26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

40|80|ለእናንተም በእርሷ ውስጥ ጥቅሞች አልሏችሁ፡፡ በእርሷም ላይ (እቃን በመጫን)

በልቦቻችሁ ያሰባችሁትን ጉዳይ ትደርሱ ዘንድ (ፈጠረላችሁ)፡፡ በእርሷም ላይ በመርከቦችም

ላይ ትሳፈራላችሁ፡፡

40|81|ተዓምራቱንም ያሳያችኋል፡፡ ታዲያ ከአላህ ተዓምራት የትኛውን ትክዳላችሁ?

40|82|የእነዚያን ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ሕዝቦች ፍጻሜ እንዴት እንደነበረ ይመለከቱ ዘንድ

በምድር ላይ አይኼዱምን? ከእነርሱ ይበልጥ ብዙዎች በኀይልና በምድር ላይ በተዋቸው

ምልክቶችም በጣም ብርቱዎች ነበሩ፡፡ ያም ይሠሩት የነበሩት ከእነርሱ ምንም አልጠቀማቸውም፡፡

40|83|መልክተኞቻቸውም ተዓምራቶችን ባመጡላቸው ጊዜ እነርሱ ዘንድ ባለው ዕውቀት

ተደሰቱ፡፡ በእርሱ ይሳለቁበት የነበሩት ቅጣትም በእነርሱ ላይ ሰፈረባቸው፡፡

40|84|ብርቱ ቅጣታችንንም ባዩ ጊዜ «በአላህ አንድ ሲኾን አምነናል፤ በእርሱም እናጋራ

በነበርነው (ጣዖታት) ክደናል» አሉ፡፡

40|85|ብርቱ ቅጣታችንን ባዩ ጊዜ ማመናቸውም የሚጠቅማቸው አልነበረም፡፡ የአላህን ደንብ

ያችን በባሮቹ ውስጥ ያለፈችውን (ተጠንቀቁ) በዚያ ጊዜም ከሓዲዎች ከሰሩ፡፡

ሱረቱ ፉሲለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው

41|1|ሐ.መ.(ሓ ሚም)፡፡

41|2|(ይህ ቁርኣን) እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ ከሆነው (አላህ) የተወረደ ነው፡፡

41|3|አንቀጾቹ የተብራሩ የኾነ መጽሐፍ ነው፡፡ ዐረብኛ ቁርኣን ሲኾን ለሚያውቁ ሕዝቦች

(የተብራራ) ነው፡፡

41|4|አብሳሪና አስፈራሪ ሲኾን (ተወረደ)፡፡ አብዛኛዎቻቸውም ተዉት፡፡ እነርሱም

አይሰሙም፡፡

41|5|አሉም «ልቦቻችን ከእዚያ ወደእርሱ ከምትጠራን እምነት በመሸፈኛዎች ውስጥ ናቸው፡፡

በጆሮዎቻችንም ላይ ድንቁርና አልለ፤ በእኛና ባንተም መካከል ግርዶሽ አልለ፡፡ (በሃይማኖትህ)

ሥስራም፤ እኛ ሠሪዎች ነንና፡፡»

41|6|(እንዲህ) በላቸው «እኔ መሰላችሁ ሰው ብቻ ነኝ፡፡ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ

ነው ወደእርሱም ቀጥ በሉ ምሕረትንም ለምኑት ማለት ወደእኔ ይወረድልኛል፡፡ ለአጋሪዎቹም

ወዮላቸው፡፡

41|7|ለእነዚያ ዘካን ለማይሰጡት እነርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም እነርሱ ከሓዲዎች ለኾኑት

(ወዮላቸው)፡፡

41|8|እነዚያ ያመኑትና በጎ ሥራዎችን የሠሩት ለእነርሱ የማይቆረጥ ምንዳ አልላቸው፡፡

41|9|በላቸው «እናንተ በዚያ ምድርን በሁለት ቀኖች ውስጥ በፈጠረው አምላክ በእርግጥ

ትክዳላችሁን? ለእርሱም ባለንጣዎችን ታደርጋላችሁን? ያ (ይህንን የሠራው) የዓለማት ጌታ

ነው፡፡

247

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!