26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

28|73|ከችሮታውም ለእናንተ ሌሊትንና ቀንን በውስጡ ልታርፉበት፣ ከትሩፋቱም

ልትፈልጉበት፣ አመስገኞችም ልትኾኑ አደረገላችሁ፡፡

28|74|የሚጠራባቸውንም ቀንና «እነዚያ ተጋሪዎቼ ትሏቸው የነበራችሁት የት ናቸው»

የሚልበትን (አስታውስ)፡፡

28|75|ከሕዝቦችም ሁሉ መስካሪን እናወጣለን፡፡ (ያን ጊዜ) እውነተኛውም አምላክነት

ለአላህ ብቻ መኾኑን ያውቃሉ፡፡ ይቀጣጥፉት የነበሩትም ከእነርሱ ይጠፋቸዋል፡፡

28|76|ቃሩን ከሙሳ ነገዶች ነበር፡፡ በእነርሱም ላይ አመጸ፡፡ ከድልቦችም ያንን መከፈቻዎቹ

ብቻ የኃይል ባለቤቶች የኾኑ ጭፍሮችን (ሸክሙ) የሚከብድን ሰጠነው፡፡ ወገኖቹ ለእርሱ

አትኩራ፤ አላህ ኩራተኞችን አይወድምና ባሉት ጊዜ (አስታውስ)፡፡

28|77|«አላህም በሰጠህ ሀብት የመጨረሻይቱን አገር ፈልግ፡፡ ከቅርቢቱም ዓለም ፋንታህን

አትርሳ፡፡ አላህም ወደ አንተ መልካምን እንዳደረገልህ (ለሰዎች) መልካምን አድርግ፡፡ በምድርም

ውስጥ ማጥፋትን አትፈልግ፡፡ አላህ አጥፊዎችን አይወድምና» (አሉት)፡፡

28|78|(ሀብቱን) «የተሰጠሁት እኔ ዘንድ ባለው እውቀት ብቻ ነው አለ፡፡ አላህ ከእርሱ

በፊት ከክፍለ ዘመናት ሰዎች በኀይል ከእርሱ ይበልጥ የበረቱትን (ሀብትን) በመሰብሰብም

ይበልጥ የበዙትን በእርግጥ ያጠፋ መኾኑን አያውቅምን አመጸኞችም ከኀጢኣቶቻቸው (ምሕረት

የሚከተለውን ጥያቄ) አይጠየቁም፡፡

28|79|በሕዝቦቹም ላይ በጌጡ ውስጥ ኾኖ ወጣ፡፡ እነዚያ ቅርቢቱን ሕይወት የሚፈልጉት

«ወይ ምኞታችን! ቃሩን የተሰጠው ብጤ ምነው ለእኛ በኖረን፤ እርሱ የታላቅ ዕድል ባለቤት

ነውና» አሉ፡፡

28|80|እነዚያም ዕውቀትን የተሰጡት «ወዮላችሁ! የአላህ ምንዳ ለአመነ ሰው መልካምንም

ለሠራ በላጭ ነው፡፡ ታጋሾችም እንጅ ሌላው አያገኛትም» አሉ፡፡

28|81|በእርሱም በቤቱም ምድርን ደረባን፡፡ ለእርሱም ከአላህ ሌላ የሚረዱት ጭፍሮች

ምንም አልነበሩትም፡፡ ከሚርረዱትም አልነበረም፡፡

28|82|እነዚያም በትላንትናው ቀን ስፍራውን ይመኙ የነበሩት «ወይ ጉድ! ለካ አላህ

ከባሮቹ ለሚሻው ሰው ሲሳይን ያሰፋል፤ ያጠባልም፡፡ አላህ በእኛ ላይ (በእምነት) ባልለገሰልን

ኖሮ ምድርን በእኛ ላይ በገለበጠብን ነበር፡፡ ወይ ጉድ! ከሓዲዎች አይድኑም» የሚሉ ኾነው

አነጉ፡፡

28|83|ይህች የመጨረሻይቱ አገር ለእነዚያ በምድር ውስጥ ኩራትንና ማመፅን ለማይፈልጉት

እናደርጋታለን፡፡ ምስጉኒቱም መጨረሻ ለጥንቁቆቹ ናት፡፡

28|84|በደግ ሥራ የመጣ ሰው ለእርሱ ከእርሷ በላጭ ምንዳ አልለው፡፡ በክፉም ሥራ

የመጡ ሰዎች እነዚህ መጥፎዎችን የሠሩ ይሠሩት የነበሩትን እንጅ አይመነዱም፡፡

28|85|ያ ቁርኣንን የተከፋፈለ ኾኖ ባንተ ላይ ያወረደው (አምላክ) ወደ መመለሻ

(ወደመካ) በእርግጥ መላሽህ ነው፡፡ «ጌታዬ በቅን መንገድ የመጣውን ሰውና እርሱም በግልጽ

ስሕተት ውስጥ የኾነውን ሰው ዐዋቂ ነው» በላቸው፡፡

28|86|መጽሐፉ ወዳንተ መወረዱን ተስፋ የምታደርግ አልነበርክም፡፡ ግን ከጌታህ ችሮታ

(ተወረደልህ)፡፡ ለከሓዲዎችም በፍጹም ረዳት አትኹን፡፡

28|87|ከአላህም አንቀጾች ወዳንተ ከተወረዱ ጊዜ በኋላ አያግዱህ፡፡ ወደ ጌታህም (ሰዎችን)

ጥራ፡፡ ከአጋሪዎቹም አትኹን፤

28|88|ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አትግገዛ፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ ነገሩ ሁሉ

ከአላህ በቀር ጠፊ ነው፡፡ ፍርዱ የርሱ፤ ብቻ ነው፡፡ ወደእርሱም ትመለሳላችሁ፡፡

203

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!