26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

የምንሻውን ሰው በእርሱ የምንመራበት ብርሃን አደረግነው፡፡ አንተም ወደ ቀጥተኛው መንገድ

በእርግጥ ትመራለህ፡፡

42|53|ወደዚያ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ወደ ኾነው አላህ መንገድ

(ትመራለህ)፡፡ ንቁ! ነገሮቹ ሁሉ ወደ አላህ ይመለሳሉ፡፡

ሱረቱ አል ዙኽሩፍ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው

43|1|ሐ.መ (ሓ ሚም)፡፡

43|2|ገላጭ በኾነው መጽሐፍ እምላለሁ፡፡

43|3|እኛ ታውቁ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን አደረግነው፡፡

43|4|እርሱም በመጽሐፎቹ እናት ውስጥ እኛ ዘንድ በእርግጥ ከፍተኛ ጥበብ የተመላ ነው፡፡

43|5|ድንበር አላፊዎች ሕዝቦች ለመኾናችሁ ቁርኣኑን ከእናንተ ማገድን እናግዳለን?

43|6|በፊተኞቹም ሕዝቦች ውስጥ ከነቢይ ብዙን ልከናል፡፡

43|7|ከነቢይም አንድም የሚመጣላቸው አልነበረም በእርሱ ይሳለቁበት የነበሩ ቢኾኑ እንጅ፡፡

43|8|ከእነርሱም በኀይል ይበልጥ የበረቱትን አጥፍተናል፡፡ የፊተኞቹም (አጠፋፍ) ምሳሌ

አልፏል፡፡

43|9|«ሰማያትንና ምድርንም ማን ፈጠራቸው» ብለህ ብትጠይቃቸው «አሸናፊው ዐዋቂው

(አላህ) በእርግጥ ፈጠራቸው» ይላሉ፡፡

43|10|(እርሱ) ያ ምድርን ለእናንተ ምንጣፍ ያደረገላችሁ በርሷም ውስጥ ትምመሩ ዘንድ

ለእናንተ መንገዶችን ያደረገላችሁ ነው፡፡

43|11|ያም ከሰማያ ውሃን በልክ ያወረደላችሁ ነው፡፡ በእርሱም የሞተችውን አገር ሕያው

አደረግን፡፡ እንደዚሁ (ከመቃብራችሁ) ትውወጣላችሁ፡፡

43|12|ያም ዓይነቶችን ሁሉ የፈጠረ ለእናንተም ከመርከቦችና ከቤት እንስሳዎች

የምትጋልቧቸውን ያደረገላችሁ ነው፡፡

43|13|በጀርባዎቹ ላይ እንድትደላደሉ ከዚያም በርሱ ላይ የተደላደላችሁ ጊዜ የጌታችሁን ጸጋ

እንድታስታውሱ፤ እንድትሉም፡- «ያ ይህንን የማንችለው ስንኾን ለእኛ ያገራለን ጌታ ጥራት

ይገባው፡፡

43|14|እኛም በእርግጥ ወደ ጌታችን ተመላሾች፤ነን» (እንድትሉ)፡፡

43|15|ከባሮቹም ለእርሱ ቁራጭን (ልጅን) አደረጉለት፡፡ ሰው በእርግጥ ግልጽ ከሓዲ ነው፡፡

43|16|ከሚፈጥረው ውስጥ ሴቶች ልጆችን ያዘን? በወንዶች ልጆችም (እናንተን)

መረጣችሁን?

43|17|አንዳቸውም ለአልረሕማን ምሳሌ ባደረገው ነገር (በሴት ልጅ) በተበሰረ ጊዜ እርሱ

በቁጭት የተመላ ኾኖ ፊቱ የጠቆረ ይኾናል፡፡

43|18|በጌጥ (ተከልሶ) እንዲያድግ የሚደረገውን? እርሱም (ለደካማነቱ) በክርክር

የሚያብራራውን ፍጡር (ሴትን) ለአላህ ያደርጋሉን?

43|19|መላእክትንም እነርሱ የአልረሕማን ባሮች የኾኑትን ሴቶች አደረጉ፡፡ ሲፈጠሩ ነበሩን?

መመስከራቸው በእርግጥ ትጻፋለች፡፡ ይጠየቃሉም፡፡

254

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!