12.07.2015 Views

ስለሰብአዊ መብቶች መሟገት - East and Horn of Africa Human Rights ...

ስለሰብአዊ መብቶች መሟገት - East and Horn of Africa Human Rights ...

ስለሰብአዊ መብቶች መሟገት - East and Horn of Africa Human Rights ...

SHOW MORE
SHOW LESS
  • No tags were found...

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

የም/አ/ቀ/ሰ/መ/ተ/ፕ (EHAHRDP)የዘመቻ መገናኛ እቅድ/መሳሪያዎችየተለያዩ ዘመቻ ማድረጊያ መሳሪዎች አሉ።ባለው መረጃና የሃብትምንጭ ተጠቅሞ ለተያዘው ስራ እንዴት ትክክለኛውን መሳሪያ መጠቀም እንደሚቻል ማወቅ መሰረታዊ ነው።አንዱ መሳሪያ ደብዳቤመጻፍ ነው።ደብዳቤዎች የመብት ረገጣን በተመለከተ ለተለዩ ተደራሲያን ችግሩን በግልጽ በማስቀመጥና ለውጥ ለማምጣት ምን መደረግ እንዳለበት ተጽፈው ይላካሉ።ለመጻፍ ቀላል፣የግልና የመንግስት ቢሮክራሲ የሚሰጠውን ጥቅም (አንዴ በአድራሻ ከተላከ በቀጥታ ለተላከለት ባለስልጣን ስለሚደርሱ ነገ ተመለስን ይከላከላሉ)።ይሁንና የቴምብር ዋጋ እና መሃይምነት ከፍተኛ በሆነባቸው ማህበረሰቦች ውስጥ ውሱንነት ስላላቸው ደጋፊዎችን ሊያሳጡ ይችላሉ።ማሳለጥ ሃሳብንን መረጃን በውሳኔ ሰጪዎች ላይ ተጽዕኖ በሚያሳድር መልክ በማቅረብ አንተ የምትፈልገው እርምጃ እንዲወሰድ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ያጠቃልላል።ይህ ማለት አብዛኛውን ጊዜህግና ፖሊሲ የሚያወጡ ባለስልጣኖችን ማግኘት፣ፍላጎትንና አመለካከትን ማስተላለፍ፣የተቃራኒ ወገንን ክርክር መጋተር እና ለያዙትአቋም ሰፊ ድጋፍ መኖሩን ማሳየት ማለት ነው።አቤቱታ የፈራሚዎችን ዝርዝር የያዘ ይፋ መግለጫ እንዲሰጥበትወይም እርምጃ እንዲወሰድ የሚጠይቅ በደንቡ መሰረት ተጽፎ ለባለስልጣን የሚቀርብ ደብዳቤ ነው።ብዙውን ጊዜ ርካሽና ለማቀነባበር ቀላል የሆኑ የህዝብንም የስጋት ደረጃ የሚያሳዩ እና በቀላሉ ህዝብ ድጋፉን የሚገልጽባቸው መንገዶች ናቸው።መገናኛ ብዙሃን ለስኬታማ ዘመቻ አብዛኛውን ጊዜ ቁልፍ ነው።መገናኛ ብዙሃንን ስላቀድከው ዝግጅት ወይም እርምጃ እና መቼና የት እንደሚከናወን በኢሜል ወይም በጋዜጣዊ መግለጫ ማሳወቅ የመጀመሪያው መንገድ ነው።ለጋዜጣ የፊት ገጽ የሚጥም ርዕስ ስጠው።የምትታይና ለዜና የሚሆን ነገር የመፍጠር ችሎታ ይኑርህ።ሰዎች በመገናኛ ብዙሃን ጋር እንዴት እንደሚናገሩ ስልጠና ስጣቸው።ዘመቻውን በሚጎዳ መልኩ የተለያዩ ሰዎች የተለያየ አስተያዬት የሚሰጡበትን ለማስወገድ ከመገናኛ ብዙሃን ጋር የሚነጋገር ስለዘመቻው የሚያብራራ ቃል አቀባይ ይኑርህ።ሌላው መገናኛ ብዙሃንን የመጠቀሚያው መንገድ የንግግር ጉብኝቶችን ማድረግ ነው።ለምሳሌ ከሰብአዊ መብት ረገጣ የተረፈ ወይም የሰብአዊ መብት ተሟጋች ልምዱን/ልምዷን እና ያጋጠመውን/ያጋጠማትን ፈተና የሚገልጹበትን ሊጨምር ይችላል።የጉብኝት ንግግሮች በተለምዶ የተመረጡ አዳማጮችን ለምሳሌ የህግ ባለሙያዎችን፣የፓርላማ አባላትንወይም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ ያነጣጥራሉ።ይህ በራሱ የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ስለሚስብ መልዕክቱን ወደ ሰፊው ተደራሲ ለማስተላለፍ ያስችላል።እንዲህ ያለውን መሳሪያ ለዘመቻ ሲጠቀሙበየትኛው ተደራሲ ላይ እንደሚያነጣጥሩ፣መልዕክቱን እንዴት እንደሚቀምሙ እና የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እንዴት እንደሚሰሩ የመሳሰሉ አይነት በርካታ ነገሮችን መመዘን ያስፈልጋል።ለምሳሌ በወጣቶች ዙሪያ የሚሰሩና ወጣት አዳማጮች ጋር የሚደርሱ ራዲዮ ጣቢያዎች አሉ።እነሱን መጠቀም ማለት ኢላማ ያደረገው ቡድን ወጣቱይሆናል ማለት ነው።ኢላማ ላደረገው ቡድን ፍላጎት በሚሰሩት የመገናኛ ብዙሃን ምንጮች ላይም ጥናት ማድረግና የሚመለከታቸውን ጋዜጠኞች አድራሻም መያዝ አለብህ።ህዝባዊ ዝግጅቶች እንደ ሰላማዊ ሰልፍ የድጋፍ ሰልፍ እና የአደባባይ ንግግሮች በተለይም ህዝብን ለማንቀሳቀስና የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ለመሳብ እጅግ ስኬታማ መሳሪያ ናቸው።ይሁንና ህዝቡን ለማሳወቅና ተሳትፎውንም ለማሳካት በመገናኛ ብዙሃን ብዙ መሰራት አለበት።የታዋቂ ሰው ድጋፍ ለጉዳዩ ተአማኒነትና ገጽታ በህዝብ አመለካከት ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር የሚችል ዝነኛ ሰውን ድጋፍ ማግኘት ለዘመቻ ሌላው አይነተኛ መሳሪያ ነው።የመረጃ መረብን ተጠቅሞ በመስመር ላይ መረጃን መካፈልና ለሰፊ ተደራሲ መልዕክትን ማስተላለፍ ከቅርብ አመታት ወዲህ ስር እየሰደደ መጥቷል።ደጋፊዎች በአፋጣኝ እርምጃ እንዲወስዱ ለማድረግና ለተመረጡ ዘመቻዎች ሰፊ ድጋፍ ለማግኘት እንደ አቫዝ የመሳሰሉ በመስመር ላይ የአቤቱታ ማቅረቢያ ገጾች አጥጋቢ በሆነ መልኩ ግልጋሎት ላይ ውለዋል።ይሁንና ይህ ጽሁፍ አዲስና በፍጥነት በማደግለዘመቻ ቅርብ ስለሆነው የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ሳያወራ ቢቀርፍጹም አይሆንም።(ጥልቀት ላለው ውይይት በዚህ ምዕራፍ መጨረሻ በምዕራፍ 4-5 ሳጥን ውስጥ ስለማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ይመልከቱ)።የባህላዊ መገናኛ ብዙሃንን ቀፍድዶ በያዛቸው ማነቆዎች ሳይነካ የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን በተወሰነ ክልል ያልታሰረን ተደራሲ ለማዳረስ ይችላል።የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን መረጃ ለመካፈል በተለይም የባህላዊው መገናኛ ብዙሃን ለዜናነት አይበቃም ብሎ ሽፋን የማይሰጠውን ሁሉ ለማስተላለፍ እድል ይሰጣል።አስተያዬትን በመለጠፍ ሙሉ ታሪክ ለማስተላለፍና መጋቢ አስተያዬትን በመቀበል ከሌሎች ጋር ውይይትን ለመክፈት እድል ይሰጣል።የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ስርጭትና ቅጽበታዊ ተፈጥሮው በህትመት የጊዜ ሰሌዳና የማሰራጫ አሸንዳ አለመወሰኑ ከፍጥነት ጋር በሚለዋወጡ ጉዳዮች ላይ እጅግ ተመራጭ መሳሪያ አድርጎታል።እንዴት በተሳከ መልኩ ስራ ላይእንደዋለ የሰሜን አፍሪካና የመካከለኛ ምስራቅ መነሳሳቶች የቅርብ ጊዜ ምሳሌ ነው።በእነዚህ አገሮች ምን እየተካሄደ እንደሆነ ለአለም ለመንገር ቪዲዮ፣ቲዊቶችና ፌስቡክ ገጾች ላይ ተለጥፏል።የመረጃ መረብን ወይም አንዳች አይነት የማህበራዊ መገናኛን ሲጠቀሙ የመስመር ላይ ደህንነትን ከግምት ውስጥ ማስገባት ያሻል። እነዚህ መሳሪያዎችም ውስንነት አላቸው በተለይም ከቅርብነት አንጻር።ዘመቻ የሚያደርጉ ድረገጽ ለመፍጠር ብቃት እና ቁሳቁስ ያስፈልጋቸዋል።ደግሞም ሁሉ ሰው ለመረጃ መረብ ቅርብ አይደለም።የድረገጽን ስኬት ለመገምገምም አስቸጋሪ ነው።በተጨባጭ የዘመቻ መልዕክትን ለማስተላለፍ የተለያዩ መሳሪዎችን መጠቀም ይመከራል።ለምሳሌ አንዳንዶች አቤቱታ በመፈረም ሲረኩ ሌሎች ደግሞ በሰላማዊ ሰልፍ በመካፈል አቋማቸውን መግለጽ ይፈልጋሉ።ይህ ልዩ ልዩ ተሳትፎን ያበረታታል።የዘመቻ መፈክር ማንገብም ጥሩ ሃሳብ ነው።ምክንያቱም መፈክሩን በየጊዜው ከተጠቀምክበት ዘመቻህ ከመፈክሩ ጋር ይቆራኛል።ከላይ ከተጠቀሱት የዘመቻ መሳሪያዎች በአንዱ ሲጠቀሙ መልዕክትን በትክክለኛው መንገድ ማስተላለፍ ለስኬት ቁልፍ ነው።ስለዘመቻህ ምንነትና ምን ልታሳካ እንደፈልግህ መልዕክትህን ሰዎች በግልጽ ሊረዱበት በሚችሉበት መንገድ ማቅረብ አለብህ።ልታስተላልፍ ያቀድከው28

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!