26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

ከአገር መባረር ነው፡፡ ይህ በነሱ በቅርቢቱ ዓለም ውርደት ነው፡፡ በመጨረሻይቱም ለእነርሱ

ከባድ ቅጣት አላቸው፡፡

5|34|እነዚያ በእነርሱ ላይ ከመቻላችሁ (ከመወሰናችሁ) በፊት የተጸጸቱ ሲቀሩ፡፡ አላህም

መሓሪ አዛኝ መኾኑን እወቁ፡፡

5|35|እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ ወደርሱም መቃረቢያን (መልካም ሥራን)

ፈልጉ፡፡ ትድኑ ዘንድም በእርሱ መንገድ ታገሉ፡፡

5|36|እነዚያ የካዱት ሰዎች በምድር ላይ ያለው ሁሉ ከእርሱም ጋር ብጤው ከትንሣኤ ቀን

ቅጣት በእርሱ ሊበዡበት ለእነርሱ በኖራቸው ኖሮ ከእነሱ ተቀባይን ባላገኙ ነበር፡፡ ለእነሱም

አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡

5|37|ከእሳት ሊወጡ ይፈልጋሉ፡፡ እነርሱም ከርስዋ ወጪዎች አይደሉም፡፡ ለእነርሱም ዘውታሪ

ቅጣት አላቸው፡፡

5|38|ሰራቂውንና ሰራቂይቱንም በሠሩት ነገር ለቅጣት ከአላህ የኾነን መቀጣጫ እጆቻቸውን

ቁረጡ፡፡ አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው፡፡

5|39|ከበደሉም በኋላ የተጸጸተና ሥራውን ያሳመረ አላህ ጸጸቱን ከእርሱ ይቀበለዋል፡፡ አላህ

መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡

5|40|የሰማያትና የምድር ንግሥና የሱ (የአላህ) ብቻ መኾኑን አላወቅክምን የሚሻውን ሰው

ይቀጣል፡፡ ለሚሻውም ሰው ይምራል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡

5|41|አንተ መልክተኛ ሆይ! እነዚያ በክሕደት የሚቻኮሉት ከእነዚያ ልቦቻቸው ያላመኑ

ሲኾኑ በአፎቻቸው «አመንን» ካሉትና ከእነዚያም አይሁድ ከኾኑት ሲኾኑ አያሳዝኑህ፡፡

(እነርሱ) ውሸትን አዳማጮች ናቸው፡፡ ለሌሎች ወዳንተ ላልመጡ ሕዝቦች አዳማጮች ናቸው፡

፡ ንግግሮችን ከቦታቸው ሌላ ያጣምማሉ፡፡ «ይህንን (የተጣመመውን) ብትስሰጡ ያዙት፡፡

ባትስሰጡትም ተጠንቀቁ» ይላሉ፡፡ አላህም መፈተኑን የሚሻበትን ሰው ለእርሱ ከአላህ

(ለመከላከል) ምንንም አትችልም፡፡ እነዚህ እነዚያ አላህ ልቦቻቸውን ማጥራትን ያልሻላቸው

ናቸው፡፡ ለእነርሱ በቅርቢቱ ዓለም ውርደት አላቸው፡፡ ለእነርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከባድ

ቅጣት አላቸው፡፡

5|42|ውሸትን አዳማጮች እርምን በላተኞች ናቸው፡፡ ወደአንተ ቢመጣም በመካከላቸው

ፍረድ፡፡ ወይም ተዋቸው፡፡ ብትተዋቸውም ምንም አይጎዱህም፡፡ ብትፈርድም በመካከላቸው

በትክክል ፍረድ፡፡ አላህ በትክክል ፈራጆችን ይወዳልና፡፡

5|43|እነርሱም ዘንድ ተውራት እያለች በውስጧ የአላህ ፍርድ ያለባት ስትኾን እንዴት

ያስፈርዱሃል! ከዚያም ከዚህ በኋላ እንዴት ይሸሻሉ! እነዚያም በፍጹም ምእምናን አይደሉም፡፡

5|44|እኛ ተውራትን በውስጥዋ መምሪያና ብርሃን ያለባት ስትኾን አወረድን፡፡ እነዚያ ትዕዛዝን

የተቀበሉት ነቢያት በእነዚያ አይሁዳውያን በኾኑት ላይ በርሷ ይፈርዳሉ፡፡ ሊቃውንቱና

ዐዋቂዎቹም ከአላህ መጽሐፍ እንዲጠብቁ በተደረጉትና በርሱም ላይ መስካሪዎች በኾኑት

(ይፈርዳሉ)፡፡ ሰዎችንም አትፍሩ፡፡ ፍሩኝም፡፡ በአንቀጾቼም አነስተኛን ዋጋ አትለውጡ፡፡ አላህም

ባወረደው ነገር ያልፈረደ ሰው እነዚያ ከሓዲዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡

5|45|በእነርሱም ላይ በውስጧ «ነፍስ በነፍስ ዓይንም በዓይን አፍንጫም በአፍንጫ ጆሮም

በጆሮ ጥርስም በጥርስ (ይያዛል)፡፡» ቁስሎችንም ማመሳሰል አለባቸው ማለትን ጻፍን፡፡

በእርሱም የመጸወተ (የማረ) ሰው እርሱ ለርሱ (ለሠራው ኃጢአት) ማስተሰሪያ ነው፡፡

አላህም ባወረደው ነገር የማይፈርድ ሰው፤ እነዚያ በደለኞቹ እነርሱ ናቸው፡፡

5|46|በፈለጎቻቸውም (በነቢያቶቹ ፈለግ) ላይ የመርየምን ልጅ ዒሳን ከተውራት በስተፊቱ

ያለውን አረጋጋጭ ሲኾን አስከተልን፡፡ ኢንጂልንም በውስጡ ቀጥታና ብርሃን ያለበት በስተፊቱ

ያለችውን ተውራትንም የሚያረጋግጥ ለጥንቁቆችም መሪና ገሳጭ ሲኾን ሰጠነው፡፡

57

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!