26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

12|66|«ካልተከበባችሁ በስተቀር እርሱን በእርግጥ የምታመጡልኝ ለመሆናችሁ ከአላህ የሆነን

ቃል ኪዳን መተማመኛ እስከምትሰጡኝ ድረስ ከእናንተ ጋር ፈጽሞ አልልከውም» አላቸው፡፡

መተማመኛቸውንም በሰጡት ጊዜ «አላህ በምንለው ሁሉ ላይ ምስክር ነው» አላቸው፡፡

12|67|አለም «ልጆቼ ሆይ! በአንድ በር አትግቡ፡፡ ግን በተለዩ በሮች ግቡ፡፡ ከአላህም

(ፍርድ) በምንም አልጠቅማችሁም፤ (አልመልስላችሁም)፡፡ ፍርዱ የአላህ እንጅ የሌላ

አይደለም፡፡ በእርሱ ላይ ተመካሁ፡፡ ተመኪዎችም ሁሉ በእርሱ ብቻ ይመኩ፡፡»

12|68|አባታቸውም ካዘዛቸው ስፍራ በገቡ ጊዜ ከአላህ (ፍርድ) ምንም ነገር ከነርሱ

የሚከለክልላቸው አልነበረም፡፡ ግን በያዕቆብም ነፍስ ውስጥ የነበረች ጉዳይ ናት፡፡ ፈጸማት፡፡

እርሱም ስላሳወቅነው የዕውቀት ባለቤት ነው፤ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም፡፡

12|69|በዩሱፍ ላይ በገቡ ጊዜም ወንድሙን ወደርሱ አስጠጋው፡፡ «እነሆ እኔ ወንድምህ ነኝ፡

፡ ይሠሩት በነበሩትም ሁሉ አትቆላጭ» አለው፡፡

12|70|ዕቃቸውንም ባዘጋጀላቸው ጊዜ፤ ዋንጫይቱን በወንድሙ ዕቃ ውስጥ አደረገ፡፡ ከዚያም

«እናንተ ባለ ግመሎች ሆይ! እናንተ በእርግጥ ሌቦች ናችሁ ሲል ጠሪ ተጣራ፡፡»

12|71|ወደነሱ ዞረውም «ምንድን ጠፋችሁ» አሉ፡፡

12|72|«የንጉሡ መስፈሪያ ጠፍቶናል፡፡ እርሱንም ላመጣ ሰው የግመል ጭነት አለው፡፡ እኔም

በእርሱ ተያዥ ነኝ» አለ፡፡

12|73|«በአላህ እንምላለን በምድር ላይ ለማጥፋት እንዳልመጣን በእርግጥ ዐውቃችኋል፡፡

ሌቦችም አልነበርንም» አሉ፡፡

12|74|«ውሸታሞች ብትሆኑ ቅጣቱ ምንድን ነው» አሏቸው፡፡

12|75|«ቅጣቱ (በያዕቆብ ሕግ) ዕቃው በጓዙ ውስጥ የተገኘበት ሰው (ራሱ መወሰድ)

ነው፡፡ እርሱም ቅጣቱ ነው፡፡ እንደዚሁ በደለኞችን እንቀጣለን» አሉ፡፡

12|76|(ምርመራውን) ከወንድሙም ዕቃ በፊት በዕቃዎቻቸው ጀመረ፡፡ ከዚያም

(ዋንጫይቱን) ከወንድሙ ዕቃ ውስጥ አወጣት፡፡ እንደዚሁ ለዩሱፍ ብልሃትን አስተማርነው፡፡

አላህ ባልሻ ኖሮ በንጉሡ ሕግ ወንድሙን ሊይዝ አይገባውም ነበር፡፡ የምንሻውን ሰው

በደረጃዎች ከፍ እናደርጋለን፡፡ ከዕውቀት ባለቤቶች ሁሉ በላይም ዐዋቂ አልለ፡፡

12|77|«ቢሰርቅ ከአሁን በፊት የርሱው ወንድም በእርግጥ ሰርቋል» አሉ፡፡ ዩሱፍም

(ይህችን ንግግር) በነፍሱ ውስጥ ደበቃት፡፡ ለእነሱም አልገለጣትም፡፡ (በልቡ) «እናንተ

ሥራችሁ የከፋ ነው፡፡ አላህም የምትሉትን ሁሉ ይበልጥ ዐዋቂ ነው» አለ፡፡

12|78|አንተ የተከበርከው ሆይ! «ለእርሱ በእርግጥ ታላቅ ሽማግሌ አባት አለው፡፡ ስለዚህ

በእርሱ ስፍራ አንደኛችንን ያዝ፡፡ እኛ ከመልካም ሠሪዎች ሆነህ እናይሃለንና» አሉት፡፡

12|79|«ዕቃችንን እርሱ ዘንድ ያገኘንበትን ሰው እንጂ ሌላን ከመያዝ በአላህ እንጠብቃለን፡፡

እኛ ያን ጊዜ በእርግጥ በዳዮች ነን» አለ፡፡

12|80|ከርሱም ተስፋን በቆረጡ ጊዜ የሚመካከሩ ሆነው ገለል አሉ፡፡ ታላቃቸው አለ

«አባታቸሁ በናንተ ላይ ከአላህ የሆነን መታመኛ ኪዳን በእርግጥ የያዘባችሁ መሆኑን ከዚህም

በፊት በዩሱፍ ላይ ግፍ የሠራችሁትን አታውቁምን ስለዚህ አባቴ ለእኔ እስከሚፈቅድልኝ ወይም

አላህ ለኔ እስከሚፈርድልኝ ድረስ የምስርን ምድር አልለይም፡፡ እርሱም ከፈራጆች ሁሉ በላጭ

ነው፡፡

12|81|«ወደ አባታችሁ ተመለሱ በሉትም፡- አባታችን ሆይ! ልጅህ ሰረቀ፡፡ ባወቅነውም

ነገር እንጂ አልመሰከርንም፡፡ ሩቁንም ነገር (ምስጢሩን) ዐዋቂዎች አልነበርንም፡፡

12|82|«ያችንም በውስጧ የነበርንባትን ከተማ ያችንም በውስጧ የመጣነውን ባለ ግመል ጓድ

ጠይቅ፡፡ እኛም በእርግጥ እውነተኞች ነን፡፡»

121

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!