12.07.2015 Views

ስለሰብአዊ መብቶች መሟገት - East and Horn of Africa Human Rights ...

ስለሰብአዊ መብቶች መሟገት - East and Horn of Africa Human Rights ...

ስለሰብአዊ መብቶች መሟገት - East and Horn of Africa Human Rights ...

SHOW MORE
SHOW LESS
  • No tags were found...

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

የም/አ/ቀ/ሰ/መ/ተ/ፕ (EHAHRDP)ሰቆቃ እና የተቀነባበረ የሃይል ተግባርሰቆቃና የሃይል ተግባር እንዲያው ዝም ብሎ “የሚሆን”ነገር አይደለም።ኢምክንያታዊ፣ሁካታማና እብደት የተሞላባቸው የወፌፌ ሰዎችተግባር አይደሉም።በደንብ የታቀዱ ምክንያታዊ የሆኑ የማህበረሰብየቁጥጥር ስልቶች ናቸው።የማሰቃያ ቴክኒኮች እና የተቀነባበሩ የሃይል ጥቃቶች ታሪክ ያላቸውና የሚማሯቸው ናቸው።የተለያዩ አገሮችየሚመርጧቸው መንገዶችና ክህነቶች አሏቸው።በግል የሚፈጽሙቱ የሃይል ጥቃቱን ሆነ ብለው ለግለሰቡ በሚስማማ መልክ ለክተውይፈጽሙታል።አንዱ ሰው ሰቆቃ እና የሀይል ጥቃትን በግለሰብ ደረጃ ሊቀበል ቢችልም ዋናው ተደራሲ ግን ግዙፉ ማህበረሰብ ነው።ጠቅላላ አላማው ግለሰቡን በአካል፣በስነልቦናና በመንፈስ በማጥፋት የእሱን ወይም የእሷን ግዙፍ ማህበረሰብ ማስፈራራት፣ማሸማቃቅ እና ማፈን ነው።በአብዛኛው የማህበረሰብ መሪዎች የመጀመሪያ የጥቃት ኢላማ የሚሆኑት በአጋጣሚ በሚደርስ አደጋ አይደለም።የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችም ተነጥለው የሚታለምባቸውም ሊያስደንቅ አይገባም።አንድ የማህበረሰብ ጠንካራ መሪ ሲወሰድና ያለምንም ግንኙነት ሲያዝ እንዲሁም ማንም የሆነውን ሳያውቅ ሲቀርና ለማን አቤት እንደሚባል ሲጠፋ ከዚያ እሱ ወይም እሷ በህይወት ተርፈው ግን ተጎድተው ተጠባብሰው እና ተሰቃይተው ሲመለሱ ለተቀረው የማህበረሰቡ አባል እንዳይታገል፣እንዳይናገር ወይም ፍትህና ርትዕ እንዳይጠይቅ ጠንካራ መልዕክት ያስተላልፋል።በጣም ስኬታም የመጨቆኛ መሳሪያ ሊሆን ይችላል።ሰዎች መታገል፣መጮህና ግፍን ማውገዝ መቀጠላቸው ራሱ ለጀግንነታቸው እና ለቁርጠኝነታቸው ምስክር ነው።ግን በአብዛኛው ከፍተኛ ዋጋ እንደሚከፍሉ ማንም ሊክድ አይችልም።ክፍል 1ሰቆቃ፣የተቀነባበረ የሃይል ተግባር እና ጤንነትየካናዳዊያን የሰቆቃ ሰለባዎች ማዕከል ልምድ(ካ/ሰ/ሰ/ማ)ካ/ሰ/ሰ/ማ ከተቋቋመበት 1969 ጀምሮ ሰቆቃ እና ጦርነት በጤንነትላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ በአዋቂዎችም ልጆችም ላይ ጭምር ለይቶ አስቀምጧል።ለአጭርና ለረጅም ጊዜ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ በርካታየማሰቃያና የተቀነባበረ የሀይል ጥቃቶች አሉ።አካላዊ• ስቃይ፣የሚያልፍ እና የሚበረታ• የተሰበሩ አጥንቶች እና የመጋጠሚያ ስቃይ• ውሃ መቋጠር ሰምበር ማውጣት• የተጎዳ ጥርስ እና ድድ• የልብ ሁከት• መኮላሸት እና መምከን• ስንፈተ ወሲብ• የአንጀት መታወክ• መስማት አለመቻል• የውስጥ ደዌ• የማህጸን መዛባት• የመዘውር መታወክ• የጀርባ ህመም እና የአከርካሪ መጎዳት• ጠባሳ ማውጣት• የደም ግፊት• የፊኛና የሽንት ቧንቧ መታወክ• የተቆረጠ የሰውነት አካል• ሽባነትና ወይም አካል በድን መሆን• የወሲብ መዛባት• ራስ ምታትስነልቦናዊ• ድብርት• የጥፋተኝነት ስሜት የመትረፍ የጥፋተኝነት ስሜትን ጨምሮ• ስጋት እና መጠራጠር• ፍርሃት• የእንቅልፍ መዛባት እንቅልፍ ማጣትና ቅዠትን ጨምሮጉዳት በማስታወስ ችሎታ ላይ፣የማስታወስ ችሎታ ማጣት• ከሚገባው በላይ ሆደባሻ መሆን• የማተኮር ችግር• ባለሥልጣኖችን መፍራት/መሸማቀቅ• መነጫነጭ• ድንገት በሽብር ስሜት መወረር• የራስ መግደል ስሜት እና ራስን የመግደል ሙከራ• መሸበር• ብልጭ የሚሉ ትውስታዎች እና ጣልቃ የሚገቡ ሃሳቦች• የወደፊቱን አሳጥሮ የማየት ግምት• የጥልቅ ስሜቶች የመንሸራሸር ችሎታ መቀነስ• ለህይወት እና ሊያስገኘው ስለሚችለው ያለ ግምት መቀነስ• ለልጆች፣ለዘመዶች እና ለጓደኞች አለቅጥ መጨነቅ• ለራስ ያለግምት መቀነስ• ወደ ውስጥ መቀበር• መታከት• አጠቃላይ ፍርሃት• ሃዘን እና ፀፀት18

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!