12.07.2015 Views

ስለሰብአዊ መብቶች መሟገት - East and Horn of Africa Human Rights ...

ስለሰብአዊ መብቶች መሟገት - East and Horn of Africa Human Rights ...

ስለሰብአዊ መብቶች መሟገት - East and Horn of Africa Human Rights ...

SHOW MORE
SHOW LESS
  • No tags were found...

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

የም/አ/ቀ/ሰ/መ/ተ/ፕ (EHAHRDP)ሐ/የብሄራዊ ህግ ሚናየብሄራዊ ህግን ሚና በተመለከተ የአዋጁ አንቀጽ 3 እና 4 በተቻለ መጠን ከፍተኛ ደረጃን የያዘ የሰብአዊ መብቶች መኖሩን ለማረጋገጥ በብሄራዊና በአለም አቀፍ ህግ መካከል ያለውን ግንኙነት ይዘረዝራሉ።የአዋጁን ግልጽ ትርጉም ለማግኘት አንቀጽ 3 ከአንቀጽ 4 ጋር የሚናበብ መሆኑን መገንዘብ ያሻል።አንቀጽ 3.ሰብአዊ መብቶችና መሰረታዊ ነጻነቶች የሚተገበሩበትና የሚጣጣሙበት እንዲሁም ማናቸውም በዚህ አዋጅ እነዚህንመብቶች ለማስፋፋት፣ለመንከባከብ እና ሙሉ ለሙሉ እነዚህ መብቶች እና ነጻነቶች ውጤታማ ሆነው እንዲተገበሩ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን የሚደግፍ የፍትህ መዋቅር ከተባበሩት መንግስታት ሰነድ እና ከሌሎችም በሰብአዊ መብቶችና መሰረታዊ ነጻነቶች ረገድ መንግስቱ ከገባው ዓለም አቀፍ ግዴታ ጋር የተጣጣመ የአገር ውስጥ ህግ ነው።አንቀጽ 4.በዚህ አዋጅ የተጠቀሰው ሁሉ በተባበሩት መንግስታት ሰነድ የተገለጹትን አላማዎችና መርሆች የሚያሰናክል ወይም የሚቃረን ወይም ስለዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች የታወጀውን እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ስለሰብአዊ መብት የተገባውን ቃልኪዳንና ሌሎች በዚህ ረገድ የተገቡ ዓለም አቀፍ ሰነዶችንና ውለታዎችን የሚገድብ ወይም የሚያኮስስ ተደርጎ ሊወሰድ አይቻልም።መ/ለሰብአዊ መብት ተሟጋቾች የተሰጡ መብቶችና ጥበቃዎችበአዋጁ አንቀጽ 1,5,6,7,8,9,11,12 እና 13 የተቀመጡት ለሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እንዲሁም ለመብታቸው የተለየ ጥበቃ ይሰጣሉ።አንቀጽ 1.ማንኛውም ሰው በግልም ሆነ ከሌሎች ጋር በመተባበር ሰብአዊ መብቶች በብሄራዊም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲያድጉ እንዲጠበቁና እንዲታወቁ ጥረት የማድረግ መብት አለው።*ሰብአዊ መብቶች በብሄራዊም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲጠበቁና እንዲታወቁ መሻት፣*የሰብአዊ መብት ስራዎችን በግልም ሆነ ከሌሎች ጋር በመተባበር መስራት፣*ማህበራትን እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን መመስረት፣*በሰላማዊ መንገድ መገናኘትና መሰብሰብ፣*ከሰብአዊ መብቶችጋር የተገናኙ መረጃዎችን መሻት፣መውሰድ፣መቀበል እና መያዝ፣*አዳዲስ የሰብአዊ መብት ሃሳቦችንና መርሆችን መጠንሰስና መወያያት ለተቀባይነታቸውም ቅስቀሳ ማድረግ፣*ከህዝብ ጉዳይ ጋር የተያያዘ አስተያዬትና ነቀፌታ ለሚቀበሉ የመንግስት አካላት፣ወኪሎችና ድርጅቶች የተሰማሩበትን ተግባር እንዲያሻሽሉና ለሰብአዊ መብቶች መከበር እንቅፋት የሆነውን ማናቸውንም ተግባራቸውን የሚጠቁም መረጃ ማቅረብ፣*ከሰብአዊ መብቶችጋር በተገናኙ መንግስታዊ ፖሊሲዎችና ውሳኔዎች ላይ አቤቱታ ማቅረብና አቤቱታዎቹ እንዲገመገሙ ማድረግ፣* ለሰብአዊ መብቶች ለመሟገት በሙያ የተደገፈ የህግ ወይም ሌላ ምክር ወይም እገዛ ለማድረግ መጠየቅና ማቅረብ፣*ከብሄራዊ ህግና ከዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ግዴታዎች ጋር መጣጣሙን ለማረጋገጥ በችሎት እየተገኙ የፍርድ ስርዐትንና የአደባባይሙግቶችን መገምገም፣*መንግስታዊ ከሆኑና ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር ያልተገደብ መስመርና ግንኙነት መዘርጋት፣*ከሚሰጠው አጥጋቢ ካሳ መጠቀም፤*ወደህጋዊ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ስራና ሙያ እንቅስቃሴ፤*በመንግስት ድርጊት ወይም ያለማድረግ ለሚደርሱ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች የብሄራዊ ህጉን በሚገባ ተጠቅሞ በሰላማዊ መንገድ አጸፋማድረግና መቃወም፣*የሰብአዊ መብቶችን ለመጠበቅ አላማ እንዲውል መንቀሳቀሻ መማጸን፣መቀበልና መጠቀም(ከውጭ አገር ገንዘብ መቀበልን ጨምሮ)ሠ/ሌሎች አስተያዬቶችአባል መንግስታት በድንጋጌዎቹ ላይ ለመስማማት ከወሰደባቸው ጊዜ አንጻርና አንዳንድ አንቀጾች የተሟጋቾችን መብት ይገድባሉከሚል አንጻር በአንዳንዶች አዋጁ አጥጋቢ ውጤት እንዳልሰጠ ተደርጎ ይታያል::3

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!