26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

61|12|ኃጢኣቶቻችሁን ለእናንተ ይምራል፡፡ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውንም ገነቶች

ያገባችኋል፡፡ በመኖሪያ ገነቶችም በሚያማምሩ ቤቶች ውስጥ (ያስቀምጣችኋል)፡፡ ይህ ታላቅ

ዕድል ነው፡፡

61|13|ሌላይቱንም የምትወዷትን (ጸጋ ይሰጣችኋለ)፡፡ ከአላህ የኾነ እርዳታና ቅርብ የኾነ

የአገር መክፈት ነው፡፡ ምእምናንንም አብስር፡፡

61|14|እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የመርየም ልጅ ዒሳ ለሐዋርያቶቹ «ወደ አላህ ረዳቴ

ማነው?» እንዳለ ሐወርያቶቹም «እኛ የአላህ ረዳቶች ነን» እንዳሉት የአላህ ረዳቶች ኹኑ፡፡

ከእስራኤልም ልጆች አንደኛዋ ጭፍራ አመነች፡፡ ሌላይቱም ጭፍራ ካደች፡፡ እነዚያን ያመኑትንም

በጠላታቸው ላይ አበረታናቸው፤ አሸናፊዎችም ኾኑ፡፡

ሱረቱ አል ጁሙዓህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው

62|1|በሰማያት ያለው በምድርም ያለው ሁሉ ለአላህ ንጉሥ፣ ቅዱስ፣ አሸናፊ፣ ጥበበኛ

ለኾነው ያሞግሳል፡፡

62|2|እርሱ ያ በመሃይሞቹ ውስጥ አንቀጾቹን (ቁርኣንን) በእነርሱ ላይ የሚያነብላቸው፣

(ከማጋራት) የሚያጠራቸውም፣ መጽሐፍንና ጥበብን የሚያስተምራቸውም የኾነን መልክተኛ

(ሙሐመድን) ከእነርሱው ውስጥ የላከ ነው፡፡ እነርሱም ከእርሱ በፊት በግልጽ ስሕተት ውስጥ

ነበሩ፡፡

62|3|ከነሱም ሌሎች ገና ያልተጠጉዋቸው በኾኑት ላይ (የላከው ነው)፡፡ እርሱም አሸናፊው

ጥበበኛው ነው፡፡

62|4|ይህ የአላህ ችሮታ ነው፡፡ ለሚሻው ሰው ይሰጠዋል፡፡ አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት

ነው፡፡

62|5|የእነዚያ ተውራትን የተጫኑትና ከዚያም ያልተሸከሟት (ያልሠሩባት) ሰዎች ምሳሌ

መጽሐፎችን እንደሚሸከም አህያ ብጤ ነው፡፡ የእነዚያ በአላህ አንቀጾች ያስተባበሉት ሕዝቦች

ምሳሌ ከፋ፡፡ አላህም በዳዮችን ሕዝቦች አይመራም፡፡

62|6|«እናንተ አይሁዳውያን የኾናችሁ ሆይ! ከሰው ሁሉ በስተቀር እናንተ ብቻ ለአላህ

ወዳጆች ነን ብትሉ እውነተኞች እንደኾናችሁ ሞትን ተመኙ» በላቸው፡፡

62|7|እጆቻቸውም ባስቀደሙት ኃጢአት ምክንያት በፍጹም አይመኙትም፡፡ አላህም በዳዮቹን

ዐዋቂ ነው፡፡

62|8|«ያ ከእርሱ የምትሸሹት ሞት እርሱ በእርግጥ አግኛችሁ ነው፡፡ ከዚያም ሩቁንና ቅርቡን

ዐዋቂ ወደ ኾነው ጌታ ትመለሳላችሁ፡፡ ትሠሩትም የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል» በላቸው፡፡

62|9|እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በዐርብ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት

ኺዱ፡፡ መሸጥንም ተዉ፡፡ ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነወ፡፡

62|10|ሶለቲቱም በተፈጸመች ጊዜ በምድር ላይ ተበተኑ፡፡ ከአላህም ችሮታ ፈልጉ፡፡ አላህንም

በብዙ አውሱ፡፡ ልትድኑ ይከጀላልና፡፡

62|11|ንግድን ወይም ዛዛታን ባዩ ጊዜም ቆመህ የተዉህ ሲኾኑ ወደእርሷ ይበተናሉ፡፡ አላህ

ዘንድ ያለው ዋጋ ከዛዛታም ከንግድም በላጭ ነው፡፡ «አላህም ከሰጪዎቹ ሁሉ ይበልጥ ሲሳይን

ሰጭ ነው» በላቸው፡፡

293

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!