26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

30|57|በዚያም ቀን እነዚያን የበደሉትን ማመካኘታቸው አይጠቅማቸውም፡፡ እነርሱም በወቀሳ

አይታለፉም፡፡

30|58|በዚያም ቁርኣን ውስጥ ከምሳሌ ሁሉ ለሰዎች በእርግጥ ገለጽን፡፡ በተዓምርም

ብትመጣባቸው እነዚያ የካዱት ሰዎች «እናንተ አበላሺዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም» ይላሉ፡፡

30|59|እንደዚሁ አላህ በእነዚያ በማያውቁት ሰዎች ልቦች ላይ ያትማል፡፡

30|60|ስለዚህ ታገስ፡፡ የአላህ ቀጠሮ እውነት ነውና፡፡ እነዚያም በትንሣኤ የሚያረጋግጡት

አያቅልሉህ፡፡

ሱረቱ አል ሉቅማን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው

31|1|አ.ለ.መ. (አሊፍ ላም ሚም)፡፡

31|2|ይህች ጥበብ ከተመላው መጽሐፍ አንቀጾች ናት፡፡

31|3|ለበጎ አድራጊዎች መሪና እዝነት ስትኾን፡፡

31|4|ለእነዚያ ሶላትን አስተካክለው ለሚያደርሱት፣ ዘካንም ለሚሰጡት፣ እነርሱም

በመጨረሻይቱ ዓለም እነርሱ የሚያረጋግጡ ለሆኑት፡፡

31|5|እነዚያ ከጌታቸው በሆነ ቅን መንገድ ላይ ናቸው፡፡ እነዚያም እነርሱ ምኞታቸውን ያገኙ

ናቸው፡፡

31|6|ከሰዎችም ያለ ዕውቀት ሆኖ ከአላህ መንገድ ሊያሳስትና ማላገጫ አድርጎ ሊይዛት

አታላይ ወሬን የሚገዛ አልለ፡፡ እነዚያ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አላቸው፡፡

31|7|አንቀጾቻችንም በእርሱ ላይ በሚነበቡ ጊዜ እንዳልሰማትና በጆሮቹ ድንቁርና እንዳለበት

የኮራ ሆኖ ይዞራል፡፡ በአሳማሚ ቅጣትም አብስረው፡፡

31|8|እነዚያ ያመኑና መልካሞችንም የሠሩ ለእነርሱ የጸጋ ገነቶች አሏቸው፡፡

31|9|በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ሲሆኑ፤ አላህም እውነተኛን ተስፋ ቃል ገባላቸው፡፡ እርሱም

አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡

31|10|ሰማያትን ያለምታዩዋት አዕማድ (ምሰሶዎች) ፈጠረ፡፡ በምድርም ውስጥ በእናንተ

እንዳታረገርግ ተራራዎችን ጣለ፡፡ በእርሷም ላይ ከተንቀሳቃሽ ሁሉ በተነ፡፡ ከሰማይም ውሃን

አወረድን፡፡ በእርሷም ውስጥ ከመልካም ዓይነት ሁሉ አበቀልን፡፡

31|11|ይህ የአላህ ፍጡር ነው፡፡ እነዚያ ከእርሱ ሌላ ያሉት ምንን እንደፈጠሩ እስኪ

አሳዩኝ፡፡ በእውነቱ በዳዮቹ በግልጽ ጥመት ውስጥ ናቸው፡፡

31|12|ለሉቅማንም ጥበብን በእርግጥ ሰጠነው፡፡ (አልነውም)፡- «አላህን አመስግን፡፡»

ያመሰገነም ሰው የሚያመሰግነው ለራሱ ብቻ ነው፡፡ የካደም ሰው (በራሱ ላይ ነው)፡፡ አላህ

ተብቃቂ ምስጉን ነውና፡፡

31|13|ሉቅማንም ለልጁ እርሱ የሚገሥጸው ሲኾን «ልጄ ሆይ! በአላህ (ጣዖትን)

አታጋራ፡፡ ማጋራት ታላቅ በደል ነውና» ያለውን (አስታውስ)፡፡

211

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!