26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

ለእነዚያ ለተጸጸቱት መንገድህንም ለተከተሉት ምሕረት አድርግላቸው፡፡ የእሳትንም ቅጣት

ጠብቃቸው፡፡» እያሉ ለእነዚያ ላመኑት ምሕረትን ይለምናሉ፡፡

40|8|«ጌታችን ሆይ! እነርሱንም፣ ከአባቶቻቸውና ከሚስቶቻቸውም፣ ከዝርዮቻቸውም፣

የበጀውን ሁሉ እነዚያን ቃል የገባህላቸውን የመኖሪያ ገነቶች አግባቸው፡፡ አንተ አሸናፊው

ጥበበኛው አንተ ነህና፡፡

40|9|«ከቅጣቶችም ጠብቃቸው፡፡ በዚያ ቀንም የምትጠብቃውን ሰው በእርግጥ አዘንክለት፡፡»

ይህም እርሱ ታላቅ ማግኘት ነው፡፡

40|10|እነዚያ የካዱት ሰዎች «ወደ እምነት በምትጠሩና በምትክዱ ጊዜ አላህ (እናንተን)

መጥላቱ ነፍሶቻችሁን (ዛሬ) ከመጥላታችሁ የበለጠ ነው» በማለት ይጥጠራሉ፡፡

40|11|«ጌታችን ሆይ! ሁለትን ሞት አሞትከን፡፡ ሁለትንም ሕይወት ሕያው አደረግከን፡፡

በኃጢኣቶቻችንም መሰከርን፡፡ ታዲያ (ከእሳት) ወደ መውጣት መንገድ አለን?» ይላሉ፡፡

40|12|«ይህ እነሆ አላህ ብቻውን በተጠራ ጊዜ ስለ ካዳችሁ በእርሱም ተጋሪ ቢደረግ

የምታምኑ ስለ ኾናችሁ ነው፡፡ ስለዚህ ፍርዱ ከፍተኛ ታላቅ ለኾነው አላህ ብቻ ነው፡፡»

40|13|እርሱ ያ (ለአምላክነቱ) ምልክቶቹን የሚያሳያችሁ ለእናንተም ከሰማይ ሲሳይን

የሚያወርድላችሁ ነው፡፡ ወደእርሱም የሚመለስ ሰው ቢኾን እንጂ ሌላው አይገሰጽም፡፡

40|14|አላህንም ከሓዲዎች ቢጠሉም ሃይማኖትን ለእርሱ አጥሪዎች ኾናችሁ ተገዙት፡፡

40|15|(እርሱ) ደረጃዎችን ከፍ አድራጊ የዐርሹ ባለቤት ነው፡፡ የመገናኛውን ቀን ያስፈራራ

ዘንድ ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ ከትዕዛዙ መንፈስን (ራእይን) ያወርዳል፡፡

40|16|እነርሱ (ከመቃብር) በሚወጡበት ቀን በአላህ ላይ ከእነርሱ ምንም ነገር አይደበቅም፡

፡ «ንግሥናው ዛሬ ለማን ነው?» (ይባላል፤)፡፡ «ለአሸናፊው ለአንዱ አላህ ብቻ ነው»

(ይባላል)፡፡

40|17|«ዛሬ ነፍስ ሁሉ በሠራችው ሥራ ትምመነዳለች፡፡ ዛሬ በደል የለም፡፡ አላህ በእርግጥ

ምርመራው ፈጣን ነው» (ይባላል)፡፡

40|18|ቅርቢቱንም (የትንሣኤን) ቀን ልቦች ጭንቀትን የተመሉ ኾነው ላንቃዎች ዘንድ

የሚደርሱበትን ጊዜ አስጠንቅቃቸው፡፡ ለበዳዮች ምንም ወዳጅና ተሰሚ አማላጅ የላቸውም፡፡

40|19|(አላህ) የዓይኖችን ክዳት ልቦችም የሚደብቁትን ሁሉ ያውቃል፡፡

40|20|አላህም በእውነት ይፈርዳል፡፡ እነዚያም ከእርሱ ሌላ የሚግገዟቸው በምንም

አይፈርዱም፡፡ አላህ እርሱ ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡

40|21|የእነዚያን ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ሕዝቦች ፍጻሜ እንዴት እንደነበረ ይመለከቱ ዘንድ

በምድር ላይ አይኼዱምን? በኀይልና በምድር ላይ በተዋቸው ምልክቶች፤ ከእነርሱ ይበልጥ

የበረቱ ነበሩ፡፡ አላህም በኀጢአቶቻቸው ያዛቸው፡፡ ለእነርሱም ከአላህ (ቅጣት) ምንም ጠባቂ

አልነበራቸውም፡፡

40|22|ይህ (መያዝ) እነርሱ መልክተኞቻቸው በተዓምራቶች ይመጡባቸው ስለነበሩና ስለ

ካዱ ነው፡፡ አላህም ያዛቸው፡፡ እርሱ ኀያል ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡

40|23|ሙሳንም በተዓምራቶቻችንና በግልጽ ማስረጃ በእርግጥ ላክነው፡፡

40|24|ወደ ፈርዖንና ወደ ሃማን፤ ወደ ቃሩንም (ላክነው)፡፡ «ድግምተኛ ውሸታም ነው»

አሉም፡፡

40|25|ከእኛ ዘንድ እውነትን ይዞ በመጣላቸውም ጊዜ «የእነዚያን ከእርሱ ጋር ያመኑትን

ሰዎች ወንዶች ልጆች ግደሉ፤ ሴቶቻቸውንም አስቀሩ» አሉ፡፡ የከሓዲዎችም ተንኮል በጥፋት

ውስጥ እንጅ አይደለም፡፡

243

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!