10.08.2015 Views

8326/henocka2001@yahoo.com 226-8326/ 612-226

medina newspaper # 1 - Ethiopian Review

medina newspaper # 1 - Ethiopian Review

SHOW MORE
SHOW LESS
  • No tags were found...

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

Medina/መዲናNovember 2011 volume I No. 1 ጥቅምት 2004 1ኛ ዓመት ቁጥር 1ተሰባስበን በመጠጣት ላይ እያለን እንዳጋጣሚ አንዱጓደኛችን ቪያግራ ስለሚባለው የስንፈተ ወሲብ መድኃኒትአነሳን፡፡ እሱ እንደነገረን ግን የስንፈተ ወሲብ ሳይሆን ለረጅምጊዜ በሞቀ ስሜት ለመቆየት የሚያስችል እና በቅርብ ጓደኛውከዱባይ እንዳመጣለት ነገረን፡፡ የተወሰኑት በእረፍትና በድፍረትመሀከል ሆነው እስኪ እንሞክረው ሲሉ ተስማሙ፡፡ እኔና አንዱጓደኛችን በድምፅ ተአቅቦ ዝም ብለን ማዳመጥ ቀጠልን፡፡እርግጥ አልፎ አልፎ ከባለቤቴ ጋር ወሲብ ለመፈፀም ስፈልግስሜቴ ስለማይነቃቃ ባለቤቴ ላይ መከፋት አያለሁ፡፡ እናምእንዲህ አይነት ሁኔታ ሲፈጠር እንደጓደኞቼ ምን አለ ብጠቀምብዬ አስባለሁ፡፡ ግን ግን ስጋቴ ከዛ በኋላስ ምን ሁኔታ ውስጥእገኛለሁ ብዬ ሳስብ ይጨንቀኛል፡፡ ታዲያ ለዚህ ብዬባለሙያዎችን ለማማከር ወደ ህክምና ብሄድ ቅብጠትይሆንብኛል ብዬ አስባለሁ፡፡ ልጠቀም አልጠቀም በሚልውዝግብ ለመውጣት ሁሉንም ለመርሳት ሞከርኩ፡፡ ነገር ግንመድኃኒቱን ከሌላ ሰው እጅ በማግኘቴ ገዝቼአስቀምጬዋለሁ፡፡ እንደው ምን አልባት ቢያስፈልግ ብዬ፡፡ሲል ስሙን እንዳልጠቅስ ከነማስጠንቀቂያ የነገረኝ ጓደኛዬያነሳልኝን ጨዋታ ተመርኩዤ በዚህና መሰል የስንፈተ ወሲብናአማራጭ መድኃኒቶች ዙሪያ ባለሙያ አነጋግሬ ይዤላችሁቀረብኩ፡፡ ችግሩ በአበባ ወጣቶች ላይ መንሰራፋቱን ከተለያዩሰዎች ለመረዳት ይቻላል፡፡ እናስ ህክምናው ምን መልስአለው፡፡ ዶ/ር ድጋፌ ፀጋዬ የቆዳና የአባላዘር ስፔሻሊስትናቸው፡፡ ከስንፈተ ወሲብ በመነሳት እንዲህ ያስረዱናል፡፡በወንዶች ላይ የሚታዩት የስንፈተ ወሲብ ችግሮችን በሶስትመልኩ ከፍለን ማየት እንችላለን፡፡ አንደኛው የብልት መነሳትችግር (Reactive dysfunction) ወይም የወሲብ ስንፈትእየተባለ የሚጠራው ነው፡፡ ሁለተኛው እርካታ ደረጃ ሳይደርስየዘር ፈሳሽ ማውጣት (premature ejaculation) ሶስተኛውየወሲብ ስሜት አልባነት ናቸው፡፡የመጀመሪያውን ስንመለከት የብልት መነሳት ችግርያለባቸው ሰዎችን በብዛት እናገኛለን፡፡ በተለያየ ዕድሜ ክልልውስጥ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ቢያጠቃም በተደጋጋሚወደ ህክምና የሚመጡት ግን ዕድሜያቸው ከስልሳ ዓመትበላይ በሆኑት ላይ ነው፡፡ አንዳንድ ወጣቶችም ሪፖርትሊያደርጉ ችለዋል፡፡ችግሩ ከየት ይነሳል? ብለን ስንመለከት ሁለት አይነትምክንያቶች አሉት፡፡ የመጀመሪያው ከስነ ልቦና (Phylogenic)ጋር የተያያዘ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ኦርጋኒክ (ምክንያታዊ)የሆኑ የተለያዩ በሽታዎች በሚፈጥሩት ተፅዕኖ ይከሰታል፡፡ዋነኛው የስንፈተ ወሲብ መንስኤ ተብሎ የሚጠቀሰው የስነ-ልቦና ጉዳይ ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የአዕምሮ ውጥረትበሚኖርበት ጊዜ ጭንቀት እና የተለያዩ ሀሳቦች ለስንፈተ ወሲብያጋልጡናል፡፡ ሌላው የአካል ድካም እና መዛል ነው፡፡ ለምሳሌአካሉ በብዙ ስራ ሲንቀሳቀስ የዋለ ሰው በግንኙነት ወቅትየብልት መነሳት፣ ስሜት ማጣት አሊያም ለወሲብ ምቹ ባልሆነሁኔታ ውስጥ ሊገኝ ይችላል፡፡ ብልት እርቀት ደረጃ ሳይደርስአስቀድሞ ጥንካሬውን የሚያጣበት ምክንያት የሀሳቦችንመደራረብ በመኖራቸው ነው፡፡ ይህን በምሳሌ ብንመለከትከፍቅር ጓደኛው ጋር ወሲብ በሚፈፅምበት ወቅት ነጋዴ ከሆነስለተጋረጠበት የንግድ ችግር የመስሪያ ቤት ኃላፊ ከሆነስላልተሳኩ የድርጅቱ እቅዶች ካለው ኃላፊነት ጫና የተነሳበአዕምሮው ሊመላለሱበት ይችላሉ፡፡ ይህም ጥሩ ያልሆነ ግብረስጋ ግንኙነት እንዲኖር ያደርጋል፡፡ግብረስጋ ግንኙነት ደግሞ በባህሪው ሙሉ ለሙሉ ትኩረትየሚሻ ጉዳይ ነው፡፡ ሌላው በባልና በሚስት መካከልአለመግባባት /ቅሬታ በሚኖርበት ጊዜ ተነሳሽነቱ በሁለቱምወገን ይቀንሳል፡፡ በቀጥታ ከአዕምሮ ጋር የሚያያይዘው የግብረስጋ ግንኙነት ስነ-ልቦናና አካላዊ ዝግጁነት ጅማሪ አይምሮውስጥ በሚፈጠር ኬሚካሎች አማካይነት ነው፡፡ የአንድሮጂንኬሚካል መመረት ወንዶች ላይ ብዛት የደም ፍሰቱ ወደ ብልትእንዲሆን በማድረግ ብልት እንዲነሳ ያደርጋል፡፡ ከላይየጠቀስናቸው ምክንያቶች ይህን ኬሚካላዊ የዝግጁነት ቅመምእንዳይፈጠር ስለሚያደርጉ የፓርኖግራፊ ፊልሞችበሚፈጥሩት፣ በአደጋ (ግጭት) ጫና፣ በሃዘን፣ በድካም መካከልስንፈተ ወሲብ እንዲፈጠር ያደርጋሉ፡፡ ለዚህም ነው ብልትየመነሳት ችግር የሚያጋጥመው፡፡ሁለተኛው ምክንያት ኦርጋኒክ የሚባለው ሲሆን የተለያዩህመሞችን ተከትሎ የሚመጣ የወሲብ ችግር ሲሆን ስኳር፣ ደምግፊትና የአባላዘር በሽታዎች ሲያጠቁን ነው፡፡ ሌላው የተለያዩአደገኛ መድኃኒቶች አልኮልና ጫት የደም ዝውውርን የሚቀንሱናቸው፡፡ በግንኙነት ወቅት ብልት እንዲነሳ ካስፈለገ ከፍተኛየደም ዝውውር ሊኖር ይገባል፡፡ በቂ የሆነ የነርቭ መነቃቃትምያስፈልጋል፡፡ እነዚህ ነገሮች የሚያስከትሉት ጫና ደግሞበወሲብ የመነቃቃትና ትክክለኛውን ኡደት ጠብቆበሚጠበቀው ደረጃ እርካታ ላይ ለመድረስ እንዳይችሉእንቅፋት ይሆናል፡፡እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የሚያስችሉን ህክምናዊመፍትሄዎች የትኞቹ ናቸው? የሚለውን ስንመለከትበቅድሚያ ወሲባዊ ህይወት እንደ ምስጢር በየሰውአዕምሮ ውስጥ በመቀበሩ ችግሮችን አውጥቶ ከህክምናባለሙያዎች እና ከትዳር አጋር ወይም ፍቅረኛ ጋርለመወያየት አለመቻል በራሱችግሩን የሚያባብሱምክንያቶችናቸው፡፡ከህክምናውጋርየተገናኙትምበትክክልህክምናተከታትለውሲያጠናቅቁአይታዩም፡፡በመሆኑም በቀላሉመፍትሄ ላያገኙከሚችሉበት አጋጣሚበመራቅ ለተለያዩ አላሰፈላጊየጊዜና ገንዘብ ብክነቶችይዳረጋሉ፡፡ በመሆኑም መፍትሄውየመጀመሪያው እርምጃ የችግሩን መነሻምክንያትን ለይቶ ማወቅ ነው፡፡እንደመንስኤው የተለያዩ ህክምናዎችእንዲሰጡበት ያደርጋል፡፡ ከስነ-ልቦና ጋርየተያያዘ ከሆነ ያለመድኃኒት ሊስተካከልይችላል፡፡ ያለውን ችግር ማለትም አካላዊናአዕምሮአዊ ሁኔታ የስነ-ልቦና ድጋፍ በማግኘትበማስተካከል ሊቀረፍ ይችላል፡፡ ከተለያዩ ህመሞችየሚነሳው የስንፈተ ወሲብ ችግር ከመቆጣጠርናከመከላከል ባሻገር መድኃኒቶችን ለደም የሚገባውንየወሲብ ስሜት መጠበቅ የሚቻልባቸው መንገዶች አሉ፡፡በዚህ ውስጥ አልፈን መፍትሄ ካልተገኘ የመጨረሻውአማራጭ ረዳት መድኃኒቶችን ማካተት ይሆናል፡፡እነዚህ መድኃኒቶች ያላቸው ጥቅም ምንድን ነው ካልንየደም ዝውውር በመጨመር ነርቮች እንዲነቃቁ የወንዱ ብልትአካባቢ ያሉት ጡንቻዎች እንዲኮማተሩ እና ብልት እንዲጠነክርየሚያደርጉ ናቸው፡፡ መድኃኒቱም በህክምና ባለሙያ ትዕዛዝመሰረት በጥንቃቄ ሊወሰድ ይገባዋል፡፡ ምክንያቱም አይነትናመጠኑ ሊያውቅ የሚችለው በህክምናው ዘርፍ በቂ ትምህርትናልምድ ያለው በመሆኑ ነው፡፡ ተያይዘው ለሚመጡ ተጓዳኝአሉታዊ ተፅዕኖዎች ተጠንተው ቅድመ እና ድህረ ጥንቃቄሁኔታዎችን በማመቻቸት ችግሩ እንዲቀረፍ 50 በመቶአስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ ከችግሩ አይነትና መጠን ተነስተን ነውመድኃኒቶቹን የምናዘው፡፡መድኃኒቶች ያሏቸውን ጥቅም ያህል ብዙ ጉዳቶችንምሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ ለዚህም ነው የባለሙያ ድጋፍአስፈላጊነት ሁኔታዎችን በማገነዛብ መድኃኒቶችን ማዘዝውጤታቸውንም መከታተል ከተቻለ መድኃኒቱ ያለምንምጉዳት የሚጠበቀውን ውጤት እንዲያስመዘግብ ይረዳዋል፡፡መድኃኒቱ መታዘዝ ያለበትን ወቅት በተመለከተ ምክንያቱታውቆ አማራጭ መፍትሄዎች ታይተው ግድ የሚሉ ሁኔታዎችሲፈጠሩ ነው፡፡ የመድኃኒቱ መጠን እና አይነት መቼስመውሰድ አለበት? እነማንናቸው መድኃኒቱን መውሰድየሚችሉት? እነማንስመድኃኒቱንሲወስዱ ችግሮችይገጥማቸዋል? የሚለውን የሚወስነው ባለሙያው ነው፡፡ሰዎች ከተለያዩ ምንጮች ካገኟቸው መረጃዎች ተነስተውመድኃኒቶችን ያለህክምና ትዕዛዝ ይወስዳሉ፡፡ ለዚህምምክንያቱ ለችግሩ ትክክለኛ መፍትሄ ሊሰጥ ወደሚችለውባለሙያ ለመሄድ ያለው ተነሳሽነት በጣም ዝቅተኛመሆን፣ የወሲብ ምስጢራዊነት እሳቤ፣ የመድኃኒቶቹን የጎንዮሽችግር ያለመረዳት፤ የጓደኛና የተለያዩ የወሲብ ትዕይንቶችከሚያስከትሉት ጫና የተነሳ ነው፡፡ ችግሩ ሳይኖር መድኃኒቶችንአፈላልጎ መጠቀም የመቻል አቅምና ድፍረት በተጨማሪ ህገ-ወጥ የመድኃኒት ዝውውር መኖሩ የራሱን አስተዋፅኦያበረክታል፡፡ለምሳሌ ቪያግራ ተሰኘውን መድኃኒት በተለያየ መልኩማግኘት የቻሉ ሰዎች ዝም ብለው ቢጠቀሙበት ምንያስከትላል ስንል የልብ ድካም ያለባቸው (አርቴፊሻልመሳሪያዎች በልባቸው የተገጠመላቸው ሰዎች) ችግርይገጠማቸዋል፡፡ መድኃኒቶቹ በዚህ ሁኔታ ከጥቅም ይልቅጉዳታቸው ያመዝናል፡፡በተጨማሪም ከልክ ያለፈ የብልት መነቃቃት ሳቢያ ብልትቆሞ ላይመለስ የሚችልበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡ ይህም Persistencestimulation ያስከትላል፡፡ ሌላው በግንኙነት ወቅትብልት በጣም ከመወጣጠሩ የተነሳ የብልት ዘንግ ስብራትሊያጋጥም የሚችላቸው ሁኔታዎች ይፈጠራሉ፡፡ አንድምጊዜያዊ ከፍተኛ ህመም፡፡ በተጨማሪም የልብ ስራን የማዛባትችግር ሊያስከትል ይችላል፡፡የስንፈተ ወሲብ መድኃኒቶቹን ማግኘት ስለተቻለ ብቻመጠቀሙ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ ብዙ ጊዜ መድኃኒቱእንደ ችግሩ ሁኔታ ታይቶ በቀን አንዴ ግንኙነት ከማድረጊያጊዜ አንድ ሰዓት ቀድሞ እንዲወሰድ የሚታዘዝ ሲሆንበተደጋጋሚ እንዲወሰድ አይመከርም፡፡መድኃኒቱን ደጋግሞ መውሰድ አስቀድመን የጠቀስናቸውንችግሮችን ማባባስ ያስከትላል፡፡ በተለምዶየወንዶች ብልት ከተነሳ ከተወሰነ ጊዜበኋላ ወደ ቀድሞ ቦታው ይመለሳል፡፡ለረጅም ሰዓት ተነስቶ በሚቆይበትወቅት እጅግ በጣም ከፍተኛ ህመምአለው፡፡ መልሶ ግንኙነት ማድረግበሚያስፈልግበት ጊዜም ሊያስቸግርይችላል፡፡እንደ ቪያግራ ያሉ መድኃኒቶችንመጠቀም የጀመረ ሰው የጥገኝነት ባህሪስለሚዋሃደው ያለው በራስ መተማመንይቀንሳል፡፡ ያለመድኃኒቱ በተፈጥሮአዊመንገድ ለወሲብ መዘጋጀት እና መደሰትምያቅተዋል፡፡ የቪያግራ መድኃኒት በኪኒን መልክየሚሰጥ ሲሆን አልፎም በመርፌ መልክወንድነትን የሚያላብሰው የቴስቴስትሮንሆርሞን በጊዜ ሂደት ሲቀንስ ቅመምአመንጭውን ክፍል ለማነቃቃት (መጠኑንለመጨመር) የሚያስችል በሳምንት አንድመርፌ ይሰጣል፡፡ ስለሆነም ስንፈተ ወሲብያስከተለው የቴስቴስትሮን ማነስ፣ የስነ-ልቦናጫና አካላዊ ድካም ወዘተ... መንስኤዎችውስጥ የትኛው እንደሆነ ታውቆ መድኃኒቶችይመረጣሉ፡፡አብዛኛው ስንፈተ ወሲብ ችግሮች ባህሪንከማስተካከል፣ ስነ-ልቦናዊ ድጋፍ እና ምክርበመስጠት ያለመድኃኒት ሊታከሙ የሚችሉናቸው፡፡ ህክምና ቦታ መጥተው ፈራ ተባእያሉ የመናገር ከፍተኛ ችግር አለ፡፡ ይህተወግዶ ግልፅነት ከዳበረ ችግሩ እንዲቀረፍይረዳል፡፡ በወጣቶች በኩል ለዚህ ችግርየሚጋለጡበት ዋነኛ ምክንያት በሱስ መጠመድሲሆን በተለይም ለረጅም ጊዜ ጫት መቃምእና በብዛት አልኮል የሚወስዱ ከሆነ ለስንፈተወሲብ ይጋለጣሉ፡፡ ከጋብቻ በፊት የሚኖርከግብረ ስጋ ግንኙነት ለስንፈተ ወሲብያጋልጣል፡፡ በደንብ ሳይተዋወቁ ስሜታዊወሲባዊ ድርጊቶችን የሚፈፅሙ ሰዎችበሚያድርባቸው ስነ-ልቦና ጫና የስንፈተወሲብ ችግር ሊያጋጥማቸው ይችላል፡፡እኛ አገር ባይኖርም በባለትዳሮች መሀከልየሚደረግ የወሲብ ህክምና በተለያዩ ሀገሮችየሚሰጥ ሲሆን ከትዳር አጋር ጋር በሚያጋጥም የወሲብአለመጣጣም ችግሮችን በማጥናት መፍትሄ ማስቀመጥየሚቻልበት ሂደት ነው፡፡ በወሲብ ህይወት ውስጥ ዝግጁነትእና ግልፅነት ትኩረት ሊሰጥባቸው የሚገቡ ነጥቦች ናቸው፡፡ስለ ወሲብ ከትዳር አጋር (ፍቅረኛ) ጋር በግልፅ በማውራትለችግሮቹ መፍትሄ ለመፈለግ ይረዳል፡፡ በዚህ ሳቢያ የሚደርስየትዳር መፍረሶችን መታደግ ይቻላል፡፡ ተገቢውን ህክምናማግኘት እና በተለይም ቤተሰባዊ መረዳዳት እና በወሲብ ወቅትማዘጋጀት፣ እራስን የተረጋጋ፣ ፍቅር የተሞላበት እና መተማመንየሰፈነበት ወሲብ ሙሉ ደስታን ያጎናፅፋል፡፡ቪያግራን ወንዶች ያለ ሐኪም ትዕዛዝ ሲጠቀሙበትከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝንም የታወቀ ሲሆን ይህመድኃኒት ለሴቶች ጥቅም ስለማይኖረው በድፍረት እናባለማወቅ የወሲብ መነቃቃትን ይፈጥራል ብለው ሴቶችእንዳይቀጠሙበት እናስጠነቅቃለን፡፡መድኃኒቶች ህጋዊ ባልሆኑ መንገዶች ሲገቡ ጥራታቸውያልተፈተነ፣ የማዳን አቅማቸው፣ የጎንዮሽ ጉዳታቸው፣የአወሳሰድ መጠናቸውና ልዩ ጥቅም የሚያስገኝባቸው ችግራዊመንስኤዎች ስለማይታወቁ ያለሐኪም ትዕዛዝ መውሰዱ ለከፋችግር ያጋልጣሉና የጥንቃቄ እርምጃው እየተስተዋለ ሊሆንይገባዋል፡፡

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!