26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

10|26|ለእነዚያ መልካም ለሠሩት መልካም ነገርና ጭማሪም አላቸው፡፡ ፊቶቻቸውንም

ጥቁረትና ውርደት አይሸፍናቸውም፡፡ እነዚያ የገነት ሰዎች ናቸው፡፡ እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች

ናቸው፡፡

10|27|ለእነዚያም ኃጢአቶችን ለሠሩት የኃጢኣቲቱ ቅጣት በብጤዋ አለቻቸው፡፡ ውርደትም

ትሸፍናቸዋለች፡፡ ለእነሱ ከአላህ (ቅጣት) ጠባቂ የላቸውም፡፡ ፊቶቻቸው ከጨለመ ሌሊት

ቁራጮች እንደ ተሸፈኑ ይኾናሉ፡፡ እነዚያ የእሳት ሰዎች ናቸው፡፡ እነርሱ በውስጧ ዘለዓለም

ነዋሪዎች ናቸው፡፡

10|28|ሁሉንም የምንሰበስባቸውን ከዚያም ለእነዚያ ለአጋሩት እናንተም ተጋሪዎችሁም

ስፍራችሁን ያዙ የምንልበትን ተጋሪዎቻቸውም እኛን ትገዙ አልነበራችሁም የሚሉዋቸው ሲኾኑ

በመካከላቸው የምንለይበትን ቀን (አስታውስ)፡፡

10|29|«(ጣዖታቶቹ ለእኛ) ከመገዛታችሁ በእርግጥ ዘንጊዎች ለመኾናችንም በእኛና በእናንተ

መካከል የአላህ መስካሪነት በቃ» (ይሏቸዋል)፡፡

10|30|በዚያ ቀን ነፍስ ሁሉ ያሳለፈችውን ሥራ ታውቃለች፡፡ (አጋሪዎች) ወደ አላህም

እውነተኛ ወደ ሆነው ጌታቸው ይመለሳሉ፡፡ ከእነሱም ይቀጣጥፉት የነበሩት ነገር ይጠፋቸዋል፡፡

10|31|«ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማን ነው መስሚያዎችንና ማያዎችንስ

የፈጠረ ማን ነው ከሙትም ሕያውን የሚያወጣ ከሕያውም ሙትን የሚያወጣስ ማን ነው ነገሩን

ሁሉ የሚያስተናብርስ ማን ነው» በላቸው፡፡ «በእርግጥም አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ

(ለምን ታጋራላችሁ) አትፈሩትምን» በላቸው፡፡

10|32|እርሱ እውነተኛ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ከእውነትም በኋላ ጥመት እንጂ ሌላ ምን አለ

(ከውነት) እንዴት ትዞራላችሁ

10|33|እንደዚሁ የጌታህ ቃል በእነዚያ ባመጹት ላይ እነርሱ የማያምኑ መሆናቸው

ተረጋገጠች፡፡

10|34|«ከምታጋሩዋቸው (ጣዖታት) ውስጥ መፍጠርን የሚጀምር ከዚም የሚመልሰው

አለን» በላቸው፡፡ «አላህ መፍጠርን ይጀምራል፤ ከዚያም ይመልሰዋል፡፡ ታዲያ (ከእምነት)

እንዴት ትዞራላችሁ» በላቸው፡፡

10|35|«ከምታጋሩዋቸው፤ ወደ እውነት የሚመራ አለን» በላቸው፡፡ «አላህ ወደ እውነቱ

ይመራል፡፡ ወደ እውነት የሚመራው ሊከተሉት የተገባው ነውን ወይስ ካልተመራ በስተቀር

የማይመራው ለእናንተም ምን (አስረጅ) አላችሁ እንዴት (በውሸት) ትፈርዳላችሁ» በላቸው፡፡

10|36|አብዛኞቻቸውም ጥርጣሬን እንጂ አይከተሉም፡፡ ጥርጣሬ ከእውነት ምንም

አያብቃቃም፡፡ አላህ የሚሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡

10|37|ይህም ቁርኣን ከአላህ ሌላ (ከሆነ ፍጡር) የተቀጠፈ ሊሆን አይገባውም፡፡ ግን ያንን

ከእርሱ በፊት ያለውን (መጽሐፍ) የሚያረጋግጥና በመጽሐፉ ውስጥ ያለውን የሚዘረዝር በእርሱ

ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ከዓለማት ጌታ (የተወረደ) ነው፡፡

10|38|በእውነትም «(ሙሐመድ) ቀጣጠፈው» ይላሉን «ይህ ከሆነ መሰሉን (አንዲት)

ሱራ አምጡ፡፡ ከአላህም ሌላ የቻላችሁትን ሁሉ (ረዳት) ጥሩ፡፡ እውነተኞች እንደሆናችሁ

(ተጋግዛችሁ አምጡ)» በላቸው፡፡

10|39|ይልቁንም (ከቁርኣን) እውቀቱን ባላደረሱት ፍቹም ገና ባልመጣቸው ነገር

አስተባበሉ፡፡ እንደዚሁ እነዚያ ከእነሱ በፊት የነበሩት አስተባብለዋል፡፡ የበዳዮችም መጨረሻ

እንዴት እንደ ነበረ ተመልከት፡፡

10|40|ከእነርሱም ውስጥ (ወደፊት) በርሱ የሚያምኑ አልሉ፡፡ ከእነርሱም በእርሱ የማያምኑ

አልሉ፡፡ ጌታህም አጥፊዎቹን በጣም ዐዋቂ ነው፡፡

104

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!