26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

7|49|እነዚያ አላህ በችሮታው አያገኛቸውም ብላችሁ የማላችሁት (ደካሞች) እነዚህ ናቸውን

«ገነትን ግቡ ፍርሃት የለባችሁም እናንተም አታዝኑም» (ተባሉ ይሏቸዋል)፡፡

7|50|የእሳትም ሰዎች የገነትን ሰዎች «በእኛ ላይ ከውሃ አፍስሱብን ወይም አላህ ከሰጣችሁ

ሲሳይ (ጣሉልን)» ብለው ጠሩዋቸዋል፡፡ እነርሱም «አላህ በከሓዲዎች ላይ እርም

አድርጓቸዋል» ይሏቸዋል፡፡

7|51|እነዚያ ሃይማኖታቸውን መሳለቂያና መጫወቻ አድርገው የያዙ የቅርቢቱም ሕይወት

ያታለለቻቸው ይህንን ቀናቸውን መገናኘትን እንደረሱ በተአምራታችንም ይክዱ እንደነበሩ ዛሬ

እንረሳቸዋልን፡፡

7|52|ከዕውቀት ጋርም የዘረዘርነው የኾነን መጽሐፍ ለሚያምኑ ሕዝቦች መምሪያና እዝነት

ሲኾን በእርግጥ አመጣንላቸው፡፡

7|53|(የዛቻውን) ፍጻሜውን እንጂ ሌላ አይጠባበቁም፡፡ ፍጻሜው በሚመጣበት ቀን እነዚያ

ከመምጣቱ በፊት የረሱት ሰዎች «የጌታችን መልክተኞች በእርግጥ በውነት መጥተዋል፡፡ ለእኛ

ያማልዱም ዘንድ አማላጆች አልሉን ወይስ ከዚያ እንሠራው ከነበርነው ሌላን ሥራ እንሠራ

ዘንድ (ወደ ምድረ ዓለም) እንመለሳለን» ይላሉ፡፡ ነፍሶቻቸውን በእርግጥ አከሰሩ፡፡ ይቀጥፉት

የነበሩትም ከእነርሱ ጠፋቸው፡፡

7|54|ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው፡፡ ከዚያም

(ስልጣኑ) በዐርሹ ላይ ተደላደለ፡፡ (አላህ) ሌሊትን በቀን ፈጥኖ የሚፈልገው ሲኾን

ይሸፍናል፡፡ ፀሐይንና ጨረቃንም ከዋክብትንም በትእዛዙ የተገሩ ሲኾኑ (ፈጠራቸው)፡፡ ንቁ!

መፍጠርና ማዘዝ የእርሱ ብቻ ነው፡፡ የዓለማት ጌታ አላህ (ክብሩ) ላቀ፡፡

7|55|ጌታችሁን ተዋርዳችሁ በድብቅም ለምኑት፡፡ እርሱ ወሰን አላፊዎችን አይወድምና፡፡

7|56|በምድርም ውስጥ ከተበጀች በኋላ አታበላሹ፡፡ ፈርታችሁና ከጅላችሁም ተገዙት፡፡ የአላህ

ችሮታ ከበጎ አድራጊዎች ቅርብ ነውና፡፡

7|57|እርሱም ያ ነፋሶችን ከችሮታው (ከዝናም) በፊት አብሳሪዎች አድርጎ የሚልክ ነው፡፡

ከባዳዎችንም ደመናዎች በተሸከሙ ጊዜ ሙት ወደ ኾነ አገር እንነዳዋለን፡፡ በእርሱም ውሃን

እናወርዳለን፡፡ ከፍሬዎችም ሁሉ በእርሱ እናወጣለን፡፡ እንደዚሁ ትገነዘቡ ዘንድ ሙታንን

(ከመቃብር) እናወጣለን፡፡

7|58|መልካሙም አገር በጌታው ፈቃድ በቃዩ (ያማረ ኾኖ) ይወጣል፡፡ ያም መጥፎ

የኾነው (በቃዩ) ደካማ ኾኖ እንጂ አይወጣም፡፡ እንደዚሁ ለሚያመሰግኑ ሕዝቦች ታምራትን

እናብራራለን፡፡

7|59|ኑሕን ወደ ወገኖቹ በእርግጥ ላክነው፡፡ አላቸውም፡- «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡

ለእናንተ ከርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም፡፡ እኔ በእናንተ ላይ የከባድ ቀንን ቅጣት

እፈራላችኋለሁ፡፡»

7|60|ከሕዝቦቹ (የካዱት) መሪዎቹ፡- «እኛ በግልጽ መሳሳት ውስጥ ኾነህ በእርግጥ

እናይሃለን» አሉት፡፡

7|61|አላቸው «ወገኖቼ ሆይ! ምንም መሳሳት የለብኝም፡፡ ግን እኔ ከዓለማት ጌታ

መልእክተኛ ነኝ፡፡»

7|62|«የጌታዬን መልክቶች አደርስላችኋለሁ፡፡ ለእናንተም እመክራችኋለሁ፡፡ ከአላህም በኩል

የማታውቁትን ዐውቃለሁ፡፡»

7|63|«አላህን ልትፈሩና ይታዘንላችሁም ዘንድ ከእናንተው (ጎሳ) በኾነ ሰው ላይ

እንዲያስጠነቅቃችሁ ከጌታችሁ ግሳጼ ቢመጣላችሁ ትደነቃላችሁን» (አላቸው)፡፡

78

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!