው። ይሁን

እንጂ ከተመክሮ ማነስ የተነሳ የተቃዋሚ

ፓርቲ መሪዎች ምርጫው ነፃ እና ፍትሃዊ

ይሆናል፣ ከምርጫው ጋር በተያያዘ

መንግስት የሚፈጽመውን ወከባ ህዝቡ

መቋቋም ይችላል ወይንም አለም አቀፍ

ታዛቢዎች የምርጫውን ድምጽ ቆጠራ

እንዳይሰረቅ ያደርጋሉ ብለው ይገምታሉ።

ይኽ የዋህነት ነው። አምባገነኖች ነጻ ምርጫ

ተደርጎ ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው ይለቃሉ

ብሎ መገመት ስህተት ነው። ሳይገደዱ

በፈቃደኛነት ስልጣን ማስረከብ የአምባገነኖች

ጸባይ አይደለም። አምባገነኖች ዲሞክራቶች

አይደሉም። አምባገነኖች ስልጣን ላይ

የሚወጡት በግድያ እና በሽብር ነው።

በስልጣን ለመቆየትም መንግስታዊ ሽብር

ይፈጽማሉ። ምርጫም ከሆነ የሚያግዳቸው

ኃይል ከሌለ ድምጽ ይሰርቃሉ። እንደ

አውሮፓ አቆጣጠር በ2000 ዓመተ ምህረት

በሰርቢያ እና በ2002 ዓመተ ምህረት

በዝንባቡዌ የተደረጉት ምርጫዎች በንፅፅር

ማየት ይጠቅማል። ሁለቱም ምርጫዎች

በስልጣን ላይ በነበሩት አምባገነኖች

ተሰርቀው ነበር። ይሁን እንጂ በሰርቢያ

የህዝብን ድምጽ ማስከበር ሲቻል በዝንባቡዌ

ግን ያን ማድረግ ሳይቻል ቀርቷል። ስለዚኽ

የሁለቱ ምርጫዎች የመጨረሻ ውጤት

ሊለያይ ቻለ። እንመልከት።

በሰርቢያ ተቃዋሚው በመላ አገሪቱ

የምርጫ ታዛቢዎች አሰልጥኖ አሰማራ።

ህዝቡ ንቅል ብሎ ወጥቶ ድምጹን እንዲሰጥ

የሚያነሳሳ እና የሚቀሰቅስ የሰላማዊ የምርጫ

ሰራዊት አሰልጥኖ በመላ አገሪቱ አዘመተ።

መንግስት ድምጽ ቢሰርቅስ ብሎ ቀደም ብሎ

በማሰብ ተቃዋሚው ድምጽ “ለማስከበር

ፕላን ለ” (Plan B) አዘጋጅቶ ነበር። አንድ

መንግስት የህዝብ ድምጽ አላከብርም ካለ

ህዝቡም በበኩሉ ለመንግስት የለገሰውን

የገዢነት ክብር እና ህጋዊነት የመንፈግ መብት

አለው። ስለዚኽ “ፕላን ለ” (Plan B) ድምጽ

ለማስከበር የሚደረግ የፖለቲካ እምቢታ፣

ትብብር የመንፈግ እና የጣልቃ መግባት

የሰላም ትግል መሳሪያዎችን የሚጠቀም

ሰላማዊ ትግል ነው። በየምርጫ ጣቢያው

የተመደቡ የተቃዋሚ ታዛቢዎች በድምጽ

ቆጠራው ላይ በመሳተፍ ቆጠራው እንዳለቀ

በዚያው ምሽት ውጤት በየጣቢያው ይፋ

እንዲሆን አደረጉ። በመጨረሻ በሞሊሶቪች

ይመራ የነበረው አምባገናንዊ መንግስት

የምርጫው ውጤት እንደፈለገው ሳይሆን

በመቅረቱ አይኑን በጨው አጥቦ አሸንፌያለሁ

ቢልም በምርጫው እለት ምሽት በየምርጫ

ጣቢያው ድምጽ ይፋ ተደርጎ ስለነበር ህዝቡ

“ድምጽ ይከበር” አለው። ተቃዋሚው ቀደም

ብሎ ያዘጋጀውን በሚሊዮኖች የሚቆጠር

ወደ 13 ይዞሯል

www.andinet.org.et