26.05.2017 Views

Amharic (Ethiopia) translation of the Quran

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

Many more Islamic media to read, listen, print and download at ww.IslamicGlobe.com and at www.QuranReciter.org

SHOW MORE
SHOW LESS

You also want an ePaper? Increase the reach of your titles

YUMPU automatically turns print PDFs into web optimized ePapers that Google loves.

9|90|ከአዕራቦችም ይቅርታ ፈላጊዎቹ ለእነሱ እንዲፈቀድላቸው መጡ፡፡ እነዚያ አላህንና

መልክተኛውን የዋሹትም ተቀመጡ፡፡ ከነሱ እነዚያን የካዱትን አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ

ይነካቸዋል፡፡

9|91|በደካሞች ላይ በበሽተኞችም ላይ በነዚያም የሚያወጡት ገንዘብ በማያገኙት ላይ

ለአላህና ለመልክተኛው ፍጹም ታዛዦች ከኾኑ (ባይወጡም) ኃጢኣት የለባቸውም፡፡ በበጎ

አድራጊዎች ላይ (የወቀሳ) መንገድ ምንም የለባቸውም፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡

9|92|በእነዚያም ልትጭናቸው በመጡህ ጊዜ «በርሱ ላይ የምጭናችሁ (አጋሰስ) አላገኝም፤»

ያልካቸው ስትኾን የሚያወጡት ገንዘብ ባለማግኘታቸው ለማዘናቸው ዓይኖቻቸው እንባን

እያፈሰሱ በዞሩት ላይ (የወቀሳ መንገድ የለባቸውም)፡፡

9|93|(የወቀሳ) መንገዱ በእነዚያ እነሱ ባለጸጋዎች ኾነው ሳሉ ለመቅረት ፈቃድ በሚጠይቁህ

ሰዎች ላይ ብቻ ነው፡፡ ከቀሪዎቹ ጋር መኾናቸውን ወደዱ፡፡ አላህም በልቦቻቸው ላይ

አተመባቸው፤ ስለዚህ እነሱ አያውቁም፡፡

9|94|ወደእነሱ በተመለሳችሁ ጊዜ ምክንያታቸውን ያቀርቡላችኋል፡፡ አታመካኙ፤ እናንተን

ፈጽሞ አናምንም፡፡ አላህ ከወሬዎቻችሁ በእርግጥ ነግሮናልና፡፡ አላህም ሥራችሁን በእርግጥ

ያያል፡፡ መልክተኛውም (እንደዚሁ)፤ ከዚያም ሩቅንና ቅርብን ሁሉ ዐዋቂ ወደ ኾነው (አላህ)

ትመለሳላችሁ ወዲያውም ትሠሩት የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል በላቸው፡፡

9|95|ወደእነሱ በተመለሳችሁ ጊዜ እንድትተውዋቸው ለእናንተ በእርግጥ በአላህ ይምላሉ፡፡

እነሱንም ተዋቸው፡፡ እነሱ እርኩሶች ናቸውና፡፡ ይሠሩትም በነበሩት ዋጋ መኖሪያቸው ገሀነም

ነው፡፡

9|96|ከእነሱ ትወዱላቸው ዘንድ ለናንተ ይምሉላችኋል፡፡ ከእነሱ ብትወዱም አላህ አመጸኞች

ሕዝቦችን አይወድም፡፡

9|97|አዕራቦች በክህደትና በንፍቅና በጣም የበረቱ፤ አላህም በመልክተኛው ላይ ያወረደውን

ሕግጋት ባለማወቅ የተገቡ ናቸው፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡

9|98|ከአዕራቦችም (በአላህ መንገድ) የሚወጣውን (ገንዘብ) ዕዳ አድርጎ የሚይዝ

በእናንተም ላይ የጊዜን መገለባበጥ የሚጠባበቅ ሰው አልለ፡፡ በእነሱ ላይ ጥፋቱ ይዙርባቸው፡፡

አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡

9|99|ከአዕራቦችም በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን የሚሰጣቸውንም (ምጽዋቶች) አላህ

ዘንድ መቃረቢያዎችና ወደ መልክተኛው ጸሎቶች መዳረሻ አድርጎ የሚይዝ ሰው አልለ፡፡ ንቁ!

እርሷ ለእነሱ በእርግጥ አቃራቢ ናት፡፡ አላህ በችሮታው ውስጥ (በገነቱ) በእርግጥ ያስገባቸዋል፡

፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡

9|100|ከስደተኞቹና ከረዳቶቹም ሲኾኑ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች እነዚያም በበጎ ሥራ

የተከተሏቸው አላህ ከእነሱ ወዷል ከእርሱም ወደዋል፡፡ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን

ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ነዋሪዎች ሲኾኑ ለእነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ ይህ ታላቅ ዕድል

ነው፡፡

9|101|በዙሪያችሁም ካሉት ከዐረብ ዘላኖች መናፍቃን አልሉ፡፡ ከመዲና ሰዎችም በንፍቅና

ላይ በማመጽ የዘወተሩ አልሉ፡፡ አታውቃቸውም፡፡ እኛ እናውቃቸዋለን፡፡ ሁለት ጊዜ

እንቀጣቸዋለን፡፡ ከዚያም ወደታላቅ ቅጣት ይመለሳሉ፡፡

9|102|ሌሎችም በኃጢአቶቻቸው የተናዘዙ መልካም ሥራንና ሌላን መጥፎ ሥራ የቀላቀሉ

አልሉ፡፡ አላህ ከእነሱ ጸጸታቸውን ሊቀበል ይከጀላል፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡

9|103|ከገንዘቦቻቸው ስትኾን በእርሷ የምታጠራቸውና የምታፋፋቸው የኾነችን ምጽዋት ያዝ፡፡

ለነሱም ጸልይላቸው፡፡ ጸሎትህ ለእነሱ እርጋታ ነውና አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡

99

Hooray! Your file is uploaded and ready to be published.

Saved successfully!

Ooh no, something went wrong!