10.08.2015 Views

8326/henocka2001@yahoo.com 226-8326/ 612-226

medina newspaper # 1 - Ethiopian Review

medina newspaper # 1 - Ethiopian Review

SHOW MORE
SHOW LESS
  • No tags were found...

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

ሰው ማለት ምን ማለት እንደሆነ ብዙ ጊዜ አይገባኝም፡፡ምክንያቴ ደግሞ ሰው ስሙና ተግባሩ ብዙ ጊዜእየተጣረሰብኝ ስለተቸገርኩ ነው፡፡ ሰው የተከበረናየተደነቀ ፍጡር እንደሆነ ብዙ ቦታ ተፅፎ እናነባለን፡፡ የሰውአፈጣጠርም ከፍጡራን ሁሉ ለየት ብሎ በክብር እንደሆነበቤተ-ክርስቲያንም እንሰበካለን፡፡ግን ይሄ አፈጣጠሩና ትርጉሙ የተካበደለት ሰው ተብዬፍጡር ምግባሩ ግን ከትርጉሙና ከክብሩ ጋር ፈፅሞ የሚገናኝአይደለም፡፡ ምናልባት ጥሩ ሰዎች ይኖራሉ፡፡ አሉም፡፡ ደግሞግን እነዛን ጥሩ ሰዎች ለማግኘት የጊዜ ትግልና ብዙምመስዋዕትነትን ይጠይቃል፡፡ብዙዎቹ ግን ስማቸው እና በሁለት እግራቸው በመሄዳቸውብቻ ነው ሰው የሚባሉት፡፡ እንጂ ምግባራቸው ፈፅሞአይገልፃቸውም፡፡ ትንሽ ነገር ካላቸው በዛች ነገር የሚኮፈሱሌላው የነሱ በታች እንደሆነ አድርገው የሚያስቡ የነሱ መብትከሌላው እንደተለየና ከፍ እንዳለ የሚቆጥሩ ባዶዎች ናቸው፡፡የሰውን ትክክለኛ ማንነት የት እንደማየው ታውቃለችሁ፤መፀዳጃ ቤት ስሆን፡፡ በቃ በጨርቅ አምሮ ከእግሩ ንጥር ንጥርእያለ በኩራት ትከሻውን እንደ ሐረር ሠንጋ እያስጨፈረ ትንሽባላቸው ስልጣንና ሚጢጢ ጉልበት እየታየ በሬን አክላለሁብላ አብጣ አብጣ ተተርትራ እንደሞተችው እንቁራሪት በባዶጉራ የሚውተረተረው ሁሉ በቃ መፀዳጃ ቤት ሲገባ ራሱንቢመለከት የሱን ትክክለኛ ማንነት ይገነዘበው ነበር፡፡አሁን ደግሞ አንድ ነገር ተገንዝቤያለሁ፡፡ ጥፋትንከሚፈፅሙ በርካታ ሰዎች መሀል የተወሰኑት ወይም ጥቂቶችባለማወቅ ነው ሰውን የሚበድሉት፡፡ ግማሹ እንደ እኔ በበቀልግማሹም ኢንጆይ ላድርግ በማለት ሰዎች ላይ ንጥር በማለትራሱን የሚያስደስት አለ፡፡ ሌላውም ሆነ ብሎና እሱ ከሰዎችየተለየ መስሎት ሰዎች ለሱ ትልቅ ስፍራ እንዲሰጡት ባለችውትንሽ ስልጣን ለምኑኝ የሚልና ክብር ፈላጊ ነው፡፡ እንዲህአይነቱ ባዶ ሰው የተሾመው ሰውን ለማገልገል እንጂ በሰዎችለመገልገል እንዳልሆነ ያልተረዳ የሰው ትንሽ ነው፡፡ ሰው ደግሞበተንኮል ከተሞላ እንኳን ነፍስ ያወቀ ሰው ቀርቶ ታዳጊ ልጅምለህይወቱ አስጊ ስራ መስራት እንደሚችል ያልተገነዘበ አዙሮመመልከቻ አንገት የሌለው ስንት አለ፡፡እኔ ሳላውቅ በአንድ ችግርና በአንድ በደል ሳቢያ ሌሎችንየምቆጣና በሌሎች ላይ ግፍ የምውል አይነት ሰው ነኝ፡፡የተወለድኩትም ያደኩትም እዚሁ አዲስ አበባ ሲሆን ግን ወጣካለ የከተማዋ ክፍል ነበር፡፡ እናትና አባቴ እኔንና የኔን ሁለትታናናሽ ወንዶች ለማሳደግ የሚጠበቅባቸውን መስዋዕትነት ሁሉየከፈሉ እናትና አባት ናቸው፡፡ በኑሮ በኩል አላቸው የሚባሉአይነት ባይሆኑም የሌላቸው ድሆች የሚሰኙም አይደሉም፡፡አካባቢው ከከተማ ራቅ ያለ ስፍራ በመሆኑ ያሉን ትርፍአምስት ቤቶች በእርካሽ የተከራዩ ሆኑ እንጂ ከተማው ውስጥቢሆን ኖሮ የቤቶቹ ኪራይ ራሱ ሁላችንንም አንቀባሮ ባኖረንነበር፡፡ ያም ቢሆን ግን የቤቱ ኪራይ ምንም አልጠቀመንምለማለት ፈፅሞ አይቻልም፡፡ከእናትና አባታችን የደመወዝ ብር ጋር ተደምሮ ኑሯችንንአሪፍ የሚሰኝ አድርጎታል፡፡ የእናታችን ዝንባሌ የቤት ውድውድ ንብረቶችን በመግዛት ቤትን ማስዋብ እንደመሆኑ መጠንቤታችንም ከታላቅ ሀብታሞች መኖሪያ ቤት የውስጥ ክፍልያነሰ አይደለም፡፡ ደረጃቸውን የጠበቁና ውድ ውድ ንብረቶችአሉን፡፡ እናታችን መጣ የተባለ የቤት ዕቃ አያመልጣትም፡፡ወዲያው ማድረግ ባትችል በተወሰኑ ወራት ውስጥ ትገዛለች፡፡ለእኛም ለልጆቿም ቢሆን እንደዛው ናት፡፡ ሌላው ሰውአድርጎት ለብሶት ያየችውን ነገር ለኛ ለማድረግ እንቅልፍየላትም፡፡ በዚህ መጠነኛ አስደሳች ፍቅርና እንክብካቤ ስናድግየኛም ደስተኝነት የትየለሌ ነበር፡፡ ከዛ ጋር ተዳምሮ የእናትናአባታችን ፍቅርና አክብሮትም የተለየ ነው፡፡ ሁለቱምየተገናኙት ገና በአፍላ ዕድሜያቸው ሲሆን እውነተኛ የሆነውፍቅራቸው ከስፍራው ሳይጎድል እንደውም ከእለት ወደ ዕለትእያየለ እንደጠጅ እየጠነከረ የአካባቢውን ሰው በሙሉ ያስገረመነበር፡፡ የእናትና አባታችንን አንድ ጥንካሬ እንወድላቸዋለን፡፡ከሁሉም ከሁሉም አብልጠን፡፡ ይሄውም በመሀላቸውአለመግባባት ሲፈጠር እንኳን አለመግባባታቸውን ለራሳቸውይዘው በንግግር ይፈቱታል እንጂ ንትርክ ፈጥረውና ጥላቸውንአባብሰው ለሶስተኛ ሰው በፍፁም አያደርሱትም፡፡በእነሱ አለመግባባት መሀል ድንገት እንኳን ጎረቤት ሰውቤታችን ሲመጣ ያንን ያለመግባባታቸውን ተወት አድርገውፍቅር በፍቅር በመሆን እንግዳቸውን ይሸኛሉ፡፡ ከዛ በኋላ ወደውይይታቸው አምርተው ያላግባባቸውን ነገር በስምምነት ወደአንድነት ያመጡታል፡፡ ዛሬ ግን ወጣቱም አዛውንቱም አንዴበትንሽ ነገር መነታረክ ከጀመረ ካልተፈነካከተ ወይ ሶስተኛሰው ገብቶ ካልዳኛቸው መመለለስን አያውቁትም፡፡በሆነ ነገር ስንጋጭ ያንን ነገር በእርጋታ ማየትን አንወድም፡፡በንግግር ወደ አንድ ሀሳብ ማምራትንም የተሸናፊነት ትርጉምሰጥተነው ትክክል አለመሆናችንን ልባችን እየተረዳው ግን‹‹አዎን ለካስ ተሳስቼ ነበር ይቅርታ የኔ ውድ›› ማለት የትልቅነትየእውነተኛነት መለኪያ እንደሆነ እንኳን ልብ አንልም፡፡ ብቻየሚታየን ትልቁ ነገር ላለመስማማት ድርቅ እና ክችች ማለትንነው፡፡ አንዳንዶች ደግሞ በራሴም የነበረ ድክመት ነው፡፡ ሰውበጓደኝነት ወይም በፍቅረኝነት የልቡን ሲናገርና ከየዋህነትአንጻር አይባልም ብለን ደረጃ ያወጣንለት ግን መናገር ያለበትንነገር ሲነግረን እኛ በልባችን ‹‹እንዴት ቢንቀኝ ነው እንዲህየሚለኝ›› እያልን ተንኮልና ቂምንም በልቦቻችን እየሸረብን የዛንዕለት ሰው መስለን በሰላም እንለይና ከዛ እለት በኋላያረገዝነውን ቂምና በሽታ ወልደን ጓደኝነታችንን አፍርሰን ጥሩአፍቃሪ እናጣለን፡፡ከበሽታ ሁሉ በሽታ ምንም መድኃኒት የሌለው ራስን ዞርብሎ ያለማየትና ሁል ጊዜ እኔ ትክክል ነኝ በማለት ወይ ትክክልመሆናችንን በእርጋታና በውይይት እናስረዳ ወይ ከተውንአንተው በልባችን አፍነን ያፈነው ድክመታችን ለገዛ ራሳችንበሽታ ሆኖ ከአፍቃሪያችን ይለየናል፡፡በቤተሰቤ እንክብካቤ ስላደኩ አንዳንድ የህይወትእውነታዎች ለማየት አልቻልኩም፡፡ በኋላ መጎዳቴን ሳውቀውነው ያንን ክፍተት ለመሙላት የተለያዩ ጋዜጦችንናመጽሔቶችን በማንበብ ለማሟላት የጣርኩት፡፡ ያንንምያደረኩት ከተጎዳሁና ሰውንም ከጎዳሁኝ በኋላ ነው፡፡ ቢሆንምግን ለቀሪ ህይወቴ ጠንካራ ትምህርት እና እውቀትን ስለሰጡኝየማነባቸው ነገሮች ለኔ ባለውለታዎቼ ናቸው፡፡አንዳንድ ጊዜ ከቤተሰብ በምክር ደረጃ የምንወርሳቸውናየምናዳብራቸው የህይወት ገጽታዎች ከተጠቀምንባቸውለኑሯችን ትልቅ መሰረቶች ናቸው፡፡ ግን ከምክር ሌላቤተሰባችን እያደረጉት የምናየው ነገር ግን በተቃራኒው መንገድእንደሚመራን ከራሴም ከሌሎችም እንዲሁም ከማነባቸውነገሮች ተረድቻለሁ፡፡ለምሳሌ የእኛ እናትና አባት እኛን ስለ ህይወት እውነታአንዳችም ያስረዱን ነገር የለም፡፡ እኛ እየቀሰምን ያደግነውየነሱን ጥሩ ሰውነትና ፍቅር ነው፡፡ መግባባት መቻላቸውንጥላቸው ያልተጋነነ እንደውም ደስ የሚል አይነት እንደሆነ ነውእያየን ያደግነው፡፡ የእነሱ ጥል ራሱ የምንናፍቀውና እኛም ወደፊት አድገን ስናገባ ብንሆነው የምንለው አይነት ነው፡፡ ለምሳሌሰው ናቸውና አለመግባባት መሀላቸው ሲፈጠርና ድንገት ሆትሲሆኑ አንዳቸው ተሳስተው የሚያስከፋ ንግግር ከተናገሩወዲያው ያላግባባቸው ምክንያት ይጠፋና ተቃቅፈው እርስበእርስ ይቅርታ እናትዬ አባትዬ እየተባባሉ ወደ ጥልቅ ፍቅርይገባሉ፡፡ይሄን እያየሁ ማደጌ ጥሩ ሰው እንድሆንና የነሱን ጠባይእንድወርስ ሳይሆን ያደረገኝ ዝም ብሎ እንደነሱ አይነትን ጥሩናጣፋጭ ህይወት እንድናፍቅ እንድመኝ ብቻ ነበር ያደረገኝ፡፡ጥሩ የፍቅር ህይወትን ማናችንም ብንሆን በምኞት ደረጃእንመኛለን፡፡ እናም ሰው ሁሉ ለእኛ ጥሩ ሰውና እኛንተንከባካቢ እንዲሆን እንፈልጋን፡፡ ይሄን ሁሉ ስንፈልግናስንመኝ ግን በዛው መጠን ከእኛ ምን እንደሚጠበቅMedina/መዲናNovember 2011 volume I No. 1 ጥቅምት 2004 1ኛ ዓመት ቁጥር 1አናስብም፡፡ ሁሌ ሰውን እንኮንናለን እንታዘባለን እንጂየራሳችንን ስህተትና ከኛ ምን እንደሚጠበቅ አናስብም፡፡አንጨነቅበትም፡፡አንድ መስሪያ ቤት ተቀጥረን መስራት መጀመራችንብቻውን ደሞዝ እንድናገኝ አያደርገንም፡፡ የመስሪያ ቤቱ አባልመሆናችን አንዱ ነገር ሆኖ ግን ደሞዝ ለማግኘት ደግሞ የግድወር መስምራት ይጠበቅብናል፡፡ በመንግስት መስሪያ ቤት ራሱየተቀመጠውን ስምንት የስራ ሰዓት በአግባቡ ባንወጣም ግንበየቀኑ በሁለት ሰዓት ቢሮ ተገኝተን መፈረም የግድ ይለናል፡፡ብዙዎቻችን የፊርማ ብቻ እንጂ የስራ ሰዎች ሳላልሆንን፡፡እናም በፍቅር ውስጥም ስንሆን መፈቀራችን አንዱየመጀመሪያው መስፈርት ሆኖ ሳለ ግን የምንፈልገውን አይነትእንክብካቤ ማግኘት ስንፈልግ እኛም ከዛ የተሻለ እንክብካቤማድረግ እንዳለብን መርሳት አይጠበቅብንም፡፡ ያንን ከረሳንሊደረግልን የምንፈልገውንም ጥሩ ፍቅርና እንክብካቤ እንደዛውመርሳት ይኖርብናል፡፡ ከቤተሰቦቼም እያየሁ ያደኩት ሰው ሁሉበአፍቃሪው ልክ እንደ አባቴ ያለ አይነት ሰው እንደሆነ አድርጌነበር ያመንኩት፡፡ለካንስ የአባቴ አይነት ወንዶችን ለማግኘት ሁለት ቅደመሀላፊነቶች ይጠበቁብኛል፡፡ እነሱም በመጀመሪያ የምንፈልገውንአይነት መልካም ፍቅርና እንክብካቤ እኔም ማድረግእንዳለብኝና አፍቃሪዬ አሪፍና ተንከባካቢ አፍቃሪ እንዲሆንማድረግ ያለብኝ ራሴ መሆኔን ዘንግቼው ነበር፡፡ እናትና አባቴከማሳደግና ከመንከብ በቀር የእነሱ አይነት ፍቅር እንዴት ባለመልኩ ሊገኝ እንደሚችል የነገሩኝ ነገር ስለሌለ ዓለም ሁሉየነሱ አይነት እንዲመስለኝና ልክ ለፍቅር ስደርስ የሚገጥመኝመስሎኝ ስላደኩ ይሄ ከልጅነቴ ጊዜ ጀምሮ አብሮኝ ያደገውእምነቴ አስተሳሰቤ ጎድቶኝ ነበር፡፡ልክ ለአቅመ ሄዋን ስደርስ ያው በልቤ ያለው ንፁህ ፍቅርንማግኘትና እንደ አባቴ ተንከባካቢ ባል ወይም የፍቅር ጓደኛንማግኘትን ስለነበር ለጠየቀኝ ወንድ ሁሉ እምቢ ማለት እንኳንተቸግሬ ነበር፡፡ ምክንያቱም እንዴት እንደ አባቴ ላለ ወንድእምቢ ይባላል፤ ይሄ እያስጨነቀኝ አቋም ቢያሳጣኝም ግንየሁሉም ወንድ መሆን አይቻልምና የአንዱ መሆን የግድ ስለሆነከሚጠይቀኝ ወንዶች መሀል በሁሉ ነገሩ ይሻላል ላልኩትእሺታዬን ሰጠሁት፡፡ልጁን የመረጥኩበት ብዙ ምክንያት ነበረኝ፡፡ አንዱ አቋሙናመልከ መልካምነቱ ነበር፡፡ መቼም ቆንጆ ነገርን የሚጠላ ሰውየለም ብዬ አምናለሁ፡፡ በዚህ ምድር ላይ እኔም ብቻ ሳልሆንብዙዎቻችን በዚህ አስተሳሰብ ውስጥ ያለን ይመስለኛል፡፡ውበት በመጀመሪያ ከአይን ጋር ሲሆን የሚገናኘው ከአይንእንዳለፈ ቀጥታ ግንኙነቱ ከልብ ጋር ነው፡፡ብዙ ጊዜ እንዲህ አይነቱን ውበት ለማግኘት አስቸጋሪ ሊሆንይችላል፡፡ ብዙው ውበት አይን ላይ ብቻ ያርፍና ይቀራል፡፡ወደ ልብ የማለፍ ብቃቱ የለውም፡፡ ብዙ ውበት ገጥሟችሁአያውቅም፡፡ አየት ብቻ አድርጋችሁት ከዛ እንደዘበትየምትተዉት፡፡ አዎን ብዙው ውበት ጎደሎ ነው ማለት ነው፡፡ ጉልበቱከአይንአያልፍም፡፡አንዳንዱደግሞ አይንን ያስደምምና አይንአልነቀል ብሎ እዛው እንዲቀር ያደርጋል፡፡ ከዛም አልፎ ፍዝዝድንግዝ ደርጋል፡፡ ከዛም ያለፈ ከሆነ ደግሞ ቀጥታ ከልብ ጋርኮንታክት ይፈጥርና መላ ሰውነትን ይቆጣጠራል፡፡ እንደዚያአይነቱ ውበት አሰቸጋሪ ነው፡፡እኔንም የገጠመኝ እንደዛ አይነቱ ነበር፡፡ የጠየቁኝን ወንዶችበራሳቸው ብቃትና ደረጃ ሰጥቼ ሳያቸው አንዱ መልክይኖረውና ማራኪ ሰውነት አይኖረውም፡፡ ወይ እንደ እንቁራሪትያበጠ ሆድ አለው ወይም ደግሞ ቤተሰቦቹ ሲበሉ እጁንእያሰሩት የሚበሉ ይመስል እፍ... ቢሉት የሚወድቅ አይነትቀጫጫ ይሆናል፡፡ አንዱ ደግሞ ሰውነቱም አቋሙም አሪፍይሆንና ረዥም መለሎ ፈርጣማ ጅብ ይመስላል፡፡ ታዲያሲያዩት ካላማረ ሲበሉት ይስማማል? ስለዚህ ይሄን ታሳቢበማድረግ የራሴን ደረጃ እየሰጠኋቸው ስተዋቸው ከርሜ እሺያልኩት አሪፍና ቆንጆ ልጅ ላይ ደረስኩ፡፡ልጁ እርጋታው፣ አስተሳሰቡ፣ አነጋገሩ፣ ውበቱ ብቻ ሁሉነገሩ የተሟላ እግዚአብሔር ለአፈጣጠሩ መገረሚያ ሊያደርገውበስንቶቹ ጥሩ ያልሆኑ ሰዎች መሀል እንደ ፈርጥ ወይም እንደአንገት ሀብል ማጫወቻ ያስቀመጠው ብርቅ ሰው ነበር፡፡ ይሄንልጅ እምቢ የማለት ጉልበት በፍፁም አልነበረኝም፡፡ በዛ ላይደግሞ ቤተሰቦቹ ያላቸውና ምንም ያልጎደለበት እንኳንስ ለራሱቀርቶ ለሌላው መሆን የሚችል ስለሆነ ቤተሰቦቼም ከጥሩ ሰውጋር ሆነችልን ብለው እንዲያስቡ ስለሚያደርጋቸው ደስተኛነበርኩ፡፡ መቼም የሴት ቤተሰብ ምን አይነት ጠባይ አለው፡፡ከልቡ ያፈቅራታል ወይ? የሚፈልጋት ለዘለቄታው ነው ወይስለጊዜው ነው? በማለት አይደለም ለልጃቸው ወዳጅንየሚመርጡት፡፡ የእነሱ ብቸኛ አመለካከት ምን አለው? የማንዘርና ልጅ ነው? ሊያኖራት ሊያስተዳድራት አልፎም ለኛመትረፍ ይችላል ወይ የሚል ስለሆነ የኔም ቤተሰቦች በገጠመኝእድል እንደሚደሰቱ አልተጠራጠርኩም፡፡የደህና ቤተሰብ ልጅ ነው ወይ? የሚሉት ብዙዎቹ የሴትቤተሰቦች ደህና ቤተሰብ ማለት ትርጉሙ ሁልጊዜም ግራያጋባኛል፡፡ በተለይ አሁን ላይ ሆኜ ትክክለኛ ትርጉሙንስረዳው ደህና ቤተሰብ ማለት እንደብዙዎች የሴት ቤተሰቦችትርጓሜ ያለው ቤተሰብ ባለሀብት የሆነ ቤተሰብ ማለት ነው፡፡ደህና ሲባል ግን ያልታመመ፣ ጤነኛ የሆነ ወይም ደህና ቀጥያለ ያልተንሻፈፈ ወዘተ... ነበር፡፡ እነሱ ግን ደህና ያለውበሚለው ተኩት፡፡ እናም በዛን ሰዓት እኔም እንደነሱ ስላሰብኩያን ያክል አልተጨነኩበትም፡፡ ዋናው አላማዬና ፍላጎቴ ያባይሆንም ግን ቤተሰብ የተቀበለው ነገር ደስ ይላል አይደል?ከነፃነቱም አንፃር ቢሆን፣ ለዛ ስል ነበር እንጂ ዋናው አላማዬእንደ አባዬ ያለ ለባለቤቱ ፍቅር የሆነ ወንድ ማግኘት ብቻነበር፡፡ የእሱን አይነት ወንድ ማግኘት ደግሞ ከባድ መስሎአልታየኝም፡፡ ምክንያቱም ሰው ሁሉ በተለይ ወንድ ሁሉ እንደአባቴ አይነት ስለሚመስለኝ፡፡ይሄን አስተሳሰቤን ይዤ ከልጁ ጋር የፊት የኋላዬንሳልመለከት ቀጥታ ወደ ንፁህ ፍቅር ገባሁ፡፡ ከተቀራረብንናፍቅር በአንድ ፍንጃል ከተጎነጨን በኋላማ የምሆነውንአሳጣኝ፡፡ በመጀመሪያ ፍቅር እንዲህ ያደርጋል እንዴ? ንግሩፍቅር አሰጣጡ በሳልነቱ እንክብካቤው ለኔ የሚያደርግልኝ ነገርብዛቱ የሆነ ነገር አይቼ ‹አቤት ደስ ሲል› ካልኩ ወዲያውይገዛዋል፡፡ በዚህ ሁሉ ሁኔታው በቃ ክንፍ አውጥቼ በፍቅሩበረርኩለት፡፡በፊት አብሮኝ ያደገውን አስተሳሰብም ስላሟላልኝ ወንዶችንየመሰለ ቀና እና ተንከባካቢ ድንቅና ልዩ ፍጥረት የሰጠችንንተፈጥሮ ደጋግሜ አመሰገንኳት፡፡ ፈጣሪንም አመሰገንኩ፡፡ እኛሴቶች የምር ያለ ወንዶች ጎደሎ ነበርን፡፡ ማን ይንከባከበን ነበርማንስ ፍቅርን ይሰጠን ነበር እንድልና ያለ ወንዶች ባዶእንደሆንን ሆኖ ተሰማኝ፡፡በእርግጥም ዓለም ያለ ወንዶች ብቻ ሳይሆን ያለ ሴቶችምባዶ ናት፡፡ ህይወትም ከንቱ፡፡ በእርግጥ ይሄ የሚሆነው በቀላሉአይደለም፡፡ በሰዎች ውስጥ አውሬዎችም ተደብቀው ስላሉመልካም ያሉት ሰው እንዳልጠበቁት ሲሆን በተቃራኒው መሆኑአይቀርም፡፡ ወንዶችን ያሞገስነውን ያክል አማረን በአንዱናበሁለቱ ምክንያት ሁሉንም እንድንጠላ ሆነን እንድንኖርመገደድንም ያስከትላል፡፡እናም ከዚህ ልጅ ጋር አለሜን ስቀጭ ከረምኩና አምኜውልቤን መላ ሰውነቴን ሰጠሁት፡፡ በፊት ለአልጋ ሲጋብዘኝ ቆይአንቸኩል መጀመሪያ እርስ በርስ በደንብ እንተዋወቅ እያልኩእከለክለው የነበርኩት ሴት በአጭር ወራት ውስጥ የሴትነትክብሬን በራሴው ፍቃድ ሰጠሁትና ፍቅሬ ባሰ፡፡ይሄን የመሰለ ስብዕና ላለው ልጅ በጣም ለሚያፈቅረኝናለሚንከባከበኝ ሰው ለማንም መስጠቱ ለማይቀረው ሴትነቴእንዴት ብዬ ለሱ እከለክላለሁ ስልም እስካሁን ላስጠበኩትምይቅርታ ብዬው ነበር ገላዬን የጋበዝኩት፡ግን...ግን... ወንዶች ለምንድን ነው ለአልጋ የሚጣደፉት?አሁን አሁንማ ይበልጥ ሴቶችም እየባሰባቸው እንዳለከምሰማውም እንዲሁም ከጓደኞቼም ጠባይ በደንብ አድርጌተገንዝቤዋለሁ፡፡ ሴቶች በርከት ብለን ስንቀመጥ የምናወራውስለዚህ ስለ አልጋ ነው፡፡ መንገድ ላይ ሁለትና ሶስት ሴት ሆነውሲሄዱ የሚያወሩትን የማዳመጡን እድል ድንገት ስናገኝከጆሯችን የሚገባው ንግግር ስለ ስሜት ነው፡፡ በአንድ ጊዜላውጣሽ አይለኝ መሰለሽ? ስትል ወደታች ከሚወርዱት አንዷወደ ላይ እያወሩ ከሚወርዱትም መካከል እገሌ እኮአውጥቶኛል የሚል የሴት ንግግር ከጆሯችን ሊደርስ ይችላል፡፡በአጠቃላይ ይሄን ዘመን የስሜትና የወሲብ ዘመንአድርገነዋል፡፡ሴቷ ለፍቅረኛዋ አትታመን፡፡ ወንዱም እንደዛው የብዙታማኞችንና ጥሩዎችን ሰዎች ስራ ያጠፉብናል፡፡ አንድ ጊዜአራት ሆነን ወክ እያደረግን ሳለን አንዷ የተናገረችውንላካፍላችሁ፡፡ ሁል ጊዜም በአዕምሮዬ ተሰንቅሮ ዛሬም ድረስራሴንም አለሙንም እንድመለከትና እንድታዘብ ወዴት እየሄድንነው እንድልና እንድጠይቅም አድርጎኛል፡፡እንዲህ ነበር ያለችው፡፡ ጓደኛዋ ዓለም ላይ አሉ ከሚባሉወንዶች ሁሉ ታማኝና እጅግ በጣም ጥሩ ሰው እንደሆነ ተናግራግን አለች ግን ለወሲብ አንቸኩል ገና መግባባት መቻል አለብንወሲብ የተከበረ ነገር እንጂ ስሜትን ማስተንፈሻ ርካሽ ተግባርብቻ እንደሆነ መረዳት የለብንም እያለ እኔን በአዕምሮት ሊገለኝነው፡፡ አሁን አሁንማ ከሱ ጋር ስሆን ከፍቅረኛዬ ጋር የሆንኩሳይሆን ከወንድሜ ጋር የሆንኩ ያክል እየተሰማኝ ስለሆነልተወው ነው፡፡ እሱ ችላ ያለውን ግን ስንቶች የሚጎመጁለትንገላ እንካ ብለው አልገባ ስላለው እኔ ከወንድሜ ጋር ምንአኖረኝ በማለት ነበር የልቧን ከልቧ ያጫወተችኝ፡፡ከሁሉም ከሁሉም የሚገርመው ደግሞ በዛን ሰዓትሁላችንም ልክ ነሽ አልን እንጂ ተይ ስሜታዊ አትሁኚአላልናትም፡፡ ያ ሰው ጥሩ ሰው ነው አላልንም፡፡ እባክሽተይውና ሌላ ጀምሪ ምን በአምሮት አቃጠለሽ? በወጣትነትሽያመረሽን አድርጊ ነበር ያልናት፡፡ አሁን ላይ ሆኜ ሳስበው ግንያቺን ልጅ ወደ ገደል እንደከተትናት እየታወቀኝ ከአዕምሮዬ ጋርእረፍት የለኝም፡፡የኔን ታሪክ ስቀጥል ከዛ ልጅ ጋር በአሪፍ ፍቅር ስንኖርከርመን ቤተሰቦቼም የደህና ሰው ልጅ እና ደህና ሰው አገኘሽእድልሽ ጥሩ ነው በማለት ሲያሞግሱኝ ከርመው ሴት ልጅማለት እንደዚህ ነው ለቤተሰቧ መኩሪያ ስትሆን እያሉ ሲክቡኝቆይተው የልጁ ፀባይ ቀስ እያለ መለዋወጥ ጀመረ፡፡ ምን ሆንክስለው ስራ በዝቶብኝ ምናምን እያለ ምክንያት ያቀርባል፡፡ እኔምበፊት በፊት የሚለኝን ሁሉ አምነው ነበር በኋላ በኋላ ግንእየተደጋገመና ፀባዩ እያስጠላ ለኔም ጊዜ አልሰጥሽ ሲልናመንሸራተት ሲጀምር እየተጠራጠርኩት መጣሁ፡፡አንድ ሰው አፍቃሪውን እንደሚያፈቅር ከተናገረአፈቅርሻለሁ ካለ አንዱ መግለጫ ስለሆነ ያስደስትና በእርግጥምእገሌ ያፈቅረኛል ያስብል ይሆናል፡፡ ነገር ግን በተግባር ላይ ዜሮከሆነ ተዓማኒነቱ ምኑ ላይ ነው? አሁን እያልኩ ያለሁት ገንዘብላይ አይደለም፡፡ ብዙዎች በተለይ የኔን ፆታ የሚጋሩ ሴቶችእገሌ ፍቅሩን ሲገልፅልኝ ይገባል ብለው የሚያምኑትበሚያደርግላቸው ውለታና በሚገዛላቸው ነገር መጠን ነው፡፡ግን ለወንድ ልጅ የሆነ ነገር ማድረግ ማለት ምንም ማለትእንዳልሆነ አይረዱትም፡፡ ምንክንያቱም ሰው የሚፈልገውን ነገርለማግኘት የቻለውን ሁሉ ያደርጋልና፡፡ ስለዚህ አንድ ገንዘብላለው ወንድ የሴቷን ገላ እስኪያገኘ ድረስ የፈለገችውንቢያደርግላት አያስገርምም፡፡ ስላለው የፈለገውን ለማግኘትአዋለው ማለት ነው፡፡ እንደውም ሴቷ እንደተፈላጊና ብዙገንዘብ የሚከፈልበትን ውድ ንብረቷን አክብራው ለትክክለኛውሰው ማዋል እንዳለባት የሚያስተምራት መሆን ነበረባት፡፡ ግንሁላችንም ስሜታችንን ብቻ ተከትለን እየሮጥን ስሜታዊያልሆነውንም ወንድ ስሜታዊ እንዳርጋለን፡፡የፍቅኛዬ ፀባይ መለወጥ ገርሞኝ ሰፈሩ ድረስ እየሄድኩስለእሱ ማጥናት ጀመርኩ፡፡ ስለ እሱ ባጠናሁ ቁጥር ደግሞየሰማሁት ነገር ፈጽሞ ይሆናል ብዬ የማልጠብቀው ነገር ነበር፡፡ልጁ ሌላ ሰፈር ሚስትና አንዲት ሴት ልጅ ያለችው ሰውመሆኑን የሰማሁ ዕለት ለማመን ተቸግሬ ነበር፡፡ በኋላ ግንወሬው ሲደጋገም ማመኔ ግድ ነበርና የተባለበት ሰፈር ሄጄማጣራት ስለነበረብኝ ቦታውን አካባቢውን በደንብ ካጣራሁበኋላ ስፍራው ተገኘሁ፡፡ አሁን በጆሮ የሰማሁትን ሐቅ በአይኔተመለከትኩት፡፡ ቤት ድረስ ገብቼ ከልጁና ከባሌቱ ጋር ማዕድቀርበው ሳገኛቸው ብፌው ላይ በትልቅ ፍሬም የተቀመጠውንየሠርጋቸውን ፎቶ ስመለከት ከእነሱ መጠየቅ አላስፈለገኝምናበንዴት የከፋነገር ሳላደርስ ልጁንም ሳላሳቅቅ እንባዬን እየዘራሁቤት ተሳስቼ ነው በማለት በፍጥነት ወጣሁ፡፡ እሱን ለመርሳትብዙ ተቸግሬ ነበር፡፡ ሰውን ማመኔ ጎድቶኛል፡፡ ሰው በንግግሩበአቋሙ ሳይሆን መለካት ያለበት በተግባሩ እንደሆነ ልብያልኩት ከዛን ቀን በኋላ ነው፡፡ከሱ እንደተለየሁ ራሴን ለማረጋጋት ሌላ ፍቅር ከተወሰነወራት በኋላ ብጀምርም ወንድን ላምን ግን አልቻልኩም፡፡እናም የቀረብኩትን ወንድ እንደዛኛው ከሃዲ እያየሁት ፍቅርሳልሰጠው በሱ ላይ ሌላ ወንድ እያወጣሁ ከርሜ እሱምሌላውም ሲተወኝ ሰው መበደሌ ታወቀኝና ጥሩ ሰው ለመሆንተነሳሁ፡፡ ምክንያቱም የበደለኝ አስር ሰው እንኳን ቢሆንሁሉንም ስለማይወክል ለሰው ጥሩ ሰው ሆኜ መገኘትነበረብኝ፡፡ከዛ በኋላ ነው ዩኒን ያገኘሁት፡፡ ዩኒ ፍፁም ታማኝና ፍቅርየሆነ ልጅ ነው፡፡ ለኔ ያለውን ፍቅር በተግባር የሚገልፅ ተግባርስል በገንዘብ በማድረግ አይደለም ማድረግ የፍቅር ተግባር ሆኖአያውቅም፡፡ የገበያ እቃ እንጂ ስሚደረግላት ተፈቅሬያለሁየምትልም ሴት ካለች እሷ እየተፈቀረች ሳይሆን በብር እየተገዛችበስጦታ እቃ እየተደለለች (በሽተኛው... ወደ ገጽ 14 የዞረ)

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!