26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

11|62|«ሷሊህ ሆይ! ከዚህ በፊት በእኛ ውስጥ (መሪ ልትሆን) በእርግጥ የምትከጅል

ነበርክ፡፡ አባቶቻችን የሚገዙትን ከመገዛት ትከለክለናለህን እኛም ወደርሱ ከምትጠራን ነገር

በእርግጥ አወላዋይ በሆነ መጠራጠር ውስጥ ነን» አሉ፡፡

11|63|«ሕዝቦቼ ሆይ! ንገሩኝ ከጌታዬ በሆነ ማስረጃ ላይ ብሆን ከእርሱም የሆነን ችሮታ

(ነቢይነት) ቢሰጠኝና ባልታዘዘው ከአላህ (ቅጣት) የሚያድነኝ ማነው ከማሳሳትም በስተቀር

ምንም አትጨምሩልኝም» አላቸው፡፡

11|64|ሕዝቦቼም ሆይ! ይህቺ ለእናንተ ተዓምር ስትሆን የአላህ ግመል ናት፡፡ ተውዋትም፡፡

በአላህ ምድር ውስጥ ትብላ፡፡ በክፉም አትንኳት፡፡ ቅርብ የሆነ ቅጣት ይይዛችኋልና»

(አላቸው)፡፡

11|65|ወግተው ገደሏትም፡፡ (ሷሊህ) «በአገራችሁም ሶስትን ቀናት (ብቻ) ተጠቀሙ፡፡

ይህ የማይዋሽ ቀጠሮ ነው» አላቸው፡፡

11|66|ትዕዛዛችንም በመጣ ጊዜ ሷሊህንና እነዚያን ከሱ ጋር ያመኑትን ከእኛ በሆነው እዝነት

አዳን፡፡ ከዚያም ቀን ውርደት (አዳንናቸው)፡፡ ጌታህ እርሱ ብርቱው አሸናፊው ነውና፡፡

11|67|እነዚያንም የበደሉትን ጩኸት ያዛቸው፡፡ በቤቶቻቸውም ውስጥ የተንበረከኩ ሆነው

ሞተው አነጉ፡፡

11|68|በእሷ ውስጥ እንዳልኖሩባት ሆኑ፡፡ ንቁ! ሰሙዶች ጌታቸውን በእርግጥ ካዱ፡፡ ንቁ!

ለሰሙዶች (ከአላህ እዝነት) መራቅ ተገባቸው፡፡

11|69|መልክተኞቻችንም ኢብራሂምን በ(ልጅ) ብስራት በእርግጥ መጡት፡፡ ሰላም አሉት፡፡

ሰላም አላቸው፡፡ ጥቂትም ሳይቆይ ወዲያውኑ የተጠበሰን የወይፈን ስጋ አመጣ፡፡

11|70|እጆቻቸውም ወደ እርሱ የማይደርሱ መኾነቸውን ባየ ጊዜ ሸሻቸው፡፡ ከነሱም ፍርሃት

ተሰማው፡፡ «አትፍራ እኛ ወደ ሉጥ ሕዝቦች ተልከናልና» አሉት፡፡

11|71|ሚስቱም የቆመች ስትኾን (አትፍራ አሉት) ሳቀችም፡፡ በኢስሐቅም አበሰርናት፡፡

ከኢስሐቅም በኋላ (በልጁ) በያዕቁብ (አበሰርናት)፡፡

11|72|(እርሷም) ዋልኝ! እኔ አሮጊት ይህም ባሌ ሽማግሌ ሆኖ ሳለ እወልዳለሁን ይህ

በእርግጥ አስደናቂ ነገር ነው አለች፡፡

11|73|«ከአላህ ትዕዛዝ ትደነቂያለሽን የአላህ ችሮታና በረከቶቹ በእናንተ በኢብራሂም

ቤተሰቦች ላይ ይሁን እርሱ ምስጉን ለጋስ ነውና» አሉ፡፡

11|74|ከኢብራሂም ፍራቻው በሌደለትና ብስራት በመጣችለትም ጊዜ በሉጥ ሕዝቦች (ነገር)

ይከራከረን ጀመር፡፡

11|75|ኢብራሂም በእርግጥ ታጋሽ አልቃሻ መላሳ ነውና፡፡

11|76|«ኢብራሂም ሆይ! ከዚህ (ክርክር) ተው፡፡ እነሆ የጌታህ ትዕዛዝ በእርግጥ

መጥቷል፡፡ እነሱም የማይመለስ ቅጣት የሚመጣባቸው ናቸው» (አሉት)፡፡

11|77|መልክተኞቻችንም ሉጥን በመጡት ጊዜ በነሱ (ምክንያት) አዘነ፡፡ ልቡም በነሱ

ተጨነቀ፡፡ «ይህ ብርቱ ቀን ነውም» አለ፡፡

11|78|ሕዝቦቹም ወደርሱ እየተጣደፉ መጡት፡፡ ከዚህም በፊት መጥፎ ሥራዎችን ይሠሩ

ነበር፡፡ «ሕዝቦቼ ሆይ! እኝህ ሴቶች ልጆቼ ናቸው፡፡ እነሱ ለእናንተ ይልቅ በጣም የጸዱ

ናቸው፤ (አግቧቸው)፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ በእንግዶቼም አታሳፍሩኝ፡፡ ከእናንተ ውስጥ ቅን ሰው

የለምን» አላቸው፡፡

11|79|«ከሴቶች ልጆችህ ለእኛ ምንም ጉዳይ የለንም፡፡ አንተም የምንሻውን በእርግጥ

ታውቃለህ» አሉት፡፡

113

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!