12.07.2015 Views

ስለሰብአዊ መብቶች መሟገት - East and Horn of Africa Human Rights ...

ስለሰብአዊ መብቶች መሟገት - East and Horn of Africa Human Rights ...

ስለሰብአዊ መብቶች መሟገት - East and Horn of Africa Human Rights ...

SHOW MORE
SHOW LESS
  • No tags were found...

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

የም/አ/ቀ/ሰ/መ/ተ/ፕ (EHAHRDP)በሰው ሰቆቃ መሰቅዬትበሰው ሰቆቃ መሰቅዬት ምን ማለት ነው?ከድህረ ሰቆቃ ምስቅልቅል ጋር ተመሳሳይ ቢሆንም ቀለል ያለ ነው።እንደሚከተለውይመስላል።• ርህራሄ--የደንበኛውን አለኝታና ተስፋ ማጣት የራስ ጉዳይ ማድረግ• ለረጂ ሚና ከሚገባው በላይ ስሜት ማንጸባረቅ-ደንበኛውን ከሚገባው በላይ መንከባከብ-የደንበኛው ጥገኛ የሆነ ባህሪእና የረዳቱን ችሎታ የሚጠራጠር• ለራስ ህይወት የጥፋተኝነት ስሜት• የሙያ ድንበርን መጣስ• የረዳቱ አቅመቢስ የመሆን ስሜት• በሁኔታው ላይ ቁጥጥር ማጣትና አንድ ቦታ ተሰንቅሮመቅረትጨካኝ ኢሰብአዊ እና አዋራጅ የሆነ ሰብአዊ ግንኙነት የአንድን ሰው በሰብአዊ ፍጡር ላይ ያለን እምነት ሊደመስስና የሰብአዊ መብት ተሟጋቹንም ቁስል ሊጨምር ይችላል።የሰቆቃ ልምድን መጋፈጥ የራስን የሰቆቃ ልምድ ሊቀሰቅስ ይችላል--የረዳትነቱን ሚና ማን ይመርጣል?በሌላ ሰው ሰቆቃ መሰቅዬት ባለበት ቡድንውስጥ ሲሰሩ ጠርጣራ የሆነ ዝንባሌ በማብቀል (“ሁሉም ሊይዘኝ ያሳድደኛል” ወይም “እሱ ወይም እሷ የመንግስት ሰላይ ናቸው”)፣ አንዱን ወንጀለኛ ሌላውን ደካማ የቡድኑን አባል በመሰዋት የአጥቂ/ሰለባ ስሜት መልሶ ሊፈጥር ይችላል።ቡድኖችና ድርጅቶች በእንደዚህ አይነቱ ችግር የተነሳ በተለይም ለእንደዚህ አይነቱ ጉዳይ መፍትሄ የሚሰጥ ቀልጣፋ የሆነ ፖሊሲና አሰራር በሌለበት ለመፍረስ ተዳርገዋል።ነዶ ማለቅቃሉን እንደቀመመው እንደኒው ዮርኩ የስነልቦና ምሁር ዶ/ር ጄፍሩደንበርገር ከሆነ ነዶ ማለቅ ማለት የቆሙለት አላማ፣የተከተሉት መንገድ፣የያዙት ግንኙነት የሚጠበቀውን ውጤት ሳያመጣሲቀር የሚከሰት መታከት ወይም መበሳጨት ነው።ነዶ ማለቅ ከጥሩ አላማ የሚጸነስ ችግር ሲሆን ይህ የሚሆነውም ሰዎች ከእውነታው ጋር ያልተገናኘ ግብ በማንገብ ሃይላቸውን ሲያሟጥጡና ከራሳቸውና ከሌሎች ጋር ሲቆራረጡ ነው።የነዶ ማለቅ ምክንያቶች• ትልቅ/ፍጹም የስሜት ጫና• የተለዩ የሰብእና ባህሪያት (ሰብአዊነት፣ርህራሄ፣መረዳት) ከብስጭት ጋር ሲሟገቱ• ደንበኛን ማእከል ያደረገ ዝንባሌ-“በእውነታ መሸበር”• የግጭቶች ሚና፤ሴቶችና የነዶ ማለቆች-መጨነቅና የጥፋተኝነት ስሜት “ከልዩ እናትነት”ወይም “ከልዩ የቤት እመቤትነት”ጋር ሲሟገቱየነዶ ማለቅ ምጸት በፍጹም ጉጉት፣ አዲስ ጉልበትና ሃሳብ ተሞልቶ ስራውን ወይም ሁኔታውን በጀመረ ያው ሰውዬ ላይ መከሰቱ ነው።እንደዚህ አይነት ሰው በአብዛኛው ሊሳካ ስለሚችለው ነገር እጅግ ከፍተኛ ግምት አለው።ጊዜ ባለፈ መጠንና የታለሙት ሁሉ ሳይሳኩ ሲቀሩ ጉጉቱ ቀዝቅዞ እንደመታከት ያለ ነገር በቦታው ይተካል።ያለሙትን ግብ አሳንሶ ከእውነታው ጋር እንደመጣጣም ንዴትን በማመቅ ግለሰቡ ይበልጥ ይፋትራል።ከነዶ ማለቅ ጋር ሶስት ነገሮች ይያዛሉ፤• የሚና ግጭት፤እርስ በርስ የሚጋጩ ሃላፊነቶች ያሉበት ሰው በብዙ አቅጣጫ፡እንደሚጎተት ይሰማዋል።እናም ቅደምተከተልሳያወጣ ሁሉንም ባንድ ጊዜ ለመስራት ይሞክራል።ውጤቱ ከነዶ ማለቅ ጋር የተያያዘ መታከትና መድከም ይሆናል።• የሚና ግልጽ አለመሆን፤ግለሰቧ ምን እንደሚጠበቅባት አታውቅም።ጥሩ የሙያ ሰው መሆን እንደሚጠበቅባት ታውቃለች ግን እንደአርኣያ የምትከተለው ወይም መመሪያ ስሌላት እንዴት እንደምታሳከው እርግጠኛ አይደለችም።ውጤቱ የሚረባ ነገር እንደሰራችሆኖ በጭራሽ አይሰማትም።• የሚና ጫና፤ግለሰቡ እምቢ ማለት ስለማይችል እስኪነድድረስ ከሚችለው በላይ ሃላፊነት ይወስዳል።ምልክቶችአጀማመሩ ዝግ ያለ ነው።የመጀመሪያዎቹ ምልክቶች ስሜታዊነትና የአካል መድከምን ያካትታል።የመገለል ስሜት፣ጨለምተኝነት፣ትዕግስት ማጣት፣አሉታዊነት እና ስራንና ከስራው ጋር የተያያዙትን እስከመጥላት የሚያደርስ የመገንጠል ስሜት በግለሰቡ ላይ መታያት ይጀምራል።ፍጹም በከረሩ ጉዳዮች በአንድ ወቅት እጅግ ሲጨነቅለትከነበረው ፕሮጄክትና ቡድን ራሱን ከልሎ እስከነአካቴው ግድ ወደማጣት ይሄዳል።• የስሜት፣የአዕምሮ እና የአካል ድካም• የአቅም እና የተስፋ ማጣት ስሜት• የባዶነት ስሜት• አካላዊ ምልክቶች፤ራስ ምታት፣ድካም፣ከሚገባው በላይ መወጠር፣በአንገትና ትከሻ አካባቢ ህመም፣የጨጓራ በሽታ፣ክብደት መጨመር፣የበሽታ የመከላከል አቅም መቀነስ፣የእንቅልፍ መዛባት• የስሜት ምልክቶች፤መደበር፣አቅም ማጣት፣ተስፋ ማጣት(“ነፍሴ ሞቷል”)• የአዕምሮ ምልክቶች፤አሉታዊ ስሜት፣ግትርነትና ከሰዎች ግንኙነት መራቅ፣በርህራሄ ምትክ ጨለምተኝነት እንደማንኛውም የሰቆቃ ልምድ ሁኔታውን ለመቋቋም ሰዎች የመከላከያ ዘዴ ወደመቀየሱ ያዘነብላሉ።አንዳንዶቹ ከሌሎቹ ጤናማ ናቸው።ጤናማ ካልሆኑት መከላከያዎቹ ውስጥ፤መካድና ያለማመን፣መሳል፤ “መንግስት ጠላት ነው፣”ከሰለባው ወይም ከአጥቂው ጋር ራስን ማመሳሰል፣መሰንጠቅ፤ረዳቶችና/ጠላቶች፤ “ከእኛ ጋር ነህ ወይም ጠላታችን ነህ፣”እና ማቃለል፤ “ትንሽ ሰቆቃ ብቻ”--በሰል ያለው መከላከል መቀለድና ስሜትን መምራት (በምርታማ ወይም ፈጠራ ስራ ውስጥ በመጠመድ)።24

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!