26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

6|67|ለትንቢት ሁሉ (የሚደርስበት) መርጊያ አለው፡፡ ወደፊትም ታውቁታላችሁ፡፡

6|68|እነዚያንም በአንቀጾቻችን የሚገቡትን ባየህ ጊዜ ከእርሱ ሌላ በኾነ ወሬ እስከሚገቡ

ድረስ ተዋቸው፡፡ ሰይጣንም (መከልከልህን) ቢያስረሳህ ከትውስታ በኋላ ከበደለኞች ሕዝቦች

ጋር አትቀመጥ፡፡

6|69|በእነዚያም በሚጠነቀቁት ላይ ከሒሳባቸው ምንም የለባቸውም፡፡ ግን ይጠነቀቁ ዘንድ

መገሰጽ (አለባቸው)፡፡

6|70|እነዚያንም ሃይማኖታቸውን ጨዋታና ላግጣ አድርገው የያዙትን ቅርቢቱም ሕይወት

ያታለለቻቸውን ተዋቸው፡፡ በእርሱም (በቁርኣን) ነፍስ በሠራችው ሥራ እንዳትጠፋ አስታውስ፡፡

ለእርሷ ከአላህ ሌላ ረዳትና አማላጅ የላትም፡፡ በመበዢያም ሁሉ ብትበዥ ከርሷ አይወሰድም፡፡

እነዚህ እነዚያ በሠሩት ሥራ የተጠፉት ናቸው፡፡ ለነሱ ይክዱ በነበሩት ምክንያት ከፈላ ውሃ

መጠጥና አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡

6|71|«ከአላህ ሌላ የማይጠቅመንን እና የማይጎዳንን እንገዛለን አላህም ከመራን ጊዜ በኋላ

የኋሊት እንመለሳለን እንደዚያ በምድር ላይ የዋለለ ሲኾን ሰይጣናት እንዳሳሳቱት ለእርሱ ወደኛ

ና እያሉ ወደ ቅን መንገድ የሚጠሩ ወዳጆች እንዳሉት (እንደማይከተላቸውም) ሰው

እንኾናለን» በላቸው፡፡ «የአላህ መንገድ እርሱ ቀጥተኛው መንገድ ነው፡፡ ለዓለማት ጌታ

ልንገዛም ታዘዝን» በላቸው፡፡

6|72|ሶላትንም በደንቡ ስገዱ ፍሩትም፤ (በማለት ታዘዝን)፡፡ እርሱም ያ ወደርሱ ብቻ

የምትሰበሰቡበት ነው፡፡

6|73|እርሱም ያ ሰማያትንና ምድርን በእውነት የፈጠረ ነው፡፡ «ኹን» የሚልበትንና

ወዲያውም የሚኾንበትን ቀን (አስታውስ)፡፡ ቃሉ እውነት ነው፡፡ በቀንዱም በሚነፋ ቀን

ንግሥናው የርሱ ብቻ ነው፡፡ ሩቁንና ቅርቡን ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም ጥበበኛው ውስጥ ዐዋቂው

ነው፡፡

6|74|ኢብራሒምም ለአባቱ ለአዘር «ጣዖታትን አማልክት አድርገህ ትይዛለህን እኔ፤ አንተንም

ሕዝቦችህንም በግልጽ መሳሳት ውስጥ ኾናችሁ አያችኋለሁ» ባለ ጊዜ (አስታውስ)

6|75|እንደዚሁም ኢብራሂምን (እንዲያውቅና) ከአረጋጋጮቹም ይኾን ዘንድ የሰማያትንና

የምድርን መለኮት አሳየነው፡፡

6|76|ሌሊቱም በእርሱ ላይ ባጨለመ ጊዜ ኮከብን አየ፡፡ «ይህ ጌታዬ ነው» አለ፡፡

በጠለቀም ጊዜ፡- «ጠላቂዎችን አልወድም» አለ፡፡

6|77|ጨረቃንም ወጪ ኾኖ ባየ ጊዜ፡- «ይህ ጌታዬ ነው» አለ፡፡ በገባም ጊዜ፡- «ጌታዬ

(ቅኑን መንገድ) ባይመራኝ በእርግጥ ከተሳሳቱት ሕዝቦች እኾናለሁ» አለ፡፡

6|78|ፀሐይንም ጮራዋን ዘርግታ ባየ ጊዜ፡- «ይህ ጌታዬ ነው፡፡ ይህ በጣም ትልቅ ነው»

አለ፡፡ በገባችም ጊዜ፡- «ወገኖቼ ሆይ! እኔ ከምታጋሩት ሁሉ ንጹሕ ነኝ» አለ፡፡

6|79|«እኔ ለዚያ ሰማያትንና ምድርን ለፈጠረው (አምላክ) ቀጥተኛ ስኾን ፊቴን አዞርኩ፡፡

እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም» (አለ)፡፡

6|80|ወገኖቹም ተከራከሩት፡፡ «በአላህ (አንድነት) በእርግጥ የመራኝ ሲኾን

ትከራከሩኛላችሁን በእርሱም የምታጋሩትን ነገር አልፈራም፡፡ ግን ጌታዬ ነገርን ቢሻ (ያገኘኛል)፡፡

ጌታዬም ነገሩን ሁሉ ዕውቀቱ ሰፋ፡፡ አትገነዘቡምን» አላቸው፡፡

6|81|«በእናንተ ላይ በእርሱ ማስረጃን ያላወረደበትን እናንተ ማጋራታችሁን የማትፈሩ ስትኾኑ

የምታጋሩትን (ጣዖታት) እንዴት እፈራለሁ! የምታውቁም ብትኾኑ ከሁለቱ ክፍሎች በጸጥታ

ይበልጥ ተገቢው ማንኛው ነው» (አለ)፡፡

68

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!