12.07.2015 Views

ስለሰብአዊ መብቶች መሟገት - East and Horn of Africa Human Rights ...

ስለሰብአዊ መብቶች መሟገት - East and Horn of Africa Human Rights ...

ስለሰብአዊ መብቶች መሟገት - East and Horn of Africa Human Rights ...

SHOW MORE
SHOW LESS
  • No tags were found...

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

የም/አ/ቀ/ሰ/መ/ተ/ፕ (EHAHRDP)ምዕራፍ4.5ማኀበራዊ መገናኛ ብዙኅን ለሰብዓዊ መብቶችየማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ዘመቻ ለማድረጊያየሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ከማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ጋር ራሳቸውን ማቀራረብና ለዘመቻ ግቦች ግልጋሎት እንዴት እንደሚውሉ ስልት መቀየስ አለባቸው።የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በሰብአዊ መብት ዘመቻ አፈጻጸም ላይጊዜና የሃብት ምንጭ ለማደላደል በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ለማድረግ እንዲያስችላቸው በተመሳሳይ ጊዜ የአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ጠቀሜታ መጤን አለበት። በተፈጥሯቸው አብዛኞቹ ዘመቻዎች ህዝባዊ ናቸው።ይሁንና በሆነ ምክንያት ዘመቻህ ከግል መረጃ ጋር የተያያዘ ከሆነና የሚያነጣጥረውም በግል ማህበረሰብ ላይ ብቻ ከሆነ የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን አጠቃቀምህን በድጋሚ ልታስብበት ይገባል።አብዛኞቹ የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ንብረቶች በህዝባዊ መናኸሪያ ይቀመጣሉ።እናም የምታስተላልፈውን መልዕክት ምስጢርነት የሚጠብቁት ደንቦች በቀላሉ ሊዘለሉ ይችላሉ።የተለየያዩ የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ገጾች ግንኙነትን የግል ለማድረግ የተለያየ ዘዴ የሚጠቀሙ ሲሆን እነዚህንም በየራሳቸው እርባና መረዳት ያስፈልጋል።ከግል ምስጢርነትና ደህንነት እሳቤ ባሻገር ስኬታማ የመሆኑ ጥያቄ አለ።በደንብ ተከሽኖ በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን የሚተላለፍ መልዕክት ይፋ ደብዳቤን፣ለሰብአዊ መብት መዋቅሮች የሚቀርቡ አቤቱታዎችን ወይም ሃላፊነቱን ከተሸከመው ባለድርሻ ጋር የሚደረጉትን ስብሰባዎች አይተካም።አንዳንድ የዘመቻ ግቦች በተሻለ መንገድ የሚመቱት በባህላዊ የምክክር ዘዴ ነው።የማህበራዊ የመገናኛ ብዙሃን ምንድን ነው?የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን የተጀመረው ሰዎች ከጓደኞቻቸውና ቤተሰቦቻቸው ጋር በድህረገጽ በኩል እየተገናኙ እርስ በራሳቸው የግል መልዕክት መለዋወጥ ሲጀምሩ ነው።እነዚህ የማህበራዊ የመገናኛ መረቦች ዝናቸው እየጨመረ በሄደ ቁጥር ይዘትያላቸው መልዕክት ማከፋፈያ መረብም ሆኑ።የሆነ ይዘት ያለው ነገር በተለይ ዝነኛ ሲሆን ከሰው ወደሰው በማህበራዊ መገናኛ በኩል ሁሉ እየተላለፈ የተደራሲውን ቁጥር ያበዛል።እንዲህ ሲሆን ይዘቱ እንደ ‘ቫይረስ’ ተሰራጨ ይባላል።ይህ በባህላዊ እና በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን መካከል ያለውን ልዩነት ይቀሰቅሳል።የአታሚዎች ውሳኔ የመስጠትንና የተደራሲያንን ነገር ይመለከታል።በባህላዊ የመገናኛ ብዙሃን ጉዳይ የተደራጁ የመገናኛ ብዙሃን ቤቶች ምን መባል እንዳለበት፣ከማን አንጻር መባልእንዳለበት፣እና ምን አቋም መራመድ እንዳለበት በማዕከላዊ የህትመት ቁጥጥር ይወስናሉ።የመገናኛ ብዙሃን ቤቶች የቱ ታሪክመዘገብ እና መዘገብ እንደሌለበት ብቻ ሳይሆን የሚወስኑት ከጠቅላላው መልዕክት አንባቢው እንዲያድርበት የሚፈልጉትን ስሜት ይመርጣሉ።የቱ ታሪክ የ ‘ግምባር ዜና’ የቱ ደግሞ በጋዜጣው የውስጥ ገጾች መቀበር እንዳለበትም ይወስናሉ።23በኒል ብላዜቪች ተፃፈ30

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!