26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

Create successful ePaper yourself

Turn your PDF publications into a flip-book with our unique Google optimized e-Paper software.

(አይሰሙትም)፡፡ እነርሱም በእነርሱ ላይ እውርነት ነው፡፡ እነዚያ ከሩቅ ስፍራ እንደሚጥጠሩ

ናቸው፡፡

41|45|ሙሳንም መጽሐፉን በእርግጥ ሰጠነው፡፡ በእርሱም ተለያዩበት፡፡ ከጌታህም ያለፈች

ቃል ባልነበረች ኖሮ በመካከላቸው በተፈረደ ነበር፡፡ እነርሱም ከእርሱ አወላዋይ በኾነ ጥርጣሬ

ውስጥ ናቸው፡፡

41|46|መልካም የሠራ ሰው ለነፍሱ ነው፡፡ ያጠፋም ሰው በእርሷ ላይ ነው፡፡ ጌታህም

ለባሮቹ በዳይ አይደለም፡፡

41|47|ጊዜይቱን ማወቅ ወደእርሱ ይመለሳል ከፍሬዎችም ከሽፋኖቻቸው አይወጡም፡፡

ከሴትም አንዲትም አታረግዝም፣ አትወልድምም በዕውቀቱ ቢኾን እንጅ፡፡ «ተጋሪዎቼ የት

ናቸው?» በማለት በሚጠራቸው ቀንም «ከእኛ ውስጥ (ባላንጣ አልለ ብሎ) ምንም መስካሪ

አለመኖሩን አስታወቅንህ» ይላሉ፡፡

41|48|ያም በፊት ይግገዙት የነበሩት (ጣዖት) ከእነርሱ ይጠፋቸዋል፡፡ ለእነርሱም ምንም

መሸሻ የሌላቸው መኾኑን ያረጋግጣሉ፡፡

41|49|ሰው በጎ ነገርን ከመለመን አይሰለችም፡፡ ክፉም ቢያገኘው ወዲያውኑ በጣም ተስፋ

ቆራጭ ተበሳጭ ይኾናል፡፡

41|50|ካገኘችውም መከራ በኋላ ከእኛ የኾነን እዝነት ብናቀምሰው «ይህ ለእኔ (በሥራዬ

የተገባኝ) ነው፡፡ ሰዓቲቱም መጪ ናት ብዬ አላስብም፡፡ ወደ ጌታየም ብመለስ ለእኔ እርሱ

ዘንድ መልካሚቱ (ገነት) በእርግጥ አለችኝ» ይላል፡፡ እነዚያንም የካዱትን ሥራዎቻቸውን

በእርግጥ እንነግራቸዋለን፡፡ ከብርቱውም ስቃይ በእርግጥ እናቀምሳቸዋለን፡፡

41|51|በሰውም ላይ ጸጋችንን በለገስን ጊዜ (ከማመስገን) ይዞራል፡፡ በጎኑም ይርቃል፡፡

መከራም ባገኘው ጊዜ የብዙ ልመና ባለቤት ይኾናል፡፡

41|52|በላቸው «ንገሩኝ (ቁርኣኑ) ከአላህ ዘንድ ቢኾን ከዚያም በእርሱ ብትክዱ

(ከውነት) በራቀ ጭቅጭቅ ላይ ከኾነ ሰው ይበልጥ የተሳሳተ ማን ነው?»

41|53|እርሱም (ቁርኣን) እውነት መኾኑ ለእነርሱ እስከሚገለፅላቸው ድረስ በአጽናፎቹ

ውስጥና በነፍሶቻቸውም ውስጥ ያሉትን ተዓምራቶቻችንን በእርግጥ እናሳያቸዋለን፡፡ ጌታህም

እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ዐዋቂ መኾኑ አይበቃቸውምን?

41|54|ንቁ! እነርሱ ከጌታቸው መገናኘት በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ ንቁ! እርሱ በነገሩ

ሁሉ (ዕውቀቱ) ከባቢ ነው፡፡

ሱረቱ አል ሹራ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው

42|1|ሐ.መ (ሐ፡ ሚም)፡፡

42|2|ዐ.ሰ.ቀ (ዓይን ሲን ቃፍ)፤

42|3|እንደዚሁ (በዚህች ሱራ ውስጥ እንዳለው) አሸናፊው ጥበበኛው አላህ ወዳንተ

ያወርዳል፡፡ ወደእነዚያም ከአንተ በፊት ወደ ነበሩት ሕዝቦች (አውርዷል)፡፡

42|4|በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ እርሱም የበላዩ ታላቁ ነው፡፡

250

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!