12.07.2015 Views

ስለሰብአዊ መብቶች መሟገት - East and Horn of Africa Human Rights ...

ስለሰብአዊ መብቶች መሟገት - East and Horn of Africa Human Rights ...

ስለሰብአዊ መብቶች መሟገት - East and Horn of Africa Human Rights ...

SHOW MORE
SHOW LESS
  • No tags were found...

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

የም/አ/ቀ/ሰ/መ/ተ/ፕ (EHAHRDP)ምዕራፍ4ለሰብአዊ መብቶች የምክክር ዘመቻዎችየዘመቻ ስልቶች፣ ማሳለጦች እና የምክክር ስራዎች በሰብአዊ መብት ተሟጋቾች የሌሎችን መብት ለማስከበር እንደመሳሪያ ሊያገለግሉ ይችላሉ።ሰዎች በገቡት ውለታ መሰረት ወይም ተግባራቸውንና ግዴታቸውን እንዲወጡ በማድረግ ዘመቻ በጎ ለውጥ ለማምጣት ያልማል።በሆነ ጉዳይ ላይም ሰፋ ያለ ግንዛቤ ለማስጨበጥም ሊውል ይችላል።ይህ ጽሁፍ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የተለያዬ ቅድመታሪክ ባላቸው ድርጅቶች ላይ የዘመቻ ስልት እንዴት ተቀርጾ ስራ ላይ እንደሚውል መሰረታዊ ዳሰሳ ለማድረግ ይሞክራል።ለሰብአዊ መብት ጉዳይ መዝመት የሰብአዊ መብት ረገጣ እንዲቆም ለማድረግና መብታቸው ለተገፈፈባቸውም ፍትህ ለማስገኘትየሚሞከርበት መሰረታዊ መንገድ ነው።ግለሰቦችና ማህበረሰቦች ለራሳቸው መብት ሊቆሙ ይችላሉ (የቅርብ ጊዜ የዜጎችን እንቅስቃሴ ይመልከቱ) ወይም ሌሎች ስለእነሱ ሊዘምቱላቸው ይችላሉ በተለይም ቡድኖቹ ስለራሳቸው መብት ያላቸው ግንዛቤ ወይምተጽዕኖ የማሳደር አቅማቸው አነስተኛ ከሆነ።በተ/መ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች አዋጅ አንቀጽ 1 መሰረት “ሁሉም ሰው በግል ወይም ከሌሎች ጋር በማበር የሰብአዊ መብቶችና መሰረታዊ ነጻነቶች በብሄራዊ በቀጠናና ዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲበረታቱ፣እንዲጠበቁና እውቅና እንዲያገኙ የመጣር መብት”አለው። ባጭሩ ማንኛውም ሰው ለራሱም ሆነ ለሌላ ሰው መብት የመዝመት መብት አለው።ዘመቻን ማቀድየተሳከ ዘመቻ ለማድረግ ልታመጣ ባሰብከው ለውጥ አንጻር ግቦች መቀመጥ አለባቸው።እነዚህ ግቦች ግልጽ የተደረጉ፣ሊለኩ የሚችሉ፣ሊደረስባቸው የሚቻል፣ተጨባጭና በጊዜ የተከለሉ መሆን አለባቸው።ግቦችህ ምን ያህል ተገልጸው የተቀመጡና ሊለኩ የሚቻሉ መሆናቸውን ለማወቅ ከዘመቻው በኋላ ምን ይለወጣል ብለህ ተስፋ እንደምታደርግና እንደምትጠብቅ ራስህን ጠይቅ።ሁለተኛ የዘመቻ ስልትህን በመረጃ ለመደገፍ ምርምር መካሄድ አለበት።በሚመለከተው ጉዳይ ላይ የተሟላ መረጃ ብቻ ነው ስኬታማ ስልት እንዲዳብር የሚፈቅደው።ልትረዳውና መፍትሄ ልታመጣለት የምትሞክረውን ችግር ለምሳሌ ለመብት ረገጣው ማን ሃላፊ እንደሆነ ወይም ለምን እንደሆነ ለመተንተን ያስችለሃል።ስትመራመር ለማስተላለፍ የምንሞክረው መልዕክት ምንድነው ምንስማየት እንፈልጋለን የሚሉትን መመለስ መቻል አለብህ።ይህን ለውጥ ለምን ማየት እንፈልጋለን?ማንንስ ነው ኢላማ ያደረግነው---እነማናቸው በጉዳዩ ላይ ድርሻ ያላቸውና ባላቸው ሃላፊነት ተጽዕኖ ማሳደር የሚችሉ?እንዴትስ እንሰረዋለን ምንስ መንገድ እንጠቀማለን?በመረጃ መረብ፣በስልክ፣በገለጻ፣በክርክር፣ሰላማዊ ሰልፍ፣ኤግዚቢሽን ወይስ አቤቱታ በማዘጋጀት?ጥረቶቻችንን ወዴት እናነጣጥራለን?በክልል፣በብሄራዊ ወይስ በአለማቀፍ ደረጃ? እና በመጨረሻ ዘመቻውስ የት ይካሄዳል? በዘመቻ ጉዳዮች ላይ ሲመራመሩ ግቡን ይበልጥ የሚያሳኩትንና19ዋናው ጽሁፍ በካሮል ማጋምቦ ተዘጋጅቶ በራሄል ኒኮልሰን የተጣጣመ።ስለማህበራዊ መገናኛ (ምዕራፍ4.5) በኒዬል ብላዜቪች20የአዋጁ ሙሉ ስም፤ግለሰቦች፣ቡድኖች እና የህብረተሰብ መዋቅሮች በአለማቀፍ ደረጃ የታወቁ ሰብአዊ መብቶችንና መሰረታዊ ነፃነቶችን ስለማራመድና ለመጠበቅ ስላላቸው መብት እና ኃላፊነት የወጣ አዋጅ።በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ቢሮ በኩል አዋጁን ለማግኘት ይቻላል።26

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!