26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

70|4|መላእክቱና መንፈሱም ልኩ አምሳ ሺሕ ዓመት በኾነ ቀን ውስጥ ወደእርሱ ያርጋሉ፤

(ይወጣሉ)፡፡

70|5|መልካምንም ትዕግስት ታገሥ፡፡

70|6|እነርሱ (ያንን ቀን) ሩቅ አድርገው ያዩታል፡፡

70|7|እኛም ቅርብ ኾኖ እናየዋለን፡፡

70|8|ሰማይ እንደ ዘይት አተላ በምትኾንበት ቀን፡፡

70|9|ጋራዎችም በተለያዩ ቀለማት እንደ ተነከረ ሱፍ (ነፋስ እንደሚያበረው) በሚኾኑበት

ቀን፡፡

70|10|ዘመድም ዘመድን በማይጠይቅበት ቀን፤ (መላሽ የለውም)፡፡

70|11|(ዘመዶቻቸውን) ያዩዋቸዋል፡፡ አመጸኛው ከዚያ ቀን ስቃይ (ነፍሱን) በልጆቹ

ሊበዥ ይመኛል፡፡

70|12|በሚስቱም በወንድሙም፡፡

70|13|በዚያችም በምታስጠጋው ጎሳው፡፡

70|14|በምድርም ላይ ባለው ሁሉ (ሊበዥ) ከዚያም ሊያድነው (ይመኛል)፡፡

70|15|ይተው! እርሷ (እሳቲቱ) ለዟ ናት፡፡

70|16|የራስን ቅል ቆዳ የምትሞሽልቅ ስትኾን፡፡

70|17|(ከእምነት) የዞረንና የሸሸን ሰው (ወደእርሷ) ትጠራለች፡፡

70|18|ገንዘብን የሰበሰበንና (ዘካውን ሳይሰጥ) የቆጠረንም፤ (ትጠራለች)፡፡

70|19|ሰው ቅጠ ቢስ ኾኖ ተፈጠረ፡፡

70|20|ክፉ ነገር ባገኘው ጊዜ ብስጪተኛ፡፡

70|21|መልካምም ነገር (ድሎት) ባገኘ ጊዜ ከልካይ (ኾኖ ተፈጠረ)፡፡

70|22|ሰጋጆቹ ብቻ ሲቀሩ፡፡

70|23|እነዚያ እነርሱ በስግደታቸው ላይ ዘውታሪዎች የኾኑት፡፡

70|24|እነዚያም በገንዘቦቻቸው ላይ የታወቀ መብት ያለባቸው የኾኑት፡፡

70|25|ለለማኝ ከልመና ለሚከለከልም (መብት ያለባቸው የኾኑት)፡፡

70|26|እነዚያም በፍርዱ ቀን እውነት የሚሉት (የሚያረጋግጡት)፡፡

70|27|እነዚያም እነርሱ ከጌታቸው ቅጣት ፈሪዎች የኾኑት፡፡

70|28|የጌታቸው ቅጣት (መምጣቱ) የማያስተማምን ነውና፡፡

70|29|እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የኾኑት፡፡

70|30|በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዙዋቸው (ባሪያዎች) ላይ ሲቀር፡፡ እነርሱ

(በእነዚህ) የማይወቀሱ ናቸውና፡፡

70|31|ከዚያም ወዲያ የፈለገ ሰው እነዚያ እነሱ ድንበር አላፊዎች ናቸው፡፡

70|32|እነዚያም እነርሱ አደራዎቻቸውንና ቃል ኪዳናቸውን ጠባቂዎች የኾኑት፡፡

70|33|እነዚያም እነርሱ በምስክርነታቸው ትክክለኞች የኾኑት፡፡

70|34|እነዚያም እነርሱ በሶላቶቻቸው ላይ የሚጠባበቁት፡፡

70|35|እነዚህ (ከዚህ በላይ የተወሱት ሁሉ) በገነቶች ውስጥ የሚከበሩ ናቸው፡፡

70|36|ለእነዚያም ለካዱት ወደ አንተ በኩል አንገቶቻቸውን መዝዘው የሚያተኩሩት ምን

አላቸው?

70|37|ከቀኝና ከግራ ክፍልፍል ጭፍሮች ሲኾኑ፡፡

70|38|ከእነርሱ እያንዳንዱ ሰው የጸጋይቱን ገነት መግባትን ይከጅላልን?

70|39|ይከልከል፤ እኛ ከሚያውቁት ነገር (ከፍቶት ጠብታ) ፈጠርናቸው፡፡

303

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!