26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

24|37|አላህን ከማውሳትና ሶላትን ከመስገድ ዘካንም ከመስጠት ንግድም ሽያጭም

የማያታልላቸው ልቦችና ዓይኖች በእርሱ የሚገላበጡበትን ቀን የሚፈሩ የኾኑ ሰዎች

(ያጠሩታል)፡፡

24|38|አላህ የሠሩትን ሥራ መልካሙን ሊመነዳቸው ከችሮታውም ሊጨመርላቸው

(ያጠሩታል)፡፡ አላህም ለሚሻው ሰው ያለ ግምት ይሰጣል፡፡

24|39|እነዚያም የካዱት ሰዎች ሥራዎቻቸው (መልካሞቹ) በበረሃ ሜዳ እንዳለ ሲሪብዱ

የጠማው ሰው ውሃ ነው ብሎ እንደሚያስበው በመጣውም ጊዜ ምንም ነገር ኾኖ

እንደማያገኘው ነው፡፡ (ከሓዲው) አላህንም እሠራው ዘንድ ያገኘዋል፡፡ ምርመራውንም

(ቅጣቱን) ይሞላለታል፡፡ አላህም ምርመራው ፈጣን ነው፡፡

24|40|ወይም (መጥፎ ሥራዎቻቸውን) ከበላዩ ደመና ያለበት ማዕበል በሚሸፈነው ጥልቅ

ባህር ውስጥ እንዳሉ ጨለማዎች ነው፡፡ (እነዚያ) ከፊላቸው ከከፊሉ በላይ ድርብርብ የኾኑ

ጨለማዎች ናቸው፡፡ (በዚህች) የተሞከረ (ሰው) እጁን ባወጣ ጊዜ ሊያያት አይቀርብም፡፡

አላህም ለእርሱ ብርሃንን ያላደረገለት ሰው ለእርሱ ምንም ብርሃን የለውም፡፡

24|41|አላህ በሰማያትና በምድር ያለ ሁሉ በራሪዎችም ክንፎቻቸውን (በአየር ላይ)

ያንሳፈፉ ኾነው ለእርሱ የሚያጠሩ (የሚያወድሱ) መኾናቸውን አላወቅህምን ሁሉም ስግደቱንና

ማጥራቱን በእርግጥ ዐወቀ፡፡ አላህም የሚሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡

24|42|የሰማያትና የምድርም ግዛት የአላህ ነው፡፡ መመለሻም ወደ አላህ ነው፡፡

24|43|አላህ ደመናን የሚነዳ መኾኑን አላየህምን ከዚያም ከፊሉን ከከፊሉ ያገናኛል፡፡ ከዚያም

የተደራረበ ያደርገዋል፡፡ ዝናቡንም ከመካከሉ የሚወጣ ኾኖ ታየዋለህ፡፡ ከሰማይም (ከደመና)

በውስጧ ካሉት ጋራዎች በረዶን ያወርዳል፡፡ በእርሱም የሚሻውን ሰው (በጉዳት) ይነካል፡፡

ከሚሻውም ሰው ላይ ይመልሰዋል፡፡ የብልጭታው ብርሃን ዓይኖችን ሊወስድ ይቀርባል፡፡

24|44|አላህ ሌሊትንና ቀንን ያገላብጣል፡፡ በዚህም ለባለ ውስጥ ዓይኖች በእርግጥ ማስረጃ

አልለበት፡፡

24|45|አላህም ተንቀሳቃሽን ሁሉ ከውሃ ፈጠረ፡፡ ከእነሱም በሆዱ ላይ የሚኼድ አልለ፡፡

ከእነሱም በሁለት እግሮች ላይ የሚኼድ አልለ፡፡ አላህ የሚሻውን ሁሉ ይፈጥራል፡፡ አላህ በነገሩ

ሁሉ ላይ ቻይ ነውና፡፡

24|46|አብራሪን አንቀጾች በእርግጥ አወረድን፡፡ አላህም የሚሻውን ሰው ወደ ቀጥተኛ መንገድ

ይመራዋል፡፡

24|47|በአላህና በመልክተኛውም አምነናል ታዘናልም ይላሉ፡፡ ከዚያም ከዚህ በኋላ ከእነሱ

ከፊሉ ይሸሻል፡፡ እነዚያም ምእምናን አይደሉም፤

24|48|ወደ አላህና ወደ መልክተኛውም በመካከላቸው ሊፈርድ በተጠሩ ጊዜ ከእነሱ ከፊሉ

ወዲያውኑ ይሸሻሉ፡፡

24|49|እውነቱም (ሐቁ) ለእነሱ ቢኾን ወደርሱ ታዛዦች ኾነው ይመጣሉ፡፡

24|50|በልቦቻቸው ውስጥ በሺታ አለን ወይስ (በነቢይነቱ) ተጠራጠሩን ወይስ አላህና

መልክተኛው በእነሱ ላይ የሚበድሉ መኾንን ይፈራሉን ይልቁንም፤ እነዚያ እነሱ በዳዮቹ ናቸው፡

24|51|የምእምናን ቃል የነበረው ወደ አላህና ወደ መልክተኛው በመካከላቸው ሊፈርድ

በተጠሩ ጊዜ ሰማን፤ ታዘዝንም ማለት ብቻ ነው፡፡ እነዚህም እነሱ የፈለጉትን የሚያገኙ ናቸው፡፡

24|52|አላህንና መልክተኛውን የሚታዘዝም ሰው፣ አላህንም የሚፈራና የሚጠነቀቀው ሰው፤

እነዚያ እነርሱ ፍለጎታቸውን የሚያገኙ ናቸው፡፡

181

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!