12.07.2015 Views

ስለሰብአዊ መብቶች መሟገት - East and Horn of Africa Human Rights ...

ስለሰብአዊ መብቶች መሟገት - East and Horn of Africa Human Rights ...

ስለሰብአዊ መብቶች መሟገት - East and Horn of Africa Human Rights ...

SHOW MORE
SHOW LESS
  • No tags were found...

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

የም/አ/ቀ/ሰ/መ/ተ/ፕ (EHAHRDP)ለመጠበቅ እንዲሁም የክብ ጠረጴዛ ውይይት በጉዳዩ ላይለመክፈት ቀደም ሲል በ10ኛው ጉባኤ የተሰጡትን ውሳኔዎች በድጋሚ ማጠናከሩ ነው።የግብረሰዶማውያን ንቅናቄበአፍሪካ በህግ፣በፖለቲካ እና ማህበራዊ-ባህላዊ ተጻራሪ የሆነ ድባብ የተነሳ ተመስርተው የሚገኙ የግብረሰዶም ንቅናቄ ድርጅቶች በአንጻራዊነት እጅግ ጥቂት ናቸው።በምስራቅና አፍሪካ ቀንድ በርካታ አገሮች ግብረሰዶም ህገወጥ ስለተደረገ ለግብረሰዶማውያን መብት መቀስቀስ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ ህጎችን በመንተራስ እና/ወይም በመያዶች ምዝገባ ሂደት ጊዜ ህጋዊ እንዳይሆን ይደረጋል።ለድርጅት በርካታ አስተዳደራዊ ፍላጎት ምዝገባ ስለሚያስፈልግ አለመኖሩ ለተሟጋቾች ስራ እንቅፋት ይሆናል።ከእነዚህ መካከል ለቢሮ የሚሆን ቦታ መከራየት፣ደህንነቱ የተረጋገጠና አስተማማኝ የመስሪያ ቤት መሰረት ለመጣል፣ከለጋሾች ገንዘብ ለመቀበልና ለቁሳቁስ መግዢያ የባንክ ሂሳብ መክፈት ይገኙበታል።የወሲብ ቅኝታቸውን ወይም የጾታ ማንነታቸውን መሰረት ባደረገው መድልዎ የተነሳ ያላቸው ስልጠና በመገደቡ እና በዚህም የተነሳ ንቅናቄያቸውን ከመጀመሪያውኑ አስፈላጊ ላደረገው ስራና ድርጅት ለማስኬድ የሚያበቃ ክህሎት ግን ከተሟጋቾቹ ዘንድ ሁልጊዜ አይገኝም።የትኛውን ጉዳይ እናስቀድም ወይም የትኛውን ስልት እንከተል በሚል በግብረሰዶማውያን ተሟጋቾች መካከል የሚነሱ ውስጣዊ ክፍፍልና ግጭቶች የግብረሰዶማውያንን መብት ከፍ ለማድረግ ያላቸውን ቀልጣፋነት ያዳክመዋል። ስለዚህ የግብረሰዶማውያን ንቅናቄ አባላትን በግጭት አፈታትና ያላቸውን ጥረቶች በማስተባበር ስልታዊ እቅድ ነድፈው በተጠናከረ መልኩ ወቅታዊ የአናሳ ጾታዎችን ችግር እንዲያነሱ መደገፍ መሰረታዊ ነው።በንቅናቄው ከሚፈጠሩ ተጨማሪ ፈተናዎች ውስጥ እርስ በርስ አለመተማመን፣መከዳዳት፣በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መገለል በተነሳ ከሚመጣ ስልጣንን አላግባብ መጠቀም፣የእለት ኑሮን ከሰፊው ትግል እንዲያስቀድሙ የሚያስገድድ የእድሎች አለመኖር እና አሉታዊ ውጤት የሚያስከትል የለጋሾች ባህሪ ይገኙበታል።አብዛኛውን ጊዜ የኋለኛው የሚከሰተው በጀት በምን መልኩ እንደሚመደብ በቂ ምርምር ባለመደረጉ፣በግለሰቡ የስራ አመራር ችሎታ ያለፈ ታሪክ ላይ አጥጋቢ ያልሆነ ግምገማ እንዲሁም ከድርጅቱ አቅም ጋር በተያያዘ ተጨባጭ ያልሆነ ግምትና የሰነድ አያያዝምክንያት ነው።የንቅናቄውን እምቅ ሃይል በማጠናከር ግዙፍ የሆነውን ውጫዊ ፈተና ለመቋቋም ሲባል ሁሉንም ባለድርሻዎች ባካተተ ጥልቅ ውይይት ብቻ እነዚህን ጉዳዮች ማንሳት ይቻላል።ከተለመዱት የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ድጋፍ የማይገኝበትን ምክንያት በአፋኝ ህግ ስርዓትና ግብረሰዶማዊነትን ህገወጥ አድርጎ በፈረጀው የህዝብ አመለካከት መግለጽ ይቻላል።በዋናው ጅረት ውስጥ ያሉት የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች የአናሳ ጾታዎችን መብት በመደገፋቸው ከመንግስት ሊመጣ የሚችለውን አፈና ይፈራሉ።በተጨማሪም አብዛኛውንጊዜ ከድንቁርና የተነሳ የግብረሰዶማውያን መብት ተገቢ እናወሳኝ ተደርጎ አይታሰብም።ይህ ታዲያ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እንደተሟጋች እንዲታወቁበት የሚፈልጉትን (ለሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ተ/መ ባወጣው አዋጅ ላይ ያለውን መግቢያ ይመልከቱ) እና ሊቀበሉት የሚገባውን ህግ በግልጽ መጣስ ነው።በዚህ የተነሳ ከመጀመሪው የተሟጋቾቹ52ከላይ የተጠቀሰው አንቀጽ 2 “በ19ኛው የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ በከፍተኛ ኮሚሽነሩ በታዘዘው ጥናት ላይ የተደረሰበትን ግኝት መሰረት በማድረግ መድልዎ በሚያደርጉ ህጎችና ልማዶች እንዲሁም የወሲብ ቅኝትንና የጾታ ማንነትን መሰረት አድርገው በግለሰቦች ላይ በሚፈጸሙ ጥቃቶች ላይ ገንቢ፣በመረጃ የተመሰረተና ግልጽ የጠረጴዛ ውይይት ለማድረግ ተወሰነ።53አጣዳፊ የድጎማ እርምጃ ለሴቶች የሰብአዊ መብቶች (1997) የግብረሰዶማውያን በምስራቅ አፍሪካ መደራጀት፤የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እውነተኛፈተና።www.urgentactionfund.org/documents/UAF-LGBTI REPORT44

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!