26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

53|52|በፊትም የኑሕን ሕዝቦች (አጥፍቷል)፡፡ እነርሱ በጣም በደለኞችና እጅግ የጠመሙ

እነርሱ ነበሩና፡፡

53|53|የተገለበጠችውንም ከተማ ደፋ፡፡

53|54|ያለበሳትንም አለበሳት፡፡

53|55|ከጌታህም ጸጋዎች በየትኛው ትጠራጠራለህ?

53|56|ይህ ከፊተኞቹ አስፈራሪዎች (ጎሳ) የኾነ አስፈራሪ ነው፡፡

53|57|ቀራቢይቱ (ኅልፈተ ዓለም) ቀረበች፡፡

53|58|ለእርሷ ከአላህ ሌላ ገላጭ የላትም፡፡

53|59|ከዚህ ንግግር ትደነቃላችሁን?

53|60|ትስቃላችሁምን? አታለቅሱምን?

53|61|እናንተም ዘንጊዎች ናችሁ፡፡

53|62|ለአላህም ስገዱ ተገዙትም፡፡

ሱረቱ አል ቀመር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው

54|1|ሰዓቲቱ (የትንሣኤ ቀን) ተቃረበች፤ ጨረቃም ተገመሰ፡፡

54|2|ተዓምርንም ቢያዩ (ከእምነት) ይዞራሉ፡፡ (ይህ) «ዘውታሪ ድግምት ነውም» ይላሉ፡፡

54|3|አስተባበሉም፡፡ ዝንባሌዎቻቸውንም ተከተሉ፡፡ ነገርም ሁሉ (ወሰን አለው)፤ ረጊ ነው፡፡

54|4|ከዜናዎችም በእርሱ ውስጥ መገሰጥ ያለበት ነገር በእርግጥ መጣላቸው፡፡

54|5|ሙሉ የኾነች ጥበብ (መጣቻቸው) ግን አስፈራሪዎቹ አያብቃቁም፡፡

54|6|ከነርሱም ዙር፡፡ ጠሪው (መልአክ) ወደ አስደንጋጭ ነገር የሚጠራበትን ቀን

(አስታውስ)፡፡

54|7|ዓይኖቻቸው ያቀረቀሩ ኾነው፤ ፍጹም የተበተነ አንበጣ መስለው ከመቃብሮቹ ይወጣሉ፡

54|8|ወደ ጠሪው አንገቶቻቸውን ሳቢዎች ቸኳዮች ኾነው (ይወጣሉ)፡፡ ከሓዲዎቹ (ያን

ጊዜ ምን ይላሉ?) «ይህ ብርቱ ቀን ነው» ይላሉ፡፡

54|9|ከእነርሱ በፊት የኑሕ ነገድ አስተባበለች፡፡ ባሪያችንንም (ኑሕን) አስተባበሉ፡፡ «ዕብድ

ነውም» አሉ፡፡ ተገላመጠም፡፡

54|10|ጌታውንም «እኔ የተሸነፍኩ ነኝና እርዳኝ» ሲል ጠራ፡፡

54|11|ወዲያውም የሰማይን ደጃፎች በሚንቧቧ ውሃ ከፈትን፡፡

54|12|የምድርንም ምንጮች አፈነዳን፡፡ ውሃውም (የሰማዩና የምድሩ) በእርግጥ በተወሰነ

ኹነታ ላይ ተገናኘ፡፡

54|13|ባለ ሳንቃዎችና ባለሚስማሮች በኾነችም ታንኳ ላይ ጫንነው፡፡

54|14|በጥበቃችን ስር ኾና ትንሻለላለች፡፡ ተክዶ ለነበረው ሰው ምንዳ (ይህንን ሠራን)፡፡

54|15|ተዓምር አድርገንም በእርግጥ ተውናት፡፡ ከተገሳጭም አልለን?

54|16|ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼም እንዴት ነበሩ?

54|17|ቁርኣንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው፡፡ ተገንዛቢም አልለን?

278

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!