26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

12|33|«ጌታዬ ሆይ! ወደርሱ ከሚጠሩኝ ነገር (ከዝሙት) ይልቅ መታሰር ለእኔ የተወደደ

ነው፡፡ ተንኮላቸውንም ከእኔ ላይ ባትመልስልኝ ወደነሱ እዘነበላለሁ፡፡ ከስህተተኞቹም እሆናለሁ»

አለ፡፡

12|34|ጌታውም ጸሎቱን ተቀበለው፡፡ ተንኮላቸውንም ከእርሱ መለሰለት፡፡ እነሆ! እርሱ

ሰሚው ዐዋቂው ነውና፡፡

12|35|ከዚያም ማስረጃዎቹን ካዩ በኋላ እስከጊዜ ድረስ እንዲያስሩት ለነሱ ታያቸው፡፡

12|36|ከእሱም ጋር ሁለት ጎበዞች እስር ቤቱ ገቡ፡፡ አንደኛቸው «እኔ በህልሜ የወይን

ጠጅን ስጠምቅ አየሁ» አለ፡፡ ሌላውም፡- «እኔ በራሴ ላይ እንጀራን ተሸክሜ ከእሱ በራሪ

(አሞራ) ስትበላ አየሁ፡፡ ፍቹን ንገረን፡፡ እኛ ከአሳማሪዎች ሆነህ እናይሃለንና» አሉት፡፡

12|37|(ዩሱፍም) አለ፡- «ማንኛውም የምትስሰጡት ምግብ ለናንተ ከመምጣቱ በፊት ፍቹን

የምነግራችሁ ቢሆን እንጂ አይመጣላችሁም፡፡ ይኸ ጌታዬ ካሳወቀኝ ነገር ነው፤ እኔ በአላህ

የማያምኑን እነርሱም መጨረሻይቱን ዓለም እነርሱ ከሓዲዎች የሆኑትን ሕዝቦች ሃይማኖት

ትቻለሁ፡፡

12|38|«የአባቶቼንም የኢብራሂምንና የኢስሐቅን፣ የያዕቆብንም ሃይማኖት ተከትያለሁ፡፡ ለእኛ

በአላህ ምንንም ማጋራት አይገባንም ያ (አለማጋራት) በእኛ ላይና በሰዎቹ ላይ የአላህ ችሮታ

ነው፡፡ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያመሰግኑም፡፡

12|39|«የእስር ቤት ጓደኞቼ ሆይ! የተለያዩ አምላኮች ይሻላሉን ወይስ አሸናፊው አንዱ

አላህ

12|40|«ከእርሱ ሌላ እናንተና አባቶቻችሁ (አማልክት ብላችሁ) የጠራችኋቸውን ስሞች

እንጅ አትገዝዙም፡፡ አላህ በእርሷ ምንም አስረጅ አላወረደም፡፡ ፍርዱ የአላህ እንጅ የሌላ

አይደለም፡፡ እርሱን እንጅ ሌላን እንዳትገዙ አዟል፡፡ ይህ ትክክለኛው ሃይማኖት ነው፡፡ ግን

አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም፡፡

12|41|«የወህኒ ቤት ጓደኞቼ ሆይ! አንደኛችሁማ ጌታውን (ንጉሡን) ጠጅ ያጠጣል፡፡

ሌላውማ ይሰቀላል፡፡ ከራሱም በራሪ (አሞራ) ትበላለች፡፡ ያ ፍቹን የምትጠይቁት ነገር

ተፈጸመ፤» (አላቸው)፡፡

12|42|ለዚያም ከሁለቱ እርሱ የሚድን መሆኑን ለተጠራጠረው እጌታህ ዘንድ አስታውሰኝ

አለው፡፡ ጌታውንም ከማስታወስ ሰይጣን አስረሳው፡፡ ለጥቂት ዓመታትም በወህኒ ቤቱ ውስጥ

ቆየ፡፡

12|43|ንጉሡም «እኔ ሰባትን የሰቡ ላሞች ሰባት ከሲታዎች ሲበሏቸው ሰባትንም ለምለም

ዘለላዎች ሌሎችንም ደረቆችን (ሲጠመጠሙባቸው በሕልሜ) አያለሁ፡፡ እናንተ ታላላቅ ሰዎች

ሆይ! ሕልምን የምትፈቱ እንደሆናችሁ ሕልሜን ፍቱልኝ» አላቸው፡፡

12|44|«የሕልሞች ቅዠቶች ናቸው፡፡ እኛም የሕልሞችን ፍች ዐዋቂዎች አይደለንም» አሉት፡፡

12|45|ያም ከሁለቱ የዳነውና ከብዙ ጊዜ በኋላ (ዩሱፍን) ያስታወሰው ሰው «እኔ ፍቹን

እነግራችኋለሁና ላኩኝ» አለ፤ (ወደ ዩሱፍ ሌደም)፡፡

12|46|«አንተ እውነተኛው ዩሱፍ ሆይ! ሰባትን የሰቡ ላሞች ሰባት ከሲታዎች ላሞች

ሲበሉዋቸው ሰባትን ለምለም ዘለላዎችም ሌሎችንም ደረቆች (በነሱ ላይ ሲጠመጠሙባቸው

ያየን ሰው ሕልም ፍች) ተችልን፡፡ ያውቁ ዘንድ ወደ ሰዎቹ ልመለስ እከጅላለሁና» (አለው)፡፡

12|47|(እርሱም) አለ፡- «ሰባትን የተከታተሉ ዓመታት ትዘራላችሁ፡፡ ያጨዳችሁትንም ሁሉ

ከምትበሉት ጥቂት በስተቀር በዘለላው ውስጥ ተዉት፡፡

12|48|«ከዚያም ከእነዚያ በኋላ ካደለባችሁት ጥቂት ሲቀር ለእነሱ ያደለባችሁትን ሁሉ

የሚበሉ ሰባት የችግር ዓመታት ይመጣሉ፡፡

119

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!