12.07.2015 Views

ስለሰብአዊ መብቶች መሟገት - East and Horn of Africa Human Rights ...

ስለሰብአዊ መብቶች መሟገት - East and Horn of Africa Human Rights ...

ስለሰብአዊ መብቶች መሟገት - East and Horn of Africa Human Rights ...

SHOW MORE
SHOW LESS
  • No tags were found...

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

የም/አ/ቀ/ሰ/መ/ተ/ፕ (EHAHRDP)መቅድምየምስራቅና አፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ፕሮጄክት ለሰብአዊ መብት ተሟጋቾች የመረጃ ምንጭ የሆነውን የመጀመሪያ እትም ለሰብአዊመብት መሟገት በሚል ርእስ መጽሃፍ ካሳተመ አምስት አመት አለፈ።በዚያ ጊዜ ውስጥ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች የሚሰሩበትን አውድ የሚፈታተኑአዳዲስ ሁኔታዎች ተለዋውጠዋል።ስለሰብአዊ መብቶች የሚከናወን ስራን ወሰን በሚገድብ መልኩ መንግስታት አፋኝ ህጎችን መጠቀም ቀጥለዋል።ከተዳከመና ዘገምተኛ የፍትህ ስርዐት ጋር የህግ አስከባሪውን ክንድ በዘፈቀደና በጉልበት ለመጠቀም እንዲያስችል ተለጥጠው የተጸነሱ የጸረ ሽብርተኝነት ድንጋጌዎችን ህጋዊ ጥያቄና ተቃውሞየሚያነሱ የሲቪል ማህበረሰብ ተዋንያንን በማመቅ ስራ ላይ በስፋት እንዲውሉ በመደረግ ላይ ይገኛሉ።ድንበር ዘለል ትብብር ማለት ለመሰደድ የተገደዱ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ጥገኝነት በጠየቁበት አገርም እንኳ በአገራቸው መንግስት የሚደረግባቸው ወከባ ሊቀጥል ይችላል ማለት ነው።ባንዳንድጉዳዮች መያዶችን የሚገድቡ ህጎች የገንዘብ ማግኛ እድሎችንና የሰብአዊ መብት ስራ እንቅስቃሴዎችን ለመገደብ ስራ ላይ የዋሉ ሲሆን ለመገናኛ ብዙሃን የወጡት ህጎች ደግሞ በዘፈቀደ እየተተረጎሙ ሃሳብን የመግለጽ መብትን በተናጠል ለማፈን ተግባር አገልግሎት ላይ ውለዋል።ምንም እንኳ የዚህ መብት ተሟጋቾች ተጻራሪ የሆነ ድባብ ቢፈጠርባቸውም በጾታ ግንኙነት የአናሳዎቹ መብት ተሟጋቾች የግብረሰዶማውያን መብት እንደሰብአዊ መብት እውቅና ማግኘቱን ለማረጋገጥ የሚያደርጉትን ትግል ቀጥለዋል።እነዚህ ፈተናዎች በተለዋወጡ ቁጥር የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በእጃቸው ያሉትም መሳሪያዎች በረቀቀና ውጤት በሚያመጣ መልኩ ይቀያየራሉ።እነዚህን መሳሪያዎች ስልታዊ በሆነ መንገድ አሟልቶ መጠቀም ለሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ፈተናና ለያዙትም እምቅ ጥንካሬ ወሳኝ ነው።የሰብአዊ መብት ጉዳዮች እውቅና እንዲያገኙ ብሎም ግዴታን የተሸከሙ ባለድርሻዎች በአደባባይ መልስ እንዲሰጡ ለማድረግ አንዱ ወሳኝ መንገድ ከአለማቀፍና አህጉራዊ የሰብአዊ መብት ተቋማት ጋር ቁርኝት መፍጠር ነው።እነዚህኑ ተቋማት እንዴት ባግባቡ መጠቀም እንደሚያስችል ምዕራፍ አንድየውይይት ሃሳብ ይዟል።የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ስራ ዘላቂ ይሆን ዘንድ የግል እንክብካቤና የሙያ ደህንነት ወሳኝ ናቸው።ምዕራፍ 2 እና 3 በየራሳቸው ስለሰብአዊ መብትተሟጋቾች ደህንነት አያያዝና ውጥረት ስለመቀነስ ሽፋን ይሰጣሉ።ለዘመቻ የሚሆኑ ስልቶች በምዕራፍ 4 የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃንን የቅስቀሳ መሳሪያነትን ከሚያወሳው ምዕራፍ 4 እና 5 ጋር ተገናዝቧል።በተለይ ስለሴቶች መብትና ስለአናሳ ጾታዎች መብት መሟገት ስለሚያጋጥመው ፈተናና ስለስልቶቹ በምዕራፍ 5 እና 6 በየራሱ ተፈትሿል።በመጨረሻም የመረጃ ምንጩ መጽሃፍ አግባብ የሆኑ ህትመቶችንና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችን በአባሪው ላይ አጣጥሞ እንዲያካትት ተደርጓል።በግማሽ ቀጠናው ለሚገኘው ህዝብ እንዲዳረስ መጽሃፉ በእንግሊዝኛ፣ፈረንሳይኛ፣አረብኛ፣ስዋሂሊ፣አማርኛ እና ሶማሊኛ እንዲቀርብ በማድረጋችን ተደስተናል።ለዚህ ፕሮጄክት ቁልፍ አጋዣችን የሆኑትን የስዊዲን ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ተቋምና በኔዘርላንድ ሥርዎ መንግሥት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ክልብ እናመሰግናለን።ም/አ/ቀ/ሰ/መ/ተ/ፕ በዚህ መጽሃፍ ጽሁፍ በማቅረብ አስተዋጽኦ ያደረጉትን ሁሉ እንዲሁም በሰብአዊ መብት ጥበቃ ስራ ላይ አሁንም ተሰማርተው መገኘታቸውን በማጤን ምስጋናውን ይገልጻል።ይህ መጽሃፍ መታሰቢያነቱ ለሰብአዊ መብት ሲታገሉ ህይወታቸውን ላጡ ሁሉ እንዲሆን ም/አ/ቀ/ሰ/መ/ተ/ፕ አበርክቷል።መጪው ጊዜ የተሻለ እንዲሆን ሁላችንም አንድ እንሁን።ሀሰን ሽሬየስራ አስፈጻሚ ዲሬክተር/ሊቀመንበርየምስራቅና አፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ፕሮጄክት/ጥምረት ም/አ/ሰ/መ/ተ/ፕ/ጥምርv

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!