12.07.2015 Views

ስለሰብአዊ መብቶች መሟገት - East and Horn of Africa Human Rights ...

ስለሰብአዊ መብቶች መሟገት - East and Horn of Africa Human Rights ...

ስለሰብአዊ መብቶች መሟገት - East and Horn of Africa Human Rights ...

SHOW MORE
SHOW LESS
  • No tags were found...

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

የም/አ/ቀ/ሰ/መ/ተ/ፕ (EHAHRDP)በአካል ላይ የደረሰ ጉዳት በመጨረሻ ሊድን ቢችልም (አንዳንዴ አይድንም) በስነልቦናና በመንፈስ ላይ የደረሰውን ለመቋቋም እጅግ ሊያስቸግር ይችላል።ማፈር፣የውርደት ስሜት፣ፍርሃትና መገለል በእንደዚህ አይነቱ ሰቆቃ ዋና ንጥረ ነገሮች ሲሆኑ እርዳታ ለመጠየቅም ለሰውዬው እጅግ አስቸጋሪ ሊሆንበት ይችላል።ይሁንና ሰቆቃን ጦርነትንና የሰብአዊ መብት ግፍን ለመቋቋም ግለሰቡ ላይ ብቻ ማተኮር አይበቃም።ሰዎች የሚኖሩት በቤተሰብ፣በማህበረሰብ፣በማህበራዊ፣ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ መዋቅር እንደመሆኑ የአንዳቸው መነካት በሌላው ላይ ተጽ ዕኖ አለው።የኑሮ ጥራት በብዙ ነገሮች የሚለካ ሲሆን ጤንነት አንዱ ዋና ቁምነገር ነው።ጤንነት ራሱ ውስብስብ ጽንሰሃሳብ ነው።የምናወራው ስለአካላዊ፣ስነልቦናዊ ወይም መንፈሳዊ ጤንነት ነው?እንዴትስ አንዳቸው ካንዳቸው ጋር ይገናኛሉ?አንዱ ከሌላኛው የላቀ ነው? ሰቆቃ የደረሰበት ሰው የሆነ የአካል እና የስነልቦና እርዳታ ሊፈልግ ይችላል።ግን ወደዶክተር ጋር ሄዶ በፕላስተር ብቻ ተለጥፎ መምጣት በቂ ነው?ወደቤት ከተመለስክ በኋላ ምን ይሆናል?ራሳቸው ፈርተውና ተሸማቀው ሊሆኑ ከሚችሉት ጎረቤቶችህና ጓደኞችህ ጋር እንዴት ትነጋገራለህ?ስለተወሰኑ ነገሮች ላለመናገር የባህልማነቆ ወዳለበትና በማያባራ የሃይል ተግባርና ግፍ ወደሚጠበሰው ማህበረሰብ ብትመለስ ምን ይሆናል?ጤናማ ባልሆነ አካባቢ ጤናማ ልትሆን ትችላለህ?ሰዎች የሚኖሩበት የኢኮኖሚና የማህበራዊ ሁኔታ ጤናን የሚወስኑየማህበረሰብ ጤና መመዘኛዎች ናቸው።የሃይል ተግባር በማህበረሰብ ውስጥ የጤና መመዘኛ ሆኖ በአግባቡ እንዲጨመር በመስኩ በተሰማሩ ጠበብት መካከል የሚከተሉትን በመጨመር ውይይት እየተካሄደ ነበር።• የገቢ እኩል አለመሆን• ማህበራዊ መደብለቅ እና መገለል• መቀጠር እና የስራ ዋስትና• የስራ ሁኔታዎች• የማህበራዊ ኢኮኖሚ አስተዋጽኦ• በማለዳ የልጅነት እንክብካቤ• ትምህርት• የምግብ ዋስትና• መጠለያሰቆቃ የሚያስከትለውን ውጤት ለመቋቋም ማህበራዊና አካላዊ ሁኔታዎችን ብቻ መጥቀስ በቂ እንዳልሆነ ግልጽ ነው።የሚያስከትለውን ጉዳት መጠን ለማሳወቅ እና ጉዳዩን ለመመዘን መንገዶች ለመሻትም የሃይል ተግባር በተናጥል ተገልጾ መታየት አለበት።ከጦርነት የሃይል ተግባር የተረፉትንና ሰቆቃ የተፈጸመባቸውን ግለሰቦች፣ቤተሰቦችና ማህበረሰቦች ለመርዳት በሚያደርገው ጥረት ኢግናሲዮ ማርቲን ባሮ ስለሰቆቃና ውድመት የገለጸውን የስነልቦናና ማህበራዊ ጽንሰሃሳብ ካ/ሰ/ሰ/ማ እንደመዋቅር ይጠቀማል።ማርቲን ባሮ በ1970ዎቹ በኤልሳልቫዶር ይሰራ የነበረ የስፓኝ የካቶሊክ ቄስና የስነልቦና አዋቂ ነበረ።ስራዎቹ በሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ማተሚያ ቤት ታትመዋል።በሃርቫርድ የሚገኙ የስራ ባልደረቦቹ ስራውን ለመተርጎም ሲቀርቡት “በእናንተ አለም ታተም ወይም ተፈጠም ነው።በእኔ ግን ታተም እና ተፈጠም ነው”ሲል መልሷል።በእርግጥም በ1981 በነፍሰገዳይ ቡድን በተደረገ ፍጅት በመስክ ስራ ላይ እንዳለ ከሌሎች ቄሶችና ምሁራን እንዲሁም የቤት ሰራተኛው ከነልጇ ጋር ተረሽኗል። “የሰቆቃ ባህል”እንዴት እንደሚሰፍን ንድፈሃሳቡ ገለጻ አድርጓል።ንድፈሃሳቡ የካ/ሰ/ሰ/ማከሰቆቃ ለተረፉ አገልግሎት የሚሰጥበትን ሞዴል መሰረተሃሳብ ጭምር አስቀምጧል።አገልግሎትን ከሰቆቃ የተረፉትን የተለያየ ፍላጎትከማሟላት ጋር በማጣመር አገልግሎት የሚሰጥ ሁለንተናዊ ሞዴል ነው።የ “ቤት ውስጥ” አገልግሎትን ጨምሮ ለካ/ሰ/ሰ/ማ ደንበኞች አገልግሎት ከሚሰጡ ወይም ከሌሎች የደንበኞቹን ፍላጎት ከሚያሟሉጋር የሚያገናኙ ግዙፍ (ውስብስብ) ግለሰቦችና ድርጅቶች ጋር ያለውን ጥምረትም ጭምር ያጠቃልላልእንደማርቲን ባሮ ሶስት አይነት የስነልቦናማህበራዊ ሰቆቃዎች አሉ።1.ምንም እንኳ ግለሰቡ ዋናው የተቀነባበረ የሃይል ጥቃቱ ሰለባ ቢሆንም የሰቆቃው ተፈጥሮ በማህበረሰቡ ምንጭ ላይ ይወድቃል።ሰቆቃና የተቀነባበረ የሃይል ጥቃት በመሰረቱ የማህበረሰብ ችግር እንጂ ተነጥለው የቆሙ በግለሰቦች የሚፈጸሙ ድርጊቶች አይደሉም።ፈቃድ በበርካታ የተለያዩ ደረጃዎች በማግኘት እንደማህበራዊ የቁጥጥር መንገድ ይከሰታል።የድርጊቱ ፈጻሚ በቅርብ አለቃው ወይም አለቃዋ ሲፈቀድለት/ላት የቅርብ አለቅዬው ደግሞ በቅርብ አዛዡ ወይም አዛዧ እያለ የእዝ ሰንሰለቱ ወደላይ ይወጣል።ማህበረሰቡም በዝምታ ወይምየነገሩን መሆን ባለማመንና በመካድ ተባባሪ ሊሆን ይችላል።2.ሰቆቃ የማህበረሰብ ምርት እንደመሆኑ ግለሰብ ሰለባውም ሁኔታውን ያባባሰው ማህበራዊ ስርዓትም ህክምናና ፈውስ ያሻቸዋል።ግለሰቡን ማሸግ ብቻ አይበቃም።እሷ ወይም እሱ ሰቆቃ እንዲፈጸም ምክንያት ወደሆነበት ቦታ ተመልሰው የሚላኩ ከሆነ እንደገና ሌላ ሰቆቃ ሊከሰት ይችላል።ሰቆቃና የተቀነባበረ የሃይል ጥቃት የማህበረሰቡችግር ከሆነ መፍትሄውም ማህበራዊ መሆን አለበት።3.ሰቆቃውን ያመጡት መንሰኤዎች ሳይነኩ ከቀሩ ሰቆቃውም ስር ሊሰድ ይችላል።የስነልቦናማህበራዊ ሰቆቃ ግንዛቤ የተቀነባበረ የሃይል ጥቃት የ “ሰቆቃ ባህል”ማበብን ሁኔታም ሊፈጥር ይችላል። በተለይም፤*ማህበራዊ ልዩነትና እኩል አለመሆን ሲሰፍን፣*በተቋም ደረጃ መዋሸትና የዝምታ ክበቦች ማህበራዊ እውነታውን ሲያድበሰብሱ፣*የተቀነባበሩ የሃይል ጥቃቶችና ጦርነት ግለሰቦችን፣ቤተሰቦቻቸውናየግል ጥምረቶቻቸውን እንዲሁም አባል የሆኑበትን ማህበረሰብ ሲጎዱ ነው።መካድ ግለሰብ ቤተሰብና መላው ህብረተሰብ የሚጠቀምበት መከላከያ ዘዴ ነው።ማርቲን ባሮ የዝምታ ክበቦች ብሎ በሚጠራው የሚከተሉት መንገዶች ይሰራል።በግለሰብ ደረጃ ተራፊው፤*ልምዱን ያምቃል--እሱ ወይም እሷ ማስታወስ አይፈልጉም።*ስቃዩን ካስከተለው ሁነት ሌሎችን መጠበቅ ይፈልጋል--አስቀያሚከሆነው ልምድ ጋር ሌሎችን ማጋፈጥ አይፈልግም።*ሌሎች ይረዱኛል ወይም ያምኑኛል ብሎ አይጠብቅም-- አንዳንድጊዜ ሰዎች እርስ በራሳቸውእንዴት እንደሚጨካከኑ መረዳት ያስቸግራል።የሰቆቃ ታሪክ በአብዛኛው የተቀባቡና የማይታመኑይመስላሉ።በአብዛኛው በፈጻሚው በኩል ይህ ሆነ ተብሎ የሚደረገው ስለአሰቃቂው ነገር ማውራት አለመታመንን እንዲጋብዝ ነው።እንዲሁም በአንዳንድ ባህሎች ስለተወሰኑ ነገሮች ማውራትን የሚከለክል ማነቆ በተለይም የጾታንና የወሲብን ጥቃት በተመለከተ አለ።ሰለባውን ራሱን ለደረሰበት ነገር መውቀስ ያልተለመደ ብቻ ሳይሆን በአንዳንድ ጉዳዮች እንዲያውም እንዲገለል ወይም ለክብር ግድያ ኢላማእንዲሆን ይደረጋል።19

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!