24.07.2013 Views

ምንጭ - Ethiopia: A voice for the voiceless

ምንጭ - Ethiopia: A voice for the voiceless

ምንጭ - Ethiopia: A voice for the voiceless

SHOW MORE
SHOW LESS

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.15

በተስፋዬ ደጉ

ወቅታዊ

ሐሙስ ጥቅምት 2 ቀን 2004 ዓ.ም ከጠዋቱ አራት

ሰዓት ላይ በመድረክ ጽ/ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ

እየተሰጠ ነው፡፡ በስድስት የተቃዋሚ የፖለቲካ

ፓርቲዎች የተመሰረተው መድረክ፣ ከቅንጅትነት

ወደ ግንባርነት መሸጋገሩን ለማብሰር፡፡ የየፓርቲዎቹ

አመራሮች ጋዜጣዊ መግለጫውን ለመስጠት

መድረኩን ይዘዋል፡፡ የአገር ውስጥም የውጭ አገርም

በርካታ ጋዜጠኞች ሁኔታውን ለመዘገብ በቦታው

ተገኝተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም ካሜራዎቹን

ደቅኖ ከአንድ ሰዓት በላይ የተካሄደውን ጋዜጣዊ

መግለጫ እየቀረፀው ይታያል፡፡ መግለጫው ተነበበ፡

፡ መድረኩ ለጋዜጠኞች ክፍት ተደረገ፣ ለአመራሮቹ

ጥያቄ እንዲያቀርቡ፡፡

የመጀመሪያዎቹ ሦስት ጥያቄዎች ከጋዜጠኞቹ

ከተሰበሰቡ በኋላ፣ ለጥያቄዎቹ መልሶች መድረኩ ላይ

ያሉት ዶ/ር መረራ ጉዲና መልስ መስጠት ጀምረዋል፡

፡ ለመጀመሪያዎቹ ሁለት ጥያቄዎች በእርጋታ መልስ

ሰጡ፡፡ ሦስተኛውን ጥያቄ ሲመልሱ ግን የተቆጡ

መሰሉ፡፡ “እናንተ የኢሕአዴግ ካድሬዎች ግን

መቼ ነው ፕሮፓጋዳችሁን መንዛት የምታቆሙት?

መቼ ነው የምትተውን?” በማለት ጥያቄውን

ወደ ጠየቃቸው ጋዜጠኛ እንደዋዛ እየተመለከቱ

ጥያቄያቸውን ሰነዘሩ፡፡ ጋዜጠኛውም “ከኢሕአዴግ

ቢሮ አልመጣሁም፡፡ የሬዲዮ ፋና ጋዜጠኛ ነኝ፡

፡” ብሎ ጥያቄቸውን መለሰ፡፡ ዶ/ር መረራም

ሃሳባቸውን ቀጠሉ፡፡ “ጋዜጠኛ ብትሆኑማ ጥሩ ነበር፡

፡ የኢሕአዴግ ካድሬ እየሆናችሁ አስቸገራችሁን

እንጂ፡፡” የሚል ምላሽ ከፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት

ለመጣው ጋዜጠኛ ሰጡ፡፡

ከፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት የመጣው ጋዜጠኛ

የጠየቀው ጥያቄ ያጠነጠነው የመድረክ “ግንባርን”

የፈጠሩት ስድስቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያላቸውን

የአይዲዮሎጂ ልዩነትን የተመለከተ ነው፡፡ ጋዜጠኛው

ስድስቱ ፓርቲዎች ያላቸው ተቃራኒ ሊባል የሚችል

የአይድዮሎጂ ልዩነት “ግንባር” ለመፍጠር

እንደማያስችላቸው ጠቃቅሶ፣ በመካከላቸው ያለውን

የአይዲዮሎጂ ልዩነት የት እንዳደረሱት የሚሞግት

ዓይነት ነበር፡፡

ከመለስተኛዋ መመላለስ በኋላ ዶ/ር መረራ ጉዲና

ለተጠየቀው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በዚህም

ምላሻቸውም አገራችን ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት

ዘርፈ ብዙ ችግሮች፤ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓቱ

መገታቱ፣ የኢሕአዴግ አምባገነን ፓርቲ እየሆነ

መሄድ፣ የዜጐች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች

መታፈን፤ የገዢው ፓርቲ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና

የመገናኛ ብዙሃንን ሙሉ በሙሉ በራሱ ቁጥጥር

ሥር ማዋሉና አገራችን ያለችበት አጠቃላይ ቀውስ

በተሰባሰቡት ወቅት በተቃዋሚዎች መካከል

ያለውን የአዲዮሎጂ ልዩነትን በሁለተኛ ደረጃ ላይ

እንዳስቀመጠው ገልፀዋል፡፡ አክለውም መድረክ

በመለስተኛ ፕሮግራሙ ያስቀመጣቸው ነጥቦችም

የጋራ መታገያቸው መሆናቸውን ገልፀው፤ የመድረክ

ዓይነት ግንባር በመፍጠር በጋራ አገር መምራትም

በሰለጠኑት አገራትም ጭምር የተለመደ አካሄድ

መሆኑን የጀርመንና የእስራኤልን ተሞክሮን ዋቢ

አድርገው አብራርተዋል፡፡

ማታ በሁለት ሰዓቱ የአማርኛ ዜና ላይ የመድረክ

ከቅንጅት ወደ ግንባር መሸጋገሩን ከደቂቃዎች

በላይ ባልፈጀ ዜና የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተናገረ፡፡

ሬዲዮ ፋናም በድረ ገጹ ላይ ባንድ መስመር ዜናውን

አስፍሮት ተስተዋለ፡፡

የመገናኛ ብዙሃንና ነፃነት

በማንኛውም አገር ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን

ለመመስረት መገናኛ ብዙሃን የሚያበረክቱት

አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ መገናኛ

ብዙሃንም ሊያበረክቱት የሚችሉት አስተዋፅኦም

ባላቸው የነፃነት መጠን ላይ ተንጠልጥሎ ይገኛል፡

፡ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ስንልም የሃሣቦች ብዝሃነት

(plurality of ideas) ዋነኛው አምድ መሆኑን

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ ጥቅምት 28 ቀን 2004 ዓ.ም.

የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን በሕገ-መንግሥቱ እውቅና የተሰጣቸውን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትንና የተለያዩ አስተሳሰቦችን ማስተናገድ ግዴታ እንዳለባቸው ተደንግጓል፡

፡ ዴሞክራሲና መገናኛ ብዙሃን በጣም የተቆራኙ በመሆናቸው፤ አንዱን ከአንዱ ለይቶ ለማየት እስኪያስቸግር ድረስ ተደጋጋፊ ናቸው፡፡ የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ደግሞ

ከየትኛውም የአገራችን የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት በበለጠ፤ ለሕዝብ ዓይንና ጆሮ በመሆን ሕገ-መንግሥቱ በተለያዩ ምክንያቶች ሲጣስ ለሕዝብ የማሳወቅ ግዴታ አለባቸው፡፡

የሕዝብን ፍላጐት ግምት ውስጥ በማስገባት ምላሽ መሰጠት የሚችሉ ፕሮግራሞችን ማዘጋጀትም ሌላው ኃላፊነታቸው ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ላይ መጠነኛ የዳሰሳ

ጥናት ያደረገው ተስፋዬ ደጉ ይሄን ለማድረግ እስካሁ ያልቻሉት “ከገዢው ፓርቲ በኩል የሚሰነዘር ጫና” በመኖሩ መሆኑን ሊያሳየን ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሮልናል፡፡

ኢሕአዴግና መገናኛ ብዙሃን

ካሰብን ደግሞ ከኢ-ዴምራሲያዊ ጣልቃ ገብነትና

ተፅዕኖ ነፃ በሆነ መልኩ መደራጀታቸውና ስራቸውን

ማከናወናቸው፤ ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱን በአጭር

ጊዜ ለመመስረት የሚያስችል የማይተካ ሚና

እንዳላቸው መረዳት ይቻላል፡፡

መገናኛ ብዙሃን ላይ የተሰሩ በርካታ ጥናቶች

እንደሚያሳዩት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመመሥረት

በመንገድ ላይ ያሉት በርካታ የአፍሪካ አገሮች

ከመድበለ ፓርቲ ይልቅ ወደ አንድ ፓርቲ አገዛዝ

እየሄዱ መሆኑን ያሳያል፡፡ በየአገራቱ መንግሥት

የሚያስተዳድራቸው ብዙሃን መገናኛዎች በስልጣን

ላይ ያለውን ገዢ ቡድን እንጂ የተለየ ድምፅ

ለማሰማት በራቸውን ዘግተው ተቀምጠዋል፡

፡ በመሆኑም በእነዚህ አገራት የዴሞክራሲያዊ

ሥርዓት ግንባታ ሂደቱ ፈተና ላይ የወደቀው የአንድ

ፓርቲ አገዛዝ ሥርዓት በመመስረቱ ብቻ ሳይሆን

የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ከገዢው ፓርቲ ሃሳቦች

በስተቀር ለሌሎቹ ወይም ለተቃዋሚዎቹ ዕድል

አለመስጠታቸው ነው፡፡ ሲከፋም አሉታዊ ይዘት

ያላቸውን ዘገባዎችን ማቅረብና “የስም ማጥፋት”

ዘመቻዎችም ሲቀርብባቸው ይስተዋላል፡፡ እዚህ

ጋ የዜናዎቹ /የዘገባዎቹ ሚዛናዊነት፣ ትክክለኛነት

ወይም እውነተኛነት የመሳሰሉት የጋዜጠኝነት ስነ-

ምግባር የሚጠይቃቸው እሴቶች አስታዋሽ ያላቸው

አይመስሉም፡፡ እነዚህ ሆን ተብሎ የሚዘነጉ እሴቶች

ደግሞ ለሃሳብ ብዝሃነት (plurality of ideas)

ዋስትና፣ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ደግሞ

መሠረት ናቸው፡፡

ሮኒንግ ሄልግ “The Role of Media in Democracy”

በተባለው መጽሐፍ እንዳስረዱት መገናኛ

ብዙሃን ከመንግስት ወይም ከገዢ ፓርቲ ቀጥተኛ

ጣልቃ ገብነት ነፃ ሆነው መደራጀታቸው በጣም

አስፈላጊ የሚሆነው፤ መንግስት ስልጣኑን አላአግባብ

እንዳይጠቀም ለመከላከል መሆኑን ያስረዳሉ፡፡

ምናልባት የመንግሥትን ስልጣንን የያዙ ግለሰቦች

ስልጣናቸውን ለራሳቸው ግላዊ ጥቅም ቢያውሉት

የህዝብ ዓይንና ጆሮ ሆነው የሚያገለግሉት መገናኛ

ብዙሃን “ስህተቱን” ለሕዝብ ያሳውቃሉ፡፡ መረጃው

የደረሰው ሕዝብም፤ ያጠፉት ወኪሎቹን ማብራሪያ

ከመጠየቅ ጀምሮ ውክልናውን እስከማንሳት የደረሰ

እርምጃ ሊወሰድባቸው ይችላል፡፡ ይህ ሊሆን

የሚችለው ግን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በመሰረቱት

እንደ አሜሪካና በምዕራብ አውሮፓ ባሉ አገራት

ነው፡፡ በኢትዮጵያስ?

ሁለቱ ወንበሮች

ወንደስን አለሙ (ስሙ ለዚህ ፅሑፍ ተቀይሯል) እንደ

ፖለቲካል ሳይንስ ተማሪነቱ የገዢው ፓርቲን ሁለት

ወንበሮች ለመለየት እንደሚቸግረው ይናገራል፡፡

እንደ ፓርቲ ስለየትኛውም ፖለቲካዊ ጉዳዮች የራሱን

አቋም መያዝ መብቱ መሆኑን የሚቀበለው ቢሆንም፤

የፓርቲውን አቋም ህገ-መንግሥቱን በመጣስ ጭምር

በመንግሥታዊ ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ መግባቱን ግን

አምርሮ እንደሚቃወመው ይናገራል፡፡

የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ዶ/ር

ኃይሉ አርአያ “መድበለ ፓርቲ በኢትዮጵያ የወደፊት

ዕጣፋንታ” በሚለው ጥናታቸው ላይ እንደገለፁት

“ከምርጫ 2002 በኋላ ኢሕአዴግ አምባገነናዊ

አውራ ፓርቲ ሆኖ ወጥቷል፡፡ ወደዚህ የደረሰበት

መንገድም ከምርጫ 97 በኋላ በወስዳቸው

ኢ-ዴሞክራሲያዊ እርምጃዎች ነው፡፡” ይላሉ፡

፡ ዝርዝራቸውን ለመቁጠር ወደ ጣቶቻቸው

እየተመለከቱ፡፡ “የመጀመሪያው ነፃው ፕሬስን

ለማዳከም የወጣው የሚዲያ አዋጅ፣ ሲቪክ

ማህበራትን ተሳትፎ ለመቀነስ የወጣው አዋጅ፣

የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ደካማ ለማድረግ የወጣው

አዋጅና የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ” መሆናቸውን

ይገልፃሉ፡፡

ይሄው የዶ/ር ኃይሉ ተመሳሳይ ጥናት

እንደሚያስረዳው ኢሕአዴግ አውራ ፓርቲ ሆኖ

ለመውጣት የቻለው “ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን

በማፈንና ነፃና ፍትሃዊ ባልነበረ ምርጫ በ2002

በማሸነፉ” ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ኢሕአዴግ

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ “አምባገነናዊ አውራ

ፓርቲ” እንጂ፣ “አውራ ፓርቲ” እንዳልሆነ

ይደመድማሉ፡፡ ሃሳባቸውን በመቀጠልም

“አምባገነናዊ አውራ ፓርቲዎች ባሉበት አገራት

ገዢው ፓርቲንና መንግሥትን መለየት አለመቻል፣

ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ መሰረት

የሆኑ ነፃ የሚዲያ፣ የፍትህ፣ ሲቪክ ማኅበራትና

የምርጫ አስፈፃሚ አካላት አለመኖር፤ ዋና ዋናዎቹ

መገለጫዎቹ” መሆናቸውን አስታውሰው፤

የአገራችን ነባራዊ እውነታም ይሄንኑ እንደሚያሳይ

አስረድተዋል፡፡

የገዢው ፓርቲ ይፋዊ ህትመቶች እንደሚያትቱት

ደግሞ መንግሥት (ኢሕአዴግ ለማለት ነው) የግሉን

የመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ፤ “ሊቆጣጠረው” የሚገባው

የአሁኑ ታዳጊ ዴሞክራሲያችን “እንዳይቀለበስ”

ለመጠበቅ ነው፡፡ እነዚህ ይፋዊ ህትመቶችና አልፎ

አልፎም የፓርቲው ሹማምንት እንደሚያስረዱት

“ኢሕአዴግ የጀመረው የዴሞክራሲያዊ ስርዓት

ግንባታ ሊቀለበስ በማይችልበት ደረጃ ላይ

ገና አለመድረሱን ነው፡፡ ለዚህም ክርክራቸው

የሚያቀርቡት ማስረጃም በምርጫ 97 ጊዜ ነፃው

ፕሬስ ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጐን

“መሰለፉ” የሚያሳየው ሐቅ ቢኖር፣ “ነፃው ፕሬስ”

ከ “ኢ-ዴሞክራሲያዊ” ኃይሎች ጋር በማበር

“ዴሞክራሲውን” አደጋ ላይ የመጣል አቅም

እንዳለው ማሳየቱን የፓርቲው ህትመቶች ይገልፃሉ፡፡

የዶ/ር ኃይሉ ጥናት የሚያሳየው ግን በሚድያ ህጉ

እንደታየው የኢሕአዴግ ዓላማ ዴሞክራሲያዊ

ስርዓቱን ለማፈን እንጂ ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱን

ለመጠበቅ የተሰራ አለመሆኑን ነው፡፡ የምሁሩ ጥናት

እንዲማሳየው የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት በኢትዮጵያ

ለወደፊት የሚኖረውን ዕጣ ፈንታን በተነተኑበት

ፅሁፋቸው እንደደመደሙት ኢህአዴግ በሥልጣን

ላይ እስካለ ድረስ የመነመነ ነው፡፡ እኚህ የአንድነት

ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ከፍተኛ

አመራር እዚህ መደምደሚያ ላይ ያደረሳቸውን

ምክንያት ሲገልፁ ገዢው ፓርቲ ከምርጫ 97

ያልጠበቀው ሽንፈት ወዲህ ያፀደቃቸውን አፋኝ

አዋጆችን ነው፡፡ አዋጆቹም የመገናኛ ብዙሃን

አዋጅ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ማቋቋሚያ አዋጅ፣

የሲቪክ ማኅበራት አዋጅና የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ

መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡ የምሁሩ ጥናታዊ ፅሁፍ

እንደተነተነው እነዚህ አራት አዋጆች በአገራችን

የዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ለማጐልበት እንዲረዱ

በማሰብ ሳይሆን የፀደቁት፣ ይልቁንም ኢህአዴግ

አምባገነናዊ አውራ ፓርቲ ሆኖ እንዲቀጥል፣

ተቺዎቹንና ተቃዋሚዎቹን ከፖለቲካው ጨዋታ

ውጭ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ያሰምሩበታል፡፡

ዶ/ር ነጋሶና አንቀፅ 29

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የአንድነት ለዴሞክራሲና

ለፍትህ (አንድነት) ፓርቲ ሊቀመንበር ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ህገ-መንግሥት ከያዛቸው ከመቶ በላይ

አንቀፆች መካከል አንቀጥ 29ን የበለጠ የሚወዷት

ያስመስልባቸዋል፡፡ ፓርቲያቸውን ወክለው

በተገኙበት ቦታ ሁሉ፣ በጋዜጠኞች ቃለ-መጠይቅ

ሲደረግላቸው….. ሁልጊዜም አንቀጽ 29 ሳያነሷት

አያልፉም፡፡

ዶ/ር ነጋሶ “ሃሰብን በነፃነት የመግለጽ መብት ” የህገ-

መንግሥት አርቃቂ ኮሚሽን ውስጥ በነበሩበት ወቅት

የፀደቀ አንቀጽ ነው፡፡ሕገ-መንግስቱም በ1987 ዓ.ም

በርሳቸው የመጨረሻ ፊርማ ፀደቀ፡፡ ፕሬዚዳንት

ስለነበሩ፡፡ ትዝታቸውንና ተስፋቸውን ወደኋላ

ተመልሰው ሲያስታውሱ “ዜጐች የተቃውሞም

ይሁን የድጋፍ ሃሳባቸውን በነፃነት እንዲገልፁ

ዋስትና እንዲሆናቸውና፤ የመንግስት መገናኛ

7

ብዙሃንን ጭምር ተጠቅመው ለሕዝብ ማድረስ

ዕድል ይሰጣቸዋል” በሚል እንደነበር ይናገራሉ፡፡

ሕገ-መንግሥቱ ሥራ ላይ ከዋለ አስራ አምስትና

አስራ ስድስት ዓመታት በኋላና ከኢሕአዴግ የፓርቲ

አባልነት ራሳቸውን ካገለሉ አስር ዓመታት በኋላ

ግን፤ ተስፋቸው አይናቸው እያየ እንደጉም መትነኑን

ይናገራሉ፡፡ ገዢው ፓርቲ ወደለየለት አምባገነንነት

የገባው በዋናነት ከ1993 ወዲህ ሲሆን፣ በተለይ

ግን ከምርጫ 97 ወዲህ መሆኑን ያስምሩበታል፡፡

ለዚህ መከራከሪያም የሚያቀርቡት ማስረጃም ህገ-

መንግሥቱንና የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁን በማነፃፀር

ነው፡፡ “የህገ-መንግሥቱ አንቀጽ 29 ሃሳብን በነፃነት

መግለፅን የሚያበረታታ ሲሆን፣ የፀረ-ሽብርተኝነት

አዋጁ ግን ወንጀል የሚያደርግ ነው፡፡” ይላሉ፡

፡ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲዊ ሥርዓት ለመመሥረት

እነዚህ ሁለት ህጐች ሊያበረክቱት የሚችለውን

አስተዋፅኦ ሲያነፃፅሩት ደግሞ “አንቀጽ 29

የሚያበረታታና ገንቢ ነው፡፡ አዋጁ ግን የሚገታ ብቻ

ሳይሆን ዜጐች በፍርሃት እንዲኖሩ የሚያስገድድ

ነው፡፡” በማለት ተናገሩ ፡፡ “የሚያሳዝነው

ደግሞ አዋጁን እየጠቀሱ፤ አንቀጽ 29ን ሲጥሱ

መመልከታችን ነው፡፡ የአንዱዓለም አራጌና

የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋም እስር የዚህ ውጤት

ነው፡፡ ሁላችሁም በነበራችሁበት፣ በዚሁ መድረክ

ላይ ሁለቱም ያሉት በአዲሱ ዓመት በ2004 ዓ.ም

በአገራችን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመመሥረት

በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ለመታገል እንዘጋጅ

ነው፡፡ ይህ በህገ-መንግሥቱ የተረጋገጠ መብት

ነው፡፡ ወንጀል አይደለም፡፡ ወንጀል የሚደረገው

በኢሕአዴግ ነው፡፡” በእጃቸው መድረኩን እያሳዩ

ንግግራቸውን ጨረሱ፡፡

እንደምን አመሻችሁ ዲሽ የሌላችሁ

ከአራት ኪሎ ተነስተው ፒያሳ እንደገቡ ቀዝቀዝ

ያለ አየር በሚነፍስበት ጥግ ቀዝቀዝ ያለ ገበያ

ያላቸው ሁለት ሱቆች ይታያሉ። የመጀመሪያው

ሱቅ ስም አልባ ቢሆንም በመስታወቱ ወደ ውስጥ

ዘልቆ አተኩሮ ለተመለከተ የኤሌትሪክ ዕቃዎች

መሸጫ መሆኑን መለየት ይቻላል። ሁለተኛው ሱቅ

አጠገብ ያለው ደግሞ ለብዙ ዓመታት መስታወቱ

ላይ በለጠፈውና የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ድርጅት

ለሚሰጠው አገልግሎት ከደንበኞቹ ክፍያ መቀበያ

መሆኑን የሚገልፀው ማስታወቂያ ያለበት ቢሮ ነው።

ዛሬ ግን አዲስ የሚመስል ነጭ ባነር ላይ “የቴሌቪዥን

ባለቤትነት ማረጋገጫና የቴሌቪዥን አገልግሎት

ክፍያ መሰብሰቢያ” መሆኑን የሚገልፅ ፅሁፍ ሻተሩ

ላይ እንደነገሩ ተንጠልጥሎ ይታያል። በሩ ክፍት

ነው። ሰው ሲገባም ሆነ ሲወጣ አይታይም። ክፍሉ

ውስጥ የሚታየው ደብዘዝ ያለ ብርሃን ክፍሉን

ህይወት አልባና ፈዛዛ ድባብ አላብሶታል። ፒያሳ

ውስጥ ያለ አይመስልም።

በ1957 ዓ.ም የተመሠረተው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን

ዛሬም ድረስ ብቸኛውና በመንግስት ቁጥጥር

ስር ያለ ጣቢያ ነው። ኢሕአዴግ ወደ ስልጣን

እንደመጣ ነፃ ፕሬስ እንዲቋቋም ቢፈቅድም

የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያውን ግን ለግል ባለሃብቶች

እንደማይፈቅድ በተደጋጋሚ ሲገልፅ መሰንበቱ

ይታወሳል። ፓርቲው እዚህ አቋም ላይ የደረሰበትን

ምክንያት ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች በባህሪያቸው

ሰፋ ላለው የህብረተሰብ ክፍል በቀላሉ መድረስ

የሚችሉ በመሆናቸው እነሱን ተጠቅሞ የሚደረግ

“ቅስቀሳ” አገሪትዋን ወደ መተላለቅና ወደ መበታተን

ሊያደርሳት መቻሉን ነው። ነፃው ፕሬስስ ? እሱማ

በከተሞች አካባቢና በተማረው የህብረተሰብ

ክፍል ብቻ ተደራሽ በመሆኑ ያን የሚያህል

አቅም አይኖረውም ተብሎ በመታሰቡ ነው።

ይህ የተጠቀሰው የፓርቲው መሠረታዊ ፍልስፍና

ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የተቀየረው ከ1997ቱ

ምርጫ በኋላ ይመስላል።

ወደ 14 ይዞሯል

www.andinet.org.et

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!