Amharic (Ethiopia) translation of the Quran
Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org
Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org
You also want an ePaper? Increase the reach of your titles
YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.
26|159|ጌታህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊው አዛኙ ነው፡፡

26|160|የሉጥ ሕዝቦች መልክተኞችን አስተባባሉ፡፡

26|161|ወንድማቸው ሉጥ ለእነርሱ ባለ ጊዜ «አትጠነቀቁምን

26|162|«እኔ ለእናንተ ታማኝ መልክተኛ ነኝ፡፡

26|163|«አላህንም ፍሩ፤ ታዘዙኝም፡፡

26|164|«በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አልለምናችሁም፡፡ ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ እንጅ

በሌላ ላይ አይደለም፡፡

26|165|«ከዓለማት ሰዎች ወንዶችን ትመጣላችሁን

26|166|«ከሚስቶቻችሁም ጌታችሁ ለናንተ የፈጠረላችሁን ትተዋላችሁን በእውነቱ እናንተ

ወሰን አላፊዎች ሕዝቦ ናችሁ፡፡»

26|167|(እነርሱም) አሉ «ሉጥ ሆይ! ባትከለከል በእርግጥ (ከአገር) ከሚወጡት

ትኾናለህ፡፡»

26|168|(እርሱም) አለ «እኔ ሥራችሁን ከሚጠሉት ሰዎች ነኝ፡፡

26|169|«ጌታዬ ሆይ! እኔንም ቤተሰቦቼንም ከሚሠሩት ሥራ (ቅጣት) አድነን፡፡»

26|170|እርሱንም ቤተሰቦቹንም በጠቅላላ አዳንናቸው፡፡

26|171|በቀሪዎቹ ውስጥ የኾነች አሮጊት ብቻ ስትቀር (እርሷ ጠፋች)፡፡

26|172|ከዚያም ሌሎቹን አጠፋን፡፡

26|173|በእነሱም ላይ (የድንጋይን) ዝናምን አዘነምንባቸው፡፡ የተስፈራሪዎቹም ዝናም

(ምንኛ) ከፋ፡፡

26|174|በዚህ ውስጥ አስደናቂ ተዓምር አልለበት፡፡ አብዛኞቻቸውም ምእመናን አልነበሩም፡፡

26|175|ጌታህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊው አዛኙ ነው፡፡

26|176|የአይከት ሰዎች መልክተኞችን አስተባበሉ፤

26|177|ሹዕይብ ለእነርሱ ባላቸው ጊዜ «አትጠነቀቁምን

26|178|«እኔ ለእናንተ ታማኝ መልክተኛ ነኝ፡፡

26|179|«አላህንም ፍሩ፤ ታዘዙኝም፡፡

26|180|«በርሱም ላይ ምንም ዋጋ አልጠይቃችሁም፡፡ ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ እንጅ

በሌላ ላይ አይደለም፡፡

26|181|«ስፍርን ሙሉ፡፡ ከአጉዳዮቹም አትኹኑ፡፡

26|182|«በትክክለኛ ሚዛንም መዝኑ፡፡

26|183|«ሰዎችንም ነገሮቻቸውን አታጉድሉባቸው፡፡ በምድርም ላይ አጥፊዎች ኾናችሁ

አታበላሹ፡፡

26|184|«ያንንም የፈጠራችሁን የቀድሞዎቹንም ፍጡሮች (የፈጠረውን) ፍሩ፡፡»

26|185|አሉ «አንተ በብዛት ከተደገመባቸው ሰዎች ነህ፡፡

26|186|«አንተም ብጤያችን ሰው እንጅ ሌላ አይደለህም፡፡ እነሆ ከውሸታሞች ነህ ብለን

እንጠረጥርሃለን፡፡

26|187|«ከእውነተኞቹም እንደኾንክ በእኛ ላይ ከሰማይ ቁራጭን ጣልብን፡፡»

26|188|«ጌታዬ የምትሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነው፤» አላቸው፡፡

26|189|አስተባበሉትም፡፡ የጥላይቷ ቀን ቅጣትም ያዛቸው፡፡ እርሱ የከባድ ቀን ቅጣት

ነበርና፡፡

26|190|በዚህ ውስጥ አስደናቂ ተዓምር አልለበት፡፡ አብዛኞቻቸውም ምእምናን አልነበሩም፡፡

26|191|ጌታህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊው አዛኙ ነው፡፡

192